Friday, April 25, 2014

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች(ክፍል ሁለት)


ከዚህ ቀደም ባለው ጽሑፍ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የሚገኘውን ገዳማችንን በተመለከተ ዐሥር ነጥቦች እንደማነሣ ቀጠሮ ሰጥቼ ነበር ያቆምኩት፡፡ ዛሬ ሦስቱን አነሣለሁ፡፡
 1. ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋም
የዴር ሡልጣን ገዳማችን ሁለት ዓይነት ችግሮች ተደቅነውበት ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው የይዞታ ባለቤትነት ያልተፈታ ችግር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ገዳሙ ላለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ምንም ዓይነት ጥገና ባለማግኘቱ የተደቀነበት የመፍረስ አደጋ ነው፡፡ የሁለቱም ችግሮች መነሻው ግብጾች በገዳሙ ላይ የሚያቀርቡት የይገባናል ጥያቄና እርሱንም ተከትሎ በመተግበር ላይ የሚገኘው ይርጋ ሕግ(states co) ነው፡፡
ይህንን የገዳማችንን ችግር ለመፍታት በዘላቂነት፣ በተጠናና ዓለም ዐቀፍ ደረጃ ባለው መልክ የሚሠራ ብሔራዊ ኮሚቴ ማቋቋም ያስፈልገናል፡፡ ይህ ኮሚቴ የሃይማኖት፣ የሕግ፣ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም የዴር ሡልጣንን ገዳም ባለቤትነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚፈታ፣ ገዳሙም ጥንታዊነቱንና ደረጃውን ጠብቆ እንዲጠገንና እንዲገነባ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡

ዛሬ ዓለም በኑሮ ደረጃ የትና የት በደረሰበት ዘመን መብራት፣ ውኃና መጸዳጃ ማግኘት ለዴር ሡልጣን መነኮሳት ፈተና መሆን የለበትም፡፡ በእሥራኤል ሀገር እንስሳ እንኳን በማይኖርበት መልኩ እንዲኖሩ ያስገደዳቸውን የይርጋ ሕግ አስቀርቶ ለደረጃቸውና ለሰብአዊነታቸው የሚመጥን የመኖሪያ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረግ አለበት፡፡ በአካባቢው የሚገኙ፣ ቦታንም ከእኛ የወሰዱ አብያተ ክርስቲያናት ሰማይ ጠቀስ ፎቅና ቤተ ክርስቲያን እየሠሩ፣  እነርሱ ግን በጎልጎታ ፍርስራሽ በተሠሩ በኣቶች እንዲኖሩ መገደድ የለባቸውም፡፡ የተቆረጠ ገመድ ለመቀጠል፣ የተሠበረ ቧንቧ ለመሥራት፣ የተበላሸ መጸዳጃ ለማስተካከል፣ የተጣመመ ሚስማር ለማቃናት ሌሎችን ደጅ መጥናት የለባቸውም፡፡
ይህ ነገር ሊፈታ የሚችለው ነገሩን የምር አድርገን ስንይዘው ብቻ ነው፡፡ በየዓመቱ በሚመጡ ተሳላሚዎች ብቻ የሚሠራ አይደለም፡፡ በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ሰባት ቀን፣ በወር ሠላሳ ቀናት፣ በዓመት አሥራ ሦስት ወራት የሚሠራ ሥራ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ከአስጎብኝ ድርጅቶች፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከታዋቂ ሰዎች፣ ከምሁራን፣ በውጭ ሀገር ከመኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ከቤተ እሥራኤላውያን፣ ወዘተ የተውጣጣ አንድ ጠንካራ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋም አለበት፡፡ ይህንን ኮሚቴ ለማቋቋም የአስጎብኝ ድርጅቶች ኃላፊዎች ተነሣሽነቱን በመውሰድ፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር መሥራች ጉባኤ መጥራት ይቻላል፡፡
ይህ ብሔራዊ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ዋና ጽ/ቤቱን በማድረግ በእሥራኤልና በሌሎች ሀገሮች ቅርንጫፎችን በመክፈት ኢትዮጵያውያንንና የኢትዮጵያን ወዳጆች ማስተባበር ይችላል፡፡ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር ጉዳዩን የተመለከተ ውይይት እንዲካሄድ ማስቻል፣ ከእሥራኤል መንግሥት ጋር የዲፕሎማሲ ውይይት መጀመር፣ ተጽዕኖ አድራጊ ተቋማትንና ግለሰቦችን በመፈለግ ተጽዕኖ አድራጊነታቸውን መጠቀም፣ ሚዲያዎች ጉዳዩን የተመለከቱ ዘገባዎችን እንዲሠሩ ማስቻል፣ ሕዝቡንም በማስገንዘብ ሀገራዊ ንቅናቄ መፍጠር፣ ደረጃ በደረጃ ሊፈቱ የሚገባቸውን ችግሮች በመለየት ደረጃ በደረጃ መፍታት፣ ሲፈቀድ የጥገናውንና የግንባታውን ሥራ ማከናወን፡፡
ይህንን ጉዳይ አሁኑኑ ማቋቋምና ሥራ መሥራት ካልቻልን ከገዳሙ በላይ በሚደረገው የጥገና ሥራ የድንጋይ መዓት እየዘነበበት የሚገኘው ገዳም፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ካልጠበቀው በቀር የመናድ አደጋ ተደቅኖበታል፡፡ ወደፊትም የመፍረስ አደጋ ሊያጋጥመው ይችላል፡፡ አስቀድመን የሕግና የዲፕሎማሲውን ሥራ ካልጀመርነው፣ የፈረሰ ጊዜ ‹‹መልሳችሁ ልትሠሩ አትችሉም›› የሚል ክርክር ያጋጥመንና ፍርስራሽ ታቅፈን መቅረታችን የማይቀር ነገር ነው፡፡ ነገን መቅደም ያለብን ዛሬ ነው፡፡ በተለይ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጡት አስጎብኝዎች ይህንን ነገር ፈጥኖ በመከወን ረገድ ሃይማኖታዊም፣ ታሪካዊም፣ ዜግነታዊም ኃላፊነት አለባቸው፡፡

 1. የጋራ የጉዞ ከሚቴ
ወደ ኢየሩሳሌም ለትንሣኤ በዓል፣ ለዳግም ትንሣኤ በዓልና ለገና የሚደረገው የኢትዮጵያውያን ተሳላሚዎች ጉዞ ተጠናክሯል፡፡ የተጓዡም ቁጥር ጨምሯል፡፡ ነገር ግን ይህንን ዕድል በሚገባ አልተጠቀምንበትም፡፡ ተሳላሚዎቹ የሚገናኙበትን፣ ስለ ገዳማቸው የሚመክሩበትን፣ ገዳማቸውን ዘላቂ በመሆነ መንገድ የሚረዱበትን መንገድ አልፈጠርንም፡፡ እንዲያውም በአንዳንዶቹ አስጎብኝዎች መካከል የማይታረቅ የሚመስል ቅራኔ አለ፡፡ በአስጎብኝዋቻቸው ምክንያት ሰላምታ ለመለዋወጥ እንኳን የማይፈላለጉ ተሳላሚዎች አሉ፡፡ ሁሉም በየሆቴሉ ከርሞ፣ በየመኪናው ተጓጓጉዞ፣ በየራሱ ፋሲካን አክብሮ ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ሰውና መላእክት አንድ በሆኑበት ቅዱስ ቦታ ተለያይተን እንመለሳለን፡፡
የኢየሩሳሌም ጉዞ ከመላው ዓለም የሚመጡ ኢትዮጵያውያን የሚገናኙበት፣ የሚተዋወቁበት፣ በአንድ ሊመክሩ የሚችሉበት፣ ፍቅርና ሰላም የሚመሠርቱበት፣ የፖለቲካና የዜግነትን ድንበር ተሻግረው የእምነት አንድነት የሚያሳዩበት መሆን ነበረበት፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ትንሣኤን እንኳን በአንድ አዳራሽ ማክበር፣ በአንድነት መመገብ አልቻልንም፡፡ አንድ ቀን ሰጥተን እንኳን መማማር፣ መመካከርና የገዳማችንን ነገር ከገዳማውያኑ ጋር መወያት አልቻልንም፡፡
ይህን ችግር ለመፍታት አስጎብኝዎች የጋራ ኮሚቴ ሊኖራቸው፣ ችግራቸውን በሰከነ፣ በሠለጠነና መንፈሳዊ በሆነ መንገድ ሊፈቱ፣ አንዳንዱንም ችግር ይቅር ተባብለው ተሻግረውት ሊያልፉ ይገባል፡፡ ከችግራችን በላይ የሆነ ጊዜ የማይሰጥ ሌላ አደጋ ከፊታችን ስላለ፣ለባሰው ችግር ሲባል የኛን መለስተኛ ችግር መፍታት አለብን፡፡‹‹ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፍ›› ይገባል፡፡ በጋራ የጉዞ መርሐ ግብራችን ማጣጣም፣ በኢየሩሳሌም ከተማ አንድ ቀን የኢትዮጵያውያንን ቀን ማክበር፣ የጋራ መንፈሳዊ ጉባኤ በማድረግ መማማር፣ ኅብረታችንን በመጠቀም የመጓጓዣ፣ የመኝታና ሌሎች ወጭዎችን እንዲቀንሱልን ማድረግ፣ ለተሳላሚዎቹ ተመሳሳይ መረጃ እንዲሰጣቸው ማድረግ፣ በመካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንም በጋራ መፍታት ያስፈልጋል፡፡
 1. የጋራ የመታሰቢያ ቀን
በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ የሚገኙት ገዳሞቻችን በመሥዋዕትነት ተተክለው በመሥዋዕትነት የጸኑ ናቸው፡፡ እነዚህን ገዳማት ለማቅናትና ለመጠበቅ ሕይወታቸውን፣ ገንዘባቸውንና ዕውቀታቸውን የሠው አያሌ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ ከዘመናት በፊት መጭው ጊዜ ታይቷቸው ቋሚ ቅርስና ታሪካዊ ሥራ የሠሩ ጠንካራ ቀደምቶቻችን ነበሩ፡፡ እነዚህ ማስታወስ ይገባል፡፡
ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ (በረከታቸው ይደርብንና) የነገሥታቱና ንግሥታቱ መታሰቢያ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ የሌሎች መኳንንታና መሳፍንት ደግሞ ግንቦት አንድ ቀን በጸሎትና በቅዳሴ እንዲታሰብ በማኅበር አስወስነው ሲሠራበት ይኖራል፡፡ እኛም ተጓዦች ደግሞ በየዘመናቱ ሲጓዙ የኖሩትን፣ ሳይደርሱ በረሃ የቀሩትን፣ በባርነት ተሽጠው የጠፉትን፣ ከመጡ በኋላም በጽናት ያገለገሉትን አባቶችና እናቶች ታሪክ የምንሰማበት፣ በጸሎት የምንዘክርበት፣ ታሪካቸውንም ለትውልድ የምናስተላልፍበት፣ ዛሬም አገልግለው በአረጋዊነት ለሚጦሩ አባቶችና እናቶች አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግበት አንድ ራሱን የቻለ የቀደምቶቻችን መታሰቢያ ቀን ያስፈልገናል፡፡
ቀደም ብሎ የጋራ የጉዞ ኮሚቴ ይኑረን ያልኩትም ይህንን የመሰለውን ለማቀናጀት ነው፡፡ አስጎብኝዎች ተመካክረው አንዱን ቀን በመስጠት፣ ጠዋት የኢትዮጵያ ቀን በኢየሩሳሌም ብለን የገዳማቱን ሁኔታ፣ በብሔራዊ ኮሚቴው የተደረገው ጥረት የደረሰበትን ደረጃ፣ ከእኛ ምን እንደሚጠበቅ፣ ለገዳማቱ በጊዜያዊነትና በዘላቂ ስለሚያስፈልገውን ነገር የምንመክርበት ቢሆን፡፡ ምሳ በአንድነት ከተመገብን በኋላ ደግሞ ‹‹የአባቶቻችን መታሰቢያ ቀን›› ብለን ታሪካቸውን በማስታወስ፣ የመታሰቢያ ሥራ በመሥራት፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ገዳማትም ርዳታ በመሰብሰብ በትምህርትና በመዝሙር የምናሳልፈው ጊዜ ቢሆን፡፡

የትናንቱ በተረሳ ቁጥር ለዛሬው የምንሰጠው ዋጋ ይቀንሳል፤ ያገኘነው ነገር እንዲሁ የተገኘ ይመስለንና እንዲሁ እናጣዋለን፤ ዛሬ እንደ እነርሱ የሚነሣ ብርቱ ጀግናም እናጣለን፣ ምሳሌ የለውምና፡፡ በተደጋጋሚ የሌሎችን በመስማት ብዛትም የራሳችንን እስከመካድ ልንደርስ እንበቃለን፡፡ በቁጭት ተነሣሥተን ለሃይማኖታችንና ለታሪካችን በጽኑ እንዳንቆምም ማበርቻ እናጣለን፡፡
በቅድስት ሀገር የጉብኝት መርሐ ግብር ውስጥ ለገዳሞቻችን የምንሰጠው ቦታ ውሱን ነው፡፡ የጉዞው መብዛትና የዐቅምም ጉዳይ ገድቦብናል፡፡ ቢያንስ አንዱን ቀን በመሠዋት እና መርሐ ግብራችንን በማሸጋሸግ ግን የቀደሙትን ውለታ መክፈል ባንችል እንኳን ‹‹ዋኖቻችሁን አትርሱ›› የሚለውን ቃል መፈጸም እንችላለን፡፡
(ይቀጥላል)
ጥብርያዶስ፣ እሥራኤል

20 comments:

 1. Dani, PDF please!

  ReplyDelete
 2. Replies
  1. I didn't get it what do you mean? Don't look at me when I ask you question, you have to comment properly intead of carelessly. God bless Meles Zanawi.

   Delete
 3. Dn Daniel, you proposed a good idea, our travel agency have to work for the benefits of the church also, not only for their business. the travel agencies have to become to coordinate and unit for helping the monasteries!! EOTC also take the lead and the coordination in collaboration with the travel agencies.

  ReplyDelete
 4. Lekomite mefeter anesash memnane Yasfelegutale,selezih gudayun yegara adergo dar lemadrse Yetesatafiwoch Teri biderge.

  ReplyDelete
 5. teruw eyta new egthabhar yebarkh edzh chegrochn bemayet ednrebareb yehulachnm gedata new !!! D/N DANIEL MASTEWHAL YABZALH AMEN

  ReplyDelete
 6. አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያልነበረንን(የሌለንን) እንዲኖረን አደረጉ የአሁኑ ትውልድ ግን…………………………….. ፈጣሪ ማሰተዋልን ይሰጠን፡፡

  ReplyDelete
 7. God bless you Dn Daniel and Let Medahnialem help us to make this idea applicable.

  ReplyDelete
 8. ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር

  ReplyDelete
 9. ሰሚ ካለ ጥሩ ነው

  ReplyDelete
 10. ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ሰውና መላእክት አንድ በሆኑበት ቅዱስ ቦታ ተለያይተን እንመለሳለን፡፡

  ReplyDelete
 11. ዳኒ በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው ችግሩ ሃሳብ ሃሳብ ነው፡
  . ሊሰራ ይችላል
  . ላይሰራ ይችላል
  . ሃሳብ ሆኖም ሊቀር ይችላል
  እና ዪህ ሃሳብ አስኪ ከሃሳብ አንዲያልፍ ትንሽ ሰው ለማነጋገር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ሞክር

  ReplyDelete
 12. DANI EGZIABHER YIBARKH BEHIMAMAT SEMON WEDE EYERUSALEM YEMIGUAZU ABATOCH YEWICHI MINIZARE LEMEWSED METEW NEBER KEHULUM GAR SAWERA YENEBEREW SILEZI GUDAY NEBER ANDU ABATIMA YENEGERUGN BETAM YASAZINAL SIGA WEDEMU ENKUAN YEMIYAKEBILUT BEDINKUAN NEW ALUGN EWNET KEHONE BETAM YASAZINAL DANI EGNA HAGERACHIN BESEMAY NEW AYDEL TADIYA KIRISTOS 1 YADEREGENIN LEMIN EGYPT ETHIOPIA TEBABILEN ENIKEFAFELALEN MASTEWALUN YADILEN AMEN.

  ReplyDelete
 13. ሰሚ ካለ ጥሩ ነው
  ሰሚ አንዲኖር ስለ ቤተክርስቴያናችን ቁመን አንይ በሕብረት እንጩህ ጌታም ይረዳናል፤ ፍሪም እናፈራለን።

  ReplyDelete
 14. እግዚአብሔር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል :: “ይህ ኮሚቴ የሃይማኖት፣ የሕግ፣ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም የዴር ሡልጣንን ገዳም ባለቤትነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚፈታ፣ ገዳሙም ጥንታዊነቱንና ደረጃውን ጠብቆ እንዲጠገንና እንዲገነባ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡” ያልከዉን እስማማለሁ :: ነገር ግን ይህንን ኮሚቴ ለማቋቋም የአስጎብኝ ድርጅቶች ኃላፊዎች ተነሣሽነቱን ይዉሰዱ ያልከዉ ትክክለኛ አይመስለኝም :: ሃላፊነቱን ቤተ ክህነት ወስዳ በትብብሩ ዙሪያ ሌሎች ተሳትፎ ቢያደርጉ የተሻለ ይመስለኛል:: ከልምድ እንደምናየዉ በሌላ ስራ የተጠመዱ ሰዎችን በኮሚቴ እናሰባስባቸዉና ስራዎች ይጓተታሉ ወይም ይረሳሉ:: ስለዚህ ቤተ ክህነት ኮሚቴዎቹን በተጠቀሱት ፍላጎቶች ዙሪያ (በዲፕሎማሲ : በህግ : በፋይናንስ በግንዛቤ ማስጨበጭያ ወዘተ) ራስዋ በምትቆጣጠራቸዉ ሰዎች የሚያስተባብሩ የኮሚቴ አባላትን በማዋቀር ብትመርጥ ይመረጣል::

  ReplyDelete
 15. I think if BEtakinat allowed it ; Mhabera Kidusan have the intellectual and power to mobilize the needed resource.

  ReplyDelete
 16. ene gin yigermegnal Ebotaw lay yalew akal silebetikirsitiyanina silegedamatu sayhon llela akal guday lemasfetsem new meserut misale patriarku enkuan ezaw bizu amet koyitew chitgirun eyawoku silezeh neger senodosu lay alakerebutim gudayun lemin? lela tiru meseran gin lemafres meruruat honual kechalk ante mokir gudayun lemasjemer beyans yihe yisera worewun titenew....akimu yalew zim bilo kuch seel llellawun halafenetun man yaskemisew , Asgobignewochum behonu enkua sira or business lemesirat new enjee yihe gudayachwum ayidelem abizagnawochu hibret, andinet&yegara neger sayizuu endet endet lehon ??? genzebinina Siltanin yedemsir adirgo lale yihe minu new hulum lezeh bareya new.....

  ReplyDelete