Tuesday, April 22, 2014

ዴር ሡልጣን፡- ዐሥር ነገሮች

ከ ሁለት ሺ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ የተገለጠው ኢየሩሳሌምን ለመሳለም የሚደረገው ጉዞ ዛሬ የሺዎች ጉዞ ሆኗል፡፡ በእግር ተጉዘው ኢየሩሳሌም ለመድረስ ሱዳንን፣ ግብጽና የሲና በረሃን ያቋርጡ የነበሩት፤ ያለበለዚያም በመካ በኩል ተሻግረው በዮርዳኖስ በኩል ይገቡ የነበሩት አባቶቻችን ክብር ይግባቸውና፣ በኢየሩሳሌም ያቆዩትን ቦታ ለመሳለምና የትንሣኤ በዓልንም በትንሣኤው ቦታ ለማክበር ኢትዮጵያውያን ከሰባ ሺ ብር በላይ እየከፈሉ ይጓዛሉ፡፡
ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የኢትዮጵያውያን ምእመናን የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዲስ መልክ የኢየሩሳሌምን ጉዞ ሲጀምር በአንድ ድርጅት ብቻ ይከናወን የነበረው ጉዞ፣ ዛሬ ከሃያ በላይ በሚሆኑ አጓጓዦች በኩል ከመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ይሰባሰባሉ፡፡ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ በሚመጡ ተሳላሚዎች የተጀመረው ጉዞ ዘንድሮ ከ27 ሀገሮች በመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደሚከናወንበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከዓመታት በፊት በአብዛኛው በሽማግሌዎችና በእናቶች ብቻ ይደረግ የነበረው ጉዞ ዛሬ ከሦስት ወር ጽንስ እስከ 94 ዓመት አዛውንት ተካትተውበት የሚደረግ ሆኗል፡፡
ከዐሥር ዓመታት በፊት የትንሣኤ በዓል በዴር ሡልጣን ሲከበር በአንደኛው የገዳሙ አጥር ጥግ ተሰባስበው ይታዩ የነበሩት ተሳላሚዎች ዛሬ ግቢው ጠቧቸው፣ መንገዶችን አጨናንቀው፣ ጠጠር መጣያ እስከ ማሳጣት ደርሰዋል፡፡ ወይም አንድ የእሥራኤል ጋዜጠኛ እንዳለው ‹‹ነጭ ጎርፍ በፍኖተ መስቀል በኩል ሲፈስ የሚታይበት ተአምር›› ላይ ደርሰዋል፡፡ ድንበር የለያያቸው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዜግነት ሳያግዳቸው፣ ሃይማኖት አገናኝቷቸው በአንድ የሚያመልኩበት፣ አንድ ማዕድ የሚቆርሱበት፣ የዘመድ ወግ የሚያወጉበት ሥፍራ ሆኗል፡፡

ይህ ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠን ዕድል ቢሆንም ከተጠቀምንበት ነገር ያልተጠቀምንበት ይበልጣል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ አስተሳሰባችን ከጠላት ተኮር ሥነ ልቡና ባለመላቀቁ ነው፡፡ ልክ ነው ግብጻውያን አሁንም በዴር ሡልጣን ገዳማችን ላይ ግፍ ይፈጽማሉ፡፡ አሁንም ችግር ይፈጥራሉ፤ አሁንም ገዳሙ እንዳይጠገን ይከላከላሉ፤ ህልውናችን ያበሳጫቸዋል፤ ብዛታችን ያንገበግባቸዋል፡፡ በግብጻውያን ምክንያት የተቀበልናቸው ብዙ መከራዎች አሉ፡፡ እንዳንሠራ የታገድናቸው ነገሮች አሉ፡፡ ግን የሁሉም ነገር መነሻና መድረሻ ግብጻውያን ናቸው ብለን መደምደም አንችልም፡፡ አንዳንዴም ‹‹እኛን የጨረሰን የራሳችን ጠማማ ነው›› እንዳሉት ዛፎች ለግብጻውያን ችግር ፈጣሪነት መነሻ እኛው ሆነን እንገኛለን፡፡
ታሪክ እንኳን እንደሚያስተምረን የዴር ሡልጣን ዋናው በር በግብጻውያን እጅ የቀረው ቁልፉ ለኢትዮጵያውያን እንዲሰጥ በተወሰነ ጊዜ በንጉሥ ምኒሊክ ተወካይና በገዳሙ ተወካይ መካከል ‹‹ቁልፉን መረከብ ያለብን እ ኔ ነኝ›› በሚል በተነሣው ውዝግብ ምክንያት ነበር፡፡ ዛሬ በየዓመቱ በስቅለት ቀን መብራት ይዘን እንለፍ አንለፍ የሚለው ውዝግብ የተፈጠረበት አንዱ ምንያት የኛው ጳጳስ በሰጡት ፈቃድ ነው፤ በገዳሙ በር አጠገብ ያሉት የብረት ቅስቶች የተገነቡት የኛው ጳጳስ በሰጧቸው ፈቃድ ነው፡፡
ግብጻውያን ጠንካራ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁመን የዴር ሡልጣንን ነገር ዓለም ዐቀፋዊ አጀንዳ እንዳናደርገው አላገዱንም፤ ግብጻውያን በየዓመቱ የሚመጡ ምእመናንን በሚገባ እንዳናስገነዝብ አላገዱንም፤ ግብጻውያን እያንዳንዱ አጓጓዥ እንደ አይጥና ድመት እንዲተያይ አላደረጉም፤ ግብጻውያን በኢትዮጵያና በግብጽ ቤተ ክህነት በኩል ድርድር እንዳይጀመር አላደረጉም፤ ግብጻውያን ለሀገሩ የሚመጥኑ አባቶችን እንዳንመድብ አልያዙንም፤ ግብጻውያን ስለ ገዳማችን ተገቢውን መረጃ እንዳናስተላልፍ እጃችንን አልቆለፉንም፤ ግብጻውያን ምእመናን ተሳላሚዎችን አስተባብረን ሥራ እንዳናሠራ አላሳገዱንም፡፡
ጠላት ሁለት ጊዜ ይጎዳሃል፡፡ የመጀመሪያው በጠላትነቱ የሚሠነዝረው ጥቃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በእርሱ እያመካኘህ ችግርህን ወደ ውስጥ እንዳታይ ማድረጉ ነው፡፡ ከሁለቱም የሚከፋው ሁለተኛው ነው ይባላል፡፡ የሁሉም ነገር ምክንያትና ሰበብ ጠላትህ ይሆናል፡፡ ሰዎችም በቀላሉ ይቀበሉሃል፡፡ አንተም ለማስረዳት ብዙ አትቸገርም፡፡ ለራስህም የችግርህ ሁሉ ምንጭ አድርገህ ትቀበለውና ሌሎች ነገሮችን አትመለከትም፡፡ አመለካከትህ ጠላት ተኮር ይሆናል፡፡

በኢየሩሳሌም ገዳሞቻችንም የሚታየው ይኼው ነው፡፡ ለማንኛውም ነገር ምክንያቶቹ ግብጻውያን ናቸው፡፡ ስለ ራሳችን ድክመት የሚያወራ የለም፡፡ ራሱን የሚወቅስም አልተገኘም፡፡ ብዙ ችግሮቻችን ግን ግብጻውያን ባይኖሩም የሚኖሩ ናቸው፡፡ ከጠባያችን፣ ከአሠራራችንና ከአካሄዳችን የሚመነጩ ናቸው፡፡ የግብጻውያኑ ችግርም መፍትሔ ያላገኘው እኛ ስለያዝነው ይመስለኛል፡፡ ነገሩን ጠበቅ አድርገን በመያዝ ብርቱ ሃይማኖታዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ ጫና ለማሳረፍ የምናደርገው ጥረት አለመኖሩ፡፡ የዴር ሡልጣን ነገር ትዝ የሚለን ለትንሣኤ በዓል ጊዜ መሆኑ፤ ከዚያ በቀር ይህን ጉዳይ ሥራዬ ብሎ የያዘ አንድም ቤተ ክህነታዊ አካል አለመኖሩ፡፡ ግብጾችኮ ጉዳዩን በፓርላማ ደረጃ በብሔራዊ ኮሚቴ ነው የሚከታተሉት፡፡ እኛኮ እንኳን ፓርላማ ቤተ ክህነት የሚያውቀው ኮሚቴ የለም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን ከኢየሩሳሌም ገዳማት በሚቀርብ ጥያቄ ይወያያል እንጂ የኢየሩሳሌም ገዳማትን ጉዳይ በዝርዝር አጥንቶ፣ የድርጊት መርሐ ግብር ቀርጾ፣ አካል አቋቁሞ፣ ከሚመለከታቸው ጋር ኅብረት መሥርቶ ዘላቂና ተከታታይነት ያለው ሥራ አይሠራም፡፡ አብዛኛው የኢየሩሳሌም ገዳማትን የሚመለከተው አጀንዳም ‹‹አቡነ እገሌ ይነሡ አይነሡ›› በሚለው ላይ የሚያተኩር ነው፡፡
በፓትርያርኮች ደረጃ በግብጽ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መካከል ውይይት ሲደረግም የኢየሩሳሌም ገዳማችን ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ የተነሣበት ጊዜ የለም ማለት ይቻላል፡፡ ቢያንስ ውይይት ለመጀመር፣ ችግሩን ለመፍታትና አንዳች የስምምነት ደረጃ ላይ በየእርከኑ ለመድረስ የሚያስችል መግባቢያ እንኳን የለም፡፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቅርቡ ወደ ግብጽ ይሄዳሉ፡፡ እስከ አሁን ባለኝ መረጃ ዴር ሡልጣን የአጀንዳቸው አካል የሆነ አይመስለኝም፡፡ ለግብጻውያን ግን ዴር ሡልጣን ከዓባይ ቀጥሎ ከኢትዮጵያን ጋር ላላቸው የዲፕሎማሲ ግንኙነት አንዱ አጀንዳቸው ነው፡፡
ይህንን በዚህ እንተወውና ለመሆኑ ወደ ኢየሩሳሌም ገዳማት የምንመድባቸው አባቶች መመዘኛቸው ምንድን ነው? የሃይማኖት ትምህርት፣ የእምነት ጽናት፣ ለጸሎትና ለአገልግሎት ያላቸው ፍላጎት፣ ለመማር ያላቸው ትጋት፣ ከአካባቢው ጋር ተዛምደው ለመኖር ያላቸው ዝግጁነት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አምባሳደር ለመሆን ያላቸው ችሎታ ይታያል? ከዐሥር ዓመታት በላይ ተቀምጠው ዐረብኛና ዕብራይስጥ የማይችሉ ከሆነ ኢየሩሳሌም መኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? አገልግሎቱ ሲሆን ከሀገር ቤት ካልበለጠ ካልሆነም እንደ ሀገር ቤቱ ካልሆነ በኢየሩሳሌም ገዳማት መኖሩ በአሜሪካ ከመኖር ልዩነቱ ምንድን ነው? በኢየሩሳሌም ገዳማችን ደረጃውን የጠበቀ፣ አባቶችን ለዓለም አቀፋዊ አገልግሎት የሚያበቃ ትምህርት ቤት ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ከሥጋዊ ዕድል በዘለለ ጥቅሙ ምንድን ነው? የራሳችን የቅብዐ ቅዱስ ማዘጋጅ፣ የዕጣን መቀመሚያ፣ የንዋያተ ቅድሳት ማዘጋጃ፣ የመስቀል መሥሪያ፣ ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ጥቅሙ በዶላር ደመወዝ ማግኘት ነው ማለት ነው፡፡
የኢየሩሳሌም ገዳማችን ቤተ ክርስቲያናችን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያጠናክሩ፣ ከአካባቢው ባለ ሥልጣናት ጋር በሚገባ ተግባብተው የገዳማችንን መብት የሚያስከብሩ፣ በልዩ ልዩ ሞያ ሠልጥነው ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ተስፋ የሚሆኑ፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን ለማወቅ የሚመጡትን ምሁራን በደረጃቸው የሚያናግሩ፣ በማንኛውም መድረክ ተገኝተው ቤተ ክርስቲያንን ሊወክሉ የሚችሉ፣ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጭ ፈጥረው የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን የሚረዱ ተቋማትን የማያፈሩ ከሆነ መነኮሳቱ ‹‹አረዳ ጠባቂ›› ከመሆን ያለፈ ለቤተ ክርስቲያን በቁዔታቸው ምንድን ነው? መቼም ይህንን ሁሉ ያላደረግነው በግብጻውያን ምክንያት ነው አንልም፡፡

በዚህ በትንሣኤ ሰሞን ከዐሥር ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ምእመናን በኢየሩሳሌም ተገኝተው ነበር፡፡ ነገር ግን እነርሱን በአንድ ጉባኤ ለማስተባበር፣ ስለ ገዳማቱ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር፣ ፕሮጀክት ቀርጾ ያንን እንዲተገብሩ ለማድረግ፣ ምእመናኑን ለማስተማርና ለማነጽ፣ ጥረት ሲደረግ አላየሁም፡፡ ከዚያ ይልቅ የሀገር ቤቱ አሠራር አልለቀን ብሎ አንዳንድ ቁራጭ ጧፍ ለመሸጥ ነበር መከራ ስናይ የከረምነው፡፡ ውኃ አዙሮ ለመሸጥ ነበር ጥረት ሲደረግ የነበረው፡፡ ምእመናኑን በሚገባ አስረድቶ፣ ዘላቂ ነገር እንዲሠሩ አወያይቶ፣ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ነገር ከመሥራት ይልቅ አንድ ሺ ጧፍ ሽጦ አንድ ሺ ዶላር ለማግኘት መድከሙ በዋናው አልጋ ላይ መተኛት ሲቻል በትራሱ ላይ እንደ መተኛት ነው፡፡
ተሳላሚ ምእመናኑም ራሳቸውን እንደ ቱሪስት ቆጥረው ተሳልሞ ለመጓዝ ከመትጋት ባለፈ የገዳሙን ሁኔታ ለማወቅ፣ ዘላቂና ችግር ፈች ሥራ ለመሥራት፣ አልከፈት ያለውን የቤተ ክህነት በር በሚገባ አንኳኩቶ ለማስከፈት አልቻልንም፡፡ አጓጓዦቹም ምእመናኑ ተገናኝተው፣ ተዋውቀውና ተወያይተው፣ በአንድ ኢትዮጵያዊ መንፈስ አንድ ሥራ እንዲሠሩ ጥረት ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ እንዲያውም ተጓዦቻቸው ባለመተዋወቅና በመፈራራት የጎሪጥ እንዲተያዩ ያደርጓቸዋል፡፡
እነዚህን ለምሳሌነት የጠቀስኳቸው በግብጻውያን ብቻ እያመካኘን በመቀመጣችን ያልሠራነው ሥራ ምን ያህል ዋጋ እያስከፈለን መሆኑን ማየት እንድንችል ነው፡፡ ግብጻውያን ርስታችንን ከመንጠቃቸው በላይ በእነርሱ እያመካኘን የኛን ሥራም እንዳንሠራ አድርገውናል፡፡ አሁን ለዴር ሡልጣን መልካም ዘመን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በግብጽ ላይ አንገቷን ቀና አድርጋለች፣ የአካባቢው የፖለቲካ ምሕዳር እየተቀየረ ነው፡፡ ምእናንም በብዛት ወደ ኢየሩሳሌም እየመጡ ነው፡፡ ከመላው ዓለምም ተሳላሚዎች እየበዙ ነው፡፡ ይህንን እግዚአብሔር የሰጠንን ዕድል ካልተጠቀምን እንነጠቃለን፡፡ ስለዚህ በአዲስ አስተሳሰብ፣ በአዲስ መንፈስና በአዲስ መንገድ መነሣት አለብን፡፡
እንዴት? በቀጣይ ዐሥር ነገሮችን እጠቁማሁ፡፡
ዴር ሡልጣን፣ ኢየሩሳሌም

51 comments:

 1. "ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት የኢትዮጵያውያን ምእመናን የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት በአዲስ መልክ የኢየሩሳሌምን ጉዞ ሲጀምር በአንድ ድርጅት ብቻ ይከናወን የነበረው ጉዞ፣ ዛሬ ከሃያ በላይ በሚሆኑ አጓጓዦች በኩል ከመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን ይሰባሰባሉ፡፡ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ በሚመጡ ተሳላሚዎች የተጀመረው ጉዞ ዘንድሮ ከ27 ሀገሮች በመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደሚከናወንበት ደረጃ ደርሷል፡፡ ከዓመታት በፊት በአብዛኛው በሽማግሌዎችና በእናቶች ብቻ ይደረግ የነበረው ጉዞ ዛሬ ከሦስት ወር ጽንስ እስከ 94 ዓመት አዛውንት ተካትተውበት የሚደረግ ሆኗል፡፡" ፈቲዉካ ፀሊካ ይህ የአስራ አንድ በመቶዉ እድገት ዉጤት ነዉ

  ReplyDelete
  Replies
  1. በስመ አብ
   የባሰ አታምጣ "ፈቲውካ ፀሊካ" አሁን ምን አመጣው እዚህ

   Delete
 2. እንኳን አደረሰህ ዲ.ዳንኤል ብዙ ነገሮችን ታሳውቀናለህና ሰላምና ጤና ከእድሜ ጋር አስተካክሎ ከነቤተሰብህ ይህስጥህ አሜን!!!

  ReplyDelete
 3. Dani hasabih betam tiru ena betekrstayanin behulet egrua enditkom yemiyaderg new hasab bicha hono endayker. endejemerkew ebakih kirstyanu keyeaktachaw teweyayto yehone neger liyadrg yemichilbet medrek bifeter tesebasbenim sinodosun chimir lemasaseb yeminchilibet mederek waga kefleh bitazegaj ....

  ReplyDelete
 4. What is the point in copying and pasting the author's words instead of writing ones own ideas?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Some people copy and past because they put what learned from the article and which part is interesting for them. Some time when people copy and paste I read that article atleast two times to understand their idea. Please don't discrage people, they have write to do what ever they want. Dani know that they are copy and past but he posted their idea. We practicing democracy so everybody has right to do what they want to do. Don't be dectater like Mengestu Hailemariam but try to think like Daneil Kbret. God bless Ethiopia.

   Delete
 5. danie lik bilehal

  hulgize egziabhar yibarkih

  ReplyDelete
 6. danie egziabhair yaqoyih tiru bilehal

  ReplyDelete
 7. ስለዚህ በአዲስ አስተሳሰብ፣ በአዲስ መንፈስና በአዲስ መንገድ መነሣት አለብን፡፡

  ReplyDelete
 8. ዘላቂ ነገር እንዲሠሩ አወያይቶ፣ ለልጅ ልጅ የሚተርፍ ነገር ከመሥራት ይልቅ አንድ ሺ ጧፍ ሽጦ አንድ ሺ ዶላር ለማግኘት መድከሙ በዋናው አልጋ ላይ መተኛት ሲቻል በትራሱ ላይ እንደ መተኛት ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. Dear Dn Daniel,

  Thank you very for your usual eagle-eyed opinions, comments and suggestions. As to Deir Sultan, I am confused when I read about it on Wikipedia: It reads "The current dispute arose in April 1970 when Ethiopian adherents entered the monastery while the Coptic followers were away for Easter rites, changing the locks to the stairs connecting it to the church below". You can read this at http://en.wikipedia.org/wiki/Deir_El-Sultan. My guess is that this text is false. If that is the case, has any one [Ethiopian] to edit this on Wiki or raised the issue [including Dn Daniel]. The world reading this text concludes that Ethiopians are the reason for the problem.

  ReplyDelete
 10. መልካም ሐሳብ ነው ዳኒ፡፡ ቀደምት አባት እናቶቻችን በሰው ሀገር ሄደው ለኢትዮጵያ እርስትነት እንደነ ዴር ሱልጣንና ሌሎችንም ቅዱሳን መካናትን በኢየሩሳሌም እንዲሰጠን ማድረጋቸው ምስጋና የሚገባቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም ለትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ ይገባል፡፡ ታዲያ ይህን ሐብት ጠንቅቆ መጠበቅ በተለያዪ የሀላፊነት እርከን ላይ ለምንገኝ የዛሬዎቹ ትውል ሀላፊነት ይሆናል፡፡ ያለውን ሙሉ ሀብታችንን ሳይቆረስ ሳይወሰድ በምሉእነቱ ይዞ መቆየት ደግሞ ይበልጥ የሚጠበቅብን ሃላፊነት ነው ብዪ አስባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል በተለያዪ ጊዜያት ለሐላፊነት ወደ ቦታው የሚመደቡ ወገኖች (ጳጳሳትን ጨምሮ) በቤተክህነቱ በኩል ተገቢው ግንዛቤ ተሰጥቷቸው ቢሄዱ መልካም ነው፡፡ ለዚህም ቢሆን ቤተክርስቲያኒቷ የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥታ ተመድበው ለሚሄዱት አካላት ከዚህ የቤት ስራ በየአመቱ ተሸንሽኖ ቢሰጣቸው አይከፋም ነበር፡፡ እንዲህ ሲሆን ሁሉም መደበኛ ስራ ሰርቶ የምደባ ጊዜው አልቆ ዝም ብሎ ከመመለስ በእነዚህ ገዳማሞቻችን ላይ አንድ እርምጃ ወደ ፊት አራምደው ቢመጡ ይቻል ነበር አሁንም ቢሆን ቢደረግ፡፡ ማንም ይሁን ማን በቤተክርስቲያን ወንበር ላይ ሲቀመጥ የቤተክርስቲያናችንን አለማቀፋዊ ተግባር ሳይረሳ ቢተገብረው ዛሬ ላይ ዳኒ ያሳሰበንን ጉዳይ ባልተከሰተ ባልሰማንም ነበር፡፡
  ስለዚህ በሀገር ቤትም ቢሆን ለህዝቡ ጠንካር ያል ግንዛቤ ቢፈጠር፡፡ ግብጾች ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ስለ አባይ ጉዳይ ብሔራዊ ጉዳይ አድረገው እንደሚያስተምሯቸው ሁሉ ለዚህ ወጣትም በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን ሌሎች አለማትም ብዙ ሀብት እንዳለው ቢያስተምሩት፡፡
  እንዲሁም ጠላት የአንድነታችን ፈተና ከማድረጋችን ይልቅ የጽናታችን ምክንያት ልናደርግ ይገባል፡፡ አባቶች፤ ጸሐፍት፤ መንግስት፤ ቤተክርስቲያን ወዘተ እባካችሁ ለነዚህ ሐብቶቻችን መከበር ስሩ፤ ትውልዱንም ባላችሁ መድረክ አሳውቁ አንቁ እላለሁ፡፡
  ዳኒም ለጫርክብን ቁጭት ቀዳሚው ተመስጋኝ ነህ፡፡
  ገበታ

  ReplyDelete
 11. መልካም ሐሳብ ነው ዳኒ፡፡ ቀደምት አባት እናቶቻችን በሰው ሀገር ሄደው ለኢትዮጵያ እርስትነት እንደነ ዴር ሱልጣንና ሌሎችንም ቅዱሳን መካናትን በኢየሩሳሌም እንዲሰጠን ማድረጋቸው ምስጋና የሚገባቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም ለትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ ይገባል፡፡ ታዲያ ይህን ሐብት ጠንቅቆ መጠበቅ በተለያዪ የሀላፊነት እርከን ላይ ለምንገኝ የዛሬዎቹ ትውል ሀላፊነት ይሆናል፡፡ ያለውን ሙሉ ሀብታችንን ሳይቆረስ ሳይወሰድ በምሉእነቱ ይዞ መቆየት ደግሞ ይበልጥ የሚጠበቅብን ሃላፊነት ነው ብዪ አስባለሁ፡፡ በኢትዮጵያ በኩል በተለያዪ ጊዜያት ለሐላፊነት ወደ ቦታው የሚመደቡ ወገኖች (ጳጳሳትን ጨምሮ) በቤተክህነቱ በኩል ተገቢው ግንዛቤ ተሰጥቷቸው ቢሄዱ መልካም ነው፡፡ ለዚህም ቢሆን ቤተክርስቲያኒቷ የረጅም ጊዜ እቅድ አውጥታ ተመድበው ለሚሄዱት አካላት ከዚህ የቤት ስራ በየአመቱ ተሸንሽኖ ቢሰጣቸው አይከፋም ነበር፡፡ እንዲህ ሲሆን ሁሉም መደበኛ ስራ ሰርቶ የምደባ ጊዜው አልቆ ዝም ብሎ ከመመለስ በእነዚህ ገዳማሞቻችን ላይ አንድ እርምጃ ወደ ፊት አራምደው ቢመጡ ይቻል ነበር አሁንም ቢሆን ቢደረግ፡፡ ማንም ይሁን ማን በቤተክርስቲያን ወንበር ላይ ሲቀመጥ የቤተክርስቲያናችንን አለማቀፋዊ ተግባር ሳይረሳ ቢተገብረው ዛሬ ላይ ዳኒ ያሳሰበንን ጉዳይ ባልተከሰተ ባልሰማንም ነበር፡፡
  ስለዚህ በሀገር ቤትም ቢሆን ለህዝቡ ጠንካር ያል ግንዛቤ ቢፈጠር፡፡ ግብጾች ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ስለ አባይ ጉዳይ ብሔራዊ ጉዳይ አድረገው እንደሚያስተምሯቸው ሁሉ ለዚህ ወጣትም በሀገር ቤት ብቻ ሳይሆን ሌሎች አለማትም ብዙ ሀብት እንዳለው ቢያስተምሩት፡፡
  እንዲሁም ጠላት የአንድነታችን ፈተና ከማድረጋችን ይልቅ የጽናታችን ምክንያት ልናደርግ ይገባል፡፡ አባቶች፤ ጸሐፍት፤ መንግስት፤ ቤተክርስቲያን ወዘተ እባካችሁ ለነዚህ ሐብቶቻችን መከበር ስሩ፤ ትውልዱንም ባላችሁ መድረክ አሳውቁ አንቁ እላለሁ፡፡
  ዳኒም ለጫርክብን ቁጭት ቀዳሚው ተመስጋኝ ነህ፡፡
  ገበታ

  ReplyDelete
 12. I could be wrong but can you ask yourself what you can help for your church?? Keep in mind I am not saying that you are not helping but I believe there is no one can solve this issue better than you. I always ask myself there are many people like, Who are writing articles and talking about this kind of issue but none of them are trying to solve/help the problem, because some time I believe if we involve our self we can make different. Of course writing and discussing is one part of the solution but I believe action is better than words or articles. Remember it could cost and some time it is difficult but been Christina is that what it take. I believe the big problem we are having today is there are many writer like you but I almost not seen you or other talking action and been responsible.

  I hope many of you writers can open your eyes and see that many people are writing books and created web site on this days. Many of them are fun and temporary news. but I think you all forgot that we/the people who are reading are becoming a big fan of you or follower and that is really scar me b/c people are not reading the bible and other spiritual book b/c its true people are more interesting to read article like your and others,, I hope you can understand me and God bless you

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes, you are wrong. You don't read Bible so you think everybody not read bible. You never did any thing but you abuse the people that inform us. If you don't participate anything how do you know that people working or not? Shame on you, you have to see your self before you order other people.

   Delete
  2. thank u for starting your comment with "I could be wrong" but it does not mean that you are right. some people like you want others to do every thing. you also want Dn. Daniel to do every thing of the church. do you think that it is possible to do so? it is unthinkable. people can participate in different ways starting from raising the issue and informing as Daniel does. others may organize events, others may do the consultancy, others may do the task of layers, others may mobilize to generate fund, etc... however, what contribution have you done till now in this or other crucial issues of the church? this is the question that you have to internalize. blaming others without doing your contribution does not bring a change. do something before blaming others who are contributing something. Daniel or his website has not also prohibited you and others from reading bible, it is your laziness. so if you are a Christian, belittle yourself, appreciate and support the works of other good workers and try to narrow the gap.

   T.A

   Delete
  3. I started by saying I could be wrong b/c I don’t believe I am perfect but I think you guys did not understand my question,, I am not saying he did not do anything or I am not blame on him, but it clear that many people write articles and still have nothing effect, let me give u an example from the oriental church’s we have more population in number but our united is very weak. And we have 2 Sino dodos (I think maybe soon it could be 2 church) if you guys see it in politics point of view I think I am 100% wrong but if you guys see it in spiritual point of view I believe people like Daniel Kibret can made big different in our church. b/c he have more capability and more sources. That why I wish that people like him can take their time and knowledge to help our church. Also they are many of us read this kind of article and check website but many of us did not read the bible that is true and that is our people problem. Don’t give me wrong but protestant read the bible better than us. But I think people don’t tolerance for other opening

   Delete
  4. I really appreciate u'r tolerance and kind response as a christian.

   Delete
  5. Please don't compare protestant and Orthodox. All protestant are educated but most of Orthodox mother, father, sister and brother are uneducated so it is hard to read and write for them. In addition that reading the bible is very important for all of us but knowledge is not leading you into heaven. I am not sure why the Anonymous person appreciate you while you are double wrong.

   Delete
 13. ጠላት ሁለት ጊዜ ይጎዳሃል፡፡ የመጀመሪያው በጠላትነቱ የሚሠነዝረው ጥቃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በእርሱ እያመካኘህ ችግርህን ወደ ውስጥ እንዳታይ ማድረጉ ነው፡፡ ከሁለቱም የሚከፋው ሁለተኛው ነው ይባላል፡፡ የሁሉም ነገር ምክንያትና ሰበብ ጠላትህ ይሆናል፡፡ ሰዎችም በቀላሉ ይቀበሉሃል፡፡ አንተም ለማስረዳት ብዙ አትቸገርም፡፡ ለራስህም የችግርህ ሁሉ ምንጭ አድርገህ ትቀበለውና ሌሎች ነገሮችን አትመለከትም፡፡ አመለካከትህ ጠላት ተኮር ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 14. Hoo!!! My God I love it so much, thank you so much Dani since I have been reading your blog I feel I know more thing about Ethiopia. I always read this blog I don’t know if other people write this kind of interesting thing. If someone knows about other people blog could you respond me please? I grew up in Addis Ababa, my family were very poor and they didn’t know about the use of visiting historical place so I didn’t get chance to visit it. I work the current government and I am in big position, if Dani wants to help your people without involving in politics I will find some place for you. If you are interested please respond for me only write yes and I will contact you. Sometimes when I read your blog I feel you don’t like this government so your position not involved with corruption. In addition that if you have any interesting strategies to create job for the poor people I will give you up to five million birr. God bless you and God bless Ethiopia.
  Sincerely Dr A.B

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ንጣት ይገድለው ነበር!

   Delete
  2. with all due Respect Dr A.B What you say is loughbable. Five million Birr? Enkuan Dn Dani Ene mehayimwa enkuan tera mehonun gebabnge. pls better nt to waste your time

   Delete
 15. ይህ ሁሉ እግዚአብሔር የሰጠን ዕድል ቢሆንም ከተጠቀምንበት ነገር ያልተጠቀምንበት ይበልጣል፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ አስተሳሰባችን ከጠላት ተኮር ሥነ ልቡና ባለመላቀቁ ነው፡፡ ልክ ነው ግብጻውያን አሁንም በዴር ሡልጣን ገዳማችን ላይ ግፍ ይፈጽማሉ፡፡ አሁንም ችግር ይፈጥራሉ፤ አሁንም ገዳሙ እንዳይጠገን ይከላከላሉ፤ ህልውናችን ያበሳጫቸዋል፤ ብዛታችን ያንገበግባቸዋል፡፡ በግብጻውያን ምክንያት የተቀበልናቸው ብዙ መከራዎች አሉ፡፡ እንዳንሠራ የታገድናቸው ነገሮች አሉ፡፡ ግን የሁሉም ነገር መነሻና መድረሻ ግብጻውያን ናቸው ብለን መደምደም አንችልም፡፡ አንዳንዴም ‹‹እኛን የጨረሰን የራሳችን ጠማማ ነው›› እንዳሉት ዛፎች ለግብጻውያን ችግር ፈጣሪነት መነሻ እኛው ሆነን እንገኛለን፡፡

  ReplyDelete
 16. የዳኒን አስተያየት በድጋሚ የሚጽፈው ዳዊት ደጋሚው ይሆን?

  አሥሩን ነጥቦችህን በጉጉት እጠብቃለሁኝ፡፡ አንዱ ነጥብ " አበሻ አብሮ መብላት እንጂ ፡ አብሮ መስራት አይችልም " እንዳይሆን?
  መንገደኛው

  ReplyDelete
  Replies
  1. እኔም ዳዊት ደጋሚ በሆንኩ

   Delete
 17. Our Church has a lot f problem, specially this days the Priest, Pops, Dicons and the preachers are not telling the truth about instead they are telling about their proud and making money out of it. Priest and Diyakons are cometing adultory( zemut) in the church and nobody wants to say any thing about I ask Dc Danel to say something since he is writing about so many thing he nevery reply it is very sad this is a BIG BIG problem to be first place this is a Ten Commandments nothing ealse we nedd to clear out our Chruch the is a big issue in UAS in Hammer Noh Kidanmehret Church in Alexandria, VA.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንደማንኛውም በምድራችን ላይ ያሉ ሀይማኖቶች ፡ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ብዙ ችግሮችን በውስጥዋ አዝላለች። በዝሙት የተለከፉ ወይም ለሆዳቸው ያደሩ የሀይማኖት መሪዎች መኖር ፡ የብዙ ሀይማኖቶች ችግር ነው። ይህንን ችግር መጋፋት የሚቻለው የሃይማኖቱ ተከታዮች ሰለመጽህፍ ቅዱስ ያለን እውቀት ሲሰፋና ፡ ቀባጣሪውን ከአስተማሪው መለየት ስንችል ፥ ብሎም አጸያፊ ነገርን እያዩ ዝም ማለት ሳይሆን ፥ መገሰጽ ስንደፍር ነው፡፡ ለመሪው ለሆድ ማደር ተጠያቂው ተመሪዎቹ ነን። ለምን ቢሉ? እነዚህ ሰዎች ነፍሳቸውን ሸጠው ፡ ዓለማዊነት ውስጥ የገቡት ፡ ሲሳሳቱ ፡ ስተታቸውን የሚጠቁም አጥተው ነውና፡፡

   በገንዘብ ስጦታ ወይም በትልቅ ድግስ እንዚህን ሰዎች ደልሎ ፡ ወደእግዜብሔር መንግሥት ለመቅረብ መሞከር ፡ በፈጣሪ እንደመቀለድ መሆኑን መረዳትን ከዚህ ድርጊት መቆጠብ ተገቢ ነው ብይ ነኝ፡፡
   መዘንጋት የሌለብን ጉዳይ ግን ፡ በጣም ቁጥራቸው የበዛ ፥ በዚህ ጉዳይ እጅጉን የሚያዝኑ ንፁህ የሀይመኖት አባቶች ሰላሉ ፥ ገጎናቸው ሆነን ብናግዛቸው ፡ ይህን መሰሉ ችግር እልባት ያገኛልና ፡ በርትተን እንሳተፍ፡፡

   Delete
 18. silasaweken Egziabher abzeto antenim ewketen yasawekih. Tatarinetehen adenkalehu.

  ReplyDelete
 19. Excellent article! But what is the real problem (I mean religious) if these Monastery is managed by the Coptic Church? Aren't we in the same religious denomination?

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአማን ነጸረApril 23, 2014 at 5:36 PM

   Z issue is not only religious.sovereignty also involves here.do u think z Muslim dominated Egypt's gvn't involvement is for z sake of religion??NO!!Hey man, emancipate ur self from mental slavery of ALEXANDRIA!!We r now free EOTC followers!!Don't be misled by proponents of His Holiness pope SHINOUDA!!By z way this pope has used all possible methods 2 uproot us from DER-SULTAN!!However u guys always try 2 glorify him in order to undermine our religious fathers!!Despite z fact that HE is a good Shepherd 4 all laity, including us, his acts on z monastery dispute and on z anointment of Patriarch 4 Eritrea w/o EOTC recognition was a crime against EOTC!!anyway let z Almighty rest his soul in peace!!!Glory 2 our fathers who make us proud in front of Christians of z world!!

   Delete
  2. I see that the whole thing is about possessions and religious politics. I thought it was religious. Now it is clear that you are struggling for earthly benefits. Sorry!

   Delete
 20. አይገርምም ! አሁን ይህን ማን አስተውሎ ያውቃል ? እግዚአብሔር ማስተዋሉን አብዝቶ ይስጥህ እኛም የበኩላችንን እንድናበረክት ለኛም ማስተዋሉን ይስጠን አሜን!

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሔር ይስጥልን ርስታችንን አንስተህ ያስተዋወቅኸን
  እንግዲህ እግዚአብሔር ከፈቀደ ከግብጽ ጥገኝነት ወጥተናል የጳጳሳት ማዕረግ ሁሉ ከአገራችን ከሆነ ብዙ ዘመናት አልፈዋል
  የአስራት አገሯን እመቤታችን ተጠብቃት ርስታችንን በጃችን ያቆይልን

  ReplyDelete
 22. በኢየሩሳሌም ገዳማችን ደረጃውን የጠበቀ፣ አባቶችን ለዓለም አቀፋዊ አገልግሎት የሚያበቃ ትምህርት ቤት ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ከሥጋዊ ዕድል በዘለለ ጥቅሙ ምንድን ነው? የራሳችን የቅብዐ ቅዱስ ማዘጋጅ፣ የዕጣን መቀመሚያ፣ የንዋያተ ቅድሳት ማዘጋጃ፣ የመስቀል መሥሪያ፣ ከሌለን ኢየሩሳሌም መመደብ ጥቅሙ በዶላር ደመወዝ ማግኘት ነው ማለት ነው፡፡

  Dear Dn.Dani tnx a lot betam siyamen yenbrewun guday anseth yetsafkiln degmo eko yemigrmew be elete siklet like papasu siyasechbechibu mewalachew anjetachinen yakoselew egna eko yehenin hulu wechi awetten yemetanew kebotaw berket agegnten lememles engi yalachewun habit beserat sayzu sele 650 shi dolar bet gezan ena enanten temamnen endilun aydelm .degmo lelaw neger egna agerachin besiklet elet sewu sitseliy sisegd enji serate tselotu sayalk weha tetu teblen weha ayshtelinm endh yale sereat keyerusalem yejemeral ende weys hige ke Eyerusalem yewetal yemilew yehon ? Jerusalem le 3 giza teguzalehu endezendero gen yazenkubet gize yelem le Abatochachin masetewal yesitlen degmo eko Areb eletm Kidame eletm sishetu yewalu ande aynet menkosatoch sigetum kidasewum enesun aymelketm ende????

  ReplyDelete
  Replies
  1. thank u Anonymous what u wrote is my observation too betam new yazenkut even I asked on one the guy who sold the water that today is sekelet yadelew yakefelal at least tselotu eskialek please weha bayeshet beye but no one heard me. Plus the eleleta and chebecha also betam betam new yasazenegn regarding betun tebaberen enesera yalut meleketu melkam bihonem seatu yachi ken aleneberechen neger gin tebaberen yehen yetebalewen bota Getachen be elete sekeletu mekerawen lemaseb ke teseyemut botawovh the 8th station bemibalew bota lay yetegezaw nebert egnan yemiakoran new ena tegagezen meserat gedetachen new endehagerem hone endehaymanot lejoch bicha bezach ken eza amanawi bota honen yegetachenen sekelet bemaseb fanta ketayu neger bemekedemu yasazenal enji

   Delete
 23. ዲ/ን ዳንኤል
  ሁል ጊዜ አዲስ ነገር ይዘህ ስትመጣ ብዙ ቁም ነገሮችን ከሚጠብቁ ሰዎች መካከል አንዱ ነኝ፡፡ ይህን ማድረግ የምትችልበት አቅሙም እንዳለህ አውቃልሁ፡፡ ግን አንድ ነገር ያሳስበኛል፡፡ እንዚህ ጉዳዮች ዳር ደርሰው በአስፈጻሚው አካል ተፈተጻሚነት የሚኖራቸው መቼ ይሆን; አሁንም ቀጣይ የምታስነብበን 10 (አስር) ነጥቦች ትዘነጋዋለህ ባልልም ምክረ ሀሳቦቹ የሚመለከታቸውን አካላትም በመጥቀስ ቢሆን እኛ ምእመናን በጉዳዩ ላይ ያለንን ግንዛቤ እናሳድጋል ብየ አስባለሁ፡፡ እግዚአብሔር የአገልግሎት እድሜህን ያርዝምልህ፤ በመንገድህ ሁሉ ይከተልህ፡፡ ስላም ሁን፡፡

  ReplyDelete
 24. Der, Dani betam teru hasab new gen ahun mefetehew endit new 'what can we do' men madereg endaleben yenegeren. lelaw kezi gar baygenagem yebefitu patriyark hawelt be Boli medehaniyalem yekomew mechi new yeminesaw yehi yehulachenem hasab new gize bekoye gezi negeru ...... yehem hasab binesa des yelegal 'I don't know if I'm wrong?'

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን ይንስል? ለመንግስት አገልግሎት በመስጠት የተሰራ ሐውልት ቆሞ ፡ ለትውልድ በማስጠንቀቂያነት ቢያገለግል ጥሩ ነው፡፡

   Delete
 25. ከዐሥር ዓመታት በላይ ተቀምጠው ዐረብኛና ዕብራይስጥ የማይችሉ ከሆነ ኢየሩሳሌምመኖር ጥቅሙ ምንድን ነው? This is more common in Ethiopia as well. for instance, many priests and others particularly in Southern Ethiopia lived for even more than 10 years! but they can't speak one word of local language. That is why many orthodox Christians changed their true religion due to lack of church knowledge! These days they are considered as parrot since no body can listen them particularly in rural areas!

  ReplyDelete
 26. አዎ ፈጥነን ተገግባራዊ ወደ ሆነዉ መፍትሔ እርምጃችንን ማድረግ ይኖርብናል ትንሳኤ ልቦና ይደርብን

  ReplyDelete
 27. በናትህ ዳኒ! በውኑ ለዚህች ቤተክርስቲያን የሚቆረቆር አባት አለብለህ ታምናለህ?
  አዕምሮህ ሳይሆን ልቡናህ ይናገርና፣ ከሆዱ በላይ ለዚህች ቤተክርስቲያን የሚያስብ አለ ፣ አንተን ጨምሮ?
  ሁላ ችሁም ከዲያቆን እስከ ጳጳስ ተራ የምትሉትን ምዕመን በማደንቆር ኑሮራችሁን ነው የ ምትኖሩት። በቃ ይሄው ነው!

  ኩሳ

  ReplyDelete
 28. ዳንኤል ሳታውቅ በጻፍከው ነገር ሳትጸጸት እንደማትቀር ነው የሚሰማኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የሚያውቁትን ቢጽፉስ? የሚያጸጽተውስ ይህኛው ንው ፡ ሆድን ሲሞሉ ኑሮ ማለፍ፡፡
   መንገደኛው

   Delete
 29. እናውቃለን ባዮች ከመተቸት ለምን አትጽፎም። እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
 30. Dn Dani EGEZIABHER yebarekeh! mechershaehen ende kedus Dawit yasmereleh!!!!!! wede Gedamat yemnemedebachew Abatoch memezengachew mendenew ? yalkew teyake ejeg emiyangebegeb new. bezu gize beteley wede wech ager yemilaku Abatoch memezengachew ejeg tekuret tedergobet litasebebet ena memezenga meseferet lezegaj yasefelegal!!!! beteley menefesawinetachewlay!! EGEZIABHER bedeferet bemenagere yeker yebelenge ena ene endemayew balehubet botamenfesawi Abatoch ke ager bet silaku melkiyachew men endehone ejeg yegermengal. menfesawit cherach yelelachew Alemawi sewe enkuan yemiyadergewen EGEZIABHEREN yemeferat tenekake yemayetayebachew nachew. lezihem wanengawmenesha Abatochu yemigemegemut and yemiyakachew sew ager bet yetkumal esu teru nachew selale becha be wech yalut sebekagubayewoch menem ayenet ketetel sayadergu yemetalu. yehe Ejeg betam yasazenal. ye EGEZIABHEREN sera be cheleta yemisera yetergeme yehun yemilewen tsenu kal eresetenewal. ye EGEZIABHER bet sera kemenem befit memezengaw MENEFSAWI mehon alemehon new enji ende alemawi drejet be Tactic ena be technic yemisera adelem ! sew Menefsawi kehone EGEZIABHEREN yemifera kehone Eweket bigolew ye eweket balebetu le Miferut tebebun endemisetachew EGEZIABHEREN meferatem yetebebe hulu mejemeriya endehone enawekalen. EGEZIABHEREN yemayefera eweketu tariya miderese sew ye EGEZIABHEREN bet astedader bibal gen eweketum senefena serawem kentu endemihonem mawek aleben. selezi wanaw netebe le EGEZIABHER bet asetedadarinet agelgayent yemimertut sewoch lay memezenga tebeke tedergo biserabet beteley wede weche yemiwetu abatoch lay betam kefetenga tenekake tedergo limertu endemigebachew lemasasebe new!

  ReplyDelete
 31. EGEZIABHER yahasubchennen yaderglene.

  ReplyDelete
 32. Dani Best, Please keep it up.

  ReplyDelete