Tuesday, April 15, 2014

የሚከራዩ አማት

(አማትና ምራት በአንድ ላይ የሚያነቡት)
አንድ ጊዜ አንዲት እናት ይህንን ታሪክ ነግረውኝ ነበር፡፡
እኔና ባለቤቴ የተጋባነው ልጆች ሆነን ነው፡፡ ያኔ እንዳሁኑ ተያይቶ፣ ተጠናንቶ፣ ሰንብቶ፣ ቆያይቶ የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ እንዲያውም የኛ ጊዜ ዘመናይ ነው ተብሎ የተወሰነ ጊዜ ትተያይና ወላጆቹ ለወላጆቿ ሽማግሌ ይልኩና፣ በስንት መመላለስ፣ አጥንትህ ጉልጥምትህ ተጠንቶ፣ ሀብት ንብረትህ ታይቶ ነበር የሚፈቀድልህ፡፡ ዛሬማ መንገድ ላይ ተንበርክኮ አንዲት የሃምሳ ብር አበባ ይዞ መለመን ነው አሉ፡፡ በኛ ዘመን በሬ ጎትተህ፣ መኪና አንጋግተህ፣ ጥሎሽ አግተልትለህም ከተሳካልህ ነው፡፡
ታድያ መጋባት አይቀርም ተጋባን፡፡ የእርሱ ወላጆች የሚያከራዩት ቤት ነበራቸው፡፡ አንዱን ቤት ሰጡንና ኑሮ ጀመርን፡፡ መቼም ፍቅርና ትዳር ለየቅል ነው፡፡ ታድያ እኛ ትዳር እንደጀመርን ባለቤቴ የልጅነት ነገር ሆነበትና ከጓደኞቹ እየተማረ ውኃ ቀጠነ ማለት ጀመረ፡፡ ባልነት ማለት መኮሳተር፣ መጎማለል፣ አንቺ እያሉ መጣራት፣ አምሽቶ መምጣት መሰለው፡፡ ይህን ጠባይ እርሱ እንዳላመጣው ዐውቅ ነበር፡፡ ጓደኞቹ ናቸው ያስተማሩት፡፡ በጊዜ ገብቶ አብረን ነበር ስንስቅና ስንጫወት የምናመሸው፡፡ እንዲያውም የኔ ባልኮ ዘመናይ ነው እያልኩ ነበር ለሰው የምናገረው፡፡ ወጥ ስሠራ እንኳን የሚያቀራርብልኝ እርሱ ነበር፡፡ በኋላ ጓደኞቹ ጠምደው ያዙት፡፡ ‹ለምን ቀሚስ አትለብስም› እያሉ መሳቂያ መሳለቂያ አደረጉት፡፡


የእነርሱን ወሬ መቋቋም ሲያቅተው እንደ እነርሱ ሆነ፡፡ ያገባሁትን ባል ወሰዱብኝና ሌላ ባል አጋቡኝ፡፡ አየህ ብዙ ሚስቶችኮ ባሎቻችንን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ስናገባ ያገኘናቸውን ባሎች ወይ ጓደኞቻቸው ወይ ወላጆቻቸው ወይም ደግሞ የሥራ ባልደረቦቻቸው ነጥቀውናል፡፡ ያላገባናቸውን ሌሎች ባሎችም አጋብተውናል፡፡ አንዳንዶቻችንኮ ከተፈራረምናቸው ባሎቻችን ውጭ ነው የምንኖረው፡፡ የኔም እንደዚያ ሆነልህ፡፡
ይህንን ሲተርኩልኝ ባልየው እያሳቁ ያዩናል፡፡ አማትዬው ደግሞ ‹‹መቼም አትረሽም አንቺ›› ይላሉ እርጅና እንኳን ብልቀነሰው ጆሯቸው እየሰሙን፡፡ እርሳቸውም ‹‹ሰው የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል›› ብለው በባላቸው ተረቱና ቀጠሉ፡፡
ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ሆነ፡፡ አምሽቶ መምጣት፣ ጠጥቶ መምጣት፣ የት እንደሄደ ሳይናገር ሶደሬና ላንጋኖ ጠፍቶ መክረም፤ የት ገባሽ የት ወጣሽ ማለት አመጣ፡፤ በእርሱ ቤት መቀናቱ ነው፡፡ ጓደኞቹ ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ እውነት አደረገው፡፡ እኔም እየመረረኝም እየሰለቸኝም መጣ፡፡
የእርሱ እናት እንዴት ጥሩ ሰው መሰሉህ፡፡ ምናለ እንደርሳቸው ያለውን አማት እንደ ካሴት አባዝቶ በየቤቱ ቢያድሉት፡፡ በዚያ ዘመን እንደ አጤ ቴዎድሮስ ቀድመው የተፈጠሩ ናቸው፡፡ ከቤታችን አይጠፉም፡፡ ምን ጎደለ? ምን ጠፋ? ነው ሐሳባቸው ሁሉ፡፡ በዚያ ዘመን አማት ልጅ ቤት የሚመጣው እንድም ሊያንጓጥጥ አንድም ሊያመናጭቅ ነው፡፡ አማት ሲባሉ ደርሰው መጥተው ሞያህን፣ ቤትህን ይገመግሙና ይዘረጥጡሃል፡፡ እርሳቸው እቴ፡፡ አንድ ቀን ክፉ ቃል ወጥቷቸው አያውቁም፡፡ ኧረ እንዲያውም ክፉ ቃል የሚባለውን ራሱን የሚያውቁት አይመስለኝም፡፡ የሚጨነቁት ለእኔ ነበር፡፡ ቁጭ ብለው ይመክሩኛል፣ ሞያ ያስተምሩኛል፣ ታሪክ ይተርኩልኛል፡፡ አቤት ቀልዳቸው፡፡ የባሌን ችግር የምረሳው በእርሳቸው ቀልድ ነበር፡፡ ከነገሩኝ በኋላ እንኳን ብዙ ጊዜ ብቻዬን እስቅ ነበር፡፡ ታድያ የቤቱን ችግር ነግሬያቸው አላወቅም፡፡ ለምን ይጨነቁ ብዬ፡፡
በኋላ ግን ባሰብኝ፡፡ ‹‹ቡችላው ሲጮህብሽ ዝም ካልሽው ውሻው ይነክስሻል›› ይባላል፡፡ ጭቅጭቁን ስታገሠው ጊዜ ዱላ ጀመረ፡፡ እርሱን ግን መቋቋም አቃተኝ፡፡ ሲብስብኝ ለእማማ ነገርኳቸው፡፡ አረሩ፣ ደበኑ፡፡ ምን አድርገሽው ነው እንኳን አላሉኝም፡፡ እስኪመጣ ድረስ አብረውኝ ቁጭ አሉ፡፡ አጅሬው አገር ሰላም ነው ብሎ ማታ ነበር የመጣው፡፡ እናቱን ይወዳቸዋልም ያከብራቸዋልም፡፡ ለእናት ለአባቱ አንድ ልጅ ነው፡፡ ከአባቱ ይልቅ እናቱን ነበር የሚፈራው፡፡ እርሳቸውን እንኳን ልጃቸው የሠፈር ሰው እንደ ንጉሥ ነው የሚያከብራቸው፡፡
ሲመጣ እሳት ጎርሰው እሳት ልሰው ጠበቁት፡፡ ‹‹አንተ ይህችን ትመስል ልጅ ያጋባንህኮ ተንከባክበህ፣ አክብረህ እንድትይዛት ነው፡፡ እንድትጫወትባት አይደለም፡፡ በእርሷ ላይ ነው ዱላ የምታነሳው፣ በእርሷ ላይ ነው አምሽተህ የምትመጣው፡፡ አየሁህኮ፣ በዓይኔ በብረቱ አየሁህ፡፡ ይህችን ትመስል ልጅ እንድታበላሽ አልፈቅድልህም፡፡ እኔ ጥሩ ሰው መስለህኝ ነበር የዳርኩልህ፡፡ ለካ እንደዚህ ሆነሃል፡፡ በይ ተነሽ፤ እኔ ምን የመሰለ ባል ፈልጌ እድርሻለሁ፡፡ ያዥ ልብስሽን›› አሉና ያን ጊዜ ሞባይል የለም በቤት ስልክ ለባላቸው ደወሉ፡፡ ባላቸው ፔጆ መኪናቸውን ይዘው መጡና ተነሥቼ ወደ አማቴ ቤት፡፡
እዚያ ስደርስ የእንግዳ ክፍል ተከፈተልኝ፤ ልብሴ ተጣጥፎ ተቀመጠልኝ፡፡ ‹‹አይዞሽ የኔ ልጅ፤ እርሱ የእኔ ልጅ አይደለም፡፡ ልጄ አንቺ ነሽ፡፡ እንኳን መምታት ዘወር ብሎ ሊያይሽ አይችልም›› ተባልኩ፡፡ መቼም የእርሳቸውን ነገር አውርቼ አልጠግበውምኮ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉኝም፡፡ የእኔ እናትና አባትማ ናዝሬት ስለነበሩ እንዲህ በቶሎ መምጣት አይችሉም፡፡ እናቴም ‹‹ምን ከእኔ የበለጠ እናት አግኝተሻል፤ እኔ ምን አደርግልሻለሁ›› ነበር የምትለኝ፡፡
ባለቤቴ ጨነቀው፡፡ ምን ያድርግ፡፡ መብረቅ የቀላቀለ ዝናብ ነው የወረደበት፡፡ እናቱን ያውቃቸዋል፡፡ አይወስኑ እንጂ ከወሰኑ ማንም አይመልሳቸውም፡፡ እንደፎከሩት ለሌላ ቢድሯትስ ብሎ ፈራ፡፡ማን ተከራክሮ ይመልሳቸዋል፡፡ እንደ ዘንድሮ ባልና ሚስት ፍርድ ቤት መሄድ ያኔ አይታወቅ፡፡ ምን ያድርግ? ወስከንቢያው ነው የተደፋበት፡፡ ከአንድ ሳምንት በኋላ የእርሱ ሽማግሌዎች የነበሩት ታላላቅ ሰዎች መጡ፡፡ እማማ እሽ ሊሉ ነው፡፡ ‹‹ልጄን እንዲያበላሽ አሳልፌ አልሰጠውም፡፡ ጓደኞቹ ካዋጡት ይዳሩት፡፡ እኔ የሚሳደብና የሚደባደብ ልጅ አልወለድኩም፤ አላሳደግኩም፡፡ ይቺን ትመስል ልጅ ብንድርለት በእርሱ ብሶ ሊማታ፡፡ የለም የለም፤ ልጄን እኔ ምን የመሰለ ጠባይ ከመልክ የተሰጠው ፈልጌ እድራታለሁ እንጂ እርሱማ አይጫወትባትም›› ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ የእኔ እናት እንጂ የእርሱ እናት አይመስሉም ነበር፡፡ ሽማግሌዎቹም ተጠራጠሩ፡፡ እኛ ቤት የመጡ ነበር የመሰላቸው፡፡ እማማኮ ስለ ምራታቸው የሚያወሩ አይመስሉም፡፡
በሁለተኛው ሳምንት አጅሬ ለካ እናቴ ጋር ደውሏል፡፡ ስትሰማ ደነገጠች፡፡ ለአባቴ ነግራው ሲበሩ መጡ፡፡ ከቤት መውጣቴን ሰሙ፡፡ ደግሞ ወጥቼ የገባሁት አማቶቼ ጋ፡፡ ጉድ ተባለ፡፡ አቤት እማማ የሠሩት ሥራ፡፡ የእርሱ እናት እኔን አልሰጥም ብለው የእኔ እናትና አባት ለእርሱ አማላጅ ሆነው መጡ፡፡ ተገላበጠ፡፡ እማማ እንደ ባሕሉ አስተናገዱና ምን ልታዘዝ? አሉ፡፡ ‹‹ልጃችሁ ሽምግልና ልኮን ነው›› አሉ፡፡ እማማ አልሰጥም ብለው እምቢ አሉ፡፡
‹‹ምንም ብትወልዷት አልፈቅድላችሁም›› አሏቸው፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲለምኑ ዋሉ፡፡ አባቴ ብልሃተኛ ነው፡፡ ‹‹እንጥራውና እዚሁ ዋስ ጠርቶ ቃል ይግባ›› አለ፡፡ እማማ ተስማሙ፡፡ ተጠርቶ መጣ፡፡ እየተንቀጠቀጠ ነበር የገባው፡፡ ወዳደገበት ቤት የሚገባ አይመስልም ነበር፡፡ ‹‹ሁለተኛ አንዳች ነገር አልናገራትም፣ እጄን አላነሣም፣ አላመሽም፣ አልጠጣም፣ ከቃሏ አልወጣም ብለህ ቃል ግባ›› አሉት እማማ፡፡ ቃል ገባ፡፡ ዋስ ጥራ ተባለ፡፡ ዋስ ማንን ቢጠራ ጥሩ ነው፤ የእኔን አባት፡፡ እዋሰዋለሁ አለ አባቴ፡፡ ‹‹በል ሁላችንምም ጉልበት ሳም›› አሉት እማማ፡፡ ሳመ፡፡ ‹‹አንድ ነገር ቢልሽ ደውይልኝ፤ ልጄን እወስዳታለሁ፡፡›› አሉ እማማ በማሠሪያው፡፡
እኔም ቤቴ ተመለስኩ፡፡ ኩሽ የለ፤ ዱሽ የለ፡፡ ሰላም፡፡ ጠባዩ ለወጥ ሲል ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› ነበር የምለው፡፡ እንዲህ ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› እያልኩ ይኼው ዐርባ ዓመት ኖርን፡፡ ስናስበው እንስቃለን፤ ለእኛ በሰላም መኖር ምክንያቱ እማማ ናቸው፡፡ ብዙ አማቶች ለልጃቸው አግዘው ከምራታቸው ጋር ነው የሚጣሉት፡፡ እንዲህ እንደርሳቸው ከዝምድና በላይ የሚያስብ አይገኝም፡፡ እናቴ ለእኔ በትረዳ ምን ይገርማል፡፡ አማቴ እናት ሲሆኑ ግን እንዲህ ትዳርን ያዘልቃል፡፡ እርሱማ ልጃቸው ነው፡፡ የት ይሄድባቸዋል፡፡ አሁን አሁን ነገሩ ሲነሣ ‹‹እማማ ግን እውነት ለሌላ ሊድሩኝ ነበር›› እላቸዋለሁ፡፡ ‹‹ባክሽ ላስፈራራው ብዬ ነው፡፡ ስቆርጥ ያውቀኝ የለ፡፡ ጉድ ትሠራኛለች ብሎ ነውኮ የፈራው፡፡ እናቱ ሚስቱን ወሰዱበት ቢባል እነዚህ ጓደኞቹ የሚለቁት ይመስልሻል? ጳውሎስ ኞኞ ነበር በጋዜጣ የሚያወጣው›› ይላሉ እየሳቁ፡፡
መከራየት እኒህን አማት ነበር፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

39 comments:

 1. የዘንድሮ አማትና ምራት እንኳን አብረው መላ ሊፈጥሩ ቀርቶ መላ ፈጥረው ማጣላት የተለመደ ተግባራቸው ነው ፡፡ የሚባለውን አልሰማህም መሠለኝ ዘመዶቹን የጨረሰ ፣በተለይ እናቱ ካረፈች ሰባት አመት ሞልቷት ቁርባኗን ያስቀረበ ቢገኝ ይመረጣል ፡፡ ስለዚህ አማትና ምራት የሚያነቡት የሚለውን ጊዜ ለማምጣት የ17ኛ ክፍለ ዘመን ሠው ለመሆን እንደገና መሠራት ያስፈልጋ እንጂ አሁን ያለንበት ክፍለ ዘመን ለአንተ የሚነገር አይደለም ትዳሩ በሜዳ ፍቅሩ በሜዳ እንደዛው ፀቡም በሜዳ ስለሆነ ለዘመኑ ትውልድ የሠራዊት ጌታ ይድረስለት እላለሁ ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በዚህ ዘመንም ወርቅ የሆኑ እናቶች አሉ።

   Delete
 2. ሰላም ዲ/ን ዳንኤል
  በእውነት ይህን የገለጹልህ እናት እድል ቀንቷቸው አንተን አግኝተዋል ለአሁኑ ትውልድም እንደ ተአምር ይታይ ይሆናል፡፡እኔም የማውቃቸው የገጠር እናቶች ነበሩ፡፡ነበሩ…ነበሩ ብቻ ምን ያደርጋል!! አሁንም ትንሽ ናቸው እንጅ አሉ፡፡ እናም አሁን ይከራዩ ቢባልስ ማን ዋጋቸውን ይችለዋል? ብለህ ነው ግን ዳንየ አማትና ምራትን በጥላቻ እንዲታወቁ ያደረጋቸውና በፈሊጥ ሁሉ አማትና ምራት ያስባላቸው የተፈጥሮ ሆኖ ነው? እኔ ግን ባልና ሚስት ያላቸው እውነተኛ የወላጅ እና የትዳር ፍቅር ጠማማውን ያቀናል ብየ ነው የማስበው ስለሆነም ባለትዳሮች ቅድሚያ ራሳቸውን ቢያዩ አማቶቻቸውንም ቢያከብሩ ጥሩ ነው፡፡አማቶችም የልጅ ባሎቻቸውንና የልጅ ሚስቶቻቸውን በቀና ቢያዩዋቸው ጥሩ ፈሊጥ ይመጣ ይሆን ይመስለኛል፡፡ አንተን ግን ቃለ ሕይዎት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 3. Ewnetem,Yemigng kehone ,Yegrmal.

  ReplyDelete
 4. እውነት ነው አማትና ምራት በአንድ ላይ የሚያነቡት

  ReplyDelete
 5. ቡችላው ሲጮህብሽ ዝም ካልሽው ውሻው ይነክስሻል

  ReplyDelete
 6. ኩሽ የለ፤ ዱሽ የለ፡፡ ሰላም፡፡ ጠባዩ ለወጥ ሲል ‹‹ለእማማ እደውላለሁ›› ነበር የምለው፡፡

  ReplyDelete
 7. amlak yibarkachw yezihi ayinet tiwild new yetefw .

  ReplyDelete
 8. የዘመኑ ትዳር የሚስፈልገው ይህ ነው፡፡
  አማት መከራየት
  ግዚከስ

  ReplyDelete
 9. አማት እና ምራት የተለውን ተረት የያፈረሰ መልካም ታሪክ፡፡

  ReplyDelete
 10. ዲን፡ እግዚአብሔር ይባርክህ! እርግጥ ነው! አሁንም ብዙ ሰዎች አሉን እኮ አስተማሪ፣ ሞዴል የሚሆኑ፣ ለምን ተስፋ እንቆርጣለን! የእኔ አባት ከባለቤቴ ጋር ነው የሚደዋወሉት፤ ምስጢር የሚያወሩት፣ እርሷ ከገጠር ና እና ትንሽ አርፈህ ትሔዳለህ ትለዋለች፣ እርሱ ደግሞ የቻለውን ሁሉ በአርሶ አደር አቅሙ ለእርሷ የማያደርግላት ነገር የለም፣ ስሟንም እናቴነሽ ብሎ ነው የሚጠራት፤ ከእለታት አንድ ቀን ለምን እናቴነሽ አልካት ብለን ጠየቅነው፡፡ መልሱ እንዲህ ነበር - የእኔም የልጄም የሁለታችንም እናቶቻችን ከዚህ ዓለም የሉም፣ እናም ልጄ ሚስት ሳይሆን እናት አገኘ ብዬ ነው አለ፤ በእውነትም እናቱን አግኝቷል አለንና ተሳሳቅን፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የእኔም አማት በጣም የምታስበው ለእኔ ነው፡፡ እኔ በአብዛኛው የመስክ ስራ እወጣለሁና ሁልጊዜ የምትለው ልጄ ምን ሆኖ ይሆን? ምነው ዘገየ እያለች እንደእናቴ ነው የምትጨነቀው፡፡ በቅርቡ ለረዥም ጊዜ በስራ ምክንያት ሳንገናኝ ቀርተን ልጄ ናፈቀኝ እያለች ነው፡፡ ሰለዚህ ለእኔ አማትና ምራት እንደ አይጥና ድመት ናቸው ሲባል ስሰማ ሁልጊዜ አዝናለሁ፡፡ በእርግጥ የሚጣላ የለም እያለሁ አይደልም፤ ነገር ግን በጣም ከእኛ በላይ ስለእና የሚያስቡ እናቶች/አማቶች አሉን፡፡ በተጨማሪ ደግሞ እንዲህ እንዲሆን የእኛም አስተዋጽኦ መኖር አለበት፡፡
  አመሰግናለሁ!!

  ReplyDelete
 11. በጣም ደስ የላል ነገር ግን አንዳንዶች ሚሰቶች ሴጣን ናቸው ልጅናእናትን ዋሽተው ያጣላሉ
  ልክ እንደኔ አጎት ሚስት

  ReplyDelete
 12. Happy Easter for you, your family & your blog members. I feel I am the luckiest person because of I know you. You don’t know me but you messages has been changed my life every day. I love you so much and God bless you.

  ReplyDelete
 13. Thank you and God bless you.

  ReplyDelete
 14. My mom always says "its you who makes the in-laws good . Treat them like family and they will treat you like one."

  ReplyDelete
 15. Minewu Dani? ye Amat chigr ale endie? /0/

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please think like human being. He is not writhing about him self, He wrote for us. Do you know almost 90 million people live in Ethiopia. So it may not apply to you but it works for other. I don't think so you understood them message. You have to go back greade one to learn reading other wise you will continue with this narrow mind. You may think you are smart by hurting other people feeling but I am tell you that you are so dum. I belive you are older than 20 years old but you thing two years old. You will never change your curructer unless you die. The only solution for you to bring change you have to die. I wish to know your mother and father how they raised you. I guess they are arogant and carless for their son or dauther other wise you don't write this kind of stupid words on this blog. I belive you don't belive in God and other thing as well. I think if you are human being you don't think this way. i love Dani, he is my HERO. For me Dani is King of the world under the GOD.

   Delete
  2. You your self don't have to say bad words about the others every one has his own though. You word is not sound like a Christian Dani can be your hero that's fine but you don't have to insult others who has a deferent opnion.

   Delete
 16. ዳኔ መንፈስ የሜያድስ መስተዋል ነው ። ኑርልን!!!

  ReplyDelete
 17. Dani ,
  Arif metatif nech!
  Ante Gin Agibitehal?
  Lastebisih biyee neew!

  ReplyDelete
 18. daniel endezih ayenetun maheberaw nuro nek neger setetseg new yemiyamerebeh.... doereso gin sele mahibere kidusan awaki negn asabi negn yemetelewen neger ebakehen akum... mengedehen kenesu leyeteh wetehal selezih enesun tewena yerasehen sera becha sera

  ReplyDelete
 19. ይህን ጽሑፍ ሳነበው እነደ ሩትና ኖኀሚን ታሪክ ውስጤ እየተቃጠለ ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ የአማትና የምራት ፍቅር ለተሠጣቸው እንጂ በአብዛኛው ዋዛ ስላልሆነ ነው፡፡ እርስዋ የባልዋን ቤተሰብ ማየት እንደማትፈልግ ሁሉ የባልዋ ቤተሰብ (በተለይ አማት) የልጃቸውን ሚስት የሚተቹበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. መከራየት እኒህን አማት ነበር፡፡

  ReplyDelete
 21. የትንሳኤ እለት የግራ ጎን ዐጥንት ሚስት መሳይ ጓደኛዬ ይህች ናት ብዬ ለእናቴ አስተዋወኳት።

  ዝናብ በመብረቅ እንዲታጀብ እንደጉድ በምረቃ ታጀብን

  ፍቅራችሁ ይለምልም
  ለትዳር ያብቃችሁ
  ውለዱ ክበዱ
  አሳ ከባህር፤ ሥጋ ከነፍስ ውጪ ምውት ነውና ነፍስና ሥጋ ሁኑ!

  አዳምን ሄዋንን አንድ ያደረገ እግዚአብሄር አንድ ያድርጋችሁ! እያለች እንደጉድ በማዘርኛ መረቀችን!

  ጉልበት ስመን ተነሳን።

  ይህች ነገር በሀገራችን ብትለመድ እንዴት አሪፍ ነበረች አልኩ በሐሳቤ።

  በሰለጠነው ዓለም ወላጆች ለልጆቻቸው እጅግ ቅርብ ናቸው። ልጆቻቸው የፍቅር ጓደኛ ሲይዙ ወላጆች ከልምዳቸ ያካፍላሉ። እኛ ሀገር ደግሞ አባት ልጁን ከወንድ ጋ ቢያያት ምን እንደሚፈጠር አስቡት! ጎረምሳው ደግሞ እህቱን ከወንድ ጋር ባይሽ እግርሽን እሰብርልሻለሁ ይላታል። ሁለቱም ሴቲቱ ችግር ላይ እንዳትወድቅ ከመሳሳት የተነሳ ቢሆንም ሁለቱም የሰለጠነ መንገድ አይደሉም።

  በሰለጠነው ዓለም ሔዋን ቀድማ የተፈጠረች እስኪመስል ቅድሜያ ለሄዋን ይባላል። በሀገራችን ደግሞ ሴትን ማክበር መሞት የሚመስላቸው በሰለጠነ ዘመን ያልሰለጠኑ ብዙ አሉ። ሴት ልጅ ብታጠፋም ባታጠፋም በቀን አንድ ጊዜ መገረፍ አለባት የሚሉም ሰዎች እንዳሉ ሰምተናል። ሴትን አላከብርም አልክን? ሴት ባትኖር እንዴት ትወለድ ነበር ? መቼስ እንደ ዶሮ ከእንቁላል አትፈለፈል!

  በህብረት ቅድሚያ ለሴት ብንልም ቅድሚያ ሰጥተን ጠቅላይ ሚኒስትር አላደረግናትም።

  ክብርት እናቴ ትዳር ምን ማለት ነው? ብላ ጠየቀችን።

  ክብርት ሚስት መሳዬ እንዲህ ስትል መለሰች፦ ትዳር ማለት እንደ አዳምና ሄዋን በገነት በለመለመ መስክ አበባ እየተወራወሩ መኖር ይመስለኛል አለች።

  ልጅ ዮናስ አንተስ?

  ትዳር ምን እዳ ነው
  ከገነት ተባሮ ሲኦል መግባት ነው ሲባል እሰማለሁ አልኳት።

  እናቴም መልሳችን ግራና ቀኝ ገባት። የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ ብላ ተረተችብን።

  ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል አለች እናቴ ቅር እንዳላት እንዳይታወቅባት ፍግግ እያለች። እውነተኛ ሚስት ባልዋን ትወልዳለች አሉ ብላ ወደ ጓደኛዬ አየች። በሴተኛ ቋንቁዋ ተግባቡ መሰል ጓደኛዬም ፈገግ አለች።

  የእናት ዓለም ምክር ቀጠለ ፦

  የትዳር ጣርያው መነጋገር መግባባት ሆደ ሰፊ መሆን ነው።

  የትዳር ማገሩ መተማመን ነው።

  የትዳር መሰረቱ ፍቅርና መተሳሰብ ነው።

  =//=

  የማይሞተው ሞተ
  በመቃብር አደረ
  ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ

  የማይሞተው ፍቅራችሁ ሞተ?
  ቤታችሁ ፈርሶ በሰው ቤት አደራችሁን?
  እንግዲያውስ ትንሴኤ ነውና የሞተው ፍቅራችሁ ይነሣ!

  ReplyDelete
 22. አያልቅበት ዳንኤል ጥሩ ነገር እስነበብከን አመስግናለሁ፡፡
  እኔ ግን ማንበብ ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ጋርም በጉዳዩ ተነጋገሬ ነበር፡፡
  የሚከራይ ምራት የሚለውን ጽሁፍ ለአቶ ሸንቁጤ\ቤቱን ያከራየኝ ግለሰብ ነው\ አጫወትኩትና እንዲህ አለኝ፡፡ ለምን ይመስልሃል በአሁኑ ወቅት አማት እና ምራት ግጭቱ እሰፋ የመጣው?
  በድሮም ጊዜ የለም ማለቴ አይደለም አለኝ፡፡ ዝም ስል እንዲህ ብሎ እራሱ መለሰው፡፡
  ወጣቱ ዘመኑ በአመጣው ሁኔታ የትዳር ጋደኛውን የሚመርጠውና የሚወስነው እራሱ ነው፡፡እራሱ ፈልጎና ፈቅዶ የሚያመጣትን ወይም የመጣውን ስለሆነ ቤተሰብ በልጁ ወሳኝ ጉዳይ ላይ ስልጣኑ እና ከሃላፊነቱ ስለተነሳ ቅሬታ ማሰደሩ አይቀርም፡፡
  በመሆኑም በልጅ በኩል የሚመጣ ባል እና ይምትመጣ ሚስትን ዘር፣ባህሪ፣ሙያ፣ችሎታ እና የገቢ አቅም ማወቅና መፈተሽ ይጀምራሉ፡፡ በዚህም አቃቂር ማውጣት በመፈተሽ እነርሱ ከፈለጉት ወይም ለልጃቸው ቢሆን ብለው በምናብ ከሚያስቡት ልጆቻቸው ካመጣቸው ባል ወይም ሚስት ጋር አነጻጸረው ሲመዝናቸው አብዛኛውን ጊዜ ፈተናውን አያልፉም፡፡ለዚህ ነው ጭቅጭቁ የሚሰፋው፡፡እዚህ የነገርከኝ ታሪክም ጥሩ ልብወለድ ታሪክ የመሰለህ ለዚህ ነው ፡፡ የሚስት መረጣው የቤተሰብ እጅ አለበት አለኝ፡፡የድሮ ሰው ጥበብ ይገርማል አለ አክሎ፡፡ ጨምሮም እንዲህ አወጋኝ፡፡
  በድሮ ጊዜ አባት ለልጃቸው ሚስት ያመጡለታል፡፡ልጅም በአፍላው ተደሰተና ወረቱ ሲይልቅ ሚስቱን አባቱን ተናግሮ ማበረር ፈለገ፡፡ዘዴንም አዘጋጀና እንዲህ አላቸው አባቱን፡፡ አባቴ ይች ያመጣህልኝ ሚስት የበቅሎዋን ጠፍር \ዘሀብ\ በላችው ይላቸዋል፡፡አባትም በመገረም ታዲያ ሌላዋ ከመጣች የባሰ የበቅሎውን የልጓሙን ብረት ነው የምትበላው፡፡ ስለዚህ እችውን ጠብቀህ መያዝ ይሻልሃል አሉት፡፡

  ReplyDelete
 23. I will be this kind of in-low for my dauther

  ReplyDelete
 24. የኔስ አማት የተባረኩ ናቸው፡፡ እንደጓደኛ ነው ሚስጢሬን ሁሉ የማጫውታቸው ልጃቸው እንኳን ሲያስከፋኝ እነግራቸዋለሁ ትዳሬን ትቼ እንዳልወጣ በእሳቸው ምክርና በሚሰጡኝ ፍቅር ከባለቤቴ ጋር አንድ ላይ አለሁ፡፡ የኔ አማት ለኔ ጥሩ እናቴ ናቸው፡፡ አማቶች ጥሩ አይደሉም ከማለት በመጀመሪያ እራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡  ReplyDelete
 25. በቅድሚያ ይህንን ትምህርት አዘል ገጠመኝ በማካፍልፍ ምስጋናዬ እጅግ ከፍ ያለ ነው
  በመጽሔት ላይም ብወጥም እንደ እኔ ለማግኘት የምይችሁ ቁትራችን ትንሽ አይሆንም:: አስደሳች ትምህርት ሰጥ እና የምያስቀናም ታርክ ነው:: ፍቅርም ትግስትና መተሳሰብኝ የተጎናጸፈች መሆን እንዳለባትም ያስረዳናል

  ReplyDelete
 26. Endihe yalu Amat ayasatan!!!

  ReplyDelete
 27. Thank you , you show us the way of the life we are using.
  but from here we can learn more things it need commitment to to live with every body.

  ReplyDelete
 28. የእኔም አማት እንዲህ ፍቅር ናት። ከልጇ አስቀድማ የምትሰማውና የምታነሳው እኔን ነው። በዚህ ዘመን ሙሉ ለሙሉ የለም ማለት አይቻልም

  ReplyDelete
 29. dani betam enameseginalen yihin yemesel kum neger endezich yale amat yabizalin

  ReplyDelete
 30. alemtsehayworku@gmail.comSeptember 5, 2014 at 5:09 PM

  Egziabher yestelen

  ReplyDelete
 31. Emama gari edewilibihalehu
  I really enjoy this article thanks
  Dear Daniel

  ReplyDelete