Sunday, April 13, 2014

‹‹እግዚአብሔርስ ምን አለ?››

 click here for pdf
ሰሞኑን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ‹‹ሊያፈርሱት ነው›› የሚል ዜና በኅትመት ሚዲያዎችም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይታያል፣ ይሰማል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍት ግን አንድ መንፈሳዊ ተቋም ሊፈርስ የሚችለው በውጭ ኃይል ጫናና ዐቅም ሳይሆን በውስጣዊ ምክንያቶች መሆኑን ይነግሩናል፡፡ ኢየሩሳሌምን ናቡከደነፆር ያፈረሳት ናቡከደነፆር ኃያልና ተዋጊ ስለነበረ አይደለም፡፡ የባቢሎኑ ናቡከደነፆር መሣሪያ እንጂ መነሻ አልነበረም፡፡ ኢየሩሳሌም የፈረሰችው እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን አሳልፎ ስለሰጣት ነበር፡፡ ኢየሩሳሌም የቃል ኪዳን ከተማ መሆኗ ቀርቶ ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ የሚቀልዱባት፣ ካህናቱም በአገልግሎታቸው የሚያሾፉባት ከተማ ሆነች፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ ለዚህም ነበር ነቢዩ ዳንኤል በጸለየው ጸሎት ላይ ‹‹ኃጢአትን ሠርተናል፣ በድለንማል፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ባሪያዎችህንም ነቢያትን አልሰማንም›› በማለት የገለጠው፡፡
አሁንም የሚጠቅመን ነገር እግዚአብሔር ለሌሎች አሳልፎ እንዲሰጠን የሚያደርግ ነገር ሠርተናል ወይስ አልሠራንም? የሚለውን ማየት ነው፡፡ ለመዋጥ የሚያበቃ ምክንያት ከኛ ዘንድ ከሌለ በቀር አንበሳው ስላገሣ ብቻ አይውጠንም፡፡ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር መሆናችንን ርግጠኞች እንሁን፡፡ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ለመሆኑ ርግጠኞች ነንና፡፡ ውስጣችን ለእግዚአብሔር የተመቸ ለመሆኑ ርግጠኞች እንሁን፣ እግዚአብሔር ለእኛ የተመቸ ነውና፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ እንሁን፡፡ በክርስትና ውስጡ ውጩን ይስበዋል እንጂ፣ ውጩ ውስጡን አይስበውም፡፡ ‹‹ዝናብም ወረደ፣ ጎርፍም መጣ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው በዐለት ላይ ስለተመሠረተ ግን አልወደቀም›› ይላልና፡፡ ያልወደቀው ስላልተመታ ሳይሆን መሠረተ ጽኑዕ ስለነበረ ነው፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዐርፈው አቡነ ቴዎፍሎስ ዐቃቤ መንበር እያሉ ቤተ ክህነቱ ይታመስ ነበር አሉ፡፡ የቤተ ክህነቱ የዘር አስተሳሰብ እያቆጠቆጠ የመጣበት ዘመን ነበርና ‹‹ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆን?›› ከሚለው ይልቅ ‹‹ቀጣዩ ፓትርያርክ ከነማን ወገን ይሆን?›› የሚለው ብዙዎችን የሚያስጨንቅበት ጊዜ ነበር፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ እንደ ዘመነ ሴዴቅያስ የሐሰት ነቢያትን በሆኑት በመሰል ባሕታውያን በኩል ‹ቀጣዩ ፓትርያርክ እገሌ ነው፣ ራእይ አይቻለሁ›› ያሰኙም ነበር፡፡
በወቅቱ ዐቃቤ መንበር ለነበሩት ለአቡነ ቴዎፍሎስ ብዙ ሰዎች እየሄዱ ‹‹እገሌ ፓትርያርክ ቢሆኑ፣ ሕዝቡ እገሌን እያለ ነው፣ መኳንንቱ እገሌን እያሉ ነው፣ ባሕታውያኑ እገሌ ይሆናሉ ብለው ትንቢት እየተናገሩ ነው፣ ቤተ ክህነቱም እገሌን እያለ ነው›› እያሉ ይነግሯቸው ነበር፡፡ ሁሉንም የሰሙት አቡነ ቴዎፍሎስም ‹‹ባሕታውያኑም፣ ሕዝቡም፣ መኳንንቱም፣ ቤተ ክህነቱም ያሉትን ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔርስ ምን አለ?›› ብለው ጠየቁ ይባላል፡፡
አሁንም የሚጠቅመው ከልዩ ልዩ ቦታ በሚነፍሰው ነፋስ መሸበር ሳይሆን እንደ አቡነ ቴዎፍሎስ ‹‹እግዚአብሔርስ ምን አለ?›› ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ ሁሉም የየራሱን ሊወስን፣ ሊፎክር፣ ሊነሣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ካልወሰነ ግን የሚሆን አንዳች ነገር የለም፡፡ የእግዚአብሔርን ውሳኔ የሚያመጣው ደግሞ የወደረኞቹ ኃይል ሳይሆን የራሳችን ስንፍና ነው፡፡
ታዋቂው ገጣሚ ጸጋዬ ገብረ መድኅን በጻፈው የቴዎድሮስ የመቅደላ ስንብት ላይ ‹‹ከሠራሁት ነገር ይልቅ ያልሠራሁት ነው የሚቆጨኝ›› እንዳሉት፡፡ ያልሠራነው ነገር እንዳይኖር፣ ምክንያት የሆንነው ነገር እንዳይኖር፣ ልንፈጽመው ሲገባን ያልፈጸምነው ነገር እንዳይኖር፣ ልናስበው ሲገባን ያላሰብነው ነገር እንዳይኖር ነው መፍራት፡፡ እንጂ ሊመጣ ያለውን ነገር አይደለም መፍራት፡፡ ክርስቲያን ሞትን አይፈራም አሟሟቱን እንጂ፡፡   
ሰውዬው በሩን በጠንካራ ብረት ዘግቶ ሲጠብቅ ያየው ጎረቤት ‹‹ምነው እንዲህ ታጠብቀዋለህ፤ አላህን አታምንም እንዴ ብሎ ቢጠይቀው ‹‹አላህንም አምናለሁ፣ በሬንም አጠብቃለሁ›› እንዳለው በእግዚአብሔር ያለንን እምነት ማጽናት በራችንንም ማጥበቅ ያስፈልገናል፡፡ የአመራር አቅማችን እንዴት ነው? መደበኛ አገልጋዮቻችንና አባሎቻችን እንዴት ናቸው? በአመራራችን ደስተኞች ናቸው? ማዕከሎቻችን እንዴት ናቸው? ከሊቃነ ጳጳሳትና ከአህጉረ ስብከት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም ነው? ግቢ ጉባኤያቱ እንዴት ናቸው? ሚዲያዎቻችንስ በቀድሞው ጥንካሬና ብስለት ላይ ናቸው? ሌሎችንም በሮች ማጠባበቁ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡
ከዚያ ወዲያ ግን፣ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ግን፣ የዐቅማችንን ሁሉ ከፈጸምን በኋላ ግን ‹‹እግዚአብሔር ምን አለ? የሚለው እንጂ እነ እገሌ ምን አሉ›› የሚለው ሊያሳስበን እንጂ ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ ቂጣ ከሆነ ይጠፋል፣ ሺልም ከሆነ ይገፋል፡፡
እንደ ክርስትና ትምህርት ከሆነ ህልውና ከግዘፋዊ ኑባሬ ጋር አይደለም የሚያያዘው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ከሚገኝ ሕይወት እንጂ፡፡ ግዘፋዊ ኑባሬ ማለት እታየ እየተደሳሰሰ፣ አካላዊ ቦታ ይዞ መኖርን ነው፡፡ እያሉ የሌሉ እንዳሉት ሁሉ እንደሌሉ የተቆጠሩ ደግሞ አሉ፡፡ ሰማዕታት በግዘፋዊ ኑባሬ አሁን በዚህ ዓለም የሉም፡፡ ነገር ግን ዘለዓለማዊ ህላዌ አላቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ግዘፋዊ ኑባሬ እያላቸው እየበሉና እየጠጡ፣ እየሠሩና እየተንቀሳቀሱ እንደሌሉ የተቆጠሩም አሉ፡፡ የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ ሲመጣ ‹ሞቶ ነበር›› የተባለው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
እኛም ህልውናችንን መመዘን ከግዘፋዊ ኑባሬ ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ከመኖር አንጻር ነው፡፡ መጨነቅ ያለብንም ያለ ዘለዓለማዊ ህልውና እንዳንቀር እንጂ ግዘፋዊ ኑባሬያችንን እንዳናጣ አይደለም፡፡ ዘለዓለማዊ ህልውና ከእምነታችን፣ ከሠራናቸው ሥራዎችና ካተረፍነው መክሊት የሚመነጭ ነው፡፡
ክርስትና የመሞት እንጂ የመግደል ሃይማኖት አይደለም፡፡በክርስትና በመሞት እንጂ በመግደል አክሊል አይገኝም፡፡ ስንክሳራችንን የሞሉት ቅዱሳን በዓላውያን ተገድለው አክሊል ሰማያዊ ያገኙ ናቸው፡፡ ይህንን ያልተረዱ ሰዎች የሚያወጧቸው ስሞች ሊገርሙን አይገባም፡፡
ባይሆን የጎዱን መስሏቸው ታሪካዊና ሀገራዊ ስሕተት ለሚሠሩት ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ አሁን ለሚሠሩት ስሕተት ግማሽ ምዕተ ዓመት እንኳን ሳይሞላ እንደሚፀፀቱበት ልንነግራቸው ይገባል፡፡ አሁን ‹‹ስቅሎ ስቅሎ›› የሚሉት የቤተ ክህነቱን ሰዎችም ይህንን ያስታውሱ፡፡ አይሁድ ጌታን ለሮማውያን አሳልፈው ከሰጡ ከ35 ዓመታት በኋላ ጌታን አሳልፈው የሰጧቸው ሮማውያን በጥጦስ አማካኝነት በእነርሱም ላይ ዘምተው እነርሱንም ከተማቸውንም አጥፍተዋቸዋል፡፡
እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡  እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡ 

111 comments:

 1. እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡

  ReplyDelete
 2. dani egziabher yibarkih .mahberunim egziabher yibarkew .minew yemitekim neger ahunim sikelew malet beza kegetachin gize gar tegenagne tarik erasun yidegmal

  ReplyDelete
 3. ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡
  Email ThisBlogThis!Share to TwitterShare to FacebookShare to Pinterest

  ReplyDelete
 4. ያልወደቀው ስላልተመታ ሳይሆን መሠረተ ጽኑዕ ስለነበረ ነው፡፡

  ReplyDelete
 5. Dear God please have mercy upon us sinners? so our ears will hear good news about your house. lately we are suffering high level of disturbance from in out please give us break so we will not be in despair? Amen!!

  ReplyDelete
 6. ዲ/ዳንኤል፣ ስለ መረጃውና ስለ ምከረ-ሃሳብህ እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ ባብዛኛው ለሥጋችን ለምንባዝን ለእኔና መሰሎቼ ቤተ/ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ በጥልቀት የተረዳነው አይመስለኝም፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሌሎች ችግሩን ከፊት ሁነው እንዲጋፈጡልንና ሌሎቻችን እንዲሁ ያለ ዋጋ በነፃነት የቤተ/ክርስቲያን አካል መሆንን እንሻለን፡፡ እኔ እንደማንኛውም ምዕመን ይህ ማኅበር እንደ ቤተ/ክርስታን ልጅነቱ ለእናት ቤተ/ክርስቲያን እያበረከተ ያለውን ሁለንተናዊ አስተዋፅዖ ከተረዳሁ ቆይቻለሁ። ግን እኮ ይህች ቤተ/ክርስቲያን አናት አባቶቻችን ብዙ ዋጋ ከፍለው ነው ለኛ ለልጆቻቸው ያስረከቡን፡፡ ስለዚህ ከምንጊዜውም በላይ የዚህች ቤተ/ክርስቲያን ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ ሊሆን ግድ ነው፡፡ ጥንተ-ጠላታችን ዲያብሎስ እንደሆነ ከቤተ/ክርስቲያ ላይ አይኑን ያነሳበት ጊዜ የለም፤ እንደ ትላንቱ ሁሉ ይኸው ዛሬም በመናፍቃን ተላላኪነት ዘምቶብናል፤ ጥቅመኝነት፣ መንደርተኝነት እና አድረባይነት በቤተ/ክርስቲያን ተንሰራፍቷል። ውሸትም ሥጋ ለብሳ እውነትን መሞገት ከጀመረች ሰንታለች። እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጣቸው። ቤተ/ክርስቲያናችንና ሀገራችን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅልን!
  ሐ.ዘ.ወ

  ReplyDelete
 7. ዳንኤል ክብረት እኔ ባጠቃላይ መልክቱ ላይ ችግር የለብኝም ግን ያንተ እይታ የተንሸዋረረ እንዳይሆን እሰጋለሁ እውነት ከሆነ ሁሉን እንቅጩዋን ነው ማስቀመጥ....... እጠቅሳለሁ......."ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ዐርፈው አቡነ ቴዎፍሎስ ዐቃቤ መንበር እያሉ ቤተ ክህነቱ ይታመስ ነበር አሉ፡፡ የቤተ ክህነቱ የዘር አስተሳሰብ እያቆጠቆጠ የመጣበት ዘመን ነበርና ‹‹ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆን?›› ከሚለው ይልቅ ‹‹ቀጣዩ ፓትርያርክ ከነማን ወገን ይሆን?›› የሚለው ብዙዎችን የሚያስጨንቅበት ጊዜ ነበር፡፡" ብለሃል እኛ ሞኞች አይደለንም ወይምማስተዋል አልጎደለንም....አሁንስ በኛ ዘመን የሆነው እንደዚሁ አይደለም እንዴ? ዎይስ ያንተ እይታ ያን አያይም? እንደዛ ከሆነ የንስሩን ምስል አንሳው.....እይታህም እንዳልከው ወደውስጥ ይመልከት!

  ReplyDelete
  Replies
  1. "አሁንስ በኛ ዘመን የሆነው እንደዚሁ አይደለም እንዴ?" What do you mean? Please explain this phrase...

   Delete
  2. tebebe yelelebte mnefesawi heywete jelnte nw selzihe wendeme ngre bmesale temare

   Delete
  3. This comment is totally out of context!

   Delete
  4. ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል ይላል መፅሐፍ..... እናም ነገር በምሳሌ ተማር እያልክ እንተ አሁን በዚህ ጌዜ በቤተክርስቲናችን ላይ ያለውን የዘር መድሎ እንደዚሁ ፅሁፍ ባላየሁ ባልሰማሁ ለማለፍ ከፈለግህ መብትህ ነው። እኔ ግን ተናግሬያለሁ ሞኞች ወይም ማስተዋል የጎደለን አይደለንም ሁሉን እያወቅን እንደው እግዚያብሄር በራሱ ጌዜ እስኪያስተካክለው ብለን በፈተናው ደፋ ቀና ማለታችን እንጂ እሚደበቅ የተሰወረ ነገር ከቶ አይኖርም የጊዜ ጉዳይ እንጂ። ከጭብጥ ውጪ ነው ላልከው ነገር እንግዲ ከ 2 አንዳችን ወይም ጭብጥ ምንእንደሆነ አልገባንም ማለት ነው። እኔ ከፅሁፉ ቀጥታ ነው የጠቀስኩት ፤ ምንናልባት ማለት የፈለከው ሌላ ነገር ካልሆነ በቀር እኔ በመልእክቱ እነደዋዛ በ አሉ ጉዳይ የተጠቀሰ ምሳሌ ነገርን ለማስቀየስ የተጠቀመማት ካልሆነ በስተቀር ስለዘረኝነት ጉዳይ ዘመን ወደሁዋላ ሄደን መጥቀስ አይኖርብንም ምክንያቱም አሁንም እንደዚህ ለውስጥም ለውጪም ችግር ካጋለጡን ምክንያቶች እንዱ እና ዋነኛው እሱ ነው። ስለዚህ የመልክቱ ችግር ለኔ ያልተመቸኝ ለዚህ ነው ሙሉ እይታ ከሆነ ማንንም ሳይፈራ እና ሳይወግን በግልጵ ቁጭ ማድረግ አለበለዚያ ባለ ጌዜን እየፈሩ ዳውላውን ቢደበድቡ ዋጋ የለውም ያስተዛዝባልም። ለዚህ ነው የንስሩን ምስል እንዲያነሳው የጠየኩት፤ ንስሩን ባየን ወይም ባሰብን ጌዜ ቅዱስ ዮሃንስ ወንጌላዊን እና ስታውሳለን እርሱ ደሞ ጌታ ሲሰቀል እንኩዋ ደፍሮ እስከመስቀሉ ስር የታመነ ሁዋላም በፍጥሞ ደሴት በግዞት ስንት መከራን ሲቀበል እውነትን ሳያዛባ እና ንጉስን ሳይፈራ ነበር። ሰለዚ አስተማሪዎቻችን ወይም መልክተኞቻችን ይህንን መንፈሳዊ ተነሳሽነት እና ድፍረት ከየት አጡት?

   Delete
  5. ወንድሜ ያነሳህው ሀሳብ ልክ ሆኖ ሳለ ፀሃፊው ምሳሌውን ያነሳበትን ትልቅ ቁምነገር ግን የረሳህው መሰለኝ። ይህውም "ሁሉንም የሰሙት አቡነ ቴዎፍሎስም ‹‹ባሕታውያኑም፣ ሕዝቡም፣ መኳንንቱም፣ ቤተ ክህነቱም ያሉትን ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔርስ ምን አለ?›› ብለው ጠየቁ ይባላል፡፡" 'እግዚአብሔርስ ምን አለ' የሚለውን ሃሳብ ለማምጣት የተጠቀመበት እብንደሆነ።

   Delete
 8. ከዚያ ወዲያ ግን፣ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ግን፣ የዐቅማችንን ሁሉ ከፈጸምን በኋላ ግን ‹‹እግዚአብሔር ምን አለ? የሚለው እንጂ እነ እገሌ ምን አሉ›› የሚለው ሊያሳስበን እንጂ ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ ቂጣ ከሆነ ይጠፋል፣ ሺልም ከሆነ ይገፋል፡፡

  ReplyDelete
 9. Our Beloved Brother Dn Daniel;
  I am your regular reader and always I got many powers from your wordings which cool down many of the people including myself. As you said what is left is to look in to our internal limitations and any dsconnections from the Almighty God. Who ever and what ever we are; he is always with us. Hence I strongly encourage our leaders as well as members including myself to look in to our internal part before blaming others. But this doesn't mean that those who are always knocking our doors are true. As to me this is not surprising as it is their regular duty. May God be with all of us.

  ReplyDelete
 10. ባይሆን የጎዱን መስሏቸው ታሪካዊና ሀገራዊ ስሕተት ለሚሠሩት ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ አሁን ለሚሠሩት ስሕተት ግማሽ ምዕተ ዓመት እንኳን ሳይሞላ እንደሚፀፀቱበት ልንነግራቸው ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 11. የአመራር አቅማችን እንዴት ነው? መደበኛ አገልጋዮቻችንና አባሎቻችን እንዴት ናቸው? በአመራራችን ደስተኞች ናቸው? ማዕከሎቻችን እንዴት ናቸው? ከሊቃነ ጳጳሳትና ከአህጉረ ስብከት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም ነው? ግቢ ጉባኤያቱ እንዴት ናቸው? ሚዲያዎቻችንስ በቀድሞው ጥንካሬና ብስለት ላይ ናቸው? ሌሎችንም በሮች ማጠባበቁ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያንተን ኮሜንት እጋራለሁ

   Delete
 12. ባይሆን የጎዱን መስሏቸው ታሪካዊና ሀገራዊ ስሕተት ለሚሠሩት ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ አሁን ለሚሠሩት ስሕተት ግማሽ ምዕተ ዓመት እንኳን ሳይሞላ እንደሚፀፀቱበት ልንነግራቸው ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 13. በአማን ነጸረApril 14, 2014 at 9:51 AM

  “እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡”
  ጥሩ አባባል ነች!!ይቺን አባባል ቤተክህነትም ራሱን ለመከላከል ሊጠቀምባት እንደሚችል እንዳንዘነጋ!!ያው ማረኅበሩን አቅፎ በውስጡ የያዘው ቤ/ክህነት!!ይሄ እንዳለ ሆኖ…..
  Better late than never!! እንዲል ፈረንጅ ዳኒ ጭስ ይሁን እሳተ ገሞራ ይታየኛል ስትል ሰንብተህ በስተመጨረሻ ብቅ ማለትህ አይከፋም፡፡ብትዘገይም Better late than never!!
  መቼም ቤ/ክህነት ስንል በተለይ ጠ/ቤ/ክህነት ስንል 18 መምሪያዎችን፣ 3 ኮሚሽኖችን፣ በተጨማሪነት ማኅበረቅዱሳንን በስሩ አድርጎ የሚያስተዳድር የሰማያዊው መንግስት የምድር እንደራሴ የሆነና ከቤ/መንግስት በንጽጽር የሚታይ በሀብትም በአደረጃጀትም ግዙፍ ተቋማችን ነው፡፡ይሁን እንጅ ተቋሙን በሀሳብም፣በንግግርም፣በድርጊትም ለማስተሀቀር የምናደርገው መሯሯጥ ብዙ ጊዜ ሳየው ማስተዋል የተሞላበት አይደለም፡፡
  በተለይ በማኅበረቅዱሳን ዙሪያ በተሰባሰባችሁ ልጆች አካባቢ ያለው ቤ/ክህነትን እንደ ቅን ልጅ አክብሮ ለማገዝ ከመጣር ይልቅ የህጸጾች ሁሉ ምንጭ አድርጎ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስሙን በማራከስ ነገርግን ማኅበረቅዱሳን የቤ/ክህነቱ አካል እንዳልሆነና ይህን የረከሰ አካል ለማንጻት እንደ መሲህ የተላከ አዳኝ አድርጎ በማቅረብ በሁሉም የሚዲያ ግንባር የሚሰራው ፕሮፖጋንዳ ስህተት ያለበት ነው፡፡
  ማኅበሩ ከሰራው ስራና በቤ/ክ ከሰጠውም ሆነ ካለው ድርሻ በላይ ሚዲያውን ተቆጣጥሮ የቤ/ክህነቱን ሌሎች አካላት እንደሌሉ ቆጥሮ ራሱን ብቻ እየሸጠ ነው፡፡ለበላይ አካላት ያለው ታዥነትና አክብሮትም የይስሙላ መሆኑ በየአጋጣሚው እያየነው ነው፡፡
  ለማንኛውም ዳኒ ለዛሬው ሺኖዳ እንዳሉት ከሚል ፈሊጥ ወጥተህ አቡነ ቴዎፍሎስ እንዳሉት የሚል ትውክልታቸውን በእግዚአብሄር ያደረጉ አባቶች እኛም እንደነበሩን ማሳየትህንና ማኅበሩ ወደ ውስጡ እንዲያይ የሰጠኸው አስተያየት መልካም እንደሆነ ሳልገልጽ ባልፍ ህሊናየ ይወቅሰኛል፡፡
  ስለ ማኅበሩና ቤ/ክህነቱ ግንኙነት እስኪ ሰሙነ ህማማቱ ይለፍና እንነጋገርበታለን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Stupid ideas emanates from stupid guys!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  2. በአማን ነጸረ አሁንም እንደገና በእኩይ ነጸረ ስልህ ሀፍረት የሰማኛል ፡ ምክንያቱም ከተነቃ ይቀራላ! ይላሉ የአራዳ ልጆች አንተ ግን እንደ ግብር አባትህ ዲያሎስ ቢነቁብኝም ተስፋ አልቆርጥም ስትል አንተን ደግሜ ማናገሬ ጊዜ ማጥፋት ስለሚሆንብኝ፡፡ ከፍሬያቸው ታዉቁዋቸዋላችሁ ስለተባለ ማንነትህን እንረዳዋለን፤ ለኛ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች አንዲት ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ብለን ለምናምን አቡነ ሺኖዳም ሆኑ አቡነ ቴዋፍሎስ አንድ ናቸው ሁሉም አባቶቻችን፡ ለአንተ በዘረኝነትና በጥፋት አስተሳሰብ ለተወጠረው ጭንቅላትህ ግን “ሺኖዳ” ግብጻዊ “አቡነ ቴዎፍሎስ “ ኢትዬጵያዊ ወይም ወርደህ (በዚህ ደረጃ ትወርዳለህ ብዬ ባላስብህ ይሻለኛል፤ ምክንያቱም ያባከንኩት ጊዜ ይበልጥ ስለሚቆጨኘ) የእገሌ ብሔር… እና ወንድሜ ምን እያልኩህ መሰለህ ስምህን ቀይር ወይም ግብርን አልያም ሜዳህን ቀይር እነ አባ ሰላማ ….ያው ታውቃቸው የለ

   Delete
  3. የበአማን ነጸረ አስተያየት ጠጣር ቢሆንም ነገሩን በሚዛናዊነት ለማየት ያግዛል፡፡ ሰዎችን ደርሰን እኛና እነሱ እያልን በአንድ ቅርጫት ውስጥ ለመጨመር አንፍጠን፡፡እንደዛ ማድረግ ስህተትን በስህተት ማረም ነው፡፡ሀሳቡን መተቸት ይበቃል፡፡ሰውየውን ትተን ንግግሩን ለማሸነፍ መጣር ይሻላል፡፡

   Delete
  4. “በአማን ነጸረ” የተባልክ ሰው ስለ አንተ መሰሪነት ለመፃፍ ጊዜ ማጥፋቴ እኔም ሀፍረት ይሰማኛል። ዲ/ን ዳንኤል ከብዕር ትሩፋቶችህ/ፅሑፎችህ በእጅጉ የተጠቀምነውን ያህል ያለቦታቸው ገብተው የሰዎችን አመለካከት ለመበረዝ በስልትና በዓላማ የሚንቀሳቀሱ እንደ በአማን ነጸረ የመሳሰሉ እኩያንና “ውስጠ-ዘ” ሰዎች የሚረጩትን መርዛም አስተያየቶችን በመለጠፍ ሌሎችን ቅር ባታሰኝ። እባክህን “ይህ የናንተ መጫወቻ ሜዳ አይደለም” በላቸው...።

   Delete
  5. ልክ ነህ ሀሳብን በሃሳብ መቃወም እንጂ ሰውየውን ከሀሳቡ ጠቅልሎ መዉቀጥ አስፈላጊ አይደለም፤ ነገር ግን ይህ ሰው የሚያይበት ዓይን ሳይሆን ችግሩ የቅንነት መንፈስ ማጣት ነው፡፡ ስላዛም ነው እንደ ቅዱስ ዬሐንስ “ሌባ “ እንደ ጌታችን ” ቀበሮ” ያልኩት፡፡

   Delete
  6. you have the right to live on earth with your unbearable idea but where is you destination?

   Delete
  7. wey medenakor ? endet new megbabat yemitchilut? please try to read the content in his comment.
   yasazinal.

   Delete
 14. ወንድማችን እግዚአብሄር አምላክ የአገልግለሎት ዘመንክን ይባርክልህ

  ReplyDelete
 15. ዲያቆን ዳንኤል መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱሳንም ሆኑ ማህበራት በተለያየ ምክንያት መከራን ስደትን ተቀብለዋል፡፡ አንድዋን ነገር አንስተህ የማህበሩን አመራር ለመተቸት መነሳትህ ተገቢ አይደለም፡፡ ከፈለክ ሃራ ተዋህዶ ላይ የሚቀርቡትን ነገሮች አንብብ ወይም መጽሔቶችን ፋክት ዕንቁ የመሳሰሉትን አንብብ ለህብረተሰቡ ትክክለኛ ነገሮችን አሳውቀዋል፡፡ በተለይ አንተ ከዚህ በፊትም በማህበሩ አመራር ላይ ሸጥተህ የነበረው የግል አስተያየት ለሌሎች ውስጣዊ እይታ በተለይ ለመንግስትና ለመናፍቃን ጥሩ መግቢያና እንደፈለጋቸው እንዲያወሩ አድርጎዋቸዋል፡፡ አንተ ብዙ ጊዜ እራስህን ብቻ ነው የምታዳምጠውና ትክክለኛ አድርገህ የምታየው፡፡ ባንተ እይታ ማህበሩ ምንም እየሰራ አይደለም ነው ወይስ ምን እያደረገ እንዳለ ላንተ በግልባጭ ማሳወቅ አለባቸው፡፡ አሁንም ማህበሩነ ለማፍረስ ከሚሮጡት አንዱ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም ችግርም ካለ በግል መመካከር እንጂ አድበስብሶ ችግር አለ ማለት ሌላ መልእክት አለው፡፡ ለመሆኑ ከቅዱሳን በነገስታቱ ያልተገደለ ማን ነበረ በተለይ እስከ ቆስጠንጢኖስ መነሳት ድረስ ብዙዎችስ ነገስታቱን እየተጠጉ አይደል እንዴ ስደትና ሞት እንዲያገኛቸው በማድረግ ምንፍቅናን ያስፋፉት ነው ወይስ አንተ እንደምትለው የውስጥ ችግር ስለነበረባቸው ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ በዛን ጊዜም ብትኖር ይህንን እንደምትል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በሐዋርያት ስራ ላይ እንደምናየው ስደት ሆነ ይላል ይህ የሆነው ክርስቲያኖች አንድ ሆነው በህብረት ማገልገላቸውና አንድነታቸው ያስፈራቸው ሰዎች ናቸው ከነገስታቱጋ ተጠግተው ፈቃድ ወስደው ስደትንያመጡባቸው እንጂ በውስጣዊ ችግራቸው አልነበረም፡፡ እኔ እንደውም እንደ አንተ አይነቶቹን ነው ለማህበሩ አለመታመን ምክንያት የማደርገው፡፡ ምክንያቱም የአገልግሎት ጊዜያችሁ ያለቀ ይመስል ከአመራር ቦታ ዞር ስትሉ መንግስትን እንተጭ ብላችሁ በጋዜጣና መጽሄት ላይ ወጣችሁ ፡፡ ትላንት ውስጥም እያላችሁ ያላችሁን ሃሳብ ያወጣችሁት ነው የሚመስለው፡፡ ታዲያ አሁን ያሉት በውስጣቸው ምንም በሌለው እንደ እናንተ መቆጠር ቢችሉ ዋናው እናንተ እንጂ እነሱ አይደሉመ ተጠያቂ፡፡ አንተ ግላዊ አስተሳሰብ እኔ ብቻ አውቃለው ባይነት ያጠቃሃል፡፡ ሁሌም ማውራት እንጂ ምን ያመጣል ብለህ መገንዘብ የለህም፡፡ ማህበሩ ስራውን እየሰራ ነው ያውም ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ፡፡ እንደ ቀድሞ ትላለህ ደግሞ እኔ በነበርኩበት ዘመን ለማለትና ያኔ የነበረውን ትክክለኛ አሁነ ያለውን የወረደ ለማሰኘትም ይቃጣሃል፡፡ ቤተክርስቲያን ወደፊት ፈተና እየበዛባት በሄደ ቁጥር ይህ ማህበር የዚችን ቤተክርስቲያን እዳ ተሸካሚ ነውና ማንም ምንም ቢለው የቅዱሳን ጸሎት ነውና የሚጠብቀው እግዚአብሔር ነውና የመሰረተው እንደ ገማልያል ተዋቸው ከእግዚአብሔር ከሆነ እንዳለው ማንም ማህበሩን ባይነካው አንተም ዝም በሉ ብለህ የውጪውን አንድምታ ብታንጸባርቅ ጥሩ ነው፡፡ ማህበሩን ለማፍረስ ምን አይነት ውጫዊ ነገሮች እንዳሉ ለመናገር አለመቻልህ እስካሁን እራሱ አህያውን ፈርቶ ሰኝብሃል፡፡ እስቲ ልብ ካለህ መንግስትና ቤተክህነት ውስጥ ያሉ ለምን ማህበሩን መተናኮል እንደሚፈልጉ እንደ ዕንቁ መጽሔትና ፋክት ነገሮችን አብራርተህ ህዝቡ እንዲያውቅ አድርግ፡፡ ማህበሩ የ6 ወር ስብሰባ አድርጎ መግለጫ በሰጠበት ሁኔታ ተጠቅመህ ቀድመህም ቢሆን ማድረግ አልነበረብህም፡፡ የግል ችግር ካለብህ በውይይት ፍታው፡፡ በተረፈ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ይበለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Very interesting. May Almighty GOD be with you and MK

   Delete
  2. you guys are sure you are the member of MK????????????? think it twice before you write!! it shows your arrogant behavior and your blame for Dn. Daniel. please please pleas there is no such kinds of MK member, even others who hate people. As a member of MK, I really ashamed of you!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  3. ሰዉ ያለሀበሳዉ መወንጀል ለእኔ ክርስቶስን አሳልፎ ከሰጠዉ ከይሁዳ ለይቸ አላየዉም፤ እዚህ ላይ የማህበሩን አመራር የሚተች ነገር አለየሁም፡፡ ሁላችንም አንብበነዋል፤ ግን ለምን እንደፍላጎታችን እንተረጉመዋለን፡፡ “እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡” ለዲ/ዳንኤል፡- እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ፤ይጠብቅህ፡፡

   Delete
  4. ወንድሜ እንደዚህ በክፉ ባንተያይ አይሻለንም ትላለህ፡ አንተ እንዳልከው አላውያን ነገስታት ጋር የተጠጉም ይሁኑ እኛ እራሳችን የችግር መንስኤዋች የሚበጀን ሁልጊዜም ወደ ውስጣችን ማየት ነውና ይሄን እንደ መልእክት እንቀበለው የውጪውን እግዚአብሔር ያየዋልና ፡፡ ከዚያ በተረፈ ግን እግዚአብሔር የሰራውን ሰው አያፈርሰውም፤ እግዚአብሔር እንዲፈርስ ፈቃዱ ቢሆን እንኩዋን በቅንነት ለነፍሳችን ሳንሳሳ ቤተ ክርስቲያናችንን ከማገልገል ወዴትም ፍንክች፡፡ ማን ያውቃል እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ መገደል ቢሆንስ ጉዳዩ

   Delete
  5. ለምሆኑ ይህ ሃሣብ ምን ሰምና ወርቅ አለው አኔ አንደገባኝ ሳጠቃልለው ውስጣዊ ጥንካሬ ይኑረን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በእምነት አንድነት እንዲኖረን ከማሳስብ ውጭ:: ለነገሩ ዋናው ሃሳባችን ግራ በተጋቡ ፅሁፎች ሳይሆን በዋናው መልአክት ስለሆነ ዲያቆን ዳንኤልን ማመስገን እፈልጋለሁ:: እ/ር ኢትዮጵያን ይባርክ:: እውነቱ ነኝ

   Delete
  6. chifn degafi anhun yemahiberu komite lay chigir endalema tenagrowal wistachinin eniy yalew manin new amerarun aydel yawm endih bemalet የአመራር አቅማችን እንዴት ነው? መደበኛ አገልጋዮቻችንና አባሎቻችን እንዴት ናቸው? በአመራራችን ደስተኞች ናቸው? ማዕከሎቻችን እንዴት ናቸው? ከሊቃነ ጳጳሳትና ከአህጉረ ስብከት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም ነው? ግቢ ጉባኤያቱ እንዴት ናቸው? ሚዲያዎቻችንስ በቀድሞው ጥንካሬና ብስለት ላይ ናቸው? ሌሎችንም በሮች ማጠባበቁ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡ daniel malet ene kalwetewetkut ayhonm yemil new. bichayen yemil sew new alsemahm bilut sew yismagn yale sew new.

   Delete
  7. አንተ ደግሞ ከየት የመጣህ ድውይ ነህ በል! ድንጉጥ ሰስ ሆንህሳ፡፡ አቅም ካለህ ውጣና በገሃድ ጻፍ፡፡ ዳኒ ቢያንስ በገሃድ ተናገረ፡፡ አንተ ድንጉጡ ፍጥረት ግን ገና ሰው መሆን የቀረህ ነህና ፈርተህ አስተያየትህን እንኳ "በስም የለሽ" ተናገርህ፡፡ ስም ከሌለህ ደግሞ ሰው አይደለህም፡፡ ስው ካልሆንህ ደግሞ የሚሰማህ የለም፡፡

   Delete
  8. yewusit chigir malet eko......not necessarily describing MK.....all people under the shade of our church.....Bete Kihinetinm yichemiral.

   Delete
  9. እዚህ አባል እዚያ አባል...እርስ በእርስ መጠራጠር ብሎም መለያየት...መፍረስ ማለት ይሄ ነው...ቤተ ክህነት ታግቷል መሰል...በማን...እንጃ...እኔ ከሰው ተልይቼ በምን አውቃለሁ...እንደ እስላሞቹ ነጻ ለማውጣት እንታገል እንዴ...እንጃ...እርሱ ያውቀል የሚሆነውን...እንደ ጊዜው በዘዴ መሥራት መልካም ቢሆንም... ለጊዜው ተብሎ ክርስቶስ አይካድም...ብቻ ጠንቀቅ ነው ነገሩ...የተመረጡት ሲደናገሩ...ስህተት፣ እንከን የለብኝም የሚለውንስ ስህተትህ እራሱ ይህን ማለትህ ነው!

   Delete
 16. quite intersitng review andadvice GOD bless you Brother

  ReplyDelete
 17. egziabher betekerstiyanachenen ena mk yetebekelen bethslot enberta...

  ReplyDelete
 18. ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡

  ድንቅ አባባል ነው፡፡
  ፈጣሪ ለወዳጆቹ ብሎ ይታደገን እንጂ የምንሰማው ሁሉ አያምርም፡፡
  ግዚክስ

  ReplyDelete
 19. Diablos kestun cherese
  Betekrstianin gin liatefat alchalem!!!

  Dani, Egziabher yitebikih!!!

  "mahiberene ekebe selam !!!"

  mahiberachinin yitebikiln!!!

  ReplyDelete
 20. ‹ዝናብም ወረደ፣ ጎርፍም መጣ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው በዐለት ላይ ስለተመሠረተ ግን አልወደቀም›› ይላልና፡፡ ያልወደቀው ስላልተመታ ሳይሆን መሠረተ ጽኑዕ ስለነበረ ነው፡፡

  ReplyDelete
 21. አቶ ዳንኤል ምልከታህ ምን እንደሆነ አልገባኝም ፡፡ ማህበሩን ድሮ እንደ መላእክት ሆነህ ነበር እንዴ ስታገለግል የነበረው፡፡ ያሁኖቹስ ሰው ሆኑብህ ለምን አስተያየትህን የነገሮች መቆስቆሻ ታደርገዋለህ ለመናፍቃንስ መረማመጃ ታደርገዋለህ ከዚህ በፊት ሰጥተህ የነበረውን የግልህን ሃሳብ መናፍቃን በየ ብሎጋቸው ላይ አወጡት ያውም ጥቅም የሌለው ወሬህን ያውም በዛን ወቅት እንዲሁ ስለማህበሩ መንግስት የተናገረበት ነበረ ያኔም እንደዚሁ አመራሩ ላይ ነው ወሬህ፡፡ አሁንም መንግስት የሆነ ነገር አለ ሲባል ጊዜውን ጠብቀህ ማንሳትህ ችግር እንዳለብህ እንድንረዳ አድርጎናል፡፡ አምድህ ላይ መናፍቃን ማህበሩን የሚኮረኩም ቃላት እንደሚናገሩ እወቅ የመንግስት ደጋፊዎችም ቢሆኑ ያደርጋሉ ይህ ደግሞ ድምጽ ማሰባሰቢያ ማድረጊያ ነው፡፡
  እኔ እንደውም የምላችሁን አድርጉ አልሰማችሁኝም እያልክ መሆኑን ነው የሚሰማኝ፡፡ መንግስት ማህበሩ ላይ ምን ያክል ጊዜ ጫና እያበዛ እንዳለ ተሰውሮህ ነው ከማህበሩ ችግር አለ ለማለት የምትደፍረው፡፡ ማህበሩን ለቀቅ አድርገህ ማህበሩን ሊገዳደሩ የሚፈልጉትን አካላት ብትነካካ ይሻላል፡፡ አሁንም እንደባለፈው ይቅርታ ብትል የሚሰማህ የለም፡፡ አንተ እንደውም የመንግስት እጅ አለብህ ፡፡ ስለ ማህበሩ ተቆርቁዋሪ መስለህ ትንሽ ነገር ተናግረህ ማህበሩን የሚያስመቱ ሃሳቦችን የምትሰነዝረው፡፡ መንግስት ማህበሩ ሳሆን ማህበሩ ውስጥ ባሉ አንድ አንድ አካላት ችግር አለ ባለ ማግስት የማህበሩ አመራር ላይ ማነጣጠርህ ምክንያቱ አይገባኝም፡፡ ችግር ቢኖር እንኩዋን የምትሄድበት አካሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ መንግስት ምክንያት ባጣበት ሁኔታ አንተ ጥቆማ እየሰጠህ መሆኑን አትዘንጋ ያውም ምንም በሌለበት ሁኔታ ፡፡ ወደፊት ለሚከሰተው ነገር ሁሉ ማህበሩ አንድ ነገር ቢሆን ከመጠየቅ ወደሁዋላ እንደማትል እወቅ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. AnonymousApril 14, 2014 at 1:58 PM
   I think you misunderstood Dn. Daniels view. He said, if we are strong and are with God, nobody can do nothing. ‹‹እግዚአብሔር ምን አለ? የሚለው እንጂ እነ እገሌ ምን አሉ››

   Delete
  2. ከላይ የተሰነዘሩት አስተያየቶች ቅንነት የጎደላቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ራስን የማኅበረ ቅዱሳን ብቸኛ ተቆርቋሪ አድርጎ ማቅረብ በራሱ ትዕቢት ይመስለኛል፡፡ ምኑ ላይ ነው የማኅበሩን አመራር ጥፋተኛ የሚያደርግ ሀሳብ ያለው? አንዳንድ የማኅበሩ አባላት ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ ይገባኛል፡፡ ለመሆኑ የወንጌሉ ቃል ተረስቶ ጸጉር መሰንጠቅ ብቻ ሆነ እንዴ አገልግሎታችን? የተሠጠውን ሀሳብ ለምን በቅን ልቡና መመልከት አቃተን፡፡ ለክፉ ታስቦ ቢሆን እንኳ እኛ በበጎ የመረዳትና የመቀበል አቅም ቢኖረን እንደተረዳነው ይሆንልን ነበር፡፡ ግን ለዚህ አልታደልንም፡፡ እግዚአብሔር ልቡና ይስጠን፡፡

   Delete
  3. be positive thinker specialy those of saying member of MK. take the positive advice. dont consider urself as saint. we have to see ourselves before pointing to other.

   Delete
  4. ለአኖኒመስ April 14, 2014 at 1:58 PM አስተያየትህ የተንጋደደ ነው፡፡ ለምን በቅን ልቡና/እይታ የዳኒን መልዕክት አትመለከተውም/አታስተውለውም፡፡ አሁንም ማህበሩ ማንነቱን ካላስተካከለ ውስጡን ካላጠራ አደጋ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ሌላ አካል ባያፈርሰውም በራሱ ጊዜ ይፈረካከሳል፡፡ አንተ አስተያየት ሰጪው አክራሪ ከሚለው ሰሞነኛ ቃል በምን ትለያለህ፡፡ ዳኒን እኮ እያስፈራራኸው ነው፡፡ ልቦና ይስጥህ፡፡

   Delete
  5. Do u think that MK is a collection of Angels? NO WAY..it is a believed fact that we will make mistakes, we will make corrective actions........Personally , the Anonymous is making mistake.....All dany told is correct and to be appreciated.

   Delete
 22. ዲያቆን ዳንኤል መልካም እይታ ነውና ላካፈልከን ጽሁፍ በጣም እናመሰግናለን

  ReplyDelete
 23. ዲያቆን ዳንኤል መልካም እይታ ነውና ላካፈልከን ጽሁፍ በጣም እናመሰግናለን

  ReplyDelete
 24. Its not first time Mhebere Kidusan,MK, faces such difficulties it has managed to pass them with submission and submersion.Now its time to confront the reality MK has grown big interms of members, assets and influence. It can not continue like the last 25 years, even its late it should have put some preventive remedies in the administrative body long ago.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This advice seems from a friend (wodaj) but sounds, it has a motivation of initiating the mahiber for unnecessary conflict. Des...kanaw wodaj mesilo telat yemisetew asteyayet new, mahiberun agul yemalatem agenda yalew

   Delete
 25. ዳኒ እግዚአብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ ኑርልን
  እኛ ከእግዚአብሔር ጋር መሆናችንን ርግጠኞች እንሁን፡፡ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ለመሆኑ ርግጠኞች ነንና፡፡ ውስጣችን ለእግዚአብሔር የተመቸ ለመሆኑ ርግጠኞች እንሁን፣ እግዚአብሔር ለእኛ የተመቸ ነውና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህ ብሎግ ጥሩ እንደመሆኑ መጠን ሁሉንም ያስተናግዳል ስለማህበረ ቅዱሳን የግል ችግር የለበት በግል መነጋገር ይችላል ብሎግህ ግን አስተማሪ ከሆነ ሰምና ወርቅ የሆነ ነገር እየተገለፀበት የሆነ ያለ ስለሚመስል ባታናውጡን ጥሩ ይመስለኛል ወዴት ሄደን መልካም ነገር እንስማ እናንተም የራሳችሁን አንተም የራስህን መግለጫ እና ሽምቅ መሳሪያ አደረግኸው አላማው ማሳወቅ ከሆነ ፈተናውን ሁሉ መቻል ያለብህ ይመስለኛል ስለዚህ ነውጥ ይቁምና እውቀት የምንይዝበትን ነገር አድርጉ እባካችሁ!!!!!!!!

   Delete
 26. አይሁድ ጌታን ለሮማውያን አሳልፈው ከሰጡ ከ35 ዓመታት በኋላ ጌታን አሳልፈው የሰጧቸው ሮማውያን በጥጦስ አማካኝነት በእነርሱም ላይ ዘምተው እነርሱንም ከተማቸውንም አጥፍተዋቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 27. please take the positive things. especialy those of mk memberes. this is not chrisitina. we have to see ourselves before pointing to other. God be with us.

  ReplyDelete
 28. ማኅበሩ ውስጥ አንዳንድ ከሚባሉት መካከል በርግጠኝነት አንተ ነህ፤ ባንተ ፖለቲካ የተነሳ ነው ማኅበሩ እየተሰደበ ያለው ስለዚህ አጥብቀህ ተዋጋ ወይ ስሙን መልስ እራስህም ወደ ልብህ ተመለስ!!!!

  ReplyDelete
 29. እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡

  ReplyDelete
 30. ሰላም ዲ/ን ዳንኤል : ይህ ያንተ ብሎግ እይታህን ፍልስፍናህን እምነትህን አመለካከትህን ዜጋ እንዲሆን የምትመኘዉን ምጥህን የምንረዳበት እየተማርንበትም ያለ ነዉ:: ነገር ግን ባይበዙም አንዳንድ አስተያየቶች ክብር የሚባል ነገር የሌላቸዉ ከመልእክቱ ያፈነገጡ በተንኮል የተለበጡ በስድብ ያጌጡ ሆነዉ ይታያሉ:: እባክህን ለቅን ሞጋቾች እንጂ ለተሳዳቢዎች ቦታ አትስጥ:: ለነሱ ብዕርን ለስድብ ማስጎንበስ እንደ መፃፍ ነፃነት የሚቆጥሩ ብሎጎች ስላሉላቸዉ እሱን ይጠቀሙ:: ይጠቀሙ ያልኩት እየፈቀድኩላቸዉ ሳይሆን ምንም ማድረግ ስለማልችል ነዉ:: ያንተ ብሎግ ግን ስድብ ሃጥያት ስለሆነ ከዚህ ይፅዳ:: ለአንተና ቤተሰብህ መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ

  ReplyDelete
 31. ‹‹እግዚአብሔርስ ምን አለ?›› ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ ሁሉም የየራሱን ሊወስን፣ ሊፎክር፣ ሊነሣ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ካልወሰነ ግን የሚሆን አንዳች ነገር የለም፡፡
  EGEZABHEREMA :-- YEWEDENALE....

  Yemekedsewna Yemekedesute ulu keande
  nachewena : EBRAWI 2:11

  KERASE YELEKE LE GATA SEME KENATEGNA UNE !!!!!!!!! + H.H POPE SHENOUDA +  ReplyDelete
 32. መህምር ግሩም ምክረ ሃሳብ ነዉ ማህበረ ቅዱሳንን ከልጅነቴ ጀምሮ አዉቀዋለሁ አገልጋይ ባልሆንም ግቢ እያለሁ የሚሰጡትን ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እሳተፍ ነበር አሁንም ቢሆን አገልጋይ የሆኑ ወንድሞችና እህቶች አሉኝናእንደድሮዉ ባይሆንም ጥቂት ጥቂት መርሃ ግብሮችን እሳተፋለሁአንዳንዶቹ አገልግሎቶቹ ያሳሱኛል አንዳንዶቹ ደግሞ ዳግም እስካገኛቸዉ ይነፍቁኛል አንዳንዴም የምከፋበት ክስተቶች ያጋጥሙኛል፡፡ አሁን እየተወራ ያለዉ ነገር እዉን ከሆነ እጅግ ያሳዝናል በተለይም የግቢ ገባዔዎችንና አስታዋሽ አልባ የሆኑ ገዳማትንና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ሳስብ ይከፋኛል፡፡ እነኝህ አካላት ያላቸዉን መንፈሳዊና አገራዊ ፈይዳ የተጋረጠባቸዉን ፈተናና በመዋቅር ደረጃ ከቤተ መንግስቱም ከቤተ ክህነቱ ከሚመለከታቸዉ አካላት ትኩረት አለማግኘታቸዉ ማህበሩ እንደተወራዉ ቢዘጋ የሚፈጠረዉን ክፍተት ማሰብ እጅግ ያማል፡፡ እርግጥ በዚህ ፈታኝ ዘመን ይህን ታላቅ ሃላፊነት እየተወጡ ያሉት ወንድሞችና እህቶች ምን ማረግ እንዳለባቸዉ ይስቱታል ብየ አላስብም ዛሬ ብዙዎቹ በእድሜም በእዉቀትም ጎልብተዋል ከቤተክህነቱም ጥፋታቸዉን የሚናፍቁ እንዳሉ ሁሉ በስስት የሚያዩአቸዎ ጳጳሳት ሊቃዉንትም ጥቂት አይደሉም ከመንግስት ባለስልጣናትም ቁጥራቸዉ ሊያንስ አቅማቸዉም ዉስንነት ሊኖረዉ ቢችልም አላማቸዉን አላማዉ ያደረገ አልያም የሚደግፍ አለና ችግር ሊፈጠር ቢችልም ነገሮች እሳተ ጎመራ የማይሆኑበት ሁኔታ ያለ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ግዜ ሊሆን የሚገባዉ ነገር መህምር እንዳልከዉ ዉስጥን መመርመር ማኝፃት ዉዥብብሩ ቢያይልም ተረጋግቶ እግዚአብሔር ምን ይላል ማለት ይሻላል እላለሁ፡፡ ይህን ከሆነ ለክፉ የተደገሰዉን በበጎ መመንዘር ይቻላል፡፡ አይሁድ እስጢፋኖስን ሲገድሉ ክርስትናን ያዳከሙ መስሏቸዉ ነበር ግን በተቃራኒዉ አሰፏት ማሕበረ ቅዱሳንም ብዙ ቀናኢ ካህናትን መምሕራንን ምዕመናንን አፍርቷል ታዲያ እነኝህ አባቶች ወንድሞችና እህቶች በየ ሃገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባዔዉና ሰንበት ትምህርት ቤቱ ቤተክርስትያንን ለማልማት ቢተጉ ቢያተጉንናስ የርሱን ጥበብ ማንያዉቀዋል፤ ይህ ግን የሚሆነዉ ሁላችንም የቤተ ክርስትያን ጉዳይ ያገባናል የምንል ወገኖች በቤቱ ቅናት ስንቃጠል ክቡር ለሆነዉ አገልግሎት ዉስጣችን ስናጸዳና እንዳንዷድርጊታችን በስጋ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንገድ ስትቃኝ ነዉ፡፡ ከዚህ ካለፈ የመድኀኔዓለም ፈቃድ ከሆነ የመጣዉ ይምጣ ክርስትና የመስቀል ጉዞ ነዉና ትክሻን ማዘጋጀት ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 33. እኔ የናፈቀኝ ዘመን ንስሀ የሚገባ የሚቆርብ ሰው መቀነሱ የሚያሳስበን ጊዜ ነው ከማህበራት ከዲያቆን እስከ ፓትሪያኩ ድረስ የስልጣንና የገንዘብ ችግር እንጂ እውነተኛ እምነት እንኳን የላቸውም የሰናፍጭ ቅንታት እንኳን የላቸውም ህዝቡ ቀድሟቸዋል በሶሻል ሚዲያ በየሰአቱ ቃሉ ይነገራል።አስተያየት ስትሰጡ ደግሞ
  አትፍሩ ዳኒ ዳኒ ብሎ ወቅሶ እናንተ anonymous. ለምን እከሌ ነኝ

  ReplyDelete
 34. ማህበሩ ብዙ ተቀፅላ ስሞች ሊሰጠዉ ይችላል እንዳልሆነ ግን ማስረዳት ከአመራር አባሎች ብዙ ብዙ ይጠበቃል። ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 35. የአመራር አቅማችን እንዴት ነው? መደበኛ አገልጋዮቻችንና አባሎቻችን እንዴት ናቸው? በአመራራችን ደስተኞች ናቸው? ማዕከሎቻችን እንዴት ናቸው? ከሊቃነ ጳጳሳትና ከአህጉረ ስብከት ጋር ያላቸው ግንኙነት መልካም ነው? ግቢ ጉባኤያቱ እንዴት ናቸው? ሚዲያዎቻችንስ በቀድሞው ጥንካሬና ብስለት ላይ ናቸው? ሌሎችንም በሮች ማጠባበቁ የሚበጅ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 36. የሚሞቱ ሰዎች በመጨረሻዋ ቅጽበት የሚጸጽታቸው ስለአመንበት እና እውነት ስለሆነው ነገር ስንል ለምን እስከመጨረሸው አልታገልንም ብለው ነው ....እንዲህ አይነቱ ህመም በጣም ከባድ ነው፡፡ዋጋም አለው!!

  ReplyDelete
 37. ማህበረ ቅዱሳን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ያበረከተው አስተዋጽኦ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ እንዲያው ዝምብሎ እግዚአብሔር ሥራህ ድንቅ ነው ማለት ነው እንጅ፡፡ በዚያ ሀይማኖተኛ መሆን በሚናቅበት ጊዜ፤ አብዛኛው የተማረው አካል ቁሳዊነት (ማቴሪያሊስት/ማርክሲስት/ሌሊኒስት) በተጠናወተው ጊዜ፤ አብዛኛው ተማሪ የተባለ ሁሉ ማተቡን በበጠሰበት ጊዜ፡ እግዚአብሔር አምላክ በተወሰኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ታላቁ ኣባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ አድሮ ይህን ማህበር ወለደልን፡፡ በዚህም ብዙዎቻቺን ከጥፋት ዳንን፡፡ አለማዎቃችን አወቅን፡፡ አሁን አሁን ግን በማህበሩ ውስጥ ተሸጉጠው የሚገኙ ተኩላዎች (አመራሮችም ሊሆኑ ይችላሉ) ማህበሩንና ህዝቡን፤ ማህበሩንና ቤተክህንትን፤ ማህበሩንና መንግስትን በማጋጨት የማህበሩን ህልውና ይሄው እንደምናየውና እንደምንሰማው እየተፈታተኑት ይገኛሉ፡፡ ለማህበሩ ከነሱ በላይ ታማኝ ላሳር የሚሉ፤ የሌላውን አገልግሎት ዋጋ የሚያሳጡ ካልሆነም የጎሪጥ የሚመለከቱ፤ የሰውን ልብና ኩላሊት መመርመር የሚቻላቸውን ያክል እገሌ ሐጢአተኛ ነው የማህበሩ ኣባል ሊሆን አይችልም የሚሉ፤ ምእመኑንና ኣባቶችን ሳይቀር ሐጢአት መሥራት አለመሥራታቸውን የሚሰልሉ፤ በምዕመኑ ላይ ቀንበር ለመጫን የሚሞክሩ፡ ነገር ግን እነሱ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ፤ የነሱ ጥቅም እስካልተመቻቸላቸው ድረስ ከመበጥበጥ ወደ ኋላ የማይሉ፤ ጎጠኛ አስተሳሰብ የተጠናዎታቸው በርካታ አመራሮች እንደተሰገሰጉበት ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ማህበሩን ማፍረስ የሚቻለው አካል ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ማህበሩ ዘሩን ዘርቶ ፍሬ አፍርቷል፡፡ በያንዳንዱ የመንግስት፣ የግል፣ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም እንዲሁም በህዝቡ ውስጥ የማህበሩ ልጅ፡ ወይም በማህበሩ ያላለፈ፤ ከማህበሩ በረከት ያልተሳተፈ የለምና፡፡ ስለዚህ ማህበሩን መንካት ይህን ሁሉ የተማረ አካል መንካት ነው፡፡ አብዛኛው ወጣት የአሁኑ መንግስት ፖለቲከኛ የዚህ ማህበር ተቋዳሽ ነው፡፡ ስለዚህ ማህበሩን ይፈረስ ቢሎ የሚወስን አካል አለ ብዬ አላምንም፡፡ ይህ ሲባል ግን በማህበሩ ውስጥ ተሰግስገው የሚገኙ መሰሪዎች፡ ከላይ የጠቀስኳቸውን እኩይ ተግባሮች የሚያከናወኑ ግለሰቦች መቀጣት የለባቸውም የሚል እምነት የለኝም፡፡

  ReplyDelete
 38. You have good point but your analysis is narrow and focused only on one specific point.

  ReplyDelete
 39. እኔ አንዳንዶቻችሁ በጣም ትገርሙኛላችሁ፡፡ ወደ ውስጥ እንይ ማለት ነውሩ ምንድን ነው፡፡ አጤ ቴዎድሮስ ያሉትን እዚህ ላይ መጥቀስ ይገባል፡፡ አጤ ቴዎድሮስና እቴጌ ምንትዋብ እልፍኛቸው ውስጥ ሲጨቃጨቁ እልፍኝ አስከልካዩ ይሰማል፡፡ እንዴት ጌታዬን እቴጌይቱ ትናገራቸዋለች ብሎ በንዴት መሣሪያውን ይዞ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ ወዲያው ንጉሡ ተገርመው ‹‹ምን ሆንክ›› ይሉታል፡፡ እርሱም ‹‹እንዴት እመቤቴ ጌታዬን ይናገሯቸዋል›. ብሎ ይናገራል፡፡ ንጉሡም ‹‹በል ተመለስ፣ አንተ የንግሥና ልብሴን ለብሼ ነው የምታውቀኝ፤ ምንትዋብ ግን ራቁቴን ነው የምታውቀኝ›› ብለው መለሱለት ይባላል፡፡ ዳንኤልም የሚያውቀውን ዐውቆ ምክሩን ለገሠ፡፡ ነውሩ ምንድን ነው፡፤ አንዳንዶቻችሁ ማኅበሩን ለብሶ ነው የምታውቁት፤ እርሱ ግን ራቁቱንም ያውቀዋል፡፡ ወደ ውስጥ እንይ፤ ውስጣችን ጠንካራ ከሆነ ከውጭ ምንም ቢመጣ ችግር የለውም ነው ያለው፡፡ ሊፈተሸ የሚገባቸውን ቦታዎችንም ጠቁሞናል፡፡ ያ ማለት እነዚህ ሰዎች አክራሪዎች፣ አሸባሪዎች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ አመራሩ በፋክት መጽሔት ለወጣው የዐመጽ ጥሪ ያለውን ዐቋም አልገለጠም፡፡ ይህ ለእኔ የአመራር ድክመት ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ምንም እንኳን ዳንኤል በሚገባ ባይገልጠውም፣ በሊቃውንቱ ጉባኤ መታገድ ላይ የአመራር ድክመት እንዳለበት የታወቀ ነው፡፡ በአንዳንድ ማዕከላት የአሠራር ድክመቶች ይታያሉ፡፡ እነዚህ ይታረሙ ነው ያለው፡፡
  እኔ ሁለት ዓይነት ሰዎችን እቃወማለሁ፡፡ በአንድ በኩል ማኅበሩ ምን አያስፈልግም፣ ጥፋት ብቻ ነው የሚሠራው ስለዚህ መኖር የለበትም የሚሉትንና ማኅበሩ ምንም ስሕተት የለበትም፣ የመላእክት ማኅበር ነው፣ አይሳሳትም የሚሉትን፡፡ ሁለቱም እኩል አደገኞች ናቸው፡፡ ማኅበሩን የምንወዳውም፣ የምንደግፈውም ስለማይሳሳት አይደለም፡፡ ሊሳሳት እንደሚችል ዐውቀን ነው አባል የሆንነው፡፤ ነገር ግን ሊሳሳት እንደሚችለው ሁሉ ሊታረምም ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ የማረሚያና የማሻሻያ መንገዶችንም በበቂ ሁኔታ አዳብሯል ብለንም እናምናለን፡፡ ስለዚህም ማኅበሩን አትንኩት፣ ደግፉት እንጂ አትተቹት፣ ብርታቱን እንጂ ድክመቱን አትናገሩ፤ ዘምሩለት እንጂ አታልቅሱለት የሚለው ነገር ተገቢ ነው አልልም፡፡ ማኅበሩን እንወደዋለን፣ እንደግፈዋለን፣ ግን ደግሞም እናርመዋለን፡፡
  ነህምያ

  ReplyDelete
 40. those who seems to be the member of mk but really not are trying to confuse others by giving very shameful ideas. please try to understand them they are neither members nor supporter of mk. awake up please!!! dani you are great.

  ReplyDelete
 41. ለተከበረርኍዉ ዉድ ወንድማችን ደ/ን ዳንኤል ለጤናህ እንዴት ሰነበትህ ፣የተለየያዩ ዝግጅቶችን ስታዘጋጅ በቪዲዮ ተቀርጸ ቢቀርቡልን ብዙዕዉቀት እናገኛለን ፡፡ስለዚህ ወደፊት አስብበ
  ት፡፡

  ReplyDelete
 42. እኔ አንዳንዶቻችሁ በጣም ትገርሙኛላችሁ፡፡ ወደ ውስጥ እንይ ማለት ነውሩ ምንድን ነው፡፡ አጤ ቴዎድሮስ ያሉትን እዚህ ላይ መጥቀስ ይገባል፡፡ አጤ ቴዎድሮስና እቴጌ ምንትዋብ እልፍኛቸው ውስጥ ሲጨቃጨቁ እልፍኝ አስከልካዩ ይሰማል፡፡ እንዴት ጌታዬን እቴጌይቱ ትናገራቸዋለች ብሎ በንዴት መሣሪያውን ይዞ ዘው ብሎ ይገባል፡፡ ወዲያው ንጉሡ ተገርመው ‹‹ምን ሆንክ›› ይሉታል፡፡ እርሱም ‹‹እንዴት እመቤቴ ጌታዬን ይናገሯቸዋል›. ብሎ ይናገራል፡፡ ንጉሡም ‹‹በል ተመለስ፣ አንተ የንግሥና ልብሴን ለብሼ ነው የምታውቀኝ፤ ምንትዋብ ግን ራቁቴን ነው የምታውቀኝ›› ብለው መለሱለት ይባላል፡፡ ዳንኤልም የሚያውቀውን ዐውቆ ምክሩን ለገሠ፡፡ ነውሩ ምንድን ነው፡፤ አንዳንዶቻችሁ ማኅበሩን ለብሶ ነው የምታውቁት፤ እርሱ ግን ራቁቱንም ያውቀዋል፡፡ ወደ ውስጥ እንይ፤ ውስጣችን ጠንካራ ከሆነ ከውጭ ምንም ቢመጣ ችግር የለውም ነው ያለው፡፡ ሊፈተሸ የሚገባቸውን ቦታዎችንም ጠቁሞናል፡፡ ያ ማለት እነዚህ ሰዎች አክራሪዎች፣ አሸባሪዎች ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ አመራሩ በፋክት መጽሔት ለወጣው የዐመጽ ጥሪ ያለውን ዐቋም አልገለጠም፡፡ ይህ ለእኔ የአመራር ድክመት ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ምንም እንኳን ዳንኤል በሚገባ ባይገልጠውም፣ በሊቃውንቱ ጉባኤ መታገድ ላይ የአመራር ድክመት እንዳለበት የታወቀ ነው፡፡ በአንዳንድ ማዕከላት የአሠራር ድክመቶች ይታያሉ፡፡ እነዚህ ይታረሙ ነው ያለው፡፡
  እኔ ሁለት ዓይነት ሰዎችን እቃወማለሁ፡፡ በአንድ በኩል ማኅበሩ ምን አያስፈልግም፣ ጥፋት ብቻ ነው የሚሠራው ስለዚህ መኖር የለበትም የሚሉትንና ማኅበሩ ምንም ስሕተት የለበትም፣ የመላእክት ማኅበር ነው፣ አይሳሳትም የሚሉትን፡፡ ሁለቱም እኩል አደገኞች ናቸው፡፡ ማኅበሩን የምንወዳውም፣ የምንደግፈውም ስለማይሳሳት አይደለም፡፡ ሊሳሳት እንደሚችል ዐውቀን ነው አባል የሆንነው፡፤ ነገር ግን ሊሳሳት እንደሚችለው ሁሉ ሊታረምም ይችላል ብለን እናምናለን፡፡ የማረሚያና የማሻሻያ መንገዶችንም በበቂ ሁኔታ አዳብሯል ብለንም እናምናለን፡፡ ስለዚህም ማኅበሩን አትንኩት፣ ደግፉት እንጂ አትተቹት፣ ብርታቱን እንጂ ድክመቱን አትናገሩ፤ ዘምሩለት እንጂ አታልቅሱለት የሚለው ነገር ተገቢ ነው አልልም፡፡ ማኅበሩን እንወደዋለን፣ እንደግፈዋለን፣ ግን ደግሞም እናርመዋለን፡፡
  ነህምያ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Stay Blessed!

   Delete
  2. ትክክል ነህ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አስተያየትህ ተመችቶኛል፡፡ ነህምያ

   Delete
  3. Great idea! I was thinking of the same idea.

   Delete
 43. Beaman thanks for ur idea

  ReplyDelete
 44. "በወቅቱ ዐቃቤ መንበር ለነበሩት ለአቡነ ቴዎፍሎስ ብዙ ሰዎች እየሄዱ ‹‹እገሌ ፓትርያርክ ቢሆኑ፣ ሕዝቡ እገሌን እያለ ነው፣ መኳንንቱ እገሌን እያሉ ነው፣ ባሕታውያኑ እገሌ ይሆናሉ ብለው ትንቢት እየተናገሩ ነው፣ ቤተ ክህነቱም እገሌን እያለ ነው›› እያሉ ይነግሯቸው ነበር፡፡ ሁሉንም የሰሙት አቡነ ቴዎፍሎስም ‹‹ባሕታውያኑም፣ ሕዝቡም፣ መኳንንቱም፣ ቤተ ክህነቱም ያሉትን ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔርስ ምን አለ?›› ብለው ጠየቁ ይባላል፡፡"

  ከልብ የማይጠፋ የምክር ስንቅ ነው፡፡
  ዲ/ን ዳንኤል፣ አንተንስ እግዚአብሔር ለዘላለም ያኑርህ!!!

  ReplyDelete
 45. Anten yeseten Egziabher yetemesegene yihun. mechereshahin yasamrilih

  ReplyDelete
 46. በክርስትና ውስጡ ውጩን ይስበዋል እንጂ፣ ውጩ ውስጡን አይስበውም፡፡ ‹‹ዝናብም ወረደ፣ ጎርፍም መጣ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው በዐለት ላይ ስለተመሠረተ ግን አልወደቀም›› ይላልና፡፡ ያልወደቀው ስላልተመታ ሳይሆን መሠረተ ጽኑዕ ስለነበረ ነው፡፡

  ReplyDelete
 47. ሰዉ ያለሀበሳዉ መወንጀል ለእኔ ክርስቶስን አሳልፎ ከሰጠዉ ከይሁዳ ለይቸ አላየዉም፤ እዚህ ላይ የማህበሩን አመራር የሚተች ነገር አለየሁም፡፡ ሁላችንም አንብበነዋል፤ ግን ለምን እንደፍላጎታችን እንተረጉመዋለን፡፡

  “እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡” ለዲ/ዳንኤል፡- እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ፤ይጠብቅህ፡፡
  ዳኔየ ሁላችሁ ሳትሆኑ ፈተናው የመጣ ለበተክርስትያን ነው ስለዚሕ መተቸት ይቅርና ከዚያም የከፋ ቤመጣ ኦንዳልከው ጾለት እየታከለበት ቆም ብሎ በማስተዋል በትአግስት በጥበብ መጏዝ ነው ።ማሕበሩን እዜሕ ያደረሰ አምላክ ያያል መልስም አለው ።እንዳልከው ጽናቱን ያብዛላችሑ፤ለበተክርስቴያናችን ይሕ የፈተና ግዜ አጭር ያርግላት ። በርቱ !!!

  ReplyDelete
 48. ከቻልንሰ ቅን እንሁን !!!

  ReplyDelete
 49. በ1525 ዓ/ም በጀርመን አገር የተካሄደው የገበሬዎች አመፅ ፡ እንዲሟሉ ካቀረባቸው 12 ነጥቦች የመጀመሪያው ፡-

  የቤተክርስቲያኑ ማህበር ቄሱን የመምረጥ (የመሾም) መብት እንዲኖረው ፡ ቄሱ ማናለብኝነተን ቢያሳይ ደግሞ ፡ ማስወገድ እንዲችል፡፡ ቄሱ ወንጌልን ፡ ምንም ተቀጥያ ሳያደርግ (ገዥዎች የጨመሩትን ሳያስገባ) ልክ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ብቻ እንደሰፈረው ፥ ሰው ለእግዜአብሔር ባለው ንፁህ እምነት ብቻ ፡ መንግስተ ሰማይን ሊወርስ መቻሉን እንዲሰብክ፡፡
  መንገደኛው

  ReplyDelete
 50. ስለ ማህበረ ቅዱሳን ያነበብኩት እዉነት አይሁን እላለሁ እነሱ ፈረሱ ማለት ቤተክርስቲያን ለመናፍቃን ና ለሌቦች እጅ እንዳትሰጥ እሰጋለሁ መድሀኒአለም ያፅናቸዉ ዉስጤ እንዴት እንደተረበሸ እራሴ አዉቃለሁ መተንፈስም መረጋጋትም ተሳነኝ እባካችሁ ባላችሁበት ፅኑ ክርሰቲያኑ ወዷችኋል በድንግል ማሪያም አማላጅነት ተመለሱ አይዟችሁ በናንተላይ የሚደርስ ጥቃት በኛም ላይ ነዉ እጅ እንዳትሰጡ አደራ !!!

  ReplyDelete
 51. melkam ababal neew wendime dn Daniel....enen yemiyasasebegne be ande ande web. ye mitsafut negeroch mahiberun be metefo liasayew yichilal beteley dn ephrem belog [adebabay .com] beterefe egizabehere ke hulachenem gara yehun amen!!! yehen comment lante asqerew atawetaw !

  ReplyDelete
 52. ከዚያ ወዲያ ግን፣ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ግን፣ የዐቅማችንን ሁሉ ከፈጸምን በኋላ ግን ‹‹እግዚአብሔር ምን አለ? የሚለው እንጂ እነ እገሌ ምን አሉ›› የሚለው ሊያሳስበን እንጂ ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ ቂጣ ከሆነ ይጠፋል፣ ሺልም ከሆነ ይገፋል፡፡

  ReplyDelete
 53. እግዚአብሔርስ ምን አለ? I love this.

  ReplyDelete
 54. Peace to you Dn Daniel. It is good for you not to write anything about Mk. Formerly you were member and tried your best. God pays/repays you for all good deeds. Now u are out of this Association. Any comments you give or article you write at this moment are not viewed positively. There are many things that we want to know from you. Depending on current sensitive issues of our church/Mk is no more viable to you. Rather entertain us by your usual writings which are full of Amharic Oral Literature. This is the center of your profession as far as I know.

  ReplyDelete
 55. "ከዚህ መከራ ባሻገር በጎ ነገር ባይኖር ኖሮ እግዚአብሔር ይህ እንዲደርስ አይፈቅድም ነበር"

  ReplyDelete
 56. በመከራ ውስጥ ማለፍና መከራን መቀበል እንዲሁ ከታላቅ ምግባር የሚመድብ ሲሆን የበለጠ ጠቃሚው ነገር ግን በመከራ ጊዜ እንደግዴታ ሳይቆጥሩ በደስታ ማመስገን ነው....

  ReplyDelete
 57. እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡

  ReplyDelete
 58. ፍቅርን እወቁ፡፡

  ReplyDelete
 59. እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡

  ReplyDelete
 60. You are all right inner-out is better than out-inner

  ReplyDelete
 61. ካልደፈረሰ አይጠራም የሚል አባበል እንዳለን እስታውሳለሁ፡ በመሆኑም ማንኛውም ሰው በማህበረ ቅዱሳን ላይ ያለው ግንዛቤ ጥርት ያለ ግልጽ ይሆን ዘንድ ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ ይህ ሁሉ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ የእውነትና የቅንነት አምላክ መልካሙን ሁሉ ያድርግልን፡፡

  ReplyDelete
 62. tebale tebale wedhiwnet endaykeyer teru masgenzebiya meliket new dani.

  ReplyDelete
 63. egziabhare yakibreh .ene addis amdegnanegne .berta

  ReplyDelete
 64. i really appreciate you Deacon Daniel

  ReplyDelete
 65. Yehine shihufe betam wedjatalhu. hulame menem neger kemewesene befit EGEZIABEHER MEN yelal yemelewen teyake askedemaleu.
  God bless you.

  ReplyDelete
 66. D/n Daniel yeseteken mikre hasabe betam des yemile astemari ena eghame bealet laye yetegeneba hentsa endinehone yemiaderg new hulem bedihere getsek ayeleyen Egziabher yebarkehe

  ReplyDelete
 67. ፕሮቴስታንቱ ወደ ሰው ሃይማኖት ጠልቀው እየገቡ፣ ሁከት እና ጦርነት በማነሣሣት፣ ሰላምን ሊያሳጡን ድንበራችንን ለማፍረስ እየሞከሩ ናቸው፤ እግዚአብሔር የሚለው ግን የሰላም አምላክ መሆኑን ነው፡፡

  ሰላም የምትገኘው በሰላሙ ገዢ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም” በሚል ቃል ኪዳን አጽናንቶናል እንጂ በሁከት ሊያምሱን አቅደዋል (ዮሐ 14፡27)፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን የሰላማዊው የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች ስለሆንን፣ የማንንም የሃይማኖት ድንበር ነክተን አናውቅም፣ ወደ ሰው ሃይማኖት ቅጽርም ገብተን ለመንጠቅ በተኩላነት ባህርይ፣ በጸብ አጫሪነት ተግባር አንሠማራም፡፡ ምክንያቱም “የቀደሙ ሰዎች የተከሉትን የባልንጀራህን የድንበር ምልክት አትንቀል” የሚል የሰላማዊ አምላክ ትእዛዝ አለንና (ዘዳ 19፡14) ሰው ላይ አንደርስም፣ እንዲደርሱበንም አንፈቅድም፤ ዘወትር ስንጸልይ የምንለው፡- “ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰላምን አጽናልን” በማለት ነው፡፡ በየአዳራሾች እንደሚጮሁት መናፍቃን፡ “የኦርቶዶክስን….እናፍርስ፣ የማኅበረ ቅዱሳን እንትን ይፍረስ፣ የኦርቶዶክስ እንትን በኢየሱስ ስም ይፍረስ” እያልን ሰውን አንራገምም፤ የሚረግሙንን እንመርቃን እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 68. እነርሱም፣ እነዚያም፣ እኛም ወደ ውጭ እያየን ችግሮቻችንን ከውጭ ከመፈለግ ይልቅ ወደ ውስጦቻችን እንመልከት፡፡ ውስጣችንን በደንብ ካየነው በውስጡ በኩል ውጩ በደንብ ያታየናል፡፡ በውጩ በኩል ግን ውስጡን ማየት አይቻልም፡፡ ቁም ነገሩ ‹ምን አሉን›› አይደለም፤ ምንድን ነን? ነው፡፡ እንዳንሆን እንጂ እንዳይሉን መከላከል አንችልምና፡፡ interesting speach!!!GOD plees all of us!

  ReplyDelete
 69. ሰውዬው በሩን በጠንካራ ብረት ዘግቶ ሲጠብቅ ያየው ጎረቤት ‹‹ምነው እንዲህ ታጠብቀዋለህ፤ አላህን አታምንም እንዴ ብሎ ቢጠይቀው ‹‹አላህንም አምናለሁ፣ በሬንም አጠብቃለሁ› Why do u want to use Arabic word , I just don't like it ..........weys Be Geezu "ala adhnene ....

  ReplyDelete
 70. ሁሉም በየግሉ የተለያየ ሀሳም ይሰጣል።ማሰሪያው ግን አንድ ነው። እሱምአምላክ ውልድ አምላክ እየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክሪስትያንን ቅፅሮቿን መጠበቅ፣አንድ ወንድሜ ሲያስተምር ባለፈው ሳምንት በ 16/02/2006 ዓ.ም አንበሳ ሲለምን አንተ መድሃኒአለም በሰለም እንዳሰደርክ በሰላም አውልኝ፣
  የእለት ምግቤንም ስጠኝ ይላል
  በተመሳሳይ ጥንቸል አምላኬ በሰላም እንዳሳደርከኝ በሰላም አውለኝ ፣ከደፋሪ አውሬ አንተ ጠብቀኝ እያለች ስትፀልይ ፊት ለፊት ከ አንበሳው ጋር ተያዩ፣ አንበሳው ሊይዛት ሲሮጥ እሷም ለመሽሽ ስትሞክር አንድ ትልቅ ገደል አገኙ እሷ ዘላ አመለጠች አንበሳውም ስዘል ገደሉ ስር ላይ አጋዘን ተኝቶ ነበርና አንበሳው በላው። ሰለዚህ አንበሳው የእለት ምግቡን አገኘ፣ጥንቸልም ከአውሬ አድነኝ እንዳለች ዳነች አመለጠች፣ መውጫ ቀዳዳ እግዝአብሔር አዘጋጀላት። ይህ አባባል የተጠቀምኩት ምን ለማለት መሰለህ ዲ/ን የለመነ በላ የተኛ ተበላ ይላሉ አባቶች ሲተርቱ። ሰለዚህ ሁሉም የማህበሩ አባለት በጎውን ቸሩን ሰራቸው ብቻ እንዲወራ ይፈልጋሉ ማለት አይቻልም፣ ነገር ግን የማህበሩ አባለት ሁሉም ሳይሆ እንደኔ ገባ ወጣ የሚሉ አባላት እግዝአብሔር አምላክ ከተኙበት ይቀስቅሳቸው፣ ማህበሩ በእግዝአብሔር ፈቃድ የተመሰረተ ማህበር ሰለሆነ ቢያፈረሰውም እግዝአብሔር ነው እንጂ በሰው ወይም በመንግስት ባለስልጣን የሚፈርስ አይደለም። ለሁሉም የእግዝአብሔር ረድኤት አይለየን።

  ReplyDelete
 71. ዳኒ እኔ እግዚአብሄርን አንድ ነገር ነው የምማጸነው ለአንተ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እንዲሰጥልኝ ጸጋውን እንዲያበዛልህ ከክፉ ነገር ሁሉ እንዲጠብቅህ ፤ እውነት እግዚአብሄር እኮ ካልባረከ ተናግሮ መደመጥን፤ በሰው ሁሉ ዘንድ መወደድን እና ግርማ ሞገስን ማግኘት በፍጹም አይቻልም፡፡ አንተን እግዚአብሄር ለኛ የሰጠን መምህራችን፤ ምልክታችን ወይም ሞዴላችን ነህ ብልህ አያንስብህም፤፤ እኛ ካንተ ብዙ ነገሮችን ተምረናል በአለማዊም ሆነ በመንፈሳዊ እውቀታችን እንድንበረታ እንድንጸና መሰረት አስጨብጠህናል፡፡ በርግጥ አንዳንድ ሰዎች በጣም ጥቂቶቹ አንዳንድ ጊዜ ባለመረዳት ሊሆን ይችላል ሌሎቹ ግን ሆን ብለው የአንተ ሀሳቦች ላይ ህጸጽ ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ ይህ ደግሞ በጣም ያስጠላልም ያስታውቅባቸዋልም፤ ግን ብዙ ባይለፉ ጥሩ ነው ያንተኮ በቃ ከእግዚአብሄር የተሰጠህ ጸጋ ነዉ ፡፡ ይህንን ሁሉም ሰው ሊያዉቀው ይገባል በሰዎች ጸጋ ሰዎች መቅናት የለባቸዉም ፡፡ለነሱ ደግሞ እግዚአብሄር ሌላ ጸጋ ሰጥቷቸዋል፡፡ ለሁሉም እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡ ይህን ሀሳብ ልጽፍ የቻልኩት ዳኒ አንዳንዶች በሚሰጡህ ኮሜንቶች discourage እንዳትሆን ብዬ ነው፡፡ ሀሳቡ ግልጽ ካልሆነላቸዉ የትችት በትራቸዉን ከመሰንዘራቸው በፊት ሀሳቡ ግልጽ እንዲሆንላቸዉ በቀናነት ቢጠይቁህ ደስ ይለኛል፡፡ በተረፈ መንፈሳዊ ስብከቶችን ቶሎ ቶሎ ብታሳትም ደስ ይለኛል፤ አሁንም ብዙ ሰዎችን ሊያስተምርና ሊለውጥ የሚችሉ ብዙ ነገሮች ውስጥህ ታምቀዉ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ስብከቶችህ ደግሞ በጣም በሳል፣ ጠንካራ መልእክት ማስተላለፍ የሚችሉ፣ መሰረታዊ ሀሳብ ከማስጨበጣቸዉም በላይ ህይወታችንን ያለመልሙልናል፡፡ እግዚአብሄር በነገሮች ሁሉ አይለይህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሔርስ ምን አለ?

   Delete
  2. እግዚአብሔርስ ምን አለ?

   Delete
 72. "ክርስትና የመሞት እንጂ የመግደል ሃይማኖት አይደለም።"

  የምንሰማህ ከሆነስ፤ እያንዳንዳችን ራሳችንን እንድናይ፣ እንድንፈትሽ ነው የነገርኸን። ማህበሩ የአባላቱ ስብስብ (አንድነት) ነውና።
  እግዚአብሄር ማህበራችንን ይጠብቅ፣ አንድነታችንን ያጽናልን። አሜን!

  ReplyDelete
 73. «ምነው በርህን እንዲህ ታጠብቃለህ አላህን አታምንም እንዴ?»
  አላህንም አምናለሁ በሬንም አጠብቃለሁ ................ለኔ ጥሩ አባባል ነች።

  ReplyDelete