Tuesday, April 1, 2014

የወፏ ዝማሬ

ሰውዬው ዛፍ ሥር ቁጭ ብሎ ያዳምጣል፡፡ ወፏን፡፡ የሚመስለው ግን የተመሰጠ በገና ደርዳሪን፣ የተሸለመ መሰንቆ መቺን፣ ከብቶቹ ለምለም ሣር ያገኙለት ባለ ዋሽት እረኛን እንደሚያዳምጥ ነው፡፡ ዐሥር ጊዜ አንገቱን ይነቀንቃል፡፡ የወፏ ዝማሬ ገብቶታል መሰል፡፡ በግጥሙ ቤት፣ በስንኙ አወቃቀር፣ በሐረጉም ቅኔ እንደረካ ሰው ነው ሁኔታው፡፡ ሰምና ወርቁን እንዳገኘ ቅኔ ሰሚ አንገቱን ግራ ቀኝ ይወዘውዛል፡፡ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ወፏ ራሷ ደንግጣ ልትበርር እስክትደርስ ድረስ ለወፏ ዝማሬ የፊልም ቤት ጭብጨባ ያጨበጭባል፡፡


ይኼ ሁሉ ሲሆን አሻግሮ ሌላ ሰው ያየዋል፡፡ ያውም የሰውየውን ጤንነት እየተጠራጠረ፡፡ መጀመሪያ የሆነ ሌላ ነገር እያዳመጠ መስሎት ነበር፡፡ ጠጋ ሲል ምንም ሌላ ነገር አጣ፡፡ የሚያነብም መስሎት ነበር፡፡እጁ ግን ባዶ ነው፡፡ በአካባቢውም አንገቱን አዟዙሮ የሚያወጋው አንዳች ነገር ካለ ብሎ ፈለገ፡፡ ሰውዬው ብቻውን ነው፡፡ የሚገርመው ግን ወፍ አዳማጩ ሰው መንገደኛውን አላየውም፡፡ እርሱ ተመስጦ ላይ ነው፡፡ አንዳች ነገር ልቡን ነክቶት እንገቱን ከላይ ወደ ታች እየነቀነቀ ነው፡፡
መንገደኛው ሰው ጠጋ አለው፡፡ ወፍ አዳማጩ ሰው ቀና አለ፡፡ በእጁ እንዲቀመጥ ጋበዘው፡፡ መንገደኛው እየተገረመ ተቀመጠ፡፡
‹‹አንዳች ነገር መጠየቅ እችላለሁ›› አለ መንገደኛው ሰው፡፡
‹‹ድምጽህን ቀንሰህ እንጂ አዎ›› አለው የሹክሹክታ ያህል››
‹‹እ-ሺ - ምንድን ነው የምታዳምጠው›› አለው በጆሮው የመናገር ያህል ቀስ ብሎ፡፡
‹‹ወፏን››
መንገደኛው በኤሌክትሪክ ወንበር ላይ ያስቀመጡት ያህል ተስፈንጥሮ ተነሣ፡፡ ከሆነ አንድ ጠንቋይ ጋር የተቀመጠ መሰለው፡፡ ወፍ ከሚሰማ ጠንቋይ፡፡ ደግሞስ ወፏ ምን እያለች እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ የምትናገረው ስለ እርሱ ቢሆንስ፡፡ ወፍ አዳማጩ ሰው ግን ግራ እጁን ይዞ ጎተተና እንደገና አስቀመጠው፡፡
‹‹ለምን ደነገጥክ?›› አለው ቀስ ብሎ፡፡
‹‹አይ ታስፈራለህ፡፡ ልሄድ ነው በቃ›› አለ እጁን ለማስለቀቅ እየሞከረ
‹‹ይልቅ ሞኝ አትሁን፤ ተቀመጥና ወፏን አዳምጥ፡፡ ስንት ነገር ታገኛለህ መሰለህ›› አለው፡፡
መንገደኛው ድንጋጤውና ፍርሃቱ ጨመረበት፡፡ ‹‹አልችልም፤ እኔ ወፍ ማዳመጥ አልችልም›› አለው መንገደኛው፡፡
ወፍ አዳማጩ ሰው በቀሰስታ ‹‹እኔ አሳይሃለሁ መንገዱን›› አለው፡፡ መንገደኛው አሁን ጭራሽ ባሰበት፡፡ እርሱንም ጠንቋይ ሊያደርገው ያሰበ መሰለው፡፡ ዘወር ዘወርወር ብሎ አካባቢውን ማተረ፡፡ በሩቁ በሚታየው የማቋረጫ መንገድ በኩል እንደርሱ ያሉ መንገደኞች ሲጓዙ ይታዩታል፡፡ እርሱም እንዳች ማረፊያ ጥላ ፍለጋ ነበር ወደዚህ አሳብሮ የመጣው፡፡ የገጠመው ግን ወፍ የሚያዳምጥ ሰው ነው፡፡ በርግጥ ይህ ዛፍ በመንገድ ለሚደክሙ መንገደኞች አሳብረው የሚያርፉበት ነበር፡፡ እርሱም ብዙ ጊዜ እዚያ ዐርፎ ያውቃል፡፡ እዚያ ሲያርፍም የወፎችን ዝማሬ በአልፎ ሂያጅ ልቡ ሰምቶ ያውቃል፡፡ በአካባቢው ትልቁ ዛፍ ያ ስለሆነ ወፎቹ ይመርጡታል፡፡ ያ ዝማሬያቸው ግን የዚህን ሰውዬ ያህል መስጦትም፣ አስደስቶትም አያውቅም፡፡
‹‹አሁን እንዴው የምርህን ወፍ እያዳመጥክ ነው›› አለው መንገደኛው፡፡
‹‹አንተ ግን ምንም አይሰማህም›› ብሎ መለሰለት አዳማጩ፡፡
‹‹በቃ ያው የወፍ ዜማ፤ በቃ፡፡ የወፍ ዜማ ብርቅ ነው እንዴ››
‹‹ወፏ የምትለውንስ ትሰማለህ››
‹‹ልጅ ሆነን የወፍ ቋንቋ እያልን እንጫወት ነበር፡፡ ያ ግን የወፍ ቋንቋ አይመስለኝም፡፡ ሰውም የወፍ ቋንቋ የሚያውቅ አይመስለኝም››
‹‹የወፍን ቋንቋኮ ማንም ሰው መስማት ይችላል››
‹‹እኔ ለምሳሌ አልችልም›› ጆሮውን በእጆቹ ዳሰሰ፡፡
‹‹ትችላለህ››
‹‹አንተ እኔን ታውቀኛለህ›› በጥንቆላው እንዳያውቀው በመፍራቱ ‹አላውቅህም› እንዲለው ፈለገ፡፡
‹‹ሰው አይደለህም እንዴ››
‹‹ብሆንስ››
‹‹ከሆንክማ ትችላለህ ማለት ነው፡፡ ሰው ሁለት ዓይነት ጆሮ አለው፡፡ የሥጋ ጆሮና የልቡና ጆሮ ወይም እዝነ ሥጋ እና እዝነ ልቡና፡፡ በሥጋ ጆሮው ማዳመጥ የሚችለው የሰው ቋንቋ፣ መስማት የሚችለውም አልፎ ሂያጅ ድምጽ ነው፡፡ በልቡና ጆሮው ግን ወፍንም፣ እንስሳንም፣ ወንዝንም፣ መብረቅንም፣ ተራራንም፣ ዛፍንም መስማት ይችላል›› አለው፡፡ ከበደ ሚካኤል ይህንን ችሎታቸውን ተጠቅመው ነው ደመናና ጽጌረዳ ሲያወሩ የሰሙትን የነገሩን፡፡ ‹ጽጌረዳና ደመና› የሚለውን ግጥማቸውን ታውቀዋለህ?
‹‹እሺ አንተ ከወፏ ምን ሰማህ?›› አለው መንገደኛው፡፡
‹‹ምን የመሰለ ቅኔ፣ ምን የመሰለ ዕውቀት፣ ምን የመሰለ የሕይወት ትርጓሜ››
‹‹እስኪ አንዱን ንገረኝ››
‹‹ወፏ ምን አለች መሰለህ፡፡ ትዘምር የነበረው ስለ ዛፉ ነው፡፡ ዛፍ ሆይ አትመካ፣ እኔን አስጠለልኳት፣ አሳረፍኳት ብለህ አትመካ፡፡ በቅርንጫፍህ አትመካ፡፡ ለእኔ ዋናው ያንተ ቅርንጫፍ አይደለም፡፡ለእኔ ዋናው የራሴ ክንፍ ነው፡፡ ቅርንጫፍህ ሊቀር ይችላል፡፡ አንተም አላስጠልልም ልትል ትችላለህ፡፡ ያ ያንተ መብት ነው፡፡ እኔ ግን የምመካውም የምተማመነውም በገዛ ክንፎቼ ነው፡፡ ክንፎቼ ካሉልኝ የትም እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ዛፍ ላይ ዐርፋለሁ፡፡ ሌላ ቤት ላይ እወጣለሁ፡፡ በተራሮች ላይ እቆማለሁ፡፡ በመስኩ ላይ እራመዳለሁ፡፡ ስለዚህ ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡ - ይህንን ነበር የምትዘምረው››
መንገደኛው ተገረመ፡፡ የወፍ አድማጩን ችሎታም አደነቀ፡፡ አብልጦ ደግሞ የወፏን ዝማሬ አደነቀ፡፡ ወፍኛ ቢችል ኖሮ መወድስ ያደርሳት ነበር፡፡
‹‹ቆይ አንተ ይህንን የወፍ ቋንቋ ከየት ተማርከው›› መንገደኛው ጠየቀ፡፡ ቅድም እንዳልፈራ ሁሉ አሁን ለማወቅ ጓጓ፡፡ የማያውቁት ነገር ምንጊዜም ያስፈራል፡፡ መቃብር ለመቃብር ቆፋና ለቀባሪ እኩል አያስፈራም፡፡
‹‹ይህ ነገር የምትማረው አይደለም፡፡ ሰው በመሆንህ የምታገኘው ነው፡፡ ግን ማሳደግ ይፈልጋል፡፡ እዝነ ልቡናህን መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ለሕይወት ትርጉም መስጠትን ይፈልጋል፡፡ ዝም ብሎ የተፈጠረ፣ ዝም ብሎም የሚኖር፣ ዝም ብሎ ነገር የለምና፤ ዝም ብለህ የምታልፈው ዝም ብሎ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ኑሮ ከንቱ አይደለችም፤ ሕይወት ቂላቂል አይደለችም፡፤ ሕይወት ቅኔ ናት፡፡ እየፈታህ የምትማርባትም የምትደመምባትም፡፡ ፍጡራን ሁሉ ልዩ ልዩ ዓይነት ቅኔዎች ናቸው፡፡ ማዳመጥ፣ ማየት፣ መንካት፣ መመርመር፣ መተንተን የሚፈልጉ ቅኔዎች፡፡ አየህ በሥጋ ጆሯችን ብዙ ቸበርቻቻዎች ስንሰማ ስለምንኖር የሕይወትን ዝማሬ የመስማት ዕድላችን ጠብቧል፡፡ አንት ግን እይ፣ ስማ፤ አካባቢውን፣ የዐየሩን ሁኔታ፣ ድምጹን፣ የፍጥረትን እንቅስቃሴ፣ የፍጥረትን የርስበርስ ተግባቦት አድንቅ፤ አድንቅና ፍታው፡፡ ድምጽ ዝማሬ፣ ትርዒትና መልእክት የሌለው ፍጡር የለም፡፡ ዝማሬያቸው ግን የሚሰማው፣ ትርዒታቸው ግን የሚታየው፣ መልእክታቸው ግን የሚረዳው ለሰው ነው፡፡ሰው ነው የሚፈታላቸው፡፡ ፍቺው ግን እንደየዕውቀታችን፣ እንደየኑሯችን፣ እንደየ ዐቅማችን፣ እንደየመረዳታችን፣ እንደየ ባሕላችን ሊለያይ ይችላል፤ የወፏን ዝማሬ እንተ ብትሰማው ሌላ ይሆናል የምትረዳው፡፡ ወፏ እንደዚያ አላለችም፡፡ እኔ ነኝ እንደዚያ የተረዳኋት፡፡ መድኃኒት እንደየበሽታው ነው፡፡
‹‹ያሬድ ያያትን፣ ሰባት ጊዜ እየወደቀች የተነሣችውን ትል አንተ ብታያት ኖሮ ሌላ ነገር ልትረዳ ትችል ይሆናል፡፡ ያሬድ ግን ወድቆ መነሣትን፣ ታግሎ ማሸነፍን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ አለመታከትን ከእርሷ ተማረ፡፡እርሷ ተጓዘች፡፡ እርሱም ጉዞዋን ተረጎመላት፡፡ ስለ ጳልቃን ጣልቃን፣ ስለ ከራድዮን፣ ስለ ዝሆን (ውርዝው ነጌና ዐቢይ ነጌ)፣ ስለ አንበሳ፣ ስለ ቀበሮ፣ ስለ ቁራ፣ ስለ ርግብ፣ ስለ ጉንዳን የምንሰማቸው ታሪኮች ሁሉ የእነርሱን አነዋወር ተመልክቶና አዳምጦ ለሕይወት የሚበጅ ትርጉም ከመስጠት የመጣ ነው፡፡
‹‹እይ፣ ዝም ብለህ ግን አትይ፤ ስማ፣ ዝም ብለህ ግን አትስማ፡፡ ዓለም መጽሐፍ ናት፡፡ ሚሊዮን ገጾች ያሏት፡፡ ገጹ እያንዳንዱ ገጠመኝህ ነው፡፡ ብልሆች እያንዳንዱን ገጽ ያነቡታል፡፡ ይማሩበታልም፡፡ ሞኞች ግን ገጹን እያጠፉ ብቻ ያልፉታል›› ይሄው ነው ወዳጄ፡፡
አሁን መንገደኛው ራሱ የወፏን ዝማሬ መስማት ጀመረ፡፡ አንገቱንም መነቅነቅ ቀጠለ፡፡ እርሱ የሰማውን ደግሞ ሌላ ደራሲ ይነግረን ይሆናል፡፡
ፍራንክፈርት፣ ጀርመን  

79 comments:

 1. ዛፍ ሆይ አትመካ፣ እኔን አስጠለልኳት፣ አሳረፍኳት ብለህ አትመካ፡፡ በቅርንጫፍህ አትመካ፡፡ ለእኔ ዋናው ያንተ ቅርንጫፍ አይደለም፡፡ለእኔ ዋናው የራሴ ክንፍ ነው፡፡ ቅርንጫፍህ ሊቀር ይችላል፡፡ አንተም አላስጠልልም ልትል ትችላለህ፡፡ ያ ያንተ መብት ነው፡፡ እኔ ግን የምመካውም የምተማመነውም በገዛ ክንፎቼ ነው፡፡ ክንፎቼ ካሉልኝ የትም እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ዛፍ ላይ ዐርፋለሁ፡፡ ሌላ ቤት ላይ እወጣለሁ፡፡ በተራሮች ላይ እቆማለሁ፡፡ በመስኩ ላይ እራመዳለሁ፡፡ ስለዚህ ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡ ግሩም ድንቅ !!!!

  ReplyDelete
 2. ዛፍ ሆይ አትመካ፣ እኔን አስጠለልኳት፣ አሳረፍኳት ብለህ አትመካ፡፡ በቅርንጫፍህ አትመካ፡፡ ለእኔ ዋናው ያንተ ቅርንጫፍ አይደለም፡፡ለእኔ ዋናው የራሴ ክንፍ ነው፡፡ ቅርንጫፍህ ሊቀር ይችላል፡፡ አንተም አላስጠልልም ልትል ትችላለህ፡፡ ያ ያንተ መብት ነው፡፡ እኔ ግን የምመካውም የምተማመነውም በገዛ ክንፎቼ ነው፡፡ ክንፎቼ ካሉልኝ የትም እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ዛፍ ላይ ዐርፋለሁ፡፡ ሌላ ቤት ላይ እወጣለሁ፡፡ በተራሮች ላይ እቆማለሁ፡፡ በመስኩ ላይ እራመዳለሁ፡፡ ስለዚህ ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡ ግሩም ድንቅ ነው እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 3. God bless you Dani. it is so intersting.

  ReplyDelete
 4. Hi, Danial I live in USA and everybody talked about your blog closed by current goverment because of the coming election . And they gave you a chance for the next two month. Is this true? Espacially in DC, Virginia and Maryland everybody talking about your blog. Some people were trying to conntact you by phone but they couldn't found it. Any way could you explain that to stop the rummer. Thank you.

  ReplyDelete
 5. Hi Daniel, I am your customary reader of your messages and I have learnt a lot so far. However, this is my first time posting my comment. Actually it is just to appreciate your effort to make people aware of critical issues. I think this article is important for this generation to consider all the treats and give wise and fundamental solutions. May God help every person to look in to the truth and the truth..........

  Stay strong and May God bless your service!

  ReplyDelete
 6. Hi Dn.Daniel, I read almost all of your articles on this blog and I have learned a lot so far. However, this is my first time posting my comment. Actually, it is just to appreciate your effort of making people aware of critical issues. I think this article is important for this generation to consider all the treats and give wise and fundamental solutions. I think this article is not very clear unless we read very carefully and pay deep attention as the person did in listening those birds songs. Looking forward to read others understanding to compare with what I have learned from the message. May God help every person to look in to the truth and the truth...........

  Stay strong and May God bless your service!

  ReplyDelete
 7. I am glad the domain issue is resolved and Thank you for comming back. God bless you and your work

  ReplyDelete
 8. ወፏ ምን አለች መሰለህ፡፡ ትዘምር የነበረው ስለ ዛፉ ነው፡፡ ዛፍ ሆይ አትመካ፣ እኔን አስጠለልኳት፣ አሳረፍኳት ብለህ አትመካ፡፡ በቅርንጫፍህ አትመካ፡፡ ለእኔ ዋናው ያንተ ቅርንጫፍ አይደለም፡፡ለእኔ ዋናው የራሴ ክንፍ ነው፡፡ ቅርንጫፍህ ሊቀር ይችላል፡፡ አንተም አላስጠልልም ልትል ትችላለህ፡፡ ያ ያንተ መብት ነው፡፡ እኔ ግን የምመካውም የምተማመነውም በገዛ ክንፎቼ ነው፡፡ ክንፎቼ ካሉልኝ የትም እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ዛፍ ላይ ዐርፋለሁ፡፡ ሌላ ቤት ላይ እወጣለሁ፡፡ በተራሮች ላይ እቆማለሁ፡፡ በመስኩ ላይ እራመዳለሁ፡፡ ስለዚህ ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡
  ትብል ማኅበረ ቅዱሳን

  ReplyDelete
  Replies
  1. እመኒ ሀለየት ከመዝ ወለት ማኅበረቅዱሳን በልዋ፡ ሁሪ ወተፈለጢ፤ወሕንጺ ቤተ ሀዲሰ፡፡አምጣነ ክልኤ አጋእዝት ኢይክሉ ነቢረ በዋህድ ማኅደር!!
   እንዲህ ባታስቡ ጥሩ ነው፡፡ዛፏ አሀቲ መባሉዋን መካድ ነውና፡፡አሀቲነቷም በቃለ ሲኖዶስ ይጸናል፡፡እንግዲህ ከዛፍ ዛፍ መዝለል ካዋጣ ጥሩ ነው፡፡እኛ እንኳ እንዲህ እስከመመካት አትደርሱም፣ትምክህታችሁም ከእምነትና ስርዐት ነው የሚመነጨው ብለን በስስት እያየናችሁ ነበር፡፡እምነት አጎደላችሁ፡፡ቅሬታ እንኳ ቢኖር ለቅ/ሲኖዶስ ይግባኝ ማለት እየተቻለ ፍሬዋን መግባ፣በቅጠሎቿ ጎጇችሁን እንድትሰሩ አድርጋ፣ነውራችሁን እንዳላየች የልጅ ነውር ነው ብላ ስታልፍ የቆየቸውን የ2ሺህ አመት ትክል ዛፍ እንደነ እንትና ክንፍ አውጥተናል ብላችሁ፣ካለእኛ አትኖርም ብላችሁ ታብያችሁ፣ የአባቶቻችሁን ገመና በየጋዜጣውና በየብሎጉ ስትረጩ ኖራችሁና በክንፌ እበራለሁ የማለታችሁ ድርጊት ክህደት ነው፡፡
   ቃል መብላት ነው፡፡በስርዐት ከህግና ከአስተዳደር በታች እደሩ መባል ይሄን ያህል የሚያንገበግብ መሆኑ የአበቃቀል ሳይሆን የአስተዳደግ ችግር ነው፡፡አበቃቀላችሁማ ከተዋሕዶው መዶሻ ከ20ኛው ክ/ዘመን የቤ/ክ መኩሪያ አቡነ ጎርጎርዮስ መሆኑን እናውቃለን፡፡አሁን ለአቅመ አዳም ደርሳችኋል፣ከፊሎቻችሁም ጎልምሳችኋል፡፡ስለዚህ ለድርጊታችሁ ሁሉ እናንተኑ እንሞግታለን እንጅ እኚያን 50 አመት ኖረው የ500 አመት ስራ ትተውልን ያለፉ አባት ስለ እናንተ ግብር አንወቅስም፡፡ስለ በዐላት አከባበርም ሆነ ስለአጽዋማት ቀኖና ቅ/ሲኖዶስ ለመወሰን ሙሉ መብት አለው የሚሉ፣ ቃለሲኖዶስን ትምክህት ያደረጉ አባት ነበሩ፡፡እኚህ አባት ሲኖዶስ ባለበት ምድር የልጆቻቸውን እንበራለን ማለትን ቢያዩ ልጆቼ የሚሏችሁ አይመስለኝም፡፡
   ይገባችኋል፡፡ በጣም እኮ ነው የሚያመው፡፡አባቶች ምንም አይነት የማስተባበል እድል በማያገኙበት ሚዲያ እኮ ነው መያዣ መጨበጫ በሌለው ሀሜት የሚደበደቡት፡፡ማን ሀይ አለ፡፡ባለትዳርና የልጆች አባት የሆኑ አስተዳዳሪዎችና ጸሀፊዎች በስማ በለው ሲብጠለጠሉ ሁሉም እንዳላየ አለፈ፡፡የቻለውም በአስተያየት ስም ጨምሮ አነወራቸው፡፡ዳንኤል አንተ በእንዲህ አይነት ሂደት ውስጥ አልፈሀልና በየብሎጉና ጋዜጣው የሚደረግ የስም ማጥፋት በተጎጂው ላይ የሚያደርሰው ስቃይ ይገባሀል ብየ አስባለሁ፡፡ለስቅለት ሰልፍ ውጡ ተብሎ ሲቀሰቀስ ማን ነውር ነው አለ፡፡ሃይማኖት ከማኅበር ተምታቶ ማኅበር በተነካ ቁጥር ሃይማኖት ተነካ ተብሎ ሲለፈፍ ማን ተግሳጽ ሰጠ፡፡ሲኖዶስ እየተቆረጠ በሚቀጠልባት ሀገር ማኅበርን አትተቹ ማለት እኮ ቅዱስ ነን ለማለት መቃጣት ነው፡፡ልናገር ብትል ውርጅብኝ ነው፡፡ተሀድሶ፣ሙሰኛ፣አማሳኝ፣ጉቦኛ፣መናፍቅ፣ዘረኛ….ስድብ እንደጥይት ጆሮህ እስኪግል ይተኮስብሀል፡፡ይሄ ያማል፡፡ባልሆንከው ሲጠሩህ ያማል፡፡ስያሜ መስጠት እኮ የማሳደድና የግድያ መጀመሪያ ነው፡፡
   ዛሬ አዛኝ ቅቤ አንጓች ሆነው ስለ እነ አቡነ ቶማስ ሊቅነትና መንፈሳዊነት የሚነግሩን ብሎጎች ትናንት እሳቸው በህይወት እያሉ ትንፍሽ አላሉም፡፡እንዲወራልህ ከፈለክ ማውሪያውን ከተቆጣጠሩት መወዳጀት ያልተጻፈ ህግ ስለሆነ እኮ ነው ቀብረን ገድላቸውን መቃብራቸው ላይ የምናወራው፡፡ይሄ ያማል፡፡ሁሌ አባት እንደሌለህ የሚነግርህ ሰው እያጽናናህ ሳይሆን እያሳዘነህ ነው፡፡እኛኮ ላለፉት 20 አመታት እንደዛ ነው የሆነው፡፡ስለ እነ አቡነ ቄርሎስ የድጓ እውቀትና ስብከት፣ስለ እነ አቡነ ያሬድ እና አቡነ እንድርያስ የትርጓሜ መጻህፍት እውቀት፣ስለ እነ አቡነ ማርቆስ ቅኔ በጉንጩ መሆን፣የአሜሪካው አቡነ መልከጼዴቅ በመንፈሳዊ መጻህፍት ህትመት ለኢተ/ቤ/ክ ስላበረከቱት አስተዋጽኦ፣ስለ እነ አቡነ ገሪማ የኢኦተቤክ የውጭ ግንኙነትን ከሩብ ክ/ዘመን በላይ በጫንቃ መሸከም ማን ነገረን፡፡ሰውን በቁሙ ሁለት ጊዜ መግደል ይቻላል፡፡አንድም የሌላውን ስም በመስጠት፣አንድም የሰራውን ሁሉ እውቅና ባለመስጠት፡፡አዝናለሁ፡፡ይሄ ትውልድ ሁለቱንም በደሎች በትጋት እየፈጸማቸው ነው፡፡
   ለማንኛውም ዛፉ ዋርካ ነው፡፡ሰፊ፡፡በግዙፍ ቅርንጫፎቹ ብዙ አእዋፋትን ማስጠለል ይችላል፡፡አሁንም አስጠልሏል፡፡ችግሩ አንዳንድ አእዋፋት የዛፍ እና ወፍ የግንኙነት ህግን ጥሰው ዛፍን በወፍ ህግ እንምራ ማለታቸው ነው፡፡እሱን እንንገራችሁ አይሆንም፡፡ አይደረግም፡፡ከፈለጋችሁ አንዴ ሳይሆን 7 ጊዜ ብረሩ እንጅ ፓትርያርካቸውን የደርግ ሰይፍ በበላበት፣ጳጳሳቱ በየከርቼሌው በታጎሩበት ወቅት በደርግ የይለፍ ወረቀት እየተንቀሳቀሱ ቤ/ክ ሲተክሉ ሲያስተምሩ የነበሩ ሰዎች አቁመው ያከረሙትን ዛፍ ገና ተብላልቶ፣ሰክኖ ላልጠራ የወጣቶች ማኅበር አስረክቡ ማለት ነውር ነው፡፡ባይሆን ተረዳድተን እናጠንክረው፣በቤ/ክ ኮሚቴዎች ተዋቅረን የድርሻችንን እናገልግል ማለት የአባት ነው፡፡
   ይልቅስ ትልቅ ሰው ጠፋ፡፡እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰው ጠፋ፡፡አዝናለሁ ዳኒ፡፡ባስቀመጥኩህ ቦታ አላገኘሁህም፡፡የማኅበሩንና የቤ/ክህነቱን አለመግባባት አቀራርቦ ለመፍታት እና ለወደፊቱም ማኅበሩ በተሰጠውና በሚሰጠው መመሪያ መሰረት እንዲሰራ ታላቅ ሚና ይኖርሀል ብየ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡ዳዊት ወሶበ እገብእ ሀጣእክዎ ያለውን አርዘሊባኖስ ሆንክብኝና ተሸማቀኩ፡፡እባክህ አሁንም እንዲህ የሚያቀራርብ ሳይሆን የሚያራርቅ ህብረቅኔ በመጻፍ ጉዳዩን ወደ አንድ ጽንፍ ወስዶ ሚዛን ከማሳጣት ካንተ የሚጠበቀውን አድርግ፡፡ቢያነስ አንተ ከሌሎቹ የተሻለ ክብርና ሞገስ በሁለቱም ወገን አለህና፡፡አሁን የምትለውን ተወው፡፡እንዲህ አይነት ጽሁፍ እኮ እንዳንተ በሰም ባይዋዛም በወርቁ እየቀረበ ቃር ቃር እስኪለን እያነበብነው ነው፡፡እሱን ለመድገም አትፋጠን!!ይልቅስ ኅስሳ ለሰላም ወዴግና ለሚለው ቃል ታምነህ የምትችለውን አድርግ፡፡

   Delete
  2. ይህ በፍጹም የማኅበረ ቅዱሳን አቋምም ሃሳብም አይደለም፡፡ ሊሆንም አይችልም፡፡ አስያየት ሰጪው ትብል ማኅበረ ቅዱሳን ብሎ በራሱ መጨመሩ ላልተረዱት የማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ መሰላቸው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፡፡
   ዲ.ን ዳንኤልም ሰው እንዳሻው ከሚተረጉምና ግራ ከሚጋባ የግል ሃሳብህ እንደሆነና ፍቺውም ምን እንደሆነ መግለጽ ይገባሃል፡፡ የራሱ ጉዳይ ይፋጭ እንደማትል እገመታለሁ፡፡

   Delete
  3. አንተ ሆይ ነገርህ እንዴት ነው? ዳነኤል ያላለውን ለጥፈህ ስታበቃ ማላዘን ምን ይሉታል:: ከላይ የጻፈው ሰውም ቢሆን አስተያየቱን ነው:: ከወቀስከውም እሱን ነው:: አንተስ ብትሆን በዛፍ የተመሰለች ቤተ ክርስቲያን የት ነው ያየኽው? አብነት አለህ? ወፉዋም ይህን አላለች:: ይልቅ ወፏ ምን ስትል ሰማሁ መሰለ ዛፉ መንግሥት ነው እኔ ደግሞ እኔ ?

   Delete
  4. ክቡር አኖኒመውስ ብዙ የጻፍኸው፡-
   ከመጻፍህ በፊት ለምን አታስተውልም ወደ ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ተረጎምኀኸው አዋቂ ቂኔ ዘራፊ መሆንህ ይበል የሚያሰኝ ነው በውነት፡፡ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ክብር፣ስለ ብጹዓን አባቶች ክብር የሰጠኸው አስተያየት እጅግ ይስማማኛል፡፡ተባረክ፡፡ግን አንዳች ነገር ይጎድልሃል፡-
   1. የብሎግ ጸሃፊዎችና አስተያየት ሰጪዎች ሁሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው ብለህ ማሰብህና መደምደምህ ለብዙ ሰዎችም መተረክህ
   2. ልታውቅ የሚገባህ ግን ሲጀመር ማኅበረ ቅዱሳን ድህረ ገጽ(የዋናው ማዕከል፣የአሜሪካ ማእከል፣የአውሮፓ ማእከል) እንጅ ብሎግ እንደሌለው በእነዚህ ድህረ ገጾች ሁሌም ፍጹም መንፈሳው ይዘት ያላቸው አጀንዳዎች ብቻ እንደሚስተናገዱ ነው፡፡
   3. ለስቅለት ሰልፍ ውጡ ተብሎ ሲቀሰቀስ ማን ነውር ነው አለ ላልኸው ማን እንዲገስጽና መልስ እንዲሰጥ ነበር የፈለግኸው፡፡
   4. ይልቅስ ትልቅ ሰው ጠፋ ላልኸው ፡-በውኑ የተጻፈው ቅኔ የመጥፋት ወይስ የማስተዋል ምልክት፡፡እኔ እንደሚመስለኝ ግን የጠፋኸው፣ሳታመዛዝን ያለመረጃ በጭፍን ጥላቻ የተመታኸው፣ፈራጅ የሆንኸው፣ለማለሳለስ እየሞከርክ ያሴርኸው አንተ ነህ፡፡ይልቅስ ትልቅ ሰው ጠፋ….

   Delete
  5. "ፍቺው ግን እንደየዕውቀታችን፣ እንደየኑሯችን፣ እንደየ ዐቅማችን፣ እንደየመረዳታችን፣ እንደየ ባሕላችን ሊለያይ ይችላል፤ የወፏን ዝማሬ እንተ ብትሰማው ሌላ ይሆናል የምትረዳው፡፡ ወፏ እንደዚያ አላለችም፡፡ እኔ ነኝ እንደዚያ የተረዳኋት፡፡ መድኃኒት እንደየበሽታው ነው፡፡" ወንድሜ ሆይ በራስህ መረዳት ተረድተህ እንዲህ እንደምትል ታውቆት ይሆን ዳኒ ይችን ያስቀመጠው እናም በፍጹም ትህትና ባንተ አረዳድ ብቻ ሰውን ለመዘወር ባትጥር ደግመህ አንብበው ለኔ ምትላቸው ብዙ ነገሮችን ታገኝበታለህ በመጨረሻም በራሱ በዳኒ ጽሁፍ ልሰናበትህ ‹‹እይ፣ ዝም ብለህ ግን አትይ፤ ስማ፣ ዝም ብለህ ግን አትስማ፡፡ ዓለም መጽሐፍ ናት፡፡ ሚሊዮን ገጾች ያሏት፡፡ ገጹ እያንዳንዱ ገጠመኝህ ነው፡፡ ብልሆች እያንዳንዱን ገጽ ያነቡታል፡፡ ይማሩበታልም፡፡ ሞኞች ግን ገጹን እያጠፉ ብቻ ያልፉታል››

   Delete
  6. አቡነ ቄርሎስ የድጓ እውቀትና ስብከት፣ አቡነ ያሬድ ወአቡነ እንድርያስ የትርጓሜ መጻህፍት እውቀት፣ አቡነ ማርቆስ ቅኔ በጉንጩ መሆን፣የአሜሪካው አቡነ መልከጼዴቅ አቡነ ገሪማ ፤ሁሉንም እናውቃቸዋለን፡፡ አንተ ግን ማን ነህ? ልንገርህ ወዳጄ ቤተ ክርስቲያን መሠረቷ አለት ነው፡፡ የዛፍም ሥሩ አፈር ነው፡፡በጎርፍ በነፋስ ይወድቃል፡፡ምናልባት አንተ እንዳሰብከው እንዳለምከውም ቤተ ክርስቲያን ዛፍ ናት ማንኛውም ደካማ ሰው በኃይሉ ገርስሶ የሚጥላት እንዳይመስልህ፡፡ አንተ የሰጠኸው ትርጉም በፍፁም ካልከው ጋር አይሄድም፡፡ ይልቅ አንተና አጋሮችህ የምትመኩበት አያ እንቶኔ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ የፀኃፊው ዕይታ እንጂ አንተ እንዳሰብከው አይደለም፡፡

   Delete
  7. ከታች ደሴ እዚህ አኖኒመስ ብለህ የጻፍከው አንተ ስለመሆነህ አስተያየቱ ከተለጠፈበት ሰዓት ተረድቻለሁ፡፡ግዴለም ያልኩት ገብቶሀል፡፡ሲኒዶስን ስለተተተቸ ማኅበረቀረዱሳንም ይተች ማለትህ ስህተት ነው ብለህ ስትመክረኝ ቆይተህ መልሰህ ደግሞ ዳኒን ለማወደስ እኔን ማንኳሰስህ ይሁን፡፡ ጥሩ ነው፡፡ለምደነዋል፡፡
   ያለ ሲኖዶስ ውሳኔ ተሀድሶ መባልን፣ያለ ፍርድ ውሳኔ ወንጀለኛ መባልን፣በስማ በለው ዘረኛ ሙሰኛ መባልን፣ፓርቲ ሳይኖረን ካድሬ መባልን፣ወዘተ….ሁሉንም ለምደነዋል፡፡የኖርነውም በእ/ር ቸርነት፣በቅዱሳን አማላጅነት፣በመላእክት ተራዳኢነት፣በብፁዐን ጳጳሳት አስተዋይነት፣በየዋሀን ምዕመናን ደግነት እንጅ እንደአንዳንዶቹማ ቢሆን…ለቤ/ክ ከእኛ በላይ ላሳር እንደሚሉትማ ቢሆን….መክረው መመለስን ሳይሆን ገፍተው ማስወጣትን እንደ መርህ እንደያዙትማ ቢሆን….ሳይሰሙ ሳያዳምጡ በተባራሪ ወሬ መንፈስን እንደሚያደቁትማ ቢሆን…..ዛሬ በደመ ክርስቶስ በቆመችው ቅድስት ቤክ ሳይሆን በሌላ በረት እንገኝ ነበር!!
   ዳኒን በ2ቱም ወገን ማለትም በማኅበሩም ሆነ በቤ/ክህነቱ ሞገስ ስላለህ ክፍተት ሲፈጠር የአቀራራቢነት ሚና ተወጣ እንጅ ወደ አንዱ አትወግን፣ያንተ ደረጃ በወጣት ዘመናዊ ምሁራንና በሊቃውንት መሀል የሚገኝ ነው፡፡ስለዚህ ለ2ቱ ድልድይ መሆን ሲገባህ አንዱን ብቻ ለይተህ ለማሳለፍ አትሞክር!!ያንጊዜ በልቤ ከሰጠሁህ ቦታ አጥሀለሁ፡፡የእኔ ሀሳብ ይሄ ነው፡፡የዳኔን ወደ አንድ ወገን ማጋደል ደግሞ የሩቁን ተውትና ባለፈው የማኅበሩ የሊቃውንት ስብሰባ በቤ/ክህነት ህገወጥ ነው ተብሎ ሲሰረዝ ከቤ/ክህነቱ ወገን ስለተሰረዘበት ም/ት ምንም አይነት ማጣራት ሳያደርግ በተደጋጋሚ ማኅበሩ ላይ ስለተጻፉት ደብዳቤዎች ግን መረጃ እንዳለው በሚያሳይ መልኩ አበሳውን ሁሉ ቤ/ክህነት ላይ ሲጥለው ታዝበናል፡፡ብሎግ ጋዜጣ ስላልሆነ የግራቀኙን ለማጣራት ካልተገደደ አላውቅም፡፡
   ስለማስተባበልና ስለ አፍቃሬ ማኅበረቅዱሳን ጋዜጦችና ብሎጎች….
   ማስተባበል ያለበትማ ራሱ ማኅበረቅዱሳን ነው፡፡ምክንያቱም በየጋዜጣውና መጽሄቱ ፊት ገጽ ሆኖ የሚመጣው…..ማኅበረቅዱሳን ቀጣዩ የኢህአዴግ ኢላማ….መንግስት ማኅበረቅዱሳንን ለምን ማፍረስ ፈለገ…የማኅበረቅዱሳን የፍጻሜ መጀመሪያ….እየተባለ ሲሆን ዝርዝሩን ስናነብም ከማኅበረቅዱሳን የውስጥ ምንጮች እየተባለ ነው፡፡
   ታዲያ ምነው ማኅበሩ መግለጫ የሚሰጠው በስሙ ስለሚቀርቡ የአመጽ ጥሪዎች ሳይሆን ቤ/ክህነት ህገወጥ ስብሰባውን ሲያግድበት ብቻ ሆነ??እውነት ይሄን ለማለት በገጸ-ድሩ ያሉትን 2 መስመሮች መጠቀም ከባድ ሆኖ ነው?? ወይስ ከዜናዎቹ የሚገኝ ትርፍ አለ??
   ምነው የስመ ኦርቶዶክስ ብሎጎች ስለማኅበሩ ስም ያገኙት ላይ ሁሉ ለአመታት ሲተኩሱ እና አንዳንዴም ለማኅበሩ የስብሰባ ጥሪ ሲያስተላልፉ እያየን ማኅበሩ የኔ አይደሉም ላለማለት አፈረ??
   በማኅበሩ እጅ ብቻ ይገኛሉ የሚባሉ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በእነዚሁ ባለቤትነታቸው ይፋ ካለመደረጉ በቀር በአቋም ከማኅበሩም በላይ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ብሎጎች ሲወጡ እያየን ማኅበሩና ብሎጎቹ ግንኙነት የላቸውም እንበል??

   Delete
  8. አስተያየት ሰጭው ምሳሌውን በገባው መልኩ ተረጎመው፡፡እሱ የግሉ ነው፡፡ሌሎቻችን ደግሞ በገባን መልኩ መተርጎም ነው፡፡ሰው የፈለገውን ትርጉም ቢሰጥ እኛ ምን አገባን፡፡የግድ እኛ እንዳሰብነው ማሰብ አለብህ ማለት የለብንም፡፡ዲ/ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡ተመልሰህ ስላገኘንህ ደስ ብሎናል፡፡

   Delete
  9. ይህ ያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ አርብ ፈታኝ ዲያቢሎስ ክርስቶስን ሊፈትንዉ ቀረበበት ታሪክ ይታሰባል ታዲ ዲብሎስ ሶስተኛዉን ፈተና ሊፈትነዉ በቀረበ ጊዜ አንተ ሰይጣን ከኔ ራቅ ነበር ያለዉ ላንተም ይህ ገባሃል፡፡ ስለማታዉቀዉ የምታወራ እበት ነህ አንጂ ማን፣ ቤተክርስትያነነ የሚያስቀድም ምእመን እንኳን በጎረምሳ ይቅርና መንግስትምየስቅለት ሰልፍ ዉጡና የሻችሁትን አደርጋለሁ የሚል መግለጫ ቢያወጣ የስቅለት ስርዐቱን ትቶ የሚሄድ አይኖርም እንዳንተ ያለዉ ምንደኛ ግን ያደርግ ይሆናል ነቀርሳ

   Delete
  10. ይህ ያዝነዉ ሳምንት መጨረሻ አርብ ፈታኝ ዲያቢሎስ ክርስቶስን ሊፈትንዉ የቀረበበት ታሪክ ይታሰባል ዲብሎስ ሶስተኛዉን ፈተና ሊፈትነዉ በቀረበ ጊዜ አንተ ሰይጣን ከኔ ራቅ ነበር ያለዉ ላንተም ይህ ይገባሃል፡፡ ስለማታዉቀዉ የምታወራ እበት ነህ አንጂ ማንም ቤተክርስትያንን የሚያስቀድም ምእመን እንኳን በጎረምሳ ይቅርና መንግስትም የስቅለት ሰልፍ ዉጡና ያሻችሁትን አደርጋለሁ የሚል መግለጫ ቢያወጣ የስቅለት ስርዐቱን ትቶ የሚሄድ አይኖርም እንዳንተ ያለዉ ምንደኛ ግን ያደርግ ይሆናል ነቀርሳ

   Delete
  11. Anonymous April 8,2014 at 7:05AM ጎሽ ጎሽ!!እንዲህ ነው ክርስትና!!
   እበት፣ምንደኛ፣ነቀርሳ….እነዚህ ቃላት በክርስትናው ያለህን ምጥቀትና ሊቅነት ያሳያሉ፡፡ግን እባክህ አሳነስካቸው፡፡እስኩ ድግም፡፡የጾም ብፌ ያስመሰልካቸው ድርድር ስድቦች አትጠራጠር አንድ ሳይሆን ሺህ አረማውያንን ምን ያህል ለሃይማኖትህ አውቀህ እንደምትጋደል ያሳዩልሀል፡፡በርታ፡፡ኮርሱዋ በደንብ ሰርጻሀለች፡፡ታዲያ ይጹም ልሳን የተባለበት ጾመኢየሱስ ሳይገባደድ ካሉህ የስድብ ቃለበረከቶች ጨማምርና ጾሙን አሳምረው፡፡እንዲህ ነው ጥብቅና!!ጥሩ የማኅበረቅዱሳን አምባሳደር ይወጣሀል፡፡ጎሽ በነጠላው ስር ያለውን ሶፍትዌራችሁን ደህና እያየነው ነው፡፡ቤ/ክ እንደናንተ ያሉት ተቀምጠው በግእዝ ሚያጨበረብሩ መጫወቻ መሆኗ አሁን ነው የገባኝ፡፡እንዴ….እንዴ….አፈሰስከው እኮ!!

   Delete
  12. to an0nymous april 8 2014 at 10:23 and
   ለዛሬ ግምትህ አልተሳካልህም እኔ ሊቅ ቀርቶ ቤተክርስትያን የምታዛቸዉን መሰረታዊ ግዴታዎች እንኳን በአግባቡ የማልተገብር ሳላዉቀዉ በልጅነቴ በቤተሰቦቼ ብርታት የቤተክርስትያን ጣዕሟን የቀመስኩ እየቆየሁ ግን ድካሜ ሰማያዊዉን ጸጋ ከማስተዋል ይልቅ ዙሪያዋን የከበቧትን አሳማዎች ብቻ እያጎላብኝ ባዝኘ የቀረሁ ባካና ነኝ ያም ሆኖ በያጋጣሚዉ ሃገሬ፣ ቤተክርስትያን ያለችበትን ሁኔታ ባየሁ ቁጥር የድሮ ማንነቴ ትዝ እያለኝ የምቃጠል ምንም ነኝ ግን እንደናንት ያለ ዉሉደ ይሁዳ በፍቅረ ንዋይ ያጠጠ ሰማያዊነቱን ንቆ በመንደርተኝነት ያበደ ምናምንቴ ሃገሬን ቤተ ክርስትያኔን ሲሞላት አሁንም አዝናልሁ እርግጥ ቤተክርስትያን የንደኔ አይነቱን ጭንጋፍ ጠበቃነት እንደማትሻ እንዳንተ አይነት ተራ ቀርቶ የሲዖል ደጆችም እነዳይችሏት አምናለሁ ቢሆንም ያቅሜን አንተ ከንቱ ሆድህ አምላክህ የሆነብህ የቤተክርስትያን መበልጸግ ልጆቿን መሰሰብሰብ የሚያቃጥልህ ጎጠኛ ሰይጣን እልሃለሁ

   Delete
  13. ይድረስ ከዚህ በላይ ሰዓት እየጠቀሳችሁ ለምትነታረኩን ወንድሞቼ/አባቶቼ
   ታናግሮ ተናገሪ ሰውረኝ አለ ምነው ዘመዶቼ/አባቶቼ እንዲህ ስርዓቱ ተዛባባችሁ እባካችሁ ወደየራሳችሁ ሃሳብ ተመለሱና ውስጣችሁን አዳምጡ እኛ የእናንተን ተረት ተረት መስማት አንፈልግም ፀሐፊው የፃፈው ትርጉም ጠፍቶችህ ከሆነ በየግላችሁ ጠይቁት ይመልስላችኋል ብየ አምናለሁ ግን የናንተ ንትርክ ቤ/ክንን ምን ያህል እንደሚያሰድብ አታውቁም ተሳድባችሁ ለተሳዳቢ አትስጡን የግል ችግር ካለም እዚያው እንጂ ሚዲያ ላይ አይደለም በእኔ እምነት ይህ ሁሉ ንትርክ እግዚሐብሄርን መውድ ሳይሆን እራስን /ጥቅምን/ መውድድ/ማስቀደም ይመስለኛል ሁላችሁም በጥቅሟችሁ የመጣባችሁ ነገር ያለ ይመስላል እባካቸሁ ክርስትና አልፎም ፆም ትህትና፣ መዋደድ፣ እራስን አሳልፎ ለወንድም መስጠትን እንጂ አንተ/አንች የሚያባብል አይደለም እባካችሁ ስለመብርሐን ብላችሁ በሚዲያ ምን እያደረጋችሁ እንደሆነ አስቡት…….. ነው ሁለታችሁም ከቤ/ክ ውጪ የሆነ ድብቅ አላማ ይዛችሁ ነው የተጠለላችሁት??????????

   Delete
 9. ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. sir have you understood who is represented by the tree??????????????????????????????????????

   Delete
 10. ‹‹ሰው አይደለህም እንዴ››
  ‹‹ብሆንስ››
  ‹‹ከሆንክማ ትችላለህ ማለት ነው፡፡ ሰው ሁለት ዓይነት ጆሮ አለው፡፡ የሥጋ ጆሮና የልቡና ጆሮ ወይም እዝነ ሥጋ እና እዝነ ልቡና፡፡ በሥጋ ጆሮው ማዳመጥ የሚችለው የሰው ቋንቋ፣ መስማት የሚችለውም አልፎ ሂያጅ ድምጽ ነው፡፡ በልቡና ጆሮው ግን ወፍንም፣ እንስሳንም፣ ወንዝንም፣ መብረቅንም፣ ተራራንም፣ ዛፍንም መስማት ይችላል›› አለው፡፡ ከበደ ሚካኤል ይህንን ችሎታቸውን ተጠቅመው ነው ደመናና ጽጌረዳ ሲያወሩ የሰሙትን የነገሩን፡፡ ‹ጽጌረዳና ደመና› የሚለውን ግጥማቸውን ታውቀዋለህ?

  ReplyDelete
 11. D/n Daniel, wold you, connect to our life for others to understand easily.For me I understand easily.

  ReplyDelete
 12. God bless you much Dani!

  ReplyDelete
 13. ዳኒ የዘወትር ተከታታይህ ነኝ በብሎግ ብዙ ተምሬአለሁ ለሰዎችም አጋርቻለሁ
  አንተን የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን
  እግዚአብሔር አምላክ ያበርታክ ፤ይጠብቅህ !!!

  ReplyDelete
 14. Magnificent View!!!! thank u D.Daniel.....this message is so crucial and very critical for current generation as well as the the challenge we are facing in different aspect of life especially from those who suppose them selves as every thing determiner!!!

  ReplyDelete
 15. ዉድ ዳኒ! በመጀመሪያ ሠላምና ጤና ይስጥህ፡፡ ረጅም ዕድሜ ያድልህ፡፡ ከዚህ ፁሁፍ ዉሥጥ ብዙ ተምሪያለሁ፤ህወት ለእኛ ለኢትዮጵያዊያ ሚስጥር ሁኖብናል፤እንዴት መኖር እንዳለብን ግራ ተጋብተናል፤ እያየን የማናይ፤እየሰማን የማንሰማ ሁነናል፤ሁላችንም ልክ እንደ ወፏ ዝማሬ አድማጭ መሪዎች ያስፈልጉናል፡፡

  ReplyDelete
 16. ዉድ ዳኒ! በመጀመሪያ ሠላምና ጤና ይስጥህ፡፡ ረጅም ዕድሜ ያድልህ፡፡ እጅግ አስተማሪና ቁም ነገር የያዘ ነዉ፤ለእኔ ነገሮችን በጥልቀት እንድመለከት አድርጎኛል፡፡ብዙዎቻችን እያየን፤የማናይ፤ እየሰማን የማንሰማ፤ የሆንን መስሎ ይሰማኛል፤ ልክ እንደመንገደኛዉ ማለት ነዉ :: ለእኛ ለመንገደኞች እያየን ለማናይ፤እየሰማን ለማንሰማ ማስተዋልና መገንዘብ ላቃተን ግን ልክ እንደ ወፏ አድማጭ መሪዎችና ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ እግዚአብሄር ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 17. ዉድ ዳኒ! በመጀመሪያ ሠላምና ጤና ይስጥህ፡፡ ረጅም ዕድሜ ያድልህ፡፡ እጅግ አስተማሪና ቁም ነገር የያዘ ነዉ፤ለእኔ ነገሮችን በጥልቀት እንድመለከት አድርጎኛል፡፡ብዙዎቻችን እያየን፤የማናይ፤ እየሰማን የማንሰማ፤ የሆንን መስሎ ይሰማኛል፤ ልክ እንደመንገደኛዉ ማለት ነዉ :: ለእኛ ለመንገደኞች እያየን ለማናይ፤እየሰማን ለማንሰማ ማስተዋልና መገንዘብ ላቃተን ግን ልክ እንደ ወፏ አድማጭ መሪዎችና ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ እግዚአብሄር ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 18. ዉድ ዳኒ! በመጀመሪያ ሠላምና ጤና ይስጥህ፡፡ ረጅም ዕድሜ ያድልህ፡፡ እጅግ አስተማሪና ቁም ነገር የያዘ ነዉ፤ለእኔ ነገሮችን በጥልቀት እንድመለከት አድርጎኛል፡፡ብዙዎቻችን እያየን፤የማናይ፤ እየሰማን የማንሰማ፤ የሆንን መስሎ ይሰማኛል፤ ልክ እንደመንገደኛዉ ማለት ነዉ :: ለእኛ ለመንገደኞች እያየን ለማናይ፤እየሰማን ለማንሰማ ማስተዋልና መገንዘብ ላቃተን ግን ልክ እንደ ወፏ አድማጭ መሪዎችና ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡ እግዚአብሄር ከሁላችንም ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 19. Dani, strong you are. But you need to also oppose critically illegal scripts of any body. I give you one idea to oppose as follows.
  ፋክት መጽሔት መረጃ (መረጃቸው ትክክለኛ መሆኑን በሂደት እያየን) መሰጠታቸውን ብቻ ቢቀጥሉ ጥሩ ነው፡፡
  ዕለተ ዓርብን የስቅለት ዕለት ወይንም ምርጫ ዕለት ለዓመጽ ተነሱ የሚለው ጥሪው ግን ፍጹም ፍጹም አልቀበለውም፡፡ ብዙዎችም አንቀበለውም፡፡
  ማኅበረ ቅዱሳንን የማያውቅ ወይንም የራሱ ዓላማ ያለው ሰው በስሜት የጻፈው ይመስላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የዓመጽ ማኅበር አይደለም፡፡ ሕግና ደንብ ያለው፤ ምንም ችግርና ፈተና ቢመጣ በሕግ በሥርዓት በቤ/ክንም በሀገርም ህጋዊ መንገዶችና መንገዶች ብቻ የሚታገል ነው፡፡ አባላቱም እንዲህ የተቃኙ መሆናቸውን እኔ ለዓይን ጥቅሻ ሳልጠራጠር እናገራለሁ፡፡ በግለሰብ ደረጃ አንዳንድ ግላዊ እንዲህ ዓይነት ስሜት ሊኖራቸው ቢችል እንኳ ስሜታቸውን እንዳሳዩ ይታረማሉ፡፡ እነርሱም ይሰማሉ፡፡ ይህን እሴት የሰጠን የቅዱሳን አምላክ ይመስገን፡፡
  ይልቁንም በማኅበሩ ስምና ሽፋን አንዳች የዓመጽ ነገር እንዳይኖር ነቅተን እንጠብቃለን፡፡ የሰንበት ት/ቤት አባላትም በመሆናችን በየትኛውም ደረጃ ዓመጽን እንከላከላለን፡፡ ከየትኛውም ጻድቅ አባትና እናት አልተማርነውምና!!!! ስለዚህ ቤ/ክ ውስጥ ያውም በዕለተ ስቅለት ዓመጽ መጥራት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ኃጢያትም ነው፡፡

  ምናልባት ፈሪ ትሉኝ ይሆናል፡፡ አዎ! ከቀደሙት አበው ያልወረስነውን መስራት ያስፈራል፡፡፡

  ReplyDelete
 20. Stay strong and May God bless your service!

  ReplyDelete
 21. ውድ አንባቢያን፤ ስለ ዕለተ ዓርብ አመጽ አንድ ጋዜጠኛ አለ እንጂ ከማንም የአቋም መግለጫ ወይም የጥሪ መልዕክት አልሰማንም። በቤተክርስቲያናችን ላይ የተጋረጠውን ታላቅ ፈተና የቤተክርስቲያን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ያስውግድልን ዘንድ በጸሎት እንትጋ።የመውጊያውን ስለት ለሚጨብጡም ልቦና ይስጥልን። ዕለተ ዓርብ ግን የክርስቶስ የመስቀል መከራና ለሰው ልጆች ድህነት የተከፈለውን የህይዎት ካሳ በጾምና በእንባ የምናስብባት ቅድስት ዕለት ነች።
  የዲ ዳንኤልን ጽሑፍም በተሳሳተ አረዳድ ወይም ለጥፋት ዓላማቸው መነሻ ለሚያደርጉትም ከሥራቸው ታውቌቸዋላችሁ ነውና አስተማሪና በመረጃ የተደገፈ መልስ እንስጥ።
  የድንግል ማርያም ምልጃ የቅዱሳን ረድኤት ከኛ ጋር ይሁን። አሜን

  ReplyDelete
 22. አቶ አኖኒመስ፤ ከላይ ዘለግ አርገህ እነዳኒን የተቸህ፣ ችኩል እና ችኮ ነህ፡፡ በስድብ ጽሁፍህ “…ዳኒ፡፡ባስቀመጥኩህ ቦታ አላገኘሁህም፡፡…” ብለሃል፡፡ ዳኒን አንተ ነህ ያስቀመጥከው? ለራስህ ልክህን አውቀህ አርፈህ በተቀመጥቅ፡፡
  ግዕዝ መቀላቀል እውቀት መስሎሃል ደሞ፤ ለመልካም ካልሆነ ሁሉም ከንተ እንደሆነ አንብብ፡፡
  እንዲህም ብለሃል፤ “…ሲኖዶስ እየተቆረጠ በሚቀጠልባት ሀገር ማኅበርን አትተቹ ማለት እኮ ቅዱስ ነን ለማለት መቃጣት ነው፡፡ልናገር ብትል ውርጅብኝ ነው፡፡ተሀድሶ፣ሙሰኛ፣አማሳኝ፣ጉቦኛ፣መናፍቅ፣ዘረኛ….ስድብ እንደጥይት ጆሮህ እስኪግል ይተኮስብሀል…” ይህ ማለት ሲኖዶሱን ስንሰድብ ዝም እየተባልን፣ ማህበረ ቅዱሳንን ስንሰድብ ግን ዝም አንባልም ማለት ነው፤ አንተ የስድብ ጥም ያለብህ ሰው ሆይ እነዚህን ክቡር አካለት (ሲኖዶስ በተለይ በስልጣኑ፤ ማ/ቅዱሳን በተለይ በምግባሩ የተከበሩ ናቸው፤ መከበርም ይገባቸዋልና) ለመስደብ የማትመለስ ግለሰቡን ዳኒን ብትወርድበት ምን ይደንቀናል፡፡ በዚህ አቋምህስ “ተሀድሶ፣ ሙሰኛ፣ አማሳኝ፣ ጉቦኛ፣ መናፍቅ፣ ዘረኛ እንባላለን” እያልክ ራስህን የሰደብክባቸው የስድብ ቃላት ያንሱሃል ወይ? አያንሱብህምና እነሱን አሜን በል፤ ሌላ አልጨምርብህም፤ ለወደፊቱ ግን እውነት የሚመስል በግዕዝ የተቀባ መርዝ ለመቀመም አትድከም፤ በራስህ ስድቦች በትክክል የምትገለጽ ሰው ነህና እንደ ዳኒ አስተማሪ፣ ገሳጭ፣ አራሚ ጽሁፎችን መቸም ካንተ ስለማልጠበቅ ቢያንስ ዝም በል፡፡ “ቤተክርስትያንን ትቻት ልሂድ አለ ዳኒ” የሚለውን ቆርጦ ቀጥል የሀሰት መርዝህን ለራስህ ዋጠው እሽ፡፡ ከታናናሾች መሃል አንዱን እንኳን በሀሰት ብታስት የወፍጮ ድንጋይ ይጠብቅሀል፡፡ ዳኒ እንደሙሴ ሊመራን እንኳን ይችላል፤ ከእግዚአብሄር ጋር፡፡ አወኩሽ ናኩሽ ነውና ግን እኩል ቆቦ ለማደር ተነሳሳህ፤ ተነሳስተህ ግን ትቀራለህ እንጅ የትም አታድርም፡፡
  አቶ አኖኒመስ፤ ከላይ ዘለግ አርገህ እነዳኒን የተቸህ፣ ችኩል እና ችኮ ነህ፡፡ በስድብ ጽሁፍህ “…ዳኒ፡፡ባስቀመጥኩህ ቦታ አላገኘሁህም፡፡…” ብለሃል፡፡ ዳኒን አንተ ነህ ያስቀመጥከው? ለራስህ ልክህን አውቀህ አርፈህ በተቀመጥቅ፡፡
  ግዕዝ መቀላቀል እውቀት መስሎሃል ደሞ፤ ለመልካም ካልሆነ ሁሉም ከንተ እንደሆነ አንብብ፡፡
  እንዲህም ብለሃል፤ “…ሲኖዶስ እየተቆረጠ በሚቀጠልባት ሀገር ማኅበርን አትተቹ ማለት እኮ ቅዱስ ነን ለማለት መቃጣት ነው፡፡ልናገር ብትል ውርጅብኝ ነው፡፡ተሀድሶ፣ሙሰኛ፣አማሳኝ፣ጉቦኛ፣መናፍቅ፣ዘረኛ….ስድብ እንደጥይት ጆሮህ እስኪግል ይተኮስብሀል…” ይህ ማለት ሲኖዶሱን ስንሰድብ ዝም እየተባልን፣ ማህበረ ቅዱሳንን ስንሰድብ ግን ዝም አንባልም ማለት ነው፤ አንተ የስድብ ጥም ያለብህ ሰው ሆይ እነዚህን ክቡር አካለት (ሲኖዶስ በተለይ በስልጣኑ፤ ማ/ቅዱሳን በተለይ በምግባሩ የተከበሩ ናቸው፤ መከበርም ይገባቸዋልና) ለመስደብ የማትመለስ ግለሰቡን ዳኒን ብትወርድበት ምን ይደንቀናል፡፡ በዚህ አቋምህስ “ተሀድሶ፣ ሙሰኛ፣ አማሳኝ፣ ጉቦኛ፣ መናፍቅ፣ ዘረኛ እንባላለን” እያልክ ራስህን የሰደብክባቸው የስድብ ቃላት ያንሱሃል ወይ? አያንሱብህምና እነሱን አሜን በል፤ ሌላ አልጨምርብህም፤ ለወደፊቱ ግን እውነት የሚመስል በግዕዝ የተቀባ መርዝ ለመቀመም አትድከም፤ በራስህ ስድቦች በትክክል የምትገለጽ ሰው ነህና እንደ ዳኒ አስተማሪ፣ ገሳጭ፣ አራሚ ጽሁፎችን መቸም ካንተ ስለማልጠበቅ ቢያንስ ዝም በል፡፡ “ቤተክርስትያንን ትቻት ልሂድ አለ ዳኒ” የሚለውን ቆርጦ ቀጥል የሀሰት መርዝህን ለራስህ ዋጠው እሽ፡፡ ከታናናሾች መሃል አንዱን እንኳን በሀሰት ብታስት የወፍጮ ድንጋይ ይጠብቅሀል፡፡ ዳኒ እንደሙሴ ሊመራን እንኳን ይችላል፤ ከእግዚአብሄር ጋር፡፡ አወኩሽ ናኩሽ ነውና ግን እኩል ቆቦ ለማደር ተነሳሳህ፤ ተነሳስተህ ግን ትቀራለህ እንጅ የትም አታድርም፡፡

  ReplyDelete
 23. እኔ ግን እንዲህ እላለሁ፡፡ ዲ/ዳንኤልን እንደወፏ ፤ራሳችንን ደግሞ የወፍ ቋንቋ ተርጓሚዎች አድረገን ሺህ እንደመሆናችን ለጽሁፉ ሺህ ትርጉሞችን እንደሰጠነው እንውሰድ፡፡ ጸሐፊው የራሱን መረዳትና አመለካከት ነገረን፤ግን ሰምለበስ ስለሆነ ሁላችንም በአንድ ዓይነትና በእኩል አረዳድ ልንገነዘበው አንችልም፡፡ አንዳንዶቻችን በበጎ ፤ሌሎቻችንም በክፉ የተቀረነው ደግሞ የልባችን ምኞት ማስፈጸሚያ መንገድ ቢሆንልን ብለን በማሰብ አጣምመን(በመሀል በግላችን ጥቅም ምናገኝ መስሎን ግን እንደማይሳካልን ባለመረዳት ምናልባትም ማህበሩንና መንግስትን ለማላተም፤ማህበሩንና አባቶችን ብሎም ቅዱስ ሲኖዶስን ላመቃረንና ለማለያየት) ልንተረጉመው እንችላለን፡፡ ግን ምንም ሆነ ምን ይሄ ጽሁፍ የዲ/ዳንኤል፤በፋክት መጽሔት የወጣውም የጋዜጠኛ ------ እንጂ የአገልግሎት ማህበር የሆነው የማኅበረ ቅዱሳን አለመሆኑን ሁላችንም ልንረዳ ይገባናል፡፡
  ቸሩ መድኃኔአለም ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡


  ReplyDelete
 24. ’ስራህን ሥራ’’!

  ሥራህን ሥራ!
  እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራ ሰጥቶታል ፣ ያንን መስራት የእሱ ፈንታ ነው፡፡ ቢቻለው አሱን ማገድ የዲያቢሎስ ሥራ ነው፡፡ በእርግጥ ሥራው እግዚአብሔር እንደሰጠህ ያህል ሠይጣን ሊያግድህ ይጥራል፡፡ ሌላ ነገር በበለጠ ደስ የሚያሰኝ ሊያቀርብልህ ይጥራል፡፡ በዓለማዊ ተስፋዎች ያባብልሃል፡፡ የሐሜት ጐርፍ ያስወርድብሃል፡፡ ደራሲያን እንዲጠይቁህ እጅግ ስመጥር ሰዎችም በክፉ እንዲናገሩብህ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ጲላጦስ፣ ሄሮድስ፣ ሃናንያ፣ ቀያፋ ሁሉም በአንተ ላይ ያድማሉ፡፡ ይሁዳም በአጠገብህ ቆሞ በሰላሳ ብር ሊሸጥህ ይከጅላል ይሄ ሁሉ የደረሰብህ ሰይጣን በዚህ ከሥራህ ሊስብህና እግዚአብሔርን ከመታዘዝ ሊያሰናክልህ መሆኑን ልትገነዘብ አትችልምን?

  ሥራህን ሥራ!
  አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፣የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፡፡ ጥንቸሎቹንም በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፡፡ ሥራህን ሥራ! ዋሾች ይዋሹ፣ጠበኞች ይጣሉ፣ማኀበሮችም ይወስኑ፣ ደራሲዎችም ይድረሱ፣ ሰይጣንም
  የፈለገውን ያድርግ፣ አንተ ግን ምንም ነገር እግዚአብሔር የሰጠህን ሥራ ከመፈጸም እንዳያግድህ ተጠንቀቅ፡፡

  ሥራህን ሥራ!
  ገንዘብ እንድታተርፍ አልተላክም፣ እንድትበለጽግም አልታዘዝክም፣ ለክብርህ ተከላከል ብሎ አልነገረህም፣ ሰይጣንና አገልጋዮቹ የሚነዙትን የሐሰት ወሬ እንድታስተባብል አልተጠየቅክም፣ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ብታደርግ ሌላ ሥራ ልትሰራ አትችልም፣ ይህም ብቻ ሳይሆን ለራስህ እንጂ ለእግዚአብሔር አልሰራህም፡፡

  ሥራህን ሥራ!
  ዓላማህ እንደ ኮከብ የፀና ይሁን ተወው ዓለም እንደፈለገው ይነታረክ፣ ይጨቃጨቅ፣ ጥቃት ይደርስብህ ትበደል፣ ትሰደብ፣ ትታማ፣ ትቆስልና፣ ትናቅ ይሆናል፡፡ ሃይለኛ ያጐሳቁልህ፣ ወዳጆች ይተውህ፣ ሰዎችም ይንቁህ ይሆናል፡፡ አንተ ግን በፀና ውሳኔ የማያወላውል ቅናት በመጨረሻ ላይ ፀንተህ፣ የሰጠኸኝን ሥራ ፈፀምኩ ሃይማኖትንም ጠበቅሁ ለማለት እሰክትችል ድረስ የሕይወትህን ዓላማ እና የተፈጠርክበትን ግብ ተከተል!

  (አባ ጎርጎሪዮስ ካልእ)

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you very much!!! I like it. ሥራህን ሥራ!

   Delete
 25. ዳኒ ሰላሙን ያብዛልህና ሰላም ላንተና ለቤተሰብ ለመላው ኢትዩያዊ በምህረት ይጎብኝን አምላካችን። አንተ ግን አይገባህም?ሰው አይደለህም?ግሩም ነው ለሚያውቀው አማ የወፋዋን ዝማሬ ለገባውማ ሰው ከሆንክ ትችላለህ ቅድስ ያሬድ ያያትን ትል ወድቃ ተነስታ ማሽነፍ፣ተስፋ ካሰቡት መድረስ እደሚቻል አንተ ዛፍ ነህ አትመካ ነገ ተቆርጦ ሊጣል እደሚቻል የረሳውን ዛፍም ወፋ ነግራዋለች ሚማር ቢኖርማ ምንም በአለም ላይ ያሉ ነገሮች ሁሉ መመካት እደሌለባቸው የሁሉም የበላይ ባለቤት እግዚያብሔር መሆኑን የሰው ልጂ እረደቶ ሚሊዮን ገጸ ያላትን እያዩ ሳይማሩባት እያጠፉ ለሚጠቀሙባት ሚሊዩኑንም ማስታወስ አቅቶአቸው ከሆነ ከሁለት ከሶስት አመት በፊት ምን እደተሰራ የሚረሱ ሰወች ካሉ ሰው አይደሉም። ታላቁ መጸሐፋ ቅድስ የሚመካ በእግዚያብሔር ይመካ ይላል ።እግዚያብሔር ዝም ያለ ይመስለዋል ሞኙ የሰው ልጂ ግን እርሱ ዝም አይልም ሰአቱ እየደረሰ ነው ያችን ሰአት በራሳችን መጠደፋ እያቀረብናት ነው ።መንገደኛው ለመሄድ እደተጣደፈ ካወቀ በሗላ ደግሞ ለማወቅ እደጎጎ ለኛም እኮ እንደናስተውል የወፋን ዝማሬ እንደነሰማ ጊዜ ተሰጦን ነበረ ግን ልማዶነው በማልት ጊዜው አለፈና አሁን ችግርላ ነው ፈራሁ ልሄድ ነው ከማለት ደርሶል መንገደኛው አወ ካላወቀ ቢሄድ ይሻለዋል ምክኒያቱም ለዛፉ የሳለ መጠረቢያ የያዘ ቆራጭ የሚያዝዝበት ባለቤቱ ከመምጣቱ በፊት ማምለጥ ይሻለዋል ያለዛ የሚያስጥለው የለም ቅርንጫፉም ግንድም አይጠቅሙትም ዋ ዋ ዋ ሰሚ ጀሮ ብቻ ሰሚ ልብ ይስጣቸው።ዳኒ ሁልጊዜም ብረታት ጉልበት የምተሰጥ መምህር ነህና እግዚያብሔረ እደአባቶቻችን ጨምሮ ጨማምሮ ሀይል በረከቱን ጸጋውን ያብዛልህ። ከበላይ ነኘ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምንድን ነው ነገሩ dani ?

   Delete
 26. እመኒ ሀለየ ብለው አስተያየት ለሰጡት ጥያቄ አለኝ ።በመጀመሪያ ህግ አለን? የቤተክርስቲያን ህጓ ስርአቷ ከጠፋ ዘመን አስቆጠርን ስለዚህ በየትኛው ህግ ነው የምንመራው ለነገሩ ህጓን ያፈረሰውን አፍርሳዋለች ለኑዛዜም አላበቃችው ።እሄው ነው መቼ አባት ነበረን እኛ አስመሳይ አባት የለንም ስለዚህ የሀገሬ ሰው ምን ይላል መሰለወት"ጨው ሲበዛ ይመራል ይላሉ"ስለዚህ ካለፈው ካልተማራችሁ የንብ አውራን መንካት እንዳይሆንባችሁ ማሰብ ያስፈልጋል ከዚህ በሗላስ አንበርም አንሰድም የሰደቱ ጊዜ አብቅቷል የመኸር ጊዜ ደርሶል የተሰደደውም ይመለሳል የሙሴ ቀን ቀርቧል ሁሉን እኛ ብቻ ማለት በቃ በቃ በቃ ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ህጉ ቃለ ዐዋዲ ይባላል፡፡ፍ/ነገስቱም አለ፡፡81ዱ መጻህፍትም አሉ፡፡ሲኖዶሱም በቦታው ነው፡፡አባቶችማ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ እንኳን ለእኛ ለሌላም ይተርፋሉ፡፡ዳሩ ሳትቀምሱት በስሚ ስሚ ጨው ጨው አለን ትላላችሁ፡፡ልቡ ሁሌ እስክንድርያ እናቴ፣ሺኖዳ አባቴ እያለ ለሚኖር አማተር የአባቶቻችን ትርጉዋሜ ጨው ጨው ቢለው አይገርመንም፡፡ቅኝቱ ከድሮው ተበላሽቷላ!!የራስን ሳይፈትሹ የሌላን መናፍቅ መገለጫችን ነው!!አቡነ ቶማስን ጠቅሰን በቁም ሳንሰማቸው ሲሞቱ ገድላቸውን መተረክ ያልነው እሱን ነው!!
   የንብ መንጋ የተባለውን ቀፎውን በጭስ አጥነን አውራውን ይዘን ስናበቃ መቀመጥ ባለበት የዛፍ ቅርንጫፍ እናኖረዋለን፡፡ሙሴነቱም የሲናን ተራራ ለወጡት እንጅ ለትርፍ ሰዐት ኮርሰኛ አማተር አይመጥንም፡፡እንደሱ ማድረግ ሰብል መሰብሰብ ሳይሆን ጮርቃውን ማሳጨድ ነው፡፡
   ንቡ በአባራራቸው እንጅ በመለሳቸው ሲመካ አይተነው አናውቅም፡፡የራሱን ድምጽ በያሬድ ምልክት ሳይቃኝ የሌሎቹን ጎረነነ፣ዘፈን መሰል እያለ ለማሳደድ የሚተጋ ራሱን ብቻ አድማጭ ወታደር ንብ ቀፎው አይፈልግም፡፡ስለዚህ ይታጠናል!!ይታጠናል ገና!!

   Delete
  2. Wey nedo, yih hulu ewket nfes lemadan welo bihon; ande tig tesheguto noro zare le mahiber kidusan tekefete. Ahunim bgubaei tgegntew astemrubet, mnekef aytekmim. MK yifresem yinurim yegeta fikad new. Eyeseru yalu likawntin endatasnekifun, yibertu!!!!!!!!!

   Delete
 27. ስለማህበረ ቅዱሳን ሌብነት ተወርቶ ያልቃል እንዴ ምነው ለማያቃችሁ ታጠኑ

  ReplyDelete
  Replies
  1. My dear, please, tell me one or two faults about MK, from your many stores?????

   Delete
 28. እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካ

  ReplyDelete
 29. ‹‹እይ፣ ዝም ብለህ ግን አትይ፤ ስማ፣ ዝም ብለህ ግን አትስማ፡፡ ዓለም መጽሐፍ ናት፡፡ ሚሊዮን ገጾች ያሏት፡፡ ገጹ እያንዳንዱ ገጠመኝህ ነው፡፡ ብልሆች እያንዳንዱን ገጽ ያነቡታል፡፡ ይማሩበታልም፡፡ ሞኞች ግን ገጹን እያጠፉ ብቻ ያልፉታል››

  ReplyDelete
 30. geta egzeabeher berketun yabzalehe

  ReplyDelete
 31. dani , geta egzeabeher yebakehe.

  ReplyDelete
 32. ወንድሞቼ የሰውን የመረዳት ደረጃ አንገድበው እንጅ ገና ለገና ዳኒ እንዲህ ነው ያለ እያልን ጭራሽ አኛ መነታረክ አይገባንም ለዚህ ደግሞ መጀመሪያ ላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ ትክክል አይደሉም ማህበረ ቅዱሳን የራሱ የሆነ ድረ-ገፅ አለው ያብቻ ነው የእርሱን መልእክት የሚያስተላልፍ በተረፈ በየብሎጉ በተፃፈ ቁጥር እና ግለሰቦች አስተያየት በሰጡ ቁጥር ማህበሩን ማያያዝ አግባብ አይደለም ማህበሩ ማንንም አይፈራም የተፈጠረው በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚያገለግለው በእግዚአብሄር ፈቃድ ነው የፈለገውን በግልጥ ይናገራል ስለዚህ በሰው ብሎግ ማህበረ ቅዱሳን ነው ብሎ መፈረጅ የጤነኝነት አይመስለኝም
  ለማንኛውም ቸር ሰንብቱ ዲያቆን ዳንኤልም እግዚአብሄር ያበርታህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. የልቤን ስለተናገርክ እግዚአብሔር ይስጥ፡፡

   Delete
 33. ወንድሞቼ የሰውን የመረዳት ደረጃ አንገድበው እንጅ ገና ለገና ዳኒ እንዲህ ነው ያለ እያልን ጭራሽ አኛ መነታረክ አይገባንም ለዚህ ደግሞ መጀመሪያ ላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ ትክክል አይደሉም ማህበረ ቅዱሳን የራሱ የሆነ ድረ-ገፅ አለው ያብቻ ነው የእርሱን መልእክት የሚያስተላልፍ በተረፈ በየብሎጉ በተፃፈ ቁጥር እና ግለሰቦች አስተያየት በሰጡ ቁጥር ማህበሩን ማያያዝ አግባብ አይደለም ማህበሩ ማንንም አይፈራም የተፈጠረው በእግዚአብሄር ፈቃድ የሚያገለግለው በእግዚአብሄር ፈቃድ ነው የፈለገውን በግልጥ ይናገራል ስለዚህ በሰው ብሎግ ማህበረ ቅዱሳን ነው ብሎ መፈረጅ የጤነኝነት አይመስለኝም
  ለማንኛውም ቸር ሰንብቱ ዲያቆን ዳንኤልም እግዚአብሄር ያበርታህ

  ReplyDelete
 34. ማስተባበል ያለበትማ ራሱ ማኅበረቅዱሳን ነው፡፡ምክንያቱም በየጋዜጣውና መጽሄቱ ፊት ገጽ ሆኖ የሚመጣው…..ማኅበረቅዱሳን ቀጣዩ የኢህአዴግ ኢላማ….መንግስት ማኅበረቅዱሳንን ለምን ማፍረስ ፈለገ…የማኅበረቅዱሳን የፍጻሜ መጀመሪያ….እየተባለ ሲሆን ዝርዝሩን ስናነብም ከማኅበረቅዱሳን የውስጥ ምንጮች እየተባለ ነው፡፡
  ታዲያ ምነው ማኅበሩ መግለጫ የሚሰጠው በስሙ ስለሚቀርቡ የአመጽ ጥሪዎች ሳይሆን ቤ/ክህነት ህገወጥ ስብሰባውን ሲያግድበት ብቻ ሆነ??እውነት ይሄን ለማለት በገጸ-ድሩ ያሉትን 2 መስመሮች መጠቀም ከባድ ሆኖ ነው?? ወይስ ከዜናዎቹ የሚገኝ ትርፍ አለ??
  ምነው የስመ ኦርቶዶክስ ብሎጎች ስለማኅበሩ ስም ያገኙት ላይ ሁሉ ለአመታት ሲተኩሱ እና አንዳንዴም ለማኅበሩ የስብሰባ ጥሪ ሲያስተላልፉ እያየን ማኅበሩ የኔ አይደሉም ላለማለት አፈረ??
  በማኅበሩ እጅ ብቻ ይገኛሉ የሚባሉ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በእነዚሁ ባለቤትነታቸው ይፋ ካለመደረጉ በቀር በአቋም ከማኅበሩም በላይ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ብሎጎች ሲወጡ እያየን ማኅበሩና ብሎጎቹ ግንኙነት የላቸውም እንበል??unanswered question!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. መንድሜ መረዳት የፈለግህ አይመስልም፡፡ ቀጥል ማንንም አትጎዳም… መልሰህ መላልሰህ አንዱን ጩኸት ትጮሃለህ

   Delete
 35. የአገልግሎት እድሜህን ያርዝምልህ፤ ይገርማለ ‹‹ሆድ ያባዉን ብቅል ያወጣዋል›› መልካም አሳቢዎች እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 36. ጥሩ የኑሮ ፍልስፍና ነዉ:: ነፍሳችን የቆመችዉ በኃላፊዉ በጎ ፈቃድ ይመስል በነጋ በጠባ ቁጥር ከስራ ላባርርህ ነዉ : አለቀልህ : ተሰናበትክ ለሚል አለቃ : ኪራይ ልጨምርብህ ነዉ : ላስወጣህ ነዉ : ሜዳ ላይ ልበትንህ ነዉ እያሉ ለሚያስፈራሩን የቤት አከራዮች በቃ መልስ አገኘሁ:: አመሰግናለሁ ዲ/ን ዳንኤል

  ReplyDelete
 37. Hello Danial I questined my self. Do I understand Amharic or not. I read you blog three times there is no a single word about the people comment. I read all the comment I don't know where they bring it from. I feel we speak, write and read the same languch but diffrent way understanding. This is the best proof I never seen it. Shame on you my people. Please write the best comment based on the writer idea not based on the way you think. I smell some writer came from Aba Sereke schoo. We apriciate you for reading this kind of blog but we don't apriciate you by understanding with Aba Sereke way. I know him very well more than anybody he doesn't belive in God. He allowed for the people to eat pork. Evenif he doesn't follow an Ethiopian Orthodox rule and regulation. He one of the best devil in 21st century.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hey body it is not the good comment. I know you want to respond for these crazy people but it is not the appropriate way because you use the same idea what they wrote on the blog. The best responded for them ignore it, pray for them and fight to take their spot. Furthermore it is not a single person issue it is our church issue. Aba Sereke Brhan doesn’t do by himself. He got permission from Abune Matias. Abune Matias take this position to satisfy the current government not to satisfy God, so whatever Abune Matias did or will do, it is his job that’s why he got this position. I work in Beteknet for eighteen years so I know everything very well. If you asked me about Abune Matias’s or Aba Sereke Brhan’s faith, I will answer it like this THEY DON’T BELIVE BY GOD. However I don’t judge people and I everyday pray for them.

   Delete
 38. Helm ende fechew new, hulum yemeselewn teregome, yeh yehonew bemestafu selehone Dn. Daniel lekeber yegebal. Do your job please. God be with you.

  ReplyDelete
 39. Excellent article...God bless you!

  ReplyDelete
 40. dani, you are such a good article keep up as usual , we are so lucky to have u..

  ReplyDelete
 41. ወንድሞቼ ምነው በሰው ብሎግ የማህበረ ቅዱሳን ነው የሌላ ነው ብለን ምን አነታረከን ማህበሩ ማንንም አይፈራም እውነትን ለመናገር እኛ የፈለግነውን መተርጎም መብታችን ነው ዝም ብለን ማህበረ ቅዱሳንን ነው ማለት ግን አግባብ አይደለም ዲያቆን እግዚአብሄር ያበርታህ ቸር እንሰንብት

  ReplyDelete
 42. Welcome! , it,s GOOD idea ,
  Stay strong and May God bless your service!

  ReplyDelete
 43. ዳኒ በመጀመሪያ እኔና ባለቤቴ የወፉን ዝማሬ እንድንሰማ ስላደረግኸን እጅጉን እናመስግነሃልለን።

  የወፍን ቋንቋ ማንም ሰው መስማት ይችላልና ሁለታችንም ወደ ዛፉ ሄድን፥ በዛፉ ስር ቆምን። አንገታችንን መነቅነቅ ቀጠልን።

  ባለቤቴ የስማው ወፍ እንዲህ አለ…
  “ፍቅሬ ሆይ ነይ፥ ፍቅሬ ሆይ ነይልኝ። ልውደድሽ ላፍቅርሽ ልከባከብሽ ነይ።
  ፅደይ ገባ፥ ምድርም ደመቀች፥ ፍቅሬ ሆይ ነይ፥ አብረን እንድመቅ።
  ሳሩና ቅጠሉን ስብስቤአለሁ፥ አንቺ ነይና ቤታችንን እንስራ።
  እንቁላላችንን እንጣልና እንታቀፍ፥እንፈልፍልም። ፍቅሬ ሆይ ነይ፥ ያለ አንቺ ብቸኝነቱ በርትቶብኛል።
  ፍቅሬ ሆይ ነይ አብረን እንዘምር። ፍቅሬ ሆይ! አንቺ ብቻ ነይልኝ።”

  እኔ የስማሁት ደግሞ…
  “ወደሚያበራው ኮከብ በረርኩ።
  የቀረብኩ በመስለኝ ቁጥር እርቄአለሁ። ወደላይ ወጣሁ፥ ኮከቡ ከእኔ ራቀ፥ እኔ ግን አየዋለሁ። ክንፌንም በብዛት አርገበገብኩ፥ደከመኝ፥ ምናልባት ነገ ይሆንልኛል ብዬ ተመለስኩ።
  ነገ ሲመጣ ተዘጋጅቼና ተጠናክሬ እጠብቀዋለሁ። አሁን ግን የኮከቡን ድምቀት አደንቃለሁ።”

  እውነትም ሕይወት ቅኔ ናት።

  ReplyDelete
 44. I read this article right away after the author posted. I developed keen interest to learn from readers after my reading. Amazingly, everyone has different understanding. I am not surprised by the difference. To my level of understanding Daniel purposely wrote open article so that readers can use of self knowledge and experience to see the reality on the ground in the direction of the article. I think that is a perfect way to develop the societies level of thinking and understanding. To this extent, the article possess multiple massages. I have read all the comments and I felt more sense about the beauty of the article. Because the message had such a power to make people think in different ways. However, I don't like way of arguments from some people which doesn't make any sense or invalid generalization(conclusion). Yes! we all can post our feeling but we should at least take time to agree with our mentality before we inject others with infected messages. There might be problems in reality but that doesn't mean that everything one does is in response to that specific challenge. Let us say Daniel wrote the article the way most readers understood. Wouldn't be better to argue with the the person who came out with the idea? How come we spray a drop of water on the world? This might be a reflection of our daily life but we are all responsible for the death of someone because of our judgment. We might think that no physical death is happening but mental killing is the worst and cruel thing to do on someone. I still keep reading next coming comments.....Good luck all!

  ReplyDelete
 45. እዉነት ነዉ ወፊቱ የነፃነት የታታሪነት አርማ በዝማሬሽ ቃና ቀልብን የምትስቢዉ እርሱም ጸጋዉን ኃላፊነቱን አዉቆ የራሱን ተንሰራፍቶ ለብዙዎች መጠጊያ እንደመሆን በልምላሜዉ በፍሬዉ በጥላዉ . . . ለህይወት ጣእምን እንደመስጠት ፍቅርን እንደመስበክ አብሮነትን እንደ መቀኘት በዉብ ቅኔሽ መመሰጡ ቀርቶ ፈርኦን ልቡ ዝም ካላልሽ ወፍነትሽን ካልተዉሽ በኔ ላይ አትጠለይም ካለሽ እንደ አንድ ወፍ ምን ታደርጊያለሽ ጥለሽዉ ከመሄድ በቀር፡፡ እርግጥ ነዉ "የትም" የሚባለዉ ስፍራ የለመዱትን ያህል ባይሆንም ማንነትን አጥቶ ነጻነትን ተነጥቆ መክሊትን ቀብሮ ከመኖር ግን ይሻላልና በረሪ ለኛ ግን ይብላኝ ወደ ሌላ ዛፍ መሄድ ለማንችለዉ በለመድ አእብሪቱ ከሩቅ የሚነቆረቆር ቅኔ ዝማሬሽን ከሰማችሁ አላስጠጋችሁም የተባልን ቀን፡፡ አንቺ ግን ቀያችን ትሁት አስተዋይ ዛፍ አስኪያበቅል ሂጂ ብረሪ . . . . . .

  ReplyDelete
 46. እኔ ወፉን የተረዳሁት፡- ሃብታም /ዛፉ/ ደሃው ደግመ /ወፉ/ ይመስለኛል፡፡ ሀብታም በጊዜያዊ ሃብቱ ተመክቶ ደሃውን ልግዛህ፣ ልንዳህ ይለዋል፡፡ ደሃው ደግሞ አገዛዝህን ቢያንስ በልክ አድርገው፡፡ አለዛ ጤና አለኝ ወደ ፈለኩት መሄድ እችላለሁ፡፡ ማለቱ ይመስለኛል፡፡ የየዋህ አረዳድ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ አምላኬ ሆይ ተመስገን ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. I like your comment. sometimes people think you don't have life if you leave them. "Even if I am poor, I am human being, I can survive without you!!!" I love it, thank you AnonymousApril 8, 2014 at 4:17 PM

   Delete
 47. Visiting , this blog it,s GOOD
  Ena lemeredawe leyandandu kale mesegana akerebalew!
  Yalteredaweten neger alekawemem adenkalew enje!
  + H.H POPE SHENOUDA +
  Any way People trying to contact you by phone but they couldn,t found it .

  ReplyDelete
 48. Not clear at all!

  ReplyDelete
 49. ወፉዋ ዘመረች የራሳን ዝማሬ
  እኔም ተረዳሁ በክንፌ በርሬ

  ReplyDelete
 50. Egziabher bewket lay ewketen yechemereleh, WENDEMOCH HOY SETANEBU SEMETACHEUN ATANBEBU!!!!!!!!!
  ‹ይህ ነገር የምትማረው አይደለም፡፡ ሰው በመሆንህ የምታገኘው ነው፡፡ ግን ማሳደግ ይፈልጋል፡፡ እዝነ ልቡናህን መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ለሕይወት ትርጉም መስጠትን ይፈልጋል፡፡ ዝም ብሎ የተፈጠረ፣ ዝም ብሎም የሚኖር፣ ዝም ብሎ ነገር የለምና፤ ዝም ብለህ የምታልፈው ዝም ብሎ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ኑሮ ከንቱ አይደለችም፤ ሕይወት ቂላቂል አይደለችም፡፤ ሕይወት ቅኔ ናት፡፡
  እይ፣ ዝም ብለህ ግን አትይ፤ ስማ፣ ዝም ብለህ ግን አትስማ፡፡ ዓለም መጽሐፍ ናት፡፡ ሚሊዮን ገጾች ያሏት፡፡ ገጹ እያንዳንዱ ገጠመኝህ ነው፡፡ ብልሆች እያንዳንዱን ገጽ ያነቡታል፡፡ ይማሩበታልም፡፡ ሞኞች ግን ገጹን እያጠፉ ብቻ ያልፉታል›› ይሄው ነው ወዳጄ፡፡

  ReplyDelete
 51. wefiye?? bekinfochishim bihon atmeki?? Metsihaf endemil '..... yemimeka be Egziyabher yimeka....."

  ReplyDelete
 52. ዛፍ ሆይ አትመካ፣ እኔን አስጠለልኳት፣ አሳረፍኳት ብለህ አትመካ፡፡ በቅርንጫፍህ አትመካ፡፡ ለእኔ ዋናው ያንተ ቅርንጫፍ አይደለም፡፡ለእኔ ዋናው የራሴ ክንፍ ነው፡፡ ቅርንጫፍህ ሊቀር ይችላል፡፡ አንተም አላስጠልልም ልትል ትችላለህ፡፡ ያ ያንተ መብት ነው፡፡ እኔ ግን የምመካውም የምተማመነውም በገዛ ክንፎቼ ነው፡፡ ክንፎቼ ካሉልኝ የትም እሄዳለሁ፡፡ ሌላ ዛፍ ላይ ዐርፋለሁ፡፡ ሌላ ቤት ላይ እወጣለሁ፡፡ በተራሮች ላይ እቆማለሁ፡፡ በመስኩ ላይ እራመዳለሁ፡፡ ስለዚህ ልሰበር ነው፤ ልወድቅ ነው፤ ልጥልሽ ነው፤ ልወዛወዝ ነው እያልክ አታስፈራራኝ፡፡ ወፍ የተባልኩት ከእኔ ጋር ባሉት ክንፎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅርንጫፎችህ አይደለም፡፡ ወፍ የሆንኩት እኔ ጋር ባሉት ላባዎቼ እንጂ አንተ ጋር ባሉት ቅጠሎች አይደለም፡፡ ወፍ የተባልኩት በቆምኩበት እግሬ እንጂ በቆምኩበት ግንድ አይደለም፡፡ እኔ ባለኝ እንጂ በምትሰጠኝ አልተማመንም፤ እኔ በያዝኩት እንጂ በተለገስኩት አልመካም፡፡ ግሩም ድንቅ !!!!

  ReplyDelete