በዓባይ ዳር በሚገኝ መንደር የምትኖር አንዲት ወፍ ነበረች፡፡ በዚያ ወንዝ ለሚዋኙም
ሆነ ለሚሻገሩ ደምፅዋን አሠማምራ ትዘምር ነበረች፡፡ ደግሞ ላባዎቿ በኅብር ቀለማት የተሞሉ ነበሩ፡፡ እርሷ ላይ የሌሉ የአዕዋፍ
ቀለማት አልነበሩም፡፡ ዝማሬና ዜማዋ ከቶ አይቀየሩም፡፡ በዚህም የተነሣ ዝማዋን ለምደውት አብረዋት የሚያዜሙ ብዙዎች ነበሩ፡፡
በዙሪያዋ ያሉ አዕዋፍ፣ ከወንዙ ለመጠጣት የሚመጡ አራዊት፣ በወንዙ ውስጥ የሚገኙ ዐሣት አብረዋት ያቀነቅናሉ፡፡ እንኳንና
በነፍስ የሚኖሩ ሰዎችና በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱ እንስሳት ቀርተው ዕጽዋት እንኳን እንደ ቅኔ ማኅሌት እንደ ገባ ደብተራ አብረዋት
ያሸበሽባሉ፡፡ የእርሷ ዝማሬ ምንም የማይመስላቸው በወንዙ ዳር የተጎለቱት ድንጋዮች ብቻ ናቸው፡፡
እንዲህ እያለች ስትኖር ለዐቅመ ዕንቁላል ደረሰች፡፡ ጎጆ ልትቀልስም አሰበች፡፡
እንጨትና ሣር ሰብስባ ቤቷን የአንድ ጎጆ ባጥ ሥር መቀለስ ጀመረች፡፡ እንጨትና ሣር ደልድላ ጭድ በመካከሉ ልታስቀምጥ ስትል
የሠፈሩ ልጆች መጡና በድንጋይና በእንጨት ፍርስርሱን አወጡባት፡፡ እርሷ ለመሥራት አንድ ወር የፈጀባትን እነርሱ ለማፍረስ
አፍታም አልወሰደባቸው፡፡ ልጆቹ ጎጆዋን አፍርሰው የጀግንነት ስሜት ተሰምቷቸው እየሳቁና እየተደሰቱ ሄዱ፡፡ እርሷ ግን መከራዋን
ታቅፋ ቀረች፡፡ መገንባት እንደ ማፍረስ መች ቀላል ነውና፡፡
መቼም ያለ ጎጆ አይኖር፤ ያለ ጎጆም ዕንቁላል አይጣል፡፡ ያለ ጎጆም ጫጩት
አይፈለፈል፡፡ አማራጭ አልነበራትምና ዛፍ ላይ ሣርና እንጨቱን መሰብሰብ ቀጠለች፡፡ ልጆቹ ዐውቀው እንዳያፈርሱባትም በቅጠል
ሸፈንፈን አደረገችው፡፡ ዕንቁላሉ መደላድል እንዲያገኝም ጭድ በመካከሉ ረበረበችበት፡፡ ነፋስ ወዝውዞ እንዳይጥለው በልጥ ከግንዱ
ጋር ጠለፈችው፡፡ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝም በስተ ምሥራቅ በኩል በር ሠራችለት፡፡ ከሥራዋ እፎይ ብላ ዕንቁላሏን ልትጥል
ስትደላደል ግን እንደ አውሎ ነፋስ የሚያስገመግም ድምፅ ከወደ ዛፉ አካባቢ ሰማች፡፡ ድምፁም ወደ እርሷ ጎጆ እየቀረበ መጣ፡፡
ጎጆዋ ተነቃነቀ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ የመጣ መሰለ፡፡ ቱር ብላ ወጣችና ዙሪያዋን
እያንዣበበች ተመለካከተች፡፡ የሰማይ ስባሪ የሚያህል አሞራ እርሷ ጎጆ የሠራችበት ዛፍ፣ ያውም ጎጆው ከተንጠለጠለበት ግንድ ላይ
ክንፉን እያማታ ቆሟል፡፡ አንዳች የሚበላ አጥንት በምንቃሩ ወሽቆ ከሥጋው ጋር ይታገላል፡፡ እርሱ ከሥጋው ጋር በታገለ ቁጥር
የእርሷ ጎጆ ይነቃነቃል፡፡ ክንፉን ግራና ቀኝ ባማታው ቁጥር ኃይለኛ ነውጥ ይፈጥራል፡፡ ነውጡ በተፈጠረ ቁጥርም የእርሷ ጎጆ
ይፈርሳል፡፡ አሞራው ጎጆዋን በግማሽ አፍርሶት ሄደ፡፡ እርሷም በዚያ አሳዛኝ ዝማሬዋ ታስተዛዝል ጀመር፡፡
እያስተዛዘለች እያለ አሞራው አሁንም እንደገና ከእርሱ ቁመት የማይተናነስ ሙዳ ሥጋ
ይዞ መጣ፡፡ ለክፋቱ ደግሞ እዚያው ግንድ ላይ ቆሞ ቀሪውን የወፍ ጎጆ ይነቀንቀው ጀመር፡፡ አሞራው አራተኛ ጉርሻ ላይ ሲደርስ
ጎጆው ሙሉ በሙሉ ፈረሰ፡፡ የወፏም ዝማሬ ወደ እንጉርጉሮ ተለወጠ፡፡የት ትሂድ? የትስ መሄጃ አላት? ወፍ ባትሆን ተመኘች፡፡ ግን
ወፍ ናት፡፡ አሞራው ለመብላት ሲል ጎጆዋን ያፈርሳል፡፡ እርሷ ግን ጎጆዋን እሠራ ብላ የአንዲት ፍሬ ፍርካሽ እንኳን ለመቅመስ
ዕድል አልነበራትም፡፡
አዝና አዝና ስትጨርስ የግድ ነውና ጎጆዋን ለመሥራት እንደገና ፈለገች፤ እንደገና
አሰበች፡፡ እንደገናም ሣርና እንጨት፣ ቅጠልና ጭድ ፍለጋ መንከራተት ጀመረች፡፡ የነበረው እንዳልነበረ ሆኗልና እንደገና ሀ ብላ
ወጠነች፡፡ አሁን ዜማዋ ከፊል እንጎርጉሮ፣ ከፊል ምሬት፣ ከፊል ደግሞ ተስፋ ሆኗል፡፡ ተስፋ ያልቆረጠችው ተስፋ ያለው ነገር
አግኝታ አይደለም፡፡ ተስፋ ከመቁረጥ የሚሻል ሆኖ እንጂ፡፡
አሁን ከሰውም ከእንስሳትም ርቃ ዓባይ ዳር በሚገኝ የደንገል ዛፍ ላይ ጎጆዋን መሥራት
ጀመረች፡፡ ምናልባት በዓለም ከመኖር ብሕትውናው ይሻል ይሆን ብላ፡፡ ‹‹ወይከውን ከመ ዕጽ እንተ ትክልት ኀበ ሙሐዘ ማይ -
በወንዝ ዳር እንደተተከለች ተክል ይሆናል፤ እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ - ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ፤ ወቆጽላኒ ኢይነግፍ
- ፍሬዋም እንደማይደርቅ›› የሚለውን አስባ፡፡
እንደ ገና ድካም እንደገና ልፋት፡፡ ጎጆዋን ልትቀልስ፣ ዕንቁላሏን ልትጥል፤ ጫጩት
ልትፈለፍል፡፡ ከመጀመሪያው ቤት ሁለተኛው፣ ከሁለተኛውም ሦስተኛው ከበዳት፡፡ እንጨቱ እየተማገደ፣ ሣሩ እየተመደመደ፣ ጭዱም እየተወሰደ
አልቋል፡፡ ለምለሙ ጊዜ አልፎ የበጋው ደረቅ ወቅት መጥቷል፡፡ በቅርብ ይገኝ የነበረው ነገር ሁሉ ርቋል፡፡ ግን ምን
ይደረጋል፡፡
ክንፏን እስከሚያማት ድረስ ባክና በሰበሰበችው እንጨት፣ ሣርና ጭድ ጎጆዋን ለሦስተኛ
ጊዜ ቀለሰች፡፡ አንድ ሦስት ቀን የቀደመው መዓት ይመጣል ብላ ብትጠብቅ ምን የለም፡፡ እንዲህ ከሰውም ከእንስሳም መራቁ ይሻላል
ብላ በምርጫዋ ተደሰተች፡፡ አንድ አንድ እያለችም ዕንቁላሏን መጣል ጀመረች፡፡ ችግሩ ግን ያን ጊዜ መጣ፡፡ እርሷ ዕንቁላሏን
ጥላ ምግብ ፍለጋ ሄዳ ስትመለስ ዕንቁላሏን አታገኘውም፡፡ ሁለት ሦስት ቀን ወድቆ ይሆናል ብላ አሰበች፤ ጥፋቱም የእርሷ
እንደሆነ አመነች፡፡ እንዳይወድቅ ለማድረግም ጎጆዋን እንደገና አጠባበቀች፡፡ በአራተኛው ቀን ግን አሁንም ዕንቁላሏን
አላገኘችውም፡፡ ፈለገችው፡፡ እንዳች ስባሪ በአካባቢው አላገኘችም፡፡ በአምስተኛው ቀን ዕንቁላሏን ጥላ ከጎጆዋ ወጣችና እልፍ
ብላ በሌላ ዛፍ ላይ ተቀምጣ የሚሆነውን ማየት ጀመረች፡፡
እነሆ ጉዱ፡፡
እርሷ ወጣ ከማለቷ አንድ ዕባብ በግንዱ ላይ እየተሳበ መጣ፡፡ ዕባቡ የመጣው ከወንዙ
ዳር ነው፡፡ አስጠሊታ ራሱን ወደ ጎጆዋ አዝልቆ ዕንቁላሏን ሰለቀጠው፡፡ ነፍስ አልነበራትም እንጂ ድንጋጤው ነፍሷን ያወጣው
ነበር፡፡ አሁን የከፋ አደጋ መጣ፡፡ ቤቷ አይደለም የፈረሰው፤ ዕንቁላሏ ነው የሚበላው፡፡ ምትኳ፣ ዘሯ፣ ተስፋዋ፣ ሀልወቷ፣ ኑባሬዋ
ነው የሚበላው፡፡ ዕንቁላል እንዳትጥል አልተከለከለችም፤ የምትጥለው ግን ለሌላ ሆነ፡፡ እርሷ አንድ ቀን ዕንቁላል መጣል
ታቆማለች፡፡ ያን ጊዜ ህ ዕንቁላል የለመደ ዕባብ እርሷን መብላት ይጀምራል፡፡ ከሁሉም ተገላገልኩ ብላ የመጣችበት ቦታ ከሁሉም
የባሰ ሆነ፡፡
በረረረች፣ ከነፈች፣ ወጣች፣ ወረደች፣ ከነፋሱም ጋር ሄደች፣ ከነፋሱም በተቃራኒም ነጎደች፡፡
መሬት ወረደች፣ ወንዝ ውስጥ ገባች፡፡ በመጨረሻ ደከማት፡፡ ሲደክማት አንድ ዛፍ ላይ ቆማ እንዲህ እያለች ታንጎራጉር ጀመር፡፡
ኦ እለሎ፣ ኦ እለሎ
ኦ እለሎ፣ ኦ እለሎ
ወዴት ሄጄ ልኑር
ወዴት ሄጄ ልሥራ፤
ባጡ ሥር ስሠራ
ልጆቹ መከራ፣
ዛፉ ላይ ስሠራ
አሞራው መከራ፣
ወንዙ ዳር ስሠራ
ዕባቡ መከራ፡፡
ወዴት ሄጄ ልኑር፣
የት ሄጄ የት ልሥራ፤
የት ውዬ የት ልደር፤
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው
ምክር ሰናይ ይእቲ ለዘይገብራ
ReplyDeleteቃለ ሕይዎት ያሰማልን
ምክር ሰናይት ለኩሉ ዘይገብራ
ReplyDeleteቃለ ሕይዎት ያሰማልን
This is what happening now in our church(EOTC) by this stupid government!!!!
ReplyDeleteዲያቆን ዳኒኤል ውፉዋኮ ምትክራትትወ ውፈ ስልሆንች ብቻ ነው ብዛላ አሞራም ራሱን ብቻ የሚወድ ነው እባብም ተኮለገኛ ነው ሰው
ReplyDeleteተባሉትም ቸልተኛ ሆነው የሰላምና የእረፈት ማብሰሪቸውን አሳደዋታል ለእርግቡዋየዋህነቱዋ ብቻ ነው ላት የየዋሀን አምላክ ይርዳታ…በእርሱዋ ዝማ ረክተው ግታቸውን የሚያመሰግኑ የበርሃ ብቸኞች ቤታቸውን ከፍተው በበአታቸው ቤት ይ ሰሩላታል ከወንዝ ውሀቀድትው ያጠጡዋታል እርሱዋ በዝማዋ እነርሱ በጠሥሎት ራዱዋታል ድሮመ የባህታውን መዝሙር ናስ ባግራ እነኩዋነ ሰው ውፍ ለምዳልሁ ኤድል
ወፍ ባትሆን ተመኘች፡፡ ግን ወፍ ናት፡፡ አሞራው ለመብላት ሲል ጎጆዋን ያፈርሳል፡፡ እርሷ ግን ጎጆዋን እሠራ ብላ የአንዲት ፍሬ ፍርካሽ እንኳን ለመቅመስ ዕድል አልነበራትም፡፡
ReplyDeleteእኔ ነኝ ወፏ - ያውም ማረፊያ ያጣሁ ወፍ!!
ReplyDeleteበተከራየሁሀተ ግቢ ትርምስ ተረብሼ እነቃለሁ፡፡ውሃ የለችም፡፡በድሃ ደሞዜ እሽግ ውሃ ገዝቼ ፊቴን አብሳለሁ፡፡ ቁርስ አልበላም፡፡አልጋየን እንደተተራመሰ ቤቴን የኋሊት ዘግቼ እወጣለሁ፡፡ለታክሲ እሰለፋለሁ፡፡ስወርድ ለባቡር የታረሰው መንገድ ይቀበለኛል፡፡ቢሮ ስደርስ ፊርማ ይነሳል፡፡ስራው ተቆልሎ ይጠብቀኛል፡፡ተደፍቼ እሰራለሁ፡፡ምሳ ይደርሳል፡፡ኪሴ ውስጥ ያለው ብር ከመ/ቤት ክበብ ውጭ ለመብላት አያስችለኝም፡፡የደሞዜና የስራየ አለመመጣጠን ያናድደኛል፡፡ባለዲግሪ ሰራተኛ ሆኘ ለአንድ ሆዴ መጨነቄ ያበሳጨኛል፡፡ስበሳጭ ብስጭት ብስጭት የሚሸቱትን ሳይቶች እመረምራለሁ፡፡ንዴቴን ያባብሱልኛል፡፡ትቻቸው የክበባችንን ወጥ አጥቅሼ ሳይሆን ተምትሜ ሆዴን አታልየው እመለሳለሁ፡፡በአስር ተኩል ከአለቃየ ተደብቄ እወጣለሁ፡፡ታክሲ እሰለፋለሁ፡፡ብሳፈርም ቤቴ አልሄድም፡፡መንገድ ላይ እወርዳለሁ፡፡የቤ/ክ አጸድ ውስጥ እገባለሁ፡፡ጸሎቴ በየቀኑ ተመሳሳይ ስለሆነ ልቤ ጠፍቶ እንኳን ከንፈሬ አይስተውም፡፡ጸሎቴ ማለቁን ከመ ይስረይ ለነ ኃጣውኢነ ስል ነው የማስታውሰው፡፡በጸጥታ ለረጅም ሰዐት እቀመጣለሁ፡፡ለእራት እንጀራ ገዝቼ ወደ ቤት ስሄድ ዓለም ድንገት እንድታልፍ እመኛለሁ፡፡ኦና ቤት ከፍቶ መግባት ያስጠላኛል፡፡አድማጭ በሌለው እንጉርጉሮ ታጅቤ መኖር ይሰለቸኛል፡፡
በናትህ ዳኒ ወፏ ወዳለችበት የባህርዳር ወንዝ ውሰደኝ፡፡ከዚህ ኑሮ ከእባብ ጋር ብታገል ይሻለኛል፡፡ለእኔ ለድሃው አንገት ከሚያቀጥነው የከተሜ የኪራይ ቤት ኑሮ በራስ ጎጆ ውስጥ ከእባብ ጋር ታግሎ መኖሩ ይሻለኛል፡፡ለስንቱ ልጨነቅ፡፡እኔ እኮ ስጋየም መንፈሴም አላረፈም፡፡ተስፋ ተስፋ የሚሸት ነገር አጣሁ፡፡ኦና ሆንኩኝ፡፡ባዶ፣ባዶ፣ባዶ፣ከንቱ፣ከንቱ፣ከንቱ፡፡የት ልብረር፡፡
Stay strong bro. I wish u the best.
Deleteayzoh wondeme hulum yalfal, abzagnaw sew temesasay new
Deleteአላማህ መንፈሳዊ ከሆነ በባዶነት ውስጥ ፍጹም መደሰትን ልመድ የእግዚአብሄር ጸጋ ባዶነትህን ይሞላዋል
Deleteአላማህ አለማዊ ብቻ ከሆነ ግን ከእባቡ የሚያስጥልህ የለም
እውነት ነው
መኩሪያ፡- ንግግርህ በእውነት ነው የምልህ እንባዬን አመጣው፡፡ ግን ግን ይችን አንብብልኝ፡፡
Deleteእግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው
ከቁጣ የራቀ ምሕረቱም ብዙ ነው
እግዚአብሔር ለሚታገሱት ቸር ነው
ምህረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው፡፡
እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው
በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው
እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል
የወደቁትንም ያነሳቸዋል
የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል
አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ፡፡
አንተ እጅህን ትከፍታለህ
ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ
እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው
በሥራውም ሁሉ ቸር ነው፡፡
እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ
በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡
ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል
ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም
እግዚአብሔር የሚወድዱትን ሁሉ ይጠብቃል
ሃጢአተኞችንም ሁሉ ያጠፋል፡፡
መዝሙረ ዳዊት 144/145
ወንድሜ ሆይ የዚህ አይነት ክፉ ሃሳቦች ሲመጡብህ የእግዚአብሔርን ቃል አንብብ፡፡ እግዚአብሔር ተስፋ ይሆንሃል፡፡ አይዞህ ባብዛኛው ተመሳሳይ ኑሮ ነው የምንኖረው፡፡ ይህ ለአንተ ብቻ የተሰጠ ፀጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ ፀልይ እግዚአብሔር ይረዳሃል፡፡ እመ ብርሃን በረድኤቷ ታስብህ፡፡
Ayzoh Tages Yetegeseten Fire tebelaleh...tsena
Deleteአይዞህ የማያልፍ የለም ጠንካራ ሁን
Deleteእባክህን ወንድሜ ላሳዝንህ ፈልጌ ኣይደለም ነገርግን ወጥቶ መግባት የማይችል፡ ለምኖ ለዳቦ መግዣ ኣልሞላ ያለው ፡ በጀርባው የስንቱን ህይወት ተሸክሞ የእኔና ያንተን ሥራ ኣጥቶ በፍለጋ የሚንከራተትም ኣለና ይህን የሰጠን እያመሰገንን ደስተኛ እንሁን ነገን ኣናውቀውምና!!!
Delete" አላማህ መንፈሳዊ ከሆነ በባዶነት ውስጥ ፍጹም መደሰትን ልመድ የእግዚአብሄር ጸጋ ባዶነትህን ይሞላዋል "
Deleteአባባሉ ልክ ነው ፡ የተርዳነው ግን ፡ በትክክል አይምስለኝም ፡፡
አዳም ከገነት ተባሮ መውጣቱንና ፡ ጥረህ ግረህ አንጀራህን ብላት መባሉን ገና ያልሰማነው አበሾች ቁጥሩ ብዙ ነው ማለት ንው? ወይም የተረዳነው ፡ ጠረጴዛው ላይ የቀረበልህን እንጀራ ፡ ጥረህ ግረህ ጉረስ እንዳለን ነው?
በህይወትህ ዉስጥ የሚያጋጥሙህን ችግሮች ሁሉ፡ ጥረህ ግረህ ተወጣ ማለቱ እንዳይሆን! የስጠሁህን ጭንቅላት ተጥቅምህ ፡ ችግሮችህን አስወግደህ ተደላድለህ ኑር ፡ የምትችለውን ሁሉ ካርግህ በሁዋላ ፡ ከአቅምህ በላይ ለሆነው ነገር ፀልይ ፡ ማለቱ ከሆንኮ ፡ እኛ ጉድ ሆነናል!
ወፍዋ አበሻ ብትሆን ኖር ፡ የመጀመሪያውንም ልጆቹ ያፈረሱባትን ጎጆ ሳትሰራ፡ ቁጭ ብላ ጎጆ እንዲሠራላት ፡ ፈጣሪዋን ትማጠን ይሆን?
መንገደኛው
ቤ/ን ሊያፈርስ የሚጥረው ሆዴ ይሙላ ደረቴ ይቅላ እያሉ የስጋ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የሚሯሯጡ ናቸው ልቦና ይስጣቸው!!!
ReplyDeleteየሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባየ!!
Deleteየሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ!!
ሞኝና ወረቀት ያስያዙትን አይለቅም!!
ውድ Anonimous @ 6:51
Deleteይቺ የጻፍካት ትንሽ ነገር
የሞኝ መወድስ? ናት ስንክሳር
ወይስ መነጽር
ያንተ መዘክር !!??
ልንገርህማ፦
ሞኝ አወዳሹ
ጅል አስታዋሹ፦
ስግብግብነት ደግሞም ስስት
የማይጠረቃ ሆድ ለመሙላት
ኅሊናን መሸጥ ደረት ማቅላት።
ለአገር ጥፋት ለሕዝብ ስቃይ
ለእምነት ፈተና ታሪክ ገዳይ
በሰማይ በምድር ውርደት አልባሽ
በቁም ቀባሪ ነስቶ አስታዋሽ
አሁን አስቆ ኋላ አስለቃሽ
ታጥቆ የሚያበላን በላተኛንም
አጥፊ አዋራጅ ገዳይ ሁሉንም።
ካልጠፋ በቀር እሱም ተገድሎ
እያታለለ ሁሉን አማልሎ
እንደሚያጠፋ ለሆድ መገዛት
እምቢ አይበቃኝም ስግብግብነት፣
ይድላኝ ለራሴ ለብቻ ማለት።
ነቀርሳ ሆኖ አንዳስቸገረ
አማሳኝ ሆኖ አንዳስመረረ
ፀሐይ የሞቀው ያወቀው አገር
ጠንቅ መሆኑን ለከርስ ማደር።
የዓለሙን ሁሉ ተራውን እውቀት
ማድረግህ ነወይ የሞኝ ጩኸት?
የጅሎች ዘፈን ብቻ ወረቀት።
ይህን ሙስና ዓይንህ ካላየው
ያዛኙን ልቅሶ ጆሮህ ካልሰማው
ካልተረዳኸው እስካሁን ድረስ
ወይም ከካድከው ዳባ በማልበስ፤
…………….. ዓይንህ ሞኝ ነው
…………….. ጆሮህም ቂል ነው
ነሆለል ነገር አእምሮህ ጅል ነው።
ወይስ …………??
ከባለግዜ ደረተ ቀይ
ጠግቦ በቁንጣን ከሚሰቃይ
ደግሞ ሚበላ ሳያቋርጥ
ክብር ኩራቱን አርጎ ስልቅጥ!
እንዳትሆን ብቻ ከዚያ ወገን
ማደንደን ሞያህ ብቻ ስጋን።
ተሥተ Bole-Shef
" እሾህ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብሰው :
ReplyDeleteእንዴት መቀመጫ መሄጃ ያጣል ሰው ::"
ብራስልስ ቤልጅየም
ስጋ በል አሞራ ቤ/ክን ገብቶ ተቸገርን እኮ
ReplyDeleteየኔዋ ወፍ
ReplyDeleteተነሳች ግን ወደቀች
በራ ነበር ባጭር ቀረች
ያች ወፍ ምስኪኗ እንዴት ሆና አደረች
የተረገመ ቀን በክፉ እጅ ጥሏት
ወኔዋን ሰለበዉ ወፍነት ጠፋባት
ክንፏን ደሸደሹ ላባዋን ነጩባት
ይኸዉ ቀረ ሲያምራት መብረርም ተሳናት
ግዳጅ የማትፈጽም ስንኩል አደረጓት
ከቤተ ማኅበሯ ከወገኗ ለዩአት
ተጠቃቀሱባት በሽሙጥ ገረፏት
አንገቷን አስደፉ ቅስሟንም ሰበሩ
ሊያጠፏት አደቡ ቀስትንም ወተሩ
በቃ ከንቱ ቀረች ሕይወቷ ባከነ
ተስፋዋ ጨለመ ሕልሟ ቅዠት ሆነ
መጡ ተንሰፍስፈዉ ዙርያዋን ከበቧት
እንዳታጠቃቸዉ አቅም ጉልበት የላት
እንዳታመልጥ ደግሞ ክንፍ አልባ ናት
የፈራችዉ ሆነ ደርሰዉ ተናነቋት
ዓይኖቿ እያዩ ዓይኗን አጠፉባት
ማህበረ ቅዱሳንን ነው ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ወይ ይች ጉድ. . . ሰውን ሁሉ አተራመሰችው አይደል፡፡
Deleteየት ትሂድ? የትስ መሄጃ አላት? ወፍ ባትሆን ተመኘች፡፡ ግን ወፍ ናት፡፡ አሞራው ለመብላት ሲል ጎጆዋን ያፈርሳል፡፡ እርሷ ግን ጎጆዋን እሠራ ብላ የአንዲት ፍሬ ፍርካሽ እንኳን ለመቅመስ ዕድል አልነበራትም፡፡
ReplyDeleteእነሆ ጉዱ፡፡
እርሷ ወጣ ከማለቷ አንድ ዕባብ በግንዱ ላይ እየተሳበ መጣ፡፡ ዕባቡ የመጣው ከወንዙ ዳር ነው፡፡ አስጠሊታ ራሱን ወደ ጎጆዋ አዝልቆ ዕንቁላሏን ሰለቀጠው፡፡
ቤቷ አይደለም የፈረሰው፤ ዕንቁላሏ ነው የሚበላው፡፡ ምትኳ፣ ዘሯ፣ ተስፋዋ፣ ሀልወቷ፣ ኑባሬዋ ነው የሚበላው፡፡ ዕንቁላል እንዳትጥል አልተከለከለችም፤ የምትጥለው ግን ለሌላ ሆነ፡፡ እርሷ አንድ ቀን ዕንቁላል መጣል ታቆማለች፡፡ ያን ጊዜ ህ ዕንቁላል የለመደ ዕባብ እርሷን መብላት ይጀምራል፡፡ ከሁሉም ተገላገልኩ ብላ የመጣችበት ቦታ ከሁሉም የባሰ ሆነ፡፡
በረረረች፣ ከነፈች፣ ወጣች፣ ወረደች፣ ከነፋሱም ጋር ሄደች፣ ከነፋሱም በተቃራኒም ነጎደች፡፡ መሬት ወረደች፣ ወንዝ ውስጥ ገባች፡፡ በመጨረሻ ደከማት፡፡ ሲደክማት አንድ ዛፍ ላይ ቆማ እንዲህ እያለች ታንጎራጉር ጀመር፡፡
ኦ እለሎ፣ ኦ እለሎ
ኦ እለሎ፣ ኦ እለሎ
ወዴት ሄጄ ልኑር
ወዴት ሄጄ ልሥራ፤
ባጡ ሥር ስሠራ
ልጆቹ መከራ፣
ዛፉ ላይ ስሠራ
አሞራው መከራ፣
ወንዙ ዳር ስሠራ
ዕባቡ መከራ፡፡
ወዴት ሄጄ ልኑር፣
የት ሄጄ የት ልሥራ፤
የት ውዬ የት ልደር፤
Geta melkamun ken yamtalin
ReplyDeletefor the above Anonymous please don't repeat the idea what has been said by the blogger.
ReplyDeleteOk my dear 10q
Deleteዲ/ን ዳንኤል ክብረት መካሪ እና አፅናኝ ወንድም ስለሰጠን እ/ር ይመስገን፣ ወፉዋ በቃ እባቡን ትፋለመው፤ ማንነቱዋን እያጠፋ ያለውን፣ ያለዘር እያስቀራት ያለውን፣ በመጨረሻም በሌሊት መጥቶ ሊያጠፋት ያቀደውን፣ ስንት ሃገር ተንከራታ የሰራቸውን ቤት ከባህር(ከቀዝቃዛው) ወጥቶ የሞቀ ቤት ወርሶ ለመኖር ያሰበውን እስከመርዙ መቅበር አለባት፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር የሚለው ቃል በምጻረ ቃለም ሆነ በአጭሩ አይጻፍም፡፡
Deleteእሺ ወንድሜ ተቀብያለሁ፡፡
DeleteHi Dn.Daniel,
ReplyDeleteThis is great view. I think the bird needs to do something before she keep making her houses. I think she tried all options with ought reacting to her enemies. But know as you mentioned, she is loosing her eg, her generation, her story, her life......What is left for her? I think before she loose her life the bird has to start defending her self. It would have been great for others to enjoy her songs, and take all the advantages of her beauty. I hope her enemies never want to see her defend herself. But unfortunately no option left after all...But how can she defend herself, while she is a bird....I wan't learn from others....Thank you and May God bless you!
ሠናይ ነጽሮት ወሠናይ ትምህርት
ReplyDeleteHi Dn. Daniel,
ReplyDeleteYou remind me a song I heard when I was a child, I wish I can write it in Amharic
"Hagere **midir
yet wuye yet lider
Ezaf lay bisera
Amoraw mekera
ATir lay Bisera
Eregnaw mekera...."
I forgot the rest and she build yer nest in the floor. That is so interested. That was what an old man translate her song for me and my friends.
I think it has deeper message than what I thought that time. It is easy to damage other people's life but challenging when you see it on the other side. Thank you for your brilliant view as usual.
ግና ይህ ዝምታ እስከ መቼ? ቤተ-መቅደስ አፈረሱብን፣ ዝም አልን፤ አቃጠሉብን ዝም አልን፤ በአደባባይ አይረቡም ብለው ተሳደቡ አሁንም ዝም፤ ልጅ ከአባት ሊለዩ አንዳንዶች ብለው አሴሩ፤ በበሬ ወለደ ተረት-ተረት እና ደረቅ ውሸት አፋችንን ሊያዘጉ ይኸው እያሴሩብን ነው፤ አሁንም ዝምታ መረጥን... ይህች ወፍ ዛሬ... «.... ቤቷ አይደለም የፈረሰው፤ ዕንቁላሏ ነው የሚበላው፡፡ ምትኳ፣ ዘሯ፣ ተስፋዋ፣ ሀልወቷ፣ ኑባሬዋ ነው የሚበላው፡፡ ዕንቁላል እንዳትጥል አልተከለከለችም፤ የምትጥለው ግን ለሌላ ሆነ፡፡ እርሷ አንድ ቀን ዕንቁላል መጣል ታቆማለች፡፡ ያን ጊዜ ይህ ዕንቁላል የለመደ ዕባብ እርሷን መብላት ይጀምራል... » ታድያ የኛስ ዝምታ እስከ መቼ? አሁንስ የህልውና ጉዳይ አይደለምን...?
ReplyDeleteDear DN Daniel
ReplyDeleteBless you! It is vary touchy, whoever you are referring too I don't want to make an assumption. However, I would like to say this prayer for both the bird in your article and Mekuria the above I hope the almighty God will give them strength to overcome the hardship they are facing today? Amen!!
thanks dani
ReplyDeleteits nice massage .
ReplyDeleteLesewum, Lamorawum lib yistachew. Ebabun gin anat anatun endemalet yemyawata meftihe alagegnehum.
ReplyDeleteZare ye abzhagnew ethiopiawi hiwot yezichi wof hiwot yimeslal. Le sigaw yikrina le nefsu enkuan ereftin yemishabetin gojo (Beteskian) beselam derso teregagto memeles aschegari honual .
bewinet wefitun sasib hazen tesemagn!!! wedet tihid? leman abet tibel? man eredat yihunat?
ReplyDeleteDn. anten Egziabher yitebkilin!
ወፍዋ ከሚገጥማት ፈተና መሸሽዋን አቁማ ታግላ የምታሸንፍበትን መንገድ ካልፈለገች ስትሰደድ ትኖራለች እንጂ ማንም አይደርስላትም፡፡
ReplyDeleteWhat I don't like on this blog is, those people who copy and paste what Dn Daniel already wrote, unnecessary repetition and doesn't give sense
ReplyDeleteማህበረ ቅዱሳንን ነው ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ወይ ይች ጉድ. . . ሰውን ሁሉ አተራመሰችው አይደል፡፡ ምናለበት የራሳችሁን ውዳሴ ማርያም ትታችሁ መልካሙን ነገር ብታስቡ
Delete"በእጇ መብላትዋ ፡ አጉርሱኝ አለማለትዋ" ሲባል አልሰማህም። በመሆኑም በመጀመሪያ እራሳቸውን ችልው በማንበባችው ተፅናና! የማንበብ ፍላጎታችው ይታያልና ። ሌላው ምናልባት ላንተና ለኔ ያልተገለፀልን ፡ ግን ለነዚህ ሰዎች ስሜት የሰጠ ነገር ይኖራል ብለን እንጠርጥር ፡፡
Deleteጌቱ ከጀርመን
ወላዲተ አምላክ ለወፏ ጠላቶቿን አስገዚላት፡፡
ReplyDeleteHi danni you definitely frustration on all areas. no body is happy and satisfied on his own country.therefore everybody wants to migrate to America and all over other countries to live safe life. i don't think there is solution and hope for Ethiopian people.God help us.
ReplyDeleteዳኒ እግዚያብሔር ቃለ ህይወትን ያሰማህ ምን አንላለን ሁሉንም አንተው አልህልን በርታ ።ከበላይ ነኝ
ReplyDeleteየዚች የምስኪን ወፍ ታሪክ እንደዚህ ዳነኤል ጽፎ ሲያስንብበን ፡ ውስጣችን ያዝናል፡፡ ስቃይዋን አናይ ብለን እንጂ ፡ መኖሪያዋ እኮ አሩቅ ሆኖ አይደለም ፡፡ እባቡ ግን በውፍዋ እንቁላል ዳብሮ ፡ ጉልበት አውጥቶ ፡ የውፍዋን ጉዳይ ካጠናቀቀ በሁዋላ ፡ ነገ ወደኛ እንደሚዞር ዘንግተንዋል፡፡ "ነግ በኔ" አሉ አበው!
ReplyDeleteእስቲ መፍትሄ በየበኩላችን እንፈልግ፡፡ ሳይጨልም!
ምን አማራጭዎች አሏት?
''እባቡ እራርቶ ቢተዋት? ለመራራት ለካ ማሰብ ያስፈልጋል! እንዳያስብ ቁንጣን ይዞታል። ሆዱ በጣም ሲሞላ ጭንቅላት ይደፈናል። የተወሰኑትን እንቁላሎች ቢተውላትና ጫጩቶች ቢፈለፈሉ ፡ አድገው እንሱም እንቁላል ይጥሉና ፡ እባቡ ተጨማሪ እንቁላል ያገኝ ነበር ። ግና በመጀመሪያ እንዳልኩት ሆዱ ጭንቅላቱን አስሮበታል፡ ፡ ነገ የሱ ልጆች ፡ የውፍዋ ዘር ካልተራባ የሚበሉት እንቁላል እንደማይኖራቸውም ዘንግቶታል። " እኔ ከሞትክኝ ሰርዶ አይብቀል" መሆኑ ነው፡
ወፍዋ ምን ታርግ? ትፋለመው ማልት እንችላለን ፡፡ ግን ምንም እንኳን ዳዊት ጎልያድን እንዳሽነፍ ብናውቅም ፡ ዳዊት ንፁህ ሰው በመሆኑ ነበር ፡ እግዚአብሔር አግዞት ለድል የበቃው። ይች ወፍ ግን ጥፋት አላት ። ጥፋትዋ የእባብን ምክር መስማትዋ ነው።
አያት ቅደም አያቶችው በአገሩ ካሉ ወፎች ጋር ተባብረው በአንድነት መኖራችው ነብር ትልቁ ጥንካሬያችው። እባብ ግን ገና ከመጀመሪያው ይህን አንድነት የሚያፈርስበትን ተንኮል ይዞ ነው የመጣው። በመሆኑም ለውፍዋ እንዲህ አላት፡
" አሁን እንዳንቺ ያለ ቆንጆ ፡በዛ ላይ መረዋው ድምፅሽ ለምን ብለሽ ነው ፡ ከሌሎቹ ጋር በጋራ የምትተራመሽው ፡ ይልቅ ፈንጠር በይና ዓልም ያድንቕሽ።" ይዋሂትዋ ወፍ እባብን አምና ተፈናጥራ ለብችዋ መኖር ጀመረች ። ውንትም መጀመሪያ ላይ ፡ አድናቂዋ በዛ ፡፡ ጉድና ጂራት ከወድኋላ!
እባብ ግን ሌሎችም ላይ ፡ የተንኮል መርዙን መርጨቱን አላቆመም ።
ለሌላው ደግሞ እንዲህ አላት፡
" አንቺ መዝፈን እንደማይችል ተደርገሽ ፡ ድምፅሽ ታፍኖ ፡ ልጆችሽ የሌላ ወፍ ዘፈን እንዲማሩ ተገደው ፡ ነጠል ብትይ እኮ ይህ ሁሉ ችግር ይወገዳል፡"
በዚህ አይነት ምክሩን የተከተሉ ዛሬ ለብቻ ሆነው ለጥቃት ተዳርጉ ፡፡ ይች ምስኪን ወፍ ፡ እንግዲህ ከነዚህ አንድዋ ናት ፡፡ግን ተንኮሉ የገባቸው ከዚህ በፊት አያቶቻቸው ተባብረው ከሩቅ የመጣውን ትልቅ ዘንዶ እንዳባረሩ የሚያውቁ ወፎች አንድነታችው አንዳይፈርስ እየወተወቱ ነው ፡፡ እባብ የነዚህ ወፎች አደገኛነት ስለገባው ፡ሊያጠፋችው ቢያሴርም አልተሳካለትም ፡፡ ሰለዚህ ይች ወፍ ተመልሳ ፡ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ከተፈበረከው ልዩነት ፡ በሺ ዘመናት አብሮ መኖር የተሳሰረውን አንድነት ፡ በጣሙን እንደሚያስተሳስር ተረድታ ፡ ከሌሎቹ ወፎች ጋር መተባበር አለባት፡፡ አባብ ይህን ሲያይ ፡ ቀዬውን ጥሎ ይጠፋል፡፡
" ድር ቢያብር ፡ አንበሳ ያሥር ! "
ቸር ይግጠመን
ጌቱ ከጀርመን
Wefuwa= beye botaw "kililachiwu ayidelem" eyetebalu yeminkeratetutin Ethiopians tiz asegnechign ena Asazenechign::
ReplyDeleteአምላከ ቅዱሳን ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ በድንጋይ የሰቀሉት የሰራትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በድንጋይ ለማፍረስ ፈለጉ፡፡ ሆዳሞች ስጋቸው በልጦባቸው ስጋቸውን ሲበሉ ኖሩ ጊዜው የእባቡ ነውና እባቡ ደግሞ እንቁላሉን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይሔነው ግን ልጆቿን እንዴት ማሳደግ እንዳለባት ቤቷን የት መስራት እንዳለባት አሁንም ሳትሰለች ወፏ እስከመጨረሻው ትተጋለች ቤቷንም ያፈረሱት ሔዱ አሞራውም ቤቷን ያፈረሰበት ዘመን አለፈ እባቡም እዛው ትታው ትሔድና ሌላ እንቁላል ትጥላለች የቀኑባት የሚቀኑባት ሊያጠፏት የፈለጉ በልጆቿ ያፍራሉ፡፡
ReplyDeleteአምላከ ቅዱሳን ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDelete