Thursday, March 27, 2014

ትናንት አልባዋ ከተማclick here for pdf
በተፈጥሮ ካልተገኙና ሰው ልጅ ከፈጠራቸው ከማይንቀሳቀሱ የሥልጣኔ ውጤቶች አንዱ ከተማ ነው፡፡ ከተማ የአንድ ሕዝብ ሥልጣኔ የሚታይበትና የሚቀላጠፍበት ማዕከል ነው፡፡ በዚህም የተነሣ የሰው ልጅን ታሪካዊ ሂደት በመመዝገብና የደረሰበትንም ሥልጣኔ በማሳየት ረገድ የከተማን ያህል የተሻለ ቦታ የለም፡፡ የጥንታዊ ሰዎችን ሥልጣኔና ታሪክ የሚያጠኑ ባለሞያዎች የጉዞውን ሂደት የሚገልጡ መረጃዎችን የሚያገኙት በቁፋሮ ከሚገኙ ጥንታውያን ከተሞች ነው፡፡ በእነዚህ ጥንታውያን ከተሞች የሰው አነዋወር፣ ታሪክ፣ የመንግሥት አሠራር፣ የንግድና የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ወግና ሥርዓት፣ እምነትና ባሕል በተሰናሰለና ሥርዓት በጠበቀ መንገድ ይገኝባቸዋል፡፡
በአብዛኛው የገጠሩ ማኅበረሰብ ባልተሰባሰበ፣ አንድ ወገን በሆነ፣ ግልጽ የአኗኗር መርሕ፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እምብዛም ባልተዘረጋበት መንገድ የሚኖር ነው፡፡ የከተማ ማኅበረሰብ ግን በተወሰነ ቦታ፣ ከተለያየ ማኅበረሰብ ተውጣጥቶ፣ በአንድ ውሱን ሕግ እየተዳደረ፣ ለክዋኔዎች ቦታ ወስኖ(ለንግድ፣ ለአምልኮ፣ ለመንግሥት አስተዳደር፣ ለመኖሪያ፣ ወዘተ) የሚኖር በመሆኑ የሥልጣኔ መገለጫዎች በከተሞች የሚገኙትን ያህል በገጠር አናገኛቸውም፡፡ ሐውልቶች፣ አደባባዮች፣ አብያተ መንግሥት፣ ሳንቲሞች፣ የኪነ ጥበብ ሕንጻዎች፣ የተደራጁ ገበያዎች፣ የውኃ መሥመሮች፣ የከተማ መከለያ ግንቦች፣ የእምነት ማዕከሎች በከፍተኛ የሥልጣኔ ደረጃ ተሠርተው የምናገኛቸው በከተሞች አካባቢ ነው፡፡

በሀገራችንም የታሪክና ቅርስ ማዕከል የሆኑትን አኩስምን፣ ሮሐን፣ ሐረርን፣ ጎንደርን፣ አንኮበርን፣ አዲስ አበባን፣ ሌሎችንም ብንመለከተ የመንግሥት፣ የኢኮኖሚና፣ የእምነት መናኸሪያ ከተሞች የነበሩና የሆኑ ናቸው፡፡ በእነዚህ ቦታዎች የምናገኛቸውን እርስ በርስ የተግባቡ፣ የተሠናሠሉና የተመጋገቡ የሥልጣኔ መገለጫዎችን ያህል በሌሎች ቦታዎች አናገኝም፡፡ በሌሎች ቦታዎች የምናገኛቸው በተናጠል የተቀመጡ የሥልጣኔ መገለጫዎችን ነው፡፡
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ምክንያት ትናንትን ይጠይቃል፡፡ እንዲሁ ዛሬን ብቻ ዝም ብሎ አይቀበልም፡፡ እንደ ሥነ ፍጥረት ሊቃውንት ይህንን የሚጠይቁት መላእክትና ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ መላእክት በተፈጠሩ ጊዜ ‹‹ከየት ተገኘን? እንዴትስ ልንገኝ ቻልን?›› ብለው የጠየቁት ግእዛን ያላቸው (ማሰብና መመርመር የሚችሉና የሚያስፈልጋቸው) ፍጡራን በመሆናቸው ነው፡፡ የሰው ልጅም በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ዘመን ጀምሮ በእምነትና በፍልስፍና መስኮች ሲጠይቃቸው ከኖራቸው ጥያቄዎች አንዱ ‹‹ዓለም ከየት መጣች?›› የሚለውን ነው፡፡
ሰው ትናንትን የማወቅ፣ ከትናንቱም የመማር፣ ከትናንት ተምሮም ወደፊት የመንደርደር ዕምቅ ፍላጎትና ችሎታ ስላለው መሬት እየጎረጎረ፣ ዋሻ እየበረበረ፣ ዐለት እየፈለጠ፣ ተራራ እየገለበጠ የጥንት ሰዎችን አድራሻ፣ ማንነትና ሥራ ሲመረምር ይኖራል፡፡
ሰው እንደ እንስሳ የዛሬን ብቻ ኑር ሊባል አይችልም፡፡ እንስሳ ትናንትም ነገም የለውም፡፡ ሰው ግን የሦስት ነገሮች ውጤት ነው፡፤ የትናንት አሻራ፣ የዛሬ ሥራ፣ የነገ ራእይ፡፡ ሰው ነገን ያለ ትናንት ማሰብ አይችልም፡፡ ተፈጥሮ አንድን ነገር ለብቻው በንጣሌ እንድንረዳው አልተወችንምና፡፡ ተፈጥሮ ራሷ የትይይዝ ውጤት ናት፡፡ ሊቃውንት ይህንን ለማስረዳት እንደ ቀላል ማሳያ የሚሰጡን ቀለማትን ነው፡፡ አንዱ ቀለም ከሌላ የሚግባባው ቀለም ጋር ስምምነት ፈጥሮ(harmony) ነው የሚኖረው፡፡ ይህንን የቀለማት ተግባቦት የሰዎች አለባበስ፣ የቤት አሠራር፣ የፀጉርና የሰውነት ቀለም፣ የሚተከሉ ዛፎችና እንዲፈጥሩት ይደረጋል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህን ቀለማት አስበን ባንመርጣቸውም ተፈጥሮ ተግባቦትንና ስምምነትን ስለምትፈልግ ደመ ነፍሳዊ በሆነ መንገድ እናከናውነዋለን፡፡ 

በአንዲት ከተማ ሕይወት ውስጥም እንደ ቀለማቱ ተግባቦት ሁሉ ትናንት፣ ዛሬና ነገ ተግባብተው መገኘት አለባቸው፡፡ እንኳን እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከመቶ ዓመታት የዘለለ ታሪክ ያላቸው ከተሞች ቀርተው የቅርብ ዘመን የምሥረታ ታሪክ ያላቸው እነ ዱባይ እንኳን አንዳች ከጥንታዊነት ጋር የሚያያዝ ታሪክ ፍለጋ ሲኳትኑ፣ ያንንም ለማሳየትና የከተማቸው የሕይወት አካል ለማድረግ ሲጥሩ እናያቸዋለን፡፡
በአንድ ከተማ ሕይወት ውስጥ በሳል ነቢብ(ቲወሪ)፣ አመራርና አሠራር ከሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አንዱ ትናንትን፣ ዛሬንና ነገን ከከተማዋ ዕድገት፣ ሥልጣኔና የአነዋወር ዘይቤ ጋር አጣጥሞ የመሄድ ብልሃት ነው፡፡ የከተማዋ ጥንታዊነት የዛሬ ዕድገቷንና የነገ ተስፋዋን እንዳይገታው፤ የከተማዋ የዛሬ መስፋፋት፣ ዕድገትና ሥልጣኔ የትናንት አሻራዋን እንዳያጠፋው፤ የከተማዋ የትናንት ታሪክና የዛሬ ዘይቤም የነገውን ትውልድ ድርሻና ዕጣ ፋንታ እንዳያቀጭጨው - በሳል የሆነ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ይጠይቃል፡፡
የአንዲት ከተማ መልክዐ ጠባይ፣ ሕይወትና እሴት የሚገነባው ከዚህ መሰሉ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ነው፡፡ የከተማዋ ሕንጻዎች፣ መኖሪያዎች፣ መንገዶች፣ የሕዝብ ቦታዎች፣ ገበያዎች፣ የእምነት ቦታዎች፣ ማኅበራዊ ተቋማት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ ጽዳትና ውበት፣ ከዚህ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ይወለዳሉ፡፡ የሚፈቀዱና የሚከለከሉ ነገሮች ከዚህ ይመነጫሉ፤ የሚጠበቁና ለሕዝብ ክፍት የሚሆኑ ነገሮች ከዚህ ይመሠረታሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ቁልፍ ችግሯ ትናንት፣ ዛሬና ነገን የምታግባባበት የራስዋ የሆነ፣ በዘመናት የዳበረ፣ የተፈተነና ውጤታማነቱ የተመሰከረለት ‹ነቢብ፣ አመራርና አሠራር› ማጣት ይመስለኛል፡፡ በአንድ የውይይት መድረክ አንድ የከተማ ዐቅድ ባለሞያ እንደገለጡት ‹‹አዲስ አበባ እያንዳንዱ መንግሥት የየራሱን ርዕዮተ ዓለም ያነባበረባት ከተማ ናት - The layer of different Ideologies ፡፡ ያ ነው ከተማዋን ሲምታታባት እንዲኖር ያደረገው››
አዲስ አበባ አሁን ዐሥረኛውን የከተማ መሪ ዕቅድ እያዘጋጀች ነው፡፡ እነዚህ መሪ ዕቅዶች ምንም እንኳን ሳይንሳዊ አሠራርን የተከተሉ ሞያዊ ሥራዎች ቢሆኑም የሚዘወሩት ግን በየዘመናቱ ሀገሪቱ በምትመራባቸው ርእዮተ ዓለሞች ነው፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ አዲስ አበባ ‹ወጥ፣ ለዘመናት የዳበረ፣ የተፈተነና የተመሰከረለት የከተማ ዘይቤ› እንዳይኖራት አድርጓታል፡፡
ባለፈው መንግሥት ጊዜ የቁጠባ ቤቶች የአዲስ አበባ የቤቶች መልክዕ ሆኖ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ኮንዶሚኒየምና ሪል እስቴት የአዲስ አበባ የቤት መልክዕ ሆነዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከንቲባነት ለረዥም ዓመታት በማገልገል የሚታወቁት ከንቲባ ዘውዴ እንደሚሉት በአዲስ አበባ ቀበሌ ሲቋቋም ከ2500 – 4000 የሚደርስ ሕዝብ የሚይዝ አንዳች የጉርብትና ማዕከል ለመፍጠር ነበር፡፡ ጉርብትናን ዘመናዊ ለማድረግ፡፡ ‹ከተማ ማለት የጉርብትና ሥርዓት ነውና›፡፡ ርእዮተ ዓለሙ ሲቀየር ግን ቀበሌዎች የጉርብትና ማዕከላት መሆናቸው ቀርቶ የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ማዕከላት ሆኑ፡፡ ቀበሌ ማለትም የአብዮት ማራመጃ ማዕከል ሆነ፡፡ በሀገራችን መንግሥታት የሚቀያየሩት በመፍረስ በመሆኑ በመንግሥታት መካከል ርክክብ አልተደረገም፡፡
ይህንን መሰሉ በየጊዜው የሚለዋወጡ ነቢቦች፣ አመራሮችና አሠራሮች አንዳቸው ከሌላቸው ጋር ተግባብተው የሚመሠረቱ ባለመሆናቸው አዲስ አበባ ስትፈርስ ስትሠራ የምትኖር መሞከሪያ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል፡፡ እንኳንስ በተለያዩ መንግሥታት ርእዮተ ዓለሞች መካከል ቀርቶ በአንድ መንግሥት ዘመናት እንኳን ሲያፈርሱ ሲሠሩ መኖር እየተለመደ መጥቷል፡፡ ከሸራተን አካባቢ የተነሡ ነዋሪዎች ለድጋሚ ተነሺነት የተጋለጡት በዚህ ያልተግባባ አሠራር ጭምር ነው፡፡ አዳዲስ ቤቶች እንደገና ለመንገድና ለሌሎች ግንባታዎች ተብለው የተሠሩበት ሲሚንቶ ሳይደርቅ እንዲፈርሱ የሚደረጉት በዚህ ወጥነት በሌለው የከተማዋ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር የተነሣ ነው፡፡ በተሠሩ በጥቂት ዓመታት ለባቡር ተብለው የፈረሱትንና 900 ሚሊዮን ብር የፈጁትን የአዲስ አበባ መንገዶችን በዚህ በበሰለ ነቢብ፣ አመራርና አሠራር ብቻ ነበር ማትረፍ ይቻል የነበረው፡፡ አንድም ቀድሞ በማሰብ፣ አለያም አጣጥሞ በመሥራት፡፡ 

አዲስ አበባ ዕድገቷንና ታሪኳን የማጣጣም ፈተና ገጥሟታል፡፡ ለመሆኑ ያለፉ ነገሮቿን ሁሉ እንዳሉ ይዛ መቀጠል አለባት? ያለፉ ነገሮቿንስ ሙሉ በሙሉ አፈራርሳስ መቀጠል አለባት? ለመሆኑ ታሪክና ዕድገት፣ ቅርስና ሥልጣኔ እንዴት ነው የሚጣጣሙት? ከተማዋ እነዚህን በትክክል ካልመለሰች ከተማ ሳይሆን ዘመናዊ የሰው ልጅ ማጎሪያ ትሆናለች፡፡ ዛሬ የሚሠሩት ታላላቅ ግንባታዎቻችንስ የነገውን ትውልድ ሥልጣኔ፣ አነዋወርና ፍልስፍና ከግምት ውስጥ እያስገቡ ናቸው? የዛሬ አምስት ዓመት የገነባናቸውንና ስናስመርቃቸው ጉሮ ወሸባ ያረገድንባቸውን እንዲህ በፍጥነት የምናፈርስ ከሆነ ሌሎቹን እንድንጠራጠር ያደርገናል፡፡
አሁን አሁን አዲስ አበባ ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገ የሚያጣጥም ነቢብ፣ አመራርና አሠራር በማጠቷ ምክንያት የአዲስ አበባ ከተማን ጥንታዊነት የሚያሳዩ ቅርሶች እንደ ነፍጠኛና ፊውዳል መገለጫዎች እየተቆጠሩ፣ ቀጥታና ቀጥታ ያልሆነ ሞት እየተፈረደባቸው ነው፡፡ ቀጥተኛ የሆነ ሞት የሚባለው ለዕድገት ፀር፣ለግንባታ ዕንቅፋት፣ ለመስፋፋት እንከን አድርጎ በማየት የማፍረስ ርምጃ መውሰድ ነው፡፡ በዚህ ፍርድ ምክንያት ጥንታውያን መንደሮች፣ ቤቶች፣ ድልድዮች፣ ሐውልቶች፣ አደባባዮች፣ የንግድ ማዕከላት፣ እንዲፈርሱ ተደርገዋል፡፡
ሁለተኛውና ቀጥታ ያልሆነ ሞት የምንለው ደግሞ እነዚህን ጥንታውያን ሀብቶች የመከባከብ ኃላፊነት ያለበት አካል ክብካቤ በመንፈግና ቀስ በቀስ እንዲፈርሱ ሆን ብሎ በመተው የሚደረግ ግድያ ነው፡፡ ይህ ፍርድ የተፈረደባቸው ቅርሶች በአካባቢያቸው ለእነርሱ ሕልውና አሥጊ የሆነ ሥራ ሲከናወን የሚያስጥላቸው የለም፤ የቆሻሻ መጣያ ሲሆኑ በዝምታ ይታለፋሉ፤ ሲፈርሱና ሲበላሹ በዝምታ ይታያሉ፤ ሲዘረፉና ሲወሰዱ የሚያስጥል አያገኙም፤ ጥበቃ አይደረግላቸውም፤ ሞያ በሌላቸው አካላት እንዲጠገኑ ይደረጋል፤ ታጥረውና ተከልለው እንዲቀመጡ ይደረጋል፤ በውስጡ ነዋሪዎች ሲቀመጡባቸውና ግንባታ ሲያከናውኑባቸው ተከታታይ አይኖርም፤ በጢስና እሳት እንዲበላሹ ይተዋሉ፡፡
በአንድ በኩል ያለፈው ነገር ሁሉ መነካት የለበትም የሚሉ የታሪክና ቅርስ ወግ አጥባቂዎች (ወግ አጥባቂነት አዎንታዊ ነው) አሉ፡፡ እንደ እነርሱ ከሆነ የአዲስ አበባ ነባር ነገሮች ሁሉ ተጠብቀውና ተከብረው መኖር አለባቸው፡፡ እነርሱ የከተማዋን፣ ብሎም የሀገሪቱን ጥንት የሚመሰክሩ ናቸውና፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በቦታው ላይ የሚሠራ ሌላ ነገር እስካለ ድረስ የጥንቱ መፍረስ አለበት፡፡ የጥንቱ ጥንት አገልግሏል፡፡ አሁን ዘመኑ የዛሬ ነው፡፡ ጥንቱ ለዛሬ ዕንቅፋት ከሆነ ያለው ዕድል መፍረስ ብቻ ነው ይላሉ፡፡
እነዚህ ሁለቱም ለእኔ ጽንፎች ናቸው፡፡ ሁሉም የጥንት ነገር እንዳለ ሊቀመጥ አይችልም፡፡ በሦስት ምክንያት፡፡ አንድ ሁሉም የጥንት ነገሮች እኩል የሆነ ታሪካዊ፣ ቅርሳዊና ባሕላዊ ዋጋ የላቸውም፤ ሁለተኛ ደግሞ ሁሉም የጥንት ነገሮች ይቀመጡ ካልን ለአዳዲስ ነገሮች ቦታ ላይገኝ ይችላል፤ በመጨረሻም ሁሉንም የጥንት ነገሮች ለማቆየት፣ ለመጠበቅና ለመከባከብ ዐቅም ያስፈልጋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ለአዳዲስና ለዘመናዊ ነገሮችና ሐሳቦች ሲባል ሁሉንም የጥንት ነገሮችን በግዴለሽነት ማፈራረስ ሦስት ጉዳቶች ያስከትላል፡፡ የሰው ልጅን የጥበብ፣ የባሕል፣ የሥልጣኔና የክሂሎት አሻራ ያጠፋል፤ አንድን ነገር ምንጊዜም እንደገና እንድንጀምረው በማድረግ ተያያዥና ተደጋጋፊ ነገርን ያሳጣል፤ በመጨረሻም የከተማዋን የቱሪዝም ገቢ ያመክናል፡፡ 

እነዚህን ሁለት ጽንፎች ለማስታረቅ የሁለቱንም አዎንታዊነት የያዘ አንድ ሌላ መንገድ ያስፈልጋል፡፡ እርሱም አዳዲስ ነገሮችን ከጥንታውያን፣ ዘመናዊነትን ከነባርነት፣ ታሪክን ከዕድገት፣ ቅርስን ከሥልጣኔ ጋር አስማምቶ፣ አደጋግፎና አመጋግቦ መምራት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ወጥነት ያለው፣ በየዘመናቱ የሚዳብር በሳል ሀገራዊ ፍልስፍና ያስፈልጋል፡፡
ይህንን መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉት አካሄዶች ያስፈልጋሉ
 1. የከተማዋን ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች የመለያ መመዘኛ ማስቀመጥ
 2. በመመዘኛው መሠረት የከተማዋን ታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች በዝርዝር መለየት
 3. እነዚህ የከተማዋ ቅርሶች በልዩ ልዩ መንገድ ለትውልድ የሚተላለፉበትን መሥፈርት ማውጣት
  • እንዳሉ ባሉበት ሁኔታ ለሌላ አገልግሎት ሳይውሉ ለትውልድ መተላለፍ ያለባቸው
  • መጠናቸው ተቀንሶ ናሙናቸው መተላለፍ ያለባቸው( ለምሳሌ አንድን መንደር ሙሉውን ቅርስ አድርጎ ማቆየት ከባድ ቢሆን እንኳን ያ መንደር ምን ይመስል እንደነበር የሚያሳይ አንድ ናሙና ቦታ ለይቶ ማቆየት ይቻላል)
  • በልዩ ልዩ የመቀረሻ መሣሪያዎች(ፎቶ፣ ሥዕል፣ ቪዲዮ፣ ወዘተ) ተመዝግበው መተላለፍ ያለባቸው(አንዳንድ ሠፈሮች የቀድሞ መልካቸውና አሠራራቸው በልዩ ልዩ መቀረሻ መንገዶች ቀርጸ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል)
  • ወደ ሙዝየም ገብተው መተላለፍ ያለባቸው
  • ቅርስነታቸውንና ይዞታቸውን በማይጎዳ መንገድ ለሌላ የማይጣረስ አገልግሎት ተላልፈው ግን ተጠብቀው መተላለፍ ያለባቸው(ጣይቱ ሆቴል እንደተደረገው)
  • ቦታቸውን ቀይረው በቅርስነት መጠበቅ ያለባቸው
 4. ማናቸውም ከተማዊ እንቅስቃሴዎች ከእነዚህ የተመዘገቡ ቅርሶች ጋር ያላቸውን ተግባቦት በቅርብ መከታተል፣ ለክትትሉም እንዲያመች የሚመለከተው አካል ከማናቸውም ግንባታ በፊት አካባቢው ከቅርስ ነጻ መሆኑን ምስክርነት እንዲሰጥ ማድረግ
 5. የከተማዋ መሪ ዕቅድ ሲዘጋጅም እነዚህን ታሪካዊ ቦታዎችና ቅርሶችን በሚገባ የለየና የእነርሱን የሕልውና መብት የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ
 6. በታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች አካባቢ ይፋዊ መለያ መለጠፍ፤ ይህ ምልክት የተለየ ቀለም ወይም ዐርማ እንዲኖረው በማድረግ ማንኛውም ሰው እንዲለየው ማስቻል
 7. የፌዴራል ቅርስ አዋጅ ቁጥር 209/92 ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች ምንም ዓይነት ሥልጣን ስለማይሰጥ ይህንን ማስተካከል
 8. የታሪካዊና ባሕላዊ ቅርሶች አካባቢዎች የተዛማጅ ልማቶች ማዕከል (የሆቴል፣ የጥበበ ዕድ መሸጫ፣  የዐውደ ርእይ ማሳያ፣ የባሕላዊ ገበያዎች) መጠቀም
 9. በተማሪዎች፣ በአካባቢው ነዋሪዎችና በቱሪስቶች እንዲጎበኙ መርሐ ግብሮችን ማመቻቸት
እነዚህንና የመሰሉትን ተግባራት በጊዜ ማከናወን ካልቻልን አዲስ አበባ ‹ትናንት የሌላት ከተማ› ትሆናለች፡፡ ያውም በታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን ሳያስቡ የሚሠሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ስላሏት ብቻ፡፡ ከተማ እንደ ፈጣን ምግብ(fast food) ለዕለት ሆድ መሙያ የምትሠራ አይደለችም፡፡ እንደ ገጠር ጠላ ለነገም ጭምር የምትጠነሰስ ናት፡፡ ከተማዋን ለሰዎች መኖሪያነት ምቹና ተመራጭ ለማድረግ መንገድ፣ ሆቴል፣ ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ፣ ባቡር፣ ሱፐር ማርኬት፣ የገበያ ማዕከል፣ የግል ኮሌጅ፣ ዓለም ዐቀፍ ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብቻቸውን በቂ አይደሉም፡፡ ጥንታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባሕላዊ፣ መንፈሳዊና ሞራላዊ እሴቶች፣ ቅርሶችና ቦታዎችም ያስፈልጓታል፡፡ እነዚህ ራሳቸው ነገ ታሪክና ቅርስ ስለሚሆኑ፡፡ ከተማ እንደ ላም ዱካ የሚተው እንጂ እንደ አዞ በጅራታቸው ዱካ የሚያጠፉ አመራሮች አያስፈልጓትም፡፡

 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው


35 comments:

 1. ትናት እና ዛሬ የሌላቸው የነገ መሪዎች……
  የሚገረመው ኢትዮጵያ በኡሁኑ ሰዓት በየቢሮው የሚመሩንና የምንመራ የህዝብ አገልጋዮች ተብሎ ታርጋ የተለጠፈልን በየትኛውም ደረጃ ያለን ያልተማርን ሙህሮች በእውነት ሀገራችንን እናውቃለን ወይ ብየ ሳስብ በጣም እጨነቃለሁ….. በየቢሮው ብዙ ልምድ ያላቸው ሰዎች መሪ እቅድ በሚዘጋጅበት ወቅት ታሳቢ ስጋቶችን በደንብ እንድናስተውል ቢነግሩንም ይባስ ብለን ለለውጥ ዝግጁ ያልሆነ አደናቃፊዎች የሚል ቅጥል ስም ሰጥተናቸው ይኸው እንደምናየው የማናውቀውን ነገር እናቦካለን…. የሚገርመው እኮ እኛ ጭራሽ እያብን ያለነው ስለ ታሪክ በጣም ደረጃችንን ከፍ ስላደረክልን ዲያቆን እናመሰግናለን… ግን እኮ እኛ ያለንበት ደረጃ አይደለም ታሪክ አንድ ሃለፊ ሲቀየር ለሱ የሚለውን ባለሙያ ይዞ ይመጣ እና አይደለም የድሮ የአባቶቻችንን የአምናውን የምግስት እቅድ ማሰቀጠል አቅቶን በየመድረኩ ከመለፍለፍ ያለፈ የሚሰራው ሥራ ምንም ግንኚነት የለውም እኔ ባለኝ ተሞክሮ የማውቀው በቴሌቪዥንና በብሮሸር እንዲሁም በየደረጀው በሚዘጋጀው ጉበኤ የአቋም መግለጫ ስናዘጋ ብቻ ነው ተመሳሳይ ነገር የምንሰመው እንጂ ስንሰራ ከቀበሌ ቀበሌም እምንተዋወቅ አይመስለኝም…. ለማንኛውም አሁን ነገሮችን ዝም ብየ ሳስበው ሁሉ ነገራችን ትናትንና ዛሬን እንዲሁ በጭፍን ወይ ማድነቅ ወይ መጥላት ካሆነ ለማወቅ ሲጠይቅ፣ ሲያነብ፣ሲመራመር፣ ምክንያታ በሆነ መንገድ የምንራመድ ቢሆን እንዲህ እንደ ካሮት ቁልቁል እንወርድ ነበር…… እኔ በራሴ ማፈርና አላወቂነቴ ምን ያክል ገደብ እንዳጣ ሳስብ አዝናለሁ ደግሞ ጓድኞችን ስመለከት ማዘኔ የበለጠ ያደጋል ምክንያቱም አባቶቻችን በተግባር ያስቀመጡልን ትናንት እና ከእጃችን ላይ ያለው ዛሬን ሙሉ ለሙሉ ወደ ጎን ትተን ነገን ናፋቂዎች ባለዕራይ ትልዶች (የራዕይን ትርጉም እንኳን በአግባቡ የማንረዳ) ተስማምተን በፉከራ መሆናችን ዋጋ ያስከፍለናል በእውነት ሁላችንም እስኪ እራሳችንን እንፈትሽ……

  ReplyDelete
 2. "ሳያስቡ የሚሰሩ አመራሮች" ያልከው ምንም ጥያቄ የሌለው ሀቅ፤ "ሳያስቡ የሚኖሩ ነዋሪዎች" በሚለው ግን ፈጽሞ አልስማማም፡፡ ብናስብስ በነጻነት እና በተነሳሽነት መንቀሳቀስ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ? የሀሳባችንን ዋጋ ማግኘት ባንችልም መገመት እንችላለን፤ በየታክሲው፣ በየፌርማታው እና በሌላውም ቦታ የአዲስአበባን ነዋሪ የጽዳት፣ የአስተዳደር፣ የታሪክ ተቆርቋሪነትና ወዘተ አስተሳሰብ በየቀኑ ማዳመጥ ይቻላል፡፡ ምን ዋጋ አለው፤ አዳምጦ የሚያበረታታና ለተግባሩ የሚያግዝ መሪ የለም፤ እውነተኛዎቹ መሪዎቹ በጉልበት ተከታይ ሆነዋል፡፡ ሀሳብ ደግሞ ወደ ተግባር ካልተለወጠ እንዳልታሰበ ይቆጠራል፡፡ አሁን መራጭ እኛ ብንሆንና በትንሹ አንተን ከንቲባ ብናረግ ስንት ለውጥ እናይ እና እናሳይ ነበር፤ ቀልዴን አይደለም፤ በእውነት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank yoy Dessi, this is great idea. Dani if you particiapte for next election I will spend my money and time. Please think about it , we need someone participate with full of knowledge and fear of God. I hope you will not carless about our message.

   Delete
 3. Dani I feel you live out side Ethiopia. At this time more than 4 million people don't have food, drink, house and electricity so why you care about old house or building. As you know that in Addis Ababa most young people didn't married becuse of house. I am not sure how you feel but I feel i don't care about the past and I want see our brother and sister get merried and have house or condominiyem house. I don't mean your idea is wrong but that is not more important than Ethiopian people. God bless me and you. Amen.

  ReplyDelete
  Replies
  1. With all due respect, my friend, your thoughts are shallow. Why is it wrong to suggest that Addis has to respect its past? You don’t need to forget the urge to solve the social problems while you think about preserving the city’s historical treasures. They can be addressed in parallel. Furthermore, I’m disappointed by your feelings towards Daniel, which he “lives outside Ethiopia,” for I suspect you’re not a regular reader to his blog. Isn’t there a time that Daniel has reflected on the social problems of the city and the nation as a whole? As an example, I recommend you to read his three-part article titled “ይድረስ ለቅድስት ድንግል ማርያም,” where he bluntly addressed the housing problem and other related issues. Please my friend, don’t rush to judge! And don’t forget: things have their own perspectives, at which they can be analyzed and commented upon, and that’s exactly what Daniel’s doing.

   Delete
  2. Amazing!!! It is irritating to hear from people being strident to history... Many are striving to annihilate the honorable history of our fathers that surprises the whole world... How come? Are you swimming in the ocean of ignorance and slumbering at this critical time when the world is rushing to know much about its respective history? Many foreigners are going to witness others' history because they don't have any. But, unfortunately, people like you are doing the reverse!!! Why are you too phobic about the deeds of our fathers? Shame on you!!! Guys, let's be rational because this world demands us to be so!!! WE ARE NO MORE PRIMORDIAL SOCIETY!!!

   Delete
  3. ከተማ እንደ ፈጣን ምግብ(fast food) ለዕለት ሆድ መሙያ የምትሠራ አይደለችም፡፡ እንደ ገጠር ጠላ ለነገም ጭምር የምትጠነሰስ ናት፡፡ አሁን ግን ከFast food የፈጠነ ነገር ካለ ለከተማዋ ቢጠቀስላት ይሻል ነበር እርሾ ድሮ ቀረ

   Delete
  4. I think I support the first Anonymous idea. Some of you may have rich family or good income so it is so difficult to understand the low income people. I am 46 years old and I have two sisters. All of us don’t married yet because of financial problem and the house market is too expensive for us to buy or to rent. The Anonymous person may struggle to get his/her personal needed so he/she wrote the fact. In addition that he/she mentioned Danial idea is not bad but it is not important than human being. As we all know that most Ethiopian people include me are poor so we need immediately help to solve our problem. I know this government destroyed some important historical house and printing station to build condominium house and more than 100,000 people benefited from this plan. It doesn’t mean this government doesn’t care about the city historical place but human being is firs than building.

   Delete
  5. “She doesn’t has to eat but she wish to wear expensive cloth” all European counties are provided all the basic necessity for their people so they focus on to keep nature and history. Our people don’t have basic necessity but we want be equal to them. Be yourself not other. Thank you the first Anonymous person. Don’t be Amhara try to be Gurage.

   Delete
  6. The history of a nation, a country, or a town is more than your personal problem or marriage interest friends. The first reply-er told you the fact what Daniel is doing. Do you expect Daniel to always write on a single issue? Shame on you!

   Delete
  7. I’m writing this reply to the comments of March 31. You both have failed to understand things and situations in perspective, that development and prosperity can be achieved in line with preserving history and treasure. The first Anonymous have suggested that some of “us” have rich family or good income, so we cannot understand the low-income people. I don’t believe people need to be poor to understand problems of the poor. We’re born and raised in this country; we have witnessed the blessings and curses of this land together. Some people may be ignorant for the misery of the poor, but most of us can understand what’s actually going on around us. So it is not an issue of not understanding the problem of the poor, it is rather an issue of making the city a meeting place for both the past and the present. As for the second anonymous, you’ve cited that European countries have provided the peoples’ needs so that they were able to focus on preserving their history. Partly right, but you’ve missed out the fact that those countries have also endured poverty for a while. Their cities have been destroyed by wars, but they’ve paid an enormous price to preserve their past. London, Paris, Berlin, Vienna, Rome, etc, have been the victims of the destruction caused by the Second World War, and yet, they are still centers of rich history. The people could have stolen the treasures and sell them to buy bread, but they didn’t. Because they knew the values of those treasures and kept them safe at the expense of their physical and material needs. Another fault that you’ve committed is trying to look things from the point of view of ethnicity. From your comment, I can confidently say that you don’t know the Gurage people. Being hard workers didn’t make the Gurage lose their respect for their culture and history. No rich Gurage person don’t bulldoze an old ‘Gojo’ and build a villa, you should know this before you label the Amhara “poor” and the Gurage “rich.” Please understand that development does not mean destroying the treasure, it is rather “keeping the past, and building the present!”

   Delete
 4. They make Ethiopia to have only 23 years history,they don't care about the past.

  ReplyDelete
 5. ከተማ እንደ ላም ዱካ የሚተው እንጂ እንደ አዞ በጅራታቸው ዱካ የሚያጠፉ አመራሮች አያስፈልጓትም፡፡

  ReplyDelete
 6. ከተማ እንደ ፈጣን ምግብ(fast food) ለዕለት ሆድ መሙያ የምትሠራ አይደለችም፡፡ እንደ ገጠር ጠላ ለነገም ጭምር የምትጠነሰስ ናት፡፡

  ReplyDelete
 7. በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው:: በአንድ ግዜ "የቅርስ ጥበቃ ባላደራ ቦርድ" የሚባል ድርጅት ነበር:: አሁንስ አለ ወይ? ስራውን በሚገባ እንዲቀጥል ምን እናግዝ?

  ReplyDelete
 8. It is an interesting article. However, those who are in the offices do not about the and are doing this intentionally. so the article will not adress the right audience. Bado hodachenen yebas blo chequrachenen kemelat wuch fayeda yelewum, wuwuwu....

  ReplyDelete
 9. This is the point ‘ከተማ እንደ ፈጣን ምግብ(fast food) ለዕለት ሆድ መሙያ የምትሠራ አይደለችም፡፡ እንደ ገጠር ጠላ ለነገም ጭምር የምትጠነሰስ ናት፡፡’ እግዚአብሔር ይባርክህ ወንድሜ!!!
  SG Dallas TX

  ReplyDelete
  Replies
  1. I know most of you guy's get mad because the current goverment doing best of the best job in Ethiopia histroy so you want obstacle for our progress. We are the poorest country in the world so we need food, cloth and house. This goverment work day and night to satsfied an Ethiopian people.

   Delete
  2. Your r z poorest mind in z world! Z gov't is doing bad in all respect, electricity, telephone, water, and soon. The price of food and House rent have risen is keeping increasing. Is it doing this to satisfy us. U can't understand, cause u r blind one of them.

   Delete
  3. To the Anonymous of March 31: Getting out of poverty doesn't need to destroy the city's treasure, and urging the administration to keep the city's treasure is not posing obstacles to development. It's just "showing the right way" to develop the city in line with preserving its history.

   Delete
 10. To those who oppose Danie's Idea " please read the Article again and try to understand the point. If you can not understand the point please ask to those who can understand well"

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ጌታየ ዘላሊበላApril 3, 2014 at 11:29 AM

  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ
  ትላንት አልባ ከተማዋ ብቻ ሳይሆን ትላንት አልባዎቹ ከተሞች ቢባልስ?

  ይኽንን መነሻ ያረግኩት ሰሞኑን ጎንደር ከተማ ነበርኩ ከተማዋ በፍጥነት እየተለወጡ ካሉት ከተሞች አንዷ መሆ•ን ያየ ምስክር ነው፡፡ በከተማዋ ሁለገብ ሕንጻዎች፣ ሆቴሎች፣ ት/ቤቶች፣ ሆስፒታል፣ ዩንቨርስቲ ይሠራል በጣም የሚገርመው ሁሉም ባይሆኑም ውስኖቹ ከጎንደር ታሪካዊ ሒደት ጋር የተቆራኙ ናቸው ይበል ያሰኛል፡፡ ቢሆንም ሌሎቹ ግን ያለታሪክ አሻራ ዘመናዊ ሕንጻ ብቻ ይገነባሉ ይህ ትላንት አልባ ከተማ እንዳትባል የሚሠሩ ባለሀባቶችም ይሁኑ ተkማት ቢያስቡበትና ከሌሎቹ መማር ቢችሉ፡፡

  በሌላ በኩል ከጥንታውያን ከተሞች መካከል አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጎንደር፣ ሐረር ወዘተ ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገነቡ ሕንጻዎች የትላንት ማንነታውን ሊገልጹ የሚችሉ፣ ታካዊነታቸውን የሚያስጠብቁ፣ ወደ ፊት እንደ ቅርሶቹ ሊጎበኙ የሚችሉ፣ ከታወቁ አርክቴክቶች ምክር በመውሰድና በመመካከር ቢሆን ቀጣዩ ትውልድ ትላንትን ዛሬ ማየት ይችላል፣ ስለ ትናንት ዛሬና ነገ መናገር ይችላል፡፡ ስለዚህ ሕንጻዎች፣ ሆቴሎች ሲሰሩ ትላንትን ቢጠብቁ መልካም ነው ብየ አምናለሁ፡፡
  ለምሳሌ ቅዱስ ላበላ ከተማ የምትታወቀው ቅ/ላሊበላ ባነፀው አስገራቢ አብያተክርስቲያና ነው፡፡ ከተማዋ ማደግ አለባት፣ መልማት አለባት ሆቴሎች፣ ሕንጻዎች፣ ተkማት፣ ት/ቤቶች ወዘተ መሠራ አለባቸው ጥርጥር የለውም ይሠሩ፡፡ ነገር ግን ትልንትን የጠበቁ፣ ከታሪኩ ያልወጡ፣ ከትውፊቱ ያላፈነገጡ አስተማሪ፣ ዘወትር የማይሠለቹ ቢሆኑ ይበልጥ ለእድገታችን፣ ለቱሪዝም ሀብ እድገት ወሳኝ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ አንድ ወቅት አንድ የውጭ ሀገር ጎብኝ ላበላን አይቶ ይህ ሕንፃ እኮ አውሮፓና አሜሪካ የሰለቸን፣ ስመረረን ነው ስለዚህ እባካችሁ ልክ እንደአባታችሁ ላሊበላ ነገን ተሻጋሪ ሕንጻ ሥሩ ሲል አስታውሳለሁ፡፡
  ከእርሱ የተማርኩት ትላንት አልባ አታድርጓት ታላቅ ንጉሥ፣ መሪ፣ አስተዳዳሪ ነበራት ማለቱ ነው ስለዚህ በታክ ተወቃሽ እንዳንሆን ትላንት ያላቸው ከተሞችን መሥራት እንማር፡፡

  ReplyDelete
 12. አዲስ አበባ ዕድገቷንና ታሪኳን የማጣጣም ፈተና ገጥሟታል፡፡ ለመሆኑ ያለፉ ነገሮቿን ሁሉ እንዳሉ ይዛ መቀጠል አለባት? ያለፉ ነገሮቿንስ ሙሉ በሙሉ አፈራርሳስ መቀጠል አለባት? ለመሆኑ ታሪክና ዕድገት፣ ቅርስና ሥልጣኔ እንዴት ነው የሚጣጣሙት? ከተማዋ እነዚህን በትክክል ካልመለሰች ከተማ ሳይሆን ዘመናዊ የሰው ልጅ ማጎሪያ ትሆናለች፡፡ ዛሬ የሚሠሩት ታላላቅ ግንባታዎቻችንስ የነገውን ትውልድ ሥልጣኔ፣ አነዋወርና ፍልስፍና ከግምት ውስጥ እያስገቡ ናቸው? የዛሬ አምስት ዓመት የገነባናቸውንና ስናስመርቃቸው ጉሮ ወሸባ ያረገድንባቸውን እንዲህ በፍጥነት የምናፈርስ ከሆነ ሌሎቹን እንድንጠራጠር ያደርገናል፡፡

  ReplyDelete
 13. respect for every suggestion. coz its the matter of philosophical difference n have a function in its world view

  ReplyDelete
 14. ዳኔየ እንካን ደህና መጣሕ

  ReplyDelete
 15. Your r z poorest mind in z world! Z gov't is doing bad in all respect, electricity, telephone, water, and soon. The price of food and House rent have risen is keeping increasing. Is it doing this to satisfy us. U can't understand, cause u r blind one of them.

  ReplyDelete
 16. ሲመስለኝ መንግስቶቻችን የታሪክ ሽሚያ ላይ ስላሉ የራሳቸውን አሻራ ጥለው ለመሄድ እንጂ ስላለፈው የከተማዋ ታሪክ እና የአገነባብ ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ ሚያሳስባቸው አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete