Tuesday, March 18, 2014

ባቡር - የሐበሻ መድኃኒት

በተለምዶ ሲኤም ሲ በሚባለው ሰፈር፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ሥር ካለው ክልል ወደ የካ ከተማ ክልል ለባቡር የተሠራውን መንገድ እንደ ጦጣ እየዘለልኩ በማቋረጥ ላይ ነበርኩ፡፡ ከእኔ ፊት ፊት ሁለት ሽማግሌዎች በምርኩዛቸው እየተረዱ እንደ ሽሪ ሚሪ የተከረተፈውን የባቡር መንገድ በጥንቃቄ ይሻገራሉ፡፡ ሽሪ ሚሪውን ተሻግረው የተነጠፈው ሐዲድ ላይ ሲደርሱ ልባቸው መለስ አለላቸው መሰል የአኩስም ጋቢ የመሰለ ፀጉር የለበሱት አንደኛው ሽማግሌ ‹‹እንዴው በቃ ይህንን ባቡር የሐበሻ መድኃኒት አደረጉት ማለት ነው?›› ብለው ጓደኛቸውን ጠየቁ፡፡
‹‹እንዴት እንዴት በል?›› አሉ ሪዛቸው እንደ ዝቋላ ጥድ ወደታች የወረደላቸው ሌላው አረጋዊ፣ በከዘራቸው የባቡሩን ሐዲድ ነካ ነካ እያደረጉ፡፡

‹‹ቆይ ይኼ ባቡር ምንድን ነው የሚመስለው? ባቡሩ ሲያልቅስ ይኼ መንደራችን ምን ይመስላል? መሳፈሪያው እንዴት ነው? በዚህ በመገናኛስ በዋሻ ያልፋል የሚባለው እንዴት እንዴት ሆኖ ነው? እንዴት የሁላችንን ሕይወት ዋጋ ያስከፈለ፤ ስንት ቤቶችን ያስነሣ፣ ስንት ሠራተኞችን ያስረፈደ፣ ስንት ሚሊዮን ብር የፈጀ፣ ለሀገራችንም እንግዳ የሆነ ነገር ሲሠራ፣ እንዴት አንድ ቦታ እንኳን ሥዕሉ አይለጠፍም? ቆይ ይህንን ሁሉ መሥዋዕትነት ከፍለን፣ ጠዋት አርፍደን፣ ማታ ተሠልፈን፣ የሃያ ሁለትና የዑራኤል ሆቴሎች ቀዝቅዘው፣ እኛም መሻገሪያ አጥተን በስተርጅና እንደ ጉሬዛ እየዘለልን የሚሠራው ባቡር ምንድን ነው የሚመስለው? ለመሆኑ ታውቃለህ?››
‹‹ይኼው የሀብታሙ ሁሉ ሕንጻ ሲሠራ ከፊት ለፊቱ ሥዕሉ በትልቁ ይሰቀል የለም እንዴ? እኛም ዐቅምና ዕድል ኖሮን ባንሠራም ቆመን ሥዕሉን አይተን እናደንቃለን፡፡ ሕንጻው ሲያልቅ ሠፈሩ ምን እንደሚመስልም እንገምታለን፤ እንደ ሽምግልናችንም ‹አልቆ ለማየት ያብቃን› ብለን እንመርቃለን፡፡ የከተማው ባቡርማ ለምርቃትም ለጸሎትም አስቸጋሪ ሆነኮ፡፡ እኛ የከተማ ባቡር አይተን አናውቅ፣ ምናለ በየሠፈሩ ሥዕሉን ቢለጥፉልን፤ ብናደንቅ፣ ሠሪዎችንም ብንመርቅ፣ እንዲያስፈጽመውም ብንጸልይ፡፡››
ሽማግሌዎቹ የባቡሩን መንገድ አቋርጠው ወደ ሲ ኤም ሲ ሚካኤል አቅጣጫ ተጓዙ፡፡ መንገዴን ትቼ ወጋቸውን ሽቼ ተከተልኳቸው፡፡
‹‹አይህ ወዳጄ እነዚህ የሃይማኖት ሰዎች ‹መንግሥተ ሰማያት ይህንን ትመስላለች› የሚሉትኮ ያለምክንያት እንዳይመስልህ፡፡ የሚደርስብህን ሁሉ መከራ የምትቋቋመው የምታገኘውን አስረግጠህ ካወቅከው ብቻ ነው ብለው ነው፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ይስሉብህና ‹ለዚህች ልዩ ሀገር ስትል ዋጋ ክፈል፣ መከራውን በጸጋ ተቀበል፤ እስከ ጊዜው ነው ቻለው› ይሉሃል፡፡ ምነው እነዚህ ባቡር የሚሠሩ ሰዎች ከእነርሱ ቢማሩ፡፡ ለመሆኑ ይኼ ሁሉ ጉድጓድ ተቆፍሮ፣ መንገድ ተከልክሎ፣ ሠፈር ፈርሶ፣ ሐውልት ተነቅሎ፣ ማቋረጫ ጠፍቶ፣ መንገድ ተዘጋግቶ፣ ንግዱ ተቀዛቅዞ የምናገኘው ነገር ምንድን ነው? ምን ይመስላል? አሁን እኛ መሥዋዕትነት እየተቀበልን ያለነው ምን ለማግኘት ነው? ማንም አያውቅም፡፡ ምነው ግን ይህንን ባቡር የሐበሻ መድኃኒት አደረጉትሳ››
‹‹እኔም ሁልጊዜ የሚገርመኝ እርሱ ነው፡፡ መገናኛ ሄድኩ፣ ዑራኤል ሄድኩ፣ መስቀል አደባባይ ሄድኩ፣ ሜክሲኮ ሄድኩ፣ በቀደምም መርካቶ ሄድኩ፤ ሕዝቡ የመሰለውን ብቻ ነው የሚያወራው፡፡ አንዱ ኤሌክትሪኩ ከላይ ነው ይላል፣ ሌላው መሬት ውስጥ ተቀብሯል ይላል፤ አንዱ ማውረጃው ከላይ ነው ይላል፣ ሌላው መሬት ውስጥ ነው ይላል፤ አንዱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት አይመለስም፣ ቦታ የለውም ይላል፤ ሌላው ይመለሳል፣ ግን ከድሮው ሬዲዮ ጣቢያ አጠገብ ይተከላል ይላል፡፡ ይህንን ሁሉ ምን አመጣው? አንተ እንዳልከው የሐበሻ መድኃኒት ይመስል ምሥጢር ስላደረጉት ነው፡፡ እንጂማ ሲሆን እኛ ሽግሌዎቹም እንድናይ ከፍ ከፍ አድርገው፣ ካልሆነም ባቅም ባቅሙ ሥዕሉን መለጠፍ ነበረባቸው፡፡››
አሁን ሽማግሌዎቹ ወደ ሲኤም ሲ ሚካኤል እየገቡ ነው፡፡ ባርኔጣቸውን ሊያወልቁና እጅ ሊነሡ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡
‹‹በቀደም አያ ተሰማ ምን አለኝ መሰለህ››
‹‹ምን አለህ ደግሞ፤ መቼም እርሱ ወግ አያልቅበትም፡፡››
‹‹የካና ቦሌ አሁን ነው ትክክለኛ ድንበር ያገኙት፡፡ ይኼው የባቡሩ መንገድ የማያገናኝ ድንበር አበጅቶላቸዋል፡፡ ካሁን በኋላ የምንገናኘው በሞባይል ብቻ ነው፡፡ ከመንገድ ማዶና ማዶ ሆነህ በስልክ እያወራህ በእጅ ሰላምታ መለዋወጥ ብቻ ነው›› አለኝ፡፡
‹‹እንዴ መሻገሪያ አያደርጉልንም እንዴ? እኛ ወዲያ ተሻግረን ሚካኤልን ላንሳለም፣ ሙስሊሞችም ወዲህ መጥተው ላይሰግዱ ነው ማለት ነው? ይህማ ደግ አይደለም››
‹‹ቢለጥፉትኮ ይኼ ጥያቄ ይመለስልን ነበር፡፡ ግን የሐበሻ መድኃኒት ነው፡፡ ያውም የወፍ መድኃኒት፡፡ ፌርማታው የት ጋ ነው? መንገዱንስ እንዴት አቋርጠን ነው የምንሳፈረው? ሰው ዘሎ ቢገባስ? እንዴው ተጨነቁ ብሎን የሚመስለንን ስንገምት እንውላለን፡፡ ቤት ስትሠራ እንኳን መሐንዲሱ የቤቱን መልክ በወረቀት ስሎ ይሰጥሃል፤ አንተም አይተህ ደስ ሲልህ ይህንንስ ወገቤን አሥሬ እሠራዋለሁ ትላለህ፤ ሰው ዛሬ ወደፊት የሚቀበርበትን ቦታ እንኳን ለማወቅ ፈልጎ በቁሙ መቃብር ያሠራል፤ ልብስ ሰፊ እንኳን ዋናው ልብስ እስኪደርስ በቾክ ጨርቁ ላይ ስሎየልብሱን መልክ ያሳይሃል፤ ደጋሽም ድግሱ እስኪደርስ ቅምሻ ብሎ ይጠራሃል፤ የሞሰቡን እንጀራም በእንጎቻው ትገምተዋለህ፤ ባቡሩን ግን እንዴት እንገምተው? ለመሆኑ ምን መልክ ይኖረዋል? እንዴት ነው የምንሳፈረው? ወጭውስ በኛ ዐቅም ይቻላል? እንደ ሰርዲን ታጭቀን ነው ወይስ ወንበር አለው? ለመሆኑ እንደ አውቶቡስ ቁጥር አለው? ሲሆን አንድ ቦታ ላይ ሠርተው እንደ ኤግዚቢሽን ቢያሳዩን፤ ‹አሃ ለካ እንደዚህ ነው› ብንል አእምሯችን ለምዶት ቢቆይ መልካም ነበር፡፡ ካልሆነም ሥዕሉን በየሠፈራችን ቢያኖሩት››
‹‹በቀደም ታናሿ ልጄ የምወልደውኮ ሴት ልጅ ነው አለችኝ››
‹‹ያቺ ነፍሰ ጡሯ››
‹‹አዎ፤ በምን ዐወቅሽው፣ የዛሬ ልጆች መጠንቆል ጀመራችሁ ወይ አልኳት››
‹‹ሐኪሙ አሳየኝ - አለችኝ››
‹‹ሆድሽን ከፍቶ አሳየሽ - ብዬ ቀለድኩባት››
‹‹አይደለም በመሣሪያ ማየት ይቻላልኮ - አለችኝ፡፡ ዛሬ ያልተወለደን ልጅ ወንድ ይሁን ሴት ማወቅ እየተቻለ እንዴት ነው እንዲህ ሠፈሩን ሁሉ አቋርጦ የሚሄደውን ባቡር መልክ ቀድሞ ማየት ያልተቻለው፡፡ ሲቆፍሩ፣ ሲገነቡ፣ ሲሚንቶ ሲሞሉ፣ አቧራ ሲያቦኑ ብቻ ነው የምናያቸው፤ የሐበሻ መድኃኒት አደረጉት አልክ፣ እውነትክን ነው፡፡››
አረጋውያኑ ወደ ሚካኤል ግቢ ዘልቀው ተሳለሙና አጥሩ ጥግ ዛፎቹ ሥር ዐረፍ አሉ፡፡
‹‹እኔ ግን ምን እንደሚመስለኝ ታውቃለህ?›› አሉ ሽበት ያጀባቸው ሽማግሌ
‹‹ምን ይመስልሃል?›› አሏቸው ሪዛሙ አረጋዊ
‹‹እኛ ብቻ ሳንሆን እነርሱም አሟልተው ያወቁት አይመስለኝም››
‹‹መጠርጠር እርሱን ነው›› አሉና መዳፋቸውን በመዳፋቸው መቱት፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

33 comments:

 1. betemi yigermal yha yehulum weyiyit new megemeriy desi bilon neber zara gin yasasibal .mechresawn amilaki yasayen.

  ReplyDelete
 2. First of all I would like to say thank you to current government for doing this great job. As we all know that we are the poorest country in the world because of war and poor management. At this movement our country struggle to compute with global market, to improve our transportation system, to improve power and to create job. Before 1997 election all Ethiopian money deposited to in Switzerland and New York bank. After 1997 election the government uses the money to change Ethiopian people mind. Even if they work hard to stay in power, it is better to see something instead of nothing. At the movement we see train infrastructure in Addis Ababa. As we all know that they don’t have any plan to build a train transportation system. If they have a plan they shouldn’t destroy many new roads however we don’t have to go back to argue with them. Our dream is to get a better transportation system in our country. Most of us we didn’t trust this government so we are seeking to see some visual floor plan to give judgment. It is not bad idea to see a master plan but it is too expensive for non-planed job. At this moment the government collecting money for Abay boned and Meles foundation. If we pressure the government to see floor plan, they will ask as to contribute money for floor plan. Please Dani I am struggling to live month to month because of my salary deduction so stop here otherwise they will take all my salary. Thank you brother in advance. God bless Ethiopia. It is fasting time so include Tigray.

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is what i call it comment we oppose what we suppose to oppose We appreciate what we suppose to appreciate and we appreciate this progress.

   Delete
 3. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዳኒ!
  እኔም የመሻገሪያው ነገር በጣም ነው ያሳሰበኝ፡፡
  መሻገሪያው እኮ የባቡሩን ስራ የሚሰሩትን የቻይናዎችን ጭንቅላት ወይም ካለምንም የነዳጅ ወጪ በመንግስት መኪና የሚንቀሳቀሰውን ባለስልጣን አቅም ያማከለ መሆን የለበትም የአካባቢውን ማኅበረሰብ አቅም አኗኗርና ዘይቤ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡ ቀለበት መንገድ እኮ ሲሻገሩ የሚያልቁት ወገኖች በአግባቡ ካለመሻገር ባቻ ሳይሆን መሻገሪያው በጣም ከመራራቁ የተነሳ መሆኑ እንደ አንድ ምክንያት የሚጠቀስ ነው፡፡ አሁን እስኪ ሲ ኤም ሲ ቅዱስ ሚካኤል ፊት ለፊት የሚኖሩ ሰዎች ለመሻገር አያት መሄድ ካለባቸው እንን ለእግረኛ ቤንዚል ለተወደደበት ባለመኪናም ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ መገመት አያዳግትም፡፡
  ይህ ደግሞ ነገ ልክ እንደቀለበት መንገዱ በባቡሩ ስር ለመሹለክ የሚሯሯጡ ወይም በላይ ለማቋረጥ የሚንጠላጠሉ ሰዎች ለአደጋ እንዲጋለጡ ማድረጋችን አይቀሬ ነው!
  እንዳልከው ለህዝቡ ምን እንደሚመስል ማሳየት ብቻ ሳይሆን የትራፊክና የመንገድ ትራንስፖርት ባለሞያዎች እንዲሁም የአካባቢ ተወካዮች መወያየት ነበረባቸው፡፡
  ለማንኛውም ያበሻ መድኃኒት የሚታወቀው ወይ ሲያድን ወይ ሲገል ነው እድሜ ይስጠንና ውጤቱን ለማየት ያብቃን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሜን። ምልከታዎ ተክክለኛና አሳሳቢ ነው። ሁሉም ሊወያይበት ይገባል።

   Delete
 4. ደቀመዝሙርMarch 19, 2014 at 9:58 AM

  ዳኒ እኔ በማውቀው ልደታ - ሜክሲኮ መንገድ ቀደም ሲል ፕላኑ ሜክሲኮ ከሸበሌ ወደ ፌ/ፖሊስ ህንጻ ስትሄድ በስተግራ በኩል ባለው ቶታል ጋዝ ማደያ ጎን፣ልደታ ጫፍ ወደ አብነት መታጠፊያው ላይ ተሰቅሎ አይቼ ነበር!!ስራው ሲጀመር ግን ፕላኑ የት እንደገባ አላውቅም!!ቆሞ የነበረበትም ቦታ ታርሶ የግንባታ ሳይት ሆኑዋል!!
  አሁንም ከፍ ተደርጎ ለአላፊ አግዳሚው እንዲታይ ፕላኑ ቢሰቀል ጥሩ ነው!!በሀሳብህ እስማማለሁ!!
  ከዚህ ውጭ ፕላን የለው ይሆን እንዴ እያልክ ያስገባሀት ስርዋጽ በደራሲነት ካገኘሀት የምናብ ጸጋ የጨመርካት ትመስላለች!!
  ቁፋሮ ከመጀመሩ በፊት ለተነሺዎች ካሳ ለመክፈል ፕላን ግድ ነው፣ፕላኑ በቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ቢሮ ተንጠልጥሎ በኢቲቪ ዶክመንተሪዎች አይተነዋል፣ሲያልቅ ምን እንደሚመስል በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማእከል አኒሜሽን ተሰርቶለት በዩ ቲዩብ እና በድሬቲዩብ እንዲሁም በፋና ገጸ-ድር ተመልክተነዋል፣የፈለገ አሁንም ጎግል አድርጎ ማየት ይችላል!!
  ችግሩ ዳኒ የጠቀሳቸው አይነት አረጋውያን ለጎግል ሩቅ መሆናቸው ነው!!ለእነሱ እና ለሌሎች እድሉ ለሌላቸው ሰዎች ፕላኑ በፍጥነት ቢሰቀል መልካም ነው!!ካልደረሰም እንግዲህ፡የሚቀጥለው አመት ምርጫ ስለሆነ ክሊፕ ተሰርቶለት እናየዋለን!!
  ዳኒ በነካ እጅህ ፕላኑ ስለተሰቀለው የዓባይ ግድብ አንድ ነገር ብትለን ደስ ይለኛል!!
  ዳኒ ላንተ ያለኝ ክብር ከዚህ…………….እስከዚህ ካለውም ይበልጣል!!ያኑርህ - ከነብዕርህ!!

  ReplyDelete
 5. በጣም ጠቃሚ ጽኁፍ ነው፤ ይቅርታ! ዳኒ የማይጠቅም ጽፎ አያውቅም፡፡ መከራችንን የሚያበላንን ባቡር ካለቀ በኋላ መመሪያ ከሚወርድልንና ከምንደናበር ካሁኑ ማንኛዉንም ጠቃሚ ባቡራዊ ጉዳይ ብናውቅ መልካም ነው፤ እባካችሁ የሚመለከታችሁ፤ ካላወቃችሁ ባስተርጓሚም ቢሆን፡፡

  ReplyDelete
 6. በጣም ጠቃሚ ጽኁፍ ነው፤ ይቅርታ! ዳኒ የማይጠቅም ጽፎ አያውቅም፡፡ መከራችንን የሚያበላንን ባቡር ካለቀ በኋላ መመሪያ ከሚወርድልንና ከምንደናበር ካሁኑ ማንኛዉንም ጠቃሚ ባቡራዊ ጉዳይ ብናውቅ መልካም ነው፤ እባካችሁ የሚመለከታችሁ፤ ካላወቃችሁ ባስተርጓሚም ቢሆን፡፡

  ReplyDelete
 7. Dani. you produce great works as usual and thank you for this and God bless you. The government is now at rush hour where lots of projects are undergoing. However, if we look seriously lots of hampering are lying in front of the undergoing projects such as lack of finance, poor management of projects and delay and increasing corruptions. Despite all this efforts made by the government, basic public services becoming deteriorating and public dissatisfaction upwards as days in days out. i don't know how the government is going to tackle all this issues at hand.

  ReplyDelete
 8. ዳኒ እ/ር ይባርክህ ያነሳኸው ሃሳብ በጣም ጥሩ ነው:: የዚህችን ሀገር ኢኮኖሚ ከሚበሉት ነገሮች አንዱ ነዳጅና የነዳጅ ብክነት ነው:: መኪኖች በማቓረጫ ምክንያት ብዙ ነዳጅ ቢያባክኑ ተጎጂው ግለሰብም ሀገርም ነው:: አግረኛም በማቓረጫ ምክንየት ቢቸገር ዞሮ ለመምጣት አላስፍላጊ ወጪ ለታክሲ ያውጣል ጊዘ ይጠፋል ሌላም ሌላም:: ምልክት ስለተባለው ለባቡር አይደለም ለህንፃ ሕጉ ያስግድዳል ዳሩ ፐላን ሲኖር ነው:: ባቡሩ በመሬት ሲሄድ እንዲታይ ለምርጫ ተብሎ ከሆነ የተስራው ወደፊት አደጋ አለው ኢንጅነር በፍቃዱና ግድይ ሊያስቡበት ግድ ይላል::
  ቸር ያስማን እውነቱ ነኝ

  ReplyDelete
 9. መጠርጠር ጥሩ ነው ።

  ReplyDelete
 10. Tim Ina Riz tedebalkewal bay negn

  ReplyDelete
 11. ዳኒ ይሄ ትል ቅ ግንዛቤ ነዉ ላስተዋለዉ ግን ማን ሰምቶ

  ReplyDelete
 12. ዳኒ ይሄ ትል ቅ ግንዛቤ ነዉ ላስተዋለዉ ግን ማን ሰምቶ

  ReplyDelete
 13. በየፌርማታው የመንገድ ማቁዋረጫ ይበጅለታል። ( የላዩ በላይ: የስሩ በስር )ግን ውዥንብር ለሚፈጥሩ ቢያሳዩን መልካም ነበር

  ReplyDelete
 14. ዳኒ....የምታይባቸው አቅጣጫዎች መልካም ናቸው፡፡ ግን ሚካኤል ግቢ የሚለውን.....ቅዱስ ሚካኤል ግቢ ብትለው መልካም ነበር....ለቀባሪው አረዱት እንዳይሆን!!!

  ReplyDelete
 15. መልካም ነው ዳኒ፡፡ ነገር ግን ቅር ያለኝ ነገር ቢኖር፡ ሽማግሌዎቹ ረጋ፣ ሰከን ያሉ፣ የማይቸኩሉ ናቸው በባሕሪያቸው፡፡ ከአንድ ዓመት በታች ለቀረው ፕሮጀክት ይህን ያህል የሚያስቸኩል ነገር አይደለም፡፡ ነገን በተስፋ ለሚጠብቅ ሰው፡፡ እንኳንስ እንዲህ በየቀኑ ለውጡን በዓይናችን በብረቱ እያየን ቀርቶ፣ በስሚ ስሚ እንኳን የሚያጣድፍና ይህን ሁሉ ሀተታ የሚያዘከዝክ አይደለም፡፡ ለማንኛውም ሀገራችን በፈጣን ጉዞ ላይ ነች፡፡ Thanks to the almighty God

  ReplyDelete
 16. መጠርጠር ጥሩ ነው ።
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዳኒ!

  ReplyDelete
 17. ኡፍ ዳኒ አንዳንዴ ለዛህ ሙጥጥ ይልብኛል፡፡ ስታይል ቀይር፡፡ አኧምሮ ብጥብጥ የሚያደርግ አትጻፍ፡፡ ጭንቅላታችን መጨናነቅ፣ መጠራጠር፣ ክፉ ክፉ ማሰብ አይፈልግም በአሁን ሰዓት፡፡ So come up with the great news which is happened in our world - Ethiopia.

  ReplyDelete
 18. እኛንስ ሊገላግሉን ነዉ:: እኔን ግራ የገባኝ መኪኖቹ የሚሮጡበት መንገድ የባቡር ፍርጎ ተሰርቶበት መኪኖቹ በየት ሊሄዱ ነዉ? ነዉ እነሱም እንደኛ ባቡር ዉስጥ ይገባሉ?

  ReplyDelete
 19. ምነው ሚኒስትር ዘነቡ ? Danial please remove this article from you blog please. I know her more than 27 years, she is very very helpful person and she loves God. I swear to God she is not this kind of cheap person. She may made mistake one time but she dinaied. Please B Mariam remove her from you blog. Human being never give forgiveness. ( Former President Mengestu Hailemariam).

  ReplyDelete
  Replies
  1. መንግሥቱ ዛሬ ቢጠየቅ ፡ ይህ ጥቅስ የኔ ነው ይላል ብዬ አላምንም ። ሰንት የትርጉም ጥቅሶች በሱ ስም አንበብን!

   Delete
 20. gena sent gud yametabenal ye terafik adegawochu gena ke aunu jemerewal siyalk demo metfiyachen new mihonew yehe ye balesletanu halafinet new

  ReplyDelete
  Replies
  1. lowid danel: ተስፋ ቢስ አነስተኛ ነህ፡፡ ያኔ ድሮ ድሮ አጼ ሚኒሊክ የስልክ ቴክኖሎጂ ወደ አገራችን በአስገቡ ጊዜ ፡ "ወይ ጉድ ንጉሱ አበዱ . . . ብለው ...ብለው ከአጋንንት ጋር ይነጋገሩ ጀመር" እያሉ ይነቅፏቸው ነበር፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ልክ እንዳንተ አይነት ደንቆሮ በሌላው አገር ተግባራዊ የሆነውን በአገራችን እውን ሊሆን በወራት የቀረውን የባቡር ቴክኖሎጂ ጉድ ሊያመጡብን ነው ትላለክ፡፡ ከንቱ ነህ፡ ይልቅ የለውጥ ሰው ሁን አሁኑኑ ማንነትክን አስተካክል፡፡ መሃይም ደደብ ነህ፡፡

   Delete
  2. " ከንቱ ነህ፡ ይልቅ የለውጥ ሰው ሁን አሁኑኑ ማንነትክን አስተካክል፡፡ መሃይም ደደብ ነህ፡፡"

   ሰው የማያውቀውን ነገር ሰለፈራ ፡ ስድቡ የምንኛ ነው?

   በዚህ ችሎታህ ፡ ከዘመኑ ባለስልጣኖች አንዱ እንዳልሆንክ ተስፋ አለኝ።

   Delete
  3. ሰው የማያውቀውን ባቡር ፡ ሞቱን አንዳያቀርብበት ስለፈራ ፡ ደደብ ማለት ተገቢ ነው?

   በዚህ ችሎታዎት ፡ ከዘመኑ ባለስልጣናት አንዱ እንዳልሆኑ ተስፋ አልኝ፡፡

   Delete
  4. AnonymousApril 7, 2014 at 2:18 PM
   "lowid danel: ተስፋ ቢስ አነስተኛ ነህ፡፡ ያኔ ድሮ ድሮ አጼ ሚኒሊክ የስልክ ቴክኖሎጂ ወደ አገራችን በአስገቡ ጊዜ ፡ "ወይ ጉድ ንጉሱ አበዱ . . . ብለው ...ብለው ከአጋንንት ጋር ይነጋገሩ ጀመር" እያሉ ይነቅፏቸው ነበር፡፡ አሁን አሁን ደግሞ ልክ እንዳንተ አይነት ደንቆሮ በሌላው አገር ተግባራዊ የሆነውን በአገራችን እውን ሊሆን በወራት የቀረውን የባቡር ቴክኖሎጂ ጉድ ሊያመጡብን ነው ትላለክ፡፡ ከንቱ ነህ፡ ይልቅ የለውጥ ሰው ሁን አሁኑኑ ማንነትክን አስተካክል፡፡ መሃይም ደደብ ነህ፡፡"

   This shows what you are:-
   - Stupidity
   - Illiterate
   - Ignorant
   - Bad-mannered.....etc
   I know its not expected from Christian to insult anybody but you deserve too!!!

   Dn. Daniel may God bless you!!!

   Delete
 21. "Tell me your friend i will tell you how you are" አንተም በንግግርህ የአይምሮ ጠባብነትህ ትገመተ ለስድብ የፈጠነ ምላስ ስትዝረጋ ወስጥህ ባዶ መሆኑን ታሳይብሀለች፡ ለማንኛውም ዲ/ዳንኤል የፖለቲካ አቆም ሳይሆን ያራመደዉ በአኢትዮጲያዊነቱ የተስማውን ምልክታ ነዉ የተናገረው ምን አልባት አንት እንጃ እኛ በሰፈራችን እየተቸገርን ነው አንተ እንግዲህ በሹፌር ይሆናል የምትንቀሳቀሰው ለማንኛወም ውድ ውንድሜ/እህቴ እንደ ብዙ ኢትዮጲያዊ ካስብክው ይህ መሰረታዊ ጥያቂያችን ነዉ መንግስት ከደበቀን ካልመለሰልን እንግዲህ መልስ ምፍትሄ ካለህ መላ በለን እግዚአብሄር ሀገራችንን ይባርክ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምናልባት ኢሣትን 24 ሰዓት የምትከታተል ከሆነ ኢቲቪ ምን እንደሚያወራ ላታውቅ ትችላለህ፡፡ ዲ/ን ዳኒ ጥያቄ የሆኑበት ነገሮች ሁሉ የሚመልስ ፕሮግራሞች በተከታታይ ተሠርቷል፡፡ ኢቲቪን መመልከት የሚደብርህ ከሆነ ጐግል ላይ ፈልግ ዋልታ የዘገበውን ታገኛለህ፡፡ ልማት ሊመጣ ከተፈለገ መስዋዕት መክፈል ግድ ይላል፡፡ እነ ጃፓን፣ ጣሊያንና ሌሎች ያደጉ ሀገራት የባቡር ቴክኖሎጂ ከሰማይ ተሠርቶ እንደ መና አልወረደላቸውም ሠርተው፣ ፈግተው ነው እንዲህ በሥልጣኔ ማማ ላይ ያሉት፡፡ ስለዚህ አገራችን ገና በዳዴ ላይ የምትገኘዋን ሰው ያየውን ወግ ማዕረግ ልታሳየን የምትታትረውን ምስኪን አገር አይዞን እንበርታ ከማለት ፋንታ በየአቅማችን የስድብ፣ የነቀፋ ዝናብ የምናዘንብ ከሆነ ያሳዝናል፡፡ በአድዋ ጦርነት፣ በዶግአሌ ጦርነት ከዛም በየደረጃው የተከፈለው መስዋዕት የደምና የአጥንት ነበር አሁን ደግሞ በአቅማችን ልንከፍል የምንችለው ተሰልፈን ታክሲ በመጠበቅ፣ በኮሮኮንችና በአቧላ የእግር መንገድ መሄድ፣ ወዘተ ትናንሽ ነገሮች ናቸው ስለዚህ ወንድ ከሆንክ እንደወንድነትህ ሮጥ ሮጥ ዘለል ዘለል በማለት ችግሩን ማለፍ ይጠበቅብሃል ሌላው ወኔ እንኳን ጠፍቶብሃል፡፡ ስለዚህ ሾፌርም የለኝ እንደው የነገው ተስፋዬን እየጠበኩ በችግር ውስጥ ለማለፍ ተዘጋጅቻለው፡፡ አንተስ???????????

   Delete
  2. " ኢቲቪን መመልከት የሚደብርህ ከሆነ ጐግል ላይ ፈልግ ዋልታ የዘገበውን ታገኛለህ፡፡"

   ጀርመኖች ይህን ዓይነቱን አማራጭ " ተስቦ ውይስ ኮሌራ ይሉታል " ፡፡
   ኢሳትም ገለልተኛ ዘጋቢ ነው ልል አይደለም ። ሁሉም ከጀርባው ያዝለው ዐላማ አለውና፡፡ ግን አንድ ግለሰብ የዜና ምንጩ ኢቲቢ እና ዋልታ ብቻ ከሆኑ ፡ ያሰው ሰው መሆኑ ቀርቶ ፡ ማሰብ መቻሉን ዘንግቶ ፡ በታማኝነት ለጌታው ጭራውን እንደሚቆላ ውሻ ይሆናል።

   ልብ በል ፡ ጠያቂ ሳይሆን ፡ የሚሳሳተው መላሽ ነው፡፡

   Delete
  3. ሰው ሆይ አባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል አሉ፡፡ የውጭው ሚዲያማ ቀኑን ሙሉ የሚያላዝኑብን የነ ዩክሬንን ብጥብጥ፣ የሶሪያን እሪታ፣ የፕሌኑ መጥፋት፣ አልፎ አልፎ ስለኢትዮጵያ እድገት /PINE/ if you don't know this abbreviation the best countries Economic rising in the world (Philipins, Insonosia, Nigeria & my best beloved country Ethiopia ናቸው ስለዚህ የውጭ ሚዲያንም አየነው ሰማነው የኛን ኢቲቪ ግን የሚመስል እንደው አላየሁም የኔ ጭፍን፡፡

   Delete
  4. ካንገት ከረባት ፡ ቂጥ ባዶ!

   Delete
 22. ጓዴ ስለ ኢቲቪ በኩራት ስታወራ አለማፈርህ ዜና እንኳን ሲጀምር እንደምን አመሻችሁ ዲሽ ስለሌላችሁ እናመሰግናለን ብሎ ነው፡፡ እነሱን ማን ያያል ኢሳትም ያው ነው ከኢሳት ለይቼ አላየውም ነገሩን አለሙን እረስቶ ፖለቲካውን ብቻ ነው የሚያስተዋውቀው ደግሞስ ውሸቱ....

  ReplyDelete