ኦሎምፒያ አካባቢ የሚገኘውን የቀለም ባለሞያውን የጌታሁን ሄራሞን ቢሮ በጎበኘሁ ቁጥር
በሁለት ነገሮች እደሰታለሁ፡፡ በአንድ በኩል ስለ ቀለማት በሚሰጠው ሕይወት ያለው ትንታኔ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ባከማቻቸው
የኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎች ሥራዎች፡፡ የእርሱ ወንበርና ጠረጲዛው የቢሮውን አንድ ሦስተኛ ብቻ ነው የያዘው፡፡ ቀሪውን የቢሮውን
ክፍል ዋናው ባለ አክስዮን ስብስብ ሥዕሎቹ ይዘውታል፡፡ መቼም ሰው ሥራውን ለምንዳዕ ብቻ ሳይሆን በፍቅርም ሲሠራው ሕይወትን
በሌሎች ላይ የመዝራት ዐቅም ይኖረዋል፡፡
እዚያ ከተሰበሰቡት ሥዕሎች ውስጥ በመጀመሪያው ክፍል ከጠረጲዛው ከፍ ብሎ ግድግዳው
ላይ የተሰቀለው ካንቫስ የፈጠራ ሃሳብ ያስደንቀኛል፡፡ በመስተዋቱ ውስጥ ሁለት ጥቋቁር ካልሲዎች በጫማ አቀማመጥ ቅርጽ
ተለጥፈዋል፡፡ አንደኛው ምንም ያልነካው ‹አዲስ› ካልሲ ነው፡፡ ሁለተኛው ግን ተረከዙ ላይ ተቀድዷል፡፡
የጥበቡ ርእስ ‹ጥንድ የመሆን ፈተና› ይላል፡፡ ምን ማለት ነው? ደጋግሜ አየሁት፡፡ ‹‹ወፍ ስትበር የሚያሳይ ሥዕል ሳሉ›› ተብለን በሥዕል ትምህርት
ቀልደን ላደግን ሰዎች የሥዕልን ጥበብ ዘልቆ ምሥጢሩን መረዳት እንደ ዋድላ ቅኔ ከባድ ምርምርን ይጠይቃል፡፡ ለረዥም ሰዓት ነው
አፍጥጬ ያየሁት፡፡ እንዲያውም በመሐሉ የሥዕሉን ምሥጢር ከመመርመር ወጥቼ እኛ ቤት የነበረች አንዲት የቤት ሠራተኛችን ትዝ አለችኝ፡፡
የምገዛቸው ካልሲዎቼ ሁሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ ከትዳር ተፋትተው ላጤ ሆነው ነበር የማገኛቸው፡፡ ‹‹ምንድን ነው?›› ስላት ‹አይጦቹ ናቸው›› ትለኛለች፡፡
ግርም ይለኝ የነበረው የነዚህ የስምንተኛው ሺ አይጦች ጠባይ ነበር፡፡ የሀብታም
ትምህርት ቤት እንደገባ ልጅ ‹ለአንድ ቀን አንድ ዓይነት› የሚል መርሕ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ ቢሞቱ ሁለቱንም ካልሲዎች
አይበሏቸውም፡፡ ከሁለቱ አንዱን ብቻ ነው የሚመገቡት፡፡ አንዳንዱን ካልሲ ወስደው ለሆቴላቸው በያይነቱ ያዘጋጁበትም እንደሁ
እንጃ፡፡ አንዱ ጓደኛዬ ደግሞ የለም ልጂቱ ባለ አንድ እግር ወዳጅ ሳይኖራት አይቀርም ይለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱ ነው፤ ወይም
ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡
አሁን እዚህ ደግሞ ካልሲ ጥበብ ሆኖ በፍሬም ተሰቅሎ ሳየው ገረመኝ፡፡
‹‹ጥንድ የመሆን ፈተና››
በኋላ ጌታሁን አንድም እያለ ተረጎመልኝ፡፡ ‹‹እስኪ እየው፤ ይኼኛው ካልሲ ደህነኛ
ነው፡፡ እንዲያውም ቅድም እንዳልከው አዲስ ይመስላል፡፡ ተጣማሪው ግን ተቀድዷል፡፡ ካልሲ ሊደረግ የሚችለው በጥንድ ብቻ ነው፡፡
በዚህ በተቀደደው ምክንያት ያልተቀደደው ካልሲም ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡ ቤቴ ውስጥ በተደጋጋሚ ሲያጋጥመኝ ጊዜ ይህንን ሃሳብ
አሰብኩት፡፡ የዚህ የደህነኛው ካልሲ ጥፋቱ ምንድነ ነው?
አልኩ፡፡ ሳስበው ጥፋቱ አንድ ብቻ ነው፡፡ የቀዳዳው ካልሲ ተጣማሪ መሆኑ፡፡ በቃ ተጣማሪው ስለ ተቀደደ እርሱም ይጣላል፤
ያለበለዚያም ለልጆች ኳስ መሥሪያነት ይውላል፡፡ ጥንድ የመሆን ፈተና ይኼ አይደለም ታድያ?›› አለኝ፡፡
እርሱ ይሄንን ሲነግረኝ ባለትዳሮች፣ ጓደኛሞች፣ የንግድ ሸሪኮች፣ የጥበብ ወዳጆች፣
የሥራ አጋሮች፤ እንዲቀያየር ሆኖ እንደተጫነ የኮምፒውተር ስክሪን ሴቨር በዓይነ ኅሊናዬ ቦግ እልም እያሉ አለፉ፡፡ ምርጥ ባል፤
የባሎች ሁሉ መለኪያ ሊሆን የሚችል፤ አባትም ባልም ተብሎ የሚነገርለት ተጣማሪው ተበላሽታ ሲበጠበጥ፣ ሲታመስ፣ ሲመሳቀል፣ ዐቅሙ
ሲደክም፣ ሥራው ሲበላሽ፣ አእምሮው ሲናወጥ፣ ይኖራል፡፡ አይቆርጠው አካል፣ አይተወው ሕመም ሆኖበት፤ አይናገር ምሥጢር፣ ዝም
አይል ብሶት ሆኖበት፤ ከዕረፍት እንደተመለሰ እሥረኛ ቤቱ እያስጠላው፣ ጥንድ መሆን ፈተና ላይ ጥሎት ይኖራል፡፡
ምን የመሰለች ሚስት፣ ዐፄ ቴዎድሮስ ‹ሚስት ናት ገረድ› ያሏት ዓይነት፣ ልጆቿን
አፍቃሪ፣ ባሏን አክባሪ፣ ትዳርዋን አሥማሪ የሆነች ሚስት፣ ባሏ ተበላሽቶባት፣ ይኼው
ትዳር ምን ዕዳ ነው፣ ጎጆ ምን ዕዳ ነው
ከገነት ተባርሮ ገሐነም መኖር ነው
እያለች ታንጎራጉራለች፡፡ ሥራዋ፣ ሀብቷ፣ መልኳ፣ ዕውቀቷ፣ ጠባይዋ፣ ሥልጣኗ፣ ክብሯ፣
ዝናዋ ከሰው በላይ ሆኖ የትዳር አጋሯ ግን የተቀደደ ጣራ፣ የፈረሰ ግድግዳ፣ የማይዘጋ በር፣ የሚዋጋ ጫማ፣ የሚኮሰኩስ ልብስ፣
የሚያቃጥል ወጥ፣ የሚኮመጥጥ እንጀራ ሆኖባታል፡፡ አትተወው ትዳር፣ አትኖረው ሲኦል ሆኖባት፤ ስንት ውስብስብ ችግር በቢሮዋ የፈታች ሊቅ፣ የአጋርን ችግር መፍታት ቸግሯት ተጣማሪ ካልሲ
ሆናለች፡፡
በአምስት ጣት የሚበላ ሰው መቼም አብሮ መሥራትን አይጠላም፡፡ ‹ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር›፣ ‹ለአንድ ብርቱ ሁለት
መድኃኒቱ›፣‹ለአንድ ጉርሻ ሠላሳ ሁለት ጥርስ› እያለ የሚተርት መቼም አብሮ ተባብሮ መሥራትን አይጠላም፡፡ ማበር የሚያስጠላው፣
ሽርክና የሚያስመርረው፤ ኅብረት፣ አንድነት፣ ማኅበር፣ ቡድን፣ ኮሚቴ፣ የሚያቅለሸልሸው እንደ ካልሲው ከተጣማጆቹ የሚቀዳደድ ካለ
ነው፡፡ አብሮ ለመሥራት፣ አብሮ ለማደግ፣ አብሮ ለመልፋት፣ አብሮ ለመትጋት ወስነው አጋና ከመቱ በኋላ አንዱ ወገን እንደ ካልሲው
የተቀደደ ከሆነ፣ የቀዳዳው ዕድል ፈንታ በደህናው መወሰን ሲኖርበት፣ የደህናው ዕድል በቀዳዳው መወሰን ከጀመረ፣ ያኔ ነው አብሮ
መሥራት እሴት ከመሆን ይልቅ ዕዳ የሚሆነው፡፡
ይህንን ካልሲ ሳይ መኪና ታወሰኝ፡፡ አራት እግር ያለው መኪና አንዱ ጎማ ሲተነፍስ የሚቆመው ለምንድን ነው? ጥንድ የመሆን ፈተና ገጥሞት
አይደል፡፡ ያልተነፈሱት ሦስት ጎማዎች በተነፈሰው አንድ ጎማ ምክንያት መቆማቸው የግድ ነው፡፡ ስንት የተጣመሩ ፓርቲዎች ከመካከላቸው
እንደ ካልሲው የተቀደደ፣ እንደ ጎማው የተነፈሰ ሲያጋጥማቸው አይደል ቆመው ወይም ፈርሰው የቀሩት፡፡
አንዳንዴ ምንም ያህል ብንፈልገው ብቻችንን ልንሆነው የማንችለው ነገር አለ፡፡ ብቻችንን ብንሠራው እንኳን ከማናውቅ
አካል ጋር የምንጣመርበት ጉዳይም አለ፡፡ ‹አይ የታክሲ ሾፌር፣ አይ አስተናጋጅ፣ አይ ነጋዴ፣ አይ ቀበሌ፣ አይ ተቃዋሚ፣ አይ ደጋፊ፣
አይ ጋዜጠኛ፣ አይ ፖሊስ› እየተባልን በምናውቀውም በማናውቀውም፤ ባደረግነውም፣ ባላደረግነውም የምንወቀሰውኮ ‹ጥንድ በመሆን ፈተና›
ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ብቻችንን መልካም ብንሠራ፣ ንጹሕና ጻድቅ ብንሆን እንኳን፣ የሆነ ቦታ በሚገኙ ሳናውቅና ሳንፈቅድ
በተጣመርናቸው የሞያ አጋሮቻችን ጥፋት መወቀሳችንና ሕዝባዊ አመኔታ ማጣታችን አይቀሬ ነው፡፡
ጥቂት የዚያ ብሔረሰብ ሰዎች፣ የተወሰኑ የዚያ ቡድን አባላት፣ እፍኝ የማይሞሉ የዚያ ሀገር ዜጎች፣ በጣት የሚቆጠሩ
የዚያ ሃይማኖት አማኞች፣ ውክልና የሌላቸው የዚያ ማኅበር አባላት፣ ለራሳቸው ብቻ ሲሉ ወጥ በረገጡ የዚያ ሞያ ባለቤቶች፣ ከሁለት
ወንበር በማይበልጡ የዚያ መሥሪያ ቤት ባልደረቦች ጥፋት ‹እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ‹ ሁሉንም አንድ አድርጎ የመኮነን አባዜ
የመጣው ጥንድ ከመሆን ፈተና ነው፡፡ በተቀዳደዱ ካልሲዎች ምክንያት የሚያገለግሉትም አብረው እንደሚጣሉት፡፡
ምርጥ የባለሞያ ወጥ፣ በስሕተት በበዛ ጨው ምክንያት ተመጋቢ የሚያጣው ጥንድ የመሆን ፈተና ገጥሞት ነው፡፡ ‹በጨው
ደንደስ በርበሬ እንደሚወደሰው› ሁሉ በጨው ጥፋትም በርበሬ ከጥቅም ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡
ዘመናዊ ኑሮ የጉርብትና ሥርዓት ነው፡፡ ዐውቀነውም ይሁን ሳናውቀው ከብዙ ነገሮች ጋር ተጣምረንና ኅብረት መሥርተን
ነው የምንኖረው፡፡ ሰው ብቻውን መጥፎ፣ ብቻውንም ጥሩ መሆን አይችልም፡፡ ብቻውን ንጹሕ፣ ብቻውንም ቆሻሻ ለመሆን አይችልም፡፡ እኛ
ቤት የምትመጣው ዝንብ ከየት መነሣት እንዳለባት ልንወስንላት አንችልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአንድ መንደር መብራት፣ ውኃና መንገድን
ለማስገባት፤ ጸጥታ፣ ንጽሕናና ውበትን ለመጠበቅ መንደሩ ሁሉ ይስማማና ጥቂት ጎረቤቶች ግን እምቢ ይላሉ፡፡ አልከፍልም፣ አልሠራም፣
አልሰበሰብም፣ አልተባበርም፣ አያገባኝም ይላሉ፡፡ የስንት ጎበዞችን ዕቅድ የጥቂት ቀዳዳ ካልሲዎች ችግር ከጥቅም ውጭ ያደርገዋል፡፡
ጥንድነት የማይቀር የኑሮ ሥርዓት ከሆነ ከባዱ ነገር ጥንድ የመሆንን ፈተና እንዴት እንለፈው ነው፡፡
‹‹ትንሽ በር በሬ ብደቁሰው፣ ብደቁሰው
ሀገሩን ሁሉ አስነጠሰው፣ አስነጠሰው››
የተባለው ይህንን ይነግረናል፡፡ ለማስነጠስ በርበሬ መደቆስ አያስፈልገንም፡፡ የሌላው ጎረቤት በርበሬ በቂ ነው፡፡
በቢሯችን ውስጥ መልካም ሽቱ የተቀባ ሰው ካለ ለሁላችን መዓዛው እንደሚተርፈው ሁሉ፣ የጫማውን ጠረን ማስወገድ ያልቻለውም የቢሯችን
ባልደረባም በተቃራኒው እንዲያ ነው፡፡
ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመወጣት አንድም የዳበረ የኑሮ ጥበብ ያሻል፣ አንድም የታሰበበትና ተገቢ የሆነ የጥንድነት
ልማድና ሕግ ያስፈልጋል፤ አንድም ደግሞ ከፈተናው የመውጫ ውጤታማ የአደጋ ጊዜ በር ሊሠራ ይገባል፡፡ ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና
ለመከላከል፣ ካልሆነም ለመፍታት የሚያስችል ከማኅበረሰቡ ጋር የተዋሐደ የኑሮ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን የኑሮ ጥበብ ለመገንባት
ደግሞ የሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ ቃል፣ ሚዲያና ዘመናዊ የኑሮ ዘዴ ትምህርቶች ታላቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፡፡
አብሮነት የሚያስከትላቸውን ፈተናዎች ማራቂያ፣ ሲመጡም የከፋ ጉዳት ሳያደርሱና እንደ ቀዳዳው ካልሲ ለመጣል ሳያበቁ፣
ማስወገጃ የዳበረ ሀገራዊ ልማድና ሕግም ወሳኘው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈተናውን አምቀን ብቻ እንድንይዘው፣ ያለ መውጫ እንድናስበው፣
የዐርባ ቀን ዕድል አድርገን እንድንቆጥረው፣ መፍትሔው አብሮ መውደቅ ብቻ አድርገን እንድናየው የሚያደርግ ሀገራዊ ልማድና ሕግ ካለ
ጥንድነት እሴት ሳይሆን ዕዳ ብቻ ይሆናል፡፡
ፍየል ቀንዷ ለምን ወደ ኋላ ዞረ? ሲባል፤ ስትገባ መውጫ መውጫውን ለማየት ነው አሉ፡፡ የምንገባበት ነገር ሁሉ አንዳች የመውጫ የአደጋ ጊዜ በር ሊኖረው
ይገባል፡፡ የአደጋ ጊዜ በር በማናቸውም ጊዜ፣ በፈለገው ሰው፣ ለማናቸውም ዓይነት ምክንያት አይከፈትም፡፡ የሚከፈትበት ምክንያት፣
ጊዜ፣የመክፈት ሥልጣን ያለው አካል አለ፡፡ በጥንድነት ፈተናም እንዲሁ ነው፡፡ እንደ መግቢያው በር ሁሉ የመውጫ የአደጋ ጊዜም በር
ያስፈልጋል፡፡ መግቢያ ብቻ ያለው ባለ አንድ በር ቤት ለጥንድነት አይመከርም፡፡ ዐውቀን የዘጋነው፤ በአደጋ ጊዜ ግን ልንከፍተው
የምንችለው፣ የመጨረሻው አማራጫችን እርሱ ሲሆን ዘለን የምንወጣበት የአደጋ ጊዜ በር ያስፈልጋል፡፡ ‹እኔ በዚህ አልስማማም፣ የእኔ
ሃሳብ የተለየ ነው፣ እኔ በዚህ መኪና ተሳፍሬ እስክገለበጥ ድረስ አልጓዝም› ብለን ልንናገርበት የምንችለው በር፡፡ ጥንድነት ዕድልና
መብት እንጂ ዕዳና ግዴታ እንዳይሆን፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ፍራንክፈርት፣ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ
U said right our brother kale hiywot yasemah
ReplyDeleteየዚህ ጽሑፍ ዋና መልእክት ሁለት የተለያዩ አካላትን ጥምረት ጥቅም ወይ ጉዳት ለማሳየት ቢሆንም ዳኒ የተጠቀምክባቸው ምሳሌዎች ላይ ግን ቅሬታ አለኝ። ለመሆኑ ባልና ሚስት ሁለት አካል ወይስ አንድ ፤ ቀኝና ግራ እግር ወይም እጅስ፤ በአንድ ሰውነት ያሉ ሁለት ነገሮች። ያንዱ ጥንካሬ ለሌላው ጥንካሬ እንደሆነ ሁሉ ያንዱ ድካምም እንደዛው ነው። ቀኜ ጠንካራ ስለሆነ በግራዬ ካማረረ ችግሩ የአንድ ሰውነት አካል መሆንን ያለመቀበል ድክመት ይሆናል። በአጭሩ ጋብቻ ጥንድ የመሆን ሳይሆን አንድ የመሆን ምስጢር ነው። በአንድነት ውስጥ ደግሞ የአንድነት ጥንካሬ ፣ ጤና ፣ ሰላም ፣ፍቅር የአንድነት ድካም፣ህመም፣ማታት ፣መስነፍ እንጂ ያንተ ያንቺ ሊኖር አይገባም።
Delete@ 12:05PM
DeleteI think you better dig further to understand marriage. My education on marriage says that marriage is leading a house with two opinions. The two opinion are always there and equal in there capacity, but they lead only one house. This very fact needs how to entertain the two opinions especially when they are different.
In the area of marriage our custom is declining, it needs attention from all stake holders. The stake holders needs also further knowledge on the very facts of marriage.
Partnership in marriage is always there, it is the life they lead is one /unified/. But I agree that in any work one of the two partners may be the role player, but it should not be said he is keeping the house. Even the concept of keeping comes due to the other partner. I always feel that for the pot to serve the water inside for the user it needs stone support, and the work of the stone should not be neglicated. But lessons from the works of one partner should be taken in the absence blaming the other, as the result is of both.
Even though it is too tough to express on the subject matter shortly let me finish by the above only.
አራት እግር ያለው መኪና አንዱ ጎማ ሲተነፍስ የሚቆመው ለምንድን ነው? ጥንድ የመሆን ፈተና ገጥሞት አይደል፡፡ ያልተነፈሱት ሦስት ጎማዎች በተነፈሰው አንድ ጎማ ምክንያት መቆማቸው የግድ ነው፡፡ ስንት የተጣመሩ ፓርቲዎች ከመካከላቸው እንደ ካልሲው የተቀደደ፣ እንደ ጎማው የተነፈሰ ሲያጋጥማቸው አይደል ቆመው ወይም ፈርሰው የቀሩት፡፡
ReplyDeleteGood views.
ReplyDeleteRegarding couples in marriage (which is the foundation of family) the globalists do not want such life enabling social contract to thrive and prosper.Around two years ago a friend of me informed me the following website about such conspiracy. It is such an aye opening information to read.
http://www.savethemales.ca/001904.html
http://henrymakow.com/220801.html
You write exactly my personal story! Tidar gojo endih kehone minale lebicha shi amet kurmit bilu!
ReplyDeleteHonestly speaking this article is not impressive unless it has an objective of promoting Ato Getahun.
ReplyDeleteTo speak honestly, first you have to be honest for yourself, but not. If you do not learn from or understand this article, you are not honest.
Delete" You are nor honest if you don't understand this article" ? What does this mean? ..
DeleteArticle is not God's word..
wey dani , gud eko new , eyetaweche hulu astemariwech nachew , ye teru memeher wetet endehonke yasmesekeral . beta bezehu ketel .
ReplyDeletehooo dani eyetaweche hulu betam astematri ena denke nachew , antem yasmesekerkew yanten tebib ena asteway mehonehen becha sayhon yastemaruhe memeroch wetet mehoneh new , berta tenkerehe sera yanen new agerem hezbem , EGZIABEHEREM yemiwedew . TEBAREK ABZETO YESTEHE
ReplyDeletebequsawi negr enji hiwt balew negr ayaskedm
ReplyDeleteWow!! Yeliben Negerkegn. God bless you
ReplyDeleteድንቅ እይታ ነው ዲን. ዳንኤል፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ የአገልግሎት እድሜህን ያርዝምልን።
ReplyDeletekale hiywot yasemah melkam mikir.
ReplyDeleteDani! . . . yih fetena beyetignawum akitacha ale mallet new. tikim gin yelewum.
ReplyDeleteHulum kumnegern+kechewata.yeyazenew.enameseginalen.D.n Daniel.
ReplyDeleteasedemaryam ke Frankfurt.
Dani, you are our manual and our asset I always excited by your writing system I wonder you.
ReplyDeleteIgziabiher yibarkih, barkohallimm.
ReplyDeleteEGEZIABHER yebarekeh!!!! Barkohalemem
DeleteI LOVED IT DANIYE
ReplyDeleteBINI
i have no word 2 thank u any way God bless u
ReplyDeleteIt seems supporting divorce. Is that? If so, what about the coexisting or harmonizing? spirituality? ...
ReplyDeleteምን ነው ዳኒ እረሳኸው ካልስ እኮ አንዳንዴ ተስፍቶ ይለበሳል፡፡አንዱ አይነት እይታ ብቻ ነው የፃፍከው፡፡
ReplyDeletenice perspective. very wise.
Deletebetam arif miliketa new!!!
ReplyDeleteRome ena Bergude. Denke new Dani
ReplyDeleteለብዙ ነገሮች እስማማለሁ፡፡ በትዳር ጥንድነት ግን የመውጫ በር ሊኖር አይገባም ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ ለዚህኛው ጥንድነት ዝሙት መውጫ በር ነው የሚለኝ ካለ ያማ ዙሪያው በር ሆኖ (ፈርሶ) ነው እላለሁ፡፡
ReplyDeleteThank you so much the Anonymous person, he is trying to separate husband and wife. Divource is not allowed in our church.
DeleteBebizu neger esmamalehu, betidar gin alsmamam.
DeleteThanks my dear..
DeleteCan you imagine looking/prepare an emergence exit for marriage ? It is so funny especially hearing such ideas from Dn. Daniel , son of our church ( Ethiopian Orthodox), preacher and social blogger..;-))
He is a human being no body is perfect. When someone is working hard it may some mistake please don't take all his advice like God words. Daneil knows that divorce is not support by Bible however his personal opinion is matter. Some people evenif they know God is not allowed to do something. They follow their personal opinion. We have to pray for him because he have been working for us many years some times mistakes happned.
Deleteውድ ወንድሜ እኔ ዳኒ ከንስር ዓይኖቹ ያራቃቸውን ለማቅረብ እንጂ መምህሬን የክፉ ዓላማ አራማጅ (የቤተ-ክርስቲያናችንን ስርዓት አፍራሽ) ነው እያልኩ አይደለም፡፡ ይህንን ደግሞ ለሁለት አስርት ዓመታት በቃል በመጻፍ ከሱ ስቀበል ኖሬያለሁና በድፍረት መመስከር እችላለሁ፡፡ ‹ እግር እኔ እጅ አይደለሁምና የአካል ክፍል አይደለሁም ብትል ይህን በማለትዋ የአካል ክፍል መሆኑዋ ይቀራልን › ብሎ አስተምሮኛልና፡፡ ይልቅስ አንዱ ለሌላው ይጸልይ!!!
DeleteWindemoch,
DeleteWe all are talking about a single blog with a specific idea from this blog (emergence exit for marriage). We are not talking about Dn. Daniel's work for a couple of decades. It is undeniable that he is one of the very few wonderful son of the church. The point is care should always be taken while broadcasting to the society.
ፈጣሪ የበለጠ እውቀት ይግለጥልህ! እንዲህ ያሉ ማህበራዊ ምሁራን ያብዛልን!
ReplyDeleteTo get our good pairs,the best solution is prayer by which Our Lord can do a.d give whatever we want our good partners,Egziabher yistelen,ejig astemari tsehuf new
ReplyDeleteAs usual it is a lesson, but I can't publish in pdf, because I always download all these articles.
ReplyDeleteAs usual it is a lesson, but I can't print it in pdf. I always download and file in a folder all your articles.
ReplyDeleteFirs copy then past into microsoft word after that click Acrobat that appear the right side of the top catagory them click creat PDF. Shame on you, you don't know how to creat PDF at 21st century. If you need more information please come to us Magic Computer school. Address next to Merkato bus stop.
Deletegirum daneil ! please don't stay write day to day.
ReplyDeleteGod bless you.
ReplyDeleteThank you so much Dani. This is the main Ethiopian problem. We always think Tigray people and Eretria people are an Ethiopian but they are not. They are the problem of Ethiopia. We have been more than 500 year in war because of this two region. At the movement Eretria is not a problem for Ethiopian growth but we have to work hard to separate Tigray from Ethiopia then we can meet our goal. I belie the old sock is Tigray people and the new sock is Ethiopian. God bless you Dani.
ReplyDeletehow on earth you give this kind of meaning to this article?
Delete"God bless you Dani" Endezih aynet astesaseb yzeh gin endet new ye Egziabhern sim yemtiteraw? Lenegeru batawkew new enji btawks noro be Esu amsaya yetefeteren hizb( Be it Tigray, Eritrea, Oromo....) endezih bleh atankuashishm neber. Demo rasihn chal, be sew lai atinteltel. Ye Dn. Dani'n hasab wedante dekama astesaseb lemamtat atmokir. Dani lemalet yefelegewun blewal. Ante man new yesun terguami yaregeh ebakih.
DeleteYou always talk about politics, where is God, Marry, Church. Please go back into your past life. I will pray for you.
ReplyDeleteIt is wonderful view really! Keep it up Dani.
ReplyDeleteejehe yebarake
ReplyDeleteHiwot alew!
ReplyDeletewell said Dn.Daniel...i like your blogs.keep it up please....
ReplyDeleteMINDINWE YTSAFIKWE?
ReplyDeleteNice looking dear & i need more ..................
ReplyDeleteDear all,
ReplyDeleteWhy we be in a hurry to make one sided translation and voice???? Who said separation is the ultimate solution? In this age, at the 21st century when the Globe is coming closer and small countries are working to merge and form economically, socially giant countries, do we think and ever dream to separate and again commit the same mistakes that others have done? Separation of a family, husband and wife, brothers and sisters, friends, etc are all the results of the Devil. Pls,lets think in another angle, narrow our differences and win those who have selfish political agenda. And this will be our exit mechanism.
ዳኒ የተመሳሳይ ፆታ ጥንድ መሆንን ምን ትለዋለህ? እግዜር ከዚህ ይጠብቀን!
ReplyDeleteዲ. ዳንኤል እጅግ በጣም ስራዎችህን ስለምወዳቸዉ ሙሉ አካላትህ ረዥም የስራ ዘመናት ይኑራቸዉ፡፡ አምላክ ያበርታህ!
ReplyDeletesima Dnai,
ReplyDeleteR U married?
or are you same people as business advisors who doesn't have a business for thmesleves!
I think you and some guys have missed the concept of this article. The article did not enhance divorce, instead it suggest what should be considered before marriage. Besides it also says that partnership in all aspects may not be successful. Even though it does not explicitly says what I understand from the article is that the only way to continue with partnership is appreciating those differences.
DeleteI feel also the best way besides improvement in manner in the marriage world is to appreciate the hard fact in our partners. What I understand and define love is giving with out expecting. To be a house holder one has to marry, to have this one has to withstand the problem of his partner.
Good choose for partner in the marriage world helps not more than 50%, instead how to live on marriage gives 100% relief in life. And I understand what Daniel says is one has to know how to live.
I am not in fever of Daniel, but I do not feel ashamed if I had had in fever of him.
አሁንም ተባረክ፡፡እግዚአብሔር ስለ እኛ ስለማናስተውልና አይነ ስውር ልጆቹ ሲል የአንተን የማስተዋል አይን ይበልጥ ያተልቅልህ፡፡ሁሌም በምህረቱና በፍቅሩ ያስብህ፡፡
ReplyDeleteጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመወጣት አንድም የዳበረ የኑሮ ጥበብ ያሻል፣ አንድም የታሰበበትና ተገቢ የሆነ የጥንድነት ልማድና ሕግ ያስፈልጋል፤ አንድም ደግሞ ከፈተናው የመውጫ ውጤታማ የአደጋ ጊዜ በር ሊሠራ ይገባል፡፡ ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመከላከል፣ ካልሆነም ለመፍታት የሚያስችል ከማኅበረሰቡ ጋር የተዋሐደ የኑሮ ጥበብ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን የኑሮ ጥበብ ለመገንባት ደግሞ የሃይማኖት ትምህርቶች፣ ሥነ ቃል፣ ሚዲያና ዘመናዊ የኑሮ ዘዴ ትምህርቶች ታላቅ አስተዋጽዖ ያደርጋሉ፡፡
ReplyDeleteዲ. ዳንኤል እጅግ በጣም ስራዎችህን ስለምወዳቸዉ ሙሉ አካላትህ ረዥም የስራ ዘመናት ይኑራቸዉ፡፡ አምላክ ያበርታህ!
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እንደምን አለህ? ቃለ ህይወት ያሰማልን!
ReplyDeleteእኔ እምለው ግን ለመሆኑ አገር የሚባለው ጋራውና ሸንተረሩ ነው ወይስ ሰዉ? አለያስ የሁለቱ ጥምረት?
መሬቱ ከሆነ አገር የሚባለው፣ በእርግጥ አገር አለን ብየ እስማማለሁ! ሰዉ ከሆነ አገር የሚባለው አገር አለን ብየ የማምነው “እግዚአበሔር ሰውን ተንኮለኛና ምቀኛ አድርጎ ፈጠረው” ከተባለ ነው፡፡ መልካም ሰዎች የሉም ብየ አይደለም ፤ ነገር ግን ከሚያጋጥምህ ብዙው እንዲህ ሆኖ ስታገኘው ትደመድማለህ፡፡ ስለዚህ አገር የሚባለው ሰዉ ከሆነ አገር የለንም ማለት ነው፡፡
የሁለቱ ጥምረትም ከሆነ አገር የሚባለው፣ አሁን ከአገር ክፍሎች (components) አንዱ ይጎድላል ማለት ነውና አገራችን ጎደሎ ናት፡፡
በጣም ተስፋ እየቆረጥኩ ስለሆነ ምን ትለኛለህ?
Three days before, we heard in the medias an Ethiopian domestic worker, who work in Kuwait, murdered a Kuwait girl and admitted it to the police. But after that her acts have caused lots of problems for other Ethiopian workers. Their employers and the people start acting differently towards them (as Dn Daniel well expressed it in this article) because of one person all Ethiopian workers have
ReplyDeleteConsidered as 'bad people.'
ጥንድነት የሚያመጣውን ፈተና ለመወጣት አንድም የዳበረ የኑሮ ጥበብ ያሻል
Deleteፍየል ቀንዷ ለምን ወደ ኋላ ዞረ? ሲባል፤ ስትገባ መውጫ መውጫውን ለማየት ነው አሉ፡፡
ReplyDeleteyou do explain it very well dear Daniel 'andande fetena new andande demo..........................' becha lebaleedar kaweran Egzeabher yerdan!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteትላልቅ የዕቃ መደብሮች ፡ ሆስፒታሎች ፡ በአጠቃላይ ብዙ ሰው ሊያሰባስቡ የሚችሉ ቦታዎች ፡ ለአደጋ ገዜ ብቻ የሚያገለግል ፡ በተረፈ ግን ሁሌ ተዘግቶ የሚኖር በር አላቸው ፡፡ አደጋ ቢነሳ ለማምለጫ ነው፡፡
ReplyDeleteየአስተያየት ሰጭው ቁጥር ግን በትዳር ላይ በርከት ብሏልና ፡ እስቲ ወደ ትዳሩ፡፡
በመጀመሪያ ተፋቱ የሚል ሃሳብ ዲ/ን ዳነኤል አላቀረበም ፡፡ ሰለዚህ አፍቃሪዎች ሆይ ተረጋጉ፡፡ ለአዳራሽ የአደጋ መዉጫ የሚዘጋጀው ፡ ሰው አስገብቶ አደጋ ለማድረስ ሳይሆን ፡ ለጥንቃቄ ነው፡፡
አቶ ጉተማ የተባሉ የሰፈሬ ሽማግሌ ትዝ አሉኝ ፡፡ በልጂነቴ ፡ ከጓደኞቼ ጋር ሰንጫወት በድንገት ብቅ ይሉና ፡ ያገኙትን ልጅ በቁንጥጫ ጆሮውን ወደላይ ይስቡታል፡፡
" ምን አርግኩኝ?" ብሎ ለጠየቀ መልሳቸው
" ምን የማታረጉት ነገር አለ" የሚል ነበር ፡፡
ልጥንቃቄ መሆኑ ነው ፡ ቁንጥጫ በታሳቢ!
ታዲያ ትዳርም ላይ እንደ ሠርጉ ሁሉ ፡ ፍችም ሊያጋጥም ይችላልና ፡ ቅድመ ዝግጅት ካለው ፡ በሁዋላ የከረረ ጦርነት የለውም፡፡ ተለያይቶም ወንድምና እህት መሆን ይቻላል፡፡
አንድ አምሳል አንድ አካል ነን ፡ ተዘጋጁ ማለት የሰይጣን ሃሳብ ነው የምትሉ ፡ የአብረሃምንና የሣራን ሕይወት እምኝላችሁዋለሁ! እንደምኞት ሳይሆን ቢቀር ግን ፡ እባካችሁ ቆንጨራ አትማዘዙ ፡፡
በቀዳዳው ካልሲ ብዛት ፡ ሳይሳኩ የቅሩት የስራ ውጥኖች ብዛት ቀላል አይደለም፡፡ ብዙ ሰው ፈጣሪ " ጥረህ ግረህ ፡ እንጀራህን ብላት " እንዳለው አልሰማም ወይም አይሰማኝም ብሎ ትቶታል ፡፡ የስው እንጀራ ሲያቆመጥጥ ይኖራል!
ቀዳዳ ካልሲ በፖለቲካው ፡- ይህ በጣም ሰፊ መወያያ ነጥብ ነው ፡፡ ለግዚው የሙሉቀን ዘፈን ላይ ያል ግጥም
እኔም ልጅ እሷም ልጅ ተጋቡ ይሉናል
የተሰቀለውን ማን ያወርድልናል
በቸር ይግጠመን!
ጌቱ ከጀርመን
ግሩም አስተማሪ ጽሑፍ ነው :: ቃለ ሕይወት ያሰማልን እድሜና ጤና ይስጥልን ::
ReplyDelete