Thursday, March 6, 2014

ሕመሜ

አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያብሰከስከው፡፡ ሯጮቻችን ሲያሸንፉ፣ ተጨዋቾቻችን ድል ሲያደርጉ፣ ስለ ኢትዮጵያ መልካም ነገር ሲሰማና ሲነገር፣ በሀገሩ ላይ ልማትና ዕድገት ሲታይ፣ አንዳች የሆነ ሀገራዊ ለውጥ ሲታይ፣ ይፈነድቃል፤ መልክዐ ገጹ ይፈካል፤ ደስታው ከልክ አልፎ ጣራ ይነካል፡፡ የሚያሳዝን፣ አንገት የሚያስደፋ፣ የሀገርን ስም የሚሰብር፣ ገጽዋን የሚያበላሽ ነገር ሲሰማና ሲያይ ደግሞ ከሥራ እንደተባረረ ሠራተኛ አንገቱን ይደፋል፤ የእናቱን መርዶ እንደ ሰማ ልጅ ዓይኑ ዕንባ ይሞላል፤ ከጨለማ እሥር ቤት እንደ ገባ እሥረኛ ፊቱ ከል ይለብሳል፤ ሲብሰከሰክ ሲብከነከን ውሎ ያድራል፡፡
አንድ ቀን ‹‹ለአንተ ግን ሀገር ማለት ምንድን ናት? ወይስ ያንተ ሀገር የተለየች ናት? ምን እንደዚህ ያብከነክንሃል?›› አልኩት፡፡
‹‹ታውቃለህ›› አለኝ ፊቱን በቀኝ መዳፉ እየሞዠለጠ፡፡ የጎፈረ ፀጉሩን ደግሞ በግራ ጣቶቹ ይልጋቸዋል፡፡ አጭርና ድንቡሼ ነው፡፡ ወግ ሲጀምር ‹ታውቃለህ› ማለት ይቀናዋል፡፡
‹‹ታውቃለህ፤ ሀገር ማለት ‹ሕመሜ› ማለት ናት›› አለኝ፡፡ ከንፈርና አፍንጫዬን አገናኚቼ በጆሮዬ በኩል ወሬውን ዋጥኩና ወደ ኋላዬ ለጠጥ አልኩ፡፡ ሰምቼው የማላውቀው ትርጓሜ ነው፡፡ ‹‹ሀገር ማለት ሕመሜ ነው››፡፡ ይህንን ሳሰላስል ‹‹ሕመም ያልኩህ እንዳይመስልህ፣ ‹ሕመሜ› ነው ያልኩህ›› አለኝ፡፡
‹‹ሕመምና ሕመሜ፣ ምን ልዩነት አላቸው››

‹‹ዘፋኞችና አንጎራጓሪዎች በጣም የሚወዱትን ሰው ‹ሕመሜ› እያሉ ሲዘፍኑለት ሰምተህ አታውቅም››
‹‹ዐውቃለሁ፡፡ ታድያ ሀገርና ያ ምን ና ምን ናቸው››
‹‹የጆሮ ጉትቻ ያንገት ሐብል ናቸው - አልልህም መቼም›› አለኝ፡፡
‹‹ሕመሜ እያሉ የሚዘፍኑትኮ ስለሚወዱት ነገር ነው፡፡ እያለቀሱ አይምሰልህ፤ ሙሾ እያወረዱም አይደለም፤ የኀዘን እንጉርጉሮ እያዘነቡም አይደለም፡፡ ደስ ብሏቸው እየዘፈኑ ነው፡፡ እስክስታ እየወረዱ የሚዘፍኑት ግን ‹ሕመሜ› እያሉ ነው፡፡ የሚወዱትን፣ ሊያገኙት የሚፈልጉትን፣ እንዲያጡት የማይሹትን፣ መልካሙን ነገር ሁሉ የሚመኙለትን፤ ልቤ፣ አንጀቴ፣ ኩላሊቴ፣ ዓይኔ፣ ሆዴ፣ ነፍሴ የሚሉትን፤ ሞትም አይለየንም፣ ካንተ ውጭ ሌላ አልሻም፣ ሌላው ሁሉ ሰው አይመስለኝም፣ የሚሉለትን ፍቅረኛቸውን ‹ሕመሜ› እያሉ ይዘፍኑለታል፡፡
‹‹ አየህ ይህ ፍቅራቸው ሕመም ያለው ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር ብቻ አይደለም፡፡ ሰናፍጭ ነው ያድናል፣ ግን ይሰነፍጣል፤ ሚጥሚጣ ነው ደስ ይላል፣ ግን ያቃጥላል፤ መርፌ ነው ይፈውሳል፣ ግን ያማል፤ ፈረስ ነው ይጋልባል፣ ግን ይገለብጣል፤ የሱፍ አበባ ነው ይመስጣል፣ ግን በእሾህ ተከብቧል፡፡ ውስጡ ደስ የሚል ሕመም አለበት፡፡ ደስታ ነው ብለህ እፎይ እንዳትል ሕመሙ እንደ ፍልስጣ ጎን ጎንህን ይወጋሃል፤ ሕመም ነው ብለህ እንዳትተወው ደስታው እንደ ወይን ጠጅ ‹እስኩ ድግሙ ድግሙ› ያሰኝሃል፡፡ ለዚህ ነው ‹ሕመሜ› እያልክ የምትዘፍንለት፡፡ የሚዘፈንለት ሕመም አይተህ ታውቃለህ? ሕመምን ይታከሙታል እንጂ ይዘፍኑለታል እንዴ? ሕመምን ያስታግሡታል እንጂ ያዜሙለታል እንዴ? እንዲያ ነው የምልህ፡፡
‹‹እና ሀገር እንዴት ነው ‹ሕመሜ› የምትሆነው?›› አልኩት ፍልስፍናው ደስ ብሎኝ፡፡ በጎድጓዳ መንገድ እንደሚሄድ ገልባጭ መኪና ወደ ግራና ወደ ቀኝ ወዝወዝ ብዬ ተስተካከልኩ፡፡
‹‹ሀገርማ ደንበኛዋ ‹ሕመሜ› ናት፡፡ ሀገር ብለህ ስታስብ ጤናና ሕመም ነው የሚሰማህ፡፡ የምትኮራበት፣ ምነው በዚያ ዘመን በኖርኩ ብለህ የምትመኝበት፣ ስታየውና ስትሰማው ደምህ የሚሞቅበት፣ ስታስበውና ስትናገረው ኩራትህ የሚጨምርበት ነገር አላት ሀገር፡፡ ምን እንደሆነ የማታውቀው እንዲሁ ፍቅር የምታስይዝህ ነገር አላት ሀገር፡፡ ታስጨፍርሃለች፣ ታስቦርቅሃለች፣ ታስዘልልሃለች ሀገር፡፡ የትም ቦታ ሆነህ ስሟን ስትሰማው ልብህን ቀጥ የሚያደርግ ነገር አላት ሀገር፡፡ ሙትልኝ ሙትልኝ፣ ድማልኝ ድመልኝ፣ ተሠዋ፣ተሠዋ የሚያሰኝ ኃይል አላት ሀገር፡፡ ምንም ጥቅም ሳታገኝ፣ ምንም ነገር ላንተ ሳይደርስህ፣ የሞተላት ቀርቶ የገደላት እየበላ እንኳን ቢሆን፤ ሞኝ ነሽ ተላላ እያል እየዘፈንክላትም ቢሆን፣ ላንዱ በጭልፋ ላንዱ በአካፋ እየሰጠች እንኳን ቢሆን፤ አንዱ እንገሯን አንዱ አሬራዋን እየጠጣም ቢሆን፤ ላንዱ ቅቤ ላንዱ ዝቃቅቤ እየሰጠችውም ቢሆን - ግን በፍቅር እንድትሞትላት የሚያደርግ ኃይል አላት ሀገር፡፡ እንዳትቀየማት፣ ቂም እንዳትይዝባት፣ እንዲሁ ይቅር እንድትላት የሚያደርግ ኃይል አላት ሀገር፡፡
‹‹ደግሞ ገልብጠህ ስታያት ሀገር ሕመም ናት፡፡ ቀዶ ጥገና አድርገህ የማታወጣት፣ ቆርጠህ የማትገላገላት፤ ታክመህ የማትድናት፤ በአበሻ መድኃኒት ነቅለህ የማትጥላት፤ ኮሶ ወስደህ የማታሽራት፤ ሕመምህ ናት ሀገር፡፡ ምነው እዚህ ሀገር ባልተደረገ የምትለው ስንት ታሪክ አላት፤ ምነው በዜጋሽ ላይ እንዲህ ታደርጊያለሽ ብለህ የምታዝንባት ስንት ግፍ አለባት ሀገር፤ ምነው እንደ እንጀራ እናት ታዳያለሽ ብለህ አንጀትህ እርር የሚልባት ስንት አድሎ አላት ሀገር፤ አንዱ
ሀገሬ ኢትዮጵያ ምድራዊት ገነት
አደላድለሽኛል በሥልጣንና በሀብት፣
ብሎ ሲያወድሳት፣ አንተ ግን -
ሀገሬ ኢትዮጵያ ምድራዊት ገነት
እስኪ ፈልጊልኝ የሚከራይ ቤት፣
 ትላታለህ፤
ለሚያሥረው ሀገር ናት፣ ለታሣሪው ሀገር፤ ለገዳይ ሀገር ናት ለሟቹም ሰው ሀገር፤ ለአሳዳጅ ሀገር ናት ለተሰዳጅ ሀገር፡፡
‹‹ ‹ሌቦ› እያሉ እንደመዝፈን ያለ፡፡ አሁን ለሌባ ምን ይዘፈንለታል፡፡ ሀገርህ ሰጭ፣ ለጋስ፣ ቸር፣ ደግ፣ ብቻ አይደለችም፡፡ ሀገርህ ሌቦም ናት፡፡ የስንቱን ሕጻን፣ ወጣት፣ ሽማግሌ፣ ልጃገረድ፣ እናት፣ ባልቴት ሕይወት ቀጥፋ ነው እዚህ የደረሰችው፡፡ ግን ሌባ አይደለችም ‹‹ሌቦ›› ናት፡፡ የሚዘፈንላት ሌባ ማለት ነው፡፡ ‹‹ያዛት፣ ያዛት፣ በላት፣ በላት፣ ኡኡኡ›› ብለህ በፖሊስ የምታስይዛት፣ በጎረምሳ የምታስደበድባት ሌባ አይደለችም፡፡የምትዘፍንላት ‹ሌቦ››፡፡
አሣሪ ሆነህ እንደወድካት ሁሉ ታሣሪም ሆነህ ትወዳታለህ፣ አሳዳጅ ሆነህ እንደወደድካት ሁሉ ተሳዳጅ ሆነህም ትወዳታለህ፤ ቀማኛ ሆነህ እንደወደድካት ሁሉ ተቀምተህም ትወዳታለህ፤ተምረህ እንደወደድካት ሁሉ ደንቁረህም ትወዳታልህ፡፡ ሀገር ማለት ይህቺ ናት፡፡ ሀገር ‹‹ሕመሜ›› ናት፡፡ ሀገር አደዋ አላት፤ ሀገር ማይጨው አላት፡፡ የአኩስም ሐውልት አላት፣ የቆሻሻ ክምርም አላት፤ መንገድ ሠሪም አላት፣ መንገድ ላይ የሚሸናም አላት፤ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የስልክ ታሪክ አላት፣ ከአፍሪካ መጨረሻ የሆነ የስልክ ኔትወርክም አላት፤ ታሪክ ትሠራለች፣ ታሪክም ታፈርሳለች፤ ቅርስ ትሠራለች፣ ቅርስም ታፈርሳለች፡፡ ሀገርህ ይህቺ ናት፡፡
‹‹ርግፍ አድርጌ ልተዋት ብትል እሺ አትልህም፡፡ ለቅቀሃት በመሄድ፣ ጥለሃት በመጥፋት፣ ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም፡፡ ሞተህ እንኳን አትለቅህም፣ አስከሬን ታስጭንሃለች፡፡ ደግሞ በዚያ ወገን ዝም ብዬ ብቻ ልውደድሽ፤ ዝም ብዬ ብቻ ላድንቅሽ ስትላት ደግሞ እሺ አትልህም፡፡ አንዳች ሕመም ነገር አላት፡፡ ያለህ አማራጭ ‹‹ሕመሜ›› እያልክ መዝፈን ነው፡፡ በሳቅህ ውስጥ ልቅሶ፣ በልቅሶም ውስጥ ሳቅ ትቀላቅልብሃለች፡፡ የጠቦቱን ሥጋ ከመራራ ቅጠል ጋር ታበላሃለች፡፡
‹‹ለእኔ ሀገር ማለት ይህቺ ነች፡፡ ‹‹ሕመሜ›› ››
ዝም ብዬ አየሁት፡፡
 © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

53 comments:

 1. What an extraordinary view! Very well done Dani!

  ReplyDelete
 2. What an extraordinary view! Very well done, Dani!

  ReplyDelete
 3. What an extraordinary view! Very well done, Dani!

  ReplyDelete
 4. ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም፡፡ ሞተህ እንኳን አትለቅህም፣ አስከሬን ታስጭንሃለች፡

  ReplyDelete
 5. ዳንኤል እንደምን ነህ

  በጣም ደስ የሚል መጣጥፍ ነው

  በትክክል ነው የሀገር ስሜት የተገለጸው፤፤

  መድሐኒዓለም ሀገራችንን ይጠብቅልን፡፡

  ወለተ ሚካኤል

  ReplyDelete
 6. እውነት ነው ዳኒ ከዚህ በላይ ሀገርን የሚያህል ለዚያውም እምዬ ኢትዮጵያ ብለን ስሙዋን እንኳን ስንጠራ እንባ የሚቀድመን በህመሙዋ ፍቅር ህይወታችንን ሰጥተናትም የማንረካ ምንጊዜም ከራሳችን በላይ የምንሳሳላት መግነጢሳዊ ሀይል ያላት ረቂቅ ህመማችን/ህመሜ/ ነች ሀገር እውነት ነው ዳኒ በሚገባ ገልፀሀታል እግዜር ይስጥልኝ ወዳጄ

  ReplyDelete
 7. በትክክል ኢትዮጵያ ህመሜ ነች.

  ReplyDelete
 8. ምንም ነገር ላንተ ሳይደርስህ፣ የሞተላት ቀርቶ የገደላት እየበላ እንኳን ቢሆን፤ ሞኝ ነሽ ተላላ እያል እየዘፈንክላትም ቢሆን፣ ላንዱ በጭልፋ ላንዱ በአካፋ እየሰጠች እንኳን ቢሆን፤ አንዱ እንገሯን አንዱ አሬራዋን እየጠጣም ቢሆን፤ ላንዱ ቅቤ ላንዱ ዝቃቅቤ እየሰጠችውም ቢሆን - ግን በፍቅር እንድትሞትላት የሚያደርግ ኃይል አላት ሀገር፡፡ እንዳትቀየማት፣ ቂም እንዳትይዝባት፣ እንዲሁ ይቅር እንድትላት የሚያደርግ ኃይል አላት ሀገር፡፡

  ReplyDelete
 9. አሣሪ ሆነህ እንደወድካት ሁሉ ታሣሪም ሆነህ ትወዳታለህ፣ አሳዳጅ ሆነህ እንደወደድካት ሁሉ ተሳዳጅ ሆነህም ትወዳታለህ፤ ቀማኛ ሆነህ እንደወደድካት ሁሉ ተቀምተህም ትወዳታለህ፤ተምረህ እንደወደድካት ሁሉ ደንቁረህም ትወዳታልህ፡፡ ሀገር ማለት ይህቺ ናት፡፡

  ReplyDelete
 10. ለቅቀሃት በመሄድ፣ ጥለሃት በመጥፋት፣ ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም

  ReplyDelete
 11. ሀገር ‹‹ሕመሜ›› ናት፡፡ ሀገር አደዋ አላት፤ ሀገር ማይጨው አላት፡፡ የአኩስም ሐውልት አላት፣ የቆሻሻ ክምርም አላት፤ መንገድ ሠሪም አላት፣ መንገድ ላይ የሚሸናም አላት፤ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የስልክ ታሪክ አላት፣ ከአፍሪካ መጨረሻ የሆነ የስልክ ኔትወርክም አላት፤ ታሪክ ትሠራለች፣ ታሪክም ታፈርሳለች፤ ቅርስ ትሠራለች፣ ቅርስም ታፈርሳለች፡፡ ሀገርህ ይህቺ ናት፡፡

  ReplyDelete
 12. ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም፡፡ ሞተህ እንኳን አትለቅህም፣ አስከሬን ታስጭንሃለች፡:
  እንዲህ አይነት ብርቱ ፍቅር ያላት ማን እንበላት? ህመሜ::

  ReplyDelete
 13. Well said, Dani.

  ReplyDelete
 14. በእውነት ዲ/ ዳንኤል የልባችን ነው የነገርከን ኢትዮጵያ ለዘላለም ህመሜ ናት፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ለዘላለም ይባርክ እኛንም በፍቅራ ያጽናን.....

  ReplyDelete
 15. ሀገሬ ኢትዮጵያ ምድራዊ ገነት
  እስኪ ፈልጊልኝ የሚከራይ ቤት....!!!!!!

  ReplyDelete
 16. Ye himemun mastagesha enigelig!

  ReplyDelete
 17. Getahun
  "‹ህመሜ" አልካት ዳኒ እውነት ነው ለእኔም ህመሜ ናት
  ዳኒ እድመህን ያራዚምህ አንቴን ያኑርልን this ie fact tale.

  ReplyDelete
 18. this deep feeling of "himeme" some still trying hard to extinguish but it still does exist.......wow dani u reminded me a friend....in the yr 1997 crisis we were in campus and the sene 1 massacre was on, same day he and his friends organized and donated blood, after he finished what he could, went to a dorm and cried loud, i couldnt resist my tears! still now he is my hidden hero, my best friend!!!
  ya Ethiopia is himeme

  ReplyDelete
 19. "‹ህመሜ" አልካት ዳኒ እውነት ነው ለእኔም ህመሜ ናት
  ዳኒ እድመህን ያራዚምህ አንቴን ያኑርልን this ie fact tale.

  ReplyDelete
 20. ህመሜ.......ህመሜ.......ህመሜ.......ህመሜ........ህመሜ

  ReplyDelete
 21. wow ! can any body give me why I cry?

  ReplyDelete
 22. Haha... Hager ende Alemayehu Atomsam merz fut belew yemimotubatim nat....

  ReplyDelete
 23. lib yemineka......awon hager.....kalate yelewem ....

  ReplyDelete
 24. የደም ያጥንት ስባሪ ርፍራፊ ማህተም ያለባት እምታምር የፅጌረዳ አበባ ናት፡፡

  ReplyDelete
 25. Dn.Getaye Ze LalibelaMarch 10, 2014 at 10:38 AM

  ዲ/ን ዳንኤል ሀገር ህመም ብቻ አይደለችም…. ፡፡
  አንተ እንደጠቀስከው ሀገር ወንዙ፣ ተራራው፣ ሸለቆው፣ ጫካው፣ እርሻው፣ የዱር አራዊቱ፣ እንስሳቱ፣ አእዋፋቱ፣ ወንዞቹ፣ ሐይቆቹ ሁሉ ሀገር ናቸው፡፡ እንዲሁም እነዚህን የሚጠብቃቸው፣ የሚንከባከባቸው፣ የሚያለማቸው፣ የሚሠራባቸው፣ የሚኖርባቸው ዋናው ተዋናይ ሰው ነው፡፡ ሀገር ተፈጥሮ ያደላት፣ አራቱም ወቅቶች የሚፈራቁባት፣ የተንጣለሉ ሐይቆች ቢኖራ፣ እየተንጎማለሉ የሚፈሱ ወንዞችም ቢከቧት፣ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች ቢኖሯት፣ የትም ዓለም የሌሉ ብርቅየ አእዋፋት፣ እንስሳት፣ የዱር አራዊት ቢገኙባትም፤ ለእድገት፣ ለብልጽግና፣ ለልማት፣ ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ፣ በልቶ ጠጥቶ ለማደር፣ ትውልድ ለመተካት የሚችለው ሰው ብቻ ነው፡፡
  ለሀገር መድኃኒቱም ሰው ነው፣ በሽታውም ሰው ነው፤ ስለዚህ ሀገር ህመም ብቻ ሳትሆን በሽታም ነው፡፡ የሚያዛምተውም፣ የሚያስተላልፈውም፣ ሰው ነው፡፡
   ሰው ሲታሰር አሳሪው ሰው ነው፤
   ሰው ሲገደል ገዳዩም ሰው ነው፤
   ሰው ድኃ እንዲሆን የድኅነት ምንጩም ሰው ነው፤
   ገንዘብ ሲዘረፍ ዘራፊው ሰው ነው፤
   መሬት ሲሸጥ ሲለወጥ ሻጩ ለዋጩም ሰው ነው፤
  ለሰው ጽድቅም ይስማማዋል ኃጢአጥም ይስማማዋል፡፡ በጎ ነገር ሲሰራም ይስማማዋል ጠማማ ነገር ሲሰራም ይስማማዋል፡፡ አባቶቻችን ‹‹ሰብዕ ይቄድሶ ለመካን፤ መካን ይቄድሶ ለሰብዕ፤ ለው ሀገርን፣ ቦታን ይቀድሳል፤ ሀገር ሰውን ይቀድሳል›› ይላሉ፡፡ ስለዚህ ሀገር ማለት ሰውና አካባቢው ነው፡፡
  ሀገርን ለማሳደግ፣ ሀገርን ባለጸጋ ለማድረግ፣ ሀገርን ለመጠበቅ፣ በሀገር ላይ ታሪክ ለመሥራት፣ ተምሮ ለመለወጥ ጥሩ ዜጋ በማፍራት፣ ወርቃማ ትውልድ በመፍጠር፣ ሥነ ምግባር ያለው ምሁር በማፍራት፣ ሀገር ወዳድ ጀግና በመፍጠር ነው፡፡ ይህ ካሆነ ሀገር እውነትም ህመም ነች፡፡ ለህመሙም፤ ለፈውሱም መድኃኒቱና መፍትሔው ሰው ነው፡፡

  ReplyDelete
 26. ሐገር ብዙ ይባልለታ አንተም ፣አንቺም ፣አንቱም ፣እንሱም ፣ እናንተም ፣ስለዚህ መገለጫዋ ብዙ በመሆኑ ህመሜ ብለን ብንደመድም ጥሩ አባባል እንደሆነ ይሰማኛል

  ReplyDelete
 27. It is very touching! Thankyou Dn.Daniel.

  ReplyDelete
 28. ሀገር ማለት አውነትም ህመሜ ናት መርዝ አጠጥቶ የሚገድለውንም በሰው ንብረት ላይ እሳት እየለኮሰ የደሐውን ንብረት የሚያወድመውንም አንድላይ ሰብስባ የያዘች ህመሜሜሜሜሜሜ ነች፡፡

  ReplyDelete
 29. ሀገር ማለት እውነትም ህመሜ ናት


  ReplyDelete
 30. ሀገሬ ኢትዮጵያ ምድራዊት ገነት

  አደላድለሽኛል በሥልጣንና በሀብት፣

  ብሎ ሲያወድሳት፣ አንተ ግን -

  ሀገሬ ኢትዮጵያ ምድራዊት ገነት

  እስኪ ፈልጊልኝ የሚከራይ ቤት፣ ሁሉም ይወዳታል አልክ የሚወዳትስ የሞተላት ታሪኳን የጠበቀ ነው በሀብትና በስልጣን የተንበሻበሸውማ ያደማታል ተባረክ

  ReplyDelete
 31. simply "himemie" well expressed!!!
  thank you Daniel

  ReplyDelete
 32. ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም፡፡ ሞተህ እንኳን አትለቅህም፣ አስከሬን ታስጭንሃለች፡

  ReplyDelete
 33. ዜግነት ቀይረህ፣ ቋንቋህን ለውጠህ እንኳን እሺ ብላ አትተውህም፡፡ ሞተህ እንኳን አትለቅህም፣ አስከሬን ታስጭንሃለች፡

  ReplyDelete
 34. I could not stop crying. Dani you are the 21st century hawaryaw kidus Pawlose. God bless you. long life.

  ReplyDelete
 35. dani i wish for you long life and yiaglegelot zemnhe yibarek betekekel gelitsehewl

  ReplyDelete
 36. አገላለጹ በጣም ገራሚ ነው፡፡ ሀገር በተለያየ መንገድ ትገለጻለች ፤ የአንተ አገላለጽ ግን በጣም ደስ ይላል፡፡ ታዲያ ምን ዋጋ አለዉ አሁን የሚታየዉ ነገር የተገላቢጦሽ እየሆነ አስቸገረ እንጂ.፡፡ እውነትም ሀገር ህመም ናት ፡፡፡

  ReplyDelete
 37. ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ የስልክ ታሪክ አላት፣ ከአፍሪካ መጨረሻ የሆነ የስልክ ኔትወርክም አላት well said Dn.Daniel Bless U.

  ህመሜ.......ህመሜ.......ህመሜ.......ህመሜ........ህመሜ

  ReplyDelete
 38. እዉነተት ነዉ ህመሜ ናት ግን ሁሉም እኩል ይታመምላታል የዬ አላስብም

  ReplyDelete
 39. በጣም ልብን የሚያሸብር መንፈስ ይፈጥራል "ህመሜ" ዋው!

  ReplyDelete
 40. ዳኒ ይህን ሰው ማን እንደሆነ ልገምት? በጋራ የምናውቀው አሉላ ይመስለኛል፡፡ ልክ ከሆንኩኝ ልክ ነሽ በለኝ፡፡ ታላቅ እውነት ያለበት ጽሑፍ፡፡ Thanks

  ReplyDelete
 41. wow i like this view.

  ReplyDelete
 42. " ህመሜ " መሰረተ ሃሳቡ ድንቅ ነው ፡፡ ይህን ጽሁፍ ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ስራዎችህን ሰለማደንቅ ፡ እግዜር ትንፋሽህን ያርዝመው!!! የውሃ ጠብታ ድንጋይ ይበሳል ፡ ይባል የለ፡፡

  ችግሩ ግን ፡ ለእኛ በአብዛኛው የአገር ፍቅርን መግለጫው ምላስ ብቻ መሆኑ ነው ፡፡ አገር የምንለው ቀዬውን ብቻ ሳይሆን ፡ ህዝቡን ባህሉን እና ሌላ ሌላውንም ነው ፡፡ አገር እንዲያድግ የእያንዳንዱ ዜጋ ኑሮ መሻሻል አለበት ፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ አንዱ ለአንዱ ማሰብ ያስፈልገዋል፡፡ ሰዎች በደል ደርሶባቸው ሲያለቅሱ ፡ እንደ ቅማል " እራስ ደህና " የሚል ሰው ፡ ስለ አገር ፍቅር ቢያወራ ፡ ስሜት አይሰጥም፡፡

  እኔ በምኖርበት በጀርመን አገር ፡ ሰው ለአገሩ ያለው ፍቅር በትግባር የሚገለጽ ነው ፡፡ ሁለቱን አገሮች ለማውዳደር አይቃጣኝም ፡፡ የማይታሰብ ጉዳይ ነውና፡፡ እዚህ አበሾች " ጀርመኖች አገራቸውን ይወዳሉ " ይላሉ ፡፡ ለምን አይውደዱ? አሁን ላሜቦራን ማን ይጠላታል?

  አዚህ በየቢሮው ጉዳይ በቶሎ ማስፈጸም በለመደ ጎኔ ፡ የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ ፡ አዲስ አበባ ጉምሩክ ለጉዳይ ብቅ አልኩኝና ፡ ባለስልጣን ተብዬው እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ፡ ማንነቱን ሊያሳየኝ ሲንጎማለል አይቼ ፡ በትንሽነቱ አዘንኩለት፡፡ ሳይኖር ሟች! ለማኞች ምን እንደሚሰማቸው ለማወቅ ግን ፡ አጋጣሚው ትምህርት ሰጪ ነበር፡፡
  ይህ ግለሰብ አገሩን መውደዱን ቢጠየቅ ፡ ያለጥርጥር አገሬ ህመሜ ሊል ይችላል ፡፡ ሁላችንም ይህንኑ ባዮች ነን ፡፡ በምላስ ብቻ ወይስ በተግባርም?
  ጌቱ ከጀርመን

  ReplyDelete
 43. ....ዝም ብዬ አየሁት፡፡

  ReplyDelete
 44. I am very happy more than i can say. you touched my heart. keep it up bro. But when you write such articles mind the consequence!
  May God be with you!

  ReplyDelete
 45. it's so wonderful the way u explain God bless bro and we ethiopians, we have to learn from your friend.

  ReplyDelete