በቤኒን በጋናና በቶጎ የሚገኙ ኢወ- ሚና(Ewe-mina) የሚባሉ ማኅበረሰቦች አሉ፡፡ በተረቶቻቸው፣ በአባባሎቻቸውና በምሳሌዎቻቸው እጅግ የታወቁ
ናቸው፡፡ ከሚታወቁባቸው አባባሎች አንዱ አዳኝና አንበሳን አስመልክተው የተናገሩት አባባል ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ አባባል በናይጄሪያ፣
በታንዛንያና በኬንያ ማኅረሰቦችም ጭምር የሚነገር የታወቀ አፍሪካዊ ታላቅ ፍልስፍና ቢሆንም ምንጩ የኢወ ሚና ማኅረሰብ ሊሆኑ እንደሚችል
ብዙዎች ገምተዋል፡፡
ኢወ- ሚናዎች የታሪክ አጻጻፍንና የታሪክ አነጋገርን ያኄሱበት፣ እንደ ቼኑዋ አቼቤ ያሉ
ታላላቅ አፍሪካውያን ደራስያንም ነጮች በአፍሪካ ታሪክ ስነዳ ላይ ያደረሱትን በደል ለመግለጥ የተጠቀሙበት ታላቁ አባባላቸው ‹‹አንበሶች
የራሳቸው ታሪክ ነጋሪ እስኪኖራቸው ድረስ፣ የአደን ታሪክ ምንጊዜም አዳኙን ከፍ ከፍ እንዳደረገ ይኖራል(Until Lions have their own
historians, tales of the hunt shall always glorify the Hunter) የሚለው ነው፡፡
በኢወ- ሚና ማኅበረሰብ
አደን እጅግ የሚያስመሰግን የጀግና ሥራ ነው፡፡ አዳኞች ለብዙ ቀናት ከአካባቢያቸው ርቀው ‹ታግለውና አሸምቀው› በማደን ታላላቅ
አራዊትን ተሸክመው ወደ አካባቢያቸው ሲመጡ ሠፈርተኛው በእልልታና በሆታ ይቀበላቸዋል፡፡ እነርሱም አንበሳውን ወይም ዝሆኑን እንዴት
እንደገደሉት፣ ያደረጉትን ትግልና የተጠቀሙበትን ድንቅ ዘዴ፣ ተአምራዊ በሆነ መልኩ እንዴት ከሞት እንዳመለጡና ያንን አንበሳ እንዴት
ድል እንደነሡት ለሀገሬው ሕዝብ በኩራት ይተርካሉ፡፡
ከአዳኙ ትረካ፣ ከያዘውም
ግዳይ የተነሣ አንዳንድ ጊዜ አዳኙ ልክ አማልክታዊ ኃይል ያለው አካል መስሎ እስከመታየት ይደርስ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ አዳኞችን
የተመለከቱ ዘፈኖች፣ ግጥሞችና ተረቶች ሁሉ በአዳኞቹ ድንቅና ገናና ድርጊቶች የተሞሉ፣ ታዳኙን ንቀው አዳኙን የሚያንቆለጳጵሱ፣ የአዳኙን
ግርማና ሞገስ አወድሰው ታዳኙን የሚያንኳስሱ ሆነዋል፡፡
ኢወ ሚናዎች ምንም እንኳን
አዳኞቹን ቢያሞግሱ፣ ቢያወድሱና በአዳኞቻቸው ገድልም ቢኮሩ፣ ምንም እንኳን አዳኞቹን ቢሸልሙና የከበሬታ ሥፍራ ቢሰጡ ነገር ግን
አዳኙና ታዳኙ በጫካ ውስጥ ብቻቸውን ፊት ለፊት በተፋጠጡ ጊዜ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ በአዳኙና በታዳኙ መካከልም የተከናወነውን ነገር
ሁሉ፣ አዳኙ ያደረገውን፣ የደረሰበትንና ታዳኙ የፈጸመውን ሁሉ እንዳልሰሙት ዐውቀዋል፡፡ አንበሳው የተገደለው በተኛበት ቢሆንስ? አንበሳው የታመመ አንበሳ
ቢሆንስ? አዳኙ አንበሳን የገደለው በአጋጣሚ ቢሆንስ? አንበሳው በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ከባድ ተጋድሎ አድርጎ ከሆነስ? የሚለውን ጥያቄም ጠይቀዋል፡፡
አሁን ታዳኙ አንበሳ የለም፤
ያለው አዳኙ ብቻ ነው፡፡ የአንበሳን ወገን ገድል የሚዘክርለት የለም፡፡ እርሱ ታሪኩን የሚያወራለት፣ ተጋድሎውን የሚመሰክርለት፣
አሟሟቱ የክብርና የጀግንነት ሞት ቢሆን እንኳን ያን የሚተርክለት የለም፡፡ አሁን ታሪኩን የሚተርከው፣ ስለ አንበሳውም የሚናገረው፣
ራሱን ጀግና አንበሳውንም ፈሪ አድርጎ የሚያወራው አዳኙ ብቻ ነው፡፡ አዳኙ ስለራሱም ይናገራል፣ ስለ አንበሳውም ይናገራል፡፡ምስኪኑ
አንበሳ ሁለት ጊዜ ነው የሞተው፡፡ በአካልና በታሪክ፡፡ ዘፈኑም፣ ቀረርቶውም፣ ፉከራም፣ ተረቱም፣ አዳኙን እንዲያሞግስ ያደረገው
ታሪክ ነጋሪው አዳኙ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ ኢወ- ሚናዎች ታሪኩ የተሟላ የሚሆነው አዳኙም ታዳኙም ታሪካቸውን የመናገር እድል ሲኖራቸው
መሆኑን ዐውቀዋል፡፡ ለዚህም ነው ‹‹አንበሶች የራሳቸው ታሪክ ነጋሪ
እስኪኖራቸው ድረስ፣ የአደን ታሪክ ምንጊዜም አዳኙን ከፍ ከፍ እንዳደረገ ይኖራል›› በማለት የተናገሩት፡፡
የአንድን ማኅበረሰብ ልዕልና ከሚያስጠብቁት፣ ነጻነቱን ከሚያስከብሩለት፣ ርእዮቱን ከሚቀርጹለት
ነገሮች አንዱ የታሪክ ንግርቱ ነው፡፡ የታሪክ ንግርት የአንድን ማኅበረሰብ ሞራል ለመግደልም ሆነ ለማዳን፣ ተገዥ ሆኖ እንዲኖርም
ሆነ ነጻ እንዲወጣ፣ ክብር ወይም ውርደት እንዲሰማው፣ ለራሱ የሚሰጠው ዋጋ እንዲወርድ ወይም እንዲጨምር ያደርገዋል፡፡
ስምኦን ሜሳን የተባሉ በአሜሪካ ኒው ጀርሲ የሚኖሩ አፍሪካዊ ጸሐፊ ለዚህ አባባል በምሳሌነት
የሚያነሡት በግብጽ የነበሩ እሥራኤላውያንን ታሪክ ነው፡፡ እሥራኤላውያን ግብጽ ውስጥ ለ400 ዓመታት ያህል ሲኖሩ ግብጻውያን በተደጋጋሚ
የሚነግሯቸው ሦስት ዘውጎች ያሉት የታሪክ ትርክት ነበሯቸው፡፡ ‹‹እናንተ ሀገር አልባ የግብጽ ስደተኞች ናችሁ፣ እናንተ ነጻ አውጭ
የሌላችሁ ባሪያዎች ናችሁ፣ እናንተ የከበሬታ ሥፍራ የማይገባችሁ ወራዶች ናችሁ››፡፡ እነዚህ ነገሮች የተፈጠሩት በግብጻውያን ነው፡፡
ግብጻውያኑ የአዳኙን ቦታ ይዘው ነበርና ሥልጣናቸውን ተጠቅመው የታሪክ ትርክቱን ይቆጣጠሩት ነበር፡፡ ደጋግመው የመናገር መብትም
ስለነበራቸው ራሳቸውን እሥራኤላውያኑን እንኳን አሳምነዋቸው ነበር፡፡
የሙሴ መነሣት በእሥራኤል ሕይወት ላይ ለውጥ ያመጣው የራሳቸው ታሪክ ነጋሪ በማግኘታቸው
ነበር፡፡ እስከዛሬ ከገዥዎቻቸው፣ ከጨቋኞቻቸውና ከአስገባሪዎቻቸው ግብጻውያን ሲሰሙት ከነበረው የማንነታቸው ትርክት የተለየ፣ ለእነርሱም
ሌላ ማንነትን ሊፈጥርላቸው የሚችል፣ ስላበት ሁኔታ አዲስ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ታሪክ ነጋሪ ተገኘ፡፡ አንድ ማኅበረሰብ እንደ ሙሴ
ዓይነት ሰዎችን ሲያጣ የሚጎዳም ለዚህ ነው፡፡ ብዙ ጊዜም ገዥዎችና ጨቋኞች እንደ ሙሴ ዓይነት የታዳኙን ታሪክ ሊነግሩ የሚችሉ ሰዎች
እንዳይነሡ፣ ከተነሡም እንዳይቀጥሉ የሚያደርጉትም ይህንን ስለሚያውቁ ነው፡፡
የእሥራኤላውያን የማንነት ግንዛቤ ሙሴ ወደነርሱ ሲመጣ ተለወጠ፡፡ የሙሴ መምጣት የመጀመሪያወን
ለውጥ ያመጣው በእሥራኤል የኑሮ ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡ በታሪክ ንግርታቸው ላይ ነው፡፡ ሙሴ አዲስ ታሪክ ነጋሪ ሆኖ ብቅ አለ፡፡
አሁን የአዳኙን ብቻ ሳይሆን የአንበሳውን ገድል የሚተርክ የታሪክ ንግርት መጣ፡፡ ሙሴ መጀመሪያ የቀየረው ሦስቱን የትርክቱን ዘውጎች
ነበር፡፡ ‹‹እናንተ ሀገር አልባዎች ስደተኞች ናችሁ፡፡›› ይሏቸው ነበር፡፡ ሙሴም ‹‹ስደተኞች አይደለንም፤ ነገር ግን በበደላችን
ምክንያት የተቀጣን ነን፤ አሁን ፈጣሪ ይቅር ብሎናል፣ ከነዓን የምትባል ሀገርም ተዘጋጅታልናለች፣ ከዚህ ወጥተንም እንገባባታለን››
ብሎ ነገራቸው፡፡ የተስፋ ሀገርም ሰጣቸው፡፡ የሚጓጉላት፣ የሚሞቱላት፣ ሀገር፡፡ በአንድ ወቅት እስራኤላዊው ነጻ አውጭ ቴዎዶር ኸርዝል
‹‹እኔን የሚቆጨኝ የምኖርባት ሀገር ስለሌለኝ አይደለም፣ የምሞትላት ሀገር ስለሌለኝ እንጂ›› እንዳለው፡፡
‹‹እናንተ ባሪያዎች ናችሁ›› ሲሏቸው ሙሴ ግን ‹‹እናንተ የተጨቆናችሁ ጭቁኖች ናችሁ፣
ባሪያዎች አይደላችሁም፡፡ ጭቁኖች ናችሁና ከጭቆና ነጻ ትወጣላችሁ›› አላቸው፡፡ ግብጻውያኑ ‹‹እናንተ ዝቅተኛ ማኅበረሰቦች ናችሁ››
ሲሏቸው ሙሴ ግን ‹‹እናንተ የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝቦች ናችሁ፣ ራሱ እግዚአብሔርም ነጻ ያወጣችኋል›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ሙሴ እሥራኤል
የነበሩበትን ሁኔታ አይደለም የቀየረው፡፡ በግብጽ ነበሩ፣ እንደ ባሪያ ይገዙ ነበር፣ ዝቅተኛ ማኅበረሰቦችም ነበሩ፡፡ ነገር ግን
ሙሴ የታሪክ ትርክቱን ነው የቀየረው፡፡ ማንነታቸውን የሚያዩበትን ዓይን ነው የቀየረው፡፡ ይህንን ለመቀየር የተቻለው ታሪክ ነጋሪው
ሙሴ በመሆኑ ነበር፡፡
ለአንደ ማኅበረሰብ የራሱ ታሪኮች፣ ተረቶች፣ አባባሎች፣ አፋዊ ታሪኮችና ሌሎችም የሚያስፈልጉት
በራሱ መንገድ የራሱን የዓለም የሚያነጽርባቸው መሣሪያዎች ስለሆኑ
ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በጣልያን ድል ተደርገው የአምስት ዓመቱ የፋሺስት አገዛዝ ሲመጣ የፋሺስቶች የታሪክ ትርክትና የኢትዮጵያውያን
የታሪክ ትርክት መለያየት ነው የአርበኝነት ትግሉን ያስጀመረው፡፡ ኢትጵያውያን ሽንፈቱን እንዴት ነበር ያዩት፣ አዝማሪዎቹ፣ ፎካሪዎቹ፣
የእምነት መምህሮቹ፣ ትንቢት ተናጋሪዎቹ፣ ምንድን ነበር ትርክታቸው? ይህ ሁሉ ለምን መጣብን? ለሚለው ጥያቄ የሰጡት መልስ ምን ነበር?
ገለል በሉና ገለል አርጓቸው
ወደመጡበት ወዳገራቸው
ለነዚህ ጣልያኖች መድኃኒት ስጧቸው
የሚያስቀምጥ ሳይሆን የሚያስመልሳቸው
አርኩም ይሄድና ሶልዲውም ያልቅና
ያስተዛዝበናል ይኼ ቀን
ያልፍና
የሚሉትና ሌሎችም የሕዝቡ ትርክቶች የጣልያንን መመለስ፣ በኢትዮጵያ ምድር ለዘለዓለም ለመቆየት
እንደ ማይችል የሚገልጡ ነበሩ፡፡ ይኼ ትርክት ‹ነጭን ማሸነፍ አይቻልም፣ አሜን ብላችሁ ለጣልያን ተገዙ› እያሉ ይለፍፉ
በነበሩት የጣልያን ፕሮፓጋንዲስቶች ሕዝቡ እንዳይዋጥ አድርጎታል፡፡ ምንም እንኳን የእነዚህ ታሪክ ነጋሪዎች ትርክት በወቅቲ ነባራዊውን
ሁኔታ ባይቀይረውም፣ ነባራዊውን ሁኔታ ለመቀየር እንዲቻል ግን የአርበኞችን የመመልከቻ መነጽር ቀይሮታል፡፡ ታሪክ ነጋሪዎቹ ኢትዮጵያ
ያጋጠሟትን ክፉ ዘመናት እያነሡ፣ እነዚህን ክፉ ዘመናት እንዴት እንደተሻገረች እየተረኩ፣ ይህም ሊያልፍ የሚችል እንጂ ነዋሪ አለመሆኑን
ይገልጡ ነበር፡፡ ኢጣልያ በየቦታው ያደረገችውን ጦርነት በራስዋ ሚዲያና ፕሮፓጋንዲስቶች በኩል በመለፈፍ የሕዝቡን ቅስም ለመስበርና
ሁሉም ነገር አልቋል ብሎ እንዲቀመጥ ለማድረግ ሞክራ ነበር፡፡ ታሪኩ የአዳኞችን ብቻ እንዲገልጥ ጥረት አድርጋም ነበር፡፡ አንዳንድ
አርበኞች ሲያዙ፣ በአደባባይ ሲገደሉ፣ አንዳንድ ባንዶች እጃቸውን ሲሰጡ፣ ስለ ጣልያን ታላቅነትና ደግነትም ሲመሰክሩ ሕዝቡ የአዳኞቹን
ብቻ ገድል እንዲሰማ ተሞክሮ ነበር፡፡
ነገር ግን አልሆነም፡፡ በወሬውም፣ በተረቱም፣ በዘፈኑም፣ በቀረርቶውም፣ በፉከራም፣ በባሕታውያኑም፣ በልቅሶ ሙሾም፣
በወፍጮ ፈጭውም፣ በውኃ ወራጁም ግጥም ውስጥ የጀግኖቹ ስምና ዝና፣ ገድልና ታሪክ እየተነሣ ከሀገር ሀገር ተዛመተ፡፡ የታሪክ ትርክቱ
በሕዝቡ እጅ መሆን፣ የተማረኩትንና የተገደሉትንም ቢሆን እንደ ተሸናፊ፣ እንደ ድል ተነሺ ሳይሆን እንደ ሰማዕታትና እንደ ጀግና
እንዲታዩ አደረጋቸው፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ በእንግሊዞች ተከብበው፣ በመጨረሻ ራሳቸውን በሽጉጣቸው አጠፉ፡፡ እንግሊዞች ድል አድራጊዎችና
ማራኪዎች ሆነው፣ ዐፄ ቴዎድሮሰ ድል ተነሺና ተማራኪ ሆነው ነገሩ ተጠናቀቀ፡፡ ይህንን ነገር ኢትዮጵያውያን እንዴት ነው የተረኩት? ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ታሪክ
የማንጽፍ፣ የራሳችንን ታሪክም የማንተርክ ቢሆን ኖሮ አሁን የምናውቃቸውንንና የጀግና ምሳሌ ያደረግናቸውን ዐፄ ቴዎድሮስን ልናገኛቸው
ባልቻልን ነበር፡፡ አንዳንድ የታሪክ ሰዎች እንዲያውም ‹‹ሕዝቡ የሚያውቃቸው ቴዎድሮስና ታሪካዊው ቴዎድሮስ ይለያያሉ›› እስከማለት ደርሰዋል፡፡
ሕዝቡ የአዳኞችን ትረካ እንደማይስማማበት የገለጠው ወዲያው በጦርነቱ ጊዜ መሆኑን የምንረዳው
ገደልንም እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው
ማረክንም እንዳይሉ ሰው የለም በጃቸው
ምን አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው
ለወሬ አይመቹም ተንኮለኞች ናቸው
በማለት መግጠሙን ስናይ ነው፡፡
የዐድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን አሸናፊነት በተጠናቀቀ ጊዜ በአፍሪካ በቅኝ ገዥነት የተሠማሩት አውሮፓውያን
ትልቁ ሩጫቸው ዜናው በኢትዮጵያውያን መንፈስ እንዳይሰማ ማድረግ ነበር፡፡ ቢቻል ፈጽሞ ዜናው እንዳይደርስ፣ ካልሆነም ደግሞ የኢትዮጵያውያንን
የአሸናፊነት መንፈስ በጠበቀ መንገድ እንዳይሰማ፣ እንዲሁ ተራና መናኛ ዜና ሆኖ እንዲቀር ማድረግ፡፡ የዐድዋ ጦርነት ቅኝ ገዥዎች
ለአፍሪካውያን ሲተርኳቸው የኖሩትን ሦስት ትርክቶች ያፈረሰ ጦርነት ነበር፡፡ ‹‹ነጭን ጥቁር አያሸንፍም፣ አሸንፎም አያውቅም፡፡
ጥቁሮች እንዲገዙ፣ ነጮች እንዲገዙ የአምላክ ትእዛዝ ነው፤ አፍሪካ ታሪክ የላትም፣ ታሪኳ የቅኝ ግዛት ታሪክ ነው›› ፡፡
የዐድዋ ጦርነት እነዚህ ሦስቱን መሠረታውያን የቅኝ ግዛት ትርክቶች አፈረሰ፡፡ ነጭን ጥቁር ሕዝብ
አሸነፈ፡፡ በአስደናቂ ሁኔታ በአንድ ቀን ጦርነት አሸነፈ፤ ነጮች ተማረኩ፡፡ ነጮች ጥቁሮችን እንዲገዙ ከእግዚአብሔር የተፈቀደ ነው፤
ለነጮች አለመገዛት የፈጣሪን ትእዛዝ አለማክበር ነው ይባሉ ነበር፡፡ አሁን ግን ኢትዮጵያውያን ታቦት ይዘው ወጥተው፣ ስመ እግዚአብሔር
ጠርተው፣ ያውም በዕለተ ጊዮርጊስ፣ ቀሳውስቱና ደባትሩም አብረው ዘምተው ጣልያንን ድል አደረጉ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ለነጭ ታዘዙ
የሚል አምላክ አለመሆኑን አሳዩ፤ ኢትዮጵያውያን ነጭ ቅኝ ገዥዎችን ድል ሲያደርጉ የተቆጣ፣ የቀሰፈ አምላክ አልታየም፡፡እንዲያውም
አብሮ ተዋጋ፡፡ የራስዋ ታሪክ ያላት፣ ሉዓላዊነቷን ጠብቃ የኖረች፣ ለማንም ያልተንበረከከች አንዲት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር መኖሯም
ታወቀ፡፡ ጥቁርም ታሪክ አለው፡፡ ከቅኝ ገዥዎችም በፊት ታሪክ ነበር የሚለው ታወቀ፡፡
የዐድዋ ጦርነት እነዚህን ሦስት ትርክቶች ሻረ፡፡ ይህን ነው ቅኝ ገዥዎች ከአፍሪካውያን ሊሠውሩት
የሞከሩት፡፡ ይህ የአድዋ ጦርነት በአፍሪካውያን ዘንድ ሲሰማ የፀረ ቅኝ ግዛት ስሜትን ቀስቅሶ ነበር፣ እኛ የምናምነው በኢትዮጵያ
አምላክ ነው የሚሉ ኃይሎችን አስነሥቶ ነበር፡፡
የአንድን ሕዝብ ማንነት፣ መንገድና መዳረሻ ለመወሰን ዋነኛው መሣሪያ የዚያን ሕዝብ ትርክት መቀየር
ነው፡፡ ስለራሱ፣ ስለ ማንነቱ፣ ስለ ታሪኩ፣ ስለ ጀግኖቹ፣ ስለ እሴቶቹ፣ ስለ ክብሩና ዝናው፣ ስለ ጀብዱውና የት መጣው የሚተርከውን
ነገር መቀየር፡፡ የአንድ ማኅበረሰብ ማነነት፣ እምነት፣ አቋምና ስለ ነገሮች የሚኖረው ምላሽ ከትርክቶቹ የሚሠራ ነው፡፡ እኛ የታሪክ፣
የተረት፣ የአባባል፣ የአፈ ታሪክ፣ የእምነት ትምህርት፣ የቀረርቶ፣ የሽለላ፣ የሙሾ፣ የዘፈን ትርክቶች ውጤቶች ነን፡፡ ከምግብ ንጥረ
ነገሮች በላይ በእነዚህ ንጥረ ነገሮች ተገንብተናል፡፡ እነዚህን በቀየርን ቁጥር አብሮ ሰብእናም ይቀየራል፡፡
ጣልያኖች አዲስ አበባ እንደገቡ ታዋቂ አዝማሪዎችን ካዛንቺስ መሸታ ቤት እየጠሩ፣ ራቁቷን ያለች ሴት
ሥዕል አቁመው ለፀጉሯ፣ ለዓይኗ፣ ለጥርሷ፣ ለአንገቷ፣ ለደረቷ፣ ለወገቧ፣ ለሽንጧ፣ ለዳሌዋ፣ ለባቷ ፣ እንዲዘፍኑ ያደርጓቸው ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያን ስለ ሴት ልጅ ውበት የሚገልጡበት የራሳቸው ነባር ትርክት ጠፍቶ አውሮፓዊ በሆነውና ውጫዊ አካልን ብቻ በሚያሞግሰው
ሌላ ትርክት እንዲተካ አደረጉት፡፡ ከዚያም የዘፈኖቻችንን ባህል፣ እኛም ስለ ሴቶቻችን የሚኖረንን እሳቤ አውሮፓዊ ርእዮት ሰጡት፡፡
የዘመናችን ሚዲያዎችና የፕሮፓጋንዳ መሣሪያዎች ትልቁ ሚናቸው የተራኪነቱን ሚና መውሰድ ነው፡፡ ተራኪነቱን
የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል፡፡ ማን ጀግና እንደሆነ፣ ማን ድል እንዳደረገ፣ ማን ታሪክ እንደሠራ፣ ማን እንዳደገ፣ ማን እንደታገለ፣
ማን ታላቅ እንደሆነ፣ ማን እንደሠለጠነ፣ ማን ነጻ እንዳወጣ፣ የሚወስነው ታሪክ ነጋሪው ነው፡፡ የአደን ታሪክ ምን ጊዜም አዳኙን
ይከተላልና፡፡ ማንዴላ ለአፓርታይድ ነጮች አሸባሪ፣ ወንጀለኛ፣ ሀገሩን የካደ፣ የዕድሜ ልክ እሥራት የሚገባው አረመኔ ነው፡፡ ማንዴላ
ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ነጻ አውጭ፣ ታጋይ፣ ጀግና፣ ለሀገሩ የሚሞት፣ የነጻት አባት፣ ቆራጥ፣ ደቡብ አፍሪካዊ ነው፡፡ የሁለቱም
ሰው ግን ማንዴላ ነው፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ለፋሺስቶች ወንበዴና ሞት የሚገባቸው ወንጀለኛ ናቸው፡፡ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ቆራጥ፣ የጀግኖች
ኮከብ፣ የጽናት ተምሳሌት፣ የእምነት አባቶች አርአያ የሆኑ ጀግና ናቸው፡፡ ታሪኩ የተወሰደበት - ጀግናውን ያጣል፣ አርአያውን ይነጠቃል፣
አይከኑ ይሰበርበታል፣ ኩራቱ ይወሰድበታል፤ ሌላ ማንነትም ይሰጠዋል፡፡ እርሱ ከብት ቢኖረውም አፍ ያለው ከብቱን ይወስንለታል፡፡
ታሪክም አንበሳውን ትቶ አዳኙን ብቻ እንዳገነነ ይቀጥላል፡፡ አንበሳው ነጋሪ የለውምና፡፡
ኳታር
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ወጥቶ ነበር
‹‹እኔን የሚቆጨኝ የምኖርባት ሀገር ስለሌለኝ አይደለም፣ የምሞትላት ሀገር ስለሌለኝ እንጂ››
ReplyDeleteThank you so much and God bless you our brother and father Danial.
ReplyDeleteጆሮ ያለው ይስማ! ልብ ያለው ልብ ይበል! ቃለ ህይወት ያሠማልን።
ReplyDeleteቃለ- ህይወት……..ወይስ……..ቃለ- ፎለቲካ
Deleteእንደ ልቤ የተባለው መዝሙረኛው ዳዊት ንጉስና(አገር አስተዳዳሪ) የእግዚአብሔር ሰው እንደነበረ ልብ ይሏል! የኔ ወንድም
Deleteቃለ ህይወት Do you know how to read? everything is fact so if someone tell us the truth we have to say ቃለ ህይወት. if you read it again you will see this " ተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል" evenif someone lie to us so we need fact.
DeleteDo you think you are the only one you love our country? Shame on you. Danial loves God and his country as well. When we see one direction Protestant, Muslim and Eritrean takeover our country. Still you didn’t wakeup but he is trying inform us. I don’t mean Ethiopia is not their country but they are working hard to destroy our church. Please wakeup or don’t be obstacle to your brother and sister.
Deleteእስክንድር አንዱአለም ርእዮት በቀለ ገርባ እና ሌሎች ስም የሌላቸው ለቁጥር የሚታክቱ በየእስር ቤቱ የታጎሩ ኢትዮጵያዊያን ለኛ ጀግኖች ለወያኔ ደግሞ አሸባሪዎች ናቸው አንድ ቀን ታሪካቸውን የሚናገር እስከሚመጣ ድርስ
ReplyDeleteተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል
ReplyDeleteDear Dani
ReplyDeleteYou raise a good point. In fact this point has been raised by prof mesfin a while ago by different way of telling it.
I think you seem now have acknowledged that History can be recorded in a wrong way or only by one side which will make it Keshafi. Anyways I greatly admire both of you for trying to make us awake.
Dear Zekios, your understanding of 'Kishfet' according to Professor Mesfin and Dn Daniel, when it comes to history, is somehow missed the point. It is about cause and effect. In the above article, I found nothing which suggests the acknowledgment, by Dn DK of the Professor's argument about 'Kishfet' of Ethiopian History as you put it. The 'Kishfet' argument was about the HISTORY itself rather than the teller. The teller defines the particular part of history or the maker. Whether it is told by the hunter or by the prey, in whatever way, that HISTORY is made and exists. We can have a history of 'Kishfet' or a history of 'Sikiet'. These words/ideas of 'Kishfet' and 'Sikiet' come to the equation, as a form of instrument to judge the out-come or end-result, only when we already have a HISTORY that we could measure. And most importantly Zekios, the Professor’s point about 'Kishfet' of Ethiopian History was not about its recording at all. It was about the effect those particular occurrences brought to the people and to the land. Whether we judge them as 'yeKeshefeu' or 'yeTesaku' they are there forever. Even when we don't know about them they exist for those who participated in and witnessed them. 'Kishfet' and 'Sikiet' are always prone to be decided relatively to other factors. Those factors are variable, but HISTORY is not. Just my thoughts.
DeleteThank you Dn Daniel.
ተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል! well said መምህር
ReplyDeleteአንበጣ አንበሳዉን አያባረረ ነዉ : አንበጣ ብዛት ስለሌለዉ ዝንብን አየተጠቀመ ነዉ :: ዝንብ አይምሮ ስለሌለዉ አንደፈለጉ ይጋልቡታል:: ይአችን ሐገር አንዳትገነጣጠልአና በቅኝ ግዛት አንዳትገዛ ያደረጋት አንበሳ ዉለታዉ ተረስቶ ዛሬ አንበጦች ስለራሳቸዉ ጀግንነት ብቻ ይነግሩናል :: አንበሳዉ አንደ ኢትዮጵያ ጠላት ተደርጎ አንዲታይ ጥረት አያደረጉ ነዉ:: ጊዜ ይፍረድ::
ReplyDeletewey chgr man yihon anbesaw, anbetawena ena znbu?
DeleteGood Point, Thanks!
ReplyDeletemengagereiawn(Micraphone) Yeyazew becha new hola giza Yemedemetew lelaw wegn edelu aystewm selezih yemensemaw neger hola ande aynet becha new.
ReplyDeleteEverything has time; long time ago a lion was Ethiopian king. He used to manage all Ethiopian people equal and fear. The lion’s relatives were educated and he told them to go all part of Ethiopia to transfer knowledge and experience. The king work day and night. He was aggressive and hard worker with love of his country. A white enemy came from Italy and the lion fought with them and won. The lion established African union in his country. Ethiopian became one of famous country in African and world. Then the lion substituted by Gorilla. Gorilla runs the country for 17 years with war and he brought more equality for all Ethiopian. When Gorilla take over the sit from the lion, he killed many lion, fly and butterfly. However Gorilla used to love his country. After 17years Gorilla substituted by Devil. Devil run Ethiopian for 20 years, with twenty years devil divided all Ethiopian by region and he gave Ethiopian’s lands to Sudan, Kenya, Eretria and Somali. After twenty year devil pass away but his dead body run the country. At the moment there is no Ethiopian government but the dead body idea run the country. Everything will pass.
ReplyDeleteእግዚአብሄር ሃግራችንን ይባርክ :: ከድንዛዜያችን እንንቃ :
ReplyDeleteDANI THIS IS THE BEST........THE BACKBONE!!!! BERTA WENDIME
ReplyDeleteThank You For your Best View.
ReplyDeleteBetam Des Yilal.
ReplyDeleteBetam Des Yilal.
ReplyDeleteየታዳኙን ጀግንነትም ለመተረክ የሚያስችል ስብእና የራስ ማድረግ የራስን ስንፍና አድኖ ድል መንሳት ነው እንደማለት ይሆን?
ReplyDeleteየኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ታሪክ በሥልጣኔ ጫፍ ደርሶ የነበረው ታሪካችን በተገላቢጦሽ የዓለም ጭራ ሆነን ስማች ራህብተኛ፣ ድሆች፣ ዝቅተኛ የሕብረተሰብ ክፍሎች የሚኖሩባት ኢትዮጵያ ለዘመናት ተፈጥሮ በድርቅ ሲመታት፣ አጼዎችና ባለሥልጣናት ሥልጣናቸውን ለማራዘም እርስ በርስ ሲተራመሱባት መሬቱም ደምና አጥንት እንጂ እህል አልቀበልም ብላ እልህ ተጋብታ የሀገሪቷ ሕዝቦች በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ የእርስ በርስ ጦርነት ሰለባ ሲሆኑ ታዳኝ ሆነው ታሪካቸውን የሚተርክላቸው አጥተው ዓለም ዞር ብላ ሳታያቸው ለዘመናት ሲኖሩ ነበር፡፡ ግን በስተመጨረሻ ታሪክ የለወጠው /የታሪክ ትርክቱን/ የቀየረው የሀገራችን ምርጥ ልጅ /መሪ/ መለስ ዜናዊ ዳግም ሀገራችንን የዓለምን /የብዙዎችን/ ዓይን እየሳበች ያለች፣ ብርቱ መሪዎች የተፈጠሩባት፣ ማንነታችን የምናይበትን ዓይን የቀየረልን የኛ ሙሴ መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ይህን የታሪክ ጥላሸት ለመቀየር ላይ ታች፣ ደፋ ቀና ሲል ሳይኖር ለኛ የኖረልን እንደ ሻማ ቀልጦ ለኛ ብርሃንን እንድናይ ያደረገልን በጐ ታሪካችንን እንድናስታውስ “የበላይ ነበርን አሁንም የበላይ እንሆናለን” የሚለውን አስተሳሰብ በሁላችንም አይምሮ እንደ ብርሃን እንዲፈነጥቅ፣ ባለተስፋ እንድንሆን ያደረገን የኢትዮጵያ ሙሴ “መለስ ዜናዊ” ነው አራት ነጥብ
ReplyDeleteThank you brother for your comment however what Meles Zenawi did while he was Ethiopian leader. I just want compare the life of Ethiopian people before Meles and during Meles. All country economy measured by THE COUNTRY MONEY STRENGHT, UNEMPLOYEMENT PEOPLE AND LIFE STANDATD.
DeleteBefore Meles 100Killo Teff 100bir, During Meles 100Killo Teff 1600birr
100KL Teff 100birr Before Meles
100KL Teff 1600birr During Meles
All Ethiopian love each other Before Meles
All Ethiopian hate each other During Meles
We have big Ethiopia map Before Meles
We gave our land to Eretria, Somali, Sudan, Kenia. During Meles
Life standard 20% high level 55% middle income, 25% low level. Before Meles
18%high level, 5% middle income and 77%low level. During Meles
Unemployment 32% Before Meles
Unemployment 63% During Meles
Educated immigrant 8% Before Meles
Educated immigrant 93% During Meles
Uneducated immigrant 7% Before Meles
Uneducated immigrant 98% During Meles
Discrimination work place 2% Before Meles
Discrimination Work place 99% During Meles
Civil organization 100% Before Meles
Civil Organization 0% During Meles
Our money strength 2birr = $1 Before Meles
Our money strength 19.14birr = $1 During Meles
Ethiopian Value in the world 84% Before Meles
Ethiopian Value in the world 31% During Meles
Hello brother/Sister could you tell me what he did for us? Do you think Saud Arabia killed our people if Mengstu Hayelemariam is Ethiopian leader? I feel Meles Zanawi was one of Ethiopian enemy like Moamed and Yodit. If I am wrong please write something what he accomplished for Ethiopian people?
DeletePLEASE DON’T BLAME HIM/HER, IF SOMEONE ONLY WACH ETV PROGRAM OR LISTEN ETHIOPIAN RADIO, WHAT DO YOU EXPECT FROM THAT PERSON. Hi brother or sister this is 21century not 17century so you have to update your mind and try to get more information from BBC,CNN,ALGEZIRA, ESAT,FACEBOOK, TWITER, MAGAZINE,NEWS PAPER, INTERNATE AND BLOOBERG WEEK. Then you will get this information Meles Zanawi daughter has 5billion dollar in New Youk bank and Azib has 3.5billion dollar in Swiss bank and Meles Zanwi has 3billioon dollar in Swiss bank. If this money come to Ethiopia, we will build at least four Abay and Ethiopia never ask food to feed Ethiopian.
DeleteIt's true when you tell us: "... ተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል፡፡ ማን ጀግና እንደሆነ፣ ማን ድል እንዳደረገ፣ ማን ታሪክ እንደሠራ፣ ማን እንዳደገ፣ ማን እንደታገለ፣ ማን ታላቅ እንደሆነ፣ ማን እንደሠለጠነ፣ ማን ነጻ እንዳወጣ፣ የሚወስነው ታሪክ ነጋሪው ነው፡፡ የአደን ታሪክ ምን ጊዜም አዳኙን ይከተላልና፡፡"
Deleteetv??????????????
DeleteDefar neh ebakh hager lematfat siaser yetekesefewn? Tarikuan atifito yetefawn? Hizbun kefafilo yemotewn? Melesn muse? Defar!
DeleteReally? You call Meles AS OUR Mosses? It is amazing how somebody like you do not has conscious mind . To tell you the truth Meles is our Fereon , Satan.
DeleteMay be your "Mosses" can be Meles Zenawi. Good for You. But not for most of Ethiopians. In case you forget most Ethiopians are still starving, thanks to this highly corrupted government, which is established by your "Mosses".
Deleteየሃይማኖት ተቋማት ምዝገባን መቃወም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ነው ከተባለ ተባለ ታዲያ .....
DeleteለAnonymous አስተያየታችሁን ለሠጣችሁኝ በሙሉ ፡- Oh my God መለስን ነው እንዲህ የወረዳችሁበት፡፡ በስመአብ እኔ ግን መለስን በጣም ነው የምወደው ሥራው ሁሉ ያኮራኛል፡፡ የእናንተ ግን ቅናት መሰለባችሁ ፡፡ ETV ንም በጣም እወደዋለሁ፡፡ እና ታዲያ የሰፈር ወሬ እየለቃቀመ የሚያወራውን ኢሣትን ልይላችሁ፡፡ የአገሩን ሠርዶ በአገሩ በሬ እንደሚባለው ጠዋትም ማታም ኢቲቪ፡፡ እናንተ ደግሞ አሸባሪ፣ ሞገደኛውን ኢሣታችሁን ተመልከቱ፡፡ እኔ በዚችው በሀገሬ ምድር የባቡር ዝርጋታውን፣ የመስኖ እርሻውን፣ መንገዱን፣ ሥልጣኔውን፣ ኮንዶሚኒየም ቤቱን እንደው ደስ ደስ የሚለውን፣ ተስፋ ተስፋ የሚሸተውን ብፈልግ በኢቲቪ ብፈልግ በአይኔ በብረቱ እየጎበኘሁ ተስፋዬን አለምልሜ የሰላም አየሬን እየተነፈስኩ ቤተክርስቲያኔን እየተሣለምኩ ስትረስ ላደቀቃቸው በውጭ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ለእናንተ እየፀለይኩ በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡
Deletewas expecting this kind of answer from you. You guys never accepted your weakness. As you read the comment nobody support you that mean you are lying us.
Deleteተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል! well said Anonymous person. Now I know who took it. When I read you comment, I feel I am waching ETV.
ReplyDeleteI am glad to see this kind of person on this site. I thought all Ethiopian people hate the current goverment and Meles Zanawi. Don't worry Anonymus person you will meet him at siol with satanl.
ReplyDeleteante buhaqa!!!meles zenawi malet ager yekeda banda new!!!yemneh ebkih????ETHIOPIA be tarik ayitaw yematawiqew zeregna meri =meles zenawi!!!
ReplyDeleteለAnonymous አስተያየታችሁን ለሠጣችሁኝ በሙሉ ፡- Oh my God መለስን ነው እንዲህ የወረዳችሁበት፡፡ በስመአብ እኔ ግን መለስን በጣም ነው የምወደው ሥራው ሁሉ ያኮራኛል፡፡ የእናንተ ግን ቅናት መሰለባችሁ ፡፡ ETV ንም በጣም እወደዋለሁ፡፡ እና ታዲያ የሰፈር ወሬ እየለቃቀመ የሚያወራውን ኢሣትን ልይላችሁ፡፡ የአገሩን ሠርዶ በአገሩ በሬ እንደሚባለው ጠዋትም ማታም ኢቲቪ፡፡ እናንተ ደግሞ አሸባሪ፣ ሞገደኛውን ኢሣታችሁን ተመልከቱ፡፡ እኔ በዚችው በሀገሬ ምድር የባቡር ዝርጋታውን፣ የመስኖ እርሻውን፣ መንገዱን፣ ሥልጣኔውን፣ ኮንዶሚኒየም ቤቱን እንደው ደስ ደስ የሚለውን፣ ተስፋ ተስፋ የሚሸተውን ብፈልግ በኢቲቪ ብፈልግ በአይኔ በብረቱ እየጎበኘሁ ተስፋዬን አለምልሜ የሰላም አየሬን እየተነፈስኩ ቤተክርስቲያኔን እየተሣለምኩ ስትረስ ላደቀቃቸው በውጭ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ለእናንተ እየፀለይኩ በመኖር ላይ እገኛለሁ፡፡
Deleteበመሠረቱ ጽሑፎችህን እከታተላለሁ ፤ በጣም የሚገርመኝ ነገር የምታነሳው ጭብጥና ጭብጡን ከወቅታዊ ክስተቶችና መሰረታዊ ከሆኑ ሌሎች ኩነቶች ጋር በማዛመድና እጥር ምጥን ያለ አስተያየትና ማብራሪያ በማከል የምታወጣው ጽሑፍ እጅግ ይደንቀኛል ፡፡ በማታው ፕሮግራሞች የተወሰኑ የአውደ ምህረት ትምህርቶችህን (ከአስር ዓመት በፊት) የመቋደስ ዕድል አግኝቸ ነበር እናም የርእስ አመራረጥህ ፣ የምሳሌ አሰጣጥህ፣ የአተራረክ ብቃትህና የታዳሚውን ጆሮ ለመዋስ የምታደርገው ጥረትና በአጠቃላይ የምታቀርባቸውን ሀሳቦች በአድማጩ ወይንም በአንባቢው አእምሮ ውስጥ ተቀርጾ እንዲቀር የምታድርግበት ጥበብ አስደናቂ በመሆኑ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን አንተን ስላስነሳልን ስሙ ለዘለዓለም የተመሠገነ ይሁን ፡፡ እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ይስጥልን ፡፡ ከዚህ ባሻገር ዛሬ ባቀረብከው ጽሁፍ ላይ ትልቅ ትምህርት ሰጭና ነገሮችን በተለያየ አቅጣጫ በማየት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረን የሚያደርግ ነው ፡፡ በአሁኑ ሠዓት የሀገራችንን ታሪክም ሆነ የቀድሞ አባቶቻችንን ስራና ለሀገርና ለወገን ያበረከቱትን መልካም ተግባር እና አስተዋጽኦ ወደጎን በመተው ሌላ ስምና ያለተፈጠረ የታሪክ ግምጃ ሲያለብሷቸው እየተሰማ ባለበት በዚህ ዘመነ ክህደት እንደአንተ ዓይነት ሰው መገኘቱ ትልቅ በረከት ከመሆኑም በላይ እግዚአብሔር ይችን ሀገር ለመቸም እንደማይተዋት ማሳያ ነው ፤ የማይዋጥላቸው አሉና ፡፡ ቸር ይግጠመን ፡፡
ReplyDeleteየሃይማኖት ተቋማት ምዝገባን መቃወም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ነው ተባለ
ReplyDeleteየሃይማኖት ተቋማት ምዝገባን መቃወም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ነው ተባለ
ReplyDeletego ahead we we will follow you reading your useful and constructive views. Dani
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል፣ ሕዝብ የሚያንጽ በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው - መዝጊያው (ማሠሪያው) መፍትሔ ወይም አቅጣጫ ካለማሳየቱ የተነሳ ከመላላቱ በቀር። ጽሑፉ ሳይታሰር መቅረቱ በጣም በትንሹም ቢሆን አንተን 'ወሳኙ ታሪክ ነጋሪው አዳኙ ነውና ያን መለወጥ አስቸጋሪ ነው' ብቻ ያልክ እንዳያስመስልህ ስጋት አለኝ።
ReplyDeleteሌላው ደግሞ በማንኛውም የታሪክ ጊዜ የአዳኙ ታሪክና ገድል ብቻ ይነገራል ማለት እንዳልሆነ እንድትገነዘበው ያስፈልጋል። ሁለቱም ተጻራሪ ንግርት (ማለትም የአዳኙና የአንበሳው) በማንኛውም ጊዜ እግር በእግር እኩል ነው የሚሄዱት። ልዩነቱ የአዳኙ በርሱ ማኅበረሰብና በያዛቸው ተቋማቱ ምክንያት ጮክ ብሎ ሊሰማ ይችላል - ለጊዜው። የአንበሳው ማኅበረሰብ ምናልባት ለጊዜው አቅሙ ከርሱ ስለተወሰደ ሬድዮና ቴሌቪዥን አይኖሩትም። መጻሕፍትም ለማሳተም አይችል ይሆናል። ከጫጫታውና ከከበሮው ወረድ ብለህ ወደ አንበሳው መንደር ሄደህ ጆሮህን ብታቀና ግን አንተም እንዳልከው በቅኔው፣ በዘፈኑ፣ በሽለላው በቀረርቶው ወዘተ የአንበሳው ንግርት ደግሞ ውስጥ ውስጡን እንደቋያ እሳት እየተቀጣጠለ ታገኘዋለህ። ይህ በየትኛውም ማኅበረሰብ ውስጥ የማይቀር ነገር ነው። በኢትዮጵያም ዛሬ አይደለም ከዓመታት በፊት በዩኒቨርሲቲው መምህራን የተደረጉ ጥናቶች ያንን አሳይተዋል። ነገር ግን አሁን ያስጨነቀን ነገር አዳኙ ከመቆየቱ ብዛት አውሮፓውያን በየዓለማቱ በቅድመ - ባለአገሮች ላይ እንዳደረጉት ዓይነት የተጠናና የተቀነባበረ ጉዳት በአንበሳው ማኅበረሰብ ላይ እንዳያስከትል ምን እናድርግ? እንዴትስ በአንበሳው ማኅብረሰብ ውስጥ ያሉት እውነተኛ ታሪኮች ጎላ ብለው ይሰሙ? የአንበሳው ደግሞ ታሪክና ገድል በሬድዮ፣ በቴሌቪዥንና፣ በመጻሕፍት እንዴት ይሰራጩና የአንበሳው ማኅበረሰብ ካቀረቀረበት እንዴት ቀና ብሎ ይሂድ? የሚለው ነው። መፍትሔው አንተም ከትረካህ ጋር አያይዘህ የጠቀስከው ‘ሙሴ’ ነው። ሙሴ በየትኛውም ማኅበረሰብ ጠፍቶ ያውቃል ወይ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ‘በፍጹም’ የሚል ነው። ከላይ ያነሳናቸው በየክፍለ ዓለማቱ ያሉት ቅድመ ባለአገሮች እንኳን ‘ሙሴ’ ን እንዳላጡ ምልክቶች እየታዩ ነው። ሁላችንም ታሪኩን ልንደርስበት የቻልነውና እኔም ይህን ልጽፍልህ የበቃሁት የአዳኙ ብቻ ሳይሆን የአንበሳውም ታሪክ እየተሰማ መጥቶ እኛ ዘንድ ለመድረስ በመቻሉ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። በየትምህርት ቤቶችም ጅምሩ እየታዬ ነው። እውነት ነው የነዚህ ቅድመ-ባላገሮች ‘ሙሴ’ አልዘገየም እንዴ? የሚል ነገር ሽው ይልብኛል። ሙሴም የአርባ ቀኑ መንገድ አርባ ዓመት ፈጅቶበት የለም እንዴ? እርሱንም እላለሁ። ቢሆንም የነርሱ የበዛ ይመስላል። እንግዲህ ለአንዱ አርባ፣ ለሌላው አራት መቶ ያደረገው እግዚአብሔር ያውቃል። የእኛ ግን የአንበሳው ድምፅ ሞቅ እያለ የመጣበት ጊዜ ላይ ስለሆንን ብዙ የምንጠብቅ አይመስልም። ሆኖም ሙሴ ሦስቱን ንግርት የቀየረ ብቻ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር የሚጮህና በእጁም ባሕሩን ይከፍልበት፣ እባቡን ያጠፋበት፣ ከድንጋይ ውኃ ያመነጭበት በትር እንደነበረው ልብ ማለት ያስፈልጋል። ስለዚህ ሁሉም የጊዜ ጉዳይ ብቻ እንደሆነ በዚህ ትረዳዋለህ። እስከዚያው ግን የአንተና የሌሎች ችሎታውና እድሉ ያላችሁ ጸሐፍት ሥራ አሁንም ከምታደርገው በተጨማሪ እነዚያን የአንበሳውን ታሪኮች እየተከታተሉ ለብርኃን ማብቃት ነው። እርሱ ራሱ ወደር የማይገኝለት ትልቅ ተጋድሎ ነውና።
DEAR Daniel Kibret
ReplyDeleteYOUR views are always balanced and well studied....your historic cultural and religious background puts you on a very critical position ....a position which is more or less similar to the Prophet Moses.......these Times we are living in ....my brother.....is a very sensitive time in history i believe......i live in the USA......what i see here is very discouraging specially in our Ethiopian community.......we are losing the essence of being Ethiopian.....we have forgotten our history and heritage......we are going in a downward path......this place is not for us dear Daniel......our soul is not happy.......our children are not ours anymore......the medias and trends have taken them away from us......please Daniel ......please.....preach about all ethiopians to go back to our motherland.......please.....our country might be poor matrialy but spiritualy our motherland is rich......so Daniel please preach to the children of mother ethiopia to go back home.......Thank you Daniel Kibret.......Thank you
አገሬ በረሃብ ሳይሆን በብልፅግና ጎዳና ላይ ናት ስትባል ከብዙ ሚዲያዎች እና ምሁራን የሰማሁት እና ያየሁት በመለስ ዜናዊ ዘመን ብቻ ነው
ReplyDeleteዳኒ በቅድሜያ ለአንተው ውድ ወንድሜ እድሜና ጤና እመኛለሁ:: ለኛ ለአንባቤወችም አንብቦ ለመተግበር የሜያስችለንን አይነ ልቦና ይክፈትልን :: በርታ !!!
ReplyDeleteመለስ ዜናዊ ትርጉም ያለው ሞት ሞተዋል። የዘመነ አኩሱም ታላቅነታችን በ21ኛው ክ/ዘመን እንዲመለስ አድርጎ አልፈዋል።
ReplyDeleteታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ልክ እንደ አድዋ ድል ለመላው የአፍሪካ ጥቁር ህዝብ አኩሪ ክስተት ሁነዋል።
ዓለም በትልቅ አድናቆት እንዲመለከተን አድርገዋል። ይህ ግድብ የመራራው ትግልና መስዋዕት ፍሬ ነው።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ30% በላይ ደርሷል፡፡ “ግድቡ የኢትዮጵያውን አቅም የፈተነና የቀጣይ ልማታችን አጉሊ መነፀራችን ነው ።
መለስ ዜናዊ የይቻላል መንፈስና ተምሳሌትና የሀገራችን/አፍሪካ ምሰሶ ነው። “ሁሉመናችን ነው፣ ግድቡም ሉዐላዊነታችን፣ ክብራችንና ሂወታችን ነው። መጪው ትውልድ በተሻለ ኑሮ እንዲኖር መለስ ታላቅ ስራ ሰርቶ አልፈዋል”።
Dear anonymous who praise meles zenawi,
DeleteWe heard you, but I am not sure how much true this is. It is the same as with what dani said, "ተራኪነቱን የወሰደ ታሪኩን ይወስነዋል" ETV make all the story, we don't see valuable result on the ground. How many people benefited from "Meles's ..." Anyways, I heard a lot about him but never convinced with what heard, more convinced with what I see. So please, we have enough to hear about him, ETV, Aiga... leave this blog for others. Thanks
Welete Amanuel
we rely thank you Dn.
ReplyDeleteልክ እንደ ጥንቸሏና ኤሊዋ ታሪክ
DeleteGod bless you dani
ReplyDeleteDn. Daniel Edemena Tena yeseteh YeEthioia Amlak.Amen.
ReplyDeletesele ethiopia muslimoch chkona man yenagerlachew.
ReplyDeletekepp it up Dani! "Eskizoruh"
ReplyDelete