በአንድ ጫካ ውስጥ አንድ ከሺ ዓመታት በላይ እድሜ የጠገበ ዋርካ ነበረ፡፡ ዋርካው
እጅግ ሰፊ፣ ውስብስብና ታላቅ ነው፡፡ በላዩ ላይ አዕዋፍ፣ በሥሩም እንስሳት ይጠለሉ ነበር፡፡ ከፊሉ ፍሬውን ከፊሉም ቅጠሉን
ይመገባሉ፡፡ ሌሎቹም ግንዱንና ሥሩን ፍቀው ይበላሉ፡፡ አንዳቸው ለሌላቸው እንስሳትና አዕዋፍ የጠቀሙበት፣ አንዳቸውም አንዳቸውን
የበሉበት ዘመን ነበር፡፡ አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር የሚጋቡበት፣ አንዳቸውም ከሌላቸው ጋር የሚዋጉበት ዘመን አለ፡፡ ፈረስና
አሞራ ተጋብቶ ክንፍ ያለው ፈረስ ተወልዶ ነበር አሉ፡፡ ታላላቆቹ እንስሳት በልተዋቸው ዘራቸው የጠፉ እንስሳትም አሉ፡፡
እነዚህ እንስሳት አለመግባባታቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ አንዳንዶቹ ወፍነት፣
አንበሳነት፣ ዝሆንነት፣ ድመትነት የሚባል ማንነት እንጂ እንስሳነት የሚባል ማንነት የለም ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ እንስሳነት
የሚባል ማንነት እንጂ ወፍነት ወይም በግነት፣ ፍየልነት ወይም ጦጣነት የሚባል ማንነት የለም ብለዋል፡፡ ከዚህ የተረፉት ደግሞ
ሁለቱም አለ ይላሉ፡፤ እስካሁን ግን በአንዱም አልተስማሙም፡፡
ከዋርካው ሥር የሚያርፉት እንስሳት የዋርካው ቅርንጫፎች መቆረጥ አለባቸው የሚል አቋም
ይዘዋል፡፡ ለምን? ሲባሉ እነዚህ ጨቋኝ አዕዋፍ በኛ ላይ
ሲዘባነኑ፣ ኩሳቸውን ሲጥሉ፣ ከዚያም አልፈው ከላይ ሆነው እኛን ሲረግጡ የነበረው በቅርንጫፉ ላይ ሆነው ነው፤ የቅርንጫፉ መኖር
ግፍና መከራውን፣ ጭቆናና ስቃዩን ስለሚያስታውሰን መቆረጥ አለበት ባይ ናቸው፡፡
ሌሎቹ ደግሞ በዋርካው ሥር ላይ ቂምና ትችት አላቸው፡፡ ይኼ ዋርካ አንድ ቦታ ተተክሎ
የቀረው፣ ከመስፋትና ከመደርጀት አልፎ ተራማጅ ያልሆነው፣ ሥሩ ከምድር ጋር ተክሎ ስለተያያዘ ነው፡፡ ሥሩ ባይዘው ኖሮ ስንፈልግ
አውሮፓ ወስደን የበረዶ ዛፍ፣ ስንፈልግ ካልሃሪ ወስደን የበረሃ ዛፍ ማድረግ እንችል ነበር፡፡ ሥሩ ቸክሎታል፡፡ ስለዚህ ሥሩ
መነቀል አለበት ይላሉ፡፡
ሦስተኛዎቹ ወገኖችም እኛ ስለቅጠሉ እንጂ ስለ ፍሬው የሚያገባን ነገር የለም ብለዋል፡፡
እነዚህ ቅጠል በል የሆኑት እንስሳት በዋርካው ላይ ብቅ የሚሉትን ቅጠሎች ሁሉ እየቀነጠቡ ለመጨረስ በሩጫ ላይ ናቸው፡፡
እነዚህን ወገኖች ፍሬ በል የሆኑ እንስሳት ተቃውመዋቸዋል፡፡ ቅጠሉ ከሌለ ፍሬው አይገኝም፡፡ ዋካው እንዲያፈራ ቅጠሉን ተውለት
የሚል ክርክር አላቸው፡፡ እነዚያኞቹ ግን ስለ እናንተ የማሰብ ግዴታ የለብንም፡፡ እኛ ማሰብ የሚጠበቅብን ስለ ቅጠሉ ብቻ ነው
ብለው ዘግተዋል፡፡
እነዚህ ቅጠል በል እንስሳት ስለ ሌላው የዋርካው ክፍል አይመለከተንም ባይ ናቸው፡፡
ለእኛ ጉዳዩ የቅጠል ጉዳይ እንጂ የዋርካ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህንን ብለው ቅጠሎችን በሚያማምሩ ባለ ቀለም ላስቲኮች
ሸፈኗቸው፡፡ ይህ ጉዳይ ደግሞ የዋርካውን ሕይወት ማሳጠር
ብቻ ሳይሆን የሌሎችን እንስሳት የመኖር ሕልውናም አደጋ ላይ ጣለው፡፡ ቅጠሉ ከተሸፈነ ይወይባል፣ አየርና ፀሐይ ወስዶ ለዋርካው
ምግብ የሚሠራም አይኖርም፡፡ ዋርካውም ሕይወቱ በጭንቅ ሆነ፡፡ ቅጠል በሎቹ ለቅጠሎች የሠሩት ጌጥ እንደ መቃብር ላይ ጌጥ
ሆነ፡፡
ሌሎች ደግሞ መጡ፡፡ ይህንን ዛፍ ዋርካ ብለን መጥራት፣ ግንዱንም፣ ቅርንጫፉንም፣
ቅርፊቱንም፣ ቅጠሉንም፣ ፍሬውንም በአንድ ዋርካ ስም መጥራት የለብንም አሉ፡፡ የዚህ ዋርካ ታሪክ የመቶ ዓመት ታሪክ ነው፡፡
ለምሳሌ ከተወሰኑ ዘመናት በፊት ቅርንጫፎቹ እንደዚህ አልበዙም ነበር፣ ከመቶ ዓመታት በፊት እነዚህን ሥሮች አልሰደደም ነበር፣
ከሺ ዓመት በፊት ደግሞ በዚህ ውፍረት መጠን አልነበረም፡፡ አሁን በዚህ መጠን ስናገኘው ዋርካ አልነው እንጂ በየጊዜው ሌላ ስም
ነበረው፡፡ ችግኝ ነበረ፣ ቁጥቋጦ ነበረ፣ ዛፍ ነበር፣ ሌላም ነበረ፡፡ ይህንን ሁሉ ታሪክ ዋርካ ብለን መጥራት የለብንም
ይላሉ፡፡ ዋርካው ችግኝ እያለ፣ ቁጥቋጦ እያለ፣ ዛፍ እያለ የሠራው ነገር አይመለከተንም ባይ ናቸው፡፡
ክርክሩ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ሀብት ማለት ጥቅም ነው፡፡ አንዳች ግላዊ ጥቅም
የማታገኝበት ሀብት ያንተ አይደለም ማለት ነው የሚሉ ደግሞ ተነሡ፡፡ እነዚህ ዋርካው በዝቷል፣ ሰፍቷል፤ ስለዚህ ከቅርንጫፉም፣
ከጎንና ጎኑም እየፈለጥን በመሸጥ መጠቀም አለብን ይላሉ፡፡ ዋርካው በሥሮቹ አማካኝነት የሚስበውን ውኃና አፈር ለጎረቤት ዛፎች
እየሸጥን መጠቀም አለብን የሚል ሃሳብ አላቸው፡፡ የዚህ ተቃዋሚዎች ደግሞ ዛፉ የሚስበው ውኃና አፈር ለቅርንጫፎቹ አልበቃ ብሎ
ቅጠሎቹ ደርቀው፣ እንጨቶቹ ጠውልገው እየታዩ እንዴት ለሌላ እንሰጣለን፡፡ የራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ
ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች የተባለው ሊደርስብን አይደለም ወይ ይላሉ፡፡
የዋርካው ግንድ ተገቢ ቦታ አልተሰጠውም የሚሉም አሉ፡፡ ሥሩንና ቅርንጫፉን
የሚያገናኘው፣ ዋርካውንም የተሸከመው ግንዱ ሆኖ እያለ የሚደነቀውና የሚመሰገነው ግን ቅርንጫፉ ነው፡፡ አበባ የሚያወጣውና
የሚለመልመው ቅርንጫፉ ነው፡፡ የሚንዠረገገውና ግራ ቀኝ የሚሰፋው ቅርንጫፉ ነው፤ ለምን? ብለው ይጠይቃሉ፡፡
አንዳንዶቹ በዛፉ ሥር የተጠለሉ እንስሳት የወፎቹን ድምጽ መስማት እንፈልግም እያሉ
ነው፡፡ ሌሊት ሌሊት ተነሥተው ከዕንቅልፍ ለምን ይቀሰቅሱናል፡፡ ለምን አንተኛበትም? ደግሞም ዜማቸው ከጥንት እስካሁን ተመሳሳይ ነው፡፡ አዲስ የወፍ ዜማ አልመጣም፤
በቃ፤ ወይ ድምጻቸውን ይቀንሱ አለበለዚያም የጠዋት ዝማሬያቸውን ያቁሙ እያሉ ነው፡፡ ወፎቹም በበኩላቸው እነዚህ አራዊት ምድርና
ሰማዩን እያደባለቁ የሚለቁትን ግሳት ወይ ይቀንሱ ወይም ያቁሙ ብለው ይከራከራሉ፡፡
ሁሉም በየራሱ ብቻ ነው የሚሰባሰበው፡፡ ግንዱን የሚመገቡት ‹የግንድ ሰንበቴ›
አላቸው፣ ቅርንጫፉን የሚበሉት ‹የቅርንጫፍ ማኅበር› መሥርተዋል፤ ሥሩ ላይ ያሉት ‹ሥር ጽዋ› አቋቁመዋል፣ አሁን ግራ የገባቸው
እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ቅርንጫፉም ላይ መሬቱም ላይ የሚኖሩ እንስሳት ምን
ዓይነት ማኅበር ማቋቋም እንዳለባቸው ተቸግረዋል፡፡
በአንድ ወቅት አንድ ዘንዶ መጥቶ በዋርካው ሥርና ቅርንጫፍ ላይ በነበሩት እንስሳት
ላይ አደጋ አድርሶ ነበር፡፡ በዚያ አደጋ ምክንያትም ብዙ እንስሳት ተሰድደው ወደ ሌሎች ዋርካዎች ሄደዋል፡፡ እነዚህ የተሰደዱ
የዋርካው እንስሳት በዋርካው ዙሪያ ካሉት እንስሳት ጋር አንዳንድ ጊዜ አይስማሙም፡፡ የዋርካው እንስሳት እዚያ ማዶ ሆኖ ከመጮህ
ጎበዝ ከሆናችሁ እዚህ አትመጡም? ይሏቸዋል፡፡ የተሰደዱት
እንስሳትም ‹‹ወኔ የሌላችሁ፣ ድፍረት ያጣችሁ፣ ፈሪዎች›› ብለው ይመልሳሉ፡፡
ዋርካው አሁንም አለ፡፡ እየተፈለጠም እየተቆረጠም ቀጥሏል፡፡ በላዩና በታቹ ያሉት
እንስሳት ግን የሚያስማማቸው ነገር አላገኙም፡፡ እስካሁን የተስማሙበት ነገር ቢኖር በዛፉ ላይ በመኖራቸው ብቻ ነው፡፡ ሚዲያ
ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደቀረበ ሰው፣ ሁሉም የራሱን ድምፅ ብቻ ነው መስማት የሚወደው፡፡ የሚፈልጥ ሊፈልጥ፣ የሚቆርጥ ሊቆርጥ፣
የሚልጥ ሊልጥ፣ የሚከልል ሊከልል፣ የሚለቅም ሊለቅም፣ የሚንጥ ሊንጥ፣ የሚቀነጥስ ሊቀነጥስ፣ የሚነቅል ሊነቅል፣ ሁሉም በየወገኑ
ተዘጋጅቷል፡፡ ዋርካው ዋርካ ሆኖ እንዳለ እንዲቀጥል ማን ያትርፈው?
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው
yewarekawe zegoche rasachewen yeyu alebelezia hulume yatutal
ReplyDeleteVery nice Dany and Awsabyos. Dont worry! Ye Ethiopia 'Tinsae' is aproaching! If you (Dikon Dany) and Mr Alemnew Mekonen really understand the only one medicine for Ethiopian Unity. My Respect to Mr Alemneh Mekonen. Ethiopia Lezelalem Tinur.
Deletenice view dani...GOD BLESS YOU ALL THE TIME.
ReplyDeleteሁሉም የዋርካዉ ነዋሪዎች እንስሳት በሚያስማማቸዉ የጋራ ጉዳያቸዉ ማለትም ዋርካዉን ማዕከል ባደረገ ጉዳይ ላይ ዋርካዉ የጋራ ጉዳያቸዉ ስለሆነ ማለት ነዉ የጋራ መግባባት ላይ ሊደርሱና የጋራ አቋም ሊይዙ ይገባል ካልሆነ ግን ለዋርካዉ ህልዉና አደጋ ነዉ፡፡ it’s a very good article ጆሮ ያለዉ ይስማ ለጋራ ሀገር የየግል ፍላጎቶችን ወደ ጎን ብሎ የጋራ አቋም መያዝ የግድ ነዉ ፡፡
ReplyDeleteNICE VIEW!
ReplyDeleteሁሉም በየራሱ ብቻ ነው የሚሰባሰበው፡፡ ግንዱን የሚመገቡት ‹የግንድ ሰንበቴ› አላቸው፣ ቅርንጫፉን የሚበሉት ‹የቅርንጫፍ ማኅበር› መሥርተዋል፤ ሥሩ ላይ ያሉት ‹ሥር ጽዋ› አቋቁመዋል፣ አሁን ግራ የገባቸው እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ቅርንጫፉም ላይ መሬቱም ላይ የሚኖሩ እንስሳት ምን ዓይነት ማኅበር ማቋቋም እንዳለባቸው ተቸግረዋል፡፡
ReplyDeleteሁሉም በየራሱ ብቻ ነው የሚሰባሰበው፡፡ ግንዱን የሚመገቡት ‹የግንድ ሰንበቴ› አላቸው፣ ቅርንጫፉን የሚበሉት ‹የቅርንጫፍ ማኅበር› መሥርተዋል፤ ሥሩ ላይ ያሉት ‹ሥር ጽዋ› አቋቁመዋል፣ አሁን ግራ የገባቸው እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ቅርንጫፉም ላይ መሬቱም ላይ የሚኖሩ እንስሳት ምን ዓይነት ማኅበር ማቋቋም እንዳለባቸው ተቸግረዋል፡፡
ReplyDeleteWarkawa Hagery Ethiopia Yanchine gude Yimeslal
ReplyDeleteHello Danial
ReplyDeleteI am very disappointed by the previous post because you don’t have any evidence that she did it or not. It is not because she is my sister but all of our family shacked by the situation. In addition that she was crying the all day. If you can please remove it from your blog. Thank you. From Zenebu Family.
Hello the Anonymous person it is not about your sister it is about 95 million people calture and relagion. You care about one person but you didn't care about your cantury. Your sister she will pass one day but her bad job will stay with Ethiopian people. Please tell her to not post this kind sheet on her blog instead of coverup her gadam idea. God bless Ethiopia
Deletetebarek
ReplyDeleteHello Danial
ReplyDeleteI read it two times but I didn’t get your message. For me it looks like abstract picture. Your examples may referee religion, politics or Ethiopian people life style. Since I didn’t pass on your way, I don’t get on my way. Thank you so much.
My friend, I don't think the article is that much abstract. In a single sentence, the message is: "Members of any given association (country, community, religion,etc) should not focus only on individual interests, but they should see the big picture and get more concerned with matters that ensure the sustainability of their common house."
DeleteGod bless you Danny!
ReplyDeleteሚዲያ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደቀረበ ሰው፣ ሁሉም የራሱን ድምፅ ብቻ ነው መስማት የሚወደው፡፡
ReplyDeleteIT IS A GOOD ARTICLE :- THIS IS A TRUE HISTORY OF ETHIOPIA .
ReplyDeleteየችግሩ ምንጭ እንስሳቱና አእዋፋቱ ጸረ-ዋርካ ሲመጣ ተባብረው የማባረር የረጅም ጊዜ ልምድ ቢኖራቸውም በዋርካው ስር እንዴት ተስማምቶ መኖር እንደሚቻል አለማወቃቸው ነው!!ጊዜያቸውን በጉባኤ እየፈጁት ነው!!ሆኖም ዋሽቶ የሚያጣላ እንጅ ዋሽቶ የሚያስታርቅ ሽማግሌ የላቸውም!!ሁሉም ይናገራል እንጅ አያዳምጥም!!
ReplyDeleteየእንስሳ ባህሪያቸውን አሻሽለው ያለዋርካው ህይወትም ማረፊያም የለንም ካሉና ለዋርካው እኩል ባለቤቶች ስለመሆናቸው አእምሮዋቸው ካመነ ፍቅር ይወርዳል!!በራስህ ሊደረግ የማትወደውን በሌላው አታድርግ የሚለው ቃል እነሱንም ከገዛ ይለወጣሉ!!ያኔ የዝሆንን መዋረድ አእዋፋቱም የራሳቸው ጥቃት አድርገው ይወስዱታል!!
እንስሳነትና ዝሆንነት አንድ ሲሆኑ ሁለት፣ ሁለት ሲሆኑ አንድ ሆነው አንደኛው ማንነት ሌላኛኛውን ሳይውጠው፣ሳይደመስሰው መኖር እንደሚችሉ ማስረዳት!!ሁለቱ ማንነቶች የሚዋሀዱ እንጅ የሚሸካከሙ አይደሉም!!
ለዋርካው የአሁን ህልውና እኩል ከቆሙ ያለፈ እድሜውን በዘመን ቆጣሪዎች እንዲሰላ ስለሚደረግ በዚህ ላይ አለመነታረክ!!ለባለሙያ እንስሳት መተው!!
ሁሉም ዋርካውን እኩል ፍግ እያቀረበ እንክብካቤ ካደረገ ግንዱን መፍለጥ ሳያስፈልግ በፍሬው ብቻ ከሰፋሪዎቹም አልፎ ዋርካው ለሌሎች አእዋፍና እንስሳት ይተርፋል!!
መፍትሄው መፍትሄውን ከዋርካው ውጭ ካሉ የሌላ ዋርካ ሰፋሪዎች ሳይጠብቁ እንደራሳቸው ዋርካ ጸባይ ችግራቸውን ራሳቸው ለመፍታት መሞከር ነው!!ስለዚህ ካለእነሱ የእነሱን ችግር የሚፈታው የለም!!
የተሰደዱት እንስሳት ወሳኞች የዋርካው ነዋሪዎች መሆናቸውን ሳይስቱ ስለቀድሞ ዋርካችን ያገባናል ማለታቸው ክፋት የለውም!!የዋርካውን ንጉሥ ለማናደድና ለማጥላላት ሲሉ በጭፍንነት የዋርካውን ጥቅም እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ማድረግ ግን ግድ ነው!!
ለምሳሌ ሰሞኑን የዋርካውን ቅጠል ዘለላ ይዞ ስዊስ ለገባው ወፍ ገና ጉዳዩ ሳይጣራ በባእድ ዋርካ ስር ሆነው ወፋችን ጀግናችን ማለታቸው ደስ አይልም!!
አምላከ ኩሉ ፍጥረት፡ እንደእንስሳም፣እንደዝሆንም በግልም በቡድንም ሆነው ማንንም ሆድ ሳያስብሱ እነኚህን የዋሀን የምድር ፍጡራን የሁሉን ልብ ለማድረስ ያብቃቸው - በፍቅር ያኑራቸው!!
ክርክሩ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ሀብት ማለት ጥቅም ነው፡፡ አንዳች ግላዊ ጥቅም የማታገኝበት ሀብት ያንተ አይደለም ማለት ነው የሚሉ ደግሞ ተነሡ፡፡ እነዚህ ዋርካው በዝቷል፣ ሰፍቷል፤ ስለዚህ ከቅርንጫፉም፣ ከጎንና ጎኑም እየፈለጥን በመሸጥ መጠቀም አለብን ይላሉ፡፡ ዋርካው በሥሮቹ አማካኝነት የሚስበውን ውኃና አፈር ለጎረቤት ዛፎች እየሸጥን መጠቀም አለብን የሚል ሃሳብ አላቸው፡፡ የዚህ ተቃዋሚዎች ደግሞ ዛፉ የሚስበው ውኃና አፈር ለቅርንጫፎቹ አልበቃ ብሎ ቅጠሎቹ ደርቀው፣ እንጨቶቹ ጠውልገው እየታዩ እንዴት ለሌላ እንሰጣለን፡፡ የራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች የተባለው ሊደርስብን አይደለም ወይ ይላሉ፡፡
ReplyDeletebe 1 dingay .... Wadla kine
ReplyDeleteከዋርካው ሥር የሚያርፉት እንስሳት የዋርካው ቅርንጫፎች መቆረጥ አለባቸው የሚል አቋም ይዘዋል፡፡ ለምን? ሲባሉ እነዚህ ጨቋኝ አዕዋፍ በኛ ላይ ሲዘባነኑ፣ ኩሳቸውን ሲጥሉ፣ ከዚያም አልፈው ከላይ ሆነው እኛን ሲረግጡ የነበረው በቅርንጫፉ ላይ ሆነው ነው፤ የቅርንጫፉ መኖር ግፍና መከራውን፣ ጭቆናና ስቃዩን ስለሚያስታውሰን መቆረጥ አለበት ባይ ናቸው፡፡
ReplyDeleteዳኒ አንዳንዴ ጽሁፍህ ይረቅብኛል ስለዚህ ነው ስለዚያ ነው ለማለት፦ደረቅ ሐዲስ፦ውስጠ ዘ ፦ ተርጓሚ እሻለሁ አንድም እያለ የሚነግረኝ እንዳንተ በመንፈስ ያለ።
ReplyDeleteሳይገቡኝ የሚያልፉኝ አሉና፦ ግን አንተ ፀጋህን ግታልኝ እንዳትል አደራህን።
good obsarvation dani i think the probelame came not from that big WAREKA the probelam is with the anmals so they must be part of soulution as they reason the probelam . but they need 3prty who have big heart and visiry that show there coomomn-intreast.so the asnwer is us we must part of soulution
ReplyDeleteNurilin. Please put your articles in another book soon
ReplyDeleteEdimeh yirzem.
ReplyDeletejoro Yalew Yesema, Enasetewel
ReplyDeleteA very nice view. Decon Daniel! are we really underestand or do we see our self to be one of the consumer of this big''WARKA''if so, when are we going to put our indivjual demand and diferences aside and come together to live in this blleseed WARKA. when is going to happen when???
ReplyDeleteyihe warka fistamewn endiyasamir kemetseley anastagul
ReplyDeleteጆሮ ያለው ሁሉ ይስማ!
ReplyDeleteየራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች
ReplyDeleteየራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች
ReplyDeleteየራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች
ReplyDeleteጌታ መዳኔአለም እና የዋርካው ስር ያሉ ፍጡራን ኃላፊነታቸውንና ግዴታቸውን በአግባቡና በእኛነት ስሜት ሱወጡ…
ReplyDeleteእኔስ እንደጦጣዎቹና ዝንጀሮዎቹ ግራ ገብቶኛል!
ReplyDeleteየቀድሞው ዘንዶ ያስሰደዳቸውና (የአሁኖቹ እባቦች እያሰደዱዋቸው ያሉት) ግራ መጋባቴን ወደ ተስፋ መቁረጥ እየገፉት ነው፡፡
መች ይሆን ባለቅርን“ጫፎቹ” በሁሉም ነገር የራሳቸውን ወገን ጥቅም በማስቀደምና ሌላውን ቸል በማለት፣ ቅጠሉን በላስቲክ በመሸፈን በዋርካው ላይ እያደረሱ ያሉትን አደጋ ሁሉም የዋርካው አካላት ተባብረው በማስቆም ለሁሉም እኩል የሆነና የሚበቃ ዋርካ እውን የሚያደርጉት!
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
እግዚአብሔር ይባርክህ!
i think this "warika" can continue as strong "warika" if and only if all stockholders make consensus by avoiding selfish interest for the sake of common good. may God bless this "warka". kb z bihere Agazian.
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል :
ReplyDeleteምርጥ እና ድንቅ እይታ።
ዋርካውንም እንደ ዋርካ ሆኖ መጠነ ሠፊ አገልግሎቱ ቀጣይነት እንዲኖረው እግዚአብሔር ጤነኛ አዕምሮ እና የሚያስተውል ልብ ይስጠን።
እግዚአብሔር ይስጥልን፣ እንደ አንተ አይነቱን አስተዋዮችንም የአገልግሎት ዘመናችሁን ያብዛልን።
BE ewnet TALAK SEW NEHE
ReplyDeleteWENDEMACHIN
DANEL KIBRET
EGZIYABHER TSEGAWEN ABZETOLHAL AHUNM YABZALHE
SEBKETOCHIHENEM EKETATELALHU YE AGWLGLOT ZEMNHEN YIBAREKLEN YABZALENM !!!
"አሁን ግራ የገባቸው እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት ናቸው"፡፡ ዳኒ እግዚያብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ!
ReplyDelete"አሁን ግራ የገባቸው እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት ናቸው"፡፡ ዳኒ እግዚያብሄር እድሜና ጤና ይስጥህ!
ReplyDeleteምን መሰለህ ዲያቆን ዳንኤል፣ በሁሉም እንስሳት መካከል የእንስሳነት ባህሪነት ጠፍቶ በዘር በዘራቸው፡ በጎጥና በጎሳ መለያየታቸው ይመስለኛል (እንደ አሁኗ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ማለት ነው)፡ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥነት በመሃከላቸው በጣም ሰፍኗል፡ አንደኛው ዘር ሌላኛውን ዘር ከቻለም ለማጥፋት ካልቻለም የበታች ለማድረግ የማይረባ ሩጫ ይዘዋል፡ በመጨረሻ ግን መፍትሄው አንድና አንድ መሆን ነው፡ እንደአንድ ማሰብ ጠላትን በአንድነት መዋጋትና ለዋርካው ህልውና ጎጠኝነትና ዘረኝነት ሳያጠቃን እንደ አባቶቻችን በአንድነት መቆም ነው፡፡ ጎበዝ ዋርካው የአንዲቷ ኢትዮጵያ ተምሳሌት ነው፡ዘረኝነትን ከህሌናችን አስወግደን በአንድነት በጋራ ለኢትዮጵያ ታላቅነት እንስራ ፡፡ እግዚአብሄር ጸጋውን ያብዛልህ ዲ/ን ዳንኤል፡፡
ReplyDeleteጎበዝ ዋርካው የአንዲቷ ኢትዮጵያ ተምሳሌት ነው፡
Deleteየራሳችን እያረረብን እንዴት የሰው እናማስላለን፣ ራሷ ሳትጠና ልታቋቁም ሄደች
ReplyDeleteሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡ እጅግ በጣም ወቅታዊና አስተማሪ ፅሁፍ ነው፡፡ ዋርካችን የሆነች ኢትዮጵያን ጌታ እግዚአብሄር ይጠብቅልን፡፡
ReplyDeleteከጎንደር ልደታ
ከተቀመጡ የየራሳቸዉን ይዘዉ ይቀመጡ አለበለዚያ በዋርካዉ ቀድመዉ የነበሩት ይኑሩበት።
ReplyDeleteplease someone help me what is ባለ ቀለም ላስቲክ & ቀለም ?
ReplyDeleteI know interpreting someone's qine is wrong but I eagerly want to know,, please
ጫካ---- አፍሪካ,ዓለም
ዋርካ -----ኢትዮጱያ
አዕዋፍና እንስሳ--- ኢትዮጵያውያን
ፈረስና አሞራ--- ጭቁኑ ህዝብና ገዢ መደብ
ወፍነት፣ዝሆንነት፣ ድመትነት የሚባል ማንነት እንጂ እንስሳነት የሚባል ማንነት የለም ይላሉ-----ትግራዋይነት ዝበሃል ንጹሕ መንነት አለና ኢትዮጵያዊ ዝበሃል መንነት የለን
ሌሎቹ ደግሞ እንስሳነት የሚባል ማንነት እንጂ ወፍነት ወይም በግነት .. የሚባል ማንነት የለም ብለዋል----ኢትዮጵያዊ ማንነት እንጅ የብሔረሰብ ማንነት የለም የሚሉ
ቅርንጫፉ መቆረጥ አለበት----እንገንጠል ባዮች
ስር-- የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን
ቅጠል በል----አርቲስቶች-- እንዲሁም ብር እስጋስገኘ ድረስ ምንም የማይስላቸው ባለሃብት,, Lnad grabbers
ችግኝ ቁጥቋጦ ዛፍ ይባል ነበር----አቢሲኒያ፣ሀበሻ፣ የኩሽ ምድር የሚሉ የጥንት ስሞች
ለጎረቤት ዛፍ እየፈለጡ መሸጥ----አሰብና ሱዳን ድንበር
ግንድ---ሰፊው ሕዝብ --አርሶ አደር
የወፎቹን ድምጽ መስማት እንፈልግም-----አማርኛ መማር አንፈልግም or የቤተክርስቲያን ቅዳሴና የመስጊድ አዛን ድምጽ ይቀነስልን የሚሉ
እንደ ዝንጀሮና ጦጣ ከላይም ከታችም የሚሆኑት እንስሳት -----በብዛት ከተማ የሚወለዱና ከተቀላቀለ ብሔረሰብ የሚወለዱ
የቅርንጫፍ ማኅበር---Ethnic based political parties or any association
ዘንዶ-----መንጌ/ደርግ/
የተሰደዱ እንስሳት-- ዲያስፖራ
Nice interpretation, I agree with your ideas indeed.
Deleteቅጠል በሎቹ “እንስሳት” ቅጠሉን በባለቀለም ላስቲክ ሸፈኑት፡፡ ፍሬ-በሎቹ ቢል በቀና ነበር - ለፍሬው ሲሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ባለቀለም ላስቲክና ቀለም --- አስመሳይ የሚዲያ ሽፋን ወይም “አላዋቂ ሳሚ” ዓይነት ሥራ የሚሰሩ ባለሥልጣናት ይመስለኛል፡፡
Deleteu got it
DeleteAm from neghpor and if it is OK I just want to say please protect your warka it is OK to have different ideas but work to stay unit and respect each other b/c love that warka. And Daniel you are my hero . God bless you
ReplyDeletewe can clearly look that how much scary and ugly is right of freedom of expression in ETHIOPIA...had it not been this article wil be naming ETHIOPIA and so called"partys"and diaspora!!!The article is whole truth...
ReplyDeleteይህ ዋርካ በቅርብ ጊዜ መቆረጡ አይቀርም
ReplyDeleteስለዚህ ምን እናድርግ??
Deleteጆሮ ያለዉ ይስማ ለጋራ ሀገር የየግል ፍላጎቶችን ወደ ጎን ብሎ የጋራ አቋም መያዝ የግድ ነዉ ፡፡
ReplyDeleteWhat is this Dani? Is this a country and its habitats? Wow, what a mystery!
ReplyDeleteKe Tana Dar.
Very interesting! but i don't agree that the difference that existed between animals is as small as the one that existed between two ethnic groups. A tiger and a bird are quite different species with totally different culture, ideology, background and hence i don't think no one says there is no such identity ....any way 'MISALE ZE YEHATSETS' keep on doing your job bro
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማህ እረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን
ReplyDeleteግዚክስ
ጠጂን በብርሌ
ReplyDeleteነገር በምሳሌ
ይሉ ነበር አበው ፡፡ የኛ ትውልድ ግን ቀጥታም ተነግሮት ተገባው ተመስገን ነው፡፡ ችግራችን ድንቁርና ንውና! ዘረኝነት እኮ ድንቁርና ነው፡፡ በዋርካው ላይ ያሉት እንሰሳት መሃል ያለው ተፈጥሮአዊ ልዩነት በመሠርቱ በኛ በሰዎቹ (ሰው ነን ይሆን?) መሀከል የለም ፡፡ ለኛ ይጣመንም አይጣመን ፡ በዓለም ላይ ያለው አንድ የሰው ዘር ብቻ ነው ፡፡ በየቀኑ እለታዊ ምግቡን አግኚቶ መኖር የተሳነው ህዝብ የተከማቸበት አገር ፡ መሰረታዊ ችግራችን ሌላ ነው፡፡ እኛ ምን ጨንቆን ፡ የዓለም ህዝብ ትባብሮ ፡ የተራበውን ይመግብልናል፡፡
Thanks Dani! you did your side. that is it.
ReplyDeleteድሮም ቢሆን ዘነቡ ለሴቶች ሳይሆን ለራሷ ስሜት የቆመች ሌባ ናት በአንድ ጉዳይ አዉቃታለሁ በሴቶች ላይ የሚሰሩ Ngoወችን ብር በኔ በኩል ይሁን የምትል ሌባ አይደለች
ReplyDelete