Tuesday, February 25, 2014

‹‹የጠቅል አሽከር¡››

በንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የንጉሡ አሽከሮች፣ ወዳጆችና፣ አድናቂዎች ‹‹የጠቅል አሽከር›› ብለው ይፎክሩ ነበር፡፡ ‹‹ጠቅል›› የዐፄ ኃይለ ሥላሴ የፈረስ ስም ነው፡፡ የጠቅል አሽከር -ማለትም የዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሽከር ብሎ እንደ መኩራራት ነው፡፡ ያ ዘመን አለፈ፡፡ ጠቅልም አሟሟታቸው በቅጡ ሳይታወቅ በደርግ ተገደሉ፡፡ የጠቅል አሽከሮች ግን መልካቸውን ቀይረው ዛሬም አሉ፡፡
ዛሬ ያሉት የጠቅል አሽከሮች ‹‹የጠቅል አሽከር›› ብለው የሚፎክሩ አይደሉም፡፡ እንዴው ዝም ብለው የሚጠቀልሉ ናቸው፡፡ አንድን ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ፣ አንድን ሀገር፣ ክልል ወይም አካባቢ እንዴው ጠቅልሎ ‹‹እንዲህ ነው እንዲያ ነው›› ብለው የሚፈርጁ ናቸው፡፡ ኦሮሞ እንዲህ ነው፣ አማራ እንዲህ ነው፣ ትግሬ እንዲህ ነው፣ ሶማሌ እንዲህ ነው፣ ሲዳማ እንዲህ ነው፣ አፋር እንዲህ ነው ብለው የሚደመድሙ ናቸው የጠቅል አሽከሮች፡፡

አንድ ሕዝብ፣ ብሔር ወይም ብሔረሰብ በውስጡ ሚሊዮን ሰዎች፣ የተለያዩ አስተሳሰቦች፣ የተለያዩ ፍላጎቶች፣ ዕውቀቶችና ለብዙ ዘመናት የተከናወኑ ለውጦች፣ የሚገኙበት የማኅበረሰብ ክፍል ነው፡፡ በርግጥ ያንን ሕዝብ አንድ ሕዝብ የሚያደርጉት የጋራ ባሕል፣ ቋንቋ፣ እምነት፣ የአነዋወር ዘይቤ ይኖረዋል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም የዚያ ብሔር ወይም ብሔረሰብ አባል ያንን ተቀብሎ፣ አምኖና ተግብሮ ይኖራል ማለት አይደለም፡፡ ከዚያ ማኅበረሰብ አንዱን ወይም ሁለቱን የጋራ እሴት ብቻ ወስዶ ሌላውን ከሌላው ብሔረሰብና አካባቢ፣ አልፎ ተርፎም ከሌላ ሀገር ሕዝብ የሚወስድ፤ ጭራሽም በትውልድ የዚያ ማኅበረሰብ አባል ከመሆኑ በቀር በቋንቋ፣ በእምነት፣ በባሕል ወይም በአነዋወር ዘይቤ የማይመሳሰል ሰውም አለ፡፡
በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚወደድ፣ የሚደነቅ፣ የሚኮራበት ባሕል፣ አስተሳሰብና አነዋወር እንዳለ ሁሉ፤ የማይፈለግ፣ የሚነወርና የሚጎዳም አለ፡፡ ከማኅበረሰቡ አንዳንዱ የማይፈለገውን፣ የሚነወረውንና የሚጎዳውን ለማስቀረት ሲታገል፣ ሌላው ደግሞ ለምን ትነካብኛለህ? ብሎ የሚታገል አለ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ ልዩ ልዩ ማኅበረሰቦች ተዋሕደውና ተዋውጠው ሌላ ዓይነት ማኅረሰብ ይፈጥሩና ያ የተፈጠረው ማኅረሰብ የብዙ ባሕሎች፣ አመለካከቶች፣ ቋንቋዎችና አነዋወሮች ቅይጥ የሚሆንበትም ጊዜ አለ፡፡  
እንዲህ ያለውን እውነታ ድጦና ደፍጥጦ አንድን ሕዝብ ‹‹እንዲህ ነው፣ እንዲያ ነው›› ብሎ ደምድሞ መናገር የጠቅል አሽከር መሆን ነው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የሚናገሩ አንዳንድ እናውቃለን ባዮች ‹‹ይሄኛው ትምክህተኛ፣ ያኛው ጠባብ፣ ይኼኛው ደግሞ ገዥ፣ ያኛው ጎሰኛ፣ ይኼ ደግሞ ተገንጣይ ነው›› ብለው በድምዳሜ ይናገራሉ፡፡ ያ ማኅበረሰብ ተነጋግሮና ተስማምቶ እኔ እንዲህ ነኝ፣ ይህንን እቀበላለሁ ባላለበት ሁኔታ አንተ እንዲህ ነህ ብሎ ደምድሞ መናገር እንዴት ይቻላል? የጠቅል አሽከር ካልሆኑ በቀር፡፡
ይህ የጠቅል አሽከርነት በዕለት ተዕለት ኑሯችንም ላይ ይታያል፡፡ አበሻ ምቀኛ ነው፣ አበሻ ቀጠሮ አያከብርም፣ አበሻ ወሬኛ ነው እያሉ መደምደም ነው የጠቅል አሽከሮች አሉ፡፡ የተወሰኑ፣ የምናውቃቸው፣ ያጋጠሙን ሰዎች ምቀኛ፣ ሸረኛ፣ ቀጠሮ የማያከብሩ፣ ወሬኞች ለሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚያ ሰዎች ግን 80 ሚሊዮን ሕዝብን ወክለው ‹አበሻ› የሚያሰኙ አይደሉም፡፡ አበሾችም እነርሱ ብቻ አይደሉም፡፡ አንዳንድ ሰዎችማ አንድ የሚያበሳጭ፣ የሚያስቆጣ ወይም ያልተገባ ሥራ የሚሠራ ሰው ሲያጋጥማቸው ‹አይ አበሻ› ‹ድሮስ አበሻ›› ማለት ይቀናቸዋል፡፡ ‹‹ደግሞ ለአበሻ›› ብላ ንቀውን ተጸይፈውን የደመደሙ የጠቅል አሽከሮችም ሞልተውናል፡፡ በተቃራኒውም እንዲሁ በጎ በጎ ነገሮችን ሁሉ ጠቅልለው ለፈረንጅ የሚሰጡ የጠቅል አሽከሮችም አሉ፡፡ ‹አይ ፈረንጅ› ብለው የሚፎክሩ፡፡  የፈረንጅ ምቀኛ፣ ተንኮለኛ፣ ሸረኛ፣ ጎጠኛ፣ ወሬኛ የሌለ የሚመስላቸው፡፡ ያውምኮ በቢሊዮን ከሚቆጠር ፈረንጅ ሃያ ሠላሳውን ይሆናል የሚያውቁት፡፡ ለእነርሱ ሂትለርና ሞሶሎኒ፣ ኢያጎና ሻይሎክ አበሾች ናቸው፡፡
‹አይ የዛሬ ሴት›፣ ‹አይ የዛሬ ወንድ› የሚሉ የጠቅል አሽከሮችስ አልሰማችሁም? ሁለት ሴቶች፣ አራት ወንዶች ባደረጉት ነገር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ወንዶችንና ሴቶችን የሚጠቀልሉ፡፡ አይ ነጋዴ፣ አይ ጋዜጠኛ፣ አይ ቀበሌ፣ አይ ወረዳ፣ አይ ሐኪም፣ አይ  ታክሲ፣ አይ ወያላ፣ አይ የዛሬ ተማሪ፣ አይ ሆስተስ፣ እያሉ የሚጠቀልሉስ፡፡ ምንም ያህል አብዛኞቹ በችግር ውስጥ ቢነከሩ፣ በሥነ ምግባር ድቀት ቢዳክሩ፣ በግል ጥቅም ቢታወሩ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለዘር የሚተርፉ አሉ፡፡ የጠቅል አሽከርነት ግን ለእነዚህ ለትሩፋን ቦታ የለውም፡፡ የጠቅል አሽከርነት ካልጠቀለለ ነጥሎም አንጥሮም ማየት አይቻለውም፡፡  
ያለፈው ታሪካችን ሁሉ አስከፊ፣ አስጸያፊ፣ አንገት አስደፊ ነው ብለው የሚደመድሙ፤ የቆየ ነገር ሁሉ ኋላ ቀር፣ ጎታችና ለዕድገት ፀር የሚመስላቸው፤ የእነርሱ አያቶች ሲዋጉና ሲራቡ ብቻ የኖሩ አድርገው የሚገምቱ የጠቅል አሽከሮች እንዳሉት ሁሉ የቀድሞው ነገር ሁሉ ምርጥ፣ ልዩ፣ ሊነካ የማይገባው፣ እንዳለ መጠበቅ የሚገባው፣ እንከን የማይወጣለት አድርገው የሚፎክሩ የጠቅል አሽከሮችም አሉ፡፡
ለእነዚህ የጠቅል አሽከሮች በንጉሡ ዘመንና በደርግ ዘመን ምንም ዓይነት በጎ ሥራ አልተሠራም፡፡ ለእነርሱ ዋናው ጉዳይ ሥራው ሳይሆን የተሠራበት ዘመን ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ሥርዓቶች ሰው ሲገደል፣ ሲጨቆን፣ ሲራብ፣ ሲገፋ፣ ሲሰደድ፣ ብቻ ነው የነበረው፡፡ ሌላ ነገር አልነበረም፤ ሌላ ነገር አልተሠራም፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አሁን ባለንበት ዘመን ምንም ዓይነት መጥፎ ነገር የለም፤ ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ ነው፡፡ ዛሬ ሁሉ ደልቶት፣ ሁሉ ተመችቶት ነው የሚኖረው፡፡ ለዚያኛው ሙሉ ጥላቻ፣ ለዚህኛውም ሙሉ ፍቅር አላቸው፡፡ ያኛው ፍጹም ሰይጣን፣ ይኼኛውም ፍጹም መልአክ ነው፡፡
በአንድ በኩል የፕላቶ የአሪስቶትልና የሶቅራጥስና የስክንድስ ፍልስፍና፣ የእስክንድር ታሪክ፣ የበርለዓም የሕንድ መጽሐፍ፣ የዮሐንስ መደብር የዓለም ታሪክ፣ ፈውስ ሥጋዊን የመሰለ የሕክምና መጽሐፍ መኖራቸውን ዘንግተው በግእዝ የተጻፈው ሁሉ ሃይማኖታዊ፣ ቅዱስና ለጽድቅ ብቻ የተጻፈ የሚመስላቸው የጠቅል አሽከሮች እንዳሉት ሁሉ፤ እንድ እና ሁለት መጻሕፍትን ብቻ ተመልክተው በግእዝ የተጻፉትን ነገሮች ሁሉ ከሃይማኖት ያለፈ ፋይዳ የሌላቸው አድርገው የሚደመድሙ የጠቅል አሽከሮችም ሞልተዋል፡፡
የአማርኛ መጽሐፍ አላነብም፣ የአማርኛ ፊልም አላይም፣ የአማርኛ ዜና አልሰማም የሚሉ የጠቅል አሽከሮች፡፡ በእንግሊዝኛ የተጻፈ ሁሉ ዕውቀትና ብልሃት የሚመስላቸው፡፡ የዚህ ሀገር ልብስ፣ የዚህ ሀገር ጫማ፣ የዚህ ሀገር ቦርሳ፣ የዚህ ሀገር ዕቃ፣ የዚህ ሀገር ሁሉ ቀሽም ነው ብለው የደመደሙ የጠቅል አሽከሮች - እዚህ፣ እዚያ እዚያ ማዶም አሉ፡፡
መጠቅለል ልዩ ነገርን እንዳናይ ይጋርዳል፡፡ ከመቶዎች ውስጥ ልዩ ለሆነው አንድ ሰው ዕድል እንዳያገኝ ያግዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ለመታየትና ለመሰማት ዕድል ባላቸው ጥቂት አካላት ምክንያትም የመጡበትን አካባቢ፣ ማኅበረሰብና ሙያ ደምድመን እንድንናገርም ያደርገናል፡፡ በዚህ ምክንያት ደግሞ የተለየ ነገር መሥራት፣ የተለየ ጠባይ መላበስ፣ የተለየ አመለካከት መያዝ፣ የተለየ አነዋወር መኖር የሚፈልግ ሰው ከተጠቀለሉት ነጥሎ የሚቀበለው ስለማይኖር በጠቅል አሽከሮች ተደፍቆ ይቀራል፡፡ ብዙ ሰው የተናገረለት ነገር ደግሞ ሰነባብቶ እማሬ ይሆናል፡፡ ከዚያም ያንን ማስተባበል ይከብዳል፡፡አንድ እግረኛ ያወራውን ሃምሳ ፈረሰኛ አይመልሰውም ይባላልና፡፡ እኛ ግን ለራሳችን  እንዲህ እንበል ‹የጠቅል አሽከር አይደለሁም››፡፡ እነዚህንም  ያለ መረጃና፣ ያለ ማስረጃ፣ ያለ ዳታና ያለ ይሉኝታ እየጠቀለሉ የሚናገሩትን ‹‹የጠቅል አሽከር›› እንበላቸው፡፡ እንዴው ቢታረሙ፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው


31 comments:

 1. ዳኒ በጣም አመሰግንሃሎህ። ካሁን ቡሃላ ‹የጠቅል አሽከር አይደለሁም› ብያሎህ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Oh D. Dany, betam teshashlehal thank you! Mizanawi honeh sagegneh des alegn. It is after 4 sth months that I'm visiting your blog now. Yehone semon ahyawun ferto dawlawn aynet neger tesemtogn, yante blog lene le oromow min yseralgnal bye neber. It is nice, you should advise both your relatives and us. Especially your relatives, as alemneh did - zat is what I do to my relatives. Actually we all are relatives. Ethiopia Lezelalem Tinur. (I just wrote this to you, you may not post it). Yibarkh

   Delete
 2. በጣም ግሩም እይታ ነው ዲ/ን ዳንኤል፤ በጠቅል አሽከሮች ምክንያት ስንት ነገር ተበላሸ? ከጠቅል አሽከሮች ይጠብቀን እኛም የጠቅል አሽከር ከመሆን እንጠበቅ

  ReplyDelete
 3. ዛሬ ያሉት የጠቅል አሽከሮች ‹‹የጠቅል አሽከር›› ብለው የሚፎክሩ አይደሉም፡፡ እንዴው ዝም ብለው የሚጠቀልሉ ናቸው፡፡ አንድን ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ፣ አንድን ሀገር፣ ክልል ወይም አካባቢ እንዴው ጠቅልሎ ‹‹እንዲህ ነው እንዲያ ነው›› ብለው የሚፈርጁ ናቸው፡፡ ኦሮሞ እንዲህ ነው፣ አማራ እንዲህ ነው፣ ትግሬ እንዲህ ነው፣ ሶማሌ እንዲህ ነው፣ ሲዳማ እንዲህ ነው፣ አፋር እንዲህ ነው ብለው የሚደመድሙ ናቸው የጠቅል አሽከሮች፡፡

  ReplyDelete
 4. Grum Mastewal!!! Egziabher Yabertah!

  ReplyDelete
 5. ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ለጠቅል አሽከሮችም ልቦና ይስጥልን፡፡
  ዳኒ ለማይጠገበው፡ የዘወትር ጽሁፍህ አምላክ አብዝቶ ይባርክህ፡፡
  ግዚክስ

  ReplyDelete
 6. Thank you very much! May God give you strength and wisdom! This is best article.

  ReplyDelete
 7. Sentu sayawkew yetekele ashker honoal???

  ReplyDelete
 8. That is a great article! I hope you would also recognize the fact that not all gays are pedophiles, sick or perverted as you once referred to them. Some people want to live their life and be left alone. I am sure you don't want someone to tell you how to live your personal life, so why interfere in somebody's private life. I know the topic is different but still you had made some harsh comments about a group of people. I wish most Christians would be CHRIST-LIKE, but instead I see a lot of hate and contempt for those they disagree with. If Jesus Christ is here on earth today, he would spend most of his time with the people who are oppressed, hated, spat-on, and so called sinners. He showed us love by loving the sinners, and now many Christians and Muslims are calling for the murder of gays and others. Please write an article about not judging others, and give people a lesson in how to love each other because I see a lot of intolerance and anger in the Ethiopian Community . Thank you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You may be homosexual and it has no no place in Ethiopia. Homosexuality is anti nature and immoral. Homosexuality is a cancer to the continuation of humanity. It should be iliminated from the face of the earth. I strongly support recent times actions of Uganda.

   Delete
  2. My friend,

   Homosexuality is a perverted phenomena. YOu can't bring the above opinion of the writer to consolidate your view on homosexuality. It is absolutely against nature and GOD. But as a christian we don't hate gays but that doesn't mean it is the right thing to be a gay. We don't accept the idea but we still respect the people, love them and care about them. As a christian our reference to see things is the bible and the bible doesn't support the idea of Homosexuality.I wish i could write more on this but i am not good in expressing my views. GOD be with you.

   Delete
  3. @Maru Kebede & Anonymous!!
   First and foremost, I am not homosexual, but I don't like to see people being oppressed. The Uganda Law allows the government to kill and arrest Gays. Can we all let God be the judge and not judge others? Isn't that what Jesus taught us? When you judge others, make sure you are without sin all your life. It is very Unchristian of you to suggest you are better than gays. Please!! I beg all of the readers!! drop the hate, stop looking at other people's lives and start cleaning up your dirt. DON'T COMMIT SIN BY SUPPORTING THE OPPRESSION OF THE SINNERS. May God bless you!! And next time, let us be nice to each other and be Christ-like when we give comment on a topic (no name calling) !!! Thank you. God bless you

   Delete
  4. @anonymous 12:49
   Do you have kids? If you have respond on the subject.
   I guess from your words that you do not have kids. Even though what I advice you is that try to differentiate the sin and the sinner. As a sin it is awesome and generation killer. And also in our culture we have a habit to express one thing with its holder. This is the reason of most of the writer against you as I understand, I believe in terms of holiness no one will say I am greater than a sinner person. Instead they may express there feeling using the holder. And I feel this is not as such a bad habit.
   Regarding the law of the government I do not agree with your thought. Any Government has an obligation to keep the social welfare of the people. To keep the social welfare a death sentence may be part of the law. This part of a law should not be compared and contrasted with individual obligation of the bible. I believe adding some time for the sinner might help for him to regret, but we are not confidential on it as well he might spoil others life. In any ways what I want to say is that do not mix individuals with governments if you got me.
   Last but not least what I have for you is one of our greatest proverb 'see it by giving birth' "WOLDEH EYEW"

   Delete
 9. ስንወለድ ተጠቅልለን ስንሞት ተጠቅልለን
  ስንኖር ጠቅለን ስነቀስድ ጠቅለን
  ስንበላ እነጀራውን ጠቅልለው
  ስነገዛ እቃውን በወረቀት ጠቅልው
  ጨረቁን ጠቅልለው
  መጠቅለል ኑራችን ነው በቃ የሄው እኔም ጠቀለልኩ

  ReplyDelete
 10. እኛ ግን ለራሳችን እንዲህ እንበል ‹የጠቅል አሽከር አይደለሁም››፡፡ እነዚህንም ያለ መረጃና፣ ያለ ማስረጃ፣ ያለ ዳታና ያለ ይሉኝታ እየጠቀለሉ የሚናገሩትን ‹‹የጠቅል አሽከር›› እንበላቸው፡፡ እንዴው ቢታረሙ፡፡ good view dani

  ReplyDelete
 11. ከደቀመዝሙርFebruary 25, 2014 at 5:05 PM

  የጠቅል አሽከሮች ያልካቸውን ለይተህ ሳይሆን ጠቅልለህ ስለነገርከን ጉዳዩ ጠቅልን በጠቅል ሆነብኝ. ያልካቸው ሰዎች ስለመኖራቸውስ አንክድም. የጠቅላይነቱ ሀሳብ እንዴት፣ ለምን፣ ከምን፣ መነጨ የሚለው ጥልቅ የማህበረሰብ ጥናት ሳይጠይቅ ቀረ ብለህ ነው. ይጠይቃል.
  ማንነት የሚያያዘው ከደም ጋር ነው ወይስ ከባህል ጋር በሌላ አነጋገር ተፈጥሮአዊ ነው ወይስ በልማድ ከማ/ሰቡ የምናገኘው የሚለው ብዙ የሚያጨቃጭቅና የሚያጽፍ ነው. ሀሳቡ ለክፋት ሳይሆን ለበጎነት፣ለመራራቅ ሳይሆን ለመተባበር ቢጠና መልካም ነው.
  የነገድና የትውልድ ዘር ቆጥሮ መመካትና የእነ እከሌ ልጅ ማለት ባፍም በመጣፍም የታወቀ ነው. በተለይ ቤተእስራኤሎች በ10ሩ እና በ2ቱ ነገድ መሀል የሆነ ብዙ የፍቅርም የጦርነትም ታሪክ አላቸው.
  በእኛም የእነእከሌ ዘር የሚሉ ብዙ ሽለላዎች አሉ. እንዲያውም የአማርኛ ባህል ዘፈኖች አካባቢያዊነትን ወደ ማንገስ የወረዱ እስኪመስሉ ድረስ የጎንደሩ ዜማ ያለ ንጉሥ ቴዎድሮስ፣የሸዋው ያለምኒልክ እንዳይሰራ የተደነገገ እስኪመስል ድንበሩን ደንብረውታል. ስለዚህ ሌላውም በተቀደደለት ይፈሳል. እኔ የዚህ ነኝ እኔ የዚያ ነኝ የሚለው ፈሊጥ ባሁን ዘመን ጎልቶ የወጣ ቢመስለንም ወትሮም የነበረ ስለመሆኑ የታሪክ ድርሳናቱም ይጠቁማሉ.
  እንዲያው ጾም ቢሆንም ዘፈን ከተነሳ ሁሉም ሰው ደግ ነው ብሎ መነሳት ኃጢኣት አይደለምና የእከሌ ልጅ የለውም ኣባይ የሚለው ያስኬዳል. ያልተፈረደበት ሁሉ ነጻ ነው ይላል ህግም. አንድን ማህበረሰብ እንዲህ ነው ብሎ በክፉ መበየን ግን ኑፋቄ ነው. አጥፊው ግለሰብ የተገኘበትን ቡድንም ሆነ ማህበረሰብ ከአጥፊው ተነስቶ መፈረጅም ወንጀል ነው. ምክንያቱም ኃጢአትም ሆነ ወንጀል በግብረአበርነት እስካልተሰራ ድረስ ግለሰባዊ ብቻ ተደርጎ ስለሚወሰድ.
  ስለዚህ ዳኒ ያነሳኸው ሀሳብ ሀሰት የለበትም. ምናልባት ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ የሚሉትንና ቅድመ ኢህአዴግ የነበረው ነገር ሁሉ በጠቅላላው ገነት ነበር ከዚያ ወዲህ ግን ምድሪቱ ሲኦል ሆነች የሚሉትን ጠቅላዮች ዘለሀቸዋል. ይሄው እሱን እኔ ሞላሁት.
  ዳኒ እረ አንተንስ ያቆይህ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተም ደጋግመህ በጻፍክና የዳንኤል ደቀመዝሙርነትህ በጸና ጃል!! የበርካታ ዋዘኞችን አስተያየት ላለማንበብ ወደአስተያየት ዝቅ ማለት ታክቶኝ ነበር ሆኖም እነደቀመዝሙርን እንዳላጣ ብዬ ዝቅ አልኩ፡፡

   Delete
 12. የጠቅል አሽከር beyachewalew

  ReplyDelete
 13. በተባለ በአሉ በአሉ
  ስንጠቀለል ሲጠቀልሉ
  ስንጠቀልል
  ስናጠቃልል
  ታርጋ ስንለጥፍ
  ነገር ስናራግፍ
  ለከንቱ ለማይጠቅም ነገር
  አቃቂር ስንከምር
  ስመ ስናወጣ ስን'ለጥፍ ከርመን
  ሲጠቀልሉ ስንጠቀልል ኖረን
  ይኸው መጨረሻ ተጠቃለን ቀረን

  ReplyDelete
 14. ዳኒ አንተም ፣ ቤተሰብሕ ለበረከት ሁኑ ። ተደጋግሞ ከተነበበ ሰምና ወርቁ ግሩም ነው።

  ReplyDelete
 15. Dani I don't have words to express my admire ! God keep for us this bright minded man ! Long life D/n Dani !

  ReplyDelete
 16. የጠቅል አሽከርነት ካልጠቀለለ ነጥሎም አንጥሮም ማየት አይቻለውም፡፡ በእውነት በዚህ ያልሳተ ሰው ብጹእ ምስጉን ነው!

  ReplyDelete
 17. great Dani, Titsifewaleh meches!
  there are people Tekili Ashikeroch who keep saying everything yeferenji is nice, great.....
  Yeferenji gilgel yemesele, Yeferji enqulal, Yeferenji lam. ...ere-minu kitu......

  ReplyDelete
 18. እኛ ግን ለራሳችን እንዲህ እንበል ‹የጠቅል አሽከር አይደለሁም››፡፡ እነዚህንም ያለ መረጃና፣ ያለ ማስረጃ፣ ያለ ዳታና ያለ ይሉኝታ እየጠቀለሉ የሚናገሩትን ‹‹የጠቅል አሽከር›› እንበላቸው፡፡ እንዴው ቢታረሙ፡፡

  ዳኒ ምን አባቴ ልበል . . .የክፍለ ዘመኑ በጎ አሳቢ ብየ ሸልሜሃለሁ !!!

  ReplyDelete
 19. Ye-Tekili Ashiker Woyanew Alemnew Mekonen letenagerew milash mesitetih neew aydel politly.
  betam wodenewal....... yidegem....yidegem!

  ReplyDelete
 20. ወንድም ዳንኤል፡ ዘመኑን ያየህበትን መንገድ እጅግ አደንቃለሁ፡፡ እንደነዚህ ያሉ ወገኖች መሪዎች አይንና ጆሮአቸው የነሱን እንከን አልባነት እንጂ ህፀፃቸውን እንዳያዩ እና እንዳይሰሙ በማድረግ የዚችን ሀገር ችግር መደምደሚያ አልባ ለማድረግ ሲጣጣሩ ይታያሉ፡፡
  እኔ ትንሽ ቅር ያለኝ በጃንሆይ ጊዜ የጠቅል አሽከርነታቸውን ተቀብለው ነገር ግን ለዚህች አገር ዘመን ተሸጋሪ ውለታ የዋሉትንም አብረው ተፈርጀው የጠቅል አሽከሮች በሙሉ አሁን እንደምናያቸው ጽንፈኞች መቆጠራቸው ነው፡፡
  ወንድም ዳንኤል፡ ስለዚህ በእኔ አመለካከት የጠቅል አሽከር የሚለው ሀረግ ለአቀረብከው ድንቅ ምልከታ እንደ ርዕስ መጠቀሙ ምናልባት የነዚያን ባለውለታዎች የላቀ አስተዋጽኦ ጥላሸት እንዳይቀባ እፈራለሁ፡፡ እነዚህ ባለውለታዎች ሲፎክሩ የጠቅል አሽከር ቢሉም ጣሊያንን መውጫ መግቢያ አሳጥተው ከአገር ያባረሩ ናቸው፡፡
  በተረፈ ምልከታህ ድንቅ ነው፡፡ በነዚህ እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ የምታቀርባችውን ጽሁፎች አነባለሁ፡፡ እውነት ለመናገር በነዚህ ጽሁፎች ብዙ ትምህርት አግኝቻለሁ፡፡ የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛልን፡ አሜን!

  ReplyDelete
 21. Gerum new D/n Dani.. Egziabher Yestelen!!!

  ReplyDelete
 22. እኔም አንዷ የጠቅል አሽከር ነኝ ለምን ይዋሻል። ከዛሬ ጀምሮ ግን አልጠቀልልም ዲያቆን ዳንኤል ሰላም ጤና የጅም የ አገልግሎት ዘመን አምላክ ያድልህ

  ReplyDelete
 23. ዳኒ ሰላም ጤና ይስጥልኝ ሰላም ላንተና ለመላው ኢትዪጰያዊ ይሁንና ሀሳብህ መልካም ነው ።ነገር ግን አድ ሀሳብ አለኝ ወቅታዊ የሆነ ነገር አለ በዚህ ጊዜ ሀሳብ ሊሰጠበትና ልንወያይበት የሚገባ:ነገር ግን ስለምን የጠቅል አሽከር እናወራለን።በአሁን ወቅት ስለአማራው ወይንም ሰ ለኢትዬጵያዊ ምን እየተባለ ነው እየሰማን ያለን ወይስ ማንነታችንም እነሱ እዳሉት ሆኗል ማለት ነው?ለምንድነው በጃችን ያለውን ትተን አባቶቻችን ስላለፉበት ጊዜ ሁሌ የምናወራ።አነሱ እኮ ምንም ቢሆን የጠቅል አሽከርም ብለው ቢፎክሩ አምሮባቸው ነው ተቀብለውት ነው።እኛስ ዛሬ የማን ብለን እንፎክር "ከባዶ ጭቅላት ይሻላል ባዶ እግር"!!!!!ብለን እንፎክር?ከዚህ በሗላ ተፈርቶ አባብሎ መኖር አይበቃም በግልፀ የተባለውን እንኳን ማውራት ያስፈራል እዴ ።አረ እስከመቼ???????በል ለማንኛውም ባንተምአልፈርድም ሀሳብንበነፃ መግለፀ በማይቻልባት የሲኦል ምሳሌ በሆነችው ሀገሬ ነውና ያለኸው ምን እላለሁ ቸር ወሬ ያሰማን ።ከበላይ ነኝ።

  ReplyDelete