Sunday, February 2, 2014

እማሆይ ባቄላ


አንዳንዱን ሰው ለምስክርነት ይፈጥረዋል፡: ደግ ሰው ጠፋ እንዳይባል፡: እርሱን የለህም እንዳንለው፣ ዓለምም ‹ጨልጦ ገርኝቶ› እንዳይጠፋ፡፡ እንዲህ ያለውም ሰው እንደ ሄሊኮሜት በዘመናት አንድ ጊዜ ብቻ ይገለጣል መሰል፡፡ መገለጡንም ብዙዎች ሳያውቁት ያልፍባቸዋል፡፡ ያወቁ ደግሞ ይጠቀማሉ፡፡

በዚህ በኛ ዘመን እንዲህ ያሉ ሰዎች ተገልጠው ነበረ ቢባል ለአብነት ከምንጠራቸው አንዷ እማሆይ ባቄላ ናቸው፡፡ ስማቸውን ማንም አያውቀውም፡፡ ግብራቸው ግን ሌላ ስም አምጥቶላቸዋል፡፡‹ እስመ ስሙ ይምርሖ ኀበ ግብሩ› ነበር የሚለው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ‹እስመ ግብሩ ይመርሖ ኀበ ስሙ› እንዲል የሚያደርጉት ሰዎችም አሉ፡፡ እንደ እማሆይ ባቄላ፡፡ 

ትግራይ ከሰላ አካባቢ መወለዳቸው የሚነገርላቸው እማሆይ ባቄላ ደሴ ከተማ የገቡት በ1963 ዓም አካባቢ መሆኑ ይነገራል፡፡ ከዚህ ያለፈ ታሪካቸውን የሚያውቅ የለም፡፡ ለእርሳቸው መልካም ሥራ እንጂ ትውልድና ዘር ትርጉም አልነበራቸውምና፡፡ የእናታቸው ስም አመተ እግዚእ፣ የአባታቸውም ስም ገብረ ትንሣኤ መሆኑ የታወቀው እንኳን በየወሩ በ29 ቀን የወላጆቻቸውን ስም በደሴ መድኃኔዓለም በጸሎት እንዲታሰብ ያደርጉ ስለነበር፣ ይህንንም ደጉ ካህን መጋ ብሉይ አባ ዮሴፍ ስላስታወሱት ነው፡፡

ደግሞም መሥራት እንጂ ማውራት አይችሉበትም፡፡ በአንድ ወቅት የቤተ ክህነቱ ነቅዐ ጥበብ መጽሔት ጋዜጠኛ ታሪካቸውን እንዲያወጉት ቢጠይቃቸው ‹‹እኔ ለአርአያነት የሚያበቃ ሥራ የለኝም፤ ለምነሽ እንጂ ተናግረሽ ኑሪ አልተባልኩም›› ነበር ያሉት፡፡

አባ ዮሴፍ እንደሚተርኩት እማሆይ በልጅነታቸው ለአንድ የአካባቢው ባላባት ይዳራሉ፡፡ እርሳቸው ግን ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ፈጣሪን አክባሪና የእምነት ሰው ነበሩና ‹‹እኔ ወደምመራሽ ቦታ ሂጂ› የሚል ቃል ከሰማይ ይመጣላቸዋል፡፡ እማሆይም ቃሉን አክብረው እንደ ገብረ ክርስቶስ ከትውልድ ቀያቸው ይጠፋሉ፡፡ ከዚያም መቀሌ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ገብተው አገልግሎታቸውን ይጀምራሉ፡፡
 
እን ስምዖን ጫማ ሰፊው ያደርጉት እንደነበረው ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን፣ አስታማሚ ያጡትን፣ በችግር የተቆራመዱትን፣ በመንገድ የደከሙትን ለምኖ መርዳት ሆነ ሥራቸው፡፡ እነርሱን ለመርዳት ሲሉ ዞረው ይለምናሉ፤ የለመኑትንም ለራሳቸው አንዳች ሳያስቀሩ እየዞሩ በየድኾቹ ቤት ያከፋፍላሉ፡፡ አረጋውያንን ይጦራሉ፤ ሕሙማንንም ያስታምማሉ፡፡ ይህን እያገለገሉ ነበር መቀሌ ላይ የተቀመጡት፡፡ 
 
በዚህ አገልግሎት ላይ እያሉ ፊታቸውን ወደ ግሼን ማርያም እንዲያዞሩ መንፈስ አነሣሣቸው፡፡ ተነሥተውም ግሼንን ሊሳለሙ መጡ፡፡ ከዚያም በሰኔ 1963 ዓም ወደ ደሴ ገብተው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀመጡ፡፡ ከደሴ መድኃኔዓለም የለያቸው የሥጋ ሞት ብቻ ነው፡፡ 
 
እማሆይ ደሴ ላይ የመቀሌውን በጎ ምግባር ቀጠሉበት፡፡ ችግረኞችን ይሰበስባሉ፣ መታከሚያ ያጡትን ለምነው ያሳክማሉ፤ በየቤታቸው ወድቀው ሰው አላያቸው ያሉትን ለምነው ያለብሳሉ፣ ያጎርሳሉ፤ የወደቁትን አንሥተው ለክብር ያበቃሉ፤ መንገደኞችን አሳድረው ይሸኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ አልፈው ደግሞ ባቄላ ቀቅለው ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም በር ላይ ቆመው ‹ስለ መድኃኔዓለም‹ እያሉ ያድላሉ፡፡ ለዚህም ነበር ሕዝቡ ‹እማሆይ ባቄላ› ያላቸው፡፡በ1977 ዓም በተከሰተው ረሃብ ጊዜ  ባቄላ ለምነው በመቀቀል፣ እህል ለምነው ጠላ በመጥመቅ  አያሌ ረሃብተኞችን ታድገዋቸዋል፡፡ ያን ጊዜ እንኳን ረሃብተኞቹ ምግብ ያልጠፋባቸው ሳይቀሩ የእርሳቸውን በረከት እንካፈል እያሉ ተሰልፈው ንፍሮ ይቀበሉ ነበር ይባላል፡፡ እማሆይ እንዲህ ሀገር ያወቀውን ችግር ቀርቶ ሰው ያልደረሰለትንም ቀድመው የሚደርሱ ነበሩ፡፡ በአንድ ወቅት አንድ ሰው ከግሼን ሲመለስ ከመኪና ወድቆ አደጋ ይደርስበትና ሰውነቱ ይበላሻል፤ እዳሪውንም መቆጣጠር ያቅተዋል፡፡ ሰው ሁሉም ይጸየፈዋል፡፡ እማሆይ ግን አልተጸየፉትም፡፡ ቤታቸው ወስደው፣ ሰውነቱን እያጠቡ፣ አልጋ ላይ ሲጸዳዳ እየጠረጉ፣ ልብሱን በየቀኑ እያጠቡ፣ ሰው ለምነው አብልተው፣ አምላክን ለምነው አዳኑት፡፡ ሰውየውም ድኖ መርቋቸው ሄደ ይባላል፡፡ 
 
በሌላ ጊዘ ደግሞ አንድ ሰው ገደል ወድቆ ሰውነቱ ከጥቅም ውጭ ይሆናል፡፤ ሆስፒታል ተኝቶ ታክሞም መዳን ይሳነዋል፡፡ የሕክምናው ወጭም ከባድ ይሆንበታል፡፡ ከሐኪም ቤት ሲወጣም መውደቂያ ያጣል፡፡ እማሆይ ይሄንን ሰው ቤታቸው ወሰዱት፡፡ እናት ለልጇ፣ ባልም ለሚስቱ ከሚያደርገው በላይ አድርገው አስታመሙት፡፡ ሰውዬው ከዐሥር ዓመት በላይ እማሆይ ቤት ተኛ፡፡ እርሳቸውም ሳይጸየፉና ሳይመረሩ አስታመሙት፡፡ በመጨረሻ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ በወግ በመዓርግ እንዲቀበር አደረጉት፡፡
 
አባ ዮሴፍ እማሆይ ባቄላን በተመለከተ በዓይናቸው ያዩት በጆሯቸው የሰሙት ብዙ ታሪክ አላቸው፡፡ እማሆይ ለአገልግሎት ሌትና ቀንን አይመርጡም፡፡ ሌሊት ጅቦች እንደ ሠራዊት አጅበዋቸው ሲንቀሳቀሱ አውቃለሁ ይላሉ፡፡ ይህንን ጸጋቸውን የተረዳው የደሴ ሕዝብም እጁን ያለ ማመንታት ይዘረጋላቸዋል፡፡ ‹ስለ መድኅኑ›› እያሉት እንኳን ክርስቲያኑ ሌላው አያልፋቸውም፡፡ 
 
እርሳቸው አስቦ የማይሰጠውን ደካማ ለምነው ተቀብለው ለማጽደቅ የመጡ ናቸው፡፡ ግዴታቸውን ያልተወጡትን ግዴታቸውን ይወጡ ዘንድ ለማሳሰብ የተሰጡ ናቸው፡፡ ለምነው ድኻ ይረዳሉ፣ ሕሙማንን ያስታምማሉ፣ ለምነው ባቄላ ቀቅለው ያበላሉ፤ ለምነው የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ያሠራሉ፡፡ ለምነው የግሼን፣ የላሊበላና የአኩስም መንገደኛን ያስተናግዳሉ፣ ይሸኛሉ፡፡ ደላንታ ውስጥ ለተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት ከ60ሺ ብር በላይ ለምነው ሰጥተዋል፡፡ ደሴ የሚገኘውን ደብረ ቤቴል ቅድስት ሥላሴን ቤተ ክርስቲያን ከቤተልሔሙ እስከ ቤተ ክርስቲያኑ የግቢ በር ያለውን ንጣፍ አስነጥፈዋል፡፡
 
እማሆይ ለምነው መርዳት፣ ለምነው ማልበስ፣ ለምነውም ማስታመም ጸጋቸው ነበርና ይህንን አገልግሎት ያለመታከትና ያለማጉረምረም ይፈጽሙት ነበር፡፡ 
 
አንድ ቀን ግን እንዲህ ሆነ፡፡
አንድ የሚያውቁት ሰው መኪና እያሽከረከረ ያዩታል፡፡ ይህ ሰው ቢሰጣቸው የሚረዷቸውን ድኾች፣ የሚያስታምሟቸውን በሽተኞች፣ የሚያለብሷቸውን ዕሩቃን፣ የሚመግቧቸውን ርኁባን እያስታወሱ ወደ ሰውዬው በፍጥነት ገሠገሡ፡፡ እርሱ ግን አላያቸውም፡፡ መኪናውን ዘወር ሲያደርግ እማሆይን ገጫቸው፡፡ እማሆይ መሬት ላይ ተዘረሩ፡፡ በየትኛው ዐቅም ያንን ግጭት ይቋቋሙታል፡፡ ሕዝብ ደነገጠ፡፡ ማንም ልቡ አልቀረለትም፡፡ ወደ ልቡ የተመለሰው ይዟቸው ወደ ሆስፒታል ሮጠ፡፡ 


እኒያ ለማገልገል ሮጠው የማይሰለቹት እናት አልጋ ላይ ዋሉ፡፡ ‹‹የእኔ ጸሎት ጥሬና ብስል ነው›› ቢሉም ተኝተውም ለሀገራቸውና ለወገናቸው መጸለይን ለአፍታ እንኳን አላቆሙም ነበር፡፡ በዚህ ሕይወትም እያሉ ታኅሣሥ 21 ለ22 አጥቢያ በ2000 ዓም ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ ሲገንዟቸው ሰውነታቸው በመስቀል የተከበበ እንደነበር፤ በደረታቸው ላይም ትልቅ መስቀል ማግኘታቸውን አባ ዮሴፍ ይናገራሉ፡፡ 
 
ደሴም በዘመናችን ብቅ ካሉት ቅዱሳን አንዷን በልቅሶና በጸሎት ሸኘች፡፡ በየአካባቢያችን ግን ለዓይነት አይጠፉም፡፡ እርሱ ሀገርን ያለ አንድ ጻድቅ አይተዋትምና፡፡ 
     
ምንጭ
የዓይን ምስክሮችና መዘክር(ለደሴ መድኃኔዓለም 100ኛ ዓመት የተዘጋጀ) መጽሔት

57 comments:

 1. awo inem yemawkewu tarik alegn yemuhayi bakela, andit set kearas lijua gar huna yemeshebet ingida indehonechi indiyasadiruat tileminachewuna on next day lijun tila tefachi, imuhay lijun azilewu indasadegut awukalehu....bizu bizu neger neber ahun min waga alewu. yenatachinin nefis yimarlin.

  ReplyDelete
 2. ኦግዚአብሔር ይባርክሕ ፤ ለኛም ከኔሕ ደገኛ እናት በረከታቸው ይድረሰን። ለእግዚአብሔር ለማገልገል መመረጥ ምን ያሕል መታደል ነው???

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኦግዚአብሔር ይባርክሕ ፤ ለኛም ከኔሕ ደገኛ እናት በረከታቸው ይድረሰን። ለእግዚአብሔር ለማገልገል መመረጥ ምን ያሕል መታደል ነው???

   Delete
 3. ሰው ለምነው አብልተው፣ አምላክን ለምነው አዳኑት፡፡ thanks Dani, best as usual ... bereketachew yedereben!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው ለምነው አብልተው፣ አምላክን ለምነው አዳኑት፡፡ thanks Dani, best as usual ... bereketachew yedereben!!

   Delete
  2. ሰው ለምነው አብልተው፣ አምላክን ለምነው አዳኑት

   Delete
 4. nefesachewn yimar!

  ReplyDelete
 5. Dani egziabher yabertah yetsadikanu amlak ytebkih!!!
  " እርሱ ሀገርን ያለ አንድ ጻድቅ አይተዋትምና!!! "

  ReplyDelete
 6. በጣም አስገራሚና አስደናቂ ነገር ነው ቅዱሣን ዛሬም ቢሆን አሉ ግን የእግዚአብሔ ፀጋ ተሰውሮብናልና ጻድቅና ሐጥኡን ሰው መለየት አቃተን ፡፡ እግዚአብሔር እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች እናውቅ እንረዳ ዘንድ መልካም መንፈሱን ይግለጽልን

  ReplyDelete
 7. ወንድም ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ ቃለ ሕይወትም ያሰማህ፡፡ ገድላቸው ተጽፎ ታሪካቸው ተነግሮ ስማችሁን የጠራ ዝክራችሁን የዘከረ ዘለዓለም ይኖራል በመንግስተ ሰማይ እንደተከበረ የሚባልላቸው እንዳሉ ሁሉ አንተ የምታነሳሳቸው አባቶች እናቶች ማንም አላወቃቸውም እንጂ ፃድቃኖች ናቸው፡፡ ደሴ እጅግ የሐይማኖት ሀገር ናት በ1982 ዓ.ም. መጨረሻ ለትምህርት ደሴ ሄጄ እስከ 1985 ዓ.ም. መጨረሻ ቆይቼ ነበር በዚያን ጊዜ በከተማው ያሉት 8 አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ ሁሉንም ጧት በህዝበ ክርስቲያን ተሞልተው ነበር የሚገኙት፡፡ በሀገረ ስብከቱ የነበሩት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ የሚባሉ ነበሩና ሕዝቡ እምነታችንን አላስጠበቁልንም አባታዊ ምክራቸውንም አላገኘንም ብሎ ከሀገረ ስብከታቸው አባሯቸው ነበርና ለብዙ ዓመታት ያለ ሊቀ ጳጳስ ነበር ሀገረ ስብከቱ የነበረው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በ1984 ዓ.ም. አንድ ቀን ደጉ አባታችን አቡነ ሰላማና ታላቁ ሊቅ አቡነ ቶማስ ደሴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እሁድ ቀን ቅዱስ ሚካኤል ሆኖ በገጠመበት ቀን ተገኝተው የሕዝቡን ሐይማኖት ወዳድነትና ጽናት አይተው እንዲህ ያለ ጠባቂ ያለ ሕዝብ ጽናቱ ምንድን ነው ከወዴትስ መጣ በማለት በመገረም አባት ያስፈልገዋል በማለት ታላቁን አባት አቡነ አትናቴዎስን በቅዱስ ሲኖዶሱ መልካም ፈቃድ እንዲመጡ አደረጉና ዛሬ የመልካም አባት ባለቤቶች እንዲሆኑ ተደረገ፡፡ ሌላ አገር ናፋቂነት የዘመናችን በሽታ ነውና ከ1985 ዓ.ም. በኋላ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገራት መኖር ጀመርኩኝ ግን እስከ አሁን የዚያን ሀገር የሐይማኖት ፍቅር ተመልሸ ማግኘት አልቻልኩም፡፡ በዚህን ዘመን ነው ታዲያ ደጋጐቹን የቤተ ክርስቲያኗን አባትና እናቶች ያየኋቸው 1ኛ/ አባ መፍቀሬ ሰብ 2ኛ/ አባ ሕፃን የሚባሉ ሰባኪ ወንጌል በባዶ እግራቸው እየሄዱ የሚያስተምሩ ነበሩ 3ኛ/ አባ ዮሴፍ ጓንጉል 4ኛ/ እማሆይ ባቄላ 5ኛ/ መሪጌታ ፈንታው 6ኛ/ መሪጌታ ይትባረክ ፀጋው ሌሎችም አሉ ጊዜው ረዘመና ማስታወስ አልቻልኩም እንጂ ስንት ደጋጐችና የተባረኩ ወገኖች ነበሩ፡፡ እማሆይ ባቄላ ታዲያ መልካም ለዛ ባለው ቃላቸው እየዞሩ የሚለምኑት ልመና ልመና ሳይሆን ቡራኬ ነበር የሚመስለው ዛሬ መሞታቸውም ስሰማ በእውነት በጣም አዝኛለሁ፡፡ ከቅዳሴ ስንወጣ በኒኬል ሳፋ የሚቀርብልን ባቄላ ሌላ ሀገር አይቼውም አላቅም፡፡ እየለመኑ ከሚያሰሯቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንድ ጊዜ በቅዱስ ቶማስ ዘሕንደኬ ዓመታዊ በዓለ ንግስ ግንቦት 26 ታላቁ መምህር አካለ ወልድ ባሰሩት ቁባፈታ ቶማስ ቤተ ክርስቲያን ማህሌት ለመቆም ሄደን ለቤተ ክርስቲያኗ ማሰሪያ ገንዘብ አሰባስበው አምጥተው እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ እናቶቻቸው የጣሏቸውን ሕፃናት አዝለው እያበሉ እያጠጡ እንደሚያሳድጉም አውቃለሁ፡፡ በጣም የማልረሳው ደግሞ ድመታቸው የቅዳሴ ሰዓት እስከሚያልቅ ታስሮ ምግብ ሳይበላ እንደሚጾምም ሲነገር ሰምቻለሁና ታላቅ እናታችን ነበሩ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን በነሱም ቃል ኪዳን እኛን ይማረን፡፡ ሌላው አባ ዮሴፍ ጓንጉልም ቀላም አባት አይደሉም መናኛ መስለው ዝቅ ብለው ቢኖሩም ትልቅ መንፈሳዊ ሕይወት ያላቸው ሰው ናቸው፡፡ እኔ ከሳቸው ሰዓታት ተምሬአለሁና በደንብ እውቅና ነበረኝና አንድ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጮ ገዳም አካባቢ እኖር ነበረና በ1989 ዓ.ም. ይመስለኛል ለህዳር ቁስቋም ንግስ አባ ጽጌ ድንግል እና አባ ገብረ እንድርያስ ገዳም ወግዲ የሚባል አገር መጥተው ተገናኝተን 15 ቀን ያህል እኔ ቤት ነበሩና ሌሊት የነበረው በረከት ልዩ ነበር ዛሬ ሳስታውሰው አለቀስኩ፡፡ እግዚአብሔር የነዚህን አባቶች በረከት ያድለን የአባ መፍቀሬን ባለፈው በጥሩ ሁኔታ ተገልጿል፡፡ የሌሎቹንም እንዲሁ ቀጥልበት እግዚአብሔር ይስጥህ በእድሜ በፀጋ ይጠብቅህ ወንድሜ፡፡
  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተም ተባረክ ወንድሜ
   አብነት ከሆሳዕና

   Delete
  2. ዲ/ ዘላለም ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ህዝቡ አባሯቸው ሳይሆን ከቦታው የተነሱት ራሱን የቻለ ሰፊ ታሪክ አለው ።

   Delete
 8. የእኚህ ቅድስት እናት ኑሮ ህይወቴን ተቸው፡፡ሰው ለምኖ ያበላል፡፡እግዚአብሔር ደግ ሰው አያሳጣን ፡፡የኛን ህይወት ይለውጠው፡፡

  ReplyDelete
 9. ደሴ መድሃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ታላቁ ባለ ታሪክ ቤተ ክርስቲያን በንጉስ ሚካኤል የተሰራው እግዚአብሔር ሲጠራ ጠራ ነው፡፡ ከእስልምና የተመለሱት አባት እግዚአብሔር ቢፈቅድልኝ የቤተሰቦቼን አጽም አውጥቼ ምነው ባስጠመቅኳቸው ብለዋል ይባላል፡፡ በዓላት ተከብረው (ሳይሰራባቸው) በአዘቦት ቀን ብቻ ተሰርቶ በ 3 ወር ከ14 ቀን የተጠናቀቀ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሥራው በተጠናቀቀ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ እየተወዛወዘና እያዘዘመመ ስላስቸገረ በአንዲት ምስማር አንዱን የመሰረት ድንጋይ ሲመቱት ፀንቶ እንደቆመ ይነገራል፡፡ ምስማሯም አሁንም አለች፡፡ ግሸን ያለው የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል ሲመጣም አብሮ የመጣው የኢየሩሳሌም አፈር በከፊል እንደአረፈበትና መስቀሉም በዚሁ ቤተ ክርስቲያን በኩል አልፎ እንደሄደ ይነገራል፡፡ በአንድ ወቅትም መሬቴ ተሰንጥቆ ልክ እንደ ልብስ የሰፉት አባቶች እንዳሉም የሚነገርለት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በግቢው ውስጥ ሲገባ ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል ያለበትና ድባብ የሚሆንበት ቦታ ነው ብዙ የተሰወሩ አባቶችና እናቶችም እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ባለ ራዕይ ቦታም ነው፡፡
  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዲ/ ዘላለም ወሎዬ ነህ እንዴ???????

   Delete
 10. እርሱ ሀገርን ያለ አንድ ጻድቅ አይተዋትምና፡

  ReplyDelete
 11. AS GOD SEID DON`T LEAVE HOMELANS WITH OUT HOLY PERSSONS 10Q DANIE

  ReplyDelete
 12. ውድ ዳነኤል ባለፈው የማውቃቸውን አባ መፍቀሬን አሁን ደግሞ በጣም የምውዳቸውን ገን ማረፋቸውን ያልሰማሁትን እማሆይ ባቄላን ታሪክ አስነብበህ መሞታቸውን ስትነግረኝ ለቤ በጣም ነው ያዘነው....
  እማሖይን የመሰለ እናት ለካስ በአካል አጥተናል፧
  ከባቄላቸው የቀመስኩት ልጃቸው ከሀገረ አሜሪካ

  ReplyDelete
 13. እናታችን እማሆይ ባቄላ በረከታቸው ይድረሰን ነው የሚባለው። ለ 6 ዓመታት እሁድ እሁድ ከቅዳሴ በኃላ የሚያድሉትን ባቄላ ተሰልፌ በልቻለሁ።

  ReplyDelete
 14. Dear Daniel;
  Do you ever think that we can be good, kind, generous, loving...... without pointing to authority over the sky? The story of the woman is awe inspiring. Did God make this woman what she is, or is she what she is as a human being irrespective of God? To say God made her what she is, takes away from the kindness she earned on her own human effort and struggle. It gives the false sensation that it is only through authority from GOD that one can become as generous and kind as she is. She is the kind person that she is irrespective of any supernatural addition to her effort. This assumption inspires lots of people to believe in the goodness of oneself as a human being. And we can choose to muster that power without any supernatural authority. And we can be good for goodness sake without expecting reward from above or in the hope of avoiding "burning fire" in the afterlife.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please understand how spirituality and day to day life are integrated. When Emhoy Bakel decided to serve God, she has also abandoned by good works. God was the light for her good work.

   Delete
  2. Dear Anonymous, read the bible(John), you will come across a word that says 'you can do nothing without me'.

   Delete
  3. Emahoy did good, not to be good in the secular world, but Christianity, is to follow the Christ by living 4 others

   Delete
 15. መግለጨጫ ቃላት ያጥረኛል አኔስ

  ReplyDelete
 16. behulum bota degagi yeEgiziabihar agelgayi yisiteni kale hiyiwet yasemaln.

  ReplyDelete
 17. WID WENDIMACHN DANIEL! TSEGANA BEREKET FIQIRNA SELAM KANTE GAR YIHUN  ReplyDelete
 18. Thank you brother Danial .
  I used to work close to government and I received several discrimination from Tigray people so I have hated them for many years. I thought all Tigray people are rude, nonbeliever and I was very happy when Meles Zenawi and Abune Paulos died. If someone came from Tigray or speak Tighrigna, I feel that person is my enemy. When I read this about Emahoy Bakala, I realized that I have been wrong to take all people in one direction. I know I will never be friend with Tigray people but I learned something. God bless Ethiopia except Tigray.

  ReplyDelete
  Replies
  1. My brother Anonymous February 4, 2014 11:42 pm,as you have already said it, you are so rude.This hatred to a specific ethnic group is evil. Please get help, let your priest pray for you or take you to the Tsebel.

   Delete
  2. Hello my brother/sister the Anonymous person February 5, 2014 at 9:56am. The first Anonymous person told us how discriminated by Tigray people. They are the problem to bring him/her in this situation so you have to blame them instead of him/her. Shame on you, you have to get help from priest. Please don’t force people to lie, he/she told us the fact that we struggle in our day to day life. God bless you the first Anonymous person.

   Delete
  3. Wow the 2nd Anonymous person why you take it personal. It is fact; they destroy our church, culture and right. In addition that, you don’t know what kind saturation happened on the first Anonymous person. I have one question, have you been in the court? If not you have to go there to see what Tigray people do on our father, mother, sister and brother then you will give feedback for the first Anonymous person. All Tigray people are not human being they are devil.

   Delete
  4. Thank you Danial for posting this kind comment, we need this kind freedom for our country. It is very educational site without fear. I love you so much both Anonymous person for practicing the real democracy. God bless Ethiopia including Tigray but not Weyana.

   Delete
  5. እኔ እግዚአብሔር በሚያውቀው ትውልደ ትግራይ አይደለሁም፡፡ ከዚህ በላይ የተሰጠውን አስተያየት ግን ብዙ አልስማማበትም የሰው ልጅ ደግነቱ፣ እውቀቱ ፣ሐይማኖቱ፣ ሥራው ፣ ጀግንነቱ ፣ ታማኝነቱ ፣ የዋህነቱ ወዘተ... በአገሩ በትውልዱ አይወሰንም እግዚአብሔር የመረጣቸው ብዙ መልካም አርአያዎች በየቦታው አሉና በዚህ በሚጥም ማዕድ ላይ የፖለቲካ ውዝግብ ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ የተገለፀውን ችግር የሚሰሩ ቢኖሩ እንኳን እኛ በደግነታችን በልጠን ማሳየት ነው የሚገባው፡፡ ካልሆነማ እኛ ከእነሱ በምን እንሻላለን፡፡ ሌላው ቀድሞ እንደምንሰማውም እንደምናውቀውም የትግራይ አባቶች እናቶች እኮ ጽኑ ሐይማኖተኞች ነበሩ፡፡ የእውነት ምንኩስና፣ቅስና፣ዲቁና፣ክርስትና ነበራቸው አገር ወዳድነታቸውም እንዲሁ ሰውነታቸው እርግፍ እስከሚል ነበር ለእግዚአብሔር የሚገዙት እኔ አባ ዘአማኑኤል የሚባሉ መናኝ አባት ከሰሜን ትግራይ አካባቢ መጥተው በወሎ ክፍለ ሀገር ባቲ ወረድ ብሎ ለጊተሚራ በሚባል ፀሐዩ እንደ እሳት በሚያቃጥልበት ቦታ በቃጫ ተክል ውስጥ ምንም ፀሐይ በማያስጠልል ቦታ መንነው ይኖሩ የነበሩ አባት አውቃለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወደ ሚሌ፣ባቲ፣ኮምቦልቻና ደሴ የእግዚአብሔርን መልዕክት ለማድረስ ሲመጡ የነበራቸው ፍቅርና ለዛ ልክ አልነበረው ሌሎችም እንዲሁ አሉና እባካችሁ አንድ ሁነን እናስብ እንዋደድ መለያየት በመጀመሪያ የሰይጣን ሥራ ነው፡፡ ከየትኛውም ቦታ ክፉ ሰው አለ፡፡ እግዚአብሔርንም ሰውንም የማይፈራ የሚያሳዝን፡፡ እኔ አዲስ አበባ የሚባለው አገር እስክገባ ድረስ በየክፍለ ሀገሩ ስዞር አንድ ቀን የማንኛውንም ብሔር ወግኜ አላውቅም አዲስ አበባ ለሥራም ይሁን ለሌላ ተግባር ስቆይ ግን እንደ በሽታ የዘረኝነት ችግር ይፈታተነኝ ነበር፡፡ ነገሩን አናጉላው ብዙ ታሪክ የተነገረላቸው አባቶች እናቶች ዘራቸው ትውልዳቸው ኢትዮጲያ እንጂ በጥቃቅን ጎሳ የተከፋፈሉ አይደሉምና እንጠንቀቅ፡፡ ጌታም በወንጌሉ የሚከፋፈል መንግስትም፣ቤትም ሌላም እራሱን ችሎ ፀንቶ አይኖርም ብሏልና አንድ እንሁን የሰይጣንን ምክር አንስማ፡፡

   Delete
 19. እማሆይ ባቄላ በእውነት በእያንዳንዳችን ልቦና ውስጥ ያሉ እናት ናቸው፡፡ ይሄን ደሴ መድኀኔዓለም ከቅዳሴ በኋላ የሚሰጡትን ባቄላ የበላ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ ዛሬ እንደ አዲስ የእሳቸውን ሞት ስሰማ አለቀሰኩ፡፡ የአለማመናቸው ቃና እንዴት ያምር እንደነበር እኮ ‹ስለ መድኅኑ ሲሉ› ኡፍ .. እሟሆይ ባቄላ ደህና ኖት ሲሏቸው እግዚአብሔር ይመስገን ሲሉ ከአንደበታቸወው የሚወጣው ሞገስ ኦሀህ የማይረሱ እናት ምንጊዜም በልቤ ውስጥ ይኖራሉ ፡፡ እግዚአብሔር ይቀበሎት እማሆይ ፡፡ ወንድም ዳንኤልም ተባረክልን ትዝታችንን ቀሰቀስከው

  ReplyDelete
 20. ከደቀመዝሙርFebruary 5, 2014 at 12:07 PM

  ደስታየ በዛ!!!በጣም ደስ አለኝ!!ደስታየ ስጋየን አልፎ ወደነፍሴ ሲፈስ ይታወቀኛል!!!
  ዳኒ፡ ስለደካማ አባቶቻችን ብቻ እየተወራ ስሰማ በትካዜና በሀዘን ተውጨ እኖር ነበር!!አሁን ግን አንተ መስመሩን ከፈትከው!!ጥሩ አያቶች ብቻ ሳይሆን ደጋግ እናትና አባቶችም እንዳሉ በአባ መፍቀሬሰብ ጀምረህ በእማሆይ ባቄላ ደግመኸናልና ሰልስልን…..ጨምር ጨማምር…. “እስኪ ድግሙ ድግሙ….እስኪ ድግሙ…”. እንዳሉት በፍቅር እስከ መቃብር ያሉት የደብረወርቅ የቅኔ ደቀመዛሙርት!!!እባከህ በየአጸዱ ስር ሆነው ለተርዕዮ ሳይሆን ለበረከት የሚተጉ በየቦታው ያሉ የደጋግ እናቶችንና አባቶችን ያልተጻፈ ገድል ንገረን!!!ያንጸናል፣እንጽናናለን፣አብነት አርአያ ይሆኑናል፣ክርስትናችን እምነት በስራ የሚገለጽባት እንጅ የተናገሩትን የማይኖሩ ሰዎች ስብስብ ስላለመሆኑዋ ህያው ምስክር ይሆኑናል!!!እና አሁንም ዳኒ ጻፍ!!!አንተም እኛም እንጠቀም!!
  ለዝ መጽሐፍ ዘአንበቦ ወዘተርጎሞ በልሳን ሐዲስ፣
  ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ-መንፈስ፣
  በጸሎተ እሙ ማርያም አራቂተ ኩሉ እምባእስ፣
  ህቡረ ይምሀረነ ኢየሱስ ክስቶስ!!!
  እንዲል የስንክሳር አርኬ. አንተም በደግነታቸው አርአያ የሆኑ አበውን እና እመውን ህይወት በብእርህ ልሳን ስትተርክልን እኛም በአይነ-መንፈስ ሆነን ደግነታቸውን ለማየት ስንከተልህ የሚገኘው መንፈሳዊ በረከትና አርያነት ብዙ ዋጋ ያለው ነው!!!ይህም ከምግባር ያዳጡ አባቶችን ገበና በማስጣት ከመንፈሰ-ቀሊልነት በሚገኝ ያንባቢ ብዛት ስተው ጥልቀት በሌለውና በማያንጽ የስህተት መንቀስ ቅኝት ለተቃኙት ብሎጎቻችን በጎ ምሳሌ ነው!!!ይበል!!አጽናኑን፣እረኛውን ከመንጋው ለማገናኘት እንዳንተ ያሉ ባለ ሁለት ስለት ጸሀፍት-በመንፈሳዊውም በዘመናዊውም (ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ) ብዙ ማድረግ ይችላሉ!!!ስለዚህ ቀጥልበት!!! “ምእመኑ አባቶቹን እንዳይጠላ እፈራለሁ” እያሉ ትንቢት መናገር ሳይሆን አባቶች ሁሉ አንድ አይነት እንዳልሆኑና የጥቂት ከምግባረ-ሰናይ የወጡ አባቶች ድርጊት መላውን የኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ጳጳሳትና ካህናት እንደማይወክል መናገር የሁሉሙ ቀናኢ ምእመን ድርሻ መሆኑን አስገንዝብ!!ቁጥር ውስጥ በማይገባ ደሞዝ 40እና 50አመት በእቃቤትነት፣በዐቃቢትነት፣በመክፈልት ጋጋሪነት፣በደዋይነት፣በአጻዌ ሆህትነት፣በአስቀባሪነት፣የሚሰሩ ብዙ ያልተነገረላቸው አባቶች አሉን!!!ታሪካቸው እንዲህ ይነገር!!
  ዳኒ ሁሌ ታኮራኛለህና በሄድክበት ሁሉ መንገድህን ይጥረግልህ!!

  ReplyDelete
 21. DANI........ TSEGAWUN YABZALIH

  ReplyDelete
 22. Dn.Getaye Ze LalibelaFebruary 6, 2014 at 12:24 PM

  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ ሌሎችንም እየፈለግህ እንድንማርባቸው ጻፍልን፡፡
  እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የሚሠጠን ቅዱሳን አሉ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በተጋድሏቸው፣ በጸሎታቸው፣ በትሩፋታቸው፣ በምነናቸው ይታወቃሉ፡፡ ይኽ ሁሉ የእግዚአብሔር ቸርነት መገለጫ መንገዱ ነው፡፡
  ዝም ብሎ እግዚአብሔርን ብቻ ማመስገን፣ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ማድነቅ ነው፡፡ ገና እግዚአብሔር ሰው በጠፋበት ዘመን፣ ሰው በሚፈለግበት ጊዜ፣ የሰው ያለህ ተብሎ ሰው ሲጠየቅ እግዚአብሔር መልስ አለው፡፡
  የእማሖይ ባቄላም ታሪክ ይህንን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እናትና አባት ልጆቻቸውን በሥርዓት በማያሳድጉበት ዘመን፣ ወንድም እኅቱን በማይጠይቅበት ጊዜ፣ ልጆች ወላጆቻቸውን በማይጦሩበት ወቅት ችግረኞችን፣ ድሆችን፣ ደካሞችን፣ ኅመመተኞችን የሚረዱ እናቶችን ማግኘት ተዓምር ነው፡፡
  ለመነሻ ይህንን ካልኩ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ውስጥ በ1980ዎቹ አካባቢ ወቅት ቦታው በውል ከማይታወቅ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጡረታ ወተው የመጡ አንድ እናት ነበሩ፡፡ የት እንደመጡ፣ የት እንደተወለዱ፣ ትክክለኛ ስማቸው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ በምነና እያገለገሉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ እናት ነበሩ፡፡ ስማቸው እማሖይ ‹‹ሙሆዶ›› ይባላል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ እንደመጡ በትልቅ እንስራ ፍህም እሳት ሞልተው ተሸክመው ንስሐ ግቡ እያሉ ይዞሩ ነበር፡፡ ፊታቸው በሙሉ ጠባሳም ነበር፡፡
  እንደዛሬው የቱሪስት ፍሰቱ ሳጨምር፣ ደብሩም ሆቴሎች ሳይገነባ፣ ካህናቱም ለደመወዝ ሳይሆን ለንስሐ፣ ለምህረት፣ ለሠላም በሚያገለግሉበት ወቅት፣ የካህናቱ ደመወዝ 15ና 30 ብር በነበረበት ወቅት፤ መናንያኑ የቅዱስ ላሊበላን አፈር ልሰው በሚኖሩበት ጌዚ፣ ቀዳስያኑ ከቅዳሴ በኋላ አፋቸውን የሚያድፉት በቅዱስ ላሊበላ አፈር በነበረበት ወቅት፤ እማሖይ ሙሆዶ ዞረው ዱቄት እየለመኑ የሰንት ቂጣ ‹‹ፀሪቀ መበለት›› እየጋገሩ በእለተ ሰንበት ተዓምረ ማርያም ከተነበበና ትምህርት ከተሰጠ በኋላ ይበላል፡፡ ጠዓሙ፣ መዓዛው ልዩ ነው አሁንም ትዝ ሲለኝ አይኖቼ እንባ ያቅራሉ፡፡ የሰንበት ቂጣው በየ አብያተክርስቲያናቱ በወርኃዊ በዓላትም ይመጣል፡፡ ያለ ማጋነን የአስቀዳሹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ ስማቸውም በአካባቢው ይነሳል፡፡
  እማሖይ ‹‹ሙሆዶ›› በዚህ ጽሑፍ ለማካተት ያልፈልግኩት በራሳቸው ላይ የሚቀልዱት ቀልድ ነበራቸው፡፡ እማሖይ የድሀ እናት ናቸው፣ ያበላሉ ያጠጣሉ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ በጣም አነስተኛ ጡረታ ብቻ የነበራው ሲሆን ሌላውን የሚያደርጉት ለምነው ነው፡፡ ይለምናሉ ያበላሉ ያጠጣሉ ሀገራው ዘመዳቸው አዝማዳቸው እግዚአብሔር ብቻ ነበር፡፡
  በጣም የሚገርመው እማሖይ የሚለብሱት ከበግ ጸጉር የተሠራ ማቅ የሚባከል ልምስ ሲሆን ወገባቸውን በሠንሠለት አሥረው ነበር፡፡ በአጠቃላይ የተለዩ መንፈሳው እናት ነበሩ፡፡ በኋላ ከቅዱስ ላሊበላ 8 ኪሎ ሚትር ርቀት ከሚገኘው ቅዱስ ነአኩቶለኣብ ቤተክርስቲያን ጫካ ውስጥ ቤት ሠርተው በምናኔ ልክ ቅዱስ ላሊበላ እንደሚያደርጉት መንፈሳዊ ተግባር እያከናወኑ ከዚህ ዓለም አልፈዋል፡፡
  ለእኔ ሕይወታቸው ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድም አስተማሪ ነው፡፡ ምሳሌና አርዓያ መሆን ይችላሉ፡፡ በዚህም ድፍን የቅዱስ ላሊበላና ነአኩቶለኣብ አካባቢ ነዋሪ በሚገባ ያውቃቸዋል፡፡ የቅዱሳን አባቶቻችንን፤ የቅዱሳት እናቶቻችንን በረከት ያሳድርብን፡፡
  አሜን

  ReplyDelete
 23. Dn.Getaye Ze LalibelaFebruary 6, 2014 at 12:28 PM

  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ ሌሎችንም እየፈለግህ እንድንማርባቸው ጻፍልን፡፡
  እግዚአብሔር በዘመናት ሁሉ የሚሠጠን ቅዱሳን አሉ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በተጋድሏቸው፣ በጸሎታቸው፣ በትሩፋታቸው፣ በምነናቸው ይታወቃሉ፡፡ ይኽ ሁሉ የእግዚአብሔር ቸርነት መገለጫ መንገዱ ነው፡፡
  ዝም ብሎ እግዚአብሔርን ብቻ ማመስገን፣ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ማድነቅ ነው፡፡ ገና እግዚአብሔር ሰው በጠፋበት ዘመን፣ ሰው በሚፈለግበት ጊዜ፣ የሰው ያለህ ተብሎ ሰው ሲጠየቅ እግዚአብሔር መልስ አለው፡፡
  የእማሖይ ባቄላም ታሪክ ይህንን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ እናትና አባት ልጆቻቸውን በሥርዓት በማያሳድጉበት ዘመን፣ ወንድም እኅቱን በማይጠይቅበት ጊዜ፣ ልጆች ወላጆቻቸውን በማይጦሩበት ወቅት ችግረኞችን፣ ድሆችን፣ ደካሞችን፣ ኅመመተኞችን የሚረዱ እናቶችን ማግኘት ተዓምር ነው፡፡
  ለመነሻ ይህንን ካልኩ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ውስጥ በ1980ዎቹ አካባቢ ወቅት ቦታው በውል ከማይታወቅ ከመንግሥት መሥሪያ ቤት ጡረታ ወተው የመጡ አንድ እናት ነበሩ፡፡ የት እንደመጡ፣ የት እንደተወለዱ፣ ትክክለኛ ስማቸው ማን እንደሆነ ሳይታወቅ በምነና እያገለገሉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ እናት ነበሩ፡፡ ስማቸው እማሖይ ‹‹ሙሆዶ›› ይባላል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ እንደመጡ በትልቅ እንስራ ፍህም እሳት ሞልተው ተሸክመው ንስሐ ግቡ እያሉ ይዞሩ ነበር፡፡ ፊታቸው በሙሉ ጠባሳም ነበር፡፡
  እንደዛሬው የቱሪስት ፍሰቱ ሳጨምር፣ ደብሩም ሆቴሎች ሳይገነባ፣ ካህናቱም ለደመወዝ ሳይሆን ለንስሐ፣ ለምህረት፣ ለሠላም በሚያገለግሉበት ወቅት፣ የካህናቱ ደመወዝ 15ና 30 ብር በነበረበት ወቅት፤ መናንያኑ የቅዱስ ላሊበላን አፈር ልሰው በሚኖሩበት ጌዚ፣ ቀዳስያኑ ከቅዳሴ በኋላ አፋቸውን የሚያድፉት በቅዱስ ላሊበላ አፈር በነበረበት ወቅት፤ እማሖይ ሙሆዶ ዞረው ዱቄት እየለመኑ የሰንት ቂጣ ‹‹ፀሪቀ መበለት›› እየጋገሩ በእለተ ሰንበት ተዓምረ ማርያም ከተነበበና ትምህርት ከተሰጠ በኋላ ይበላል፡፡ ጠዓሙ፣ መዓዛው ልዩ ነው አሁንም ትዝ ሲለኝ አይኖቼ እንባ ያቅራሉ፡፡ የሰንበት ቂጣው በየ አብያተክርስቲያናቱ በወርኃዊ በዓላትም ይመጣል፡፡ ያለ ማጋነን የአስቀዳሹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ ስማቸውም በአካባቢው ይነሳል፡፡
  እማሖይ ‹‹ሙሆዶ›› በዚህ ጽሑፍ ለማካተት ያልፈልግኩት በራሳቸው ላይ የሚቀልዱት ቀልድ ነበራቸው፡፡ እማሖይ የድሀ እናት ናቸው፣ ያበላሉ ያጠጣሉ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ በጣም አነስተኛ ጡረታ ብቻ የነበራው ሲሆን ሌላውን የሚያደርጉት ለምነው ነው፡፡ ይለምናሉ ያበላሉ ያጠጣሉ ሀገራው ዘመዳቸው አዝማዳቸው እግዚአብሔር ብቻ ነበር፡፡
  በጣም የሚገርመው እማሖይ የሚለብሱት ከበግ ጸጉር የተሠራ ማቅ የሚባከል ልምስ ሲሆን ወገባቸውን በሠንሠለት አሥረው ነበር፡፡ በአጠቃላይ የተለዩ መንፈሳው እናት ነበሩ፡፡ በኋላ ከቅዱስ ላሊበላ 8 ኪሎ ሚትር ርቀት ከሚገኘው ቅዱስ ነአኩቶለኣብ ቤተክርስቲያን ጫካ ውስጥ ቤት ሠርተው በምናኔ ልክ ቅዱስ ላሊበላ እንደሚያደርጉት መንፈሳዊ ተግባር እያከናወኑ ከዚህ ዓለም አልፈዋል፡፡
  ለእኔ ሕይወታቸው ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዩ ትውልድም አስተማሪ ነው፡፡ ምሳሌና አርዓያ መሆን ይችላሉ፡፡ በዚህም ድፍን የቅዱስ ላሊበላና ነአኩቶለኣብ አካባቢ ነዋሪ በሚገባ ያውቃቸዋል፡፡ የቅዱሳን አባቶቻችንን፤ የቅዱሳት እናቶቻችንን በረከት ያሳድርብን፡፡
  አሜን

  ReplyDelete
 24. ከእድሜዬ ግማሹ ወሎ ነው የኖርኩት ስለዚህ ወሎዬ ለመሆን ምን ያንሰኛል፡፡

  ReplyDelete
 25. ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያስማልን የእናታችንም ነብሰ በአጸደ ገነት ያኑርልን አሜን

  ReplyDelete
 26. እኔም ባቄላቸውን በልቻለሁ:: በጣም መልካም እናት ነበሩ:: በረከታቸው ይድረሰን::

  ReplyDelete
 27. "ትግራይ ከሰላ አካባቢ መወለዳቸው የሚነገርላቸው እማሆይ ባቄላ…" ይላል ዲያቆን ዳንኤል ይህን ፅሁፍ ሲጀምር። አንድ ነገር ልጠይቃችሁ እስቲ፣ ተሳስቼ ሊሆን ይችላል። ከሰላ ትግራይ ነው ወይስ ጎንደር ውስጥ ነው? የምታውቁ ሰዎች መልሱልኝ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከሰላ ትግራይም ሆነ ባሌም ሆነ ሐረርም ሆነ ሞያሌም ሆነ ወለጋም ሆነ ጉዳያችን አይደለም የዳኒም ጉዳይ አይመስለኝም ዋናው ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ ነው:: እግዚአብሔር ከደጋጎቹ ለመማር ያብቃን: ዘር ከመቁጠር ይሰውረን:: አሜን::

   Delete
 28. kesela ...Asela yihun gonder yihun minchegereh ..hasabachinen atwsedbin....

  ReplyDelete
 29. DANI EGZIYABHER REJIM EDEMENA TENA YESTEH

  ReplyDelete
 30. YEZERENA YEHAGER BESHETA TETENAWTOT YEHONAL

  ReplyDelete
 31. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ
  እያወቅናቸው ያልተጠቀምናባልው እናት በመሆናቸው
  ውስጤ በጣም ያዝናል፡፡

  ReplyDelete
 32. እማሆይ ባቀላ በመጽሐፍ የማነባቸውን ቅዱሳን በአይኔ ያሳዩኝ እናት ናቸው አንድ ዳንኤል ሚባል ወንድሜ ሲናገር ሰማሁትና እኔም ያመንኩበት፣ ለምን እንዚህ እናቶች ቅዱሳን አልተባሉም ደረጀ ጌጡ አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 33. Diakon Daniel, Egziabher yibarkih! Dessie Emahoy Bakelan yemayawk yinor yohon??... Egziabher nefsachewn begenet yanurilin!

  ReplyDelete
 34. I don't think God let you to left your marriage and make you beggar........this seems TERET TERET......But he answered, “It is written, “‘Man shall not live by bread alone, but by every word that comes from the mouth of God.’”Matthew 4:4 it's better that she preached Gospel (including) Jesus is the only savior.


  ReplyDelete
 35. After approval???

  ReplyDelete
 36. ሰዎች ለምን የማይመለከታቸውን ነገር ያነባሉ?

  ReplyDelete