Tuesday, February 18, 2014

እየጠፋ ያለው የመጽሐፈ መነኮሳት ትምህርት ቤት

እኔ እንግዲህ የሚቻለኝን ደክሜያለሁ፤ ከዚህ በላይ ለማድረግ ዐቅሙም ዕውቀቱም የለኝም፡፡ ይህን ጉባኤ ቤት ደርቡሽ ፈተነው፣ መንግሥት ፈተነው፣ እሳት ፈተነው፣ ረሃብ ፈተነው፤ ይህንን ሁሉ ተቋቋመ፡፡ አሁን ግን እኔም አልፋለሁ፡፡ ትምህርት ቤቱም ይዘጋል፡፡ ሁላችንም ታሪክ ሆነን እንቀራለን››
click here for pdf
ጎንደር ከተማ በሄድኩ ጊዜ ሠለስቱ ምእት እየተባለ ወደሚጠራው አካባቢ ተጉዤ ነበረ፡፡ በዐፄ ቴዎፍሎስ (1700-1704 ዓም) ተሠርቶ በ1880 እና በ1881 ዓም በተደጋጋሚ በደርቡሽ ተቃጥሎ የጠፋውን የሠለስቱ ምእት ቤተ ክርስቲያን ፍራሽ ለማየት፡፡ ይህ በአንድ ወቅት እንደ ኒቂያ 318 ሊቃውንት ተሰባስበው ይመክሩበት ነበር የሚባለው ዋናው የጉባኤ ቦታ ደርቡሽ ካፈረሰው በኋላ እንደገና ሳይሠሩ ከቀሩት የጎንደር አድባራት አንዱ ነው፡፡
ከዚሁ ፈርሶ ከቀረውና ዛሬ መጸዳጃ ቤት ከሆነው የሠለስቱ ምእት ቤተ ክርስቲያን ፍራሽ አጠገብ በቆርቆሮ የታጠረ አንድ ግቢ አለ፡፡ ወደ ውስጥ ስትዘልቁ ዳዋ የለበሰ ግቢና በጭቃና ቆርቆሮ የተሠሩ ሦስት አነስተኛ ክፍሎችን ታገኛላችሁ፡፡

እኔ በጥግ ወዳለው ክፍል ዘለቅኩ፡፡ አንድ ዓይነ ሥውር አረጋዊ አባት አልጋ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ቤቷ ጠባብና በዕቃዎች የተሞላች ናት፡፡ የመጽሐፈ መነኮሳቱ መምህር መጋቤ ምሥጢር ተሾመ ታደሰ ናቸው፡፡ በዚህ ቦታ ላይ መጀመሪያ ረዳት መምህር ሆነው ከ1987 ዓም ጀምሮ አገልግለዋል፡፡ በ1991 ዓም ደግሞ ሙሉ መምህር ሆነው ጉባኤ ቤቱን ተረክበዋል፡፡
የ66 ዓመቱ መምህር የሚያስጨንቃቸው የሚበሉት ምግብና የደመወዛቸው ሁኔታ አይደለም፡፡ የመጽሐፈ መነኮሳቱ ጉባኤ ቤት እየጠፋ መምጣት ነው፡፡ በሀገራችን በመጥፋት ላይ ከሚገኙት ጥንታውያን ትምህርቶች አንዱ የመጽሐፈ መነኮሳት የትርጓሜ ትምህርት ነው፡፡ በዋናነት መነኮሳት እንዲመከሩበት የተጻፈውና የተተረጎመው፣ በሦስት ክፍል (ማር ይስሐቅ፣ አረጋዊ መንፈሳዊና ፊልክስዩስ) ይህ መጽሐፍ  በጉባኤ ቤት የሚማረው እየጠፋ መጥቷል፡፡ በሀገራችን ለምንኩስና ሥነ ምግባር መበላሸት አንዱ ምክንያትም ይህንን የትምህርተ ሃይማኖት፣ የሥነ ምግባርና የእምነት መጽሐፍ ያልተማሩ፣ የስም መነኮሳት መብዛት መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡

ይህን ትምህርት ቤት ታላቁ ሊቅ አለቃ አየለ (ዶክተር) በ1948 ዓም እንደገና እንዲያንሠራራ አድርገውት ለብዙ ዘመናት ቆይቶ ነበር፡፡ ቦታውን በተመለከተ የአካባቢው መስተዳድርና መምህራኑ እየተወዛገቡበት፣ ጉባኤው ግን ሳይታጠፍ ኖሯል፡፡ በ1988 ዓም ኅዳር 30 ቀን የአካባቢው መስተዳድር ቦታውን ለትምህርት ቤቱ ሰጠ፡፡ መምህሩና ደቀ መዛሙርቱ በዚህ ሲደሰቱ ግን ጉባኤ ቤቱ በ2004 ዓም የካቲት 7 ቀን በተነሣ እሳት ወደመ፡፡ በዚህ ቃጠሎ በ1714 ዓም የተጻፈ መጽሐፈ መነኮሳትን ጨምሮ አያሌ ቅርሶችና መጻሕፍት ወድመዋል፡፡
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ትምህርት ቤቱ ችግር ላይ ወደቀ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በጭቃ እና በቆርቆሮ እነዚህን ሦስት ክፍሎች ሠሩ፡፡ ግቢውንም ዳዋ ዋጠው፡፡ ተማሪዎቹም ከምግብና ልብስ ችግራቸው ላይ የመጠለያ እጦትም ተጨመረበት፡፡ ውኃውን የማራኪ ግቢ ጉባኤ ልጆች አስገብተውላቸዋል፡፡ መብራት ግን የለም፡፡ አሁን አሥር ተማሪዎች ዳዋ ተንተርሰው እየኖሩ ጉባኤው እንዳይታጠፍ ይተጋሉ፡፡

መምህሩም እንዲህ አሉኝ ‹‹እኔ እንግዲህ የሚቻለኝን ደክሜያለሁ፤ ከዚህ በላይ ለማድረግ ዐቅሙም ዕውቀቱም የለኝም፡፡ ይህን ጉባኤ ቤት ደርቡሽ ፈተነው፣ መንግሥት ፈተነው፣ እሳት ፈተነው፣ ረሃብ ፈተነው፤ ይህንን ሁሉ ተቋቋመ፡፡ አሁን ግን እኔም አልፋለሁ፡፡ ትምህርት ቤቱም ይዘጋል፡፡ ሁላችንም ታሪክ ሆነን እንቀራለን››
እንዲህ ያሉት ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ብዙ ሀገራዊ ጉዳት አላቸው፡፡ ከዘመን ዘመን የተጠራቀመ ዕውቀት፣ ታሪክ፣ ትውፊትና መረጃ ይጠፋል፡፡ ከሀገራዊ ማዕድ ውስጥም አንድ ዓይነት ይጎድላል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ የምንኩስና ሕይወትም ያለ ዕውቀት ይቀራል፡፡ የኔ ቢጤው ደግሞ በሰማይም በምድርም አይተህና ሰምተህ ታድያ ምን አደረግክ? ተብሎ ይወቀሳል፡፡
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ያመኑና ያወቁ አበውና ምእመናን ተባብረው አስበልጠው ያሠሩታል፡፡ ትምህርት ቤት ፈርሶ ትምህርቱና ሊቃውንቱ ከጠፉ ግን እንደገና መመለስ ከባድ ነው፡፡ እስኪ በየቦታው የተመሠረታችሁ በጎ አድራጊ ማኅበራትና ግለሰቦች የልባችሁ አጀንዳ አድርጉት፡፡

69 comments:

 1. አይ ዲያቆን ዳንኤል የዋህ ነህ። አሁን ማን ይሰማህና በከንቱ ትደክማለህ ወንድሜ ሆይ? እኔ እርሜን አዉጥቻለሁ። ቤተ ክርስትያኒቱ ከሞተች ቆየች እኮ። ዜማ፣አቋቋም፣ቅኔ፣መጽሐፍት ትርጓሜ፣ ግብ አተ መሬት ገብተዋል። አሁን ምድረ መሃይምና ካድሬ ቤተ ክርስቲያኗን እያጠፋት ነው። በጥቂት አመታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኗ ትዉፊት ታሪክ ብቻ ሆኖ ይቀራል። እነ ቤተ ልሄም፣ ዙር አምባ፣ቆማ፣ዋሸራ፣ተክሌ፣ሳንኳ፣ ወዘተ ከነዜማ፣ አቋቋምና ቅኔ ስልታቸው ወድመዋል። ዋ ያሳዝናል!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. hello Anonymous @ 6:34 PM, tesfa kortew tesfa ayaskortun hulachinim yechalinewun bemerdat ena betselot enmokir. Dn Daniel Medahnialem yibarkih

   Delete
  2. I support the first Anonymous person, everything has been gone. I don't we don't have to try but it look like impossible unless all Tigray pass away. Tigray is created by davil so we have to destroy them first to change our country. God bless Ethiopia.

   Delete
  3. እባካችሁ የሰሞኑ ንፋስ አላማረኝም ሁዳዲን በጾሎት እንበርታ።
   ዳኒ መድኀኒዓለም አይለይሕ። በርታ

   Delete
  4. How can we help? Dani would you please tell us how we can reach the school.
   Samuel

   Delete
  5. እግዚአሔር ተስፋ አይቆረጥበትም እኛ የድርሻችንን እንወጣ በፀሎት እንበርታ

   Delete
  6. አውቀህ፣ ተናግረህ ሞተሃለ። እንዳንተ አዋቂ መሰል ተባይ ውስጣችን ተሰግስጎማ ቤተክርስቲያን ግብዐተ መሬቷን ለማፋጠን ይታትራል። አሁን የቤተክርስቲያን ትንሣኤ ዘመን ነው። አንተ ብትተኛ ሌት ከቀን የማያንቀላፋ፣ የትምህርት ተቋማቷ መዳከም የሚያንገበግበው ትውልድ ተፈጥሯል። ደግሞም የቤተክርስቲያን ህልውና በባለቤቷ እጅ ላይ እንጂ በአንተና እኔ አይነቱ ደካማ ላይ አይደለም። “እርሜን እውጥቻለሁ” ስትል ትንሽ ውዳሴ ከንቱህ ሰማይ እንደነካ እንኳ አይታወቅህም? ከዳንኤል ፉክክር ነው የያዝከው ወይስ ቤተክርስቲያንን የማዳከም ተልእኮ አንግበሃል?

   Delete
 2. ተጠቃሚው ማነው?
  ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ዐረፉ
  በአንድ ሰሞን ፓትርያርኩንና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ያጣንበት ምክንያት ምን ይሆን? የእግዚአብሔርስ መልእክቱ ምንድን ነው? ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የኀዘን ቦታ ላይ ‹‹ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ነገርግን የሚያነበው የለም›› እንዳሉት ከሰሞኑ ሁኔታ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ሌሎቻችንስ ምን እንማራለን?
  ለዚህ ነው «አጣልቶ የሚያፋቅር፣ አጋጭቶ የሚያጣብቅ ፍቅር ይስጣችሁ» ብዬ መመረቅ የጀመርኩት፡፡ ጠብን የሚያሸንፍ ፍቅር፣ ጦርነትን የሚያሸንፍ ሰላም፣ ጨለማን የሚያሸንፍ ብርሃን ነው የሚያስፈልገን ብዬ፡፡
  መሪ በመፈንቅለ መንግሥት ሳይገለበጥ፤ በጦርነት ተሸንፎ አገር ጥሎ ሳይወጣ፤ በአብዮት ከዙፋን ወርዶ እሥር ቤት ሳይገባ በተፈጥሮ ሞቶ በክብር ሲቀበር ለእኔ ትውልድ አዲስ ታሪክ ነው፡፡ የኔ ትውልድ ስለ መሪው ስደትና ሞት ሲሰማ እንጂ መሪውን አልቅሶ ሲቀብር አላየሁም፡፡ መለስ በዚህ ታሪክ ሠርተዋል በተግባር አርአያ የሚሆኑ አባቶች ያላሳጣን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር አስታዋሽ አያሳጣህ ረጅም እድሜን ከአገልግሎት ዘመን ጋር ያብዛልህ ውድ ወንድማች ዳኒ፥ የበረክት ሥራህ ሁሉ ይባርክልን፤ እግዚአብሔር አምላክ ።

  የተከበሩ አባታችን፥ አለቃ አያሌው ታምሩን ብናጣቸውም፤
  በዘመናችን አንተን የመሰለ፥ የሃይማኖት መምህር፣ የወግ ጸሐፊ፣ የታሪክ ሰው፣ የሃገር አስተዋዋቂ፤ ማግኘታችን በእውነት እጅግ ደስተኞች ነን።

  ዛሬ ዛሬ፥ ስለ መልካም ሃይማኖትህና እምነትህ ቀንተህ ሠዎችን ስትረዳ፤ አላስተዋይ የሆኑ ሠዎች ሲመለከቱህ የሚያወጡልህ ስም ለለ፤ እርሱም "አንተ ደግሞ ምን የሚሉህ ምግባረ ሠናይ ድርጅት ነህ?" ይላሉ።

  እንግዲህ፥ አላስተዋይና ፌዘኞች ሠዎች ማለት እነዚህ ናቸው ነው። ፌዘኛን ሠው አትገስጸው፤ ማለት ይሄኔ ነው። /ምሳ 14፥6 ፤ 15፥12 ፤ 19፥25 ፤ 21፥11/

  ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ሠውንም የሚያከብር ሠው ደግሞ፤ ልክ እንደ ወንድማች ዳኒ፥ ይጽፋል፣ ይናገራል፣ ያስተምራል "ለርሳቸው ለአባ መፍቀሬ ሰብእ፥ ዘርና ሃይማኖት ሰውን ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም፡፡ ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል።" ይላል! Who will be build this church? Who will be help our father and mother? We gave money every day for different churches why this kind of church don’t get help from other churches? What is doing Aba Sereke Brhan the leader of Sebekagubaya? What is doing St Patriarc Mathias?

  Dear Dani thanks and God bless you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you crazy the Anonymous person? I read it three times but I don’t understand what are talking about. It looks like you read something and you give comment. There is no relationship with the topic. It has more than ten different ideas. Please don’t confuse people by writing this kind of fable. Be a human being!!!

   Delete
 3. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ያመኑና ያወቁ አበውና ምእመናን ተባብረው አስበልጠው ያሠሩታል፡፡ ትምህርት ቤት ፈርሶ ትምህርቱና ሊቃውንቱ ከጠፉ ግን እንደገና መመለስ ከባድ ነው፡፡

  ReplyDelete
 4. በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሆነዉና የሚሆነው ነገር እጅግ አሳዛኝና ተስፋ አስቆራጭ ቢመስልም ሁሉን በሚችለው አምላክ ለውጥና ትንሣኤ እንዲመጣ በአቅማችን መረባረብና መጸለይ እንጂ ተስፋ መቁረጥማ የልኡል እግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት መጠራጠርና ለቤቱ የማይቀና አድርጎ ማሰብ ይሆናል። ረድኤተ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን

  ReplyDelete
 5. libachin ynka, libachin keneka lebego sira ejachin yzeriga,
  thanks!

  ReplyDelete
 6. የኢትዮጵያን ዕውቀት ባለ አደራ ቅድሰት ቤተ ክርስትያን ናት፡፡ በተለያዩ ግዜያት በተነሱ የሀይማኖት እና የሃይል ግጭቶች ምክንያት መፅሃፍቶች ቢወድሙም (ዮዲት፤ ሞሃመድ ግራኝ፤ ደርቡሽ፤ እንግልጣ፤ ጣልያን)… ለዚህም ይሆናል ዛሬ እነ አክሱም፣ ላሊበላ እና ሌሎች አቢሲኒያዊ ጥበቦችን ለአለም ማስጎብኘት እንጂ ማስረዳት አልያም ደግመን መስራት ያቃተን፡፡

  ReplyDelete
 7. የኢትዮጵያን ዕውቀት ባለ አደራ ቅድሰት ቤተ ክርስትያን ናት፡፡ በተለያዩ ግዜያት በተነሱ የሀይማኖት እና የሃይል ግጭቶች ምክንያት መፅሃፍቶች ቢወድሙም (ዮዲት፤ ሞሃመድ ግራኝ፤ ደርቡሽ፤ እንግልጣ፤ ጣልያን)… ለዚህም ይሆናል ዛሬ እነ አክሱም፣ ላሊበላ እና ሌሎች አቢሲኒያዊ ጥበቦችን ለአለም ማስጎብኘት እንጂ ማስረዳት አልያም ደግመን መስራት ያቃተን፡፡

  ReplyDelete
 8. እንዲህ ያሉት ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ ብዙ ሀገራዊ ጉዳት አላቸው፡፡ ከዘመን ዘመን የተጠራቀመ ዕውቀት፣ ታሪክ፣ ትውፊትና መረጃ ይጠፋል፡፡ ከሀገራዊ ማዕድ ውስጥም አንድ ዓይነት ይጎድላል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ የምንኩስና ሕይወትም ያለ ዕውቀት ይቀራል፡፡ የኔ ቢጤው ደግሞ በሰማይም በምድርም አይተህና ሰምተህ ታድያ ምን አደረግክ? ተብሎ ይወቀሳል፡፡

  ReplyDelete
 9. ዳ/ን ዳንኤል እግዜር ይስጥህ ማወቅ በራሱ ትልቅ ነገር ነው ሰው ሲያውቅ ነው የሚቀጥለውን የሚያደረገው:: መቼም ይህን ሰምቶ ከኔ ምን ይጠበቃል የሚል ጥቂት ሰው አይጠፋም:: እግዝእ አብሄር ይርዳን:: ለአንተም ጸጋውን ፅናቱን ይስጥህ::

  ReplyDelete
 10. wendem daniel berta egeziabehar kante gar yehun bewent telk hawarianet new sew bealew new yemiredaw eskemechershaw leb yalew yetagel lebetkrstian lemangnawem tesfa ankuret.

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል በእውነት በጣም የሚያሳዝን ነው ግን እስቲ መፍትሔ እናምጣ ከኛ ምን ይጠበቃል? ምን ብናደርግ ይሻላል? የሚለው ላይ ብንነጋገርበት እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hi the Anonymous person, I am not Daneil but I would like to give you some idea to help this church. At the movement the only solution to go Gonder and to help this church directely. If you ask someone for our church you will lose your money. If Aba Sereke Brhan knows your idea please belive me, he will send you to jail. He work day and night to destroy Ethiopian Orthodox Church. He has been working hard with Tadso and protastant leader to destroy this church. He hired by the current goverment to do this job.

   Delete
  2. ሰላም ለሁላችን:: ማድረግ ያለብን ሁላችንም በረፍት ግዛችን ብያንሰ እንደ Extra-curricula activities ቢሆነም እንኩአን መማር ካሉን አባቶች እውቀቱን ማስቀረት አለብን :: የገንዘብ እርዳታ ማድረግ አለብን :: በየከተማው ያሉ አብያተ ክርይስትአናት ለገጠሮች መርዳት አለባቸው::

   Delete
  3. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ያመኑና ያወቁ አበውና ምእመናን ተባብረው አስበልጠው ያሠሩታል፡፡ ትምህርት ቤት ፈርሶ ትምህርቱና ሊቃውንቱ ከጠፉ ግን እንደገና መመለስ ከባድ ነው፡፡ እስኪ በየቦታው የተመሠረታችሁ በጎ አድራጊ ማኅበራትና ግለሰቦች የልባችሁ አጀንዳ አድርጉት፡፡

   Delete
 12. ውኃውን የማራኪ ግቢ ጉባኤ ልጆች አስገብተውላቸዋል፡፡ መብራት ግን የለም፡፡ አሁን አሥር ተማሪዎች ዳዋ ተንተርሰው እየኖሩ ጉባኤው እንዳይታጠፍ ይተጋሉ፡፡

  ReplyDelete
 13. የማርያም መንገድ ስጡን ፡፡ የምንሰራ ፡ለራሳችንና ለቤተሰቦቻችን ብቻ ሳይሆን ለቤተክርስቲያናችንም እንስራ፡፡ የምናገኘዉ ለራሳችንና ለቤተሰቦቻችን ይበቃ ይሆናል ለቤተክርስቲያናችንስ ? ያለንን ትርፍ ነገር ;ጊዜ ፣ ገንዘብ ፣ ቁሳቁስ ፣ ጉልበት ፣ ሌላም ሌላም እንዴት አድርገን አቀናጅተን ለቤተክርስቲያናችን እንትረፍ ? የማርያም መንገድ ስጡን፡፡
  የማርያም መንገድ ስጡን፡፡
  ማዘን ምን ሊሰራ፡
  ከሌለ ወጋግራ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማዘን ከተገኘ ለማነጽ ቤቱን
   መከታና ታዛ እድሞ ማቆሙን
   ተራዳ ወጋግራ ጠርቦ ማቅረቡን
   እንተጋበታለን አፈር ማንሳቱን
   ማዘኑ ካሳየን የሕንፃው ልኩን።
   ማዘኑ ካልጥፋ ዋናው ቁም ነገር
   እኛ ማገር ከሰው ካላጣን በቀር
   ሳትሠራ አትቀርም ያሰብናት አገር
   የስጋ ማረፊያ የነፍስ ማዕድ ቤቷ
   የነጻነት መቅደስ የታሪክ ማኅቶቷ።
   የጠላት ሺ አጥር ተሰባብሮ ወድቆ
   የወደዳት ልጅዋ ይሠራታል ታጥቆ
   የከፋፈላትን ሺ አጥር አፍርሶ
   ያንፃታል እንጂ በአንድነት መልሶ።
   ማዘን ያሳየኸን ዳንኤል ወንድማችን
   እግዚአብሔር ይስጥልን ጥበቡን ያብዛልን
   ማገር የት እንዲገኝ እንድትገልጥልን።

   Delete
 14. ዳኒ ከ2004 ቃጠሎ በኋላ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንደነበርና የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራ እደጀመረ አስታውሳለሁ መረጃው ከዲያቆን መላኩ እዘዘው አልያም ከወጣት ማህበራት ጥምረት አይጠፋም ስለዚህ መረጃውን አጣርተህ ተጨማሪ ነገር ብትጽፍ ይበጃል እሱ ያበርታህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you brother for the real information. Somethime Daneil writ some false statment to abuse the current goverment. I know this goverment did many bad thing on Ethiopian people but daneil !!! more. God bless you Ashenafi Desalegn.

   Delete
  2. Anonymous @ 10:45 PM, what a moron you are! Do you know what the word moron mean? What are you doing here to read something you can not understand? Ashenafi's comment was written in Amharic... you didn't understand it and, stupid of you, tried to explain it in English. Dn Daniel already stated the current situation of the place by citing the Teacher's statement. Ashenafi didn't say Dn Daniel presented a false accusation on any one and certainly not mentioned the government let alone abuse them. He just asked for more information and that is it. In fact Dn DK wrote በ1988 ዓም ኅዳር 30 ቀን የአካባቢው መስተዳድር ቦታውን ለትምህርት ቤቱ ሰጠ፡፡ About the problems before then he wrote ቦታውን በተመለከተ የአካባቢው መስተዳድርና መምህራኑ እየተወዛገቡበት፣ ጉባኤው ግን ሳይታጠፍ ኖሯል፡፡ He mention the parties involved in the dispute in a fair manner. That is what in your definition is an abuse.

   If there was enough support and fund raising which has been done after the fire in 2004 as Ashenafi remembered, the explanation by the Teacher would have been different. Dn Daniel supported his article with pictures, if you can see and processes them in your insult induced mind. I hope you will understand what I mean. Or please get help to understand what has been written in Amharic and English before you dare to touch the keyboard.
   Thank you Dn Daniel

   Delete
  3. Anonymous @ 5:48 PM Thank you so much for your explanation with the supportive idea. However you use some bad words to respond your answer. I just want let you know that when someone oppose from the majority that means everybody read this site. So we have to be happy when we see this kind of person with us. Otherwise this site will be Ethiopian parliament. If you see Ethiopian parliament there is no opposition so they don’t get feedback. Even if we love Danial Kebret still he is a human Bing so we need someone from the opposite side. I am not sure where you live but if you travel in Europe or USA, you will see best opposition and that is the key to their civilization. Do you think Esknder Nega or Riot Alemu did any mistake to this government? No , but our society not accepts any opposition.

   Delete
  4. እልፍ ለአንድFebruary 23, 2014 at 7:09 PM

   (Part I)

   ስሜን እልፍ ለአንድ ብየዋለሁ።

   Hello there @ Ano 7:26. Thank you for your response. I am disappointed you felt offended by some words written for someone to express their inadequacy. I know opposition is important to develop ideas and to get the best of conclusions. But to qualify as a competent opponent you need to understand what the subject is and equip yourself with up-to-date information and knowledge. Otherwise there is no point being an opponent. If that is the case that person who doesn't know what they are talking about just exposes themselves as an idiot or even worse a moron. When that happens one should tell them exactly where there place is and awaken them to learn more before they try to look intellects in front of the world. Without this compatibility there will be no progress towards a result. Opposition for the sake of it is nonsense. It should be re-enforced with knowledge, courage, plan, technique & tactic, consistency, tenacity, honesty, truthfulness, heroism e.t.c. I am not intolerant of different opinion if it is based on facts and a better understanding of the subject matter. But when the above individual based his accusations on someone's idea without understanding it, it beggared my belief and made me react. For him my words are just. We are all here to learn from each other. And we learn in different ways.

   You mentioned feeding back- don't you think feedbacks should be as much accurate as possible and better than the original idea? Would you be happy if someone feeds you back with junks of entofonto እንቶፈንቶ? በዉሸት የተሞላ ከሰሳ ወቀሳ?
   Otherwise I am happy to have genuine and decent people with different opinions and observations. The only thing is I do not follow them blindly. I accept as a human being Dn Daniel Kibret would make mistakes or unintentionally overlook details. But I do not accept (based on the information in the article) he misled his readers or accused some entity of anything. We have to deal with things by separating our emotion from the facts/realities in hand. I think we need to defend the purity of ideas as they are (write or wrong) to come to a right judgment. When a person twists the original information for their own interest, the readers must say 'you are wrong' and say it loud. That person not only twisted the information on the article but also used someone's comment to support their nonsense.

   You mentioned the Ethiopian Parliament to support your argument. That is a very different and complicated scenario, my fellow. I totally understand what you mean. But that place is not a learning/teaching arena. To me it is a war zone with no visible hard weapon. It decides the survival of the powerfuls. If necessary the elimination would go from ideas to as far as a physical one, from the face of the earth. We don't do that here on Daniel Kibret's Views you know! But if it was about survival, you my friend, as a product of our society, what would you do? Time and time again it has proven most African oppositions yearn for democracy until they get to power. They beg the people for their support until they get the key to the palace. Then alas!!! ... they throw all the promises and the hope, the trust and faith of the mass through the window. For the genuine democratic (ሃቀኛ) fighters the job and the commitment are not like writing on someone's blog from a laptop/pc in the bedroom.

   Delete
  5. እልፍ ለአንድFebruary 23, 2014 at 7:12 PM

   (Part II)

   I do not need to live in Europe or USA to know about opposition. However it is not the opposition that is key to their civilization. It is the tolerance and understanding of what they want as a society. Democracy by itself is a very very broad term. Each democratic society has passed through different stages to create their own type of tolerance and understanding. In our case we just copy and paste from different experiences of other nations. Hence we ended up having a quilt like (ድሪቶ) understanding of Democracy. We never started from our own experiences. As a free nation for many centuries, we had different kinds of democratic practices in different cultures and traditions. We didn't try to develop those good practices for the benefit of the nation. Instead we choose to try copying from UK, France, USA then form Russia (USSR), China, Cuba, Hungary, Romania....... then again from USA, UK, Switzerland, Germany...... Bloc by Bloc. Even we copied and pasted the imprisonment, killings and massacre in the name of rebuilding the nation, democracy and revolution. It is still going on. The difference is the killing of the nation and its citizens has become a prolonged and sophisticated one. The system became 'Westernised'. It has a legal cover. Now you can be 'fiends' with the same countries you referred as model democracies, and continue oppressing your people in all sorts of level. No one would care, because 'Europe's and USA's democracy' is made for themselves. Not for Ethiopian poor. Having the word 'democracy' on your constitution doesn't make you a democratic nation. Like having a Christian name doesn't make you a Christian. So until we get our own solution to our own problems of 'democracy', just by looking to direction of 'the promised land' ,as some call it, we get nowhere. Have you ever asked yourself why we are different from the rest of the world and the 'copy / paste' politics refused to work for us? Until we get rid of the culture of deceive, unfaithfulness and cowardliness in all forms and shapes from all places of importance in our society, we will keep suffering. So I would rather prefer my society see the needs of it's own and work for it than looking elsewhere to bring some sort of covering that doesn't fit.

   You asked me about my thoughts on Kibur Ato Eskender Nega and Kibirt W/o Ri'eyot Alemu. Well I could have written a lot on this because they are symbols of Ethiopian bravery. How can I try to say much other than admiration when they put the bar for writing the truth, in its best quality, so high? I do not represent our society when I present my arguments. I merely expressed my understanding of a certain subject and some individual's mistake when they want to deviate people's attention to something out of the realm of the topic.

   One day I will come back to you about the brave Ethiopians languishing in prison today for loving Ethiopia, for standing for the truth, for keeping their conscious clean, for awakening their fellows, for staying faithful to their people and honouring their profession.

   There are many who try to plaster their cowardly ambitions with the names of this unique Ethiopians of the century. Down with the cowards who unjustly try to profit from their sacrifices!!!

   Long live the heroes and heroines of Ethiopia. I trust in the almighty God that He will grant them their freedom and long life to Hon Mr Nega and Hon Mrs Alemu and other thousands soon.
   I do not trust on any one who themselves are prisoners of something in someway would bring their freedom!!!

   Thank you Dn Daniel Kibret for all your efforts to educate us.

   Delete
  6. Thank you so much እልፍ ለአንድ and I read it again. It was my miss understand. I apologize to Danial Kebret and to you. I think I am better than the current government because they never ask apologies to their fault. Have blessed fasting time.

   Delete
  7. እልፍ ለአንድFebruary 25, 2014 at 4:53 PM

   I am sure they will apologize, for the bads they did and they are doing, when the time comes. Whether they understand the meaning of it or not, whether they like it or not, whether they accept it as a sign of wisdom or not, whether they believe it is a starting point to healing or not, whether they'll do it tomorrow or years later, believe me they will do it. I hope they will do it in a dignified way and when it gives a deep meaning.

   May the Almighty God give us strength during this fasting season in order to see beyond the current tribulations we are in and grant us time and chance to see better days full of hope love and blessings. May the love and protection of His blessed Mother and the prayers of all Saints be with us all. Thank you ወገኔ።

   Delete
 15. ለምን ቶምቦላ ነገር ተዘጋጅቶ ገቢ ማሰባሰቢያ አይዘጋጅም፡፡ለዚህ ደግሞ የእያንዳንዱ ትምህርት ተkም ጊቢ ጉባኤ በቂ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ለዚህ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንና አንተም ዲያቆን ካላቹ ተሰሚነት አንፃር ጅማሬውን ለምን አትወስዱም፡፡በተማሪዎቹ በኩል ቲኬቱን ለተkሙ ሰራተኞች ማድረስ ይችላል፡፡እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Where you live brother/sister? I like your idea but it is imposible, I feel you came from Mars or Jupiter other wise you don't bring this kind imposible idea to us. At this movement Ethiopia Orthodox Church run by Aba Sereke Brhan. He nominated by the current goverment to destroy Ethiopian Orthodox Church. If anybody bring this kind idea to help the church he will give order for federal police to take you jail. Amen God bless Ethiopia.

   Delete
  2. hey, forget this 'Aba Sereke' ... the agenda is beyond a single individual issue

   Delete
  3. Hello the Anonymous person on February 21,2014 at 10:42am. Thank you for your comment but some people know the situation very well. It may matter a single person. If we don't say something there is no progress.

   Delete
 16. The so called tehadiso are sheking our orthodox twahido base.They cancelled yelikawent goubae and they don't care for our abenet timhrtebet to be desroyed and yet this aba sereke guy said we are responsible for the department of education of our church.He is the messenger of devil and should go to where he belongs.Althogh they tried to shek it, our church is based on our lord Medhanie alem Eyesus Christos,they will neve distroy it.Have been tried for centuries but still stand strong and expanded all over the world.
  Never get furstrated and let us be stronger and find a way to support lekawente betekrstian and abenet temhirtbetochn.Egziabher kegna ga kehone mane yekawemenal?????

  ReplyDelete
 17. ማዘን ከተገኘ ለማነጽ ቤቱን
  መከታና ታዛ እድሞ ማቆሙን
  ተራዳ ወጋግራ ጠርቦ ማቅረቡን
  እንተጋበታለን አፈር ማንሳቱን
  ማዘኑ ካሳየን የሕንፃው ልኩን።
  ማዘኑ ካልጥፋ ዋናው ቁም ነገር
  እኛ ማገር ከሰው ካላጣን በቀር
  ሳትሠራ አትቀርም ያሰብናት አገር
  የስጋ ማረፊያ የነፍስ ማዕድ ቤቷ
  የነጻነት መቅደስ የታሪክ ማኅቶቷ።
  የጠላት ሺ አጥር ተሰባብሮ ወድቆ
  የወደዳት ልጅዋ ይሠራታል ታጥቆ
  የከፋፈላትን ሺ አጥር አፍርሶ
  ያንፃታል እንጂ በአንድነት መልሶ።
  ማዘን ያሳየኸን ዳንኤል ወንድማችን
  እግዚአብሔር ይስጥልን ጥበቡን ያብዛልን
  ማገር የት እንዲገኝ እንድትገልጥልን።

  ReplyDelete
 18. bless you DN Daniel for doing what you are doing.
  It is responsibility of all of whom belonging to the mother church to do what they can. you did well in that aspect now we all need to know what to do in order to help them so they can help themselves while the maintain the continuity of the school to the next generations. I am hoping to hear the to do steps in the near future from you with the will of the almighty God.

  ReplyDelete
 19. በአማን ነጸረFebruary 20, 2014 at 1:25 PM

  1. ዳኒ ይሄኛው ጽሁፍ ባለፈው ‘ማን ይጠቀማል?’ በሚል ላወጣሀው ጽሁፍ በአስረጅነት ግብዐት እንዲሆን የወጣ ይመስላል!!ጥሩ ነው!! በዛኛው ጽሁፍህ ሊቃውንቱን ለማወደስ ስትል ጳጳሳቱን ወደማቃለል የሄድክ መስሎ ስለተሰማኝ ሊቃውንት አንተ ባልከው ልክ ያን ያህል የተረሱ እንዳልሆኑ ለማሳየት ሌላኛውን ጽንፍ ይዠ ሀሳቤን ገልጫለሁ!!አሁን እሱን ልተወውና ስለመፍትሄው የሚመስለኝን ልናገር!!
  2. መፍትሄው በጠቅላይ ቤ/ክህነት ስር ያለው የመንፈሳዊ ትምህርት ክፍል ጠንክሮ እንዲወጣ በቅንነት እገዛ ማድረግ፣ ቅ/ሲኖዶስም በየጊዜው ለአብነት ትምህርት ቤቶች በጀት ስለመያዙ ከነገረን በሁዋላ ዜናው የውሃ ሽታ ሆኖ ስለሚቀር በጀቱ በእቅድ እና በተግባር ተመንዝሮ ተግባራዊ እንዲሆን የአባትነትንና የልጅነትን ምግባር ሳያፋልሱ ቀርቦ ግፊት ማድረግ፣ከተቻለም ት/ቤቶቹ ወደ አዳሪ ት/ቤትነት እንዲያድጉ መጣር ተገቢ ይመስለኛል!!
  3. በዚህ ሂደት ውስጥ ማህበረቅዱሳንም ሆነ ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቁዋማት እንዲሁም ጉባኤዎቹን ለአመታት ከየአጥቢያው ቤ/ክ ጋር ሆኖ በትብብር ለዚህ ያደረሳቸው ምእመን ለመጽሐፈ መነኮሳት ደቀመዛሙርት በተለየ መልኩ ድጋፍ እንዲያደርግ ማሳወቅ ይቻላል!! ለምሳሌ የተወሰነ ጎጥ ቁራሹን ለእነሱ ብቻ እንዲሰጥ፣ወይም የሆቴል ባለቤቶች እነሱን ብቻ ለይተው እንዲዘከሩዋቸው ማድረግ አንዱ ጊዜያዊ አማራጭ ሊሆን ይችላል!!የረጅም ጊዜው ዘላቂ መፍትሄ ግን አሁንም ተቁዋማዊ መሆን እንዳለበት አምናለሁ!!ተቁዋም ስል ቤተክህነት ማለቴ ነው!!እንደተቁዋም አለመራመድ እንደተቃዋሚ መታየትን እንደሚያመጣ ከሰሞኑ መከራ በላይ አስተማሪ የለም!!
  4.በበኩሌ አንድ ሰሞን ሂዶ ቪዲዮ ቀርጾ በማምጣት ለአመታት በስማቸው የሚካሄዱ ልመናዎች ብዙም አመርቂ ሆነው አይታዩኝም!!መምህራኑም ‘በአመት አንድ ጊዜ ጉባኤያችንን ጎብኝተው 170 ብር እና አዘነ ጎጃም ከጣሉልን በሁዋላ ገጻችንን በየአደባባዩ ሲያሰጡት ይውላሉ’ እያሉ ነው!!ከዛ ይልቅስ በቅርቡ ስኮላርሺፕ ተብሎ ከማህበረቅዱሳን የመጣው ሀሳብ ገና በመምሪያው ሳይመከርበት በየሚዲያው የተራገበ ቢሆንም ብሩህ የሆነ ሀሳብ ይመስላል!!ሀሳቡ በደንብ ተመክሮበት ባለቤትነቱን የሚመለከተው የቤተክህነቱ መምሪያ በጀት መድቦ ከያዘው በሁዋላ ማህበረቅዱሳንም ሆነ ሌሎች በጎ አድራጊዎች የየድርሻቸውን ቢያበረክቱ መልካም ነው እላለሁ!!ቤተክህነቱ ባለቤት ሳይሰኝበት ወይም በተባባሪነት እንኩዋ ስሙ ሳይጠቀስ የሚካሄድ ፕሮጀክት በሉት ጥናት ወይም በጎ አድራጎት የቤተክርስቲያኑዋን ሉዐላዊ ስልጣን ይጋፋል ብየ ስለማስብ ምንታዌ ይይዘኛል-አልደግፍም!!በዚህ መንገድ የሚመጣን ልግስና እንኩዋን እንደልጅ እንደጎረቤት ልግስናም ለመቀበል አልችልም!!
  5. በዚህ አጋጣሚ ግን ብዙ ቀደምት የማህበረቅዱሳን ልጆች በአሜሪካና በአውሮፓ ቀሲስ ተብለው በልዩ ልዩ የአስተዳደር እርከኖች ቤ/ክ ሲያገለግሉ አያለሁ!!ምናለ ታዲያ እነሱስ በየድረገጹ የምንሰማውን ስብከታቸውን ብቻ ከሚልኩልን አጥቢያቸውን አስተባብረው አንድ አንድ ጉባኤ ቢይዙልን!!ለቤ/ክ አገልግሎት እኮ የግድ ጳጳስ መሆን አያስፈልግም!!ጳጳሱ ያልሰራውን ለማጉላት ብዙ ደቂቃዎችን ኮምፒተር ፊትለፊት ተደቅኖ ሀሜትና ጽርፈት ከመዝራት ጳጳስም በሌላ ገጹ ሰው መሆኑን ተገንዝቦ ስህተቱን እያጎሉ ለማስተሀቀር ሳይሆን በትህትና ቀርቦ ልክ ሴም የአባቱን የኖህን ነውር ለመሸፈን እንደሞከረው የድርሻችንን በፍቅር ቀርቦ ማገዝ የልጅነት ግዴታችን ይመስለኛል!!
  6. ሌሎች ኦርቶዶክሳዊ ብሎግ ነን ባዮች ለቤ/ክ አስተዳደርና ለምዕመኑ መገናኛ ድልድይ በመሆን ከመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቀውን አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ “መለያያ ብዙሃን” በመሆን በጥፋት መንገዳቸው ስለቀጠሉ እስኪበስሉ ብዙ የቤ/ክ ልጆችን በማገዶነት ለመጨረስ አሰፍስፈዋልና ልቡና ይስጣቸው ከማለት ውጭ ተስፋ አንጥልባቸውም!!ራሱ ስም ሳይኖረው፣ስም የሌለው ምንጭ ጠቅሶ ቤ/ክ ለአመታት ደክማ ለማህሌትና ለዐውደምህረት ያበቃቻቸው የመንፈስቅዱስ ልጆቹዋን ስም እንደ ግራኝ መሀመድ መድረሻ አሳጥቶ ከሚያሳድድ ሀላፊነት የጎደለው ባለቤት አልባ ሚዲያ ብዙ አንጠብቅም!!
  7. ትምህርትህን ይግለጽልህ፣እንደጨረቃ ያድምቅልህ፣እንደፀሀይ ያሙቅልህ… የሚለው የየኔታ ምርቃት ግን ዛሬም ይታየኛል!!ለእነሱ ደስታቸው የእኛ የልጆቻቸው ተምሮ በአደባባይ መዋል ነው!!የተማረ ሁሉ ያስተማረውን በመልካም ግብሩ የእከሌ ተማሪ ነበርኩ እያለ ከማስጠራት በለይ የመምህር ኩራት እንደሌለ እናውቃለንና ጳጳሳትን ለመኮነን አንፋጠንም!!እንዲያ ቢሆነማ የጠ/ሚ/ር መለስ መምህራን ዛሬም ድረስ እዛው ከቾክና ከጠመኔ ጋር ሆነው አይታዩም!!እንዲያ አይደለም!! መለስ የመምህራኑን ብድር 32 ዩኒቨርሲቴ በመመስረት ነው የመለሰው!!አቡነ ጳውሎስም ለአብነት ጉባኤው ብዙም ባይበረቱም መንፈሳዊ ኮሌጆችንና መለስተኛ የካህናት ማሰልጠኛዎችን በማስፋፋት በተቻላቸው መጠን በመጣር ያለፉባት ኮሌጅ እንድታንሰራራ በማድረግ ቀደምት የቲዎሎጅ መምህራኖቻቸውን ነፍስ ለማስደሰት ሞክረዋል!!አሁን ተራው የእኛና የሃይማኖታችን የበላይ የሆነው ቅ/ሲኖዶስ ነው!!ስለዚህ ተራችንን ጉባኤ-ቤቶቻችንም ሆነ ቤ/ክ ከዚህ ችግር ወጥታ ለሌላው የምትተርፍ እንድትሆን ከአፋዊነት እና ውዳሴ ከንቱ ከተጫነው የመጠቁዋቆም ድርጊት ወጥተን ሃይማኖታችንን በተግባር እንተርጉም!!
  ወነአምን በአሃቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hello Beaman Netere
   1.First thank you for accepting your mistake.
   2.You said that every year Beteknet has budget for all Ethiopian Orthodox Church but we never seen. That means Beteknet cheat us. Every year they have budget but they never release any money so what is the point having budget?
   3.I don’t understand why are you separate Mahibere Kidusan from church? If my father or mother lazy, I will work so still I represent them. When Mahibere Kidusan does something good, all Ethiopian people say Ethiopian Orthodox Church did this. The only party that wants separate Mahibere Kidusan from the church is Weyana or the current government.
   4.Mahibere Kidusan has been trying for many years to convince Beteknet about all Ethiopian Orthodox Church budget. I mean to get for all church priest and diacon salary but beteknet never approve it.
   5.Shame on you, you shouldn’t use this word “ቀሲስ ተብለው” However if you come USA or England you will see who work for the church. For example if you come USA, you will find only seven churches under Ethiopian Orthodox Church authority all these seven church run by Mahibere Kidusan priests. The other churches are not part of Ethiopian Orthodox Church include St George church that stablished by Sereke Brhan. When Aba Sereke Brhan nominated to lead beteknet, he passed it to his friend and the church run under the current priest not under Ethiopian Orthodox Church. And when Abune Mathias was in USA he established two churches they are Medanialem in DC and Slasa in Virginia both churches are not part of Ethiopian Orthodox Church. They owned by individual priest.
   6.If you read beteknet blog you will read all false statement for example as you mention on # 2 paragraph every year beteknet has budget for each church but we never seen it. When you read other blog you will read the fact that all Ethiopian Orthodox Church money go to Weyana banks and individual Papas and priest account. If you are part of this you don’t like to read your corruption.
   7.You are untruth or lire, if they are happy to our progress why Abune Paulos went South African when Federal police killed our brother and sister. First of all abune Paulos and Abune Mathias are not come this position because God permission or Ethiopian people interest. They came to power by help of Weyana.
   8.God bless Ethiopia except Tigray.

   Delete
  2. @BeAman Tseare,

   I think you tried to recomend the MK members to contritute for this purpose. However, they already doing that. I remember last time there was a movement to help those fathers, I think they helping those assistance for those fathers who were part of the meeing. This is how they collaborate for this purpose. I live in NY. I know about it. I am not a member but support what they doing, and appreciate that. Do you think you bring some thing new envention how they do their part since they already doing it. I don't think so. Please wake up. I read you comments, sound like you don't like MK, but can't help yourself you see their job. Please tell us what did you do.

   Delete
  3. Hello Beaman could read this also ‹አንበሶች የራሳቸው ታሪክ ነጋሪ እስኪኖራቸው ድረስ፣ የአደን ታሪክ ምንጊዜም አዳኙን ከፍ ከፍ እንዳደረገ ይኖራል(Until Lions have their own historians, tales of the hunt shall always glorify the Hunter.
   I would like to say somthing what Meles and Abune Paulos did for their county and people.
   What Meles Zanawi did to Ethiopia?
   He gave Asab to Ertira
   He gave our land to Sudan and Kenia
   He killed more than 5000 people on 1997 election.
   He killed more than 37,000 Oromo (Oneg)
   He killed 4000 Banishangulian
   He destroyed 67000 house and killed 673 people from Amhara community.
   He sent jail 1,387,000 people more of them from Oromo
   He killed Azeb husband and he married her.

   What Abune Paulos did to our church?
   He killed priest at Sent Slasa church.
   He travelled to South Africa when Federal police took and killed Addis Ababa university students from church.
   He didn’t say something when Federal police takeover our Gedamats and churches place. They killed 23 Menekosat from Gedam and church.
   He didn’t take any action when Muslim people killed our father, mother, sister and brother.
   He built in St Slase church his monument.
   He follows Catholic Church not Orthodox Church. He wears Catholic Church cloth   Delete
  4. Hello ETV, I bought dish to escape your false report but you follow me.

   Delete
  5. አንተ በአማን ነጸረ የምትባል ሰውዬ ሳስብህ ከዚያ ቤተክህነት አጥር አካባቢ የማትጠፋ የሙዳዬ ምጽዋትዋ ሰርሳሪ ሰው ነህ። እስኪ ቤተክህነት ለአብነት ትምህርት ቤቶች መጠንከር የሠራውን አንዲት ነጥብ ጻፍልን። ካልቻልክ ለአብነት ትምህርት ቤቶች መጎልበት የሚነሱ ሀሳቦችን ለመድፈቅ የምትጥረው ለምንድን ነው?ሁሉም ገንዘብ ወደቤተክህነት ይፍሰስ የምትልበት ዋነኛ ምክንያት ቤተክህነት ላይ ያላችሁ ሰዎች ሥራ ስለሠራችሁ ሳይሆን የሰረቀ ብርሃን ረድእ እና ጥቅመኛ በመሆንህ ብቻ ነው።

   Delete
 20. ዳንኤል እንደምን ነህ

  እንዴት ነው የምንረዳቸው ሀምሣ ሎሚ ለአንድ ሠው ሸክሙ

  ለሀምሣ ሠው ግን ጌጡ ነው፡፡

  እና የአቅማችንን እንረዳለን፡፡

  ወለተ ሚካኤል

  ReplyDelete
 21. Dani endi aynet yetarik metfat betam yaschenkal eko mindnew madreg yalbin pls we hv to do smtng..............

  ReplyDelete
 22. ዳኒ በጣም እናመሰግናለን ለሰጠአን መረጃ ፣ግን አኡን ምንድነው መፍትሔው ነው ዋናው አላማው ፣የትናንቱን አንስተን መማረሩ ምንም ትርጉም አልባ ነው፣ቢያንስ ሞክረን ነበር ማለቱ ሳይበጀን አይቀርም።እኛም ነገ ከምንፀፀት እስቲ ከፈታሪ ጋር በምንችለው ፣በፀሎትም፣በአሳብም፣በገንዘብም የምንችልውን በናደርግ የተሻለ ይመስለኛል፣በተል በተለይ ለቤተክርስቲያናን ጠንቅ የሆነውን ዲያቢሎስን ሐይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ችለን በዚ ጉዳይ የምንችለውን እናድርግ አምላከ ቅዱሳን የመቤታችን ምልጃ፣ትበቃ ከሁላችን ጋር ይሁን።እድሜና ጤና ለአንተ!የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምረው ሐይማኖታችንን ያፅናልን አባቶችን ይጠብቅልን . ፈጣሪ ይርዳን!

  ReplyDelete
 23. ዳኒ በጣም እናመሰግናለን ለሰጠአን መረጃ ፣ግን አኡን ምንድነው መፍትሔው ነው ዋናው አላማው ፣የትናንቱን አንስተን መማረሩ ምንም ትርጉም አልባ ነው፣ብቢያንስ ሞክረን ነበር ማለቱ ሳይበጀን አይቀርም።እኛም ነገ ከምንፀፀት እስቲ ከፈታሪ ጋር በምንችለው ፣በፀሎትም፣በአሳብም፣በገንዘብም የምንችልውን በናደርግ የተሻለ ይመስለኛል፣በተል በተለይ ለቤተክርስቲያናን ጠንቅ የሆነውን ዲያቢሎስን ሐይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ችለን በዚ ጉዳይ የምንችለውን እናድርግ አምላከ ቅዱሳን የመቤታችን ምልጃ፣ትበቃ ከሁላችን ጋር ይሁን።እድሜና ጤና ለአንተ!,፣የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምረው ሐይማኖታችንን ያፅናልን አባቶችን ይጠብቅልን . ፈጣሪ ይርዳን!

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳንኤል, እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን አብዝቶ ይባርክልህ።
  እንደነ ፍላጎት እና ሌሎች ቀና ሰዎች፣ ቀጣዩ ደረጃ ምንድነው? እንዴት እና በምንስ መልኩ ነው መርዳት የሚችሉ እና እርዳታም ማሠባሠብ የሚሹ ወገኖች በቀጥታ እዚያ እንዲደርስ ማድረግ የሚችሉት፣ በመሐል የሚገኙትን ቀማኞች አስወግዶ? ኮሚቴና አሰባሳቢ ድርጅትም የሚባሉትን ሳይጨምር ማለት ነው? የቀጣዩ ደረጃ ይሄንንም በሚያካትት መልኩ ያስረዳን።
  እግዚአብሔር አገራችንን እና ሕዝባችንን ይጠብቅልን!

  ReplyDelete
 25. DN Danie EGZIABHIER yabertah.

  ReplyDelete
 26. Ethiopians What is wrong with you Peple? when I read the comments I feelsick instead of solving the proplem we have, why do you fight in disguess what is this new generation is learning from this? please stop arguing and do what we suppose to do! YEGZEABHERE MENGEST BEMESDDADEB WEYME BEMEKFFAFEL AYEWERESEM! At least when you think you want to support and do some thing better please don't be Emotional.Thank you! Decon Daniel.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hello brother or sister I agree with you and I don’t support bad word however this is part of democracy to express opinion. So don’t take it personal. To bring change some people declare war so expression war is better than real war. I feel this is democracy and thank you Diakon Danial for doing this great job to your country and people.

   Delete
  2. I just want let you know that when someone oppose from the majority that means everybody read this site. So we have to be happy when we see this kind of person with us. Otherwise this site will be Ethiopian parliament. If you see Ethiopian parliament there is no opposition so they don’t get feedback. Even if we love Danial Kebret still he is a human Bing so we need someone from the opposite side. I am not sure where you live but if you travel in Europe or USA, you will see best opposition and that is the key to their civilization. Do you think Esknder Nega or Riot Alemu did any mistake to this government? No , but our society not accepts any opposition.

   Delete
 27. Kehulum hasab yemilkew wedemefthew yemilew newna wenmachin dn daniel ante hasabun endemansath lemefthewm finch sitenina esti astebabreh lekum neger enbka.

  ReplyDelete
 28. ዲያቆን ዳንኤል, እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን አብዝቶ ይባርክልህ።
  እንደነ ፍላጎት እና ሌሎች ቀና ሰዎች፣ ቀጣዩ ደረጃ ምንድነው? እንዴት እና በምንስ መልኩ ነው መርዳት የሚችሉ እና እርዳታም ማሠባሠብ የሚሹ ወገኖች በቀጥታ እዚያ እንዲደርስ ማድረግ የሚችሉት፣ በመሐል የሚገኙትን ቀማኞች አስወግዶ? ኮሚቴና አሰባሳቢ ድርጅትም የሚባሉትን ሳይጨምር ማለት ነው? የቀጣዩ ደረጃ ይሄንንም በሚያካትት መልኩ ያስረዳን።
  እግዚአብሔር አገራችንን እና ሕዝባችንን ይጠብቅልን!
  Reply

  ReplyDelete
 29. ለምን ቶምቦላ ነገር ተዘጋጅቶ ገቢ ማሰባሰቢያ አይዘጋጅም፡፡ለዚህ ደግሞ የእያንዳንዱ ትምህርት ተkም ጊቢ ጉባኤ በቂ ነገር ማድረግ ይቻላል፡፡ለዚህ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንና አንተም ዲያቆን ካላቹ ተሰሚነት አንፃር ጅማሬውን ለምን አትወስዱም፡፡በተማሪዎቹ በኩል ቲኬቱን ለተkሙ ሰራተኞች ማድረስ ይችላል፡፡እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
 30. ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ቢፈርስ ያመኑና ያወቁ አበውና ምእመናን ተባብረው አስበልጠው ያሠሩታል፡፡ ትምህርት ቤት ፈርሶ ትምህርቱና ሊቃውንቱ ከጠፉ ግን እንደገና መመለስ ከባድ ነው፡፡

  ግዜክስ

  ReplyDelete
 31. Dear Dn Daniel,
  Many thanks for your message. I have a comment though. I don't think it is a good practice to let derogatory remarks be posted in your blog.

  ReplyDelete
 32. አቤቱ የጉባዔ አምላክ ሆይ ጉባዔህን እና መምህራኑን ጠብቅ ለልጆችህ መልካም አእነና የአበባተቶቸቹነን ተታረሪከክ የመሚጠበብቅ ልቦናን ስጥ

  ReplyDelete
 33. አይ ዲያቆን ዳንኤል የዋህ ነህ። አሁን ማን ይሰማህና በከንቱ ትደክማለህ ወንድሜ ሆይ? እኔ እርሜን አዉጥቻለሁ። ቤተ ክርስትያኒቱ ከሞተች ቆየች እኮ። ዜማ፣አቋቋም፣ቅኔ፣መጽሐፍት ትርጓሜ፣ ግብ አተ መሬት ገብተዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. አታሙዋርት!!ያልካቸው ሁሉ ጉባኤያት ሩቅ ሳትሄድ ታዕካ ነገስት በዓታለማርያም፣እዚሁ አራት ኪሎ ይሰጣሉ!!አሁኑኑ ሂደህ አረጋግጥ!!አንድ የማኅበር ጉባኤ ተሰረዘ ብለህ ህዝብ ተስፋ አታስቆርጥ!!ከበረታህ ደብረሊባኖስም፣ዓዲስዓለምም ሂደህ እይ!!በልመና ሳይሆን በቤ/ክህነት ተቆራጭ የሚማሩ ደቀመዛሙርትን ትጎበኛለህ!!ደርሰህ ክፉ አታውራ!!

   Delete
 34. enedete lereda echelalewe manene managere yemechelewe please tell me.

  ReplyDelete
 35. Thanks Dani,

  God Bless you !
  we need to play role on our part,
  can we get somebody so that we can contribute what we can do. contact me via vget36@gmail.com

  ReplyDelete
 36. dont say tigray people in general plse readd yetekle ashekere.

  ReplyDelete
 37. *** To whom it may Concern!!!Who is "Aba" Sereqe Birhan??? pls let us know him????

  ReplyDelete
 38. Egizihabher yistelen diyakon Dinel but I felt so sorry for those giving negitve comments come-one gays this is a moral every Ethiopian should do what expected for my side if there is any thing to help those please let me know

  ReplyDelete
 39. እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
  የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
  መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
  ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

  ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
  ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
  ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
  ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
  ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

  ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
  የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
  ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
  እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
  ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
  ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
  ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
  እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

  ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
  ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
  እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
  ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
  የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
  በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
  ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
  የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
  ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
  ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
  አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
  ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
  ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
  ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

  የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
  ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
  የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
  ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
  እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
  የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
  መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
  በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
  ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

  በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
  መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
  የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
  እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
  የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
  የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
  የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
  የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
  ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
  ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
  እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
  ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

  ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
  መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
  ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
  ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
  ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
  ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
  በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
  ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

  ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
  እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
  ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
  ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

  የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
  ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
  ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
  የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
  ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
  የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

  ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
  ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
  ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
  መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
  ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
  መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

  እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
  ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
  ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
  የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
  መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
  ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

  ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
  ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
  ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
  ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
  ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

  ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
  የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
  ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
  እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
  ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
  ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
  ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
  እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

  ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
  ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
  እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
  ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
  የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
  በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
  ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
  የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
  ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
  ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
  አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
  ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
  ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
  ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

  የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
  ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
  የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
  ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
  እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
  የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
  መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
  በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
  ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

  በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
  መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
  የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
  እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
  የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
  የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
  የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
  የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
  ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
  ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
  እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
  ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

  ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
  መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
  ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
  ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
  ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
  ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
  በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
  ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

  ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
  እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
  ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
  ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

  የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
  ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
  ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
  የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
  ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
  የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

  ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
  ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
  ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
  መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
  ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
  መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

  እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
  ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
  ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

  ReplyDelete