Wednesday, January 29, 2014

አትውረድ
በድምጽና ምስል ለመከታተል እዚህ ይጫኑ

አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በዋናው በር በኩል ወደ አውራ ጎዳናው ይወጣል፡፡ ጥቂት እንደተጓዘ ደግሞ እዚያ አካባቢ ቆመው አላፊ አግዳሚውን ከሚላከፉ ጎረምሶች ጋር ይጨቃጨቃል፡፡ ጭቅጭቁ በምን እንደተጀመረ ማናችንም አላወቅንም፡፡ እነዚያ ጎረምሶች ግን በመምህሩ ላይ ‹ሙድ› ይዘውበታል፡፡ ‹እሺ - - ሊቁ› እያሉ በስድብ ጠረባ ይረፈርፉታል፡፡ እርሱ ደግሞ ስድቡን አልቻለበትም፡፡ ‹‹ያልተማራችሁ፣ ማይሞች፣ ከስድብ በቀር ሌላ የማታውቁ፣ ደደቦች›› ይላል ሥሩ እስኪገታተር ድረስ በቁጣ፡፡ በትከሻው ያንጠለጠለው ቦርሳ ይወዘወዛል፣ መነጽሩም ልውደቅ ልውደቅ ይላል፡፡
‹‹እሺ ሊቁ፣ ለምን ላፕቶፕሺን ከፍተሺ ዕውቀት አትጭኝብንም›› እያሉ ጎረምሶቹ ይሳሳቁበታል፡፡እርሱ ይበግናል፡፡ ‹ኤፍ ብቻ ነው እንዴ ቦርሳሽ ውስጥ የያዝሺው፤ በናትሺ አንድ አምስት ኤ የለሽም›› ይሉታል፡፡ እርሱ ይንዘፈዘፋል፡፡ ‹‹አንድ ሁለት ኤ ብትሰጭን ቸብ አርገን በርጫ እንገዛበት ነበር›› ይሉታል፡፡ ሰው እየተሰበሰበ፣ እየከበበው ይሄድና የጎረምሶቹን ስድብ እንደመዝናኛ ቆጥሮት አብሯቸው ይሳሳቃል፡፡ እርሱን ኮሜዲ ፊልም እንደሚሠራ ተዋናይ ቆጥረውት በነጻ ይኮመኩማሉ፡፡ ጎረምሶቹ አንድ ተረብ በወረወሩ ቁጥር ከብቦ የተሰበሰበው ‹አስገቡለት› እያለ እንደ ጎጃም ልቅሶ ያጅባቸዋል፡፡ 
 እየቆየ ከበባው እየሰፋ፣ ሳቁ እየደራ፣ የመምህሩ ንዴት ወደ እሳተ ገሞራነት እየተቀየረ ሄደ፡፡ መምህሩ ከዚያ ከበባ ልውጣ ቢል እንኳን ሰው በጎረምሶቹ ተረብ ስለተዝናና በቀላሉ የሚያስወጡት አይመስልም፡፡ የተከፈለው አዝማሪ መስሏል፡፡ የሚያውቃቸው ስድቦች አልቀውበት አሁን ጣቱን ማውጣትና ‹‹አሳይሃለሁ›› እያለ መዛት ጀምሯል፡፡ የአንዳንድ የእንግሊዝኛ ስድቦችን ሲሳደብም
የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው›› ብለው ሳቁበት፡፡ በልቡ አንዳች የፖሊስ ኃይል መጥቶ እንዲገላግለው እየተመኘ ነበር፡፡ ወደ ስድቡ ሜዳ አስቦ ስላልገባ አስቦ ሊወጣ አልቻለም፡፡
በዚህ መካከል በግራ እጃቸው ጋዜጣ አጣጥፈው የያዙ አንድ አዛውንት ሁላችንንም እየገፈተሩ፣ እንደ ሙሴ የሕዝቡን ባሕር ለሁለት እየከፈሉ ወደ መካከል መጡና ያንን መምህር እጁን ይዘው በዝምታ ጎትተው ከከበባው አወጡት፤ ጎረምሶቹም ‹ሼባው ልቀቀው እንጂ›› እያሉ ተረቧቸው፡፡ እርሳቸው ቀናም አላሉ፣ መልስም አልሰጡ፡፡ እየሰነጠቁ እንደገቡ፣ እየሰነጠቁ ወጡ፡፡
ከዚያም ወደ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን መታጠፊያ ዘወር አደረጉትና ‹‹ለምን ልጄ፣ ለምን?›› አሉት፡፡
‹‹ከዩኒቨርሲቲ ስወጣ ለከፉኝ፣ እኔም መልስ ሰጠኋቸው››
‹‹ተማሪ ነህ?››
‹‹የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ››
‹‹እና መምህር ሆነህ ነው ከእነርሱ ጋር ስድብ የገጠምከው፤ ጥፋተኛው አንተ ነህ›› አሉት፡፡ እኛ ትንሽ ራቅ ብለን የሚሉትን መስማት ጀመርን፡፡
‹‹ተመልከት እዚያ›› አሉት በአመልካች ጣታቸው ወደ አንበሳ ግቢ አቅጣጫ እያመለከቱ፡፡ ‹‹እዚያ ግቢ ውስጥ ምን አለ?›› አሉና ጠየቁት፡፡
‹‹አንበሳ ነዋ››
‹‹አንበሳ ግን መኖሪያው ግቢ ውስጥ ነው እንዴ?››
‹‹አንበሳማ የዱር እንስሳኮ ነው፤ ምን ዓይነት ጥያቄ ነው የሚጠይቁኝ፤ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ እያልኩዎ›› መምህሩ ተናደደና ጥሏቸው ሊሄድ ከጀለ፡፡ እርሳቸውም ከእናቱ ጋር መንገድ እንደሚሻገር ሕጻን እጁን አጥብቀው ያዙት፡፡ ‹‹ወዳጂ፣ ሰው በሁሉም ነገር ሊቅ አይሆንም፡፡ በአንዱ ሊቅ ሲሆን በሌላው ማይም ነው፤ በአንዱ መምህር ሲሆን በሌላው ተማሪ ነው፤ በአንዱ ጎበዝ የሆነ ለሌላው ሰነፍ ነው›› አሉት፡፡ ትንሽ ቀዝቀዝ አለ፡፡
‹‹አንበሳው በገዛ ጫካው ውስጥ ቢሆን ኖሮ ማን ይደፍረው ነበር? ማን ጀግና ነበር ሃምሳ ሳንቲም ከፍሎ በሃምሳ ሜትር ርቀት የሚያየው? ማን ጀግና ነበር ቀርቦ ፎቶ የሚያነሣው? ማን ጀግና ነበር ከአንበሳው ጋር ፎቶ ሲነሣ የሚውለው? ጫካው የእርሱ ክልል ነው፤ የእርሱ ሠገነት ነው፡፡ እዚያ የቀለበቱ ጌታ (Lord of the Ring) እርሱ ነው፡፡ ከተማው ግን የአንበሳ መደብ አይደለም፣ እርሱ ለከተማ አልተፈጠረም፣ ከተማውን አይችልበትም፤ በግቢ ውስጥ መኖር፣ በአጥር መከለል፣ ከአንበሳው ተፈጥሮ ውጭ ነው፡፡ ስለዚህ ከሚያውቀው ወደማያውቀው፣ ከሠገነቱ ወደ ባርነቱ፣ ከሚያሸንፍበት ወደሚሸነፍበት፣ ከሚችልበት ወደማይችልበት፣ አወደርነውና፤ በከተማ፣ ግቢ ውስጥ አሥረን እንደልባቸውን እንጫወትበታለን፡፡ አሁን የሚፈልገውን አድኖ ሳይሆን የምንሰጠውን ይበላል፣ በፈለገው ሰዓት ሳይሆን በሰጠነው ሰዓት ይመገባል፣ ወደፈለገው ቦታ ሳይሆን ወደፈለግነው ቦታ ይሄዳል፣ የፈለገውን ሳይሆን የፈቀድንለትን ብቻ ያያል፡፡ ለምን? ወደኛ ሜዳ አውርደንዋላ፣ ሜዳውን ትቶ መጥቷላ፤››
ዝም አሉና ቀና ብለው አዩት፡፡ ቦርሳውን ወደ ላይ ገፋ ገፋ እያደረገ ይመለከታቸዋል፡፡ እኛም መጨረሻውን ለማወቅ ጓጉተን አፍጠን እናያቸዋለን፡፡ ስድብና ድብድብ ለማየት ተሰብስቦ የነበረው ሰውም ነገሩ ዕውቀትና ቁም ነገር ሲሆንበት ጊዜ ቀስ በቀስ ‹‹ሼባው ነገሩን ትምሮ አደረጉት›› እያለ ከአካባቢው ሸሸ፡፡ ‹‹የሚቧቀሱ መስሎኝ ነበር፤ ሼባው አበላሸው፡፡ ስድድቡ ተመችቶኝ ነበር ›› እያሉ በቁጭት ጥለዋቸው ሄዱ፡፡
‹‹አንተም እንደ አንበሳው ሆንክ›› አሉ ሽማግሌው፡፡ ወረድክ ከመደብህ፣ ከምትችለው የዕውቀት ክርክር ሜዳ፣ ከምታሸንፍበት የሃሳብ ክርክር ሜዳ፣ ከለመድከው የጥናት ክርክር ሜዳ፣ ወረድክላቸው፡፡ ጎበዞች ናቸው ደግሞ አድንቃቸው፡፡ አወረዱህና በሚችሉት ሜዳ ላይ በደንብ አድርገው ቀጠቀጡህ፡፡ አንተም ሞኝ ነህ በማታውቀው ሜዳ ላይ ትግል ገጠምክ፡፡
‹‹ሶምሶን ከፍልስጤማውያን ዐቅም በላይ ሲሆንባቸው፡፡ ፍልስጤማውያን ምን አደረጉ? በደሊላ በኩል ሶምሶን ወደማይችለው እነርሱ ግን ወደሚችሉት ሜዳ አወረዱት፡፡ በሚችሉት ሜዳ አውርደው ደኅና አድርገው ቀጥቅጠው ያንን ኃያል ሰው ወፍጮ ፈጭ አደረጉት፡፡
‹‹ብልጥ ከሆንክ አትውረድ፣ ጀግና ከሆንክ የወረዱትን አውጣቸው፡፡አሁን አሁን ብዙ ሰው በዚህ እየተሸነፈብን ነው፡፡ እስኪ ጋዜጣውን፣ መጽሔቱን፣ ፌስ ቡኩን፣ ሰልፉን፣ የፖለቲካ ክርክሩንም ተመልከተው፡፡ ብዙዎቹ ከሜዳቸው ወርደዋል፡፡ ብልጦቹ ከፍ ወዳለው ሃሳብ፣ ዕውቀት ወደሚጠይቀው ክርክር፣ በመረጃና በማስረጃ ወደሚደረገው ውይይት፣ ላቅ ወዳለ ትግል፣ ወደ ልዕልናና ወደ ሠለጠነ አስተሳሰብ ማደግ እንደማይችሉ ያውቁታል፡፡ በዕውቀትና በሃሳብ ክርክር፣ በሠለጠነና ደርዝ ባለው ትግል፤ ማንበብን፣ ማወቅን፣ መመራመርን፣ በሚጠይቅ መሥመር መጓዝ፣ ተጉዘውም ማሸነፍ እንደማይችሉ ያውቁታል፡፡ ስለዚህ አንተን መሰል ሰዎችን ወደ ሜዳቸው ‹ውረድ እንውረድ› ብለው ያወርዷችኋል፡፡ በእነርሱ አጀንዳ፣ በእነርሱ ዐቅም፣ በእነርሱ ተራ ነገር፣ በእነርሱ አሉባልታ፣ በእነርሱ ስድድብ፣ በእነርሱ ጠባብነትና ጎጠኝነት፣ በእነርሱ ወንዘኛነትና መንደርተኛነት፣ በእነርሱ ተረብ ይገጥሟችኋል፡፡ ከዚያም ያሸንፏችኋል፡፡ አሁንማኮ ሁላችንንም አወረዱን፣ እንደነርሱ እንድናስብ፣ እንደነርሱ እንድንጽፍ፣ እንደነርሱ እንድንደራጅ፣ እንደነርሱ እንድንናገር፣ እንደነርሱ እንድንዘፍን፣ እንደነርሱ እንድናምን፣ እንደነርሱ እንድንለብስ አደረጉንኮ፡፡
አትውረድ ልጄ፣ ዕውቀት ዋጋ ወደማታገኝበት፣ ሃሳብ ልዕልት ወደማትሆንበት፣ ችሎታ ወደሚያስቀጣበት አለማወቅ ወደሚያስከብርበት፣ ማይም አለቃ ወደሆነበት፣ ክርክር ተረብ ወደሆነበት፣ ውይይት እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ዓይነት ወደሆነበት፣ አላዋቂዎች ወደሠለጠኑበት፣ ከብት ካለው ይልቅ አፍ ያለው ወደተሾመበት ሜዳ አትውረድ፡፡ ከወረድክ ግን በማታውቀው ሜዳ፣ በማታውቀው ስልት፣ በወረደ ትግል ይደበድቡሃል፡፡ አትውረድ ልጄ፡፡ አትውረድ፡፡

© ይህ ጽሑፍ በራስ ሆቴል ግጥም በጃዝ መድረክ ላይ ቀርቦ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ ታትሞ የነበረ ነው

38 comments:

 1. ብልጥ ከሆንክ አትውረድ፣ ጀግና ከሆንክ የወረዱትን አውጣቸው፡፡

  ReplyDelete
 2. "አትውረድ ልጄ፣ ዕውቀት ዋጋ ወደማታገኝበት፣ ሃሳብ ልዕልት ወደማትሆንበት፣ ችሎታ ወደሚያስቀጣበት አለማወቅ ወደሚያስከብርበት፣ ማይም አለቃ ወደሆነበት፣ ክርክር ተረብ ወደሆነበት፣ ውይይት እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ዓይነት ወደሆነበት፣ አላዋቂዎች ወደሠለጠኑበት፣ ከብት ካለው ይልቅ አፍ ያለው ወደተሾመበት ሜዳ አትውረድ፡፡ ከወረድክ ግን በማታውቀው ሜዳ፣ በማታውቀው ስልት፣ በወረደ ትግል ይደበድቡሃል፡፡ አትውረድ ልጄ፡፡ አትውረድ፡፡"
  Girum new Egziabiher yistilin Deacon Dani.

  ReplyDelete
 3. ወደ ስድቡ ሜዳ አስቦ ስላልገባ አስቦ ሊወጣ አልቻለም፡፡
  Do not play with stupid guys, they let you down and they will beat you with their experience.

  ReplyDelete
 4. An excellent observation. You points are always lessons for me.

  ReplyDelete
 5. ዳኒ ሙት! እንዴት አስተማሪ የሆነ ፅሁፍ መሰለህ ብዙ ተማርኩበት በመምህሩም ራሴን አየሁበት እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶ ይስጥህ.kb z Adigrat

  ReplyDelete
 6. 'ብልጥ ከሆንክ አትውረድ' አሁንማኮ ሁላችንም አወረዱን እንደነርሱ እንድናስብ እንድንጽፍ እንድንደራጅ እንድንናገር ወዘተ አደረጉን
  መልካም እይታ.

  ReplyDelete
 7. a very nice view, as usual!! .... Dani please the back ground makes reading difficult for old people like me

  ReplyDelete
 8. ሰው በሁሉም ነገር ሊቅ አይሆንም፡፡ በአንዱ ሊቅ ሲሆን በሌላው ማይም ነው፤ በአንዱ መምህር ሲሆን በሌላው ተማሪ ነው፤ በአንዱ ጎበዝ የሆነ ለሌላው ሰነፍ ነው››

  ReplyDelete
 9. ብዙቻችን ካለንበት ለመውረድ ቅረብ ነን ልምጣት ግን ዝመናት እየፈጁብን ነው፡፡ ልነገሩ መውለድ ቀላል ነው ክባዱ ምጣቱ ነው፡፡ አዳም ክገነት በሰከነድ እፀበለስ ወረዶ ወደክብሩ ለመመለስ 5500 ዘመን ፈጀበት እስራኤል ክቀያቸው 40ቀን ወተው ለመመለስ 40 ዘመን ፈጀባችው፡፡ ይህ መምርም ለቀፅበት ገብቶ መውጫው ክበድው፡፡ ወገን ስለዚ እነዳነውርድ ነብረታ፡፡ ማንም ይቆመ ቢመስለው እነዳወድቅ ይጠንቀቅ

  ReplyDelete
 10. ብዙቻችን ካለንበት ለመውረድ ቅረብ ነን ልምጣት ግን ዝመናት እየፈጁብን ነው፡፡ ልነገሩ መውለድ ቀላል ነው ክባዱ ምጣቱ ነው፡፡ አዳም ክገነት በሰከነድ እፀበለስ ወረዶ ወደክብሩ ለመመለስ 5500 ዘመን ፈጀበት እስራኤል ክቀያቸው 40ቀን ወተው ለመመለስ 40 ዘመን ፈጀባችው፡፡ ይህ መምርም ለቀፅበት ገብቶ መውጫው ክበድው፡፡ ወገን ስለዚ እነዳነውርድ ነብረታ፡፡ ማንም ይቆመ ቢመስለው እነዳወድቅ ይጠንቀቅ

  ReplyDelete
 11. ብዙቻችን ካለንበት ለመውረድ ቅረብ ነን ልምጣት ግን ዝመናት እየፈጁብን ነው፡፡ ልነገሩ መውለድ ቀላል ነው ክባዱ ምጣቱ ነው፡፡ አዳም ክገነት በሰከነድ እፀበለስ ወረዶ ወደክብሩ ለመመለስ 5500 ዘመን ፈጀበት እስራኤል ክቀያቸው 40ቀን ወተው ለመመለስ 40 ዘመን ፈጀባችው፡፡ ይህ መምርም ለቀፅበት ገብቶ መውጫው ክበድው፡፡ ወገን ስለዚ እነዳነውርድ ነብረታ፡፡ ማንም ይቆመ ቢመስለው እነዳወድቅ ይጠንቀቅ

  ReplyDelete
 12. amilak tigst yisten .

  ReplyDelete
 13. Betam astmari getm new Daniel, Betam Egzier yakberling!

  ReplyDelete
 14. It is an excellent view as usual. God bless you.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks for the nice words. for me all i can say you are of the best person.


   Delete
  2. Thanks for the nice words. for me all i can say you are one of the best person

   Delete
 15. እግዚአብሔር ይስጥህ!

  ReplyDelete
 16. "አንበሳው በገዛ ጫካው ውስጥ ቢሆን ኖሮ ማን ይደፍረው ነበር? ማን ጀግና ነበር ሃምሳ ሳንቲም ከፍሎ በሃምሳ ሜትር ርቀት የሚያየው? ማን ጀግና ነበር ቀርቦ ፎቶ የሚያነሣው?"
  "ሶምሶን ከፍልስጤማውያን ዐቅም በላይ ሲሆንባቸው፡፡ ፍልስጤማውያን ምን አደረጉ? በደሊላ በኩል ሶምሶን ወደማይችለው እነርሱ ግን ወደሚችሉት ሜዳ አወረዱት፡፡ በሚችሉት ሜዳ አውርደው ደኅና አድርገው ቀጥቅጠው ያንን ኃያል ሰው ወፍጮ ፈጭ አደረጉት፡፡"
  ሁሌም ክርክራችን በእውቀት ይሁን፡፡ ያኔ እውነተኛ አሸናፊ እንሆናለን፡፡

  ReplyDelete
 17. I don't like it at all. If we scare to take risk how we can bit our enemy. As we all know that our enemy control everywhere such as work, school, agriculture, Kebele and so on. They have been taken as much as they can. If we say something, you will see us in the jail by next day. It has been 22 years and how long we will continue unless we take risk. To bring light for the next genaration we have to go into dark and fight our enemy until we die. God bless Ethiopia

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't think you're getting what he's talking about, read it again... It's not about being in jail...

   Delete
  2. My friend, what 's "taking risks" got to do with the idea raised in the article? As the previous respondent to your comment, I ask you to read the article again. All Daniel has said in the article was, "Don't get down to the level of those who don't know anything but insults. If you can, try to reason with them, and show them the right way." Trading insults with idiots does not make one smart, it rather creates another idiot.

   Delete
  3. Thank you so much guys for your positive feedback. I read and listen him again and I realized that I understood his message wrongly. Especially the second Anonymous person description was very helpful to me to understand his message. I apologize to Danial and his follower. God bless Danial and Ethiopia.

   Delete
 18. Hello Danial I like your back bround please keep it as it is. It has been uguly for a while.

  ReplyDelete
 19. Dani! . . . alwerrdim!

  ReplyDelete
 20. really genuine looking of socio-political situation of ourselves  ReplyDelete
 21. GOD abezeto yegletsleke!!!

  ReplyDelete
 22. Dani, AMLAKE KIDUSAN yabertak!!!

  ReplyDelete
 23. አትውረድ ልጄ፣ ዕውቀት ዋጋ ወደማታገኝበት፣ ሃሳብ ልዕልት ወደማትሆንበት፣ ችሎታ ወደሚያስቀጣበት አለማወቅ ወደሚያስከብርበት፣ ማይም አለቃ ወደሆነበት፣ ክርክር ተረብ ወደሆነበት፣ ውይይት እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ዓይነት ወደሆነበት፣ አላዋቂዎች ወደሠለጠኑበት፣ ከብት ካለው ይልቅ አፍ ያለው ወደተሾመበት ሜዳ አትውረድ፡፡ ከወረድክ ግን በማታውቀው ሜዳ፣ በማታውቀው ስልት፣ በወረደ ትግል ይደበድቡሃል፡፡ አትውረድ ልጄ፡፡ አትውረድ፡፡"

  ReplyDelete
 24. እግዛብሄር ይባርክህ እድሜህን ያርዝመው

  ReplyDelete
 25. wawo it is so interesting view

  ReplyDelete
 26. ሁሌም ያንተን ብሎግ አንብቤ እውቀት ልዩ እይታን ማስተዋልን እና ተስፋን አገኛለሁ፤፤ እግዛብሄር እድሜ ይስጥልን ሁሌም ያንተን ብሎግ አንብቤ እውቀት ልዩ እይታን ማስተዋልን እና ተስፋን አገኛለሁ፤፤ እግዛብሄር እድሜ ይስጥልን

  ReplyDelete
 27. It is very constructive article.
  Thank you Dani!

  ReplyDelete
 28. Dani Astemari neger new Egziabher yibarkh!!

  ReplyDelete
 29. ሰው በሁሉም ነገር ሊቅ አይሆንም፡፡ በአንዱ ሊቅ ሲሆን በሌላው ማይም ነው፤ በአንዱ መምህር ሲሆን በሌላው ተማሪ ነው፤ በአንዱ ጎበዝ የሆነ ለሌላው ሰነፍ ነው››

  ReplyDelete
 30. ዲያቆን ዳንኤል ረዥም እድሜ ከ ብእርህ ጋር !!!

  ReplyDelete
 31. አትውረድ ልጄ፣ ዕውቀት ዋጋ ወደማታገኝበት፣ ሃሳብ ልዕልት ወደማትሆንበት፣ ችሎታ ወደሚያስቀጣበት አለማወቅ ወደሚያስከብርበት፣ ማይም አለቃ ወደሆነበት፣ ክርክር ተረብ ወደሆነበት፣ ውይይት እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ዓይነት ወደሆነበት፣ አላዋቂዎች ወደሠለጠኑበት፣ ከብት ካለው ይልቅ አፍ ያለው ወደተሾመበት ሜዳ አትውረድ፡፡ ከወረድክ ግን በማታውቀው ሜዳ፣ በማታውቀው ስልት፣ በወረደ ትግል ይደበድቡሃል፡፡ አትውረድ ልጄ፡፡ አትውረድ፡፡"

  ReplyDelete