Sunday, January 26, 2014

በዐረብ ፔኒዙኤላ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልትታነጽ ነው


 click here for pdf

በመካከለኛው ምሥራቅ ከእሥራኤልና ቤይሩት ቀጥሎ ሦስተኛዋ፣ በዐረቢያ ፔኑዙኤላ ደግሞ የመጀመሪያዋ የምትሆነው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በኳታር ምድር ልትታነጽ ነው፡፡ 
በኳታር ምድር የዛሬ አሥር ዓመት ለጸሎትና ለትምህርት መሰባሰብ በጀመሩ ወንድሞችና እኅቶች የተጀመረችው የኳታር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ወደ አካባቢው ለሥራ የሚጓዙ ምእመናንን በማሰባሰብና በማገናኘት፣ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋትና ክርስቲያናዊ ማኅበራዊ ኑሮን በማጠናከር የምትታወቅ ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋ አገልግሎቷን የምትፈጽመው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲሆን በዓረቡ ዓለም እንደተለመደውም ዘወትር ዓርብ ከሰዓት በኋላ የቅዳሴና የትምህርት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የኳታር ቅድስት ሥላሴ ምእመናን የሥራ ጫናውን ሁሉ ተቋቁመው ተግተው በማገልገል ብቻ ሳይሆን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው በማስጠበቅም የሚታወቁ ናቸው፡፡
በአብዛኞቹ የዓረበ ሀገሮች እንዳሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በኳታር ለነበረችው ቤተ ክርስቲያንም ዋና ፈተና የነበረው የራስዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን አለመኖር ነው፡፡ ይህም አገልግሎቷን በሳምንት ወደ ተወሰኑ ቀናትና ሰዓታት ከማሳነሡም በላይ፣ ምእመናን የሚፈልጓቸውን ሁሉን አገልግሎቶች ለመስጠት እንዳትችል አድርጓት ነበር፡፡ ለቤተ ክርስቲያንዋ የራስዋ ሕንጻ መሥሪያ ቦታ በመፈለግ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ የነበረው የሰበካ ጉባኤ ባሳለፍነው ሳምንት በዐረቡ ዓለም የመጀመሪያ የምትሆነውን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት የሚያስችል መሬት ተረክቧል፡፡ 
እስካሁን ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየመን፣ በዓረብ ኤምሬትስ፣ በባሕሬን፣ በኩዌት፣ በሊባኖስና በግብጽ የራስዋ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሯትም በራስዋ ገንዘብ የተሠራና ንብረትነቷ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ግን ከእሥራኤልና ቤይሩት በቀር አልነበራትም፡፡ የኳታር ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከተሠራ በመካከለኛው ምሥራቅ ሦስተኛው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ‹ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን› ይሆናል፡፡
በኳታር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ መሠራት ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል፡፡ በአንድ በኩል የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን አገልግሎት ከሳምንት እስከ ሳምንት የማያቋርጥ እንዲሆን ሲያደርገው በሌላ በኩል ደግሞ በአካባቢው ላሉት ሌሎች አጥቢያዎችም አርአያነት ይኖረዋል፡፡ ከኳታር በፊት እንቅስቃሴ የጀመሩት እንደ አቡዳቢ መድኃኔዓለም ያሉትን አጥቢያዎች የጀመሩትን በርትተው እንዲፈጽሙ ያነሣሣቸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያነት ታሪክ በዐረቢያ ፔኒዙኤላ የነበረው ቤተ ክርስቲያን ከ1400 ዓመታት በፊት በየመን ናግራን ታንጾ የነበረው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነበር፡፡ እርሱ ከጠፋ ከ1600 ዓመታት በኋላ በዓረቢያ ፔኑዚኤላ ሁለተኛው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በቅድስት ሥላሴ ስም እንደገና በኳታር መታነጹ የታሪኩ ተገጣጣሚነት የሚያስደንቅ ነው፡፡
ይህ ቤተ ክርስቲያን በአንድ በኩል ታሪካዊ፣ በሌላ በኩል የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ተልዕኮ ወደ አንድ ምዕራፍ የሚያሸጋግር፣ ሲሠልስም ለሌሎች አርአያነት ያለው በመሆኑ ሥራ በኳታር ለሚገኙ ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ ግብጻውያን እንደዚህ ባሉ አካባቢዎች የሚታነጹ የተለየ ታሪክና ጠቀሜታ ያላቸውን አብያተ ክርስቲያናት በመተጋገዝ እንደሚገነቧቸው ሁሉ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም እያንዳንዷን የሕንጻዋን ብሎኬት ተካፍለው በመገንባት በታሪክ ምዕራፍ ላይ አሻራቸውን ማስቀመጥና በረከት ማግኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡

 በሀገር ቤት፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በአውስትራልያ የሚገኙ ምእመናን በአካባቢያቸው ቤተ ክርስቲያን ባይኖር ነድተውም ሆነ ተሳፍረው ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ ቤተ ክርስቲያን መገልገል ይችላሉ፡፤ በዐረቡ ዓለም ግን በአንድ አካባቢ አንድ አጥቢያ ብቻ ስለሚገኝ ወጣ ብሎ በሌላ አጥቢያ መገልገል አይቻልም፡፡ በተለይ ደግሞ እንደ ኳታር ባሉ ሀገሮች ያለው ቤተ ክርስቲያን አንድ ነው፡፡ ይህን ቤተ ክርስቲያን ማነጽና አገልግሎቱን ማጠናከር፣ በዐረቡ ዓለም የሚገኙ ወገኖቻችን በመንፈሳ ሕይወታቸው በርትተው፣ ከመንፈስ ጭንቀት ተላቅቀው፣ የሚደርስባቸውን ፈተናም አሸንፈው ለሀገራቸውና ለወገኖቻቸው የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡ በመሆኑም በመላው ዓለም የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሚታነጸው የራሳቸው አጥቢያ መሆኑን አስታውሰው ልባቸው ኳታር ሊሆን ይገባል፡፡ 
 
የገባው ክርስቲያን እግዚአብሔር ሲሠራ አብሮ ይሠራል፡፡ 


ዶሃ፣ ኳታር

24 comments:

 1. Yetselotu guday endayiresa, wanaw ersu newuna! hulum kiristian betselot ysibachew (genzebu endale hono malete new).

  Lefitsame beqto yasayen!

  ReplyDelete
 2. እኛ እንነሳለን እግዚአብሄር ያከናውንልናል ደግሞም አከናወነልን

  ReplyDelete
 3. selam wendem Danial yehe lemejemereya geze yemelew post Sehetete Naw Lemejemereya Geze Bet Kereseteyan Areb Hager yeteseraw Lebanon Naw Ena Yehenene Matsarat Yegebal beye Asebalehu yebetekereseteyanuam sem " Be Birut Lebanos Yedeberesena Kidus Geberial catederal betekereseteyan..yebalale ..

  ReplyDelete
 4. ሰው ያስባል እግዚአብሄርም ይፈጽማል::

  ReplyDelete
 5. Selam D/n Dani, I'm very proud of these true Ethiopian Orthodox sisters and brothers.

  ReplyDelete
 6. አዎ! ቸር ወሬ ያሰማን፡፡ ለአንተም በረክቱን ያብዛልህ፡

  ReplyDelete
 7. "ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል" የማቴዎስ ወንጌል 24:14

  ReplyDelete
 8. "ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል" የማቴዎስ ወንጌል 24:14

  ReplyDelete
 9. belocet megzat yemiyasechel cupon bizegaje.

  ReplyDelete
 10. Good news! And thanks for your information!

  ReplyDelete
 11. I don't think so this is good idea. We have many old churches in Ethipia that need rebuild so investing in other country is west of money. They can rent one building to give service. Please rethink about this church before you build or buy.

  ReplyDelete
 12. በእውነት በጣም ደስ የሚል ነው ሰው ያስባል እግዚአብሔር ይፈጽማል።ለእኛም በፐርዝ የቅድስት ሥላሴ በ/ክ የደረሰብንን ትንሽ ጻፍ ጻፍ ብታደርግልንና የተበደልነውን በደል ለመላው ህዝበ ክርስቲያን ብትገልጽልን እንዴት ጥሩ ነው እንላለን ጉዳዩን በደንብ አንተ ስለምታውቀው

  ReplyDelete
 13. Yetewetene sayifetsem xyikeremena Yeabatochachin amlak yimesgen. amlakachin wetane kulu fetsame kulu newina!!!

  ReplyDelete
 14. " እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ። " ኤፌ5:27

  "That he might present it to himself a glorious church, not having spot, or wrinkle, or any such thing; but that it should be holy and without blemish." Ephesians 5:27

  ReplyDelete
 15. betami desi yilali yasefan amlaki yimesigen.

  ReplyDelete
 16. dibora elias kemalJanuary 28, 2014 at 6:12 PM

  Dn ,Dani egzeabher abzto yebarki 4tu hayalan metsehafin satiz endematmeta amnalew tadia minew zim alk??

  ReplyDelete
 17. thanks for information

  ReplyDelete
 18. oh...i feel too happy!!!only i say, Thanks to God.

  ReplyDelete
 19. God bless you Dn.Daniel for the sharing of this kind evilical history of Ehiopian orthodox church.

  ReplyDelete
 20. እጅግ የሚያስደስት ነው። እግዚአብሄር ስራውን ባርኮ ለመፈፀም ያብቃው።

  ReplyDelete
 21. እጅግ የሚያስደስት ነው። እግዚአብሄር ስራውን ባርኮ ለመፈፀም ያብቃው። gena bizu yisral

  ReplyDelete
 22. ቤተ ክርስቲያኑ መገንባተዋ መልካም ነው ነግር ግን በሀገራችን በአክሱም መስጊዶች እንዳይገነቡ የእስልምና ተከታይ ጸሓይና ውርጭ እየተፈራረቀባቸው በረንዳ ላይ እየሰገዱ ይገኛሉ፡፡በሃገራቸው የእምነት ተቋማቸውን እንዳይመሰርቱ እንቅፋት እየሆንባቸው በኳታር ለመገንባት የታሰበ ቤተ-ክርስቲያን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ፡፡ ስለዚህ ዳንኤል በዚህ ላይ ምን ትላለህ

  ReplyDelete