click here for pdf
ልጁ አባቱን ሊጠይቅ ነበር የመጣው፡፡ ሐኪም ነው፡፡ ሐኪም ደግሞ በመንደሩ የተከበረ
ነው፡፡ እርሱ መጣ ሲባል በመንደሩ የነበሩ ሕሙማን ሁሉ የአባቱን ቤት ሞሉት፡፡ ብዙዎቹ እንዲሁ አይቶ በሽታቸውን የሚያውቅላቸው
ስለሚመስላቸው ‹‹ምንዎትን ነው ያመመዎት›› የሚለው ጥያቄ ግራ አጋብቷቸዋል፡፡ ‹‹ያመመኝን ካወቅኩትማ ምን ችግር ነበረበት፤
በሽታዬን ሊነግረኝ አዶለም እንዴ ሐኪም የሆነው›› ይሉታል ከቤት ከወጡ በኋላ፡፡
አባቱ አንድ ቀን እንዲህ አሉት ‹‹ድሮ ትዕግሥተኛ ነበርክ፤ አሁንኮ በረባ ባልረባው
ትነጫነጫለህ፤ ያሳደጉህን ሠፈርተኞችህን ሁሉ ትሰድባቸዋለህ፡፡ ደግሞ አንዳንዱ በሽታ አዲስ ሆኖብሃል፡፡ ድሮኮ ‹እጁ መድኃኒት
ነው›› ትባል ነበር፡፡ ቀንና ሌሊት ሠርተህ አይደክምህም ነበር፡፡ እንግዳ ነገር እንኳን ሲገጥምህ ጓደኞችህን ለመጠየቅ በስልክ
ስታጨናንቃቸው ነበር የምታመሸው፡፡ አሁን ምነው ያለ ጊዜህ አረጀህ ልጄ›› አሉት፡፡
አሁን አዲስ ነገር የሆነበት አባቱም ተመሳሳይ ነገር መናገራቸው ነው፡፡ ለወትሮው
‹ዓይኔ ብርሃኔ› እያሉ ለመጣ ለሄደው ስለ እርሱ እየተረኩ ሰው የሚያሰለቹት አባቱ ዛሬ ለራሱ ቅሬታቸውን መንገራቸው አዲስ
ታሪክ ሆኖበታል፡፡ መንደርተኞቹን ካከመ በኋላ በቤት ውስጥ ቡና ተፈልቶ ምርቃትና ምስጋና ይዥጎደጎድ እንዳልነበረ፣ ዛሬ
‹‹ምነው ልጄ›› የሚል ስሞታ መጣበት፡፡
ለአባቱ አልመለሰላቸውም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ እርሳቸውን ካዳመጣቸው በኋላ ቀጥሎ ውስጡን
ነበር የሚያዳምጠው፡፡ ሥራ እንጨት እንጨት ብሎታል፡፡ ሞያው ሐኪም መሆኑ ትዝ የሚለው ሰዎች ‹ዶክተር› ብለው ሲጠሩት ነው፡፡
ስብሰባው፣ ሴሚናሩ፣ ደብዳቤው፣ ንግግሩ ሁሉ የቢሮክራሲ እንጂ የሞያ አይደለም፡፡ የሚያደንዝ እንጂ የሚስል አልሆነም፡፡
የሚያስረሳ እንጂ የሚያነቃ አልሆነም፡፡
‹‹ልጄ›› አሉት አባቱ ከረዥም ዝምታ በኋላ፡፡
‹‹አቤት›› አላቸው ከተጓዘበት በፍጥነት ተመልሶ፡፡
‹‹ለመሆኑ ሞያህን ለማሳደግ ልምምድ ታደርጋለህ? ከወዳጆችህ ጋር ትወያያለህ? ሌላ ቦታ ሄደህ ልምድ ትቀስማህ? ታነባለህ? እንደገናስ ትማራለህ?
በጎንደር መምህር ኤስድሮስ የሚባሉ መምህር ነበሩ አሉ፡፡ መጻሕፍቱን ሁሉ መርምረው ትርጓሜ አቅንተው ሲያስተምሩ ኖሩና
‹ምናልባት ያልደረስንበት አዲስ ነገር ቢኖርስ› ብለው በዚያ በጣና ገዳማት ውስጥ ገብተው መጻሕፍቱን ሁሉ ሲያገላብጡ ኖሩ
አሉ፡፡ እውነትም ያልደረሱበት ብዙ ነገር ቢያገኙ ተማሪዎቻቸውን እንደገና ጠርተው ‹እኔም ያላወቅኩት እናንተም ያልተማራችሁት
አዲስ ነገር አግኝቻለሁና ኑ እንደገና እንማር› ብለው ሰበሰቧቸው፡፡ እሺ ብለው ለአዲስ ዕውቀት የመጡ አሉ፡፡ እምቢ ብለው
በቀድሞው ብቻ የቀሩ አሉ፡፡ እሺ ብለው የመጡት የሄዱበት መንገድ ‹የታች ቤት ትርጓሜ› ተባለ፡፡ እምቢ ብለው የቀሩት የሄዱበት
መንገድ ደግሞ ‹የላይ ቤት ትርጓሜ› ተባለ፡፡ ለመሆኑ አንተስ ምናልባት ያልደረስኩበት ነገር ቢኖር፤ አዲስ የመጣ ነገር ቢኖር፤
ማወቅ ሲገባኝ ሳላውቀው የቀረሁት ነገር ቢኖር ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ዕውቀትኮ ካልጨመሩበት አንድም እየዛገ አንድም እየጠፋ ይሄዳል፡፡ ትዶለዱማለህ ልጄ፡፡ አንድ ምሳሌ ልንገርህ ፡-
‹ሰውዬው ሥራ ፍለጋ ሲንከራተት ወደ አንድ የጣውላ ፋብሪካ ይደርስና ይጠይቃል፤
ሰውነቱ ግዙፍና ጠንካራ መምሰሉን ይመለከትና ባለቤቱ እንዲገባ ይጋብዘዋል፡፡ ያላቸው የሥራ መስክ እንጨት ቆራጭነት መሆኑን
ይነግሩታል፡፡ ሰውዬውም ያገኘውን ሁሉ ለመሥራት ታጥቆ የተነሣ ነበርና ተቀበለ፡፡ የተወሰነ ሰዓት በመጥረቢያ እንዴት ዛፍ እንደሚቆረጥ
አሠለጠኑትና ወደ ሥራው ተሠማራ፡፡ ክፍያው በቆረጠው ዛፍ ልክ ነበር፡፡
በመጀመሪያው ቀን ሃያ ዛፍ ቆረጠና ጥሩ ክፍያ አገኘ፡፡ በዚህ ደስ ብሎት በማግሥቱ
ተነሥቶ ወደ ሥራው ገባ፡፡ በዚያ ቀንም ዘጠኝ ዛፍ ቆረጠ፡፡ በሦስተኛው ቀን ሰባት፣ በአራተኛው ቀን ስድስት፣ በአምስተኛው ቀን
አምስት፣ በስድስተኛው ቀን አራት ቆረጠ፡፡ ድካሙ ያው ነው፡፡ የሚቆርጠው ዛፍ ግን እያነሰ ሄደ፡፡ ዛፉ ሲያንስም ክፍያው
አነሰው፡፡ ለዕለት ምግቡ እንኳን አልበቃው አለ፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ቆረጠ፡፡
ወደቀጠረው ሰው ዘንድ ሄደና ሥራን ለማቆም እንደሚፈልግ ነገረው፡፡ ‹‹ለምን
ታቆማለህ፤ ክፍያው አልተስማማህም?›› አለው፡፡ ‹‹ሂሳቡ በቂ
ነው፤ ነገር ግን ብዙ ዛፍ በአንድ ቀን ለመቁረጥ አልቻልኩም፡፡ ካደር አደር እየቀነስኩ መጣሁ፡፡ በዚያውም ልክ የሚከፈለኝ
ገንዘብ እየቀነሰ ሄደ፡፡ አሁን ችግር ውስጥ ከመውደቄ በፊት ሥራውን ለማቆም ወሰንኩ›› አለው፡፡
አሠሪውም ‹በመጀመሪያ ስንት ዛፍ ነበር የቆረጥከው?›› አለው፡፡
‹‹አሥር››
‹‹በመጨረሻስ?››
‹‹አራት››
‹‹ለመሆኑ መጥረቢያውን ስለህው ታውቃለህ?›› አለው፡፡
‹‹ኧረ በጭራሽ›› አለ ቆራጩ፡፡
‹‹ታድያ ምን አድርግ ነው የምትለው፡፡ በመጀመሪያ ቀን የተሳለ መጥረቢያ ሰጥተንህ
ስለነበር አሥር ቆረጥክበት፡፡ በየቀኑ በሠራህበት ቁጥር እየዶለዶመ ስለሚሄድ በመጨረሻ አራት ላይ ደረስክ፡፡ ብትቀጥል ደግሞ
አንድ ዛፍ መቁረጥ የማትችልበት ደረጃ ላይ ትደርስ ነበር፡፡ በሠራህ ቁጥር መጥረቢያውን እንደገና መሳል አለብህ፡፡ ሁልጊዜም
አዲስ ሆኖ ሌላ ዛፍ ለመቁረጥ እንዲችል በየጊዜው መሳል አለብህ፡፡ አሁንም ሂድና እንደዚያ አድርግ›› ብሎ አሰናበተው፡፡
‹‹አየህ ልጄ አእምሮም እንደዚያው ነው፡፡ በየጊዜው መሳል ይፈልጋል፡፡ እንደገና
መማር፣ እንደገና ማንበብ፣ እንደገና መሠልጠን፣ እንደገና ሞያ መለማመድ ይፈልጋል፡፡ ያለበለዚያማ የዛሬ ስንት ዓመት በተማርከው
ከተቀመጥክ ትዶለዱማለህ፤ መጥረቢያውኮ አልጠፋም፡፡ አልተለወጠም፡፡ አሁንም መጥረቢያ ነው፡፡ ግን ስለቱ ቀነሰና አገልግሎቱ
ደከመ፡፡ አንተምኮ አሁንም ሐኪም ነህ፤ አልተለወጥክም፡፡ ግን ትዶለዱምና ውጤታማነትህ ይቀንሳል፡፡
ስለዚህ ልጄ ሂድና ተሳል፤ በየጊዜውም ተሳል፤ በሠራሀ ቁጥር ተሳል፤ አዲስ ዛፍ
ለመቁረጥ መጥረቢያው መሳል እንዳለበት ሁሉ፤ አዲስ ችግር ለመፍታት፣ አዲስ ሃሳብ ለማመንጨት፣ አዲስ መንገድ ለማግኘት፣ አዲስ
ሕመም ለመፈወስ እንድትችል ሂድና አንተም ተሳል›› አሉት፡፡
ጉልበታቸውን ስሞ ቀና ሲል ግንባሩን ሳሙት፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው
What a lesson!!
ReplyDeleteWow you got me Dani,may God bless the rest of your life..
ReplyDeleteThank you Deacon Daniel, for remembering us a critical issue in our life.
ReplyDeleteGod bless you, I love it so much.
ReplyDeleteDanniye,Tebarek !!! you feed us always.
ReplyDeletethank you Dani berta!
ReplyDeleteGood advise! God bless you Dn Daniel! Keep your contribution for this brilliant generation!
ReplyDeleteThank you Dn. Daniel. This is really a good lesson for all of us.
ReplyDeleteYeteshtut Abat bikatetu
ReplyDeleteThank you deacon danie for yourlesson.God bless you.
ReplyDeleteit is real.tnx. d/n daniel
ReplyDeleteThank you Dn Daniel , specially it is a good lesson for most of the government officers and teachers who took a certain skill and position till their time of retirement.
ReplyDeleteWow its nice lesson thanks.
ReplyDeleteአዲስ ችግር ለመፍታት፣ አዲስ ሃሳብ ለማመንጨት፣ አዲስ መንገድ ለማግኘት፣ አዲስ ሕመም ለመፈወስ እንድትችል ሂድና አንተም ተሳል
ReplyDeleteThank u deacon Daniel, I am so surpraised and initiated to do it
ReplyDeleteDn. Daniel tsuhufu ke Ante "blog archive" gara ymesaselal. yhnnm yemlew tsuhufochn slemwedachew new; ena metsafun abzteh ketl.
ReplyDeleteInen new??
ReplyDeleteas usual you are a supper genius! but your lesson for today is for me!!!! and for those working @ universities being both instructors and managers. if you have their address please send to them, lov u
ReplyDeleteIt's really impressing. I have no words to express my appreciation to you. God bless you.
ReplyDeleteበሠራህ ቁጥር መጥረቢያውን እንደገና መሳል አለብህ፡፡ ሁልጊዜም አዲስ ሆኖ ሌላ ዛፍ ለመቁረጥ እንዲችል በየጊዜው መሳል አለብህ፡፡ አሁንም ሂድና እንደዚያ አድርግ›› ብሎ አሰናበተው፡፡
ReplyDelete‹‹አየህ ልጄ አእምሮም እንደዚያው ነው፡፡ በየጊዜው መሳል ይፈልጋል፡፡ እንደገና መማር፣ እንደገና ማንበብ፣ እንደገና መሠልጠን፣ እንደገና ሞያ መለማመድ ይፈልጋል፡፡ ያለበለዚያማ የዛሬ ስንት ዓመት በተማርከው ከተቀመጥክ ትዶለዱማለህ፤ መጥረቢያውኮ አልጠፋም፡፡ አልተለወጠም፡፡ አሁንም መጥረቢያ ነው፡፡ ግን ስለቱ ቀነሰና አገልግሎቱ ደከመ፡፡ አንተምኮ አሁንም ሐኪም ነህ፤ አልተለወጥክም፡፡ ግን ትዶለዱምና ውጤታማነትህ ይቀንሳል፡፡
ዋው ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡
God bless you & your family.
ReplyDeleteOn the shadow of leaving the work and joining the NGO are many reasons. On our country situation most of the reasons are acceptable. One of the main reason is economy. A doctor in Government hospital at its upper maxi mun earns 6,000 ETB / 300$US/. To rent a house on his standard minimum he needs 2000 ETB /100 US$/. For transportation he costs not less than 500 ETB / 25 US$/ . For food consumption he needs 1,500ETB /75 US$/. For cloth and miscellaneous leaving costs he needs minimum of 10% of his salary. At the end his cost will be 4,600ETB/ 230 US$/. Considering his extended families interest Zero what is left is 1,400 ETB /70 US$/. In ten years he will have 168, 000 ETB / 8,400 US$/, unable to buy a house, or a car.
ReplyDeleteUnder the same condition of the current market to save the country I propose the following monthly salary for the top officials
Ministres ------------------- 80,000 ETB
For Deputy Ministers --- 70,000 ETB
For Regional Presidents --- 75,000ETB
For office heads / Bureau Halafie/ ---- 50,000ETB
For deputy office heads --------- 40,000ETB
ETC
This might be the first solution for the case and relevant million cases.
i love the idea but I disagree abotut reason why the naming of Tache bet and Lay bet comes ,according to Yohannes G/Mariam(M.A.T)kirstina be Ethiopia kifel 2 page 101.
ReplyDeletegrum newa! berta
ReplyDeleteBrother in Jesus, I see that you do the same for yourself to show us always with new brilliant and inspiring ways of life. May God bless you.
ReplyDeleteIt is really a good advice May God bless u ...
ReplyDeletewhat can I say?.......................just THANK YOU!!!! God bless you and your family ever.
ReplyDeleteምክር ከድሃ ነበርሽ ማን ቢሰማሽ አሉ!
ReplyDeleteየአበውን ምክር ብንሰማ የትና የት በተተኮስን ነበር! እንደ ፍራሽ አዳሽ ራስህን አድስ እንደ ንስር ታደስ ተሳል አሉ አባቱ!
ማይጽፍ ደብተራ ክንፍ የሌለው አሞራ አሉ! ዳንኤል ክብረት ድንቅ ሰው ነህ እያሉ ብዙ ሰዎች ያሙሃል አሉ! ልታወቅ አይል እዉቅ እከብር አይል ክቡር ነው! በነጻ እውቀትን ሰጥቶናልና!
ዘወትር ቅዳሜ በክቡር ዳንኤል ክብረት ብዬ ጽሁፍህን በፌስ ቡኬ እንደማወጣው ብዙ ሰውም ሼር እንደሚያደርገው ይታወቅልኝ!
10q dani
ReplyDeleteD.D it is a good observation
ReplyDeletethank you
ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ የዘመኑ ሰው ችግር ይህ ነው፡፡ አንድ ጊዜ በተማረው ብቻ በዚያውም አስቦት ሳይሆን በአጋጣሚ አዋቂ፣ ሊቅ፣ ምሑር፣ ተመራማሪ …. እየተባለ እንዲጠራ ብቻ ይፈልጋል፡፡ እስከመቸ ዘመኑ እየተለወጠ፣ ትውልዱ እየቀደመው፣ ነገሮች ሁሉ ውስብስብ በሆኑበት እርሱ እኛ ስንማር፣ እኛ ስናስተምር፣ …. እያሉ ብቻ ዛሬም ማውራት፣ ነገም ማውራት ብቻ መለወጥ ባንተ አገላለጽ መሳል የለም ሁላችንም ለለውጥ ማንበብ፣ ለለውጥ መማር ያስፍልጋል ካልሆነ ያልቃል፡፡
ReplyDeleteዳንኤል በአሁን ግዜ ለእውቀት ከማንበብና ለመልካም ነገር ከመጨነቅ ይልቅ ወንዱ(ሁሉም ኣይደሉም) የነጭን ፋሽን ቂጥ እያሳዩ መሄድን: ሴቶች(አሁንም ሁሉም ሴቶች አይደሉም) ግልገል ሱሪያቸውንና ገላቸውን በቆራጣ ቀሚስ እያሳዩ ለመሄድ የሚያደርጉት ጥናትና ኩረጃ ያየለበት ግዜ ላይ ነው ያለነው:: ለዚህ ሁሉ ተጠያቁው የኢህአዴግ መንግስት ነው: ትውልድ ማንነቱን እንዲያጣ ጠንክሮ እየሰራ ያለ::
ReplyDeleteወይ ዳኒ ሁሌ የሚናፍቀንን የአበው ጨዋታ አዘል ወጎች ካንተ ጦማር ላይ ስናይ እንዴት ደስ እንደሚለን ከሃገር ቤት ያልራቅን ይመስለናል እውነትም ከቀን ወደ ቀን በሚዘለው የጊዜ ምህዳር ምን እማራለው እንዴት እራሴን ወደ ተሻለ ነገር እቀይራለው ብሎ ማሰብ ያለብን እንደሆነ ነው ያስነበብከን የሰው ልጅ ልብ እንደ አሎሎ በጠነከረበት ዘመን፣የማያውቀውን አውቃለው ባይ በበዛበት ዘመን፣ነገሮች እንደ ድመት አይን ተለዋዋጭ በሆኑበት ዘመን፣ቴክኖሎጂው እርስ በእርሱ በተበላላበት ዘመን አውቃለው ብሎ መቀመጥ እንደማያኩራራ አስተማርከን እኛ አንጋፋው የሃገራችን ደራሲም አይደል እንዴ “መልህቅ በውሃ ውስጥ ብዙ አመት በኖረ ተዘፈዘፈ እንጂ መች ዋና ተማረ” ያሉን እውነትም ከመዘፍዘፍ አድኖን በጥሩ ነገር እንድንሳል ያርገን ይኸው እኔማ ሞረዱ ጠፍቶብኝ እንዳለው አለው በል ቸር ሰንብትማ።
ReplyDeleteit is very interesting.....ilike it and it is a good lesson
ReplyDeleteits an interesting advice. Daniel egezer yebarkehe.
ReplyDeleteWow! Egziabher Yisteh!!
ReplyDeleteMay God Bless you
ReplyDeleteለዚህ ልጄ ሂድና ተሳል፤ በየጊዜውም ተሳል፤ በሠራሀ ቁጥር ተሳል፤ አዲስ ዛፍ ለመቁረጥ መጥረቢያው መሳል እንዳለበት ሁሉ፤ አዲስ ችግር ለመፍታት፣ አዲስ ሃሳብ ለማመንጨት፣ አዲስ መንገድ ለማግኘት፣ አዲስ ሕመም ለመፈወስ እንድትችል ሂድና አንተም ተሳል›› አሉት፡፡ I Have too. tnx
ReplyDelete