Monday, January 20, 2014

ለቤተ መጻሕፍትዎ - የሚያስታውሱን አይጥፉ

ሰሞኑን ኤፍሬም ሥዩም ያዘጋጀውን ‹ተዋነይ -ብሉይ የግእዝ ቅኔያት ፍልስፍና› የተሰኘ መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ አንዳንድ ‹ጻፍን› ብለው የሚያስቡ የኔ ብጤዎች የጥንቱን ሁሉ እንደ አሮጌ በሚያዩበት ዘመን ኤፍሬምን የመሰለ አስተዋሽ ማግኘት መታደል ነው፡፡ ባለማወቃችን ምክንያት የለንም ልንል ስንነሣ፣ እንዲህ የሚያስታውሱን አይጥፉ፡፡
ቀደምት ኢትዮጵያውያን ፈላስፎች ሃሳቦቻቸውን የገለጡባቸውን የግእዝ ቅኔያት በግጥም መልኩ እየተረጎመ ግራና ቀኝ አድርጎ አቅርቦልናል፡፡ ኤፍሬም የግእዝ ቅኔያቱን የሰበሰበበት መመዘኛው ፍልስፍና ነክነት ይመስለኛል፡፡ ሊቃውንቱ ከምድር እስከ ሰማይ ያሉ ፍጡራንንና ኃያላንን የሞገቱበትንና የመረመሩበትን መንገድና ምጥቀት እናያለን፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ 83 የግእዝ ‹ቅኔዎች› ቀርበዋል፡፡ አንዳንዶቹን አንብባችሁ ስትገረሙ ልትውሉ ትችላላችሁ፡፡

ለምሳሌ እንዲህ ያለውን የአለቃ ገብረ ሐና ቅኔ ስታዩ፡-
ኮንኖ ኃጥኣን ክርስቶስ ኢይደልወከ ምንተ
አፍቅሩ ጸላዕተክሙ እስመ ትብል አንተ
አንዳንዶቹን አንብባችሁ ደግሞ ስትመሰጡ ታነጋላችሁ፤
እንዲህ የሚሉትን ስታነቡ፡-
ሙሴ ፈጠረ ፈጣሪሁ፣
ወፈጣሪ ፈጠረ ኪያሁ፤
አንዳንዶቹ እንደገና እንደገና እንድትመራመሩ ያደርጓችኋል፤
ባሕቲቶ ነቢረ እግዚአብሔር ፈርሀ
እም ኢሀልዎ ንዋም እስመ ዓለመ አንቀሐ
አንዳንዶቹም ብቻችሁን እያወራችሁ እንድትሄዱ ያደርጓችኋል፡-
እመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብአ ዛቲ ዓለም ይጸልዑኒ፣
ወከመ ኢይንብብ ሐሰተ ኩነኔ ዚአከ ያፈርሀኒ፣
እም ኩሉሰ አርምሞ ይኄይስ ወይሤኒ
በውጭው ዓለም አንድን ዕውቀት ለመረዳት ይቻል ዘንድ በየፈርጁ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ የኤዞፕ ተረቶች አንድ ዓይነት ቢሆኑም በልዩ ልዩ ዘርፎች እየተዋቀሩ እንደገና እስካሁን ይቀርባሉ፡፡ ኤፍሬም ለግእዝ ቅኔያት ይህንን መንገድ አመላክቷል፡፡ ፍልስፍናውያን፣ ታሪካውያን፣ መንፈሳውያን፣ ትርጓሜያውያን፣ ዶግማውያን፣ ወዘተ እያልን በየዘርፉ ልናያቸውና በሚገባ ልናውቃቸው እንደምንችል አመላክቷል፡፡
ባይሆን ኤፍሬም ለወደፊቱ የቅኔዎቹን ታሪካዊ ዳራ በግርጌ ማስተዋሻ በኩል ጣል ቢያደርግልን የኔ ብጤዎች በሚገባ ለመረዳት በር ይከፍትልናል፡፡ በመጽሐፉ መጀመሪያ ሊቀ ኅሩያን በላይ እና ራሱ ኤፍሬም የጻፏቸው መቅድሞችም የቅኔዎቹን ያህል ተወደውና ልብ ገዝተው የሚነበቡ ናቸው፡፡
ይህንን በ190 ገጽ የተጠቃለለ፣ በ100 ብር የሚሸጥ፣ በሻማ ቡክስ የታተመ መጽሐፍ ታነቡት ዘንድ እየጋበዝኩ እስኪ ይኼን ቅኔ ፍቱ
ድንግል ወለት ትመስለነ ዕቤርተ
አኮኑ ትውዕል እንዘ ተሐቅፍ እሳተ
መልካም ንባብ፡፡ 

21 comments:

 1. እመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብአ ዛቲ ዓለም ይጸልዑኒ፣
  ወከመ ኢይንብብ ሐሰተ ኩነኔ ዚአከ ያፈርሀኒ፣
  እም ኩሉሰ አርምሞ ይኄይስ ወይሤኒ

  ReplyDelete
 2. I couldn't wait to have this book! tnx daniel for your recomendation.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ህጻነ ዕድሜ ደንኤል ለአረጋዊ ውሉዱ
   ይተግህ ለለመዋእሉ መግቦ አዝማዱ
   ሕብስተ ሕይወት ምስጢረ ጣዕማዌ ከመ ክርስቶስ አሐዱ።

   Delete
 3. Dani, you should have put the translations as well.

  ReplyDelete
  Replies
  1. He don't know it,what do you
   expect from him.

   Delete
  2. You pot head! Why don't you write a single word? Afraid of how readers will laught at you?

   Delete
 4. good D/n Daniel. but I can not Translate it.can I teach geez beyond the age of 36?

  ReplyDelete
 5. ድንግል-ወለት= ምሳሌ፣ ወለት፡- ሰም፣ ድንግል፡- ወርቅ
  ሴት ልጅ ድንግል (ማርያም) ሥራ ፈት ባልቴትን ትመስላለች፤ እሳትን ታቅፋ ውላለችና።
  ሰሙ፡- ሥራ መሥራት ያልቻለች (የደከመች) ባልቴት አሳት ዳር ቁጭ ብላ ጊዜዋን ታሳልፋለች።
  ወርቁ፡- እመቤታችን ድንግል ማርያም አሳተ መለኮት ጌታን በማኅጸንዋ መሸከምዋን መናገር ነው።

  ReplyDelete
 6. ድንግል-ወለት= ምሳሌ፣ ድንግል= ወርቅ፣ ወለት= ሰም
  ሰሙ ድንግል ማርያም፣ ከመድከምዋ የተነሳ እሳት ታቅፋ (እሳት ዳር ተቀምጣ) የምትውል ባልቴትን ትመስላለች።
  ወርቁ ግን ማርያም ድንግል አሳተ መለኮት ጌታን በማኅጸንዋ ለመሸከምዋ ምሳሌ ነው።

  ReplyDelete
 7. Thanks! GOD bless you

  ReplyDelete
 8. ዲን ዳንኤል እግዚኣብሔር ይባርከ ። ። ወያኑህ ዕድሜከ ከመ ትኩን ብርሃና ለሃይማኖትከ ፡ ሁር ቅድሜከ ወፈጽም ገድለከ እግዚኣብሔር ይዕቀብከ በኩሉ ህይወትከ ።
  ኣሜን ። እመ ተናገርኩ ጽድቀ ሰብአ ዛቲ ዓለም ይጸልዑኒ፣
  ወከመ ኢይንብብ ሐሰተ ኩነኔ ዚአከ ያፈርሀኒ፣
  እም ኩሉሰ አርምሞ ይኄይስ ወይሤኒ

  ReplyDelete
 9. ዳኔ ፣ ቅኔ፣ ላቴን የሆነብን ብዙ ነን ። ከአዴሱ ትውልድ በቀላሉ ዓይናችን የሜያስከፍት ይኖር ይሆን?

  ReplyDelete
 10. ዳኒ ጦጣ አደረጋችሁን እኮ!! ኧረረረ ትርጉሙንም ጣል አድርጉበት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. "learn giiz ግእዝ ይማሩ "is an open facebook group plese join lern giiz

   Delete
 11. wht du mean ? Eynas Gizze Emanarfiwe ? Weye Fite Post atarigem !!!!

  ReplyDelete
 12. lemawek metar yerasachin halafinet nw.

  ReplyDelete
 13. "learn giiz ግእዝ ይማሩ "is an open facebook group plese join lern giiz

  ReplyDelete
 14. Ewnetim Astawash Ayasatan!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. If he doesn't know why you didn't tell us . empty mind has a lot of noise.

  ReplyDelete