ሁለት የጎዳና ልጆች የገና ዋዜማ አመሻሽ ላይ፣ ጎዳና ዳር ቁጭ ብለው አላፊ አግዳሚው
ለዓመት በዓሉ ሲራወጥ ያያሉ፡፡ ዶሮ ያንጠለጠለ፣ በግ የሚጎትት፣ ቄጤማ የቋጠረ፣ በሬ የሚነዳ፣ እህል ያሸከመ፣ ‹የገና ዛፍ›
የተሸከመ፣ አብረቅራቂ መብራት የጠቀለለ፣ ዋዜማ ሊቆም ወደ ቤተ ክርስቲያን ነጭ ለብሶ የሚጓዝ፣ ምሽቱን በዳንስ ሊያሳልፍ ሽክ
ብሎ ወደ ጭፈራ ቤት የሚጣደፍ፣ ብቻ ምኑ ቅጡ፣ ከተማዋ ቀውጢ ሆናለች፡፡
እነርሱ ደግሞ የተበጫጨቀች ልብስ ለብሰው፣ የደረቀ ዳቦ ይዘው፣ በቢል ቦርድ ላይ
የተለጠፈውን የጥሬ ሥጋ ሥዕል እያዩ፣ መጣሁ መጣሁ የሚለው የገና ብርድ እያቆራመዳቸው፣ የቆሸሸ ሰውነታቸውን እየፎከቱ፣ የቀመለ
ፀጉራቸውን እያከኩ፣ በታኅሣሥ 15ና በታኅሥ 29 መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው፣ የበግ ድምጽ እንጂ ሥጋው ርቋቸው፣ የበሬው
ፎቶ እንጂ ሥጋው ጠፍቶባቸው፣ ያገኙትን ወረቀት እያነደዱ ጎዳናው ዳር ተቀምጠዋል፡፡
‹‹ቆይ ግን ገና ምንድን ነው?›› አለ አንደኛው ሰውነቱን እየፎከተ፡፡
‹‹የክርስቶስ ልደት ነዋ፤ በማይክራፎን ሲሰብኩ የሰማሁት እንደዚያ ነው››
‹‹የት፣ መቼ፣ ለምን ተወለደ?››
‹‹እነርሱ የሚሉት ቤተልሔም በምትባል ከተማ፣ በእኩለ ሌሊት፣ በብርድ ወቅት፣
ራቁቱን፣ እናቱ በከተማዋ ማደሪያ የሚሰጣት አጥታ፣ በተናቀው ቦታ በከብቶች በረት ውስጥ ተወለደ፡፡ በጣም ስለበረደውና ራቁቱን
ስለነበር ከብቶቹ በትንፋሻቸው አሞቁት፤ ሌላ ሰው ስላልነበረ እረኞቹ መጥተው ዘመሩለት፡፡ እንዲህ ነው የሰማሁት፡፡››
‹‹እኛምኮ እንደርሱ የሚያስጠጋን አጥተን ነው ጎዳና የወደቅነው፡፡ እንደርሱ ራቁታችንን ነን፤ እንደርሱ የሚበላ የለንም፤
እንደርሱ እኛንም የሚያሞቁን እነዚህ ውሾች ናቸው፤ እንደርሱ እንደርሱ እኛም በተናቀው ቦታ ላይ ነን›› አለ ሁለተኛው ልጅ ውሻውን
እየደባበሰ፡፡
‹‹የሚገርምህ ነገር ጌታ የተወለደው በከብቶች በረት ዋሻ ውስጥ ነው፡፡ ያኔ ጥድ የለም፤ በረት እንጂ፡፡ ጌታኮ ጫካ
ውስጥ አልተወለደም፡፡ ያኔ ከረሜላ የለም፤ ያኔ ጥጥ የለም፣ ያኔ ፖስት ካርድ የለም፣ የሰብአ ሰገል ወርቅ፣ ዕጣንና ከርቤ እንጂ፡፡
አሁን ይኼን ሁሉ ከየት እንዳመጡት እንጃ፡፡ ይልቅስ ራቁታችንን ሆነን፣ የሚበላ ናፍቆን፣ በእንግዶች ማረፊያ ሥፍራ የሚሰጠን አጥተን፣
ከእንስሳት ጋር ተኝተን እኛ አለንላቸው፡፡ ገናኮ መከበር የሚገባው ከእኛ ጋር ነበር፡፡ ገና የሀብታሞች ሳይሆን የድኾች፣ የተከበሩ
ሳይሆን የተዋረዱ፣ ቤት ላላቸው ሳይሆን ማደርያ ያጡ፣ ዘመድ ያላቸው ሳይሆን ወገን ያጡ ሰዎች በዓል ነው፡፡ ገና የሚወርዱበት እንጂ
የሚወጡበት በዓል አልነበረም፡፡››
‹‹እኔም እሱን እያሰብኩ ነበር፡፡ ተመልከት ያኔ የዘመሩትን እረኞች አሁን ማንም አያስታውሳቸውም፡፡ ያኔ የቤተልሔም
ሰዎች በጥጋብና በዕንቅልፍ ተወስደው አላስጠጋው ሲሉ በረታቸውን የሰጡት ከብቶች ነበሩ፡፡ አሁን የእነርሱ ዋጋ መታረድ ሆነ፡፡ በዓሉኮ
የከብቶች በዓል ነበረ፡፡ እኔ ከብቶች ውለታ በዋሉበት፣ ከሰው የሚበልጥ ሥራ በሠሩበት በገና ቀን መታረዳቸው ይገርመኛል፡፡››
‹‹አይግረምህ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ሁሉ እንደዚህ ነው፡፡ ታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት
እንደሆኑ ናቸው፡፡ በኋላ የሚጠቀመው ታሪክ ሠሪው አይደለም፤ ታሪክ ተራኪው ነው፡፡ ‹የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ› የተባለው ዝም
ብሎ እንዳይመስልህ፡፡ አንተ በሠራኽው ታሪክ አንተን አርደው ያንተን በዓል የሚያከብሩ ሞልተዋል፡፡››
‹‹እርሱማ አታይም እንዴ፤ በኛ በድኾች ስም ይለመናል፤ ብር ይሰበሰባል፤ እኛ በፊልም እየተቀረጽን ታሪኩን እንሠራዋለን፤
በኋላ ግን እኛው ራሳችን በድህነት ቢላዋ እንታረድና የኛን በዓል ሌሎች ያከብሩልናል፡፡ ታሪኩን የሚሠሩት እረኞች፣ አበሉንና ደመወዙን
የሚበሉት ግን የቤተልሔም ሰዎች፡፡ አንተ ፖስት ካርድ ብቻ ሆነህ ትቀራለህ፡፡ እስኪ የገናን በዓል ተመልከት፡፡ እረኞቹ የታሉ፤
በረቱ የታለ፤ ከብቶቹ የታሉ፤ ከሩቅ ሀገር የመጡት የጥበብ ሰዎች የታሉ፤ ጌታ የተኛበት የእንጨት ርብራብ የታለ፡፡ ሁሉም የሉምኮ፡፡
የእረኞቹን ቦታ ተኝተው የነበሩት የቤተልሔም ሰዎች ወስደውታል፤ የበረቱን ቦታ የገና ዛፍ ወስዶታል፤ የጥበብ ሰዎችን ቦታ የገና
አባት ተረክቦታል፤ የከብቶቹን ታሪክ ሰባኪዎቹና ዘማሪዎቹ፣ ፓስተሮቹና ቄሶቹ ወስደውታል፤ የመላእክቱ ዝማሬ በጭፈራ ቤቶቹ ዘፈን
ተተክቷል፡፡ ከብቶቹንም፣ እረኞቹንም፣ ሰብአ ሰገልንም፣ በረቱንም፣ መላእክቱንም፣ የምታገኛቸው ፖስት ካርድ ላይ ብቻ ነው፡፡››
‹‹የሚገርመኝ ምን እንደሆነ ታውቃለህ፤ በዚህ መንገድ ዳር በተሰቀለ ትልቅ ቴሌቭዥን ላይ ሳይ፣ የሃይማኖት አባቶች
‹በዓሉን ከተቸገሩት ጋር በማክበር አሳልፉት› ሲሉ እሰማለሁ፡፡ አንዳቸውም ግን ከመናገር ባለፈ ከተከበረ መንበራቸው ወርደው ከእኛ
ጋር ሲያሳልፉ አይታዩም፡፡ ‹ክርስቶስ ከሰማያት ወረደ› ማለት እንጂ መውረድ ለካስ ከባድ ነው፡፡››
‹ካመጣኸውማ ገናኮ የመውረድ በዓል ነበር፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ የሚባልበት በዓል ነበር፡፡ አሁን ግን
የሚወጣ እንጂ የሚወርድ የለም፡፡ ወደ እኛ የሚወርድ የለም፡፡ ሰው አምላክ መሆን ቢያቅተው አምላክ ሰው ሆነ ይላሉ፡፡ እኛ እንደነርሱ
መሆን አቅቶናል፤ ታድያ ምናለ እነርሱ እንደኛ ቢሆኑ፡፡ በጣም የሚገርመው ሰብአ ሰገል ስጦታ የሰጡት ራቁቱን ለነበረው፣ ቤት ላጣው፣
የቤተልሔም ሰዎች አላስጠጋ ላሉት፣ ከሰው ወገን ጠያቂ ላልነበረው ለክርስቶስ ነበረ እንጂ ሁሉ በእጃቸው፣ ሁሉ በደጃቸው ለሆኑት
ለቤተልሔም ሰዎች አልነበረም፡፡ ዛሬ ግን ስጦታው ለቤተ ልሔም ሰዎች ሆነ፡፡››
‹አንድ ቀን አንድ ሰው ሲያስተምር ምን ሰማሁ መሰለህ፡፡ ክርስቶስ ‹ተርቤ አላበላችሁኝም፣ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም›
ይላል፡፡ የሰሙት ሰዎች ‹የት አግኝተን እናብላህ እናጠጣህ› ቢሉት ‹ለታናናሾቹ ካላደረጋችሁ ለእኔ አላደረጋችሁትም፣ ለታናናሾቹ
ካደረጋችሁ ለእኔ አድርጋችሁታል› አላቸው አሉ፡፡ ታድያ ከኛ የባሰ ታናሽ ማን አለ? ያኔምኮ ክርስቶስ ተራ፣ ድኻ፣ እዚህ ግባ የማይባልና የተናቀ መስሎ ስለመጣ ነው የቤተልሔም ሰዎች ያላስጠጉት፡፡
ዛሬስ ድንገት ከእኛ መካከል ቢኖርስ፣ እዚህ ጎዳና ዳር ከውሾቹ ጋር ተኝቶ ቢሆንስ፤ በገዛ የልደቱ ቀን ሰዎች እርሱን ንቀው እያለፉ፣
ተጸይፈው እያለፉ፣ በጽድና በከረሜላ፣ በበግና በዶሮ፣ በጠላና በጠጅ፣ በፖስት ካርድና በስጦታ የራሱን በዓል እያከበሩለት ቢሆንስ፤
››
‹ማን ያውቃል ወዳጄ፤ ሰው እንደሆነ በዓሉን እንጂ ራሱን ክርስቶስን የሚፈልገው አልመሰለኝም፡፡ ቢፈልጉት ኖሮማ አንድ
ጥድ የሚገዙበት እኛን አልብሶ ‹ታርዤ አላለበሳችሁኝም› ከሚለው ያወጣቸው ነበር፤ የአንድ ፖስት ካርድ ዋጋ ለኛ የወር የቤት ኪራያችን
ነበር፤ በጉን በልተው እንኳን ቆዳውን ቢሰጡን ለኛ የዓመት ቀለብ ነበር፤ ለከረሜላው የሚወጣው ገንዘብ የኛን የዓመት ጤና ይጠብቅ
ነበር፡፡ አሁንማ የበዓሉ ምክንያት ተረስቶ በዓሉ ብቻ ቀርቷል፡፡››
‹‹እና አሁን ገና እየተከበረ ይመስልሃል››
‹‹ምን እየተከበረ ነው፤ እየተቀበረ ነው እንጂ››
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት
የወጣ ነው
Dear D/n Daniel k!!!
ReplyDeleteI'm one of your reader recently.. and I wish you long live for you and family. now i'm very eager to know beyond the mission of TIENS company which is become popular in our country, this company is advising itself in nekemte town currently in 2006,,
what is your view regarding this company , in respect of religion, can you recommend us to be a member???
God bless you all day and night!! from Nekemte
በጣም ውስጥን የሚነካ ነገር ነው በእውነት እስቲ ሁላችንም እናስብበት
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል!!
እግዚአብሄር እረጅም እድሜ ከ ጤና ጋር ይስጥህ
ReplyDeletetiru eyta new
ReplyDeleteማን አውቆት?
ReplyDeleteፈጣሪ ተወለደ .... በበረት
እስትንፋስ ገበሩለት ... እንስሳት
አህያም አወቀ ... ጌታውን
ላምም አስታወሰ ... አምላኩን
እረኞቸም ዘመሩ ... ተደስተው
ዕቡያኑ አይሁድ ግን ... ነበር ተኝተው
ትንቢቱን እያወቁት ... ማረፊያ ነፍገው
ዛሬም ቆሟል በበራችን... ማረፊያ ሽቶ
ማነው "ግባ" የሚለው ... በሩን ከፍቶ
መንገድላይ ወድቆ ዛሬም ... አንሱኝ ይላል
እንደ ጻድቁ ብሶይ ... ማን አስተውሏል
አምላኩን ከመንገድ አንስቶ ... ይሸከማል?
ደግሞስ ቁራሽ ፍርፋሪ ... ማን ሰጥቶታል
ራበኝ እያለ ጌታ ... ሰምተነዋል?
ተትረፍርፎለት ሀብቱ ... ለሚተፋው
ሁሉም ያሸረግዳል ... ላልጎደለው
በግብዣው ይጋብዘዋል ... በጥሪው
ደሀው ክርስቶስ ግና ... ቁራሽ የለው
በላይ በላዩ ደጋግሞ ይጋታል ወይን
ለጌታ ግን ሳይቸረው ቀዝቃዛ ውኃን።
ከራሱ ተርፎ ውሻው ልብስ ደርቧል
በብርድ ቆራምቶ ጌታን ትቶታል።
እንግዳ ሆኖ መጥቶ ጌታ እኛ ቤት
"ወግድ" ተብሎ ተሰዷል በታላቅ ውርደት።
ታስሮም አልጠየቅነውም ፈረድንበት
ታሞ ወድቆም አይተነው ንቀን አለፍነው
ታዲያ በፍርድ ለታ በየት ልንቆም ነው?
እርሱ የሰጠንን ሁሉ ከከለከልነው።
ልቡና ይስጠን ጌታ አውቀን እንዳናልፈው
እርሱ ከሰጠን ላይ እንድንመጸውተው
እንደ አንጢላርዮስ ክፉ እንደነበረው
ደግነት ያድለን እርሱ ነው መዳኛው።
you are good writer
Deleteማን ያውቃል ወዳጄ፤ ሰው እንደሆነ በዓሉን እንጂ ራሱን ክርስቶስን የሚፈልገው አልመሰለኝም፡፡ ቢፈልጉት ኖሮማ አንድ ጥድ የሚገዙበት እኛን አልብሶ ‹ታርዤ አላለበሳችሁኝም› ከሚለው ያወጣቸው ነበር፤ የአንድ ፖስት ካርድ ዋጋ ለኛ የወር የቤት ኪራያችን ነበር፤ በጉን በልተው እንኳን ቆዳውን ቢሰጡን ለኛ የዓመት ቀለብ ነበር፤ ለከረሜላው የሚወጣው ገንዘብ የኛን የዓመት ጤና ይጠብቅ ነበር፡፡ አሁንማ የበዓሉ ምክንያት ተረስቶ በዓሉ ብቻ ቀርቷል፡፡››
ReplyDelete‹‹እና አሁን ገና እየተከበረ ይመስልሃል››
‹‹ምን እየተከበረ ነው፤ እየተቀበረ ነው እንጂ›
i was crying when i read this. Thank you dn daniel. God bless you and your family.
ReplyDeletedenk eyta new!!! selam ena tenan lehulachen mastewalen yesten aman
ReplyDeleteIt is very interesting message. D/n Daniel Kale Hiwot yasemalin.
ReplyDeleteKalehiwot yasemalin.Ke Gegena befit bihon tiru neber
ReplyDeleteትክክል ብለሃል ወይ ጉድ እኔም ዛፍ የገና አባትን ልዩ ልዩ ግጣጌጥችን ገዝቼ ልጆችን በቤት ውስጥ ደስ ለማሰኘት ከደከሙ እናቶችውስጥ ነኝ የሚገርመው ግን ከዚህ ምን ይማራሉ እያልኩ ነበር በደመነፍስ የማረገው ምንም ከዛፉ እና ከተገዛው ጌጣጌጥ ትምህርት እንደማይ ወስዱ ገብቶኛል ገን በብዛ እየተደረገ ያለው ይሄው ስለሆነ:: እራሴን ከአካባቢዬ ወጣ አርጌ የተለየ ነገር ለማድረግ አልቻልኩም :: አንተ በዚህ ታድለሃል ወጣ ብሎ ማሰብ በተለየ መልክ ማየት መታደልን ይጠይቃል::ዕንደኔ እነዚህ የጎንደር ጎዳና ተዳዳሪዎች ከገና ቀደም ብለው ቢመጡ ከብዙ ነገር ያድኑን ነበር:: እድሜውን ያድልህ ለኛም ማስተዋልን::
ReplyDelete".........ማን ያውቃል ወዳጄ፤ ሰው እንደሆነ በዓሉን እንጂ ራሱን ክርስቶስን የሚፈልገው አልመሰለኝም..."
ReplyDeleteይህን ከበዓሉ በፊት አንብቤው ቢሆን ኖሮ ከሁለቱ ታናናሾች ጋር አከብረው ነበር። ለካስ አይኔ ተከፍቷል እንጂ አያይም። እንኳን አነተን የመሰለ መነፅር ጣለልኝ። ከእንግዲህ ግን የማይ ይመስለኛል። አንተንም መሳሪያው አድርጎ የቀረጸህ እግዚአብሔር ለኛ ሲል ያቆይልን። ከ መዘናጋትም ከ መታበይም ይጠብቅህ። ልክ እነዳሁኑ
ReplyDeleteAMEN
Deleteyou put one stone in my heart ,even if i am student,i am willing to help as much as i can in the future, tomorrow!
ReplyDeleteTiru eyeta new
ReplyDeleteበጣም ነው የተሰማኝ ምናለ የህንን ቀድሜ ባነበብብኩነና የተቻለኝን ባረግኩ ነው ያልኩት በርግጥ ይሄ የአንድ ወቅት ሥራ ብቻ እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡ እግዝአብሄር ትዕዛዙን ለመፈፀም ሁላችንንም ይርዳን፡፡ አሜን
ReplyDeleteI want to know what you did and how you spent the holiday
ReplyDeletekadem bil tru naber. GBU & ur family
ReplyDelete............ታድያ ከኛ የባሰ ታናሽ ማን አለ? ያኔምኮ ክርስቶስ ተራ፣ ድኻ፣ እዚህ ግባ የማይባልና የተናቀ መስሎ ስለመጣ ነው የቤተልሔም ሰዎች ያላስጠጉት፡፡ ዛሬስ ድንገት ከእኛ መካከል ቢኖርስ፣ እዚህ ጎዳና ዳር ከውሾቹ ጋር ተኝቶ ቢሆንስ...........
ReplyDeleteዳኔ ፣ በበኩሌ ከራሴ ጋር ቃል ኬዳን በዛሬው ለት ገብቸ አለሁ ። ይሕ ትልቅ ቅዱስ ትምሕርት ስለሆነ ብትችል የዜያ ሰው ይበለን እና ለከርሞ በበዓሉ ዋዜማ ጽሑፎን በድጋሜ ቤወጣ ብዙውን ምእመን ወደቀኝ ሌመራ ይችላል።በተረ ፈ መልካም የጥምቀት በዓል። የድንግል ልጅ አንተንና ቤተ ሰብሕን ይባርክ።
ReplyDeleteIsn't this what the church has been preaching for the last hundreds of years, only to fail till the present moment?. Your whole text is to sensationalize and grasp attention by stirring emotion. But not to find pragmatic solution to those homeless kids you are talking about. We don't have to help the poor to score a point in the heavens, or to make the creator happy, or because its Christmas. We ought to help because we are humans. we owe it to our humanity. your intention is good, but i am afraid you write in a sensational, fictional and unreal characters that looses touch with reality.
ReplyDeleteI am amazed by the 'qedem bil tiru neber' comments. This appears to mistakenly suggest there is only one holiday and that had passed. We have Timket, Fasika...and then Gena again ahead of us. What matters is to have the giving heart as of this moment. For that matter, you don't need Gena to be charitable as those in the street go hungry not only on Gena but every single hour. So, please go for it, and live the good Samaritan's way as of now! Dear Dani, more blessings for you and your family!
ReplyDeleteታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው
ReplyDeleteታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው
ReplyDeleteታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው
ReplyDeleteThe idea is generally good, let alone Christians non-believers would also support it. It is good to remind Christians to mind what they do during such great Holidays.
ReplyDeleteBut, I do not in general find your fictional way of writing interesting. I find it difficult to finish the story as I could not imagine fictional street boys rehearsing such deep preaching.
Daniel, please focus on ideas. Most of us are grown up citizens not children and we will get bored in the middle of your stories. You could present this story without involving the two characters.
የተቸገረ ብታይ ከንፈር ከመምጠጥ የቻልካትን ትንሿን አድርግለት! ሐዋርያው በሥራና በምግባር እንጂ በቃል ብቻ አንዋደድ እንዲል ለድኾች የቻልነውን እንስጥ! በየበአላቱ ዶሮ በማይጮኽበት ጢስ በማይጤስበት ቤት ያለችንን ተካፍለን እንብላ! ትዝ ይለኛል ልጅ እያለኹ እንደ ልደተ ክርስቶስ ባሉ በዓላት ላይ ከክፍል ጓደኞቼ ጋር ዶሮ እያሰራን ለድኾች እናበላ ነበር።
ReplyDeletehttp://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/
D/daniel Egiziabehe Edmena tena yesteh
ReplyDeletebadoneten enday aderekegn
ዳኒ እንኳን አደረሰህ።ሰው አምላክ መሆን ቢያቅተው አምላክ ሰው ሆነ።እስኪ እናስበው ለምን ይሆን አስተውለነው እናውቅ ይሆን? ክርስቶስ ከሰማዬ ሰማያት ወረደ ሰውግን መውረድአይፈልግም ወደላይ መውጣት እጁ ።ይገርማል ሰውግን ከየት የተማረውን ይሆን የሚሰራ? አባታችን መድሀኒታችን ያሰተማረን ሌላ ሰው በራሱ ያልተማረውን ከየት እደሚያመጣው በጣም ያሳዝናል። ዳኒእእግዚያብሔር ይባርክህ ምናልባት ከመቶ አስር እንኳን ይህን አስታውሶ ሊድን ቢታደል ማን ያውቃል አንም አስታዋሽ አትጣ ባለቤቱ ያስታውስህ መልካም በአል እስከ ቤተሰቦችህ እመኝልህ አለሁ ።ቸር ወሬ ያሰማን ከበላይ ነኝ።
ReplyDeleteENASTEWELE!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteENASTEWELE!!!!!!!!1111
ReplyDeleteAmilake kidusan azang libi yisiten kale hiyiwot yasemaln.
ReplyDeletebetam talak mikir yalew melekt new ,,,egzaibaker yistilin ye agelglot zemenhn yarzmln
ReplyDeleteMay God blees you brother!
ReplyDeleteአንተ በሠራኽው ታሪክ አንተን አርደው ያንተን በዓል የሚያከብሩ ሞልተዋል፡፡››
ReplyDeleteየዛሬው አለም ህዝብ መመሪያ ይህ ነው መርዳቱ ቀርቶ መግደሉን በሰዎች መነገዱን በተወ
keshim negn
ReplyDeleteገናኮ የመውረድ በዓል ነበር፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወረደ የሚባልበት በዓል ነበር፡፡ አሁን ግን የሚወጣ እንጂ የሚወርድ የለም፡፡
ReplyDeleteገናኮ የመውረድ በዓል ነበር!!!!!!
ReplyDeleteገናኮ የመውረድ በዓል ነበር፡
ReplyDeleteታሪክ የሠሩትና መሥዋዕትነት የከፈሉት ምንጊዜም መሥዋዕት እንደሆኑ ናቸው
ReplyDeleteIn this article i was seeing my self from the begging to the end. Love it. Nice thought dear Deacon Daniel.
ReplyDeleteአሁንማ የበዓሉ ምክንያት ተረስቶ በዓሉ ብቻ ቀርቷል
ReplyDelete