click here for pdf
አራት መዓዝኑ የመቅደሱ ግንብ ለስድስት ሜትር ያህል ወደ ላይ ከወጣ በኋላ መቅደሱን
ከጣራው ጋር በክብ ግድግዳ ያያይዘዋል፡፡ ወደ ቅድስቱ መግቢያው በር የጥንቱን ይዘት አልለቀቀም፡፡ በአራት ደረጃ የተሠራው
መቃን በሥዕል የተሞላ ነው፡፡ በመጨረሻው መቃን ላይ ደግሞ የአሥራ አምስቱ ነቢያት ሥዕል በትንንሹ ተሥሎ ይታያል፡፡
ሰንደባ ኢየሱስ - ከሩቁ
|
ከባሕርዳር ወደ ጎንደር ስትጓዙ አርኖ የምትባል አነስተኛ ከተማ ታገኛላችሁ፡፡
የከተማዋና የወንዟ ስም አንድ ነው፡፡ አርኖ ላይ ወርዳችሁ ወደ ቀኝ ለአንድ ሰዓት ተኩል ያህል በእግራችሁ ስትጓዙ ሜዳውን
ትጨርሱና ገደሉን ፊት ለፊት ትጋፈጡታላችሁ፡፡ በገደሉ መካከል እንደ ሞሰበ ወርቅ በተሸለመች ተራራ አናት ላይ የሰንደባ ኢየሱስ
ወተክለ ሃይማኖትን ጥንታዊ ደብር ታገኙታላችሁ፡፡
የደብሩ ካህናት የቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ ከአንድ ሺ ዓመት በላይ እንዳለፈው
ይናገራሉ፡፡ በአካባቢው የምናገኛቸው የሥነ ሕንጻና አካባቢያዊ ማስረጃዎች ደግሞ ታሪኩ ቢያንስ ሰባት መቶ ዓመት ሊሆነው
እንደሚችል ይጠቁማሉ፡፡
የሰንደባ ኢየሱስ ወተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ሥነ ሕንጻው ከዛግዌ ዘመን፣
አካባቢያዊ መረጃዎቹ ደግሞ ከ13ኛውና 14ኛው ዘመን ጋር የሚገናኙ ናቸው፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ክብ ሆኖ ውጩ በጭቃ የተገረፈ ነው፡፡ የጭቃ ግርፉ በቤተ ክርስቲያኑ
ላይ የደረሰውን የመፍረስ አደጋ ለመታደግ በአካባቢው ባለሞያዎች የተገነባ ነው፡፡ ወደ ውስጡ ሲዘልቁ ግን ሁለት ጥንታዊ
ክፍሎችን ያገኛሉ፡፡
ሰንደባ ኢየሱስ - ከቅርብ ሲታይ
|
የደብሩ መስኮቶች እንደ ይምርሐነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ወጥ እንጨት
የተሠሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ መስኮት ያራሱ ቅርጽ ያለው ሲሆን፣ አንደኛው ከሌላኛው የተለየ ዲዛይን አለው፡፡ ብዙዎቹ መስኮቶች
ለውበት የተሠሩ እንጂ የሚከፈቱ አይደሉም፡፡ የመስኮቶቹ መቃኖች
ከአንድ ወጥ እንጨት ወጣ ብለው የተሠሩ፣ በአራቱም መዓዝን ወጣ ወጣ ያሉ ጌጦች ያሏቸው ናቸው፡፡ ይህ አሠራራቸው ከይምርሐነ
ክርስቶስ አሠራር ጋር ያዛምዳቸዋል፡፡
ሰንደባ ኢየሱስ ወተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንን ከይምርሐነ ክርስቶስ ጋር
የሚያዛምዳቸው መስኮታቸው ብቻ አይደሉም፡፡ የመቅደሱ ግድግዳ አሠራርም ተመሳሳይ ነው፡፡ ግድግዳው በቀጫጭን ጠፍጣፋ ድንጋዮች
እየተሰካካ፣ በኖራ መሰል ነገር እየተያያዘ ቀጥ ብሎ የተሠራ ነው፡፡ እጅግ የሚገርመው ግን ድንጋዮች የተያያዙበት ኖራ መሰል
ነገር የተለሰነበት መንገድ ነው፡፡ የደብሩ ሊቃውንት ኖራ ከተነከረ ቆዳ ጋር እየተያያዘ እንደተሠራ ይናገራሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ
ከውጭ ክብ ቢሆንም ሁለቱ የውስጥ ክፍሎቹ ግን አራት መዓዝን ናቸው፡፡ መዓዝኖቹ በርግጠኝነት 90 ዲግሪ ናቸው፡፡ ወደ ላይም
በቱምቢ ሲለካ ቀጥ ብሎ የወጣ ወጣ ገባ የሌለው ነው፡፡
በግድግዳው አማካይ በሐረግ የተጌጠ ነው፡፡ ጌጡ ከጥግ እስከ ጥግ በሁለት ወይም
በሦስት መሥመር እየተዘረጋ ተገጥግጧል፡፡ ከመስኮቶቹ በላይ ደግሞ ሌላ ጌጥ አለ፡፡ በመስኮቶቹ መቃን ርዝመት ልክ ከአንድ ወጥ
እንጨት የተሠራ ሐረግ፡፡ ይህ ሐረግ በመስኮቱ ላይ በቻ ሳይሆን ከበሩ በላይም እንዲሁ በየመዓዝናቱ ተሰክቶ ይታያል፡፡
በተሰካኩ ድንጋዮች የተሠራው ግድግዳ
|
የተጌጠው መስኮት
|
የአሥራ አምስቱ ነቢያት ሥዕል- የበሩ ላይኛው
መቃን
|
ከበሩ በላይ ሌላ ጌጠኛ መስኮት አለ፡፡ መስኮቱ ባለ ሦስት መቃን ሲሆን ሦስቱም
በሥዕል ያጌጡ ናቸው፡፡ የሚገርመው ግን መስኮቱ ለውበት የተሠራ እንጂ የሚከፈት መስኮት አይደለም፡፡ ከአንድ ወጥ እንጨት
የተቀረጸው መስኮት የመስኮቱ ውስጣዊ አካል ራሱ በቀለም ያሸበረቀ ነው፡፡ የመስኮቱ ውስጣዊ አካል ደግሞ እርስ በርሳቸው
በተያያዙ ክቦች ቅርጽ የተሠራ ነው፡፡ እያንዳንዱ ክበብም የየራሱ ቀለም ተቀብቷል፡፡
ዋናው በር በበሩ ላይ የቅዱሳን መላእክት ሥዕል በትልቁ ተሥሎበታል፡፡ ሥዕሉ
እንዳይበላሽ በመጋረጃ የተጋረደ ሲሆን ሥዕሉን ባለ ሦስት ደረጃ መቃን አጅቦታል፡፡ ወደ በሩ የመግቢያው ደረጃ ከእንጨት የተሠራ
ባለ ሰባት እርከን ነው፡፡ ሊቃውንቱ የሰባቱ መዓርጋት፣ የሰባቱ ሰማያትም ቢሉ ምሳሌ ነው ይላሉ፡፡ ከበሩ ግራና ቀኝ ቢያንስ
አራት መቶ ዓመታትን የዘለቁ፣ የሥዕል አጣጣላቸው ከጎንደር ዘመን ቀደም ያሉ ዓመታትንና የጎንደርን ዘመን አሻራ ያዙ ሥዕሎች
አሉ፡፡
ባለ ሰባት ደረጃው በር
|
በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መንበር የሚመስሉና የቤተ ክርስቲያኑን ቅርጽ
የያዙ ወጥ ከሆነ እንጨት የተቀረጹ ሳጥኖች አሉ፡፡ አንዳንድ ሊቃውንት ቅዱስ ላሊበላ ሕንጻዎቹን ከመውቀሩ በፊት ዲዛይኑን
በእንጨቶቹ ላይ ማስቀመጡን ይናገራሉ፡፡ በሰንደባ ኢየሱስ ወተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንም የመቅደሱን ቅርጽና የመቅደሱን
ሐረጎችና በሮች ቅርጽ ያዘ አነስተኛ መንበር መሰል ነገር አለ፡፡ እንደ እኔ ግምት ቤተ ክርስቲያኑ ሲታነጽ የቤተ ክርስቲያኑ
ቅርጽ አራት መዓዝን የነበረ ይመስላል፡፡ በኋላ ሲፈርስ ለማደስ ሳይሆን አይቀርም ውጩ ክብ የሆነው፡፡
የቤተ ክርስቲያኑን ቅርጽ የያዘው ጥንታዊው አንድ
ወጥ ‹መንበር›
|
የመቅደሱ ታችኛው ግድግዳ በዕውቅ ጠራቢ ተስተካክለውና አምረው በተጠረቡ ግዙፍና አራት
መዓዝን በሆኑ ዐለቶች የተገነባ ነው፡፡ የዚህ ግድግዳ አሠራሩ በአኩስም ከተገኙ የጥንት መቃብሮች አሠራር ጋር የተዛመደ ነው፡፡
ዐለቶቹ እርስ በርስ የተገጣጠሙበት መንገድ ትኩረት ቢደረግበት ለዛሬውም የግንባታ ችግሮቻችን መፍትሔ የሚሰጡ ናቸው፡፡
በግዙፍ ጥርብ ድንጋዮች የተገነባው ግድግዳ
|
የሰንደባ ኢየሱስ አስደናቂ ታሪክ የሚጀምረው አሁን ቅድስት የሆነውን ክፍል ሲገልጡት
ነው፡፡ ቅድስቱ ሁለት ክፍል ያለው እጅግ ሰፊ ክፍል ነው፡፡ ምናልባትም በጥንቱ አሠራሩ ይኼ መቅደሱ ሳይሆን አይቀርም፡፡
በቅድስቱ ውስጥ ያለው ውስጠኛው ክፍል ባለ ሦስት በር ሲሆን የግራና ቀኙ በር ቅስት መልክ ሲኖረው፣ የመካከለኛው በር ግን
የከፊል ክብ መልክ ያለው ነው፡፡ ግድግዳው ከጥርብ ድንጋይ የተሠራ፣ በዓምዱ መጨረሻ ላይ ዓምዱን ከቅስቱ የሚያያይዙ መከዳዎች
የተሠሩለት ጌጠኛ ግድግዳ ነው፡፡
በውስጠኛው ክፍል ውስጥ የሚገኙት ሦስት መናብር ለየት ያሉ ናቸው፡፡ መካከለኛው
መንበር እጅግ ግዙፍ ከመሆኑም በላይ አሠራሩ የላሊበላን መናብርት የመሰለ ነው፡፡ በግራና በቀኝ ያሉት መናብርት እስካሁን
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ካየኋቸው መናብርት ለየት ያሉ ናቸው፡፡ ቅርጻቸውም የኦሪቱን መንበረ ታቦት የሚመስሉ ሲሆኑ ካህናቱ
መሥዋዕተ ኦሪት ሲሠዋባቸው የነበሩ ናቸው በማለት ይገልጣሉ፡፡ በላያቸው ያለውን ጌጥና ቅርጽም ጊዜ ወስዶ ማጥናት ይጠይቃል፡፡
አስደናቂው ቅድስት
|
በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ጥንታዊ ሚዛን፣ ከድንጋይ የተሠራ አገልግል፣ ከአንድ ወጥ
እንጨት የታነጸ የመብራት ማብሪያ፣ ከአንድ ወጥ እንጨት የተሠራች አገልግል፣ የኦሪቱን የመሰለ የዘይት ማብሪያ ይገኛል፡፡ አሁን
አገልግሎት የማይሰጥ ‹ተሰማ ጎንደር› የሚባል ከበሮም ነበራቸው፡፡ ይህ ከበሮ በማኅሌት ጊዜ ሲመታ እስከ ጎንደር ከተማ ይሰማ
ስለነበር ‹ተሰማ ጎንደር› ተብሎ መሰየሙ ይነገራል፡፡
ሰንደባ ኢየሱስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን አካባቢውም ከመካከለኛው ዘመን ጋር
የተያያዘ ነው፡፡ በአካባቢው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ የሚነገረው ታሪክ፣ የአሥራ ሁለቱ ንቡራነ እድ ቦታዎች ናቸው
ተብለው የሚነገሩት ቦታዎች፣ ደብሩ ከአቡነ ታዴዎስ ዘጽላልሽ ጋር
ተያይዞ የሚነገርለት ታሪክ፣ ጠለቅ ብለው ቢጠኑ በሀገራችን የሕዝቦች መስተጋብርና በቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን አገልግሎት ላይ
ተጨማሪ ዕውቀት የሚሰጡን መረጃዎችን ልናገኝ እንደምንችል መገመት ይቻላል፡፡ የአካባቢው ሽማግሌዎችና የየደብሩ ታሪክ
ከአንድ ወጥ እንጨት የተሠራው አገልግል
|
ሰንደባ(ታዴዎስ)፣ ጉርሐች(ኤልሳዕ)፣ ቀልቀል (ገብረ ዮሐንስ)፣ ምጓዕ(በርሶማ)፣
ጥቃራ(መርሐ ክርስቶስ)፣ ደብረ ቅድስት(ጳውሎስ)፣ ዳንጉሬ(ቀሌምንጦስ)፣ ሰውበዳ(ዮሐንስ ከማ)፣ ዋሻ(እንድርያስ)፣
ገረገራ(አኖሬዎስ)፣ አግድ(እጬ ፊልጶስ)፣ ውሻ ጥርስ(እጬ ፊልሞና) ቦታቸው መሆኑን ይገልጣል፡፡ የሰንደባ ኢየሱስ መጽሐፍ
‹ቡራኬ ዘሰንደባ ታዴዎስ፣ ሲመት ዘኤልሳዕ፣ ወመጽዑ ፲ወ፪ ንቡራነ ዕድ ዘሀገረ ሴዋ ዘደብረ ሊባኖስ - ቡራኬ የሰንደባ ታዴዎስ፣
ሹመት የኤልሳዕ ነው፤ አሥራ ሁለቱ ንቡራነ ዕድ በሀገረ ሸዋ ከምትገኘው ደብረ ሊባኖስ መጡ› ይላል፡፡
‹ከኦሪት ዘመን ጀምሮ‹ አገልግሎት ላይ የነበረው
የመብራት ማብሪያ
|
እጅግ አስደናቂው ነገር አዲስ የሆነ የንቡራነ ዕድ ዝርዘር እዚህ ማግኘታችን፣
ከንቡራነ ዕዱ መካከልም ታዴዎስ፣ ኤልሳዕ፣ አኖሬዎስ፣ ፊልጶስ
በሌሎች መጻሕፍት ከሚገኙት ዝርዝሮች ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ - ገብረ ዮሐንስ፣ መርሐ ክርስቶስ፣ ጳውሎስ፣ ቀሌምንጦስ፣ ዮሐንስ
ከማ፣ እንድርያስ፣ እጬ ፊልሞና በንቡራነ ዕድ ዝርዝር የምናገኛቸው አዳዲስ ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህን አድባራት በእነዚህ ቅዱሳን
ርስትነት ቢጠሩም የየደብሩ ታቦታት ግን በሌሎች ቅዱሳን ስም የሚጠሩ ናቸው፡፡
ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተቀረጸው አገልግል
|
ይህ ጉዳይ ሁለት ነገሮችን እንድንገምት ያደርጋል፡፡ በዛሬው ወሎና ኤርትራ
እንደነበረው የአሥራ ሁለት አበው ሥምሪት በጎንደር አካባቢም ነበር ማለት ነው? ይህ ከሆነ ደግሞ የጥንቷን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ሥምሪት የሚያጠናክርልን ተጨማሪ ነገር አገኘን ማለት ነው፡፡
ወይስ ደግሞ የአካባቢው ቃላዊና ጽሑፋዊ መረጃ እንደሚገልጠው ከደብረ ሊባኖስ የተነሡ አሥራ ሁለት ንቡራነ ዕድ ወደዚህ አካባቢ
መጥተው ነበርን? ያ ከሆነ ደግሞ በዚህ ዝርዝር ያገኘናቸውን
አዳዲስ ንቡራነ ዕድ ታሪካቸውን መፈለግ የግድ ይለናል ማለት ነው፡፡
ሁሉም ተጨማሪ ጥናት የሚጠይቁ ፍንጮች ናቸው፡፡ ፍላጎትና ዕውቀት ያለው ሰው አጥንቶ
ቢነግረን እንመርቀዋለን፡፡
ከደብረ ሊባኖስ የተነሡ አሥራ ሁለት ንቡራነ ዕድ ወደዚህ አካባቢ መጥተው ነበርን? ያ ከሆነ ደግሞ በዚህ ዝርዝር ያገኘናቸውን አዳዲስ ንቡራነ ዕድ ታሪካቸውን መፈለግ የግድ ይለናል ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteወይ ይህች ታምረኛ ቅድስት ሀገር ገና ስንት ያልተነካ ምስጢር ይኖራት ይሆን?
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል ክብረት ምስጋና ይገባሃል ያልታየውን እንድናይ፣ አብዝተንም እንድንፈልግ፣ አገራችን ኢትዮጵያን የበለጠ እንድንወዳት እንድናከብራትም ዓይናችንን ገልጠህልናልና፡፡
Abet Ethiopia sintun tarik yizawalech??? Ante gin tebarek yihen tarikawi bota seleastewaweken
ReplyDeleteፍላጎትና ዕውቀት ያለው ሰው አጥንቶ ቢነግረን እንመርቀዋለን፡፡
ReplyDeleteዉድ ወንድማችን ዳ.ዳንኤል እግዚያብሔር አምላክ እድሜና ጤና ሰጥቶ በጽናትህ ያዝልቅህ።
ReplyDeleteበዉነቱ ታላላቅ ታሪኮችን እየመገብከን ነዉ እና ያበርታህ መጨረሻህንም ያሳምርልህ።
Enamesegnalen Memhr.
ReplyDeleteቅድስት ቤተ ክርስትያን ገና ግዙፍና ድንቅ ታሪኮችዋን ገላልጣ ታሳየናለች፡፡ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እግዜር ይስጥልን፡ ያላየነውን ያልሰማነውን አሳይተሃል፡፡
ReplyDeleteEGZIABHER YSTLIN ABATACHN DANI
ReplyDeleteዲ/ን ፀጋና በረከቱን ያብዛልሕ ። ለኛም ለዝች ቅድስት፤ ምልእት ቤተክርስቲያናችን እንደተሰጠን ፀጋ እንድናገለግል ቅዱስ ፍቃዱ ይሑንልን።
ReplyDeleteሰርክ አዲስ የሆነች አገር
ReplyDeleteሰርክ አዲስ የሆነች አገር
DeleteI wish God to give for you long age and health!!
egzhihbher yebarkh
ReplyDeleteአንዴ አምላክ እጅህን ለበረከት አደረገልህ ፈጣሪ የፈቀደው ብዙ
ReplyDeleteይሠራል አንተ የተባረክ ነህ ዕድሜ ከሰጠህ ገና ብዙ ታሳየናለህ
ግን ዳኒ አውሮፓን መዳሰስ ተውክ እንዴ አውትራልያ ያቆምከው ጉዳይ
ማን ነህ ባለ ሳምንትን ልቡናችን ያሰላስላልና አንድ በለን ።
ምሥጢሩ ነኝ ከጀርመን
Dear Daniel Kibret Yageliglot Zemenihin Yarzimilin Dingle Timirahe, Betesebochihin Yebarkilih
ReplyDeleteሰርክ አዲስ የሆነች አገር, Esub Denik ,
Esub Denik ,Esub Denik Belenal.
Dani, EGZIABHERE YABERTAH!!!
ReplyDeletelegna gena bizu yebetekrstian tarik mawok lemitebekbn wotatoch endante aynet " merahe fnot" EGZIABHER ayasatan!!!
Mati,
kesidistkilogibigubaea.
እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንዎን ይባርክ። በጣም በተመስጦ የሚከታተሉት ድንቅ ትረካ ድንቅ ቦታ ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ የአበው ታሪክ ድንቅ... ዕፁብ ድንቅ። ብቻ ቃለ ሕይወት ያሰማዎ መንግሥተ ሰማያት ያውርሰዎ እንደጨፌ ያለምልምዎ እንደ ዋርካ ያስፋዎ። አሜን።
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ አንተን እና መላ ቤተሰብህን የማናቀውን ታሪክ ነዉ ያሳወከን!!
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ያገልግሎት እድሜህን ያርዝምልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን!!
የማናቀውን ታሪክ ነዉ ያሳወከን!! እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ!!!!!!!
ReplyDeleteTebarek
ReplyDeleteዕፁብ ድንቅ!!!ረጅም እድሜ እና ያገልግሎት ዘመን ይስጥልን፡፡ቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDeleteሰርክ አዲስ የሆነች አገር
ReplyDeleteYes it is the secret land of God, the promise land with the undiscovered or unearthed ancient civilization.
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ይህ ጥበብ ለምን ከኛ ሸሸ?እባክህን ሰለ አባቶቻችን ድካም ብለህ ግለፅልን፡፡ ዳን እግዚአብሔር ደግሞ ደጋግሞ ይግለፅልህ አሜን፡፡
ReplyDeleteMensira na nwe yehenakile wedesa le Dk Daniel yemetisetute ? Hedoko menfisun adeso zena bilo Tebarko nwe yemetawe esu sayansew lela jebed endisera Elelta Yemetabizute Weregna wela !!!
ReplyDeleteDeacon daniel egezeabhere yebarekehe guzo bezegajena endehe ayenet botawoch enderedu bederege des yelal yaberetahe! abezagawene sew akeme selelelewe begele hedo lemayet ayecheleme ena guzo teru negere new!
ReplyDeleteበእውነት ዳኒ የልፋትህን ዋጋ መድሃኒአለም ይክፈልህ
ReplyDeleteየማናቀውን ታሪክ ነዉ ያሳወከን!! እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ!
ReplyDeleteየማናቀውን ታሪክ ነዉ ያሳወከን!! እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ!
ReplyDeleteየማናቀውን ታሪክ ነዉ ያሳወከን!! እግዚአብሔር አምላክ ይባርክህ!
ReplyDeleteለምትሰራው ስራ እግዝብሔር ይባርክህ ለቀጣይ ደግሞ ትግራይ ክልል ቡዙ የማይታወቁ ጥንታውያን ገዳማት አሉና የማስተዋወቅ ብትሰራልን እላሎህ
ReplyDeleteDiyakon daniel kiberet, bewenet hulam yanten tsehuf saneb westane yemayihone semate yesemagnale,..Ye desta, yemanenat,Ye hager Ye hayimanote fiker sematoch beka leba lay sefesu nw yemiwelut...Ebakihen yemetechil kehone wede europ metetak mekeren...
ReplyDeleteEgizeyabihar amilak edma Tena, gulebetun Abezeto yesetek..enodekalen!!!
Henok, ke PARIS
Diyakon daniel kiberet, bewenet hulam yanten tsehuf saneb westane yemayihone semate yesemagnale. Desta, yemanenat semate, Ye hager Ye hayimanote fiker sematoch beka leba lay sefesu nw yemiwelut. endew Egizeyabihar amilak tsegawen, edmana Tenawen Abezeto yesetek.
ReplyDeleteEbakihen yemetechil kehone wede europ metetak mekeren. Enodekalen...
Henok ke PARIS
Diyakon daniel kiberet, bewenet hulam yanten tsehuf saneb westane yemayihone semate yesemagnale. Desta, yemanenat semate, Ye hager Ye hayimanote fiker sematoch beka leba lay sefesu nw yemiwelut. endew Egizeyabihar amilak tsegawen, edmana Tenawen Abezeto yesetek.
ReplyDeleteEbakihen yemetechil kehone wede europ metetak mekeren. Enodekalen...
Henok ke PARIS
Diyakon daniel kiberet, bewenet hulam yanten tsehuf saneb westane yemayihone semate yesemagnale,..Ye desta, yemanenat,Ye hager Ye hayimanote fiker sematoch beka leba lay sefesu nw yemiwelut...Ebakihen yemetechil kehone wede europ metetak mekeren...
ReplyDeleteEgizeyabihar amilak edma Tena, gulebetun Abezeto yesetek..enodekalen!!!
Henok, ke PARIS