Thursday, January 9, 2014

‹አራቱ ኃያላን› በጎንደር

                         ጉባኤው በጸሎት ሲከፈት
‹አራቱ ኃያላን› መጽሐፍን የተመለከተ ልዩ መርሐ ግብር ጎንደር ላይ ለማዘጋጀት ከታቀደ ቆየ፡፡ በአዲስ አበባ እንዲመረቅ ከታቀደበት ጊዜ ጋር አብሮ ነበር መርሐ ግብሩ የተያዘው፡፡ በአንድ በኩል ጎንደር ታሪካዊት ከተማ በመሆኗ፤ በሌላም በኩል የሊቃውንቱ መፍለቂያ፣ የሀገሪቱና የቤተ ክርስቲያኒቱ የዕውቀት ማዕከል (Center of Excellence) በመሆኗ፣ ከዚያም አልፎ ደግሞ ከዚህ በፊት በምሥራቅ ኢትዮጵያ ራእየ ዮሐንስን በተመለከተ በድሬዳዋ አድርገን ነበርና ዕድሉን ለሰሜኑ ለመስጠት፣ በመጨረሻም ከደሴ እስከ ደብረ ማርቆስ ላሉት ማዕከል ናትና ለአካባው ነዋሪዎችም አማራጭ ለመስጠት የታሰበ ነበር፡፡

ከመጀመሪያው ጀምሮ ሦስት አካላት ለመርሐ ግብሩ መሳካት ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአግዮስ ዋናው ቢሮ፤ በጎንደር ከተማ የሚገኙት የጎንደር ከተማ ወጣቶች ጥምረትና ሁለቱ የዝግጅት ኮሚቴው መሪዎች (ዲያቆን ሙሉቀን ብርሃኑና ዲያቆን ኢንጂነር መላኩ እዘዘው)፡፡
                                       የጉባኤው ተሳታፊዎች
አስቀድሞ መርሐ ግብሩ የተያዘው በታየ በላይ ሆቴል ነበር፡፡ ይህንን መሰል መርሐ ግብር በከተማዋ ማካሄድ የተለመደ ባለመሆኑ ለመጥራት የታሰበው ከአራት መቶ የማይበልጡ እንግዶችን ነበር፡፡ በኋላ ግን የከተማዋም ሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ፍላጎት እየጨመረ መጣ፡፡ መርሐ ግብሩንም በሌላ ቦታ ማከናወን የግድ ሆነ፡፡  በዚሁ አጋጣሚ አስቀድሞ አዳራሹን በአነስተኛ ዋጋ በመስጠት፣ በኋላም ቦታው ሲቀየር ያስያዝነውን ገንዘብ በመመለስ የታየ በላይ ሆቴል ያደረገውን ትብብር እዚህ ላይ አመስግነን እናልፋለን፡፡
                       የጥናት አቅራቢዎች
ለሰፊው መርሐ ግብር የተመረጠው ቦታ በጣልያን ዘመን የተሠራውና በጎንደር ከተማ እምብርት የሚገኘው የጎንደር ሲኒማ ቤት ነው፡፡ ሲኒማ ቤቱን የሚፈቅደው የከተማዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በመሆኑ ዲያቆን ሙሉቀን የከተማውን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ባልደረባን አናገራቸው፡፡ እርሳቸውም ፈቃደኛ ሆነው አዳራሹን እንድንከራይ ደብዳቤውን ወደሚመለከተው አካል መሩት፡፡ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊው አቶ ጌታሁንም ለዚህ መርሐ ግብር አዳራሽ መከራየት የለባችሁም ብለው በነጻ ፈቀዱልን፡፡ የከተማው ከንቲባም መርሐ ግብሩን በደስታ ተቀበሉት፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም የሚቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ መመሪያ ሰጡ፡፡
የከተማው ሲኒማ ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን ምንም መርሐ ግብር እንዳልያዘ ተረጋገጠ፡፡ ለሌሎች በኪራይ ይሰጥ የነበረው አዳራሽም በነጻ ተፈቀደ፡፡ ማስታወቂያውም ተቀይሮ ወደ ጎንደር ሲኒማ ቤት ተዛወረ፡፡ የታተመው የመግቢያ ካርድ 800 ያህል ነበር፡፡ ከጎንደር ዙሪያ ከተሞች፣ ከባሕርዳር፣ ከደብረ ታቦር፣ ከደብረ ማርቆስ፣ ከሞጣ፣ ከወልድያና ከሌሎችም ከተሞች መርሐ ግብሩን ለመሳተፍ የሚጠይቁ ሰዎች በመብዛታቸው ስማቸውን በስልክ መመዝገብ ተጀመረ፡፡

ፋና ሬዲዮ ዋናው ጣቢያ፣ ፋና ሬዲዮ የጎንደር ጣቢያና የባሕርዳር ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች መርሐ ግብሩን የተመለከቱ ማስታወቂያዎችንና ፕሮግራሞችን መሥራታቸው ከጎንደር ከተማ ወጣ ባካሉ ከተሞች የሚገኙ ተሳታፊዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርገውታል፡፡
የከተማው የሥራ ኃላፊዎች፣ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሥራ አስኪያጅና የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች፤ የጎንደር ወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሥራ ኃላፊዎች፣ የከተማው አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በኣታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ቤት መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም የሐዲሳት ትርጓሜ ትምህርት ቤት መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የአቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል የቅኔ ጉባኤ ቤት መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የሠለስቱ ምእት የመጽሐፈ መነኮሳት ትርጓሜ መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ የብሉያት ምስክር ትምህርት ቤት መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የመንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባኤያት የምስክር ተማሪዎች፣ በደብረ ብርሃን ሥላሴ የገለዓድ የቅኔ ትምህርት ቤት መምህርና የምስክር ተማሪዎች፣ የመካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም የአቋቋም መምህርና የምስክር ተማሪዎችና ሌሎችም ታላላቅ ሊቃውንት ተጋብዘዋል፡፡
በጎንደር ከተማ ከ4000 በላይ የአብነት ተማሪዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ሁሉ እየመገበ የሚያስተምረው ደጉ የጎንደር ከተማ ሕዝብ ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ለመጥራት ብንፈልግ እንኳን ሁሉንም የሚይዝ አዳራሽ ግን በከተማዋ ውስጥ የለም፡፡ በዚህም ምክንያት ልንጋብዝ የቻልነው አስመስካሪዎችን (የዶክትሬት ተማሪዎችን) ብቻ ነው፡፡
መርሐ ግብሩን ለመሳተፍ ከዱባይ፣ ከአውስትራልያ፤ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተማ እንግዶች ወደ ጎንደር ተጉዘው ነበር፡፡ ታኅሣሥ 19 ቀን በጎንደር ልደታ ቤተ ክርስቲያን የአኮቴት መንፈሳዊ የሌቴቭዥን መርሐ ግብር የልደት በዓል ዝግጅት ቀረጻ ስለነበረው ሁለቱንም መርሐ ግብሮች በካሜራ ለማስቀረት የወንድ ወሰን ዲጂታል ስቱዲዮ ባለቤት አቶ ወንድ ወሰን ከአዲስ አበባ፣ ወንድማችን ደረጀ ደግሞ ከዱባይ በሥፍራው ለቀረጻ ተገኝተው ነበር፡፡ በአጠቃላይ ከአዲስ አበባ ሃያ ልዑካን በሥፍራው ተገኝተዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊው አቶ ጌታሁን
እሑድ ታኅሣሥ 20 ቀን ከቀኑ ሰባት ሰዓት አዳራሹ ሲከፈት የከተማው ሕዝብ እንደ ንብ ነበር የተመመው፡፡ የጎንደር ከተማ ወጣት ማኅበራት ጥምረት አባላት አዳራሹን በማስተካከል፣ ባነሮቹን በመለጠፍ፣ እንግዶቹን በማስተናገድ፣ ካርድ የያዙትን ካልያዙት በመለየት፣ ሊቃውንቱንና ሽማግሌዎችን፣ እናቶችንና እንግዶችን ቅድሚያ በመስጠት ባይተባበሩ ኖሮ ያንን ሁሉ ሕዝብ ማስተናገድ ከባድ በሆነ ነበር፡፡ አዳራሹ የሞላው በተከፈተ በ30 ደቂቃ ውስጥ ነው፡፡ የጥምረቱ ወጣቶች የሲኒማ ቤቱ ላይኛውን ክፍል በማስከፈት የመጥሪያ ካርድ ያልያዙት ተሳታፊዎች ወደ ፎቅ እንዲገቡ አደረጉ፡፡ አዳራሹ ወንበር በያዙ፣ መሬት ላይ በተቀመጡና ቆመው በሚከታተሉ ታዳሚዎች ተሞላ፡፡
መርሐ ግብሩ የተጀመረው በብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎት ሲሆን ቀጥሎም ዲያቆን ምንዳየ ብርሃኑ መዝሙር አቀረበ፡፡ ከዚያም የመጽሐፉን አዘገጃጀት በተመለከተ ገለጻ ተደረገ፡፡ ከገለጻው በኋላ ሦስቱ ምሁራን ወደ መድረክ እንዲመጡ በአወያዩ በዐሥራት ከበደ ጥሪ ቀረበ፡፡
ዶክተር ውዱ ጣፈጠ፣ ዶክተር አምሳሉ ተፈራና ሠርጸ ፍሬ ስብሐት ወደ መድረክ ወጡ፡፡ የመጀመሪያውን ዕድል ያገኙት ዶክተር ውዱ ጣፈጠ መጽሐፉ ከታሪክ አንጻር ያለውን ፋይዳ ተነተኑ፤ ዶክተር አምሳሉ ተፈራ ደግሞ ለመንፈሳውያን መሪዎች የሚኖረውን ፋይዳ አመለከቱ፣ ሠርጸ ፍሬ ስብሐትም ቅርስንና ታሪክን ከመዘገብ አንጻር ያለውን ፋይዳ ገለጸ፡፡
ከገለጻው በኋላ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆነ፡፡ ከሊቃውንት፣ ከምሁራንና ከከተማው ነዋሪዎች አያሌ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ተነሡ፡፡ ከመጽሐፉ አልፈው ታሪክንና ቅርስን፣ ባህልንና ማንነትን፣ የትምህርት ተቋማትንና የተተኪውን ትውልድ ድርሻ፣ የቤተ ክህነትንና የሊቃውንቱን ኃላፊነት የተመለከቱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ቀርበዋል፡፡ የመድረኩ አቅራቢዎችም ያላቸውን ሃሳብ አካፍለዋል፡፡
        ከጎንደር ከተማ የተበረከተ ስጦታ
በመርሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም መምሪያና የጎንደር ማዕከል ለመጽሐፉ አዘጋጅ ያዘጋጁትን ስጦታ በብጽዕ አቡነ ኤልሳዕ በኩል አበርክተዋል፡፡ መርሐ ግብሩም በብጹዕ አቡነ ኤልሳዕ ጸሎት ተዘግቷል፡፡
   ከማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማዕከል የተበረከተ ስጦታ
ከአዳራሹ መርሐ ግብር በመቀጠል ጉዞ የተደረገው የከተማው ከንቲባ ለልዑካን ቡድኑ ወዳዘጋጁት እራት ነበር፡፡ የጎንደርን ከተማ መርሐ ግብር ልዩ ከሚያደርጉት አንዱ የከተማው ከንቲባና የከተማው ባህል ቱሪዝም መምሪያ በንቃት የተሳተፉበት፣ ቢሮክራሲ ሳያበዙ ጉዳዩን ጉዳያችን ብለው የሠሩበት፣ በመርሐ ግብሩም ላይ በንቃት የተሳተፉበት፣ በመጨረሻም ለልዑካኑ የእራት ግብዣ ያደረጉበት መሆኑ ነው፡፡ የከተማው አስተዳደር ድጋፍ ከመርሐ ግብሩ መወጠን ጀምሮ እስከ ፍጻሜው የዘለቀ ነበር፡፡
               ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የተበረከተ ስጦታ
ለዚህ መርሐ ግብር መሳካት የከተማው ከንቲባ አቶ ጌትነት አማረና የባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊው አቶ ጌታሁን ሥዩም ያደረጉት አስተዋጽዖ በጉባኤው በተገኙት የከተማዋ ነዋሪዎች ሁሉ ያስመሰገናቸው፣ ከሌሎች ቦታዎች በመጡት እንግዶችም ያስደነቃቸው ነበር፡፡ ከእነርሱም በተጨማሪ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ የጎንደር ከተማ ወጣት ማኅበራት ጥምረት ይህ ቀረሽ የማይባል ሥራ ሠርተዋልና ይመሰገናሉ፡፡
              የከንቲባው የእራት ግብዣ
እንግዶቹ ያረፉበት የጃን ተከል ሆቴል  ባለቤት አቶ ተመስገን አምስት ክፍሎችን በነጻ በመስጠት፣ ለሌሎች ደግሞ ቅናሽ በማድረግ ለመርሐ ግብሩ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽ አድርገዋል፡፡ አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ወንድማችን ለመርሐ ግብሩ የተዘጋጀውን ውኃ በራ ወጭ ያቀረበ ሲሆን፣ ዳሽን ቢራ ደግሞ ሌሎች ወጭዎችን በመሸፈን አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
ይህ መርሐ ግብር እንዲሳካ ቀን ከሌት የጣረው ዲያቆን ሙሉቀን ብርሃኑን ሁሉም ሰው እድሜ ከጤና ያድልህ ብሎታል፡፡ አብሮት ነገሮችን ሁሉ ሲያመቻች የቆየውን መልአኩ እዘዘውንም እንዲሁ፡፡
የጎንደር መርሐ ግብር በክልል ከተሞች ጠንክረን መሥራት እንዳለብን የተማርንበት፤ ከኳስና ከዘፈን፣ ከጫትና ከጌም ውጭ ቁም ነገር ትቷል ብለን የምንወቅሰው ወጣት ለቁም ነገር ያለው ትጋት ያየንበት፤ ቀና የሆኑና ለሥራ የተነሡ የመስተዳደር አካላት ከተገኙ ሕዝብና መንግሥት ተቀራርበው በመሥራት የተግባቦት ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ የታየበት፣ ‹እኛ ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፣ የሰማዩም አምላክ ያከናውንልናል› የተባለውን ቃል በተግባር ያየንበት መርሐ ግብር ነበረ፡፡
                የጎንደር ከተማ ከንቲባ 
የጎንደር ከተማ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይነቱና ደግነቱ ገና ያልጠፋበት፣ ለታሪኩና ለባሕሉ የሚቆረቆር፣ ሳይሰቀቅ ከየሀገሩ የሚመጡ ተማሪዎችን አብልቶ አሳድሮ የሚያስተምር፣ ባወቁት ቁጥር ይበልጥ የሚናፈቅ ሕዝብ መሆኑን አይተናል፡፡ ያኑርልን፡፡
(የጉባኤውን ሥዕላዊ መግለጫ በጦማሩ በስተቀኝ በሚገኘው ቦታ ላይ ይመልከቱ)

40 comments:

 1. I wish i was there!!! Those who attend this ceremony are lucky

  ReplyDelete
 2. የጎንደር ከተማ ሕዝብ እንግዳ ተቀባይነቱና ደግነቱ ገና ያልጠፋበት ... ባወቁት ቁጥር ይበልጥ የሚናፈቅ ሕዝብ መሆኑን አይተናል፡፡ 100% right!!!

  ReplyDelete
 3. የጎንደር መርሐ ግብር በክልል ከተሞች ጠንክረን መሥራት እንዳለብን የተማርንበት፤ ከኳስና ከዘፈን፣ ከጫትና ከጌም ውጭ ቁም ነገር ትቷል ብለን የምንወቅሰው ወጣት ለቁም ነገር ያለው ትጋት ያየንበት፤ ቀና የሆኑና ለሥራ የተነሡ የመስተዳደር አካላት ከተገኙ ሕዝብና መንግሥት ተቀራርበው በመሥራት የተግባቦት ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ የታየበት፣ ‹እኛ ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፣ የሰማዩም አምላክ ያከናውንልናል› የተባለውን ቃል በተግባር ያየንበት መርሐ ግብር ነበረ፡፡

  ReplyDelete
 4. ዲ/ን ዳንኤል፡- እግዚአብሔር ረዥም ዕድሜ ከሙሉ ጤናና ፍጹም ጸጋ ጋር ያድልልን፡፡ ሌላ ምን ይባላል በቃ ኑርልን ክፉ አይንካብን፡፡

  ReplyDelete
 5. Dn. Daniel antenim Yaqoyiln. rejim edme setitoh bizu lemesirat yabikah . Amen.

  ReplyDelete
 6. አንቀጸ ሰላምJanuary 9, 2014 at 4:57 PM

  አንቀጸ ሰላም
  ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት እንኳን ደስ አለዎት!!! መጨረሻዎትን አምላክ ያሳምርልዎት:: ከዕውቀትና ጥበብ መፍለቂያና ማስመስከሪያ ከጎንደር፥ ከታላቁ አባት ከአቡነ ኤልሳዕ ደግሞ መኾኑ ሹመቱን ልዩ ደርገዋል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. yigebawal kekifu yisewrih Dn. Daniel

   Delete
 7. DANI STTEFE MINGETEMEBN BLENE TECHENKEN NEBER የጎንደር ሊቃውንትን በረከት አብዝቶ ያድልህ

  ReplyDelete
 8. በጣም ደስ ይላል፡፡

  ReplyDelete
 9. ከአራቱ ሃያላን 5ኛ መለስ መሆኑ ነው ፡፡ በፊት በተሰሩት ዲዛይናቸው ባለቀ በነ አባይ ግድብ ፣ በቀለበት መንገድ ሞሽረህ ማቅረብህ ፡ በጣም አከብርሃለው ግን እስቲ ተወው ፖለቲካውን የሰማዩን መንገድ አሳየን ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. wendme/ehte, ye meles poster dani yesekelew aydelem. Ye cinema betu poster new. neger menekakat tiru aymeslegnim

   Delete
  2. I was there, I think you missed something. The picture of the former PM was posted before six months. It wasn't done intentional.

   Delete
 10. ዳኒ ደስታዬን መግለጽ ተስኖኝ እንባ ተናነቀኝ ሰላሙንና ጤናውን ያብዛልህ

  ዲያቆን ሙሉቀንና መላኩ አዘዘው እግዳ ተቀብሎ መልካም ነገር ለመስራት
  ቅኖች ሆናችሁ በገኝታችሁ ገና ብዙ ሥራ በጎንደር ከተማ ይሰራል

  ReplyDelete
 11. dani sele waldbas men alk? weldban ersahwe enda?

  ReplyDelete
 12. እግዚአብሔር ያለ አንዳች አይተወንም ……. በርታ ዳኒ ሌላ እንዳልጨምር አንደበት ያንሰኛል ቤተሰቦችህን እግዚአብሔር ይጠብቅልህ ውድ ወንድማችን!!!

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሔር ያለ አንዳች አይተወንም ……. በርታ ዳኒ ሌላ እንዳልጨምር አንደበት ያንሰኛል ቤተሰቦችህን እግዚአብሔር ይጠብቅልህ ውድ ወንድማችን!!

  ReplyDelete
 14. አይኖቼ በእምባ ተሞልተው ነው አንብቤ የጨረስኩት በአዲስ አበባው ምረቃ ላይም ነበርኩ ያኔ የታየኝ ያንተ ድካም ለብቻህ እንዴት ይዘለቃል በማለት ነበር ብዙ ያልተነኩ ነገሮች ገና ስላሉን:: አሁን ግን ሌሎች ገና ብዙ የሚሰሩ ለሚሰሩም ክብር የሚሰጡ አሉን ተመስገን::

  ReplyDelete
 15. I am proud of being the part of the ceremony at Gondar. God bless you!

  ReplyDelete
 16. I am proud of being a part of the ceremony at Gondar. Dn. Daniel Igziabher Yobarkih.

  ReplyDelete
 17. ለከተማው ከንቲባና ለባህልና ቱሪዝም ሃላፊዎች ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ የራሳቸውና የሚመሩት ህዝብ ጉዳይ መሆኑን ከልብ ተገንዝበዋልና፡፡ ለማንኛውም ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ከልብ ምስጋና እናቀርብልሃለን፡ እግዚአብሄር ጸጋውን አብዝቶ ይጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 18. ድሮም ጎንደሪ ከ ጥንት ከ አባቱ የወርሰው ነው ሰውን ምክበር በህላችን ነው!
  ድሮም 44ቱ!!

  ReplyDelete
 19. ለከተማው ከንቲባና ለባህልና ቱሪዝም ሃላፊዎች ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል፡ የቤተክርስትያን ጉዳይ የራሳቸውና የሚመሩት ህዝብ ጉዳይ መሆኑን ከልብ ተገንዝበዋልና፡፡ ለማንኛውም ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ከልብ ምስጋና እናቀርብልሃለን፡ እግዚአብሄር ጸጋውን አብዝቶ ይጠብቅህ፡፡

  የጎንደር መርሐ ግብር በክልል ከተሞች ጠንክረን መሥራት እንዳለብን የተማርንበት፤ ከኳስና ከዘፈን፣ ከጫትና ከጌም ውጭ ቁም ነገር ትቷል ብለን የምንወቅሰው ወጣት ለቁም ነገር ያለው ትጋት ያየንበት፤ ቀና የሆኑና ለሥራ የተነሡ የመስተዳደር አካላት ከተገኙ ሕዝብና መንግሥት ተቀራርበው በመሥራት የተግባቦት ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ የታየበት፣ ‹እኛ ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፣ የሰማዩም አምላክ ያከናውንልናል› የተባለውን ቃል በተግባር ያየንበት መርሐ ግብር ነበረ፡፡

  ReplyDelete
 20. i have nothing to say just i am crying when i read this article . and i proud by the people of Gondar . i know people's of Gondar are honest, respectful, loyal and confident and also they know it how treat gusts .
  dn.Daniel please keep it up doing such good things.
  God bless u!!

  ReplyDelete
 21. the Arch bisho of north gondar diosis Abune Elsa has gave a title to Dn. Daniel as "ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት" from now and then we all shall call him on his name bravo dani!! be sure your next book will also be here

  ReplyDelete
 22. What can I say? just God bless you.

  ReplyDelete
 23. Temesegen Amlakachen Babatoches fenta legoch Teeledulesh Yetebalew kale eyetefeseme bemayetachen Dn. Daniel Edemehen Yarzemelen.

  ReplyDelete
 24. D/N Daniel lemtadergew menfesawi tiret hulu Egziabhier Amlak edeme ena tena yestih

  ReplyDelete
 25. ውድ የኢትዮጽያ ልጅ ዳኒኤል ክብረት እግዚአብሔር ይባርክህ ጎንደር የኢትዮጽያ ቅርስ ናትና እንከባከባት

  ReplyDelete
 26. GREAT did dani!!! abe Mekellem begugut eyetebekin new!!!!

  ReplyDelete
 27. "ሙሓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት" እውነትም መንገዱ ለጠፋብን ለዘመኑ ሰዎች የጥበብ ምንጫችን ነህ ዳኒ፣ እግዚአብሔር አምላክ ጸጋዉን አብዝቶ ይስጥልን፣ ገና ብዙ እንጠብቃለንና

  ReplyDelete
 28. I wish I could attend it, I would be lucky to be part of it .....Long live Daniel , love Gonder !

  ReplyDelete
 29. ዳኔ ለደስታየ መግለጫ ሌሆን የሜችለው ያው ምርቃት ስለሆነ የቀራንዮው ንጉሥ አብዝቶ ይስጥሕ ፧ ልጆቾሕን ተተኪ ያርግልሕ ።አሜን !

  ReplyDelete
 30. Amen,Dn.Daniel,yibel blenal,edmena tena yistlen

  ReplyDelete
 31. God bless u n ur family,we proud of u bro..i leave in uk,how can i get the book pls diakon danel?

  ReplyDelete
 32. i leave in uk so how can i get the book pls diakon?

  ReplyDelete
 33. tebarek bro,we proud of u.

  ReplyDelete