Monday, December 9, 2013

ድንገቴ

መምህሩ ናቸው፤ የእነዚህን ባለሀብቶች የሕይወት ታሪክ ሥሩ ብለው የሰጡን፡፡ ስምንት ባለ ሀብቶች፡፡ እነዚህን ሰዎች የምናውቃቸው በቴሌቭዥን እየቀረቡ ስለ ልማት ሲናገሩ ነው፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ተሸልመዋል፡፡ እኛ መምህራችንን ጠየቅናቸው፡፡ እነዚህን ለምን መረጧቸው? ስንል፡፡ እርሳቸውም ‹‹እነዚህን በሦስት መመዘኛ መረጥኳቸው›› አሉ፡፡ ‹‹አንደኛ ልማታውያን ናቸው፣ ሁለተኛ ተሸላሚ ናቸው፣ ሦስተኛ ደግሞ ዛሬ ቢጠሯቸው የማይሰሙ የናጠጡ ባለጠጎች ናቸው፡፡›› አሉ መምህራችን፡፡ ‹‹ስለዚህም ወጣቱ ትውልድ ከእነርሱ ትምህርት መቅሰም አለበት፡፡ ሀብት እንዲሁ አይገኝም፡፡ ተለፍቶ ነው፤ ተደክሞ ነው፡፡ ደም ተተፍቶ ነው፡፡ ‹ፐ› ላይ ለመድረስ ከ‹ሀ› መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ከዕንቁላል ንግድ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከሱቅ በደረቴ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከአንዲት ሱቅ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከጉልት ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ እነዚህ ለትውልዱ አርአያ ናቸው›› አሉን መምህሩ፡፡
ስምንት ቡድን ተቋቋመ፡፡ ስምንቱ ቡድኖች አንዳንድ ሚሊየነር ያዙ፡፡ ታሪካቸውን የምንሠራበት ቅጽ ተሰጠን፡፡ የመጀመሪያዋን ብር እንዴት አገኟት? ወደ ሚሊየነርነት በየት መንገድ ተጓዙ? ምን ዓይነት ውጣ ውረዶችን አለፉ? እያንዳንዷን ሀብት እንዴት አጠራቀሟት? የሚሉ ጥያቄዎች ተሰጡን፡፡ እኛም የደረሱንን ባለሀብቶች እያነሣን ‹የኛ ባለሀብት ምርጥ ታሪክ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ እንዲህ እና እንዲያ ሰምተናል እያልን እንፎካከር ጀመር፡፡ በቡድን የተሰጠኑንን ባለሀብቶች ታሪክ ሠርተን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለመገናኘትና የደረስንበትን ለመወያየት ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡

ከሁለት ሳምንት በኋላ በመወያያ ክፍላችን ስንገናኝ ሁላችንም ፈገግታችንን ለባለሀብቶቹ ሽጠንላቸው የመጣን ይመስል እንዳኮረፍን ነበርን፡፡ ሁሉም እንደ ነፋስ አቅጣጫ መጠቆሚያ ራሱን ይወዘውዛል፡፡ መምህራችን እስኪመጡ ድረስ የረባሽ ስም ይጻፋል የተባልን ይመስል ዝም እንዳልን ነበር፡፡
መምህሩ መጡና ‹በሉ የደረሳችሁበትን አቅርቡ› አሉን፡፡ ሁሉም ዝም አለ፡፡ ‹‹የቤት ሥራችሁን አልሠራችሁም ማለት ነው?›› አሉን፡፡ ዝም፡፡
የመጀመሪያውን ቡድን ጠሩ፡፡ ልጀቹ ወጡ፡፡
‹‹እኛ ያገኘናቸው ባለሀብት ምንም ነገር አልነበራቸውም፡፡ የሀብት ማግኛ መንገዳቸውም ‹ማመቻቸት› ይባላል፡፡ድንገት አንድ ዘመዳቸው ከአንድ ድርጅት በርካሽ የግንባታ ማሽነሪዎችን እንዲገዙ አመቻቸላቸው፡፡ ማሽነሪዎቹንም ለመግዛት ከባንክ ብድር ተመቻቸላቸው፡፡ ብድሩንም ለመውሰድ ኳላተራል ተመቻቸላቸው፡፡ በዚህም የተነሣ በአንድ ጊዜ በሁለት እጅ የማይነሡ ባለሀብት ሆኑ፡፡››
‹‹እሺ ከድህነት እንዴት ነው ወደ ባለሀብትነት የተለወጡት፣ ሂደቱ ምን ይመስል ነበር››
‹‹ምንም ሂደት የላቸውም፡፡ በድንገት ተነሡ፤ በድንገት አደጉ፤ በድንገት ተመነደጉ››
እሺ እናንተስ› አሉ ወደ ሁለተኛው ቡድን ዞረው፡፡ ልጆቹ ተነሡ፡፡
‹‹የኛ ባለሀብት ምንም ነበሩ፡፡ የሀብት መንገዳቸውም ‹ማስገባት› ይባላል፡፡ ድንገት አንድ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሕንጻ ሲሠሩ ታዩ፡፡ ምንድነው ተብሎ ሲጣራ ሚስታቸው የእነ እንትና ዘመድ ናቸው አሉ፡፡ እንዴው አንድ ቀን ነው አሉ፡፡ መኪና ሙሉ ሞባይል ጭነው ከሐርቲሼክ አዲስ አበባ የገቡት፡፡ ፈታሾቹም ምን አፍዝ አደንግዝ እንደተደገመባቸው አይታወቅም እንደ ኤድስ ማስታወቂያ አላየንም አልሰማንም ብለው አሳለፏቸው፡፡ ይሄው ሚሊየነር ሆኑ››
‹እናንተስ›› አሉ ገርሟቸው ሦስተኛዎቹን ቡድኖች
‹‹የኛ ባለሀብት ደግሞ ንክኪ ናቸው ይባላል፡፡ ሳይነካኩ በፊት ግንበኛ ነበሩ፡፡ ከተነካኩ በኋላ ግን በሞቱ ሰዎች ስም ሳይቀር መሬት እየወሰዱ ቸበቸቡት፡፡ አሁን ስለ መሬት ፍትሐዊ አጠቃቀም ትምህርት የሚሰጡ የሪል ስቴት ባለሀብት ሆነዋል፡፡ ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው›› አለ የቡድኑ መሪ፡፡
አራተኛው ቡድን ተነሣ፡፡
‹‹የኛው ለየት ይላሉ፡፡ የሀብት ማግኛ መንገዳቸውም ‹መጠጋት› ይባላል፡፡ ከአንድ ሀብታም ሰው ጋር አንድ ወዳጃቸው ያገናኛቸዋል፡፡ የእርሳቸው ሥራ ሀብታሙ ሲያዝን እርሳቸው ማልቀስ፣ ሀብታሙ ሲስቅ እርሳቸው መንከትከት፣ ሀብታሙ ሲያመው እርሳቸው መርፌ መወጋት፣ ሀብታሙ ሲሸተው እርሳቸው ማነጠስ፣ ሀብታሙ ሲናደድ እርሳቸው መደባደብ ብቻ ሆነ፡፡ ከዚያም እርሳቸውም ሳያስቡት፣ ኧረ እንዲያውም ሳያውቁት ሚሊየነር ሆነው ተገኙ፡፡
አምስተኛው ቡድን ቀጠለ፡፡
‹‹እኒህኛው ባለሀብት ‹መሰጠት› በተባለው መንገድ ነው ሀብት ያገኙት፡፡ ምን ነገር አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን በአንድ ባለ ሥልጣን አማካኝነት እኔ ነኝ ያሉ ፕሮጀክቶች ሁሉ ይሰጧቸው ጀመር፡፡ ቢወዳደሩም ያልፋሉ፤ ባይወዳደሩም ያልፋሉ፡፡ እንኳን የመንግሥት የኤን ጂ ኦ ፕሮጀክቶችም ይሰጧቸዋል፡፡ እነሆ በዚህ መንገድ ዛሬ የሀገሪቱ ወሳኝ ባለሀብት ሆነዋል››
ስድስተኛው ቡድን ተከተለ፡፡
‹‹የኛ ባለሀብት የሀብት መንገድ ‹ብቻ› ይባላል፡፡ አንድን ዕቃ ለማስገባት የሚፈቀድላቸው ‹እነ እገሌ ብቻ› ናቸው፡፡ ስለዚህም በፈለጉት መንገድ የፈለጉትን ዓይነት ዕቃ ያስገባሉ፡፡ በፈለጉት ዋጋም ይሸጣሉ፡፡ መመሪያቸው ብትፈልግ ግዛ ባትፈልግ ተወው ነው፡፡ እኒህ ባለ ሀብት ከዐሥር ዓመታ በፊት አንዲት የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ብቻ ነበረቻቸው፡፡ በአንድ እርሳቸውም በማያስታውሱት ቀን ግን የሆነ ዕቃ ‹ብቸኛ አስመጭ› እንዲሆኑ ተሾሙ፡፡ ተሾመውም አልቀሩ ይኼው ሚሊየነር ሆኑ፡፡
‹ሰባተኛውስ ቡድን› አሉ መምህሩ
‹‹የኛው ሰው የሀብት መንገድ ‹ትብብር› ይባላል፡፡ እርሳቸው መርካቶ ሱቅ ከፍተው ከዱባይ ዕቃ ያመጡ ነበር፡፡ እንድ ባለ ሥልጣን ግን ‹ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ ረዳት እንፍጠርልዎ› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ተስማሙ፡፡ ረዳት የመንግሥት ባለ ሥልጣንም ተፈጠረላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሸሪክ ሆኑ፡፡ እነሆም መንገዱን እርሱ ሲጠርግ ሥራውን እርሳቸው እየሠሩ ባለሀብት ተባሉ፡፡
ጉድ ነው ዘንድሮ አሉ መምህሩ፡፡ ስምንተኛው ቡድን ቀጠለ፡፡
‹‹የዚህኛው መንገድ ‹ቀንዶ› ይባላል፡፡ ባለ ሀብቱ ከብት እያረዱ በመሸጥ ይታወቃሉ፡፡ አንድ ሰው ግን ከብት እዚህ ከምትሸጥ ለምን ድንበር ሄደህ አትሸጥም አላቸውና፡፡ ወሰዳቸው፡፡ የሀገሪቱንም የቀንድ ከብቶች ድንበር እያሻገሩ ሶማሌና ሱዳን መላክ ጀመሩ፡፡ ሰውም ቀንዶ ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ቀንዳም ባለሀብት ሆነዋል፡፡
መምህሩ ተነሡና አፈጠጡብን፡፡
‹እና ታሪካቸው ይኼ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህ አልፈው፣ እንዲህ ሆነው፣ ይህን ተፈትነው፣ ይህንን ውጣ ውረድ አልፈው፣ ይህን ልምድ ቀስመው የሚባል ታሪክ የላቸውም ማለት ነው?›› አሉ መምህሩ፡፡
አንዱ ጓደኛችን ተነሣና ‹‹አዎ፤ ሀብት እንጂ ታሪክ የላቸውም፡፡ ሀብታቸው ድንገቴ ነው፡፡ በቃ ድንገት ተነሥተው እንደ ሮኬት ተተኮሱ፡፡ በቃ፡፡ ከአንድ ቀጥለው ሚሊየን ነው የቆጠሩት፡፡››
‹‹ታድያ እንዴት ነው ለእናንተ አርአያ የሚሆኑት›› አሉ መምህሩም ተናደው፡፡
‹‹አርአያ ባለ መሆን ነዋ› አልናቸው፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው 

53 comments:

 1. ሁላችንም ዙሪያችንን ጠንቅቀን ካስተዋልን ከሥምንቱ ባለሃብቶች ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ያለው ሰው አናጣም ጉዳዩ ስር የሰደደ በሽታ እየሆነ ነው ትውልድና ሀገርን የሚገድል

  ReplyDelete
 2. ዲ/ዳንኤል ጸጋውን ያብዛልህ በእውነት የምታነሳቸው ነጥቦች በጣም አይን ገላጭ፣አስተማሪ እና ትውልድን ቀራጭ ናቸው፡፡ እኔም ብሎግህን ሳላይ የማድርበት ቀን የለም ሳትጽፍ ስትቀር ሁሉ ቅር ይለኛል፡፡ ስለዚህ በርታ አስተማሪ የሆኑ ጽሑፎችን ከመጻፍ አትቆጠብ፡፡ በድግሜ ድንግል ማሪያም ትባርክህ ዘመንህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፡፡ ይህ አባባል ደስ ስላለኝ ኮፒ አድርጌዋለሁ በርታ፡፡ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው››

  ReplyDelete
 3. ዲ/ዳንኤል ጸጋውን ያብዛልህ በእውነት የምታነሳቸው ነጥቦች በጣም አይን ገላጭ፣አስተማሪ እና ትውልድን ቀራጭ ናቸው፡፡ እኔም ብሎግህን ሳላይ የማድርበት ቀን የለም ሳትጽፍ ስትቀር ሁሉ ቅር ይለኛል፡፡ ስለዚህ በርታ አስተማሪ የሆኑ ጽሑፎችን ከመጻፍ አትቆጠብ፡፡ በድግሜ ድንግል ማሪያም ትባርክህ ዘመንህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፡፡ ይህ አባባል ደስ ስላለኝ ኮፒ አድርጌዋለሁ በርታ፡፡ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው››

  ReplyDelete
 4. betam yemegerm new....Egzabhare yaberthi dn.daniel

  ReplyDelete
 5. በቅርቡ በሸገር ሬዲዮ ቡዙ ኢትዮጵያውያን ሚኒየነሮች እንዳሉ በጥናት ተረጋገጠ የሚልዜና ሰምቼ ነበር ክፍላቸው ከስምንቱ ውጭ ይሆናሉ የሚል ግምት የለኝም ታዲያ መንግስት የባለስልጣናትን/‹ትብብር› የሚሰሩትን/ የሀብት መጠን አሳውቃለሁ ካለ እነሆ አመታት አለፉ ሚኒየነሮችስ ብዛታቸው ብቻ ነው ወይስ ተምሳሌትነታቸው ……. ብዙ ነው ግን ምን መፍትሄ ምን ይሆን፡፡

  አድህነነ እግዚኦ እስመ ………

  ReplyDelete
 6. በሸገር ሬድዮ የተሰማዉ ዜና ላይ ጥናቱ ምን ያህል ደሀዎች እንደተፈጡሩ አልተናገሩም ?

  ReplyDelete
 7. Nice View!
  ‹‹ታድያ እንዴት ነው ለእናንተ አርአያ የሚሆኑት›› አሉ መምህሩም ተናደው፡፡
  ‹‹አርአያ ባለ መሆን ነዋ› አልናቸው፡፡

  ReplyDelete
 8. ማመቻቸት, ማስገባት, ንክኪ, መጠጋት, መሰጠት,ብቻ,ትብብር, ቀንዶ ስምንቱ ምስጢራተ ነዋይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማመቻቸት, ማስገባት, ንክኪ, መጠጋት, መሰጠት,ብቻ,ትብብር, ቀንዶ ስምንቱ ምስጢራተ ነዋይ

   Delete
 9. አሁን ስለ መሬት ፍትሐዊ አጠቃቀም ትምህርት የሚሰጡ የሪል ስቴት ባለሀብት ሆነዋል፡፡ ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው›› kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk Abo Yemechike kkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 10. ዲ/ዳንኤል በጣም እናመሰግናለን ለዚህ እኮነው ሀገሬን ድበሬን አላስነካም እቢ ለሀገሬ እንዳለው ጀግና አንተንም አባ ኮስትር በሌ ያልሁህ ።ሁሉንም አድርገዋል የቀራቸው የለም የቀራቸውን ድበር መቸብቸብ ጅምረዋል የያዛቸው ቀንዳሙ ነው ግን ሁሉም ሚሊየነሮች መክሰሪያቸው ደርሶል እንኮን ከኛ የወጡት ስንምቱ ባለሀት አሳልፈው ለአረብ ፣ለህንድ ለመሳሰሉት የሸጡት ይመለሳል ቅርብ ነው አይዘገይም ።አንተ ግን በርታ እግዚያብሔር ካንተ ጋር ይሁን ።ቸር ወሬ ያሰማን ።

  ReplyDelete
 11. really it is heart touching! this where we live and how we live! Enenes man yastegagn? lol

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳንኤል በጣም በጣም አድናቂህ ነኝ በርታ ሁሉም ፅሁፎችህ አስተማሪና አዝናኝ ናቸው እግዚአብሔር ዘመንህን ይባርክልህ፡፡

  ReplyDelete
 13. Dear Dn Daniel
  As a responsible citizen you have already done what is expected from you. From here on the readers of your blog, every sect of the society and any religious individuals should think about it and act accordingly. We have to pause and think. It is not all about money or material thing, let us think about life and death.
  Thank you Dani
  God bless you,as it is seen he already does it.

  ReplyDelete
 14. በሃገርችን ባሁኑ ሰአት ሁለት አይኔት ዜጉውች አሉ ፩ኛ፣ ሳይሰሩ በዘራቸዉና በፖሊቲካ ከዜሮ ቴነስተው ባንድ ሌሌት ሚልንየር የሚሆኑ ምሳሌ አዲስ አበባ ፎቅ ሁሉንም የሰሩ እንሱ ነቸው ፪ኛ፣ አብዛኛው ዚጎች ሲሆኑ ሜስራትና ሃብት ማፍራት እንኳን አይችሉም ከስረዉና በሀይል ግብር ከንግድ እንዲወገዱ ይደረጋል።
  ሴሙኑን ማንዲላ መሞቱን ሲሴማ ምናሌ ለኢትዮጵያ እንደሱ ያለ ሰው ቢኖር አሁን ካለንበት አፓርታይድ የሚያወጣን ብየ አሰብኩ፣ ወገንቴኝንትና አድሉ በእግዛብሄርም ያስቀጣል። ጌታ ክዚህ ሲጋዊ እርኩስ መንፌስ ያውጣን ሁላችኒም እኩል የሚንሆንበት ግዘ ያምጣ። አሜን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይዞህ ወንድሜ እነወደ ማንዴላ ያለ መሪ መምጣቱ አይቀሬ ነው የፊተኞች ሓለኞች ይሆናሉ የሚለው አምላካዊ ቃል ይፈፀም ዘንድ ነው ለማንዴላም በአፍሪካነቱ እንዲኮራ ያደረገችው የኛዋ እማማ ናት አይዞህ ።

   Delete
 15. ዲ/ዳንኤል ጸጋውን ያብዛልህ በእውነት የምታነሳቸው ነጥቦች በጣም አይን ገላጭ፣አስተማሪ እና ትውልድን ቀራጭ ናቸው፡፡ እኔም ብሎግህን ሳላይ የማድርበት ቀን የለም ሳትጽፍ ስትቀር ሁሉ ቅር ይለኛል፡፡ ስለዚህ በርታ አስተማሪ የሆኑ ጽሑፎችን ከመጻፍ አትቆጠብ፡፡ በድግሜ ድንግል ማሪያም ትባርክህ ዘመንህ ሁሉ የተባረከ ይሁን፡፡ ይህ አባባል ደስ ስላለኝ ኮፒ አድርጌዋለሁ በርታ፡፡ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው›› Wonderful view and comment

  ReplyDelete
 16. Replies
  1. Really, WOW!!! are you one of those "8"?

   It is not zibazinke, unfortunately, it is true. Thanks Dn. Daniel

   Delete
  2. አእምሮህ? ምናልባት ካለህ¡

   Delete
  3. We know that you are a son of one of illegal millioners. Hodam yehodam lij neh. Rash zibznke!

   Delete
  4. I do not think you know the meaning of the word, or you might be .....

   Delete
  5. ውድ ወንድሜ ዳንኤል፡-
   እንደምን አለህ
   በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ያነበብኩት ያንተን ብቻ ሳይሆን ምላሽ የሰጡህንም ሠዎች ጭምር ነበር፡፡ እስከዚህኛው ሠውዬ ድረስ የተሠጠህ ምላሽ ተመሳሳይ በመሆኑ፤ እኔ በግሌ ይህን የመሰለ ቆንጣጭ አመለካከት እንዴት ተጨበጨበለት ብዬ ግራ እያጋባኝ ነበር፡፡ ምክንያቱም የብላግህ ተደራሲያን በሙሉ ተመሳሳይ መደብ ያላቸው የመስሉ ስለነበረ፡፡ እዚህ ጋ ስደርስ ግን አመለካከትህ በትክክል ግቡን እንደመታ፣ ተደራሲያኑም ከአንድ መደብ ባላይ እንደሆንን ለማወቅ አስችሎኛል፡፡ በትክክል ግብ መትቷል፡፡ ቆንጥጧል፡፡ እረግቶ የተቀመጠውን እቋሪ ውሃ በጥብጧል፡፡ ይህ ለእኔ የመልዕክትህ ኦና አለምቅረት ምልክት ነው፡፡
   አንተ ሠው ነቢየ እግዚአብሔርነት እያየሁብህም ነው፡፡ ታዲያ ዋጋው በምድር ከባድ በሠማይም ግዙፍ እንደሚሆን አትጠራጠር፡፡ በርታ፡፡ አሁንም እራስክን ክደህ ትንቢትህን ቀጥል፡፡ ህዝብን፣ መንግስትን መልስ፡፡
   በእኛም ላይ እጅህን ጫንብን እና ቢያንስ ቢያንስ ደቂቀ ነቢያት እንድንሆን እርዳን፡፡
   ከጣና ዳር፡፡

   Delete
 17. You are always post on your blog the very interested and heart touching view in addition of this they are the current issue . specially they are very useful for change our properties
  ከቀበሌ ቤት ወጥተው ቀበሌ የሚያህል መሬት ወስደው ለቀበሌ ደንብ ማስከበር የሚያስቸግር የሀብታም ቀበሌ የሚሆን ሪል ስቴት እየገነቡ ነው፡፡ ይኼው ነው.
  this daniel tesfaye strictly day to day follow your blog .

  ReplyDelete
 18. Zibazike bileh yetsafikew minew fes yalebet honiksa lemin kenkenh ke 8tu andu selhonik new minehin/ mineshim letiewlid areya lihon yemichil tarik seleleleh/sh ye tiwild zikachna zibazinke endenante ayntu new Dn.Danii YE DINGEL LIJ MEDEHANIALEM ye agelilelot zemenhin yarizemilen

  ReplyDelete
 19. What an Incredible analysis! Daniel put it properly . This is the source of income and the type of millionaires we have. The Teacher said, some might have started from small boutique, or selling eggs, etc,. But, this is how it is. No hard working, through Menekakat, Metegagaat, etc,.

  ReplyDelete
 20. Oh! An artistic literature based on the present day Ethiopia. No one except who has ' in touch' on the ways the so called present day "Ethiopian wealthy" people denounce this fact.I and my generation is a living witness. Thanks D/n Daniel for all your effort to teach the generation. You are the icon of my generation and remembered in history. May God bless with your family!

  ReplyDelete
 21. Interesting and timely article, but I do not like this phrase ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ ረዳት እንፍጠርልዎ. The phrase is from religious article for sole companion, but used for .... Better not to use from the spiritual to .....

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree with you. Everything was great except that phrase. Let us have respect for the Word of God. Because we are going to answer for every lazy thing we say. Other than that Great article D/n Daniel!

   Delete
 22. ዘይገርም!!!!!!ሁሉም እውነት ነው; አምላክ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 23. ጥሩ መጣጥፍ ነው. ግን ደክመው በፊታቸው ወዝ ሚሊኒየር የሆኑትን አለመጥቀስህ ሁሉም ሰው ካልተሰረቀ ሀብታም አይኮንም ብሎ እንዲደመድምና የስራ ሞራሉ እንዲላሽቅ ስለሚያደርግ ጽሁፉ ምሉዕ ሆኖ አልተሰማኝም.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዳኒ ሃሳብ አሪፍ ነው፡፡ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ለምልከታው አድናቆቴ ከፍ ያለ ነው፡፡ ሆኖም፤ በቀለመወርቅ አስተያየት በጣም እስማማለሁ፡፡ ጥቂቶች በላባቸው በወዛቸው ሚሊንየር የሚሆኑም እንዳሉ መጠቀስ ነበረበት፡፡ ልምን ለሚለው ቀለመወርቅ ጥሩ ገልጾታል/ገልጻለች

   ገበታ

   Delete
 24. wey zibazinke yihe beahun gize behegerachin sir yesedede tilk chigir new. It is truth. wusha bebelabet yichohal. Thanks Dani. God Bless You.

  ReplyDelete
 25. ድንቅ ነው ዳኒ!!!! በርታ !!!!!

  ReplyDelete
 26. ዲ/ን ዳንኤል እግዜር ይስጥልን፡ ያነሳሃው ሃሳብ በጣም ትክክለኛና በጊዜውም በተወሰኑና በጥቂት ሰዎች እየተከነናወነ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ዲ/ን እኔ የኢትዮጵያን ጉዳይ፡ እጣፈንታ ባሰብኩ ቁጥር በጣም ይጨንቀኛል አለቅሳለሁም(እግዚአብሄር ሁሉን አዋቂ ቢሆንም እንደእኔ)፡ እንዲህ ለተፈጠሩባት፡ላዳጉባት፡ ሁሉንም ነገር ለሆነችላቸው ሃገር ለኢትዮጵያ መጥፎ ማሰብ፡ በዘር ከፋፍለው የሃገርን ታሪክ ማጥፋትና፡ ለዚህም ተልእኮ ማስፈጸሚያ የሚሆን ደባሪና መጥፎ ፖለቲካ ማርቀቅና መተግበር እውነቴን ነው በአለም ላይ ከኢህአዴግ በቀር ማንም ያልተገበረው ጉዳይ ነው፡፡ ይህችን ሃገር እግዚአብሄር ይሁናት፡ እግዜር ያስባት፡፡ ሁላችንም ባለንበት በርትተን እንጸልይ፡፡

  ReplyDelete
 27. የያዙትን ይዘው ቢበቃቸውስ?

  ReplyDelete
 28. አለቀስኩ፣ አቅመ ቢስ መሆናችንን ፣ ልቤ ተሰበረ

  ተዉኝ ነፍሴ ሽሽት ላይ ነች። ችግርን እያዩ ለችግሩ መፈት ሄ መስጠት አለመቻልን ያክል አቅመ ቢስነት የለም ልብ ይሰብራል። ራሴን በፊልማን በሙዚቃ ደብቂያለው። ''አቅም አጣን፣አቅም አጣን፣አቅም አጣን፣አቅም አጣን..,።'' ምንም መስማት አልፈልግም ተዉኝ ይህች አቅም አልባ ነፍሴ ትረፍ የዉሸት እረፍት ቢሆንም

  ReplyDelete
 29. ‹‹አርአያ ባለ መሆን ነዋ...

  ReplyDelete
 30. ‹‹አርአያ ባለ መሆን ነዋ......

  ReplyDelete
 31. ene yeselechegn gin zer mansat new ebakachhu zer minamn eyalachhu atileyayun yamal ende Dn daniel yalew neger megilets yishalal. zer meleyayet gin lemanachm aybejenm ena!

  ReplyDelete
 32. ዲያቆን ዳንኤል እኔም ፅሁፉን አነበብኩ፡፡ በፅሁፌ መሃል ግን ምናልባት ከስምንቱ አንዱ በእውነት ሰርቶ ሚሊየነር የሚሆን ይኖራል ብዬ አስቤ ነበር፡፡ ግን እንዴት ሁሉም ትክክል ባልሆነ መንገድ ሚሊየነር ሊሆን ይችላል? ለመሆኑ እኛ ሀገር ሚሊየነር የሚኮነው በዚህ ዐይነት መንገድ ብቻ ነው? አይመስለኝም! ግን ዳኒ ይህንን ብሎግ የሚያነቡ ወጣቶች የትኛውን የሚሊየነር ታሪክ ተከትለው ሀብታም ይሁኑ? ለኔ አልተመለሰልኝም፡፡ ምናልባት በኛ ሀገር ውሥጥ የተገኘ ኢትዮጵያዊ ሀብታም ሁሉ በመጠጋጋት፣ በማመቻቸት፣ ......ብቻ ሀብታም የሆነ ነው ማለት ነው? ሁላችንም ደሀ እና የደሀ ደሀ ሆነን መኖር የለብንም፡፡ አንዳንዱም በኢትዮጵያ ውስጥ ሚሊየነር መብዛቱ ያናደደው ይመስላል፡፡ በደቡብ አፍሪካ፣ በናይጄሪያ፣ በግብፅ፣ በኬንያ እና በሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ብዙ ሚሊየኖሮች አሉ፡፡ በኢትዮጵያም 2700 ሚሊየኖሮች ተፈጥረዋል የሚል ሰማሁ ደስ አለኝ፡፡ እኛኮ የእድር ሊቀመንበር እራሳችን መርጠን ለልጆቹ እና ለርሱ ልብስ በቀየረ ቁጥር በኛ ገንዘብ ነው የሚዘንጠው የምንል አይደለንም እንዴ? ሁሉንም በጥርጣሬ የምንመለከት ነን፡፡ እኔ ስሰማ የሚያስደስተኝ እና ስሰማ ያደኩት በቀለ ሞላ እንቁላል ሸጦ እዚህ ደረሰ የሚል ነበር አሁን ግን ......በበኩሌ ኢትዮጵያ ውስጥ 2700 አይደለም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሚሊየነር ቢኖር ደስ ይለኛል፡፡ ሌላውም እንጀራ እየበላ ነገ ደግሞ በተራው ሚሊየነር ይሆናል፡፡ ደግሞም ዘርፎ እና ገንዘብ ጠራርጎ መርካቶ በዶላር እየዘረዘረ አጥቦ ወደውጭ ከሚያሸሽ እዘሁ ሀገር ውስጥ ቀበሌ የሚያክል ሪል ስቴት ወይም ፋብሪካ ከፍቶ ለሌላውም ቢያስተርፍ እመርጣለሁ፡፡ ይህ ሁለተኛ ምርጫዬ እንጂ የመጀመሪያ ምርጫዬ በትክክል ሰርቶ ቢያመጣ ነው;; በሀገሬ ሚሊየነሮች ብዙ ተባዙ፡፡ እኔ ደሀ ሆኜ ለኔና ለልጆቼ የሚሆን ቤት እንኳን መስራት ቢያቅተኝም እናንተ እና ከናንተ ጋር ያለው ሲበላ ደስ ይለኛል፡፡ ሰርታችሁ የምትበሉ እና ሚሊየነር የምትሆኑ ብዙ ተባዙ፡፡ በሀብታችሁ ደስ ይለኛል እንጂ ከኋላችሁ ሆኜ ሰርቆ ነው ብዬ አላማችሁም፡፡ ስሩ ሌላውንም እንዲሰራ ፍቀዱለት፡፡ ገንዘብ አለን ብላችሁ ፍርድ አታጣሙ፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ይህንን ባይፅፍ ኖሮ እኔም እንዲህ አላስብም ነበር፡፡ ዳኒ በርታ፡፡ እንዲህም እንዳስብ መብት ስላለኝ ለምን እንደኛ አላሰበም እንዳትሉኝ፡፤ ሰውን መበደል የሚጀመረው እንደኔ አስብ በማለት ነው፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you so much Seife Michael Ejere. Ten years before I was very poor and my family were poor as well. I used to sell cloth in Merkato on the road. Then I bought small shop in Kolfa Atenatera. My sister run the shop and I distribute cloth for her and other people while I was working that I met a person that distribute cloth and we became very friendly then he told me about his business and I joined him. We work for five years and we became a milliner then people starting gossip. Most people said that I went to magic house "Tenkway Bate" God know that my heart I never been there for one day. That hurt me because I worked without any rest more than ten years but people give me bad name. So don't blame Daneil, it is Ethiopian culture when you change your self, they will say something without knowing you. God bless you.

   Delete
  2. Hahahah...this dude's English is so impeccable that he perfectly fits the profile of ye'Merkato selbaj negade!!! C'mon man, at least make some intentional mistakes in your grammers...endew at least don't use capital letters in the appropriate manner next time...you need more sophistication than this to become a good Kotteta'm cadre...alalefekem, try harder next time...may be you will succeed...

   Delete
 33. ye ante ayenetu men ale beta bale Dani berta

  ReplyDelete
 34. በጣም አድናቂሕ ነኝ እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛልሕ ተባረክ

  ReplyDelete
 35. I like your ideas!! God bless you

  ReplyDelete
 36. turu kolisehatal, gin eko yebalsiltan kimitoch yehabit minch zedie terestual ......lol

  ReplyDelete
 37. ዲ.ዳንኤል እግዚአሔር እድሜህን ያርዝመው በተለየ መንገድ የማየት ችሎታ አለህ፡፡ ብዙዎቻችን በያይነቱን ከመብላት ውጭ ብዙ አናስተውለውም ብናስተውለውም በመግቡ ዙሪያ ከመነጋገር ውጭ አንተ ግን..... ፐፐፐፐ በጣም ደስ የሚል እንደ ጥሩ በያይት ምግብ አንጀት የሚያርስ ነው፡፡ እግዚአብሔር ከመጥፎ ነገር ይጠብቅህ ከለላ ይሁንህ

  ReplyDelete