Wednesday, December 4, 2013

የአራቱ ኃያላን ቅኝት

   ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ 
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል)
ርእስ - አራቱ ኃያላን፦ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ አኖሬዎስ፣ አቡነ አሮን
አዘጋጅ - /ዳንኤል ክብረት
የገጽ ብዛት - 460 (መግቢያውን፣ ዋቤ መጻሕፍትን እና መዘርዝሩን ጨምሮ)
አሳታሚ - አግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ. የተ. የግል ማኅበር
ማተሚያ ቤት - አማኑኤል /ቤት
• ምረቃው የተካሄደበት ቦታ - መንበረ ፀባዖት /ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ
ቀን - ኅዳር 15/2006 ..
አስተያየት ሰጪ - አምሳሉ ተፈራ

የመጽሐፉ ሥነ ድርሳናዊ (ፊሎሎጂካል(1)ጠቀሜታ
. መግቢያ
መጽሐፉ በጣም ብዙ እና አዳዲስ ነገሮችን ይዟል። ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ የዓላማ ጽናት፣ በዘመኑ የነበረው ቅጣትና ፍርድ አሰጣጥ ወዘተ2 ... ከያዛቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የታሪክ አሰናሰሉ፣ የቋንቋ አጠቃቀሙ፣ የማስረጃዎቹ ተአማኒነት (ባብዛኛው ጥሬ መረጃዎችንና የመጀመሪያ ምንጮችን ማቅረቡ) ወዘተ... ለየት ያደርገዋል።

ይህ ደግሞ እስካሁን ድረስ ያልተሟላውን የሀገራችንን መካከለኛ ዘመን ታሪክ እንዲሟላ ብዙ ድርሻን ይወስዳል። በዋናነት ደግሞ የቤክርስቲያን ታሪካችንን የዚያን ዘመን ገጽታና የአበው ቅዱሳንን ታሪክ በስፋት ስለሚያሳይ ፋይዳው የጎላ ነው(2)


ገድላቸው ተተርጉሞ የቀረበው አራቱም አባቶች - አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ አኖሬዎስ፣ አቡነ አሮን - በተመሳሳይ ዘመን የኖሩ ስለነበር በአንዱ ገድል ውስጥ የሌላውንም ታሪክ እናገኛለን። ይህም ታሪኩን ይበልጥ ተአማኒና ተያያዥ ያደርገዋል። ገድላቱ የቅዱሳኑን የተጋድሎ ዜና፣ ሐዋርያዊ አገልግሎትና ያደረጓቸውን ተአምራት አካተዋል። እነዚህን ገድላት ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠኗቸው 100 ዓመት በፊት የውጭ አገር ሊቃውንት ሲሆኑ፤ አራቱንም ገድላት በግእዝ አትመው ወደ አውሮፓ ቋንቋዎች ተርጉመዋቸዋል(3)3 እኔ እስከማውቀው አራቱም ገድላት እስካሁን በአማርኛ ያልተተረጎሙ ሲሆን የአባ በጸሎተ ሚካኤል ገድል4 ግን በቅርቡ (2004 ..) ተተርጉሞ(4)ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገድል ጋር በአንድ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን ታትሟል(5)5 ስለዚህ ይህ የዲ/ ዳንኤል ዝግጅት በተፈላጊው ሰዓት የቀረበና ተፈላጊነቱም እጅግ የጎላ ነው የሚል እምነት አለኝ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበላቸውንና የምትገለገልባቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት፣ ድርሳናት፣ ገድላት እንዲሁም ልዩ ልዩ መጻሕፍትን ስናጠና ምንጫቸውን በተመለከተ 2 እንከፍላቸዋለን።

የመጀመሪያዎቹ መሠረታቸው የውጭ ቋንቋ ሆኖ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋ (ግዕዝ) የተመለሱ እና ሁለተኛዎቹ ደግሞ ሀገር በቀል ሆነው ከመጀመሪያው በግዕዝ የተጻፉ ናቸው። በውጭ ቋንቋ ማለትም በግሪክ፣ በሱርስት፣ በዐረብኛ ተጽፈው ወደግዕዝ የተተረጎሙ በርካታ ናቸው። አንዳንድ አጥኚዎች ይህን ዘመን ከአክሱም (በተለይም ከ5ኛው ...) እስከ 15ኛው ... ያደርሱታል። በሌላ በኩል ደግሞ ሀገርኛ ሥራዎች ይበልጥ የተስፋፉት ከ15ኛው ... በኋላ ሲሆን ከዚያ በፊትም ግን እንደነበሩ ለአብነት ያህልም የቅዱስ ያሬድን ድርሰቶች መጥቀስ እንደሚቻል ባማስረዳት የሚሞግቱ ብዙዎች ናቸው።

ተጋድሏቸውና ትምህርታቸው እንዲሁም ታሪካቸው ተተርጉሞ የቀረበው እና አዘጋጁ አራቱ ኃያላን ብሎ የሠየማቸው
አበው ገድላቸው ሀገር በቀል፣ ምንጩም ግዕዝ ነው። ወደ አማርኛ ቋንቋ መመለሱም የአንባቢውን ቁጥር በእጅጉ እንዲጨምርና ቅዱሳኑም የተጋደሉለትን ዓላማ ሁሉም በውል እንዲረዳው በእጅጉ ያግዛል። ከዚህም ጋር እያንዳንዱ ለብቻ ቢዘጋጅ 4 ታላላቅ መጻሕፍት ሊወጣው የሚችለውን እና እንደ መቅድም የቀረበው ታሪካዊ ትንታኔ ደግሞ ራሱን የቻለ 5 መጽሐፍ ሆኖ ሊወሰድ የሚገባው ሲሆን ሁሉንም በአንድ ላይ በማቅረቡ /ዳንኤል ለአንባቢ አሳቢነቱን ያሳያል የሚል እምነት አለኝ።

. መጽሐፉ ከሥነ ድርሣናዊ ሙያ አንጻር ሲታይ
ረጅም ዘመን ባስቆጠረው የጥንታዊ ጽሑፎች ጥናት መስክ የጥናቱ ማዕከል ሆነው የሚወሰዱት ጥንታዊ፣ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው የብራና ጽሑፎች፣ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ ልዩ ልዩ መዛግብት፣ ደብዳቤዎችና በመጽሐፍ መልክም ይሁን በጥቅልል መልክ የተዘጋጁ ሠነዶች ናቸው። ከዘመን አንጻርም ስናያቸው ከዘመነ አክሱም (አንዳንዴም ከዚያ የሚቀድሙ ተገኝተዋል) እስከ መካከለኛው ዘመን ገፋ ካለም እስከ ቅድመ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ (19ኛው መ...) ያሉት ናቸው። የጥንታዊ ሰነዶቹ ቋንቋ ባብዛኛው ግዕዝ ሲሆን የድንጋይ ላይ ጽሑፎቹን ቋንቋ ስንመለከት የሳባ ቋንቋ፣ አናባቢ የሌለው ግዕዝ እና ግሪክኛም ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ በጥንታዊ አማርኛና ሐረሪ(6)  ቋንቋ፣ እንዲሁም በክርስቲያናዊ ዐረብኛ የተጻፉ ሰነዶች በኢትዮጵያ ተገኝተዋል። እነዚህ ሁሉ በወጉ ሊጠኑ፣ ሊተረጎሙ እና የያዙት መልእክትም ለሕዝብ ሊዳረስ ይገባዋል። ከዚህም ባሻገር የተለያየ ቅጅ ካላቸው አፈላልጎ ማስተያየትና የጎደለውን ማቃናት ተገቢ ነው።

ከነዚህ እውነታዎች አንጻር በዛሬው ዕለት እየመረቅነው የሚገኘውን የዲ/ዳንኤል መጽሐፍ ስንቃኘው:-
1. ከቋንቋው አንጻር ከግዕዝ ወደአማርኛ መተርጎሙ፣ ከዘመን አንጻር የሀገራችንን መካከለኛ ዘመን ታሪክ በተለይም በዓምደ ጽዮን እና ንጉሥ ሰይፈ አርዕድ የነበረውን ታሪክ በስፋት በመያዙ ፍይዳው ብዙ ነው።
2. የተለያዩ ቅጂዎች ይኖሩ እንደሁ ብሎ ማሰቡና ይህንንም ለማሳካት የተለያዩ ገዳማትና አድባራትን፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ አብያተ መጻሕፍትንና መዘክሮችን ማሰሱ፣ እንዲሁም በአንዳንድ ግለሰቦች ይዞታ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎችን ማፈላለጉ፣ ይህንንም ባብዛኛው ማሳካቱ /ዳንኤልን ያስመሰግነዋል።
3. ተጨማሪ የገድል ቅጂዎችን ማግኘቱ እና መጠቆሙ በጣም ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ ያህልም፥

እስካሁን ከሚታወቀው የዳጋ እስጥፋኖስ ገድለ አባ በጸሎተ ሚካኤል (ኮንቲሮሲኒ 1905 ያሳተመው) በተጨማሪ በተንቤን እንዳ እጨጌ ኪዳነ ምሕረት ሌላ ገድል መኖሩን መጠቆሙ ለሌላ አጥኚ ጥሩ መረጃ ነው።
ገድለ ፊልጶስን በተመለከተ ቱራኤቭ 1905 ካሳተመው ውጭ ሌሎች 6 መኖራቸውን ከነዚህም መካከል የአምሐራ ሳይንቱ አዲስና እርሱ ያገኘው እንደሆነ መጠቆሙ በጣም ጠቃሚ ነው።
ገድለ አኖሬዎስን አስመልክቶ ኮንቲሮሲኒ 1905 ካሳተመው በተጨማሪ 10 ቅጂዎችን ማግኘቱ የሚደነቅ ነው።
ገድለ አቡነ አሮንን ቱራኤቭ 1905 አሳትሞት ነበር። /ዳንኤል ይህን እትም ከመቄቱ ገድለ አሮን ጋር አስተያይቶ ነው ወደ አማርኛ የመለሰው። ከዚህ ሌላ ግን በብሪቲሽ ሙዚየም የሚገኝ አንድ ገድልና በትግራይ ተንቤን ሌላ ቅጅ ሊኖር እንደሚችል እርሱ ግን ሊያገኘው እንዳልቻለ መጠቆሙ መልካም ጥረት ነው።
4. የትርጉም ሥራው የግርጌ ማስታዎሻ ጠቀሜታ - /ዳንኤል አራቱንም ገድላት ከመገኛቸው ቋንቋ ከግዕዝ ወደ አማርኛ መልሷል። አይግለጸው እንጅ ትርጉሙ የቃል በቃል ቀጥታ ትርጉም ይመስላል። ከዚህ በላይ ግን ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውንና እርሱ ያገኛቸውን አዳዲስ መረጃዎች ቁጥር በመስጠት አብራርቷል፣ ተንትኗል። በጥቅሉ በገድለ በጸሎተ ሚካኤል ላይ 251 በገድለ ፊልጶስ ላይ 378 በገድለ አኖሬዎስ ላይ 156 በገድለ አሮን ላይ 181 ማብራሪያዎችን በግርጌ ማስታዎሻ አስቀምጧል። ይህም ለሥራው ምን ያህል እንደተጨነቀ የሚያሳይ ሲሆን እስካሁን ከተለመደው የገድላት የአማርኛ ትርጉም የእርሱን የተለየ ያደርገዋል። ከዚህም በላይ የሚተነትናቸው ጉዳዮች አዳዲስና ተዛማጅ ጉዳዮች ስለሆኑ መጽሐፉን የበለጠ ተመራጭ ያደርገዋል።
5. በአንዳንድ ነጥቦች ላይ እስካሁን የተሰሩ ሥራዎችን ከዳሰሰ በኋላ መረጃዎች ተስተካክለው እንዲቀመጡ ማድረጉ ሌላው ጠቀሜታው ነው። ለምሳሌ ቱራኤቭ ያሳተመው ገድለ ፊልጶስ ዘመኑ 14ኛው ... ሳይሆን 18ኛው ... የተገለበጠ መሆኑን ማሳየቱ፤ ገድለ አቡነ አሮን 15ኛው ... ሥራ ሊሆን እንደሚችል ለማሳያነትም ገድሉ የደብረ ሊባኖስን እጨጌዎች ሲዘረዝር የሚያቆመው አቡነ መርሐ ክርስቶስ7 (1455-1489) ላይ መሆኑን መጥቀሱ(7) ወዘተ... ጥንታዊ ሰነዶች/መዛግብት ሲጠኑ እንዲህ እየተገናዘቡ መሆን እንደሚገባው የሚያስረዳ ነው።

. አስተያየት
ከላይ ባጭሩ እንዳየነው ይህ ሥራ በጣም ማለፊያ ነው። ሆኖም እጅግ የተወጣለት ለማድረግ እና ምናልባት ጊዜ ቢፈቅድለት /ዳንኤል ይህን ሥራ በድጋሚ ቢያሳትመው ወይም ተመሳሳይ ሥራዎችን ለወደፊቱ ሲሰራ ቢጠቀምባቸው ብየ የምጠቁመው ሁለት አስተያየቶች፣
የሚያገኛቸውን የገድል ቅጂዎች ሁሉንም እያመሳከረ ልዩነታቸውን እየነቀሰ አንድ ወጥና የተመሳከረ ከሁሉም ቅጂዎች የተውጣጣ እትም (8) ቢሰራ፣ ቢተረጉም።
የውጭ ሊቃውንት ያጠኗቸውን ከሚተረጉም ይልቅ እርሱ ያገኛቸውን አዳዲስ ገድላት ቢተረጉም ወይም በፊት ከተሰሩት ጋር እያነጻጸረ ቢሠራ የርሱ ሥራ ሚናው የጎላ ሊሆን እንደሚችል ይታየኛል፤ በማለት ሃሣቤን እዚህ ላይ እደመድማለሁ።
በመጨረሻም ውድ ወንድሜ /ዳንኤል እግዚአብሔር ኃይልና ብርታቱን ሰጥቶ እንኳን ይህን ጠቃሚ ሥራ አስፈጸመህ፤ እንኳንም ደስ አለህ፤ ለወደፊቱም የበለጠ ያትጋህ በማለት መልካም ምኞቴን በመግለጽ አስተያየቴን እደመድማለሁ።
ስላደመጣችሁኝ ሁላችሁንም እግዚአብሔር ያክብርልኝ !!!!
                                         
1 ፊሎሎጂ የተሰኘውን ጥናት ስያሜ ወደ አማርኛ በቀጥታ አቻ ትርጉም ለመስጠት ለጊዜው አልተቻለም። በዚህ አቀራረብ ግንሥነ ድርሳንወይምጥንታዊ  የጽሑፎች ጥናትብለን ልንወስደው እንችላለን።
2 ከዚህ መካከል እኔ የማቀርበው ፊሎሎጂያዊ ጠቀሜታውን ነው።
3 የአቡነ አሮንና አቡነ ፊልጶስ ገድላት በራሺያዊው ሊቅ በቱራኤቭ (Boris Turaev, 1905, Acta S. Aaron et S. Philippi,
Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium, Scri. Aeth., ser xx) የበጸሎተ ሚካኤል እና የአኖሬዎስ ገድላት
በጣሊያናዊው ምሁር በካርሎ ኮንቲሮሲኒ (K. Conti Rossini, 1905, Acta S. Basalota Mikael et S. Anorewos , in
Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium, vol. 28-29, Scri. Aeth., 11-12) ታትመዋል።
4 የጋስጫው ቅጅ
5 ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና ገድለ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል - ግእዝ እና አማርኛ - አሳታሚ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ታኅሣሥ ፳፻፬ ..
6 በሐረሪ ቋንቋ ቀድመው ከተጻፉት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መካከል በቀዳሚነቱ የሚጠቀሰው 16ኛው // እንደተጻፈ የሚገመተው ስለ ሐረር 4 ከሊፋዎች ታሪክ የሚናገረው ነው።
7 በእርግጥ የእርሱ ትርጉምኁልቈ ተዝካሮሙ ለአቡነ አሮን ወዘደቂቁብሎ በገጽ 435 ላይ የደብረ ዳሬቶቹን አበው ብቻ ይዟል እንጅ የደብረ ሊባኖስ እጨጌዎችን አይዘረዝርም።
8 በሙያው አጠራር Critical Edition የሚባለው ሲሆን የበለጡቱ የቅጂ ቤተሰቦች የተስማሙበት ዘር በንባቡ (text) ውስጥ ሲካተት ልዩነቶቹ (Variants) ደግሞ ለንጽጽር በግርጌ ይቀመጣሉ። ይህም Critical Apparatus የሚባለው ነው።

16 comments:

 1. ዳኔ ምንም ማድረግ የማይሴነው የቀራንዮው ንጉሥ በምታከናውነው ተግባራ ት በሙሉ አይለይሕ ። ግሩም ድንቅ ሥራ ነው ። በርታ!

  ReplyDelete
 2. nice keep it up and let God bless and He may keep your family also long live for u.

  ReplyDelete

 3. ከዚህም ጋር እያንዳንዱ ለብቻ ቢዘጋጅ 4 ታላላቅ መጻሕፍት ሊወጣው የሚችለውን እና እንደ መቅድም የቀረበው ታሪካዊ ትንታኔ ደግሞ ራሱን የቻለ 5ኛ መጽሐፍ ሆኖ ሊወሰድ የሚገባው ሲሆን ሁሉንም በአንድ ላይ በማቅረቡ ዲ/ዳንኤል ለአንባቢ አሳቢነቱን ያሳያል የሚል እምነት አለኝ።

  ReplyDelete
 4. I proud on his effort to maintain Ethiopian history succeeding the passed scholars mentioned on the first page of the book.

  ReplyDelete
 5. I proud to say Daniel is working good for the generation on Ethiopian history succeeding the known scholars in the field are passed away. (Hiyente abewuki tewolu leki deqiqe)

  ReplyDelete
 6. I proud to mention my opinion that Daniel is working good on Ethiopian history just like the passed scholars. we need such kind of guys stand the nation on mutual understanding and politically influenced lectures. I attended the ceremony hears Dr. Shiferaw Bekele's witnessing that the book qualifies to be academic reference.

  ReplyDelete
 7. Good job, Dani. May God Bless you and the family! amen.

  ReplyDelete
 8. “ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን”
  እንኳን አስቦ ለመጸነስ፣ ጸንሶ በትዕግስት ለመስራት፣ ሰርቶ ጊዜው ሲደርስ ለማማጥ፣ አምጦ በድካም ለመገላገል፣ ተገላግሎ የወለድከውን ለምዕመናን ለማብቃት አበቃህ!
  በዘመናት የሸመገለው ከማያልቀው ዕድሜ ለሥራ ፍሬ ቢሆንልህ የስጥህ!
  ከጣና ዳር፡፡

  ReplyDelete
 9. God bless you dani. I wish long life to serve God's people of Ethiopia.

  ReplyDelete
 10. Good work doesn't need advertising,
  BC his work goon set the truth.i am not
  agree all this comments,it is cover up
  we how he is,

  ReplyDelete
 11. ከወ/ት ታህሳስ አብቧል
  ለተከበርከው ውድ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
  እንደሚታወቀው እግዚያብሔር በየዘመኑ ፈቃዱን የሚፈጽሙለት ሰዎችን ይመርጣል፡ ይባርካል፡ ስራዎችንም ያሰራል። እግዚያብሔር ለሰዎች ያለው ፍቅር መጠንና መለኪያ ስለሌለው ለመግለጽ ያስቸግራል። ይህንን መጽሃፍ ለጊዜው አላነበብኩትም። ያነበቡት ሰዎች የሰጡትን አስተያየትና ሌሎች ስራዎችህን መሰረት በማድረግ የሚከተለውን ማለት እፈልጋለሁ።
  ይህንን መጽሃፍ ለመጻፍ አስጀምሮ፤ በሂደቱ ውስጥ ያለውን ውጣ ውረድ አሳልፎ እንዲጠናቀቅ የረዳህን እግዚያብሄርን አመሰግናለሁ። ተቀብረው የነበሩ ታሪኮችንና ማስረጃዎቻቸውን በኩራዝ እየመራ እንድታገኛቸው የረዳህና ሚስጢራቸውን የገለጸልህን እግዚያብሄርን አመሰግናለሁ። ጊዜህን፣ ጉልበትህን፣ እውቀትህን፣ ገንዘብህን ለትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መሰረት ያለው ጉድይ ላይ እንድታውል የፈቀደልህን እግዚያብሄርን አመሰግናለሁ። ያወቅከውን፣ የተረዳሀውን፣ ያየህውንና ያነበብከውን ለሌሎች በሚገባ ቋንቋ እንድትገልጽ የፈቀደልህን እግዚያብሄርን አመሰግናለሁ።
  ቀሪውን የህይወት ዘመንህን በርካታ መልካም ስራዎችህን እንድናይ እግዚያብሄር ጤናውን፣ ጉልበቱን፣ እውቀቱን፣ትእግስቱን አብዝቶ እንዲሰጥህ የዘወትር ጸሎቴ ነው። እግዚያብሄር ያንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክልህ። አሜን።

  ReplyDelete
 12. Ausabyos
  God bless u and ur family I am very glad by ur servise.

  ReplyDelete
 13. እግዚአብሄር ያንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክ። አሜን።

  ReplyDelete
 14. i proud this great idea,you are wonderful person .....thank you thank you.

  ReplyDelete
 15. Thanks to God!!! God may bless you a lot.

  ReplyDelete