Tuesday, December 3, 2013

የዳንኤል ክብረት አራቱ ኃያላን መጽሐፍ ምረቃ


ውዱ ጣፈጠ (ዶ/ር)
ታሪክ ትም/ ክፍል
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
በሀገራችን ውስጥ ለኦርቶዶክስ ክርስትና መስፋፋትና መደርጀት ትልቁን ሚና የተጫወቱት ሀገራዊ ቅዱሳን ካህናትና የሃይማኖት መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም በመካከለኛው ዘመን መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሁነው አብረው ሰርተዋል፡፡ ነገሥታቱና ካህናቱ አብረው የሰሩትን ያህል በመካከላቸውም አንዳንድ ከሃይማኖት ጋር የሚጋጩ ነገሮች እየተከሰቱ ሲያጋጩዋቸውና ሲያጣሉዋቸው ኑረዋል፡፡ በመካከሉም እርቅ እተፈጠረ የተለመደ ስራቸውን ሰርተዋል፡፡ ያለ ውህደታቸውም የመንግሥትና የቤተ-ክርስቲያኗ  መስፋፋት በጥንካሬ ሊቀጥል አይችልም ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያን ካህናት ከዛጉዌ ስርወ-መንግሥት ጀምሮ የሃይማኖት መÍህፍትን ከቅብጥ፤ ከአረብኛ፤ ከጽርእ በመተርጎም ለሃይማኖት ስራ እንዲዉሉ አድርገዋል፡፡ በጊዜውም የግእዝ kk ትልቅ የሥነ ጽሑፍ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ጥረዋል፡፡ የገድል መÍሕፍት በብዛት ተጽፈዋል፡፡ የሀገራቸውን ቤተ ክርስቲያን አሰራር የተመቸ ለማድረግ አዳዲስ ነገሮች እንዲለመዱና እንዲaaሉ ለውጥም እንዲመጣ ጥረዋል፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያኗ የቅብጥ (ግብፅ) ጳጳሳት በስተቀር ለቤተ-ክርስቲያኗ ለውጥ እዲጀመር ጥረት ያደረጉ የቅብጥ ጳጳሳት የሉም፡፡


ኢትዮÉያውያን ቅዱሳንን ከዘመኑ ነገስታት ጋር ሲያጋጭ የኖረው ነገስታቱ ለውጥንና አንዳንድ Bይማኖታዊ ትችቶችን ለመቀበል ባለመፈለጋቸው ነበር፡፡ ቅዱሳኑና  ነገRታቱ መጋጨት የጀመሩት በመካከለኛው ዘመን የኢትዮÉያ ታሪክ ዘመን ነግሶ ከነበረው ከአÑð አምደ Òዮን ዘመነ መንግRት ጀምሮ ነበር፡፡
      ዛሬ የሚመረቀው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት የገድላት የአማርኛ ትርጉም መÎÙ ግልÎ የሚያደርገው እነዚህ የመካከለኛው ዘመን ቅዱሳን ለBይማኖታቸውና ለሀገራቸው የሰሩትን kሚ ስራ፤ Bይማኖታዊ ተጋድሎና መንፈሳዊ Òናት ቆልጭ አድርጎ የሚያሳየን ነው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ገድላትን፤ ታሪከ-ነገስታትን እንዲሁም ሌሎች የታሪክ ድርሳናትን ወደ አማርኛም ይሁን ወደ ሌላ ሀገራዊ kk ተርጎሞ ለማቅረብ ራእይ ያለው ጠንካራ የስራ ሰው ለማየት ብርቅ በሆነበት ጊዜ እነዚህ ድንቅ Bይማኖታዊ  ገድላት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ወደ አማርኛ ተተርጉመው መቅረባቸው ይበል፤ እጅ ይባርክ፤ በለመደ ጣትህም ሌሎቹን ለመተርጎም እንድትበቃ እግዚአብሄር ይርዳህ ከሚል ማበረታቻ ቃላት ጋር መሆን አለበት፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙት የደቂቀ እስጢፋኖስ በህግ አምላክ የሚልና የአባ ባሕርይ ድርሰቶችን አስነብበውናል፡፡ አቶ አለሙ ኃይሌ የአፄ ገላውዴወስን፤ የአፄ ሰርፀ ድንግልንና የአፄ ሱስንዮስን ታሪከ ነገሥታት አሳትመው ለአንባቢ አቅርበዋል፡፡
        ይህንን አራቱ yያላን የሚለውን ደጎስ ያለ መÎÙ (ከመታተሙ በፊት እንዳነብለት ጠይቆኝ ሳነበው በሶስት ቅÎ የተዘጋጀ ነበር) ተመልክቸ አስተያት እንድሰጠው በጠየቀኝ ጊዜ ስው መቸም ብርቱ ነው በሚል የግርምት ህሳቤ ነበር የተቀበልኩት፡፡ ወቅቱ የአመቱ የትምህርት ማጠቃለያ ስለነበርና ሌሎች አጣዳፊ ነገሮች ስለነበሩብኝ፡፡ ቀስ እያልኩ ማንበብ ስጀምር ግን እንዳነብ ስለ ሰጠኝ እድል እያመሰገንኩት ጭምር፡፡
ይህ አራቱ yያላን በሚል ርእስ ወደ አማርኛ የተተረጎመው መÎÙ የአቡነ  በÐሎተ-ሚካኤል፤ አቡነ ፊልÊስ፤ አቡነ አኖሪዎስና አቡነ አሮን ገድል ነው፡፡ እነዚህ አራቱ yያላን ለBይማኖታቸው መስፋፋት ወደር የማይገኝለት ታሪክ የሠሩ፤ Bይማኖትን ያስፋፉ፤ ብዙ ደቀ መዛሙርት ያስተማሩና ያፈሩ፤ ገዳማትን የመሠረቱ፤ Bይማኖታዊ ክርክር አንሥተው በጊዜው ከነበሩ ነገሥታት ጋር ፊት ለፊት የተፋለሙ፤ የደረሰባቸውን ቁጣ፤ ግርፋት፤ እንግልት፤ ስቃይና መከራ፤ እንዲሁም ስደትና ግዞት ለBይማኖታቸው  በጸጋ የተቀበሉና ማንኛውንም መስዋእትነት በBይማኖታቸው በጽናት የተወጡ ናቸው፡፡
      ሌሎች የታሪክ መÑህፍትም እንደሚያስነብቡን ክርክሩ የተጀመረው በአÑðð አምደ Òዮን ዘመነ መንግስት ጊዜ ነው፡፡ እነዚህ ቅዱሳንና ሌሎች የBይማኖት ወንድሞቻቸው ወደ መንግስቱ መቀመጫ ተጉዘው Bይማኖታችን የሚያዘውን ነገር አልፈÐምክም በማለት ለምመከርና ለመመለስ በሄዱበት ወቅት ነበር፡፡ የነገሩ ጭብጥ “ለምንት አውሰብከ ብእሲተ አቡከ - ለምን የአባትህን ሚስት አገባህ” የሚል ነበር፡፡ የክሱ ጨብጥ  Bይማኖታዊ ህግን ጥሰሀል የሚል ነበር፡፡ በጊዜው ንጉሱ ይህንን ተቃውሟል፡፡ የምትጠቅሱት አባቴ አይደለም በሚል፡፡ ንጉሱን በአደባባይ እንደወቀሱት በትእግስት ሊያሰናብታቸው አልፈለገም፡፡ በአደባባይ እንዲገረፉ ከዚያም በግዞት ወደ ትግራይ እንዲሄዱ ተደረገ፡፡
      ከጥቂት አመታት በ|ላ ተመልሰው በመምጣት ሌላ ጥያቄ አነሱ፡፡ በገዳም ውስጥ በአንድነት የሚኖሩ ወንድና ሴት መነኮሳት መቀመጫ ተለይቶ እዲወሰን ጠየቁ፡፡ በጊዜው ወንድና ሴት መነኮሳት በአንድነት ይኖሩ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ በትግራይ ውስጥ የመነኮሳት መኖሪያ የተለያ ቦታ ነበርና ይህ ጥያቄ ወዲያውኑ ተቀባይነትን አገኘ፡፡ ከዚያም በሸዋና በሌሎች አካባቢዎች ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ፡፡
      በሶስተኛ ደረጃ የቅብጡ ሊቀ-ጳጳስ የቅስናና የዲቁና ማዕረግ ለመስጠት ገንዘብ ይቀበላል (simony) የሚል ክስ አቀረቡ፡፡ ምክንያቱም እነዚህን የክህነት ማዕረጋት ለመስጠት ገንዘብ ማስከፈል በሐዋርያት የተወገዘ ነበርና፡፡ ንጉሱ  ይህንን ክስ አልተቀበለውም፡፡ የቅብጡ ጳጳስም ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ እኔም ተቀብያለሁ ስህተት የለበትም በሚል ክሱን በማጣጣል ካህናቱን አወገዘ፡፡ እነዚህ ካህናትም በግዞት ወደ ዝዋይ ሀይቅ እንዲጋዙ ተደረገ፡፡ በሀካባቢው የእስልምና የመስፋፋት ችግር ስለነበር በዚያ በኩል ለመኖር አይችሉም ይቀጣሉ በሚል እሳቤ፡፡ ነገር ግን ለጥቂት አመታት በዝዋይ አካባቢ ከኖሩ በ|ላ የአባይን ወንዝ እየተሻገሩ ክርስትናን ለማስፋፋት ወደ ጎጃምና ወደ ጣና ሀይቅ አካባቢ አገሮች በስደት ራቅ ብለው ሄዱ፡፡
      ይህ ክርክር በአÑðð አምደ Òዮን ዘመነ መንግስትና በልጁና በወራሹ በአÑðð ሰይፈ አርእድ ዘመነ መንግስታት ጊዜ ተጠናክሮ ቀጠለ፡፡ ሰይፈ አርእድ ወደ ስልጣን በመጣ ጊዜ በአንዲት ሚስት ተወስኖ ለመኖር አስቀድሞ ቃል የገባ ቢሆንም ቃሉን አክብሮ አልኖረም፡፡ በዘመኑም እነዚህ ቅዱሳን ወደ መቀማጫ ከተማው እየመጡ ከስህተቱ ለመመለስ ሞከሩ፡፡ ነገር ግን አልተሳካላቸውም፡፡ እንዲያውም እንግልቱ፤ ቅጣቱና መጋዙ እተባባሰ ሄደ፡፡ ከዚያም እነዚህ አበው ቅዱሳን ወደ ሩቅ ሀገር፤ በጣም ሞቃታማና ቆላማ ወደ ሆነ ሀገር ተጋዙ፡፡ በረሀብና በጥም እንደዚሁም በስቃይ ሲጠበሱ ከእንደዚህ አይነት ድርጊታቸው ይቆጠባሉ በሚል፡፡
      በመÒኃፉ ውስጥ እንደምታነቡት አበው ቅዱሳኑ የደረሰባቸው ቅጣት፤ ግርፋትና እንግልት በዘመናችን ካየነው የደርግ ዘመን ተመሳሳይና በጣም ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ አንዱ በሃይማኖት ሌላው በፖለቲካ ሰበብ የተፈፀመ፡፡ እንዲያው ለቅንጣት ምሳሌ ያክል ክብራቸውን ለማዋረድና መሳለቂያ ለማድረግ በንጉሱ መቀማጫ ከተማ በአደባባይ ልብሳቸውን አውልቀው እርቃናቸውን እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡ ረ ስንቱ ይነሳል፡፡ እነርሱ ግን በአቋማቸው Ðንተው የሀይማኖታቸውን ስነ-ምግባር አጥብቀው ያዙ፡፡ ባላቸው ሀይማኖታዊ Òናት ግፉና መከራውን እንዲሁም ግርፋቱንና ስቃዩን በፍስሀ ተቀበሉት፡፡ ስደቱንና ግዞቱን እንደ ቀላል ችግር ተጋፈጡት፡፡ በደረሰው አለማዊና ዘግናኝ ቅጣት የወደቁትንና መስዋዕት የሆኑትን ብዙሀኑን የሀይማኖት ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን አርማ ተሸክመው እስከመጨረሻው ድረስ Ðንተው መንከራተቱንና ስቃዩን በአምላክ ስም አሸነፉ፡፡
      በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው ነገር አቡነ ያእቆብ በተባሉ የቅብጥ ሊቀ-ጳጳስ ዘመነ ፕትረክና ሀይማኖትን ለማስፋፋት ሲባል ኢትዮጵያ በአስራ ሁለት አገረ ስብከታት መከፋፈሉዋንና መምህራን መመደባቸውን ነው፡፡ ይህ ሊቀ ጳጳስ የአቡነ ተክለ-ኃይማኖትን አስራ ሁለት ደቀ መዝሙራትንና የደብረ ሊባኖስ ገዳም ምሩቃንን በመመደብ አገሪቱን ከፋፍሎ እንዲስተምሩ አሰማራቸው፡፡ በዚህ የለውጥ እንቅስቃሴና ቅዱሳኑ በተደረገባቸው መጋዝ ቤተ ክርስቲያንዋ ተስፋፋች፡፡ የሀገረ-ስብከት መከፋፈልም መሰረት ተጣለ፡፡ በቅብጡ ሊቀ ጳጳስ የተፈለመው ብቸኛ የለውጥ መንፈስ ከቅብጥ ከሊቀ ጳጳሳት መካከል ይህ ሊቀ ጳጳስ ብቻ ስሙ በበጎ ሲዘከር የሚኖር ነው፡፡
      በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከምናገኛቸው አያሌ ቁም ነገራት መካካል በጣም ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡ የሀገራችን ገድላት፤ ታሪከ ነገስታትና ሌሎች ጥንታዊ Òሁፎች በግእዝ የተÑፉትን ወጣቱ ትውልድ ምን እንደተሰራ ለማወቅ ይቸግረዋል፡፡ የሀይማኖት ታሪክን፤ ድርሳናትን፡ ገድላትንና አለማዊ የጥንት ታሪከ ነገስታትን የማንበብና የመመርመር ፍላጎት በአእምሮው ካልሰረÐ በስተቀር፡፡ በቅርቡ ልናገኛቸው የምንችላቸው ገድላት፤ ወይንም በሌላ የውጭ kk ተተርጉመው የሚገኙና እኛ ግን በቅርብ የማናገኛቸው፤ እንዲሁም የት እንደሚገኙ ለማናውቅ ሁሉ ዘለግ ያለ እድሜና ብርታት ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይድረሰውና እነሆ ይህንን መÒኃፍ በእጃችን መዳፍ ውስጥ  አስገባልን፡፡ ለመንፈሳዊ ተማሪዎች፤ ለሃይማኖትና ለታሪክ፤ በተጨማሪም ለሌሎች ምሁራን፤ እንዲሁም አግባብነት ላላቸው ሌሎች የትምህርት ዘርፎች የሚረዱ ዋቢ መጻሕፍት ያልተተረጎሙትንና በእጃችን ያልገቡትን ስራዎች የሚችሉ ሁሉ ተርጉመው እንዲያቀርቡልን ይህ ስራ ያበረታታል፡፡                      
      ባለፉት ክፍለ ዘመናት በሀገራችን በደረሰው የፖለቲካ ምስቅልቅል፤ ጦርነትና የህዝብ ፍልሰት በመካከለኛው ዘመን የጥንት የቦታ ስያሜዎች አንድም ተረስተዋል፤ ጠፍተዋል ወይንም በሌላ አዲስ ስም ተተክተዋል፡፡ የጥንቱን ዋና የመረጃ መጻሕፍትን ለሚያነብ ተመራማሪ እነዚህን የጥንት ስያሜዎች የት አካባቢ እንደነበሩ ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ትልቅ የራስ ምታትም ነው፡፡ እነሆ በዚህ መፅሀፍ ዲያቆን ዳንኤል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የጥንቱን ስያሜ ይዞ ታሪኩ ተፈፅሞባቸዋል በሚባሉት አካባቢዎች ተዘዋውሮ የአብዛኞቹን ቦታዎች የጥንት አካባቢ ሊደርስባቸው ችሏል፡፡ አብዛኞቹም ስማቸው ተቀይሮ በሌላ ተተክቷል፡፡ አንዳንዶቹም ትንሸ ለወጥ ብሎ ሙሉ ለሙሉ ሳይጠፉ ተገኝተዋል፡፡ ይህን ለማድረግ ለብዙ ቀናት ሳይሰለች አቀበትና ቁልቁለት፤ ሸለቆና ወንዝ ሳይበግረው የጥንቱን አካባቢ ሊለይ በመቻሉ አድናቆት ይገባዋል፡፡ በግርጌ ማስታዎሻ ሰፋ ካለ ማብራሪያ ጋር አቅርቦልናል፡፡ ስሞቹ የተገኙበትን ሌሎች መረጃዎችንም አካቶልናል፡፡ በአገራችን ጥናቱ ስለተደረገበት ዘመንና ለሌላም ነገር የፖለቲካ ካርታ የሌለ ቢሆንም ይህንን ስራ ይዘው ለመቀጠል ለሚፈልጉ ጎዳናውን አስቀድሞ ጠርጎ መንገዱን አመቻችቶላቸዋል፡፡
      እነዚህ አበው ቅዱሳን የደረሰባቸው ስቃይና እንግልት፤ እስራትና ግዞት ምን ያህል ስር የሰደደ እንደነበር በግልፅ ያስተምረናል፡፡ ለመሆኑ የእግዚአብሄርን ስም አንግበው የሃይማኖት ስራ ሲሰሩ ህይወታቸውን ሁሉ ለተንገላቱ አበው ቅዱሳን በክርስቲያኑ መንግስት ይህ ስቃይ ይገባቸው ነበርን ብለን ታሪኩን በጥልቀት እንድንመረምር ይረዳናል፡፡ አሁን በቅርቡ በተለያዩ ሀገራት የእኛንም ጨምር በፖለቲካ ጉዳዮች ዜጎች የደረሰባቸውን መጎሳቆልና መንገላታት ስናጤን አበው ቅዱሳን አባቶቻችን ያለፉበትን የስቃይ ዘመን እንድንገመግም እንገደዳለን፡፡ ሌላው ቀርቶ አሁን በቅርቡ በደርግ መንግስት ያለቁትን የቀይና የነጭ ሽብር ሰለባዎችን ስናስብ ወጣቱ ትውልድ በስንት አይነት ጣእርና ስቃይ ተለብልበው እንዳለቁ ለመገንዘብ ይረዳናል፡
      ሌሎች ተመራማሪዎች አዲስ መረጃ በማግኘታቸው ሰፊና ጥልቅ ምርምር አካሂደው ታሪኩን አገናዝበው እንደሚያስነብቡን አልጠራጠርም፡፡ በዚህ አጋጣሚ የደቂቀ እስጢፋኖስ ተከታዮች የደረሰባቸውን እልቂትና ጭፍጨፋ ከጥቂት አመታት በፊት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ተርጉመው ያቀረቡልንን መፅኃፍ ያነበባችሁት ስለሆነ ነገሬን እዚሁ ልkጭ፡፡
      ዲያቆን ዳንኤልን ሊያስመሰግነው ከሚገባው ስራ መካከልም በብዙ ድካም የግርጌ ማስተወሻውን ፅፎ ማካተቱ ነው፡፡ በግርጌ ማስታወሻ የተዘረዘሩት ማብራሪያና መግለጫ እጅግ አድካሚ ስራ ነው፡፡ ይሁንና ስራውን ምን ያህል አድቅቆ እንደሰለቀው ግልፅ ያደርግልናል፡፡ በተጨማሪም ተካቶ የቀረበው የቦታና የሰው ስም መዘርዝር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም አታካችና አድካሚ ሲሆን በምንም ሁኔታ ሰሞች እንዳይረሱ ሳይፃፉ እንዳይቀሩ ለማድረግ በተደጋጋሚ የተደረገውን የአርትኦት ትኩረት ነው፡፡ ሰለ አንድ ነገር ለማወቅ የሚፈልግ ሰው መፅሀፉን ገፅ በገፅ አንብቦ የሚፈልገውን ስም በቶሎ ለማግኘት የሚረዳ በመሆኑ ስራን ያቃልላል፡፡ የህትመት ስራ የናረ ባይሆን ኖሮ የግእዙ ፅሁፍ ቢካተት ጥሩ ነበር፡፡
      ይህ ጥልቅ ስራ ሌሎች ተመራማሪዎች የርሱን አርአያነት ተከትለው እንዲህ አይነቱን የትርጉም ስራ ለመስራት ያነሳሳቸዋል፡፡ በሀገራችን የተደረሱ ብዙ ስራዎች እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ kk ወደ ግእዝ የተተረጎሙ የብዙ መጻሕፍት ትርጉም ስራ ገና አልተነካም፡፡ ይህ የማንቂያ ደወል በብዙ ሰዎች ጆሮ ላይ ሊደውል ይገባል፡፡ በተለይም የቤተ-ክርስቲያናችን ካህናትና ምሁራን - ከሊቅ እስከ ደቂቅ - ይህንን የትርጉም ስራ ስራየ ብለው እንዲጀምሩት ይሞግታቸዋል ያበራታታቸዋልም ብየ እገምታለሁ፡፡ በተለይም ጠቅላይ ቤተ-ክህነትም ሆነ የባህል ሚኒስቴር ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ምንም እንኳ የተጠናከረ ድርጅትና የስራ ተነሳሽነት የሚያስፈልገው ቢሆንም በተለይ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት እኔ አለሁ ብሎ ብእሩን ሊያነሳ ይገባል፡፡
      ስራው መበረታታት ያለበት ከግእዝ ወደ አማርኛ kk በመተርጎሙ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ወደ ሌሎች የብሄረሰብ kkዎች ቀስ በቀስና በጊዜ ሂደት ስራው መጀመር ያለበት መሆኑ ጭምር ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ከታሰበው መድረስ ስለሚቻል አቢይ ቁም ነገሩ ለመጀመር ቆርጦ መነሳሳቱ ላይ ነው፡፡
      ለማጠቃለል ያህል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ሰራኸው ስራ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የድካምህን ዋጋ ባለቤቱ ይክፈልህ፡፡ ሌሎች ሰራዎችህንም አሁን የተወጠኑት ጨምሮ በተከታታይ እድታስነብበን በትህትና እመኛለሁ፡፡ ቅዱሳን አበውን የባረከ አምላክ አንተንና ቤተሰብህን ይባርክ፡፡

አመሰግናለሁ፡፡           
                      

23 comments:

 1. "ይህ ጥልቅ ስራ ሌሎች ተመራማሪዎች የርሱን አርአያነት ተከትለው እንዲህ አይነቱን የትርጉም ስራ ለመስራት ያነሳሳቸዋል፡፡ በሀገራችን የተደረሱ ብዙ ስራዎች እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ kንk ወደ ግእዝ የተተረጎሙ የብዙ መጻሕፍት ትርጉም ስራ ገና አልተነካም፡፡ ይህ የማንቂያ ደወል በብዙ ሰዎች ጆሮ ላይ ሊደውል ይገባል፡፡ በተለይም የቤተ-ክርስቲያናችን ካህናትና ምሁራን - ከሊቅ እስከ ደቂቅ - ይህንን የትርጉም ስራ ስራየ ብለው እንዲጀምሩት ይሞግታቸዋል ያበራታታቸዋልም ብየ እገምታለሁ፡፡ በተለይም ጠቅላይ ቤተ-ክህነትም ሆነ የባህል ሚኒስቴር ሊያስቡበት ይገባል፡፡ ምንም እንኳ የተጠናከረ ድርጅትና የስራ ተነሳሽነት የሚያስፈልገው ቢሆንም በተለይ ጠቅላይ ቤተ-ክህነት እኔ አለሁ ብሎ ብእሩን ሊያነሳ ይገባል፡፡"

  እግዚአብሔር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል፡፡ እግዚአብሔር በጸጋ ላይ ጸጋን ይጨምርልህ፤ ክፉ አይንካህ፡፡

  ReplyDelete
 2. ፕሮግራሙን ቅድስት ስላሴ ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ተገኝተን ተከታትለነው ነበር በጣም አሪፍ ነበር ዲ/ን ዳንኤል ከመላው ቤተሰብህ ጋር ረጅም እድሜና ጤናን እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥልን፡፡
  ቀጣይ ስራዎችህንም እንጠብቃለን እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስቀናኸኝ ጃል!
   ዳኒ እግዜር ይስጥህ፡፡

   Delete
 3. እንግዲህ ምን እንላለን? እፁብ ድንቅ እንጂ!!! አምላከ እስራኤል ስራህን እንዲባርክ ፈቃዱ ይሁን፡ ለቀጣይ ስራ ጉዞህን እንዲባርክልህ ፈቃዱ ይሁን፡፡እመብርሃን ሕይወትህንና ኑሮህን ትባርክልህ ዘንድ ምኞቴ ነው፡፡ዲያቆን እኛ ወጣቶች ካንተ ብዙ እንጠብቃለን ብዕርህን ቶሎ ቶሎ አድርሰን፡፡

  ReplyDelete
 4. ንዑ ኀቤየ ቡሩካኑ ለአቡየ... የሚለውን የሕይወት ቃል ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል ።

  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ሰራኸው ስራ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የድካምህን ዋጋ ባለቤቱ ይክፈልህ፡፡ ሌሎች ሰራዎጭንም አሁን የተወጠኑት ጨምሮ በተከታታይ እድታስነብበን በጥትና እመኛለሁ፡፡ ቅዱሳን አበውን የባረከ አምላክ አንተንና ቤተሰብህን ይባርክ።

  ዲ/ን K.G !!!

  ReplyDelete
 5. How a poor studnet like me can read this BOOK,Dani?

  ReplyDelete
 6. መግዛት ለማንችል ምን እናድርግ?

  ReplyDelete
 7. አራቱ ሃያላን ባሁኗ ቤትክርስቲያን ውስጥ አሉ...?የሉም!ሊሳስበን የሚገባው ያ ነው!

  ReplyDelete
 8. በአሁኑ ወቅት ሊያሳስብ የሚገባው የአራቱ ሃያላን በቤትክርስቲያናችን መነሳት ነው! በግብጽ ሶስት ሃያላን ተነስተው እንዴት ቤትክርስቲያናቸውን እንደለወጡ ተመልከቱ!!!!! Few would dispute that the Coptic Church, which was founded by St. Mark the evangelist, began its modern renaissance towards the latter half of the nineteenth century, after many centuries of darkness. A darkness which was forced upon her by two major historical events. The first of which were the woeful decisions of the Council of Chalcedon (451 A.D.) which separated her from the rest of Christiandom. The second was the Arab conquest of Egypt (641 A.D.), as a result of which the church's major preoccupation was sheer survival. Indeed the survival of the Copts till this day is a miracle and a witness for thirteen centuries of unwavering faith.
  T'he renaissance of the church is due to three important developments:
  1.The establishment of the Coptic Theological College.
  2.The Coptic Sunday School movement.
  3.The founding of Coptic Benevolent Societies
  + College graduates for the last one hundred years have been responsible for spreading Orthodox Christian education.
  + Sunday School which was a tiny seed planted and watered by men and women of faith, grew by the Almighty till it became a great tree giving fruit and shelter to countless many.
  + Coptic Benevolent Societies were responsible for the establishment of the great majority of newer churches, Coptic schools, hospitals, orphanages, and publishing houses, spreading education and social welfare to all Egyptians without discrimination!!!Behind these three institutions lies a great army of selfless workers who were moved by faith and love for their church to arise and build with all the support and encouragement of the church leadership. Our church has recently celebrated the fortieth anniversary of the departure of one of the pioneers of Coptic renaissance, one who stands as a giant among his contemporaries, Archdeacon Habeeb Guirguis, a man of vision who inspired many generations of Copts.he most noteable of the lay leaders of that age was Archdeacon Habeeb Guirguis, who was so outstanding not only because of his momentous deeds, but also because of the number of brilliant disciples he left behind, who followed his path and also wrote at length about his achievements since his death in 1951.
  This giant man, who lived to the age of seventy-five, dedicated his whole life to the service of his church, even refusing marriage in order to channel time and many talents to its service. His vision was to see the resurrection of the glories of the church and he went about the task with unwavering love and enthusiasm. The main traits of his service were his perfection and comprehensiveness, and the combination of hard work with vision. In that he achieved the mark of greatness as stated by our Lord Jesus Christ, “...he who does (these commandments) and teaches them shall be called great in the kingdom of Heaven...”...

  ReplyDelete
  Replies
  1. A fascinating comment, God bless you!!!

   Delete
  2. You have really a pen and a brain.
   stay blessed!
   Ze Tana Dar.

   Delete
 9. Dn. Daniel Egziabher yibarkih ,Erejim yagelgilot edme yistih. Gin zare yanebebnew tsihuf kene computer new weyis amarigna beand egru mehonu new?

  ReplyDelete
 10. Thank you so much for your contribution , I live in USA , I hope I will meet you one day. God bless you and your family.

  ReplyDelete
 11. ድካምህን ከመጽሃፍ መግቢያ ላይ አነበብነው ምን አይነት ፍቅር እንዲህ አደከመህ ምን አይነት ቅናት በውስጥህ አደረ እረፍት የሚነሳ የሃገር እና የቤተክርስቲያን ሃላፊነት በውጥህ ማን አሳደረ በዚህ በገንዘብ ለመክበር የሃገር ቅርስሶች የከበሩ መንፈሳዊ ቅርሶች ሳይቀሩ በሚሽጡበት ዘመን እንደምን ያለ ሃላፊነት እንቅልፍ ነሳህ...በእርግጥ እግዚአብሄር መረጠህ ጸጋውን ያብዛልህ ከከንቱ ውዳሴ ይጠብቅህ..

  ReplyDelete
 12. Thank you so much for your enormous contribution. It really shows that you are amongst the few who are chosen. Let alone translating saints book people are now in confusion and I think you are the only one who stands above all these conditions to testify about the good and the only road. Thank you again. God bless Ethiopia, our church and you and your family

  ReplyDelete
 13. ስራው መበረታታት ያለበት ከግእዝ ወደ አማርኛ kንk በመተርጎሙ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ወደ ሌሎች የብሄረሰብ kንkዎች ቀስ በቀስና በጊዜ ሂደት ስራው መጀመር ያለበት መሆኑ ጭምር ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ከታሰበው መድረስ ስለሚቻል አቢይ ቁም ነገሩ ለመጀመር ቆርጦ መነሳሳቱ ላይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 14. “ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን”
  እንኳን አስቦ ለመጸነስ፣ ጸንሶ በትዕግስት ለመስራት፣ ሰርቶ ጊዜው ሲደርስ ለማማጥ፣ አምጦ በድካም ለመገላገል፣ ተገላግሎ የወለድከውን ለምዕመናን ለማብቃት አበቃህ!
  በዘመናት የሸመገለው ከማያልቀው ዕድሜ ለሥራ ፍሬ ቢሆንልህ የስጥህ!
  ከጣና ዳር፡፡

  ReplyDelete
 15. Dannie I hope you will not going to leave us to read your poster with this green color. It seems to me like child post. Sorry so can you change it for us, I don't whether if that just for me or to others too.But I don't feel good with this color. I love the one you had, it was really good.

  ReplyDelete
 16. berta edimena tena yistih

  ReplyDelete
 17. እናመሰግናለን!!

  ReplyDelete
 18. Egziabiher yitebikihi hulachnmi betegawi yaberitan.

  ReplyDelete
 19. Diakon Daniel EGIZIABIHIER Ybarikih.Aderahin 3um Lijochih Yanten Feleg Yiketelu!!!

  ReplyDelete
 20. እግዚያብሄር የአገልግሎትዎን ጊዜ ይባርክ ። የስዎን ብዙ መጽሐፍት አንብቤአለሁ ። እያየን ያማናስተዉላቸዉን ሀሳቦች አጉልተዉ አዉጥተዉ ሲያሳዩን ግሩም ድንቅ ብለናል ። የሚተቻቸዉ ጉዳዮች በዕዉቀት ላይ የተመሰረተ የማንኛዉም ወገን ሳይሆኑ ነገር ግን ለሀገርና ለወገን ጥቅምና ክብር የሚሆነዉን ለማሳየት ሞክረዋል ። እንዳለመታደል ሆኖ አሁን አገራችን የገጠማት ትልቁ ፈተና የሚያነብና በዕዉቀት ላይ ተመስርቶ ከሚተች ይልቅ እነ እከሌ ይህንን ሀሳብ አልወደዱትም ተብሎ የሰዎች የሀሳብ ሳጥን ኮሮጆ ማራገቢያ የበዛበት ጊዜ እና ትዉልድ ላይ ደርሰናል ። እና ከዚህ አስቸጋሪና አስፈሪ ብዙዎቻችን ለነፍሳችን ሳይሆን ለስጋችን ያደርን እዉቀትን የምንሸሽ ፊኛዎች ብዙ አዉርተን ስራችን ግን ... በሆነበት ጊዜና ምድር ላይ በመገኘትዎ ለካስ እግዚያብሔር ሰዉ ማስነሳት ምን ይሳነዋል አልኩ ። እግዚያብሔር እስዎንና ቤተሰብዎን ይባርክ ። ዮሐንስ ነኝ ከሞቃዲሾ / ሶማሊያ /

  ReplyDelete