Wednesday, December 4, 2013

የት ነው ያለነው?


ይህ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የሰባተኛ/ስምንተኛ ክፍል መማሪያ ውስጥ የተገኘ 
የባዮሎጂ ትምህርት ማስተዋሻ (ኖት) ነው፡፡
ወይ ባል አላገባሽ ወይ አልመኮስሽ
እንዴው ልጅ አገረድ ይባላል ስምሽ
እንደሚባለው ወይ በአማርኛ(በራሳችን ቋንቋ) በሚገባ ተምረን አልተግባባን፤ ወይ በፈረንጅ ቋንቋ በሚገባ ተምረን አልተግባባን፡፡ እንዴው ምን ይሻላል?
ድሮ ድጎማ የሚባል መምህር ነበር አሉ፡፡ መቶ ብር በማይሞላ ደሞዝ ነበር አሉ የሚቀጠሩት፡፡ ክፍል ውስጥ ክኖው፣ ዲጂቡቲ፣ ክናይፍ know, Djibouti, knife, እያለ ያስተምራል፡፡ ተቆጣጣሪው (ሱፐርቫይዘሩ) እንዴት እንዲህ ታስተምራለህ? ኖው፣ ጂቡቲ፣ ናይፍ በል ይለዋል፡፡ መምህሩም ‹‹በድጎማ ደሞዝማ እንዲያ ብዬ አላስተምርም›› አለ ይባላል፡፡
በባሕላዊው የጥንት ትምህርታችን ንባብ ወሳኙና የመጀመሪያው ትምህት ነበር፡፡ የፊደል ዘር መለየት ብቻ ሳይሆን አነባበብም ጭምር፤ በየሠፈራችን የነበሩትን የቄስ ትምህርት ቤቶች እናስታውሳቸው፡፡ ፊደሎቹን ከነዜማቸው እስክንሸመድድ ድረስ አንገት ላንገት ተቃቅፈን የምንናጥባቸውን ትምህርት ቤቶች አስታውሱ፡፡
ማንበብ የዕድገት ቁልፍ ነው፡፡ ለዚህም ነው በጥንት ሥልጣኔ የምናውቃቸው ሀገሮች ሁሉ የራሳቸውን ፊደል ለመፍጠር የተሳካላቸው ሀገሮች የነበሩት፡፡ በሥልጣኔ መጥቆ ፊደልና ጽሕፈት የሌለው ሀገር አናገኝም፡፡ የማያነብብና የማይጽፍ ትውልድ መፍጠር ከዕውቀት የተቆራረጠ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በዐረብ ሀገሮች በሚገኙ ዜጎቻችን ዘንድ አንዱ ፈተና ‹ማኑዋል አንብቦ› መሣሪያዎችን ለመጠቀም አለመቻል ነው፡፡
ወላጆች፣ የእምነት ተቋማት፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሚዲያዎችና የሚመለከተን ሁሉ ልናስብበት የሚገባ ቁልፍ ችግር - ማንበብ የማይወድ ሳይሆን ማንበብ የማይችል ትውልድ በየክልሉ እየተፈጠረ ነው፡፡ ፊደልና አጻጻፍ መለየት የእንግሊዝኛም የሀገራዊ ቋንቋዎችም ችግር እየሆነ ነው፡፡
እናም፣ የፊደልን ዘር መለየት፣ አጻጻፍን ማወቅና አነባበብን ማርታትን ከነባሩ የትምህርት ሥርዓታችን በሚገባ ቀስመን ወደ ዘመናዊ ትምህርት በጊዜ ካላስገባነው - ትውልድ አደጋ ላይ ነው፡፡

17 comments:

 1. ዳኒ ይህ በአንድ ጸሃፊ አባባል ኢንጋማር(english-amharic) ይባላል!ኢንጋማር የሚባለውን ቋንቋ የሚናገሩት አዲሳበቤዎች ናቼው!ባብዘሃኛው ከሌሎች ቋንቋዎች የሚለየው ዜማ ስላለው ነው!ወሬዎቹ የሚያጠንጥኑት ስለhoolywood እና bilboard ነው ! አብዘሃኞቹ ይሄን ቋንቋ በመናገራቼው ይኮራሉ!!! በዚህም የተነሳ በጥንታዊው አምሃረኛ ይስቃሉ...ኪኪኪ....ብዙዎቹ የባነኑ ናቼው... እኛ ግን ብዙ ጊዜ አንባንንም...ኪኪኪ

  ReplyDelete
 2. ይሄን ስልጣኔ... ኢንጋማርን ማለቴ ነው!... አንድ ጽሁፍ አስታወሰኝ .. in Asmara in the ‘40s and ‘50s when the Italians left in droves. When the previously powerless rural migrants suddenly acquired properties and jobs they could only dream of, they did feel the power surge. They took over Asmara in their tens of thousands, became business men and owned whatever they could put their hands on. Property was affordable and jobs were everywhere for the taking – just the exact opposite of what is happening around the world right at this moment.

  This is our country, our land and our city! That sounds like the slogan of that era. They must have felt the glow in their bloodstream… let alone in what they saw. It probably looked like a peaceful transition from a colonised state to an early stage of a free market economy over a period of ten short years. They never had it so good.

  How can one accommodate or internalise a new urban identity with a loaded rural background running in one’s veins?

  The easy way out was to take a short cut. They chose not to identify with it [the rural element] by denying or eliminating traces of one’s make-up or upbringing. Anything that ignites unpleasant memories of the perceived ‘backward’ culture has to be shunned, ignored, laughed at and downgraded to a level of insignificance.

  Listening to the generation that was born and brought up in Asmara in the ‘40s and later, one can tell that so much negativity has been absorbed on countryside values or style of living. The trend was to push oneself to aspire and indulge in being ‘urbane’ or mutate to a newly manufactured Asmarino. Denial became the entry fee or a way of life for the new generation and, sixty years later, it’s happening all over again in a totally different mental setting.

  What an upgrade and to what kind of software?

  Asmara became the Disneyland where everyone headed and pretended all was well… a happy-go-lucky kind of attitude was in vogue.

  Instead of combining the redeeming features of a rural lifestyle and probably be taxed for it for the advantages acquired for a new style of living, putting a mask of an urbane persona became the dream ticket to a new heaven. It’s really not that different from changing the background set in a theatre play. All of a sudden, one absorbs a different and magical aura – similar to experiencing a conversion ‘on the road to Damascus’ – from a pagan or a heathen mindset to a brand new ‘religion’ in lightning speed. And in that new context, cultural values – from traditional religion to an agricultural mode of living – became suspect of being backward or rural-oriented!Gabriel Guangul..analyse asmera

  ReplyDelete
 3. YHE BECHA NEW YEGREMH----

  ReplyDelete
 4. ሁላችንንም ሊሰማን ይገባል ምክንያቱም ችግሩ በአንድም በሌላም ----
  በእውነት ያነሳኸው ርዕሰ ጉዳይ አውነትም ሁሉም ኢትዮጰያዊ የሚመለከት ጉዳይ ነው ምክንያቱም ችግ በእያንዳንዳችን ቤት በአንድም በሌላም መግባቱ አይቀርም ይሁን እንጂ የሚገርመው አሁን አሁን እንደባህል ማሳድግ የሚገባን በመስራት መለወጥን በተለይም እንደኛ ዓይነት ችግር ውስጥ ያሉ ሀገሮች ውስጥ ከተማሪው/ከተተኪው ትውልድ/ የሚጠበቀው በመማር ያለውን እውነታ ማወቅ ብቻ ሳይሆን ካንበት ችግር ለመውጣት በእያንዳንዱ የእለት ተለት ችግራችን መፍትሔ የሚሆኑ አዳዲስ አሠራሮን እራሱን በማላመድና የፈጠራ ክህሎትን በማሰደግ ሳይታክት መስራት የግድ የሚልብን ጊዜ ላይ ነን በጣም የሚየሳዝነው እና የሚያስደነግጠው ግን ትውልዱ አይደለም በትጋት ማንበብ ይቅርና መስረቅ/መቅዳት/ጥገኛ መሆንን ነውር መሆኑ ቀርቶ መብቴ ነው መስረቅ የሚል ትውልድ ላይ እየደረስን ነው ለዚህም እንደመሸፈኛ በብዙሃናችን የሚስተዋለው ከትንሽ እስከ ትልቁ እኔ ከማለት እነሱ እያልን ስንፍናችንን በምክንያት በመደበቅ በተቃራኒው እየተጓዝን እገኛለን በእውነት እውቀቱና አቅሙ ያላችሁ ሁሉ አንድ ነገር ለማለት እንሞከር ምክንያቱም በታሪክ ክስተት በዓለም ላይ ሳይሰራ የውም በእውነትና በብቃት ሳይታመን የተለወጠ ሀገር አልገጠመኝምና አምላክ ወደ ቸሩ መንገድ ይምራን--------

  ReplyDelete
 5. Grade 7 ohuuuu soo pain full.The education system kills the teachers and the teachers kills the students.The vicious circle of poor quality of education.

  ReplyDelete
 6. ወላጆች፣ የእምነት ተቋማት፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሚዲያዎችና የሚመለከተን ሁሉ ልናስብበት የሚገባ ቁልፍ ችግር - ማንበብ የማይወድ ሳይሆን ማንበብ የማይችል ትውልድ በየክልሉ እየተፈጠረ ነው፡፡ ፊደልና አጻጻፍ መለየት የእንግሊዝኛም የሀገራዊ ቋንቋዎችም ችግር እየሆነ ነው፡፡

  ReplyDelete
 7. የሚመለከታቸው አካላት እና ህብረተሰቡ ትኩርት ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. Dani that is good article and you always write very interesting issues. I read your article most of the time, but your blog design is not attractive, So please please please redesign it. Because design is one factor as your nice article. look this blog .....> www.geezbet.com , its very attractive blog.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you so much Dani. I love you blog but I don't like your back-ground on your blog. I agree with the above Anonymous person idea, please redesign or don't post background on your blog.

   Delete
  2. You have a gentle mood! I liked the way you suggested.

   And I pray for Dani to be strengthen as you strive to gain knowledge.

   Delete
 9. የማያነብብና የማይጽፍ ትውልድ መፍጠር ከዕውቀት የተቆራረጠ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡

  ReplyDelete
 10. አረ እንዲያውም የእውነት ያጋጠመኝ ነገር ትዝ አለኝ ፤ ነገርየው የሆነው AA University ነው ። የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል የስብሰባ ሰአት ብዛት እና የቃለጉባኤው እርዝመት ያሳሰባቸው ሀላፊ፣ ሲጨንቃቸው የስቡሰባውን መግባቢያ ቋንቋ ወደ እንግሊዘኛ ቀይሩት ብለው እርፍ። ከዛም ስብሰበዎች 30 ደቂቃ እልቅ ቃለጉባኤም እጥር አለች።እንደኔ እንደኔ ይሄ አዲስ ነገር ወይም የትምህርት ስርዐት ለዉጥ ያመጣው ችግር አይደለም። ድሮውንም ቢሆን እንግሊዘኛ ማይችል መምህር ቋንቋ ሲያስተምረን ነው የኖርነዉ። የዚህም ውጤት የሆኑት የዩኒቨርሲቲ ዶክተሮቻችንን እንግሊዘኛን ከጽሁፍ ውጪ ለንግግር ሲጠቀሙት መስማት ከበቂ በላይ ነዉ። ከቀድሞ ይልቅ ከተማሪ ብዛት አንፃር አሁን ላይ ጎልቶ ይሆናል። ነገርየው መንጋደድ ሚጀምረው ዳኒ የጠቀስካቸው ባህላዊው እንግሊዘኛ ማይችሉት ቄስ ወይም መዋለ ሕጻናት መምሕሮቻችን ፊደል ስንስት ሲመቱን ነው። ልብ በል እነሱም አይችሉም፤ ስለዚህ እውነተኛው ሲመጣ ግራ ሲገባን መልሶ ማይችለው ደግሞ ሲያጣምመን አስራ ምናምን አመት አልፎን ከላይ የተመሳከረውን የባዮሎጂ ሀሳብ በገባን መልኩ እንጽፋለን። ወደፊትም እንግሊዝ አፍ የሚችል እስኪያስተምረን ድረስ እንቀጥልበታለን! We can't help it!

  ReplyDelete
 11. ካልተሳሳትኩ ይሕ የድሕረ ገጽ ሽፋን ጊዛዊ ነው።

  ReplyDelete
 12. ኸረ እሱሰ ተትቶ የራሳችንን ታሪክ በሰው ሃገር ቋንቋ መማሩ በምንም መልኩ ማብራሪያ ሚገኝለት አይደለም::ወይስ ሁላችንም ቱሪስት አስጎብኚ እንድንሆን ነው ???

  ReplyDelete