በአውሮፓ ክርስቲያኖች ዘንድ የታወቀ አንድ የአራተኛው መክዘ ታሪክ አለ፡፡ ድኾችን
እጅግ የሚወድ፣ የተቸገሩትን ለመርዳት ምንም ነገር የማያግደው፤ ከእራሱም አብልጦ ለሌሎችን የሚሞት አንድ ሰው ነበረ፡፡ ይህ
ሰው በበጎ ምግባሩ የተነሣ ስሙ ተረስቶ ‹እኁ ቅዱስ- ቅዱሱ ወንድም› እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ በታሪክ ድርሳናትም
የተመዘገበው በዚሁ ስም ነው፡፡ ሠርቶ የሚያገኘውን ምንም ለሌላቸውና ለምነው እንኳን ለማግኘት ዐቅም ላነሣቸው በመስጠት የታወቀ
ነበር፡፡
አንድ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አጣ፡፡ ብዙ ችግረኞች ደግሞ መልካም ዜናውን ሰምተው ጥቂት
ነገር ለማግኘት ወደ እርሱ ዘንድ መጡ፡፡ ምን ይስጣቸው፡፡ የሚያያቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡
ብዙዎቹ ገንዘቡን ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር በመምጣታቸው አዘኑ፡፡ መመለሻ እንኳን የላቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ እኁ
ቅዱስ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹እኔን ሽጡኝና ተካፈሉ› አላቸው፡፡ እነዚያ ችግረኞችም ምን አማራጭ ስላልነበራቸው እርሱን በባርነት
ሸጡትና ገንዘቡን ተካፈሉ፡፡
ደሴ የምትታወቀው በፍቅር ከተማነቷ፣ የኢትዮጵያ ባሕላዊ ዜማዎች አምባ በመሆኗ፣
በንጉሥ ሚካኤል ታሪክና በአይጠየፍ አዳራሽ፣ በዘመናዊው የኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ውስጥም በያዘችው ቦታ ብቻ አይደለም፡፡ ብዙ
ያልተነገረላቸው ፣ በደሴ ተራሮች ላይ የሚያበሩ፣ የሚንቀሳቀሱ፣ የሚተነፍሱና ሕይወት ያላቸው የደሴ ውድ ቅርስም አሉ፡፡
እኒህ ሰው የትውልድ ቦታቸው ወሎ እንዳልሆነ በቅርበት የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡
ምናልባት ወደ ሰሜን ሸዋ አካባቢ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ እስካሁን ግን የተወለዱበትን ቦታና ዘመን በርግጠኝነት የሚያውቅ
የለም፡፡ እርሳቸውም ሃይማኖታቸውንና ምግባራቸውን እንጂ ሰው ትውልዳቸውንና ጎሳቸውን እንዲጠይቃቸውም እንዲያውቅላቸውም
አይፈልጉም፡፡ ከጥንት ጀምሮ የሚያውቋቸው የደሴ ከተማ ሽማግሌዎች ግን እርሳቸውን ያወቁበትን ጊዜና በዚያ ጊዜ የስንት ዓመት
ሰው ሊሆኑ እንደሚችሉ በመገመት እድሜያቸውን በሰባና ሰማንያ መካከል ይገምቱታል፡፡ ወደ ጎንደር ለትምህርት ሲሄዱ ደሴ ደረሱ
አሉ፡፡ እዚያ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትና የተጎዱ ሰዎችን አዩ፡፡ እዚህ በተግባር የሚሠራ ሥራ እያለ እዚያ የቃል ትምህርት
ለመማር ምን ወሰደኝ ብለው እዚያው ደሴ ቀሩ አሉ፡፡
እኒህ ሰው የሚታወቁት በሥራና በፍቅር ነው፡፡ በደሴ ከተማ የሚገኙትን አብያተ
ክርስቲያናት በማሳነጽ፣ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር አሻራ አኑረዋል፡፡ እንዲያውም እርሳቸው ካልገቡበት የሚሳካ አይሆንም ብለው
ደሴዎች እስኪገምቱ ድረስም ደርሰዋል፡፡ እርሳቸው ካዘዙ ምደርም ትታዘዛለች እንኳን ሰው ይባላል፡፡ የርሳቸው በጎ ሥራ ግን
በዚህ የሚያቆም አይደለም፡፡ የተቸገረና የተጨነቀ ሰው ካገኙ ግንባር ቀደም ደራሽ ናቸው፡፡ ለርሳቸው ዘርና ሃይማኖት ሰውን
ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም፡፡ ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል፡፡ ይህ ርዳታቸው ከመከራ ያወጣቸው፣ ከችግር የታደጋቸውና ሕይወታቸውን
ያቀናላቸው ሰዎች ስለ እኒህ አባት ሲያወሩ ከማያቋርጥ ዕንባ ጋር ነው፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም ከንግግር ይልቅ እርሳቸውን
እያሰቡ ዝም ብለው በማልቀስ ይገልጧቸዋል፡፡
መቼም ለአንዳንዱ አብዝቶ አይደል የሚሰጠው፡፡ እርሳቸው የአካባቢ ጥበቃ አርበኛም
ናቸው፡፡ በዚህ የእርግና እድሜያቸው እንኳን መኮትኮቻና መቆፈሪያ፣ አካፋና ባሬላ ይዘው በደሴ ተራሮች ላይ ዛፍ ሲተክሉ ይውላሉ፡፡
ደሴን በአራቱ መዓዝን ስታዩዋት አረንጓዴ ብትሆንባችሁ አትገረሙ፤ እርሳቸው ከአርባ ዓመት በላይ ለፍተውላት ነው፡፡ ለእርሳቸው
ዛፍ የሚቆርጥ ቀርቶ ቅጠል የሚበጥስም የማርያም ጠላት ነው፡፡ አይከፈላቸውም፤ አልተመደቡም፤ ደብዳቤ የሰጣቸው የለም፤ እርሳቸው
ግን የሀገሬ መራቆት የኔ መራቆት ነው ብለው ደን ሲተክሉና ሲከባከቡ ይኖራሉ፡፡
የእኒህን አባት ስም የሚያውቀው የለም፡፡ ስማቸው ተረስቷል፡፡ ስማቸው የተረሳው ሕዝብ
ሌላ የፍቅር ስም ስላወጣላቸው ነው፡፡ ሕዝብ የንቀት ስም፣ የውርደት ስም፣ የሃፍረት ስም ይሰጣል - ለጠላው፡፡ ሕዝብ የፍቅር
ስም፣ የክብር ስም፣ የቁልምጫ ስም ይሰጣል - ላፈቀረው፡፡ ለእርሳቸውም ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም የሚያስረሳ ስም
ሰጥቷቸዋል፡፡ መፍቀሬ ሰብእ (ሰውን የሚወድድ፣ ሰውም የሚወደው) የሚል ስም፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብእ ይባላሉ፡፡
አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፡፡
የደሴ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተጀመረና ለመጨረስ ገንዘብ አጠረ፡፡ ወዲህ ቢባል
ወዲያ ገንዘብ ከየት ይምጣ፡፡ የደብሩ አስተዳዳሪ አውጥተው አውርደው አንድ ሃሳብ አመጡ፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብእ እንደ እኁ ቅዱስ
መሸጥ አለባቸው፡፡ ሄዱና አማከሯቸው፡፡ ‹‹አባ እርስዎን ሸጠን የገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ልንጨርስ ነው›› አሏቸው፡፡
‹‹እኔ ምን አወጣላችኋለሁ›› አሉ ገርሟቸው፡፡ ‹‹በደንብ ያወጣሉ፡፡ ብቻ ለመሸጥ ይስማሙልን›› አሏቸው፡፡ ‹‹ካወጣሁ እንኳን
እንድ ጊዜ ዐሥር ጊዜ ልሸጥ›› አሉ አባ መፍቀሬ ሰብእ፡፡
በእርሳቸው ስም የርሳቸው ፎቶና ስም ያለበት ቶምቦላ ተዘጋጀ፡፡ ድፍን ደሴ - ሙስሊም
ከክርስቲያኑ ተሻምቶ ገዛው፡፡ መፍቀሬ ሰብእ አይደሉ፡፡ ያልተሰበሰበውን ጨምሮ ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ተሸጡ - አባ መፍቀሬ
ሰብእ፡፡ ሌሎቹ የሀገር ሀብት፣ ቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና
ለዓላማቸው ሸጡ፡፡ ሌሎች በቤተ እምነቶች ውስጥ ተደብቀው ለጥቅማቸው ሲሉ የምእመናንን ገንዘብ በሚበሉበት ዘመን፤ ለምእመናን
ሲሉ አባ መፍቀሬ ሰብእ ተሸጡ፡፡ ሌሎች በጎቻቸውን ለራሳቸው ሲሸጡ፤ አባ መፍቀሬ ግን ለበጎች ሲሉ ራሳቸውን ሸጡ፡፡ እልም ባለ
በረሃ ውስጥ የምትገኝ ቀዝቃዛ ምንጭ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ እንድታረካ፤ ታማኝነትና ሕዝብን መውደድ፣ በዓላማ መኖርና ለዓላማ
መሠዋት እየጠፋ ባለበት ዘመን፣ እርሳቸውን ማየት እንደዚያ ነው፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው
aba mefkeran ketkit ametat befit awkachew neber ewnet new enam des alegn
ReplyDeleteእርሳቸውም ሃይማኖታቸውንና ምግባራቸውን እንጂ ሰው ትውልዳቸውንና ጎሳቸውን እንዲጠይቃቸውም እንዲያውቅላቸውም አይፈልጉም፡፡
ReplyDeletemelkam yezera mekalm fire yaferal !!!
ReplyDeleteYegermal DNK yemtanesachew hasaboch letewled yeterfaluna !!
E/her abzito yebarkelin AMEN!!!
በተግባር አርአያ የሚሆኑ አባቶች ያላሳጣን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ReplyDeleteegziabher endezih aynet abatochin yabzalin
ReplyDeleteእንደው ታድለሃል ስንቱን ይሆን የምታየው?
ReplyDeletelike
ReplyDeleteWe need such kind of persons in our politics. Let’s pray to the almighty to give them the wisdom to see beyond themselves. Thank you D/n dani
ReplyDeleteinteresting
ReplyDeleteየዘንድሮ ፍቅር ሰኞ አዲስ ማክሰኞ ልብስ እሮብ ብጥስጥስ አሉ መፍቀሬ ሰብእ!
ReplyDeleteመፍቀሬ ሰብእን የመሰሉ የፍቅር አባት ዳንኤልን የመሰለ የጥበብ ወጣት አያሳጣን አለ ዮኒ!
Impressive
DeleteYes, great
DeleteDani astewash atita silesachewu yetenagerkewu tinishuan neger newu gin esachewu kedesem wetitewu be agorabach weredawoch bizu sertewual endesachewu yela ayimesilegnim
ReplyDeleteOh Dany..., He is well respected not only in Desse also in the near by town like Kobolcha, Bati and so on. Well said, God bless you and Aba Mefkire.
ReplyDeleteድንቅ አባት
ReplyDeleteEgeziabeher tena & regim edme yesteh Dn.Dani. I have no word to express what I feel when I read it. Ende Aba Mefkere Sebe aynet abatochen Egeziabeher yabzalen!!!!!!
ReplyDeleteዳንየ እንደምን ሰነበትህ? መቼም መመስገን ያለበትን ሰው በአግባቡ ስለማናመሰግን እንጅ የኒህን ሰው ታሪክ ቀድሞ ግቢ ውስጥ እያለን ጓደኛየ ይነግረኝ፡፡ ነበር ግን እግዚአብሔር ፈቅዶልኝ እኔ ደግሞ ከ አንድ ዓመት በፊት ግሸን አይቻቸዋለሁ በትክክል አርዓያ የሚሆኑ ለተፈጠሩበት ዓላማ የዋሉ ሰው ናቸው አንተንም ላላወቃቸው ስላሳወቅህ እግኢአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ፡፡በዚህ ዘመን ደግ ሰው የለም ብሎ በቲፎዞ ኃጢአት ውስጥ ለሚዋኝ ልቦናችን አፍ የሚያስይዝ ታሪክ ነው፡፡
ReplyDeleteEgziabhire regem edema yestachew. and God bless you Dn Daniel.
ReplyDeleteI personally thank Aba Mefekere, because he helped my family during the time of difficulties
ReplyDeleteአባ መፍቀሬ ሰብእ ድምጻቸውን ለመስማት እንኳን የሚናፈቁ፣ በጣም ላስተዋለ ሰው ደግሞ እግዚአብሔር አምላኩን የሚያይባቸው አባት ናቸው።
ReplyDeleteDear Deacon Daniel, thankyou so much. minim alilihim asitewashi ayasatah. Aba Mefikeren yemayawuk ye Dessie sewu bicha aydelem Wollo bemulu yawukachawal, Gishenin yetesaleme sewu hulu Aba Mefikeren yawukal. Gin sile Moriniho ina Runny awurta yematitegibewu hagere Sile Aba mefikere aynet sewu lemaseb lemawurat gize yelatim. rejim idime ketena gar Deacon Daniel.
ReplyDeleteEgziabhere Amlak yitebikilin!
ReplyDeleteDani Egziabhair yistiln, Egziabhair Endih Yalutn Sewoch Yabzaln,!!!!!!!!
ReplyDeletetikikil newu dani
ReplyDeleteDani,
ReplyDeleteYeselasa Amet Tiztayen Kesekeskibign... I know aba Mefkere years back. He was very amazing father, he is and will be. Selamtayen Adirslighn... Kehagere Amerika
ዳኒ በእውነት ድንቅ ሰው አስተዋወከን እስቲ ሌሎችም እየፈለክ አስተዋውቀን እግዚአብሔር እድሜ ና ጤና አብዝቶ ይስጥህ
ReplyDeletekb ze Adigrat
ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ከአገልግሎት ዘመን ጋር ያብዛልህ
ReplyDeleteዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር አስታዋሽ አያሳጣህ ረጅም እድሜን ከአገልግሎት ዘመን ጋር ያብዛልህ
ReplyDeleteEgzabher mastewalun yabzaleh Dn Daniel.
ReplyDeleteBerhanu besefet yemiyabera Aba mefker Sebe, egzabher amlak endhi kidusanun yabzalegn ena yehen alcha Alem Yataftut, I am impressed he doesn't want to be questioned about where he is from, great lesson for Love doesn't ask where we are from, or what background we have what matter is we have been created in the image of our GOD so we all are humans that is why we should love unconditionally.
God bless all of us!
እግዚአብሔር በእድሜ በፀጋ ይጠብቅልን እንዲህ ያሉ አባቶችን አብዝቶ ያኑርልን፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል አንተንም እግዚአብሔር ይባርክህ በጤና ይጠብቅልን
ቃለ ሕይወት ያሰማልን!!!!
kale hiwet yasmalen yantena yesachewun aynet sew bemidrachin fetari yabzalin
ReplyDeletedes yemil Tarik new
ReplyDeleteውድ ወንድማች ዳኒ፥ የበረክት ሥራህ ሁሉ ይባርክልን፤ እግዚአብሔር አምላክ ።
ReplyDeleteየተከበሩ አባታችን፥ አለቃ አያሌው ታምሩን ብናጣቸውም፤
በዘመናችን አንተን የመሰለ፥ የሃይማኖት መምህር፣ የወግ ጸሐፊ፣ የታሪክ ሰው፣ የሃገር አስተዋዋቂ፤ ማግኘታችን በእውነት እጅግ ደስተኞች ነን።
ዛሬ ዛሬ፥ ስለ መልካም ሃይማኖትህና እምነትህ ቀንተህ ሠዎችን ስትረዳ፤ አላስተዋይ የሆኑ ሠዎች ሲመለከቱህ የሚያወጡልህ ስም ለለ፤ እርሱም "አንተ ደግሞ ምን የሚሉህ ምግባረ ሠናይ ድርጅት ነህ?" ይላሉ።
እንግዲህ፥ አላስተዋይና ፌዘኞች ሠዎች ማለት እነዚህ ናቸው ነው። ፌዘኛን ሠው አትገስጸው፤ ማለት ይሄኔ ነው። /ምሳ 14፥6 ፤ 15፥12 ፤ 19፥25 ፤ 21፥11/
ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ሠውንም የሚያከብር ሠው ደግሞ፤ ልክ እንደ ወንድማች ዳኒ፥ ይጽፋል፣ ይናገራል፣ ያስተምራል "ለርሳቸው ለአባ መፍቀሬ ሰብእ፥ ዘርና ሃይማኖት ሰውን ለመርዳት መመዘኛዎች አይደሉም፡፡ ሰውነት ብቻ ይበቃቸዋል።" ይላል!
Dear dani thanks and god bless you!
ለተፈጠሩበት ዓላማ የዋሉ ሰው ናቸው አንተንም ላላወቃቸው ስላሳወቅህ እግኢአብሔር ዋጋህን ይክፈልህ፡፡በዚህ ዘመን ደግ ሰው የለም ብሎ በቲፎዞ ኃጢአት ውስጥ ለሚዋኝ ልቦናችን አፍ የሚያስይዝ ታሪክ ነው፡፡
ReplyDeleteትዉልድ ከዚህ ምን ይማራል?
ReplyDeleteእዉነት ለመናገር እራስን ክዶ ለሰዎች መኖር በጣም ከባድ ነው ነገር ግን በፍቅር ሁሉ ይቻላል።
ዳንኤል በርታልን።
Egziabiher yimesigen ! That we still have such fathers. I'm scared of the future without such good fathers and mothers. But I known God will never let his peoples alone !
ReplyDeleteGod bless you D. Daniel !
Betam DES Yilal, Betam Yasazinal! Mamen hulu yikebdal? Lemehonu egnih abat Be hiwot alu? Ere betam yidenkal! Dn. Daniel, Leul Egziabher Yitebikih, yabertah. Silante malet alfeligim, bicha berta! Gin sile ABA MEFKERE SEB, menagerachin bicha yibekal? Binayachew? binihed? GUZO...GUZO...ye hiwot guzo....Lekas behiwot yeminor alen! Kale hiwot yasemah wondime!
ReplyDeleteAba mefikera talaki abati nachw beye ametu ayachw slenebere amilki yitebikiln.
ReplyDeleteBetam dink new egiziabiher ahunim Ethiopia endezih yale abat be ahun sat yasifeligatal? Egiziabiher cher new esu yisitsat!!!
ReplyDelete፡በዚህ ዘመን ደግ ሰው የለም ብሎ በቲፎዞ ኃጢአት ውስጥ ለሚዋኝ ልቦናችን አፍ የሚያስይዝ ታሪክ ነው፡፡
ReplyDeleteመመረጥ ይላችኋል እንዲህ ነው፡፡
ReplyDeleteወንድሜ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የደሴ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ በተከታታይ ሁለት ቀናት ተገኝቼ ትምህርትህን ሰምቻለሁ በእውነት እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶ አገልግሎትህን ይባርክልህ፡፡ አንተ ወንድማችን በመገኘትህ ደሴዎች በጣም ደስ ብሎናል፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ በተረፈ በጣም የምንወዳቸውን አባ መፍቀሬን አስመልክተህ የፃፍከው ቢያንስባቸው እንጂ አይበዛባቸውም ለእኛ ታላቅ አባታችን ናቸው፡፡ ከሚያዝነቀው ጋር የሚያዝኑ ካለቀሰው ጋር የሚያለቅሱ ቤተክርስቲያን ለማሰራ ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ የሰው ቅርስ ናቸው፡፡ ተባረክልን ዳኒ እግዚአብሔር ከዘመኑ ይሉኝታ ይጠብቅህ፡፡
ReplyDeleteበዚህ ዘመን ደግ ሰው የለም ብሎ በቲፎዞ ኃጢአት ውስጥ
ReplyDeleteቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና ለዓላማቸው ሸጡ
ReplyDeleteቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና ለዓላማቸው ሸጡ
ReplyDeleteesachew rasachwen shetu egna gen be ejachen yalenen neger enkuan letechegeru sewoch enereda yehone?
ReplyDeletethank you dani great father realy
ReplyDeletekale hiwot yasemalin d/n dani
ReplyDeleteEgziabher yimesigen bezih gizea endezih ayinet abat. Kegnih abat gar tinish menor temegnehu! edime yisitilign
ReplyDeleteየአባ መፍቅሬ ምሳሌነት አጀብ ያሰኛል፤ ዲ/ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
DeleteThank you so much Dani however this is not Meles Zanawi or the current Goverment dream, they want us to separate by state and region. If they meet this kind of person, they will take them into jail. I am very happy to see this kind of person at this time. God bless Ethiopia.
ReplyDeletehi Dany it was a good view.
ReplyDeleteI appreciate your tallent ideas
መፍቀሬ ሰብእ አይደሉ፡፡
ReplyDeleteጎሽ ዳኒ!!! ዛሬም እንዲህ ዐይነት አባቶች እንዳሉ አሳየኸን!!!ጥቂት የከተማው ወጀብ የዋጣቸውን የተሰናከሉ አባቶች በማየት ብቻ መላው ምዕመን የሓይማኖት አባት እንደሌለው ተደርጎ መቅረቡ ሁሌም ያሳዝነኛል!!!በተለይ እስከ 7፡00 ሰዓት ሲያርሱ ውለው ስጋቸውን ካደከሙ በሁዋላ እየቀደሱ በዐመት ከምዕመኑ በሳህን የተሰበሰበ 2 ኩንታል እህል ብቻ የሚከፈላቸው የገጠሪቱዋ ኢትዮጵያ ቅን ካህናት ተረስተው በከተማው ጥቂት ካህናት ምግባር የተነሳ በጅምላ ሲወቀሱ ሳይ ልቤ ይደማል!!!
ReplyDeleteዳኒ!!! አንድ ወቅት ባወጣኸው ጦማር መሪን የሚፈጥረው ህዝብ እንደሆነ ነግረኸን ነበር!!!እኔም ታዲያ ህዝብ መሪ መፍጠር ከቻለ ምዕመንስ የሃይማኖት አባቱን ቅንና ደግ አድርጎ መፍጠር አይችልምን እላለሁ!!!ቅን አባት እኮ የሚወጣው ቅን ምዕመናን ሲኖሩ ነው!!!አሁን እያየን ያለነው ግን እንደ ምዕመን የሚጠበቅበትን ሳይወጣ የአባቶችን ሀጢአት የሚዘከዝክ ምዕመንና ወጣት ነው!!!ከላይ እስከ ታች ያሉ አባቶች ገበና የሁለት ግሩፕ ሲሳይ ሆኖ በየቀኑ በአደባባ ሲሰጣ ማየት ያሳምማል!!!በተለይ እንደእኔ የካህን ልጅ ብትሆን ስቃዩ ይገባሀል!!!
ዳኒ!!!የሳተ ህዝብ ካለ የሚሳሳት ካህን መኖሩ ግድ ነው!!!ቆይማ ታሪክ ልንገርህ!!!
መቼም አራት አይና ጎሹ የሚባሉትን ታላቅ የመጽሀፍ መምህር ታውቃቸዋለህ-ዐይነስውሩን!!!እንግዲህ ሊቃውንት ሲራክ እንዳለው ወይ በመጠጥ ወይ በሴት የመውደቅ ፈተና አለባቸው አይደል!! ተማሪያቸው እየመራቸው ካንድ ገበሬ ሚስት ጋር ሲወሰልቱ ገበሬው ይደርስባቸዋል. ሆኖም የገበሬውን መምጣት ከሩቅ የተመለከተው ተማሪያቸው እንደምንም አድርጎ በጉዋሮ አጥር ጥሶ ይዙዋቸው አመለጠ. ሚስትየዋ ግን እንደፈረደባት የገበሬ ባሉዋን ቅጥቀጣ/ሰበራ በቁሙዋ ተቀበለችው!!!ታዲያ አራት አይና ጎሹ የኔታ ተረፉ ላላቸው ተማሪ ሲመልሱ ….መስገርትሰ ተቀጥቀጠት ወንህነሰ ድህነ….ወጥመዱዋ ተሰበረች እኛ ግን አመለጥን ….ሲሉ የቅዱስ ዳዊትን መዝሙር ጠቅሰው መለሱ ይባላል!!!
አሁንም ምዕመናን የአባቶች ወጥመድ አንሁን!!!ደግ ልጅ እንዲኖር ደግ አባት እንደሚያስፈልገው ሁሉ አናዳንዴ የተገላቢጦሹም ይሰራል!!!
አምናለሁ!!! ከላይ እንዳቀረብካቸው አይነት ብዙ አባቶች አሉን!!!አቅርብልን!!!ሁሌ ስለሳቱት መነጋገር ምዕመኑንም ጨለምተኛና በሃይማኖት አባቶቹ እምነት እንዳይኖረው እያደረገ ነው!!
ዳኒ መቸም ጥሎ አይጥልም ይባል የለ ተባረክ አሳቢ አትጣ። እንኮን ለቤተክርስቲያን ለሀገር ብሎ እራሱ የሚሸጥ ቀርቶ አባቶች በዚህ አይነት ሁኔታየሰሩትን ቤተክርስቲያን በቁሟ የሸጠ፣የተከሉትን ደን ለሱዳን የሚሽጥ፣ሀገሩን የሽጠ፣ከዛም ትውልድን እንኮን ክቡር የሰውን ልጂ የሚሽጥ አሁንም ያልበቃው የሚወለድ ህፃናትን እንኮን የሚሽጥ ነፍሰ በላ ወንበዴ ነው ያለን እንኮን እንኮን ለሀገር ለወገን ለሰው ልጂ የሚያስብ እንዲህ አይነት ልዩነት ነው ያለን ።እንዲህ አይነቶች አባቶች ስለነበሩን እማነው እስካሁን የምንተነፍሰው ከዚህ በሓላ እንጃ እጅ በል ወንድሜ ሰላምና ጤናን እመኘልሀለሁ ቸር ወሬ ያሰማን።እንዴው ግን የኢትዪጵያ ጉዳይ እንዲህ ሁኖ ቀረ ማለት ነው?????????????????????????????????
ReplyDeleteAba mefekire yehulum abat nechewu ke hesaninite jemero awukachewalihu be hiwote ds yalegn ken benor ye kedus gebriel betekerestiyan mereka beal lay esachewun saye nw kemer nw yalekeskut yedesta eneba!!!!
ReplyDeleteበመጀመሪያ መልካሙን ሁሉ ላንተ በመመኘት ሲሆን
ReplyDeleteአምላክ ጥሩ ማስተዋልን ስለ ሰጠህ አንተም ደግሞ ተጠቀምክበት።
አንድ ወቅት ዝዋይ ወደ አቡነ ጎርጎርዮስ ገዳም ሄጄ ነበር ጥሩ ነገር
ስለ ተመለከትኩ ምን አልባት ቦታው ላንተ አዲስ ባይሆንም ባንተ
እይታ የተሸጡ አባትን ታገኛቸዋለህ ብዬ እገምታለሁ መልካሙን
ሁሉ እመኝልሃለሁ።
‹‹ካወጣሁ እንኳን እንድ ጊዜ ዐሥር ጊዜ ልሸጥ›› አሉ አባ
ReplyDeleteመፍቀሬ ሰብእ፡፡
አባ መፍቀሬ አሁን በህይወት አሉ ?
ReplyDeleteበእኛ ዘመን እንዲህ ያሉ አባት ማየት በራሱ ተስፋ ነው:: እግዚአብሀር አለተወንም::
ስለ እኒህ ቅዱስ ሰው እጅግ የተወደደ ስራ ደሴ ሄጄ በነበረበት ወቅት ሰምቻለሁ፡፡ ሙሃዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ስላስታወስካቸው እግዚአብሄር ዋጋህን አይረሳም፡፡
ReplyDeleteDear Daniel bless you more and more!
ReplyDeleteI am always thinking of telling you how much you inspired me to the love of St's in fact you infected me !! saying that I don't want to fall out of love I rather starving for more and more of that .Although I like the fact you preach and write about everything I always wish you to tell us about inspiring individuals so we can see how behind we still are.
thanks dani!
ReplyDeleteDn Daniel
ReplyDeleteAba Mefikre is an honorable and a saintly father. Please prepare and publish his biography. There are a lot of things to say about him.
F.G
Dessie
Dany I Miss ur post....it has been 1 week.. owkay hope u will b back soon!!! Seeyalata
ReplyDeleteዳኒ አንተም ተሸጥክ እንዴ? ጠፋህብን እኮ፡፡
ReplyDelete'ሌሎቹ የሀገር ሀብት፣ ቅርስና ታሪክ በሚሸጡበት ዘመን አባ መፍቀሬ ራሳቸውን ለሀገርና ለወገን፣ ለእምነታቸውና ለዓላማቸው ሸጡ፡፡'
ReplyDeleteygermal and amet wollo dessie koychalehu esachewunm awukachewalehu betekrstan lay atatachewum betely St Gebriel hulea alu slesachew gn alawukm neber. Daniel ante asaweken ye fkr abat mehonachewun lezih twuld astemari tegegneln. bzu abatoch alat yegna ager ebakh endih eyenegerken ye tibit ye zeregn net ye tenkol lbachn sberln bedeb. ye ethiopia ye kdusan ager mehona teresta lbwelde hunobn newu yalewu tariku hulu silezih bedeb ende aba mefkrea seba yalut astemari nachewuna bezuf ahutewu. berta
ReplyDeleteEGZIABHER BUZU MENGED ALEW .... D/Y DANIEL KBERT LE AMET BALE YEMIHON DES YEMIL KAL ASMEHTEHNGAL KALEHIWT YASMLN...
ReplyDeleteGod bless you Daniel,i wish many people read this blog.
ReplyDeleteዲያቆን፡ዳንኤል
ReplyDeleteዕውቀቱን፡ያብዛልህ።
የሠራዊት፡ጌታ፡ሙሉ፡ጤንነትና፡ረዥም፡ዕድሜ፡ሰጥቶ፡
ያሰብከውን፡እንድትፈፅም፡ይርዳህ።
እግዚአብሔር፡ይባርክህ።
ዲያቆን፡ዳንኤል
ReplyDeleteዕውቀቱን፡ያብዛልህ።
የሠራዊት፡ጌታ፡ሙሉ፡ጤንነትና፡ረዥም፡ዕድሜ፡ሰጥቶ፡
ያሰብከውን፡እንድትፈፅም፡ይርዳህ።
እግዚአብሔር፡ይባርክህ።
የአባ መፍቀሬየ ሰው ልቦና ይስጠን።
ReplyDeleteዳኒ አንተም እደመልካሙ አባት እደአባ መፍቀሬ ለሀገርህ፣ለቤተክርስቲያንህ ተሽጠሀል እየተሽጥህም እኮነው ከዚህ በላይ ዋጋው እጂግ ውድ በሆነ በኢትዪጵያ ህዝብ መገዛት እኮ እዴት መታደል ነው።አሁንም የበለጠ ዋጋ ስለምታወጣ በርታ ከፈጣሪህ ጋራ እሱም ውድ የሆነውን ዋጋ እንድታወጣ እያዘጋጀህ ነው።ደስ የሚለው ግን ለካ አባቶቻችንም ድካማቸው እንዲሁ አልቀረም የሚተካ ፍሬ አፍርተዋል እዴት ደስ ይላል ።በለረ ወድማለም በርታ እግዚያብሔር ካተጋራ ከቤተሰብህም ጋር ለዘለዓለም ይሁን።ከበላይ ነኝ ቸርወሬ ያሰማን።
ReplyDeleteእልም ባለ በረሃ ውስጥ የምትገኝ ቀዝቃዛ ምንጭ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ እንድታረካ፤ ታማኝነትና ሕዝብን መውደድ፣ በዓላማ መኖርና ለዓላማ መሠዋት እየጠፋ ባለበት ዘመን፣ እርሳቸውን ማየት እንደዚያ ነው፡፡
ReplyDeletegerume sehafi neh betame edenekalehu yantene sehufoche sanebe menegha metadele newe denke setota egezeabehere yebarekeh
ReplyDeleteአባ መፈቀሬ ሰብ አዉቃቸዋለሁ እናም ሁሌም ከደሴ መድሃኒአለም እኩል የሚናፍቁኝ ለቤተክርስትያን የቆሙ አባት ናቸዉ
ReplyDeleteአባ መፍቀሬን የማስታውሳቸው በተለይ ለተዓምረ ማርያም ያላቸው ፍቅር ከልባቸው የመነጨ ወደው የሚያስወድዱ አባት የእመብርሃን ወዳጅ ናቸው
ReplyDeleteGod protect ABA MEFKERY ! he is the roll model of every one I know Aba mefqry he is more that Daneal explain words really god give him a long age and health!!!!!
ReplyDeleteእልም ባለ በረሃ ውስጥ የምትገኝ ቀዝቃዛ ምንጭ ተስፋ የቆረጠውን ሁሉ እንድታረካ፤ ታማኝነትና ሕዝብን መውደድ፣ በዓላማ መኖርና ለዓላማ መሠዋት እየጠፋ ባለበት ዘመን፣ እርሳቸውን ማየት እንደዚያ ነው፡፡
ReplyDeleteohhhhh...my GOD !!!! Its absolutelytruth i, knew aba mafkere 12 years ago when i was Ethiopia /DESSIE....he was praying for temket at mehal piazza...same thing for muslims alfeter ....every body knows him at dessie ....he is well respected by almost the entire population of wollo...not only dessie.......thanks dani to remember his holly ness aba MAFKERE ZDESSIE,,,,,,LONG LIFE ABA,,,,WE...ALWAYS PRAY FOR U!!!
ReplyDeleteEgziabhier yegnanm lib endesachewu yararaln
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ
ReplyDeleteአባ መፍቀሬ ሰብእ በእኔ ቃላት እንዲህ ናቸው ተብለው የማይገለጹ አባት ናቸው፡፡ እኔ ሳውቃቸው ሥልጣን፣ ሓላፊነት፣ ገንዘብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ወገን፣ ጎራ፣ ጎጥ፣ ቋንቋ የማይለውጣቸው ትጉኅ አገልጋይ ናቸው፡፡ እኝህን አባት በተለይ ግሸን ማርያም የሔደ፣ ቅዱስ ላሊበላ የተመላለሰ ያውቃቸዋል፡፡
ብዙ ያልተነገረላቸው፣ ያልተወራላቸው፣ ያልተጻፈላቸው፣ አባት ናቸው አባ መፍቀሬ ሰብእ፡፡ ሰው ኃብታም ይሁን ደኃ፣ የተማረ ይሁን ያልተማረ፣ የለበሰ ይሁን ያልለበሰ በእርሳቸው ዘንድ ያው አንድ ነው፡፡
እኔ ሁል ጊዜ የማልረተሳው ሕጻናት ሆነን ልደትና ጥምቀት ሲደርስ አዲስ ልብስ አይናፍቀንም ትዝም አይለንም ትዝ የሚለንና የልጅነት ድካምና የፀሐዩ ሙቀት ሳይበግረን አባ መፍቀሬ ሰብዕ ጋር የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘን ታቦታቱን ስናጅብ ብቻ ነው፡፡ የሚሰጡን ፍቅር ልዩ ነው ክፍያችንም ፍቅር ነው፡፡ የታቦታቱ መነሻ ሰዓት ሲደርስ በተንቀሳቃሽ ቴፕና በእጅ የድምጽ ማጉያ የሊቀ መዘምራንን መዝሙር እያዘመሩ እልል በሉ ውጡ እያሉ ሲቀሰቅሱ ልዩ ለዛ አላቸው፡፡
በተለይ የእርሳቸው ልዩ ጸጋ ሌሎች የተሸለሙበት እርሳቸው ግን ተረስተው ያልተሸለሙበት፣ ቃለ መጠይቅ ያልተደረጉበት በገዳማት፣ በአድባራት፣ በገጠር አብያተክርስቲያናት፣ በጥምቀተ ባህር አካባቢ ዛፍ ይተክላሉ፣ ያስተክላሉ፣ ወኃ ያጠጣሉ ሌሎች እንዲያጠጡ አደራ ይላሉ፣ አጥር ያሳጥራሉ፣ አጠቃላይ ለዛፍ ልዩ ፍቅር አላቸው ልዩ እንክብካቤ ያደርጋሉ፡፡
አባ መፍቀሬ ሰብእ ቅዱስ ላሊበላ የጥምቀትና የልደት ቢታመሙም ሔደው ይተኛሉ እንጂ አይቀሩም፡፡ ለልደት አሁንም አይቀሩም ለጥምቀት ግን ከ1989 ዓ.ም በኋላ አልሔዱም ምክንያታቸው ጥቅም፣ ሥልጣን፣ ገንዘብ ሳይሆን ደብሩ ጥምቀተ ባህር አካባቢ ያለውን ዛፍ አስቆርጦ ለምን ብለው ቢጠይቁ ምን አገባዎት ስለተባሉ ነው፡፡
በአጭሩ ጊዜ ቢኖር ስለ አባ መፍቀሬ ሰብእ ብዙ መጻፍ ይቻላል፡፡ አባ መፍቀሬ አንደበተ ርቱእ፣ ሲጠይቁ ለዛ ያላቸው ሲሆኑ ሌባ፣ ወንበዴ፣ ቀጣፊ፣ መናፍቅ አይወዱም፡፡ አሁን ምንም ንብረት፣ ገንዘብ፣ ደመወዝ፣ ቤት፣ መኪና፣ ዘመድ የላቸውም ‹‹ዘአልቦ ጥሪት›› ማለት አባ መፍቀሬ ሰብእ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ቀሪ ጊዜአቸውን ይባርክ እርሳቸውን የመሰለ አባት ይተካልን አሜን፡፡
ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ
ReplyDeleteአባ መፍቀሬ ሰብእ በእኔ ቃላት እንዲህ ናቸው ተብለው የማይገለጹ አባት ናቸው፡፡ እኔ ሳውቃቸው ሥልጣን፣ ሓላፊነት፣ ገንዘብ፣ ዘመድ አዝማድ፣ ወገን፣ ጎራ፣ ጎጥ፣ ቋንቋ የማይለውጣቸው ትጉኅ አገልጋይ ናቸው፡፡ እኝህን አባት በተለይ ግሸን ማርያም የሔደ፣ ቅዱስ ላሊበላ የተመላለሰ ያውቃቸዋል፡፡
ብዙ ያልተነገረላቸው፣ ያልተወራላቸው፣ ያልተጻፈላቸው፣ አባት ናቸው አባ መፍቀሬ ሰብእ፡፡ ሰው ኃብታም ይሁን ደኃ፣ የተማረ ይሁን ያልተማረ፣ የለበሰ ይሁን ያልለበሰ በእርሳቸው ዘንድ ያው አንድ ነው፡፡
እኔ ሁል ጊዜ የማልረተሳው ሕጻናት ሆነን ልደትና ጥምቀት ሲደርስ አዲስ ልብስ አይናፍቀንም ትዝም አይለንም ትዝ የሚለንና የልጅነት ድካምና የፀሐዩ ሙቀት ሳይበግረን አባ መፍቀሬ ሰብዕ ጋር የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዘን ታቦታቱን ስናጅብ ብቻ ነው፡፡ የሚሰጡን ፍቅር ልዩ ነው ክፍያችንም ፍቅር ነው፡፡ የታቦታቱ መነሻ ሰዓት ሲደርስ በተንቀሳቃሽ ቴፕና በእጅ የድምጽ ማጉያ የሊቀ መዘምራንን መዝሙር እያዘመሩ እልል በሉ ውጡ እያሉ ሲቀሰቅሱ ልዩ ለዛ አላቸው፡፡
በተለይ የእርሳቸው ልዩ ጸጋ ሌሎች የተሸለሙበት እርሳቸው ግን ተረስተው ያልተሸለሙበት፣ ቃለ መጠይቅ ያልተደረጉበት በገዳማት፣ በአድባራት፣ በገጠር አብያተክርስቲያናት፣ በጥምቀተ ባህር አካባቢ ዛፍ ይተክላሉ፣ ያስተክላሉ፣ ወኃ ያጠጣሉ ሌሎች እንዲያጠጡ አደራ ይላሉ፣ አጥር ያሳጥራሉ፣ አጠቃላይ ለዛፍ ልዩ ፍቅር አላቸው ልዩ እንክብካቤ ያደርጋሉ፡፡
አባ መፍቀሬ ሰብእ ቅዱስ ላሊበላ የጥምቀትና የልደት ቢታመሙም ሔደው ይተኛሉ እንጂ አይቀሩም፡፡ ለልደት አሁንም አይቀሩም ለጥምቀት ግን ከ1989 ዓ.ም በኋላ አልሔዱም ምክንያታቸው ጥቅም፣ ሥልጣን፣ ገንዘብ ሳይሆን ደብሩ ጥምቀተ ባህር አካባቢ ያለውን ዛፍ አስቆርጦ ለምን ብለው ቢጠይቁ ምን አገባዎት ስለተባሉ ነው፡፡
በአጭሩ ጊዜ ቢኖር ስለ አባ መፍቀሬ ሰብእ ብዙ መጻፍ ይቻላል፡፡ አባ መፍቀሬ አንደበተ ርቱእ፣ ሲጠይቁ ለዛ ያላቸው ሲሆኑ ሌባ፣ ወንበዴ፣ ቀጣፊ፣ መናፍቅ አይወዱም፡፡ አሁን ምንም ንብረት፣ ገንዘብ፣ ደመወዝ፣ ቤት፣ መኪና፣ ዘመድ የላቸውም ‹‹ዘአልቦ ጥሪት›› ማለት አባ መፍቀሬ ሰብእ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ቀሪ ጊዜአቸውን ይባርክ እርሳቸውን የመሰለ አባት ይተካልን አሜን፡፡
amlak yetebkachhu
ReplyDeleteይድረስ ለወንድሜ ደያቆን ዳኒኤል ክብረት፡፡ ለሚታደረገው ደግ ስራ ሁሉ እግዚአብሄር አምላክ ይክፈልህ፡፡እንደ እኔ አይነቱ እምነት እንጂ አውቀት ለሌው ፍጡር ጥሩ የሆነ ትምህርት እየሰጠህ ነው፡፡እመቤቴ ማርያም ካንተ ጋር ትሁን አባ መፍቀሬ ሰብእም ዕድሜና ጤና ይስጥልን፡፡
ReplyDeleteDani egiziabher yistih! betam tilik abat........egiziabher beyezemenu le ethiopia yemibju lijochin setoal antem andu neh.....bakih leloch abatochinm beyebotaw deginetn melkamnetn yaderegu abatochn astewawken......beterefe egiziabher le sirah waga yikifelh
ReplyDeleteTalak Bereketen bezih zemen ayehu! bereketachew tedereben! Zer gosa eyale hezbu tebetatno balebet zemen Fikir be ejegu bekezekezebet zemen enih talak tsega yalacehwn abat bemagegnetachen be ewnet edelegnoch nen! beka Hiwot malete yeh new. Bereketachew tedereben!
ReplyDeleteThanks Dani! Godd News!
ReplyDelete