Thursday, December 12, 2013

የሥልጣኔ ሞት- ከድርሰት ሞት

የዛሬ 600 ዓመት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተባለ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ‹አርጋኖን› የተሰኘ መጽሐፍ ይደርሳል፡፡ ይህንን መጽሐፍ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም እጅግ ያደንቁና ለንጉሡ ለዐፄ ዳዊት ያቀርባሉ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መጽሐፉን ተመልክተው በማድነቅ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘዙ፡፡ አባ ጊዮርጊስንም ሸለሙ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም አባ ጊዮርጊስ ‹መጽሐፈ ምሥጢር› የተባለ መጽሐፍ ደረሰ፡፡ ይህንን የተመለከቱ ሊቃውንትም አድናቆታቸውን ‹‹ቄርሎስና ዮሐንስ አፈወርቅ በሀገራችን ተገኙ፤ ኢትዮጵያም እንደ ሮምና ቁስጥንጥንያ፣ እንደ እስክንድርያም ሆነች› ብለው በማሸብሸብ ነበር የገለጡት፡፡
ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ ግን ለደራሲዎቿ ቦታ የሌላት፣ ማንበብና መጻፍም ብርቅ የሆነባት፣ ድራፍት ቤት እንጂ መጻሕፍት ቤት፣ ጫት ቤት እንጂ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ቤት የማይበረታታባት ሀገር ሆናለች፡፡ ክልል ያላት በክልል ደረጃ የሚጠቀስ ቤተ መጻሕፍት የሌላት፣ መንግሥት ያላት፣ ነገር ግን መንግሥት ዕውቅና የሚሰጠው ድርሰትና ደራሲ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለጀማሪ አቀንቃኞች የሰጠችውን አይዶል እንኳን ያህል ለበካር ደራስያን ለመስጠት ያልፈቀደች ሀገር ሆናለች፡፡ ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር ሆናለች፡፡ ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር ሆናች፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ብርሃን በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ‹‹እስመ ጽሙዐን ለትምህርት ብሔረ ኢትዮጵያ ኄራን - ምርጦቹ የኢትዮጵያ ሰዎች ትምህርትን የተጠሙ ናቸው›› ይላል፡፡ በዚህ ጥማታቸውም የተነሣ ሕንድ ተሻግረው እነ መጽሐፈ በርለዓምን፣ ግሪክ ገብተው እነ ዜና እስክንድርን፣ አምጥተው ነበር፡፡ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥተ ሳባ እንኳን ወደ ሰሎሞን የሄደችው ‹ጥበብን ፍለጋ› መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ እዚህች ሀገር ውስጥ ቆዳ ለጫማ ከመዋሉ በፊት ለመጽሐፍ ነበር የዋለው፤ ብርዕ ለማገዶ ከመዋሉ በፊት ለጽሕፈት ነበር የዋለው፤ ቀለም ለግድግዳ ከመዋሉ በፊት ለፊደል ነበር የዋለው፡፡
በዚህች ሀገር ጥንታዊ ታሪክ መጻሕፍትን መጻፍ ብቻ ሳይሆን፤ ማንበብ፣ ማስነበብ፣ ማስጻፍ፣ ሲነበቡ መስማት ጭምር እጅግ የተከበረ ነገር ነበር፡፡ የተከበረ ብቻም ሳይሆን የቅድስናም ምንጭ ነበር፡፡ በየገድላቱና ድርሳናቱም ‹የጻፈ ያስጻፈ፣ ያነበበ የተረጎመ፣ የሰማ ያሰማ› የሚሉት ቃል ኪዳኖች መጻፍን ብቻ ሳይሆን የተጻፈውን ማንበብ፣ ማንበብ ለማይችሉትም ድምጽን ከፍ አድርጎ እያነበቡ ማሰማት፣ ሲነበብም በጽሞና መስማት ጭምር ዋጋ እንዲኖራቸው ያደረጉ ነበሩ፡፡ የደራስያኑ መጻሕፍት እንዳሁኑ በማተሚያ ማሽን በብዛት አይባዙም ነበርና ለጸሐፊዎች ከፍሎ ማስጻፍ፣ ዋጋ ተቀብሎ በሚገባ መጻፍ የሚያስመሰግን የሚያጸድቅም ነገር መሆኑን ኢትዮጵያውያን ያምኑ ነበር፡፡
ለዚህም ነው በዚያ ሁሉ የእርስ በርስ ጦርነቶች ውስጥ አልፋ፣ አንዳንድ ጊዜም ሀገሪቱ ራስዋ ከጥፋት በተአምራት የተረፈችባቸውን ታሪኮች አስመዝግባ፣ ነገር ግን አያሌ የብራና መጻሕፍትን እስከ ዛሬ ድረስ ጠብቃ ለማቆየት የቻለችው፡፡ በመከራም ጊዜ ከከብቶቿና ከበጎቿ፣ ከእህሏና ከማሯ፣ ከወርቋና ከብሯ ይልቅ መጻሕፍቷን ለማቆየት ነበር ሩጫዋ፡፡ በገድለ ዜና ማርቆስ ላይ በ15ኛው መክዘ መጨረሻ ላይ የተፈጠረውን የእርስ በርስ ጦርነት በመሸሽ የገዳሙ መነኮሳት ከሸዋ ወደ ደቡብ ጎንደር ሲሰደዱ ከአንድ ሺ የሚበልጡ መጻሕፍትን በሦስት ቦታ ዋሻ ውስጥ ደብቀው ማስቀመጣቸውን ይነግረናል፡፡
የደራስያኑ የድርሰት ሥራ የተወደደ፣ ባለቤትነቱም የተከበረ በመሆኑ በቃል የሚፈስሰው ቅኔ እንኳን ‹የእገሌ ቅኔ; እየተባለ ይጠቀስ ነበር እንጂ የባለቤትነት መብቱን የሚያስከብርለት ሕግና ሕግ አስከባሪ አካል የለም ተብሎ አይደፈርም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ጎጃም ከመምህሩ የሰማውን ቅኔ ትግራይ ሄዶ እንደራሱ አድርጎ ሲቀኝ የተሰማ ተማሪ ቅኔውን ሲጨርስ ‹ቅኔያቸውስ ደረሰን፣ ለመሆኑ የኔታ ደኅና ናቸው?› የሚል ውርደት የገጠመው ለደራስያኑ የባለቤትነት መብት ጠበቃ የሆነ ማኅበረሰብ ስለነበረን ነው፡፡ የጎንደሩ ደብረ ብርሃን ሥላሴ ለሸዋው ደብረ ብርሃን ሥላሴ 2000 መክሊት ወርቅ  ‹ደብረ ብርሃን› የሚለውን ስም ለመጠቀም የከፈለውኮ ለባለቤትነት መብት ክብር የነበረው ሕዝብ ስለነበረን ነው፡፡
ዛሬ ግን በዚህች ታሪካዊት ምድር፤ በዚህች ሥነ ጽሑፍ ተፈጥሮ፣ አድጎ፣ ዳብሮ፣ ሠልጥኖ ለወግ ለማዕረግ ደርሶባት በነበረች ሀገር፤ ደራስያንና ድርሰት የተረሱ ዕቃዎች ሆነዋል፡፡ እነርሱን የሚያበረታታ፣ የሚሸልም፣ ዕውቅና የሚሰጥ፣ ማዕረግ የሚሰጥ፣ በዝተውና መልተው ምድርን እንዲሞሏት የሚያደርግ ማኅበረሰብም፣ ተቋምም መንግሥትም አጥታለች፡፡
በታደሉት ሀገሮች የዓመቱ ምርጥ ደራሲ፣ የዓመቱ ምርጥ መጽሐፍ፣ በዓመቱ በብዙ ቅጅ የተሸጠ መጽሐፍ እየተባለ ደራስያንንና ድርሰትን የሚያበረታታ፣ እንደ ጻፉበት ጉዳይም በየዘርፋቸው የሚሸልም ተቋምና መንግሥት አለ፡፡ በስማቸው መንገዶችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ አደባባዮችን፣ ፓርኮችን፣ ሙዝየሞችን የሚሰይም መንግሥትና ሕዝብ አላቸው፡፡ ሥራዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የሠሩባቸው ቤቶችና የተጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች ሳይቀር የሀገሪቱ ታሪክና ቅርስ ሆነው ይጎበኛሉ፡፡
ለመሆኑ የገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ የብላታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፣ የአለቃ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ የአቤ ጉበኛ፣ የበዓሉ ግርማ፣ ቤታቸው የት ነው? የት ነበር የጻፉት? ረቂቃቸው አለን? የጻፉበት ብዕር አለን? ምን ሰየምንላቸው? በምን እናስታውሳቸዋለን? ለመሆኑ የኢትዮጵያን የድርሰት ጉዞ የሚያሳይ አንድ ሙዝየም እንኳን አለን? የሺ ዓመታት የሥነ ጽሑፍ ታሪክ የምንደሰኩር ጀግኖች ሥነ ጽሑፋችን ከየት ተነሥቶ የት ደረሰ? የድርሰት ጉዟችን ከየት መጥቶ የት ጋ ደረሰ? የዕውቀት አባቶቻችንና እናቶቻችን እነማን ነበሩ? እስካሁን ምን ያህል ደራስያንን አፍርተናል? እነማን መቼ ተነሡ? እነማንስ ምን ሠሩ? የመጀመሪያው ገጣሚ፣ የመጀመሪያው የልቦለድ ደራሲ፣ የመጀመሪያው የወግ ጸሐፊ፣ የመጀመሪያው የቴአትር ደራሲ፣ የመጀመሪያው ሃይማኖታዊ መጽሐፍ ደራሲ፣ የመጀመሪያው የጋዜጣ ጽሑፍ ጸሐፊ፣ የመጀመሪያው የፊልም ጽሑፍ ጸሐፊ፣ የመጀመሪያው የጉዞ ማስተዋሻ ጸሐፊ ማነው? ብንባል አንዳች ስምምነት አለን? የምናሳየውስ ነገር አለን? የትስ ነው መረጃው ያለው? ለተተኪው ትውልድስ የት ወስደን ነው የምናሳየው?
የሀገር የሥልጣኔ ሕዳሴ የሚጀምረው ከዕውቀትና ከኪነ ጥበብ ሕዳሴ ነው፡፡ የአውሮፓንም ሆነ የእስያን የሕዳሴ ታሪክ ብንመለከት ዕውቀት ያልመራው ኪነጥበብ ያላቀጣጠለው ሕዳሴ አናገኝም፡፡ የኢኮኖሚውንም፣ የባሕሉንም፣ የፖለቲካውንም ሕዳሴ ዕውቀት ሊመራ ኪነ ጥበብም ሊያቀጣጥለው ይገባዋል፡፡ ኪነ ጥበቡ ደግሞ ፖለቲካ መር፣ ብሔር መር፣ ገንዘብ መር ሳይሆነ ዕውቀት መር መሆን አለበት፡፡ ሕዳሴ የተሳካና የጸና እንዲሆን የዕውቀት አባቶችና እናቶች ያስፈልጉታል፡፡ የሚታወቁ ሳይሆን የሚያውቁ፣ የሚናገሩ ሳይሆን የሚነገርላቸው፣ ‹አለን አለን› የሚሉ ሳይሆን ‹አሉ አሉ› የሚባልላቸው የዕውቀት ምንጮች ያስፈልጋሉ፡፡
እነዚህ የዕውቀት ምንጮች ዕውቀታቸውን እንደ ጉንፋን ማጋባት እንዲችሉ መጻፍ አለባቸው፡፡ ጊዜ ወስደው፣ ዐቅም ሰብስበው፣ መረጃ አስሰው፣ ሰርዘው ደልዘው፣ ቀምረው ሰድረው መጻፍ አለባቸው፡፡ የምንጠቅሰው፣ የምንመራበት፣ ብርሃን የምናይበት፣ ዓይነ ልቡናችንን የምናበራበት የዕውቀት ማዕድ ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ ይኼ ደግሞ የደራሲው የጸሐፊው ድርሻ ብቻ አይደለም፡፡ የጥንት እናቶቻችንና አባቶቻችን ቀለም ገዝተው፣ ብራና አስፍቀው፣ ለጸሐፊው ድርጎ ሰጥተው፣ ርስት ከፍለው፣ ዋጋ ቆርጠው፣ ሲጨርስም ሸልመው ያስጽፉ እንደነበረው ሁሉ ደራስያኑን የሚያበረታታ፣ የድካማቸውን ዋጋ እንዲያገኙ የሚያደርግ፣ ለውጥ የሚያመጣ ዓይነተኛ ሥራ ሠርተው ሲገኙም የሚሸልም መንግሥትና ሕዝብ ያስፈልጋል፡፡ ከወረቀትና ከማተሚያ ዋጋ እስከ ሥራ ግብር፣ ከማከፋፈያ ችግር እስከ መብት ማስከበር፤ ከትምህርት ቤት የንባብ ባህል እስከ ሀገራዊ የጽሕፈትና የንባብ አብዮት፣ ከዓመታዊ ሽልማት እስከ የማዕረግ ስሞች፣ የሚሰጥ ተቋማዊ አሠራርና ባህል ያስፈልገናል፡፡ የሀገር ሥልጣኔ ከድርሰት ሥልጣኔ እንደሚጀምረው ሁሉ የሀገር ሞትም ከድርሰት ሞት ይጀምራልና፡፡ 
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

63 comments:

 1. nice article dani i strongly aree!

  ReplyDelete
 2. ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር ሆናለች፡፡ ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር ሆናች፡፡

  ReplyDelete
 3. እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ዳንኤል ክበረት

  ReplyDelete
  Replies
  1. እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ዳንኤል ክበረት

   Delete
 4. Well said Daniel! We have reached in a period where a vocalist becomes a historian, politician and a hero!!! What a shame!!!!!!!!! let me put what George Orwell said 'War is peace. Freedom is slavery. Ignorance is strength' Keep it up!

  ReplyDelete
 5. Ewunet blehal diakon, gin min waga alew? yemanireba sewoch hunen keren endet endeminanserara erasu alawukim.

  ReplyDelete
 6. ዳኒ ፀጋው ጌታ ያብዛልህ:: ፍትፍት ተደረጎ የሚነበብ ፅሁፍ ርቦናል፡፡ ሰው እርቦት በልቶ እንደሚጠግበው ያለ እርካታ አንብበን የምንረካበት ፅሁፍ አጥተናል፡፡

  ReplyDelete
 7. ዳኔየ እኔም ምረቃየ እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥሕ ነው። ዳኔ፣ አባ ሰላማ ክተባለው ድሕረ ገጽ ያንተን ብሎግ ያሳያል፤አስተውለኸው ይሆን ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰዎቹ ይሄ መለያቸው ነው፡፡ የዳኒን ብሎግ በመጠቆማቸው ለየዋሀን እውነተኞች መስሎ መታየት ፡፡ እውነታው ግን ምንም እንከዋን አልፎ አልፎ አንጀት የሚያርሱ ጦማሮችን ቢለጥፍም እንደ አራቱ ኃያላን በመጽሐፍ ካልሆነ በብሎጉ ላይ ብዙም ሃይማኖታዊ ጽሑፍ ስለማይጽፍ ለነሱ አላሳሰባቸውም፡፡ አይመስልሽም ውድ እህቴ፡፡

   Delete
  2. አባ ሰላማዎች ለዳንኤል ጠላት ናቸዉን ሲሳሳት ማረም ያለ ነዉ ግን ደግሞ ዳንኤል የሚጽፈዉን አንብቡለት ማለታቸዉ የትልቅነት ምልክት ነዉና በየምክንያቱ አዋራ ማንሳታችሁን አቁሙ

   Delete
 8. የሀገር ሥልጣኔ ከድርሰት ሥልጣኔ እንደሚጀምረው ሁሉ የሀገር ሞትም ከድርሰት ሞት ይጀምራልና፡፡

  ReplyDelete
 9. እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ወንድሜ ዳንኤል ክበረት

  ReplyDelete
 10. Thanks Dn Daniel. You always raise very good points. Your articles are an eye opener, a reminder to our history. I know you are doing your best. You have published many books and articles over the last decade or so. Your blog is one of the most read, (I believe so). But I think you need people to work with you for some of the issues which you have been raising so far. Otherwise, your efforts and probably other's wish will vanish. I will share my ideas here, I know people have probably suggested something before, if not for this for other kind of projects.

  Dn Daniel, we need to start acting immediately. Probably we need to create say "Ye Hadis Alemayehu YeKinetibeb Maekel". "Ye Hadis Alemayehu Library", if we don't have yet or something of that sort.

  We have "Ye Deresayinan mahibere" and other additional organizations who can collaborate.

  Financial and logistical issues are usually a challenge. However we can start simple where volunteers and investors could help. Let us have some sort of big plan for “Ye Kinetibeb Maekel” or Libray. It may include, library, meeting halls, class rooms, research centre, playing ground, guest houses, student accommodation. We put a clear master plan for that and advertise to the Ethiopian with in Ethiopia and all over the world. After putting this we can work things by phase.

  phase 1 - organizing technical team and administrative team. Those teams could work on looking for volunteers, like architects to design the whole premises for free. Those who are looking for financial support.

  phase 2 - getting accredited from the govt and municipalities to give us a plot of land for such projects.

  phase 3 - to start simple and probably build the library, or hall in the name of one of our icon as the first project.

  phase 4 - we could finalize other projects at later stages, not necessarily in one or two years. We could have 10 or 15 years of plan for establishing "YeKinetibeb Maekel"

  Let us start now, and I know we will be somewhere in 10 years from now. I can volunteer myself for this, we can start contributing monthly. We can follow work of Dr Belay Abegaz's, "Anid birr l'and lib" principle. We could start by saying "anid birr l'and Kinetibeb"

  Dani, I look forward to hear from you on your blog sometime soon so that we all could contribute something. Since it might be a burden for one person, please be as a team and come up with some start up project.

  Thanks Daniel, I love you and I am your admirer. You are a true Ethiopian. Berta, may God be with you as always.

  Bewketu

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you Dani for your awaking article. I strongly agree with the above comment by Bewketu. I (and many others) always inspired by your articles. But since most of us, I think, are occupied by our own life, we don't usually act. So, I am sorry to say this, but you have to take the initiative to work on some of the issues you are discussing. In particular, you are the most appropriate person to tackle the issue you raised in this article. So, try to start some initiative and l hope a lot of people will be part of the effort. I am sorry for pushing the responsibility back to you. Berta!
   Zelias

   Delete
  2. Dear Bewket what an initiative! As they say its better to be late than never. we can rant and rave about the current situation yet after ten yrs we will still find ourselves doing the same unless we act on it immediately. We know that you, Dn Daniel are inundated with so much work, so many tasks on your plate but if you could donate some of your time for such an important issue and came up with starting action plan there are people who are in the position to help and who feel the irony of all the accolades given to all the foreigners while ignoring our own (its like punching ourselves in the face "balebetu yalakeberewun..." yibalal). Anyways "hamsa lomi endemibalew" obviously you cant do this by yourself but I am sure people will take the responsibility once you start the project idea. Its easier said than done but if we are not going to take action it will be pointless and lame to just talk about it "yechat bet wore endayhon".

   Respect
   Sam

   Delete
  3. I don't need to take time to realize this kind wonderful idea, I just accepted it. I'm a student but I believe I can contribute something for the project. please, let's put ourselves into action, soon, now!
   Dn. Daniel Egziabher rejim edme yistih; amen.
   Dear Bewketu, please keep on inventing such kind of initiative Ideas.

   Delete
 11. ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር.... ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር .... ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር .....

  ReplyDelete
 12. ዲ/ዳንኤል እግዚያብሔርን የኔን እድሜ ጨምሮ ይስጥህ ብየ እለምናለሁ ተባረክ ብሩክ ሁን የተባረኩ ልጆችን ይስጥህ ብሩክ ነህና ካንተ የሚመጣው ሁሉ መልካም ነው ይታደሉታል እጆ አይታገሉትም ይባል የለ ሰው መልካም ከሆነ ሁልጊዜ መልካምን ፍሬ ያፈራል።አወ ሌሎች በግድ ማንነትዋን አፈር ሊያስግጡት ታሪኮን ሊሽሩት አሸራዋን ሊደመስሱት ይወድቃሉ ይነሳሉ ።አንተ ግን የናትህን የማማን እውነቱ ታሪኮን ይዘህ ለሚያውቀው እውቀቱን እንዲመሰክር ለማያውቀው ለንደኔ አይነቱ አዲሱ ትውልድ በሚገባው መልኩ ትመግበዋለህ ።ቆዳ ለጫማ ሳይውል ለመጸሐፍ ነው የዋለው ብእር ፣ለማገዶ ሳይውል ለፊደል ነበር የዋለው ፣ንግሥተ ሳባም ጥበብን ናፍቃ ነበር ወደሰሎሞን የሄደችው እነዚያ ኢተዩጵያዊ ናቸው አሀን ያሉት በመጀመሪያ እነማን ናቸው??????በሌላ መልኩ ማህይም ናቸው ለደዚህ አይነቱ የሀገር ዋልታ ቦታ የላቸውም የነሱ ኑሮ ያገኙትን እስካሉ ዘርፈው አወናብደው ፣ሽጠው ጥሪት አራግፈው ይኑሩ እጂ ለማን ይጨነቃሉ፣ለትውልድ ለሀገር እኮ ለማን!አባቶቻችን ያፈሩትን ቅርስ ሀገር ማውደም ነው ስራቸው እንኮን የሀገር ተስፋ የሆነውን ደራሲ ሊያደራጁ ይቅርና እሱማ ነገ ምን እደሚሆን ያውቁታል እረባክህ ወንድሜ ስንቱ ይነሳል ሰለነሱ አንተ የድርሻህን በርታ ።ለዚህ ነው አንተን አባ በላይ ኮስትር ያልሁህ ሞት አይፈሬ ጀግና በሀገሩ በታሪኩ ጉዳይ የማይደራደረው ጀግና ።ቸር ወሬ ያሰማን ።ኢትዮጵያ ተከብራ ለዘለአለም ትኑር።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

  ReplyDelete
 13. We corrupt society in order to conquer and rule. “Gussepe Mazzini”

  The very deepest sense of corruption is not as such that of material corruption that is hyped nowadays in our media. The very deepest sense of corruption is rather moral and spiritual corruption. And one of the insidious schemes to make a society doomed to such moral and spiritual corruption is by making it devoid of critical thinking, critical knowledge and wisdom.የኢህአዲግን አላማ በታማኝነት እስካስፈፀመ ድረስ መሃይምም ቢሆን ስልጣን እንሰጣለን የሚለው ቅኔው ይህ ነው፡፡ወርቅ ይረክሳል መዳብ ይወደደዳል የተባለበት ቅኔውም ጠቢባን ይዋረዳሉ ይገፋሉ በተቃራኒው ደግሞ አድርባይ ደንቆሮዎችና አረመኔዎች ከፍ-ከፍ ይላሉ ነው፡፡በቁሙ ሙታን እንዲሆን በተፈረደበት ማህበረሰብ ውስጥ የተሻለ አንፃራዊ ገድልና ዘላለማዊ ክብር ማግኘት ማለት እንግዲህ ይህ ነው፡፡
  ህዝቤ እውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፋ የተባለውም ለዚህ ነው፡፡ኢትዮጵያዊቷ ንግሥተ ሳባ እንኳን ወደ ሰሎሞን የሄደችው ‹ጥበብን ፍለጋ› መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ብለሃል፡፡አዎ ትክክል ነው ፡፡ነገር ግን ዛሬ ሴቶቻችን አውሮፓና አሜሪካ የሚሄዱት ምን ፍለጋ ነው?የመንፈስ ልእልናን ንቆ በምትኩ ቁሳቁስ አምላኪ የሆነ ማህበረሰብ መጨረሻው ውርደትና ጥፋት ነው፡፡We corrupt society in order to conquer and rule. “Gussepe Mazzini”አዎ ጥቂት እኩያን ልሂቃን ህዝብን እንደፈለጋቸው እየረገጡ እየዘረፉ እያምታቱ ግራ እያጋቡ እራሳቸው እንደ ጣኦት እየተመለኩ ለመግዛት የግድ ህዝቡን እውቀት የተጠማ ደንቆሮና የመንፈስ ልእልናና እሴትና ሞራል የጎደለው የተኮላሸ የተቅበዘበዘና የቁም ሞት የሞተ መካኒካል Zombie ማድረግ መቻል አለባቸው፡፡አዎ የጥቂቶች የበላይነትና ልማት በብዙሃኑ ውርደትና ጥፋት የሚገኝ እየሆነ ነው የመጣው፡፡ለአንድ ማህበረሰብ እንደ ፋና ወጊ አገልጋይ የሆነው ድርሰት እንዲሞት እየተደረገ ያለውም ለዚህ ነው፡፡


  ReplyDelete
  Replies
  1. አየህ አላማ ካስፈፀመ መሀይምም ቢሆን ስልጣን እንሰጠዋለን አልህ?ግን እውነት የሌለበት ለህዝብ ያልሆነ ስልጣን እንደሰው በአምሮው የማይታዘዝ ሁልጊዜ እንደ እንስሳ ለሆድ የሚያድር እሄ ለኔ ሰው አልለውም ።ብስናታም ፣የሞተ ነው!!!!!!!!!""""""አንተም እነዚህ አይመት ጠባይ ያላቸውን መደገፍህ ምን ስሜት እንደሚፈጥርብህ መልሱን ላንተ ትቻለሁ።

   Delete
 14. ዲ/ዳንኤል አንተእኮ ለኛ የዘመናችን ቄርሎስና ዩሐንስ አፈወርቅ ነህ ።ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጆ ጋር አትለይህ በረከቷን ታብዛልህ ።እንግዲህ ምን እንላለን ብሏል ታላቁ ሐዋርያ ።በርታ ይህ ጨለማ ተገፎ በስራችሁ የምትሽለሙበት የምትሾሙበት ጊዜ ይመጣል በሰው ሰወኛው ለሞራል ያህል እንጀ ከሰው ስጦታ በላይ የሆነው አምላክ ሽሞሀል ሽልሞሀል ከእርሱ ባይሆንማ መቼ እንዲህ የሚጣፍጥ የማይጠገብ ሁሌተናፋቂ መካሪ አስተማሪ ተስፋ ሰጭ ይሆን ነበር ።ይሄ የአምላክ በረከት ነው በርታ የሰው ስጦታ ታይቶ እንደሚጠፋ ነው አሁንም መድሐኒያለም ለዘላለም ቤተሰብህን አንተን ስራህንም የባርክ።

  ReplyDelete
 15. I hate people's who repeat the words of z main script, here on the comment box!...parots plse don't do this.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why you hate the Anonymous person. They read the all sentence and they picked what they like and they posted. That is the way their expression. don't expect everybody think you way. You mean If we don't think you way, we have to go in high way. That is the dectator leader. Daniel has been fighting this kind of dectator leader but you didn't learn anything from him, shame on you. shame, shame, shame. Respect other people idea, don't give us hard time. I don't blame you because you didn't grow up with the freedon world. You grow up with ordering other and if someone different from you that person is your enemy. If you read all Daniel comment some people didn't support him but he posted their idea as well. We need someone acept us what we are not what he/she want. I know you are part of Weyana but you have to change your veiw. Bye for now.

   Delete
  2. አይ እኔም በመድገም አልስማማም፡፡ ሌላ ቦታ ላይ ግን ዳንኤል እነዳለው እየተባለ ቢደገም እስማማለሁ፡፡ እዚህ ጋ ግን ቢያንስ ቢያንስ ትንሽ የግልን አስተያየት መናገር ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ወይም በተጠቀሰው አረፍተ ነገር ላይ የደገመውን አባል ከግል አስተያየት ወይም እንዴት እንደተገነዘበው ቢያክልበት ወዝ ይኖረዋል፡፡ አለበለዚያ ሁሉንም መልዕክት ሙልጭ አድረጎ ላነበበው ተደራሲ ዲቃላውነ ማቅረብ ቋቅ ሊል ይችላል፡፡
   ከታላቅ ይቅርታ ጋር፡፡
   ከጣና ዳር፡፡

   Delete
 16. ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር.... ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር .... ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር .....

  ReplyDelete
 17. ጀሮ ያለው ይስማ፡ ነገሩ ኢህአዴግ ምን ጀሮ አለውና:: ዲ/ን ዳንኤል አይዞህ በርታ እግዚአብሄር ለዘላለም ከአንተ ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 18. lekas sew alen!!! Anten yeseten geta yimesgen!!!!
  Amen !!!

  ReplyDelete
 19. ዲ_ዳንኤል፤- ብዙ :ሃሳቦችን አንስተሃል፡፡ ለንጽጽር የተጠቀምከውም የድሮውን መንፋሳዊ ድርሰቶችን(በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት የተጻፉትን) እና የዘመናችንን ነባራዊ ሁኔታ ነው፤፤ ይህ ደግሞ በመንፈሳዊ ዓይን ላየው ሰው ሁሉም ድርሰት ጥበብ ነው? የሚል ጥያቄ ያጭራል፤፤ ስለ ስጋዊ ፍቅር የተጸፈ ሁሉ (የሀዲስ አለማየሁን ጨምሮ) የፍቅር ድረሰት ነው? እኔ በበኩሌ የድሮውን ዕንቁ መንፈሳዊ ድርሰቶች ከአሁኑ ልቦለዶች (ለሥጋ ብቻ እንዲመቹ ተደርገው ከተጻፉት) ጋር ብዙም አላወዳድርም፤፤

  ReplyDelete
 20. 1. እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ወንድሜ ዳንኤል ክበረት .

  ReplyDelete
 21. i strongly believe in this article.i will try my best to improve my poor reading habit and i will decide to give priority for my country authors.

  ReplyDelete
 22. ታውቃለህ ለምንድር እንደሆን ከዚህ ቀደም “ነቢይ” ያልኩህ? ነቢይ የጎደለን ይሟላ፣ የተንሻፈፈን ይስተካከል፣ የተዛባን ሚዛኑ ይጠበቅ፣ የተረሳን ያስታውሳል፣ የተዳከመን እንዲያስንሰራራ ኡኡ ይላል፡፡ ሰሚ ሲያገኝ ነፍሱ ትለመልማለች፣ ድምጹ ይታደሳል፡፡ ሰሚ ሲያጣም መጮሁን ይቀጥላል፡፡ ይሰደባል፣ ይዋረዳል፣ ጎሽ ከሚለው ይልቅ ይደፋህ የሚለው የበዛል፡፡ ለእረሱ ግን ይህ ሁሉ ምኑም አይደለም፡፡ ይጮሀላ፡፡ ያሰማል፡፡ ይናገራል፡፡ አንተም ይህንኑ እያደረግህ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡
  ዳንኤል፡ የጻፍከውን እያነበብኩ አለቀሰኩ፡፡ ልቤ በብዙ ማዕበል ወዲያና ወዲህ ሲል ይሰማኝ ነበር፡፡ ታዲያ አሁን ምንድር እናድርግ የሚል ድምጽ በውስጤ ሰማሁ፡፡ ሃብት አለን፡፡ የሰው ሃብት፣ ሌላውም ሃብት፡፡ ምናልባት ይህንን ለማድረግም የሚከለክለን ይኖራል ማለት ነው? ምናልባት ጎኑ ይጠና የሚያስብል እንደሆነ ታስብ ይሆን? ለዚህም መጸለይ ያስፈልገን ይሆን? እንነሳና እናድርገው፡፡ አኔ ለዚህ ተግባር እጄን እሰጣለሁ፡፡ tanadar6@gmail.com.
  ከጣና ዳር

  ReplyDelete
 23. Brother Daniel,
  I am glad our poor country , Ethiopia, has great minds such as yours. Please keep writing such articles with intellectual depth which bring us back to Reason. you are full of not only Knowledge but Wisdom. May God bless you and may he make us good students.

  ReplyDelete
 24. yours articles are always spacial and i wish to see your works at international level.

  ReplyDelete
 25. ኢትዮጵያ ግን ለደራሲዎቿ ቦታ የሌላት፣ ማንበብና መጻፍም ብርቅ የሆነባት፣ ድራፍት ቤት እንጂ መጻሕፍት ቤት፣ ጫት ቤት እንጂ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ቤት የማይበረታታባት ሀገር ሆናለች፡፡ ክልል ያላት በክልል ደረጃ የሚጠቀስ ቤተ መጻሕፍት የሌላት፣ መንግሥት ያላት፣ ነገር ግን መንግሥት ዕውቅና የሚሰጠው ድርሰትና ደራሲ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለጀማሪ አቀንቃኞች የሰጠችውን አይዶል እንኳን ያህል ለበካር ደራስያን ለመስጠት ያልፈቀደች ሀገር ሆናለች፡፡ ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር ሆናለች፡፡ ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር ሆናች፡፡

  ReplyDelete
 26. ምን ታረገዋለህ ዳኒ! እንዳንተ አይነቱ ይብዛ እንጂ አውቀናል ያሉትማ ታሪክ እያዛቡ ና እያበላሹ እኮ አገር አስቸገሩ kb z Adigrat

  ReplyDelete
 27. Dani it is great article and looking! but we ordinary people what shall we do? and why not you try to organize something like that Organization? Namely you try and people will follow you! and each interested groups will contribute something, like finance and other! so try! try!
  Thanks

  ReplyDelete
 28. Dn Daniel
  God bless you.
  This is such a wonderful article as usual. I wish there is somebody who can immediately grab your ideas and put it to practice to change things. I believe you are blessed with special eyes who can see the societies problems.
  Dani you are a real Ethiopian. You a true son of the late Abune Gorgorios. May God give you move energy and strength to do more to your beloved country. Believe brother your ideas will inspire people to something to their country.
  Look Bewuketu has inspired by you and raised such a wonderful idea of putting your ideas in to the ground. This is what is needed. Change starts in one place by somebody. It comes in to a reality with a real participation of others.
  Lets have that gut and do something.
  God bless you and Ethiopia

  ReplyDelete
 29. I am just thinking of creating a kind of social network where people with reading interest become a member, individuals who read a book post a summary of their readings and those who excel by reading many books get a reward or recognition. And a site where authors become a special member and introduce their new book for free. What do u think guys?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks is great idea. Put it there and we will continue to endeavour it.

   Delete
  2. That's very great idea. I was also thinking a similar idea a month ago. Creating a kind of website where artists /getamian will present their poetry in the form of text, audio or video. And people will rank, comment, encourage.... Please go ahead!!!! Please!!!

   Delete
  3. Looks like we already have such an online resource. Maybe, we will build up on this --
   http://ethioreaders.com/

   Peace.

   Delete
 30. I agree strongly and we have to start now.

  ReplyDelete
 31. This is good idea! በነገራችን ላይ ለምን የዚህን አጋጣሚዎች ለለዉጥ አንጠቀምም ! ለምሳሌ : መጻሕፍትን ሰብስቦ ትንሽ ቤተ መጽሓፍ መክፍት...... ያለበለዚያ ማዉራት ብቻ እንዳይሆንብን::

  ReplyDelete
 32. ብዙ ግዜ አነብና ሁሌም ምን እንደምል ታውቃለህ አሁን ያልተባለ ነገር አለ እንዴ ምን ቀረ እላለው ግን አንተ አያልቅብህም አባ አያልቅበት ግን አሁን እንዳልከው ያለ ነገር ለምን አንተ የኢትዮጲያን ደራሲ እናስታውሳቸው ብለህ መርሃ ግብር ይዘጋጅ እና ከዛ ላይ ይጀመር በዛ ላይ ሚዲያ ሲጨመርበት የኔ ባይ ይኖረዋል ደሞስ ሸገር ከአመቱ ነጠላ ዜማ ጎን ምን አለ የአመቱ ምርጥ መጥሃፍ ቢጨጨምሩ እኔ የምለው ከሆነ ቦታ ይጀመር ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ቀን እንደ ጳጉሜ የይቅርታ ወቅት ዳኒየየ ይጀመር።።

  ReplyDelete
 33. "የሚታወቁ ሳይሆን የሚያውቁ፣ የሚናገሩ ሳይሆን የሚነገርላቸው፣ ‹አለን አለን› የሚሉ ሳይሆን ‹አሉ አሉ› የሚባልላቸው የዕውቀት ምንጮች ያስፈልጋሉ"፡፡
  መኩሪያዉ ወንድሜ( D.Daniel) በእዉነት ታስፈልጉነናላችሁ፤፤

  ReplyDelete
 34. አሻራን የማጥፋት ስራ
  ይህው መንግሥታችን ተጨማሪ ትምህርት ቤት ከመስራት ይልቅ አዲስ አበባ መሀል መገናኛ ጋር ያለውን ከ60 ዓመት በላይ ያስቆጠረውን ትምህር ቤት በኢንቨስትመንት ስምና ለክፍለ ከተማ ቢሮዎች በማለት ሙሉ በሙሉ አፍርሶ ተለዋጭ ቦታ እያዘጋጀ እና ተማሪዎችን ወደ ተለያዩ ትምህር ቤቶች የመበተን ስራ ለመስራት በቅድመ ዝግጅት ላይ ይገኛል ፤ ቀድሞ ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ቤተመንግሥታቸውን ለወገን የዕውቀት መገብያ ለዩኒቨርሲቲነት አሳልፈው ሰጡ ፤ አሁን ያለው መንግሥት ደግሞ የተሰራውን እያፈረሰ አሻራን የማጥፋት ስራ እየሰራ ይገኛል ፤ እንዴት 60 ዓመት የቆየ ትምህርት ቤት ፤ ስንት ኢንጅነሮችን ስንት ዶክተሮችን ስንት ምሁራንን ያፈራ ትምህርት ቤት በመሀል አዲስ አበባ የማፍረስ ስራ ይከናወንበታል…? ያሳዝናል ፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚማሩት ተማሪዎች ወደ ተለያዩ ትምህር ቤቶች የመበተን ስራ በ2007 መስከረም ወር ላይ ይሰራል ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. wedaj yihin hasab yizeh new and adrgen emtilew, bayhon sew bemiyaweraw be ajendaw tiruna and liyaderg yemichil hasab kaleh amita

   Delete
 35. ዛሬ ትውልዱ እንዲሆን እየተጠፈጠፈ ያለው ሆዱን ብቻ እየሞላ በጫትና በድራፍት ቤት ተረት እየተረት እድሜውን እየገፋ በራሱ እየቀለደ እንዲኖር (ትቂቶች)፤ ብዙኀኑ ደግሞ ሹሮ ያረረበት አኗኗሪ እንዲሆን ነውና ምን ያህል መስዋዕትነት በነማን፥ ዘርፈ ብዙ ጥማታችንን የምናረካበት ዘማን መቼና እንዴት ይመጣ ይሆን። የግፉአን አምላክ ስለናቱ ብሎ እንዲታደገን ፆታና ዘር ሳንለይ እንደራሔል እንባችንን ወደ መንበረ ጸባዖት እንርጭ።
  ነገር ግን ትውልድንና ሃገርን ለማዳን የአቅማችንን ሳይሆን ከአቅማችን በላይ መስዋዕትነት ለመክፈል አሁኑኑ ካልወሰንና በተግባርም አንድ ላይ ሆነን ካልሠራን ለሆነው ሁሉ ቢያንስ ከዚች እለት ጀምሮ በታሪክም በእግዚአብሔርም ተወቃሾች ነን። ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር ብሎ መፈክር ከማሰማት አንድ ርምጃ ወደፊት እንራመድ።

  ReplyDelete
 36. Dear Dn Daniel
  As usual your point of view is superb. You know what I always think if you want to have a quite, entertaining reading place in Addis there is none. Is not it sad not to have any reading place and ironically we have so many Chat and shisha bets. I wish i could do the same as you do and carry responsibilities in my shoulder. Bless you.

  ReplyDelete
 37. We need Engineers and Technologists who try their best in solving our problems than writers and authors who should come following that. We don't need theoreticians who just reflect our problems.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't agree on your idea.the base for change is not only Engineering or ... but also art and other related areas.

   Delete
  2. Yaa as you said we need Enginners and technical persons more...but we have to give attention also for those idea creators and writers.In deed daniel mentiond most of the writers and art workers were belongs to amhara...my question is ...is there any writers from hadya,kembata,oromya?

   Delete
 38. YES IT IS TRUE,WE DIDNOT GIVE A RESPEST FOR OUR GREATEST WRITERS...NOW WE HAVE TO START SOMETHING TO ENHANCE AND PROMOTE THE NEW GENERATION. GOD BLESS YOU BROTHER DANI

  ReplyDelete
  Replies
  1. eytawech betam des ylala mengst yersawun endineka tadergewaleh neger gn yanten hasab mn yahl tekami endehone le poletikegnoch yemiyas yasfelgal. meknyatum yhn yemiyanebut tikitoch nachewuna. yanten blog bedeb biketatelut gez partiwoch betely lewut lemamtat ytataru yhona bye asbalehu. goood

   Delete
 39. good article.
  እብክህን ዳኒ ስለ ዘርዓያዕቆብ ፃፍ ፥ብዙ ሰዎች ስለሱ መጥፎ ያወራሉና

  ReplyDelete
 40. ebakhin dani sile zerayakob tsaff

  ReplyDelete