Tuesday, December 24, 2013

የተሸጡት አባት

በአውሮፓ ክርስቲያኖች ዘንድ የታወቀ አንድ የአራተኛው መክዘ ታሪክ አለ፡፡ ድኾችን እጅግ የሚወድ፣ የተቸገሩትን ለመርዳት ምንም ነገር የማያግደው፤ ከእራሱም አብልጦ ለሌሎችን የሚሞት አንድ ሰው ነበረ፡፡ ይህ ሰው በበጎ ምግባሩ የተነሣ ስሙ ተረስቶ ‹እኁ ቅዱስ- ቅዱሱ ወንድም› እየተባለ ነው የሚጠራው፡፡ በታሪክ ድርሳናትም የተመዘገበው በዚሁ ስም ነው፡፡ ሠርቶ የሚያገኘውን ምንም ለሌላቸውና ለምነው እንኳን ለማግኘት ዐቅም ላነሣቸው በመስጠት የታወቀ ነበር፡፡
አንድ ጊዜ የሚሰጠው ነገር አጣ፡፡ ብዙ ችግረኞች ደግሞ መልካም ዜናውን ሰምተው ጥቂት ነገር ለማግኘት ወደ እርሱ ዘንድ መጡ፡፡ ምን ይስጣቸው፡፡ የሚያያቸው አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ሌላ አማራጭ የላቸውም፡፡ ብዙዎቹ ገንዘቡን ከጨረሰ በኋላ ከሩቅ ሀገር ሳይቀር በመምጣታቸው አዘኑ፡፡ መመለሻ እንኳን የላቸውም ነበር፡፡ በመጨረሻ እኁ ቅዱስ አንድ ውሳኔ ላይ ደረሰ፡፡ ‹‹እኔን ሽጡኝና ተካፈሉ› አላቸው፡፡ እነዚያ ችግረኞችም ምን አማራጭ ስላልነበራቸው እርሱን በባርነት ሸጡትና ገንዘቡን ተካፈሉ፡፡

Monday, December 23, 2013

አምሳሉ፤ እንኳን ትሞት ትታመምም አይመስለኝ ነበር

 
ጌታቸው ኃይሌ
ኮሌጅቪል፤ ታኅሣሥ 12 ቀን፤ 2006 (12/21/2013)

ፕሮፌሰር አምሳሉ አክሊሉና እኔ አብሮ- አደግ አብሮ- ጎልመስ፥ አብሮ -አረግ ነን። 1947 . . የእንግሊዝ ፊደል አብረን ከቆጠርንበት ጊዜ አንሥቶ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ አንድ ዓይነት ትምህርት ለማስተማር እስከተቀጠርንበት ጊዜ ድረስ በቦታ እንኳን ሳንለያይ አብረን ነበርን። በዚህ አምላክ በመረቀልን ረጅም ጊዜ አንድ ቀንም አንዳችን ሌላውን ቅር የሚያሰኝ ቃል ከአፋችን መውጣቱ ትዝ አይለኝም። የተለያየ ጠባይ ያላቸው ሰዎች መፋቀር፥ መተሳሰብ፥ መረዳዳት፥ እንደሚችሉ የአምሳሉና የእኔ ወዳጅነት ምሳሌ ሊሆን ይችላል። ለጻፍኩት የሕይወት ታሪኬ ርእሱን የአምሳሉና የጌታቸው ታርክ ብለው የተገባ መሆኑን ያነበበው ሁሉ ሊገምት ይችላል። ረጅሙን በወንድማማችነት አብሮ የመኖር ሕይወታችንን ለማስቀረት ደርግና ሞት ሸመቁበት።

Friday, December 20, 2013

ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ ዐረፉ

አብዛኞቻችን የመዝገበ ቃላትን አጠቃቀም የተማርንበትንእንግሊዝኛ -አማርኛ መዝገበ ቃላት›› ያዘጋጁት ዶክተር አምሳሉ አክሊሉ 83 ዓመታቸው ታኅሣሥ 11 ቀን 2006 ዓም ዛሬ ዐረፉ፡፡ ዶክተር አምሳሉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ከሚባልበት ዘመን ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያስተማሩ መምህር ነበሩ፡፡ 

ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን፡፡

Wednesday, December 18, 2013

ምግብና ፖለቲካ

በየዓይነቱ የሚባል ምግብ መቼም ታውቃላችሁ፡፡ በጾም ጊዜ የሚዘወተር የሀገራችን ምግብ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ሦስት ዓይነት ሲኖረው አንዳንድ ቦታ ደግሞ ሠላሳ ዓይነት አለው፡፡ ‹በየዓይነቱ› የሚለውን የምግብ ቤቶች መዝገበ ቃላት ሲተረጉመው ‹‹አንድ ቀይ የምሥር ወይም የሽሮ ወጥ በእንጀራው መካከል ጎላ ብሎ ይቀመጥና እነ አልጫ ሽሮ፣ እነ አልጫ ምስር፣ እነ ምጣድ ሽሮ፣ እነ ቃሪያ፣ እነ ስልጆ፣ እነ ቲማቲም ፍትፍት፣ እነ አበሻ ጎመን፣ እነ የፈረንጅ ጎመን፣ እነ ሩዝ፣ እነ ሱፍ ፍትፍት፣ እነ ቀይ ሥር፣ እነ ድንች ወጥ፣ እነ ተልባ ፍትፍት በዙሪያው አጅበው ይሰለፋሉ›› ማለት ነው ይላል፡፡
በያይነቱ ሕግም አለው፡፡ ባይጻፍም እኛ ‹የበያይነቱ ሕግ› ብለነዋል፡፡ በበያይነቱ ሕግ መሠረት በመካከል የሚቀመጠው ዋናው ወጥ በቀላሉ የሚገኝና የሚሠራ መሆን አለበት፡፡ ለዚህም ነው ወይ ምስር ወይም ሽሮ የሚሆነው፡፡ ርካሽነቱ የጥሬ ዕቃው ብቻ ሳይሆን በአንድ ትልቅ ድስት ውስጥ በቀላሉ በብዛት ሊሠራ የሚችል ማለትም ነው፡፡ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ምሥርና ሽሮ ወጥ፣ በልቅሶ ቤትም ዕድሮች በብዛት ይዘዋቸው የሚመጡት፡፡  አንድ ድንኳን ሙሉ ለቀስተኛና ዕድርተኛ ለማብላት እንደ ቀይ ምስርና ሽሮ ወጥ የሚበቃ አይገኝም፡፡

Thursday, December 12, 2013

የሥልጣኔ ሞት- ከድርሰት ሞት

የዛሬ 600 ዓመት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተባለ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ‹አርጋኖን› የተሰኘ መጽሐፍ ይደርሳል፡፡ ይህንን መጽሐፍ የተመለከቱ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትም እጅግ ያደንቁና ለንጉሡ ለዐፄ ዳዊት ያቀርባሉ፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም መጽሐፉን ተመልክተው በማድነቅ በወርቅ ቀለም እንዲጻፍ አዘዙ፡፡ አባ ጊዮርጊስንም ሸለሙ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላም አባ ጊዮርጊስ ‹መጽሐፈ ምሥጢር› የተባለ መጽሐፍ ደረሰ፡፡ ይህንን የተመለከቱ ሊቃውንትም አድናቆታቸውን ‹‹ቄርሎስና ዮሐንስ አፈወርቅ በሀገራችን ተገኙ፤ ኢትዮጵያም እንደ ሮምና ቁስጥንጥንያ፣ እንደ እስክንድርያም ሆነች› ብለው በማሸብሸብ ነበር የገለጡት፡፡
ከስድስት መቶ ዓመታት በኋላ ያለችው ኢትዮጵያ ግን ለደራሲዎቿ ቦታ የሌላት፣ ማንበብና መጻፍም ብርቅ የሆነባት፣ ድራፍት ቤት እንጂ መጻሕፍት ቤት፣ ጫት ቤት እንጂ የመጻሕፍት ማከፋፈያ ቤት የማይበረታታባት ሀገር ሆናለች፡፡ ክልል ያላት በክልል ደረጃ የሚጠቀስ ቤተ መጻሕፍት የሌላት፣ መንግሥት ያላት፣ ነገር ግን መንግሥት ዕውቅና የሚሰጠው ድርሰትና ደራሲ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለጀማሪ አቀንቃኞች የሰጠችውን አይዶል እንኳን ያህል ለበካር ደራስያን ለመስጠት ያልፈቀደች ሀገር ሆናለች፡፡ ለአርተር ራምቦ እንጂ ለጸጋዬ ገብረ መድኅን ቦታ የሌላት ሀገር ሆናለች፡፡ ለፑሽኪን እንጂ ለሐዲስ ዓለማየሁ አደባባይ የሌላት ምድር ሆናለች፡፡ ደራሲዎቿ ሲኖሩ ሳይሆን ሲሞቱ ዜና የምትሠራ ሀገር ሆናች፡፡

Monday, December 9, 2013

ለጎንደር መርሐ ግብር ተሳታፊዎች


   ጎንደር ላይ በታኅሣሥ 20 ለሚኖረን የ‹‹አራቱ ኃያላን›› መጽሐፍ መርሐ ግብር የተመረጠው 
ታየ በላይ ሆቴል አዳራሽ ነበር፡፡ 
ነገር ግን ከጎንደር ከተማና አካባቢው (ከደብረ ማርቆስ፣ ባሕርዳር፣ ደብረ ታቦር፣ አዲስ ዘመን፣ እስቴና ሌሎችም) በመርሐ ግሩ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡት ታዳሚዎች ቁጥር ከአዳራሹ ዐቅም በላይ በመሆኑ አዳራሽ ለመቀየር ተገደናል፡፡
በዚህም መሠረት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ባደረገልን ድጋፍ መርሐ ግብሩ የሚካሄደው በጎንደር ከተማ ሲኒማ ቤት መሆኑን እንገልጣለን፡፡ በዚሁ አጋጣሚም አስቀድሞ ትብብሩን ላደረገልን ታየ በላይ ሆቴል ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ጎንደር ላይ እንገናኝ፡፡

ድንገቴ

መምህሩ ናቸው፤ የእነዚህን ባለሀብቶች የሕይወት ታሪክ ሥሩ ብለው የሰጡን፡፡ ስምንት ባለ ሀብቶች፡፡ እነዚህን ሰዎች የምናውቃቸው በቴሌቭዥን እየቀረቡ ስለ ልማት ሲናገሩ ነው፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ተሸልመዋል፡፡ እኛ መምህራችንን ጠየቅናቸው፡፡ እነዚህን ለምን መረጧቸው? ስንል፡፡ እርሳቸውም ‹‹እነዚህን በሦስት መመዘኛ መረጥኳቸው›› አሉ፡፡ ‹‹አንደኛ ልማታውያን ናቸው፣ ሁለተኛ ተሸላሚ ናቸው፣ ሦስተኛ ደግሞ ዛሬ ቢጠሯቸው የማይሰሙ የናጠጡ ባለጠጎች ናቸው፡፡›› አሉ መምህራችን፡፡ ‹‹ስለዚህም ወጣቱ ትውልድ ከእነርሱ ትምህርት መቅሰም አለበት፡፡ ሀብት እንዲሁ አይገኝም፡፡ ተለፍቶ ነው፤ ተደክሞ ነው፡፡ ደም ተተፍቶ ነው፡፡ ‹ፐ› ላይ ለመድረስ ከ‹ሀ› መጀመር ያስፈልጋል፡፡ ከዕንቁላል ንግድ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከሱቅ በደረቴ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከአንዲት ሱቅ ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ ከጉልት ተነሥተው ሚሊየነር የሆኑ አሉ፡፡ እነዚህ ለትውልዱ አርአያ ናቸው›› አሉን መምህሩ፡፡
ስምንት ቡድን ተቋቋመ፡፡ ስምንቱ ቡድኖች አንዳንድ ሚሊየነር ያዙ፡፡ ታሪካቸውን የምንሠራበት ቅጽ ተሰጠን፡፡ የመጀመሪያዋን ብር እንዴት አገኟት? ወደ ሚሊየነርነት በየት መንገድ ተጓዙ? ምን ዓይነት ውጣ ውረዶችን አለፉ? እያንዳንዷን ሀብት እንዴት አጠራቀሟት? የሚሉ ጥያቄዎች ተሰጡን፡፡ እኛም የደረሱንን ባለሀብቶች እያነሣን ‹የኛ ባለሀብት ምርጥ ታሪክ ሳይኖራቸው አይቀርም፡፡ እንዲህ እና እንዲያ ሰምተናል እያልን እንፎካከር ጀመር፡፡ በቡድን የተሰጠኑንን ባለሀብቶች ታሪክ ሠርተን ከሁለት ሳምንት በኋላ ለመገናኘትና የደረስንበትን ለመወያየት ተቀጣጥረን ተለያየን፡፡

Friday, December 6, 2013

ጎንደር ላይ እንገናኝ


 አራቱ ኃያላን መጽሐፍን በተመለከተ በኢትዮጵያ የመካከለኛው ዘመን ታሪክና በጽንዐት በሚታወቁት አባቶች ታሪክና አስተዋጽዖ ዙሪያ ጎንደር ከተማ ላይ ልዩ መርሐ ግብር ይኖረናል፡፡ በጎንደር ዙሪያ፣ በባሕርዳር፣ በደብረ ታቦርና አካባቢው ያላችሁ ሁሉ ተጋብዛችኋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ
·   ዶክተር ውዱ ጣፈጠ
·   ዶክተር አምሳሉ ተፈራ
·   ረዳት ፕሮፌሰር ባንተ ዓለም ታደሰ
- ጥናት ያቀርባሉ

ቀን ፡- ታኅሣሥ 20 ቀን 2006 ዓም
ሰዓት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ ፡- ጎንደር ታየ በላይ ሆቴል
የመግቢያውን ካርድ ለማግኘት የሚከተሉትን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ
0918190868 / 0913788769

Wednesday, December 4, 2013

የት ነው ያለነው?


ይህ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የሰባተኛ/ስምንተኛ ክፍል መማሪያ ውስጥ የተገኘ 
የባዮሎጂ ትምህርት ማስተዋሻ (ኖት) ነው፡፡
ወይ ባል አላገባሽ ወይ አልመኮስሽ
እንዴው ልጅ አገረድ ይባላል ስምሽ
እንደሚባለው ወይ በአማርኛ(በራሳችን ቋንቋ) በሚገባ ተምረን አልተግባባን፤ ወይ በፈረንጅ ቋንቋ በሚገባ ተምረን አልተግባባን፡፡ እንዴው ምን ይሻላል?
ድሮ ድጎማ የሚባል መምህር ነበር አሉ፡፡ መቶ ብር በማይሞላ ደሞዝ ነበር አሉ የሚቀጠሩት፡፡ ክፍል ውስጥ ክኖው፣ ዲጂቡቲ፣ ክናይፍ know, Djibouti, knife, እያለ ያስተምራል፡፡ ተቆጣጣሪው (ሱፐርቫይዘሩ) እንዴት እንዲህ ታስተምራለህ? ኖው፣ ጂቡቲ፣ ናይፍ በል ይለዋል፡፡ መምህሩም ‹‹በድጎማ ደሞዝማ እንዲያ ብዬ አላስተምርም›› አለ ይባላል፡፡
በባሕላዊው የጥንት ትምህርታችን ንባብ ወሳኙና የመጀመሪያው ትምህት ነበር፡፡ የፊደል ዘር መለየት ብቻ ሳይሆን አነባበብም ጭምር፤ በየሠፈራችን የነበሩትን የቄስ ትምህርት ቤቶች እናስታውሳቸው፡፡ ፊደሎቹን ከነዜማቸው እስክንሸመድድ ድረስ አንገት ላንገት ተቃቅፈን የምንናጥባቸውን ትምህርት ቤቶች አስታውሱ፡፡
ማንበብ የዕድገት ቁልፍ ነው፡፡ ለዚህም ነው በጥንት ሥልጣኔ የምናውቃቸው ሀገሮች ሁሉ የራሳቸውን ፊደል ለመፍጠር የተሳካላቸው ሀገሮች የነበሩት፡፡ በሥልጣኔ መጥቆ ፊደልና ጽሕፈት የሌለው ሀገር አናገኝም፡፡ የማያነብብና የማይጽፍ ትውልድ መፍጠር ከዕውቀት የተቆራረጠ ትውልድ መፍጠር ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በዐረብ ሀገሮች በሚገኙ ዜጎቻችን ዘንድ አንዱ ፈተና ‹ማኑዋል አንብቦ› መሣሪያዎችን ለመጠቀም አለመቻል ነው፡፡
ወላጆች፣ የእምነት ተቋማት፣ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ሚዲያዎችና የሚመለከተን ሁሉ ልናስብበት የሚገባ ቁልፍ ችግር - ማንበብ የማይወድ ሳይሆን ማንበብ የማይችል ትውልድ በየክልሉ እየተፈጠረ ነው፡፡ ፊደልና አጻጻፍ መለየት የእንግሊዝኛም የሀገራዊ ቋንቋዎችም ችግር እየሆነ ነው፡፡
እናም፣ የፊደልን ዘር መለየት፣ አጻጻፍን ማወቅና አነባበብን ማርታትን ከነባሩ የትምህርት ሥርዓታችን በሚገባ ቀስመን ወደ ዘመናዊ ትምህርት በጊዜ ካላስገባነው - ትውልድ አደጋ ላይ ነው፡፡

የአራቱ ኃያላን ቅኝት

   ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ 
(አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል)
ርእስ - አራቱ ኃያላን፦ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል፣ አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ አኖሬዎስ፣ አቡነ አሮን
አዘጋጅ - /ዳንኤል ክብረት
የገጽ ብዛት - 460 (መግቢያውን፣ ዋቤ መጻሕፍትን እና መዘርዝሩን ጨምሮ)
አሳታሚ - አግዮስ ኅትመትና ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ. የተ. የግል ማኅበር
ማተሚያ ቤት - አማኑኤል /ቤት
• ምረቃው የተካሄደበት ቦታ - መንበረ ፀባዖት /ሥላሴ ካቴድራል ሁለገብ አዳራሽ
ቀን - ኅዳር 15/2006 ..
አስተያየት ሰጪ - አምሳሉ ተፈራ

የመጽሐፉ ሥነ ድርሳናዊ (ፊሎሎጂካል(1)ጠቀሜታ
. መግቢያ
መጽሐፉ በጣም ብዙ እና አዳዲስ ነገሮችን ይዟል። ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ባህል፣ የዓላማ ጽናት፣ በዘመኑ የነበረው ቅጣትና ፍርድ አሰጣጥ ወዘተ2 ... ከያዛቸው ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የታሪክ አሰናሰሉ፣ የቋንቋ አጠቃቀሙ፣ የማስረጃዎቹ ተአማኒነት (ባብዛኛው ጥሬ መረጃዎችንና የመጀመሪያ ምንጮችን ማቅረቡ) ወዘተ... ለየት ያደርገዋል።

ይህ ደግሞ እስካሁን ድረስ ያልተሟላውን የሀገራችንን መካከለኛ ዘመን ታሪክ እንዲሟላ ብዙ ድርሻን ይወስዳል። በዋናነት ደግሞ የቤክርስቲያን ታሪካችንን የዚያን ዘመን ገጽታና የአበው ቅዱሳንን ታሪክ በስፋት ስለሚያሳይ ፋይዳው የጎላ ነው(2)

Tuesday, December 3, 2013

የዳንኤል ክብረት አራቱ ኃያላን መጽሐፍ ምረቃ


ውዱ ጣፈጠ (ዶ/ር)
ታሪክ ትም/ ክፍል
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
በሀገራችን ውስጥ ለኦርቶዶክስ ክርስትና መስፋፋትና መደርጀት ትልቁን ሚና የተጫወቱት ሀገራዊ ቅዱሳን ካህናትና የሃይማኖት መሪዎች ናቸው፡፡ በተለይም በመካከለኛው ዘመን መንግሥትና ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሁነው አብረው ሰርተዋል፡፡ ነገሥታቱና ካህናቱ አብረው የሰሩትን ያህል በመካከላቸውም አንዳንድ ከሃይማኖት ጋር የሚጋጩ ነገሮች እየተከሰቱ ሲያጋጩዋቸውና ሲያጣሉዋቸው ኑረዋል፡፡ በመካከሉም እርቅ እተፈጠረ የተለመደ ስራቸውን ሰርተዋል፡፡ ያለ ውህደታቸውም የመንግሥትና የቤተ-ክርስቲያኗ  መስፋፋት በጥንካሬ ሊቀጥል አይችልም ነበር፡፡
ኢትዮጵያውያን ካህናት ከዛጉዌ ስርወ-መንግሥት ጀምሮ የሃይማኖት መÍህፍትን ከቅብጥ፤ ከአረብኛ፤ ከጽርእ በመተርጎም ለሃይማኖት ስራ እንዲዉሉ አድርገዋል፡፡ በጊዜውም የግእዝ kk ትልቅ የሥነ ጽሑፍ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ጥረዋል፡፡ የገድል መÍሕፍት በብዛት ተጽፈዋል፡፡ የሀገራቸውን ቤተ ክርስቲያን አሰራር የተመቸ ለማድረግ አዳዲስ ነገሮች እንዲለመዱና እንዲaaሉ ለውጥም እንዲመጣ ጥረዋል፡፡ በጣት ከሚቆጠሩ አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያኗ የቅብጥ (ግብፅ) ጳጳሳት በስተቀር ለቤተ-ክርስቲያኗ ለውጥ እዲጀመር ጥረት ያደረጉ የቅብጥ ጳጳሳት የሉም፡፡