በኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ታላቅ ቦታ ያላቸውን ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትንና ፕሮፌሰር ዶናልድ
ክራሚን ለማሰብ ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በወቅቱ የሁለቱም
ደቀ መዝሙር የነበረው ዶ/ር ውዱ ጣፈጠ ያቀረበውን ማስታወሻ እንብቡት፡፡
ዝክረ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራትና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚ
ዉዱ
ጣፈጠ( ዶ/ር)
ከተማሪዎቻቸው
አንዱ
ፕሮፌሰር
ታደሰ ታምራትና ፕሮፌሰር ዶናልድ ክራሚ ሁለቱ በዩነቨርስቲ የትምህርት ቆይታዬና ብሎም በህይወቴ ላይ ቀና ተፅእኖ ያሳደሩ ታላቅ
መምህሮቼ ነበሩ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የቅድመ-ምረቃ የታሪክ የአራተኛ ዓመት ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ ከፕሮፌሰር
ታደሰ ጋር የመጀመሪያን ትውውቅ አደረግን፡፡ ለቅድመ
ምረቃ (ለቢ.ኤ.) ዲግሪ ማóማóያ
የምረቃ Òሁፍ
ምርምር ለማድረግና ውጤቱንም ለመፃፍ እንድችል
እርሳቸው አማካሪዬ ሁነው ተመድበው ነበር፡፡ በወቅቱ እርሳቸው የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ስለነበሩ እርሳቸውን አግኝቶ ለማነጋገር
ትንሸ ችግር ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ከትንሸ መመላለስ በኋላ አግኝቸ ራሴን ሳስተዋውቅ ትኩር ብለው እየተመለከቱ በርጋታ አዳመጡኝ፡፡
ከዚያም እስኪ ወደ ሌላ ነገር ከመግባታችን በፊት የራስህን ታሪክ፤ የቤተሰብህን፤የአስተዳደግህንና የትምህርትህን ነገር ግለፅኝ ብለው
ጠየቁኝ፡፡ በጊዜው ይህ ሁሉ ምን ያደርጋል ብየ በየዋህነት ራሴን ጠይቄ ነበር፡፡ የርሳቸው አካሄድ የገባኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር፡፡
ለቅድመ ምረቃ የምርምር ስራ የሰራሁበት ርእስ ስለ ራጉኤል አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ነበር - እንጦጦና አዲስ አበባ
መርካቶ ስለሚገኙት መንትያ አብያተ ክርስቲያናት፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ በጣም ረጋ ያሉ፤ በተመስጦ የሚያዳምጡ፤ ቀስ ብለው የሚናገሩና እንዲህ
አይነቶቹን ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች አስተውለሀዋል ብለው በማስታወሰ መንገድ የሚያሳዩ ነበሩ፡፡ በዜያ ጊዜ እኔን ለመሰለው ገና
ጀማሪ በማበረታታትና በሚቀጥለው ጊዜ ስንገናኝ
አዲስ መረጃ እንደምታመጣ ተስፋ አለኝ ብለው የሚሸኙ ነበሩ፡፡ የሚያውቁትን መረጃ ጠቅሰው ፈልግ የሚሉ፤
መረጃ ሊሰጡ የሚችሉና ያውቃሉ ብለው የሚገምቷቸውን ሰዎችን ስም የሚነግሩና ሲቻልም የሚያስተዋውቁ ነበሩ፡፡
በዚያ ጊዜ እጅግ ያስቸገረኝ ነገር ቢኖር ጽሕፈታቸውን ማንበቡ
ነበር፡፡ ይህም ቢሆን ዲኑ ቢሮ ትሰራ የነበረች ወ/ሮ እልፍነሽ እንዳለ ተረር አድርጋ እያነበበች ችግሬን ታቃልልኝ ነበር፡፡
ብዙ ጊዜ አብራቸው ስለሰራች ጽህፈታቸውን ያለችግር ማንበብ ችላ ነበርና፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመቀጠር እድል ባጋጠመኝ ወቅት ሁል ጊዜ
ያለማቋረጥ ድጋፋቸውንና አበረታች ቃላቸውን ያለ ምንም ስስት ይነግሩኝ ነበር፡፡ ይህም የታሪክ ትምህርት ክፍል በርሳቸው ስር
ሆኘ ምክራቸውን እጠየቅሁ እንዳነብና ልምድ እንዳገኝ መድቦኝ ነበርና፡፡ የመካከለኛውን ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ለማጥናት
የሚረዳኝን የግእዝ ቋንቋ ትምህርት ሁለት ኮርስ እንድወስድ አበረታቱኝ፡፡ በጊዜው ኮርሱን ይሰጡ ለነበሩት ለዶ/ር አምሳሉ
አክሊሉ አስተዋወቁኝ፡፡ ብዙ አልገፋሁበትም እንጅ የፈረንሳይኛና የጣሊያንኛ
ቋንቋ ትምህርት እንድማር አበረታተውኝ ነበር፡፡
ቀጥሎም የታሪክ
የማስትሬት ትምህርት በምማርበት ጊዜ ትልቅ ድጋፍ በማድረግ የተለመደ የማማከር ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ ለዚህ ዲግሪ ማóማóያ የምርምር ጥናቴ
ርእስ የነበረው የዋግና የላስታ ታሪክ የሚል ነበር፡፡ እርሳቸው እንደነገሩኝም የላስታ መሪዎች የዛጉዌን ታሪክ ለመፃፍ እቅዳቸው
እንደነበርና ይህንን ታሪክ ለመፃፍ በማሰቤ፤ የትምህርት ክፍሉም ሆነ እርሳቸው ሰለገፋፉኝ፤ በመቀበሌ ደስ እንዳላቸው ገልፀውልኛል፡፡
የምሰራበት
የታሪክ ዘመን ራቅ ያለ በመሆኑና ታሪኩን ለማያያዝና መስመር የያዘ የታሪክ ዳራ እንዲኖረው ለማድረግ ያለ መሰልቸት ይመክሩኝ
ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ስራየ ደከም ያለ ሲመስላቸው በራሳቸው ፅፈው ይህንን ጨምረው እያሉ ታሪኩ ወጥነት ኖሮት እንዲተረክ
እጅግ ለፍተዋል፡፡ በምሳ ሰአት ጭምር ቁጭ ብለው እያረሙና እያስተካከሉ ይህ ነው ተብሎ የማይገለጽ ድካም አሳልፈዋል፡፡ በዚያ
ጊዜ የማስተርስ ድግሪ ትምህርት አራት አመት ይወስድ ስለነበር የማስረከብያ ጊዜው እንዳያልፍብኝ ብለው አሜሪካን አገር ትኖር
የነበረች የልጃቸውን የቀለበት
ቀን በኔ ምክንያት ሳይሳተፉ ቀርተዋል፡፡ “ችግር የለም አንተም ልጄ ነህ እንዳሉኝ” አስታውሳለሁ፡፡
በ|ላም
በአሉ እዚህም ተከበረ፡፡
በተለይም ደግሞ የታሪክ የዶክተሬት ትምህርት እንድማር በማሰብ፤
ለሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ፤ እኔንም ከÝሮፌሰር ክራሚ ጋር አስተዋወቁኝ፡፡ በ1991 —.ም.
ወደ ኢሊኖይ ዩኒßርስቲ
- ኧúርባና aምፔይን - በሄድኩ ጊዜ Ýሮፌሰር
ክራሚ እንደ Ýሮፌሰር
ታደሰ ሁሉ አገሩን በማስተዋወቅ፤ በማበረታታት፤ የሚቸግረኝን ነገር ሁሉ በማደረግ ትልቅ ድጋፍ አድርጎልኛል፡፡ እኔ በሄድኩበት
አመት ከኬንያ የመጣውን ሌላ ተማሪ አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመሄድ ተቀበለው፡፡ እኔንም እንደዚሁ፡፡ ሁለታችንም እቤቱ ወስዶ
አሳረፈን፤ አስተናገደን፡፡ ቤት ተከራይተን ራሳችንን እስክንችል ድረስ ለሳምንት ያክል እቤቱ ተቀመጥን፡፡ እንግድነት በጣም
ሳይሰማንና ተሳቀንም በችኮላ ቤት እድንከራይ ሳንሆን፡፡ አሜሪካ በደረስኩበት ጊዜ ምንም ገንዘብ አልነበረኝምና ገንዘብ እስካገኝ
ድረስ ቤቱ እንድቀመጥ ጋብዞኝ ነበር፡፡ በተለይም
ባለቤቱ ሚስ ሎሬይን ክራሚን እንደ እናት ነበር የምንመለከታት፡፡
አገርን
ለቅቆ፤ ባህርን ተaግሮ በሌላ አገር መኖር የሀገርና የወገን ናፍቆት አስቸጋሪ
ቢሆንም በአመት በአል ቀናት ማለትም የአሜሪካን የምስጋና ቀን፤ ገናና፤ ፋሲካ በደረሰ ቁጥር Ýሮፌሰር
ክራሚ ቤት እየተጋበዝን በአላቸውን በአል አድርገን
ውለናል፡፡ ምናልባት በአጋጣሚ በከተማው ካልኖሩ በስተቀር፡፡ በእነዚህ በአላት ሌላ ከተማ የሚኖሩ ልጆቹና ¹ደኞቹ ስለሚሰባሰቡ በአላቸውን ደመቅ አድርገን ተደስተን አብረን አሳልፈናል፡፡ የኢትዮÉያ
ቡና ተፈልቶ፤ የኢትዮÉያ ቱሪስት አስጎብኚ ድርጅት በሰራቸው የንግስተ ሳባ ስእል
ባላቸውና በሚያማምሩት የቡና ስኒዎች አገራችን ያለን እስኪመስለን ድረስ ተጋብዘናል፡፡ ቢራና ወይንም ተጎንጭተናል፡፡
በዩኒቨርስቲው
የትምህርት መርሀ ግብርና ሌሎች ችግሮች በተከሰቱ ቁጥር እንደ አባታችንና እናታችን ቤት ሳንሳቀቅና ሳንፈራ ቢሮው ሄደን የገጠመንን
ችግር አማክረን መፍትሄ አግኝተናል፡፡ በተቻለው ጊዜ ሁሉ እኛን ለማረጋጋትና ችግራችንን ለማቃለል ከልቡ ጥ[ል፡፡
አንዳንዴም ንዴታችንን ለማስረሳት ቢራ እየጋበዘ፡፡ ያውም ከሚያውቃቸው አንዳንድ ቀልዶች ጋር እያዋዛ፡፡ “ባርባ አራቱ የጎንደር
ታቦታት’ እና ‘ነው እንዴ” ከሚሉ ሀገርኛ ቀልዶች ጋር፡፡
በዚሁ
የአሜሪካ ቆይታየም Ýሮፌሰር
ታደሰም እዚያው ስለነበሩ የሁለቱ አማካሪዎቼና መምህሮቼ በአንድ ከተማ መገኘት ለአኔ ጥሩ አጋጣሚ ነበር፡፡ የዶክተሬት ዲግሪ ማóማóያ
የጥናት ሰራየ በኢትዮÉያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ ስለነበር በቂ የሆነ ድጋፍና ምክር ለማግኘት ችያለሁ፡፡ ቀደም ብሎ ሁለቱ
መምህሮቼና Ýሮፌሰር
ሁሴን በኢትዮÉያ የሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ምርምር ለማደረግ እቅድ ስለነበራቸው፤ እኔም በዚሁ እቅድ ውስጥ ተካትቸ
ስለነበርና፤ የጥናት ርእሴም የዚሁ አካል ስለነበር የሁለቱ መምህሮቼ ድጋፍ አልተለየኝም ነበር፡፡
ከሁለቱ መምህሮቼ ጋር የነበረኝ ቅርርብ በምርምር ስራ ላይ ብቻ
የተወሰነ አልነበረም፡፡ ቤተሰባዊ ጭምር እንጅ፡፡ የÝሮፌሰር ታደሰ ሁለት
ሴት ልጆች - ህይወቴና ህሊና ታደሰ - የቀለበት ስነ-ስርአታቸውን በተለያየ ወቅት ባደረጉ ጊዜ መጋበዝ ብu
ሳይሆን እኔም ሆንኩ የታሪክ ትምህርት ክፍል አባሎች እንደ ቤተሰብ አባል ንቁ ተሳታፊ ነበርን፡፡ ምንም ጊዜ የማይረሳኝና ምን
ያህል Ýሮፌሰር
ታደሰ እንደሚያቀርቡኝ የተረዳሁት በጊዜው ¹ደኛየ የነበረችውን ያሁኗን ባለቤቴን ይŸት
እንድገኝ በጋበዙኝ ጊዜ ነበር፡፡ እር]óን በአካል አያውkትም
ነበር፡፡ ነገር ግን መጠየቅ ይወዳሉና በማስተርስ ዲግሪ ማóማóያ
Îሁፌ ውስጥ ስማóን አይተው ጠይቀውኝ
ነበርና አስረዳሁዋቸው፡፡ ታዲያ የግብŸ ጥሪ ወረቀት ሲሰጡኝ “¹ደኛህን
ትተሀት እዳትመጣ፡፡ ልብ በል እር]ó ካልመጣች እዳትመጣ” ያሉኝ ነበር፡፡ የቀለበቱን
ስነ-ስርአት አንስተን ባወራን
ቁጥር እኔና ዶ/ር አበበ ፍስሀ የተጫወታችሁት አይረሳኝም ይሉ ነበር፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት ከውጭ ለመጡ ቀደምት
¹ደኞቻቸው
ግብŸ
ባደረጉ ጊዜ እኔና የአሁኗ ባለቤቴ ተጋብዘን የባለቤታቸውን የወ/ሮ አልማዝን የተዋጣ የባልትና
ሞያ ተkድሰናል፡፡
Ýሮፌሰር ክራሚ የ60ኛ
አመት የልደት በአሉን ባከበረበት ጊዜ በወዳጅነት ተጠርተን ተጋብዘን ነበር፡፡ ከባለቤቴ ጋር ምን እንስጠው ተባብለን
ተመካከርንና ወይን እንግዛለት ተባባልን፡፡ መቸም የተማሪ አቅም ነው ብለን አነስ ያለች የጣሊያን ወይን ወሰድንለት፡፡ ከጥቂት
ቀናት በ|ላ
በÑፈልኝ
ማስታወሻ ሌሎች ለልደቴ ከላኩልኝ ነገር ሁሉ እንደናንተ የሚጥም ወይን ያመጣልኝ የለም የሚል ቃል ነበረው፡፡
በጉዞ ላይ ምንጊዜም መምህራችን ከማለዳ ጅምረው እያጫወቱን እን¹ዘለን፡፡
በማንኛውም ጉዳይ ላይ በርከት ያሉ ቀልዶችና ወጣቶች የሚያወሩትን ወሬ ሁሉ እያወጉ ያስቁናል፡፡ ከአራት ሰአት በ|ላ
“እንግዲህ የኔን ጨረስኩ፤ በሉ አሁን ደግሞ የናንተን አምጡ” ይሉንና ከዚያ በ|ላ
ተራቸውን አድማጭ ይሆናሉ፡፡ እኛም ምንም ሳንፈራ ማንኛውንም ነገር እናወራለን፡፡ ሀብታይ ዘራይ የተባለ ወፈር ያለ ተማሪ ከ|ላቸው
ይቀመጥ ነበርና አጫጭሮቹን አላሳይ ብሎ ሲከልላቸው ጊዜ “መገዘዝ ዘወር በል አጫጭሮቹን ልይበት” እያሉ ያስቁን ነበር፡፡ መገዘዝ
ቡልጋ ውስጥ የሚገኝ ግዙፍ ተራራ ነው፡፡ ከወራት በ|ላ የማጠቃለያ ስራየን
ጽፌ ስሰጣቸው በአጋጣሚ ቡልጋን መÍፍ ረሳሁት፡፡ ቡልጋ ደግሞ የርሳቸው አገር ነው፡፡ ቁም
ነገር መርሳቴን ለመግለጽ ‘poor Bulga ምስኪኗ ቡልጋ’ ብለው ስህተቴን በቀልድ አዋዝተው
አስገረሙኝ፡፡
ከቀን
ጉዞአችን በ|ላ
ማታ ወደ ማደሪያችን ስንመለስ ሁልጊዜም ቅድሚያ የሚሰጡት ስልክ ደውለው ባለቤታቸውን ማነጋግር ነበር፡፡ ይህ ምንም ቢሆን የማይቀር፤ስልክ
አይሰራም ካልተባለ፤ በቀር የምይዘነጋ የእለቱ ስራ ነበር፡፡ እውነትም Ýሮፌሰር
ሽፈራው
እንዳለው “ምሳሌ ሊሆኑ የሚገባቸው አፍቃሪ ባል” ነበሩ፡፡ በ1990 —.ም.
ለ13ኛው የኢትዮጵያ ጥናት ጉበኤ ወደ ቶክዮ፤ ጃፓን፤ በሄድንበት ጊዜ Ýሮፌሰር
ባህሩ የጋበዘንን ውስኪ አንድ ምሽት እየጠጣን እንዴት የትዳር ¹ደኛችሁን
እንደተዋወቃችሁ አውሩ ተባለ፡፡ መጀመሪያ በእድሜ የምናንሰው አወራንና ቀጥሎ ደግሞ ትላልቆቹ አጫወቱን፡፡ በመጨረሻም Ýሮፌሰር
ታደሰ ከባለቤታቸው ጋር እንዴት እንደተዋወቁ ሲያወሩን ፍቅር እስከ መቃብርን የሚወዳደር የፍቅር ጥምረት፤ እውነተኛና አስገራሚ
ታሪክ ነበር፡፡ Ýሮፌሰር
ታደሰና ወ/ሮ አልማዝ ፍቅራቸው እንደÐናና እንደ ደመቀ አብረው በፍቅር ኖረው አንድ አመት
ባልሞላ የጊዜ ርቀት በሞት ተከታትለው አረፉ፡፡
ዶ/ር ተካልኝ እንደሚያጫውተን Ýሮፌሰር
ታደሰ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ወደ መስክ የምርምር ስራ በየአመቱ ሲወጡ በጣም የሚያቀርቡአቸው ተማሪዎች አሉአቸው፡፡ ቦርሳቸውን
የሚይዝላቸው፡፡ እነዚህን ተማሪዎች ‘ዳዊት’ የሚል ስም ተማሪዎቹ ያወጡላቸዋል፡፡
የመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመምህራቸውን ዳዊት ተሸክመው እንደሚከተሉ ሁሉ፡፡ ታዲያ ዶ/ር ተካልኝ አንድ ጊዜ ይህንን
ለÝሮፌሰር
ታደሰ ሲያጫውታቸው “ለዚህ ነበር እንዴ ጉሉማን ዳዊት ትሉት የነበር፤ እኔ እኮ እስካሁን አላወቅሁም ነበር” ብለው ሳቁና
አሳቁን፡፡ ዶ/ር ጉልማ አሁን የሚኖረው አሜሪካን አገር ነው፡፡ እኔም በወቅቱ ዳዊት መባሌን አልሰማሁም እንጅ የአመቱ ዳዊት
ነበርኩ ማለት ነው፡፡
Ýሮፌሰር ታደሰና Ýሮፌሰር
ክራሚ ብዛት ያላቸውን የቅድመ ምረቃ፤ ማስተሬትና ዶክተሬት ተማሪዎች አማክረው አስመርቀዋል፡፡ ከድሮ ተማሪዎቻቸውም ጋር እንደ
ስራ ባልደረባና እንደ ¹ደኛ ሁነው ብዙ ዘመናትን አሳልፈዋል፡፡ ተማሪዎቻቸውም
እነዚህን የእወቀት አባቶቻቸውን አክብረው ኖረዋል፡፡ ሁለቱም ለንደን የዶክተሬት ድግሪ ተማሪ ከነበሩበት ጊዜ ጀምሮ በፍቅርና
በመግባባት አብረው ሰርተዋል፤ ኖረዋልም፡፡ በሞትም ቢሆን ሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ በሞት ተከታትለው አልፈዋል፡፡ Ýሮፌሰር
ታደሰ በግንቦት እንዲሁም Ýሮፌሰር ክራሜ በነሀሴ 2005 —.ም.፡፡ ሞት አይቀሬ ነውና ሞት አለያይቶአቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን በአብርሀምና በያ˜ቆብ
ቦታ እንዲያሳርፍ እንመኛለን፡፡ ለቤተሰባቸውም መÒናናትን ይስጣቸው፡፡
ሰኞ፤ ጥቅምት 18/2006 —.ም.
Wow, what a wonderful testimony! I felt I have been there! Thanks Daniel.
ReplyDelete+++
ReplyDeleteGod blessed you and your families. Your wok is very important for all of us.
Thanks for sharing .I appreciate those professors who could became fathers for their students truly.
ReplyDeleteIt is an important & interesting God Bless You
ReplyDeleteDn Dani..thanks a lot..those are real ethiopian with their good job. ..the teachers and thier student."Dr Wudu ye Abeyikun Abat edeme ke tena yistilin God blessed you & your beloved family"
ReplyDeleteinteresting history!
ReplyDeleteZERACHEW YBZA
ReplyDeleteyemyasdest tarik
ReplyDeleteReally thank you for sharing this personal history which we lack in most of our professors now a days.
ReplyDeleteGood always to be a good example to others.
ReplyDeleteke memhiru deke mezimuru
ReplyDeleteከቀን ጉዞአችን በ|ላ ማታ ወደ ማደሪያችን ስንመለስ ሁልጊዜም ቅድሚያ የሚሰጡት ስልክ ደውለው ባለቤታቸውን ማነጋግር ነበር፡፡ ይህ ምንም ቢሆን የማይቀር፤ስልክ አይሰራም ካልተባለ፤ በቀር የምይዘነጋ የእለቱ ስራ ነበር፡፡ እውነትም Ýሮፌሰር ሽፈራው እንዳለው “ምሳሌ ሊሆኑ የሚገባቸው አፍቃሪ ባል” ነበሩ፡፡
ReplyDeleteThank you very much wonderful testimony for your Fathers
ReplyDeleteGizachew
ሞት አይቀሬ ነውና ሞት አለያይቶአቸዋል፡፡ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን በአብርሀምና በያ˜ቆብ ቦታ እንዲያሳርፍ እንመኛለን፡፡ ለቤተሰባቸውም መÒናናትን ይስጣቸው፡፡ AMEN
ReplyDeleteፍፁም ዘ
ReplyDeleteየሆነስ ሆነና የተሰጠውን ምስክርነት አነበብን፡፡ ሁለቱ ፕሮፌሰሮች በርግጥም እንደተሰጠው አስተያየት ከሆነ እጅግ ምሳሌ ሊሆኑ የሚገባቸውና ተማሪዎቻቸውም እንዲህ ካሉ መምህራን ጋር ሲሰሩ የቱን ያህል ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው ግልፅ ነው ፡፡ የፕሮፌሰሩ ተማሪዎችም ቢሆኑ በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የርሳቸውን የስራ ድርሻ ይዘው በስራ ገበታቸው ላይ ‹‹ይገኛሉ፡፡›› ነገር ግን በስራ ገበታቸው ላይ መገኘታቸው ብቻም ሳይሆን እነሱስ(የፕሮፌሰሩ የቀድሞ ተማሪዎች የአሁኖቹ መምህራን) የፕሮፌሰር ታደሠ እና የፕሮፌሰር ክሪሚን ባህርይና ጠባይ ለአሁኖቹ ተማሪዎች ያሳያሉ ወይ? ነው ጉዳዩ፡፡
የታሪክ የትምህርት ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡የመጀመርያ ዲግሪዬንም ያጠናቀቅኩት ከ4 አመት በፊት ነበር፡፡ በርግጥም እንደተጠቀሰው ከሆነ የኔ መምህራኖች ጥሩ አርአያ የሚሆንዋቸውን መምህራን አግኝተው ነበር፡፡ የታደሉ ናቸው፡፡ ነገርግን ጥያቄው የአሁኖቹስ ከኛ ከአሁኑ ዘመን ተማሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት የአባትነት ወይስ የሌላ?
መወሻሸት አያስፈልግም ፡፡ አይደለም የአባትና የልጅ ግንኙነት ሊኖረን ቀርቶ ትምህርቱንም በአግባቡ ቢሰጡን ይበቃል ባይ ነኝ፡፡ የነዚህን መምህራኖቻችንን ቢሮ ረግጠን የምናውቅ ምን ያህሎቹ ነን? በጣም በርካቶቹ መምህራንስ ለቀጣዩ ሶስት ሳምንታት ክፍል አልገባም ብለውን የራሳቸውን ገንዘብ ለማግኘት በውጪ ሀገራት ጉዞ የተጠመዱትስ መምህራን ምን ያህሎቹ ናቸው?
ፕሮፌሰር ታደሠ ታምራት እንዲህ አይነት ሰው ነበሩ ብሎ ምስክርነት መስጠቱ ወይም በርሳቸው እጅ ተምርያለው ብሎ መኩራራቱ በቂ አይደለም፡፡ የኚህን ሰው ባህርይና ጠባይ የገባው ሰው እሱም ለተከታዮቹ የተቀበለውን ይሰጣል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የፕሮፌሰሩን እጀ ሰባራነት እየመሰከረ እንደሆነ አይዘንጋ፡፡
የመምህራን አቅምና ድካም የሚለካው በፍሬው ነው፡፡ የፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ፍሬዎች መቼም የጥናትና ምርምር ስራ ላይ ጥሩ ናቸው፡፡ መፃህፍት አሳትመዋል ጥናትና ምርምር ስራ ላይም ተሰማርተው ታይተዋል፡፡ የነዚህ መምህራን ልጆችስ?
እኔ በዚያ የትምህርት ክፍል ቆይታዬን ሳስታውሰው የጥናት ወረቀት (Research paper) እንድናዘጋጅ የተደረገው የመመረቂያ ፅሁፋችንን ብቻ ነው፡፡በየመንፈቁም ሆነ በየትምህርት አይነቱ ተማሪዎች ምንም አይነት ልምምድ ስለማናደርግ በ 4ኛው አመት ላይ ድንግርግራችን ሲወጣ ቢታይ የሚያስገርም አይሆንም፡፡ በርግጥ Research Methodology በሚል የትምህርት ክፍሉ የቀረፀው የትምህርት ዓይነት ቢኖርም እዚህ ግባ የማይባል ደረጃውን ያልጠበቀና ተማሪን በጥናትና ምርምር ስራ ላይ የሚያግዝ አለመሆኑን ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ እኛም እናውቀዋለን፡፡ Title, Acknowledgment, Preface, Footnoot… እና የመሳሰሉትን ክፍል ውስጥ ሳቀመጡ በራስ ሊረዱት የሚችሉትን አይነት ጉዳዮችን ለማስተማር ይሞከራል፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ይህንን ትምህርት እንዲሰጡ የተመደቡት መምህር እኒያ ወደ ክፍል ከመግባት ይልቅ አውሮፕላን ውስጥ መግባት የሚያዘወትሩት ‹‹መምህር›› መሆናቸው ያስገርማል
በቅርቡ እንኳን ስም መጥቀስ ሳያስፈልግ በታሪክ የትምህርት ክፍል የፒ.ኤች.ዲ ተማሪዎች ለሴሚናር የተመደበው መምህር ሊያገኙት እዳ ቢሆንባቸው ጊዜ ለትምህርት ሚኒስቴር ደብዳቤ እንደፃፉበትና ይኸውም መምህር ቅጥያ መጠርያውን ‹‹ ፕሮፌሰር›› ለማስባል ጥያቄውን ከመረጃዎቹ ጋር አዳብሎ አቅርቦ ስለነበር በዚህ የስሞታ ደብዳቤ ሳቢያ ችግር እንደገጠመው ሰምቻለሁ፡፡ አሁን ግን ያንንም አልፎ ፕሮፌሰር እከሌ እያሉ ሲጠሩት ወይ አንብብያለሁ ወይ ሰምቻለሁ (እንኳን ደስ ያልዎት ፕሮፌሰር ! )
ሌላ ትዝብት ልጨምር ከነዚህ አንጋፋ መምህራን መሀል የሆኑ በታሪክ የትምህርት ክፍል የአርኪዮሎጂ መምህራን መሀል ደግሞ አንዱ አሉላችሁ ፡፡ ተማሪዎቻቸውን ካልተገዛቹ የሚሉ አይነት ፣ ክፍል ውስጥ ተማሪ እያስነሱ ይዘልፋሉ፡፡ ተማሪውም መከላከያውን አያቀርብም ለምን ቢባል <> የሚባል ውጤት በመፍራት፡፡ አሁን ከዛ ጊቢ ለቅቄ ከወጣሁ በኋላ ትዕግስቴ ያስገርመኛል ፡፡ ትምህርቴ ላይ መሰናክል ቢገጥመኝ ምን ይውጠኛል ብዬ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ውጪ ሌላ ምንስ ህይወት አለ ብዬ አስብና:: (ውድ መምህር አሁንም እንደድሮው ነዎት ወይስ አመል አይለቅም እንደሚባለው ዘንድሮም እንደዛው ነዎት
አሁንም ቢሆን ጊዜው ረፍዷል ብዬ አላስብም፡፡ እርስ በርስ መሿሿማቸውን ትተው ስራቸውን ቢሰሩ የታሪክ ትምህርት እዚህ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ይሰጥ ነበር ከመባል ሊያድኑት ይችላሉ፡፡ መንግስት በያዘው የማህበራዊ ሣይንስ ትኩረት ማነስ ላይ ብቻ በማሳበብ ጣታቸውን በመቀሰር በማሕበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ድካም እና መቀዛቀዝ ይታያል እያሉ ማላዘኑ ይብቃ፡፡
Dear Fistum
ReplyDeleteYour comment not related to Daniel article. Your comment should send to your department. You mss your the intent of the writer. we have to appercaite Professor Tadesse contrbution for history of Ethiopia. The only reliable reference book for Ethiopian hstory, acknoweledge academic enviorment " NOT in Poltical historian".
Such as Juhar,Tsefaye and so forth.For those outdated / expired poltician ...we do not have time to listen " garbage story ..not history"
Dani please share us unread Ethiopian hitorian has great contbution this country..
zecanada