Tuesday, November 5, 2013

የሌለውን ፍለጋ - ክፍል ሁለት

click here for pdf
በይምርሐነ ክርስቶስ ጣራ ላይ የሚገኘው የዳዊት ኮከብ
ባለፈው ሳምንት ተስፋዬ ገብረ አብ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ያነሣቸውን ነጥቦች ማየት ጀምረን ‹የሦስቱን ተክለ ሃይማኖቶች› ጉዳይ ለዛሬ አቆይተነው ነበር፡፡ እንቀጥል፡፡
1)        የሰባተኛው መክዘ ተክለ ሃይማኖት
ተስፋዬ የጠቀሳቸው የሰባተኛው መክዘ ተክለ ሃይማኖት የሉም፡፡ እስካሁንም እንደርሱ ፈጠራቸውን የሚናገሩ እንጂ ማስረጃ ያመጡ አልተገኙም፡፡ ይህንን ነገር መጀመሪያ ያነሣው የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ገድለ ተክለ ሃይማኖትም ስለ ጽላልሽ (ኢቲሳ) ተክለ ሃይማኖት እንጂ ስለ ሰባተኛው መክዘ ሌላ ተክለ ሃይማኖት አይናገርም፡፡ ገድለ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ልዩ ልዩ ቅጅዎች ቢገኙም ሁሉም ግን በተወለዱበት ቦታ፣ በተወለዱበት ዘመን፣ በወላጆቻቸው ስም፣ በሠሯቸው ሥራዎችና በገዳማቸው ላይ የሚተርኩት ታሪክ ተመሳሳይ ነው(Encyclopedia Aethiopica, Vol., IV,.P.833) በአንድ ወቅት ታላቁን የታሪክና የኢትዮጵያ ጥንታውያን መዛግብት ሊቅ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ስለዚህ ጉዳይ ስጠይቃቸው ‹አለኝ ያለ ማስረጃውን ያምጣ፣ የለም የምንለው ፈልገን ልናመጣ አንገደድም›› እንዳሉት አለን የሚሉት እስኪያመጡ ድረስ የምናውቀውን ይዘን እንቀጥላለን፡፡
2) መራ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ንጉሥ ነበረ፡፡ እንደ ደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና(ኤርትራ) እና ደብረ ሐይቅ መዛግብት ከሆነ መራ ተክለ ሃይማኖት የዛግዌ ሥርወ መንግሥት መሥራች ንጉሥ እንጂ ‹ቄስ› አልነበረም፡፡ የዛግዌን ዘመን በተመለከተ የተጻፉ የዛግዌ ቅዱሳን ገድሎች(ፔሩሾ የጻፈውን የገድለ ላሊበላ መቅድም መመልከት) ይህንን አይነግሩንም፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የዛግዌን ታሪክ ያጠኑት ሊቃውንት(ለምሳሌ E. A. Wallis Budge, A History of Ethiopia, London, 1928; Sergew Hable Sellassie, Ancient and Medieval Ethiopian History) መራ ተክለ ሃይማኖት ቄስ ነበረ አይሉንም፡፡ የላስታ ትውፊትም ይህን አይናገርም፡፡ በላስታ አድባራትና ገዳማት የሚሳሉት ቅዱሳን አራቱ ነገሥታት ናቸው (ቅዱስ ላሊበላ፣ ቅዱስ ሐርቤ(ገብረ ማርያም)፣ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስና ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ)፡፡ ከእነዚህም ክህነትና ንግሥናን እንደያዘ የሚነገረው ይምርሐነ ክርስቶስ ነው፡፡ ተስፋዬ እንዲሆን የሚፈልገውን ብቻ ነው የነገረን፡፡ 
ስለዚህም በገድለ ተክለ ሃይማኖት የሦስት ሰዎች ገድል ተቀላቅሏል የሚለን ማስረጃ አልባ ሕልም ነው፡፡ 

ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጻፈው በገድላቸው ብቻ አይደለም፡፡ በብዙ ጥንታውያን መዛግብትም ጭምር እንጂ፡፡ በገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞአ(ወሎ)፣ በገድለ አቡነ ፊልጶስ፣ በገድለ አቡነ አኖሬዎስ(ባሌ)፣ በገድለ አቡነ እንድርያስ(ደቡብ ጎንደር) በገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን (ኤርትራ፣ እንዲያውም በ ደብረ ቢዘኑ(ኤርትራ) ገድለ አቡነ ፊልጶስ ወአቡነ ዮሐንስ ላይ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት አልፎ የእርሳቸውን ደቀ መዛሙርት ዝርዝር በሚገባ ይነግረናል፡፡ C. Conti Rossini, Gadla Filipos e il Gadla Yohannes,1901, P.156)፣ በገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ(ሰሜን ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ቀውስጦስ፣ በገድለ አቡነ ዕንባቆም(ወለጋና ምዕራብ ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ተክለ ሐዋርያት(ምዕራብ ሸዋ)፣ በገድለ አቡነ ተክለ አልፋ(ምሥራቅ ጎጃም)፣ በገድለ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ(ትግራይ)፣ በገድለ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ(ኤርትራ)፣ በገድለ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ(ምዕራብ ሐረርጌ)፣ ተጽፎ ይገኛል፡፡ እነዚህ በተለያዩ ዘመናት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተጻፉ ገድሎች በደብረ ሊባኖስ በ12ኛው መክዘ መጨረሻና በ13ኛው መክዘ መጀመሪያ ላይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉ አባት ተነሥተው እንደነበረ ታሪካቸውን በአጭርም ሆነ በስፋት ይነግሩናል፡፡ ከኢትዮጵያውያንም ውጭ በ16ና17ኛው መክዘ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት እነ ኢማኑኤል አልሜዳና ፓድሮ ፓኤዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ ያገኙትን ነገር መነሻ ስለ ደብረ አስቦው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጽፈዋል፡፡ ሌላ ተክለ ሃይማኖት ስለመኖሩ ግን ያነሡት ነገር የለም፡፡
በርግጥ አልሜዳ ተክለ ሃይማኖትን በሰባተኛው ወይም በስምንተኛው መክዘ የተነሡ ናቸው ብሎ ገምቷል፡፡ ወደዚህ ግምት የወሰደው የኢትዮጵያውያንን ገድላት አጻጻፍ ባለቁ ነበር፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ ‹‹ወደ ኢትዮጵያ ታሪክ ጥናት ይበልጥ ራሴን ባስገባሁ ቁጥር ሀገራዊውን ትውፊት ማወቅ እንዳለብኝ ይበልጥ እየተረዳሁ መጥቻለሁ፡፡ ይህንን ሀገራዊ ትውፊት፣ ከሕዝቦችን ንቅናቄ ታሪክና ከተከታታይ መሪዎቹ ታሪክ ጋር(ምንም እንኳን አንዳንዴ አፈ ታሪክም ቢሆን) እያወቅን በመጣን ቁጥር ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ ርግጠኛ የሆነ ግንዛቤ ይኖረናል›› እንዳለው(C. Conti Rossini, "Note di agiografia etiopica (Abiya- Egzi, Arkaledes e Gabra Iyesus)," Rassegna di studi orientali, 17(1938), 409-10. ) የኢትዮጵያን ባህል ና ትውፊት ካላወቁ የሚፈጠረውን ስሕተት ነው አልሜዳ የፈጠረው፡፡ ለምሳሌ አልሜዳ እንደ አንድ ማሳያ ያነሣው ‹በገድለ ተክለ ሃይማኖት ውስጥ ስለ ሙስሊሞች አልተገለጠም› የሚል ነው፡፡ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ገድሎች ግን ከክርስትና ውጭ ያሉትን ሕዝቦች ‹ተንባላት› እያሉ ነው የሚጠሯቸው፡፡ ሙስሊም ወይም እስላም የሚለውን ስም በሚገባ የምናገኘው የክርስቲያን ሙስሊም ግንኙነት እየሻከረ በመጣባቸው የመካከለኛው ዘመን የመጨረሻዎቹ ዓመታትና ከግራኝ አሕመድ ጦርነት በኋላ ነው፡፡ በገድለ አኖሬዎስ፣ በገድለ አቡነ አሮን፣ በገድለ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልና በገድለ አቡነ ፊልጶስም በተመሳሳይ ሁኔታ ነው የሚገኘው፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር የማያያዝ ነገር በተስፋዬ አልተጀመረም፡፡ ሌሎች አካላትም ሲያራምዱት የኖሩና የሚራምዱትም ነገር ነው፡፡ በዚህ ረገድ ያልተጠኑ ሦስት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው የሰሎሞናዊ መንግሥት ምለሳ (Restoration) የሚባለው ነገር፡፡ ሁለተኛው በዚህ ምለሳ ላይ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ነበራቸው የሚባለው ሚና እና የታሪኩ ምጮች ናቸው፡፡
የንጉሥ ሐርቤ የዳዊት ኮከብ ያለበት ማኅተም
እንደ እውነቱ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በአኩስም ዘመን የነበሩ ነገሥታት ራሳቸውን ሰሎሞናውያን ብለው የጠሩበት መረጃ የለንም፡፡ ለኢትዮጵያ ነገሥታት ግን ራሳቸውን ከኢየሩሳሌምና ከቅድስት ሀገር ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ረገድም የዛግዌ ነገሥታት ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያትም የለም፡፡ እንዲያውም ለሰሎሞናዊነቱ ከኋለኞቹ ነገሥታት ይልቅ የዛግዌ ነገሥታት ይቀርባሉ፡፡በውቅር ቤተ ክርስቲያኖቻቸውም ሆነ በማኅተሞቻቸው ላይ የዳዊትን ኮከብ በብዛት እናየዋለን፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድም የዛግዌ ነገሥታት ይበልጣሉ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም የሮሐን አብያተ ክርስቲያናት ሲያንጽ ኢየሩሳሌምን እያስታወሰ ነው፡፡ በኋላ ዘመን ‹ሰሎሞናውያን› ከተባት የይኩኖ አምላክ ዘሮች ነገሥታት ወገን እንድም ንጉሥ ኢየሩሳሌም ሄደ ተብሎ አልተጻፈለትም፣ አልተነገረለትምም፡፡ የዛግዌ ነገሥታትን ግን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ የሚተካከላቸው የለም፡፡
የአኩስምን ነገሥታት (በተለይ ዐፄ ካሌብና ዐፄ ገብረ መስቀል በወሎ አካባቢ አያሌ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ የዛግዌ ነገሥታትም (በደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና ወንጌል እንደ ተገለጠው) ለኤርትራና ትግራይ ገዳማት ርስት ሰጥተዋል፡፡ የሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት መላሽ የሚባለው ይኩኖ አምላክም ቢሆን በእናቱ የቡግና ተወላጅ ነው፡፡ ውትድርና ተቀጥሮ የኖረውም ቡግና ነው፡፡ የተማረውም ወሎ ሐይቅ እስጢፋኖስ ነው፡፡ አቡነ ኢየሱስ ሞአ ትውልዳቸው ቡግና ስለሆነ ነው ይኩኖ አምላክ ወደ ሐይቅ ለትምህርት የሄደው፡፡ እርሱ ሲነግሥም መጀመሪያ ያሳነጸው የወሎዋን ገነተ ማርያምን ነው፡፡ አጽሙም የሚገኘው በወሎዋ አትሮንሰ ማርያም ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ በሸዋ ውስጥ ስሙ እንጂ ቅርሱ ያለ አይመስልም፡፡
ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ የወረደው እርሱ ሸዬ ስለሆነ አይመስልም፡፡ የዛግዌ ነገሥታት የበረታ ኃይል ከሚገኝበት ከወሎ አካባቢ ለመሸሽና የደቡቡን ኃይል ለማሰባሰብ እንጂ፡፡ ኮንቲ ሮሲኒ ከኤርትራ አግኝቶ ባሳተመው እንድ ጥንታዊ የብራና ጽሑፍ ላይ  ‹‹(የይኩኖ አምላክ ሠራዊት) ሰባቱ ጉደም ናቸው፡፡ እነርሱም ወግዳ - መለዛይ፣ ዲንቢ - ዳባራይ፣ ሙገር - እንደ ዛቢ፣ ወጅ - እነጋሪ፣ ወረብ - እነካፌ፣ ጽላላሽ እነ ጋፌ እና ሙዋይ - አውዣዣይ ናቸው፡፡ የእነርሱም አለቃ መለዛይ ከንጉሡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ ተዋግቶም ጠላቶቹን ድል ነሣ›› ይላል (Taddesse Tamrat, Ethnic Interaction and Integration In Ethiopian History: The case of The Gafat, JES, Vol. XXI,1988, P. 125)
ይኩኖ አምላክ የዛግዌ ነገሥታትን ሊያሸንፍ የቻለው በዚያ ዘመን በጥበበ ዕድ አንድነት በፈጠሩት(ሰባት ጉዳም) ጋፋቶች ርዳታ ነው፡፡ ምንጊዜም የመሣሪያ ኃይል ያለው ያሸንፋልና፡፡ ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ ባደረገው መስፋፋት ወደ ክርስትና ተመልሶ ከደጋው ሸዋ ክፍል ጋር የነበረውን ጠላትነት ያጠፋውን የዳሞትን መንግሥት ኢኮኖሚያዊ ዐቅም ተጠቅሞበታል፡፡ ልክ በኋላ ዘመን ዐፄ ምኒሊክ የደቡቡን ኃይልና ዐቅም በመጠቀም ገንነው እንደወጡት ማለት ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ ወደ ሸዋ በመምጣት ኃይሉን በማደራጀቱ ሸዬ ሆኖ ቀረ፡፡ ልክ በኋላ የሸዋ ነገሥታት ወደ ጎንደር ሄደው ጎንደሬ ሆነው እንደቀሩት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ‹ሰሎሞናዊ› የሚባል የተለየ መንግሥት አልነበረንም፡፡ ነገሥታቶቻችን ሁሉ ራሳቸውን ከኢየሩሳሌም ጋር ያያይዙ ነበር፡፡ ዐፄ ካሌብም ከናግራን ዘመቻ መልስ ዘውዳቸውን ኢየሩሳሌም ነው የላኩት፡፡ የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ ሙሴም መጀመሪያ ወደ ኢየሩሳሌም፣ በኋላም ወደ ሶርያ በመጓዝ በዚያ ገመንነው ገዳም መሥርተዋል፡፡ ገዳማቸውም ‹ሙሴ አል ሐበሽ ገዳም› ይባላል፡፡
የዛግዌ ነገሥታትም ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያት የላቸውም፡፡ በገድሎቻቸው ላይ ኢየሩሳሌምን አብዝተው የሚያነሡ፣ ማኅተሞቻቸው ሁሉ የዳዊት ኮከብ የሆኑ፣ በውቅር ቤተ ክርስቲያኖቻቸው የዳዊትን ኮከብ የቀረጹ የዛግዌ ነገሥታት እንዴት ሰሎሞናውያን አይሆኑም፡፡
የኢትዮጵያዊው የቅዱስ ሙሴ(የዐፄ ገብረ መስቀል ልጅ) ገዳም በሶርያ
በመሆኑም የጠፋና የተመለሰ የሰሎሞን መንግሥት አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ሥርወ መንግሥታቱንም ‹የአኩስም፣ የላስታ፣ የሸዋ፣ የጎንደርና የሸዋ 2ኛ› ብሎ መክፈሉ የተሻለ ነው፡፡
ሲባል እንደኖረው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት ቢቀበሉ ኖሮ በገድለ አቡነ አኖሬዎስና በገድለ አቡነ ፊልጶስ ላይ እንደምናነበው እነዚህ ሁለት ቅዱሳን ወደ ደብረ አስቦ(የአሁኑ ደብረ ሊባኖስ) ሲመጡ ግንባር በምታክል መሬት ላይ አተር ዘርተው ሲሰበስቡ ባላገኟቸው ነበር፡፡ ደብረ ሊባኖስ ይበልጥ እየታወቀና በማዕከላዊ መንግሥት ቦታ እያገኘ የሄደው ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በኋላ ነው(ምናልባት ኤርትራ ይገኝ ከነበረው ከደብረ ሊባኖስ ዘሺምዛና ጋር ያለው ግንኙነት እየተዳከመ ሲመጣ)፡፡ ደብረ ሊባኖስ የሚለውን ስም ያገኘውም ያኔ ነው፡፡(Les chroniques de Zara Ya’eqob.,P. 91) አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከነገሥታቱ ጋር የተለየ ቀረቤታ ቢኖራቸው ኖሮ በዓለ ዕረፍታቸው ነገሥታቱና መኳንንቱ በተገኙ ነበር፡፡ ነገሥታቱ በደብረ ሊባኖስ መገኘት የጀመሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ ከ100 ዓመታት ቆይተው ከዐፄ ይስሐቅ ዘመን (1406-1421 ዓም) በኋላ ነው፡፡ እንዲያውም የደብረ ሊባኖስ አባቶች በነበራቸው ጽኑዕ አቋም የተነሣ ከነገሥታቱ ጋር ባለ መስማማት ነው የሚታወቁት፡፡ 3ኛውን እጨጌ አቡነ ፊልጶስን፣ አሥራ አንዱን ንቡራነ ዕድና እጨጌ እንድርያስን ማስታወሱ ይበቃል፡፡
ከላስታ ወደ ሸዋ የመንግሥት ዝውውር ሲደረግ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐይቅ እስጢፋኖስ በትምህርት ላይ ነበሩ(የሚጣቅ ዐማኑኤሉ ገድለ ተክለ ሃይማትና ገድለ ኢየሱስ ሞአ በዝርዝር እንደሚተርከው)፡፡ በዚህ የሥልጣን ዝውውር ላይ ይበልጥ ተሳታፊ የነበሩት አቡነ ኢየሱስ ሞአ ዘሐይቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ሐይቅ የዐቃቤ ሰዓትነት ሥልጣን ነበረው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሦ መንግሥት አግኝተዋል የሚለው ትረካ መንግሥት ወደ ጎንደር ከተቀየረ በኋላ(17ኛው መክዘ) በተጻፈው በብዕለ ነገሥት ላይ የተገለጠ ነው፡፡ ብዕለ ነገሥት የነገሥታትን ሀብት ለማሳየት የተጻፈ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ነው ከይኩኖ አምላክ ጋር ቃል ኪዳን ገብተዋል ተብሎ የተጻፈው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ መንግሥት ወደ ጎንደር ሲዞር ደብረ ሊባኖስ ከማዕከላዊው መንግሥት ራቀ፡፡ በአካባቢውም ክርስቲያን ባልሆኑ ሕዝቦች ተከበበ፡፡ የጎንደር ነገሥታት ገዳሙን እንዳይረሱትም በብዕለ ነገሥት የአባታቸውን ይኩኖ አምላክን ቃል ኪዳን እንዲያስታውሱ የሚያደርግ ነገር ተጻፈ፡፡
እናም ተስፋዬም ሆነ ሌሎች እንደሚሉት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከቅድስና ሥራ በቀር የገቡበት ፖለቲካ የለም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ደብረ አስቦ ሲገቡ ይኩኖ አምላክ በመንበሩ ላይ ነበር፡፡ ነገር ግን የጠበቃቸው ዘንዶ ይመለክበት የነበረ ዋሻ እንጂ ከሲሦ መንግሥት የተገኘ ግብር አልነበረም፡፡ ያንን ዋሻም ያገኙት ከጣዖት አምላኪዎች አስለቅቀው ነው፡፡ 28 ዓመት በደብረ አስቦ ሲቀመጡም የጎበኛቸው ንጉሥ አልነበረም፡፡ ደቀ መዝሙሮቻቸውም ከዝንጀሮ ጋር እየተሻሙ እህል ዘርተው ከማብቀል ውጭ የተለየ ርስት አልነበራቸውም፡፡ ደብረ ሊባኖስ ሲተከልም የአካባቢውን ሕዝቦች በማሳመን እንጂ በነገሥታቱ ድጋፍ አልነበረውም፡፡ ከይኩኖ አምላክ በኋላ የመጣው ያግብዐ ጽዮንና አምስቱ የያግብዐ ጽን ልጆች ለአቡነ ተክለ ሃይማትም ሆነ ለደብረ አስቦ ያደረጉት ነገር አልነበረም፡፡ ዐፄ ዐምደ ጽዮንና ዐፄ ሰይፈ አርእድም ከደብረ ሊባኖስ እጨጌዎች ጋር በሰላም አልኖሩም፡፡
አቡነ ፊልጶስ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሲመጣ የአካባቢው ሰዎች ‹የገዳሙ መነኮሳት ሰው ይበላሉ›› ብለው ነው የነገሩት፡፡ ይህም ደብረ አስቦ በዚያ ዘመን የመነኮሳት ማኅደር እንጂ እንኳን ነገሥታቱ የአካባቢው ሰዎችም በቅጡ እንዳልቀረቡት ያሳየናል፡፡ የደብረ ሊባኖስ የመጀመሪያዎቹ አባቶችም በራሳቸው ጥረት በደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ገዳም የተከሉ እንጂ በነገሥታቱ ድጋፍ ሲሦ መሬት የያዙ እንዳልነበሩ ያሳየናል፡፡ 
ከዐሥረኛው መክዘ ጀምሮ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት በሰሜኑና በደቡቡ የሀገራችን ክፍል ምክንያት የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ ነበር፡፡ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት እንደሚገልጡትም የሰዎች ፍልሰት ከሰሜኑ የሀራችን ክፍል አሁን ሸዋ ወደሚባለው አካባቢ በየተወሰነ መጠን ብቻ ይከናወን ነበር፡፡ ይህንን ከሦስት መቶ ዓመታት በላይ ለሆነ ዘመን የተለያየ ሕዝብ እንደገና ያዋሐዱት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዳሞትን ከሸዋ ጋር ካገናኙ በኋላ ወደ ወሎ በመሄድ ሐይቅ ቆዩ፤ ቀጥለውም ወደ ትግራይ በመጓዝ ደብረ ዳሞ ገቡ፡፡ ለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የምንኩስና ሕይወት ማንሠራራት አንዱ ምክንያት የሆኑትን አቡነ መድኃኒነ እግዚእን አመነኮሱ፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ አምስቱን ከዋክብት(አቡነ አሮን ዘክቱር፣ አቡነ መርቆሬዎስ ዘዶባ፣ አቡነ ዘካርያስ ዘኬፋ፣ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ዘዳኅና፣ አቡነ ዳንኤል ዘጸዐዳ)ና ሰባቱን ከዋክብት በማመንኮስ(R. Basset, Etudes sur I historie d Ethiopie,.p 10) የሰሜኑን ገዳማዊ ሕይወት እንደገና ነፍስ ዘርተውበታል፡፡ በዚህም ምክንያት የሰሜኖቹ ወደ ደቡብ በመምጣት፣ የደቡቦችም ወደ ሰሜን በመሄድ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ እንዲያንሠራራ አድርገውታል፡፡
ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡  

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው

ማስተዋሻ


አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የተመለከተ አንድ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነኝ፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው ቢረዱኝ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይወጣ ይሆናል፡፡ እናንተም ጸልዩበት፡፡

98 comments:

 1. D/n Daniel it is a fantastic argument so Keep it up!! God bless you.

  ReplyDelete
 2. Dn. Daniel, I have to say first God bless you and keep it for your timely response articles about the esteemed Ethiopian Church. I was expecting your research writing on 'Abune Teklehaimanot' since you had declared in your two articles almost a year before(one of it while you give response to Bewketu Seyum about his comment on 'Abune Teklehaimanot' and followers. Thus I kindly requested you what is the status of that writings.

  ReplyDelete
 3. long live Dani.
  ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡

  ReplyDelete
 4. D/Dani God bless you!!!

  ReplyDelete
 5. ዲ/ዳንኤል ወንድማችን አባታችን እንበልህ አንተ የእውነተኞች የሐዋርያት የቅድሳን ልጂ በርታ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ።መላቀቅ የለም እሾህን በሾህ ነው ጠላት መግቢያ ሲያጣ አስሩነው ሚጨብጥ ለዚህ ደግሞ እውነት አለ እውነትም ልጆቹን እዲህ አዘጋጅቶ አስቀቀምጦል እውነት ለዘለአለም ያሸንፋል ቅድስት በተክርስቲያናችን ኢትዮጵያ በእውነት ለዘለአለም አሸንፋና ተከብራ ትኖራለች ።አወ እውነት ከእርሶ ጋር ስላለ።አተግን በርታ ኢትዮጵያ ወልዳ ቅድስት ቤተክርስቲያን ያሳደገችህ ።እኔማ ያንተን ነገር ም ን እላለሁ ቃል በማጣቴ የቤተክርስቲያን ጠላት ሲነሳባት ጠላቷን በመጣበት መድረሻ መፈናፈኛ አሳጥተህ የምትመልስ ህዝቦቾ ደሰ ሲሰኙ በደስታ በተስፋ መንግስተ ሰማይ የገባ ያህል ተስፋን እየሰጠህ ስደተኛውን መንፈሱን የምታነቃቃ በሀገሩ ያለውንም የምትጠግን የኔ ኢትዮጵያዊው ወንድሜ ደመላሽ ብየህአለሁ። ሌላው ሁሉ ስም አየረካኝም አባ ኮስትር በሌ በርታ።እግዚየብሔር ኢትዮጵያን አሜን።

  ReplyDelete
 6. Monastery of Saint Moses the Abyssinian

  http://en.wikipedia.org/wiki/Monastery_of_Saint_Moses_the_Abyssinian
  http://www.utoronto.ca/nmc/mason/DMM.html

  ReplyDelete
 7. kale hiwotin yasemalin.wuhan ketiru negerin kesiru malet yihe new enji zim tebilo kelay kelay ayikedim.
  Egziabher yisitilin

  ReplyDelete
 8. I think it is the best time to you and us to answer such mis use of our history.

  ReplyDelete
 9. The more i read ur article i am blaming myself were am i ,thank u Dani, it tells a lot for Ethiopian people to see z truth ...

  ReplyDelete
 10. ደመላሽ ብየህአለሁ። ሌላው ሁሉ ስም አየረካኝም አባ ኮስትር!!!!!!! nothing to add, you are a SUPPER INTELLECTUAL IN WHICH YOUR BLOOD IS FULL OF BELIEF!!! LOVE YOU!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ይገባዋል አይደል? እሄ ቅድስ ሀዋርያ አቢ ሀገሬን እቢ ቤተክርስቲያኔን የሚል ጀግና በጠፋበት ጊዜ እኔአለሁ የቁርጥ ልጂእያለ ከባንዳጋር ፊትለፊት የሚጋፈጥ አባ ኮስትር ይገባዋል ዳንዪ ጀግናነው።

   Delete
  2. እንዲያ በል አንተ!

   Delete
  3. አወ እዲያበል ያገር ልጀ።እትትትት! የሰውየው ልጂ ይላል ያሀገሬ ጀግና!

   Delete
  4. u guys are so funny.

   Delete
 11. RELLAY YOU ARE WONDERFULL BROTHER.

  ReplyDelete
 12. how could I express what I feel, but weather they like it or not the hand of God is with Orthodox church. you are one of the best child of this church. don't give up what ever comes. Be proud of orthodox Christin people.

  ReplyDelete
 13. Thank you Dani Medehanialem Edimena tena yistih kehadiowochin Egziabher Yastagsilin Honestly Thank you Dani Again

  ReplyDelete
 14. እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከ ሐሳዊ ፀሃፍት ይጠብቅ ላንተም ረጅም ዕድሜ ከ ሙሉ ጤና ጋር ያድልህ ያገልግሎት ዘመንህን ያስረዘምልህ! አሜን

  ReplyDelete
 15. “ሰው ማለት ሰው ነው ሰው የጠፈ እለት”ያለው ማን ነበር ዳንኤል ሰው በጠፋ ጊዜ ተገኘተሃልና እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልህ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 16. አምላከ ቅዱሳን ስራህን ለፍሬ ያብቃልህ።

  ReplyDelete
 17. it is good argument suggested from both sides because it is hidden issue mainly among highly scholars in the church. do no blame tesfaye simply without checking where is the reality. i said this just observe today situation it is full of forgery in the name of the church. similar condition may be happen in the past.so, till you get the reality involve your self to be part of the reality not just good writer ideas and opinion. no one can check the reality unless otherwise God help us.

  ReplyDelete
  Replies
  1. min malet endefelek inkuan lene lantem algebah. ebakihin bemitchilew kuankua tsaf. degmom irasih anbib ante astemari neh ende yebet sira mitsetew

   Delete
 18. ለካስ በዚህ ዘመን ቅዱስ ዪሐንስ አፈወርቅ፣ አባታች አባ ጎርጊስ ዘጋስጫ አሉ፡፡ የዘመናችን አፈወርቅ ዳኒ ዕድሜ እና ጤናውን ጌታዮ ስላሴ ይስጡህ ድንግል ትጠብቅህ የቅዱሳን አባቾችንን ፀሎታቸው አይለይህ፡፡

  ReplyDelete
 19. ጻድቁ አባት በእግዚአብሔር ኃይል ዲያብሎን ድል የነሱ፣ ጣዖታትን ያወደሙ፣ ወንጌልን የሰበኩ ሐዋርያ ናቸው።

  አንተም እውነቱን አሳውቀኸናልና የጻድቁ በረከት ይብዛልህ።

  ReplyDelete
 20. አቡነ ጎርጎርዮስ ዘር ዘሩ አሉ
  ፀሐይ ወጣ ዝናብ መጣ ዘር ጸደቀ እንዲሉ
  አንተን መሳይ ዋርካ እንዲያየው ሰው ሁሉ!

  ነፍሳቸውን ይማረና ይኸው የአቡነ ጎርጎርዮስ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ! ዳንኤል ክብረት ለሀገርና ለቤተክርስቲያን መልካም ሰርቶ አለፈ ብቻ ይባላል ወይስ በተለይ በግልህ ተተኪ ዘር ለመዝራት ምን ታስባለህ??? አስብበት!

  ReplyDelete
 21. We are waiting the book for long time. Please try to finish it as early as possible.
  What can be said about the article ...

  ReplyDelete
 22. Thank you Deacon Daniel. God bless you. በወሎ(ቤተ አምሐራ) ዘዴየ ልመርቅህማ።
  አንተየዋ እንደው ባሻዬ ይሙት ዴግ ሰው ነህ። እንዴው እንዴው ሽ በክንፉ ሽ ባክናፉ ይከተልህ። አያ ጥላና ከለላ ይሁንህማ።ኸረ ተባረክ ዲያቆን ዳንኤልዋ። እግዚሃር ይባርክህ።


  ጌታሁን ዴምለው(ላስቴው) ነኝ ካይና ቡግና፣ ዋሻ ሚካኤል።

  ReplyDelete
 23. Ye oromo teret "Ol kaa'an Malee ol ka'aniif hin fudhanii" yilaal. tirgumum የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና new, Dani tsihufi min yahil tarik indemalawuk new yasayegn. Beka kengedih silehagere manbeb allebign!!!

  ReplyDelete
 24. Thanks Dani for the two researched articles.

  Tesfa k'Arat kilo

  ReplyDelete
 25. It is very nice argument.

  ReplyDelete
 26. ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡

  ReplyDelete
 27. አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የተመለከተ አንድ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነኝ፡፡ ጻድቁ በጸሎታቸው ቢረዱኝ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ይወጣ ይሆናል፡፡ እናንተም ጸልዩበት፡፡ዲ/ን ዳንኤል ጸጋውን ያብዛልህ፡፡ አምላከ ተክለ ሃይማኖት ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 28. you are a gift of God for orthodox Christians !
  I wonder if you would get sponsors and spread your writing to reach most people. because now days, false are free and abundantly available all over place.
  Thank you so much! May God gives you strength and long life to serves us.

  ReplyDelete
 29. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እውቀትህን ይባርክ ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥህ

  ReplyDelete
 30. Your rebuttal to G/Ab's claim about Kedus Teklehaimanot is sensible, informative and reasonable. You have listed several supporting references and citations to substantiate your argument. The fact that you combined your faith with knowledge of history works great.

  I disagree with your conclusion that G/Ab is trying to erode the basic tenets and culture of Ethiopia. This is such a sweeping allegation without any basis. In doing so, in a way, you tarred your beautiful argument for the specific points. G/Ab has the right to point out issues, historical, cultural, etc, that he thinks are confusing, or untrue, or myth. You don't have to criminalize him to make your point. Just do what you do best, i.e, rebut his allegation point by point.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think G/Ab(so called writer), writes something against ones nation religious believes and followers with out any substantial evidence and in a degrading manner its not because he has doubts rather its because of malicious intent. A person who has doubts refers and asks question to clarify not blatantly writes his personal disbelief & misjudgment in a matter that doesn't concern him. That is why is essential to say what G/Ab intention is (we all know it but Daniel brought the evidence to show how he is trying so hard in tarnishing Ethiopians culture, religious beliefs and history). Don't think that he is innocent because you probably doesn't follow the same religion as we do. It's all about the truth

   Delete
 31. yezemenu berihane alem paulos God bless you dani

  ReplyDelete
  Replies
  1. paulos eko Ysebek Eyesus kirstosn bicha new. beziyam sayabeqa

   በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤
   7 እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።
   8 ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። new yalew tadiya keziga endet paulos meta newu tekelehayimanoten end gedlu kirstos silehon new

   Delete
  2. anonymous, please wede Adarashih hid, to ur fake lord. Yihe ewunetegnawun christos yemiyamelku ye christianoch bota new

   Delete
 32. እግዚአብሔር ይርዳህ ቤተክርስቲያናችንም ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 33. ለካስ በዚህ ዘመን ቅዱስ ዪሐንስ አፈወርቅ፣ አባታች አባ ጎርጊስ ዘጋስጫ አሉ፡፡ የዘመናችን አፈወርቅ ዳኒ ዕድሜ እና ጤናውን ጌታዮ ስላሴ ይስጡህ ድንግል ትጠብቅህ የቅዱሳን አባቾችንን ፀሎታቸው አይለይህ፡፡ለካ እነ አትናትዮስ ፣እነ ቄርሎሰ፣እነ ዲዮስቆሮስ................ዛሬም አሉ??? አምላክ ሆይ ተመስገን፡፡

  ReplyDelete
 34. As mentioned on Saturday - I am grateful to you and the great job you did and doing on Abune Teklehaimanot as no one worried about the conflicting ideas surrounding/influencing the society/congregation - You DID and DOING it. I pray for the book happen soon.

  ReplyDelete
 35. <>Absolutely!! Many thanks Dany!! God Bless you!!

  ReplyDelete
 36. Hello Dn. Daniel
  Tesfaye has tried his best to stir the country by using ethinic clashes but that does not come to be successful. He now tries to dismantle the pillars of our church and country and as you said that will not be possible.
  The best thing for him is to be quiet.
  Thanks Dani

  ReplyDelete
 37. ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡

  ReplyDelete
 38. ተስፋየ ግን ምንድን ነዉ ? ይመስለኛል የሆነ ነግር ይጎድለዋል ! አንዴ መንግስትን ይኮንናል አንዴ አንድን የመንግስት ባለስልጣንን የህይወት ታሪክ ይዘከዝካል አንዴ አንዱን ብሔር ከሌላዉ ጋር ያጣላል አንዴ ለነጻነት እስክሞት እታገላለሁ ይላል ሌላ ጊዜ ደግሞ ቤተክርስትያንን እና የቅድሳንን ታሪክ ያዛባል፡፡ወይኔ አቋም የሌለዉ ሲያስጠላ !ከዳኔ ጠጋ ብለህ ተማር ወንድሜ አትዋዥቅ!

  ReplyDelete
 39. ዳኒ እግር ሥር ቁጭ በልእና ታሪክ አጥና

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዳኒ ሳይሆን እግር ስር ቁጭ የሚለው አንተ እግር ስር ቁጭብለህ የሀገርህን የቤተክርስቲያንህን ታሪክ ማወቅ መማር ያለብህ አንተ ነህ። ዳኒማ የሀገር መመኪያ የቤተክርስቲያን ተስፋዋ ነው ወሬ ስታወራ አማረኛ ስትሰነጥቅ ለሀገር ሳትጠቅም እንዲሁ ትሽኛለህ ዳንዪን ለቀቅ እግር ስርህ ቀጭ እግዚያብሔር ካልመረጠ አይሆ አቅምን ማወቅ ብሏል ታላቁ ዘፋኝ ጥልዪ የሀገር ቅርስ።

   Delete
  2. በጣም በጣም ይቅርታ ልል የፈለኩት ተስፋዬን ነው
   ልትቆጣ ይገባሃል ስለአምታታሁ በዘውም እኔ ጹሁፍ አለማወቄን ተምሬበታለሁ
   የተስፋዬን ስም ጠቅሼ መጻፍ ነበረብኝ ግን ዳኒ ብሎ አቆላምጦ ጠርቶ ዘለፋ ይከብዳል ለማንኛውም
   እንደዚህ ተብሎ ይነበብ፡፡ ተሥፋዬ ዳኒ እግር ሥር ቁጭ በልእና ታሪክ አጥና

   Delete
  3. ወንድሜ ሆይ ስህትህ ከተቀበልህ መልከም ነው ሁሌም ይቅርታ ለማድረግ እኛም ዝግጁን የውልህ እዲህ የሚል ዜጋ ጠፍቶብን እኮነው ሀገራችን ምትበጠበጠው አጠፍቻለሁ ስህቴን ልማርና እኔም በተራዪ ለስተምር የሚል የተሰበረ ለብ ነው የሚያስፈልገው መሽነፍ አይደለም ለወገን ለሀገር ለሰላም አብሮ በፍቅር ለመኖር የገድ ስለሚያስፈልገን ነው ።ወንድሜ እግዜያብሔር ይባክህ አመሰግናለሁ አየህ አንተ ስህትህ በመቀበልህ እንዴት ደስ የሚል የምስጋና ቃል አደተሰጠህ እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም እደምንማርበት አምናለሁ ።ተሰፋየ ሚሉትን ተወው ከዳንየ እግር ስር ሆኖ ቢማርም አይገባውም ምክኒያቱም ገና ከናቱ ማህፀን ለጥፋት የተመረጠ ከሆነ ልታስተምረው አትችልም እሱ ደግሞ የጥፋት ልጂ መሆኑን ምንም መረጃ አየስፈልግም የሰው ልጆች ጠላት የሆነውን ሳጥናኤልን የሚያንቀጠቅጠውን ሐዋርያው መለኩሴ ዘኢትዮጵያ ተክለ ሃይማኖትን ነው የተቃወመ ተወው መጥፊያው ቀሮቦ ነው ።በቅርብ ታያለህ ስህተቱ አምኖ ንስሀ ካልገባ ታያለህ። ሰይጣን የመልካም ነገር ተቃዋሜ እጂ የመልካተስራ ተባባሪ ሆኖም አያውቅ ።አድነገር ትዝ አለኝ አባታችን አብርሀም እንግዳ በመቀበል የታወቀ ነበር እሄው ክፉየክፉ ልጂ እንደተስፋየ ያለ አብርሀምን ተቃወመ መንገድ ላይ ቁጭ እያለ የአብርሀምን ስም በክፉ በረዘውአብርሀም እንግዳ አይቀበልም እዳይደበድባችሁ ተመልከቱ እኔን ደሜ እስኪፈስ እዲህ አደረገኝ እያለ ሲወነጂለው መጨረሻው ሲደርስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደማይመለስበት መቀመቅ በአብርሀም አምላክ ለዘለአለም ተጣለ አብርሀምም ጠላቱን ድል ነሳው ያውም በፈጠሩት ጌታ በሥላሤ በአምላካችን በፈጣሪያችን። አና ወንድሜ እንኮን አንተ እራስህን አዳንህ እጂ ተስፋየን ተወው መጥፊያው ደርሶ ነው። ጥላሁን ገሰሰ ታላቁ ዘፍኝም ብዙ አስተምሮን አልፎአል አቅምን አውቆ መኖርጥሩ ነው ታላቅ ችሎታ ነው የሚለውን ለተስፋየ ጋብዘዣለሁ።ዳንየ እያለ ማቆላመጥ ላልኸው ያንጀቴን ያሰብሁትን ለኔ ብቻ ሳይሆን ላንተም ለወገን በሙሉ የልብ አድራሽ በመሆኑ እንኮን ዳንዪ ሌላ ብለው አያረካኝም በሳት የተፈተነ ወርቅ ታውቃለህ ።እዴውም እኮ እኔ ምጠራው ዳንዪን እድታውቀው አንተም ትለዋለ አርግጠኛነኝ ።ደመላሽ አባ ኮሰትር በላይ ነው የምለው እሄን ስም ያገኝው ዝም ብሎ አደለም በስራው ነው ።በላይ ዘለቀም እኮ እቢ ለሀገሬ ለወገኔ አለስነካም ስላለ እኮነው ጃንሆይ ለስልጣኔ ያስፈራኛል ብለው አዲስ አበባ መርካቶ የሰቀሉት።አየህ ዳኒም ሆዳም ቢሆን ኑሮእደምናያቸው የክደት ካባውን ደሮቦ በሚፋለቀለቀው መኪና ሲፈስ ሲታጀብ እናየው ነበር ዳኒ ግን አይደለም እንቁ የኢትዮጵያ ልጂ የቤተክርስቲያን ልጂ እዴውም እሄን ልበልና ለብቃ ምክንያቱም ተፀፎ አያልቅም ።ሰው በጠፋበት ዘመን መጥምቁ ዩሐንስ የጌታ ቀን ቀርቦልና ንስሀ ግቡ ጠማማው ይቅና ጐባጣው ይስተካከል ይለናል እነ ወንድሜ እኔስ ምለው አጥቸ ነው አጂ ሌላም ባልሁት ።አባ ኩስትር ያልሁት በል መልካሙን የሰማን ያሀገሬ ልጂ ደህና ሁንልኝ ።


   Delete
 40. ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና ከነ ሙሉ ቤተሰብህ ይስጥልን!!!
  መፅሀፉንም በሰላም ጀምረህ እንድትፈፅም የአቡነ ተክለሀይማኖት አምላክ እግዚአብሔር ይርዳህ
  አሜን!!

  ReplyDelete
 41. ዲ/ን ዳንኤል- ከመ ቀደምት ሐዋሪያት አምዳ ወድዳ ለዛቲ ቤተክረሰቲያን

  ReplyDelete
 42. ተስፋዬም ሆነ መሰሎቹ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የሚዘምቱት የእምነትም ሆነ የታሪክ ክርክር ስላላቸው አይደለም፡፡ ሀገሪቱ የቆመችባቸውን ተራዳዎች የመናድና እሴት አልባ የማድረግ ተልዕኮ ስላላቸው እንጂ፡፡ ይህ ተልዕኮ ደግሞ በዚህች በብዙ ቅዱሳን ጸሎት በታጠረች ሀገር ላይ ፈጽሞ የሚሳካ አይደለም፡፡ የሌለን ነገር የሚፈልግ አያገኝምና፡፡
  እግዚአብሄር ይባርክህ!!!!

  ReplyDelete
 43. ጻድቁ በቃል ኪዳናቸው ይርዱህ

  ReplyDelete
 44. ዲ/ን ዳንኤል ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ይሰጥልን በጣም ብዙ ነገር አስተማረከን፡፡ ዲላ እያለሁ ከአንድ የ‹‹ሰንበት ተማሪ›› አቡነ ተክለ ሃይማኖት እግራቸው የተቆረጠው ‹‹በጦርነት ነው›› የሚል ነገር ሰምቸ ያኔ እንደቀላል ነገር ነበር ያየሁት ነገር ግን………ዲ/ን ወ/ኢሱስ ከጎጃም

  ReplyDelete
 45. let us say TESFAYE go hell.... we never forget what u wrote about amahara.......

  ReplyDelete
 46. ዳኒ፤- ስለ ጥልቅ ጽሑፍህ እያመሰገንኩ፣ ስለ ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት ጉዳይ ባነሳኸው ላይ የአቡነ ተ/ሃይማኖት ገድል ራሱ ስለዚህ ጉዳይ ሳይጠቅስ አላለፈም፤፤ይኸውም በመጀመሪያ የቅ/ተ/ሃይማኖትን የዘር ሐረግ ይገልጽና ቀጥሎ በሌላ ምዕራፍ ሰለሞናዊ ላልሆነው የዛጉዌ ወገን 300 ዓመት የሰጠሁት ይበቃዋልና ሰለሞናዊ የሆነውን ይኩኖ አምላክን ቀብተህ አንግስልኝ ብሎ ጌታ ራሱ ቅ/ተ/ሃይማኖትን እንደላከው ያስረዳል፤፤ከዚህም ሌላ መንግሥት የሄደባቸውን ሰለሞናዊያን ስም ይዘረዝራል፤፤በሰማይም በምድርም ንግስና ከእግዚአብሔር መሆኑን እንዳለን፤፤ ዛሬ ያለው መንግስት ተዋግቼ በጀግንነቴ ሥልጣን ያዝኩ እነደሚለው ሳይሆን ጌታ መንግሥቱን ለወደደው ወገን እንደሚሰጥ እንረዳልን፤፤

  ReplyDelete
 47. ወይ ታሪክ እድሜ ይስጥህ

  ReplyDelete
 48. ወይ ታሪክ እድሜ ይስጥህ

  ReplyDelete
 49. እግዚአብሔር ይባርክህ ዲያቆን ዳንኤል፡፡ ለወደፊትም አንተም ብዙ እንድትጽፍልን እኛም ብዙ እንድናነብ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ ከጽሑፎችህ የተረዳሁት ትልቅ ነገር ክርስቲያን ነን የምንል ሁላችን የቅዱሳን አባቶችን ገድልና ታሪክ ለማወቅ ብዙ ብዙ ማንበብ እንዳለብን ነው፡፡ በስነጽሑፍ ተሰጥኦው እንወደው የነበረ ተስፋዬ ግን እውነት የዚህችን አገር ውድቀት ከሚመኙት እንደ አንዱ ሆኖ መርዙን በማር ለውሶ እያጎረሰን ከሆነ እግዚአብሔር ልቡና እንደዲሰጠው ልንጸልይለት ይገባል፡፡ ይህች አገር ግን በቅዱሳን አባቶች ጸሎትና በእግዚአብሔር ቸርነት ለዘለዓለም ትኖራለች፡፡

  ReplyDelete
 50. Egziabher hayelunena beretatun yeseteh....hulun akef meles...new..

  ReplyDelete
 51. Egziabher anten ena zerihin yibark Dn.Daniel Kibret

  ReplyDelete
 52. ዲያቆን ዳንኤል አንተ መባል ያልብህን በሙሉ ሁሉም አስተያየት ሰጪዎች ብለዋል። እኔ ምን ልበልህ ፨ የሀገር ሽማግሌ ፨ እግዚአብሔር ይጥብቅልን።

  ReplyDelete
 53. የእመቤታችን በረከት አይለይህ!!!!!!!

  ReplyDelete
 54. እንግዲህ ምን እላለሁ? አምላከ ተክለሃይማኖት እረጅም እድሜና ጤና ይስጥህ ወንድሜ!!

  ReplyDelete
 55. Yelele yemefelg menem ayezem
  Berta tsgawen yabezaleh
  Ke Atlanta.GA

  ReplyDelete
 56. እናንተም ጸልዩበት፡፡

  ReplyDelete
 57. በእዉነቱ ከሆነ ተስፋዮ አመሰግንሃለሁ፤ ባትሳሳት ንሮ ያለዉን እዉነታዉ ዲያቆን ዳንኤል መች ይጥፍልን ነበር??
  ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር እውቀትህን ይባርክ ረጅም ዕድሜና ጤና ይስጥህ

  ReplyDelete
 58. God is the only Almighty!!! Amen

  ReplyDelete
 59. በጎግግል ኣማካኝነትበዚሕ ሳምንት የተሰፋየ መፅሓፍ እጄ ላይ ገብቶ ኣንብቤው ኣለሁ የፍስሓ ፅዮን ፖለቲካ የሚለው ርእስ ብዕሮቹ በማሰረጃ እና ብጥናት ያልተረጋገጡ መሆናቸውን ባምንም ለብዙ ሰዎች ወዳልተፈለገ መንገድ የሚመራ በመሆኑ እረፍት ነስቶኝ ነበር መልስ ለመስጠት የሚያስችለኝ ጥልቅ እውቀትኣልኝ ብየ ስላላመንኩ ከሆነ ሰው ጋር ተነጋግረርእና ለዳንኤል ክብረት ለምን ኣንልክለትም እሱ በማስረጃ መልስ ሊሰጥበት ሰለሚችል በሚል ብሎግሕ ጋ ስንገባ ቀድመሀን መለስ ሰጥተሕበት ኣገኘን በእውነት ምን ያህል ደስ እንዳለን ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚኣብሔር ይባርክሕ

  ReplyDelete
 60. አማራው ከኦሮሞ፣ ኦሮሞው ከኦሮሞ፣ አማራው ከአማራው፣ትግራዋዩ ከአማራው፣ትግራዋዩ ከትግራዋይ፣ ትግራዋዩ ከኦሮሞው እርሰ በርስ ለማፋጀት በሚፅፋቸው መርዝ የተቀቡ መፅሐፎቹ የሚታወቀው ተስፋየ ገብረኣብ የኤርትራ ሰላይ መሆኑን አለማየሁ መሰለ በተባለ ኢትዮጵያዊ ‹‹አክቲቪስት›› መጋለጡን አውራምባ ታይምስ የተባለው ድረ ገፅ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡
  ተስፋየ ‹‹የስደተኛው ማስታወሻ›› የሚባል ሌላ አዲስ መፅሐፍ ለማሳተም እፍን ጭንቅ ሲል መሰንበቱን የሚታወቅ ቢሆንም የመፅሐፉ ህትመት መቋረጡን በፌስቡክ ገፁን ገልፀዋል፡፡ተስፋየ በፌስቡክ ገፁ የፃፈውን ማየት ያልቻላችሁ እንደሚከተለው ቃል በቃል አቅርቤላችኋለሁ፡፡
  “የስደተኛው ማስታወሻ” ህትመት ተቋረጠ...

  ReplyDelete
 61. Dn. Daniel, Geta Egziabher yekidusan Amlak Anten ena betesebochihn yitebik. Ye Agelglot zemenehn yabzalh. Mechereshahinm yasamrlih. Ke Misgana ena ke madnek wuchi minm kalat yelegnm. Yekomklachew Teklye Kedmewulh beneger hulu yejemerkewun yesachewun wudase yasfesimulih Egnam anbiben lemebarek yabkan. Selam hunlign wondme!!!!!

  ReplyDelete
 62. አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮ-ኤርትራ የመጀመርያ የጦርነት
  ሰሞን የተናገረውን እንዳስታውስ አደረገኝ፡፡ ያ የምድራዊው ትንቢተ-ኢሳያስ እንዲህ ብሎ
  ነበር፡- “ኢትዮጵያዊያንን እርስ በራሳቸው እንዲተላለቁ ለመቶ አመት የሚሆን የቤትስራ
  እሰጣቸዋለሁ::” ለተፈፃሚነቱም በብዙ መልክ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

  ReplyDelete
 63. የድንግል ልጅ አይለይሕ። በርታ!

  ReplyDelete
 64. ማንም ሰው ወደደም ጠላም ይህችን ቅድስት ሀገር ጠብቃ ያቆየችው ይህች ቤተክርስቲያን ነች፤፤ "የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ"
  ዳን በርታ እግዚአብሔር ይርዳህ !

  ReplyDelete
 65. Kale Hiwot Yasemah Dn. Daniel, Felegihin Eketelalehu.

  ReplyDelete
 66. DN Daniel God bless you. Dear all let us pray for Tesfaye he is in the hands of Satan.

  ReplyDelete
 67. he is spay for shabia, Tesfay.

  ReplyDelete
 68. God bless you Dani. Keep it up. Long live for you

  ReplyDelete
 69. Awesome article!
  May the Almighty god of St.Tekelehimanote be with you!

  ReplyDelete
 70. "ኦ! ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናአብየኪ" እንዳለ አባ ሕርያቆስ…እኛም እንላለን…ኦ! ዳንኤል ስለዚህ እናከብርሃለን እንጸልይልሃለንም…ሰይጣንን አሳፍረህልናልና፡፡
  ከጎንደር ልደታ

  ReplyDelete
 71. Dear bro Daniel , am so happy to read these .
  No words to add .
  May the almighty GOD , savior of Abune Tekle Haimanot , be with you .
  A/D

  ReplyDelete
 72. ሰላም ወንድም ዳንኤል። ተስፋየ የሚባለው ሰውየ ላቀረበው ትርኪ ምርኪ መልስ ስለሰጠህ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። እሱን ሰውየ አንተ ሳትነካው እግዚአብሔር ጥሎታል። በኢትዮጵያና በኃይማኖቷ ላይ እጁን ያነሳ ሁሉ ቅጣት አለበትና እሱም እነሆ ጽዋው ደረሰው። መልስ መስጠትህ መልካም ቢሆንም ያንተ አኪያሄድም ቢሆን ከተስፋየ አኪያሄድ ብዙ የተለየ አልነበረም። የሰነዘርካቸው አንዳናድ አስተያየቶች የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መሠረት ለማዛባት የሚሞክሩ ሆነው ነው ያገኜኋቸው። ጽሁፍን ሳነብ የተረዳሁት ነገር አነሳስህ የተስፋየን እኩይ ሥራ ለመቃወም ሳይሆን የተሳሳቱ መልእክቶችን ለማስተላለፍ እንደሆነ ነው። ልክ የኢትዮጵያ የኃይማኖቷ ጠላቶች የሆኑ የውጭ አገር "ምሁር" ነን ባዮች እንደሚያደርጉት በትንሹ የደገፉ አስመስለው በትልቁ መሠረቷን ለመናድ እንደሚሞክሩት ሆነህ ነው ያገኜሁህ። ለማስረጃነት የጠቀስካቸው የፈረንጅ መጻሕፍት ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሚነቅፉ ናቸው። አንተ ግን አንባቢ አያውቃቸውም ከሚል አስተሳሰብ ይመስላል በድፍረት መረጃየ ናቸው ብለህ ያቀረብካቸው። አቀራረብህ ሴኩላር መሠረትን የሚሻ መንፈሳዊነትን በሁለተኛ ደረጃነት የሚያይ ሆኖ ነው የሚታየው። የተሃድሶ ዝንባሌም አይበታለሁ። ኮኮቡ ምስል የዳዊት ምልክት መሆኑንስ እንዴት አወቅህ? ያገኜህበትን የመጽሐፍ ማስረጃ ልትጠቁመን ትችላለህ? ስህተቶችህን አንድ ባንድ ተንትኜ ብጽፍ ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን እንደማታወጣው ስለማውቅ ሌላ መንገድ መፈለግ ይሻለኛል አልኩ። ከዚህ ቀደምም የጻፍኩትን ስላላወጣህልኝ አሁንም ትደግመዋልህ። ከላይ ከጻፍካቸው ነገሮች ሁሉ ያለው አንድ እውነት የተስፋየ አስተያየት ስህተት ነው ያልከው ብቻ ነው። ለመነጋገር ከፈለግህ ግን ያንተ ባልሆነ በሌላ ብሎግ ላይ ለመነጋገር እንችላለን። ኃይለ ሚካኤል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Hailemichael, why dont you take the initiation and write your critics on some other blog? what you have said here is not strong for me. please take the lead and write what you feel, I hope Daniel will respond accordingly. In the mean time, we will learn more!!

   Delete
 73. ስደተኛው ማስታወሻ” የተባለውን የተስፋዬ ገ/አብ አዲስ መጽሃፍ “በብላሽ” ወስጄ አነበብኩት። መጽሃፉን በነጻ የበተነው እራሱ ነው ይላሉ። አንድ ሰው የለፋበትን ነገር በነጻ ሲሰጥ ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። በተለይ ደግሞ እንዲህ አይነት አወዛጋቢ መጽሃፍ ሲሆን ይበልጥ ያስጠረጥራል። ከዚያም አልፎ አንዳንድ ሰዎች የሚሉትን ያጠናክራል። ተስፋዬ ደግሞ አሳታሚዎቹ “ጫልቱ እንደ ሄለን” ብዬ የጻፍኩትን ምዕራፍ አውጣ ስላሉኝ ነው ይላል።
  ለማንኛውም ዛሬ ይህንን አወዛጋቢ መጽሃፍ ከሌላ ማእዘን ለመዳሰስ እሞክራለሁ። የተስፋዬን ስራዎች ከ-እስከ አንብቤአለሁ። ብዙ ቃለ መጠይቆቹን ሰምቼዋለሁ። በተደጋጋሚ ፓል ቶክ ላይ ሲያደንቁት፤ ሲያሞካሹት፤ ሲያፋጥጡት፤ ሲያበሻቅጡት እና ሲከሸክሹት አድምጫለሁ። የግል ድረ ገጹ ላይ የሚያትማቸውን ጽሁፎች ተሸቀዳድሜ አንብቤዋለሁ። በአላማው ሲጸና አይቻለሁ። ኮፍያ ሲቀያይር ታዝቤያለሁ። ሲገለባበጥ ተመልክቼዋለሁ። አሪፍ መልስ ሲሰጥ ሰምቻለሁ። ሲምታታበት አስተውያለሁ። ፈንጂ ሲረግጥ አይቻለሁ። እንደ ሀር ተለሳልሶ ሲያመልጥም ተገርሜያለሁ።
  ስለዚህም የተስፋዬ ጉዳይ በጥንቃቄ መታየት እንዳለበት አምናለሁ።
  ተስፋዬ “አሊጎሪካል” ጸሃፊ ነው። ማስተላለፍ የሚፈልገውን መልእክት በአሊጎሪ (ተምሳሌት) ይገልጻል። በዚህም የበአሉ ግርማ ተጽእኖ በደንብ ይታይበታል። በእርግጥ አሊጎሪ ጥሩ ዘይቤ ቢሆንም የተስፋዬ ግን ይበዛል። ሁሉን ነገር ተምሳሌት ማድረግ ያምረዋል። በእያንዳንዱ ትረካ ውስጥ ስለ መልእክቱ መጨነቁ ይታያል። ለመልእክቱ የበዛ ትኩረት በመስጠቱ የመጽሃፉን ርእስ የማይመጥን ትረካ አጭቆበታል። የስደትን ጉዳይ ችላ በማለት ብዙ ቅንጥብጣቢ አሊጎሪካል ታሪኮች አካቷል። ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያደርገው ሽግግርም ድምዳሜውን (conclusion) ቀድሞ ይዞ የሚደግፍበት ታሪክ የሚፈልግ አስመስሎታል። ታሪኩ ከመልዕክቱ ጋር አልገጥም ሲለው ደግሞ “የደራሲነት ስልጣኔን ተጠቅሜ አስተካክዬዋለሁ” ይላል። ለማንኛውም ብዙ ርእሶችን ቢያነሳም ማስተላለፍ የሚፈልገው መልዕክት ግን ከአራት ወይም ከአምስት የሚበልጥ አይመስልም። ከዚህ ውስጥ የማንነቱ ጥያቄ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

  1. የማንነት ጥያቄ
  የሰው ማንነት የሚገነባው በትውልድ አካባቢው ባህል (ቋንቋ፣ አለባበስ፣ አመጋገብ፣ ሥነ ጥበብ…) ነው። ተስፋዬ በደም ኤርትራዊ ቢሆንም ያደገው ቢሾፍቱ ነው። ስለዚህ የተስፋዬ ማንነት የተገነባው በቢሾፍቱ ባህል ነው። ተስፋዬ ከኤርትራዊነት ይልቅ ኢትዮጵያዊነቱ ከፍተኛ ነው። እንደዛም ቢሆን ግን የተስፋዬ ማንነት እስከ ዛሬ ድረስ በጣም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል። ኤርትራዊ ደም ስላለው ብቻ ብዙዎች አያምኑትም። “ኤርትራዊ ሆነህ ለምን ስለ ኢትዮጵያ ትጽፋለህ?” ተብሎ እስኪሰለቸው ተጠይቋል። በዚህ ምክንያት የማንነት ጥማት ያጋጠመው ይመስላል። አብዝቶ ስለ ቢሾፍቱ የሚጽፈው ከዚህ ጥማት የተነሳ መሆኑን መረዳት ይቻላል። ይህ የማንነት ጥማት በአብዛኛው ስደተኛ ዘንድ የሚያጋጥም ነው። የተስፋዬ ደግሞ የባሰ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ፓስፖርቱን በመነጠቁ ነው። በእርግጥ ፓስፖርቱን ቢያጣም ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንዳላጣ ለማሳመን የመጽሃፉን ሰባት ምዕራፎች ቢሾፍቷዊ አድርጎቸዋል።
  ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ ኢትዮጵያ የነፈገችውን ማንነት ከኤርትራ ለማግኘት ይጣጣራል። “የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ” መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው። ኢትዮጵያዊ አይደልህም ሲባል ኤርትራዊነቱን ማንቆለጳጰሱ አይገርምም። ለዚህም ይመስላል ኢትዮጵያን እና ኤርትራን በማወዳደር የተጠመደው። ውድድሩ ከታዕታይ ምስቅልቅል (inferiority complex) የመጣ ማካካሻ (coping mechanism) መሆኑ ነው። ይሄ ደግሞ በተስፋዬ ብቻ ሳይሆን በአብዛኛዎቹ ኤርትራዊያን ስደተኞች ዘንድ የተለመደ ሽምጠጣ ነው። ከዚህ ባሻገር ግን “የኤርትራ ሰላይ ነው” የተባለው ብዙም ውሃ አይቋጥርም። በእርግጥ የሚያውቀውን መረጃ ሁሉ ለወዲ አፎም እንዳስረከበ ግልጽ ነው። የወቅቱን መረጃ ግን ሊያገኝ አይችልም። ስለዚህ ሰላይ ነው ብዬ አላምንም።

  2. ኢትዮጵያ እና ኤርትራ
  ተስፋዬ ኢትዮጵያንና ኤርትራን በብዙ ነገሮች ያወዳድራል። አንዳንዴ እንደ ህጻን ልጅ ብሽሽቅ ውስጥ ይገባል። ለምሳሌ ኤርትራ ከደርግ የተገነጠለችው በሻእቢያ የውጊያ ብቃት እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገልጻል። ኢህአዴግ ባይኖር ሻዕቢያ ዘላለም መገንጠል አለመቻሉን ሽምጥጥ ያደርጋል። ይህንን ለማስረዳት በርካታ ታሪኮች ጽፎልናል።
  - የጄኔራል ታሪኩ ዓይኔን ግድያ በስማ በለው መረጃ ላይ በመመስረት “ከሻዕቢያ ጋር እንደራደር በማለቱ” እንደሆነ ሊያሳምነን ይሞክራል።
  - ውድድሩን በመቀጠልም “አጸደ አደዋ” የተባለች ታጋይ ታሪክ አንስቶ የህወሃት ሰራዊት የትም የወደቀ መሆኑን ለማሳየት ሲጠቀምባት፤ “ጥቁር ጽጌሬዳ” በሚለው ቀጣይ ምእራፍ ውስጥ ደግሞ የኤርትራዊቷን ወጣት ምቾች እና ውበት ያሳየናል።
  - እናት አገር ኢትዮጵያን “በአባት አገር ኤርትራ” ተክቶ አንድ ምእራፍ ሰጥቶ ያሳየናል።
  - ሁላችንም የምናውቀውን መለስ ዜናዊ ስል ኦሮማይ መጽሃፍ የሰጠውን “ትርጓሜ” በአንድ ምእራፍ
  አድምቆ ተርኮታል።
  - የንስር አሞራው ታሪክ እና የኦርዮሌዎቹ ታሪክ በማምጣት የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ጦር እንድሚያሸንፍ ሊያሳምነን ይጥራል።
  እነዚህ እና ሌሎች በርካታ ታሪኮች መተረክ የፈለገበት ምክኒያት ኢትዮጵያ የኤርትራን አይበገሬነት አምና መደራደር እንዳለባት ለማሳየት ይመስላል። ለነገሩ የሱማሊያዊው ስደተኛ ህጻን (ማሊክ) ታሪክም ተመሳሳይ ነው። ተስፋዬ ለማሊክ ኳስ ገዝቶለት እንዳታለለው ኢትዮጵያም ጥቂት ነገር በመስጠት የሱማሊያን ችግር መፍታት ትችላለች ይለናል። ሱማሊያ የሚለው ኦጋዴንን ይሁን ወይም ሞቃዲሾን አይገልጽም። የቀጠናው ችግር ግን ተስፋዬ እንደሚለው ቀላል አይደለም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተስፋየ ገብረአብ የሚፅፋቸው ነገሮች በጣም ያሳዝናሉ ስለኢትዮጵያ ጥሩ ነገር ፅፎ ኣያውቅም ምንጭ በሌለው ፅሁፉ ስለ ኤርትራውያን ጀግነነትና ስለኢትዮጵያውያንና ኢሃድግ አናሳናት ይፅፋል ለኔግን እነዚህ ቃላቶች አዲስ አይደሉም ከኤርትራውያን ጓደኞቻችን ጎሬቤቶቻችን እየሰማን ስላደግን ኤርትራውያን ጥሩ ጥሩ የሆነ ነገር የኤርትራ መሆኑን መጥፎ መጥፎ የሆነ ነገር እየለዩ የኢትዮጵያ እንደሆነ ከልጅ እስከ አዋቂ መናገር ይወዳሉ በቅዱሳን ጭምር ግን መሆን የለበትም ስለ ቅዱሳን ምንጭ የሌለው ፅሁፍ መፃፉ ደግሞ ይበልጥ አሳዝኖኛል ፡፡ ተስፋየ ግን በጥሩ ተንደላቆ ስላደገበት አገር አጉሩ ባይሆኑም ማለት (ኤርትራውያን አገርህ የዘርህ መገኛ ወይም በትግርኛ መቦቆል እንጂ የተወለድክበት አይደለም ብለው ስለሚያምኑ) ጥሩ ማሰብና መፃፍ ነበረበት ቢየ ባስብም ሰው የሚያስበው አንዳንዴ በተለይ ኤርትራውያን እንደ አደጉበት አካባቢ ሳይሆን እየተማሩ እንዳደጉበት ቤታቸው ስለሚሆኑ ለዚህም ምስክሩ ተስፋየ ብቻ ሳይሆን ብዙ ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉና ወደ ኤርትራ የተመለሱ ኤርትራውያን ጓደኞቼ የሚያደርጉትና የሚሉትን የነበሩ ትዝ ስለሚለኝ ነው ፡፡ ተስፋየ ገብረአብ መጀመሪያ መዕሃፉ ሳነበው ነበር ወዲያው ኤርትራዊ መሆኑን ያወቅኩት ኢትዮጵያ ቢያድግም ኤርትራዊ ስለሆነ የሚያደርገውና የሚፅፈው ልክ እንደሌሎች ኤርትራዊያን ነው ሰላይ አይሆንም ብየም አላስብም ሌሎች ኤርትራውያን ከተመቻቸላቸው ለኢትዮጵያ ከመሰለል ወደኋላ እንደማይሉ ሁሉ ምክንያቱ ኤርትራውያን በደምብ አውቃቸዋለሁኝ ተወልጀ ያደግኩን ኤርትራ (አስመራ) ውስጥ በመሆኑ አባቴም ጭምር ነው ተወልዶ ያደገውና እስከ እለተሞቱ አስመራ የኖረው አያታችን ነበር ድሮ በልጅነቱ ወደ ኤርትራ የመጣው እናቴም በልጅነታ ነበር ወደ ኤርትራ የመጣችው ግን አባታችን ይሁን እኛ ልጆቹ ኢትዮጵያ ባናውቀውም ሁሌ ኢትዮጵያውያን መሆናችን በኤርትራውያን እየተነገረን ስላደግን አገራችን የምንገባበት ጊዜ ሁሌ እንደናፈቀን ነበር ምንም ስለ ኤርትራ ጥሩ ነገር ተሰምቶን አያውቅም ትምህርት ቤት በተለይ ሸዕብያ አስመራ ከገቡ በሃላ ጓደኞችህ የሚጠይቁህ እነሱ መበቆል ይሉታል በትግርኛ የዘርህ መገኛ የት እንደሆና አባትህ ወይ አያትህ ከየት እንደመጣ ነው ምክንያቱ በኤርትራውያን አባትህ ተወልዶ ያደገበት ወይም አንተ የተወለድክበት ሳይሆን አገርህ የዘር ግንድህ መገኛ ነው ብለው ስለሚያስቡ ይህ ጥያቃ በትምህርት ቤት ይሆን ሌላ ቦታ ሁሌ የምትጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ነው ታድያ ያነ ልጅ ሁኘ ሁሌ ከነሱ መለየቴ ያስጨንቀኝ ነበር አንዳንዴም አያታችን ወደ አስመራ መምጣቱ አማርር ነበር ፤ ቡዙ ኤርትራውያን ጓደኞች ቢኖሩኝንም ኤርትራውያን ከህፃንነትህ ጀምረም ዘራችን እየቆጠሩ እኛ ኢትዮጵያውያን መሆናችን የነሱ ዘር ከኛ ዘር እንደሚበልጥና ኤርትራ በስደት የምንኖርበት አገር እንጂ አገራችን እንዳልሆነኝ ይነግሩን ስለነበር የኛ ህልምም ኢትዮጵያ መምጣት ነበርና እንደምንም ግማሹ የቤተስብ ክፍል ከኢትዮ ኤርትራ ጣርነት በፊት ግማሻችንም ከጦርነቱ በሃላ ኢትዮጰያ ለመምጣት ችለናል ቡዙ ሌሎች እንደኛ በዘራቸው ኢትዮጵያዊያን ሁነው እነሱም ቤተሰቦቻቸውም ኤርትራ ተወልደው ያደጉት ቤትና ንብረት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ቤትና ንብረታቸው እንዳይነጥቃቸው በተወለዱበት የሁለተኛ ዜጋ የኤርትራ ዜግነት ቢሰጣቸውም የዘር ግንዳቸው በመታወቂያቸውና በሌሎች የኤርትራ ዶኩመንቶቻቸው ስለሚሞሉ ሁሌ እንደተገለሉ ነው በህግደፍ ስብሰባም እንዲገቡ አይፈቀደላቸውም ለኤርትራ የሁለተኛ ዜጋ ዜግነት ያገኙት ነገር ቢኖር እንደ ሌሎች ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን500 ናቅፋ እየከፈልክ መኖር ብቻ ነው ምክንያቱም ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በኋላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ድሃም ሆነ ሃፍታም ለመኖር በዓመት 500 ናቅፋ መክፈል ይጠበቅበታል የሚከፈል ከሌለውም እስርቤት ይበሰብሳታል እንጁ አይፈታም ስለዚህ የቀረላቸው ቢኖር ሳይከፍሉ መኖር ብቻ ነው ለዚህም ሁሌ እንደተቆጩ ነው ድሮም አላመኑበትምና እኛ ግን ንብረታችንና ቤታችን ሳንሸጥ ከኢትዮ-ኤረትራ በሃላ የኢትዮጵያውያን ቤት መሸጥ ይሁን ከባንክ ገንዘብ መውጣት ስለማይቻልና እናታችን ከኢትዮ-ኤርትራ በሃላ ስለመጣች ንብረታችን እነሱ ጋር ቢቀርም እኔ ይሁን ወንድሞቸ ኢትዮጵያ አገራችን ያስገባን አምላክ ሁሌ እንዳመሰገን ነው ለኤርትራውያን ግን ክፉ ቢሆንም ክፉ ተመኝተን አናውቅም ፡፡ የተስፋየ ነገር ግን በጣም ይገርመኛ ኢትዮጵያውያን ከኤርትራውያን በጣም ይለያሉ ምክንያቱ ሌሎች ህዝቦች በተለይም ለኤርትራውያን እንደባእድ አርቆ አያዩም እዚህ ላደጉት ኤርትራውያን እንደኢትዮጵያውን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍቅር ይለግስላቸዋል እንደኛ ልዩና ከሌላ ቦታ እንደመጣንና የበታችነት እንዲሰማን እድርገው ኤርትራውያን አሰቃይቶ እንዳሳደጉን አይደለም ያሳደጉዋቸው ኤርትራውያን መሆናቸው ራሳቸው በጉራቸውና ኤርትራውነት ልዩ ስለሚመስላቸው እንዲታወቅላቸው በማድረግ ነበር ብዙዎች ወደ አገራቸው ኤርትራ የተላኩት ኢትዮጵያ ያደጉት ኤርትራውያን አስመራ ተመልሰው የመጡ ኤርትራውያን ጓደኞች ነበሩኝ አስተሳሰባቸው ግን እንዳደጉበት አካባቢ ሳይሆን እንዳደጉበት ቤተሰብና ዘር ነው ልክ እንደ ተስፋየ ገብረአብ ፡፡ በዚህ ጊዜም ብዙዎች ኤርትራውያን አገራቸው ምቾት ስላጡበት ወደ ኢትዮጵያ እየመጡ ነው ቡዙ ጓደኞቻችን ወደኛ ቤት ይመጣሉ እኛ ግን በኤርትራውነታቸው እንዲሰቀቁ ማድረግ አንፈልግም አንዳንድ ጊዜ ግን ምላሳቸውና ትዕቢታቸው አይጣል ስለሆነ እዚህ መጥተውም ምንም አይቀየሩም ግርም ይሉኛል ፡፡ በኤርትራውያንና በኢትዮጵያውያን በጣም ትልቅ የአስተሳሰብ ልዩነት አለ ኢትዮጵያውያን ለኤርትራ እንደ ጥሩ ጎረቤት ብሎም ከዛ በላይ ያስባሉ የኤርትራውያን ጥሩ ነገር ያደንቃሉ ክፉ ነገር በነሱ ሲደርስ ያዝናሉ በድለው ሂደውም ተመልሰው መጥተው እዚህ ቢኖሩ ምንም አይመስላቸውም የኤርትራውያን አስተሳሰባቸው ግን የተገላቢጦሽ ነው ለዚህም ነው ለኔ እዚህ ለምለም አገር ተመልሰው መለመናቸው ቢያስደስተኝም ተገላግለናቸዋል ብለን እዚህ መመለሳቸው እንደገና ግፋቸው ትዝ ስለሚለኝ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ኤርትራዊ መጥቶ ባላይና አገራቸው ቢችላቸው ደስታውየ አልችለውም ይሀ ሳስብ ግን እንደነሱ የሆንኩት ይመስለኝና ክፉ ለራሱ ደግ ለራሱ ነው ምን አገባኝ እላለሁኝ ሆኖም ግን ኤርትራ ሁለተኛ ሰላም ሆኖ ኢትዮጵያዊያን እዛ ሂደው እንዲኖሩ አልመኝም ለኢትዮጵያዊ ከነሱ ጋር መኖር ምን ማለት እንደሆነ ስለማውቀው፡፡ ስታስበው ግን ለካ ደግነት ለራስህ ነው ትላለህ ለዚህም ነው እግዚአብሄር ኢትዮጵያ የባረካትና ከክፉ የሚጠብቃት እላለሁኝ ለየዋህ ህዝቦችዋን ሁሌም ይጠብቃቸዋል ምንም ቢወራ ምንም ቢሰራ ከሁሉም የእግዚአብሄር ሃይል ስለሚበልጥ የእሱ በረከት ብቻ አይለየን እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን ፡፡

   Delete
  2. Betam yegeremegn neger binor ke topic weteh mawrath new. migermh neger ene tewelije yadekut mekele new ..be Ertrawnete yederesebgn shigr ena mekera bawerah, yante mnm aydelem. ezim ezam be politica Mknyat sew tebedlewal yalefe ybkan blen fkr mesbek yshalenal. America na Japan yesalefut tornet restew ykr sletebabalu new ezi dereja yederesut. lemn egnas demachin and, quamquachin and, smachin habesha. are ybkan

   Delete
 74. 3. የጫልቱ ግርግር
  ተስፋዬ እንደሚለው ከሆነ መጽሃፉ በነጻ የተበተነው በምእራፍ ሰባት ምክንያት ነው። በእውነቱ “ጫልቱ እንደ ሄለን” የሚለው ምእራፍ እንዴት አዋራ ሊያስነሳ እንደቻለ አልገባኝም። ሁላችንም ተመሳሳይ ታሪኮችን እናውቃለን። እንዲህ አይነት ታሪክ ተፈጽሞ አያውቅም የሚል ሰው ገጥሞኝ አያውቅም። ግን በደፈናው ለምን ጻፈ የሚል ተቃውሞ በብዛት አንብቤያለሁ። የጫልቱ ታሪክ መታተሙ በሁለት ምክንያት ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ። የመጀመሪያው ሃሳብ በነጻነት እንዲገለጽ ስለምፈልግ። ሁለተኛው ችግሮችን በማለባበስ ትክክለኛ መፍትሄ ይመጣል ብዬ ስለማላምን ነው።
  በእርግጥ የጫልቱ አይነት ችግር በዚህ ዘመን እጅግ ቀንሷል። ታዲያ ተስፋዬ ለምን ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ ሊጽፈው ፈለገ? ታሪኩ ከስደተኛነቱ ጋር የሚያይዘው ምንም ጉዳይ የለም። ይህንን ታሪክ በመጽሃፉ ውስጥ እንዲካተት የፈለገበት ትልቅ ምክንያት እንዳለው አስባለሁ። ከነዚህም አንደኛው ተስፋዬ እራሱን እንደ ኦሮሞ ስለሚቆጥር፣ የኦሮሞን ችግር ማስተጋባት እንዳለበት በማመኑ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በፊት ለሰራው ስራ በውጪ የሚኖሩ የኦሮሞ መብት ታጋዮች “ኦቦ” የሚል ማእረግ እንደሰጡት ነግሮናል። በተጨማሪም ከተስፋዬ አጻጻፍ ተነስተን ጫልቱን በገሃዱ አለም ብንፈልጋት የምናገኛት ይመስለኛል። የጫልቱን ታሪክ ተስፋዬ በደራሲ ብእሩ እንደለወጠው ጽፎዋል። ይህም ማለት ጫልቱ በዚህ ዘመን ያለ ሰውን ታሪክ እንድትወክል ተፈልጓል ማለት ነው። ከዚህ በመነሳትም የጫልቱ ሚደቅሳ ታሪክ፤ የብርቱካን ሚደቅሳ ታሪክ እንደሆነ መገመት ይቻላል። ምክንያቱም ብርቱካን ኦሮሞ መሪ ሆና የአማራ ማንነት እንደሸፈናት ጽፎ አንብቤያለሁ። መቼም ተስፍሽ “Conspiracy theory” በጣም ይወዳል። የ”ሰው ለሰው” ድራማ መሪ ተዋናይ የሆነው አስናቀ፤ መለስን የሚወክል ነው ሲል ከርሞ ነበር። ወዲያው ግን የአስናቀ ሚስት አዜብን አትመስልም በማለት ነገሩን አፍርሶታል።

  4. የታሪክ እና የሃይማኖት ክለሳ
  ተስፋዬ በአዲሱ ማስታወሻው አይነኬ አርዕስቶችን አንስቷል። ማንሳት ብቻ ሳይሆን ዘርጥጧቸዋል። ታሪክ እና ሃይማኖትን በተመለከተ ጥልቅ ጥናት ቢያስፈልግም ተስፋዬ ግን በድፍረት ብቻ ተጋፍጦታል። ይህ ትክክል አይመስለኝም።
  የአቡነ ተክልዬን ገድል መሰረት የሌለው ነው ለማለት ሞክሯል። በዛም ሳይገደብ የፕሮቴስታንትን “ጌታ ተናገረኝ” የሚሉት ከህሊናቸው ጋር እያወሩ ነው ብሏል። በእርግጥ “የፍቅር በለጠ” ታሪክ በጣም አስቂኝ ነው። የፍቅር እየሱስ “ስለ ቁሳቁሶች ዋጋ ለመንገር የሚሯሯጥ የንግድ ወኪል” ይመስላል ብሏታል። እውነትም እንዲህ አይነት አማኞች ያሉ ይመስለኛል።
  በተጨማሪም እኛ ኢትዮጵያዊያን ስለ አካል ጉዳተኞች ያለንን አመለካከት በሚገባ ተችቶበታል። “የጨለለቃ ዝይ” እና “ደስተኛ ዝይ” በሚለው ጽሁፉ ውስጥ ይህንን በደንብ ማየት ይቻላል።
  ተስፋዬ ታሪክን ከአፈ-ታሪክ እያደበላለቀ ሊጋግረው ሞክሯል። እነዚህን ርዕሶች መፈተሹ ባልከፋ ነበር። ሆኖም ግን በጥልቅ ጥናት ላይ ተደግፎ እና ማስረጃውን አደራጅቶ ቢሆን ምንኛ ጥሩ በሆነ ነበር።
  እነዚህ ሁሉ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች እንደ ችግር ተይዘው የበለጠ ጥናት ሊደረግባቸው እንደሚገባ የተስፋዬ መጽሃፍ ጥሩ ማመላከቻ ነው።
  መጀመሪያ ባሳተመው “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” መጽሃፉ ላይ ላይ የነቆረውን የኢትዮ-ሚድያ ባለቤት አብርሃ በላይን ለመካስ እዚህ ግባ የማይባል የራያ ላይ ገጠመኝ በአንድ ምእራፍ አትሟል። እጅ መንሻ ካልሆነ ጥቅም የለውም። ከዚህም ሌላ በመጀመሪያ መጽሃፉ “ሙት” ብሎ ስላላገጠባቸው፤ ሁለተኛ መጽሃፉን በኢንተርኔት በተኑብኝ ካላቸው የኢህአፓ አባላት ጋር እሰጥ አገባው ቀጥሏል። በዚህ መጽሃፉ ውስጥ ኢህአፓን “ኢሃባ” በሚባል ውሻ መስሎ አቅርቦታል። “ኢሃባ” መልኩ የማይለይ የሰፈር ውስጥ ልክስክስ ውሻ ነው ይላል።
  በእርግጥም ተስፋዬ በዚህ መጽሃፉ “ፈንጂ” ረግጧል። ይህ ጉዞው የት እንደሚያደርስው ወደፊት የምናየው ይሆናል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. I dare say, it is a very nice observation

   Delete
 75. ተስፋየ የበላበት አገር ታሪክ ለማጥፋት ለምን እንደሚጨነቅ ይገርመኛል አሁን ደሞ በሃይማኖት መጣ ድሮስ ከኤርትራዊ ምን ይጠበቃል ፣ ለምን ታሪክ ካለው ስለ አገሩ ስለ ኤርትራ አይፅፍም ስለ ኢትዮጵያውያን የማያውቀው ከሚቀባጥር እሱ በፃፈው ምንጭ በሌለው አሉባልታ መቼም የኢትዮጵያውያን
  ታሪክ አይቀየርም ምክንያቱ ተስፋየ ገብራአብ የዞረበት ፀረ ኢትዮጵያዊያን ኤርትራዊ መሆኑ ሁሉ ስለሚያውቀው የበላበት ወጪት ሰባሪ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ke Eritrawi mn ytebekal aybalm. Do u hv a stereo type problem. I guess so. yand sew opinion mimeleketew sewun enji hager aydelem.

   Delete
 76. በመጀመሪያ ምስጋና
  ዲ/ን ዳንኤል ለተስፋዬ አሉባልታ የሰጠኸው በማስረጃ የተደገፈ ምሁራዊ ምላሽ አደንቃለሁ። ምንም እንኳን ተአማኒነት ያላቸው ማስረጃዎችን ሳይጠቅስ ትልቅ መደምደሚያ ላይ መድረሱ ከቁም ነገር የሚገባ ባይሆንም የዋህ አንባቢያንን ሊያደናግር ስለሚችል/የተስፋዬ አላማም ይህ ይመስለኛል/ ይህን የመሰለ በማስረጃ የተደገፈ ምላሽ መስጠቱ ነገሩን ለሚጠራጠሩ እንዲያረጋግጡ እድል ይሰጣልና ይበል የሚያሰኝ ነው።
  በመቀጠልም
  በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ከተስፋዬ ባልተናነሰ አንድ ፈንጅ ያፈነዳህ ይመስለኛል። ይኸውም የሰሎሞናዊ ስርወ መንግስት claim ማስረጃ የለውም መደምደሚያ/በገደምዳሜም ቢሆን/። እጠቅሳለሁ ''ለኢትዮጵያ ነገሥታት ግን ራሳቸውን ከኢየሩሳሌምና ከቅድስት ሀገር ጋር ማያያዝ የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ረገድም የዛግዌ ነገሥታት ሰሎሞናውያን የማይሆኑበት ምክንያትም የለም፡፡ እንዲያውም ለሰሎሞናዊነቱ ከኋለኞቹ ነገሥታት ይልቅ የዛግዌ ነገሥታት ይቀርባሉ፡፡''
  ይህ መደምደሚያ በዚህ አያበቃም። በመጽሐፍ ቅዱስ፤በሌሎች መጻሕፍት እና በትውፊት ስለ ሶሎሞንና ስለንግሰተ ሳባ ግንኙነት፣ ስለ ዳዊት /ስመ መንግሰቱ ቀዳማዊ ምኒልክ/፣ስለ ኦሪት እምነት መቀበላችን ያለንን ታሪካዊ መረዳት እንድንፈትሽ የሚጋብዝ ነው። ይህ ነገር የበለጠ ማብራሪያ የሚሻ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ሌላውም እንደ እኔ ተረድቶት ሊን ስለሚችል ምላሽ ያሻዋል።

  ReplyDelete
 77. Abune teklehaymanot yrdah. Kalehiwot yasemaln.

  ReplyDelete
 78. What a great Article May God bless you our brother Dn Daniel. I would like to mention about debrelibanos ze shimejana. Shimejana is about 20km away from debrelibabos also,it's a rich farming soil, and a historical place of Metera mountain and Quhaito. so from m experience it's not the write name to call ze shimejana. debrelibanos ham is the write name to call bcz It's located in southern part of Eritrea in a small village named Ham.

  ReplyDelete
 79. ጠላታችን ዲያብሎስ የዘመኑን መጠናቀቅ ተረድቶ በጥድፊያ ነፍሳትን ወደ ሲኦል ይዞ ለመውረድ በሚጣደፍበት በዚህ ጊዜ ስለታሪክ የምትነታረኩ እናንተ እነማን ናችሁ? አረ እባካችሁ እግዚአብሄርን መፍራትን ለሌላው የምታስተምሩ ኢትዮጵያውያን አዚም ያደረገባችሁ ማነው? ታሪክ ነው ወይስ ክርስቶስ ከጨለማ የሚያወጣው ብርሃን? እናስተውል በጨለማ የሚኖረው ሕዝብ ክርስቶስን ያወቁትንና የዳኑትን መገለጥ፣ በእውቀትና በክርስቶስ ክብር መገለጥ፣ በፀጋው ተፅእኖ የአጋንንትንና የጉስቁልናን ተፅእኖ ከላያቸው በማራገፍ ወደ ዘላለም እረፍት ይገቡ ዘንድ በተስፋ በሚጠብቅበት ወቅት እናንተ የታሪክ ጠበቃ ሆናችሁ ቆማችኋል፤
  አዎን አውቃለሁ ይህንን ስታነቡ የታሪክ ጠበቆች ወዲያ በል! ትላላችሁ፡፡ የክርስቶስ መልእክተኞች ደግሞ አዎን መንገዱን ስተናል በዚህ ጉዳይ መነጋገር ክርስቶስን ከማሰደብ በቀር ዋጋ የለውም ብላችሁ ትወጣላችሁ፡፡
  ከሁሉ የሚገርመው ወንጌልን እንደ ልብሳቸው ጥንቅቅ አድርገው የለበሱ አገልጋዮች አውቀው እንዳላወቁ አስከመቼ እንደሚሸሹ ያልገባኝ ነው፡፡ ምናልባት እንዳያረጅባቸውና ከላያቸው አልቆ ባዶአቸውን እንዳይቀሩ እሰጋለሁ፣ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete