Wednesday, November 27, 2013

የሙሴ እናት

እሥራኤልን ዐርባ ዓመት በበረሃ የመራ፣ ፈርዖንን ድል የነሣ፣ የኤርትራ ባሕርንም ለሁለት እንደ ድንጋይ የከፈለ ሰው ነው ሙሴ፡፡ እርሱን በተመለከተ አያሌ መጻሕፍትን ጽፈዋል፣ ፊልሞችን ደርሰዋል፣ ብዙዎችም በእርሱ ስም ተጠርተዋል፡፡ ሕዝብን ከባርነት የማውጣት፣ ለሕዝብ ብሎ የመከራከር፣ ለሕዝብ ብሎ ራስን የመሠዋት፣ ሕዝብን ከራሱ በፊት የማስቀደም፣ ሕዝብን በትዕግሥትና በጥበብ የመምራት፣ ለሕዝብ ብሎ ተከራክሮ ድል የማድረግ ተምሳሌት ነው - ሙሴ፡፡
ሙሴ ከወገኖቹ ጋር የኖረው ከተወለደ እስከ ሦስት ወር እድሜው ብቻ ነው፡፡ ያ ጊዜም ቢሆን ወገኖቹ በግብጻውያን እጅ ከባርነት በከፋ ስቃይ ውስጥ ገብተው የሚንገበገቡበት ጊዜ ነው፡፡ እንኳን ሌላውን ዓይነት ነጻነት ቀርቶ ልጅ ወልዶ የማሳደግ መብት እንኳን አልነበራቸውም፡፡ በተለይም ልጁ ወንድ ከሆነ፡፡ በምድርም ላይ እነርሱን ሊመለከት፣ ሊታደግና ሊራዳ የሚችል አንዳችም ኃይል አልነበረም፡፡ ዓለም እንደ ወስከንቢያ በላያቸው ላይ ተደፍታባቸው ነበር፡፡
ሙሴ ለዐርባ ዓመታት ያህል የኖረው በፈርዖን ቤተ መንግሥት ውስጥ የፈርዖን ልጅ ተብሎ፣ ግብጻዊነቱ እየተነገረው ነው፡፡ የተማረው የግብጽን ጥበብ፣ የበላው የግብጽን ምግብ፣ የሚያውቀው የግብጽን ቋንቋ፣ የኖረው ከግብጻውያን መኳንንትና መሳፍንት ጋር፣ የሚያየው የግብጻውያንን አማልክት፣ የተወዳጀው ከግብጻውያን ጠንቋዮችና አስማተኞች ጋር ነበር፡፡


ሙሴ የኖረበት የኑሮ ደረጃ ወገኖቹ ከነበሩበት የኑሮ ደረጃ እጅግ ከፍ ያለ ነበር፡፡ እርሱ በመኳንንት ወግ፣ በቤተ መንግሥት፣ ችግር የሚባል ነገር ሳይነካው፣ ግፍ የሚባል ነገር ሳይደርስበት፣ መብቱ በሚገባ ተጠብቆ፣ ከቅንጦትና ከድሎት አንዳች ሳይጎድልበት፣ የፈርዖን የልጅ ልጅ እየተባለ የኖረ ሰው ነበር፡፡ በተቃራኒው ወገኖቹ ደግሞ ሰው ሊደርስበት የሚችለውን የመጨረሻ መከራ እየተቀበሉ፤ ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነው ነበር የሚኖሩት፡፡ ህልውናቸው በሌሎች ፈቃድ እየተወሰነ፣ ፈንግል እንደያዘው ዶሮ ሞታቸው የሰዓታት ጉዳይ እየሆነ፣ መኖር ራሱ ቅጣት ሆኖባቸው ነበር የሚንገፈገፉት፡፡
ሙሴ እንዲህ በምቾትና በቅንጦት፣ ችግርን በጆሮው እንኳን ሳይሰማት አድጎ፣ የቤተ መንግሥቱን ቅምጥል አጣጥሞ፣ በፈርዖን ዕቅፍ ተቀምጦ - በዐርባ ዓመቱ ግን የወገኖቹ ነገር ያንገበግበው፣ ግፋቸው ይሰማው፣ መከራቸው ያመው፣ ስቃያቸው ያቃዠው፣ ሕመማቸው ያንቀጠቅጠው፣ ሞታቸው ዕረፍት ይነሣው ጀመር፡፡ እርሱ በቤተ መንግሥት ቢቀመጥም ልቡ ግን ከቤተ መንግሥቱ ወጥቶ ግፍ ከሚደርስባቸው ወገኖቹ ጋር ግፍ ይቀበል ጀመር፤ እርሱ ከፈርዖን ማዕድ ቢሰለፍም፣ ልቡ ግን ከወገኖቹ ጋር ይራብ ጀመር፡፡ እርሱ በሐር ልብስ ቢሞቀውም፣ ኅሊናው ግን ከወገኖቹ ጋር ተራቁቶ ይበርደው ነበር፤ እርሱ በሥልጣን ላይ ቢቀመጥም፤ ኅሊናው ግን ከወገኖቹ ጋር ለባርነት ተላልፎ ተሰጥቶ ይገረፍና ይታሠር ነበር፡፡ እርሱ ንጉሣዊ ሕይወትን ቢያጣጥምም፣ ልቡ ግን ከወገኖቹ ጋር ይሞት ነበር፡፡
ለዚህም ነበር አንድ ቀን ወደ ወገኖቹ ሲወጣ አጋዥ አልባ መሆናቸውን ያየ፣ ለግፍ ተላልፈው የተሰጡ መሆናቸውን ያጠና፣ የእነርሱ ሕይወት እንደ ጢንዚዛ ሕይወት ባለቤት የለውም ብሎ ያሰበ ግብጻዊ አንዱን ዕብራዊ ሲመታው ያየው፡፡ ለተመታው ዕብራዊ እርሱ አመመው፡፡ እርሱ የዚህ ግፍ የሚፈጸምበት ማኅበረሰብ አካል መሆኑን አመነ፡፡ ስለዚህም ታዳጊ ለሌለው ታዳጊ ለመሆን ወሰነና በራሱ ላይ ሞት ፈርዶ ያንን ግብጻዊ መታው፡፡ ልቡ ዐርባ ዓመት ከኖረበት ቤተ መንግሥት ሸፍቶ ሦስት ወር ወደኖረበት የእሥራኤላውያን የድህነት መንደር ገባ፡፡
እንዴት? ነው ጥያቄው፡፡ እንዴት?
ሙሴን ማን ነው ያስሸፈተው? ማንነቱን ሳይረሳ ዐርባ ዓመት በፈርዖን ቤተ መንግሥት ያኖረው ማነው? ከድሎቱ ይልቅ የወገኖቹን ስቃይ እንዲመርጥ ያደረገው ማነው? ሰዎች ለአንድ ዓመትና ለሁለት ዓመት ከሀገርና ከወገን ርቀው ባህላቸውንና ቋንቋቸውን ይረሳሉ፣ ማንነታቸውንም ይጥላሉ፡፡ እርሱ ግን ዐርባ ዓመት በፈርዖን ቤተ መንግሥት ሲኖር ለምን ማንነቱን ጠብቆ ኖረ? አንዳንድ ሰዎች ምቾትና ድሎትን ካገኙ፣ ከከበሩና ከተሾሙ ሀገራቸውን፣ ሕዝባቸውንና ወገናቸውን አሳልፈው ለመስጠት ዝግጁ ናቸው፡፡ ሙሴ ግን እምቢ አለ፡፡ እነርሱ ከበሉ ሕዝባቸው የበላ፣ እነርሱ ሲሾሙ ሕዝባቸው የተሾመ፣ እነርሱ ሲያገኙ ሕዝባቸው ያገኘ የሚመስላቸው ባለ ሥልጣናት ብዙ ናቸው፡፡ ሙሴ ግን ከወገኑ ተለይቶ ያገኘው ክብርና ምቾት፣ ሥልጣንና ሀብት ቆረቆረው እንጂ አልተስማማውም፤ ከእርሱ ድሎት ይልቅ የወገኑን መከራ መረጠ፡፡
መንግሥቱ ለማ፡-
የተለመደ ነው የመጣ ከጥንት
ከተጠቂው መራቅ አጥቂን መጠጋት
እንዳሉት የሀብታም፣ የባለ ሥልጣን፣ የታዋቂ ሰው፣ የባለ ጊዜ፣ የከበረ ወገን፣ የሚፈራና የሚከበር ሕዝብ ወገን ነኝ፣ ዘመድ ነኝ፣ አባል ነኝ ማለት ከጥንትም የነበረ ነው፡፡ የአጥቂው ወገን ሆኖ ከተጠቂው ጋር መቆም፣ የጨቋኝ ወገን ሆኖ ከተጨቋኝ ወገን መቆም፣ የክቡራን ወገን ሆኖ ከተዋረዱ ጋር መሰለፍ፣ የገፊዎች ዘመድ ሆኖ ከተገፊዎች ጋር መወገን፣ የሀብታሞች አካል ሆኖ ከድኆች ጋር መሰለፍ፤ የሹመኞች ቤት ሆኖ ለተራው ሕዝብ ዘብ መቆም ግን ብዙም የማይገኝ እንደ አልማዝ ብርቅ የሆነ ነገር ነው፡፡ ታድያ ሙሴ ይህንን ከየት አገኘው?
የሙሴ እናት ሙሴን በቤቷ ለመደበቅ የቻለችው ለሦስት ወራት ብቻ ነው፡፡ በዚያ ዘመን ሲወለድ ወንድ መሆኑ የታወቀ ዕብራዊ ሁሉ እንዲገደል በፈርዖን ዐዋጅ ወጥቶ ነበርና፡፡ የጨነቃት እናት መላ አታጣምና ዓባይ ወንዝ ወስዳ በሳጥን አድርጋ ጣለችው፡፡ የጣለችበት ቦታ የፈርዖን ሴት ልጅ ገላዋን የምትታጠብበት ቦታ ነበርና የፈርዖን ልጅ ሳጥኑን አየችው፡፡ ስትከፍተው የሚያምር ወንዝ ልጅ አገኘች፡፡ አምላክ የሰጠኝ ነው ብላ ወሰደችው፡፡ የሙሴ እናት ብልሃትና ጀግንነት ከዚህ ይጀምራል፡፡ እርሷ ባትኖር ኖሮ ሙሴ ከእነዚያ ሁሉ ሟች ሕጻናት ተለይቶ ባልተረፈ - በኋላም ታሪክ ባልሠራ ነበር፡፡
እናቱ ሙሴን ዓባይ ወንዝ ላይ ሰትጥለው እኅቱ መጨረሻውን እንድታይ ልካት ነበር፡፡ የፈርዖን ልጅ ሙሴን ከባሕር አውጥታ(‹ሙሴ› ማለት ከባሕር የወጣ ማለት ነው) ሞግዚት ስትፈልግ የሙሴ እኅት እናቱን ሞግዚት አድርጋ አመጣችላት፡፡ እናቱም ሞግዚት ሆና ሙሴን አሳደገችው፡፡ በፈርኦን ቤተ መንግሥት ውስጥ በእናቱ ሞግዚትነት ነበር ያደገው፡፡ ሁለተኛው ብልሃቷ ይሄ ነው፡፡ ሙሴ ሲያድግ እናቱ እውነቱን እየነገረችው ነው ያደገው፡፡ ‹‹አንተ በፈርዖን ቤተ መንግሥት ብትኖርም ግብጻዊ ግን አይደለህም፤ አንተ በምቾት ብትኖርም፣ የሚሰቃዩት የእሥራኤላውያን ወገን ነህ፤ አንተ የግብጽን ቋንቋ ብታጠናም ቋንቋህ ግን ዕብራይስጥ ነው፡፡ እዚህ ያገኘኸውን ልምድና ዕውቀት፣ሥልጣንና ክብር፣ ከሞት የመትረፍ ዕድል ወገኖችህን ነጻ ለማውጣት ተጠቀምበት፡፡ ይህ የምታየው ሕዝብ እንዲህ አልነበረም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነበር፣ ታላቅ ሕዝብም ነው፡፡ የአሁኑን መደኽየት፣ የአሁኑን መዋረድ፣ የአሁኑን መገፋት፣ የአሁኑን መጨቆን አትይ፡፡ ነገ ታሪክ ይለወጣል፡፡ አንተ ዛሬ ይህችን ክብርና ሥልጣን፣ ምቾትና ድሎት አገኘሁ ብለህ ከወገንህ ብትርቅ ታሪክ የተለወጠ ዕለት አንተም ስትረገም፣ ስትዋረድና ስትወቀስ ትኖራለህ፡፡ አንት ባታየው ዐጽምህ ይዋረዳል፡፡ ዛሬ ግን ከተገፉትና ከተዋረዱት ወገን ሆነህ ታሪክ ሲለውጥ አብረህ ብትሠራ ስምህ በወርቅ ቀለም ይጻፋል› - እያለች አስተማረችው፡፡
ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡ በሙሴ ውስጥ ያለችው፣ ከፈርዖን ጋር የተከራከረችው፣ ቤተ መንግሥቱን ጥሎ ለወገኑ ሲል በረሃ እንዲንከራተት ያደረገችው፣ ባሕር እንዲክፍል ያበቃችው፣ የሕዝቡን ስድብ፣ ማጉረምረም፣ ሐሜትና ዐመጽ ችሎ ሕዝቡን እንዲመራ ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡፡
እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡
የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

74 comments:

 1. እውነት የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

  ReplyDelete
 2. Nation Building is a process of constructing and fashioning a national identity. The choice of these key words, process, and construction and fashioning are very fundamental because they are the basic ingredients of nation building. Taking a critical look at these words one will realize that nation building is indeed a process which takes place over a long period of time. It is gradual and not drastic or a sudden occurrence. Construction and fashioning are also very important in nation building because there are things to be constructed and fashioned out, both in physical and intangible terms. Fashioning here is a conscious effort at creating an identity and a national image. Among those things to construct and fashion out are behaviors, national image, values, institutions and even physical monuments that depict common history and culture of the people of the state. Furthermore, national identity has to do with shared feelings among a people with a common or similar heritage, a sense of belonging to a common nation, a feeling of togetherness that is expressed through the sharing of a common national language, national anthem, show of respect for a common national flag, etc. Nation Building is also about forging a sense of unity among the various units of a country; it include making conscious efforts in uniting heterogeneous societies as one indivisible unit, united in national goals, believes and common national aspirations. It not only involves rebranding of image, but also includes the revamping, restructuring and reorientation of a nation.
  Indeed, Nation building is different from State building, because while the later is more of building and strengthening states institutions which could also be from an outside influence, the later is more concerned with the building of a strong national identity. ..http://www.studymode.com/essays/The-Role-Of-Women-In-Nation-1366230.html ...The task of nation building requires the participation of all regardless of their race, ethnicity or
  gender in the creation of a strong state. The challenge of balancing between the need for unity
  and the recognition for diversity.According to Stein, the physical differences between men and women profoundly mark their
  personalities. The woman’s body stamps her soul with particular qualities that are common to
  all women but different from distinctively masculine traits.one of the fundamental characteristic closely
  linked to a woman’s essence her maternal nature. This maternal nature is understood not
  purely as a physical motherhood but also as spiritual motherhood. Spiritual motherhood like
  physical motherhood, demands spousal love, that is, the gift of self. The key and core of woman
  is to be mother and companion. The distinctive feminine nature belongs essentially to the
  woman in any role that she plays whether married or single. Women are thus called to highlight
  the centrality of the role of motherhood in society. In the case of physical motherhood, woman plays a crucial role in the
  determination of societal values as the task of educating children in values is primarily hers.
  Woman is thus called to contribute to society’s values by inculcating in her physical children
  these values. As noted earlier, her maternal role is not constrained to biological motherhood.
  Woman’s role in educating in values transcends the family AND THE NATION.ETHIOPIAN MOTHERS must thus not lose sight of this role which they can exercise in whatever
  position they occupy in society .

  ReplyDelete
 3. መምህር እግዚብሔር ይስጥልን፡፡ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 4. ተዝቆ ተዝቆ የማያልቅ
  ተፍቆ ተፍቆ የማይለቅ
  ተጨምቆ ተጨምቆ የማይደርቅ
  የእሷ ፍቅር
  ከማር በላይ ማር

  ድንቅ ናት ድንቅ
  የሩቅ መንገድ ስንቅ
  ብርቅ ናት ብርቅ
  ከወርቅ በላይ ወርቅ

  ታስቀይም ይሆናል
  በሆነ ምክንያት
  እሷም ትቀየም ይሆናል
  በሆነ ምክንያት
  ሆኖም ዞሮ ዞሮ
  እምዬ ናት
  እናትhttp://kweschn.wordpress.com/2012/05/13/%E1%8B%A8%E1%8A%A5%E1%88%B7-%E1%8D%8D%E1%89%85%E1%88%AD/

  ReplyDelete
 5. ኧይ ዳንኤል የሙሴን እናት ፈልጉ ትላለህ ? ወዳጆችህን አትድከሙ በላቸው
  በ2007 ምርጫ ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ይመረጣሉ……..እናም የዳግማዊ አጼ ቴዎድርስ ትንቢት ይፈጸማል…….ኦሮማይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. yich hager kendant aynet fezegna meche yihon yemitetsedaw?

   Delete
  2. ኧረ በሕይዎት መቀለድ ቢበቃን ምን አለበት?"ኢይጻእ ከንቶ ነገር እማፍክሙ" አይደል የተባለው::


   ኤፌ 4፥29
   ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
   ቆላ 3፥8
   አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ።

   Delete
  3. I was not consumed or will not consume the idea like " Anonymous, November 27, 2013 at 11:38 AM" always negative minds has attracts a negative idea even converts the positive to a negative. That is actually a sign of living with unconscious mind

   Delete
 6. ሙሴ ሲያድግ እናቱ እውነቱን እየነገረችው ነው ያደገው፡፡ ‹‹አንተ በፈርዖን ቤተ መንግሥት ብትኖርም ግብጻዊ ግን አይደለህም፤ አንተ በምቾት ብትኖርም፣ የሚሰቃዩት የእሥራኤላውያን ወገን ነህ፤ አንተ የግብጽን ቋንቋ ብታጠናም ቋንቋህ ግን ዕብራይስጥ ነው፡፡ እዚህ ያገኘኸውን ልምድና ዕውቀት፣ሥልጣንና ክብር፣ ከሞት የመትረፍ ዕድል ወገኖችህን ነጻ ለማውጣት ተጠቀምበት፡፡ ይህ የምታየው ሕዝብ እንዲህ አልነበረም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነበር፣ ታላቅ ሕዝብም ነው፡፡ የአሁኑን መደኽየት፣ የአሁኑን መዋረድ፣ የአሁኑን መገፋት፣ የአሁኑን መጨቆን አትይ፡፡ ነገ ታሪክ ይለወጣል፡፡ አንተ ዛሬ ይህችን ክብርና ሥልጣን፣ ምቾትና ድሎት አገኘሁ ብለህ ከወገንህ ብትርቅ ታሪክ የተለወጠ ዕለት አንተም ስትረገም፣ ስትዋረድና ስትወቀስ ትኖራለህ፡፡

  ReplyDelete
 7. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡

  የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው? God bless you more and more Dn.

  ReplyDelete
 8. ዲ/ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ድምፅህን ስሰማ መፅናናትንና ኢትዮጵያዊ መንፈስ ጉልበት ሞራል ይሆነኛል።እኛም ባለቤት የሌለው ጢንዝዛ ከሆን ዘመን ተቆጠረብን ።እና እነደ ሙሴ እናት የምትሆነን እናት በዚህ ዘመን ፈልገን ባናገኝም የሙሴ እናት ለሙሴ አንድ ናት ።ለኛም ለኢትዮጵያዊያን ዘራችን በአለም እንደ ጨው ለተበተንነው እናታችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት ልጆቿም በየ በረሀው ተጥለዋል፣ በየአረብ ሀገሩ ሞተዋል በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣በጃፓን በደቡብ አፍሪካ ወዘተ ኢትዮጵያው ሙሴ ያልተጣለበት ባህር የለም ለሙሴ አርባ አመት ለኢትዩጵያ ከዛም በላይ ነው መከራው የበረታው በሰደት ሲኖር እናቱን ፣ወገኑን ሀገሩን ሳይረሳ ያው አንደ ሙሴ ሆኖ ቆይቷል አሁን ግንበበቃ ሁኔታ ሙሴ ከፈርኦን ቤተመንግስት ለወገኖቹ ብሎ በረሀ እንደገባ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያዊው ሙሴ በረሀ ወርዷል እናቱን ወገኑን ሀገሩን ሊታደግ አሁን ነው የእግዚያብሔር ሰዓት ኢትዮጵያን ባህር ከፍሎ ህዝቦቿን ሊታደግ ሊያሻግራት የእግዚያብሔር ቀኝ እጂ ተዘርግቷል።ኢትዩጵያውያን ደስ ይበላችሁ ።ሁላችሁም በምትችሉት ሁሉ እናታችሁን እርዶት እናቴ ምን ልርዳሽ በሏት እናት እኮ አንድ ናት ምትክ የላት እባካችሁ ልጆቸ ብላ ድምፅ አያሰማች ነው ።ብልሀተኛዋን የሙሴ እህት እንሁን እባካችሁ በሰውሀገር ያደገው ፣የተማረው ፣የተጠበበው፣ዶ/ር ፣ሳይንትስት፣ሁሉም በየችሎታው እናቱን ለረዳ ተዘጋጂቷል በርቱ ልጆቸ ድረሱለረኝ ትላለች እማማ ማን ይሆን ምትክ በሌላት እናቱ የሚቀልድ የሚደራደራ ጊዜ የሚያጠፍ እሄን ማንም እንደ ማያደርግ ተስፍ አለኝ እንበርታ ኢትዩጵያ እማማ በልጆቿ ተከብራ ለዘለአለም ትኑር! !!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is A POSITIVIST VIEW "Anonymous November 27, 2013 at 1:48 PM"
   THANK YOU

   Delete
  2. Thank you for such a positive outlook, yes we have so many Amaizing heroes that has not been reaveled to the public eye.

   Delete
 9. ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡

  ReplyDelete
 10. "ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካሉን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡ በሙሴ ውስጥ ያለችው፣ ከፈርዖን ጋር የተከራከረችው፣ ቤተ መንግሥቱን ጥሎ ለወገኑ ሲል በረሃ እንዲንከራተት ያደረገችው፣ ባሕር እንዲክፍል ያበቃችው፣ የሕዝቡን ስድብ፣ ማጉረምረም፣ ሐሜትና ዐመጽ ችሎ ሕዝቡን እንዲመራ ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡፡
  እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡
  የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?"

  ውድ ወንድማችን እግዚአብሔር ይጠብቅልን ረዥም እድሜን ከሙሉ ጤና ጋር ያድልልን፡፡ የጥበብ ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር ጥበቡን አብዝቶ አብዝቶ ይግለጽልህ፡፡

  ReplyDelete
 11. የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

  ReplyDelete
 12. ‹‹አንተ በፈርዖን ቤተ መንግሥት ብትኖርም ግብጻዊ ግን አይደለህም፤ አንተ በምቾት ብትኖርም፣ የሚሰቃዩት የእሥራኤላውያን ወገን ነህ፤ አንተ የግብጽን ቋንቋ ብታጠናም ቋንቋህ ግን ዕብራይስጥ ነው፡፡ እዚህ ያገኘኸውን ልምድና ዕውቀት፣ሥልጣንና ክብር፣ ከሞት የመትረፍ ዕድል ወገኖችህን ነጻ ለማውጣት ተጠቀምበት፡፡ ይህ የምታየው ሕዝብ እንዲህ አልነበረም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነበር፣ ታላቅ ሕዝብም ነው፡፡ የአሁኑን መደኽየት፣ የአሁኑን መዋረድ፣ የአሁኑን መገፋት፣ የአሁኑን መጨቆን አትይ፡፡ ነገ ታሪክ ይለወጣል፡፡ አንተ ዛሬ ይህችን ክብርና ሥልጣን፣ ምቾትና ድሎት አገኘሁ ብለህ ከወገንህ ብትርቅ ታሪክ የተለወጠ ዕለት አንተም ስትረገም፣ ስትዋረድና ስትወቀስ ትኖራለህ፡፡ አንት ባታየው ዐጽምህ ይዋረዳል፡፡ ዛሬ ግን ከተገፉትና ከተዋረዱት ወገን ሆነህ ታሪክ ሲለውጥ አብረህ ብትሠራ ስምህ በወርቅ ቀለም ይጻፋል› - እያለች አስተማረችው፡፡

  ReplyDelete
 13. Very nice as usual and timely.

  ReplyDelete
 14. Dani, Egziabher yabertah!!!
  mati, kesdistkilo gibigubae

  ReplyDelete
 15. ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡ በሙሴ ውስጥ ያለችው፣ ከፈርዖን ጋር የተከራከረችው፣ ቤተ መንግሥቱን ጥሎ ለወገኑ ሲል በረሃ እንዲንከራተት ያደረገችው፣ ባሕር እንዲክፍል ያበቃችው፣ የሕዝቡን ስድብ፣ ማጉረምረም፣ ሐሜትና ዐመጽ ችሎ ሕዝቡን እንዲመራ ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡

  ReplyDelete
 16. cheru Amlak Yemusien enat yisten

  ReplyDelete
 17. የኤርትራ ባሕር.......dear dn Daniel, i wanna know from historic perspective we all the time naming the red sea as " የኤርትራ ባሕር". as historians tell us the name ኤርትራ is Italian so why is this name always related(in our EOTC) with Israelis return to their holy land?
  thank you!

  ReplyDelete
 18. ዳ/ን እንደ ሁሌውም አስገራሚ እይታ ነው ጸጋውን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 19. Good article. Moses' mother gave him three loves.Love of God, Love of his people, and love of his country (the promised land). While he was at the Palace of Pharaoh he never seen God the Almighty and the promised land, but he heard about God and Canaan from his mother. He accepted all what she told him from the depth of his heart. That is why he left the Palace of Pharaoh which was full of luxury. When he left that Palace, he knows as the love of God, his people and the promised land is more than all the luxurious life which he has tasted since his childhood. Look as Moses met God in the wilderness after he left all honor and respect for the sake of God, the chosen people and the promised land.
  Nowadays our planet needs mothers who have a sound faith just like Moses' mother. The Palace of Pharaoh was filled by idols and a number of evil deeds which highly tempts that humble lady. But look how she was steadfast to her faith. Even she was born in Egypt. She never been in Canaan. But she never forget her root. As a sitter of Moses, who was supposed at that time grandson of Pharaoh, she could enjoyed a harmonious life. But she never forget her people's life which was filled by griefs and misery. That was what helped her to tutor her son accordingly. She was good instructor who could help her son to bring behavioral change.
  At present time we have a number of governmental and nongovernmental educational institutions. There we had millions of students, and thousands of teachers. Our beloved Ethiopian Orthodox Church has half million priests and deacons. Do you believe that we helped our pupils to bring behavioral changes in their life and give priority to their PEOPLE? Even do you think that we the teachers whether at the secular or religious sectors, have got that change? Those people who were under the yoke of Pharaoh's operation have value in the eyes of Moses. In fact they were uneducated. They were not wealthier. But Moses respected them. When Moses left the Palace nobody negotiated him to pay salary or daily allowances. Even at the midst of the Sinai wilderness they hardened their heart and tempted God. What ever it be Moses led them till he rest in peace. You people who are at different level of political, social, religious or any kind of positions the people whom you are leading may not that much valuable. They may be weak, backward or troublesome. But never forget that they are people of your Nation. Our honor is nothing but let us respect and honor our people who helped us to be what we are now.

  ReplyDelete
  Replies
  1. GOD bless you. Love can forgive. Love each other!

   Delete
 20. ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡

  ReplyDelete
 21. ሙሴ የእናቱ ውጤት ነው፡፡ ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡ አካን ቤተ መንግሥቱ ሲቀርጸው የሀገርና የወገን ፍቅር፣ ጽናትንና ብርታትን፣ ለወገን ሲሉ መሥዋዕት መሆንን የተማረው ከእናቱ ነው፡፡ የጥንቱን ታሪክ እየነገረች ልቡ በወገኑ ፍቅር እንዲቃጠል ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ያንን ታሪክ የመመለስ፣ ይህንን ሕዝብም ታላቅ የማድረግ ድርሻ ያንተ ነው ያለችው እናቱ ናት፡፡ ሙሴን ነጻ አውጭ እንዲሆን አድርጋ የሠራችው እናቱ ናት፡፡ በሙሴ ውስጥ ያለችው፣ ከፈርዖን ጋር የተከራከረችው፣ ቤተ መንግሥቱን ጥሎ ለወገኑ ሲል በረሃ እንዲንከራተት ያደረገችው፣ ባሕር እንዲክፍል ያበቃችው፣ የሕዝቡን ስድብ፣ ማጉረምረም፣ ሐሜትና ዐመጽ ችሎ ሕዝቡን እንዲመራ ያደረገችው እናቱ ናት፡፡ ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡፡
  እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡
  የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

  ReplyDelete
 22. እኔ የወረቀት የብአዴን አባል ነበርኩ።ከባንዳዎቹ አንዱ ነበርኩ። ለብአዴን አመራሮች፣ካድሪዎችና ደጋፊዎች መልእክቴ ይህ ነው፣
  ''አምላካችሁ ፈርኦኑ ህወሃት አይደለም። የወለዳችሁን ህዝብ ከድታችሁና አይንህን ለአፈር ብላችሁ ለፈርኦኑ ማደራችሁ ትልቅ ክህደትና ውርደት ነው። እንስሳት እንኳን መንጋቸውን ይፈቅዳሉ። እናንተ ግን አሁን የምታገኙት ፍርፋሪ ተደልላቹ የህዝቡ ሞት፣ስደት፣ውርደት፣እልቂት፣መጥፋት፣ሃፍረት ምንም የሚሰማቹ አይደለም። ይህም ከሰብአዊ ፍጥረት በታች መሆን ነው።''

  ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ ከዪኒቨርሲቲ ለለመባረርና ስራ ለመያዝ ብየ አባል እሆናለሁ በየ ገባሁ። ምክንያቱም አባል ያልሆነ ስራ አይዝም ወይም ጸረ ሰላም ነው ተብሎ በህወሃት ደህንነቶች ማንቁርቱን ተይዞ ይገረፋል፣ይባረራል። ይህ የገሃድ እውነት ነው።
  አባል በሆንኩባቸው ትንሽ አመታት ብ አዴንን ታዘብኩት፣ የክህደቱንና የድንቁርናዉን ስፋትና ጥልቀት። ምን ያህል ፍጹም የህወሃት አግልጋይ እንደሆነ፣ ምን ያህል ምንም የህዝብ መንፈስ የሌለው በህወሃት ሳንባ የሚተነፍስ መኖኑን አወቅሁ። ተራው አባል ምንም ግንዛቤ የለውም፣ በህዝቡ ላይ የሚደርሰው በደል፣ ግፍና ሞት አይገባዉም ወይም አያወቅም። የብአዴን ባንዳነት ለመግለጽ ቃላት አይበቃም። ወደ ሶስት ሚሊዮን ባንዳ አለ በድርጅቱ የታቀፈ። የአንድ ለ አምስት አደረጃጀትን ሳይጨምር ማለት ነው። ህዝብ እንዲህ በራሱ ልጆች ሲሞትና ሲጠፋ እንዲህ ነው። አየ ጊዜ

  አንድ ስብሰባ ላይ ልብን የሚሰብር የ ብ አዴን አመራሮችን መልስ ላካፍላቹ፣
  የ ብ አዴን ከብ ረ በ አል ላይ ነው። ቱባዎቹ ሁሉም የድርጅቱ መሪዎች አሉበት። አንዱ እንዲህ ሲል ጥያቄ አነሳ፣

  ''የድርጅታችን ሰላሳኛ ክብረ በ አል ማክበራችን መልካም ነው። ግን ምን ያህል የህዝባችንን ችግር ተረዳን? በርካታ ተነግሮ የማያልቅ ችግር በህዝባችን ውስጥ አለ፣ ይፈናቀላል፣ይገደላል፣ ይሰደባል፣ አድሎ ይደረግበታል። አሁን በውጭ ሚዲያ እንደምንሰማው ከሆነ ደግሞ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ነው።ካባለፈው ከህዝብ ቆጠራ ጋር ተያይዞ ሶስት ሚሊዮን ህዝብ የጠፋው በዘር ማጥፋት ሴራ ነው ይባላል። የ ኤድስ ስርጭትም በ አስጊ ሁኔታ ነው ያለው። ከቤተሰብ ምጣኔ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ቅሬታም አለ። ተገልጋዩ ህብረተሰብ ላይ የመካነንት ችግር አስከትሏል ይባላል። እነዚህ አሳሳቢ ጉዳዮች ለምን ዝም ተባሉ? ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመዉና የሚያስፈጽመው ህወሃት ነው እየተባለ እንሰማለን። ድርጅታችንም ተባባሪ ነው ይባላል። ይህ ከሆነ ለምንድን ነው ድርጅታችን ይህን የሚያደርገው? ለምንድን ነው ህዝባችንን ከሚያሳደደውና ከሚገድለው ህወሃት ጋር አብረን የምንጓዘው? እኔ አልገባኝም፣ ይህ ከሆነ የብ አዴን መኖሩ ትርጉሙ ምንድን ነው?ክብረ በ አል እያሉ ማክበሩስ በህዝብ ሞትና መከራ ማሾፍ አይሆንም? ክህደት አይደለም አለ?'' አዳራሹ በዝምታ ተሞላ፣ ቲባዎቹ መሪዎችም ይህ የጸረ ሰላም ሃይሎች አስተሳሰብ ነው። የጅምላ ማስፈራሪያቸውን አወረዱት። ማንም ምንም አላለም። ልጁን የህወሃት ደህንነቶች አንቀው ወሰዱት አሉ። ይግደሉት ምን ያድርጉት አይታወቅም።

  የኔ ጥያቄ ይህን ያህል በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ባንዳ እያለ እንዴት ለ ኢትዮዽያ ህዝብ ሙሴ መሆን ይቻላል ቢያንስ እስራኤላዊያን በመካከላቸው ባንዳ አልነበረም። ህወሃት ጅኒየስ ነው። አንድን ህዝብ እንዴት ራሱ በወለዳቸው ልሂቃን፣ልጆች ባንዳነት ማጥፋት እንደሚችል አሳይቷል፣ አሁንም እየሰራበት ነው። ብአዴንን በደንብ ለዚህ ሂትለራዊ እኩይ ተግባር ተጠቅሞበታል፣እየተጠቀመበትም ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ''ህወሃት ጅኒየስ ነው'' ጽዋው እስኪሞላ፡፡ደርግም እኮ ጽዋው እስኪሞላ ጅኒየስ ነበር፡፡ዋናው ጅኒየስ ግን ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ ነው፡፡እርሱም ጽዋው ሲሞላ(ጊዜው ሲደርስ፣ዓለም ስታልፍ ) ሥልጣኑ ያበቃል፡፡ እስከዚያው ግን ወጥመዱን ዘርግቶ ማጥመዱን ተው የሚለው ማነው?ዓለምን መውደድ ዓይንን ያሳውራል፤የወገን ፍቅር እንዳይታሰብ ያደርጋል፡፡እንግዲህ በየክልሉ የተሾሙት ለወገኖቻቸው እንዳያስቡ የሚያደርጋቸው ሌላ ነገር ሳይሆን ዓለምን መውደድ ነው፡፡ ዓለምን የሚወድ ሰው ደግሞ ለሰይጣን ሥራ ምቹ የእርሻ ማሳ ይሆንና የምናያቸውን ክፉ ነገሮች ያመጣል፡፡

   Delete
  2. “ሰይጣን ለዓመሉ ከመጸሀፍ ቅዱስ ይጠቅሳል አሉ፡፡” ለሀገር የተጻፈውን ነገር በጎጥ ማጥበብ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ ህወሃትን እንደ ፓርቲ መጥላትና የኢህአዴግን መንግስት መጥላት የሚደገፍ ነገር ነው፡፡ መቃወምም ተገቢ ነው፡፡ ግን ለበጎ የተጻፈውን ፅሁፍ ወደ ዘር አውርዶ የዘረኝነት ቅስቀሳ ፅሁፍ አድርጎ የራስን ክፉ አላማ ማዳመቂያ ማድረግ ምን የሚሉት ነው፡፡ ዘረኛ በመሆን ዘረኝነትን መቃወም አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት አስተዳደር ያልተበደለ ግለሰብ ዜጋ የለም፡፡ ሁሉም የራሱ ዘር ተለይቶ የዘር ማጥፋት እርምጃ እየተደረገበት ነው ብሎ በማመንና በመቀስቀስ ምን አይነት ለውጥና መፍትሔ እንደሚመጣ አላቅም፡፡ የሰውን ሰብዓዊነት መሰረት የአደረገ መፍትሔ መቼ ነው ማምጣት የምንችለው ??? ሙሴ እኮ የተቃወመው እንዲሁ ግብጾችን ስለጠላ አደለም አህዛብነታቸውንና የግፍ አገዛዛቸውን እንጂ… ህወሃት ቢጠፋ ምን ዋጋ አለው የሱን የዘረኝነት መንፈስ እኮ በአንተ ውስጥ ተክሎ ሄዶዋል እኮ አንዱ ዘረኛ ሲወርድ ሌላ ዘረኛ መተካት ነው የሚሆነው፡፡ ልቦና ይስጠን፡፡

   Delete
  3. ሙሴ የተቃወመው ግበጾችን ስለጠላ አይደለም ስራቸውን ግፋቸውን ነው ጥሩ አስተያየት ነው። እኛም እኮ ይህንን ግፍና በደል ዘር የሚያጠፋውን ገዳዩን ህዋትን ወያኔን ነው ዘረኛውን ነው የምንቃወመው እጂ ፁሁፉ ላይ: ሰውን በመቀስቀስ የተደረገ ነገር የለም ማንም ሳይቀሰቅሰው የኢትዩጵያ ህዝብ ሁሉም በደል ተፈጽሞበታል ትግስት ስላለው መከራውን ችሎአል ፈረኦናዊው ቡድን ትግስት ፍራት ከመሰለው ጊዜ ካላስተማረው በገረፈበት ጂራፍ ሊገረፍ ጊዜው አሁን ደርሶል ያውም በከፋ ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የወለደች እናትም ልጆ ቢበድላት ቡዙ ታስተምራለች ትራራም አለች ባለጌው ልጆ ግን ደፍሮ ካስደፈራት ካዋረዳት እናትም በቃ ብላ የመጨረሻውን የእናትነት ፍቅራን ታቆማለች ያውም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ዳግም አዳታየው ያጠባችውን አፍስሳ የምትለይበት ሁኔታ አለ ያም ማለት ለገዳዩ ለጨካኙ ለውሸታሙ ለሰው በላው ለሌባዉ ለውሸታሙ በቁሟ ለሸጣት ላስደፈራት ላሰደዳት ላስራባት ላሳረዛት ላስለመናት ኦረ ስንቱ ነነግሮ ያልቃል ይህንን ነበር እማማ የቻለች አሁን ግን በቃ ከልክ በላይ ሞልቶ ፈሰሰ አለች እማማ በዘር የተከፋፈለ ልጂ የላትም አሁን ሁሉም አንድ ሁነዋል ዘረኛው ከተወገደ ዘረኛ ልጂ የላትም እሱ እንዲኖር ነበር የዘረኝነቱን መረዝ ሲረጭ የኖረው አሁን የዘራውን እርሱ በሚገባ ያጭደዋል የልቅስ የመኸር ጊዜ እንደረሰ ነረገረው እንዲዘጋጂ የማይቀር እደሆን አንተም ካለህበት ተዘጋጂ አይቀሬው መጧል አማማ ጨክናለች ከንፀጽህ ከታማኝ አክብረው ከሚያስከብሯት ልጆቿ ጋር በጋራ ለመኖር ቤቷን እየሰራች በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።ደሞ ከዚህ በሓላ ለአስር አመት እድገት ያስባል ትንሽ አያፍርም ከየት ነው የመጡት እውነት ኢትዩጵያዊ ናቸው እነዚህ አረመኔዎች በጣም ይገርማል እንዴው ሌላው ቀርቶ ሰሞኑን እንኮን ያደረጉት በሳውዲ አይበቃቸውም ለወገን ምን ሰሩ ምን አደረጉ ሳውዲ ሲመልስ እነሱ ከተመለሾች ጋር ፎቶ በመነሳት ለወገን የደረሱ መሰላቸው ይህ ታሪክ እግዚያብሔርና ኢትዩጵያ አትረሳውም።ከአባ ኮስትር ከበላይ ነኝ።

   Delete
 23. Amazing expression !! your excellency diakon daniel kibret
  i learning more things from u. thanks the almighty God .because he give u for us .

  ReplyDelete
 24. Egziabiher yemussiena yemussien enati yisiten bereketunmi.

  ReplyDelete
 25. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡
  የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

  ReplyDelete
 26. , it is not related with above issue...but it is related to our mother ethiopia so i posted it. http://shenkutayele.wordpress.com/ እድሜዬ ለፖለቲካ ግንዛቤና ትንታኔአዊ ፍች ከደረሰ ብሁዋላ አንድ አስገራሚ የስነልቦና ቀዉስ ማህበረሰባችንን ዉጦት አስተዉላለሁ:: ይህም የጥላቻን ፖለቲካ በአደባባይ የሚያራምዱ ምሁራን: ፖለቲከኞች : ታላላቅ ሰዎች: የሚዲያ ባለሞያዎችን: የሀይማኖት አባቶች እና የዉጭ ሀገር ሰዎችን በስፋት ማስተዋል ችያለሁ:: የኢትዮጵያን ፖለቲካ እያነሱና እያብጠለጠሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ማንነት እንዲሁም የሚያስተሳስሩት የጋራ የአብሮነት ህልዉና የሌለዉ እስኪመስል ድረስ ሀገሪቱ በፍርስራሽ ማንነት ላይ የቆመች እስኪመስል ድረስ ብሎም ወደፊት ህዝቡ እርስ በእርስ ተማሮ ና ተጠላልቶ በመጨርሻም የወላለቀችና የተበጣጠቀች ኢትዮጵያን ለማስተዋል የቆረጡ ታላላቅ ሰዎችን ማስተዋል ችያለሁ:: በርካታ ኢትዮጵያዉያንም ይሄን የጥላቻ ማዕበል ሀገር ማስተዋል ብቻ ሳይሆን በማዕበሉ ዉስጥ ገብቶ ለመዋኘት ተገደዉ ነገሩን በተገርሞም በፍርሃትም እያስተዋሉ አሉ::

  ጠላትህን እንዴት ታጠቃዋለህ ቢሉህ – ብልህ ከሆንህ ፈላስፋ እንደሚነግርህ “ጠላት አፈራለታለሁ” ብለህ ትመልሳለህ:: ወዳጅህንስ እንዴት ትጠቅመዋለሁ ቢሉህም ” ወዳጅ አፈራለታለሁ” ብለህ ትመልሳለህ:: ይህ እንግዲህ ጠቢብ ከሆንህ ብቻ የሚገባህ ነገር ነዉ:: መቼም ጥበብ የራቀዉ ሰዉ እንዲህ ያለ ጥበባዊ አስተሳሰብ አይገባዉም:: ኢትዮጵያዉያን አንድ የቤት ስራ አለብን:: ያም የጥላቻዉን ወንዝ መሻገር ነዉ:: በርግጥ የኢትዮጵያ ሰዉ አንድ ሆኖ ሳለ በዘርና በማንነት በመሰረታዊነት ሳይለያይ በቁዋንቁና በወንዝ የተወሰን ስለተለያዬ ብቻ በዚህ ህዝብ መሃከል አጥርና ልዩነት ለማበጀት የጋራ የማንነት ወንዞቻችንን በጥላቻ የበከሉብን ፖለቲከኞችን እግዚአብሄር አስነስቶልናል:: እንዲህ ማለቴ ነገር ሁሉ አለ እግዚአብሄር ፈቃድ አይሆንም የሚለዉን ለማመስጠር ነዉ እንጅ እግዚአብሄርማ መች እንዲህ ክፋት ስሩ ብሎ ያስነሳል:: አንድም ፖለቲከኞቻችን በራሳቸዉ ጊዜ ተነስተዉ በራሳቸዉ ህሳቤ ወንዙን ሁሉ በጥላቻ በክለዉታል:: ምክንያቱም እግዚአብሄር ፍቅር እንዲያዉጁና ፍቅር እንዲያራምዱ እንጂ ሰዎችን ሃያላን አድርጎ የሚያስነሳቸው ጥላቻን እንዲተበትቡ አይደለምና::ጥላቻ ጥላቻን ይወልዳል:: ፍቅር ፍቅርን ይወልዳል:: እናንተ ዉስጥ እሱ ጥላቻን ሲዘራባችሁ እናንተ ለምትወልዱት ጥላቻ አቻ የሚሆን ምላሽ በጠላችሁት ወገን ዉስጥም ተረግዞ ይወለዳል:: ሁለት ወገኖች ሲጠላሉ ምን ይፈጠራል? ማንኛዉም ወገን አያሸንፍም:: ቢያሸንፍም እኩል ከተጠፋፉ ብሁዋላ ብቻ ነዉ::

  አስቂኙ ነገር ታዲያ ከብዙ ጥፋት ብሁዋላ አሸናፊ የሚሆነዉ ወገን አለመታወቁ ነዉ:: መሸናነፍ በራሱ ማቆሚያ የለዉም:: ልክ ህጻናት ትንቅ ሲገጥሙ ወይም ረስለሮች/ነጻ ትግል ታጋዮች/ ሲታገሉ አንዴ አንዱ ሲጥል ሌላ ጊዜ ሌላዉ ጉልበቱን አጠራቅሞ ሲገለብጥ ማለቂያ ወደሌለዉ የእርስ በእርስ ትግል ዉስጥ መግባት እንደማለት ሊወሰድ ይቻላል:: በጥላቻ ሁለቱም ወገን ይዝላላ:: ሁለቱም ወገን ይደክማል:: መጨረሻም ማንም ወገን ሳያሸንፍ በያለበት ተዳክሞ ይዘረራል:: እንግዲህ በዚህ ሂደት ዉስጥ አጥፊ መሳሪያዎችና አጥፊ ሀሳቦች ተካተዉበትና ከምድረ ገጽ ለመጠፋፋት የሚደረገዉን ሂደት አክላችሁ አስቡት::

  ጥላቻ የመጨረሻ ፍሬዉ መጠፋፋት ነዉ:: አሁን ይህ ጥልቅ አባባል ለሞኞች እንደማይገባቸዉ እሙን ነዉ:: ሞኞች የሚገባቸዉ የጥፋቱ ቀን መጥቶ እየጠፉ ባለበት ሰዓት ብቻ ነዉ:: አንድም መጥፋታቸዉ እንኩዋን አይገባቸዉም:: ፈጽመዉ እየጠፉ ባለበት ሰአት ቢያዉቁትም አላወቁትምና:: አሳዛኙ ነገር ታዲያ ሰነፎች በስንፍናቸዉ ትዉልዳቸዉ እንኩዋን እንደሚጠፋ ለማወቅ የሚያስችል አስተዉሎት የጎደላቸዉ ናቸዉና ጠላት በእነሱ ዉስጥ የሚዘራዉን ጥላቻ ተሸክመዉ መልሰዉም እየዘሩት ለዘለአለም ይኖራሉ:::

  ስለዚህ ጠቢባን የሆናችሁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ወደ አስተዉሎታችሁ ማዕከላዊ ጭብጥ ልታዉሉት የሚገባዉ እዉነት አንድ ነገር አለ:: ማንም ወገን እናንተን ወደ ጥላቻ የሚገፋችሁ ከሆነ የደገፋችሁ ቢመስልም ጠላታችሁ ነዉ እንጅ ወዳጃችሁ አይደለም:: የዚህ ዘመን የማህበረሰብ ግንኙነት አንዱ በአንዱ በጋራ ተሳልጦና ተዋህዶ ወደ ጋራ ብልጽግና መራመድ ቁልፍ መርሁ ነዉ:: አለሙ ተለዉጡዋል:: እጅግም ተሳስሮአል:: እጅግም ይፈላላጋል:: እያንዳንዱ የአለም ህዝብ ሌላዉን የአለም ህዝብ ይፈልገዋል:: የበለጠም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሌላዉን ኢትዮጵያዊ አጥብቆ ይፈልገዋል:: በዚህ የመፈላላገ ሂደት ዉስጥ ፍቅር: እዉቀትና እዉነት መርህ ሊሆኑ ይገባል::ጥላቻዉ መርዝን በልባችሁና በአዕምሮአችሁ ከከተታችሁ ግን እራሳችሁን ብሎም ትዉልዳችሁን እያጠፋችሁ መሆኑን አትርሱት:: ግልጽ ነዉ ሰነፍና ማስተዋልን የተነጠቀ ሰዉ ግን በዚህ አባባል እንደሚስቅ እሙን ነዉ:: ሰነፍ ነዉና:: እንዲህ አይነቱን ሰዉ ከስንፍናዉ ጋር ተዉት::

  እንድገመዉ :- ጠላትህን እንዴት ታጠቃዋለህ ቢሉህ ብልህ ከሆንህ ፈላስፋ እንደሚነግርህ “ጠላት አፈራለታለሁ” ብለህ ትመልሳለህ:: ወዳጅህንስ እንዴት ትጠቅመዋለሁ ቢሉህም ” ወዳጅ አፈራለታለሁ” ብለህ ትመልሳለህ:: ይህ እንግዲህ ጠቢብ ከሆንህ ብቻ የሚገባህ ነገር ነዉ::

  ReplyDelete
 27. ሙሴ ታላቁ አባት

  እስራኤል በግብፅ በስደት ሃገር ላይ
  ሁሉን አሳለፉ ጌታ ባይኑ እስኪያይ
  ንጉስ ፈርኦን ይህን ብሎ አዘዘ
  እንዳይበረቱብን እንግዛቸው እያለ
  የተወለደውም ወንድ ሆኖ ሲገኝ ወንዝ ይጣል አለ
  ሙሴ እስኪወለድ 7 ወር በሙሉ በእንዚህ አለፈ

  ሙሴም ተወለደ ያ ታላቁ አባት
  ንጉሱ ፈርኦን ልጇን እንዳይገድልባታ
  እናቱ በሳጥን ወንዝ አጠገብ አኖረች
  ተርሙት የፈርኦን ልጅ ህፃን ሲያለቅስ ሰማች
  ሳጥኑን በመክፈት ላንተ ስትራራልህ
  እህትህ ማርያም ሃሳብ አቀረበች
  ከእብራዊያን ወገን ልጁን ምታጠባ
  ልጥራልሽ ብላ እናትህን ጠራች
  ንጉስ ፈርኦንም ልጁ አደረገህ
  የንጉስን ቤት ተድላ ደስታ ንቀህ
  ስደትን ተሰደድክ ስለወገኖችህ


  እግዚአብሄር አዘዘህ ግብፅ ተመልሰህ
  ለህዝበ እስራኤል መሪ አደረገህ
  አንተም ታላቅ መሪ ሆነህ
  ያን ሁሉ ህዝብ መራህ ጌታ እየደገፈህ።

  ገበሬው ወይኑን ኮትኩቶና ውሃ አጠጥቶ አሳደገ። የወይኑ ፍሬም የቀመሰው ሁሉ አደነቀ! ለሀገርም ሆነ ለቤተክርስቲያን መልካም የወይን ፍሬ እናገኝ ዘንድ እንደ መልካሙ ገበሬ መልካም እናት ታስፈልገናለች! እናት የወይናችን ስር ናትና!

  © ከልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር ብሎግ የተወሰደ
  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ReplyDelete

 28. © ከልጅ ዮናስ ቀልድ እና ቁም ነገር ብሎግ የተወሰደ
  http://yonas-zekarias.blogspot.com/

  ”ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጣልን? “ ተብሎ በታላቁ መፅሐፍ ተጽፏል። ነብር እስከ ዛሬ ድረስ ዥንጉርጉርነቱን አልለወጠም፤ ኢትዮጵያዊያን ግን መልካችንን ከለወጥን ዘመናት አልፈዋል። ”ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጣልን? ስንባል እኛ ደግሞ “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ጸጉር” ብለን ዘር በዘር ሆነናል! ደም ከደም ስር ጋር እንደማይጋጭ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ከዘር ጋር አይጋጭም ብንል ሞኞች ነን። አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያዊነቱ ከዘሩ ጋር ያልተምታታበት የት ይገኛል? እዚህ ጋር አንድ እውነተኛ ታሪክ ላውጋችሁ። አንድ ዘረኛ ሰው ነበር አሉ። እናላችሁ ይህ ዘረኛ ሰው ከእርሱ የባሰ ዘረኛ ሚስት አገኘና አገባት። ሲጀመር አንድ ዘረኛ ብቻ ነበር አሁን ግን ሁለት ጥንድ ዘረኛ ሆኑ። እናላችሁ ዘረኞቹ ወላጆች ልጃቸው ለአቅመ ዘረኛነት ሲደርስ አሪፍ ዘረኛ ሴት እንዲጠብስ አደረጉት። እንዲህ ያደገ ልጅ ደግሞ የሀገር ፍቅር ሳይሆን የዘር ፍቅር ይይዘዋል። እናማ አዲስ የተጣበሱት ዘረኞቹ ወላጆቻቸውን ለመምሰል ይሞክራሉ። የጎባጣ አሽከር ጎንበስ ብሎ ይሄዳል፤ ለምንድን ነው ሲሉት ጌታዬን ለመምሰል ነው አለ አሉ። ልጆቹም ወላጆቻቸውን ለመምሰል ዘረኛ ቢሆኑ አይደንቅም። የዘር ፍቅርን የሚያስተምር ወላጅ ሞልቷል፤ የሀገር ፍቅርን የሚያስተምር ወላጅ ማን ይሆን? ከእባብ እንቁላል ርግብ አይፈለፈልም አይደል የሚባለው።

  ReplyDelete
 29. አሁን ወንዶች እብሪተኛ በሆኑበት ዘመን ሳይሆን ዱሮ ዱሮ --- እናትነት እንዲህ ነበር Mothers

  “The Mother is held as the object of affectionate reverence in ethiopian Culture. She is the home-maker, the first teacher of the child, the person who lovingly transmits the culture of this ancient ethiopian land to its heirs in their most formative years. The mother and the father are the first examples in social behavior that the child sees and learns to imitate. Thus, they should aid in the spiritual awakening of the child.“Everyone has a mother as the source of his life and body. So the mother has to be strong in mind and body, steeped in culture and good character, sanctified by holy thoughts and full of love and dedication. Good mothers make a good nation.If you want to know how advanced a nation is, study its mothers; are they free from fear and anxiety, are they full of love towards all, are they trained in fortitude and virtue.o save at least the next generation, women have to be educated in a well planned manner and endowed with the wisdom, fortitude and faith that can equip them for the great responsibility that rests upon them…

  ReplyDelete
 30. When a person is born on earth, his mother is important as his source. He brought to this world through his Mother who took the pain of 9 months in her womb and made the egg enough matured to suit it to the earthly atmosphere. It is a great time for every mother, awaiting him as a relief to her for her old age - the Son - (It is not merely a principle, but a physical reality to her).Nation is built on strong citizenry. and strong citizenry is result of wel-bred children. So obviously mothers have the prime and important role in nation building. As foundation stone has role to play in sustaining building. Mothers are foundation stone who arburieded and norecognizeded or rewarded. So are mothers doing their selfless duty.I hope in ethiopia in the future a time will come when women will be awarded with prizes and cash incentives for bearing child. and men will be praising her for being a mother. mother has an important role. mother should give her child all d good qualities, good education, good manners . she should taught how to behave, what is good what is bad, what is right wht is wrong, what should he do, and what his duty,role towards the country/nation as a good citizen or as a good person . and their their child will build the nation

  ReplyDelete
 31. ሰላም ለኪ እናታችን
  ባለሽበት እንዳለሽ
  አንቺ የተባረክሽ ነሽ
  ሰላም ለዓይኖችሽ
  ከጭስ ጋራ ለሚማጎቱ
  ከእንቅልፍ ጋር ለተፋቱ
  ተቅበዝባዥ ፍጡር ሆኜ ኑሮዬን ከምገፋ
  ምነው እንባሽን በሆንኩ
  ከዓይኖችሽ ስር እንዳልጠፋ፡፡
  ሰላም ለከንፈሮችሽ ትላንት ለማውቃቸው
  ዛሬ ለምናፍቃቸው
  ውዳሴ ክብር ምርቃት
  ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
  ምነው ያ'ንቺን እርግማን - ይናፍቃል ጆሮዬ
  ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
  ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ፡፡
  ሰላም ለጣቶችሽ
  ለሰዎች የቀረቡ፣ከራስሽ ግን የራቁ
  መስጠት መለገስ እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
  ሰላም ለኪ!
  ባለሽበት እንዳለሽ፡፡
  (በዕውቀቱ ስዩም፣ የግጥም ስብስብ፣ 2001 ዓ.ም)

  ReplyDelete
 32. በአንድ ልጅ እድገት ላይ የቤተሰብ ተጽእኖ ለልጁ መልካም መሆን አልያም መጥፎ መሆን አብላጫውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ ስለዚህ በልጆች አስተዳደግ ላይ የአባትና የእናት ሚና ቀላል አይባልም፡፡ አበው “እናትነት እውነት፣ አባትነት እምነት ነው” ይላሉ፡፡ ምክንያቱም እናት ከእርግዝናዋ ጀምሮ እስከ ምጧ ድረስ ያለው ሂደት ለማንም ግልጥ ነው፡፡ አባትን አባት ብሎ መጥራት ግን ማመንን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት የአባትን አባትነት (ወላጅነት) ለማረጋገጥ ነው፡፡ ስለዚህ ከእናት ይልቅ አባት አባትነቱን በተግባር መግለጽ አለበት፡፡እናትነት ግን ግልጽ ነው የናት ሆድ አይችልማ!በተለይ ለኢትዮጵያውያን የእኛ አገር እናቶች አባትም ጭምር ሆነው ያሳደጉን ናቸው፡፡ ጠቁረው እንድንቀላ፣ ደክመው እንድንጠግብ፣ ከስተው እንድንፋፋ፣ ኖረው ብቻ ሳይሆን ሞተውም ያኖሩን ናቸው፡፡

  ጆርጅ ዋሽንግተን ስለ እናቱ ሲናገር “እናቴ በሕይወት ዘመኔ ካየኋቸው ሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋበች ናት፡፡ መላው እኔነቴ ሁሉ ለእናቴ የተሰጠ ነው፡፡ በሕይወት ዘመኔ ያገኘሁት ስኬት ሁሉ ከእናቴ ከተቀበልኩት ሞራላዊ፣ ስነ ልቦናዊና አካላዊ ትምህርት የተነሣ ነው” በዓለም ላይ እጅግ ተወዳጁ ቃል እናት የሚለው ነው፡፡ ይህም መስማማት ያመጣው ሳይሆን ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ አንድ ወጣት ስለ እናቱ ሲናገር “ከጥቂት ዓመታት በፊት እናቴን በሞት አጥቻለሁ፡፡ በእናቴ ሞት የተነሣ የደረሰብኝ ጥልቅ ሀዘንና ውስጣዊ ሕመም ስር የሰደደ ከመሆኑ የተነሣ አሁንም ድረስ ጠባሳው አልሻረም፡፡ ነገር ግን መለስ እልና በእናቴ ልዩ ፍቅር እንዲሁም እንክብካቤ ያሳለፍኩትን ዘመን በማስታወስ ልጅነቴን እናፍቃለሁ” ብሏል፡፡ አንድ ያልታወቀ ሰው “ብዙ እናቶች እጅግ ደስ የሚሉ ናቸው፡፡ ግን የማንም እናት እንደ እኔ እናት ጽኑ አይደለችም፡፡ ነገሮች እየከበዱ ቢሄዱም፣ ችግሮች ቢከሰቱም እርሷ ግን ተስፋ አትቆርጥም ፈጽሞ አትወድቅም፡፡ በየዕለቱ ለእኔ ያላት ትምህርት ከሚሊዮን ጊዜ የሚበልጥ ማለቂያ የሌለው ነው፡፡ መክፈል የማልችለውን ፍቅርና ምቾት ከእርሷ አግኝቻለሁ፡፡ ለእርሷ ያለኝን ፍቅር ለመግለጽ አልጀምረውም፡፡ ይህ ልክ እንደ መስመር መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ነው፡፡ ግን የማንም እናት እንደ እኔ እናት የተለየች አይደለችም” በማለት ስለ እናቱ ተናግሮአል፡፡

  ሁላችንም ብንሆን ስለ እናት ጥቂት የማለቱን እድል ብናገኘው ማቋረጥ እንደሚሳነን እገምታለሁ፡፡ ስለ እናት የተባሉ ጥቂት የልብ መልእክቶችን እንመልከት፡-
  · የእናት ጥበብ የመኖርን ጥበብ ለልጆች ማስተማር ነው፡፡
  · የእናት ልብ የሕፃናት ትምህርት ቤት ነው፡፡
  · እናት ጉዳታችንን እና ጭንቀታችንን ሁሉ የምንቀብርበት ስፍራ ናት፡፡
  · እናት ምግብ ናት፣ ፍቅር ናት፣ ምድር ናት፡፡ በእርሷ መወደድ ማለት በሕይወት መኖር፣ ስር መስደድና መታነጽ ነው፡፡
  · አንድ ወቄት እናት ከአንድ ፓውንድ ካህናት ይልቅ ትመዝናለች፡፡
  · ከመላው ዓለም እጅግ ውብ የሆነ አንድ ሕፃን አለ፡፡ እያንዳንዷ እናት ደግሞ ይህ ሕፃን አላት፡፡http://betefikir.blogspot.com/2012/05/blog-post_15.html

  ReplyDelete
 33. በነዛ ጀግኖች ትውልድ እና በእኛ በእንዝህላሉ ትውልድ መካከል ያለውን ልዮነት ለመተንተን ሞከርኩ:: ባያረካኝም:: የድሮው ወጣት የሀገር ፍቅር አለው:: ፈሪሀ እግዚያብሄር አለው:: ምናልባት የባህል ወረራ ሰለባ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ ነገር ይሆናል:: አሁን በግልጽ እንደሚታየው የሀገር ፍቅር የለም:: ወይ እምነት የለም:: ወይ ሁሉም የለም:: እነዚህን ሁሉንም አንድ ሰው ላይ ማግኘት አስቸጋሪ ነው የሚሆነው:: የማህበረሰባዊ አስተሳሰብ እና ትኩረት ልዮነትም ይመስለኛል:: ከስነ-ጥበብ አቅም ከእኛ ቀደም ያሉት የሚያንጸባርቁት ፍጹም ሀገራዊ ስሜት እና ማህበረሰባዊ ፋይዳ ያላቸውን ነገሮች ነው:: ይሄን ለማስተዋል ቀደም ያሉትን የሙዚቃ እና የድርሰት ስራዎች ብቻ ማገላበጡ ይበቃል:: ስለ አርበኝነት ስለ ሀገር ፍቅር ኢትዮጵያውያን ስላደረጉት ደጋድሎ ይዘመር ነበር:: "እንኳንስ በህይወት እያለሁ በቁሜ ለሀገሬ ነጻነት ይዋደቃል አጽሜ"" የተቀነቀነው በ70ዎቹ አጋማሽ ወይ መጨረሻ ነበር:: የተደረገውን ተጋድሎ እየሰሙ ያደጉ ትውልዶች በመሆናቸው የሀገር ፍቅር ስሜት እና ለሀገር መጋደልን በባህሪ ስለወረሱ ይመስለኛል::

  አሁን ዘመን ተቀይሯል::ገጣሚያን እና ጻሀፍት የሚያነሱት የሚጥሉት ነገር እንደምታዘበው የፍቅር አርበኝነት ነው":: የወጣቱ ተግባር "ማፍቀር ማፍቀር አሁንም ማፍቀር ነው"በሚል አይነት መንፈስ እንኳን አሁን እና ከአስራ አምስት አመት በፊት የነበሩ የልብ-ወለድ ድርሰቶች "የፍቅር አርበኝነትን" የሚያንጸባርቁ አይነት ነበሩ:: የ"ሀብታም ልጂ" የደሀን ልጂ ስታፈቅር ወይ ሲያፈቅር ወይ የሚወዳትን ልጂ ለማግኘት የተፈጠሩ መሰናክሎችን ሲያልፍ … "እምቡጥ ጽጌሬዳን ለምቅጠፍ እሾሁን ማለፍ ያስፈልጋል” አይነት ትረካ ያስነብቡናል ...." “ ውዴ አንቺኮ ማለት ለኔ ሁለ ነገሬ ነሽ”....”አንተ እኮ ማለት ማለት ‘ድቅ ድቅ ባለ ጨለማ ብርሀን ለመፈንጠቅ እንደምትወጣው ውብ ጨረቃ ነህ ...ህይወቴ ያላንተ ብርሀን አይኖረውም” ያስነብቡና እና መጨረሻ ላይ ገጸ-ባህሪ ጭምር ይገሉና የፍቅር አርበኝነቱም በሞት ተጠናቆ አሳዛኝ እንዲሆን ይደረጋል:: ጨለምተኝነት አና የአቸናፊነት ስነልቦና የማያውቀው ሆኖብኝ ቁጭ ይላል::የድሮዎቹ ወጣቶች የሚያነሱት የሚጥሉት (ሮማንቲሳይዝ የሚያደርጉት ሀገር እና ህዝብን ነው:: ) “አንቺ እኮ ማለት ለኔ” የሚሉት ኢትዮጵያን ነው:: አስተሳሰባቸው ርባና በሌለው ምክንያታዊነት የተበረዘ አልነበረም:: የህይወትን ትርጉም የሚያዮበት መነጸር ኢትዮጵያ ነበረች:: የፍቅር ህይወት የላቸውም ማለት አይደለም:: ለመለያየት ካለመፈለጋቸው የተነሳ ተያይዘው ጦር ግንባር የሚሄዱ ሁሉ ነበሩ:: የሚንቀለቀል የሀገር ፍቅር ስሜት በዛን ዘመን ከእድሜ ጋር እንኳን አብሮ የሚያረጂ አልነበረም:: የጦር ምክር ተደርጎ ለመዝመት ከተወሰነ በኍላ የኢትዮጵያ ገበሬ ወታደሮች በራስ ካሳ ፊት የገቡት ቃል ሁኔታውን የሚያመላክት ይመስላል:: በገጽ 50 ላይ እንዲህ ጽፎታል :-
  "አንድ ቆፍጣና በራስ ካሳ የሜዳ ላይ ተንቀሳቃሽ ዙፋን ፊት ቀርቦ ጎራዴውን እያወናጨፈ 'በዚህ ጎራዴ አስራ አምስት አንበሶች ገድየበታልሁ: ሁለት እጥፍ ጣሊያንም እገላለሁ' እያለ ፎከረ:: ከማልረሳው ለመጥቀስ ያህል አንድ አዛውንት ጎራዴያቸውን እያወናጨፉ 'በዚህ ጎራዴ ከእምየ ምኒሊክ ጋር አስር ጣሊያን ገድያለሁ:: አሁንም መቶ እጥፍ ጣሊያን እገላለሁ" የሚለው ፉከራ አንዱ ነው:: ሌላው አንድ በግምት ሀያ አመት የማይሞላው ጎረምሳ ሲናገር "እኔ ወጣት ነኝ: ከዚህ በፊት ጀግንነቴንና ታማኝነቴን ለማሳየት እድል አልነበረኝም:: አሁን ግን ሀገሬን ሊወር የመጣን ጣሊያን እንደ ቆሎ አቆላዋለሁ:: አንዱንም አልምርም ሲል በስሜት ተናገር"" ገጽ 50- 51 [ የሀገር ፍቅር እና የአሸናፊነት ስነ-ልቦናው ከትንሽ እስከ ትልቅ ተመሳሳይ እንደነበረ የሚጠቁም ይመስለኛል]

  ሴት ወንድ ሳይል የሚያጠቡ ጭምር እንደዘመቱ የሚያመላክትም መረጃ አለ:-
  ...በዚህ እንደሞላ ወንዝ እያጓራ በሚጓዝ ጦር ውስጥም እንደነገሩ ሸማ የተከናነቡና በጀርባቸው በቅርጫት ሙሉ የማብሰያ ቁሳቁሶች ያዘሉ ሴቶችም ነበሩ:: የሚጠባ ልጂም የተቸከሙ ታይተዋል..."ገጽ 72

  በዘመናችን ያለውን ወኔ ቢስነት ከመመዘን በፊት በዚያን ዘመን የታየውን ከልክ ያለፈ ጀግንነት ምክንያት መጠየቅ ያስፈልጋል:: የዚህ የጀግንነት ሚስጥር ምን ነበር?? ምናልባት ብዙ ትንተና እና ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ ሊሆን ይችላል:: ብዙ ምርምር የማይጠይቀው ነገር ግን የሀገር ፍቅር ለክብር እና ለነጻነት የሚሰጥ ዋጋ ከምንም በላይ ደሞ በፈጣሪ ላይ ያለ ጠንካራ እምነት ይመስለኛል:: ክርስቲያኑ ከልቡ ክርስቲያን ነው:: እስላሙም እንዲሁ ከልቡ እስላም ነው:: ስለ ነበረው የእምነት ጥንካሬ ያንጸባርቃሉ ያልኳቸውን ልጥቀስ:-

  ...በጦር ሜዳም ሳይቀር መጸለይይቻላቸው ዘንድ እያንዳንዱ ከፍ ከፍ ያለ ሹም ሳይቀር የራሱን ቄስ የራሱን ነብስ አባት ይዞ ነው ወደ ጦር ሜዳ የመጣው:: ቄሶችም ሆኑ ሼኮች የራሳቸውን የሆኑ ወታደሮች ያላቸው ከመሆኑም በላይ በጦር ግንባር ሜዳም ጠመንጃ ይዘው ይሳተፋሉ …
  ….በጸሎታቸውም ያገራቸውን ድንበር በማን አለብኝነት ደፍሮ የመጣን የጠላት ሰራዊት ከሀገራቸው ጠራርገው ያወጡ ዘንድ እግዚያብሄር ብርታቱን ሰጥቶ ይረዳቸው ዘንድ ሳይታክቱ በየምሽቷ ይለምናሉ: ይማጸናሉ:: ... ' ጦራችንን ሰብቀን ጎራዴያችንን መዝዘን ጠመንጃችንን አንስተን እናባርራቸዋለን::ገጽ 166-167 [በእግዚያብሄር/በአላህ ርዳታ መሆኑ ነው::]

  ReplyDelete
  Replies
  1. AnonymousNovember 27, 2013 at 7:48 PM

   በዘመነ ግሎባላይዜሽን መልካም ከሆነው ከሳይንስና ከቴክኖሎጂው እድገት በተጨማሪም ጥንት የነበረው መልካም ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ሆኖ በአዲስ ሰይጣናዊ ነገር እየተተካ ያለ ነው የሚመስለው፡፡እናም በእኛ በሀገራችን ውስጥም ብቻም ሳይሆን በተቀረው በሰለጠነው አለም ውስጥ ጭምር እናትነት አባትነት ባል ሚስት ወንድ ሴት ልጅ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጎረቤት ማህበረሰብ እቁብ እድር ሀገር ባህል ሃይማኖት ፍቅር እውነት ተስፋ ወዘተ የነበረው መልካም ነገር ሁሉ እንዳልነበር እየሆነ በአዲስ መጤ ሰይጣናዊ ነገር እየተተካ ነው ያለው፡፡ብዙዎቻችን ጊዚያዊና አማላይ በሆኑ ብልጭልጭ ነገሮች ከመዝናናትና ከመደንዘዝ በዘለለ ከበስተጀርባ ምን አይነት ሰይጣናዊ ነገር እየተደረገ እንደሆነ በቅጡ የገባን አልመሰለኝም፡፡ ለማንኛውም ዲያቆን ዳንኤል የፃፈው መልካም ነገር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን በዘመነ ግሎባላይዜሽን በአጠቃላይ በሀገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባነሳኸው ጉዳይ ላይ አንድ ወዳጄ ከዚህ በፊት የላከልኝን የመረጃ ምንጭ በትእግስት እረጋ ብለህ ብታነበው ምን እየተደረገ እንደሆነ የተወሰነ ተጨማሪ ግንዛቤ ይኖርሃል ብዬ አስባለሁኝ፡፡በዚህ አስቸጋሪና ቀውጢ ዘመን ኢትዮጵያዊ ሙሴዎችንና የሙሴን እናት መሰሎች ማግኘት የከበደው ለዚህ ነው፡፡

   http://www.savethemales.ca/001904.html
   http://www.savethemales.ca/200202.html
   http://www.savethemales.ca/001170.html
   http://henrymakow.com/ten_signs_we_are_satanically_p.html
   http://henrymakow.com/2013/09/the-end-of-woman.html
   http://henrymakow.com/220801.html
   http://henrymakow.com/2013/03/what-is-love.html
   http://henrymakow.com/001189.html
   http://henrymakow.com/would-you-take-a-bullet-for-a-feminist.html
   http://henrymakow.com/000319.html
   http://henrymakow.com/they-took-our-women.html
   http://www.henrymakow.com/the_effect_of_sexual_deprivati.html
   http://henrymakow.com/feminist_at_the_end_of_her_rop.html
   http://henrymakow.com/251001.html

   ከምስጋና ጋር   Delete
  2. thanks a lot my brother/sister

   Delete
 34. ,,,Patriotism is not a luxury, an illusion or mere love for adventure as some tend to put it. It’s a response to a situation created by others. It’s a pursuit of dignified life and the sanctification of freedom -not ’personal freedom’, if there is such a thing in the real sense of the phrase. Patriotism is an act of doing something great with one’s life in the interest of freedom of your people whose values you cherish most.

  Patriotism has to be distinguished from pursuit of personal desires and goals so strongly (often times at the expense of collective desires, societal values and even the values of being human) in a fashion we observe in Hollywood movies where a loner wins his battle at the end of the day and is celebrated as a person of ‘extraordinary’ achievement. Once celebrated, the celebrated could be used in the conquest of collective values and creation of other loners. That is not patriotism.

  Patriotism is not born out of the desire to create personal wealth or fame. It springs from spiritual and philosophical approach to life, and attachment to society, not detachment from society. Personal desire that is not related to the task of defending the interest, freedom and dignity of one’s own people has to vanish first for the noble virtue of patriotism to flourish. Patriotism is a virtue that people with great insight about life and imagination pursue. It’s partly divine in that all the great messengers in different religious traditions lived up to the ideals of patriotism-living for what they believed to be true and something that benefit others ,not just self. In an organic society patriotism is a way of life and mass action. Patriotism is not an enterprise of loners! Patriotism is essentially a rejection of mediocrity in life. It is an act of defiance of what is ordinary and pursuit of the extraordinary. Patriotism is real, deep, fulfilling and rewarding in terms of satisfaction. He who is selfish cannot be a patriot.

  Selfishness is at odds with values essential for patriotism. Selfishness is the work of illusion. It tends to impel the thinking that what is noble is ‘self.’ For selfishness, the ‘collective’ is a source of threat and yet a means to achieve an end for ‘self.’ For patriotism the ‘collective’ is a friend, not a source of threat. Selfishness emanates from, among other things, greed and immorality, which could in a way be related to atheism of a sort.

  Selfishness pretends to be genius and rational while it is an ultimate expression of irrationality. Selfishness could sell ones country out to others- irrespective of the way it manifests itself. The destructive nature and aspects of selfishness is not so much related to ‘bounded rationality.’ It’s related to illusion of faith in “self.” Selfishness in matters related to the interest of one’s own country is fundamentally a declaration (whether it is in action, word or some other forms) that one do not belong to the society she/he came from. It could be a way of looking society, from which one came from, down. It could be an act of venerating “self” and venerating the party that one thinks is in the service of ‘self’ as distinct from society or country. Selfishness sounds like affirming “self” while it is denial of ‘self’? What is “self” without the whole? What is in selfishness is fear. What is in Patriotism is faith and courage.dimetros birku

  ReplyDelete
  Replies
  1. The best eye opening comment i have ever read in Ethiopian websites.Why we gradually evolve to loose our humanity tune and classical and intrinsic values and virtues?
   በዘመነ ግሎባላይዜሽን መልካም ከሆነው ከሳይንስና ከቴክኖሎጂው እድገት በተጨማሪም ጥንት የነበረው መልካም ነገር ሁሉ እንዳልነበረ ሆኖ በአዲስ ሰይጣናዊ ነገር እየተተካ ያለ ነው የሚመስለው፡፡እናም በእኛ በሀገራችን ውስጥም ብቻም ሳይሆን በተቀረው በሰለጠነው አለም ውስጥ ጭምር እናትነት አባትነት ባል ሚስት ወንድ ሴት ልጅ ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ጎረቤት ማህበረሰብ እቁብ እድር ሀገር ባህል ሃይማኖት ፍቅር እውነት ተስፋ ወዘተ የነበረው መልካም ነገር ሁሉ እንዳልነበር እየሆነ በአዲስ መጤ ሰይጣናዊ ነገር እየተተካ ነው ያለው፡፡ብዙዎቻችን ጊዚያዊና አማላይ በሆኑ ብልጭልጭ ነገሮች ከመዝናናትና ከመደንዘዝ በዘለለ ከበስተጀርባ ምን አይነት ሰይጣናዊ ነገር እየተደረገ እንደሆነ በቅጡ የገባን አልመሰለኝም፡፡ ለማንኛውም ዲያቆን ዳንኤል የፃፈው መልካም ነገር እንዳለ ሆኖ ነገር ግን በዘመነ ግሎባላይዜሽን በአጠቃላይ በሀገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባነሳኸው ጉዳይ ላይ አንድ ወዳጄ ከዚህ በፊት የላከልኝን የመረጃ ምንጭ በትእግስት እረጋ ብለህ ብታነበው ምን እየተደረገ እንደሆነ የተወሰነ ተጨማሪ ግንዛቤ ይኖርሃል ብዬ አስባለሁኝ፡፡በዚህ አስቸጋሪና ቀውጢ ዘመን ኢትዮጵያዊ ሙሴዎችንና የሙሴን እናት መሰሎች ማግኘት የከበደው ለዚህ ነው፡፡

   http://www.savethemales.ca/001904.html

   http://www.savethemales.ca/200202.html

   http://www.savethemales.ca/001170.html
   http://henrymakow.com/ten_signs_we_are_satanically_p.html
   http://henrymakow.com/2013/09/the-end-of-woman.html

   http://henrymakow.com/220801.html

   http://henrymakow.com/2013/03/what-is-love.html

   http://henrymakow.com/001189.html

   http://henrymakow.com/would-you-take-a-bullet-for-a-feminist.html

   http://henrymakow.com/000319.html

   http://henrymakow.com/they-took-our-women.html

   http://www.henrymakow.com/the_effect_of_sexual_deprivati.html

   http://henrymakow.com/feminist_at_the_end_of_her_rop.html

   http://henrymakow.com/251001.html

   ከምስጋና ጋር

   Delete
 35. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡

  ReplyDelete
 36. Yehywet Kalune Yaseman Dn.Daniel kebret Edmena Tena Yestn Yedengele leg Eyesus kirestos!!!

  ReplyDelete
 37. ‹ሕዝቤ ከሚጠፋ እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ› ያሰኘችው እናቱ ነች፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yes, gelbetesh kanebebeshew!...endihe endile yaderegechewe ale enji endihe alech belwale..hohooo sewe endate newe yemiyanebew bakachehu :)

   Delete
 38. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው? ጀግናዋን የሙሴን እናት ፈልገን እንድናገኛት የሷን ተግባር የሚሰሩ እናቶች ይስጠን ቃለ ህይወት ያሰማህ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 39. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው? ጀግናዋን የሙሴን እናት ፈልገን እንድናገኛት የሷን ተግባር የሚሰሩ እናቶች ይስጠን ቃለ ህይወት ያሰማህ ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 40. ዳ/ዳንኤል እግዛብሄር በዘመናት ሁሉ ነብያትን እንዳስነሳ አንተም የዚህ የመረጃ ዘመን ነብይ ነህ፡፡ ጌታ ይባርክህ

  ReplyDelete
 41. ነብዩ ሙሴ (Mosses )
  የተወለደው በግብጽ አገር በአባይ ወንዝ አቅራቢያ ነው። ያደገው በፈርዖን ቤተ መንግሥት ነው። የፈርዖን ልጅ በወንዝ ተጥሎ ስላወጣችው ሙሴ አለችው። (ሙሴ ማለት መዋሴ፣ መዋስ፣ መዳን፣ ነጻ ማውጣት ማለት ነው። ዋስ ከወንዝ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ከእስራት፣ ከእርዛት፣ ከባርነት፣ ከግዞት፣ ከስደት የሚያወጣ ሁሉ ዋስ ሊባል ይችላል።)ጊዜው እሥራኤላውያን በባርነት፣ በከባድ የሥራ ጫና በሚማቅቁበት ወቅት ነው። ያን ጊዜ ግብጻውያንም ሆኑ ባሮቻቸው የሚያመልኩት የጥጃን ምስል ነበር። ይህንም የምንገነዘበው ከግብጽ እንደወጡ በሲና ተራራ አቅራቢያ በአሮን አማካኝነት ከወርቅ የተሰራ ጥጃ ሰርተው የአምልኮት ስርዓት በመፈጸማቸው ነው። “ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው። ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉት።” “አሮንም። በሚስቶቻችሁ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው።” “ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት።” “ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።” (ዘጸ 32: 1-4) ሙሴ የአርባ አመት እድሜ ሲሆነው የግብጻዊ በመግደሉ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደደ። አርባ አመት በኢትዮጵያዊው ካህን በራጉኤል(ዮቶር) ቤት በእረኝነት እያገለገለ ተቀመጥ። የራጉኤልን ልጅ ሲፖራን አግብቶ ሁለት ልጆች ወለደ። እግዚአብሔርን ማምለክን፣ የመመስዋእት፣ ማቅረብ አገልግሎትን፣ ታሪክን፣ ህግን፣ ፍርድ መስጠትንና የመሳሰሉትን እውቀትና ጥበብ ሁሉ ከአማቱ ከራጉኤል(ዮቶር) ተማረ። ይህንም የምንገነዘበው እሥራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኋላ ሙሴን አማቱ ኢትዮጵያዊው ካህን ሲመክር በማስተዋላችን ነው። “እንዲህም ሆነ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር።” “የሙሴም አማት በሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ባየ ጊዜ። ይህ በሕዝቡ የምታደርገው ምንድር ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመው ሳሉ አንተ ብቻህን ስለ ምን ተቀምጠሃል? አለው።” “ሙሴም አማቱን። ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ” “ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው።” “የሙሴም አማት አለው። አንተ የምታደርገው ይህ ነገር መልካም አይደለም።” “ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም።” “አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ” “ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው።” “አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው።” “በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ አውራውን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ታናሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልልሃል።” “ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል።” “ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፥ ያለውንም ሁሉ አደረገ።” (ዘጸ 18: 13-24) ከዚህ ንግግር የምንገነዘበው ሙሴ የአምልኮት ህግንና ስርዓትን ለአርባ ዓመት የተማረው በአማቱ በኢትዮጵያዊው በዮቶር ቤት መሆኑን ነው። እውነቱ ይህ ሁኖ እያለ ሌላ ታሪክ መተረኩ ለማን እንደሚበጅ አይገባኝም። ሌሎች እራሳቸውን ከፍ ከፍ ለማድረግ ብለው የእኛን ታሪክ ሲያቃልሉና ሲያናንቁ፥ የሚናገሩትን ተረት ተረት እውነት መስሎን ደግመን ልንናገረው አይገባም፡ ታሪክና ሕዝብ ይወቅሰናልና።
  እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን። አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Celleab7 , I appreciate. GOD bless both of you.

   Delete
  2. የርስዎ አስተያየትና እርማት በጣም ተገቢ ነው። ሙሴ ከግብፅ ከተሰደደ በኋላ ላገኘው እውቀትና ጥበብ ትክክለኛ መልስ ነው። ዲያቆን ዳንኤል ደግሞ ወግ ጸሐፊ በመሆኑ ሊያስተላልፈው ለፈለገው መልእክት (የእናትን ድርሻ ማጉላት) እንዲመቸው ሙሴ ከግብፅ ከመሰደዱ በፊት የራሱንና የወገኖቹን ማንነት የተረዳበትን መንገድ ይመስላል ወደ እናቱ የወሰደው። ሆኖም ለአንባቢዎች ሙሴ እውቀቱንና ጥበቡን ሁሉ ያገኘው ዲ/ን ዳንኤል በጠቀሰው መንገድ ብቻ እንዳይመስል በኢትዮጵያዊው ዮቶር የተደረገውንም መጥቀሱ ተገቢ ነው - የእናትን የጎላ ድርሻም አያሳንሰውም።

   Delete
 42. ዳኔ ፤እድሜና ጤና አመኝልሕ አለሁ።ገሩም እይታ ነው ። ማን ያወቃል የሙሴ አናት በዚሕ 40ኛው ዓመት ማብቄያ ብትገኝ ? የኢትጵያ ሕዝብ ስደት ከጀመረ 39 ዓመት አስቆጠረ ፤ሙያ በልብ ይሁንና ጠንክረን እንጸልይ።በረታ

  ReplyDelete
 43. የዘመንዋ የሙሴ እናት በኢትዮጵያ አሁን በቅርብ ትመጣለች የልጀቿን ጩኸት ሰምታ፡ እኛ ብቻ በርትተን እንፀልይ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ዘረኛ መንግስት በቃችሁ ይበለን፡፡

  ReplyDelete
 44. Dn Daniel Thanks A Lot!!! This is Timely
  We all need to cry and Pray to get Mussess and His mother at the Right Time. By then We all Understand that the Belessing of the almighty God Is in our Big country. Thanks Daniel Onec Agian. God Beless Ethiopia. I wish I could write This comment in Amharic. But I have the probelem to get the Softwear.
  Egiziabher Ethiopian Yibark. ETHIOPIA LEZELALEM TENUR!!!

  ReplyDelete
 45. dani really amazing

  ReplyDelete
 46. bless you Daniel Ihope God will top up you with more and more wisdom.

  ReplyDelete
 47. እንዲህ ያለች እናት በሌለችበት፣ እንዲህ ያለ ሙሴ መፈለግ ጉም መዝገን ይሆናል፡፡ እኛ የምንለፋው ሙሴን ለማግኘት ነው፡፡ የሚበጀን ግን ጀግናዋን የሙሴን እናት ማግኘት ነው፡፡
  የሙሴ እናት የት ነው ያለሽው?

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን።

  ReplyDelete
 48. Diaqon Danel geta yebarkrh enatachen mariamtakbereh yegnas Musse ena enatun medehanete-alem erasu yamechachelen yegna negerma beyeaktachaw bealem zuria rehab torenet sedet werdet ena mot honal

  ReplyDelete
 49. ኧይ ዳንኤል የሙሴን እናት ፈልጉ ትላለህ ? ወዳጆችህን አትድከሙ በላቸው
  በ2007 ምርጫ ዶ/ር ቴዎድሮስ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ይመረጣሉ……..እናም የዳግማዊ አጼ ቴዎድርስ ትንቢት ይፈጸማል…….ኦሮማይ

  ReplyDelete
 50. what a great article!!! we all are accountable in taking the place as a mother for Mosses. That means we all are accountable in creating a generation with love for its nations and for the people. We have a responsibilities for our children to make them know who they are and love their county and die for their country. we don't have to look further , we just have to find it in ourselves the strength and the courage of our love for our country and create more "Mosewoch " for our beloved country. may God help us to have more like Mose's Mother, we so very much need that.

  ReplyDelete
 51. "ስትከፍተው የሚያምር ወንዝ ልጅ አገኘች" Hi daniel could you edit this article please thank you.

  ReplyDelete
 52. Dane endante ayentu yabezalen.

  ReplyDelete
 53. መምህር እግዚብሔር ይስጥልን፡፡ ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 54. i thank u Dani it was really wonderful........ i was to ask abt the use of the phrase የኤርትራ ባሕር in our church. .....as we all know the name Eritrea is Italian and recent. so how can we relate it with the history of Moses ?

  ReplyDelete
 55. እናቶች የሚማሩት ካሉበት ነባራዊ አለም ነው ፡፡ የሙሴን እናት ኢትዮጵያ ውስጥ ለመፍጠር ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊነታቸው ለሰሩ፣ ለታገሉ፣ ለቆሰሉ፣ ለሞቱ፣በቅንነት ላገለገሉ የኢትዮጵያዊነት ማስታወሻ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል(በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለፉ በቅርቡ ከንጉሰ ነገስቱ እሰከ ኢሃዲግ ከተራ ወታደር እስከ ሹማምንት ያለፉትን እና ያለፈባቸውን ማሰብ ነው፡፡) አንድ ሰው ለኢትዮጵያዊነቱ ሲሰዋ ቅድሚያ ለሃገር በሚል መርህ ቤተሰቡን ሰውቶ ነው፡፡ እንደሙሴ እናት ሁሉ የሙሴ ሌሎች ቤተሰቦች ሁሉ ሙሴን የመሰለ ታሪክ ሰሪ እንደቤተሰብ አባልነት ሊያገለግላቸው ሲገባ ለብዙሃኑ በመስዋእትነት አጥተውታል፡፡ አንድ ሰው ለታሪክ አደራ ሲወጣ የግለሰባዊ ሃለፊነቱን የሚረከብለት የህዝብ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል፡፡ በኢትዮጵያ ደረጃ በተለያዩ መንግስታት ታሪክ ተተኪው ያለፈውን ‹‹የሞተ ገዳይ›› የመስል ባለበት ማሳደድ እንጅ፣ ኢትየጵያዊቷ እናት የባለታሪኩ ምክንያተዊ ትግል ከግምት ውስጥ ገብቶ ፍጻሜው ሲያምር አላየችም፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊያን ለሀገራቸው ብዙ ጉዳት ከደረሰባቸው በኋላ እሰከ ቤተሰባቸው የት እንደወደቁ በማይታሰቡበት ሁኔታ የኢትዮጵያዊ ሙሴ እናት ለኢትዮጵያዊ ሙሴ ምን አይታ ምን ትንገረው????
  ዳኒ፡- ህዝቡ አደራ ባላ ሳይሆን ባለመቀናጀት ምክንያት አደራ ባላ እየሆነ ያለበት ፣ ተተኪ ለማፈራት ትንሽም ቢሆን የሰሩትን ማድነቅና መንከባከብ ግድ ሆነበት ሁኔታ ላይ ነው ያለነው፡፡
  ከቻልክ (ደግሞ ትችላለህ) አንድ ህዝባዊ ማእከለነት ያለው ህዘባዊ ምላሽ መስጠት የሚችል ‹‹ፋውንዴሽን›› ተቋቁሞ በህዝብ ድምጽ እና ይሁንታ የታሪክ ሰሪ ጀግኖች ቤተሰባዊ ሃላፊነቶችን ሕዝቡ የሚቀበልበትና የሚወጣበት መንገድ ቢቀየስ የሙሴ እናቶች እንደ አሸን፣ ብዙ ሙሴዎች እነደ ከዋክብት ካልፈሉ ከመጻፊያ ጣቴ ጸጉር ይነቀል፡፡
   ጊዜው በፈጠረው ቴክኖሎጂ (ማህበራዊ ድህረ ገጽ)
   ጊዜው የሚጠይቀውን የቤት ስራ ተሰጥቶሃል፡፡ ስራው፡፡
  የአገልግሎት ዘመንህን ሀያሉ እግዚአብሔር ያብዛልህ!!!

  ReplyDelete
 56. ሰውነቱን ፈርዖን ሲያሳድገው ልቡን እናቱ ናት ያሳደገችው፤ ምግቡን ፈርዖን ሲሰጠው ጥበቡን እናቱ ናት የሰጠችው፡፡

  ReplyDelete
 57. ዋናው እኛ በርትተን ወደፈጣሪ መጸለይ ነው ሙሴን እና የሙሴን እናት አንድ ቀን እናገኛቸዋለን።

  ReplyDelete