Monday, November 11, 2013

‹የዜግነት ክብር›

ኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር ሲዘመር ከሚያነሣቸው ነጥቦች መካከል ‹የዜግነት ክብር› የሚለው የተለየ ስሜት ይሰጠኛል፡፡ ለአንዲት ሀገር ሰው ትልቁ ዋጋው ‹የዜግነት ክብር› ነው፡፡ ሀገር አለኝ ብሎ ማሰብ፤ የሚያስብልኝ፣ የሚጮህልኝ መንግሥት አለኝ ብሎ ማመን፤ የእኔ ጉዳይ ጉዳዩ የሆነ አካል አለ ብሎ መመካት፡፡
እንዲህ እንደ ሰሞኑ ያለ፣ በሳዑዲ እየተፈጸመ እንዳለው ነገር ያለ ስናይና ስንሰማ ደግሞ ‹የዜግነት ክብር› መዝሙር ብቻ ይሆንብናል፡፡ ‹ኢትዮጵያዊ ማለት› ብለን ልንተረጉም ይቸግረናል፡፡ ማንም  የአራዊት ጠባይ ያለው ሁሉ ተነሥቶ መንገድ ላይ ደሙን የሚያፈሰው፣ እግሩን የሚቆርጠው፣ የሚደበድበውና በፈለገበት ቦታ የሚያሥረው ከሆነ፣ ይህማ እንኳን የዜግነት ክብር የስደተኛነት ክብርም አላገኘም ማለት ነው፡፡ ሀገር አልባ ጂፕሲዎች ከሚደርስባቸው ግፍ በላይ ባለሀገሩ ኢትዮጵያዊ ከደረሰበትማ ‹የዜግነት ክብር› የቱ ላይ ነው፡፡ ደግሞስ በአንድ ኢትዮጵያዊ ላይ ሰው መሆኑን የሚያጠራጥር ከዚህ በላይ ምን ሊደርስበት ይችላል፡፡
ይህ ነገር ሁለት ነገሮችን እንድናስብ ማድረግ አለበት፡፡
1.   የመንግሥት አካላት በየሀገሩ ያሉትን ዜጎቻችንን ለማወቅ፣ ለመከታተልና መብታቸውን ለማስከበር ያላቸውን ብቃት
2. እንዲህ ዓይነት ነገር በሌላ ጊዜና በሌላ ሀገር እንዳይደገም ልናደርገው የሚገባንን ዘላቂ መፍትሔ
የዜግነት ክብር የሚኖረው አንድ ዜጋ የትም ቦታ ቢኖር የዜግነት መብቱ እንዲከበርለት፣ በዜግነቱ እንዲኮራና የዜግነቱንም ግዴታ እንዲወጣ ሲደረግ ነው፡፡
ይህ የዜግነት ክብር እንዲጠበቅ መንግሥት፣ የዲፕሎማቲክ ሚሽኖች፣ የዲያስጶራ ማኅበረሰቦችና ጠቅላላው ሕዝብ ከዚህ ጊዜ የተሻለ የመንቂያ ጊዜ አያገኙም፡፡ ይህንን ለማሰብ እስከዛሬ የፈሰሰው ደም በቂ ካልሆን፤ የሚያስፈልገን የስንት ሰው ደም ይሆን?

50 comments:

 1. የፈሰሰው ደም በቂ ካልሆን፤
  የሚያስፈልገን የስንት ሰው ደም ይሆን? yonas abebe

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምን የዜግነት ከብር አለን ማንነታችን ከተዋረደ መብታችን ከተገፈፈ ኢትዪጵያዊነታችን ከላያችን ከተነጠቅን ቆየን እኮ ጐበዝ? የፈሰሰው ደም የሚፈሰውም ደም አይበቃም አልበቃቸውም ።እሄንን ጉድ ሳያዩ ያለፉ ጀግኖች አባቶቻችን እንዴት እድለኞች ናቸው እራሳቸውን ሰውተው ለልጆች ያቆዯትን ሀገርና ህዝብ አንገቱን እንዳይደፋ ቀና ብሎ እንዲሄድ እኮ ነበር አባቶቻችን የለፉት ዛሬ ታሪክ ተቀይሮ ።ስቦ ያስገቡት ስቦ ያወጣል እነረዲሉ እሄው ዛሬ የዜግነት ክብር ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በስደት ይሞታል አውሬ እንደበላው እንስሳ በየመንገድ ይጉተታል።እኔ በአረብ አልፈርድም መክኒያቱም ባለጌ ነው ለዚህ ላበቂን ባዳ ወያኔ ነው ።ሰው ቤቱን እራሱ ከላስከበረው ጉረቤቱ ሊያስከብረው አይችልም።ወገኔም ይሄው በችግር እስከ ሞት ድረስ ወጦ ቀረ ።እሄ ጉዳይ እኛው ካላቆምነው ይቀጥላል።የኛ ጠላት ወያኔ ነው አረብም አይደለ ቅማጩን እያንጠበጠበ በነጠላ ጫማ በቁምጣ ገብቶ ዛሬ እሱ ናሪ የኢትዮጵያ ልጆች ተሰደው የመከራው ቀማሽ የምንሆንበት ምክንያት አልገባኝም ።ለመሆኑ አንድ ጥያቄ አለኝ ለአንባብያን ሙሉ ኢትዮጵያ የማንናት?እኔ እደሚገባኝ የሁላችንም ናት ጀግኖች የሞቱልን ለሁላችንም ነው። ታዲያ ምነው በሀገራችን ሁለተኛ ዜጋ ከሁለተኛም በታች ስንሆን ዝም ብለን እናያለን ደሞ የኛን ሁለተኛም ከዛም በታች አደሆን የሚነግሩን ስበን ያስገባናቸው አሁን ስበው ብትንትን አድርገው ያስወጡን ምን እስኪያረጉን ነው የምንጠብቃቸው ምነው ጉበዝ ሞትኮ ክብር አለው እንደ ጀግኖቻችን እዴው ጨው ሲበዛ ይመራል እኮ አይበቃም! እነደዚህ አይነቱን እየሰማንና እያየን ከምንኖር ምናለ ያለቀው አልቆ ክብራችን አስመልሰን ለትውልድ ዜግነትን ሰጠን በናልፍ ወገን የተዋረደውን ክብራችን ምናስከብረው እኛ ን አንድ ሁነን ።ማንም አያስጠብቅልንም ወያኔማ አላማው እሄ ስለሆነ ተሳካለት ምን ብሎ ለዜጋ ያስባል አንዴ ባህር አዴ በበረሀ አሁን ደግሞ በሳውዴ እያለ ቁጥር ይቀንስ እጀ ለሱማ ሰርግና ምላሽ ነው ።መጀመሪያ መንግስት ሲኖር እኮነው?እና ወገን እነሱ ቡዙ ሲያደርጉን እኛ ምላሽ አንሰጥ ተስማምቶናል ግዙን የምንል እኮ ነው የሚመስለው።አሁንም የአንድ ሰሞን ዜና ሁኖ ያበቃል። ማለቂያም ለው ነው የምለህ ወገኔ ምናሳልቃቸው እኛ ካልሆን ያልቃል ብለህ እዳትሞኝ በያለህበት ተነስ ።ቀን እስኪያልፍያባትህ ባሪያ ይግዛህ ይባል የለ ።ደሞ ባንዳና ባሪያ በታሪክም የለ ኢትዮጵያን ገዝቶ አያውቅም በቃ እንበለው።ባለጌን ባለጌ ማለት ያስፈልጋል ።በርግጥ የኢትዮጵያ ልጆች ትግስ ፍቅር አስተማሪም ናቸው ባለጌ ግን ሁሌም አይ ማርም ።ለባለጌ መዳህኒቱ ሁላችንም ነን።መዳህኒቱም መሰጠት ያለበት አሁን ነው ቡዙ ሰው ታሟል ከመሞቱ በፊት መድረስ አለብን።የገርማል የሳት ለጂ አመድ እንዲሉ።እንዴው ወያኔ ወንድ ሆኖ ይሆን እዲህ የሚሆነው? ወይንስ እኛነን እድሜውን ምናራዝመው?እባክህ ወገን ተነሰ ተነሰ ተነስ! !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! አባ ኮስትር በላ ቸር ያሰማን።

   Delete
  2. ና ጀምር ጎበዝ… 8000 ኪ.ሜ ላይ ሁኖ አይደላም መፎኮር!!!

   Delete
  3. yes, Kuch blo afih endametalih menager betam kelal new..."if we elect you to be the Ethiopian Prime Minister Right Now Today, at the time(moment) this invitation to be Ethiopian Prime Minister, what would you do to Overcome all the Issues of Ethiopians and how would you implement it, and how long would it take you to accomplish it...???" Keboro be sew ej yamr Siyzut yadenagr yemibalewn teret minim semteh weym mesleh atawkim yan yahl buzu gize ke Bete kristyan abatoch gar sitnor (rasih endemtlew Dn. Daniel)...EgziAbHear Bebale sltanoch (Hager Meriwoch) lay Afachinin ena Ejachinin mesenzer titen rasachinin ena sirachinin endnmeremir yirdan...AMEN!!! why? Because Saying IS ONE, BEING WHAT YOU SAY IS ANOTHER.... .

   Delete
 2. በወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው ስቃይ ልብ ይነካል። ሁሉም በየማሕበራዊ ድረ፡ገጹ ስሜቱንና ተቆርቋሪነቱን እየገለጸ ነው። ይህ መልካም ነው።

  አንድ ግን የሚያበሳጭ ነገር ታዘብኩ። ግብዝነትን ታዘብኩ። እነዚህ ወንድሞቻችንስ ሃገራችሁ አይደለም ተብለው የተባረሩት ከባእድ ሃገር ነው ምንም እንኳ ድርጊቱ ተገቢ ባይሆንም። ምነው በገዛ ሃገራቸው(ኢትዮጵያ) ውስጥ እናንተ ከሰሜን(አማራ) የመጣችሁ ሕገ ወጦች ናቸው ተብለው ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች፣ሕጻናት፣ልጆች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲሰደዱ፣ ሲሞቱ፣ እናቶች በየዱሩ ሲወልዱ፣የእንግዴ ልጃቸዉን ቀበሮ ሲበላው፣ በሃገራቸው ላይ ስደተኛ ሲሆኑ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም ምንም ያላለው ሁሉ አሁን ሲጮህ ፍጹም ግብዝነትን አየው።

  በገዛ ሃገሩ ስንቱ ሁለተኛ ዜጋ፣ ስንቱ ስደተኛ እየኖረ እንደሆን ያደባባይ ምስጢር ነው።ኢትዮጵያን ከሚያስተዳድሯት ባእዱ የሳዉዲ መንግስት በእጅጉ ለኢትዮጵያን የተሻለ ነው። አይ ግብዝነት

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think you are right! Your comments show how this author is hypocrite. He did forget the suffering of his ethnic group since long period of time because of marriage relationship, benefit obtained from government and fear of truth(prison)

   Delete
  2. I know Dn. has better or equal understanding than those of our fiends who have cried to stop the injustice against Amara people. I could not imagine why he kept silent when the people intentionally displaced and impoverished. What does spiritual teaching mean to you Dn. Daniel?

   Delete
  3. በአኖኒመስ እንዲህ አይነት አስተያየት ከመስጠት በላይ ምን ግብዝነት አለ?

   Delete
  4. በየትኛው መድረክ ይሆን ሀሳብን በነፃነት መግለፅ የሚቻለው።አንተ ደግሞ በ Anonymous ሀሳብመን መግለፅ ግብዝነት ነው ትለናለህ ሰው ግብዝ ለሆመ በመጀመሪያ ሀሳብን መግለፅ አይችልም እንዳተ ያለው መለት ነው አንተ ብቻ ሰው ሚለውን እያየህ ነገር ሰንጥቅ አሁንም አልባነንህም? የልቅስ ወሬውን ተውና ሀሳብንም በመግለፅ የምትችለውን ጠጠር ለመወርወር እራስህን አዘጋጂ።አለዚያም ከክፉዏች ዘንድ ከሆንህም ቁርጥህን እወቅና አረፈህ ተቀመጥ።ቀንህ ደርሶል ።

   Delete
  5. አንድ ያልተረዳሀው ነገር አለ፡፡ በዚህ በሰለጠነ ዘመን እኛ ኢትዮጵያውያንን እኮ በገዛ ሀገራችን በዘር በሃይማኖት ወዘተ…በመከፋፈል መጨቆን /በራሳችን ዜጋ ልበልህ/ ከጀመርን ከ20 ዓመት በላይ ሆኖናል በራሳችን መንግስት ስንንገላታ 20 ዓመት አለፈ፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ሰዎች ጽፈዋል፣ታስረዋል፣ ተገለዋል ከሀገር ተሰደዋል…..ይህ ሁኔታ አሁንም እናዳልከው፡-
   (በገዛ ሃገራቸው(ኢትዮጵያ) ውስጥ እናንተ ከሰሜን(አማራ) የመጣችሁ ሕገ ወጦች ናቸው ተብለው ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች፣ሕጻናት፣ልጆች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲሰደዱ፣ ሲሞቱ፣ እናቶች በየዱሩ ሲወልዱ፣የእንግዴ ልጃቸዉን ቀበሮ ሲበላው፣ በሃገራቸው ላይ ስደተኛ ሲሆኑ፣)
   እንደቀጠለ ነው፡፡ የአሁኑ ግን እጥፍ ድርብ ነው ዜጎቻችን በባእዳን ይንገላታሉ መንግስትም ኃላፊነት የሚሰማው ለመምሰል ይሞክራል /ግን የውሸት/ ግን ሓላፊነቱን ለመወጣት ሲፈጥን አይታይም፡፡ ታዲያ እዚህ ጋ ሁሉንም ሰው አነጋገረ የሚጽፈው ጻፈ፣ሚያወራው አወራ፣ እበንባ ያለው አነባ፣ጩኸት የሚችል ጮኸ፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ዲ/ዳንኤልንም ግብዝነት ሳይሆን ያጻፈው ስሜታዊነት ነው ፣ተቆርቋሪነት ነው፡፡ ዲ/ዳንኤል እኮ እኔ አስከማውቀው የደረሰበትን ልዩ ልዩ ጉዳዮች አንስቶ በፊት ለፊት ጽፏል፡፡ አስቲ ነገሮችን ሰፋ አድርገህ እያቸው ግድ የለህም ወዳጄ፡፡ዘመኑ የሚያናቁር ስለሆነብህ ነው፡፡

   Delete
  6. አንድ ያልተረዳሀው ነገር አለ፡፡ በዚህ በሰለጠነ ዘመን እኛ ኢትዮጵያውያንን እኮ በገዛ ሀገራችን በዘር በሃይማኖት ወዘተ…በመከፋፈል መጨቆን /በራሳችን ዜጋ ልበልህ/ ከጀመርን ከ20 ዓመት በላይ ሆኖናል በራሳችን መንግስት ስንንገላታ 20 ዓመት አለፈ፡፡ በዚህ ጉዳይ ብዙ ሰዎች ጽፈዋል፣ታስረዋል፣ ተገለዋል ከሀገር ተሰደዋል…..ይህ ሁኔታ አሁንም እናዳልከው፡-
   (በገዛ ሃገራቸው(ኢትዮጵያ) ውስጥ እናንተ ከሰሜን(አማራ) የመጣችሁ ሕገ ወጦች ናቸው ተብለው ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች፣ሕጻናት፣ልጆች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲሰደዱ፣ ሲሞቱ፣ እናቶች በየዱሩ ሲወልዱ፣የእንግዴ ልጃቸዉን ቀበሮ ሲበላው፣ በሃገራቸው ላይ ስደተኛ ሲሆኑ፣)
   እንደቀጠለ ነው፡፡ የአሁኑ ግን እጥፍ ድርብ ነው ዜጎቻችን በባእዳን ይንገላታሉ መንግስትም ኃላፊነት የሚሰማው ለመምሰል ይሞክራል /ግን የውሸት/ ግን ሓላፊነቱን ለመወጣት ሲፈጥን አይታይም፡፡ ታዲያ እዚህ ጋ ሁሉንም ሰው አነጋገረ የሚጽፈው ጻፈ፣ሚያወራው አወራ፣ እበንባ ያለው አነባ፣ጩኸት የሚችል ጮኸ፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ዲ/ዳንኤልንም ግብዝነት ሳይሆን ያጻፈው ስሜታዊነት ነው ፣ተቆርቋሪነት ነው፡፡ ዲ/ዳንኤል እኮ እኔ አስከማውቀው የደረሰበትን ልዩ ልዩ ጉዳዮች አንስቶ በፊት ለፊት ጽፏል፡፡ አስቲ ነገሮችን ሰፋ አድርገህ እያቸው ግድ የለህም ወዳጄ፡፡ዘመኑ የሚያናቁር ስለሆነብህ ነው፡፡

   Delete
 3. ene behagere balegedelim sosetegna zega hogne endenore tederegiyalehu. yezeginet kiber yelelebet hagere eyenore.............dani bezih guday laye esti ande belene yemotuten geta yimarachewe

  ReplyDelete
 4. It is always sad to see our people treated so badly like they are not even humans. That so sad. The worst part is we heard many stories, still many Ethiopian wish to go to Gulf countries to try their luck, still many brokers wants to sell their brothers and sisters to them, not only the brokers also the parents and families. Sometimes i want to understand that , may be they didn't have a choice , they wanted to change their lives and their families' lives . It is true , there are many cases like that. it is sad to see people migrated just because they wanted more, because what is there is better than being in Ethiopia, because they want to be rich in one moon... " Yeteshale Ken yamitaline". May God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 5. ይህ ዘመን የምጥ ዘመን ነው፡፡እኔ በዚህ ዘመን ሁሌም የሚያስፈራኝ ጉዳይ ወደ ውጭ ሀገር(በተለየይ ወደ አረብ) የሚሄዱ ሰዎች( ክርስቲያኖች ልበል) ጉዳይ ነው፡፡ የሃይማኖት ልዩነቱ እነዳለ ሆኖ አረቦች ለኛ ሀገር ያላቸው ዝቅተኛ አመለካከት(ምንጩም ያው ሃይማኖት ነው) የሆነ ቀን አለመግባባት ሲፈጠር ቁጣው እዚያ ባሉት ኢትጵያውያን ላይ ይነዳል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የአረብ ምድር ለኛ ህዝብ መቀበሪያ እየሆነ የመጣውም ለዚህ ነው፡፡ ግሎባላይዜሽን ለሃይማኖት እንዳንጨነቅ እያደረገን ነው እንጂ የድሮዎቹ ኢትዮጵያዊያን ለሃይማኖታቸው ቅድሚያ ስለሚሰጡ እንዲህ ዓየነት ነገር አየታሰብም፡፡ የሚሞቱትና ደማቸው የሚፈሰው ለሃይማኖታቸው ብቻ ነበር፡፡ ዛሬ ግን የልጅነትን ጸጋ ከሥላሴ ተቀብለን ለዚች ስጋ ስንል ተሰደን ይህ ሁሉ ይደርስብላል፡፡፡፡ በእርግጥ 'የትም ሀገር ሠርቼ ብኖር ምን ችግር አለው' ወይም ደግሞ 'እዚህ ሀገር ውስጥ ሆኜ ከምቸገር የትም ሄጄ እግዚአብሔር እንዳደረገኝ ልሁን' ባዮች ይኖራሉ፡፡ እኔ ግን ወደሰዎች አረብ ሲሄዱ ሁሌም ምቾት አይሰማኝም፡፡ መሞት እኮ አንዳንዴ ሳይሻል አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ቤት ውስጥ አስገብተው ክርህን በጥስ ስለም ቢሉስ? ስለዚህ ይህ የሰሞኑ መከራ አሁን ለመሄድ የሚያልሙትን ሊስተምር ከቻለ መልካም ነው፤፤ሀገር ውስጥ ያለነው እግዚአብሔርን በቁርጥ ህሊና ደጅ ብንጠና የምንሻውን ይሰጠን ነበር፡፡ በርግጥ በማንም መፍረዴ ሳይሆን መጀመሪያ ህይወታችንን ከጌታ ጋር ብናጣብቅ ለምንበላው ባልተጨነቅን ነበር ለማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is hard to say. Only God has power to keep our people.

   Delete
 6. ከዚህ ቀደም በተሰጠው አስተያየት አልስማማም፡፡ ስለዜግነት ክብር እየተወራ ነው፡፡ አንተ የምታወራው ስለሓይማኖት ነው፡፡ አንተ የምታወራው የከርሳቸውን ስሜት እንዲክዱ ነው፡፡ የማይቻል ነው፡፡ መፍረዴ አይደለም ብለሃል፡፡ አይደለም ከማለትህ ያለፈ ምክንያት አላቀረብህም ላለመፍረድህ፡፡ ፈርደሃል! አሁን የተጠየቀው ስለዜግነት ክብር የመንግስት ጥብቅና እስከምንድን ደረጃ ነው? ነው የተባለው፡፡
  የአንድ ሠው የዜግነት ክብሩ እስከምንድን ድረስ ነው? ይህ ብቻ አይደለም ብዙ ብዙ ግፍ ከአገር ውጭ ባለው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ የዜግነት ክብሩን ለማስጠበቅ ይቅርና ከእነዚሁ ስደተኞች የሚገኘውን ዕለታዊ ገቢ ለማስጠበቅ እንኳን መንግስት አስቦ መስራት ነበረበት፡፡ ከአገር ውጭ ያለው ስደተኛ ወደ አገሪቱ የሚያሰገባው ዕርዳታ እንኳ በፐርሰንት ሲሰላ መንግስት ከማንም መጸዋቾቹ ከሚያገኘው የላቀ ነው፡፡ ታዲያ እንደዚህ ያለውን የገቢ ምንጩን እንኳ ለመንከባከብ ቢሞክር ምናለበት?
  ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ጨው ባለዕዳ አይቀበለውም፡፡ መንግስት ለህዝቡ ያለውን ንቀት ባይረዱት ኖሮ ይህንን ግፍ ማናቸውም ባልፈጸሙትም ነበር! አሁን ግን መንግስት ሕዝቡን አዋርዷል፡፡ ሰለዚህም ይህንን ደግሞ አረቦች አስተውለዋል፡፡ ስለዚህ ይኸው በስደተኛው ላይ የተጀመረው ግፍ ይቀጥላል፡፡ እግዚኦ እንበል! አምላክ ካልደረሰልን በቀር ኢትዮጵያዊነትን? እግዚኦ እንበል! የኢትዮጵያዊነትን ክብር የሚያስመልስ እስኪነሳ እግዚኦ አንበል!

  ReplyDelete
 7. በወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የደረሰው ስቃይ ልብ ይነካል። ሁሉም በየማሕበራዊ ድረ፡ገጹ ስሜቱንና ተቆርቋሪነቱን እየገለጸ ነው። ይህ መልካም ነው።

  አንድ ግን የሚያበሳጭ ነገር ታዘብኩ። ግብዝነትን ታዘብኩ። እነዚህ ወንድሞቻችንስ ሃገራችሁ አይደለም ተብለው የተባረሩት ከባእድ ሃገር ነው ምንም እንኳ ድርጊቱ ተገቢ ባይሆንም። ምነው በገዛ ሃገራቸው(ኢትዮጵያ) ውስጥ እናንተ ከሰሜን(አማራ) የመጣችሁ ሕገ ወጦች ናቸው ተብለው ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች፣ሕጻናት፣ልጆች ከመኖሪያ ቀያቸው ሲሰደዱ፣ ሲሞቱ፣ እናቶች በየዱሩ ሲወልዱ፣የእንግዴ ልጃቸዉን ቀበሮ ሲበላው፣ በሃገራቸው ላይ ስደተኛ ሲሆኑ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸም ምንም ያላለው ሁሉ አሁን ሲጮህ ፍጹም ግብዝነትን አየው።

  በገዛ ሃገሩ ስንቱ ሁለተኛ ዜጋ፣ ስንቱ ስደተኛ እየኖረ እንደሆን ያደባባይ ምስጢር ነው።ኢትዮጵያን ከሚያስተዳድሯት ባእዱ የሳዉዲ መንግስት በእጅጉ ለኢትዮጵያን የተሻለ ነው። አይ ግብዝነት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ሆይ ስማኝ ግብዝነት አይደለም ።ክቡር የሆነው የሰው ልጂ ኢትዮጰያዊ በሀገር ውስጥ ቢሰደድ ቢገደል መብቱ ቢገፈፍ ዝም አላልንም በያለንበት ሙስሊም ክርስቲያኑ በአነድ ሆኖ ኢትዮጰያዊነት በአንድነት የተፋፋመበት ወያኔን መግቢያ ቀዳዳ እንዲያጣ ያደረግንበት ለውድቀቱም ስለት የሳልንበት ጊዜ ነው ።የወገኖቻችን ከየ ስፍራው መፈናቀል መነካት ንብ ያለበትን ቀፎነው ሳያውቅ የነካው ንቡም ሊያጠፋው ግልብጥ ብሎ ወጦል ።ይጠፋአልም አይቀርም።እንግዲህ አንተ ባገር የለህ ይሆናል። በሳውዲ ላሉ ወገኖቻችንም መጮህ አይለም እድል ቢሰጥ የለበሰውን ቀሚስ ከላዩ ነበር እየተረተሩ አንገቱን መቅላት አረብም ወንድ ሆኖ ዜጉቻችን ገደለ አሰቃየ የነገን ማን ያውቃል እነሱም እንደልማዳቸው ቀን ጉሎ ኢትዮጵያን በግድነት እድታስጠጋቸው ይማፀኗት ይሆናል።አዲት መንፈሳዊት ዘማሪ እህቴ በመዝሙራ ሊነጋ ሲል ይጨልማል ፣አለው ነገር እግዚያብሔር እንዲህ አብዝቶ ዝም ሲል የሞለውን መዝሙር ስሰማ በሀገሬና በወገኔ የሚመጣውን መከራ እንድችል ያፀናናኛል ።ስለዚህ ለወገን መጮህ ግብዝነት አይደለም።እሄን ልበልና ላብቃ ።ሁሉንም ሙስሊም ወገኖቻችን አይደለም አዳንድ ወገኖች ካለማወቅም ሊሆን ይችላል ሳውዲ ሂደው ከመጡ በሓላ አብራቸው የኖረውን የተወለድበትን ያሳደጋቸውን ህዝብ እንደ እርኩስ የነሱ ሳውዲ ደርሶ መምጣት የበቁ የሚመስላቸው አሉ ግን ስህተት ነበር እሄው ሙስሊም በዜግነት እንኮን አንድ ባይሆን በሀይማኖት አይለያይም ይባል ነበር ታዲያ የሳውዲ ሙስሊሞች ምነው ነኛላይ ጨከኑ?ገን ማለት የፈለግሁት ወገኔ አሁንም አስተውል ከኛ በላይ ለኛ ማንም ደራሽ እንደለለን አውቀን ሙስሊም ከርስቲያን አማራ ኦሮሞ ትግሬ አፍር ሳንል የአዲት ማህፀን ልጆች መሆናችንን እንዲህ ላስደፈረን እንዲሀ ላስገደለን ላዋረደን ጠላታችን ተጠያቂነቱን ለህዋት ለወያኔ ባንዳ ትተን? የአዲት ኢትዮጵያ ልጆች ሁነን አንድነታችን ፣ክብራችን ሰንደቅ አላማችን መጉናፀፍ መቻል አለብን። ያለዚያ ሰውየው ሚስትህ ወለደች አሉ ቢሉት ማንን ወንድ ብላ አለ ይባላል ለነሱ እሄ ምንም ማለት አይደለም 80ሚሊወን አልቆ የወያኔ የህዋት ግሩፕ በኖር ደንታ የለውም መልሱ በእጀችን ነው።እግዚያብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።ቸር ያሰማን፣ከበላይ ነኝ።

   Delete
 8. ወገኖቻችን በስደት ሀገር አለቁ አሉ
  ደማቸው እንደ ዓባይ ወንዝ ፈሰሰ አሉ
  ዓባይስ ሊገደብ ነው የወገኔን ደም የሚገድበው ማን ይሆን?

  የዜግነት ክብር

  በስደትም በሀገርም የዜግነት ክብር ምነው ቅኝቱ አልመታ አለ?

  የታደሉ ሀገሮች በየመንደራቸው ባቡር አስገብተው ልጆቻቸውን “ባቡር መጣ ባቡር ሔደ እያሉ ይጫወታሉ። የኛ ልጆች ግን እስከ መቼ “ውኃ መጣ ውኃ ሄደ፤ መብራት መጣ መብራት ሄደ እያሉ ይኖራሉ?” በሉ በሉ መብራቱ ሳይጠፋ ወደ ፍሬው ልግባ።

  “እኔ የማምነው ሀገሬ ኢትዮጵያ ዘሬም ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነው!!”

  “ጥጋበኛ ዶሮ በለሊት ያዛጋል” ትል ነበር አናቴ። እትዬ ጣይቱም “ከተኛ አንበሳ ዞር ዞር ያለች ጥንቸል ትሻላለች” አሉኝ! እናቴ ለምን በረዥሙ አዛጋህ ማለትዋ ሲሆን አያቴ ደግሞ ለምን በረዥሙ ተጋደምክ ማለትዋ ነበር። እስኪ የእትዬ ጣይቱን እሮሮ ልጋብዛችሁ፦

  ”ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጣልን? “ ተብሎ በታላቁ መፅሐፍ ተጽፏል። ነብር እስከ ዛሬ ድረስ ዥንጉርጉርነቱን አልለወጠም፤ ኢትዮጵያዊያን ግን መልካችንን ከለወጥን ዘመናት አልፈዋል። ”ኢትዮጵያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጣልን? ስንባል እኛ ደግሞ “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር እንደ ነብር ጸጉር” ብለን ዘር በዘር ሆነናል! ደም ከደም ስር ጋር እንደማይጋጭ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ከዘር ጋር አይጋጭም ብንል ሞኞች ነን። አሁን ማን ይሙት ኢትዮጵያዊነቱ ከዘሩ ጋር ያልተምታታበት የት ይገኛል? እዚህ ጋር አንድ እውነተኛ ታሪክ ላውጋችሁ። አንድ ዘረኛ ሰው ነበር አሉ። እናላችሁ ይህ ዘረኛ ሰው ከእርሱ የባሰ ዘረኛ ሚስት አገኘና አገባት። ሲጀመር አንድ ዘረኛ ብቻ ነበር አሁን ግን ሁለት ጥንድ ዘረኛ ሆኑ። እናላችሁ ዘረኞቹ ወላጆች ልጃቸው ለአቅመ ዘረኛነት ሲደርስ አሪፍ ዘረኛ ሴት እንዲጠብስ አደረጉት። እንዲህ ያደገ ልጅ ደግሞ የሀገር ፍቅር ሳይሆን የዘር ፍቅር ይይዘዋል። እናማ አዲስ የተጣበሱት ዘረኞቹ ወላጆቻቸውን ለመምሰል ይሞክራሉ። የጎባጣ አሽከር ጎንበስ ብሎ ይሄዳል፤ ለምንድን ነው ሲሉት ጌታዬን ለመምሰል ነው አለ አሉ። ልጆቹም ወላጆቻቸውን ለመምሰል ዘረኛ ቢሆኑ አይደንቅም። የዘር ፍቅርን የሚያስተምር ወላጅ ሞልቷል፤ የሀገር ፍቅርን የሚያስተምር ወላጅ ማን ይሆን? ከእባብ እንቁላል ርግብ አይፈለፈልም አይደል የሚባለው።


  ልብ ብለን ስናስተውል እራሳችንን ካልፎገርን በስተቀር ዛሬ ዛሬ ሁላችንም በዘር በሽታ ተመትተናል። አንዲት ክብርት ኢትዮጵያ ሳትሆን በየልቡናችን ብዙ የዘር ሀገር አሉ። እንደ ዶሮ ብልት ለአስራ ሁለት መገነጣጠል የሚል ሐሳብም የሚመጣው በዘር በሽታ ስንመታ ነው። ይህ ደግሞ ያስፈራል። የተነቃነቀ ጥርስ ሳይወልቅ አይቀርም አሉ።


  እኔ ብናገር አያምርም፤ ይሄ አህያ ታሟል አለ ጅብ! እስኪ እኔ ከምናገር እትዬ ጣይቱ ይናገሩ። እትዬ ጣይቱ የሚናገሩት አስደሳች አባባል አለ “እኔ የማምነው ሀገሬ ኢትዮጵያ ዘሬም ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነው!!” የምትል አስደሳች አባባል አለቻቸው። እስኪ እኛም ይልመድብን። እስኪ ባለሥልጣኖችም ይልመድባችሁ። እስኪ ሁላችንም “እኔ የማምነው ሀገሬ ኢትዮጵያ ዘሬም ኢትዮጵያዊ መሆኔን ነው!!” እንበል።


  እትዬ ጣይቱ እንዲህ ብለው መመረቅ ይወዳሉ።


  “የዘር በሽታ አይምታችሁ”

  ReplyDelete
  Replies
  1. your message very nice as before.
   thank you bro

   Delete
 9. ሰሞኑን እየሰማነው ያለው ነገር እጅግ ይሰቀጥጣል፤፤ ኢትዮጵያዊነት ትልቅ ጥያቄ ምልክት የተቀመጠበት መንግስት አለን ወይስ ብለን የጠየቅንበት፡፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያን ይጠብቅ፤፤

  ReplyDelete
 10. I am completely agree with the comment that given by solomon.Where were you through the last twenty years when your boses evicted innocent people from they land because of their ethnicity. We know you very well since you are become a business man thanks to your supporter behind your back. Now you are going to preaching about "Yezegnet kiber". What a joke! It is to late Dani please focus on your business do not meddling things.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Chifin, yalbesele, tera asteyayet new

   Delete
 11. Esat mechar bcha hone srah deacon Daniel. Esti yebekulhn sra. Esti be kne syahon ket'tegna yehone amargna eyetetekemk astemren. Esti le andnet, le fikirna le hakegna orthodoxawi emnet tenesasa. Can you be apolitical and preach unity and equality. Do you worship Our Almighty God or pseudo pride? I doubt u will post this but is enough you read it.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I can't stand this now you blame Dani for telling as the trues come on see your self what did u do???????????????????????????? its is for you to seat back and judge
   he is doing what he can and you know that this is the gift what he has what are you doing with yours?????????????

   Delete
  2. Your statement is sickening. If you have made a single effort as Deacon Daniel has done then the outcome would be different. Talk is cheap so please be quiet for now. Enough is enough and our people are dying and if this issue is not bothering you then join the Saudis...and leave this matter to concerned Citizens.

   Delete
  3. Why do you expect Dani to fight for you? What is your role and responsibility as a citizen? He has done a wonderful job and God Bless him.

   Delete
  4. በኢትዮጵያ ወደ 93 000 000 ህዝብ አለ ተብሎ ይገመታል፡፡ በሁለት ዐይን ስታባዛው ውጤቱ እጥፍ አስተዋይነት ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ከነጠላነት ባለፈ ድርብ ሊያሰተውል የሚችልበት ሁለት ዐየን እንዳለው አስተውላለሁ፡፡ በእርግጥ አንዳንዱ ሠው እንደ ዳንኤል ያለው ደግሞ ሶስት እጥፍ አራት እጥፍ የሚያስተውል ይመስላል፡፡
   ወንድሜ ያምሆነ ይህ ሠው ሁሉ ተባብሮ ለማስተዋል ካልጣረ ፍጹሙን ማስተዋል ማየት አይቻልም፡፡ ዳንኤል የአሁኑን ጉዳይ አስተውሎታል፡፡ ብታውቅ ኖሮ ደግሞ አንተ የአገር ውስጡን መከረኛ ደግሞ አስቀድመህ አስተውለህ ነበር ማለት ነው፡፡
   እሽ የጻፍከው ጽሁፍ ከትዝብትና ከወቀሳ የጸዳ ቢሆን ኖሮ ደግሞ የሠው ልጆችን የትብብር የማስተዋል ጥናካሬ አዳበርከው ይባል ነበር፡፡ ስለዚህ አንተ ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይና ወደፊትም እንደዚሁ በምታስተውለው ላይ የራስክን እይታ ብታደርሰን የበለጠ የትብብር አስተውሎታችን ይጎላልናል፡፡ አስተውል፡፡
   ልብ በል፤ አምላክ ሁላችንንም በድንቅ ጥበቡ በመልኩ ስለፈጠረን ማስተዋል እንችላለን፡፡ በአምላክ ቸርነት ቅዱስ ያሬድ ዜማ መዋሲቱን ግዘፈ አካሉ ከዚሁ ቁጭ እንዳለች - ነፍሱ ደግሞ ሹልክ ብላ - ጭልጥ ብላ - ወደ አርያም ጠልቃ - ምስጢርን ፈልቅቃ ጥበብን አርቅቃ - መሳሪያን ከጉሮሮ ጋር አጥምቃ አመጣች፡፡ በአምላክ ቸርነት ቅዱስ ላሊበላ ግዘፈ ሥጋው ከዚሁ እንደተጎለተ - ነፍሱ ደግሞ ነቅታ - ከአርአያም ኮረብታ ወጥታ - ምህንድስናን ቀድታ - አገነባብን ሰርታ አቆመች፡፡ ቅዱስ ቶማስ ሳሙኤል አልባ ኤድሰን ከስጋው ተለይቶ - በነፍሱ ሰልጥኖ - ጨለማውን አዋረደው - አስልችውን ሌሊት አስወገደው - ቀን ላጠረበት ሠራተኛ ቀኑን አረዘመው፡፡
   ኦሆሆሆሆሆሆሆ…. ስንቱ ስንቱ ቀናውን አስተዋለ - ስንቱ ስነቱ ቀናውን ፈለሰፈ - ስነቱ ስነቱ ቀናውን ፈጠረ - ስንቱ ስነቱ ቀናውን ደረሰ - ስንቱ ስንቱ ቀናውን ተቼ - ስንቱ ስንቱ ቀናውን ሳለ - ስነቱ ስነቱ ቀናውን መራ - ኦሆሆሆሆሆ…. ስነቱ ስንቱ ስንቱን አደረገ፡፡
   ይ¤ውልህ፡- በሰናኦር ብንተረማመስም፤ በቀራኒዮ ደግሞ ስለምንግባባ እንጠቃቀማለን፡፡ ሠናኦር እንዳንግባባ ያለመግባባት እንቅፋት ሲሆንብን፤ ቀራኒዮ ደግሞ እንድንተባበር ያግዘናል፡፡ አሁንም ቢሆን ሠናኦር እንድንተረማመስ የመተረማመስ መንስኤ ሁኖ በእያንዳንዱ አስተዋይ ውስጥ ሲሰራ፣ ቀራኒዮ ደግሞ ተግባብቶ ተደጋግፎ ተረዳድቶ የመጠቃቀም መፍትሄ ሁኖ ይሰራል፡፡ በሰናኦር መንስኤነትና በቀራኒዮ መፍትሔነት መካከል ሁኖ - አንዱ ለመልካም ይሆንልኛል ብሎ የፈጠረው ሌለው ደግሞ ለመጠፋፊያ አድረጎ ግራ አጋባው፡፡
   ለዚያ ነው - አንዳንዱ አስተዋይ ያለደሞዝ ሳይቀጠር ወገቡን ታጥቆ የሚያገለግለው፡፡ እንደ ዳንኤል ያለው ሳይቀር ቀራኒዮ መፍትሔው ስለሆነ ነው ቀጥ ብሎ የሚያገለግለን፡፡ እናስ ምናለበት ሳንወቃቀስ እንዳስተዋልነው መጠን ሌላውን ለመጥቀም የማንታጠቀው፡፡ እናስ ምናለበት ሳንተቻች እንዳስተዋልነው መጠን የሌላውን ክፍተት እየሞላን የማንጠቃቀመው፡፡
   አስተውል ጓዴ 93 000 000 ሕዝብ በሰናኦርና በቀራኒዮ መካከል ሁኖ መኖሩን፡፡ ዘጠና ሶስት ሚሊየናችን ሁሉ ድርብ ጥንድ ዐይን አለን፡፡ ሰናኦር የሰለጠነበት ያለያየናል - ያራርቀናል - ያበላላናል፡፡ ቀራኒዮ መፍትሄው የሆነለት ደግሞ ያግባባናል - ይጠቅመናል - የመጠቃቀም መድረክ ይሆነናል፡፡ እንደኢጥዮጵያ ላሉት ደግሞ ብዙ የአስተዋይነት ትብብር ብቻ ያሻል፡፡
   ከጣና ዳር፡፡

   Delete
 12. ዓረቦቹ አንዴ ዘጎቻችንን ያሰቃያሉ ይገድላሉ አንዴ ድግሞ ዓባይ አይግድብም ይላሉ ለምሆኑ አኛ በድን ሆን አንዴ?

  ReplyDelete
 13. የዜግነት ክብር
  የተሰደድነው ከአረንጓዴ ምድር
  ከድህነት ከነጻነትእስር ለማምለጥ ነበር
  ግና
  አልቀረልንም በሰው ሃገር
  መረገጥ መሞት የስቃዩ ቀንበር።
  ጠያቂ በሌለበት በባእድ አፈር
  አካላችን እዩት ተጨምድዶ ሲታሰር
  ሰውነታችን ተመልከቱት እንደ ከብት ሲደረደር
  ሲጣስ ኢትዮጵያዊነት ሲረገጥ የዜግነት ክብር
  የወንድ ልጅ አምላክ ካላየው በቀር።
  ድምጽ አልባው ድምጻችን

  ታፍኖ በመጓዝ ሄዶ
  በመታፈን ተጸንሶ ተወልዶ
  ተሰዶ ባህር ማዶ
  ዛሬም ጀርባ ሰጠ ተገዶ።

  ReplyDelete
 14. እጅህን ስጥ ይለኛል
  ፈረንጅ
  እጅህን ስጥ ይለኛል ፈረንጅ
  ምን እጅ አለና የሚሰጥ
  ያልኩ ነበርኩ የቴዎድሮስ ልጅ
  ሽንፈት ሞቴ የሆንኩኝ ሃበሻ
  እናንተ ሳትሆኑ ድህነት ማርኮኝ
  ወደ እናንተ ቀዬ ሃገር መጣሁ ለአምባሻ
  ዛሬ ግን እጅ ልስጥ
  ድንገት እንኳን ከሞት ባመልጥ
  ምን አልባት ብበቃ ለሃገሬ አፈርእናሰርጥ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የረከሰውና የተዋረደው ድሆች ስለሆንን ብቻ ነው? ስንት ድሃ አገር ሞልቶ የለምን? ምነው እንደዚህ አልተንቋሸሹ?
   ኢትዮጵያዊውን “አለኹልህ” የሚለው ማነው? ውስጤ ሐዘን ሳይሆን ንዴት፣ ቁጭት፣ እልህ ነው ያለው። ካልተንገበገብን ታዲያ ምን ዋጋ አለን?

   Delete
 15. Danie the national anthem ye-zegnet kibiri be-Ethiopiachin sefno ale enji be sawdi alalem ena change the title but the core issue needs to be discussed by all ethiopians openly and truthfully.

  ReplyDelete
 16. ''ይድረስ ለጠ/ሚ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ''

  በዐረብ ሀገር የስንቱ እንባ ፈሰሰ?
  እንባስ እንባ ነው ውሃ ጅረት ነው
  የስንቱ ደም እንደ ዐባይ ፈሰሰ?

  ዓባይ ሊገደብ ነው አሉ

  የህዝብ እንባ የህዝቡን ደም የሚገድብ ማን ይሆን???

  አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል ለካ
  ወገኔ ሲሰቃይ አልችል አለ አንጀቴ
  አንጀቴ ለዓይኔ ምስጢሩን ቢነግረው
  ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ገንፍሎ ስሜቴ
  የወገኔ ደም ለሊት እየጮኸ
  እንቅልፍ ይነሳኛል ድረሱልን እያለ።
  የወገኔ ደም በቀን እየጮኸ
  ሰላም ይነሳኛል አለቅን ድረሱ ፍጠኑ እያለ።

  የቴዎድሮስ ደም ከሰሰ ሀገሩ እንዲህ ስትዋረድ እያየ
  አጥንት ድረስ ዘልቆ ቅስሜ ተሰበረ
  የዜግነት ክበሬ ስለተዋረደ

  ለጣልያን ያልተንበረከከ ጉለበት ለአረመኔ አረብ ሰገደ
  ምንይልክ ምን ይበል ይህን ሁሉ እያየ?

  የዛሬ 10 ዓመት ለንደን የገባሁ እለት
  አስተማሪው ሀገራችሁን አስተዋውቁ አለ

  ደረቴን ነፍቼ አፌን ሞልቼ

  በአፍሪካ ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ ሀገሬ ኢትዮጲያ ናት አልኩት!

  ለካ ግን ባርያ ነን ፉከራው ሁሉ ከንቱ ነው።
  አባቶቻችን የሞቱልን ለዜግነት ክብር መስሎኝ እኮ ነበር!

  ዛሬ ግን ኢትዮጲያዊነት ያስግድላል! በአረቡ ኢትዮጲያዊያን ናችሁ ? ይባላሉ አዎ ካሉ ይታረዳሉ! አረብ በኢትዮጲዊያን ፖሊሶች ደህንነቱ ተጠብቆ በሀገሬ ሲዝናና ህዝቤ በአረብ ፖሊስ ይታረዳል!  ባንድ በኩል ህሊናዬ ይጠይቃል
  አረብ ማለት ትርጉሙ እንስሳ ጨካኝ አረመኔ ማለት ነውን?

  አጥንት ድረስ ዘልቆ ቁጣን ቀሰቀሰ
  እልህ ተያያዘኝ የእናትና አባቴ
  ዘራፍ የቴዎድሮስ ልጅ ዘራፍ የምንይልክ
  የነ አቡነ ጴጥሮስ የጣይቱ ብጡል
  እያልኩ በጀገንነት ልፎክር ተነሳሁ
  ለካስ አጥንት ድረስ ዘልቆ ቅስሜ ተሰብሮ ኖሯል
  ለካስ ባርያ ሆኜ ክብሬ ውርደት ሆኗል!


  በአሜሪካ አንዱ በሽጉጥ ህዝቡን ሲፈጅ ባራክ ኦባማ እንባ እየተናነቃቸው ህዝቡን አጽናኑ። ክቡር ጠ/ሚ ሃይለማርያም ሆይ እርሶ ምን አደረጉ? ቢያንስ ህዝቡን ማጽናናት የአባት ነበር! ለዜግነት ክበር ዘብ መቆም ደግሞ የእናትነት ነው!


  አንድ ወታደር ለማዳን 200 ወታደር የገበረች ሀገር ዐውቃለሁ
  የሀገር የዜግነት ክብር ይህን ያህል ነውና።


  ከመከራው ሀገር አንድ እህት እንዲህ ብላለች፦ ወላጆቻችን የት አሉ? ህዝብም መንግስትም ሬሳችንን ነው የምትጠብቁት?

  እራሴን አመመኝ አዞረኝ ሊጥለኝ
  መላ ሰውነቴን እራሴን እኔኑ አመመኝ
  የማየው ፎቶ የማየው ቪዲዮ ዐይኔን አሳወረኝ።


  ባለስልጣናት ሆይ ይህ የፖለቲካ ጫወታ አይደለም! በፍም አይደለም ! ይህ የዜግነት አንድም የህሊና ጉዳይ ነው!
  ከፖለቲካ ጫወታ ውጪ ነኝና የመንግስት ደጋፊም ተቃዋሚም ዐይደለሁም!ስለ ሀገሬ ኢትዮጲያ ግን ከቶ ዝም ልል አልችልም።


  በዐረብ ሀገር የስንቱ እንባ ፈሰሰ?
  እንባስ እንባ ነው ውሃ ጅረት ነው
  የስንቱ ደም እንደ ዐባይ ፈሰሰ?

  ዓባይ ሊገደብ ነው አሉ

  የህዝብ እንባ የህዝቡን ደም የሚገድብ ማን ይሆን???

  ReplyDelete
  Replies
  1. በመጀመሪያ ሰው ሲሆን እኮነው ይጠቅልለውና የጠቅልል አሽከር ፣ለጠቅላይ የሚፃፈው እርሟንጠምቃ ጠልቃፈጀች አሉ እድሜን ለማራዘም ያለቆቹን እራዩ ያስፈፅም እጂ ሰው ቢሆን እማ ጥሪም ፅሁፍም ግጥምም አያስፈልገው ነበር በዜግነት ሀላፊነቱን ይወጣ ነበር ወይንም በገገኔ የደረሰው በልጆቻቸው በደርስ የቁስሉ ተካፋይ ይሆን ነበር። ነገር ግን የሚመጣው ቁስልይበልጣል ለሱ አቤት ማለት አያስፈልግም ህዝብ አልመረጠው እንደ አባ ግርማ ተቀምጦ ቀን ይቁጠር እኛም በራሳችን መንነታችን ስንረከብ እሱም በተራው ማያልቀውን መከራ ተቀባይ ይሆናል እስከ ግብራበሮቹ።የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረደን ።

   Delete
 17. ኢትዮጵያዊነት በአደባባይ ሲወድቅ

  የፋሽሽት ጣልያንን ወረራ ጊዜና እርሱን ተከትሎ የነበረውን ሰቆቃ ያስተዋሉ ሰዎች፥ ሁሉ አልፎ ነጻነት ካገኙ በኋላ፥ አንዳንድ ጊዜ ነጻነታቸው ሲገፈፍ እና መብታቸው ሲታፈን “ በሕግ አምላክ ወድቆ በተነሣው ባንዲራ!” ይሉ ነበር። ዛሬ በአረብ አገር ላይ ወድቆ እያየነው ያለነው ባንዲራው ወይም ሕጉ ሳይሆን ኢትዮጵያውነት ራሱ ነው።
  ዛሬ በአረብ አገሮች እንደ አበዱ ውሾች እየታደኑ የሚደበደቡት የሚታሠሩት ኢትዮጵያውያን የሚጮኽላቸው ለዜጎቹ የሚቆምላቸው አካል እንደማይኖር ስለታወቀ ነው። በእኛ ኢትዮጵያውያን ነን ስንል በኖርነው ዘንድ እንኳ ኢትዮጵያውነታችን ነውረኛ አሳብ ስለሆነብን፥ ከኢትዮጵያውነታችን ይልቅ ጎጣችንን መንደራችንን ጎሳችንን ዘራችንን መቍጠር ስለጀመርን ኢትዮጵያዊን ከሰው የሚቆጥረው የለም።

  ኢትዮጵያዊነት በአደባባይ የወደቀው በአረብ አደባባይ አይደለም፤ በአረብ አደባባይስ ኢትዮጵያዊነትን ለመግደል፥ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለዘመናት ተጎንጉኖ፥ ተቋጥሮ ተፈቶ አልተሳካም ነበር። የአልጄሪያው ደባ፥ የሊቢያው ስጦታ፥ የሳውዲው ስለት፥ የደማስቆው ፖለቲካ ምንም አላመጣም ነበር።
  ኢትዮጵያውያዊነት የወደቀው በራሷ በኢትዮጵያ አደባባዮች ላይ ነው። ኢትዮጵያዊነት ክብር ሳይሆን መርገም እንደሆነ የተነገረው በራሷ አደባባይ ነው። ወጣቱ በገዛ አገሩ ተስፋውን ሲያጣ አብሮ የመኖር ተስፋን ሲያጣ፥ የማደግ ተስፋን ሲያጣ፥ በገዛ አገሩ የዝግታ ሞት ከሚሞት፥ በሶማሊያ በረሃዎች በረሃብ ተቃጥሎ መውደቅ ይሻለኛል አለ። ጠኔ በገደለው አንጀቱ በገዛ አገሩ የሞት ሞትን ከምሞት በሲናይ በረሃዎች በበድዊኖች ተገድሎ ሬሳው ለሽያጭ እንዲቀርብ አደረገው። ወደየመን ለመሻገር ሲሉ ቀይ ባሕር የበላቸው ወደ ማልታ፥ ወደስፔይን፥ ወደጣልያን ለመሻገር የሜዲተራኒያን ባሕር የበላቸው ስንቶች ናቸው።
  ዛሬ ጥቂት የዩቱዩብ ቪዲዮዎች ስሜታችንን መቀስቀሳቸው መልካም ነው። ግን ይህ የተቀሰቀሰው ስሜታችን ሊጠይቀው የሚገባው ነገር ይህ ነው። በገዛ ደጃፋችን የወደቀው ኢትዮጵያዊነታችን የሚነሣው መቼ ነው? ኢትዮጵያዊው በብሔሩ፥ በጎሳው ወይም በመንደሩ ሳይሆን በሰውነቱ ክብር የምንሰጠው መቼ ነው? ይህ በሽታ ሁላችንም ላይ ከላይ እስከታች የተጋባብን ነን።

  ለገዛ ወገናችን፥ ለዚያ ለአንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ክብር መስጠት እስካልቻልን ድረስ ለብዙዎቹ ክብር መስጠት አንችልም። እኛው ለራሳችን ክብር ካልሰጠን ማንም ክብር ሊሰጠን አይችልም። ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ . . . እንዲሉ አባቶች።
  Posted by Kesis Melaku

  ReplyDelete
 18. ቅዱስ ከተማ አሏት ድንቄም ቅዱስ የሰው ጭራቆች የተሰባሰቡባት ከተማ...saudi arabia

  ReplyDelete
 19. ኢትዮጵያዊነት እንዲህ የረከሰውና የተዋረደው ድሆች ስለሆንን ብቻ ነው? ስንት ድሃ አገር ሞልቶ የለምን? ምነው እንደዚህ አልተንቋሸሹ?
  ኢትዮጵያዊውን “አለኹልህ” የሚለው ማነው? ውስጤ ሐዘን ሳይሆን ንዴት፣ ቁጭት፣ እልህ ነው ያለው። ካልተንገበገብን ታዲያ ምን ዋጋ አለን?

  ReplyDelete
 20. ጠላት የሆኑት አረቦች፦ተበድለው የሥራ ቦታዎቻቸውን እንዲቀይሩ የሚገደዱትን ወንድሞቻችንን “ILLEGAL” በማለት ያድኗቸዋል ፣ ይደበድቧቸዋል ፣ ይገድሏቸዋል ፤ የተረፉትን ደግሞ እየሰለቡና እያኮላሹ ካገራቸው ያባርሯቸዋል። ቆሻሻ ለሆነው ዘራቸው ማጣሪያ ይሆኑ ዘንድ እህቶቻችንን እያታለሉ በመድፈር ዲያብሎሳዊ ልጆቻቸው እንዲወለዱ ያደርጋሉ
  በታሪካችን ብርቅ እና ልዩ የሆነው የኢትዮጵያ ስልጣኔ የዳበረው ኢትዮጵያ ዝግ ሆና ከአካባቢው አደንዛዥ የአረብ አገር ጋር ግኑኝነት ባቋረጠችበት ዘመን ነበር
  በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ከሺህ ዓመታት በፊት በአፍሪካውያን ላይ ሲፈጸም ከነበረው አስከፊ የባርነት በደል የተለየ አይደለም
  አረቡ አገሬ ናቸው የሚላቸው 22 አገሮች አሉት። ሙስሊሙም እንደዚሁ የእስላም ብቻ ናቸው የሚላቸው 52 የሚሆኑ አገሮች አሉት። ለኢትዮጵያውያን ግን ልንንከባከባት የሚገባን አንዲት ኢትዮጵያ ብቻ ነች ያለችን።
  ክቡሩን ሰንደቅ ዓላማችንን ባደባባይ ለማቃጠል በበቁት እና ልባቸው ለውዲቷ ኢትዮጵያ ሳይሆን ለመካ መዲና በሚመታባቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የአገር ፍቅር ፈተና የሚቀርብበት ጊዜ ደርሷል
  ሁሉም እንዲወዱን መፈለግ የለብንም፡ ከእባብ አብልጠው የሚጠሉን የዲያብሎስ ልጆች ባይወዱን ይመረጣል“Throughout history, it has been the inaction of those who could have acted, the indifference of those who should have known better, the silence of the voice of justice when it mattered most, that has made it possible for evil to triumph.” Haile Selassie

  ReplyDelete
 21. If you want to evade responsibility, rely on wishful and mystical worship. If it does not happen, then you say "it is God's wish", evasion of personal responsibility.

  Our people are being treated as subhumans by ignoramuses with money, and our answer to that is "oh please God, bring us the solution". what a pity way of thinking. If there is a huge and fierce roaring lion lunging towards you, you would never say "oh God please make him stop". no you don't. you would do the right thing. Either you run away, or defend yourself with whatever you have. Our brothers and sisters in Saudi are suffering at this moment. Why don't we start fundraising campaign using this website, and then raise money, and send it at this difficult time for them. Or to create awareness to the whole world about the situation. do something in terms of action. once we did that, then we all do the mystical stuff later on. how about that. Those of you who are questioning the author about his response during the domestic displacement of citizens are also evading your responsibility of the urgency of now. Now there are our people bleeding in the streets of Saudi, and now you want to settle score for what happened a year ago?. that is the prototype of irresponsibility and hypocrisy.

  ReplyDelete
 22. God bless you Daniel. I always get the comfort from your article on national matter. For some it is one of the opporchinity to tray thir political rivals in Ethiopa incase if they can grab people atteshion while it is a sadest week for the majority to see their brother and sisters seffering with one hand helplessly! Do don't be discourage by their coment.

  ReplyDelete
 23. DID YOU KNOW THAT A LOT OF ERITREANS WORK FOR ETHIOPIAN EMBASSY AROUND THE WORLD? SO WHAT DO YOU EXPECT FROM THE EMBASSY.

  ReplyDelete
 24. ኡኡኡኡ እረ የመንግስት ያለህ ወገን አለቀ ገና ልጆጭ ናጨው አሁን ነው ማልቀስ እናት መከራዋ ። ተው ብዙ አንፍረድ እንፀልይ። በተረፈ ዳንኤል የዜግነት ክብርን ህዝቡ እንጂ እ ነ ሱ አልዘመሩትም


  ReplyDelete
  Replies
  1. ዳንኤል ያለው ካልገባህ ሞተሃላ።

   Delete
  2. የሞት ሞት እንጂ ፡፡

   Delete
 25. have i government ?i don't think so b/c he watched silently why for take a measure ,our people we must be together or individually we pray to god every time tile they get the settled them life ,god please keep them ,we have god b/c we are Ethiopians

  ReplyDelete
 26. Gude Belu Zendro!!! I miss Meles Zanawi. When he was a prime minister I feel he is devil but he was better than now. Who is our leader? Ethiopian are shouting to get help but no body answer their question. Why this happen on us. Are we far from God? is this 21st century? God bless you Daniel at least you have been tried to distribute their voice.

  ReplyDelete
 27. በሆነው ሁሉ እኔም አዝናለሁ፡፡ ግን አሁንም የማየው የኔ ባልሆነ ሀገር መኖር አንድ ቀን እንደውሻ እንደሚያስጎትተኝ እንደሚያስደፍረኝ ደሜ ደመ ከልብ ሆኖ እንደሚቀር ነው፡፡ ስለዚህ ማናችሁም በራችሁ ብትሄዱ እኔ በሀገሬ እኖራለሁ፡፡ ሳገኝ በልቼ ሣጣ ተደፍቼ፡፡ ወኔዬ ለስራ ከቆረጠ የሚበላ እንደማይጠፋ ተረድቻለሁ፡፡ ስለዚህ ማንንም ተሰደዱ ብዬ አልመክርም፡፡ ለትምህርት፣ ለስራ፣ በህጋዊ መንገድ እኔም ዞር ዞር ብዬ ተመልሻለሁ፡፡ ግን አንድም ቀን በባእድ ሀገር ልስራ ብዬ አላውቅም፡፡ ከሱ የማገኘውን ገንዘብ ያለፍላጎቷ እያለቀሰች በየቡናቤቱ ገላዋን ሸጣ እንደምታገኘው የሴትኛ አዳሪ ገንዘብ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ ላቤንና ደሜን እዚሁ አገሬ ላይ አፈሳለሁ፡፡ ጫጫታ የለመዳችሁ በየሀገሩ የተበታናችሁ ወገኖቼ የበለጠ ኡኡ በሉ፡፡ እኔ ይሄን ብዬአለሁ፡፡ ያለሀገር መኖር መጨረሻው ይህ ነው፡፡ አንዳንዱም በኢትዮጵያ እየሰራሁ መሆኔን ዋጋ ሊያሳጣ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ከምወለድ አውስትራሊያ ሆኜ ፈረስ ሆኜ ብፈጠር ብሎ የሚሟርት አለ፡፡ ይሄ እንግዲህ እንደ ሰው ተናገረ እንጂ ልቡ እና ጭንቅላቱ የአጋሰስ ነው፡፡
  ያም ሆነ ይህ መስሎአቸው ያለህጋዊነት እንዲሁም ያለስራ እና መኖሪያ ፈቃድ ሄደዋል፡፡ መንግስታችን ሆይ ክፉም ሆንክ በጎ እነዚህ በሳውዲ የሚገኙ እስላምም ክርስቲያንም ወገኖቼ፣ የሁሉም ብሄር ዝርያዎች እየተሰቃዩ ነውና እኛን ሆነህ እኛን መስለህ ድረስላቸው፡፡ ከሰቆቃ እና ከችግር አድናቸው፡፡ ባዶ ተስፋ ሰንቀው ለጊዜው ያገኙትን እየበሉ ያሉ ወገኖቻችን እንፈልጋቸዋለን፡፡ ሀገራችን ለሁሉ ትተርፋለች ከሰራንባት፡፡ የናቋትንም ትንቃለች፡፡ አንድ ቀን ወይ ሀገሬ እንዲሉም ታደርጋቸዋለች፡፡ ሁላችሁም ኑ በሀገራችን እንኑር እንስራ፡፡ የጥላቻ መርዝ በጭንቅላታችን ሞልቶ እስከመቼ፡፡ እኔ መንግስትን ብወደውም ባልወደውም ህገ ወጥ የሆነ አካል ቢደፍረኝ የመንግስት ያለህ ማለቴ አይቀርም፡፡ ሀገር እና መንግስት አለኝ፡፡ እነዚያ በአሜሪካ የሚኖሩ ጥቂቶች የሚናፍቁት መንግስት በኢትዮጵያ ቢመጣም እሱንም መንግስቴ እለዋለሁ፡፡

  ReplyDelete
 28. the story should have long and mention many aspects to the ethiopian government on current situation.. i know Dany your writing it doesn't end in 3 paragraph. we look at you as public figure i am hoping more to come....

  ReplyDelete
 29. ያሳዝናል ፍርድ ቤቱ ብቻዉን መቅረቱ አሉ አበዉ

  ReplyDelete