‹ዛሬ በናትሽ ዳጎስ ያለ ሰነድ ወይም መጽሐፍ ወይም ዶሴ መብላት አማረኝ›› አለች
አንዲት ነጭ አይጥ ለጓደኛዋ፡፡
‹‹ለምን አንዱ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አልወስድሽም›› አለቻት ጥቁሯ አይጥ፡፡
‹‹እኔን ለማስደብደብ ነው እንዴ ፍላጎትሽ›› አለቻት ነጯ
‹‹ማነው ደግሞ የሚደበድብሽ››
‹‹ሠራተኞቹ ናቸዋ››
‹‹ስለ ሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አታውቂም ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥኮ አንድ ነገር
የሕዝብ ነው ከተባለ ሁለት ነገር ነው ማለት ነው፡፡ ወይ የማንም አይደለም፤ ወይም የጥቂቶች ብቻ ነው፡፡ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት
ማለት የማንም ያልሆነ ቤተ መጻሕፍት ማለት ነው፡፡ በጀት የለው፤ ተቆጣጣሪ የለው፤ ባለቤት የለው፡፡ ማዘጋጃ ቤት የባህል ቢሮ
ነው ይለዋል፤ የባህል ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው ይለዋል፤ ኮሙኒኬሽን ጽ/ ቤት የወጣቶች ሊግ ነው ይለዋል፤ የወጣቶች ሊግ
የሕዝብ ነው ይለዋል፡፡ ስንትና ስንት የጥንት መጽሐፍ ባለቤት ስላጣ ማንም ዘወር ብሎ አያየውም፡፡ ይልቅ ተነሽ እንሂድ››
ተያይዘው ሄዱ፡፡ ገቡ፡፡ አንድ አስነባቢ ገቢያቸውን ለብሰው ጠረጲዛ ላይ ክንዳቸውን
ተንተርሰው ሸለብ አድርገዋል፡፡ አይጦቹ በበሩ ሲገቡ እንኳን አላዩዋቸውም፡፡
‹‹ያንን መጽሐፍ አውርጂው›› አለቻት ጥቁሯ፡፡ ነጯ አይጥ ሄደችና አወረደችው፡፡ ዳስ
ካፒታል የሚለው የማርክስ መጽሐፍ ነው፡፡ ‹‹ለእኔ ደግሞ እዚያ ማዶ ያለውን አምጭልኝ›› አለቻት፡፡ ኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ
መዝገበ ቃላት ነው፡፡ ሁለቱም ተቀምጠው መቆርጠም ጀመሩ፡፡
አስነባቢው የሆነ ድምጽ ስለሰሙ ቀና አሉና መልሰው ተኙ፡፡
‹‹እንዴ በሙሉ የድሮ መጽሐፍ ብቻ ነው እንዴ›› አለች ነጯ አይጥ፡፡
‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣
ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡፡ አታይም ሠላሳ ሺ ሕዝብ
የሚይዝ ኮንዶሚንየም ሲገነባ በግ ማረጃ እንጂ ቤተ መጻሕፍት ተገንብቷል? ለመጠጥ ቤት፣ ለጫት ቤት፣ የሚሆን ቦታ ግን ሕንጻዎቹ ሥር ተሠርቷል፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቹ በየቢሮው ያሉት
ከዕውቀት የጸዱ፣ ከሆድ የተዛመዱ ናቸዋ፡፡ ያለ አእምሮ ልማት ቁሳዊ ልማት ከየት ይመጣል፡፡ መገንባት ብቻውን አያለማምኮ፡፡
የገነባሽውን በሚገባ የሚጠቀም፣ የሚከባከብ፣ እድሜውን የሚያረዝም፣ እሴት የሚጨምርም ዜጋ ያስፈልጋል፡፡ በጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ
ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው፡፡ ከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤ ኪነ ጥበብ ከማይበረታቱ ኢንዱስትሪዎች መደብ በተመደበባት ሀገር ምን
ትጠብቂያለሽ›› አለች ጥቁሯ፡፡
‹‹ባለፈው አንዲት ጓደኛዬን ለአዲስ ዓመት ወጣ ብለን እንዝናና ስላት የት
እንደወሰደችኝ ታውቂያለሽ››
‹‹ዱከም ወስዳ ሥጋ ጋበዘችሽ››
‹‹ኧረ አይደለም፤ አቃቂ››
‹‹አቃቂ ደግሞ ምን አለ?››
‹‹ድሮ በደርግ ጊዜ ኩራዝ አሳታሚ እያለ ሊታተሙ የተሰበሰቡ ረቂቆች አሉ ብላ ይዛኝ
ሄደች፡፡ አንድ ትልቅ የቆርቆሮ መጋዘን ውስጥ ተከምረውልሻል፡፡ እዚያ ይዛኝ ገባች፡፡ እዚህ ሀገር የታወቁ ደራስያንን ሥራ
ስንከሰክስ ስንከሰክስ ዋልንልሽ፡፡ አንዳንዱ ታርሟል፤ አንዳንዱ አልፏል የሚል ተጽፎበታል፡፡ አንዳንዱ ማኅተም አለው፡፡
‹‹ዝም አሏችሁ››
‹‹ማንም ዝር አይልም ከአይጥ በቀር አሉ የለመዱትማ ሲነግሩን››
‹‹ወይ ይህቺ ሀገር፣ ከገዛ ታሪኳና ቅርሷ፣ ከገዛ መዛግብቷና ሰነዶቿ ጋር የምትጣላ
ሀገር፡፡ ባለፈው የባድሜ ጉዳይ በዓለም ፍርድ ቤት ሲዳኝ አንዱ
የተጠየቅነው ሰነድ ነበር አሉ፡፡ የተቆረጠ ደረሰኝ፣ የተሰጠ ሹመት፣ ከዚያ አካባቢ የተጻፈ ነገር፣ የሐኪም ቤት ካርድ፣ ያ ቦታ
የኢትዮጵያን እንደነበረ የሚያሳይ ዶሴ አምጡ ተብሎ ነበር አሉ፡፡ እዚህ ሀገርኮ ስንቱ ፋይል፣ ስንቱ ዶክመንት፣ ስንቱ ደብዳቤ፣
ስንቱ መረጃ አሮጌ ነው እየተባለ ተጥሎ በየቆርቆሮው ቤት ታሽጎበታል መሰለሽ፡፡ ለኛማ ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ እርሱን እየበላን
እንኖራለን፡፡ ሀገሪቱ ግን ታሳዝናለች፡፡››
‹‹ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት የሚባል ድርጅት አለ አይደል እንዴ››
‹‹አንድ ለእናቱ የሆነውን ነው የምትይኝ? ይኼው ሰማንያ ዓመት ሆኖታል አንድ ለእናቱ ነው፡፡ እስኪ ክልል ውረጅ አንድ
የመዛግብት ማዕከል ታገኛለሽ? በተለይማ ባለፉት ሥርዓቶች የነበሩ
መዛግብት የጠላት ገንዘብ ተደርገው የማንም መጫወቻ ሆነዋል፡፡ ወይ ቆርቆሮ ቤት ገብተዋል፤ ወይ ተቃጥለዋል፤ ያለበለዚያም በኪሎ
ተሸጠዋል፡፡››
‹‹ይበላቸው እባክሽ፤ እነርሱ በዘመናቸው እኛ ድርሽ እንዳንል ድመት ለሚያረባ ሰው የድመት
መሬት እየሰጡ አሳድደውናል፡፡ይኼው ዛሬ የሀብታም መሬት እንጂ የድመት መሬት የለ፡፡እንደልባችን ታሪክ ስንበላ እንውላለን፡፡››
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ በሽታ መቼ ተከሰተ፣ የት የት ቦታ ተከሰተ፣ ምን ያህል
ሕዝብ ተያዘ፣ ምን ተደረገ፣ መቼ ጠፋ? ብለሽ ብትጠይቂ መልሱ
ያለው የት እንደሆነ ታውቂያለሽ?››
‹‹ጤና ጥበቃ ነዋ››
‹‹ተሳስተሻል፡፡ እኛ ሆድ ውስጥ ነው፡፡ የሆስፒታል የድሮ ካርዶችኮ እንድንበላቸው
ተፈቅደውልን የተከፋፈተ መጋዘን ውስጥ ተጥለዋል፡፡ እንደ ጓያ ነቃይ የዛሬን እንጂ የነገን የሚያስብ የለም፡፡ አሁንኮ ሀገሪቱ
ስላደገች የወዳደቀ ትራፊ ሳይሆን አልፎልን ታሪክና መረጃ ነው የምንበላው፡፡ አንዳንድ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን አሉ
ጋዜጠኞች፡፡ የሚደርሰውኮ ወደኛ ነው፡፡››
‹‹አንድ ነገር አስታወስሽኝ፡፡ ከሆነ ዓመት በፊት አንድ ትልቅ ባለ ሥልጣን
የተናገረው ነገር፡፡ ኢሕአዴግ ባሕርዳር ሲገባ እነርሱ የኢሠፓ ጽ/ቤት ነበር ያደሩት፡፡ ብርድ ስለነበር ሌሊቱን ፋይል እያነደዱ
ሲሞቁ፡፡ በመካከል የአንድ ደራሲን ልቦለድ አግኝቶ እንዳነበበውና አዲስ አበባ ፈልጎ እንደሰጠው ሲናገር ነበር፡፡ አሁን ሰነድ
ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው?
ሰዎቹ ናቸው እንጂ ኢሠፓ ፋይሉኮ ኢሠፓ አይደለም፡፡ ፋይሉማ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡››
‹‹የኢትዮጵያን ዕቃ ገዥ ከሌላው ዓለም ገዥ የሚለየው አንዱ ነገር ምን እንደሆነ
ታውቂያለሽ?››
‹‹አላውቅም››
‹‹ሌላው በተራ ወረቀትና ፌስታል ዕቃውን ይጠቀልላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በታሪካቸው
ስለሚኮሩ በታሪካዊ መዛግብትና ሰነዶች፣ በታሪካዊ ደብዳቤዎችና ፋይሎች ዕቃቸውን ይጠቀልላሉ፡፡ በየሱቁ ከምትገዥው ስኳር በላይ
ባለ ሱቁ የጠቀለለበት ፋይል ዋጋው ውድ ነው፡፡
‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››
ቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡
‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡
‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡
ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ታሪክ እንበላለን፡፡
© ይህ
ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው
‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››
ReplyDeleteቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡
‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡
‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡
ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ታሪክ እንበላለን፡፡
"""አታይም ሠላሳ ሺ ሕዝብ የሚይዝ ኮንዶሚንየም ሲገነባ በግ ማረጃ እንጂ ቤተ መጻሕፍት ተገንብቷል? ለመጠጥ ቤት፣ ለጫት ቤት፣ የሚሆን ቦታ ግን ሕንጻዎቹ ሥር ተሠርቷል፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቹ በየቢሮው ያሉት ከዕውቀት የጸዱ፣ ከሆድ የተዛመዱ ናቸዋ፡፡
ReplyDeleteበጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው፡፡
‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››"""
Brilliant idea as always thanks!!!
nice observation!
ReplyDeleted/n tiru milketa neew egziabher yisth
ReplyDelete‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡፡
ReplyDeleteከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤
ብርድ ስለነበር ሌሊቱን ፋይል እያነደዱ ሲሞቁ፡፡
በመካከል የአንድ ደራሲን ልቦለድ አግኝቶ እንዳነበበውና አዲስ አበባ ፈልጎ እንደሰጠው ሲናገር ነበር፡፡
አሁን ሰነድ ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው?
በየሱቁ ከምትገዥው ስኳር በላይ ባለ ሱቁ የጠቀለለበት ፋይል ዋጋው ውድ ነው፡፡
‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››
God bless you D.Daniel Kibret
Long life for you!!!!!
Tebarek! yes it is right you did your share to alert all but we all have responsibility it is our history too, let us ask ourselves what I have contributed, do I'm really discharging my responsibility properly or because my salary is small or because it is just government's responsibility why do I care like 'balegabiw' librarian let me sleep then while living with the penny/salary of our poor country. Dears there is something called scarifies/devotion lets stop complaining & come up with the solution of change then we will see what we wish to see!
DeleteMay God help us to be a person of change!
Thank u Daniel for giving us the insight!!!
HAHAHAHA
ReplyDeleteYimechih avo.
ReplyDelete//ይድረስ ለዳንኤል ክብረት//
ReplyDeleteብልጥ አይጥ ከባለቤት እኩል ስትበላ ትኖራለች አሉ! ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም ታሪክ እንበላለን፡፡ ቁንጫ መሄድ ሳትማር መዝለል ተማረች አሉ! ታሪክን ዘሎ እራመዳለሁ ማለትም እንዲሁ ነው። ፋይል እያነደዱ የሚሞቁ በምትኩ ፀሐይ ይሙቁ። በመጋዘን የታሰሩ መፅሐፍት በዳኞች ትእዛዝ ይፈቱልን! ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ አሉ እቴጌ ጣይቱ!
Thank You Daniel
ReplyDeleteWhen I was two years old my father pass away and I was wondering why my mother raised me by herself until I turned six old. When I turned six old, I asked her about my father and she told me that he died by accident and she showed me his picture. If my mother never kept my father picture how do I know my father but she is a wise mom so she showed me his picture. All our histories tell us about the past situation and we can tell about Ethiopia for the next generation because of what we have in the past. Who is responsible to keep Ethiopian history? I know most of us we blame government but what we did or contribute is important than blaming government. As we all know that most of our leader came from forest so they don't have any idea about document or history because they grow up with war in the forest. That's why they told us Ethiopia has only one hundred year history because they never read about Ethiopian history. And then as we all know that if you oppose them by writing your idea, they will put you in the prison like Esknder Nega and Riot Alemu. I am not opposing the current government because what they saw when they grew up, they think that is always right because they never read other people idea. We have responsible to teach them and to tell them about the important of document, history and writhing idea then they may be changing their view one day. Starting today I will teach for my entire brother, sister and friends to contribute my part. God bless you our brother Daniel Kebret. God bless Ethiopia.
"And then as we all know that if you oppose them by writing your idea, they will put you in the prison like Esknder Nega and Riot Alemu. I am not opposing the current government because what they saw when they grew up, they think that is always right because they never read other people idea. We have responsible to teach them and to tell them about the important of document, history and writhing idea then they may be changing their view one day."
DeleteYou say this...... how can teach this government? i have no idea or cant understand wat u want to say.........
Thank you so much for reading my comment and giving your thought. The only way to teach the goverment to take risk like Daniel Kebret, Esknder Nega, Riot Alemu and others sisters and brother. I wrote the fact, not the solution. When I write the fact I have to write the true situation evenif the contecsts are not agree each other. I agree with your comment but I wrote to express the current situation with out adding my opinion. It is exelent comment I like it.
Deleteቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ReplyDeleteታሪክ እንበላለን፡
ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ReplyDeleteታሪክ እንበላለን፡
The following comment is wrong
ReplyDeleteከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤ ...
News print in rolls customs duty 5%
Beer customs duty 35%
printed books customs duty 5%
whisky customs duty 35%
on top of this , alcohol has an additional excise tax but paper has no excise tax at all ,
Elias k/mariam
.
This message is to Mr Elias.
DeleteI realy apriciate for your comment. The message of the article is how we can keep Ethiopian document to the next generation not math. Examples are not always right but to give more detail about the situation writer give example to make inpresion into their reader. In addition that you didn't opose about having beer shop everywhere insteady of book store or liberery. The writer point is to keep our country safe we have to respect the past. Have blessed day!!!
so why is that the cost of book is very expensive?
Deleteአቶ ኤልያስ ክፍለማርያም፡-
Deleteእባክዎት አንድ ጊዜ ደግመው ለማንበብ ይሞክሩ፡፡ አለበለዝያ የወጉን ማዕከል እስኪያገኙት ደረስ ያለማቋረጥ ማንበብዎን ይቀጥሉ፡፡ ወርቅና ሰሙን ሲያውቁት ያን ጊዜ ቆም ብለው በግልዎ እንኳን ሊወስዱት የሚገባ የኃላፊነት እርምጃ ሊኖር እንደሚችል ግንዛቤ ይሰጥዎታል፡፡
የግል ግንዛቤዬ፡- ወጉ የዛሬ አስቂኝ ወግ፤ እየዋለ እያደረ ደግሞ ወደማንኛውም ሰው እየጠለቀ የሚገባ ቁም ነገር ይሆናል፡፡ የማህበረሰቡም አካል ይሆናል፡፡ይህ ወግ የሁለቱን ዓይጦች ህልውና ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ - እንደአስፈላጎነታቸውም እየተጠቀሱ - እየተሳተፉ እንዲኖሩ ይፈቅዳል፡፡ ቁሳአካላዊ አባላት አድርጓቸዋል፡፡
በሰሙም፡- በአገራችን ያለውን የሠነድ አያያዝ ዘፈቀደነት እርቃን የሚገልጥ ነው፡፡
በወርቁም፡- የሠው አይጦችን ያሳያል፡፡ አንዳንድ በየቤተ መዘክሩ መጽሐፍትን እየቀደዱ የሚመዘብሩትን ያሳያል፡፡ በአንጻሩም የቀደሙትን ጥንታውያን ሠዎቻችን ለሠነድ ያላቸውን ታላቅ ዋጋ እንድንመረምር ይረዳል፡፡ የዛሬዎቹ ሠዎች ደግሞ ለሠነድ ያለውን የግንዛቤ ማነስ ያስረዳል፡፡
አመሰግናለሁ!
ዘጣና ዳር፡፡
Dear Elias,
DeleteWe appreciate ur comment!
Dn. Dany! Nice observation as usual! Egzer Yitebikilin::
HEY MY BROTHER THE PERCENTAGE IS NEVER... BUT THE VALUE OF THE TAX ON PAPER IS MUCH MORE UNEXPECTED FOR COUNTRIES LIKE ETHIOPIA... WE SHOULD BE LET O WRITE A LOT ND THE PRINTING COSTS ARE THE HINDRANCES...
Deleteይገርማል!!!
ReplyDeleteAlfo Ayichew
ReplyDeleteYe'Ethiopia sened bedebo sitefa
egnam ehhhh.... eyalin gizewin engifa
minew emiye hagere mekerash kefa
It is an Incredible view Mr
ReplyDeleteከሆነ ዓመት በፊት አንድ ትልቅ ባለ ሥልጣን የተናገረው ነገር፡፡ ኢሕአዴግ ባሕርዳር ሲገባ እነርሱ የኢሠፓ ጽ/ቤት ነበር ያደሩት፡፡ ብርድ ስለነበር ሌሊቱን ፋይል እያነደዱ ሲሞቁ፡፡ በመካከል የአንድ ደራሲን ልቦለድ አግኝቶ እንዳነበበውና አዲስ አበባ ፈልጎ እንደሰጠው ሲናገር ነበር፡፡ አሁን ሰነድ ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው? ሰዎቹ ናቸው እንጂ ኢሠፓ ፋይሉኮ ኢሠፓ አይደለም፡፡ ፋይሉማ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡››
ReplyDelete‹‹የኢትዮጵያን ዕቃ ገዥ ከሌላው ዓለም ገዥ የሚለየው አንዱ ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?››
‹‹አላውቅም››
‹‹ሌላው በተራ ወረቀትና ፌስታል ዕቃውን ይጠቀልላል፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በታሪካቸው ስለሚኮሩ በታሪካዊ መዛግብትና ሰነዶች፣ በታሪካዊ ደብዳቤዎችና ፋይሎች ዕቃቸውን ይጠቀልላሉ፡፡ በየሱቁ ከምትገዥው ስኳር በላይ ባለ ሱቁ የጠቀለለበት ፋይል ዋጋው ውድ ነው፡፡
ዳኒ መቼ ይሆን የምንማረው ? ስንት ታሪክ ስንት የስነ ጥበብ ውጤት በተራ ጥላቻ ባከነ ፡፡በርታ የሳምንት ሰው ይበለን፡፡
Egnam bemeblat lay nen. Kortem. Kortem.
ReplyDeleteMechem Altsedikim bileh, Zimbleh titsifaleh ayidel!
ReplyDeleteGehanem Sile-molach Asibibet!
I am sure you are one of the rats that eat Ethiopian History.
DeleteThank you Daniel by posting this kind of comment as well. Now I know some rats supportes read your blog.
Deleteበጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው፡፡
ReplyDeleteDaniyee,Beruuk hun !!! real talk. I wish everyone read your blog and think where we are and where we are going !! then we will stand togather for a change.Vote Dani for Presdent.
ReplyDeleteweye Ante seweye!!!!
ReplyDeleteየሰሚ ያለህ!111111111
ReplyDeleteዳኒ ቃለ ህይወት ያስማልን
ገጊዘዛቸወው
Tarik mesrat banchil tarik metebek enkuan yakiten?
ReplyDeleteNice Observation .
ReplyDeleteehhhhhhhhhhhhhhhhhehhhhhhhhhhhehehheheheheeeeeeee ......HAGERIE
ReplyDeletethose all of the readers; please don't repeat the article, i told you so many times but you don't realize it. omit all things and write by your own. don't copy-paste.......the original it.
Deleteyours-- simachew from Addis.
Thank you so much Mr Simachew. However anybody can express him/her idea by their way not your way. Don't tell for the people to follow your way, they have right to express their felling by taking the writer idea and repeat that because when they read they are very happy with small paragraph from all article. My suggestion is for you don't descurage people to particpate with their idea or veiw. You don't know other people education status or level, some ot them are brliant so to support the writer idea they copy and pest to stand with the writer. I was on meeting with Meles Zenawi four years before and when he spoke two hours to us I was stack after five minute because he said that "Ethiopia has only hundred years old histor" until he finished his two hour I got mad and I didn't give him any attantion what is taking about. When we finished the meeting when I taked with my freinds all us were upset on him and we didn't get the all point because of that one word. I thing this example is good for you to understand other people idea. Have bless day.
DeleteExcellent observation!
ReplyDeleteአሁን ሰነድ ማቃጠል፣ ፋይል ማንደድ በቴሌቭዥን በኩራት የሚቀርብ ገድል ነው? ሰዎቹ ናቸው እንጂ ኢሠፓ ፋይሉኮ ኢሠፓ አይደለም፡፡ ፋይሉማ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው፡፡››
ReplyDeletedanny true astewelehale tarik yemeyaku serachew tefat yehonue bezetew new eko amelake yemeleketen agerachen eyetefea new teslot tosme yasefelegenale
ReplyDeletehulun awkalew bay
ReplyDeleteAbo Yimechih. Qolo eyeqoretemu tarik manbeb amaregn.
ReplyDeleteበአንድ ወቅት የባለፈው መንግስት (ደርግ) የተለያዩ ፋይሎች ከጥቅም ውጪ ሲደረጉ ተመልክቼ ነበር: ያኔ ምንም ሳይታሰበኝ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እውነትም ጉዳት አለው:: ታሪክ የምንለው ደጉንም መጥፎውንም ታሪክ ጭምር ነውና::
ReplyDeleteወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታዎችህ ሁሉ ተስማምተውኝ ዕለት ከዕለት ከማንበብ አልቦዘንኩም:: ጤና እና ሰላም ላንተ::
whatever had been done or happened in the past, the event or incidence can undoubtedly be informative though regarded as bad or good depending on the way we perceive. my verdict as to the current situation is that eprdf is behaving dreadfully and needlessly. we should care and keep documents. I truly appreciate you Daniel. God bless Eth.
ReplyDeleteEre besntu enkatel menden new yekerat yehch ager endeh yale neger be geragn mehamedena be yodet gudet gezem alneberem ahunem bezehu bekacheu yebelen!!!
ReplyDeleteበጎጆ አስተሳሰብ ዘጠኝ ፎቅ ላይ መኖር ትርፉ በረንዳ ላይ በግ ማረድ ነው።this is a nice article
ReplyDeleteከእኛ ውስጥስ አይጦች ይኖሩ ይሆንን???????
ReplyDeleteIt is true, the filing and documentation system is very poor. For instance, after Decentralization, in our zone, different rules and regulations have been passed from the region to woredas. However, when we go to woredas we can't find them; even the budget proclaimed at woreda level is not properly handled. One reason for this is high turnover of the staff specially the leading one. When the head of an office is transferred another office proper handover is not done. Consequently, the whole thing becomes new for the new comer.
ReplyDeleteThe other forgotten issue is different types of assets(such as vehicles, machinery, etc.) that are out of use and found in different government office compounds. These assets would have been renovated or sold for the benefit of the economy rather than rusting and ruining.The problem in this country is not lack of budget, but lack of wise management. It is not new when we always hear at different meetings that woredas and zones are unable to use millions of birr allocated for them for capital projects and funds obtained as support(eg.Health bureau).
great view!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteGood observation dani . no one concern for this thing specially the stakeholder they are not well educated . i am very sorry for our .muhuran .
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥህ ዲ/ን ዳንኤል….ለወደፊቱ አይጦቹ የተበላሸ ታርክ ይበሉ ይሆን?…..አሁን ታርክ የሚያበላሹስ ማን ይበላቸው ይሆን?…..እንጃ ራሱ ታርክ ይበላቸው ይሆን????????
ReplyDeleteየሀገሪቱ የቅርስ ግምጃ ቤት የሆኑትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ዕቃ ቤቶች ዘነጋሀቸው መሰል? እዚያስ የሉም ለማንኛውም አይጦቱ የኖረ ባሕላችን መሆኑ ገብቷቸዋል:: በታሪክ እፈክራለን እንጂ ቃላዊውን ከጽሑፋዊው ለይተን በርግጠኝነት የምንናገረው ታሪክ የለንም:: ይህ ግን የአያያዝ ችግር ያመጣው እንጂ ጥንታዊያኑ ጠንቃቆች ሆነው ታሪክ ሰርተው ብቻ ሳይሆን ሰንደውም አውርሰውን ነበር::
ReplyDeleteሰነድ ከሚያሸሽ፣ ቅርስ ከሚሸጥ የሰው አይጥ ይሰውራችሁ::
ይገርማል ! ያስቀመጥከውን ከነወለዱ ታገኛለህ የዘራሃውን ታጭዳለህ ምንም ትኩረት በማይሰጠው የዕውቀት መዕድ የታሪክ መዘክር በአይጥ ሲበላ ስታይ ስልጣኔ ምንን ይዞ ያስብላል ፡አንተም በርታ ዲያቆን
ReplyDeleteይህች አገር ግን የማን ናት?
ReplyDeleteNice observation and everyone needs to be alarmed on this major issue. No Library, but too many Chat & Shisa Bet in the country.
ReplyDeletePlease let us make an effort to build a library.
Thank you,your message is for all of us
ReplyDeleteወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታዎችህ ሁሉ ተስማምተውኝ ዕለት ከዕለት ከማንበብ አልቦዘንኩም:: ጤና እና ሰላም ላንተ::
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይጠብቅህ
thank you dani I love it!
ReplyDeleteያለ አእምሮ ልማት ቁሳዊ ልማት ከየት ይመጣል፡፡ መገንባት ብቻውን አያለማምኮ፡፡ የገነባሽውን በሚገባ የሚጠቀም፣ የሚከባከብ፣ እድሜውን የሚያረዝም፣ እሴት የሚጨምርም ዜጋ ያስፈልጋል፡፡ It's true!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteለነቁጥ ፈላጊ (fault finders) አስተያየት ሰጪዎች- አረረም መረረ በፅሁፉ ውስጥ እውነታ አለ ያንን እውነታ መካድ የሚፈልግ ካላ እሱ ሌላ ነገር ነው፡፡ ግን ጽሁፍ በሚጻፍበት ግዜ ጠቃሚ የሆነውን ነገር ወስደን የጸሀፊውን አቋም ለራሱ መተው ነው፡፡ እውነታው አልዋጥ ሲል የጸሀፊውን ማንነት (ፕርሰናሊቲ) ከመሞገት፡፡ በየቢሮዋችን እና ቤታችን ያለን ሰነድ እስቲ ለራሳችንም ለትውልድም እንዲጠቅም አርገን እንጠብቅ፡፡ ለውጥ ከራስ ይጀምራል እንዲሉ….
ReplyDeleteዳንየ! እንዴት ሰነበትህ? እይታህን ወድጀዋለሁ ፌስ ቡክና ትዊተር በነገሱበት ዘመን የባዕድ ሃገር ታሪክ እያንቆለጳጰስን ፤በኢንተርኔት ያልተጻፈ ታሪክ ታሪክ ሳይመስለን ይኸው ፍጻሜያችን ይደርሳል ልብ ይስጠኝ እንጅ ምን እንላለን፡፡
ReplyDeleteአይጦቹ ገግ they are allowed everywhere.
ReplyDeleteታሪክ ቀርጣፊዎቹ
amazing dani god keeps you and your family it is an intersting view......... yes........ awo "enesu musinachewn yiblu egnam tarikachin enibila"
ReplyDeleteHow can I get the contact information for Deacon Daniel? I live in North America and would like to get his email or I can give him either my email address or phone number.
ReplyDeleteThanks
Gizaw legesse
ታሪክ የሚጠላ መንግስት ነው ያለን. እስቲ በ ዪኒቨርስቲዎቻችን ያሉት የታሪክ ትም/ት ክፍሎች እንይ ሁሉም ማለት ይቻላል በተማሪ ድርቅ ተመትተዋል ችግሩ ምንድን ነው??? ለማንኛውም ዳኒ ሌላ ግዜ በመጥፋት ላይ ያሉ ትም/ት ክፍሎች ብለህ እንደምትጦምርልን ተስፋ አደርጋሎህ የሁል ግዜም ተማሪህ ክብሮም ዘ ዓዲገራት
ReplyDeleteወረቀት ቢረክስ ተቃዋሚ ይፅፋላ! ቢራ ግብሩ ቢቀንስ ቢራ ይጠጣላ! መንግስት እውቀታችን ሳይሆን ሆዳችን እንዲሰፋ ነው የሚፈልገው፡፡ ይሄ ህዝብ ከነቃ ይጥለዋላ! ኢህአዴግ 100 አመት ሳይገዛ እንዴት ይለቃል!!! ግን የታሪክ ሀቅ ነው ኢህአዴግ ይወድቃል!!! ለዘላለም አይገዛም!!! ማንም ቢመጣ ግን ለኢትዮጵያ ቢሆን መልካም ነው ኢህአዴግም ቢሆን እራሱን ካረመ! መቼም ማይሳሳት የለም
ReplyDeleteዳኒ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን
ReplyDeleteVery interesting and important issue Dani.Let us have an attitude change first then start from personal to national filing system. Keep it up.
ReplyDelete‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡፡ አታይም ሠላሳ ሺ ሕዝብ የሚይዝ ኮንዶሚንየም ሲገነባ በግ ማረጃ እንጂ ቤተ መጻሕፍት ተገንብቷል?
ReplyDeleteyehan ye iandent semat be ye sament,were,amet......sayhon ethiopia tekedem iyalku.fetarin ilemenalw inde iyalku ethiopiaya yemelwen kall ke iafa afatefia hulam bemeliasa yeje indezoriat.tadya yehan iandent yemiatefu benen ye ethiopia amelak yemels weyes yiatefa lebel emama? I LOVE SHE LOVE YOU LOVE WE LOVE MAMA ETHIOPIA.D/N ye inata lij nurelen ignam inemarebh.mekoya from hawassa
ReplyDelete‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››
ReplyDeleteቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡
‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡
‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡
ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ታሪክ እንበላለን፡፡
ከወረቀት ግብር የቢራ ግብር በሚቀንስባት ሀገር፤ ኪነ ጥበብ ከማይበረታቱ ኢንዱስትሪዎች መደብ በተመደበባት ሀገር ምን ትጠብቂያለሽ
ReplyDelete‹‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡›› የሰሚ ያለህ!
ReplyDeleteI am wordless, simply, God bless you. You have done great and impressive work.
ReplyDeleteDaniel - as always this is a great story. Your writing and contribution touch each of us to revolutionized for change of norm, culture, and way of thinking. I wish the people of Ethiopia read your books and learn from it. God bless you and thank you for your contribution.
ReplyDelete‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡
ReplyDelete‹‹እዚህ ከተማ ለስብሰባ፣ ለድግስ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣ ለቢል ቦርድ፣ ለሲምፖዝየም፣ ለምናምን መታሰቢያ ቀን፣ ለምናም መመሥረቻ ቀን የሚሆን በጀት እንጂ ለዕውቀት የሚሆን በጀት የለም፡
ReplyDeleteYes you are write that's way we oppose EFDRE B/C they have no knowledge about country how to put history for theiR child absolutely they are like Muhamed giragn and Yodit Gudit
ReplyDelete‹ባክሽ አሁን ወሬውን ትተን እነርሱ ሙስናቸውን እኛ ታሪካችንን እንብላ፡፡››
ReplyDeleteቆርጠም ቆርጠም ሲል አስነባቢው ቀና አሉ፡፡ እንዳጋጣሚ አንድ አንባቢ ገብቷል፡፡
‹‹አባት፣ አይጥ ሳይሆን አይቀርም›› አላቸው፡፡
‹‹ባክህ በጨረሱትና እኔም ወደሌላ ቦታ በተዛወርኩ ይሻለኝ ነበር›› አሉት፡፡
ቆርጠም፤ ቆርጠም፤ ቆርጠም
ታሪክ እንበላለን፡፡