Tuesday, October 29, 2013

የሌለውን ፍለጋ -ክፍል አንድ

አቡነ ተክለ ሃይማኖትና አቡነ ኤዎስጣቴዎስ( ጎርጎራ፣ ደብረ ሲና ማርያም)
ተስፋየ ገብረ አብ ‹የስደተኛው ማስተዋሻ› የተሰኘ መጽሐፍ ማውጣቱንና ባነበው መልካም እንደሆነ ገልጦ አንድ ወዳጄ ‹ስስ ቅጅውን› ከሀገረ አሜሪካ ላከልኝ፡፡ ከዚህ በፊት ሌሎች መጻሕፍቱን አንብቤያቸዋለሁ፤ በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል እንደ አበሻ መድኃኒት ነገሩን ሁሉ እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምስጢር ስለሚያደርገው፤ በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ፤ ተስፋዬ ለምን እንደዚህ ይጽፋል? እያልኩ የምጠይቃቸው ነገሮች ነበሩ፡፡
በዚህ መጽሐፉ ውስጥም ያንን ጥርጣሬየን አጉልቶ ሥጋ ነሥቶ እንዳየው የሚያደርገኝ ነገር ገጠመኝ፡፡ ተስፋየ በገጽ 306 ላይ ‹‹የፍስሐ ጽዮን ፖለቲካ› በሚል ርእስ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የማያውቀውን ነገር ጽፏል፡፡ ስለማያውቀው ነገር የጻፈው ባለማወቁ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አንድም ለማወቅ ባለመፈለጉ፣ አለያም ሆን ብሎ የማፍረስ ዓላማ ይዞ ይመስለኛል፡፡
ይህን የምለው በሁለት ምክንያት ነው፡፡ ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለመጻፍ ሲፈልግ ሊያነባቸው የሚችላቸው መጻሕፍት በምድረ አውሮፓ እንደ ማክዶናልድ በዝተው ሞልተው ይገኛሉ፡፡ አብዛኞቹ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ባልሆኑ ሰዎች የተጻፉ ናቸው፡፡ ሌላው ቢቀር ኤንሪኮ ቼሩሊ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔቶች ታሪክ(Gli Abbati di Dabra Libanos, 1945)፣ ኮንቲ ሮሲኒ ከሐተታ ጋር ያሳተመውን ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣በዋልድባ ቅጅ (Il Gadla Takla Haimanot secondo la redazione Waldebbana, 1896)፣ የዊልያም በጅን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወትና ተአምር (The Life and Miracles of Takla Haymanot, 1906)፡፡ ከኢትዮጵያውያን ጸሐፍትም ውስጥ የታደሰ ታምራትን Church and State in Ethiopia, ማንበብ በተገባው ነበር፡፡


ከዚህም ዘልሎ ጥልቅ ጥናት አድርጌ ደረቴን ነፍቼ እናገራለሁ ለሚል ደግሞ እንግሊዝ ምቹ ናትና ሎንዶን ወደሚገኘው ብሪቲሽ ሙዝየም ሄዶ በማይክሮ ፊልም የተነሡትንም ሆነ በአካል ያሉትን ብራናዎች ማየት ነው፡፡ እዚያም የማያደርሰው ከሆነ በዋና ከተማው በሆላንድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙትን የጌታቸው ኃይሌን THE MONASTIC GENEALOGY OF THE LINE OF TÄKLÄ HAYMANOT OF SHOA, (Rassegna di Studi Etiopici, Vol. 29 (1982-1983), pp. 7-38)፤ የተስፋዬ ገብረ ማርያምን A Structural Analysis of Gädlä Täklä Haymanot(African Languages and Cultures, Vol. 10, No. 2 (1997), pp. 181-198)፤ የሐንቲንግ ፎርድን (G.W.B. Huntingford, "The Lives of Saint Takla Haymanot," Journal of Ethiopian Studies, 4(1966), 34-35.) የአሉላ ፓንክረስትን Dabra Libanos Pilgrimage Past and Present, The Mytery of the Bones and the Legend of Saint Takla Haymanot,(the sociology ethnology Bulletin) 1,3 (1994), P. 14-26 ጥናቶችን ማየት ይቻል ነበር፡፡ ያም ካልሆነ ወደ ቤልጅየም ሄዶ ፒተርስ አሳታሚ ከጥልቅ ጥናት ጋር የሚያሳትማቸውን የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዛግብት ኅትመቶች ማገለባጥ ይቻል ነበር፡፡
የገረመኝ ገድለ ተክለ ሃይማኖትን ያህል በኢትዮጵያ ታሪክ (History)ና የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) ታላቅ ቦታ ያለው፣ በኢትዮጵያ ገድላት ጥናት(Hagiography) ቀዳሚ የሆነና በብዙ አጥኝዎች የተጠና ጉዳይ ያለ ምንም በቂ ማስረጃ አፈርሳለሁ ብሎ መነሣቱ ነው፡፡ ይኼ ደግሞ ከማይወጣበት የክርክር አዘቅት ውስጥ እንዲወድቅ አድርጎታል፡፡
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ሥዕል( እስክንድርያ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን - ግብጽ)
ተስፋዬ ጽሑፉን የጀመረው በስድብ ነው፡፡ ኤርትራዊት እናቱ ‹ይዘምሩት ነበር‹ ብሎ ያቀረበው ጽሑፍ የራሱን ስድብ በእና ያሳበበበት ነው፡፡ የኤርትራን ቤተ ክርስቲያንና ኤርትራውያን ክርስቲያን እናቶችን ከእርሱ በላይ አውቃቸዋለሁ፡፡ ተሰድደው በየሀገሩ ከተበተኑት ጋር አብረን ቋንቋና ድንበር ሳያግደን አገልግለናል፡፡ አሥመራ ከተማ ከሚገኙት ታላላቅ አድባራት አንዱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በምንም መልኩ አንዲት ኤርትራዊት እናት ተስፋዬ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተሳለቀውን ‹መዝሙር› አትዘምርም፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደማቸው የፈሰሰው ሰባት ዓመት ሙሉ ለጸሎት የቆሙበት እግራቸው በጸሎት ብዛት በመቆረጡ እንጂ ሰይጣን ‹ፈንግሏቸው› አለመሆኑን ኤርትራውያን እናቶች በሚገባ ያውቁታል፡፡ የሚገርመው ነገር ተስፋዬ በጆሮ ጠገብ የሆነ ቦታ የሰማውን መዝሙር አጣምሞት እንጂ መዝሙሩ እንዲህ አይደለም፡፡
ተክለ ሃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው
ይኼው ለዘላለም ያበራል ገድላቸው
ነው የሚለው፡፡
ተስፋዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ አነበብኳቸው የሚለን አምስት መጻሕፍትን ነው፡፡ የአባ ዮሐንስ ከማ፣ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ የጽጌ ስጦታው፣ የዳኛቸው ወርቁና የኢረይን ሙራይ፡፡ አባ ዮሐንስ ከማን እንደማያውቃቸው፣ የጻፉትንም ገድል እንዳላነበበ የሚያሳብቅበት ‹ደብተራ› ሲላቸው ነው፡፡ አባ ዮሐንስ ከማ ሰባተኛው የደብረ ሊባኖስ እጨጌ እንጂ ደብተራ አልነበሩም፡፡ በዚያ ዘመን ‹ደብተራ› ማለት የንጉሡን ደብር(ድንኳን) የሚያገለግሉት ካህናት ናቸው፡፡ አባ ዮሐንስ ከማ በዐፄ ይስሐቅ(1407-1423)ዘመንና በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ(1437-1461)የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበሩ ደብረ ሊባኖስን እንደገና ያሳነጹ ገድለ ተክለ ሃይማኖትንም ያስጻፉ አባት ናቸው፡፡ ተስፋዬ አባ ዮሐንስ ከማ ከ200 ዓመታት ቆይታ በኋላ ስለ ጻፉ ተሳስተዋል ይላል፡፡ ባታውቀው ነው እንጂ ሙሴ ኦሪትን የጻፈው ዓለም ከተፈጠረ ከሺዎች ዓመታት በኋላ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ገድሎች ዘግይተው የሚጻፉት የአንድን ቅዱስ ቅድስና ለመመስከር ካረፈ ቢያንስ ግማሽ ምእተ ዓመት ስለሚያስፈልገው ነው፡፡ በመቃብሩ ላይ የሚሠሩት ተአምራት፣ በአማላጅነቱ የሚሠራቸው ተአምራትና ሌሎችም መታየት አለባቸው፡፡ 
ተስፋዬ አላዋቂነቱን እንደ ዕውቀት ስለወሰደው እንጂ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል የመጀመሪያው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድል አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አራት ቀደምት ሰዎች ጽፈዋል፡፡ 1)በስንክሳር ተጽፎ የሚገኘው(በተለይም በፓሪሱ ስንክሳር) አጭር የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ፣ 2) የትግራይ ተወላጅ በሆነው በተክለ ጽዮን የተጻፈው የዋልድባው ገድለ ተክለ ሃይማኖት [አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት (በቆብ) የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ መድኃኒነ እግዚእን ሲያመነኩሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደግሞ ሰባቱ ከዋክብት የተባሉትንና በጣና ዙሪያ የሰበኩትን (አቡነ ዮሐንስ ዘቁየጻ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቋ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልተዋርና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን) ሲያመነኩሱ ነው ምንኩስናን ተቀብለው ለተልዕኮ የተሰማሩት፡፡ ለዚህም ነው የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ዋልድባዎች የጻፉት፡፡] 3)ያልታወቀ ጸሐፊ አጭሩንና የሐይቅ እስጢፋኖስ ቅጅ የሚባለውን ጽፏል፡፡ ይኼኛው ገድል ቀዳሚ ሳይሆን አይቀርም፤ አንደኛ የተጻፈው ከሌሎች ቅዱሳን ገድሎች ጋር እስትግቡእ ሆኖ በስንክሳር መልክ ነው፡፡ ሁለተኛ የተጠቀማቸው አማርኛዎች በአሁኑ ጊዜ ጥቅም ላይ የሌሉ ዓይነት ናቸው፣ 4)አቡነ ዮሐንስ ከማ የጻፈው የደብረ ሊባኖስ ቅጅ ናቸው፡፡
ይህ የአቡነ ዮሐንስ ከማ ገድል ምናልባት ከ1418-19 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ይስሐቅ ዘመን የተጻፈ መሆኑ ይገመታል(Encyclopedia Aethiopica, Vol. IV, P. 832) በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘው ዐረብኛው ገድል በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመን(1533-1551) የተጻፈ ይመስላል(Encyclopedia Aethiopica,Vol.IV, P.832)፡፡ ያልተመዘገቡ አያሌ ገድላት በየገዳማቱ መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ 22 የብራና ገድሎች በአውሮፓ፣ 20 በኢትዮጵያ የማኑስክሪፕት ቤተ መጻፍት(EMML)፣ 3 በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት፣ 5 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገድሎች ይገኛሉ፡፡ በአንድ ቅዱስ ላይ የተለያዩ ቅጅዎች መገኘታቸው መረጃዎችን ያሰፋቸዋል እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ስለ አንድ ክርስቶስ አራት ዓይነት ወንጌሎች መጻፋቸውን ማስታወስ ይበቃል፡፡
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በብዙ ሥራዎቻቸው የተከበሩና የተመሰገኑ ሊቅ ናቸው፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ ላነሡት ሃሳብ ግን ያቀረቡት ማስረጃ የላቸውም፡፡ ከኢትዮጵያ ገድሎች ሁሉ የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ገድል ያህል የሚታወቅና የተጠና የለም፡፡ ከሌሎች ጋር እየተነጻጸረም ሆነ በራሱ(Textual analysis) ገድለ ተክለ ሃይማኖት በአውሮፓውያንም ሆነ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ተጠንቷል፡፡ እስካሁን ግን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌም ሆኑ ሌሎች የሚሉት ‹ሌላ ገድል› አልተገኘም፡፡ አለቃም ያነበቡት ከሆነ ያነበቡትን፣ ያገኙት ከሆነም ያገኙበትን አልነገሩንም፡፡ ምንጭ የላቸውምና ለታሪክ ክርክር ሊጠቀሱ አይችሉም፡፡
ጽጌ ስጦታውም ቢሆን ምናቡንና አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ጠቀሰ እንጂ አለ የሚለውን ‹የዚያኛውን ተክለ ሃይማኖት› ገድል ሊያመጣልን አልቻለም፡፡ ዳኛቸው ወርቁ የጻፈው ልቦለድ እንጂ ታሪካዊ ዋጋ ያለው ነገር ስላልሆነ ለክርክር የሚቀርብ አይደለም፡፡ ይባስ ብሎ ተስፋዬ ኢለይን ሙራይ ለልጆች ብላ የጻፈችውን ተረት ጠቅሶልናል፡፡ ይህ ነገር የቦሩ ሜዳን ክርክር ነው ያስታወሰኝ፡፡
 በቦሩ ሜዳ ክርክር ‹ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደት አለው› የሚሉና ‹ሦስት ልደት አለው› የሚሉ ሊቃውንት ተከራክረው ነበር፡፡ በዚህ ክርክር የሁለት ልደትን ወክለው ከተከራከሩት መካከል የነበሩት መልከአ ብርሃን ወልደ ዮሐንስ ‹ነአምን ክልኤተ ልደታተ› የሚል ንባብ ከሊቃውንት መጽሐፍ ጠቅሰው ተከራከሩ፡፡ ዐፄ ዮሐንስም የሦስት ልደቶችን ተከራካሪ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስን ‹በል አንተም እንደ እርሱ ከሊቃውንት መጽሐፍ ሦስት ልደት የሚል ንባብ አምጣ› አሉት በዚህ ጊዜ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ ‹በደብረ ብርሃን ተአምረ ማርያም ይገኛል› አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ‹ከምታስተምረው ከአራቱ ጉባኤ አጣህና ነው ከተአምረ ማርያም ትጠቅሳለህ›› ቢሏቸው ‹ ከጉባኤው መጽሐፍስ የለም››  አሉ ይባላል፡፡
የተስፋዬ አጠቃቀስ ከዚህም የወረደ ነው፡፡ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ የተወቀሱት ለእምነት ክርክር የማይጠቀስ የተአምር መጽሐፍ በመጥቀሳቸው ነው፡፡ ተስፋዬም ከዚያ ወርዶ ወርዶ ለታሪክ ክርክር የማይጠቀስ የተረትና የልቦለድ መጽሐፍ ሲጠቅስ ይገኛል፡፡
ተስፋዬ ወግዳ የተሸሸገ ለሕዝብ የማይቀርብ ገድለ ተክለ ሃይማኖት አለ ይላል፡፡ በሀገራችን ጠንቋይ እንዳይጋለጥ ሲፈልግ የሌለ ነገር ያዝዛል ይባላል፡፡ ተስፋዬም ወግዳ የተደበቀ ገድል አለ አለ፡፡ ወግዳ በሰሜን ሸዋ በደብረ ብርሃን ዙሪያ ወረዳ ሥር የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የብራና መጻሕፍት በ1964 ዓም ማይክሮ ፊልም መነሣት ሲጀምሩ ከሰሜን ሸዋ ነበር የተጀመረው፡፡ እነ ሥርግው ሐብለ ሥላሴ(አጥንታቸውን ያለምልመው እንጂ) እያንዳንዷን ወረዳ ለቅመው አንሥተውታል፡፡ እንኳን በገዳማት አድባራት የሚገኙት በግለሰቦች እጅ የሚገኙትም አልቀሯቸውም፡፡ እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ መጽሐፍ የሕንድ፣ የግሪክ መጻሕፍት አልቀራቸውም፤ እንኳን ገድልና ተአምር የቤተ ክርስቲያንን እምነት የሚቃረኑ መጻሕፍት በክብር ተጠብቀው ነው የተገኙት፡፡ ተስፋዬ ወግዳ የማይደረስበት መስሎት መደበቂያ ዋሻ አለ ይላል፡፡ ወግዳኮ ከአዲስ አበባ የ120 ኪሎ ሜትር ጉዳይ ነው፡፡
በማይክሮ ፊልም ቀረጻው ወቅት በሥራ ላይ የተሠማሩት የሀገሬው ተወላጆች ነበሩና ያስቸገራቸው ነገር አልነበረም፡፡ በዚህ ጉዞ ውስጥ ይህ ‹የወግዳ ገድል› ይገኝ ነበር፡፡ ግን የለምና አልተገኘም፡፡ ይህ ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ዛሬ አልተጀመረም፡፡ በትግራይ፣ በወሎ፣ በጎጃም በተክለ ሃይማኖት ስም ስለሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን የተጻፉ ገድሎች አሉ እየተባለ እንዲሁ በአፍ ታሪክ ይነገራል፡፡ እስካሁን ግን ማስረጃ አምጥቶ ያረጋገጠ አልተገኘም፡፡ የትግራይ ገዳማት የብራና መጻሕፍት በቅርቡ ዲጂታላይዝ ተደርገዋል፡፡ ግን የተባለው አልተገኘም፡፡ በመካከለኛው ዘመን ሌላው ቀርቶ ከማዕከላዊው መንግሥት ተጋጭተው ርቀው በነበሩት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ገዳም በጉንዳ ጉንዲ እንኳን የደብረ ሊባኖሱን ገድል የመሰለ ቅጅ ነው የተገኘው፡፡
ማንኛውም ክርክር ሲቀርብ ለክርክሩ ብቁ የሆነ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡ ልቦለዱንም፣ ቀልዱንም ለታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ቧልት እንጂ ቁም ነገር አይሆንም፡፡
ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባለውን የታወቀ ታሪክ (official history) ለመቀበል አልፈለገም፡፡ ያ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ አዲስ ማስረጃ አምጥቶ ወይም ነባሩን ማስረጃ በክርክር አፍርሶ ያላየነውን ካሳየን እናመሰግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን፡፡
ሮማውያን የሕግ ሊቃውንት Argumentum ad Contrario የሚል መርሕ ነበራቸው፡፡ ‹አንድን ነገር የታመነውንና የታወቀውን ትተህ በተቃራኒው ያለውን አረጋግጥ› ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን በተመለከተ የሚባለውንና የሚታመነውን ተወውና ተቃራኒውን በማስረጃ፣ በተጠየቅና በትንታኔ አረጋግጥ ማለት ነው፡፡ ተስፋዬ ይህንን ለማረጋገጥ ዐቅም አላገኘም፡፡ እንዲሁ ቧልቱን ብቻ ነገረን፡፡
ተስፋዬ የታሪክ ስሕተቱን የሚጀምረው በሰባተኛው መክዘ ዐፄ ዳዊት የሚባሉ ንጉሥ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ ሲለን ነው፡፡ ተስፋዬ በቀላሉ የሚገኘውን የሬኔ ባሴን ታሪከ ነገሥት፣ የሥርግው ሐብለ ሥላሴን የነገሥታት ዝርዝር፣ የተክለ ጻድቅ መኩሪያን መጻሕፍት አለያም የብላቴን ጌታ ኅሩይን ‹ዋዜማ›፣ የጌታቸው ኃይሌን ባሕረ ሐሳብ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1975 አሳትሞት የነበረውን The Dictionary of Ethiopian Biography, ብታይኮ እንዲህ ካለ ስሕተት ውስጥ አትወድቅም ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዳዊት በሚል ንጉሥ መጀመሪያ የነገሠው ዐፄ ዳዊት አንደኛ ከ1374-1406 ዓም ነው፡፡ ከየት አምጥተህ ነው በሰባተኛው መክዘ ያደረግከው፡፡
እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?
ለመሆኑ ተስፋዬ እናዳለው ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች  አሉን? ሦስቱስ በገድለ ተክለ ሃይማኖት ተቀላቅለዋልን? ሳምንት እንመለሳለን፡፡
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ ላይ የወጣ ነው

196 comments:

 1. best argument !! I believe you will win!!!

  ReplyDelete
 2. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 3. Don't forget his real name is Tesfaye GEBRE-EBAB!!

  ReplyDelete
 4. I have a chance to read the soft copy of Tesefaye's recent literature the so called Yesedetegnaw Masetawoesha and we discussed the objective of his paper with my colleagues. He always try to destroy the history of our country,Ethiopia and our religion the Ethiopian Orthodox church. Thanks Danny, God bless you!!!

  ReplyDelete
 5. u are best arguer man! tesfaye has little knowledge about church & politics.

  ReplyDelete
 6. edmie ena tena yistilin

  ReplyDelete
 7. Tesfaye and Dawit Kebede are two still walking dead individuals. They have addicted not to value what TRUTH is all about. Of course, that is what spies do for living and glad that these food for nothing guys have now become naked

  ReplyDelete
 8. He is so Chewa.....Shame on him

  ReplyDelete
 9. D/n Daniel 'Eqibete emenetihin"betedegagami silemeitasay Egziabher kale hiwotin yasemalin. Awaki nen bayoch ezaw kemayawukibet hedew yinageru.

  ReplyDelete
 10. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 11. እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thanks D/N Daniel I am really surprised about your argument fantastic! God bless you

   Delete
 12. Amlake Teklehaymant yerdah!!!

  ReplyDelete
 13. አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት የቄሱን መጸፍ አጠበች አሉ፡፡ ምን አለበት ስለማታዉቀዉ ሐይማነኖት ትተህ ተረት የመሰለ ፖለትካህን ዐርፈህ ብትፀፍ ማጣፈጫ መሆኑ ነው!!!!
  ዲ.ን ዳንኤል ረጅም ዕድሜን ይስጥልን!

  ReplyDelete
 14. እግዚአብሔር የአገልግሎት እድሜህን ያስረዝምልን

  ReplyDelete
 15. yehen tsehufe endetesfe yanesasaehe egziabhere yemsgne.

  ReplyDelete
 16. እናመሰግናለን ዳኒ የተክልዬ ጸሎት ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 17. አቤት ሐገሬ ገመናሽ አቤት ያውቃሉ ያልናቸዉ ፀሐፊዎቻችን(ሁሉንም አይደለም)
  አላዋቂነታቸው አቤት የዚች ቤተክርስቲያን ፈተና(ተ/ሐይማኖት ላይ ጥያቄ ያነሳ ማለት ቤተክርስቲያን ላይ ጥያቄ አነሳ ማለት ነዉና)ዳኒ እንዳንተ ያለ እግዚአብሔር አያሳጣን

  ReplyDelete
 18. ortodokisin lematilalati tireti yaderigalu gini yafiralu yihi fetera enigi begh hageri tareki bilo yeminegirew yelemi menifesi kidusi yigiletileti.

  ReplyDelete
 19. Thank you Dani, may the intercession of Abune Tekle Haimanot be with you. Amen

  ReplyDelete
 20. God bless you Dn Daniel

  ReplyDelete
 21. Wow!!! I don't have any idea what are you talking about. I can say only one thing that is " THANK YOU DANI" I never know that we have these many books about Saint Takla Haymanot. I mean I don't know about your knowledge about Ethiopian Saints history but it is a detail answer for him. He may not know about your respond, if anybody knows Tesfaye GEBRE-EBAB please send him this message. I guess Dani Met him before he respond this answer if not please contact with Tesfaye to discuses and to teach him about how Ethiopian people feel about our history.

  ReplyDelete
 22. ዲ/ን: ከአስመሣይ የደራሲ (ደራሲ ከተባለ) ስህተት ስላተረፍከን እግዚአብሄር ይባርክሕ

  ለርሱም ልቦና ይስጠው

  ReplyDelete
 23. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 24. Thanks Dani, May God bless your work, life, and your family.

  ReplyDelete
 25. ጎሽ! ጎሽ! ዲያቆን ዳንኤል፤ እግዚአብሔር ይስጥህ! እንዲህ ነው እነኚህን ቅሌታሞች፣ ውሸታሞችና፣ የሰይጣን ጋሻ ዣግሬዎችን ማሽቆጥቆጥ። ይበል ነው!እ እንዲህ ነው ልሣኑን ማር አድርጎ የከፈተለት የቤተ ክርስቲያናችን ልጅ የሰይጣንን ኃይሎች የሚዋጋው። የዲያብሎስ ወገን የሆነው መርዘኛው ተስፋዬ እና ወገኖቹ በንደዚህ ዓይነት በመረጃ የዳበረና የበሰለ ሙግት ሲጋፈጡ እንደአባታቸው ሙሽሽ ብለው እንጦሮንጦስ ነው የሚወርዱት። እግዚአብሔር አምላክ እናት ኢትዮጵያን ለማቆራቆዝ የተነሱትን እንደተስፋዬ ዓይነቶቹን የዲያብሎስ ጭፍራዎች ያውድማቸው፤ እናት ኢትዮጵያንም በቸርነቱ ይጎብኛት! አሜን

  ReplyDelete
 26. እንዳንተ ያሉ የረጉ ጥልቅ ኣዋቂዎች ስላጣን ነው ይህ ሁሉ ጣጣ የተደራረበብን። ካጻጻፍህ፣ ካቀማመጥህ፣ ማስረጃ ከምቅረብህ፣ የሁሉም ኣቅጣጫዎች ማስረጃዎች፣ የቀረ የለም እግዝ ኣብሔር ይባርክህ። ተስፍየን ኣጋለጥከው ብቻ ሳይሆን እኛንም መንገድ ኣስያዝከን። ባንዳዎች ኣቀራረባቸው ሁሌ እንደተጋለጡ ናቸው። ኣንተ ግን በሰላም ትተኛለህ።
  ነጋ

  ReplyDelete
 27. Yalawaqi sami Nft Yleqelqal alu. Dani awqo metsaf. Endih yarekal.Geta. Ybarkh abo .

  ReplyDelete
 28. Thanks Dn Daniel! still we need original Ethiopian to write and tell the general truth/facts as well as the real history for this poor reader people (including me). I really proud of you Dani; we want such kind of people to convince, teach, ... such uneducated people!!!

  ReplyDelete
 29. I need ‹የስደተኛው ማስተዋሻ) book; anyone of my brothers would you please attached e soft copy? Thank you in advance!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይቅርብህ ወዳዴ ሙሉ በሙሉ በውሸት የተሞላ ነው

   Delete
 30. ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 31. Di Dani edmehin yematusala yahel yadrglin and neger gin tesfaye yalteredeaw. tekelye eko ethiopiyawi nachew maletim be tekeleye meta malet be ethiopia meta malet new lengeru yemoten wesha yemidebedb yelem yechi hiwot yalat betekrsityan minew ayen bezebat

  ReplyDelete
 32. tks D/N Daniel.....I don't like most part of his new book. It seems he has something behind......God bless u!!
  Yitbsh

  ReplyDelete
 33. Dani, kale heyewot yasemalen !!!

  ReplyDelete
 34. tewew ebakeh molachw new

  ReplyDelete
 35. አሁን ገና ተሰፋየን አመሰገንኩት እርሱ ይህንን ስህተት ባይሰራ ዳኒ መች ይኼን ይፅፍ ነበር። በተረፈ ተስፋዮ ጥላቻው ከኢትዩጵያዊነት ጋር ነው።አለማወቅም ፈልጎ አይመስለኝም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዉይ በእናትህ የልቤን ነገርከኝ፤ እንኳንም ተስፋየ ተሳሳተ፡፡

   Delete
  2. Enquanm Tesfaye tesasate.

   Delete
 36. Wow thanks Dn Dani I read tesfaye G/abe book some of people I know,told me that they grow up with him Deberezeyt , but I told them he wrote so much lies, and I flipped page to page and showed them he wrote wrong information. Again thanks to you and God the Almighty Ethiopian orthodox tewahido church has such a great Dn can answer with complete proof
  God bless you!

  ReplyDelete
 37. I don't know why, Tesfaye do not have respect for people he wrote about. I have the soft copy, but didn;t read it. After I read your comment, I just check it the page referred. There is no respect at all in his writing. Libona Yistew. Egziabhere kante gar yihun Dn. Daniel.

  ReplyDelete
 38. Yesewyewn anbibe neberna and sew yitsifletal biye tebike neber yihew testafelet.Dehina senbit.

  ReplyDelete
 39. ye daikon Daniel Keberet eweket tariya indeneka yeteredahubet tsihufe newu ..... betam newu yegeremegn yehen hulu mereja indalen rasu alawekem neber ...ebekehe Diakon bezu mesihafeten legna le addisu tewelede tsifehe aserekeben bezu indenemar ..egezabeher yisetelign.

  ReplyDelete
 40. ድሮም ከ ቡርቃ በስተጀርባን ሲጽፍ ምን እንደሆነ ና ምን እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር ዝም ስለተባለ ዛረም ደገመ፡፡ አላማህን በደንብ እናዉቀዋለን

  በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ

  ReplyDelete
  Replies
  1. it is not "ke burka bestegerba" ,but "ye burka zimta"...

   Delete
 41. ድሮም ከ ቡርቃ በስተጀርባን ሲጽፍ ምን እንደሆነ ና ምን እንደሚፈልግ ግልጽ ነበር ዝም ስለተባለ ዛረም ደገመ፡፡ አላማህን በደንብ እናዉቀዋለን

  በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት የመንግሥት ምሥጢሮች እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ::

  ReplyDelete
 42. ለተስፋዬ እግዚአብሔር ልቦናውን ይክፈትለት፣ለእኛ ማስተዋሉን ይስጠን፣ላንተ ደግሞ ዲ/ን ዳንኤል ረጅም እድሜ ይስጥልን፡፡ እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 43. እንዳለመታደል ሆኖ የሃገራችን ፖለቲካ ምሥጢራዊነት ስለሚያጠቃው እና ተስፋዬ ገብረአብን የመሰሉ ‹‹ውስጥ አዋቂ›› ነን ባዮች የሚጽፉአቸው ‹‹ታሪኮች›› ትኩረት መሳባቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህም ቢሆን የጸሐፊዎቹን ችሎታ ሳይሆን የሀገራችንን የፖለቲካ ድብቅነት ነው የሚያጎላው፡፡
  የተስፋዬን ጽሑፎች ‹‹አጋለጥኩ›› ከሚላቸው እውነታዎች (ፋክትስ) ለይተን ያየናቸው እንደሆነ ግን ነባሩን የኢትዮጵያውያን የአኗኗር ባህል፣ ትውፊት እና ታሪክን ከመሠረቱ ነቅሎ የሚጥሉ፣ የሚዘነጥሉ ጀብደኛ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ነገስታቱን፣ ቅዱሳኑን፣አንዳንዴም ሕዝቡን አዋራጅ በሆነ መልኩ ሲገልጻቸው ሲያብጠለጥላቸው እናገኘዋለን፡፡ ተስፋዬ ጀማሪ ጎረምሳ ጸሐፊ ቢሆን ኖሮ ከተራ ጀብደኝነት እንቆጥርለት ነበር፡፡ የአዋቂ አጥፊ ሲሆን ግን ከስተጀርባው መግፍኤ የሆነው ከኢትዮጵየዊነት ጋር አንዳች ጥላቻ መኖሩን እንድንጠረጥር እንገደዳለን፡፡

  ReplyDelete
 44. kalhywit yasemalen dn.daneil Egzabhare amalak yetebkhi

  ReplyDelete
 45. aheya fesa teblo afencha ayeyazem!!!! thank you Daniel

  ReplyDelete
 46. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን.
  ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

   Delete
 47. You are right Deacon Daniel, We Eritreans have no such song that insults Abune Tekle Haymanot. We have so many churches with their holy water all around our country. I can't find Tesfaye's Book. But If he really wrote like that, he is not only wrong but he is deliberatelly doing some disusterous thing pointing to our holy church.

  ReplyDelete
  Replies
  1. thank you bro, that is true,Eritreans do not insult abune Tekle haymanot, he is a lair dog.

   Delete
 48. ሰላም ወንድም ዳንኤል አመሰግናለሁ፡፡
  ተስፋያን ይህን እድል ሰለሰጠን ብናመሰግነው ምንአለበት፡፡ ሟች አወሬ ገዳዩን ያስመሰግናል፡፡ ስለ አባታችን ታሪክ ዳንኤልን እንዲያነብ እና እንዲጽፍ ፣እኛም እንድንማር የምናወቀውም እንድንከልስ ፣ አሁንም አዚህ ላይ እንድንጽፍ እድሉን ሰቶናልና፡፡ መልሳችንን በአንድ እወነተኛ ታሪክ ብናሰደግፈውስ ምንአለበት
  አንድ ሰው ነበር አሉ 50ኪግ የሚመዝን ነገር በቦርሳው ይዞ የሚዞር
  አንድ ቀን ይህን እቃ በእጁ አንጠልጥሎ ሱቅ ውስጥ ይገባል፡፡ቦርሳውን ያስቀምጥና መሸመት የሚፈልገውን ከውኖ ዘወር ሲል ቦርሳውን ካስቀመጠበት ያጣዋል፡፡ ከሱቁ ወጣ በሎ አካባቢውን ሲቃኝ
  አንድ ሌባ እየተንገዳገደ ቦርሰውን ተሸከሞ ሲሄድ ያየዋል፡፡ ሌባውም በጉዞው ላይ በቦረሳው ውስጥ ያለው ነገር ሂወቱን ለውጦት በተንደላቀቀ ንሮ ሲኖር በሃሳብ ማእባል ይዋዥቅ ነበር ፡፡ብዙ ሳየጓዝ ሰወየው እሩጦ ደረሰበትና ቦርሳውን በአንድ እጂ ሌባውን በአንድ እጁ ማጅራቱን ጭምድዶ አምሳ ሜትር ያህል አንጥልጥሎ ከወሰደው በውኃላ ሌባውን አንጠልጥሎ ከያዝው እጁ አወረደውና አመሰገነው ፡፡ ሰውየውም ሻንጣውን ከፈቶ አሳየው፡፡ በቦርሳው ውስጥ ያለው ድንጋይ ነው ፡፡ ክብደት ለማነሳት ስለሚጠቅመኝ ነው ይዥው የምዞረው፡፡አንተም ለትንኝ ጊዜም ቢሆን ረድተህኛል እና አመሰግንሃለሁ ብሎ ሸኘው፡፡
  “ክፉ ሰው ክፉ ሰው ውደዱ ይረዳቸሃልና እንዳታንቀላፉ”
  ከበደ ሚካኤል መሰለኝ ያሉት
  አመሰግናሁ፡፡

  ReplyDelete
 49. Abo Egziabher yibarkih. Klehiwot Yasemalin Dn. Berta

  ReplyDelete
 50. የኤርትራን ቤተ ክርስቲያንና ኤርትራውያን ክርስቲያን እናቶችን ከእርሱ በላይ አውቃቸዋለሁ፡፡ ተሰድደው በየሀገሩ ከተበተኑት ጋር አብረን ቋንቋና ድንበር ሳያግደን አገልግለናል፡፡ አሥመራ ከተማ ከሚገኙት ታላላቅ አድባራት አንዱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በምንም መልኩ አንዲት ኤርትራዊት እናት ተስፋዬ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተሳለቀውን ‹መዝሙር› አትዘምርም፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደማቸው የፈሰሰው ሰባት ዓመት ሙሉ ለጸሎት የቆሙበት እግራቸው በጸሎት ብዛት በመቆረጡ እንጂ ሰይጣን ‹ፈንግሏቸው› አለመሆኑን ኤርትራውያን እናቶች በሚገባ ያውቁታል፡፡ የሚገርመው ነገር ተስፋዬ በጆሮ ጠገብ የሆነ ቦታ የሰማውን መዝሙር አጣምሞት እንጂ መዝሙሩ እንዲህ አይደለም፡፡
  ተክለ ሃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው
  ይኼው ለዘላለም ያበራል ገድላቸው
  ነው የሚለው፡፡

  ReplyDelete
 51. Ahuns ewnetn mekber beza.ere yesew yaleh yasblal eko sew endet hulem tekarani mehon yifelgal?ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን.
  ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 52. ሰላም ወንድም ዳንኤል አመሰግናለሁ፡፡
  ተስፋያን ይህን እድል ሰለሰጠን ብናመሰግነው ምንአለበት፡፡ ሟች አወሬ ገዳዩን ያስመሰግናል፡፡ ስለ አባታችን ታሪክ ዳንኤልን እንዲያነብ እና እንዲጽፍ ፣እኛም እንድንማር የምናወቀውም እንድንከልስ ፣ አሁንም አዚህ ላይ እንድንጽፍ እድሉን ሰቶናልና፡፡ መልሳችንን በአንድ እወነተኛ ታሪክ ብናሰደግፈውስ ምንአለበት
  አንድ ሰው ነበር አሉ 50ኪግ የሚመዝን ነገር በቦርሳው ይዞ የሚዞር
  አንድ ቀን ይህን እቃ በእጁ አንጠልጥሎ ሱቅ ውስጥ ይገባል፡፡ቦርሳውን ያስቀምጥና መሸመት የሚፈልገውን ከውኖ ዘወር ሲል ቦርሳውን ካስቀመጠበት ያጣዋል፡፡ ከሱቁ ወጣ በሎ አካባቢውን ሲቃኝ
  አንድ ሌባ እየተንገዳገደ ቦርሰውን ተሸከሞ ሲሄድ ያየዋል፡፡ ሌባውም በጉዞው ላይ በቦረሳው ውስጥ ያለው ነገር ሂወቱን ለውጦት በተንደላቀቀ ንሮ ሲኖር በሃሳብ ማእባል ይዋዥቅ ነበር ፡፡ብዙ ሳየጓዝ ሰወየው እሩጦ ደረሰበትና ቦርሳውን በአንድ እጂ ሌባውን በአንድ እጁ ማጅራቱን ጭምድዶ አምሳ ሜትር ያህል አንጥልጥሎ ከወሰደው በውኃላ ሌባውን አንጠልጥሎ ከያዝው እጁ አወረደውና አመሰገነው ፡፡ ሰውየውም ሻንጣውን ከፈቶ አሳየው፡፡ በቦርሳው ውስጥ ያለው ድንጋይ ነው ፡፡ ክብደት ለማነሳት ስለሚጠቅመኝ ነው ይዥው የምዞረው፡፡አንተም ለትንኝ ጊዜም ቢሆን ረድተህኛል እና አመሰግንሃለሁ ብሎ ሸኘው፡፡
  “ክፉ ሰው ክፉ ሰው ውደዱ ይረዳቸሃልና እንዳታንቀላፉ”
  ከበደ ሚካኤል መሰለኝ ያሉት
  አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 53. አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት የቄሱን መጸፍ አጠበች አሉ፡፡ ምን አለበት ስለማታዉቀዉ ሐይማነኖት ትተህ ተረት የመሰለ ፖለትካህን ዐርፈህ ብትፀፍ ማጣፈጫ መሆኑ ነው!!!!
  ዲ.ን ዳንኤል ረጅም ዕድሜን ይስጥልን!

  Reply

  ReplyDelete
 54. ዲን. ዳንኤል ብዙ መናገር አልፈልግም፤ ብቻ እግዚአብሄር ይጠብቅህ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ትፈልግሀለች፡፡ ይህን ስልህ እንደ አንዳንዶቹ ለራስህ የማይሆን ቦታ ትሰጣለህ ብየ አላምንም፡፡ ከአሁን በፊት ለበውቀቱ አሁንም ለተስፋየ የሰጠኸው መልስ የዘመናችን አትናቴዎስ መሆን እንደምትችል ያስረዳል፡፡ እኔ በበኩሌ የተስፋየ ገ/አብ (ስምን መልዓክ ቢያወጣው ኖሮ ተስፋየ ገብረ እባብ ይባል ነበር ሲባል ሰምቻለሁ) ተንኮል በደምብ ገብቶኛል፡፡ ነገር ግን ውሸት ሲደጋገም እውነት እንዳይመስል ያሰጋልና መልስህን በጣም ወድጀዋለሁ፡፡ ብዙዎቻችን ተንኮሉን ብንረዳም፣ እንደአቅማችን እውነቱን ብናስረዳም እንዲህ በእውቀትም፣ በእውነትም መለኪያ የተሟላ መልስ መስጠት ሳናችል ስንቀር ሰይጣን የልብ ልብ እያገኘ ነበር፡፡ እግዚአብሄር አገልግሎትህን ይባርክልህ!!
  ከጎንደር ልደታ

  ReplyDelete
 55. ሐገራቸውን ፣ህዝባቸውን ፣ ባህላቸውን እና ሐይማኖታቸውን በሌላው ፊት ማዋረድ መሣደብ እንደተስፋዬ ጀብዱ የሚመስላቸው አይታጡም የናት ሆድ ዥንጉርጉር አይደል

  ReplyDelete
 56. ተስፋየ ገብረ-አብ እኮ የኦሮሞ ልጆችና የአማራ ልጆች እንዲጫረሱ በሚፅፈው መፃፍ ያደርግ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፤ እንጅ ስለመንፈሳዊ ነገር ሲጀመር ለመፃፍ ምን ዐይነት ሞራልስ ሊኖረው ይችላል፡፡

  ReplyDelete
 57. እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን ለልጃቹ የሚበጀንን አስተምሮናልና ዲ/ን ዳኒኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን!

  ReplyDelete
 58. እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን፡፡

  ReplyDelete
 59. Dn. Dani, you are a true son of Ethiopia. I am proud of you and please give him a lesson for this .........!!


  fm

  ReplyDelete
 60. Thank you Dani, may the blessing of Abune Tekle Haimanot be with you. Amen

  ReplyDelete
 61. ቤተክርስቲያን ላይ መቼም ቢሆን ጠላት አይጠፋም ለኔ ተስፋዬ አልገረመኝም ወደፊትም እንደዚ አይነት ነገሮች ይፈጠራሉ ግን በጣም ደስ ያለኝ ነገር ቢኖር በዚ ዘመን ዲ ዳንኤል አይነት ሰው መኖሩ ነው በጣም ተገርሜ ነበር ሳነብ የነበረው ለሚነሱ ጥያቄዎች በሙሉ ቤተክርስቲያናዊ መልስ መስጠት የሚችል የኃይማኖት ጠበቃ መኖሩ ከልብ ያስደስታል ማንም ምንም ይበል ምንም እኛ ሙሉ መረጃ አለን ደስ ነው ያለኝ ሌሎችም እንደ ተስፋዬ ጎንተል ቢያደርጉና አንተም ይኼንን እውቀትክን ባካፈልከን ጸጋውን ያብዛልክ ዲ ዳንኤል

  ReplyDelete
 62. ተስፋዬ ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የሚባለውን የታወቀ ታሪክ (official history) ለመቀበል አልፈለገም፡፡ ያ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ አዲስ ማስረጃ አምጥቶ ወይም ነባሩን ማስረጃ በክርክር አፍርሶ ያላየነውን ካሳየን እናመሰግነው ነበር፡፡ እርሱ ግን ወይ የታወቀውን አልተቀበለ፣ አለያም አዲስ ማስረጃ አላመጣ፣ ከሁለት የወጣ ጎመን ሆነብን፡፡

  ReplyDelete
 63. ተስፋዬ አባ ዮሐንስ ከማ ከ200 ዓመታት ቆይታ በኋላ ስለ ጻፉ ተሳስተዋል ይላል፡፡ ባታውቀው ነው እንጂ ሙሴ ኦሪትን የጻፈው ዓለም ከተፈጠረ ከሺዎች ዓመታት በኋላ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ገድሎች ዘግይተው የሚጻፉት የአንድን ቅዱስ ቅድስና ለመመስከር ካረፈ ቢያንስ ግማሽ ምእተ ዓመት ስለሚያስፈልገው ነው፡፡ በመቃብሩ ላይ የሚሠሩት ተአምራት፣ በአማላጅነቱ የሚሠራቸው ተአምራትና ሌሎችም መታየት አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 64. I have a chance to read the soft copy of Tesefaye's recent literature the so called Yesedetegnaw Masetawoesha and we discussed the objective of his paper with my colleagues. He always try to destroy the history of our country,Ethiopia and our religion the Ethiopian Orthodox church. Thanks Danny, God bless you!!! .....................ya I agreed with your idea.

  ReplyDelete
 65. Wow! Interesting. God bless you.

  ReplyDelete
 66. //ይድረስ ለዳንኤል ክብረት!//

  ፀጋሁ ዘእግዚአብሔር ይህደር በላእሌከ፡ አሜን!


  የክብረት ልጅ ክቡር ነው! ሁል ጊዜ በአንተ በእናት ቤተክርስቲያን ልጅ እረካለሁ! በሃይማኖትም ሆነ በበሀገር ላይ ያለህ አእምሮ ህሊናን ያረካልና! ደግሜ እላለሁ ህሊናን ያረካል!  /1/ በቦሩ ሜዳ ክርክር ዐፄ ዮሐንስም የሦስት ልደቶችን ተከራካሪ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስን ‹በል አንተም እንደ እርሱ ከሊቃውንት መጽሐፍ ሦስት ልደት የሚል ንባብ አምጣ› አሉት በዚህ ጊዜ አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ ‹በደብረ ብርሃን ተአምረ ማርያም ይገኛል› አሉ፡፡ ካለ ነገሩ ቢገለጽልን ምሥጢሩም ቢብራራልን መልካም ነበር።

  /2/ በገድለ ተክለሃይማኖት ላይ የአባታችንን ሞት በተመለከተ የሆድ ህመማቸውን እንደ ስጋ ወደሙ ቅቆጥርልሃለሁ የተባለውን ትርጉም ከአንተና ከሊቃውንተ አበው አንደበት መስማት እጅጉን እፈልጋለሁ!

  /3/ እባብ የገደለ መነግስተ ሰማይ ይገባል መባሉ በቁሙ እባብ ሳይሆን ገድሉ እንደተረከልን በእባብ የተመሰለው ዲያቢሎስ እንደሆነ ባውቅም ተጨማሪ ማብራሪያ ካንተ እጠበቃለሁ!


  ብትችል በክፍል ሁለት ብታካትተው ከጽሁፍህ ጋ ባይሄድልህ በሌላ ጊዜ ብትመለስበት መልካም ይመስለኛል!

  ሰላም ለከ!

  ReplyDelete
 67. O My God! what an argument! what a shame to write such a trash article by ignoring this much facts? I don't think he didn't see all the documents. He wrote it to express his deep hate towards EOTC, Amhara and Ethiopianism. What would happen if we don't have you Man?

  ReplyDelete
 68. Kentu ye kentu lig deros min yawekina new ye Ethiopian tarek atefalehu bilo yerasun dedebinet new yasmeseketew

  ReplyDelete
 69. ante yekurt ken lij edmehn new yemlenew tebarek endih new ethiopiawnet ena orthodoxawnet.

  ReplyDelete
 70. This man as said above can be best described by Tesfaye Gebre-EBAB.
  This man is really working for people who do not want Ethiopian Integrity; his books are centered or modeled by peoples name like Chaltu, Anole, .... or previous female member of TPLF.
  I wonder how this man has been key member of government body of EPRDF and I doubt there are still some left over which are Gebre-EBABs for our country's development and Integirity.
  Generally, he and the people/country he is working for are losers.

  ReplyDelete
 71. Kentu ye kentu lig deros min yawekina new ye Ethiopian tarek atefalehu bilo yerasun dedebinet new yasmeseketew

  ReplyDelete
 72. thanks dani you are always the best tell them that Ethiopian orthodox church is always right.

  ReplyDelete
 73. ልቦለዱንም፣ ቀልዱንም ለታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ቧልት እንጂ ቁም ነገር አይሆንም፡፡......
  ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 74. Tesfaye Gebre-EBAB

  ReplyDelete
 75. ዲያቆን ፍጹምOctober 30, 2013 at 4:14 PM

  "በመካከለኛው ዘመን ሌላው ቀርቶ ከማዕከላዊው መንግሥት ተጋጭተው ርቀው በነበሩት የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን"

  ተባረክ ዲያቆን ዳንኤል "እውነትና ንጋት እያደር....

  ReplyDelete
 76. ዮናስ ዘካርያስ ጌታ ባርክህ፤ ብዙ ግዜ በልቦናዬ የማብሰለስለውን ጥያቄ ነው ያነሳህልኝ፡፡ ተስፋዬ ገብረአብን በማመስገን ፈንታ ለምን እንደምንወርድበት ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እንደኔ እንደኔ ደራሲው ቤተክርስቲያናችንን የሚጠቅም ስራን ሰርቷል - እንድንጠይቅ አነሳስቶናል፡፡ አብዘኞቹ አስተያየት ሰጭዎች ስድብን ነው ያስቀደሙት፡፡ ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ ለማረጋገጥ የሞከረ እንኳ ያለ አይመስልም፡፡ ተስፋዬ ገና ከኢለመንተሪ ጀምረን የቅዱሱን አባት ታሪክ ከፖለቲካ እንደተዛመደ ተደርጎ ስንማረው የመጣነውን ት/ት ስህተት ሊሆን የሚችልበትን መንደግ ጠቁሞናል፤ ስለሆነም ገለታ ይገባዋል፡፡
  ከዚህ በተጨማሪ ዮናስ ዘካርያስ እንዳነሳቸው ያሉ በየገድላቱና ተአምራቱ የምናገኛቸው ስህተቶች ምንም እንኳን የፃድቁን ወይም የሰማእቱን ክብር የማይቀንሱ ቢሆንም ለትችት በር ከፋች መሆናቸው አይቀርም፡፡ ማስተዋል ያለብን ገድላትም ሆነ ተአምራት በሰው የተፃፉ ናቸው፤ ስለሆነም ስህተት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ የቅዱሳን የተጋድሎ ስራም ከተፃፈው በላይ ድንቅ ነው፤ ቋንቋ ሊገልፀው አይችልም፡፡
  በመጨረሻም እንደ ትእቢት ካልተቆጠረብኝ ቤተክርስቲያናችን የምታሳትማቸውን ቅዱሳት መፃህፍት በተለይም እንደ ገድላት ያሉ መልሳ በጥንቃቄ ብትመለከታቸው ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 77. Dear Dn Daniel,
  Egziabher yeagelglot zemenihin yibarkilih yarzimilih. Betam dink mels new. Enameseginalen.
  Tesfaye has a clear mission to distort history and destroy Ethiopia

  ReplyDelete
 78. "ጨዋ" ደፋር ነው!!!

  ReplyDelete
 79. ወይ አንቺ አገር፤ ወይ አንቺ ሃይማኖት የግር እሳትሽ መብዛቱ። ዳኒ ያንተ ብዕር ሃገሩንና ሃይማኖቱን ሊጠብቅ ከዘመተና ድል ካደረገ ስልጡን ብርጌድ ጦር ጋር ቢስተካከል እንዲያዉም ቢበልጥ ነው። እግዚአብሄር ጥበብንና ያገልግሎት ዘመንህን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 80. ተሰድደው በየሀገሩ ከተበተኑት ጋር አብረን ቋንቋና ድንበር ሳያግደን አገልግለናል፡፡ አሥመራ ከተማ ከሚገኙት ታላላቅ አድባራት አንዱም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በምንም መልኩ አንዲት ኤርትራዊት እናት ተስፋዬ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ላይ የተሳለቀውን ‹መዝሙር› አትዘምርም

  ReplyDelete
 81. tesfaye gazetagna nawu enji muhur ayidelm.ehaninim yetsafawo ka sawu tara hamet/nufake nawu.lamin bibbal gazetagna yesamahun bicha akanabro mawurat nawu sirawu.mirimirr makahed ka akimu balayi nawu.gazetagna yeminagarawo nager ri'isu bicha nawu ewunat,lelawu propoganda nawu,DANIEL EGIZABHERI yibarkih!!!

  ReplyDelete
 82. ተስፋየ ገብረ አብ was born in Eritrea and brought and raised in Debrezeyt .
  He was 11 years old when he come to Debrezeit. I knew him since he came to debrezeit but, He lie even his born place for his political motive.

  He write fiction in intersting ways ,but he is liar...wushetu beza!

  ReplyDelete
  Replies
  1. This is absolutely true I am borned and raised in Debrezeit /Bishoftu/ I am raised Near tesfayes Village. I learned with him I know him well , He use little true thing , and try to attract attentions of those who doesnot know him Well. One thing that surpised me to much is why he is heating this poor nation ethiopia???

   Delete
  2. Di Dan
   I would like to take this oportunity to thank you for your excellent teaching for this false writer.
   I read tesfayes's new book when i got the soft copy. Many things surprised me. Becuse I know tesfaye well becsuse I am his village meet you know what he did he just mention a few true things and try to use his wexcellent letrature ablity and try to convince others hwo does not know the fact well. by the way please Diaqon Daniel Pray for him. I think he is taken by evil. He write which is not important for him and for others.

   Delete
 83. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ እጅግ በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው።
  በሁለት ነገሮች ላይ ግን ያለኝ አስተያየት ትንሽ የተለየ ነው። የመጀመሪያው፦
  "በአጻጻፍ ችሎታው የምደሰተውን ያህል" ያልከው እንደገረመኝ አልደብቅህም። አንተ የሥነጽሑፍ ምሩቅ ትመስለኛለህ። ለመሆኑ የተስፋዬን ጽሑፎች የትኛው የሥነጽሑፍ ክፍል ውስጥ ትመድባቸዋለህ? እስቲ ምድቡን ንገረን። ለመሆኑ ፕሮፖጋንዳ ድርሰት ነውን? ለዚያውም በአንድ አገር ሰዎች ሁለንተና ላይ ያነጣጠረ ርካሽ ፕሮፖጋንዳ ድርሰት ይሆናልን? የርሱ ጽሑፍ በሰለጠነው ዓለም ‘Hate Literature’ (‘ጥላቻን የሚያስፋፉ ጽሑፎች’) ውስጥ የሚመደብና በሕግም የሚያስጠይቅ ነው።
  እርሱ እያቀረበልን ያለው ግማሽ እውነት፣ ግማሽ ልብወለድ (ታሪካዊ ልብወለድ) የሆነ የፈጠራ ሥራ ነው በሚል ነው። ለመሆኑ አንድ የፈጠራ ሥራ የሚሠራ ደራሲ በጠቅላላ በአምስቱ የስሜት ኅዋሳት የተረዳውን እንደወረደ ምንም ሳይቀንስና ሳይጨምር በጥሩ ቋንቋ ለአንባቢ የሚያቀርብ ነው ከተባለ የርሱ ድርሰቶች አንዳቸው እንኳን ይህን የሚያሟሉ ናቸውን? ሌላ ሌላውን ትተህ እርሱ ቂም የያዘባቸውን ሰዎች ሳይቀር (ዶ/ር ነጋሶና ጀነራል ባጫ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ) በመጽሐፉ አንድ አንድ ሙሉ ምዕራፍ እያደረገ የጻፈ ሰው እኮ ነው። ልብ አድርግ ይህ የሕይወት ታሪካቸውን የሚመለከት አይደለም። "እኔን እንዲህ ብለው አሉኝ....እነርሱ ደግሞ እንዲህ ናቸው" እያለ ተራ የቡና ላይ ሐሜት ነው ድርሰት ብሎ ያቀረበልን። ይህን ለምሳሌ አነሳሁት እንጂ ጠቅላላ የጻፋቸውን መጻሕፍት አንብበሃቸው ሊሆን ከቻለ ጎሳን ከጎሳ ለማጋጨት ይሆናሉ፣ አለቆቸንና ገንዘብ የሚከፍሉኝን ሰዎች ያስደስታሉ ያላቸውንና በግሉ ደግሞ ቂም የያዘባቸውን ሰዎች ያስጠሉልኛል ብሎ ያሰባቸውን ከመወትወት የተለየ ሌላ ነገር አታገኝባቸውም።
  ኢትዮጵያ በሚኖርበት ጊዜ እንደማንኛውም ቅጥር ጻሓፊ (Hack Writer - who is paid to write low-quality, rushed articles or books, often with a short deadline) ከራሱ ባልሆነና በተሰጠው ርዕስ ላይ ሲጽፍ የቆየ፣ ከአገር ከወጣ በኋላም አለቆቹን ቀይሮ የገንዘብ ምንጩ እንዳይደርቅ “ኢትዮጵያን አሳልፎ መስጠት” እነርሱን ያስደስታል ብሎ በማመን የገመተውን ሁሉ የሚለቀልቅ፤ ከማንም ይልቅ ኤርትራውያንን፣ መንግሥታቸውንና የኦሮሞን ሕዝብ “ይህን ብጽፍላቸው ያምናሉ” ብሎ እንደቂል የሚቆጥር፤ በግሉ ደግሞ በግለሰቦች ላይ ካለው ቂም የተነሳ በጽሑፉ ይህንኑ ቂሙን ለመወጣት ጥረት ከማድረግ በስተቀር ተስፋዬ ገብረአብ የፈጠራ ግፊት ኖሮበት ወይም ለማስተላለፍ የሚፈልገው የጠራና ገንቢ የሆነ ዓላማ ኖሮት ለዚያ ለሚያምንበት ነገር የሚጽፍ ሰው አይመስለኝም። ይህ ደግሞ በበለጠ ወደፊት እየጠራ ይመጣል።
  (ወረድ ብሎ ይቀጥላል)

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስተያዬት ሰጭ ሆይ ካንተ ጋር የማልስማማበት፡- የጠላነውን ሠው ሁሉ ምኑንም ማዬት አያምረኝም የሆነብህ ይመስለኛል፡፡ ከዳንኤል ጋር የምጋራው ነገር አለኝ፡፡ አሳቡን ወደ ጽሁፍ የመግለጽ ብቃት አለው (“ይመስለኛል” የሚል ቃል የምትጠላ ይመስለኛል እንጂ) ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ አይካድም፡፡ አዎ ይችላል፡፡
   ካንተ ጋር የመስማማበት ደግሞ፤ ጊዜውን ለመጻፍ መስዋዕት ካደረገበት አንጻርና እርሱ እራሱ በመሰከረው መሰረት በየመንግስታቱ እየዞረ በመጻፌ በደሉኝ - ሊገድሉኝ ነው - ድረሱልኝ ማለቱ ካልቀረ ከዚህ ጋር የሚጣጣም የአስተሳሰብ ብስለት አላገኝሁበትም፡፡ ጮርቃ ነው፡፡ ከዚህ ከዚህስ ባይጽፍ ይመረጣል! እውነቴን ነው፡፡

   Delete
 84. ሌላው ካንተ አስተያየት ጋር የማልስማማበት ደግሞ “…በአንዳንድ ጉዳዮችም ሆን ብሎም ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ” በማለት የገለጽከው ነው።
  "የስደተኛው ማስታወሻ" የተባለውን ቡትቶ ሁሉንም አንብበኸው ከሆነ ከምዕራፍ ምዕራፍ አንድ ነገር ላይ ያነጣጠረ ነው - ኢትዮጵያውያን አለን የምንላቸውን እሴቶችና በየመስኩ ያሉንን ዋኖቻችንን ማንንም ከማንም ሳይለይ ማጣጣል። ተስፋዬ እንደጠላቶቻችን ሁሉ አማራውን ከኢትዮጵያዊነት ጋር አቆራኝቶ የሚያይ ከመሆኑ የተነሳ አማራውን በተዘዋዋሪ “systemic violence” በሚል ሸፍኖ ቢያንቋሽሽም ከዚህ ሁሉ በላይ ግን በግልጽና በእያንዳንዱ ምዕራፍ ሳያሰልስ በ”ስደተኛው ማስታወሻ” ዒላማ ያደረገው በኢትዮጵያ ላይ መሆኑን ሁሉም ልብ ሊለው ይገባል። አንተ ያነሳኸው የአቡነ ተክለሀይማኖት ጉዳይ አንዱ ነው። ምክንያቱም አቡነ ተክለሀይማኖት ከኢትዮጵያዊ ቅዱሳን አንዱና ምናልባትም ዋነኛው ናቸውና። ልብ አድርግ ስለአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስም ሆነ ስለሌላ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ ቅዱስ አልጻፈም። ከዚያ ምዕራፍ ቀድሞ “ጫልቱ እንደ ሄለን” የሚለውን ምዕራፍ ብታነበው ብዙ ሰው እንደተረዳው በአማራ ሕዝብ ላይ የተነጣጠረ ከመሆኑ በበለጠ “የራሳቸው የሆነው የእሬቻና የጨሌ እምነት ቀርቶ የጨቋኞች እምነት ስለተጫነባቸው ኦሮሞዎች” በመወትወት የኢትዮጵያውያንን ጎሳ ከሀይማኖት ጋራ አጣምሮ በመከፋፈል በቀጥታ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ላይ የሚያነጣጥር ሆኖ ነው የምታገኘው። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ለኢትዮጵያ እስከምን ድረስ እንደሆነ ተስፋዬ እንደጠላቶቻችን አሳምሮ ያውቃል። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት የ”አባቱ አገር” ትልቁ እምነት እንደሆነ ተስፋዬ አጥቶት አይደለም። ነገር ግን በርሱ አባት አገር ኦሮሞዎች የሉም። የኤርትራ ሕዝብ ደግሞ አማርኛ አያነብም። ተተርጉሞለት ሕዝቡ ማንበብ ቢችል እንኳን ተስፋዬ ስለማያውቀው የኤርትራ ሕዝብ አይጨነቅም። ዋናው ነገር መተዳደሪያውን የሚቆርጡለት የአባቱን አገር ገዢዎች እንዳይቀየሙ መጠንቀቁ ነው። ማርክሲስቶቹ የአባቱ አገር ገዢዎች ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መተቸቱ እንደማያስቆጣቸው ተስፋዬ ይተማመናል።
  ተስፋዬ ገብረአብ በውጭው ዓለም የንግሥተ ሳባ ታሪክ ምን ያህል ከኢትዮጵያ ጋራ የተቆራኘና ሥር የሰደደ እንደሆነ ይልቁንም ከአገር ከወጣ በኋላ በበለጠ ተገንዝቧል። “የሳባ ንግሥት” በሚለው ምዕራፍ ሥር በንግሥተ ሳባ ላይ ምን እንደጻፈ ታገኘዋለህ። ስለ አፄ ቴዎድሮስ አሟሟት የጻፈውን በገጽ 390 ላይ ስለ “28ቱ ውሽሞቻቸው” በገጽ 302 የጻፈውን ተመልከተው። “ፋሲለደስ አብራው ያደረችውን ገድሎ ይቀብር” እንደነበረ በገጽ 302፣ ስለ በላይ ዘለቀ በገጽ 59 የጻፈውን ተመልከተው። “ናደውና ታሪኩ” በሚለው ሌላው ምዕራፍ ደግሞ ጀነራል ታሪኩ ላይኔ በጨቦና ጉራጌ መወለዱን በመንገር ይጀምርና (ገጽ 219)፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም ታሪኩ ላይኔን በጉራጌነቱ ምክንያት በለስላሳ መጠጥ ችርቻሮ በሙስና ከሰሰው በማለት ቀጥሎ (ገጽ 220) የኤርትራ መንግሥት አባላትን የበለጠ ለማስደሰት የአፍአበት የጦርነት ገድል በውጭ ደራሲያን የተመዘገበ የሻእብያ ጦር ጀግንነትና ኃያልነት የተመሰከረበት “በአፍሪካ ትልቁ ጦርነት” እንደሆነ ይነግርህና (ገጽ 222) ታሪኩ ላይኔ የተገደለበትን ምክንያት እኔ ደርሼበታለሁ በሚል ሰበብ የታሪኩ ሚስት በሐረር ከተማ መሸታ ቤት እንደነበራት ይነግርሃል (ገጽ 224)። ለእንዲህ ዓይነት መሠሪነት ከሆነ ተስፋዬ ገብረአብ የሰቀለውን አውርዶ በአንድ ወንጭፍ ሁለትና ሦስት ወፍ መምታቱን ይችልበታል። (to be continued below)

  ReplyDelete
 85. “የመሪዎች አሟሟት” በሚለው ምዕራፍ የምታገኘው ሰበብና መንገድ እየፈለገ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ማብጠልጠል ነው። በገጽ 301 - 302 “ጤፍ በአፈታሪክ አክሱምን ይገዛ የነበረ ዘንዶ ሲገደል የዘንዶው እዥ ከፈሰሰበት መሬት ላይ እንደበቀለ” ይነግርሃል። “ኦሮማይ በዓሉ”ን አንብብና ምን ለማስተላለፍ እንደፈለገ ትረዳዋለህ። ዝርዝሩ ረጅም ነው።
  ስለዚህ ነው “ሊያናጋቸው የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ እሴቶች ያሉ ስለሚመስለኝ” በማለት በጻፍከው የማልስማማው። መምሰል ሳይሆን የተስፋዬ ሀሳብ ይህ መሆኑን በግልጽ እንድታውቀው ያስፈልጋል። ምክንያቱም ጊዜ ስታገኝ በእያንዳንዳቸው ርዕሶች ሥር ያጣመመውን እንድታቃና ይጠበቅብሀልና። እውን ተስፋዬ “እሬቻና ጨሌ”ን ከኦሮሞ ነገድ ጋር በማቆራኘት የጻፈው ትክክል ነው? እውን የክርስትና እምነት በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ በሌሎች ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን የተጫነባቸው ነው? ለሌሎችም ተስፋዬ ላጣመማቸው ሁሉ እግር በእግር መልስ ያስፈልጋቸዋል። ምንም እንኳን የተስፋዬ ጽሑፍ ብዙ ሕዝብ ያሳስታል የሚል እምነት ባይኖረኝም “አንድ ጅል የተከለውን ሃምሳ ሊቅ አይነቅለውም” እንዲሉ አንዳንድ የዋሀን በሆኑ ሰዎች እጅ መጽሐፉ ገብቶ እንዳያሰናክላቸውና ይልቁንም ጉዳዩን ስለማያውቀው ስለወደፊቱ ትውልድ ስንል ተስፋዬ ከቡርቃ ዝምታ ጀምሮ እስከዛሬ ላጣመመው መልስ የሚሆን ደህና ዝግጅት እንደሚያስፈልገው ይሰማኛል። እርሱ ይህን መጻፉ ለእኛ ትልቅ እድል ነው የከፈተልን። ስለአቡነ ተክለሀይማኖት ይህ ሁሉ የተጻፈ መረጃ መኖሩን በአንተ ጽሑፍ ያወቅነው በዚህ ምክንያት ነው። ያ አላዋቂ መናፍቅ የጻፈውን ባይጽፍ ኖሮ ለሀይማኖት ምሰሶ የሆነውን የአድማሱ ጀምበሬን መጽሐፍ ባላገኘን ነበር። የአንተ ሥራ ተስፋዬ በአቡነ ተክለሀይማኖት ላይ ለጻፈው አንድ ምዕራፍ በቂ መልስ መሆኑ አያጠያይቅም። እንደዚሁ ሁሉ በሌሎች ምዕራፎች ለጻፋቸው ተረታ ተረቶች መልስ ያስፈልጋቸዋል ለማለት ነው።

  ይህ ሁሉ ሆኖ በግሌ ተስፋዬ ገብረአብ እርሱ በጻፈው ጽሑፍ መነሻ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ውለታ አድርጓል ብዬ አምናለሁ። የመጀመሪያው “የስደተኛው ማስታወሻ” ውስጡ ከተሞላው ኢትዮጵያን፣ ምርጥ ልጆቿንና እሴቶቿን ሁሉ የማኮሰስ ይዘት ጋራ ለመታተም ታስቦ የነበረው በኤርትራ መንግሥት በኩል መሆኑን ስንሰማ ወንድሞቻችን የኤርትራ መንግሥት አባላት አሁንም በዚሁ ሥነልቦና ውስጥ መሆናቸውን በሌላ አቅጣጫ የሚያመለክት መሆኑ ነው። የኤርትራ ወገኖቻችን አሁንም እዚሁ ላይ መሆናቸው ቢያሳዝነንም ግንኙነታችንን በዚሁ መንገድ እንድናስተካክል በጣም ይረዳናል። ነገሩ የተነጣጠረው አሁን ባሉት የኢትዮጵያ ገዢዎች ላይ በሆነ ባልገረመ ነበር። እንደዚያ ሳይሆን በኢትዮጵያ ላይ መሆኑን ስታስብ ደግሞ የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያውያንን ቅስም በመስበር ውስጥ እያሰላ ያለው ጊዜያዊም ሆነ ዘለቄታዊ ጥቅም ምንድን ነው? ብለህ ሁሉን እንድትገመግምና እንድትዘጋጅ ያደርግሀል። ይህ ከነርሱ ጋራ በትብብር እየሠሩ ያሉትንና ወደፊትም ለመሥራት እየተዘጋጁ ያሉትን የሚጠቅም ነው። ተስፋዬ በተዘዋዋሪ ይህን እንድናውቅ ውለታ ውሎልናል። ሁለተኛው ደግሞ ተስፋዬ የጻፈው ጽሑፍ መጠነኛ አቧራ ሲያስነሳ ይሰጡ ከነበሩት አስተያየቶች መካከል ጥቂት ከማይባሉት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ብዙ ትምህርት በመቅሰም ለመጭው ጊዜ የሚያደርገውን ትግልና የትግል አቅጣጫ ያስተካክልበታል፣ መዘጋጀት ባለበት እንደአንቂ ደወል ወስዶ ይዘጋጅበታል፣ በተስፋዬ ቅስቀሳ ተወስደው በወገኖቻቸው ላይ ተጨማሪ ጥቃት እየደገሱ ያሉ ወገኖች ምናልባት ቢኖሩ ጥቂትም ቢሆኑ ያንንም ቢሆን ችላ ሳይሉ ኢትዮጵያውያን በጋራ ለመቋቋም የሚያስችላቸውን መንገድ ቀድመው እንዲያበጁ ይረዳቸዋል የሚል እምነት አለኝ። ሰላምና ደህንነት ሳይዘጋጁበት እንዲሁ በነጻና በመልካም ምኞት አይገኝምና። ለዚህ ነው እንዲህ ዓይነቱ መረጃ በቀላሉ የሚገኝ ስላልሆነ ተስፋዬ ከጎዳው የጠቀመው ይበልጣል ለማለት የሚያስደፍረው።
  እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yoftahe; you get the point , thank you.

   Delete
 86. ተስፉየ ገብረ አብ አስመሳይ ደራሲ ዳኒ ልዩ የቤተክርስትያን ቀኝ እጅ ሙሉ ኢትዮጵአዌ ጌታ ይጠብቅህ ለሱ መልስ ለኛ እውቀትን አካፈልከን ዮናስ ከሮማ

  ReplyDelete
 87. ተስፋየ በሚያምር የአፃፃፍ ስልቱ የብዙዎቻችንን ቀልብ በቀላሉ መግዛት ቻለ እንጂ የፅሁፎቹ ጭብጥ የግለሰቦችን ስብዕና ከማጉደፍ፥ የአንዲት አግርን ፖለቲካና ታሪክ በአመድ ከመለወስ አይዘልም።

  "ማንኛውም ክርክር ሲቀርብ ለክርክሩ ብቁ የሆነ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡ ልቦለዱንም፣ ቀልዱንም ለታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ቧልት እንጂ ቁም ነገር አይሆንም፡፡"

  ReplyDelete
 88. እንዲህ ጥርጣሬን አርቀው እውነትን የሚገልጡና እምነትን የሚያስጨብጡ ወንድሞችን እግዚአብሔር ባያዘጋጅልን ኖሮ ስንቱ ስሑት እየሳተ አስቶ ይጨርሰን ነበር? ሁሉን ያዘጋጀ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ እጅግ የማከብርህ ውድ ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት እግዚአብሔር የሰጠህን መክሊት እንዲህ ከእጥፍም በላይ እያተረፍክበት እስከ መጨረሻው ሕቅታ ለተፈጠርክለት ዓላማ ጸንተህ እንድትኖር እግዚአብሔር በአባትነቱ ይጠብቅህ እመብርሃን ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ በምትሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ትርዳህ፤ ሥራዎችህ ከአገር አልፈው ለዓለምም ይተርፋሉና በርታ፡፡

  "እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ› (እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?"
  ጥሩ ገልጸኸዋል፡፡ ተስፋዬ ገብረአብ እውነትም እጅግ ጨዋ ነው፡፡

  ReplyDelete
 89. Daniel..May God Bless You ....Tesfaye May God help you to understand....I Love Teklyaaa

  ReplyDelete
 90. ታውቃለህ ዳኒ በማታዉቀዉ ነገር ላይ ማዉራት ለካ ያስገምታል ልጁ የመጻፍ ችሎታ አለዉ ግን አሁን አበላሸው ሌላ ሌላዉን እንደፈለገ ይበል እዉነትም ይሁን ዉሸት ልክም ይሁን ስህተት የሚያስበዉን ይጻፍ አባቶቻችን ጋ ግን ወራጅ አለ እግዚአብሄር እድሜ እናጤና ይስጥህ

  ReplyDelete
 91. ውብሸት ተክሌOctober 31, 2013 at 11:42 AM

  "ጨዋ ደፋር ነው" ሲሉ አባቶች ምን ማለታቸው ነው። ጨዋ ማለት ያልተማረ፡ ከአባቶች እግር ስር ፊደል ያልቆጠረ፡ መጽሐፍ ያላገላበጠ፡ ከሊቃውንቱ ጉባዬ ያልዋለ መሃይም እንዲያው በጆሮ ጠገብ የሰማውን ብቻ አምኖ የሚቀበል ተቀብሎም የሚከራከር ማለት ነው የደስታ ተክለ ወልድ አዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ 601 ተመልከት። እውነት እውነት እላችኃለው እግዚያብሔር አምላክ ሙሴን በፈርኦን ላይ አምላክ አድርጎ እንደሾመው አስራሁለቱን ሐዋርያት በአስራሁለቱ ነገደ አስራኤል ላይ ፈራጅ አድርጎ እንደሾመ ዲያቆን ዳንኤል ክብረትንም በተስፋዬ ገብረአብ ላይ አምላክ አድርጎ ሾሞታል። አፈራርሶ እንዲሰራው ሁሉ ስልጣን ሰጥቶታል። በጣም የሚገርም ነው ሁለቱም በዕድሜ እኩያሞች ናቸው የበቀሉትም ከዚህችው ኢትዮጵያ ነው የእውቀት የአስተሳሰብ የአገር ፍቅር የወገን ፍቅር የወገን ክብር ደረጃቸው ግን ከአዲስ አበባ ሲኤምሲ አስከ ሆላድ ቴር አፕል የስደተኞች ካምፕ ሩቅ ነው። የዲማ ጊዮርጊሱ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን ሞተ የሚል ማነው የለም የለም አልሞተም ይኸው በህይወት አለ።

  ReplyDelete
 92. የ፳፩ኛው ዘመን የቤተክርስቲያናችን ጠበቃ ብልህ ያነሰብህ መሰለኝ

  ReplyDelete
 93. የ፳፩ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቤተክርስቲያናችን ጠበቃ ብልህ ያነሰብህ መሰለኝ

  ReplyDelete
 94. ዳኒ አከበርኩክ፡፡ ድሮም አከብርሃለሁ፡፡ አሁን ደሞ በሰብኝ፡፡ እግዚአብሔር አንተንም ቤተሰብህንም ደግሞ ደግሞ ያክብርክ፡፡

  ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 95. ተክለ ሃይማኖት የዓለም ብርሃን ናቸው
  ይኼው ለዘላለም ያበራል ገድላቸው
  ነው የሚለው፡፡

  ReplyDelete
 96. ውድ ዳኒ፣ እንዴት እንደተደሰትኩብህ ምን ብዬ ልንገርህ? ብስለት የተሞላበት አቀራረብ፣ የመረጃ አጠቃቀም፣ ጣርያ የነካ ኢትዮጵያዊነት………. እግዚአብሔር አምላክ ረጅም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥልን,ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!

  ReplyDelete
 97. ለተስፋየ እኮ ያች የሃያ ስኩል አስተማሪው ልኩን ነግራዋለች እራሱ በጻፈው መጻፍ ላይ እንደገለጸው/የጋዜጠኛው ማስታወሻ/ እናም ጨዋ ደፋር ነው ኣትፍረዱበት

  ReplyDelete
 98. ለተስፋዬ እኮ የጋዜጠኛው ማስታወሻ በሚለው መጻፉ ላይ ራሱ እንደገለጸው ያች የሃያ ስኩል አስተማሪው ልኩን ነግራዋለች እናም ጨዋ ደፋር ነው የሚለው ብቂው ነው ለሁሉም ዳኒ ምስጋና ይግባህ፤

  ReplyDelete
 99. ግሩም ነው! እግዜር ይባርክህ!

  ReplyDelete
 100. We have father, we have brother, we have sister, we have mother, we have grand mother, we have grand father,we have teacher, we have preacher, we have writer, we have best Ethiopian. However I never see a person that he has all thing exept Dani. I know Dani very well he went many time USA, England, Australia, South Africa and so on. All countries asked him to stay their but he didn't acept their request because he live for us not for him or money. I don't want mention by name but as we all know that many spritual educated people live in USA because of money and freedom. But Dani live in Ethiopia because he is Dani. God bless you and your family our hero Dani.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Tnank you so much the Anonymous person for your comment. I agree with you and Amen God bless Dani and his family.

   Delete
 101. ቃለ ህይወት ያሰማልን ደ/ን ዳኒ
  ምሁራዊ መልስ ነው፡፡ ተስፋይ የፃፈውን ባለፈው ሳምንት ነበር ያነበብኩት፡፡ በርግጥ መልስ ካንተ ስጠብቀቅ ነበር!
  ተስፋዬ በጣም ካስገረመኝ ነገር እነ በውቀቱም ፅፈው ነበር የሚለው ነው፡፡ በዛኑ ወቅት አነተ ፅፈህ የነበረውንስ እንዴት አላየም? “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም አሉ”

  ReplyDelete
 102. ዲ/ን ዳንኤልና ሌሎች ደቀመዛሙርቶች ሁሉ የተጋነነ ነገር አትጻፉ የእርሳቸው እግር ለምን እንደቆረጠ ሌላ ታሪክ አለ?የእኛ ሀገር የቤ/ክ ታሪክ ጸሐፊዎች እኮ የሃይማኖት አባቶችን ታሪክ ያጋንናሉ ተው ተው ነገሮች ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ የአዲሱ ኪዳን ዘመን ይገምገም ይህ ሁሉ ወሸት የተባለው አንድ ቀን መዘክዘኩ አይቀርም በእስራኤልና በይሁዳ ምድር የተተከለውን የኮረብታ መስገጃ ታሪክ አስታውሱ አንድ ቀን《ኢዮስያ》የተነሳ ዕለት ጉድ ይፈላል ዲያቆንም ሚዛኑን ጠብቀህ ብትሄድ እስቲ ስለ 7 ቱ ተክለሃይማኖቶች ታሪክ አስነብበንና እንለያቸዋለን።
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኒቆዲሞስ፡- በሃሳብህ አልስማም፤፤ ምክንያቱም የተጋነነ ነገር አልተጻፈም፤፤ ስለ አቡነ ተ/ሃይማኖት ክብር ካወቅህ ማለቴ ነው፤፤ ሰው ሲሆኑ የመልኣክ ብቃትና ቅድስና ደረጃ ላይ መድረስ መንገዱን የሚያውቀው ብቻ ይናገር፤፤ ለማያምኑት የጻድቃን ክብር ምንም አይደለም፤፤ እነርሱ የማያውቁትን ይሳደባሉ፣ እኛ የምናውቀውን እናከብራለን፤፤ ይህ ተ/ሃይማኖት ምስጢራዊ ስም ነው፤፤ ያወጣለትም ክርስቶስ ነው፤፤ ትርጉሙም የሃይማኖት ተክል ማለት ነው ፣ የኦርቶዶክስ ተክል፤፤ ጉድና ጅራት ከወደሁዋላ ነው እንዲሉ የዛሬው ጉደኛ ዘመን እንደሚመጣ ጌታ ስለሚያውቅ ለዚህ ዘመን ትውልድ ይህ ስም እንደ ኢያሱ የምስክር ሐውልት ሆኖ እንዲያገለግል አድርጎ ጌታ ያወጣለት ነው፤፤ ይህ አባታችን መጠጊያችን፣ ጋሻችን ነው፤፤ከእርሱ በሁዋላ ሌሎች በርሱ ስም ሊጠሩ ይችላሉ፤፤ ይህ ኣባታችን ለኢትዮጵያችን ስጦታችንና የሃይማኖታችን ኩራት ሆኖ ይኖራል፤፤

   Delete
 103. ዳኒ አከበርኩክ፡፡ ድሮም አከብርሃለሁ፡፡ አሁን ደሞ በሰብኝ፡፡ እግዚአብሔር አንተንም ቤተሰብህንም ደግሞ ደግሞ ያክብርክ፡፡

  ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  ReplyDelete
 104. this is a disease for tesfaye and the likes they are full of hate for Ethiopia in general and Amhara and EOTC in particular read the new book by andargea mesfin "በሙት መንፈስ አገር ሲታምስ" for the detail

  ReplyDelete
 105. people are always trying to value him about his style and info his book.To me he is just collecting knowledge less wore from us and prepare it and feed back us. As a writes of Ethiopian , I have not yet seen any creativity and inspiration in his book ALWAYS. So please don't even talk about him, just neglect the dead fish since it dead!!

  ReplyDelete
 106. Thank you Dani! May God bless you with His endless wisdom!

  ReplyDelete
 107. ያው መፅሃፉን ለማንበብ ባልጓጓም፣ እንደተለመደው በአንዱ የኢትዮጵያውያኑ ድረ ገፅ ላይ በማግኘቴ አንብቤዋለሁ። ስለመፅሃፉ አስተያየት ለመስጠት ፍላጎት የለኘም። እንዲያ ባደርግ ለተስፋዬ ፅሁፍ ቁብ ሰጥቼ ያራገብኩለት ይመስለኛል። በጥላቻ የተመሉ፣ዘረኞች፣ጠባቦች እና ች ያልታደለች ምስኪን አገር ጠላቶች ለጀግናቸው ብዙ ሊጮሁለት ይችላሉ። መብታቸው ነው።
  ይልቅ ይህን ፅሁፍ ሳነብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ከሁለት ዓመታት በፊት በአንድ የስታር ባክስ ቡና መጠጫ ከአንድ በቀድሞው ዘመን የታወቁ ፀሃፊ ፣ጋዜጠኛና የመንግስት ባለስልጣን ጋር ቡና እየጠጣን ወግ እንጠርቃለን። ስለፖለቴካ፣ታረክ፣ስለመፅሃፍት•••••••በድንገት ጨዋታችን ወደ ተስፋዬ ገብረ እባብ ዞረና አንዳንድ ነገሮችን ስንጨዋወት ሰውዬው እንዲህ አሉኘ:_
  " ተስፈዬ ስለ ኢትዮጵያና ኤርትራ ታሪክ መፅሃፍ መፃፍ ይፈልጋል። የሚችል አይመስለኘም። በመጀመሪያ እንዲህ አይነት ፁሁፍ ለመፃፍ የሚያስችል የአካዳሜ እውቀት የለውም።ሁለተኛ ተስፋዬ ቃላትን ከመሰካካት ያለፈ ጮሌነት በቀር ስራው የሚያስፈልገውን ምርምር የማድረግ ችሎታም፣ ብቃትም የለውም።" አሉኘ። ዛሪም የሰውዬው ንግግር በጆሮዬ ያቃጭላል። ያንተ ፅሁፍ ደግሞ ይበልጥ ይህን ሃሳብ ኣጠናክሮልኛል። የሆነ ሆኖ ሊፅፈው ያሰበውን የታሪክ መፅሃፍ ለማንበብ አልጓጓም። ገና ከወዲሁ ምን ሊፅፍ እንዳሰበ ከወዲሁ አውቄዋለሁ።
  መልካም ንባብ ለወዳጆች! ዴያቆን ዳንኤልን ግን በእጅጉ እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 108. ዲ. ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥህ

  ReplyDelete
 109. እግዚአብሔር በአባትነቱ ይጠብቅህ እመብርሃን ወላዲተ አምላክ በምልጃዋ በምትሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ትርዳህ

  ReplyDelete
 110. ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

  .

  ReplyDelete
  Replies
  1. You just realized that. Please going forward don't take anything face value and do your own research. Tesfaye has been lying about several individuals on his books and when confronted with evidence he has a tendency to disappear or ignore you.

   Delete
 111. ደስ የሚለወዉ ነገር ሁሉም ማለት ይቻላል የእባቡን አላማ ተረድቶታል በፖለቲካዉ ከስሮ ተባረረ፣ በስነ ፅሁፍም መካን መሆኑ ተገልጠል፤፤ እኛ እንቶፈንቶ ስብስቡላይ የጠቀሳቸዉን የአባት አገሩን መንደሬ ሰዎች ና ስሞች የትእናዉቅለታለን፤፤እሱ የሰዉን የሚያጣጥለዉ፤በሉ በርቱ እራሱን አሳዉቁት ፣ ካልነገሩት አይገባዉም ለነገሩ የሚገባዉ ዓየይነት ሰዉ ቢሆን እንደዚህ ዓይነት ኪሳራ ዉስጥ ቀድሞዉንም አይወድቅም ነበር፤፤ እግዚአብሄር ይባርካችሁ፤፤

  ReplyDelete
 112. Thanks Deacon Daniel.

  Tesfaye has two targets

  1. The common target: amhara. the defenseless amhara peoples have been the target of the ruling party and other groups and persons like tesfaye.This is the weakness of amhara elites. they talk,. talk...without helping and organizing their people.

  2. The Ethiopian Orthodox Church. The church is the new taget.


  ReplyDelete
 113. thanks Daniel, u did great. nuriln

  ReplyDelete
 114. ፀጋሁ ዘእግዚአብሔር ይህደር በላእሌከ፡ አሜን!


  የክብረት ልጅ ክቡር ነው! ሁል ጊዜ በአንተ በእናት ቤተክርስቲያን ልጅ እረካለሁ! በሃይማኖትም ሆነ በበሀገር ላይ ያለህ አእምሮ ህሊናን ያረካልና! ደግሜ እላለሁ ህሊናን ያረካል

  ብዞች በምዕራባውያን አስተሳሰብ ውስጥ ስለሚያድጉ ክቡር ለሆነው ማንነታቸው አያውቁም፤ ማወቅም አይፈልጉም በመሆኑም ለማንነታቸው የወረደ ግምት አላቸው ተስፋይም የዛ ችግር ተጠቂ ይመስለኛል፡፡ብዞች በምዕራባውያን አስተሳሰብ ውስጥ ስለሚያድጉ ክቡር ለሆነው ማንነታቸው አያውቁም፤ ማወቅም አይፈልጉም በመሆኑም ለማንነታቸው የወረደ ግምት አላቸው ተስፋይም የዛ ችግር ተጠቂ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. thank you Anonymous you explained them exactly.

   Delete
 115. ደስ የሚለዉ ሁሉም የእባቡን ተንኮል ተረድቶታል እኛ አሱ አባት አገር ኮተት ላይ የጠቀሳቸዉን መንደሬ ሰዎች ና ስሞች የት እናዉቅለት ና ነዉ እሱ የእኛን የሚያጣጥለዉ፤፤በሉ እራሱን አሳዉቁት ካልነገሩት አይገባዉም፤ለነገሩ የሚገባዉ ሰዉ ቢሆን ቀድሞዉንም እንደዚህ ዓይነት ኪሳራ ዉስጥ አይድቅም ነበር፤፤

  ReplyDelete
 116. ሲጀመር ተስፋዬ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንድትጠፋ ሲኳትን ውሎ ሲኳትን የሚያድር ትንሿ ሻቢያ አይደል ስንዴ

  ReplyDelete
 117. i never believed any of the religious and political books published by diaspora. All of them are sick. their life is sick so they always try to destroy the history and politics of their country. ስንት የሚጻፍ ሞልቶ. ያልታደለች ሀገር

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't agree with you the Anonymous person because many Ethiopian live out side the county to fight their people. I know some of them they use their freedom to distroy our country history but most of them they fight to bring freedom for Ethiopian people. God bless Ethiopia.

   Delete
  2. So, where is your disagreement?

   Delete
 118. Hello Dani, Thank you so much for your time. We get knowledge with out paying anything. I know God will pay you with unlimit money. I would like to ask you one more thing to add on your Blog. "Thmeret Hymanot" If you write some thing about The Father, The Son and The Holisprit, Mary, apostel and so on it will be more helpful for us to know about our relagion. God Bless You.

  ReplyDelete
 119. አሜን ! የድንግል ልጅ የገልግሎት ዘመንሕን ያስረዝምልሕ።

  ReplyDelete
 120. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?
  ዳኒዬ ስለ ተስፋዬ ማንነት እኮ የጋዜጠኛው የደራሲው እያለ ሲዘላብድ ቆይቶ ከቡርቃው በስተጀርባ ላይ እውነተኛ ማንነቱን በግልፅ አሳይቶናል፡፡
  ግልፅ አሳይቶናል፤፤

  ReplyDelete
 121. ዲ/ን ዳንኤል፡ ከዚህ በፊት ለበዕውቀቱ ስዩም የሰጠኸው ምላሽ እጅግ በጣም አስደሳች ነበር፡፡ አሁንም ለተስፋዬ ገ/አብ የጀመርከው ምላሽ በጣም የሚገርም፣ በበቂ ማስረጃና ጥናት ላይ የተደገፈ ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንተም በቤተክርስቲያን ላይ ምን ያህል ጥናት እንዳደረግህ ከማሳየቱም በላይ የጋን ውስጥ መብራት አለመሆንህ ደግሞ ብዙዎችን ከክህደት አውሎ ነፋስ የሚታደግ ነው፡፡ ግን ስትጽፍ ስሜታዊ ሆነህ ኃይለ-ቃል አትጠቀም - ለዘብ አድርገው፡፡
  "አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ የተወቀሱት ለእምነት ክርክር የማይጠቀስ የተአምር መጽሐፍ በመጥቀሳቸው ነው፡፡" የሚለው አባባል አልተመቸኝም፤ ለመናፍቅ በር የሚከፍት ነው፡፡
  በተረፈ ቀጥልበት!!! የተክልዬ ጸሎትና ረድኤት አይለይህ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርሳቸውስ መናፍቅ መሆናቸው ጠፍቶህ ነው?

   Delete
 122. Wow bemasereja yetedegef tsehufe God of st. Tekelhsyemanot be with u

  ReplyDelete
 123. yetesfaye telatoch 3 nachewe enesume...1.Ethiopia..2.Orthodox.3.Amara...yasazenale beewenetu kehulume gen yetetekem sewe neber...yenate tute nekash hono ker...

  ReplyDelete
 124. God bless you, Deacon Daniel! Continue to educate others and protect our history. Tesfaye is on a TPLF/Shabia mission to destroy anything Ethiopian. He is one of the most evil people that I have ever heard of... He will not succeed tarnishing our history and heritage. God is with us, of course for the sake of His name and the intercession of His saints.

  ReplyDelete
 125. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥህ።!

  የድንግል ልጅ የገልግሎት ዘመንሕን ያስረዝምልሕ።!!

  ተስፋዬ ጨዋና እባብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 126. ተስፋዬ፣ሥልጣን ላይ ያለው ፓርቲና መሰሎቹ፣ በዋናነት ኢትዮጵያዊነትን እሴትና ቤተ ክርስቲያኗን ማዳከም፣መሳድብ፣ ማውደም፣ ማሳደድ ዋና ተግባራቸው ነው። ለዚህ መላው የኦርቶዶክስ ልጆች በአንድነት መላ ሊፈልጉለት ይገባል።


  ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የ አማራን ሕዝብ ማዋረድ፣ ማንቋሸሽ፣ መሳደብ፣ መግደል፣ ማፈናቀል፣ ትውልዱን ማምክን፣ የእየለቱ ተግባራቸው ነው። ታዲያ በነሱ ፍርድ የለም። የአማራ ልሂቃን፣ የተማረው ክፍል፣ ፊደል የቆጠረው ሁሉ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው በደል ዋና ተጠያቂ ነው። በ አማራ ሕዝብ ላይ ይህን ያህል በደል እየተፈጸመ ዝም ብሎ ማየት እጅግም ያሳፍራል። የቁም ሞት ነው። የአማራ ሕዝብ የሚያደራጀው፣ የሚያታግለው፣ እዉነተኛ መሪና ድርጅት ያስፈልገዋል። ታዲያ ምን ዋጋ አለው ይህ በ ቁሙ የሞተ ትውልድ፣ ወገኑ እያለቀ በደመ ነፍስ ዝም ብሎ ያያል። እጅግ አጥንት የሚሰብር ሃፍረት፣ ማቅ የሚያስለብስ ሃፍረት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እዚህም ላይ ወራጅ አለ።

   Delete
  2. ሌላ ወራጅ!

   Delete
  3. እዚጋ ወራጅ አለ፡፡ እንዴ ፍሬንድ ተቀየስ እንጂ፡፡ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ፡፡ አሉ እቴሜቴ፡፡

   Delete
  4. ተስፍሽን የሚያናደው ይሄ ፀባያችሁ ነው፤ እኔንም.... ሰልፍሾች ናችሁ
   መግፋት ትወዳላችሁ... ለማንኛውም ዳኒ የገባው መሆኑን መግለፅ እፈልጋለሁ፤ ሁሌም የሚመለከተውን ጉዳይ ብቻ ያነሳል፡፡

   Delete
 127. ዳንኤል፡- ጥሩ ብለሃል፡፡ በ ኦክቶበር 15/2013 እንደዚህ የምትል ደብዳቤ ልኬለት ነበር፡-
  ጸሐፊ ሆይ፡-
  የጻፍከውን አንብቤ አሁኑኑ አጠናቀቅሁ፡፡
  የግል ህይወትህንና ገጠመኝህን በመጻፍ ላይ ያነጣጠረ ለዛ ስለወረስክ፤ እንደዚህ ዓይነት ነገር ስለምወድ ሳልሰለች በአንድ ትንፋሽ አንበለበልኩት፡፡
  ታዝቤሃለሁም፡፡ አላዋቂነት አግኝቸብሃለሁና፡፡ ደፋር ስለሆንክ፡፡ ድፍረትህም የማታውቀውንና በቂ መረጃ በሌለህ ነገር ላይ ሳይቀር ለትዝብት ተጋላጭ የሆኑ ነገሮችን ስለምትደፍር፡፡ ምን አልባት ለመነጋገሪያነት እንዲበቁ አልመህ ይሆን?
  መጻፍ ግን ትችላለህ፡፡
  አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብዙ ገጽ ለመሙላት አትፈልግ፡፡ ፍሬ ነገርህ ካለቀበት ይለቅ፡፡ ችግር የለም፡፡ ያለበሰለ ምግብ ያገርህን ሰው እንደሚያቅለሸልሸው አትዘንጋ፡፡ ጎመን ሳይቀር ንጥረ ነገሩ እስኪጠፋ ድረስ በእሳት አብስለው እንደሚበሉ አትርሳ፡፡ ያልበሰለ አሳብም ያንባቢዎችህን የአሳብ ማጠራቀሚያ - ሆድ ጭንቅላት ያዞራል፡፡ አብስል፡፡ ምረጥ፡፡ ጡጥ ሁሉ ስፍራ አላት፡፡
  መጻፍህን ግን አትተው፡፡
  አላስተምርህም፡፡ ግን መረጃ አበዛልሃለሁ፡፡
  መልሰህ ከጻፍክልኝ ጓደኛ የምንሆንበት መንገድ ብዙ ነው፡፡
  በርታ!

  ከጣና ዳር፡፡ ባሕር ዳር፡፡

  ReplyDelete
 128. yeteklye bereket yiderbh indihu tebeqa yiqumulih!!

  ReplyDelete
 129. ethiopiane wongel endaysefafa ke alem hulu wedehwala endetkere yaderegachehuate endante aynete kesena yekahnate aleka negne bayoche nachihu....Kirstoseneme yesekelute yante aynete hege atbakiweche nachewe...

  ReplyDelete
  Replies
  1. Keyetignawu aleme newu wede huwala yekerenewu? Ke Abatochek gibre sedomawiyan maltek newu? weyis abiyatkiristiyanachewun le buna bet ke keyerut? est nigren bakh?

   Delete
 130. Dn Daniel
  I would like to take this oportunity to thank you for your excellent teaching for this false writer.
  I read tesfayes's new book when i got the soft copy. Many things surprised me. Becuse I know tesfaye well becsuse I am his village meet you know what he did he just mention a few true things and try to use his excellent letrature ablity and try to convince others who does not know the fact well. by the way please Diaqon Daniel Pray for him. I think he is taken by evil. He write which is not important for him and for others.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?

   Delete
 131. ke starbacks yesebesebewun were tarik bilo tsafelen
  awekesh...awekesh siluat.........alu!!!!
  edmie yestlegn wendmie.

  ReplyDelete
 132. ምስኪን ተስፋዬ፣ የቅዱሳንን ነገር መጻፍ ትንሽ እውነታ ይዞ እየመዘዙና እያዋዙ በመተርተር ወደ ተነባቢ ልብወለድነት እንደመቀየር አይቀልም እኮ፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ የተስፋዬ የስነጽሑፍ ተሰጥኦና ማስታወሻ ይዞ ታሪኮችን የማቀናበር ችሎታ በየትኛውም የስነጽሑፍ ሚዛን ቢመዘን እንከን የሚወጣለት አይመስለኝም፡፡ እርግጥ ነው ከሁዋላው ያለው ዓላማ ጫት ሊያቃቅም ይችላል፡፡ ዳንኤል ስላቀረብከው የረቀቀ የመከራከሪያ ጽሑፍ በጣም አደንቅሃለሁ፡፡ እንደ አንድ ትልቅና አስተዋይ ሰው ተስፋዬ መጃዎችን አንብቦና ግራቀኙን አይቶ ስህተቱን ካመነ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 133. http://st-takla.org/Story-index.html

  ReplyDelete
 134. ለገንዘብ (ለጥቅም) ሳይሆን ለእውነተኛ ታሪክ ወይም ታሪክ እንዳይበላሽ (ታሪክ የምትወድህ ና የምትወዳት) ሰው በመሆን እውነት ታወጣኀለች እና በርታ…

  ReplyDelete
 135. GOD Bless You, Deacon Daniel !!!

  ReplyDelete
 136. i have read the book he wrote and he state that he has followed orthodox because only his family is orthodox so please do not feel bad he is not knowledge based writer

  ReplyDelete
 137. Oh GOD thank you! you never lost these land (Ethiopia)a man which have been your blessing like Daniel please be produce more and more men like Dan. to serve our lost and going lost generation.Ethiopia tabsedwya abe EGZIYABHER...AMEN!

  ReplyDelete
 138. Glory to God in highest!
  Dy. Daniel may God give you the blessing he promise to Abune Tekelehayamanote.

  ReplyDelete
 139. DANI AMLAKE-TEKLEHAYMANOT YITEBIKEH !!! amen

  ReplyDelete
 140. If I look at Tesfaye's chapter on our saints (ours includes him) as if it is written by some anonymous person other than "Tesfaye", I see an atheist who doesn't believe a human would stand for seven years or giving up on his eye sight to satisfy a bird's thirst (she better look for water else where)... I don't believe at least from this piece that he is bent on destroying Ethiopian Orthodox, as Eritrean Orthodox christians are less outraged by his slight of their saints. I wonder whether he claims to be an expert in history. But he has the right to believe (rightly or wrongly) that Ethiopian, Eritrean or European saints stories are legends other than stories, in spite of the fact that their "histories" were written and rewritten by hundreds of scholars. I think he can find hundreds of scholar who concur with him.
  Otherwise I appreciate your knowledge of religious history, as a body of knowledge.
  Keakbrot Selamta gar

  ReplyDelete
 141. የደራሲውን ማስታወሻ በመጠኑ አይቻለሁ፤ አጅሬ ስሜታዊነት በተሞላበት ብጥስጣሽ ታሪኮቹ ሰውን በከንቱ እስካሳቀለትና ሳቢ እስከሆነለት ድረስ ውሸትም ለመጻፍ የማይመለስ ብኩን እንደሆነ በቀላሉ ማየት ይቻላል፡፡ተስፋዬን አጃጅሎ ያስቀረው ጂል ሰይጣን በአባታችን ጠበል ካልሆነ በቀር በምክርና በተግሳጽ የሚወጣ አይደለም፤ ገና በብዙ እሚጀል ይመስለኛል፡፡ ባለፈው ጊዜ እንዲህ እንዳሁኑ በውቀቱ ስዩም ካለውቀቱ ገብቶ ስለ አቡነ ተ/ኃይማኖት ዘባርቆ ዳኒ አለዝቦና በመረጃ አስደግፎ አስተምሮት እኛም ተማርንበት፤ በውቀቱም ይቅርታ ጠይቆ ተስተካከለ፡፡ “ተስፋችን” ደሞ (ቅንጣት እንኳን በእሱ ተሰፋ ባናደርግበትም) ምናልባት ይቅርታ ከጠየቀ ለራሱ ይጠቅመዋል፤ እጅ የሱ ይቅርታ መጣም ቀረም አይጠቅመንም፤ የሚጠቅመን መች ጠፋን፡፡

  ReplyDelete
 142. እጂግ የሚገርመው ነገር የሀገራችን ሊቃውንት ‹ጨዋ ደፋር ነው› እንደሚሉት ተስፋዬም ያለ ምን ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ እርሱ ራሱም እንደሚለን ‹ኢትዮጵያ ሳለ የሰማቸውን አፈ ታሪኮች ሰብስቦ›(እኔ ግን አይመስለኝም፣ አሜሪካ ሆኖ ፈጥሮ እንጂ) በድፍረት ‹ሦስት ተክለ ሃይማኖቶች አሉ ይላል፡፡ ቢያንስ ለዕውቀት ክብር ሰጥቶ ‹ያሉ ይመስለኛል› ቢል እንኳን ምን አለበት፡፡ ለካስ እስከዛሬም በሌሎች መጻሕፍቱ ሲነግረን የነበሩት ‹የመንግሥት ምሥጢሮች› እንዲህ የተሰበሰቡ አፈ ታሪኮች ነበሩ ማለት ነው?............Dani this is not only from you.....It must be from holly spirit..........I always cry when I used to read every literature of you.........I think and feel I am created for nothing.......losing my compass

  ReplyDelete
 143. ተስፋዬ አባ ዮሐንስ ከማ ከ200 ዓመታት ቆይታ በኋላ ስለ ጻፉ ተሳስተዋል ይላል፡፡ ባታውቀው ነው እንጂ ሙሴ ኦሪትን የጻፈው ዓለም ከተፈጠረ ከሺዎች ዓመታት በኋላ ነው፡፡

  ReplyDelete
 144. ቃለ ህይወት ያሰማልን
  የተስፋዬ ጽሁፍ በማር የተለወስ እሬት መሆኑ አሁን ግልጽ ሆኗል፥፥
  አገር ቤት ሆኖ ያልጨረስውን በዘር በሃይማኖት የመከፋፈል ስራውን ቀጥሏል
  ጻድቁን ደሞ እስቲ ምን አርጉ ብሎ ነው,

  ReplyDelete
 145. ዳኒ፣ መደሰትስ በአንተ የአጻጻፍ ችሎታ ነው፡፡ ይገርመኛል፣ አቡነ ተክለሃይማኖትን ያህል ታላቅ ቅዱስ አባት ተስፋዬ በምድራውያን ላይ እንደለመደው ሲጽፍ፤ በእውቀቱም እንዲሁ ከዚህ በፊት እንደተዘባበተ ይታወቃል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ስሜት (ስህተትን ብቻ በማሳየት) መፃፍ መታደል ነው፡፡ አንተ የምታውቀውን በንጹህ ልቦና በማሳወቅና ሰዎች የተሳሳቱትን በመረጃዎች በማስደገፍ ሃሳባቸው ከንቱ መሆኑን ለማሳየት የምትከተለው አካሄድ ሁሌም ይመስጠኛል፡፡ ሰዎች ለምን እንዲህ አሉ እንዲሁም የማይረባም ቢሆን ሃሳብ ያነሳውን ሰውዬ ከማብጠልጠል ይልቅ በሃሳቡ ላይ ብቻ በማተኮር የምታቀርበው ትንታኔ የአንተን ብቃት ከማሳየቱም በላይ ለሰዎች ሃሳብና መብትም ዋጋ የምትሰጥ መሆንህን ያሳያል፡፡ አንተ እንዲህ ያሉ ገድሎችን በምትሰራበት ዘመን በመሆኔ እድለኛ ነኝ፡፡

  ReplyDelete
 146. Thank you, Dy. daniel kibret . GOD bless you.

  ReplyDelete
 147. በእውነት ዳ/ን ዳንኤል እግዚያብሄር ይባርክሕ፤ ዕድሜና ጤና ይስጥሕ፤ እንዳተ ዓይነቱን ያብዛልን

  ReplyDelete
 148. ሀሁሂሃሄህሆ

  ReplyDelete
 149. it is good argument

  ReplyDelete
 150. lets talk with reality every orthodox blocks tesfays idea ...how many of u read gedle abune teklehymanot ...read first try to evaluate it but deacon danial himselfs as gedlat has no contraverse with bible why not we talk truth & try to correct zat are written in gedlat but every one talks with full confidence as gedleabune teklehymanot is full of truth with reading....in some chapters it is against bible & in some try to exaggerate honour of saints....haleka weldekflie has written as there were 3 abuneteklehymanot definitely we can't say haleka was wrong ,if we say therefore we ail say haleka was wrong in his other book of orthodox church but our church accepts books haleka weldekflie & count him as among z great expert of ethiopian church....therefore lets judge things in reality by avoiding internal emotion , defense mechanism & hostility....mistakes of gedle abuneteklehymanot are great implication as there were 3 teklehymanot....my friend make deep investigation on zat & really judge it....gedle abune teklehymanot has very big mistake sat is not expected to be written by orthodox follower

  ReplyDelete
 151. አይ ዳኒ ሁሌምኮ አንጀት አርስ ነህ !! ታሪክን ካወቁ አይቀር እንዲህ ነው ! ስህተትን ሲነግሩም እዲህ በትህትና:: ለገባው ይህ የዕውቀት ጥግ ነው:: ይህ ዘባባል ተስፋየን አይመለከትም:: ምክንያቱም ተስፋየ የገባው መሳይ ጨዋ በመሆኑ::

  ReplyDelete
 152. i think he is good mad

  ReplyDelete
 153. ዳኒ እጅግ በጣም እናመሰግናለን ትክክል ሃሳብ ነው ያቀረብከው ሰውየው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተዘጋጀ ሰው ነው ትክክለኛ ምላሽ ሊሠጠው ይገባል እንደ ህጻን እያባበለ ህዝቡን እያረደው ነው ያለው በተለይም ጎጋውን ህዝብ ፣ እኒህንና ሌሎች የእለት ዉሎውን እየደረሰ ህዝቡን እያሳሳተ ነው ያለው ፣ የእርሱ ጽሁፎች በሙሉ ቧልት ፣ተረት፣ሸር ፣ሃሜት ናቸው ፡፡ ስለአንድ ህዝብ የዎገነ ይመስላል እዉነታው ግን ሌላ ነው የህዝቡን እሴት ዎደማይፈለግ ቁልቁለት ለማንከባለል እየተጋ ያለ ሰው

  ReplyDelete