Wednesday, October 23, 2013

ስሜ ናፈቀኝ

ዕቃ ለማውጣት ቦሌ ወደሚገኘው የካርጎ ተርሚናል ሄጃለሁ፡፡ መቼም ዘመድ ውጭ ሀገር ያለው ሰው ደጋግሞ የሚሄደው አንድም ለወዳጁ እድሜ ከጤና ለመለመን ቤተ ክርስቲያን፣ አንድም የተላከለትን ዕቃ ለመውሰድ ካርጎ ተርሚናል፣ አንድም የዓመት በዓል ብር ለመቀበል ባንክ ቤት ነው፡፡
ወረፋውን ጠብቄ መስኮቱ ጋ ደረስኩና ስሜን አስመዘገብኩ፡፡ እስክትጠራ ጠብቅ ተብዬም ወንበር ፈልጌ ተቀመጥኩ፡፡ ከጎኔ አንድ ጎልማሳ ተቀምጦ ይቁነጠነጣል፡፡ አንዴ ፀጉሩን አንዴ ዓይኑን ያሻል፡፡ ኩኩሉ እንደሚል አውራ ዶሮ አንገቱን ከወዘወዘ በኋላ ወደ እኔ ዞር አለና ‹‹ስምህ ናፍቆህ ያውቃል›› አለኝ፡፡
ገረመኝና ‹‹ስሜማ አብሮኝ ነው የሚኖረው፤ ምን ብሎ ይናፍቀኛል›› አልኩት፡፡
‹‹ስምህን ሰጥተህ አታውቅም፤ አሁን ስምህን አልሰጠህም እንዴ›› አለኝ፡፡
ይበልጥ ግራ ገባኝና ‹‹እና ወሰዱት ማለት ነው›› አልኩት ሳቅ እያፈነኝ፡፡

‹‹ታድያስ፤ አሁንኮ ወሳኙ እነርሱ ጋር ያስመዘገብከው ስምህ እንጂ አንተ ጋ ያለው ስምህ አይደለም፡፡ አንተ እገሌ መሆንህ ቁም ነገር የለውም፡፡ እነርሱ ‹እ-ገ-ሌ› ብለው ሲጠሩህ ነው ሕይወትህ የሚንቀሳቀሰው፡፡ እኔ አሁን ስሜ ናፍቆኛል፡፡ ስሜ ሲጠራ መስማት፣ ስሜ ሲጠራ አቤት ማለት ናፈቀኝ፡፡››
የእርሱን ስሰማ እኔም ስሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ ‹‹ትጠራላችሁ›› አይደል ያሉን፤ እውነትም ስማችንን ወስደውታል ማለትኮ ነው፡፡ ካልጠሩን ቁጭ ብለን መቅረታችን ነው፡፡ የተጠሩት ደግሞ እየተፍነከነኩ ወደ መስኮቱ እየተጠጉ ነው፡፡ ሰልፉ ሲረዝም፣ ጊዜው ሲሄድ፣ መቀመጥም ሲሰለቻችሁ ደግሞ ስማችሁ ይበልጥ ይናፍቃችኋል፡፡
‹‹እዚህ ብቻ ነው ወይስ ሌላውም ቦታ ወረፋ አለው›› አልኩት፡፡
‹‹ምን እዚህ ብቻ ኑሮህኮ እንደዚሁ ነው፡፡ ስም ትሰጣለህ፣ ትጠብቃለህ፣ ስምህን ትናፍቃለህ፣ እድለኛ ከሆንክ ትጠራለህ፣ አቤት ትላለህ፣ ወደ ሌላው ምእራፍ ትሻገራለህ፡፡ እዚያም ስም ትሰጣለህ፣ ስም ትናፍቃለህ፣ ትጠራለህ፣ አቤት ትላለህ፣ እንዲህ እያልክ ትኖራለህ፡፡ አቤት ካላልክ ደግሞ ችግር ነው፡፡ ያልፍሃል፡፡ አሁን ያ ሰውዬ ስልክ እያወራ አለፈው፡፡ ‹አቤት› ማለት ነበረበት፡፡ አሁን እንደገና ስሙ እየናፈቀው ነው፡፡ ያኛው ደግሞ ስሙ ቢናፍቀው፣ ቢናፍቀው የሚጠራው አጥቷል፡፡እየደጋገመ ‹ጥሩኝ እንጂ› ይላል፡፡‹ቆይ እንጠራሃለን› ይሉታል፡፡ አሁን አንተን በስልክ ጠርተውህ ነው አይደል የመጣኸው? አሁን ይኼ ጋቢ ነገር የለበሰው ሰው ለምን አትጠሩኝም ብሎ ነው ከክፍለ ሀገር የመጣው፡፡ ስሙ ናፍቆት፡፡ ልጁ ደውላ ዕቃ ልኬልሃለሁ አለቺው፡፡ እርሱ ካሁን አሁን ስሜ በስልክ ይጠራል ብሎ ቢጠብቅ ቀረበት፡፡ ስሙ ሲናፍቀው መጣና ‹እባካችሁ ጥሩኝ› አለ፡፡ እነርሱ ደግሞ ‹ሀገርህ ተመለስና ስንጠራህ ትመጣለህ› ይሉታል፡፡ ስሙ የናፈቀው ሰው መች እንዲህ በቀላሉ ይመለሳል፡፡››
‹‹እውነትምኮ ስም የሚያስናፍቁ አሠራሮች ሞልተዋል›› አልኩት ለመጎትጎት
‹‹ቤት ለማግኘት ትመዘገባለህ፣ ስምህ ይናፍቅሃል፡፡ ጋዜጣ ላይ ወጣ፣ ተለጠፈ፣ በሬዲዮ ተነገረ በተባለ ቁጥር ስምህን ማየት ትናፍቃለህ፡፡ እዚያ ዝርዝር ውስጥ ስታጣው ቅር ይልሃል፡፡ ስኳር ለማግኘት ትመዘገባለህ፣ ከሻሂው ሱስ ይልቅ ስምህን የመስማት ሱስ ይይዝሃል፡፡ ሥራ ለማግኘት ትመዘገባለህ፣ እንጠራሃለን ስትባል ትጠብቃለህ፤ ከዚያ ስልክ ባቃጨለ ቁጥር እመር ብለህ ትነሣለህ፤ የሆነ ሰው ስምህን ሲጠራው፣ አንተም አቤት ስትል ለመስማት ትናፍቃለህ፡፡ ጓደኛህ ደውሎ በቅጽል ስምህ ከጠራህ ትናደዳለህ፡፡ አንተ የምትጠብቀው ‹አቶ እንትና ነዎት› ተብሎ ሲጠራ መስማት ነዋ፡፡ ››
‹‹ቆይ ግን ለምን ይመስልሃል ስማችን እስኪናፍቀን የምንደርሰው››
‹‹አንደኛ ለምዶብናል፡፡ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ ስም ጠሪ መምህር ተመድቦ ስም መጥራት ተለምዷል፡፡ ዕድር ላይ ይጠራል፤ ፍታት ላይ ይጠራል፤ ዕቁብ ላይ ይጠራል፤ ቡና ለመጠጣት ይጠራል፤ እሥረኛ ለመጠየቅ ይጠራል፤ ቪዛ ለመጠየቅ ይጠራል፤ ስም መጥራት ባህላችን ሆኗል፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ስማቸው የሚጠራና የማይጠራ ስላሉ ነው፡፡ ስማቸው ሊጠራ የሚችል፣ ስማቸው የማይጠራና ስማቸው ሳይጠራ እንደተጠራ የሚቆጠሩ አሉ፡፡ ስማቸው ሊጠራ የሚችለው እንደ እኔና አንተ ያሉት ናቸው፡፡ ዕድል ካለህ ስምህ ይጠራል፡፡ ስማቸው የማይጠራው ደግሞ አንዳች ምክንያት የሚኖራቸው ናቸው፡፡ ስማቸው መጠራት የማያስፈልጋቸው ደግሞ ጉዳያቸው በውስጥ የሚያልቅላቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ስማቸው የወርቅ ቁልፍ ነው፤ ብዙ ቢሮዎችን ይከፍታል፤ ወይም ደግሞ የወርቅ ቁልፍ ያንጠለጠለ ስም የሚያውቁ ናቸው፡፡ አንዳንዴኮ ስምን መናፈቅ ይሻላል፡፡ ጭራሽ ስምህ ይጠፋልኮ››
‹‹አንተ ዋናው ክፉ አትሥራ እንጂ ስምህ ቢጠፋ ምን ችግር አለው? ከባሰ በሕግ መጠየቅ ነው››
‹‹ኖ ኖ ኖ ኖ ኖ እንደዚያ አይደለም፤ ስምህ ከነ ጭራሹ ከመዝገብ ላይ ይጠፋል እንጂ፤ ስምህ አልተመዘገበም፤ ‹ዳታ› ውስጥ የለም፡፡ ኮምፒውተር ውስጥ አልገባም፤ መዝገብ ላይ አልተገኘም፤ ፋይሉ ጠፍቷል፤ ትባላለህ፡፡ አንዳንዱ ስምማ ይገርምሃል እንደ ቁልፍ ማንጠልጠያ ወልቆ የሚጠፋ ነውኮ የሚመስለው፤ በተመዘገበበት ቦታ አታገኘውም፡፡ አሁን የእኔ ስም ዕድር ልከፍል ከሄድኩ አንደኛ ነው የሚጠራው፤ ስኳር ልወስድ ከሄድኩ ግን ጭራሽ ሳይጠራ ሊቀር ይችላል፡፡ ለክፍያና ለመዋጮ ብቻ የታደሉ ስሞች አሉ፡፡ ለመቀበል ብቻ የታደሉ ስሞችም አሉ፡፡ ሁለቱንም ስሞች በየመዝገባቸው ነው የምታገኛቸው፡፡ አንተ አንዴ እንኳን ስምህ አልጠራ ብሎህ እየናፈቀህ አንዳንድ ሰዎች ሁለትና ሦስት ጊዜ ስማቸው ሲጠራ ስታይ፣ ስም የሌለህ ሁሉ ይመስልሃል፡፡››
‹‹ግን ለሥራና ለስም የታደሉ ሰዎች የሉም››
‹‹ሞልተው፤ አሁን እኛ ሀገር ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ እውነተኛ ነጋዴ፣ ባለሞያ፣ ሥራ ፈጣሪ፣ ገበሬ፣ ምናምን ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ ስማቸውን የደመወዝ መክፈያና ግብር ሰብሳቢ ብቻ የሚያውቀው፤ አርቲስት፣ ዘፋኝ፣ ቀልደኛ፣ ደግሞ ለስም የታደሉ፡፡ እስኪ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአንድ ሳይንቲስት ቤት ዓመት በዓል ሲያከብር አይተህ ታውቃለህ? የአንድ የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ቤት ገብቶ ኑሮውን ሲያስቃኝ አይተህ ታውቃለህ? እነዚህ ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሥራውን የሠሩት፣ የደከሙት፣ የለፉት ስማቸው ሳይጠራ መጨረሻ ላይ የሚጨመሩ ቅመሞች ስማቸው ሲጠራ ትሰማለህ፡፡›› 
ይህንን እያወራልኝ በድምጽ ማጉያ ስም መጥራት ተጀመረ፡፡ አምስት ሰዎች ተጠሩ፡፡ አብሮኝ የነበረው ሰው ግን አልተጠራም፡፡ በድምጽ ማጉያው ‹መሐሪ ተሾመ› የሚል ስም ሲጠራ ከእኛ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰው ‹ወንድ ከሆንሽ መሐሪ አስቻለው ብለሽ አትጣሪም›› አለ፡፡
‹‹መሐሪ አስቻለው ብሎ መጣራት የወንድነት መለኪያ ሆነ እንዴ›› አልኩት
‹‹መሐሪ አስቻለው እኔ ነኛ››
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው
42 comments:

 1. Interesting.Dani I eagerly expect those days in which we will using different systems which are linked electronically to avoid such problems.

  ReplyDelete
 2. ‹‹እውነትምኮ ስም የሚያስናፍቁ አሠራሮች ሞልተዋል››

  ReplyDelete
 3. "እስኪ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአንድ ሳይንቲስት ቤት ዓመት በዓል ሲያከብር አይተህ ታውቃለህ? የአንድ የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ቤት ገብቶ ኑሮውን ሲያስቃኝ አይተህ ታውቃለህ? እነዚህ ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ "

  ReplyDelete
 4. Hello Dn Dani; it is general truth 100% real in particular in our beloved country. Many many problems in each sector to wait to listen our names while calling or posting in different announcement medias. probably you may registered for one purpose in one sector, no one understand your problem rather wait, wait and wait. Recently my younger brother assigned in AAU, the department announced through their websites but missed my brother name.

  ReplyDelete
 5. ‹‹ አሁን እኛ ሀገር ሊቅ፣ ሳይንቲስት፣ እውነተኛ ነጋዴ፣ ባለሞያ፣ ሥራ ፈጣሪ፣ ገበሬ፣ ምናምን ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ ስማቸውን የደመወዝ መክፈያና ግብር ሰብሳቢ ብቻ የሚያውቀው፤ አርቲስት፣ ዘፋኝ፣ ቀልደኛ፣ ደግሞ ለስም የታደሉ፡፡ እስኪ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የአንድ ሳይንቲስት ቤት ዓመት በዓል ሲያከብር አይተህ ታውቃለህ? የአንድ የረዥም ርቀት አሽከርካሪ ቤት ገብቶ ኑሮውን ሲያስቃኝ አይተህ ታውቃለህ? እነዚህ ለስም ያልታደሉ ናቸው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ሥራውን የሠሩት፣ የደከሙት፣ የለፉት ስማቸው ሳይጠራ መጨረሻ ላይ የሚጨመሩ ቅመሞች ስማቸው ሲጠራ ትሰማለህ፡፡››
  አቦ ይመችህ ዳኒ በርታ !

  ReplyDelete
 6. Thank you Dani. I was Jimma University ten yers ago. Most of my room mate came from Oromia. I born In Addis but my Mom and Dad were from Oromia but they didn't teach me their languche inaddition that my name is not Oromian people name. My mom called me Abrham from the Bible. All my class mate talking with Oromia and they never talk to me. One day I asked them why they descrimnate me and they told me that " you are not an Oromian and I told them , I am Oromo. All of my room mate didn't agree because my name is not Oromo people name. When I grow up in Addis no body asked me this kind of question so I couldn't answer to them. I callem for my Mom and she came and talked to the school director then, the school leader sent me into other room. We born in Ethiopia and we are an Ethiopian. It doesn't matter if we have any kind of name but our goverment bring this stupid situation by dividing us with race, relagion and languche. God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Anonymous; just as I was getting ready to lose it because of your appalling English for a University student/maybe even a graduate, I managed to calm myself down as the thought that you may just have been visiting Jimma University after all. If you are indeed a University graduate and if your level of English is the standard to be expected from today's University graduates, God help Ethiopia!!

   Delete
  2. My brother, you took me back to 1980 memory when I was campus student sharing 1 dorm with 1 Tigrian, 2 Gojame and I was from Oromia. We played freely without any fear of ethnic discrimination. After the coming into power of this Government things got worser and worser. Ethnic clashes in many campuses occurred. Who is responsible? It is both the government and participant of these rows. While the objective of the government is known, why do the people fail to wake and restrain. I think many youngsters are filled with hostile ethnic preaching and that is why they discriminated you. But, no one benefits from this devil work. When you go to regions, subdivision goes up to kebeles. Therefore, don't worry, but prey, because Satan is now released from jail to tempt all human beings, the ethnic and religious division being its running track and it sits on a horse known as 'democracy'. But I appreciate those people who love all languages equally and try to learn them when they came across suitable condition. I wonder when many people lived in Oromia without knowing a word of Oromigna. Had I lived in other regions I would have learned their language.

   Delete
  3. Dear Yimeku Tamirat,

   I read your adverse comment (for the participant name Anonymous). This participant share us his or her experience at one the higher institutions (Jimma University), " how he or she was discriminated by his or her roommate with the reason of language barrier." The participant (anonymous) clearly forwards his or her experience by his or her second language (English). Dear Yimeku Tamirat, before you are giving such kind adverse comment, you need to look at your self first. I am telling you, I couldn't understand some most of your sentences. For example , what do you want to say in the open sentence - "If you are indeed a University graduate and if your level of English is the standard to be expected from today's University graduates," you open with If , you should close the sentence "GETAWE." Or tell us the sources you copy from. I am telling the person you gave him or her a bad comment has a better English than you. The only problem I found was spelling errors.

   At least, at the end of his or her comment wrote "God Bless Ethiopia" but you choose to said "God help Ethiopia." Why not you weren't said " God Bless Ethiopia?" Ha! Ha! I left the rest for the participants. I got you who you are!

   God Richly Blessing Ethiopia and America!!!

   Delete
  4. Dear Yimeku Tamirat
   Thank you so much for your comment. I would like to respond about your comment. As you know that, Ethiopia has Ethiopian languche and alphabet. That called Amharic. If you go everywhere you don't get anything written by English because we use Amharic alphabet that accepted by Ethiopian government and people. When people finished their school they write by Amharic. I read it three times, the Anonymous person expression was very clear for me and it was understandable. I am giving you suggestion, if you don't understand that message; you have to practice more to understand English. In addition that with my understanding that person family came from Oromia and he/she told us about his/her ethnic group. So we have to appreciate this kind of unique people because they stand for Ethiopia culture and unity not for a certain group. I am supporting you the Anonymous person. As you said God Bless Ethiopia.

   Delete
  5. O my God this message is to Yimeku Tamirat. I don't understand you why you don't understand the Anonymous expression. I have diploma and degree but I can't express something with English. He/She wrote everything clear and I pray to God to rich in that level. Shame on you, you have to ask him/her apology for your stupid comment.

   Delete
  6. YEMEKU TAMIRAT ... YOUR COMMENT FULL OF ARROGANCE WHILE YOUR ENGLISH IS NO BETTER THAN HIM... EVERYBODY UNDERSTOOD HIM BUT YOU. ...ask apology and swallow you your acrid comment back.

   Delete
 7. keep it up dani may GOD bless you.

  ReplyDelete
 8. ድንቅ እይታ ነው ዳንየ! እውነትን ይዘህ ከሆነ ስምህ ወይም አይጠራም ወይም ደግሞ ይዘገያል፡፡አንዴ ከተጠራ ግን ለዘላላም አይጠፋም፡፡ዛሬ ዛሬ ስምን ለማስጠራት ለስም ጠሪዎች ብዙ ነገር እየተከፈለ ነው ግን ምን ዋጋ አለው እርሱ ሲጠራ እንጅ… አንተ ግን በርታ እግዚአብሔር ያበርታህ፡፡

  ReplyDelete
 9. ግሩም፤ እድሜና ጤና።

  ReplyDelete
 10. This interesting view D.Daniel Kibret Thank You...........

  ReplyDelete
 11. ልቤ እስኪፈርስ ነዉ ያሳቀኝ ሆሆ ሰዉ የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩት ያህል ይስቃል አሉ!! ዲ/ን ዳንኤል እኔ እራሴ ብዙ ግዜ ስሜ ሲጠራ መስማት ይናፍቀኛል አሁንም እራሱ እየናፈቀኝ ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 12. abo dani yimeche E/R idmena tenawn yeste. betam atkoy yemtitsifew neger yenafekegnal.

  ReplyDelete
 13. ስሜ ብዙ ጊዜ ናፍቆኝ ነበረ በተለይ ሰራ ተወዳድሬ..........!!! አይጣል ነው! እንቅልፍ የለ ምግብ የለ ስሜ እስኪጠራ መናፈቅ ብቻ! kb

  ReplyDelete
 14. Please change the Font to make it readable

  Thank you for the content.

  ReplyDelete
 15. I used to live Japan. They most of the time say, if the leader not good and the follower are bad and if the leader is best the follower are best. We have to work hard to change the foundation of the country not the branch. The most goal should be to cut the log instead of the branch. Right now most of us not try to participate in poltics but we allways condem our goverment to get the right service. As we all know that Ethiopia lead by dead body or Meles Zenawi sprit. He aready passed away but still he lead us. No one anwer our question because we passed away and we don't know our leader so how we can get the right service. My suggestion is to get the right service we have to take over our country otherwise the dead body lead us until the end of the world. I have plan to participate fot the next election and I will let you know my self if you can help me. I promise to stand for our people and Ethipian Orthodox church if I elected for next election. I love you Danny, I have been learning from your CD, Blog, Book and in person. I will continue God bless you.

  ReplyDelete
 16. አንተ በአንድ ቀን ነው የገረመህ
  ሀዋሳ በኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ3 ወር ቀጠሮ ተሰጥቶህ ትሄዳለህ ከሶስት ወር በኋላም ስምህ ይናፍቅሃል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. wedaje teshewudeh new enji berr lay lezebegnochu be5 tederajiteh 100 birr keseteh beseat wust yisetihal .teselfe worefa litebik kalk ayidelem be 3 wor beametim atagegnim. Its From my experience!!!

   Delete
 17. Ho, Dani I was there two times I waited more than six hours but I didn't mind to wait that long. When I received my first stuff it was ok to pay three thousened birr by next time they asked me for one Vedio camara 17,000 Birr and I told them to return it back after four month they retuned back with my expense. My brother bought 500 hundred dollar but they asked me 17,000 Birr this is more than my brother paid the camara. I got some information from my friends when they need the stuff to keep for them they asked you to pay them expensive price and most Ethiopian didn't attempt to ask to return back. I just want inform for your follower if they don't want pay they have right to ask about returning back to the sender. I love you Dani.

  ReplyDelete
 18. በድምጽ ማጉያው ‹መሐሪ ተሾመ› የሚል ስም ሲጠራ ከእኛ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰው ‹ወንድ ከሆንሽ መሐሪ አስቻለው ብለሽ አትጣሪም›› አለ፡፡

  ‹‹መሐሪ አስቻለው ብሎ መጣራት የወንድነት መለኪያ ሆነ እንዴ›› አልኩት

  ‹‹መሐሪ አስቻለው እኔ ነኛ››

  ReplyDelete
 19. እግዚአብሔር ያበርታህ

  ReplyDelete
 20. ‹ቆይ ግን ለምን ይመስልሃል ስማችን እስኪናፍቀን የምንደርሰው››

  ReplyDelete
  Replies
  1. Thank you everybody for giving comment with Daniel Blog. I always open his Blog to read your supportive or objection comment. I know he has many followers but only the few people respond their opinion. Please participate to get more information from different direction. God bless Dani and Ethiopia.

   Delete
 21. realy its with us,but why its?.make it honest,panctual,accountable all ethiopians this ur positive action pay one day to you.all the best for all ethiopians brothrs,sisters in the year.thanks D/N daniel.mekoya from hawassa

  ReplyDelete
 22. ሰዎች ብልህ ከሆኑ ከብዙ ይማራሉ፡፡ በተለይ መሪዎች ደግሞ ከምንም ይማራሉ፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማምጣት፡፡ ብዙ ጥናት ከማደረግ ወጪ ከማውጣት እነዲህ አይነት ነገሮችንም ከግምት ውስጥ በማስገባት አገልግሎትን ጥራት መጨመር ይቻላል፡፡ ይህ አተያይ ውስጠ ወይራ ነው፡፡ እውነት ነው በኢ.ቲ.ቪ ያለውም ነገር እንዲሁ፡፡ ዲያቆን ዳኒኤል አንድ ቅር የምታሰኘኝ ነገር አለ እሱም ቶሎ ቶሎ እነድዚህ ባለ መጣጥፍ ብቅ ባለማለትህ! ሰዎች ብልህ ከሆኑ ከብዙ ይማራሉ፡፡ በተለይ መሪዎች ደግሞ ከምንም ይማራሉ፡፡ መልካም አስተዳደርን ለማምጣት፡፡ ብዙ ጥናት ከማደረግ ወጪ ከማውጣት እነዲህ አይነት ነገሮችንም ከግምት ውስጥ በማስገባት አገልግሎትን ጥራት መጨመር ይቻላል፡፡ ይህ አተያይ ውስጠ ወይራ ነው፡፡ እውነት ነው በኢ.ቲ.ቪ ያለውም ነገር እንዲሁ፡፡ ዲያቆን ዳኒኤል አንድ ቅር የምታሰኘኝ ነገር አለ እሱም ቶሎ ቶሎ እነድዚህ ባለ መጣጥፍ ብቅ ባለማለትህ!

  ReplyDelete
 23. We always have to wait for our turn for everything in most places we went to receive the services we demand because usually there is lack of fairness. You wait decently until your name to be called but somebody who knows some one inside may come and be up front and got what they want in a second. Imagine you are still waiting for your name to be called. May God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 24. ድምጽ ማጉያው ‹መሐሪ ተሾመ› የሚል ስም ሲጠራ ከእኛ ፊት ለፊት ባለው ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰው ‹ወንድ ከሆንሽ መሐሪ አስቻለው ብለሽ አትጣሪም›› አለ፡፡
  ‹‹መሐሪ አስቻለው ብሎ መጣራት የወንድነት መለኪያ ሆነ እንዴ›› አልኩት
  ‹‹መሐሪ አስቻለው እኔ ነኛ››

  ReplyDelete
 25. Nice catch Dani the great !!once again,my hat goes off to U.You are legit.

  ReplyDelete
 26. ስማቸው ሊጠራ የሚችል፣ ስማቸው የማይጠራና ስማቸው ሳይጠራ እንደተጠራ የሚቆጠሩ አሉ፡፡

  ReplyDelete
 27. መቅደስ መሐሪ

  ትክክል ነው ዳኒ ስንት ስማቸው መጠራት ያለባቸው ግን ሳይጠሩ የቀሩ አሉ ጥሩ ጥቆማ ነው

  ReplyDelete
 28. Achraresa betam yaznananal abo temechaleh

  ReplyDelete
 29. *እረ ለመሆኑ ሰው እስከጠራ የሚጠብቀው
  እኔ ነኝ ብሎ አይነሳም ወይ ሥም ያለው ሰው?
  ቢጠሩት አይሰማ ምን ቢጮሁበት
  ምንኛ ዘመን ነው ሥም የጠፋበት!?

  ReplyDelete
 30. Thank you Dn. Daneal ... it is realy true God bless you and Ethiopia.

  ReplyDelete
 31. Geta yibarikih Dn Daniel... Yebetekristiyanachin alegnita... Egziabher edimewin ena tsegawin yaberkitilih

  ReplyDelete