Thursday, October 17, 2013

አንድ ከሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ

የመንበረ ፓትርያርክ 32ኛው ጉባኤ የረቡዕ ዕለት ከሰዓት ውሎ ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳው ‹መቻቻልን› የተመለከተ ሲሆን አቅራቢዎቹም ከፌዴራል ጉዳዮች የተወከሉ አካላት መሆናቸውን በዕለቱ የመርሐ ግብር ዝርዝር ላይ ተገልጧል፡፡ ከሰኞ ጀምሮ ይቀርብ በነበረው የአህጉረ ስብከት ሪፖርቶች ላይ የመብት ጥሰትና ሥልጣንን ለግል ሃይማኖት ማስፋፊያ የመጠቀም አዝማሚያዎች መኖራቸውን፣ በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው እምነትን የመያዝ፣ የማስፋፋትና የአምልኮ ቦታ የማግኘት መብት እየተጣሰ መሆኑን የሚገልጡ ዘገባዎች ይሰሙ ነበር፡፡

በትናንትናው የከሰዓት ውሎ ስለ መቻቻል ገለጣ ከተሰጠ በኋላ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳትና የጉባኤው ተሰብሳቢዎች የየአካባቢያቸውን ችግሮች በዝርዝር ነበር ያነሷቸው፡፡ ‹‹መቻቻል እስከ ምን ድረስ ነው›› ብለው ነበር ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ የጠየቁት፡፡ ‹‹አሁን በምዕራብ ወለጋ ያለው ሁኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ይመስላል ወይ? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል እንዴእንድንቻቻል አድርጉን፣ እንችላለን›› ነበር ያሉት፡፡
የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ ‹በነጆ ወረዳ በሕጋዊ መንገድ ተሠርቶ የነበረው ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ባለ ሥልጣናት ተጽዕኖ እንዲፈርስ መደረጉን፣ ለምን ታፈርሳላችሁ ብለው ድርጊቱን የተቃወሙ ስድሳ ምእመናን መታሠራቸውን›› በኀዘን ነበር የገለጡት፡፡ አያይዘውም ‹‹በባኮ ወረዳ የተመደቡ አንድ ካህን እያረሱ እያሉ የአካባቢው ባለ ሥልጣናት መጡ፤ ካህኑን በሰደፍ እየደበደቡ ‹ከዚህ ሀገር ልቀቁ፣ ይህ የነፍጠኛ መኖሪያ አይደለም› እያሉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ካህኑን ሲደበድቧቸው አንበርክከው፣ ለ15 ደቂቃ አተኩረው ፀሐይዋን እንዲያዩ እያስገደዱ ነበር፡፡ ድብደባውን ሰምተው የወጡት ባለቤታቸው በድንጋጤ ታመው ከጥቂት ቀናት በኋላ ሕይወታቸው አለፈ››
‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ፤ ይህ ቦታ ለእነርሱ አይሆንም ብሎ በመከራከሩ አንድ ዲያቆን ተደብድቦ ሞተ፡፡ የሕክምና ውጤቱም ሆን ተብሎ በወባ በሽታ ሞተ ተብሎ ተሠራ፡፡ ለሁለት ዓመት ያህል ተከራክረን አሁን ቦታው ለእኛ ተወሰነ፡፡
ጊምቢና መንዲ ላይ የምእመናን ልጆች ትምህርት ቤት ውስጥ በፖሊስ ማተባችሁን በጥሱ እየተባሉ ነው፡፡ ለምን ስንላቸው ከላይ የወረደ መመሪያ አለ ይሉናል፡፡››
ቀጥለው የሀገረ ስብከታቸውን ችግር ያቀረቡት የጋሞጎፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ነበሩ፡፡ ‹‹በጋሞ ጎፋ መቱ ወረዳ፣ ዋጁ ኡቆ ላይ የመስቀል ማክበሪያ ቦታችን ለሱቅ መሥሪያ ቦታ ተሰጠ፡፡ አቤት ብንል የሚሰማን በማጣታችን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መስቀል ሳናከብር ዋልን፡፡ ሀገሪቱ በችግር ላይ በነበረች ጊዜ እንኳን መስቀል ሳይከበር ቀርቶ አያውቅም ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ለመንግሥት እየተሰጠ ነው፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን በቅዱስነታቸው በኩል ለክልሉ ደብዳቤ ጻፍን፡፡ ክልሉ ወሰነልን፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተረከብንም፡፡››
ቀጥለው ሃሳባቸውን የሰጡት የባሰ ካልመጣ በቀር ድምጻቸው ማይሰማው ብጹዕ አቡነ ያሬድ የሶማሌ ክልል ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ ‹‹በሶማሌ ክልል አምስት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ናቸው ያሉን፡፡ ምእመናኑ ብዙ ናቸው፡፡ ሲወልዱ የሚያስጠምቁበት፣ ሲያርፉ የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን እንትከል ብንል የሚሰማን አጥተናል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዱ ምእመናን በግላቸው ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ለዚህ መልሳችሁ ምንድን ነው›› ብለዋል፡፡
በገለጻው ላይ ኢትዮጵያ ክርስትናን የተቀበለችው በ4ኛው መክዘ ነው የሚለውን የተቃወሙት ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››
የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ እንድርያስም ‹‹በቤተ መንግሥት የወርቅ ዕቃ ብቻ አይኖርም፣ የእንጨትም፣ የድንጋይም ዕቃ አለ፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ሁሉም ጥሩ አይሆንም፣ መጥፎም ይኖራል፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል ብሏል፡፡ በእኔ ሀገረ ስብከት ስድስት አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፡፡ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በሌላ ቦታ፡፡ ይህንን ለክልሉ መንግሥት ብናሳውቅ አልረዱንም፡፡ የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ ድሮ ያስቸገረን የንዋያተ ቅድሳት ዘረፋ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ወደ ማቃጠል ተዛውሯል፡፡ አንዱ ባለ ሥልጣን እንዲያውም ችግሩን ሳቀርብለት ተቆጣኝ፤ ብዙ ብናገር ነፋስ ስለሚወስደው እዚህ ላይ ይብቃ››
ከብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት ቀጥሎ የተናገሩት የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ‹‹በበዴሳ ወረዳ ያለ አንድ የሌላ እመነት ተከታይ የሆነ ዳኛ ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጋር ቄራ አንካፈልም፤ በመኪና አብረን አንሄድም› ብሎ ዐወጀ፡፡ በጋራ በመቻቻል የኖርንበትን ዕድር ሁሉ ለዩ ብሏል፡፡ ታድያ እንዴት መቻቻል ሊመጣ ይችላል፡፡››
ከጉባኤው የቀረበውን ቅሬታና ሃሳብ ያዳመጡት የፌዴራል ጉዳዮች የሥራ ኃላፊዎች የቀረቡት ቅሬታዎች በሰነድ ተደግፈው ቢደርሷቸው እነርሱም በመፍትሔው ላይ መሥራት እንደሚችሉ፤ ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ጉባኤም ጉዳዩ በየደረጃው ቢቀርብለት መፍታት እንደሚችል፡፡ ቅሬታዎችን እንደዚህ ባለ መድረክ ከሚሆን በየጊዜው እየተገናኙ መፍታት ቢቻል›. የሚሉ ሃሳቦችን ሠንዝረዋል፡፡
የዘንድሮው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ በአደረጃጀቱ ውበት፣ በተሳታፊዎቹ ብዛት፣ በአህጉረ ስብከቶች ቁጥር(50 ደርሰዋል)፣ በስብሰባው ቁም ነገረኛነት ካለፉት የተለየ ነበር፡፡ እነ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ የሰበካ ጉባኤ ስብሰባ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በብርቱ እንደ ደከሙበት ያሳያል፡፡ በየዘገባዎቹ የተሰሙትን የመብት ጥሰቶች፣ ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ጫናዎች፣ የአምልኮ ቦታ እጥረቶች፣ በካህናቱ ላይ የሚፈጸሙትን ግፎችና፣ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ የመንጠቅ ርምጃዎች ግን ሊገቱ ይገባቸዋል፡፡ ከአንዳንድ ክልሎች በቀር በብዙዎቹ የዞንና የክልል ባለ ሥልጣናት ችግሩን ተረድተው ለመፍታት እንደሚጥሩ ተገልጧል፡፡ በወረዳ ደረጃ የሚገኙት ግን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የግል እምነታቸውን እያስፋፉ መሆኑን ያሳያል፡፡ በደቡብ ጎንደርና በምሥራቅ ጎጃም የተፈጸሙት የአብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡
በየአካባቢው በሚገኙ ባለ ሥልጣናት የሚፈጸሙ ትንኮሳዎችም መቆም አለባቸው፡፡ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳቱ ‹አታስቆጡን› እያሉ ደጋግመው የተናገሩት ነገር የዋዛ አይደለም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማቸው አካላት የሚፈጽሙት ገደብ አልባ ትንኮሳና ጫና ወዴት እያመራ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም አደረጃጀቷንና አሠራርዋን ይበልጥ የምትፈትሽበት፣ አሁን ለገጠማት ተግዳሮት ብቁ የሚሆን አሠራና አወቃቀር የምትይዝበት፣ ችግሮችን በስብሰባ ብቻ ሳይሆን በአካባቢያዊ ውይይት፣ በሕግ መሥመርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ በመሥራት የምትፈታበት መንገድ ሊኖር ይገባል፡፡  
ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡
በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ 

128 comments:

 1. Amlake Kidusan Yitbkat Enji lela min yibalal?

  ReplyDelete
 2. ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡

  ReplyDelete
 3. the work of devils is still continued, it is really time to cray, pray and stand together to our church!. this is the objectives of this government, the Muslims and protestants are aiming to attack the truth( EOTC). They want their leadership to accomplish to fight our church. the Federal Affairs asking the document but they knows each and every thing happen in the church. In every direction and corner all this devils including the government are objectively working day and night to undermine the work or the contribution of EOTC for this country. why? why? why...? the people of EOTC are choosing silent? why our church leaders are strong enough to challenge the government and teach the people so as to keep his church and ask his right of living, prying and take measure on devils.........

  ReplyDelete
  Replies
  1. yeah, you are right. we have expected to fight legally with these people. GOD may bless you!.

   Delete
  2. Thank you D.Daniel for sharing. It is a sign that we ETOC beleivers need to be strong at prayers. Even if mass prayer is prohibited can't we pray at home ? I think we can pray for our church leaders strength and for passing the test of these times.

   Delete
 4. አብያተ ክርስቲያናትን የማቃጠል ርምጃዎች በጊዜው ተጣርተው መፍትሔ ካልተሰጣቸው ፍጻሜያቸው አያምርም፡፡

  ReplyDelete
 5. ...መቼስ ዦሮ መስማት...ዓይን ማየት አይከለከል... ለሊቃውንቱ ለአባቶቻችን ያውም በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ....ስለመቻቻል፣ ስለ ክርስትና መጀመር በኢትዮትያ ሊናገሩ ከፌዴራል ጉዳዮች መጡ!...እህህህህህህ.... እስቲ ይሁን... የኦርቶዶክሱን ክርስቲያን የተማረከ ወታደር አደረጉትኮ... ለነገሩ ምን ያድርጉ በማያገባቸው እየገቡ የፈለጉትን ሲያደርጉ...ትላንትም...ዝም...ዛሬም ዝም....ነገም.... ?????? ዝም ከሆነ መልሳችን... ???????

  ReplyDelete
 6. አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት?

  ReplyDelete
 7. ቃለ ሕይወት ያሰማልን! 'እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ' አሉ! ግሩም ነው! እስኪ በዚህ ይብቃንና የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በቃ ለማለት ልቦናውን ፈጣሪ ይስጠን አሜን!

  ReplyDelete
 8. mengst be ye akababi endngach aderegen yehager smetachin yaferese meselew gn yihe metfo zemen alfo betekrstianachin yemtkeberbet ken yimeta yihon?

  ReplyDelete
 9. ‹‹በሰንበትና በቅዱስ ሚካኤል ቀን ምእመናን ሊያስቀድሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ‹ለቅዳሴ ካህናቱ ይበቃሉ፤ እናንተ ውጡ›› እየተባሉ እንዳያስቀድሱ ይደረጋሉ፡፡ ከእኛ ቤተ ክርስቲያን 70 ሜትር ርቀት ላይ ሆን ተብሎ እርስ በርስ ለማጋጨት ለፕሮቴስታንቶች የጸሎት ቦታ ተሰጠ፡፡ ለምን ታጨቃጭቁናላችሁ

  ReplyDelete
 10. ግሩም አስተያየት! እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያንን ከነፎች ይጠብቅልን፡፡ ዲያቆን ዳንኤል እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 11. በኢትዮጵያ የሚገኙ ፕሮቴስታንት ድርጅቶች አብዛኞቹ እንደ አላማ አስቀምጠው ከሚሰሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የመንግስትን ስልጣን መዋቅር መቆጣጠር ነው ። ይህን ደግሞ የሚናገሩት በህቡዕ ሳይሆን በየአዳራሾቻቸው በሚደረጉ ስብከቶችና እንደ መስርያ ቤቶች ራዕይ ዓላማ ግብ ተብለው ተጽፈው በሚሰቀሉ ቢል ቦርዶች ላይም ጭምር ነው። ልብ በሉ ሌሎች ባለፈው ስርአት ተጎድተናልና አሁን እኛ ስልጣኑን መያዝ አለብን ብለው በተደራጀ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱና ፕሮቴስታንት ደግሞ ሲጨመርበት ኦርቶዶክሳውያን ምን እየተሰራ እንደሆነ መረዳት አልቻልንም።

  ReplyDelete
 12. HI D/DANIEL. THANKS FOR YOUR POSTS
  Min yishalenal endih yemeselech betekirstianachin sikatel mayet. bizu lela yalteneger bewolaita zone wust ale mihmenun masferarat. ara mela yibal lebizowch yemaytay neger ale bicha....eg/r mechereshawun yasayen. dani ameseginalew

  ReplyDelete
 13. God bless our fathers.

  ReplyDelete
 14. Egziabhaer Melkam new Bemekera kenim Mesheshegia New !!!!!!

  ReplyDelete
 15. እግዚአብሔር ይባርክህ፣ይጠብቅህ እድሜና ጤና ይስጥህ
  አባቶቻችን ለካ አሉ ማለት ልጀምር ይሆን

  ReplyDelete
 16. ........ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡ ...EG/R yerdane

  ReplyDelete
 17. እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

  ReplyDelete
 18. Yekidusan AMLAK Yitebkat enji lela min yibalal?

  ReplyDelete
 19. ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

  ReplyDelete
 20. Thanks a lot for sharing this and I appreciate our fathers. We all know what intentional harassment to the Christians and the church is happening in our area as well. We are expecting our fathers to be courageous enough and lead Christians so as to protect our church from any type of abuse.
  "Betekedesew Sefra Yetefate erkuset Kumo sytau anbabew Yastewel"

  ReplyDelete
 21. እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብር ምን ነበር ምሥጢሩ
  የክርስትና ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ
  መቃብሩን ክፈቱና አበው ይመስክሩ፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ
  ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ፡፡

  ነብያት በመጋዝ የተሰነጠቁት
  ሐዋርያት ቁልቁል የተዘቀዘቁት
  ሰማዕታት በእሳት የተለበለቡት
  ቅዱሳን በገዳም ደርቀው የተገኙት
  ምሥጢሩ ምን ነበር? አበው ይናገሩት፡፡

  ይናገር ዝቋላ ግሸን ላሊበላ
  የቅዱሳንን ዐፅም ለምን እንዳልበላ፡፡
  ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር
  እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡
  ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት?
  ወይስ ሀብት ንብረት የተሟላ ቤት?
  ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት?
  እናንተ ገዳማት ምሥጢሩን አውሩት፡፡

  ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
  ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
  እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
  ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
  የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
  በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
  ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ሰው አማረው
  የሃይማኖት ጀግና የትነው የማገኘው?
  ልግባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት
  ማኅበረ ሥላሴ ከቅዱሳን ቤት?
  አክሱም ግሸን ማርያም ከቃል ኪዳን ቦታ
  ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ?
  ፈሪሐ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ
  ቤተ ክርስቲያንን ያልተደፋፈረ፡፡

  የት ነው የማገኘው ለሃይማኖቱ ሟች
  ለተዋሕዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች፡፡
  የወገን መመኪያ የከሀዲ መቅሰፍት
  ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሣ ቀስቅሱት፡፡
  እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ
  የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምሥጢሩ?
  የክርስቲያን ሕይወት ምን ነበር ተግባሩ?
  መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

  ወገን ሰው ናፈቀኝ ዐይኔን ጀግና አማረው
  በእምነቱ የፀና የትነው የማገኘው?
  ብቅ ይበል እንየው እሱ ማነው ጀግና?

  በጐችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ
  መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ
  የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ
  እንደዚያ እንደ ጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ?
  የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው
  የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው
  የዓለም አሸክላ ልቡን ያልማረከው
  የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?
  ምሥጢርን ከምሥጢሩ አንድ አድርጐ ቀምሮ
  ወልድ ዋሕድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ
  እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ
  ከአትናቴዎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

  ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር
  መሆኗን የሚያምን ማኅደረ እግዚአብሔር
  ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን
  ትንታግ ምላስም ጭንግፍግፉን
  ልሳነ ጤዛ መናፍቅን
  ወልደ አርዮስ ዲቃላውን፡፡
  በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ
  ጀግና ማነው ዝቅ ይበላ፡፡

  ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት
  እስኪ ጎርጎርዮሰ ይምጣና ጠይቁት
  ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ
  ምሥጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ፡፡

  የክርስቶስ ባርያ የአጋንንት መቅሰፍት
  ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት
  ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት
  የጸሎት ገበሬ ገብረ መንፈስ ቅዱስንም ይነሣ ቀስቅሱት
  ይነሣ ጊዮርጊስ ይመስክር ምሥጢር
  የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

  ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ
  ዲያብሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ፡፡
  ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ
  መር ብለው የወጡት ከሥጋ ገበያ
  ጾም ጸሎት ነበረ የሃይማኖት ጋሻ
  መልከስከስ ምንድነው እንደ አበደ ውሻ፡፡

  እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት
  ዓላማው ምንድነው የዘመኑ ወጣት፡፡

  እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና
  ወልድ ዋሕድ ብሎ በእምነቱ የፀና
  ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ
  ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

  ምንጭ፡- መለከት 1ኛ ዓመት ቁጥር 6

  ReplyDelete
  Replies
  1. thank you!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
  2. ጐበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና
   ምግባር ሃይማኖቱ በእጅጉ የቀና፡፡
   እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት
   ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡
   የጊዮርጊስ ወገን የት ነው የማገኘው?
   በመሀል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው?
   ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው?

   Delete
 22. how body this is!!! is this all happening in my country? we are too critics!! for the Western welleg's case, revenging persons after 100 years for attacks done by some others from the group they are is irrational!! Naftegna is group of persons that were before 50 years ago, no people or nations should be considered as naftegna!!

  ReplyDelete
 23. Thank you. I think all Ethiopian people know about the situation. It is not new information for us. Our father mentioned only five percent of the problem. Most of our church leader are working for goverment and they don't belive by God. Their main purpuses are to destroy our church, strength, unity. One years ago when Hilemariam came to the prime minister. One of weyana leader Shibat told for ESAT news. The Weyana dream is to destroy Ethiopian orthodox church and Amhara. They have been working the past 22 years but God is with us so still we are alive. The solution is to pray to God and he will give us answer soon. God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 24. ‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡››Well said D.Dani

  ReplyDelete
 25. Let God be with our fathers!
  Dani thanks

  ReplyDelete
 26. Mechachal? Manen newe yemtechelew bete christianachene. Awo, enesu altesasatum. Yemelut, seytan ena serwitun chelachu nuru newe. Yeman bete endehon erestewal, betachene ye kirstos agerache ye egizabiher habet hager nat. Eshi, Egna enechlalen, aganentun, menafekun, sedomawiyanen. Esu amalk gene ayechelem Ferdum kerbe newe. Wow to you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. መናፍቅ እና እናትህ እንዲህ ትሁን የሚሉት ስድቦችይመሳሰሉብኛል ....

   Delete
 27. ስለቤተክርቲያናችን ከዚህ የበለጠ ልንጮህ ይገባል

  ReplyDelete
 28. Yetewededachehu Wendimoche

  we all know about the situation but no one is taking any initiative at least by exposing the harassment and the killings .let us work together to help this poor fathers who sacrifice a lot in every corner of the country to protect the church,just think the one who do this harassment was our followers every blog, magazine and mass media will talk about it .the harassment started before 22 years now it reaches at peak level. it is done now by using the government hands so that we should stand together to protect our church
  In my opinion our churches main treat comes from Neo- protestants who controlled the government higher position in Southern Region ,Oromia Region , Addis Ababa , pertialy Amahara region and mainly the Fedraral Key poations

  Orthodoxians Wake up.

  ReplyDelete
 29. Nበጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

  ReplyDelete
 30. Dani ejig yemiasfera zemen!!!! Elohe elohe lama sebktannnnnnnnnnni

  ReplyDelete
 31. EGZIABHER KEGNA NEW TENKREN LEHAYMANOTACHN KOMEN BETEKRSTIYANN ENTEBK DNGL MARYAM TTEBKEN

  ReplyDelete
 32. ዲያቆን ዳንኤል ለመረጃው እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡አባቶቻችንን አምላክ ያበርታልን ዕድሜ ይስጥልን እጅ አንሰጥም የሚሉትን ያብዛልን እኛም ተራራ ከመሆን ይሰውረን አሜን

  ReplyDelete
 33. የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም

  ReplyDelete
 34. የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም

  ReplyDelete
 35. የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር በሀይማኖታችንና በሀገራች ፊቱን አያዞርም የመቤታችን አማላጅነትም አይለይም

  ReplyDelete
 36. አባቶቻችን ጳጳሳት እግዚአብሔር ይህንን ፍርሃት የሌለበት አገላለጻችሁ ይበል የሚያሰኝ የእውነተኛ እረኛ ድምጽ ነው እና በአንድነት ሆናችሁ ቤተክርስቲያንን /ሕዝቡን / አድኑ፡፡ እንከተላችኋለን እናንተ ግን በእውነት በርቱ እግዚአብሔር የክፉን ልብ ይመልስ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ ፡፡ ተመስገን በዋናው የሲኖዶስ ስብሰባስ ምን እንሰማ እናይ ይሆን? ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ነገር እንድንሰማ ድንግል በቃል ኪዳኗ ትርዳን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 37. EGZIABHER YIMELKETEN ENJI LELAMA MIN YIBALAL?

  ReplyDelete
 38. EGZIABHER YITEBIKEN ENJI LELAMA MIN YIBALAL?

  ReplyDelete
 39. ዳኔ: እግዜአብሔር እየሰማን አይመስልህም ?

  ReplyDelete
 40. እውን ጳጳሳቱ ሊመነኩሱልን ይሆን፧ ቢመሽም አልነጋም።

  ReplyDelete
 41. actually the meeting has been much more hostile than the above. Daniel might be trying a bit moderate.

  ReplyDelete
 42. The problem initiated when Ethiopia is led by protestant PM. As can be seen most EPRDF leaders are protestant, speacially when you go Zone and Wereda level. They are killers of history and anti-orthodox church

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yemiyawataw Wongeln mastemar enji amets masinesat aydelem lemehonu bepente/protestant/ lay wushetna amets ayibekam!!! yegeta mihiret yihunlachihu

   Delete
  2. D/n Yihe madalatna bEGIZIABHER zend Endayasteyikih yilikun bmastemaru bitbereta!!!!!

   Delete
  3. the repliers please come back your true church Ortodox tewahedo you are hijacked by the ancient devil, he is anti Christ please pleas don't be against JESUS and his mother St.Marry

   Delete
 43. Thanks danail God bless Ethiopia

  ReplyDelete
 44. ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤›› ብጹዕ አቡነ ማርቆስ

  ReplyDelete
 45. lets stand together! my heart is broken!!!

  ReplyDelete
 46. The silence should be broken properly. The EPDRF is aiming to destructing the church from the beginning. There should not be compromise on the church issue. Thank you fathers you have expressed our heart. We will follow you if you are leading us. አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? Best Quote from Bishop Markos of Debre Markos.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? Best Quote from Bishop Markos of Debre Markos.

   Delete
 47. next then government will attack taliban( your mehber mehiber rekusan)

  ReplyDelete
 48. የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ አምላካችን ይሄንን የአባቶቻችንን ጥብዓት ስላሳየን ይመስገን፡፡….እኛ ክርስቲያኖች ሁልግዜም ቢሆን ስለ ድኅነት ከመማርና ከማስተማር ውጪ በቡድን ተደራጅቶ የሌላን እምነት የመበረዝና የማውደም መርህ ኖሮንም አያውቅም ሊኖረንም አይችልም፡ አምላካችን ‹‹ ልትድን ትወዳለህን›› እያለ ሲያድን አሳይቶናልና፡፡ ይሄንን በሰዎች ነጻ ፈቃድ ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴያችንን ያዩ ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት እንዲይዙ የረዳቸው ይመስለኛል..አትሳቱ ጠላትህን ውደድ የተባልነው በግል ጉዳያችን ቂም የያዘብንን ወንድማችንን እንጂ በሃይማኖታችን/በአምላካችን ላይ የተነሳ ጠላታችንን አይደለም..‹‹ ለጣሊያን ብትገዛ እንኩዋን ሕዝቧ መሬቱዋ የተረገመ ይሁን ›› የሚለውን የሰመዕተ ጽድቅ የአቡነ ጴጥሮስን ግዝት ልብ ይሉዋል፡፡…‹በአምላካችሁ/ማለቴ ስታሊን › ንግግር ልዝጋ ይሆን-ያመነን ማስካድ እንጂ ዕምነት የላችሁምና..ፕሮቴስታንት(ካፒታሊዝም) እና አብታዊ ዲሞክራሲ አንድናችሁ ብዬ በማሰብ) ‹‹ ክርስቲያንና ምስማርን ሲመቱት ይጠብቃል››

  ReplyDelete
 49. Every one is complaining no one shows us or tell us what to do please brothers and sisters don’t expect from others lets us work hard and stand together everyone knows our power if we stand together, that is why they are attacking from inside and outside.
  Please write something which could unify us before we lost everything.
  To our enemies don't underestimate us we are simply silent because we are wise enough not be part of chaos and not to be part of our historical enemies strategy but if the people one day think that it is enough no one will stop us .

  ReplyDelete
  Replies
  1. "When the spider unit they can tied up the lion".Better to listen solution & do our parts.

   Delete
 50. አባቶቻችን ጳጳሳት እግዚአብሔር ይህንን ፍርሃት የሌለበት አገላለጻችሁ ይበል የሚያሰኝ የእውነተኛ እረኛ ድምጽ ነው እና በአንድነት ሆናችሁ ቤተክርስቲያንን /ሕዝቡን / አድኑ፡፡ እንከተላችኋለን እናንተ ግን በእውነት በርቱ እግዚአብሔር የክፉን ልብ ይመልስ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይታደግ ፡፡ ተመስገን በዋናው የሲኖዶስ ስብሰባስ ምን እንሰማ እናይ ይሆን? ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ነገር እንድንሰማ ድንግል በቃል ኪዳኗ ትርዳን እኛንም ተራራ ከመሆን ይሰውረን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 51. አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል?

  ReplyDelete
 52. It is a very serious warning to the government.Go buck to the country history how king Tewoders came to an end ,there was some contribution to his regime to collapse that was said because of his disagreement with the Orthodox church. It is not working ,if the gov thought this time that the followers will turn their checks to the right or left when attacked. I warn you don't, spark the fire it would not extinguish with any thing once bathed the ground. I have a bad dream if some thing not done very soon the consequence would be an measurable.It is now and timely for the gov before the coming election to count the figure other wise the 40 million Orthodox and the 35 million Muslims hands is enough to fill the bullet box to........

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you kidding? what election are you talking about? It is all fake, if it was by election 97 was the end of this government.

   Delete
 53. well said let us change this idea to well done with God!!

  thanks Dani

  ReplyDelete
 54. diakon danel betame tesmtognal, egziabhere
  yehunen new eneji lela mene yebalale

  ReplyDelete
 55. ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡

  ReplyDelete
 56. በኢትዮጵያ የሚገኙ ፕሮቴስታንት ድርጅቶች አብዛኞቹ እንደ አላማ አስቀምጠው ከሚሰሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የመንግስትን ስልጣን መዋቅር መቆጣጠር ነው ። ይህን ደግሞ የሚናገሩት በህቡዕ ሳይሆን በየአዳራሾቻቸው በሚደረጉ ስብከቶችና እንደ መስርያ ቤቶች ራዕይ ዓላማ ግብ ተብለው ተጽፈው በሚሰቀሉ ቢል ቦርዶች ላይም ጭምር ነው። ልብ በሉ ሌሎች ባለፈው ስርአት ተጎድተናልና አሁን እኛ ስልጣኑን መያዝ አለብን ብለው በተደራጀ ሁኔታ ሲንቀሳቀሱና ፕሮቴስታንት ደግሞ ሲጨመርበት ኦርቶዶክሳውያን ምን እየተሰራ እንደሆነ መረዳት አልቻልንም።

  ReplyDelete
 57. Yetewahido Lijoch Tseliyu. Bertu teberatu

  ReplyDelete
 58. ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡

  ReplyDelete
 59. "Abren endenikebir abren mekera binqebel ye kirstos werashoch nen" Rome 8+17


  ReplyDelete
 60. ‹‹ታሪክ ክፉም ሆነ በጎ እንደ ታሪክነቱ መተረክ አለበት፤ አቅራቢው ወንድማችን በ4ኛው መክዘ ክርስትና ገባ ያልከው ተሳስተሃል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8 ላይ አለ፡፡ ይህንን ዛሬ ‹ግራጁዌት አድርገው›፤ ልዑካኑ ስትመጡ ስለምትናገሩት ነገር ዕወቁ፤››
  ዳን ይህ የሀይማኖት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይም ከፌደራል ጉዳዮች የሚመጡ ሰዎች መንግስት ጥንቃቄ ሊያረግባቸው ይገባል፡፡ ታሪክን እያዛቡ ህዝብን ለማጋጨት መሞከር ለማንም አይጠቀ
  ቅምም፤፤ በአንድ ወቅት ከዚሁ መስሪያ ቤት የመጡ ግለሰብ በአንድ መስሪያ ቤት ባቀረቡት እንዲህ አይነት ትችት ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን አስታውሳለሁ፡፡
  ስለሆነም ይህን መስሪያ ቤት መንግስት ሊፈትሸው ይገባል፡፡ አለበለዚያ ነገሩ እንደተራራው ይሆንና ................ ሁሉን ቢናገሩት ንፋስ ይወስደዋል እንዳሉት አባታችን፡፡
  ዳኒ እግዚአብሔር ይጠብቅህ !

  ReplyDelete
 61. ኢትዮጵያዊ ማንነትን መማሪያ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን የሰንደቅ ዓላማ ክብር መስተዋያ ሥፍራ ይህችው ሐዋርያት ያነፅዋት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ናት። ኢትዮጵያዊ ማንነትን እና የባንዲራ ፍቅርን ከእያንዳዳችን የዛሬው ትውልድ ዜጎች ለማጥፋት ደግሞ በዋነኝነት የተነጣጠረው ይህቺኑ እናት ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት ነው። ይህ ደግሞ እያንዳንዳችንን በእጅ አዙር ከማጥፋት ዓላማ ጋር ይቆራኛል። ክቡራን ተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያን ከመጥፋታችን በፊት ራሳችንን እንከላከል።

  ReplyDelete
 62. ኢትዮጵያዊ ማንነትን መማሪያ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን የሰንደቅ ዓላማ ክብር መስተዋያ ሥፍራ ይህችው ሐዋርያት ያነፅዋት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ናት። ኢትዮጵያዊ ማንነትን እና የባንዲራ ፍቅርን ከእያንዳዳችን የዛሬው ትውልድ ዜጎች ለማጥፋት ደግሞ በዋነኝነት የተነጣጠረው ይህቺኑ እናት ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት ነው። ይህ ደግሞ እያንዳንዳችንን በእጅ አዙር ከማጥፋት ዓላማ ጋር ይቆራኛል። ክቡራን ተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያን ከመጥፋታችን በፊት ራሳችንን እንከላከል።

  ReplyDelete
 63. lets stand together! my heart is broken!!!

  ReplyDelete
 64. Egziabheir ethiopian ena hezebochwan kezihe meate yawta yedengel lemena ayleyen

  ReplyDelete
 65. ስለ ቤተ ክርስትያን በትክክል ኣዝነው ኣስተያየት የሚሰጡት በጣም ጥቂቶች ናቸው! ኣብዛኛዎቹ ኣስተያየት ሰጪዎች ቤተ ክርስትያኒቱ ኣያውቁኣትም! ከፖሎቲካዊ ኣመለካከታቸው ተነስተው ኣባቶችን መሳርያ ለማድረግ ይመስላል! ለማነኛውም ዲን ዳንኤል ለመረጃህ እናመሰግናለን! ቤተ ክርስትያናችንን ኣገራችንን ይጠብቅልን!

  ReplyDelete
 66. በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡
  Mamush, MN

  ReplyDelete
 67. ዲ ዳንኤል ሁል ግዜ እገሌ እንዲህ አለ እነ እገሌ እንዲ አሉ ነው እንጂ አንድም ቀን የራሱን አቌም በዚህ በፈተና ወቅት ለቤተ ክርቲያናች ተናግሮ አያውቅም:: እስቲ ምንድነው ያንተ አስተያየት አባቶች ባሉት ላይ? እውነት ነው ወይስ ሃስት? ለመሀል ትሆናለ? ወይም የብሎጉ ስም ክዳንኤል እይታዎች ወደ ሌላ ስም ቀይርው!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Your comment is too fanatic. I have seen his position in his writings. Even on this writing it is clear to understand his position.

   Delete
  2. so, what is his position on this writing? can u elaborate it? I don't see it at all. He is just dancing around the circle!

   Delete
  3. you, deaf cadre, better to keep quite.

   Delete
 68. Bewnet weta bilen kemehal ketema sinay betekiristiyan lay yemidersew neger ejig betam yemiyasazin new ,Egziabher ersu melkamun ken endiyametalin yetewhido lijoch be tsomina betselot lintega yegebanalina,tarik madmeti bich sayhon kabatochchin linimar yigebanal

  ReplyDelete
 69. Mechachale limeta yemichelew menegeset be hayemanot tekuwamat laye eyaderse yalewn sere yesedede telach akumo be kedeset biet kersetiyan laye eyetefetsem yalewn gefe temeleketo mefetehie mesete sichil bech new

  ReplyDelete
 70. EMEBRHAN TRDAN .... BE ETHIOPIA ENDIH YADERGUT BE AHZAB HAGER BENHON ME YADERGUN NBER......

  ReplyDelete
 71. The time is information age but we didn't hear these level discrmnation in my mother land to my families in Christ.

  We need: prayer, Information, Education, Resonances and the good fight against any injustice.

  ReplyDelete
 72. 'ጥንቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ' አለ ያገሬ ሰው። ደግሞም 'አብዮት ልጇን ትበላለች' ተብሏል በዘመነ ደርግ። ባለሥልጣናቱ ሁሉ መናፍቃን ሲሆኑ ዝም ብላችሁ/ተስማምታችሁ፣ የለም ይህ አካሔድ ለአገርም ለቤተክርስቲያንም አይበጅም እያሉ ሲወተውቱ የነበሩትን ተቃዋሚ ፖለቲከኛ እያሉ ከሚፈርጁት ጋር ስትሞዳሞዱ ኖራችሁ፣ያሁሉ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ዋልድባን ያህል ቦታ ሲደፈር ድምጽ ሳይሰማ አሁን የምን መንጫጫት ነው? እንዴ! እሺ መናፍቃኑ ባለሥልጣናት ምን ይሥሩ? ለምን ሆነና ነው ይህን ሁሉ ቦታ ከ ሀ እስከ ፐ የያዙት? ያኔ ገና ሹመት ሲታሰብ በንጉሥ ቀኝ የሚቀመጠው ተው የለም ይህ አይሆንም ማለት የነበረበት። ይደልዎ ይደልዎ ሲባል ተከርሞ አሁን የምን መንጫጫት ነው? የአሕዛቡን የመናፍቃኑን ክፍከፍ ማለትና ይህንንም ሆን ብሎ ያደረገውንና እያደረገ ያለውን ኃይል ፣ ለዚህም ከለላና መከታ ከሆትን ሁሉ ጋር አናብርም አንተባበርም ያሉትን እኮ ከሥርዓት የወጡ ከቤተክርስቲያን የተለዩ እየተባሉ እንዲወገዙ እንዲገለሉ ተደርጓል። የለም የለም ዝም ብለን መበላት ብቻ ነው። ወደ ልቦናችን ከተመለስን ደግሞ ለእውነትና ለእምነት ብቻ ሁል ጊዜም መቆም ነው። እንደቅዱሳን እስከሞት ድረስ።

  ReplyDelete
 73. ያለበለዚያ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል የተረተው ተረት መድረሱ የማይቀር ነው፡፡
  በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

  KALE HIYET YASEMALIN DIYAKON

  HULACHIN LEBETEKIRISTIYANACHIN MEKOM ALEBIN

  ReplyDelete
 74. I am an I witness. I have been working with EPRDF and its cadres for a long time. Most of them give respect to their political identity that their spiritual being. They don't know about their country's history, the peoples religious values and the reality of the people. They speak more about religious equality and tolerance. But they don't know how they make it. They don't give a damn attention to the reality that the people lived in peace and tolerance for thousands of years. But after they declared that they have come with religious equality now the people lacked to live in peace and tolerance. They want to segregate the people by his religion. They have clear hate to old and long existed big religions like Orthodox and Muslim.
  Though you tell that their policy is wrong they don't listen to you. Most of them are either atheists or fake religious identities. The people should collaboratively ignore them. Religious fathers should work towards gaining the old means of living in peace and harmony. Forget these atheists.
  God Bless Ethiopia

  ReplyDelete
 75. yegeremale eko gobeze wegeben tebeke adergo meserate new jebe kehede wesha chowe endayehone negeru .sayekatele beketele alu

  ReplyDelete
 76. ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡

  ReplyDelete
 77. የአርሲ ሀገረ ስብከት ስለ ቆሬ እና ስለ ገደብ ኣሳሳ ምን ኣሉ!!!

  ReplyDelete
 78. ብጹዕ አቡነ ቄርሎስ ወደ አውሮፓ ባለፈው የመጡ ጊዜ ከተናገሯቸው፦

  ሰው እንዲበዛ ያደረገ እግዚአብሄር እንዲረዳዳ ነው ስለዚህ ተረዳዱ፤
  ሰው እየበላ እየጠጣ ዝም ብሎ የሚኖር ከሆነ በፈቃዱ እንስሳ ሆኗል።
  በቀድሞ ጊዜ እናቶቻችን የሚያጌጡት በልብሳቸው በመስቀላቸው ፤
  ግንባራቸው ላይ ባለ መስቀል ነበር። አሁን ግን ራቊትነት ያሳዝናል አዝናለሁ ለሚመጣ ትውልድ።
  እግዚአብሄር ለአንድ ሰው ሀብት ሲሰጥ እንዲያከፋፍል ነው። የድሆችን
  የቤተክርስቲያንን ለሁሉም እንደሚገባው አከፋፋይ መሆን ማለት ነው።
  ወንደ ላጤ ወይም ሴተ ላጤ በገጠሩ የሚባለው ግመሌ ዝንጀሮ ነው
  ዝም ብሎ እየተደበቀ የሰው ክምር ያበላሻል ይበላል ፤ያጠፋል እናም
  ሁለት መንገድ ነው ያለው ወይ ማግባት ወይ መመንኮስ ከዚህ የወጣ
  የሌላ ነው። ዝም ብሎ የሚኖር ሌባ ነው ወይም በሌባ መንገድ ላይ
  ነው ያለው ሲመቸው ሊሰርቅ፦
  ስለ ጸሎት፦አምኖ መጸለይ
  በተበላሽ ስልክ ትደውላላችሁ ወይም ይደወላል አይደወልም ከታሰበው
  ቦታ መልዕክት አያደርስም ስለተበላሸ። እኛም በቂም በሀሜት በበቀል
  ሆኖ እንዴት ጸሎቱ ይድረስ የተበላሸ ስልክ ነውና አጥርቶ የማያሰማ።

  ከማስታወሻ ደብተር ቡራኬዎ ይድረሰኝ
  ከአውሮፓ

  ReplyDelete
 79. በጣልያን ጊዜ ነው አሉ፡፡ ጎንደር ላይ ጣልያን በድማሚት አንዱን ተራራ ያናውጠዋል፡፡ ተራራው ‹እድም› እያለ ይፈርሳል፡፡ አንዲት የከብት እረኛ ልጅ ፈርታ ወደ እናቷ ሄደችና ‹እማዬ ኧረ ጣልያን ተራራውን እያፈረሰው ነው›› አለቻት፡፡ እናቷም ‹‹እነ ደጃዝማች እገሌ፣ እነ ፊታውራሪ እገሌ፣ እነ ራስ እገሌ እጅ አንሰጥም ብለው እየተጋደሉ ዐለፉ፡፡ ተራራውንስ ተይው ያፍርሰው፤ እርሱም መቀመጡን አብዝቶት ነበረ፡፡›› አለቻት አሉ፡፡

  ReplyDelete
 80. ብፁአን አባቶች ለምን ዘገዩ ብየ አላማርርም፡፡ አሁንም ከምር ከእንቅልፍ የባነኑበት የንጋት ጊዜ ከሆነ ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወገግታ ይሆናል፡፡ ሆኖም ሠው ሁሉ በእንቅልፉ መካከል ብንን ብሎ የእኩለ ሌሊት ወግ አደራርሶ ተመልሶ የሚተኛበትን ዓይነት ከሆነ ያደረጉት ወደፊት ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከአሁኑ የከፋ አደገኛ ጊዜ ያጋጥማታል፡፡
  “አንች መንጋ ያለሽ መስሎሻል ተበልተሸ አልቀሻል” እንዲሉየኢትዮጵያ ቤተክርሰቲያን የተለያየ ስልታዊ ጥቃት ሲደርስባት ቆይታለች፡፡ ይህንን ዓይነት ጥቃትም ላለፎት አራት አስርተ ዓመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያለማቋረጥ ስታስተናግድ ኖራለች፡፡ እንደተሰነዘረባት ጽዖር ያልከሰመችው ጠነካራ መሰረት ላለፉት ሁለት ሽህ ዓመታት ስትገነባ በመቆየቷ ብቻ ሲሆን፤ የመሰረቱ ጥልቀት በቀላሉ ሊቆፈር ባለመቻሉ ብቻ ነው፡፡ እንደዚህማ ባይሆን ኖሮ እንዳስተናገደችው ማዕበልስ በአሁኑ ጊዜ እንደሌሎቹ እህት አብያተክርስቲያናት ትዳከም ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ከዚሁ ላይ እንዲቆም የማድረግ ስራ ካልተሰራ ውስጡ የተቦረቦ ይመስለኛል የሚል ስጋት አለኝ፡፡
  ብዙ የስውር ሴራዎች በኢትዮጵያ ቤተክርሰቲያን ላይ እንደሚቀነባበሩ ግልጽ ነው፡፡ ለምሳሌ የአገሪቱንም ሆነ የሉሉን (ግሎባላይዜሽን) ፖሊሲ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሚዛኑን ያልጠበቀ የወሊድ መቆጣጠሪያ የአጠቃቀም ጫና በገጠሩ ምእመናናችን ላይ እነማን እያደረሱብን እንዳሉ እንኳን ሲጠቀስ አልሰማም፡፡ “ዴታ” ለመሰብሰብ ብንሞክር ለዚሁ ዓላማ ማስፈጸሚያ አንዲያገለግል ተማሪ ልጆቻቸውን ወደ ጤና ነክ ትምህርት ቤቶች እንዲገቡ የሚያበረታቱት እነማን እንደሆኑ ለማወቅ እንችል ነበር! እውነት ለመናገር የእኛ ቁጥር ባለበት እየሄደ አንደሆነ ተደርጎ የሚቀርብልን ለምን ይሆን? እውነት “ፕሮቴስታንት” ሁኖ አልቆብን ነው? የፕሮቴስታንቱ የስርጭት ሚዛን ደግሞ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ሲሆን ይህም ህዝብ ከጠቅላላው ህዝብ ወደ ሃያ ከመቶ የሚሆነው ብቻ ነው፡፡ በስደት ወጥቶ አለቀ ልንል ነው? ይህም አባይን በማንኪያ ነው!
  ኢህአዴግ ገና ከጫካ እያለ ቤተክርሰቲያኗን የማዳከም ስለት እንደነበረው በሾማምንቶቹ የአደባባይ እውነት ሲሆን አድምጠናል፡፡ በፕሮግራም ደረጃ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ እራሳቸው አጋልጠዋል፡፡ ይህንንም እኩይ ተግባር ከሌላው ፕሮግራማቸው በተሻለ ደረጃ አሳክተው እንደረኩ ነግረውናል፡፡ የዚህ ውጤት ግን የእራሳቸውን ህልውና ሊፈታተን በሚችልበት ደረጃ ገዝፎ ሚዛን ወደሌላ ሲደፋ ተገንዝበውታል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ግን በአገሪቱ ውስጥ የህይወት መጠበቂያ የስነምህዳር አካል ሁኖ ተዋህዷል፡፡
  በቅዱስ ሲኖዶሱ ኮምሲዮን የቀረበው ነገር ሁሉ ከመሬት ጠብ የሚል ነገር የለውም፡፡ እውነትም ለመንፈስቅዱስ የተተወው አንድ መቀመጫ እስካሁን እንዳልተነሳ ማስረጃ ነው፡፡ የሰው አንደበት አልነበረም ሲናገር የነበረው፡፡ በእርግጥ እንደነቢየ እግዚአብሔር ድምጽ አስተጋብቷል! እንደዚያ ሊናገር የሚችል ሰው ብቻ ሳይሆን ሰው እንደምሳሌ ሁኖ እራሱ ፈጣሪ ከስንት አንድ ከሚናገራቸው የሚመደብ ነው፡፡ ይኸው እራሱ ስላለንበት ጊዜ ጠቋሚ ነው፡፡ ይህን ወሳኝ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ከብፁአን መሪዎቻችን ጥበበ እግዚአብሔር፤ ከልጆቻቸው ደግሞ ታዛዥነት ይጠበቃል፡፡
  ብጹአን አባቶቻችን በትክክል በሚመሩበት ጎዳና ላይ እንዳሉ እየተመለከትኩ ነው፡፡ እንደዙህ ስትመሩን እኛ ደግሞ እንከተላችኃለን፡፡ ስትመሩን እንኮራባችኃለን፡፡ ስትመሩን ትከበሩናላችሁ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት አመራራችሁ ላይ ጸጋ እግዚአብሔር ያጸናችኃል፡፡
  ዳንኤል ጥሩ አድርገሃል፡፡ አመሰግንሃለሁ፡፡
  ከባህር ዳር፡፡


  ReplyDelete
 81. የኣርሲው ሊቀ ጳጳስ ስለ ቆሬ እና ስለ ኣሳሳ ወርዳዎች ምን ኣሉ!

  ReplyDelete
 82. ጎበዝ እያንዳንዳችን ወደ ልባችን እንመለስማ! ንስሃዋን ገብተን እንጸልይማ ያኔ ውጤቱን እናገኘዋለን ያለበለዚያ ጉንጭ ማልፋት ነው፡፡ይህ ጋኔን ያለ ጾምና ያለ ጸሎት አይወጣምና፡፡ አባቶቻችንን ግን አምላክ ይጠብቅልን ይሄንን ትግላቸውን ይቀጥሉ በቤተ ክርስቲያኒቷ ሚዲያዎችም ድምጻቸውን ያሰሙ እኛም እንከተላለን እየተከተልንም ነው ለምን እንፈራለን?

  ReplyDelete
 83. gin eske meche new egna yeminkeberew,engda blen tekeblen ene enja

  ReplyDelete
 84. DANY IGZIABHER TSEGAWUN YABZALIH IYALKU YEMASTELALIFILIH NEGER BINOR. YANTE BLOG THE MOST TRUSTED NEWS SOURCE SILEHONE, BETECHALE METEN SEBER ZENAWOCH INA YEBETEKRSTIAN WEKTAWI MEEJAWOCHIN INDIH BEWEKTU KADERESKEN MESERETAWI LEWUT MAMTAT YICHALAL.

  ReplyDelete
 85. Egizeabehare yesteh batame nawe lamaserate yanasasale
  Anekamate pls pls pls

  ReplyDelete
 86. Ooooooooooooooo I am a big mountain

  ReplyDelete
 87. የተበደለ ሰው ይጮኻል፤ ሲጮህ ደግሞ ፖለቲካ ነው ይባላል፡፡ በእኔ እምነት ትልቁ ችግር ይሄ ነው ፡፡ መብት ይጣስና እባካችሁ ሲባል አንዳንድ ጸረ-----ሀይሎች የሚል ታርጋ ይለጠፋል፡፡ ለማንኛውም እኛም ክርስትያኖች በፀሎት እንጠንክር፡፡ እንደተራራው መቀመጥ አናብዛ፡፡

  ReplyDelete
 88. እግዚአብሔር ቤትን ካልስራ ስራተኞች በከንቱ ይደክማሉ የሚለውን ቃል በማስተዋል እንገንዘብ። እግዚአብሔር እንኻን ቤቱን ይቅርና የስውን ከተማ ይጠብቃል። የእሱ ጥበቃ የራቀን የመስለን፥ መልሱ የዘገየ የመስለን.... እኛ በንሰሀ አልቆምንም በፅሎት አልተጋንም በፆምም አልበረታንምና የእግዚአብሔር መልስ እንዴት እንስማ? " ይህ ጋኔን ያለ ጾምና ያለ ጸሎት አይወጣምና" አረ... በመጀመርያ አይነ ልቦናችን ይብራልን። እንፅልይ፥ እንስገድ፥ ንስሀም እንግባ። አለበለዚያ እንደተራራው " መቀመጡን አብዝቶት ነበረ" ተብሎ ይተረትብናል....

  ReplyDelete
 89. እኛ ግን ስለ ሃይማኖታችን እንሞታለን እንጂ ፣ ሰው ገድለን ሃይማኖታችንን ለማስፋፋት አንጥርም፡፡ “እምግባራቲሆሙ ተአምርዎሙ ፣ ከሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ” ማለትስ የኸው አይደለምን! ከመናፍቅና ከካደ ሰው መልካም ነገር አንጠብቅም፡፡ በሃይማኖታችን ሲመጡ ግን ዝም አንልም፡፡ የፌዴራላ ጉዳዮች ሚኒስቴር አካላትም ይኽንን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ በግል ፣ በመሥሪያ ቤት ስትገፉን ዝም እንዳልን እንዳይመስላችሁ ሃይማኖት የዘላለማዊ ሕይወት ጉዳይ ስለሆነ እስከ ሞት ድረስ እንታመናለንና ብታውቁ እወቁ ያለበለዚያ ግን ለቤተክርስቲያን የሚበቀልላት ፈጣሪ አምላክ በቁጣው እንድታውቁ ያደርጋችኋል፡፡እኛ ግን ስለ ሃይማኖታችን እንሞታለን እንጂ ፣ ሰው ገድለን ሃይማኖታችንን ለማስፋፋት አንጥርም፡፡ “እምግባራቲሆሙ ተአምርዎሙ ፣ ከሥራቸው ታውቋቸዋላችሁ” ማለትስ የኸው አይደለምን! ከመናፍቅና ከካደ ሰው መልካም ነገር አንጠብቅም፡፡ በሃይማኖታችን ሲመጡ ግን ዝም አንልም፡፡ የፌዴራላ ጉዳዮች ሚኒስቴር አካላትም ይኽንን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ በግል ፣ በመሥሪያ ቤት ስትገፉን ዝም እንዳልን እንዳይመስላችሁ ሃይማኖት የዘላለማዊ ሕይወት ጉዳይ ስለሆነ እስከ ሞት ድረስ እንታመናለንና ብታውቁ እወቁ ያለበለዚያ ግን ለቤተክርስቲያን የሚበቀልላት ፈጣሪ አምላክ በቁጣው እንድታውቁ ያደርጋችኋል፡፡

  ReplyDelete
 90. መቻቻል አሉ ! Who can teach what? How can moralless, valueless, and foodie people speak about how to live together and endurance. Don't they know these people are religious fathers who are teaching their children saying "for the one who hits your right face give the left and don't have sword for enemies it might be the means for your death"

  ReplyDelete
 91. Our church has been in constant war with internal enemies. False teachers (so called bahtawis), looters, heretics, and so on. And now comes the external one. Could this be the turning point from internal problem to external? The latter undermines but the former destroys. God uses all means to separate the sheep from the got. What is needed is to stand firm in both cases.

  ReplyDelete
 92. የመጀመሪያው መጨረሻ አይደለም፡፡ እንደዚህ ባለመድረክ ብቻ ሳይሆን አባቶች በሕይወታቸው ሙሉ የቤተክርስትያን አለኝታነታቸውን ሊያሳዩን ይገባል፡፡ አንድ ነገር ግን አምናለሁ ይሕች ቤተክርስትያን ትቀጥናለች እንጂ አትበጠስም ቅዱስ ዮሐንስ አፈቀርቅ እንደተናገረው፡፡ ግን ለምንስ ትቅጠን ነው ጥያቄው?
  ረድኤተ አግዚአብሔር አይለየን፡፡

  ReplyDelete
 93. Dn. Daniel, Thank you for sharing this time sensitive article. May God bless you and all your families.

  The protestants and the Muslims have been enemies in the past but now they are united to destroy our church and identity.

  Let us be one as Ethiopian Orthodox Tewahedo followers and stop dividing ourselves as an inside, outside and geleltegna Synodos. We need to wake up before it is too late.

  May our mother the Blessed Virgin Mary be with us and protect our true faith. Amen.

  ReplyDelete
 94. O my God.I am really very very disappointed.Let us pray together God to send His mercy.

  ReplyDelete
 95. kalat yatiregnal, Dany Egzieabiher yibarkih, dingil titebikih............

  ReplyDelete
 96. ሲበዛ ጨው ይመራል አለች እመየ ጎሽ አባቶችችን በርቱ

  ReplyDelete
 97. አግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ከካደና....ይጠብቃታል
  Daniel, what was the last of that congress. Would you mind to brief us about the proceedings? What was the response from the delegates of the federal affairs
  Terbu

  ReplyDelete
 98. It's very horrable. We are in denger. Tell this to our idiot government in sake of EOTC 'ATASKOTUN' as our fathers said. For all Orthdox followers this the time to stand together in praying.

  ReplyDelete
 99. አምላከ ተክለ ሃይማኖት በሃይማኖት ያኑርህ! ዳንኤል
  ለስዱ ድ ተስፋዬ ግብዣ አለኝ
  ግጥም ይወድ የለ በግጥም ልንገረው እስኪ
  በፀሐይቱ ልጀምር
  ሚኬኤለይ በአል ዱር በረካ
  ሀልወኒ አብዘለካ ሊካ
  ንሰብ እኳ ትብሎ ሀደራካ
  እሂላሎ ኮሊባሎ
  ክንድዚ ኩርሚድ አሎ
  ሀሪስካ ምብላእን ከሎ:: ብላሀለች
  ቢገባው በቴድሮስ የፍቅር ቅኝት ደግሞ እንዲህ በልልኝ
  ቢመች አመላችን ሰክኖ ቢችላቸው
  እየለሰለሰ መሬት ቢሆናቸው
  ማረሻ ሞፈሩን ተቸግረው ገጥመው
  ቀንበር ሊያበጁልን ብዙ ጊዜ ደክመው
  ሊያጣምዱን መጡ ተሸክመው
  ሳይዙ ማስጠቃት ሳይራቡ ማጥገብ
  ሳይጨብጡ መዝራት ሳያርሙ ማጨድ
  ይህም ሥራ ሆኖ ሀሜትን መፈልፈል
  እንደሸት ሰመመን ኑሮን መከፋፈል
  ሊበትኑ አሉ ሊለዩ ን በወንፊት::
  መውደዴ የትም ቢወራ ማፍቀርሽ የትም ቢወራ
  አፈኛ ቤትም አይሰራ ተንኮሉም ፍሬ አያፈራ ::
  ኢትዮጵያ በዜማ ጋብዛሀለች

  ReplyDelete
 100. leFikir endet mechachaln astemarut jal?

  ReplyDelete
 101. እነ ጆሮ ጠገብ ሊቃውንት ኧረ ተዉ ተዉ ባካችሁ ተጸጸቱ፡፡
  እስከመቼ ድረስ ነው ሙት ስትቀሰቅሱ የምትኖሩት፡፡ የቅዱሳኑን የሰማዕታቱን መቃብር የምታንኳኩት አስከመቼ ነዉ እነርሱ አኮ በጊዜአቸው መስራት የሚገባቸውን ሰርተው አልፈዋል፡፡ አርፈዋል፡፡ እናንተስ ምን ትሰሩ፡፡ አንድ አይውል ጉረኛ ወሬኛ ሁሉ፡፡ ምነዋ አሁን በእናንተ ዘመን የተላኩላችሁን ጀግኖች የሃይማኖት ገበሬዎች እነ አለቃ አያሌው ታምሩን ከዓላውያን ነገሥታት ከከሃድያን ጳጳሳት ጋር ወግናችሁ ጆሮ ደባልበስ አላላችኋቸውም እንዴ?
  የራሳችሁ አንሶ ህዝቡ እንኳ በምክራቸው እንዳይጠቀም ካህን አየደሉም ማውገዝ አይችሉም አላላችሁም አንዴ፡፡ ሲላችሁ ደግሞ ዓለም ዓቀፋዊ አመለካከት የላቸውም ጠባብ ናቸው እያላችሁ አላጣጣላችኋቸውም እንዴ እነ ጆሮ ጠገብ ሊቃውንት ምነው ሥራችሁን እያወቃችሁ አጉል ባትመጻደቁ፡፡ ይልቅስ ልባችሁን በንስሃ ቅደዱ ፡፡ ተጸጸቱ ፡፡ይቅርታ ጠይቁ ፡፡አባ አባ እያላችሁ የምታሞጋግሱአቸውን ግብዝ ጳጳሶታችሁን ጭምር ምከሯቸው፡፡ አለበለዚያ የመጣው መጥቷል በእንዲህ ያለ አለባብሶ ጉዞ የትም አይደረስም፡፡ በግድ እያንዳንድሽ ጽዋሽን ትጨልጫለሽ፡፡ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!

  የዘመናችን ሊቃውንት ይህን አስተያየት አንደማታወጡት እናውቃለን፡፡ ግን ሌላ ቦታና ግዜ ስለማናጣለት አነጨነቅም፡፡ እናንተ ግን የእግዚአብሔር ቀን ሳትደርስባችሁ ተመለሱ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!!!!!!!

  ReplyDelete
 102. ወገኖቸ ሁሉንም ትተን ሁላችንም በራችን ዘግተን ማልቀስ አለብን ስለቤተክርስቲያናችን
  እኔ የምፈራው በሃገራችን ስደተኛ እንዳንሆን ነው
  የኢትዮጵያ አምላክ ሃገራችን ይባርካት!!!!!!!

  ReplyDelete
 103. ወገኖቸ ሁሉንም ትተን ሁላችንም በራችን ዘግተን ማልቀስ አለብን ስለቤተክርስቲያናችን
  እኔ የምፈራው በሃገራችን ስደተኛ እንዳንሆን ነው
  የኢትዮጵያ አምላክ ሃገራችን ይባርካት!!!!!!!

  November 22, 2013 at 6:17 PM

  ReplyDelete
 104. ለመሆኑ ይህንን ለማለት ‹ላይሰንስ አለህ?› አባቱን የሚኮንን ልጅ ምን ያደርጋል? ነገሥታቱን ወቀሳችሁ፣ ቤተ ክርስቲያንን ነቀፋችሁ፤ ለመሆኑ ከማን ነው ይህቺን ሀገር የተረከባችሁት? ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጌታ ባረገ ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 8

  ReplyDelete
 105. Thank you diakon daniel . our father stragle together for our church EOTC. astatkun ,azmtun besgawim bemenfesawim wetatu hulun madreg yechelale enkuan weyanenena menafikanen keaganetemgare tagelo mashenfe yechelal lemen " kegnagar yalut kenersu kalute yebeltaluna "
  God protect the EOTC church from weyane ande menafikan

  ReplyDelete