Thursday, October 3, 2013

አርጤምሳውያን

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዛሬዋ ቱርክ ኢያዞሎክ፣ በጥንታዊቷ የኤፌሶን ከተማ ተገኝቶ ነበር፡፡ በዚህች ከተማ እጅግ የታወቀች፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች አማንያን የሚጎርፉላት፣ ምስሏን የሚሠሩ አንጥረኞች ብር በቁና የሚያተርፉባት አርጤምስ የምትባል ጣዖት ትመለክ ነበር፡፡ ጳውሎስ እዚህ ከተማ ገብቶ ወደ አርጤምስ ቤተ መቅደስ በመጓዝ ‹‹አርጤምስ አምላክ አይደለችም›› ብሎ አስተማረ፡፡
ይህን ሲሰሙ የአርጤምስ ወዳጆች፣ ምስሏን በመሥራት የሚያተርፉት አንጥረኞችና፣ አርጤምስን ለመሳለም ከሚመጡ አማኞች ጠቀም ያለ ትርፍ የሚያገኙ ነጋዴዎች በከተማዋ ሑከት አስነሡ፡፡ ከተማዋ ተደበላለቀች፡፡ ከየአቅጣጫው ሕዝቡ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ጎረፈ፡፡ የሐዋርያት ሥራ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹ብዙዎች ወዲያና ወዲህ እያሉ ይጮኻሉ፡፡ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ፣ የሚበልጡት ስለምን እንደተሰበሰቡ እንኳን አያውቁም ነበር፡፡››

አርጤምሳዊነት ባልተረዱት፣ ምስክርነት በማይሰጡበት፣ በማያውቁት ጉዳይ ላይ ሌሎች ስላደረጉት ብቻ፣ ወይም ደግሞ ሕዝቡ ሁሉ ሲያከናውነው ስለታየ ብቻ መደገፍ ወይም መቃወም፣ ወይም ያንኑ መሥራት ማለት ነው፡፡ የሚሰበሰቡበትን ምክንያት ሳያውቁ መሰብሰብ፣ የሚደግፉበትን ምክንያት ሳያውቁ መደገፍ፣ የሚቃወሙበትን ምክንያት ሳያውቁት መደገፍ፣ የሚወዱበት ምክንያት ሳይኖር መውደድ፣ የሚጠሉበትንም ምክንያት ሳይረዱት መጥላት ነው፡፡
ለምን? ሲባል ‹‹እኔ ከሰው እለያለሁ እንዴ›፣ ሰው ሁሉ እንዲህ እያደረገኮ ነው፣ መቼም አንድ ምክንያት አይጠፋም ብዬ፣ እነ እገሌ ሲሄዱ ሄድኩ፣ ዝም ብሎ ያስጠላኛል፣ እንዲሁ ጥሎብኝ እወደዋለሁ፤ ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ሆኖ፣ አህያ ሲጭኑ ሦስት ሆኖ ስለሚባል፣ እየተባለ ዝም ብሎ መደገፍና መቃወም ነው አርጤምሳዊነት፡፡
መመሪያ ስለሆነ፣ አድርጉ ስለተባልን፣ አሠራር ነው፣ የተለመደ ነው፣ በኛ ጊዜ አልተጀመረም፣ ድሮም የነበረ ነው፣ ምን ይደረግ ታዝዘን ነው፣ እኔ ከማን እበልጣለሁ፣ እኔ ከማን አንሣለሁ፣ ከበላይ የመጣ ነው፣ ውጡ ስለተባልን ነው፣ የሚሉ ነገሮችን የምትሰሙባቸው መሥሪያ ቤቶች ካሉ እነዚህ መሥሪያ ቤቶች በአርጤምሳውያን የሚመሩ ወይም የተሞሉ ናቸው ማለት ነው፡፡ ይፈርማሉ፤ ለምን? ማብራራት አይችሉም፤ ይሰበሰባሉ፤ ለምን ተሰበሰባችሁ? ሳትሰበሰቡ ማድረግ አትችሉም ነበር ወይ? ሲባሉ ምክንያት ያለው መልስ የላቸውም፡፡ ይውደም ይላሉ፤ ማንን እንደሆነ አያውቁትም፡፡ ይቅደም ይላሉ ማን እንደሚቀድም ግን አልወሰኑም፡፡
አንዳንዶች ጓደኞቻቸው ያደረጉት፣ የተከተሉት፣ ያወሩት፣ የወደዱት፣ የጠሉት፣ የደገፉት፣ የተቃወሙት ሁሉ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ፡፡ አመክንዮ የላቸውም፡፡ የተደረገውን ከመድገም በቀር፡፡ ከዚህም አልፈው ከራሳቸው አእምሮ ይልቅ በሰው አእምሮ ያስባሉ፡፡ ሌላውን ሰው መከተል እንጂ የት ይወስደኛል፣ ለምን አከተለዋለሁ፣ ትክክል ነው ወይ? እኔ የተሻለ ሃሳብ የለኝም ወይ? ብለው አይጠይቁም፡፡ እንዲሁ ይከተላሉ፡፡
አርጤምሳውያን ሰውን እንጂ ሃሳብን አይከተሉም፡፡ ሰውን እንጂ ሃሳብን አይቃወሙም፡፡ ለእነርሱ ቁም ነገሩ እነማን አሉበት? የሚለው እንጂ ምን ነገር አለበት? የሚለው አይደለም፡፡ አንድ ጊዜ አንድ ድልድይ ላይ ብዙ ሰዎች ተሰብስበዋል፡፡ ተሰብስበውም ወደ ድልድዩ ሥር ይመለከታሉ፡፡ እኔ ማዶ ቆሜያለሁ፡፡ ቀስ በቀስ ድልድዩ ላይ ቆመው የሚመለከቱት ሰዎች ቁጥራቸው እየበዛ መጣ፡፡ በኋላም በድልድዩ ላይ መኪና ማለፍ እስኪያቅተው ድረስ በሰው ተሞላ፡፡የምጠብቀው መኪና መጣልኝና በድልድዩ ላይ ለማለፍ ከሌሎች መኪኖች ኋላ ወረፋ ያዝን፡፡ መኪኖቹ በሕዝብ በተጣበበው ድልድይ ላይ እንደ ዔሊ እየተንፏቀቁ ነበር የሚጓዙት፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ ነገሩ ሲጀመር አካባቢ ድልድዩ ላይ ያየሁትን ሰው አገኘሁትና የመስኮቱን መስተዋት አውርጄ ‹‹ምንድን ነው ጉዳዩ?›› ብዬ ጠየቅኩት፡፡
እጁን ኪሱ ውስጥ ከትቶ ትከሻውን እያራገፈ ‹‹የሆነ ነገር ሳይገባ አይቀርም›› አለኝ፡፡
‹‹አንተ አላየኸውም›› አልኩት፡፡
‹‹አላየሁትም፤ አንዳንዶች ከብት ነው ይላሉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሰው ነው ይላሉ›› አለኝ፡፡
‹‹አንተ ምን ትላለህ›› አልኩት
‹‹እኔ እንጃ›› አለ፡፡
‹‹ይህንን ካላጣራህ ታድያ ለምን መጣህ››  አልኩት
‹‹ሰው ሲሰበሰብ ጊዜ ዝም ብዬ ነው የመጣሁት›› አለኝ፡፡
ቢያንስ ከሠላሳ ደቂቃ በላይ ቆሟል፡፡ እንዲህ ሰው ሳይጨናነቅ ነበር የመጣው፡፡ የመጣበትን ምክንያት ግን አያውቀውም፡፡ ሰው ተሰበሰበ፣ እርሱም አብሮ ተሰበሰበ፡፡ ሰው ወደ ድልድዩ ሥር ያያል፤ እርሱም ያያል፡፡ ምን እንደሚያይ ግን አያውቅም፡፡ ብቻ ያያል፡፡ አርጤምሳዊ፡፡
አርጤምሳውያን ነገሩ ሳያስቃቸው ነው የሚስቁት፡፡ የተሰበሰበው ሰው ከሳቀ ይስቃሉ፡፡ ቀልዱ ግን ላይገባቸው ይችላል፡፡ ባይገባቸውም ያጨበጭባሉ፡፡ ከዐዋቂ መካከል ከተቀመጡም ራስ ሲነቀነቅ ሲያዩ ይነቀንቃሉ፡፡ የሆነ ወረቀት ሲታደል ካገኙ ይቀበላሉ፤ ግን አያነቡትም፡፡ ማስተዋሻ ሲሰጥ ካዩ ተስገብግበው ይወስዳሉ፤ ግን አይጽፉበትም፡፡ የሆነ ምዝገባ ነገር ከተመለከቱ ወደ ሲኦል ለመሄድ ቢሆን እንኳን አያጣሩም፤ ብቻ ይመዘገባሉ፡፡ የሆነ ኮሚቴ፣ ማኅበር፣ ቡድን ሲመሠረት ዘለው ይገባሉ፤ ዓላማው፣ አሠራሩ፣ ማንነቱ አይመለከታቸውም፡፡ ዓላማቸው መቀላቀል ብቻ ነው፡፡
ኢሜይል አላቸው፣ የሚገናኙት ሰው የለም፤ ፌስ ቡክ አላቸው የሚለጥፉት ነገር የለም፡፡ ትዊተር አላቸው፣ የሚያስተላልፉት ነገር የለም፡፡ በሞባይላቸው ይቀዳሉ፣ እነርሱስ ከማን ያንሳሉ፡፡ ግን የቀዱትን አያዳምጡትም፡፡ እንዲያውም በቀጣዩ ደምስሰው ሌላ ይቀዱበታል፡፡ በሞባይል ፎቶ ያነሣሉ፤ ደግመው ግን አያዩትም፡፡ አርጤምሳውያን፡፡
አርጤምሳውያን ቤት የሚገዙት፣ መኪና የሚገዙት፣ ድርጅት የሚከፍቱት፣ ልብስ የሚገዙት፣ ውጭ የሚሄዱት፣ ርዳታ የሚረዱት፣ ድግስ የሚደግሱት፣ ሞባይል የሚቀይሩት፣ ምክንያት ስላላቸው አይደለም፡፡ እገሌ ስላደረገው፣ የዘመኑ ፋሽን ስለሆነ፣ ሰው እጅ ላይ ስላዩት፣ የሆነ ሰው ሲያወራለት ስለሰሙ ብቻ ነው፡፡  
አንድ ሰው መንገድ ዳር ቆሞ ይለምናል፡፡ ‹‹አግኝቼ ያጣሁ ነኝ›› ይላል ደጋግሞ፡፡ ከሚያልፉት መንገደኞች አንዱ ጠጋ አለውና ‹‹እውነት አንተ አግኝተህ ያጣህ ነህ?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ይለምን የነበረው ሰውም ‹አዎ›› ሲል መለሰ፡፡ መንገደኛውም ‹‹ለመሆኑ ከዶሮ ብልቶች በጣም ጣፋጩ ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ሲለምን የነበረው ሰውም ‹‹ቆዳው›› ሲል መለሰለት፡፡ መንገደኛው ሰው ‹‹እውነትም አንተ አግኝተህ ያጣህ ነህ›› ብሎ ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጠው፡፡
ከጎኑ ቆሞ ሲያይ የነበረ አንድ ሰው ቀበል አደረገና ‹‹አግኝቼ ያጣሁ›› ማለት ጀመረ፡፡ 
ሌላ መንገደኛም ጠጋ ብሎ ‹‹አግኝተህ ያጣህ ከሆንክ ከበግ ሥጋ የሚጣፍጠው ምንድን ነው›› ሲል ጠየቀው
‹‹ቆዳ›› አለ አሉ፡፡
  © ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው


39 comments:

 1. Good observation ????

  ReplyDelete
 2. አርጤምሳውያን ሰውን እንጂ ሃሳብን አይከተሉም፡፡ ሰውን እንጂ ሃሳብን አይቃወሙም፡፡ ለእነርሱ ቁም ነገሩ እነማን አሉበት? የሚለው እንጂ ምን ነገር አለበት? የሚለው አይደለም፡፡‹‹አግኝቼ ያጣሁ››

  ReplyDelete
 3. I wish such messages get prime time on radio and TV. This theme should be treated well in a wider range of medias. The tradition of 'sqilo, sqilo' like in the time of Jesus, is killing us wherever. I think it is the result of illiteracy, poverty, and unemployment.

  ReplyDelete
 4. I was expecting U to say something about the horrible incident that happened at Anbesa Gibi THAT CLAIMED A LIFE. How could a detained lion kills a person? in Addis! in this hightech era! They could even install a simple alarm that alarms the house-keeper to lock the door..... So, Daniel, it is not to let to say something about it and I am expecting YOU to post............

  ReplyDelete
  Replies
  1. Anbesaw Agessa yemilew mastaweqiya keye siga betu kaltenesa weyim anbesochu wede dur kaltelaku, enesun bezih yemiyabequ aymeslm. Sidist killo anbesa gibi anbesa lay zegten egna sigawn betrew bebsilu mekerawn sinasay ende..enesum eko anbesoch nachew. Lefegegta!

   Delete
  2. Fekadu,why every thing is fingered to Daniel? we need things to be carried out by others shoulder and want to share the benefits

   Delete
  3. Daniel why do travel to Turkey? here we are live Example for the whole of my life.

   Delete
 5. Dani it is really awesome.All of us must see ourselves in respect of your observation.I appreciate your way of expression & observation as usual.By the way you were too late to post this.Please most of us eager to read your views so please not to be late.God bless you with your beloved ones.

  ReplyDelete
 6. Yetekeberkew daniel kebret xehufehen benafkot anbbie sechress etiye duub new yalew. eniess end entnochuu ehonn?
  Berta!!!

  ReplyDelete
 7. ግን ለምን፦ እንዴት ፦ማን፦ምን የሚሉትን መጠየቅ የመረጋጋትና በራስ
  መተማመን ነው ላደለው ፦ አዕምሮ ልብ የተሰጠን እንደ እንስሳ ልንመራ
  አልነበረም። ለነገሩ እኔም ያው ነኝ

  ReplyDelete
 8. Geta becherenetu abezeto yebarkh

  ReplyDelete
 9. the new generation!!!!!
  good view!!!

  ReplyDelete
 10. Typical observation

  ReplyDelete
 11. What happen to you man, I couldn't see consistency in your articles very recently, any thing wrong? Some times just take a break and bring good things, God bless you

  ReplyDelete
 12. dani yabertalin!!!  ReplyDelete
 13. ወንድም ዳንኤል መልካም አስተያየት ነው፡፡ እግዚአብሔር ያበርታህ፡፡ ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ሆኖ፣ አህያ ሲጭኑ ሦስት ሆኖ ማለት እኮ እኔ አፈ ቀላጤ ነኝ ለሚሉ ምን እውቀት ቢበዛ፣ ቢኖር ትህትና እንዲገባ ለመምከርና አህያ ሲጭኑ አንዱ አህያውን ሲይዝ ሁለቱ በግራና በቀኝ ሚዛኑን ጠብቀው ቢጭኑ ረጅም መንገድ መጓዝ እንደሚችሉ ሁሉ ተባብሮ፣ተረዳድቶ መኖርና መስራት በሕይወታችን ማህበራዊ አኗኗር እንደ ወጥ ቅመም እንደሚያስፈልግ ለማስገንዘብ ነበር፡፡ ታዲያ ሰው ሰውነቱን ረስቶ ማስተዋልን አጥቶ እንደ እንሰሳት በሄዱበት መነዳት በተለይ በአሁኑ ዘመን የተለመደ በመሆኑ ጥሩ ባህርይና ስርዐት ያለው እንኳን ሳይቀር እኔ ብቻየን ይሄን ይዤ እንዴት እኖራለሁ ልቀላቀል ወይም ልመሳሰል እንጂ አለበለዚያ ኋላ ቀር ወይም በአራዳው ቋንቋ ፋራ እባላለሁ ወይም እሆናለሁ እየተባለ ከደጉ ነገር ሞኙን እስከመምረጥ ተደርሷልና ማስተዋሉን እግዚአብሔር ያድለን፡፡ ቅዱስ ዳዊት መዝ 31፣9 ላይ እንደተናገው በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጉሟቸው ማስተዋልም እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ የሚለውን ቃል በመመልከት በግንዛቤ የምንሰራውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡


  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 14. That is nice brother, we all need to know the reason why we are taking actions, whatsoever.

  ReplyDelete
  Replies
  1. YOU ARE ONE OF THE EAGLE EYE , WHO SEE THINGS IN DIFFERENT DIMENSION AND DEPTH

   Delete
 15. ‹ሰው ሲሰበሰብ ጊዜ ዝም ብዬ ነው የመጣሁት››

  ReplyDelete
 16. I began following your website recently. Most of issues you raise are good for anyone. I even read all of your previous blogs and they are exemplary Let God bless u.

  ReplyDelete
 17. excellent article ,keep it up.

  ReplyDelete
 18. ከምድር ዳርቻ ያለኸው ወንድማችን፤ እንደተለመደ ው መልካሙን አመላክተኸናል። ምን ይባላል ? ለኛ የምናነብበት ብቻ ሳይሆን ፤ አንበን የምንተገብርበት ልቦና እንድንሰጥ አጥብቆ መጸለይ ነው።
  ላንተም በሰላም ይመልስሕ ። ግሩም ነው፤ በርታ።

  ReplyDelete
 19. አርጤምሳውያን ነገሩ ሳያስቃቸው ነው የሚስቁት፡፡ የተሰበሰበው ሰው ከሳቀ ይስቃሉ፡፡ ቀልዱ ግን ላይገባቸው ይችላል፡፡ ባይገባቸውም ያጨበጭባሉ፡፡ ከዐዋቂ መካከል ከተቀመጡም ራስ ሲነቀነቅ ሲያዩ ይነቀንቃሉ፡፡ የሆነ ወረቀት ሲታደል ካገኙ ይቀበላሉ፤ ግን አያነቡትም፡፡ ማስተዋሻ ሲሰጥ ካዩ ተስገብግበው ይወስዳሉ፤ ግን አይጽፉበትም፡፡ የሆነ ምዝገባ ነገር ከተመለከቱ ወደ ሲኦል ለመሄድ ቢሆን እንኳን አያጣሩም፤ ብቻ ይመዘገባሉ፡፡ የሆነ ኮሚቴ፣ ማኅበር፣ ቡድን ሲመሠረት ዘለው ይገባሉ፤ ዓላማው፣ አሠራሩ፣ ማንነቱ አይመለከታቸውም፡፡ ዓላማቸው መቀላቀል ብቻ ነው፡፡
  ኢሜይል አላቸው፣ የሚገናኙት ሰው የለም፤ ፌስ ቡክ አላቸው የሚለጥፉት ነገር የለም፡፡ ትዊተር አላቸው፣ የሚያስተላልፉት ነገር የለም፡፡ በሞባይላቸው ይቀዳሉ፣ እነርሱስ ከማን ያንሳሉ፡፡ ግን የቀዱትን አያዳምጡትም፡፡ እንዲያውም በቀጣዩ ደምስሰው ሌላ ይቀዱበታል፡፡ በሞባይል ፎቶ ያነሣሉ፤ ደግመው ግን አያዩትም፡፡ አርጤምሳውያን፡፡
  ዳኒ ብዙ አርጤምሳውያንን አስታወስከኝ፤፤ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፡፡ በርታ

  ReplyDelete
 20. hahhahhhahha what a real life situation you have revealed

  ReplyDelete
 21. this is the best article for your reader, just admiring commenting and discourage any one who criticize you

  ReplyDelete
 22. This piece of write looks a bit negative ,and not specific , though I like most of your write. We as Ethiopians , have lots of specific social problems, please write about them, i expect lots of things from you, I know you have done remarkable things for the society.I want as part of young generation , I ask lots of questions, Why We are so poor? , Why we fail to feed ourselves? Why we are so lazy on school and work ( I know we have bright students ,but most of our students do not like studying ? why? ).
  Keep on writing , and God Bless You!

  ReplyDelete
 23. Thank you so much our brother and father. When I read the article I was surprising and I lerned many thing about myself. I put my self in different situation and I asked my self that " Do I lead my self or someone lead me?" Do I know why I support someone or not? and then last week I was arguing with my friend about Ethiopian muslim and the current goverment. My friend support the muslim veiw and I don't support both. As we all know that the past 19 years our church has been destroyed by muslim and the current goverment didn't take action. Now when they ask him to practice their right, the goverment tried to change their subject instead of answering their question, make them into our enemy. Our church leader support to the goverment with out knowing their view. My message is for all our church leader, please don't be " Artemesamweyan" with out knowing the issue. God bless us.

  ReplyDelete
 24. Dear Dani May GOD Bless u and ur family

  YOU ARE ONE OF THE EAGLE EYE , WHO SEE THINGS IN DIFFERENT DIMENSION AND DEPTH

  ReplyDelete
 25. ይድረስ ለዳንኤል ክብረት

  ከእለታት አንዲት ቀን በምድረ አሜሪካ እንዲህ ሆነ አሉ። ፈረንጅ እንደ ጉድ ተሰብስቦ f እንደ ጉድ ይጮኻል! ጫጫታ የለመደ ሰው ዐባይ ዳር ቅበሩኝ ይላል አለ አሉ ኦባማ! እናልህ የፈረንጆቹ ስብሰባ ማረከን። መቼስ አጠር ብለው ረዘም ያሉ ስብሰባዎችን እንደ ጉድ እንወዳለን! እናማ ስብሰባውን ተቀላቅለን ቀወጥነው። ምን እንደሚሉ ለምን እንደተሰበሰቡ የምናውቀው ነገር የለም! ለካ ስብሰባው ግብረ ሰዶም ይከበርልን የሚል ነበር!!

  በሰው አእምሮ የሚያስቡ በሰው ሳምባ የሚተነፍሱ በሰው ልብ ደም የሚያዘዋውሩ በሰው ዓይን የሚያዩ ሞልተዋል! ለነገሩ ሰው ለሰው መድኃኒት ነው። ሰው ለሰው ድራማ ላይ በአቶ አስናቀ ሳምባ የሚተነፍሱ በእሳቸው የልብ ምት የሚኖሩ ለዚህ ምስክር ናቸው። እነዚህ ሰዎች ሲራመዱ እንኳን ሰዎችን እንደ ምርኩዝ ተደግፈው ነው። "ምርኩዜ" የሚል ቅጥል ስም ብናወጣላቸው የሚያስኬድ ይመስለኛል!

  ReplyDelete
 26. መልካም እይታ ነዉ ዲ/ን ዳንኤል፡፡ “ኢሜይል አላቸው፣ የሚገናኙት ሰው የለም፤ ፌስ ቡክ አላቸው የሚለጥፉት ነገር የለም፡፡ ትዊተር አላቸው፣ የሚያስተላልፉት ነገር የለም፡፡ በሞባይላቸው ይቀዳሉ፣ እነርሱስ ከማን ያንሳሉ፡፡”

  ReplyDelete
 27. አብቾ ዘፉት ስክሬይOctober 7, 2013 at 7:36 AM

  አርጤምሳውያን ሰውን እንጂ ሃሳብን አይከተሉም፡፡ ሰውን እንጂ ሃሳብን አይቃወሙም፡፡ ለእነርሱ ቁም ነገሩ እነማን አሉበት፧ የሚለው እንጂ ምን ነገር አለበት፧ የሚለው አይደለም፡፡ ወይ ዳኒ እንደው ሳንጠግብህ ከምድር ጥጉ አገር አውስትራሊያ ሄድክብን ደስ የምትል እይታ ነች ሁል ጊዜ እራስን ሆኖ መገኘት እንዴት እድል ነው እንደው ፈጣሪ
  ሰላሙን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 28. ወደ ሲኦል ለመሄድ ቢሆን እንኳን አያጣሩም

  ReplyDelete
 29. እንዲሁ ተወልዶ እንዲሁ አድጎ እንዲሁ የሚሞት ሰው....... አርጤምሳዊ kb

  ReplyDelete
 30. Dn Daniel;
  As usual you have let us see our true nature in light of your piece of writing. Many people lack independent thinking and decision. Some people do something just because someone whom they believe is their role model do that thing. You have made us have our own rational whenever we do things.

  ReplyDelete
 31. A typical behavior of (WE) most ETHIOPIANS!

  ReplyDelete
 32. Betam astemare new Dn. Dani .

  Egziabher mastewalun yechimerilih !!!

  Dn.K.G

  ReplyDelete
 33. ይህ በጣም እውነት ነው፡፡ የ ብርሐኑ ድንቄ አልቦ ዘመድ የተሰኘ መጽሐፍ ላይ ተመሳሳይ ሃሳብ አንብቤአለው፡፡ ሰው ስለሳቀ የሚስቁ፡፡ ክፉ አመል፡፡

  ReplyDelete