Monday, October 14, 2013

ዋልያው ንሥሩን ጋለበው

‹ይህቺ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር የሚጠብቅና የሚታደግ አንዳች ኃይል አለ› የሚባለውን ነገር እንድናምን የሚያደርጉ ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ሕዝቧ ብትን፣ ቅዝቅዝ፣ ድብዝዝ ሲል ከየት እንደሚመጣ ሳይታወቅ ብቅ የሚል፣ እንደ አውሎ አጥለቅልቋት፣ እንደ እቶን አንድዷት፣ እንደ ሐረግ አስተሣስሯት፣ እንደ ደመና ከልሏት፣ እንደ አደይ አበባ አስውቧት፤ እንደ ቀስተ ደመና ቃል ኪዳኗን አድሶ፣ እንደ ጠል አረስርሶ፣ እንደ ሸማ ፍቅር አላብሶ፣ እንደ ደመራ የሀገር ፍቀር ስሜት ለኩሶ፣ እንደ ጨረቃ አድምቆ፣ እንደ ፀሐይ አሙቆ፣ እንደ ሰም አጣብቆ፣ የሚጎበኝ መንፈስ አላት፡፡
እውን ኳስ ነው ያስለቀሰን? እውን ግብ ነው የናፈቀን? እውን የጨዋታ ጥበብ ነው የጠማን? እውን ለዓለም ዋንጫ መድረሳችን ነው እንዲያ ፍቅርን እንደ ሸማ ያላበሰን? እኔ ግን ያየሁት ከዚህ ሁሉ በላይ የሆነውን ነው፡፡ አንዳች ያጣነው ነገር፣ አንዳች የጠማን ነገር፣ አንዳች የተነጠቅነው ነገር፣ አንዳች ቁጭት ውስጥ የከተተን ነገር፣ አንዳች እንደ ዋልታ የሚይዘን፣ እንደ ማገር የሚያስተሣስረን፣ እንደ ተራዳ የሚደግፈን፣ እንደ ደመራ የሚሰበስበን፣ እንደ ችቦ አንድ የሚያደርገን፣ አንዳች ነገር የጠማን ይመስለኛል፡፡

ትናንት የኳስ ደጋፊዎችን አልነበረም ያየሁት፣ የኢትዮጵያን ደጋፊዎች እንጂ፡፡ አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት ለኳሱ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ዓላማቸው ከኳስ በላይ ነበር፡፡ ፍላጎታቸው የኳስ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ብቻ አልነበረም፡፡ ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር - አምጣቷልም፡፡
ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡
የሰሜኑ ዋልያ ከወጣበት የዳሽን ተራራ ይልቅ፣ ዋልያዎቹ የወጡበት የኢትዮጵያዊነት ተራራ ይበልጥ ነበር፡፡ ከዋልያው ብርቅዬነት የዋልያዎቹ ብርቅዬነት በልጧል፤ እንዲህ አንድ አድርጎ የሚያስደስተን፣ አንድ አድርጎ የሚያስለብሰን፣ አንድ አድርጎ በቁጭት የሚያስለቅሰን አጥተን ነበር፡፡ ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡ ዋልያዎች ሆይ ክብር ይስጣችሁና ከዚያ ከፍ አድርጋችሁናል፡፡ አልተሸነፋችሁም አሸንፋችኋል፡፡ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡
ልጆቻችን አንድ፣ ከፍ ያለ፣ አድማስ ላይ ብቻ የሚታይ፣ ከሁላችንም ድምር በላይ የሆነ ሀገራዊ ስሜት እንዲሰማቸው አድርጋችኋል፡፡ በየተወሰነ ዘመን ራሱን እንደሚያድሰው የከራድዮን ወፍ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ እንደገና አደሳችሁት፡፡ በየትኛው ሕግና መመሪያ፣ በየትኛው አሠራርና ቅጣት፣ በየትኛው መዋቅርና አደረጃጀት ይህንን የሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ክብር፣ ይህን የሀገር ፍቅርና ክብር፣ ይህን የአንድነት ስሜትና መንፈስ ልናመጣው እንችል ነበር? እንኳን ኖራችሁ፡፡
እናንተ አላዘዛችሁንም፣ ግን አደረግነው፤ አልነገራችሁንም፣ ግን ፈጸምነው፤ ዐዋጅ አላወጣችሁም፣ ግን ተገበርነው፤ መዋቅር አልዘረጋችሁም፣ ግን ልባችን ውስጥ ገባችሁ፤ አልቀጣችሁም፣ ግን ታዘዝናችሁ፤ ጥሪ አላስተላለፋችሁም፣ ግን ሆ ብለን ወጣን፤ አልመዘገባችሁንም፣ ግን አባላችሁ ሆንን፤ ደወል አልደወላችሁም፣ ግን ሌሊት በስታድዮም ሰዓታት አደርን፤ አበል አልከፈላችሁንም፣ ግን ሳይደክመን ተሰለፍን፤ ወደ ከፍታው መራችሁን፣ እኛም  በደስታ ተከተልናችሁ፡፡
በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡ ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡
አሁን ስለ እናንተ ስንናገር በኩራት ነው፤ አሁን ልጆቻችን የሚጨዋወቱት በቁጭት ነው፡፡ ‹ዋልያው ንሥሩን ጋልቦታል› እንላለን፡፡ ይህንን ድሮ በ ‹ዜና እስክንድር› ብቻ ነበር የምንሰማው፡፡ እስክንድር ጠቢቡ ወደ ገነት ለመሄድ ብሎ ንሥሩን ከፈረስ ጋር አዳቅሎ ጋለበው አሉ፡፡ እናንተም እንዲሁ ንሥሩን ጋልባችሁ ወደ ልዕልናው ገነት፣ ወደ ኢትዮጵያዊነት ገነት፣ ወደ አንድነት ኤደን ወሰዳችሁን፡፡
ይህቺን ቀን እንደ አድዋ ድል፣ እንደ ዶጋሊ ድል፣ እንደ ሚያዝያ ሃያ ሰባት፣ ስናከብራት ትኖራለች፡፡ የድል ቀን ናትና፡፡ አንድነት መለያየትን፣ ኅብረ ብሔርነት ጠባብነትን፣ ኢትዮጵያዊነት ጎጠኛነትን፣ ሉዓላዊነት ተዋራጅነትን ድል ያደረጉበት ቀን ናት፡፡ 

124 comments:

 1. ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. dani you are a wonderful person the ethiopian national team will win in NIGERIA and WALIYA will be in rio 2014 good luck for our national team it is a beautiful encouragement for the whole ethiopian ppl as well as national team go waliya go

   Delete
 2. yes that is what happened we we will always remember the day

  ReplyDelete
 3. ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡
  ‹ዋልያው ንሥሩን ጋልቦታል›

  ReplyDelete
 4. እናንተም እንዲሁ ንሥሩን ጋልባችሁ ወደ ልዕልናው ገነት፣ ወደ ኢትዮጵያዊነት ገነት፣ ወደ አንድነት ኤደን ወሰዳችሁን፡፡ Dn. Daniel Egziabher yibarkeh

  ReplyDelete
 5. am still crying yes that's true

  ReplyDelete
 6. Walias play brilliant game over Eagles. Hope Walias will be tactiful and will see incredible play as well as goals on return play in Nigeria.Turn Up your head...Don't cry brother.....be happy!!

  ReplyDelete
 7. ይድረስ ለዲያቆን ዳንኤል ብሎግህን ሁሌም ተከታታይና እጅግ አድናቂም ነኝ። ይሄኛው ግን በተለይ ስሜቴን ነክቶታል ምክንያት ቢባል ኳሱ እሁድ ሊሆን አርብና ቅዳሜ ዕለት የሕዝቡ ስሜት እጅግ የሚያስደንቅ ነበርና እኔም ልክ እንዳንተ በጣም ተገርሜ ስለ ኳስ ማሰቡን ትቼ መቼ ነው እንዲህ የምንሆነው መቼ ነው በብሔርና በዘር ሳንከፋፈል አንድ ኢትዮጵያ የምንለው መቼ ነው እንዲህ የምንከባበረው እያልኩኝ እራሴን ስጠይቅ የቆየሁት እናም ብሎግህን ሳነብ ግን ከእንባዩ ጋር እየታገልኩኝ ጨረስኩት።የ እኔ ምኞት እግዚአብሔር በኛ እድሜ ይህችን የምንመኛትን ኢትዮጰያ እንዲያሳየን የምንግዜም ፀሎቴ ነው። እግዚአብሔር ሁሌም ካንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 8. yimechih dany! You have extracted the implication of the current football momentum on Ethiopianism - that is marvelous brother. But the football inspiration evaporates after the match. To get a lasting solution why dont you teach those few people who provoke others by narrating the superiority of one ethnicity over the 80+ ethnic groups in Ethiopia as that was the case in the previous regimes. If these 'unity disturbing' people get disciplined then the the largest umbrella - Ethiopianism, wont be replaced by excessive ethnic affiliation. These few individuals are the enemies of not only the 80+ ethnic groups but also Ethiopianism. Teach them because I know they listen to you.

  ReplyDelete
 9. Well said, Daniel. Walias are the engines, the jump starts of our nationalism after a long long time it has been diminished. We praise, respect, adore, them as they are history makers.

  ReplyDelete
 10. Great message!!!
  thank you

  ReplyDelete
 11. ሁሌ ስለ ሃገሬ ኢትዮጵያ ሳስብ በእንባ ነው። ይሄንን ጽሁፍ እያነበብኩ እንባዬ አልቆመም አለ። ኢትዮጲያዊነት ለኔ,,,,,,

  ReplyDelete
 12. ውድ ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል እግዚእብሔር ጸጋውን ያብዛልህ! ሰው ልብ ውስጥ ያለውን እንዲህ አሳምረህ ስትከትበው እንዴት ደስ ይላል መሰለህ

  ሰንፍራንሲስኮ

  ReplyDelete
 13. በጣም ደስ የሚል እና ልብ የሚነካ አገላለፅ ነው።

  ReplyDelete
 14. Wow betam yameral ewenete newe agerebet yalewen Becham ayedel besdet yalewenm hooooooo asbelol

  ReplyDelete
 15. 'lehulum gize alewu' so our day will come soon, still our people doesn't loss hope!!

  ReplyDelete
 16. እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ እጅግ ደስ የሚል ቀን!
  ለካ የናይጀሪያን ተጫዋቾች ለካ የካሜሩኑን ዳኛ ለካ የኢቲቪን ጋዜጠኞች ስንሰድብ ስናማርር አልዋልንም!
  ተመስገን!

  ReplyDelete
 17. በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡ ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡ ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡

   Delete
 18. Dani..you explicate the situation in a very comprehensible and lovely manner....God bless you!!!

  ReplyDelete
 19. Go to hell segregationists, you do not know Ethiopia is a great nation. Your nightmares of separating its people will going to be disappeared in few years. Your discriminatory treatments is outweighed by the people's merciful responses. At least, even if it is too late, now is high time to think on our conscience not on ethnic based calculations. You have to begin thinking of the fact that as a nation we have no future unless we forgive to each other. A wholeheartedly repentance will construct the lost identity of the nation. God bless Ethiopia and its people.

  ReplyDelete
 20. Ooooooooooo tabarake

  ReplyDelete
 21. The football fans were actually highly emotional, and I was thinking of what would happen if we win; some dire consequences, I fear, might have occurred including human lives, because the emotion was just beyond control and I think a wise and responsible movement should be followed in such kind of scenes.

  ReplyDelete
 22. ጥቂት ስለ ኢትዮጵያና የነብር ዝንጉርጉርነት ላንሳ፡፡ ታዲያ ወደ ክፉ አትቀይሩብኝ አደራ፤ዛሬ ዘር የሚቆጥር በዝቶአልና፤፡ በዘር ቆጠራ አላምንም፡፡ የራሴን ላንሳ፡፡ እኔ በአባቴም በእናቴም ከነገደ አዳምና ሄዋን የተገኘሁ ስሆን በአባቴ ሙሉ ኦሮሞ በእናቴ 75 በመቶ ኦሮሞ 25 በመቶ አማራና ጉራጌ ነው፡፡ የልጄ እናት ውዴ በአባትዋ አማራ በእናትዋ ኦሮሞ ስትሆን 1ዱ ወንድምዋ ጉራጌ አገባ፤ ሌላው ትግሬ አገባ፡፤ እህቴ የወላይታ ሰው አግብታ ልጆች ወልዳለች፡፡ እንግዲህ ከሰሜን እስከ ደቡብ ጠቀስኩ፤ ከዚህ በላይ ዝንጉርጉር ምን አለ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በኩዋስ ጊዜ ብቻ አንድ መሆን ለምን? ዘር የምትቆጥሩና ሰውን የምትለያዩ ሰዎች ወዮላችሁ ይህ የአጋንንት ሥራ ነው፡፡ ፖለቲከኞቸ ተነስተው የእገሌ ብሔር ድሮ ጥፋት ሠርቶአል እያሉ የመለያየት መርዝ ቢዘሩም እምቢ ማለት አለብን፡፡የድሮ ትውልድን ለመውቀስማ እነ ጣሊያን አሉ አይደለም? በቃ ያለፈ ታሪክ ነው፤፤ በቅን ሕሊና ወደ ፊት እንመልከት( ክፉም በጎም ሰው ለራሱ ነው);
  Ilalchi dhiphummaa fi gosummaa nu kessa bahu qaba. Namonni bu'aa siyaasaa fi dhagahamuu argachuf oduu yoo afarsan dhugaa nutti hinfakkaatin.

  ReplyDelete
 23. I was looking forward to your blog on this. It was so amazing...............God Bless you!!!

  ReplyDelete
 24. Thank you Dani for putting what we feel in nice way. God bless you more!

  ReplyDelete
 25. ኢትዬጵያዊነት በኅዝባችን ልቦና ውስጥ ተተከረሎ መቆየቱ እንዲሁም በሚናፈሰው የሊኩሊየር ዝቃጭ የተሸከመ የፖለቲካ ንፋስ አለመበከሉ እና አለመጠውለጉ እጅግ ደስ የሚል ነገር ነው ፡፡ ከትልቅ ይቅርታ ጋር … በሌላ መልኩ ይሄ ሕዝብ ግራ የሚገባኝ እብዛኛውን ማለቴ ነው በራሱ ስሜት የወጣ እና የጨፈረ ነው ማለት ይከብደኝአል…. ምክንያቱም በባለፈው ጽሁፍህ እንዳነሳኽው አርጤምሳዊ የሚበዛ ይመስለኝአል፡፡ ታስቦ ለማይሰራና በደመ-ነፍስ ለሚደረጉ ነገርች ሆ.. ማለት ስለለመድን………

  ReplyDelete
  Replies
  1. I do not think the majority of the crowed was 'artemsawi'. But I have a doubt about the crowds effort for his country on his day to day life.

   Delete
 26. ይድረስ ለዲያቆን ዳንኤል ብሎግህን ሁሌም ተከታታይና እጅግ አድናቂም ነኝ። ይሄኛው ግን በተለይ ስሜቴን ነክቶታል ምክንያት ቢባል ኳሱ እሁድ ሊሆን አርብና ቅዳሜ ዕለት የሕዝቡ ስሜት እጅግ የሚያስደንቅ ነበርና እኔም ልክ እንዳንተ በጣም ተገርሜ ስለ ኳስ ማሰቡን ትቼ መቼ ነው እንዲህ የምንሆነው መቼ ነው በብሔርና በዘር ሳንከፋፈል አንድ ኢትዮጵያ የምንለው መቼ ነው እንዲህ የምንከባበረው እያልኩኝ እራሴን ስጠይቅ የቆየሁት እናም ብሎግህን ሳነብ ግን ከእንባዩ ጋር እየታገልኩኝ ጨረስኩት።የ እኔ ምኞት እግዚአብሔር በኛ እድሜ ይህችን የምንመኛትን ኢትዮጰያ እንዲያሳየን የምንግዜም ፀሎቴ ነው። እግዚአብሔር ሁሌም ካንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 27. Tank you Dani nice view

  ReplyDelete
 28. ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡
  ‹ዋልያው ንሥሩን ጋልቦታል› TOO INSPIRATIONAL MAKES ME CRY WITHOUT KNOWING THE REASON

  ReplyDelete
 29. Thank you ...... Boss..E/r edeme yeseteh

  ReplyDelete
 30. Woy Dani!!!
  you do good always!!!! am so surprized

  ReplyDelete
 31. በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡

  ReplyDelete
 32. Winning Strategy for Wallias
  We believe this generation and Wallias will write new history. Thus, let us materialize the following.
  1. Conduct intensive Campaign by all Medias including social Medias to support Wallias in all perspectives and incentives.
  2. Let private and government organizations (here and abroad) sponsor up to 5000 fans to travel to Nigeria.
  3. Let the Football Federation arrange friendly match with renowned country.
  4. If possible technically, call Ethiopian national football players from around globe subject to their current performance and competency. At least they can be put in the Bench to energize the team.
  5. Boost Wallias Psychologically.
  a. Remember what Pepe Gardiola did to Barcelona Football club when they had to win UEFA Championship League from Man. Untd. He showed them GLADIATOR film in the eve of the game.
  b. Our Gladiator film is Ethiopian History. The defeat of Italy on the battle of Adwa, the recent history at Bademe war front and current peace keeping missions in African countries reveal our patriotism and can be considered as our Gladiator Film.
  c. We think it is good to boost Wallias by showing them some films related to the history of Ethiopian Patriotism by mobilizing the films from ETV, Individuals, etc.
  d. Let Ethiopian renowned Patriots and Heroes of the past and current (especially from the National Defense members) give lectures to Wallias for half a day before traveling to Nigeria.
  6. Not the least, mobilize all Ethiopians here and abroad to pray in their respective beliefs with unity and one heart for one cause and only one cause; i.e., for Wallias.

  Thanks

  Fan of Wallias

  ReplyDelete
 33. I have no word, Thank you Dani

  ReplyDelete
 34. D.D

  YAMERAL, DESYELAL,SEMETEN YEFETATENAL EGZIABHER YESTELEGN AMESEGENALEW

  KETEMA

  ReplyDelete
 35. D.D

  YAMERAL, DESYELAL,SEMETEN YEFETATENAL EGZIABHER YESTELEGN AMESEGENALEW

  KETEMA

  ReplyDelete
 36. በኳስ ሜዳማ ብራዚልም ይሸነፋል፤ ስፔንም ይሸነፋል፤ የኳስ ወላጅ እናቱ እንግሊዝም ትሸነፋለች፡፡ የአኩስምና የላሊበላ፣ የጀጎልና የጎንደር ግንብ ጥበብ የተሞላበት ያንን የመሰለ ኳስ፣ የጠጅ አጣጣላችን፣ የጠላ አጠማመቃችን፣ የቅመም አቀማመማችን፣ የወጥ አሠራራችን፣ የክትፎና የቆጮ፣ የገንፎና የአምባሻ ጥበባችን በእናንተ ጨዋታ ታየ፡፡ ኳስን ገረማት፡፡ እንግሊዝ አፍ ያዘች፣ ስፔንን ገረማት፣ ብራዚል ልትቀሩ ነው ብላ ቅር አላት፣ ፈረንሳይ አጀብ አለች፣ ጀርመን ተደነቀች፤ ጣልያን ተደመመች፡፡

  ReplyDelete
 37. አለቀስኩ፣ ታመምኩ፣ ደበረኝ፡፡ ግን እንደዚያ የሚያደርገኝ የነበረው ኢትዮጵያዊነት ደሜ ነው፡፡

  ReplyDelete
 38. Abo Danil betam dese yelale eninem aselekesehugn eko God bless you!

  ReplyDelete
 39. ሩፊኖሰ ዘ ኤረርOctober 16, 2013 at 11:45 AM

  . . . . . ከኳስ ጨዋታው ይልቅ ኢትዮጵያ-እናት ሀገራችን ልዩነት ጠፍቶባት ፤ አንድነት እንደ ወይን ሀረግ አስተሳስሯት ደምቃ ታይታ ነበረ .... በሁሉም የህይወታችን መንገድ ሁሌም እንዲሆን እመኛለሁ . . . . . . .... . . . . - - - - - - - - - - - - ---- -- -- - - - - - - - - - - - - - - - - ወንድማችን ዲ/ዳንኤል
  .... እንዲህ አይነት እይታዎችህ ናቸውና በናፍቆት የሚጠበቁት በርታ ብርታ በርታልን፤በርታ ብርታ በርታልንበርታ ብርታ በርታልን

  ReplyDelete
 40. thank you Dani God bless you.

  ReplyDelete
 41. yihen asteyayet yemeleyayet abate yeseytan liji woyae kayew.waaa

  ReplyDelete
 42. ይህቺን ቀን እንደ አድዋ ድል፣ እንደ ዶጋሊ ድል፣ እንደ ሚያዝያ ሃያ ሰባት፣ ስናከብራት ትኖራለች፡፡ የድል ቀን ናትና፡፡ አንድነት መለያየትን፣ ኅብረ ብሔርነት ጠባብነትን፣ ኢትዮጵያዊነት ጎጠኛነትን፣ ሉዓላዊነት ተዋራጅነትን ድል ያደረጉበት ቀን ናት፡፡

  ReplyDelete
 43. Wow,Thanks to our God we a brother like you

  ReplyDelete
 44. temsgen new yehulunem sew comment and yadereg andente ena article continue dani

  ReplyDelete
 45. betam Yamral. betam des Yelal EGZIABHER AMLAK tsgawen yabzalek

  ReplyDelete
 46. I have nothing to say Dani boy.Simply better to say amazing.I share your observation.God bless you.

  ReplyDelete
 47. ኡፈይ አንጀቴን አራስከው። እጅህ ይባረክ ብዕርህ አትንጠፍ።

  እውነትም
  "በየትኛው ሕግና መመሪያ፣ በየትኛው አሠራርና ቅጣት፣ በየትኛው መዋቅርና አደረጃጀት ይህንን የሰንደቅ ዓላማ ፍቅርና ክብር፣ ይህን የሀገር ፍቅርና ክብር፣ ይህን የአንድነት ስሜትና መንፈስ ልናመጣው እንችል ነበር? እንኳን ኖራችሁ፡፡"

  ReplyDelete
 48. እናንተ አላዘዛችሁንም፣ ግን አደረግነው፤ አልነገራችሁንም፣ ግን ፈጸምነው፤ ዐዋጅ አላወጣችሁም፣ ግን ተገበርነው፤ መዋቅር አልዘረጋችሁም፣ ግን ልባችን ውስጥ ገባችሁ፤ አልቀጣችሁም፣ ግን ታዘዝናችሁ፤ ጥሪ አላስተላለፋችሁም፣ ግን ሆ ብለን ወጣን፤ አልመዘገባችሁንም፣ ግን አባላችሁ ሆንን፤ ደወል አልደወላችሁም፣ ግን ሌሊት በስታድዮም ሰዓታት አደርን፤ አበል አልከፈላችሁንም፣ ግን ሳይደክመን ተሰለፍን፤ ወደ ከፍታው መራችሁን፣ እኛም በደስታ ተከተልናችሁ፡፡

  ReplyDelete
 49. that is all what was inside all real Ethiopians. thank you D.D

  ReplyDelete
 50. ዳኒ በእውነት የኔንም ስሜት በሚያምር ሁናቴ ስለገለጽክልኝ አመሰግንሃለሁ::

  ReplyDelete
 51. ግንቦት 20ን ምነው እንደድል ቀን ሳትጠቀሰው አለፍክ ወንድሜ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን አንተ አጽፈውም???????

   Delete
  2. ቂቂቂ… በጣም አሳቅኸኝ፡፡ አንተ ምነው ከተረፋት የድል ቀኖች ሁሉ ግንቦት 20 ብቻ ለይተህ ጠየቅህ ጃል? አይ ነገር ፍለጋ….

   Delete
  3. እያየህ እያነበብክ እንኳ ትንሽ ስቅ አይልህም የግንቦት 20ው ሰው

   Delete
  4. menawu endazi ayenate hola ker asetesaseb bentawowu

   Delete
  5. yebase atamta!!!,menew wendime kemola qen genbot 20,e/re yiqeryibelih

   Delete
  6. እባክህ ወንድም አሁንም ገና ግንቦት 20ታስባለህ እንዴትምን ታሪክ አለውና ይታሰብልህ ከጥፋት በቀር ምንም መልካም ታሪክ ስለለው በኢትዮጵያችን በታሪክ መህደሯ በጭራሽ አይገባም እንዲገባም አታስብ ገናታሪኮን ያጠፍ በግንቦት 20 ብን ብለው እደጭስ ይጠፋሉ።ስለዚህ ጊዜ ሳታጠፋ እጀህን ሁሌም ይቅርታ እናት ለሆነችው እማማ ኢተዮጵያይቅርታ ሰጠህ ጠላትህን በጋራ ተዋጋ ልብ ይሰጥህ!

   Delete
  7. Keditu wedematu sele andenet eyetewera selemeleyayet tasebaleh huuuuuuuuuuuummmm.

   Delete
 52. Thanks to God!! we have seen the past history of dignity and respected Ethiopia!!!! good Dany!!!!

  ReplyDelete
 53. What a swift mind? You are one among many millions! Edimena tena yistih avo!

  ReplyDelete
 54. great dani yegna we proud of you!! we expect much from you !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 55. እንዴት በሚጥም አማርኛ እንደገለጽከው ያነበበው ሁሉ ይረደዋል፡እግዚአብሄር ጸጋውን ያብዛልህ። ኢትዮጵያዊነት አይሞትም ፡ ኢትዮጵያዊነት የደበዘዘ እንካን ቢመስል እንደ ፍም እሳት በልባችን ውስጥ የሚቀጣጠል በመሆኑ ተዳፍኖ አይቀርም።ሁሌም ይነሳል እንደገናም የወደቀ የመስላል። ጠላቶቻችን አሁንስ አበቃ ሲሉ በሚገርምና በሚደንቅ መልኩ ኢትዮጵያዊነትን የተራራው ሰገነት ላይ ደምቆ እናየዋለን።ይህንን በልቦናችን ላኖረ አምላክ ምስጋና ይግባውና ለጊዜው የደበዘዘ የመሰለውን ኢትዮጵያዊነት እንዴት እየፈካ እንደመጣ ተመልከቱ በ እጃችን ሲገባ ዳግም እንዳይደበዝዝ አያያዛችንን እናሳምር። በዛን ጊዜ ኢትዮጵያ እጆቻን የምትዘረጋው ወደ እግዚአብሄር ይሆናል።ዳግመኛም አንወድቅም አናፍርምም አንሰደድምም በውድ ሀገራችን ላይ ኮርተን እንኖራለን።በድጋሚ ለወንድም ዲያቆን ዳን ኤል ክብረት እሱ አምላካችን አልፋ ኦሜጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋውን ያብዛልህ አሜን

  ReplyDelete
 56. I am 22 n I read all ur books n books.I know u have z power to change z perspective mind of z people by ur pen.and I beg u pls dont stop writing.zat's all I say because words can not explain my appreciation.

  ReplyDelete
 57. ይድረስ ለዲያቆን ዳንኤል ብሎግህን ሁሌም ተከታታይና እጅግ አድናቂም ነኝ። ይሄኛው ግን በተለይ ስሜቴን ነክቶታል ምክንያት ቢባል ኳሱ እሁድ ሊሆን አርብና ቅዳሜ ዕለት የሕዝቡ ስሜት እጅግ የሚያስደንቅ ነበር ......... God Bless You ..Daniel Kibert

  ReplyDelete
 58. ውድ ዲ.ዳኒ......ፈጣሪ ይይልሀ......እንዲህ የምር በስሜታዊነት እንባዬን እያፈሰስኩ ካለቀስኩ ዘመናት አለፉኝ.....ወይ ጉድ እያነበቡ ለቅ በለቅሶ...ምን ጉድ ነው ዳኒ....ምን አለ ይህ ስሜት ለዘላለም አብሮን በኖረ እያለቀስንም ቢሆን....ከውስጤ የሆነ ሸክም እንዳራገፍክልኝ አይነት ስሜት እዲሰማኝ አደረከኝ.....አቦ እንደ ዓሸን ያብዛህ....ረዥም እድሜ ይስጥልን

  ReplyDelete
 59. It is awesome! Both your writing and Walia's inspired Ethiopian unity! what an expression and what a feeling!
  I really bow for your writing and the great Ethiopian people!
  My mouth is still wide opened in appreciation.

  ReplyDelete
 60. በጣም እጀግ በጣም አመሰግናለሁ የልቤን ስለጻፍክልኝ፡፡
  የእሁድን ሁኔታ አይተው መሪዎቻችን ምን አለ አንድ
  አድርገው ቢገዙን አለበለዚያ አንድነት ሀይል ነውና
  ይህ የእሁድ ህዝብ እንቢ አንድ ነን ያለ እንደሆን
  የሚመጣውን መዘዝ ከወዲሁ ቢያስቡበት ይበጃል
  ጌታ አንድ የአደረጋትን አገር ማንም መበታተን አይችልም

  ReplyDelete
 61. ዳኔ ፤ ያለፈውን ሆነ ይሕን ጽሑፍ የተመለከቱ ፣ ሑሌም ሐቅ ነውና ያደንቁሐል፣ ያመሰግኑሐል ብየ አምናለሑ። እኔ ግን ከዜሕም በላይ ስለምወድሕና ስለማከብርሕ ፤ ከኦርቶዶክስ ሐይማኖቴ ፤ ከአገሬ ኢትዮጵያ ፤ ለዝች ላለሑባት ምድረ አሜሪካ ፤ እንዲሁም በጣም ለምወዳቸው ቤተሰቦቸ ሰጸልይ ፤ አንተንም ረስቸሕ አላውቅም። ግሩም የበተክርስቴያን ታሪክ ጸሐፌ ብቻ ሳይሆን ፤ ትልቅ የሐይማኖት አባት ትሆናለሕ ብየም ተስፋ አለኝ።የድንግል ልጅ አይለይሕ ፤ በርታ!

  ReplyDelete
 62. Brilliant Views and expressions.
  Dani, we always love you.
  Long Life!!

  ReplyDelete
 63. አንድነትን የሚጠላ የለም ነገር ግን……እንደማንኛውም ጊዜ በኛም ዘመን ነፃነት ታርክን ማፋለስ የለበትም፡፡ ታርክም የነፃነት ወጥመድ ሊሆን አይገባም፡፡ ጋብቻ፣ትስስር፣ አብሮ መኖር የራስን ዕድል ለሌላው አሳልፎ የመስጠት ግደታ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ የተፈጥሮ መብት ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው በተንኮልና በኃይል ታፍኖ ቆየ እንጂ ከተንኮል አልመነጨም፡፡ ያለውጤት የሚያስቀረውም አይኖርም፡፡ እንደሞት የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡
  ጀግኖች ለታርክ ሲሉ ይጠላሉ፣ይሰደባሉ፣ይሰደዳሉ ስበዛም ይወድቃሉ፡፡ ታርክ ግን ለዝንተ-ዓለም ወድቃ አትቀርም ፡፡ ውሸትም ለዘለዓለም አትነግስም፡፡ በዚህ ረገድ ፕረዝዳንት ኒልሰን ማንደላ አንድ ወቅት ያሉት እንደት ያለ ግሩም እውነት ነው!
  “የሁሉ ኃይማኖቶች፣ፍልስፍናዎችና የሕይወት የራሷ ገጠመኞች እንደሚያረጋገጡት ክፋት ለጊዜው የበላይነት ሊይዝ የሚችል ቢሆንም በመጨረሻ አይቀረውን ድል የሚቀዳጀው እውነት ነው”
  ያ እውነት በደቡብ አፍሪካ የበላይነቱን ተቀዳጅቷል፡፡ በአፍሪካ ቀንድም እያንዣበበ ነው፡፡ ነፍጠኞችንና አምባገነኖችን ጨንቋቸዋል፡፡ አንዴ ይህ እውነት ኢትዮጵያን ይበታትናታል፣ ለላ ጊዜ ደግሞ እነ አውቅልሃለው እና ይህ መንገድ አያወጣህም እያሉ ወድና ወዲያ ይሮጣሉ፡፡ ነገርግን የፀሐይቱን ብርሃን ጋርዶ የሚያስቀር ማነው; ሌሊቱስ እንዳይ ነጋ የሚከለክልስ ማነው;
  ከእንግዲህ ወዲህ ኦርሚያን በኃይል አፍኖ መግዛት አይቻልም፡፡ ይህ ጊዜው ያለፈበትና ያበቃ፣ያለቀለት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ሕዝባችን እስካሁን የደረሰበትን ውርደት በትግሉ በማጠብ ላይ ነው፡፡ ይህንንም ወደኃላ ለመመለስ ደፋ ቀና የሚሉ የትም አይደርሱም ሰለሆነም እውነቱን ተቀብሎ አብሮ መጓዝ ካልሆነ በስተቀር፡፡ ይህ በማንም ላይ ጦርነት ማወጅ አይደለም ፡፡ የታወጀውን ጦርነት መመከት ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. tadiya yante tsehufe kedaniel hasabe gare mine agenagnewu yen geta?

   Delete
  2. ወንድሜ ይህ ብሎግ እኮ ስለመንፈሳዊ ጉዳይ የሚያወያይ እንጂየጎሣ ፖለቲካ መድረክ አይደለም፤፤ ይህን ያንተን ሃሳብ ከኦህዴድ ካድሬዎች በየቀኑ እንሰማዋለን፤፤በጣም የሚገርመኝ የዲያቢሎስ ጥበብና ሽንገላ ነው፤፤አጅሬ ዋና ግቡ ነፍሳትን መማረክ ነው፤፤ ስለሆነም አንዳንድ የዋህ ኦሮሞዎች(አንተን የመሰሉ) ኦርቶዶክስ የነፍጠኛ ቤ/ክ ናት እያሉ ጥለው ወጥተው ስማቸውን ከህይወት መጽሐፍ ያስፋቁ አሉ፤፤ ሌሎች ደግሞ በኦሮምኛ ብቻ ወንጌል የሚሰበክበት(መነ አመንታ ለለበ ወንጌለ አፋን ኦሮሞ) መሥርተዋል፤፤ከሃይማኖትና ከዘር ቅድሚያ የምትሰጠው ለማነው? መልሱን ለራስህ፤፤ አብርሃም ከጣዖት አምላኪ ወገኑ ተለይቶ የወጣው እነ ራኬብና ሩት ህዝባቸውን ትተው ከሌላ ብሔር ጋር የኖሩትና ዘራቸውን ያስ ከበሩት ተሳስተው ሳይሆን እ/ር መርቶአቸው ነው፤፤ለምሳሌ የኔ ወላጆችባለማወቅ በወንዝ ያመልኩ ነበር፣ ልጆችን ሀመቺሳ(ማስታቀፍ) ይወስዳሉ(ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ መከራ)፤፤እኔም በአዋሽ ወንዝ ላይ በግ ሲታረድ ተካፍዬ ነበር፤፤ሰኔ12ና ህዳር 12 አዋሽ፤፤ ከዐሥሩ ትዕዛዛት አንዱ (ኢታምልክ) ተጣሰ ማለት ነው፤፤የኦሮሞ ህዝብ መጀመሪያ ክርስቲያንም እስላምም አልነበረም፤፤አሁን ነው፤፤ ሀገሬ በሰማይ ነው ለሚል ክርስቲያን ለላንጉጅ መጨነቅ ፤፤ላንጉጅ መግባቢያ ነው፣ መለያያ አይደለም፤፤የግሪክ ሰዎች ጥበብን ፣አይሁድ ምልክትን ይሻሉ፣ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ብሎኣል ቅ.ጳውሎስ፤፤

   Delete
  3. gay I think you jump the cross. min aleat gemare menafikan satihun atikerm

   Delete
 64. Ethiopiawi Ethiopiawinetun, Neber zhengurgurenetun aytewem. anelayeyem

  ReplyDelete
 65. it so sensational! keep it up Dani z great....KB

  ReplyDelete
 66. እውን ኳስ ነው ያስለቀሰን? እውን ግብ ነው የናፈቀን? እውን የጨዋታ ጥበብ ነው የጠማን? እውን ለዓለም ዋንጫ መድረሳችን ነው እንዲያ ፍቅርን እንደ ሸማ ያላበሰን? እኔ ግን ያየሁት ከዚህ ሁሉ በላይ የሆነውን ነው፡፡ አንዳች ያጣነው ነገር፣ አንዳች የጠማን ነገር፣ አንዳች የተነጠቅነው ነገር፣ አንዳች ቁጭት ውስጥ የከተተን ነገር፣ አንዳች እንደ ዋልታ የሚይዘን፣ እንደ ማገር የሚያስተሣስረን፣ እንደ ተራዳ የሚደግፈን፣ እንደ ደመራ የሚሰበስበን፣ እንደ ችቦ አንድ የሚያደርገን፣ አንዳች ነገር የጠማን ይመስለኛል፡፡

  ትናንት የኳስ ደጋፊዎችን አልነበረም ያየሁት፣ የኢትዮጵያን ደጋፊዎች እንጂ፡፡ አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት ለኳሱ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ዓላማቸው ከኳስ በላይ ነበር፡፡ ፍላጎታቸው የኳስ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ብቻ አልነበረም፡፡ ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር - አምጣቷልም፡፡
  ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡
  የሰሜኑ ዋልያ ከወጣበት የዳሽን ተራራ ይልቅ፣ ዋልያዎቹ የወጡበት የኢትዮጵያዊነት ተራራ ይበልጥ ነበር፡፡ ከዋልያው ብርቅዬነት የዋልያዎቹ ብርቅዬነት በልጧል፤ እንዲህ አንድ አድርጎ የሚያስደስተን፣ አንድ አድርጎ የሚያስለብሰን፣ አንድ አድርጎ በቁጭት የሚያስለቅሰን አጥተን ነበር፡፡ ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡ ዋልያዎች ሆይ ክብር ይስጣችሁና ከዚያ ከፍ አድርጋችሁናል፡፡ አልተሸነፋችሁም አሸንፋችኋል፡፡ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡

  ReplyDelete
 67. ትናንት የኳስ ደጋፊዎችን አልነበረም ያየሁት፣ የኢትዮጵያን ደጋፊዎች እንጂ፡፡ አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት ለኳሱ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ዓላማቸው ከኳስ በላይ ነበር፡፡ ፍላጎታቸው የኳስ ቡድኑ ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ብቻ አልነበረም፡፡ ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር - አምጣቷልም፡፡ DANI WUDU YEMAMA LIJ ENWODHALEN!

  ReplyDelete
 68. D/N Daniel God Bless you. You know Ethiopian people feeling. " ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡"

  ReplyDelete
 69. D/N Daniel God Bless you. You know Ethiopian people feeling."ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡"

  ReplyDelete
 70. ትናንት ናይጄርያ ቡድናችንን፣ እኛ ታሪካችንን አሸንፈናል፡፡"ግዜከስ

  ReplyDelete
 71. ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡ ዋልያዎች ሆይ ክብር ይስጣችሁና ከዚያ ከፍ አድርጋችሁናል፡፡ አልተሸነፋችሁም አሸንፋችኋል፡፡ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡ ልቤን ነክተኸዋል ዳኒ ምን ልበልህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 72. ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡ ዋልያዎች ሆይ ክብር ይስጣችሁና ከዚያ ከፍ አድርጋችሁናል፡፡ አልተሸነፋችሁም አሸንፋችኋል፡፡ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡

  ReplyDelete
 73. egzeabhare regime edmaena tena yesteh ewnate d.d amelak yebarkeh

  ReplyDelete
 74. ዲያቆን ዳንኤል የምትለው አልገባኝም ፡፡ ሰዎች ቡድናችንን ኢትዮጵያን ባይደግፉ የምትለውን እቀበለው ነበር፡፡ አሁን ግን የምትለው ትክከል አይደለም፡፡ ደፍተራ አስተሳሰብ ነው የተጣመመ ፡፡ ኢትዮጵያ እኮ የብሔር ብሔረሰቦች አገር ነች፡፡ የፊውዳል ውርስናህ እያሰቸገረህ ነው፡፡ ህዝብን በመጨፍለቅ አንድ አታደርገውም መብቱን ስታከብርለት እንዳየኸው አንድ ይሆናል፡፡ ጨፍልቄ አማራ አደርገዋለሁ ስትል ግን ትጨፈለቃለህ አንድነት አይኖርም፡፡ እኔ ከአንተ ጋር እኩል ሳልሆን ከአንተ ጋር ቁሜ አልደግፍም፡፡ አለምን ለምን አንድ አትሆንም፡፡ ሁሉም ለምንድን አይሆንም በአለም ያሉ ቡድኖች ለምን ኢትዮጵያ አልሆኑም፡፡ ለምን አልምን ጨፍልቀን አንድ አናደርገውም? ልዩነት እና አንድነት አታውቅም ጠባብ!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን አልምን ጨፍልቀን አንድ አናደርገውም? ልዩነት እና አንድነት አታውቅም ጠባብ!!

   Delete
 75. Thank you so much Daniel for sharing us this important discusion. Most of Ethiopian that live out side the country always the demonstrate the current goverment to bring freedom for Ethiopian people but they didn't contribute more than five percent and many Ethiopian the fight their right while they live in Ethiopian but the didn't bring any change . Even if we demonstrate everyday it is so difficult to bring freedom for our country the only way to bring human right for our country by participating election. If possible to you if you participate or other best orthodox christian people participate to get sit in "Bete Mengest" they can transfer our voice for the goverment. Right now all the goverment position sit taken by non beliver, protestant and muslim. I don't see any body that fight for our Ethiopian Orthodox Church. Please Please Please participate or motivate other Orthodox christian to participate in poltics to keep our church for the next generation. The main Weyana goel is to destroy Ethiopian Orthodox Church. That is their plan as Mr Sebat Nega express for ESAT TV last year. God bless Ethipia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ARE BAKACHUE KE TSEHUFU GARE GINEGNUNET YALEW NEGER TSAFU!
   esti temeliseh/she ande eyewut ewnete etsafekewu negere ledaniel hasbe reb alewu

   Delete
 76. You are jegna too !Dani.I read the previous post about Sewenet Bishaw and you said very well back then and now again you are here to tell us somthing special which already we have seen it !! you tell us perfectly than we saw all game ,you narrated eloquently than any one.Dani, God be with you ma men !!Peace be with you and family.

  ReplyDelete
 77. That is the beauty of sport is Dani!! to make us united State of Ethiopia.We love you Dani.

  ReplyDelete
 78. we are children of mam ethiopia.no one break this is bond for ur information look 1886(adwa)........ today2006(A.A)

  ReplyDelete
 79. ዋልያው ንሥሩን ጋልቦታል›

  ReplyDelete
 80. Thanks Dani, just felt what i missed and it was exactly what u said.

  ReplyDelete
 81. wow dani I finished reading thru crying

  ReplyDelete
 82. ደም እና በቀል ይረሳል, ታሪክ ለዘለአለም ይታወሳል;
  አብርሃም ሊንከን

  ReplyDelete
 83. gooooooooooood idea

  ReplyDelete
 84. this is great views.D/N inamesgnaln.we LOVE ETHIOPIA, OUR MAM

  ReplyDelete
 85. አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት..........ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር - አምጣቷልም፡፡እንዲህ አንድ አድርጎ የሚያስደስተን፣ አንድ አድርጎ የሚያስለብሰን፣ አንድ አድርጎ በቁጭት የሚያስለቅሰን አጥተን ነበር፡፡ ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡ልጆቻችን አንድ፣ ከፍ ያለ፣ አድማስ ላይ ብቻ የሚታይ፣ ከሁላችንም ድምር በላይ የሆነ ሀገራዊ ስሜት እንዲሰማቸው አድርጋችኋል፡፡ በየተወሰነ ዘመን ራሱን እንደሚያድሰው የከራድዮን ወፍ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ እንደገና አደሳችሁት፡፡ይህቺን ቀን እንደ አድዋ ድል፣ እንደ ዶጋሊ ድል፣ እንደ ሚያዝያ ሃያ ሰባት፣ ስናከብራት ትኖራለች፡፡ የድል ቀን ናትና፡፡ አንድነት መለያየትን፣ ኅብረ ብሔርነት ጠባብነትን፣ ኢትዮጵያዊነት ጎጠኛነትን፣ ሉዓላዊነት ተዋራጅነትን ድል ያደረጉበት ቀን ናት፡፡

  ReplyDelete
 86. ........"walyawu neserun galbotal" denek agelalets newu

  ReplyDelete
 87. አንድነቷን፣ ኅብሯን፣ ልዕልናዋን፣ ታላቅነቷን የሚደግፉ፤ መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ መጠፋፋትን፣ የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያንን ነው ያየሁት፡፡ ሰንደቋን ከንሥር በላይ ከፍ ያደረጉት፣ መዝሙሯን በባዶ ሆዳቸው ሰማይ እስኪገረም ድረስ የዘመሩት፣ ከተማዋን በአረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ያጥለቀለቁት..........ፍላጎታቸው አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ሕዝባዊነት፣ ጀግንነት፣ ኢትዮጵያዊነት ሦስት ነጥብ እንዲያመጣ ነበር - አምጣቷልም፡፡እንዲህ አንድ አድርጎ የሚያስደስተን፣ አንድ አድርጎ የሚያስለብሰን፣ አንድ አድርጎ በቁጭት የሚያስለቅሰን አጥተን ነበር፡፡ ልቅሷችን የበደል፣ ደስታችን የግላዊ ጥቅም፣ መሰባሰቢያችን ብሔረሰብ፣ መገናኛችን የወንዝ ቋንቋ፣ መነጋገሪያችን አካባቢያዊ ጉዳይ፣ ንግግራችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ሆኖብን ነበር፡፡መለያየትን፣ መከፋፈልን፣ መገፋፋትን፣ ወንዝ ለወንዝ መሄድን፣ በሰፋ ግብ አሸንፋችኋል፡፡ ባንዲራ አስለብሳችሁ፣ ለባንዲራ አስዘምራችሁ፣ ለባንዲራ አስለቅሳችሁናል፡፡ልጆቻችን አንድ፣ ከፍ ያለ፣ አድማስ ላይ ብቻ የሚታይ፣ ከሁላችንም ድምር በላይ የሆነ ሀገራዊ ስሜት እንዲሰማቸው አድርጋችኋል፡፡ በየተወሰነ ዘመን ራሱን እንደሚያድሰው የከራድዮን ወፍ የኢትዮጵያዊነትን መንፈስ እንደገና አደሳችሁት፡፡ይህቺን ቀን እንደ አድዋ ድል፣ እንደ ዶጋሊ ድል፣ እንደ ሚያዝያ ሃያ ሰባት፣ ስናከብራት ትኖራለች፡፡ የድል ቀን ናትና፡፡ አንድነት መለያየትን፣ ኅብረ ብሔርነት ጠባብነትን፣ ኢትዮጵያዊነት ጎጠኛነትን፣ ሉዓላዊነት ተዋራጅነትን ድል ያደረጉበት ቀን ናት፡፡

  ReplyDelete
 88. ዳንኤል በእውነት ነው የምልህ በእግር ኳስ ቀን የተሰማኝ ስሜት ይህን ፁሁፍ ሳነበው መልስ አገኘሁኝ፡፡ እንባየ አላቆም ብሏል በእውነት አንድነት ናፍቆኛል፡፡

  ReplyDelete
 89. የሰሜኑ ዋልያ ከወጣበት የዳሽን ተራራ ይልቅ፣ ዋልያዎቹ የወጡበት የኢትዮጵያዊነት ተራራ ይበልጥ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 90. እውን ኳስ ነው ያስለቀሰን? እውን ግብ ነው የናፈቀን? እውን የጨዋታ ጥበብ ነው የጠማን? እውን ለዓለም ዋንጫ መድረሳችን ነው እንዲያ ፍቅርን እንደ ሸማ ያላበሰን? እኔ ግን ያየሁት ከዚህ ሁሉ በላይ የሆነውን ነው፡፡

  ReplyDelete
 91. ለምን አልምን ጨፍልቀን አንድ አናደርገውም? ልዩነት እና አንድነት አታውቅም ጠባብ!!

  ReplyDelete
 92. ጤና ይስጥልኝ ዲ/ን!! በብሎግህ የምታወጣቸውን ጽሑፎች ሁሌም እየተከታተልኩ አነባቸዋለው እጅግ በጣም አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን በ ለሚነበቡት ፎቶዎች አብረው መውጣት ቢችሉ የተሻለ ይሆናል የሚል አስተያየት አለኝ!!

  ReplyDelete