Tuesday, September 24, 2013

አምፖልና ኩራዝ

ኩራዝ ከጓሮ ማድቤት ተወሽቃ ትኖር ነበር፡፡ ለብዙ ዘመናት፡፡ ድንገት ሳሎን የምግብ ጠረጲዛ ላይ ታየች፡፡ ይህ ነገር ኮርኒስ ላይ የተንጠለጠለችውን አምፖል በእጅጉ አስገረማት፡፡
‹‹ኩራዝ፣ ዛሬ ከየት ከየት ተገኘሽ፡፡ እኔኮ እንደ ዳይኖሰር ዝርያሽ የጠፋ መስሎኝ ነበር›› አለች አምፖል እየተወዛወዘች፡፡
‹‹እናንተ የተጋደመ አታስተኙ፣ የተቀበረ አታስሞቱ›› አለቻት ኩራዝ ብል ብል እያለች፡፡ በዙሪያዋ የቤቱ ባለቤቶች ከብበው እራት ይበላሉ፡፡ ከተመጋቢዎቹ አንዱ ጭል ጭል በምትለው የኩራዟ ብርሃን በእንጀራው መሐል ያለውን ወጥ ፍለጋ ጠጋ ብሎ እያየ እንዲህ አለ፡-
‹‹ዛሬ ፌስ ቡክ ላይ ያየሁትን ግጥም ልንገራችሁ››
‹‹ምን ተባለ ደግሞ፡፡ ድሮ እረኛ ምን አለ? ነበር የሚባለው፡፡ ዛሬማ ፌስ ቡክ ምን አለ ሆነኮ፡፡›› አለችው የአባ ወራው ሚስት ወጡን ያገኘው ዘንድ ኩራዙን እያስጠጋችለት፡፡

‹‹እራትና መብራት ይባል ነበር ድሮ
እራቱም መብራቱም የት አለ ዘንድሮ›› አጨበጨበችለት፡፡ አምፖሏም ግርምቷን ይበልጥ በመወዛወዝ ገለጠችው፡፡ ኩራዝም ለመጎረር አስባ ትንሽ ኃይል ጨመረች፡፡ የሰውየውን ግጥም አጣጥማ ስትመለስም አምፖሏ ‹‹የጀመርሽውንኮ አልጨረስሽልኝም፡፡ የተጋደመ አታስተኙ፣ የተቀበረ አታስሞቱ ለምን አልሽን ›› አለቻት፡፡
‹‹እንዴ አዲስ አበባ ከተማ ላይ መብራት ከገባኮ መቶ ዓመት አለፈው፡፡ እኔ፣ ጧፍና ሻማ በቃን ብለን ጡረታ ወጥተን ነበር፡፡ ሻማና ጧፍም እንግዲህ ሲያረጁ ወደበተስኪያን ነው ብለው መንኩሰው በተስኪያን ገብተው ነበር፡፡ እኔም ባይሆን ስሜ እንኳን ለታሪክ ይቀመጥ ብል ስሜን ቀየራችሁት፡፡ ስሜ ከጠፋ እኔም ተረስቻለሁ ብዬ ሞቼ ነበር፡፡ እድሜ ለመብራት ኃይል እኔን ከተቀበርኩበት መቃብር፣ ሻማና ጧፍን ከመነኮሱበት ገዳም አመጣን፡፡ መቼም እናንተ ያለውን ከማክበር ይልቅ የሞተውን መቀስቀስ ትወዳላችሁ፡፡ ቆይ ግን አንቺና ፍሬቻ ልዩነታችሁ ምንድን ነው?››
‹‹ምን ልዩነት አለን፡፡ እርሱ መኪና ላይ እኔ ኮርኒስ ላይ ከመሆናችን በቀር፡፡ ያው ሁለታችንም ቦግ እልም ነው የምንለው፡፡ ሳንጠፋ ማብራት አይሆንልንም፡፡ ድሮ እኔ ሳቀው ቦግ እልም ብልጭ ድርግም የሚሉ ሦስት ነገሮች ብቻ ነበሩ››
‹‹ምን ምን ናቸው?››
‹‹አንድ መብረቅና፤ ከነ ድምጡ ብልጭ ብሎ ድርግም ይላል፡፡ ሁለት የገና መብራት፣ የገና ዛፍ ላይ ተጠብልሎ ቦግ እልም ይላል፡፡ ሦስት የዳንስ ቤት መብራት፣ ከሙዚቃ ጋር ተዋሕዶ በሙዚቃው ድምጥ ቦግ እልም ይላል፡፡ አሁን አሁንማ ወይ እንደ መብረቅ ነጎድጓድ የለኝ፣ ወይ እንደ ገና መብራት ዛፍ ላይ አልተንጠለጠልኩ፣ ወይ እንደ ዳንስ ቤት ሙዚቃ የለኝ እንዴው ብቻዬን ቦግ እልም ስል አመሻለሁ፡፡ አገልግሎቴኮ የሰዓት መቁጠሪያ ሆነ፡፡ መጀመሪያ መብራት የጠፋ ጊዜ፣ ሁለተኛ የጠፋ ጊዜ እየተባለ ሰዓት ይቆጠርብኛል፡፡ እንዴው ግን በናንተ ዘመን ሄደ መጣየሚባል ነገር ነበር እንዴ?››
‹‹ነበረ እንጂ›› አለች ኩራዝ፡፡ ‹‹ነጋዴ ሄደ መጣ፣ ወታደር ሄደ መጣ፣ እድሜ ሄደ፣ መሬት ሄደ መጣ፡፡ ስንት የሄደና የመጣ ነገር አለ፡፡››
‹‹መብራትስ ይሄድ ነበር››
‹‹መብራት መጣ፣ መብራት ሄደ አሁን እናንተ ስትሉ ነው የምሰማው፡፡ የመሠረተ ትምህርት ማስተማሪያ ላይ እንኳን አበበ ሄደ፣ ከበደ መጣ የሚል እንጂ መብራት ሄደ መብራት መጣ የሚል አላየሁም፡፡ እኛኮ በቅብዐ ኑግም ብትይ፣ በጥጥ ዘይትም ብትይ፣ በጉሎ ዘይትም ብትይ እንሠራ ነበር፡፡ ከባሰ ደግሞ ጤፍ የምታስለቅም ጨረቃ ትወጣለች፡፡ ያለበለዚያ ምድጃ ከብበሽ እሳት ዳር መብላት መጠጣት ነው፡፡ የእናንተኮ የሚገርም ነው፡፡ ዘይት መሥራቱን ኋላ ቀርነት ብላችሁ ተዋችሁት፡፡ ምድጃ ዳር እንዳትቀመጡ ሳሎናችን ለቴሌቭዥንና ለሶፋ ብቻ ነው አላችሁ፡፡ ከሁለቱም ያጣችሁ ሆናችሁኮ፡፡ እንደ ዘንድሮ ነጋዴኮ መከራ ያየ የለም፡፡ ገቢዎች፣ ጉምሩክ፣ ንግድ ቢሮ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ያወጣሉ፡፡ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ያስነግራሉ፡፡ ገና ማስታወቂያው ሲጀምር መብራቱ እልም፡፡ ተመዝገቡ ይባል፣ ክፈሉ ይባል፣ ተሰለፉ ይባል፣ ወረፋ ያዙ ይባል፣ ጥፉ ይባል፣ ሽሹ ይባል በምን ይታወቃል፡፡ ከዚያ ትቀጫለሽ ትባያለሽ›› ‹‹ምነው›› ያልሽ እንደሆነ ማስታወቂያ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ነግረን ነበር ይሉሻል፡፡ እነርሱ መናገራቸውን እንጂ እኛ አለመስማታችንን አያዩ፡፡ ቴሌቭዥንና ሬዲዮኮ ለራሳቸው እንጂ ለሁላችን የሚሆን ጀነሬተር የላቸውም፡፡ የስንቱ ሞያ ተበላሸ በእናንተ ምክንያት፡፡ ግማሽ በስሎ ግማሽ ሳይበስል የሚወጣ እንጀራ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?››
አምፖል መልሱን ለመስማት ጓጉታ ‹‹አላውቅም›› አለች
‹‹የመብራት ኃይል እንጀራ›› ይባላል፡፡
አምፖል በሳቅ ስትፈርስ በውስጧ የነበሩት ቀጫጭን ሽቦዎች ረገፉ፡፡ ደነገጠች፡፡
‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡
‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው››
‹‹እንዴት እንዴት››
‹‹ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡››
‹‹ መቃጠሌን ያወቁብኝ እንደሆነ ግን ከዚህ ቦታ መውረዴ ነው››
‹‹ተይ እባክሽ እዚህ ሀገር አንቺ ብቻ ነሽ እንዴ ስትቃጠይ የምትወርጅው፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየፓርቲው፣ በየእምነት ተቋሙ፣ በየግል ድርጅቱ ስንት የተቃጠለ አምፖል አለ አይደለም እንዴ፡፡ ማን አወረደው፡፡ መብራት ስለሌለ ማንም ሳይለየው የሚሠራ  አምፖል መስሎ ይኖራል፡፡ አየሽ ጨለማ ለአጭበርባሪ ይመቻል፡፡ በብርሃን ግን ሁሉ ይገለጣል፡፡ እንዲህ ጨለማ የምንሆነው ኤሌክትሪክ በሀገር ጠፍቶ መሰለሽ?››
‹‹ታድያ ለምንድን ነው?››
‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡›› ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡
‹‹በይ ደኅ እደሪ፣ እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል›› አለችና ቆርቆሮዋ ውስጥ ገብታ ተኛች፡፡  
© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

85 comments:

 1. ‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡

  ReplyDelete
 2. "... ግማሽ በስሎ ግማሽ ሳይበስል የሚወጣ እንጀራ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?››
  አምፖል መልሱን ለመስማት ጓጉታ ‹‹አላውቅም›› አለች
  ‹‹የመብራት ኃይል እንጀራ›› ይባላል፡፡
  አምፖል በሳቅ ስትፈርስ በውስጧ የነበሩት ቀጫጭን ሽቦዎች ረገፉ፡፡ ደነገጠች፡፡
  ‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡
  ‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው ...››"

  Betam Des Yilal Dn. daniel. Berta

  ReplyDelete
 3. ‹‹ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡›› GBU my hero.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mulle; Why do you repeat the written words?

   Delete
  2. may be i didn't have my own words better than the above one.

   Delete
  3. so read and don't repost the same thing

   Delete
 4. ስላም ላነተ ይሁን ዳኒ…
  ህይታህን እወዳዋልሁ ዘዎትርም አነባልሁ ሆኖም በሥነ ጹሁፍ ላይ ያልህ ክህሎት ጥሩ ነው ህይታህም ድነቅ ነው ቢቻ በሃይማኖት ጉዳይ ባት ገባ ድስ ይለገኛል የሥነ መለኮት ሕወቀተ ዝቅታኛ መሆኑ ብዙዎች ትችታቸውን እያቀረቡብ ስልሆን ብትተሆ መለከም ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. yegna liki(li sadis) endet new bakih?ra'eye yohanis ante neh ende yeteregomikew

   Delete
  2. afe sikefet hode yetayal alu, that is the proof

   Delete
  3. eshi yegna eweket leki"". ye dn. danielen eweket lemelekat ante berasehe eweket linorehe yegebale enji gena legena yemanem menafeke seleteche. DANIEL ZEM AYELEM. esti wendeme berasehe chenekelate temerah yerasehen mizan asekemet kalechalek degemeo ZEM BEL.

   Delete
  4. If you write and share your idea with the public, we can compare and may conclude that Daniel is wrong. But it is Daniel who is writing and sharing his idea than you and me. As far as my knowledge is concerned, Daniel is doing good and accomplishing his responsibility than any of us.

   Delete
  5. Your comment is false about theology .

   Delete
  6. it is not scholastic argument guys. Please you (both) rather keep silent. You diverted the main article into rubbish direction.

   Delete
  7. My dear friend, I dont think D Daniel has lack of knowledge (whether theological or general). Rather he has a highly diversified and deep knowledge with a gifted insight as well as great speech skill and remarkable charisma. His problem is (I am not sure but may be), when it comes to ethnic politics. But this is supposed to vanish as one acquires more religious knowledge. And D Daniel is expected to be like that since he have vast theological knowledge. Happy Damera and Meskel for all of YOU

   Delete
  8. ቢቻ በሃይማኖት ጉዳይ ባት ገባ ድስ ይለገኛል የሥነ መለኮት ሕወቀተ ዝቅታኛ መሆኑ ብዙዎች ትችታቸውን እያቀረቡብ ስልሆን ብትተሆ መለከም ነው
   eregetegna negne anedem kene temeretun kuche beleke temere atawekem degemom anete yelekewene sayehon seweche yaluten atnagere nege degemo metsafunm akum enedemtele eregetgna negne selezi sene melekotene maneme geletso lecheresewe ayechelemena matechelewe neger wese ategeba legna gene ke dn daniel hulum yasefelegunaln aterebeshen

   Delete
  9. I am sorry you have wrong mind, I will like to say (Daniel) he is intellectual. and have broad mind about Theology Lessons. you don.t Know Daniel.

   Delete
  10. have you read some of his book both both religion and none religion, have you seen the way how to he wrote about any thing ....... any one could not criticize his brief about thought of nature of GOD and he do has well knowledge towards theology, a religious theory and system of belief because he inherited all his wisdom from early fathers ........

   Delete
  11. as far as I know orthodox never use this word <> .
   could any one else briefly discribe what i want to mean ?

   Delete
 5. ‹‹ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡››

  ReplyDelete
 6. Wow really wonderful! አንጀቴን ነዉ ቅቤ ያራስከዉ፡፡

  ReplyDelete
 7. ‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡
  ‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው›› what a view........!

  ReplyDelete
 8. ምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡

  ReplyDelete
 9. ይድረስ ለዳንኤል ክብረት!

  ጫማ የለንም ብለው የሚያጉረመርሙ እግር የሌላቸውን አይተው ይጽናኑ አሉ! መብራት ኃይላችን መብራት የለም ብለው ለሚያጉረመርሙ የዓይን ብርኃን የሌላቸውን አይተው ይጽናኑ የሚል ይመስለኛል።

  ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ ብለኸናል፡፡ ፌዴሬሽን አለ እንዴ? ባለፈው ሞቶ ለቅሶ የደረስን መስሎኝ ነበር። ስፖርት አለ ቀነኒሳ አለ ሰውነት ቢሻው አለ ቢባል ደግ ይመስለኛል።

  ክቡር ሆይ ኢትዮጲያ ወልዳ ቤተክርስቲያን ያሳደገችህ ድንቅ ሰው ነህ አሉ። አንድም በነጻ እያዝናናህ የምታስተምር ነህና ማመስገን ይገባናል!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክቡር ሆይ ኢትዮጲያ ወልዳ ቤተክርስቲያን ያሳደገችህ ድንቅ ሰው ነህ አሉ። አንድም በነጻ እያዝናናህ የምታስተምር ነህና ማመስገን ይገባናል!

   Delete
 10. ‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡›› ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡

  ReplyDelete
 11. አንጀቴን አራስከው፡፡

  ReplyDelete
 12. MELKAM NE TSUHUFU HIWOTN YISERESRAL LETEREDAWU SEWU... BERTAMELKAMNEW!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. Are maneh wedaje snemelekot ayawkim blew sitechuh esemalew yalkew/ yalshiw endew mexaf enj manbeb atawkim ende lemanignawm sitechu semto asteyayet kemestet mexahftun lemanbeb mokir ትንቢተ ዳንኤል yemilewn yediyakonun mexhaf anbib ena techiwocu degmo yabereketutn asteel keza ተቸው፡፡

  ReplyDelete
 14. I always become angry from my heart when I see some white hairs on your head. I wish you to be everlasting for Ethiopia. You are one among many millions in the current generation. Let God bless you long years of age to serve the public.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አስተያየት ሰጭ ሆይ፡- እረ ለመሆኑ ዳንኤል ዕድሜው ስንት መስሎህ ነው?

   Delete
 15. your view + good character + good .....

  ReplyDelete
 16. ‹በይ ደኅ እደሪ፣ እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል››

  ReplyDelete
 17. ‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡››

  አወ፡ ለጨለማ ብርሃን ያስፈልገዋል።

  ዲ/ን እግዚአብሄር ያበርታህ።

  ReplyDelete
 18. ወይ ዳኒ፣
  እዚህ የፌዝ ሳቅ ብቻ የሚሳቅበት አሜሪካ አንድንድ ጊዜ ከልቤ የምስቀው እናንተ ወንድሞቼና እነ ሕይዎት የሚጽፉትን መጣጥፍ ሳነብ ነው.... ዛሬስ በጣም ነው ያሳቅኽኝ....ዳኒ አሁንስ እኔም ሳልቃጠል አልቀረሁም.... ሲቃጠል አይደል ማሽላስ የሚስቀው!!!

  ReplyDelete
 19. ‹‹እናንተ የተጋደመ አታስተኙ፣ የተቀበረ አታስሞቱ››

  ‹‹እራትና መብራት ይባል ነበር ድሮ
  እራቱም መብራቱም የት አለ ዘንድሮ››

  ‹‹ለምሳሌ መብራት ኃይል ሲባል ሰምተሻል? ኃይል አለ መብራት የለም፡፡ ኔት ወርክ ሲባል ሰምተሻል? ‹ኔት› አለ ‹ወርክ› ግን የለም፡፡ ቴሌ ኮሙኒኬሽን ሲባል ሰምተሻል? ‹ቴሌ› አለ ‹ኮሙኒኬሽን› ግን የለም፡፡ የሃይማኖት ተቋም ሲባል ሰምተሻል? ‹ሃይማኖት› አለ ‹ተቋም› ግን የለም፡፡ ስፖርት ፌዴሬሽኖችን አልሰማሽም? ‹ስፖርት› የለም ‹ፌዴሬሽን› ግን አለ፡፡ የደንበኛ አገልግሎት ሲባልስ? ‹ደንበኛ› አለ፤ ‹አገልግሎት› ግን የለም፡፡ ነጻ ፕሬስ ሲባልስ? ‹ፕሬስ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ የርዳታ ድርጅት ሲባልስ? ‹ድርጅት› አለ ‹ርዳታ› ግን የለም፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲባሉስ አልሰማሽም? ‹ፓርቲ› አለ ‹ፖለቲካ› ግን የለም፡፡ ነጻ ገበያስ አታውቂም? ‹ገበያ› አለ ‹ነጻ› ግን የለም፡፡ ዴሞክራሲ ሲባልስ አልሰማሽም? ‹ዴሞ(ሕዝብ)› አለ፣‹ክራሲ(አስተዳደር)› ግን የለም፡፡ በየቢሮው በኮምፒውተር ሲስተም መሥራት ጀምረናል ሲሉ አትሰሚም አዎ ኮምፒውተር በየቢሮው አለ ‹ሲስተም›› ግን የለም፡፡ እንዲህ እያልሽ መቀጠል ነው፡፡››

  ዳኒ ምርጥ አባባሎች ................. ውሀም አለልህ መስመሩ የተዘረጋው ለውሀ ይሁን ለአየር አይታወም፡፡ ብቻ ስትከፍተው ሽሽሽ ይልሀል፡፡ ወይ ኢትዮጵያ .............

  ReplyDelete
 20. ‹‹አንቺ ሳልቃጠል አልቀርም›› አለቻት ኩራዝን፡፡
  ‹‹ምን የተቃጠለውም ያልተቃጠለውም አምፖል አንድ ነው፡፡ ሁለታችሁም አትበሩም፡፡ አይዞሽ ማንም አያውቅሽም፡፡ እዚህ ሀገር እንደሆነ የሚሠራው ከማይሠራው ጋር አብሮ ነው የሚኖረው››

  ReplyDelete
 21. Dn. Dani what can I say about you !!! Wow ! Wey Egziabher beneger hulu mastewalun seadeleh !!!

  Bertalin !!!

  ReplyDelete
 22. ግሩም የሆነ አይታ ነው:: ነገር ግን "እድሜ ለመብራት ኃይል እኔን ከተቀበርኩበት መቃብር፣ ሻማና ጧፍን ከመነኮሱበት ገዳም አመጣን"...ይህ አባባል/አገላለጥ/ ገዳምን ወደውትና ፈቅደው ሳይሆን ልክ የግዞት ቦታ ወይንም በግዳጅ የሚኖሩበት ቦታ ስለሚያስመስለው ቢታረም::

  በተረፈ በርታ

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think the phrase you pick is in Amharic we call 'miset zeybie'. Do you to this character he is not condemning the life of monastery.

   Delete
 23. Dani yih tiwuld Golmasa sihon lelijochu min indemiterik asibehewal? ine aSEBKUT? 'YELLEM' YEMILIN KAL IYECHEMERE MAWURAT NEW.

  ReplyDelete
 24. Yemeseram Ymayesram badona mulu duldumena selete yalew meleyet yaschegeral

  orke bele

  ReplyDelete
 25. This is wonderful. Satirical but very thoughtful. Thank you, dead Daniel.

  ReplyDelete
 26. ወይ ታሪክ መልሶ ማልማት ይሁን መልሶ ማጥፋት
  አናውቅም ከደናው ሰፈር ወደ አልታወቀ ሰፈር
  እንደ ሰፈራ ሊያነሱን ነው
  የሮማን ልጅ ነኝ

  ReplyDelete
 27. ያደጉ ሀገሮች በየሰፈራቸው ባቡር ሰርተው "ባቡር መጣ ባቡር ሄደ" እያሉ ልጆቻቸውን ያጫውታሉ። እኛ ደግሞ "መብራት መጣ መብራት ሄደ" እያልን ልጆቻችንን እናጫውታለን!

  ፀሐይ የተባለች እናት ልጅዋን ስትወልድ መብራቱ ድንገት ድርግም አለ! በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ብርኃን ያያልና ወንድ ልጅ ተወልዷልና ከእንግዲህ ብርኃን ይሁን ሲሉ የተወለደው ልጅም "መብራቱ" ተባለ! እናቲቱ ፀሐይ ተብላ ልጁ መብራቱ ተብሎ ብርኃን ጠፍቶ ጨለማ ሲውጠን ገረመን። ባስመዘገብነው እድገት መሰረት በጨለማ መኖራችንን እነ ለንደን ቢሰሙ በጨለማ በተዋጡ ነበር። ከፍታ ሲጨምር የሙቀት ኃይል ቅቀንሳል አሉ፤ እድገት ሲጨምር መብራት ኃይል ይቀንሳል ብዬ ተነተንኩት።

  እነሆ መብራቱ ሲወለድ ድርግም ያለችው መብራት ይኸው እስከ ዛሬ ድርግም እንዳለች ናት። በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርኃን ያያል የሚለው ትንቢት መቼ ይሆን የሚፈጸመው? እያልን ይኸው በተስፋ አለን። መብራቱ መጣ በተባለ ቁጥር ማን እንደመጣ በውል አይታወቅምና የሰፈሩ ሰው ግራ ይጋባል አሉ። አቶ መብራቱ "መብራቱ" በተባለ ቁጥር ስቅ ይላቸዋል አሉ።

  አቶ መብራቱን የመብራት ኃይል ኃላፊ ብናደርጋቸው ለኛ ባያስቡ አስሬ መብራቱ እያልን ስቅ እንዳይላቸው ሲሉ በብርኃን ሳያኖሩን አይቀርም!

  አበባዮሽ ለምለም /፪/

  መብራት አለ ወይ? የለም
  ውኃ አለ ወይ? የለም
  መንገድ አለ ወይ? የለም
  ኔትወርክ አለ ወይ? የለም
  አዳዬ ሁሉም የለም ወይ እንበል ዋይ ዋይ /2/


  ከብረው ይቆዩ ከብረው
  አቶ መብራቱን ወልደi
  ብርኃን ለኛ ሰጥተው
  ከብረው ይቆዩ ከብረው /፪/


  ይሸታል ዶሮ/፪/ የእማሚዬ ጓሮ
  ይታያል ብርኃኑ /፪/ ከፀሐይ ቤት ግቡ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wow very impressive poem

   Delete
  2. እንዲያ በል!

   Delete
  3. አበባዮሽ ለምለም /፪/

   መብራት አለ ወይ? የለም
   ውኃ አለ ወይ? የለም
   መንገድ አለ ወይ? የለም
   ኔትወርክ አለ ወይ? የለም
   አዳዬ ሁሉም የለም ወይ እንበል ዋይ ዋይ /2/


   ከብረው ይቆዩ ከብረው
   አቶ መብራቱን ወልደi
   ብርኃን ለኛ ሰጥተው
   ከብረው ይቆዩ ከብረው /፪/


   ይሸታል ዶሮ/፪/ የእማሚዬ ጓሮ
   ይታያል ብርኃኑ /፪/ ከፀሐይ ቤት ግቡ

   Delete
 28. Dear brother Dn. Daniel, I had an opportunity to learn from you about Bible Study, Biblical Geography,... in AAU Sunday School Program in 1990 E.C ( 1997/98 G.C). I was always mesmerized by your deep theological and historical knowledge. More importantly, your effective delivery of what you know in a simple day today life analogy [Am sure your knowledge of pedagogy as a teacher has an impact on it; I presume]. Ever since I came across to know you through your teachings, I am your top admirer. Thank you for giving back to the Mother Church and the Nation as a whole. To this very day, I learn a lot from you via different media that you deliver: Youtube videos, your website, books, articles and interviews. You are one of the Best & Chosen Scholars, Ethiopian Orthodox Tewahido Church has produced. May God Bless you and your family abundantly to serve more and more.

  ReplyDelete
 29. Eysakum eyazenkum anebebikut ayee emama ethiopia Tinsayeshin ayrikew CHERU MEDEHANIALEM

  Danii bierih ayntef edime ke tena gar yestih AMILAKACHIN

  ReplyDelete
 30. ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን
  ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡

  ReplyDelete
 31. ዳኔ፤ የድንግል ልጅ ከሔድክበት በሰላም ይመልስሕ።እንደተለመደው ግሩም ጽሑፍ።በርታ ! መልካም የመስቀል በዓል ባለሕበት።

  ReplyDelete
 32. ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡›› ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡

  ReplyDelete
 33. May God Bless you and your family abundantly to serve more and more.

  ReplyDelete
 34. Dani Dani Dani Dani ይመችህ ብሉአል አስናቀ

  ReplyDelete
 35. I always love and enjoy reading your articles. This one is special as usual. May God bless you and your work!

  ReplyDelete
 36. ለሚገባው እንደዚህ በፈሊጥ......
  ለማይገባው ደግሞ?????????????

  ReplyDelete
 37. ‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡
  አንድም ብርሃን ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ እውነት ነው፡፡ እውነተኛነትም ከክርስቶስ ይወጣል፡፡ እውነተኛነት በሌለበት ሁሉ አጭበርባሪነት ትበረታለች፡፡ እውነት በአጭበርባሪነት ላይ ክርኗ ይደቁሳል፡፡ ክርስቶስ በበጎቹ ይወከላል፡፡ በግ ንጹህ ሕዝብ፣ ምስኪን ሕዝብ ነው፡፡ ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ እንዲል፡፡ በጎቹም የብርሃኑ ተካፋዮች ናቸው፡፡ በጎቹ ያበራሉ፡፡ በጎቹ ካሉ ለማጭበርበር አያመችም፡፡ በጎቹ እየተመናመኑ ከሄዱ ግን አጭበርባሪነት ትታበያለች፡፡
  በጎቹ አለቁ ፍየሎቹ በዝተው፣
  ወራጅ ወጭ ሆነ ከላይ ከተራራው፡፡ እንዲል፡፡
  በጎች ተኩላ ፍራ ይላቸዋል፡፡ አንድም ተኩላ በግ መስሎ በግን አክሎ ስለሚያጠቃ፡፡ ተኩላ ጨለማን ተገን አድርጎ ስለሚንቀሳቀስ፡፡ ብርሃንንም ጥፋት የሸመቀ እንደሚታናኮላት ሁሉ፡፡ አንድም በጎችን ለማጭበርበር - በጎችን ለመበዝበዝ - በጎችን ለመቦጥቦጥ - በግን አክለው - በግን መስለው - ለበግ ታጋይነን እያሉ - በበግ ስም እየተደራጁ - በበጉ ለመጠቀም የበጎች ታጋዮች ብርሃን ስለማይፈልጉ ነው፡፡ ትንሽ የብረሃን ጭላንጭል ቀርታለች፡፡ እርሷም እንኳን የማጋለጥ የመገዳደር አቅም እንዳላት ስለሚያውቁ፤ እርሷንም ለማክሰም ይጥራሉ፡፡

  ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡
  ብርሃን አዳሽ ነው፡፡ ብርሃን አድማቂ ነው፡፡ ብርሃን ሲበረታ በመዳከም ላይ የነበረው ያንሰራራል፡፡ ብርሃን ሲረጭ የደበዘዘ ውበት ይደምቃል፡፡ አምፖል ሕዝብ ነው፡፡ የተቃጠሉ አምፖሎች አንድም የተጨቆኑ ሕዝቦች ናቸው፡፡ የተቃጠሉ አምፖሎች አንድም ቅንነትን የሸጡ ሕዝብን የማይወክሉ የሕዝብ ልጆች ናቸው፡፡ ብርሃኑ ሲደምቅ የተበላሸ የሕዝብ ቅንነት መልሶ ለሕዝብ እንደሚጠቅም ይሆናል፡፡ ብርሃን ሲበረታ በጭቆና ብዛት እየተዳከመ ያለው ሕዝብ ያንሰራራል፡፡

  ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡››
  ሆዴ ባክህ ቻለው፣ ሁሉን አትጨርሰው፤
  ሞኝ ትባለለህ ባዶ ካሳደርከው፡፡

  ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡
  አንድም ሕዝብ ጉልበት ላይኖረው ይችላል እንጅ ግርምት እንደማያጣ ሁሉ፡፡ ጉልበት ያለው ደግሞ ግርምትንም ሳይቀር እንደሚጨፈልቅ ሁሉ፡፡

  ‹‹በይ ደኅና እደሪ፣ እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል››
  አንድም እንደልባችሁ ተናገሩ እንደልባችሁ ውደዱን እንደልባችሁ ጥሉን እንዲሉ፡፡ እንደተፈቀደው እንደልብ መውደድንና መጥላትን ተከትሎ የሚመጣው ክፉ አጸፋ፡፡ እንደልብ ከተናገሩ በኃላ የሚመጣው መጥፎ አጸፋ፡፡ ዛቻው፡፡ ኩርኩሞ፡፡ ተጽእኖው፡፡
  አለችና ቆርቆሮዋ ውስጥ ገብታ ተኛች፡፡ ሕዝብ ትንጫጫለች እንጅ የማታ ማታ ማደሪያዋ ቤቷ፡፡ መክረሚያዋ ዘብጥያ፡፡

  የጣና ዳር ትርጓሜ

  ReplyDelete
 38. እኛኮ በቅብዐ ኑግም ብትይ፣ በጥጥ ዘይትም ብትይ፣ በጉሎ ዘይትም ብትይ እንሠራ ነበር፡፡ ከባሰ ደግሞ ጤፍ የምታስለቅም ጨረቃ ትወጣለች፡፡ ያለበለዚያ ምድጃ ከብበሽ እሳት ዳር መብላት መጠጣት ነው፡፡ የእናንተኮ የሚገርም ነው፡፡ ዘይት መሥራቱን ኋላ ቀርነት ብላችሁ ተዋችሁት፡፡ ምድጃ ዳር እንዳትቀመጡ ሳሎናችን ለቴሌቭዥንና ለሶፋ ብቻ ነው አላችሁ፡፡ ከሁለቱም ያጣችሁ ሆናችሁኮ፡፡ እንደ ዘንድሮ ነጋዴኮ መከራ ያየ የለም፡፡ ገቢዎች፣ ጉምሩክ፣ ንግድ ቢሮ፣ ቀበሌ፣ ክፍለ ከተማ ማስታወቂያ ያወጣሉ፡፡ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ያስነግራሉ፡፡ ገና ማስታወቂያው ሲጀምር መብራቱ እልም፡፡ ተመዝገቡ ይባል፣ ክፈሉ ይባል፣ ተሰለፉ ይባል፣ ወረፋ ያዙ ይባል፣ ጥፉ ይባል፣ ሽሹ ይባል በምን ይታወቃል፡፡ ከዚያ ትቀጫለሽ ትባያለሽ›› ‹‹ምነው›› ያልሽ እንደሆነ ማስታወቂያ በቴሌቭዥንና በሬዲዮ ነግረን ነበር ይሉሻል፡፡ እነርሱ መናገራቸውን እንጂ እኛ አለመስማታችንን አያዩ፡፡ ቴሌቭዥንና ሬዲዮኮ ለራሳቸው እንጂ ለሁላችን የሚሆን ጀነሬተር የላቸውም፡፡ የስንቱ ሞያ ተበላሸ በእናንተ ምክንያት፡፡ ግማሽ በስሎ ግማሽ ሳይበስል የሚወጣ እንጀራ ምን እንደሚባል ታውቂያለሽ?››kkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 39. ግሩም አገላለጽ ነው:: ግን መቼ ይሆን ከዚህ ሁሉ ችግር የምንላቀቀው?

  ReplyDelete
 40. dani god bless you don't be discourage by some nonsense comment

  ReplyDelete
 41. የሚገርም እይታ ነው ዳኔ እያሣቀ የሚያሥተምር ነው። የድሮ ትዝታየን አመጣእብኝ የፍንጨዋ መብራት ኃይል ማመንጫ በዙሪያ ያሉት ሕብረተሰብ የመብራተ ተጠቃሜ ሳይሆን ነገር ግን የአከባቤው ሰው ምሥሥው እናደይሠረቅ በተራ እንዲጠብቅ ይገደድ ነበር። የአከባቤው ሰው ጯናው ሲበዛበት ግዜ መቀለድ የጀመረው መቸስ የሀገሪ ሰው ያቅበታል እያረሩ መሣቅ እንዲ እያለ ይቀልዱ ነበር ዛሬ በለተራ መብራት ይዞ የሚያበላ ማነው ይል ነበር ። ለካስ ዛሬ ሁሉም መብራት ያዥ ሆኖል ለዛውም የማይበራ መብራት እንደው ምንኛ አለመታደል ነው። ለሁሉም ነገር እግዜአብሔር የይርዳን።

  ReplyDelete
 42. በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየፓርቲው፣ በየእምነት ተቋሙ፣ በየግል ድርጅቱ ስንት የተቃጠለ አምፖል አለ አይደለም እንዴ፡፡ ማን አወረደው፡፡ መብራት ስለሌለ ማንም ሳይለየው የሚሠራ አምፖል መስሎ ይኖራል፡፡ አየሽ ጨለማ ለአጭበርባሪ ይመቻል፡፡ በብርሃን ግን ሁሉ ይገለጣል፡፡
  It is great view Dn. Daniel. May God help us.

  ReplyDelete
 43. ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ የእድሜ ዘመንህን ያርዝመው፡፡

  ReplyDelete
 44. DANI GOD BLESS YOU!

  ReplyDelete
 45. ኡፈይ ዳኒ አንጀቴን አራስከው፡፡

  ‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡›› ኩራዝ ይህንን ስትል የቤቱ አባወራ መጣና ‹እፍ› ብሎ አጠፋት፡፡
  ‹‹በይ ደኅ እደሪ፣ እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል›› አለችና ቆርቆሮዋ ውስጥ ገብታ ተኛች፡፡


  ‹‹እፍ ብለው ያበሩናል እፍ ብለው ያጠፉናል››

  ReplyDelete
 46. I always become angry from my heart when I see some white hairs on your head. I wish you to be everlasting for Ethiopia. You are one among many millions in the current generation. Let God bless you long years of age to serve the public.

  ReplyDelete
 47. wendmachin egziabher amlakachin behiywot, betena yakoyih

  ReplyDelete
 48. yemigebachew kehone endih eyalk nigerilin

  ReplyDelete
 49. Wow it is a great message to whom may concern. At this moment many Ethiopian are fighting to get the right service for them and others. You are one of example that you put yourself endanger to speak our voice. I know speaking or writing is freedom of human being but in African that low only exist on paper. That why many our brother, sister, father and mother are in the prison because of what write or speak to deliver Ethiopian voice. I know we will get better democracy soon because this and next generation have been getting excellent education in addition that civilization teach us to understand democracy and to respect other interest. As God show as last year, we have to pray and fast to remove Ethiopian enemy. Meles Zenawi and Abune Paulos destroyed many Ethiopian culture because they think they will live forever but they died before Menegestu and Abune Markorios. However the Weyana government not take lesson from last year situation so they continue to put more Ethiopian people in the prison. I will pray to God to destroy all Ethiopian enemies from our country. God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ሆይ በፅሁፍህ የሚሰማህን ፅፈሃል፡፡ በመለስ ዜናዊ እና በአቡነ ጳውሎስ ሞት ተደስተሃል፡፡ ምክንያቱም በአንተ አመለካከት የተቀስካቸው ሰዎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው፡፡ አንተ የምትፈልገው መንግስት ወይም አመለካከት ወያኔን የሚረግም እና በመለስ ዜናዊ ሞትና በአቡነ ጳውሎስ ሞት የሚሳለቅ ነው፡፡ ግን እኮ መለስ ዜናዊን እንደ ጥሩ እና አርቆ አሳቢ መሪ የሚቖጥር ሞቱ የሚያንገብገው ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ እርሱ ቢኖር ኢትዮጵያ ብዙ ወደፊት ትራመድ ነበር የሚል ተፈጥሯል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ጥሩ አባት ነበሩ የሚልም አለ፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው እያልክ አንተም ወይም የአንተን መሰል ሃሳብ ሲመጣ የማይመስላችሁን ስትገሉ እና ስታስሩ ልተከርሙ ነው፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ ህዝቦች መቼም አብረው አይከርሙም፡፡ በኔ በኩል ሃሳቦች መከበር አለባቸው፡፡ ሰው ኢትዮጵያዊነቱን በሚስማማው መልኩ ገልፆ መኖር አለበት፡፡ እኔ እንደማየው ማየት እንደማስበው ማሰብ አለብህ ከተባለ መኗኗር ከባድ ይሆናል፡፡ ወንድሜ ሆይ እኔም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵዊነቴን እወዳቸዋለሁ፡፡ ግን እነ እከሌ ይሙቱ እያልኩ አይደለም፡፡ በድብቅ አሲሮ የኢትዮጵያን ውድቀት ለማፋጠን ሆን ብሎ ቀንና ለሊት የሚሰራ ሃሳብ ይሙት ይሸነፍ እላለሁ፡፡ ግን ወያኔ፣ ኢሠፓ፣ ኢህአዴግ፣ መንግስቱ፣ መለስ፣ አቡነ ጳውሎስ፣ አቡነ መርቆሪዎስ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ በነሱም ውስጥ የተወሰነ እውነትና ኢትዮጵያዊነት አለ፡፡ ችግራቸው ብዮ እምለው ሌላው ጠፍቶ እኛ ብቻ መኖር አለብን ብለው የሰሩት ካለ ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን (ሙስሊም ክርስቲያኑን፣ አማራው፣ ኦሮሞው፣ አገው፣ ሺናሻ፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ሶማሌው፣ ጋምቤላው፣.........) እወዳቸዋለሁ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ፕሬዘዳንት ወይም ጠቅላ ሚኒስትር ሆኖ ቢመራኝ እወዳለሁ፡፡ ይሄ ዘር ይሄ ሃይማኖት ብቻ ነው ኢትዮጵያን መምራት ያለበት ብዬ አላምንም፡፡ ልክ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ የአሸናፊነት ጎል ሲያገባ ተነስቼ እንደምጨፍረው፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ አንዱን ለማኖር የአንዱን መጥፋት ሳንመኝ ብንኖር ኢትዮጵያ ለሁላችንም ትበቃለች፡፡ወንድሜ ሆይ በፅሁፍህ የሚሰማህን ፅፈሃል፡፡ በመለስ ዜናዊ እና በአቡነ ጳውሎስ ሞት ተደስተሃል፡፡ ምክንያቱም በአንተ አመለካከት የተቀስካቸው ሰዎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው፡፡ አንተ የምትፈልገው መንግስት ወይም አመለካከት ወያኔን የሚረግም እና በመለስ ዜናዊ ሞትና በአቡነ ጳውሎስ ሞት የሚሳለቅ ነው፡፡ ግን እኮ መለስ ዜናዊን እንደ ጥሩ እና አርቆ አሳቢ መሪ የሚቖጥር ሞቱ የሚያንገብገው ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ እርሱ ቢኖር ኢትዮጵያ ብዙ ወደፊት ትራመድ ነበር የሚል ተፈጥሯል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ጥሩ አባት ነበሩ የሚልም አለ፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው እያልክ አንተም ወይም የአንተን መሰል ሃሳብ ሲመጣ የማይመስላችሁን ስትገሉ እና ስታስሩ ልተከርሙ ነው፡፡ ይህ የሚሆን ከሆነ ህዝቦች መቼም አብረው አይከርሙም፡፡ በኔ በኩል ሃሳቦች መከበር አለባቸው፡፡ ሰው ኢትዮጵያዊነቱን በሚስማማው መልኩ ገልፆ መኖር አለበት፡፡ እኔ እንደማየው ማየት እንደማስበው ማሰብ አለብህ ከተባለ መኗኗር ከባድ ይሆናል፡፡ ወንድሜ ሆይ እኔም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵዊነቴን እወዳቸዋለሁ፡፡ ግን እነ እከሌ ይሙቱ እያልኩ አይደለም፡፡ በድብቅ አሲሮ የኢትዮጵያን ውድቀት ለማፋጠን ሆን ብሎ ቀንና ለሊት የሚሰራ ሃሳብ ይሙት ይሸነፍ እላለሁ፡፡ ግን ወያኔ፣ ኢሠፓ፣ ኢህአዴግ፣ መንግስቱ፣ መለስ፣ አቡነ ጳውሎስ፣ አቡነ መርቆሪዎስ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው ብዬ አላምንም፡፡ በነሱም ውስጥ የተወሰነ እውነትና ኢትዮጵያዊነት አለ፡፡ ችግራቸው ብዮ እምለው ሌላው ጠፍቶ እኛ ብቻ መኖር አለብን ብለው የሰሩት ካለ ነው፡፡ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን (ሙስሊም ክርስቲያኑን፣ አማራው፣ ኦሮሞው፣ አገው፣ ሺናሻ፣ ትግሬው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ሶማሌው፣ ጋምቤላው፣.........) እወዳቸዋለሁ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ጥሩ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ፕሬዘዳንት ወይም ጠቅላ ሚኒስትር ሆኖ ቢመራኝ እወዳለሁ፡፡ ይሄ ዘር ይሄ ሃይማኖት ብቻ ነው ኢትዮጵያን መምራት ያለበት ብዬ አላምንም፡፡ ልክ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመርጦ የአሸናፊነት ጎል ሲያገባ ተነስቼ እንደምጨፍረው፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ሆይ አንዱን ለማኖር የአንዱን መጥፋት ሳንመኝ ብንኖር ኢትዮጵያ ለሁላችንም ትበቃለች፡፡

   Delete
 50. It is highly interesting and very enlightening piece of writing. It tells a lot. God bless you D.Daniel.

  ReplyDelete
 51. በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየፓርቲው፣ በየእምነት ተቋሙ፣ በየግል ድርጅቱ ስንት የተቃጠለ አምፖል አለ አይደለም እንዴ፡፡ ማን አወረደው፡፡ መብራት ስለሌለ ማንም ሳይለየው የሚሠራ አምፖል መስሎ ይኖራል፡፡ አየሽ ጨለማ ለአጭበርባሪ ይመቻል፡፡ በብርሃን ግን ሁሉ ይገለጣል፡፡
  ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡

  ReplyDelete
 52. ‹‹ብርሃን ለማጭበርበር ስለማያመች ነው፡፡ ብርሃን ከመጣ የሚወልቁ ብዙ የተቃጠሉ አምፖሎች አሉ፡፡ ተቃጥሎ ቦታን ላለመልቀቅ ዋናው መፍትሔ ጨለማ ነው፡፡››

  ReplyDelete
 53. God bless u and ur family . you are the best writer always !!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 54. you guys!!! who said that the education of our church is given only in the compounds of the church!!!. please my friend read more to understand better and don't speak for that you don't know it!!! i think you don't have any knowledge or even heard about the education of our church!! your part is simply read read read and ask help for the meaning of you read out please......you are not enough to give comments and suggestion!!!!!!!
  Thank you so much Dn. Daniel

  ReplyDelete
 55. le Kirkose sub city gebiwoche nigerlen

  ReplyDelete
 56. best of the best you are one of mert zega

  ReplyDelete
 57. ጨለማ ለአጭበርባሪ ይመቻል፡፡ በብርሃን ግን ሁሉ ይገለጣል፡፡

  ReplyDelete
 58. አንጀቴን አራስከው፡፡

  ReplyDelete