እዚያው ፉትስክሬይ ቁጭ ብለን ወግ በመሰለቅ ላይ ነን፡፡ ባለፈው ወዳጄ ስለ
‹‹ኢምፖርት›› አንሥቶ ነበር ያቆመው፡፡ እስኪ ይቀጥል፡፡
‹‹ምንድን ነው ኢምፖርት የሚያደርጉት ኢትዮጵያ ሄደው››
‹‹ሚስት ነዋ››
‹‹እንዴት ነው ደግሞ ሚስት ኢምፖርት ማድረግ ማለት››
‹‹እዚህ ሀገር ያለ ሐበሻ በሦስት መንገድ ነው ሚስት የሚያገኘው››
‹‹በምን በምን››
‹‹በኢምፖርት፣ በኤክስፖርትና በባላንስ››
‹‹ይሄ ትርጓሜ ያስፈልገዋል››
‹‹ኦኬ፤ ኢምፖርት የሚባለው ሀገር ቤት ትሄድና ሚስት ወይም ባል ይዘህ ስትመጣ ነው፡፡
ኤክስፖርት የሚባለው ደግሞ የውጭ ሀገር ሰው በተለይም የዚህን ሀገር ሰዎች ስታገባ ነው፡፤ ባላንስ ሠራህ የሚባለው ደግሞ ሁለት
አበሾች እዚሁ ተገናኝተው ሲጋቡ ነው፡፡››
‹‹ታድያ የትኛው ነው የሚሻለው››
‹‹ሁሉም የራሱ ጣጣ አለው፡፡ ኢምፖርት ስታደርግ ከታደልክ ትዳር የጠማትን ወይም
የጠማውን ታገኘዋለህ ወይም ታገኛታለህ፡፡ ካልታደልክ ደግሞ እዚህ ከመጣች በኋላ አቢዩዝ አደረገኝ ብላ ልትፈነግልህ ትችላለች፡፡
ወንዱም ትቷት ሊሄድ ይችላል፡፡ ወይም ይፋታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ ኢምፖርት ተደርገው ከመጡ በኋላ ስቃያቸውን ያዩም
አሉ፡፡ ውጭ እንሄዳለን፣ ባል እናገኛለን፣ አለፈልን ብለው ሳያመዛዝኑ ውጭ ሀገር ስለተባለ ብቻ ይመጡና አበሳቸውን ያያሉ፡፡
በተለይ ስደት ላይ ብዙ ዘመን ኖረው፣ እድሜያቸውን ጨርሰው፣ ራሳቸውን መልጠው፣ ሁለት ጠጉር አውጥተው ከሀገር ቤት ዘልላ
ያልጨረሰች ሚስት የሚያመጡ ፌንት ይገጫሉ፡፡››
እንዴት ነው የሚገጩት››
‹‹አየህ አንተ ሃያ ዓመቷን ሱዳንና ኬንያ ከጫርካት በኋላ አባባ የምትልህን ቆንጆ
ልጅ ስታመጣ፤ እርሷ እያማረባት ሲሄድ አንተ ግን እድሜ ሲያናጭርብህ ቅናቱን አትችለውም፡፡ የነገር አባቷ እንጂ ባሏ
ስለማትመስል ሥጋት እየገባህ ይሄዳል፡፡ ያም ያም አንተን ረስቶ
የሚስትህን ቁንጅና ሲያወራ እርሷ ተጨዋች አንተ ተመልካች የሆንክ ይመስልሃል፡፡ ያን ጊዜ አበሻነትህ ይነሣብሃል፡፡ አውስትራልያ
መሆንክን ትጠላውና መንዝና ሞላሌ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ሽሬ እንዳ ሥላሴ መሆን ያምርሃል፡፡ መሳደብ፣ መጨቃጨቅ፣ ሲብስም መማታት፣
ሲያልፍም አካል መጉዳት፣ በመጨረሻም ሕይወት እስከ ማጥፋት ትሄዳለህ፡፡
እዚህ ሜልበርንኮ አንዱ እልኩና ቅናቱ አልወጣለት ሲል ከሕንድ ቤት ቀይ ቃርያ ገዝቶ
ሚስቱን በበርበሬ አጥኗታል፡፡ ስንቱ ሚስቱን ገድሏል፤ ስንቶቹስ ተደብድበውና ተፈንክተው በሐኪም ጥረት ከሞት ተርፈዋል፡፡
ኢምፖርት ዕዳው ብዙ ነው፡፡
የዚህን ሀገር ሰዎች አግብተው የሚኖሩ ብዙ አበሾች አሉ፡፡ በተለይ ሴቶቹ በዚህ
ጎበዞች ናቸው፡፡ እነርሱ ጋር እስካሁን የሰማሁት የከፋ ችግር የለም፡፡ ባይሆን ወንዶቹ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ፈረንጅ ወዳጄ
ፍቅራዊ (ሮማንቲክ)
ነገር ይወዳል፡፡ እኛ ደግሞ ሃኒ፣ ስዊት፣ ዳርሊንግ የሚል ነገር አልለመድነው፡፡ እኔ ሐኒ የማውቀው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ማር
በእንግሊዝኛ ሐኒ መሆኑን ነው፡፡ ስዊት - ጣፋጭ ነው፤ በቃ፡፡ ዳርሊንግ እዚህ ነው የሰማሁት፡፡ እኛ ደግሞ ቆፍጠን ያልን
ነን፡፡ ‹ሌቱን ለአራዊት ቀኑን ለሠራዊት› ነው ወዳጄ፡፡ የኛ አኗኗር ለእነርሱ መሥሪያ ቤት ይሆንባቸዋል፡፡ እንኳን እነርሱ
እዚህ ሀገር ቆየት ያሉት ሴቶች እንኳን ‹‹የኛ ወንዶች አባወራነት እንጂ ፍቅረኛነት አይችሉም›› ይሉናል፡፡
ከቻልክ እዚህ ሀገር ባላንስ መሥራት
ነው፡፡ ተዋውቀህ፣ ሀገሩንም ዐውቀህ መጋባት፡፡ ችግሩ እዚህ እንደ አሜሪካ ዲቪ የለ፣ እንደ አውሮፓ በመርከብ የሚገባ የለ፣
ከየት ታመጣለህ፡፡ ወይ እዚያው ስደት ላይ ተጋብተህ ካልመጣህ በቀር፡፡ ››
‹‹ይህን ችግርኮ ተባብራችሁ መፍታት ትችሉ
ነበር››
‹‹አንዳንዱን አበሻ ተባበር ከምትለው
ተሰባበር ብትለው ይሻለዋል፡፡ ሁሉም በየጎጡና በየሠፈሩ ነው፡፡ አብዛኞቹ ቤተ ክርስቲያኖች እንኳን ዘርን መሠረት ያደረጉ
ናቸው፡፡ የአማራውን፣ የትግሬውን፣ የኦሮሞውን ቤተ ክርስቲያን ትለየዋለህ፡፡ ትግሬውም አንድ መሆን እያቃተው አድዋ፣ ሽሬ ሲል
ታገኘዋለህ፡፡ አማራውም ወልቃይት፣ ጎንደር እየተባባለ ለብቻው ቸርች ይከፍትልሃል፡፡ ኮሙኒቲውም ለየብቻ ነው፡፡ እዚህ ሀገር
የኦሮሞ፣ የሶማሌ፣ የሐረሪ፣ የትግራይ ኮሙኒቲዎች አሉ፡፡ አንደኛው ከአንደኛው ጋር የሚጠራጠሩ፣ የማይተባበሩ፡፡ ከትብብር ርቀው
ንጽሕ ጠብቀው የሚኖሩ፡፡ በፍቅር የተጎዱ፣ ከኅብረት የጸዱ፡፡ አንዳንዶቹ ኢትዮጵያውያን ነን ይላሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ‹‹ምሥራቅ
አፍሪካ›› የሚባል ሀገር ፈጥረውልሃል፡፡ …››
‹‹ኧረ እንዲያውም አዳሙ ተፈራ በጻፈው
‹‹ገመናችን በሰው ሀገር› የሚለው መጽሐፍ ላይ ሜልበርን የሚገኘው የኦሮሞ ኮሙኒቲ በ2010 እኤአ 25ኛ ዓመቱን ሲያከብር
የጻፈውን አይቼ ገርሞኝ ነበር፡፡
‹‹The Oromo are
indigenous African people from the north eastern of Africa .›› ይላል፡፤ ኢትዮጵያ ላለማለት አዲስ ሀገር ፈጥረዋል፡፡ ››
‹‹እይውልህ እንደዚያ ነው እንግዲህ፡፡ የሚገርምህኮ እዚህ ያለ ሰው መገንጠልን
የሚጠላ ተገንጣይ መሆኑ ነው››
‹‹በዚህ ብቻ አይበቃም ትርጓሜ ያሻዋል - ብሏል ኪነ ጥበብ›› አልኩት፡፡
‹‹በውጭ ያለ ዳያስጶራ ስለ ኤርትራ መገንጠል ሁል ጊዜ እየተንገበገበ ያወራል፡፡
እርሱ ግን ራሱ በፈቃዱ ያለ ሪፈረንደም ተገነጣጥሏል፡፡ በምትቃወመው ነገር ውስጥ ራስህን እንደማግኘት ያለ አስነዋሪ አካሄድ
የለም፡፡ በየስብሰባው ‹ዐንቀጽ 39› የምትባል ነገር ትነሣለች፡፡ ‹‹የብሔረሰቦች መብት እስከ መገንጠል›› የምትባለው፡፤
ይህች ዐንቀጽ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ አልተደረገችም፡፡ እዚህ ግን ተግባራዊ ተደርጋለች፡፡ የተገበሯት ደግሞ
የሚቃወሟት ሰዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ‹‹መገንጠልን የማይደግፍ ተገንጣይ›› ያልኩህ፡፡ አሁን ዘመን መለወጫ እየመጣ አይደለ?
ሦስት ቦታ ነው ፕሮግራም የተዘጋጀው፡፡ ከዚያ መርጠህ እንደየብሔረሰብህ መሄድ ነው፡፡ ወዳጄ እዚህ ሀገር ጩኒ ይምጣብኝ››
‹‹ማነው ጩኒ ደግሞ››
‹‹ጩኒ ሰው አይደለም፤ ሕዝብ ነው››
‹‹ጩኒ የሚባል ሕዝብ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ መስማቴ ነው፡፡››
‹‹ጩኒ ማለት ቻይና ነው፡፡ እዚህ ሀገር ጩኒ ነው የምንላቸው፡፡ ጩኒ እርስ በርስ
በመደጋገፍ ማንም አይችላቸውም፡፡ ብድር ይሰጡሃል፤ መረጃ ይሰጡሃል፡፡ ያቋቁሙሃል፡፡ ከዚያ ምርጥ ኢንቨስተር ትሆናለህ፡፡
ያለበለዚያ ደግሞ ወጥሬ እሠራለሁ ካልክ በቀላሉ የምትከራየው ቤት ይሰጡሃል፡፡ እንዲት ክፍል ተከራይተህ ኑሮ ሳይከብድህ ወጥረህ
ትሠራና በዓመትህ ቀና ትላለህ፡፡ ወዳጄ ጩኒ አንገቱን ደፍቶ እየሠራ ልጁን ምርጥ ትምህርት ቤት ነው የሚልከው፡፡ ኮሙኒቲያቸው
ልጆቹን በሚገባ ነው የሚረዳቸው፡፡ ስለዚህ ልጆቹ ውጤታማ ናቸው፡፡ እኛጋኮ ወላጆችና ልጆች አልጣጣም ብለዋል፡፡ ልጆቹን የቤት
ሥራ ማን ያሳያቸው፡፡ ማን በትምህርት ያግዛቸው፡፡
አገርሽ ምንኛ መንደርሽ ምንኛ
አላውቅበት አልኩኝ ያንችን አማርኛ
ሲባል አልሰማህም፡፡ በምን ቋንቋ በምን ዕውቀት ከልጆቻችን ጋር እንግባባ፡፡ ልጆቻችን
አያውቁም ብለው ንቀውናል፡፡ በዚህ የተነሣ ከትምህርት የሚያቋርጡት ብዙ ናቸው፡፡››
‹‹ቆይ ግን እዚህ መጥተው የተሳካላቸው የሉም››
‹‹ለዓይነት ያህልማ አሉ፡፡ መቼም ለስማችን መጠሪያ ቁና ሰፍተናል፡፡ ለአካባቢ ምርጫ
እስከመወዳደር የደረሱ አሉ፡፡ ያው ከሆቴልና እንጀራ ቤት ባናልፍም ቢዝነስ ያላቸውም አሉ፡፡ በተማሩት ሞያ የሚሠሩም በመጠኑ
አሉ፡፡ እኔ የሚገርመኝ ግን በኢሕአፓ፣ በኢሕአዴግ፣ በግንቦት ሰባት፣ በኢዲዩ፣ በቅንጅት ውስጥ ለመግባት እንጂ በምንኖርበት
ሀገር በሚገኙ ፓርቲዎች ውስጥ ገብቶ፣ አባል ሆኖ፣ ተወዳድሮ ፓርላማ ለመግባት፣ የአካባቢ ተመራጭ ለመሆን የሚተጋ አበሻ ብዙ አናይም፡፡
አሜሪካ እንኳን ሚሊዮን የሚሞላ ኢትዮጵያዊ ተከማችቶ እስካሁን አንድ የአካባቢ ተወካይ እንኳን አለማግኘታቸው ይገርመኛል፡፡ እኛ
በሀገራችን አምባሻ ነው የምንራኮተው፡፡ ለምሳሌ እዚህ አውስትራልያዊ ዜግነት ካለህ መምረጥ ግዴታህ ነው፡፡ እንደ አሜሪካ
አይደለም፡፡ የመምረጥ ግዴታ አለብህ፡፡ ያለበለዚያ ቅጣት አለው፡፡ የፓርቲዎቹ አባል ስትሆንና ሳትሆን ዕድልህ ይለያያል፡፡ if
you are not a member, you are a number ይሉሃል፡፡
ችግሩ ግን እዚህ ሀገር ተመልካች እንጂ ተጨዋች የለም፡››
‹‹ማለት››
‹‹ኳሱ ጉዳያችን ነው፡፡ ሜዳው አውስትራልያ ይባላል፡፡ ሕጉ የሀገሪቱ ሕግ ነው፡፡
ዳኛው ሲስተሙ ነው፡፡ ዋንጫው ውጤትህ ነው፡፡ እዚህ በሚገባ ተጫውተህ የስኬትን ዋንጫ መሳም ትችላለህ፡፡ ምን ያደርጋል
ታድያ፡፡ በዙሪያህ ቆሞ ለምን ይህ አይሆንም? ለምን ይሄ አይደረግም? እገሌ ለምን እንዲህ ያደርጋል? እንዲህ በመሆኑ አኩርፌ
ቀርቻለሁ፣ የሚል የዳር ተመልካች እንጂ ሜዳው ውስጥ ገብቶ ለመጫወት የሚፈልግ የለም፡፡ እዚህ ያለውን ሰው ‹‹ሰይጣን››
ከምትለው ‹ኮሙኒቲ› ብትለው ደንግጦ ያማትብብሃል፡፡ ተበላ፣ ተጠጣ፣ ተጣሉ፣ ተከፋፈሉ ብቻ ነው የምትሰማው፡፡ አንድ ወዳጄ ምን
ይላል መሰለህ
የትልቅ ሰው ልጅ ቀረ በከንቱ
ሀገር ሳይገዛ ሳይባል አንቱ - እንዲህ ነው እንግዲህ፡፡
ካሮላይን ስፕሪንግስ፣
አውስትራልያ
ዳኔ እምን ውስጥ ይሆን የገባሀኃው ? የድንግል ልጅ በሰላም ይመልስህ። በርታ
ReplyDeleteToo good to come from a passer by in Footscray
ReplyDeleteበፉትስክረይ የሚውሉ ሰዎች ልክ እንደዚህ ሰውዮ አይነት ናቸው። ተጨባጭ ያልሆነ እሮሮ ማሰማት እንጅ ለውጥ ለማምጣት የማይጥሩ ናቸው። እዛው ፉትስክረይ ቁጭ ብለው በስሜት አባዝዮ ተይዘው ያላዩትን ተባለ ወይም ሊሆን ይችላል በሚል ያልተረጋገጠ ጉዳይ ላይ ሲያሰኛቸው ዳኛ፣ ጠበቃ፣ ጠቅላይ ሚንስተር፣ አማካሪ፣ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ጳጳስ.....በመሆን ተሹመው ማረጋገጫ የሌለው የወርዬ ፓርላማቸው ከፍተው ስያቦኩ ውለው ያመሻሉ። የእንዲህ አይነቱ አባወራ ሚስት ደግሞ የሱንም የራስዋንም ስራ ጨርሳ እሱን ለማንሳት እዛው ፉትስክረይ ትሄዳለች በማታ ለምን ቢባል ከጠጣ መንዳት ስለማይችል።እረ ስንት ጉድ ነው የቻለችው ይህች ሰፈር በራሱ መተማመን የሌለው፣ ለለውጥ ራሱን ያላዘጋጀ እና መደመጥ ካልሆነ ማድመጥ የማይፈልግ ሰው ለማግኘት እሩቅ መሄድ አያስፍልግም ፉትስክረይ ጥሩ መጋዝን ናት። ይህ ጽሁፍ ለመሳቅና ጊዜን ለመግደል ካልሆነ በሰተቀር እውነታው ግን ይህ አይደለም።
ReplyDeleteለሁሉም ነገር ዲያቆን ዳንኤል እግዛብሔር አገልግሎትህን ይባርክልህ።
አመሰግናለሁ
Thank you, I think Dn Daniel got some one who are negative thinker, and who are looking only him self. Daniel that is not true, I hope you will find some one who tell you the fact.
DeleteThank you
Wow, what a sad! It is embarrassing. May the Lord of hosts help us!
ReplyDeleteThanks Daniel Ze Tana Dar.
እረ ቀጥል በለው እንዴት ተጫዋች ነው ጃል!!!
ReplyDeleteዳኒ ቢቻል ቤትህ ይዘኸው ግባ ብዙ ቁም ነገር አለው፡፡
‹‹በዚህ ብቻ አይበቃም ትርጓሜ ያሻዋል - ብሏል ኪነ ጥበብ››
ReplyDeleteChelema le enkfate Habesha lekifate sibal alsemahim Dni.
ReplyDeleteENGDAHEN EGZIABHER YEBARKEH BELEW YELEBACHENEN; TEKEKLEGNAWEN NUROACHENEN NEGEREN
ReplyDeleteDaneal leantem egziabher endieh betebeb lay tebeb bemastewal lay mastewalen yesteh
Thanks Daniyee for sharing us this amizing and intersting way of view !!that was a real talk.
ReplyDeletePeace be with u and family.
I like your post.It is interesting,may GOD bless all Ethiopians living out side Ethiopia.
ReplyDeletebetam tiru new
ReplyDeleteGIN ESKEMECHE?
ReplyDeleteI am really enjoyed what you saying its the truth about my fellow Ethiopian!! what can we do to change this image? by the way I couldn't find part one of this article.
ReplyDeleteThank you keep reporting what you know good work.
seyoum
Nice conversation. Please come back soon.
ReplyDeleteእዚህ ሀገር ያለ ሐበሻ በሦስት መንገድ ነው ሚስት የሚያገኘው:: በኢምፖርት፣ በኤክስፖርትና በባላንስ::
ReplyDeleteኢምፖርት የሚባለው ሀገር ቤት ትሄድና ሚስት ወይም ባል ይዘህ ስትመጣ ነው፡፡ ኤክስፖርት የሚባለው ደግሞ የውጭ ሀገር ሰው በተለይም የዚህን ሀገር ሰዎች ስታገባ ነው፡፤ ባላንስ ሠራህ የሚባለው ደግሞ ሁለት አበሾች እዚሁ ተገናኝተው ሲጋቡ ነው፡፡
ጩኒ ማለት ቻይና ነው፡፡ (ዐይናቸው ጮንጯና ስለሆነ) እዚህ ሀገር ጩኒ ነው የምንላቸው፡፡
ReplyDeleteኳሱ ጉዳያችን ነው፡፡ ሜዳው አውስትራልያ ይባላል፡፡ ሕጉ የሀገሪቱ ሕግ ነው፡፡ ዳኛው ሲስተሙ ነው፡፡ ዋንጫው ውጤትህ ነው፡፡ እዚህ በሚገባ ተጫውተህ የስኬትን ዋንጫ መሳም ትችላለህ፡፡
Why u are talking such rubbish.
ReplyDeleteWowwww how u r gentle sir cos ur comment it shows that u r a great man,very kind,who r talking like philosophers..... u look u think ur self like that but when i c ur comment,i guess u r retarded or low mind next time before u post ur comments try to show for u psychiatric
Deleteይህ ፅሁፍ አንተ እንዳልከው እንቶ ፈንቶ አይደለም ብዙ ዕውነታዎችን የሚዳስስ ነው። ይህ ፅሁፍ እኛ ኢትዩጰያውያን መሆን የምንፈልገውን ወይም አቋማችን ነው የምንለውን እና እንዲሆን የምንመኘውን በተግባር ከሆነው ወይም እያረግን ያለውን የሚያስቃኝ ነው። ስለዚህ እኔ የምመክሮት እንደዚህ አይነት ፍርድ ከመስጠት እንደገና እንዲያነቡት ነው።
Deleteአዲሱን ፳፻፮ ዓ.ም ዘመነ ማርቆስን
የንሰሐ፣ የዕርቅ፣ የሠላም፣ የብጽግና፣ የደስታ፣ የመለወጥ፣ በመንፈሳዊ ሕይወት የመጠንከር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ እንዲሁም ይህ የጡመራ መድረክ የምንጠላለፍበት ሳይሆን የምንማማርበትና የምንተራረምበት፣ እንቃወመዋለን የምንለውን ነገር እራሳችን ስናረገው የማንገኝበትና ሌሎች እንዲያረጉ የምንጠብቅበት ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሀላፊነት የምንወጣበት ዘመን ያድርግልን አሜን።
የሚገርምህኮ እዚህ ያለ ሰው መገንጠልን የሚጠላ ተገንጣይ መሆኑ ነው. tiru ababal.
ReplyDeletewhy are u so concerned about Oromo?It is true that this nation is from East Africa. From Ethiopia, Kenya, Uganda and other countries.Because you do not know this or ignored it that your children take you as illiterate and ignore you!
ReplyDeleteya I also agree! oromon lekek, haymanothin tebek! This is may be my 4th or 5th time when I coment on this website on the same essue of ethnicity view of our good teacher (D Daniel) on oromo! Dany u should do or say something about it. Ethiopia lezelealem tinur
Delete"በምትቃወመው ነገር ውስጥ ራስህን እንደማግኘት ያለ አስነዋሪ አካሄድ የለም....."
ReplyDeletei thnk evry ethiopian who are out side dis story one thng dat differs in ma side in sa 'mazelel'mibale neger ale hahaha mistehen yazeleluwatal hahahah one day in god will when u get around pls say smthng about dis thng in ur beautiful hand may god bless u dn
ReplyDeleteEwnet new yetenagerew ende dirikosh enjera bezerna begosa alitebtatsenim ende yeih weshet new? Ende doro bilits altegentatelinm? Be hagerachin Ethiopia yemayetayew neger new ke hagerachin wechi balenew lai yemitayew endewm yalitenagerew bezu ale wedaje edeme yesteh Danii leantem MEDEHANIALEM kemayalikew berketu abizito yadilih
ReplyDeletethis is a reality history .......thank u diakon daniel
ReplyDeleteዳኒ ወግ ይጠረቃል፣ ስላቅ ደግሞ ይሰለቃል!!
ReplyDeleteAYE HABESHA, EWENETU SINEGEREW AYIWEDEM, BETELEYE DIASPORAWEMA EWENETE YEMIBALE NEGERE FETSEMO AYIWEDEM, BETELEYE GEMENACHEW TENEGEROM AYILIKEM, DN. DANI LIMIDUN SILAKAFELKEN BETAM ENAMESGENALEN
ReplyDeleteያልታደለ ህዝብ እኮ ነው:: ጀርመንም ያው በሰፈር ን ጎጥ ተከፋፍሎ አለንልህ :: ኢትዮጵያዊ አይደለንም የሚሉ አበሾችም በዝተውልናል ::አፍርካን በ1 አገር ከፍ አድርገዋት ይሀው "እስት አፍሪካ" ተፈጠረ :: ወራዳ ትዉልድ !!
ReplyDeleteimpressive expression!!
ReplyDeleteThank you. ! D. Daniel
ReplyDeleteGOD BLESS YOU!!!
Becha yigermal!
ReplyDeleteGod may bless all marge!
ዲ/ን ዳንኤል እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እስከ ቤተሰቦችህ አደረሰህ!
ReplyDeleteየመከፋፈልን መንፈስ ልታጠፋው የምትችለው በህግ፣በፖሊሲ፣በመመሪያና በደንብ አይደለም፡፡
መከፋፈልን ከልብ ውስጥ ነው ማጥራትና ማስወገድ ሁሉም ከጠራ ደግሞ ቦታ ያጣል ማለት ነው፡፡እውነት መቼ ይሆን የምንቀየረው?
Dn. Daniel
ReplyDeleteI really feel sad to know that Ethiopian in the foreign land involve in tribalism. They are living with civilized people, but they have primitive attitude. Please broaden your outlook!
F.G. from Dessie
bediyasporaw bisobetal!besew ager eyenoru begox mikefafelu bettam tebaboch nachew.enema tazibe tazibe selchitognal.
Deleteandande enezih sewoch ager bett bihonu yacharsunal biye asibina enkuan keager raqu elalehu.keseletenu ageroch yeweresut quanqua bicha new.
Lehulum Tibebun ena Mastewalun Yistew..Beteley Lee Diasporaw...Egam sintun eyetazebin new Bee switherland....God Bless u dani...Happy New Year.
ReplyDeleteDn Daniel, It was a privilege to listened some of your preaching here in Melbourne. We had really blessed and learned a lot from you. Please come back again in the near future. The person you talked to in my opinion has some truth on it...generally Ethiopians live here in Melbourne are good in going church...but we are far from God's word ...we still do not know the test of god..do not understand spiritual live..his plan to our life ...as such we tent to follow people rather than god.
ReplyDeletePls post or attach links if you have records from those preaching.
DeleteDaniel asteyayete lela guday new yetazebikut new be likso lay vidio keretsaw ke serg keretsa ekul keretsa be likso min yilutal?
ReplyDeleteEwneten manem wedot aykeblewem ewntegnawen selawetabachu yesemachehwale Dani Merte ye Tarik mehur new lezehem evidence alew!!
ReplyDeleteየትልቅ ሰው ልጅ ቀረ በከንቱ
ReplyDeleteሀገር ሳይገዛ ሳይባል አንቱ
ዳኒ በጣም የተመቸኝ አባባል ነው፡፡
የትልቅ ሰው ልጅ ቀረ በከንቱ
ReplyDeleteሀገር ሳይገዛ ሳይባል አንቱ
እኔ ሐኒ የማውቀው ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ ማር በእንግሊዝኛ ሐኒ መሆኑን ነው፡፡ ስዊት - ጣፋጭ ነው፤ በቃ፡፡
ዳኒ በጣም የተመቹኝአባባሎች ናቸው፡፡ በርታ፡፡
"እዚያው ፉትስክሬይ ቁጭ ብለን ወግ በመሰለቅ "
ReplyDeleteIt is a good message for importer and exporters of Ethiopia.
ReplyDeleteአማራውም ወልቃይት፣ ጎንደር እየተባባለ ለብቻው ቸርች ይከፍትልሃል፡፡ ኮሙኒቲውም ለየብቻ ነው፡፡ welkait amara newu amennnnnn
ReplyDeleteArif weg new. Ezihim lalenew tiru lesson yimesilegnal.
ReplyDeleteያን ጊዜ አበሻነትህ ይነሣብሃል፡፡ አውስትራልያ መሆንክን ትጠላውና መንዝና ሞላሌ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ሽሬ እንዳ ሥላሴ መሆን ያምርሃል፡፡ መሳደብ፣ መጨቃጨቅ፣ ሲብስም መማታት፣ ሲያልፍም አካል መጉዳት፣ በመጨረሻም ሕይወት እስከ ማጥፋት ትሄዳለህ፡፡ዳንኤል ጽሁፎችህን በጣም እወዳቸዋለሁ አድናቆትም አለኝ፡፡ ግን በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ከላይ የጠቀስካቸው ቦታዎች በጣም ጨቃቾችና ሰው ገዳዮች በሚል መግለጽህ ትንሽ ቅር አሰኝቶኛል፡፡
ReplyDeleteif you are not a member, you are a number ይሉሃል,tanx Dani from kebaro
ReplyDeleteቅርሶች ዳንኤል ክብረትንይጣራሉ
ReplyDeleteጤና እና አድሜን አብዝቸ ለምመኝልህ ለዲያቆን daniel kibret እደምን አለህ ከሰላምተየ ከዚህ በመቀጠል የማሳስብህ ቢኖር in your orthodox church heritage studying research in Ethiopia you didn't visit or tour and others the same is true and the government can not give attention the ethiopian orthodox church heritage place in south gondar andabet woreda ( አንዳቤት ወረዳ ጎኖ ቀበሌ ግንብ ጊወርጊስ church )
በሚባል ቦታ አሰደናቂ ታሪካውይ ቅርስ አለ :: ይህም ታሪካው ቅርስ ተሰራ የሚባለው በ 1370 መቶ ክፍለዘመን ነው :; አሰራሩ ልክ የጎንዳርን የፋስል ግንብ ነው : : aste fasil ሰሩተ የሚባለው የጎንዳረን ቤተ መንግስተ ከዚሁ ከደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ከሚገኘው ታርካውይ ቦታ ልምድ በመቅሰም ነው ይላሉ የዛው አካባቢ ነዋረወች :; ነገርግን ቦታውን እስካ ውን ድረስ ማንም ቀና በሎ ያላየው ቀደምት የፋሲል ግንብ ከመሰራቱ በፊት የነበረ ታርካውይ ቦታ ነው:: እናም ድያቆን ዳንኤል ክብረት ይህ ቦታ አንተን ሰለሚመለከት የorthodox የማነንታች መለያ የሆኑ ብዙ የchurch ቅርሶች መደበር የሆነች ቦታ ሰለሆነች በጥናትህ እንድታካትተው ስል በትህትና እጠይቅሀለው:; ቦታው አስካሁን ድረስ እንደተቆለፈነው::ቦታው ከእስቴ መካነእየሱስ 20 ኪሜ ይርቃል :: የቱሪስት መዳረሻ መሆነ የሚገባው ታርካውይ ቦታ መንግስት ጭራሹን ያላየው ግንብ ጊወርጊስ ከ 1370- 2006 ዓ ም ያው እንደአለ አለ???????????????????????
for further information
ገ / መስቀል ደጉ
gebredegu@yahoo.com
ጎንደር university አንዳቤት ግንብ ጊወርጊስ original homeland
Enamesgenalen Danial! ye sew hager noro yeha ena kezim yebelete bezu tarik alew. Man ende Ethiopia! ena andu Europa hager new yemenorew 5 amet lihogn new kewetahu kezerezerkew yeteleye noro adelem yalehu, andanda sew lemen ke hageru yewetal elalhu gomen be tena ena be netsu lebona yeshalal. mecham bihon ke hager wechi neh awo neh mesewat lemehon mezegajet new. yeteleyaye eta fenta yegatmehal mekebel new. Lemen ande honen Amelk le hagerachen be setat tsga amesgenen serten terdadten ke sew ager mekera ers bersachen medan endemanechel alawekem betam eras wedad honen be ye areb ageratu yemisekayut ehetochachen yeteleyu nachew? beye sew hageru yemeyabdut yeteleyu nachew? gezeb yale be genzebu ewket yalew be ewketu gulebet yalew be gulbetu kena mehon manan yegedelal ande sew be accountu weset 2 billon binorew men yedenkal kerasu terfo kalgeze 2 enjera ayebela ena men hulum afer new le Ethiopia belo rasun sewa ena Ethiopian tarikuan gelo hezbuan adekeko alefe ehangaw kentu yanga yetewld adang yehonal ye kome yemimeselw endayewdek yetenkek ye andu feda le andu liyagebaw yegebal Ethiopia hulem Ethiopia nech ande nech ye andu behar kandu tenetelo Ethiopian aymolam hlum yasfelegatal Talaku amelakach Egziabher ande yadergat Dengel Mariam ye aserat hageruan Tetebek!!!
ReplyDeleteእናንተ የብድር የሚያስፈልገን ??
Deleteሰላም,
የእኔ ስም Mr ፍሬድ ነው. እኔ የግል እና የኮርፖሬት ግለሰቦች ብድር መስጠት አንድ የግል አበዳሪ ነኝ. እናንተ ወደ ታች ዞር ብለዋል
ብዙ ባንኮች? የእርስዎ ለማቋቋም ፋይናንስ ያስፈልገናል አድርግ
የንግድ? ከእናንተ መስፋፋት የሚሆን የፋይናንስ ያስፈልገናል አድርግ
የንግድ? ወይስ የግል ብድር የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? የእኔ ብድር
ክልሎች. የግል ከ የንግድ ብድር ነው. የእኔ ፍላጎት
መጠን በጣም ያገናዘበ ነው. 3%, እና 50,000.00 € € 500,000,000,000.00 € ቢበዛ ቢያንስ, የእኛን የብድር ሂደት በጣም ፈጣን ነው
እንዲሁም. እኔ ሁሉንም የገንዘብ ለማድረግ በጣም ፈቃደኛ ነኝ
ባለፈው አንድ ነገር ያጠቃቸዋል. እናንተ በእርግጥ ዝግጁ ከሆነ
የገንዘብ ችግር መፍትሔ እንዲያገኙ, ከዚያም ምንም ፍለጋ
ተጨማሪ እና ብድር በዛሬው በኢሜይል በኩል ለ ተግባራዊ ይሆናሉ:
(Fredlarryloanfirm@gmail.com). እኔ በማድረግ በጉጉት እንጠባበቃለን
ከእናንተ ጋር የንግድ.
አቶ ፍሬድ ላሪ
ዋና ሥራ አስኪያጅ.