Thursday, September 19, 2013

አናብስት

ቀነኒሳን አንበሳ አሉት፡፡ ኃይሌንም አንበሳ አሉት፡፡ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ አንድም አንበሳ ሲተኛ የሞተ፤ የደከመ፣ የታመመ ይመስላል፡፡ እንስሳት እየመጡ ይጎበኙታል፡፡ ያዩታል፤ አንዳንዶቹም ይራመዱታል፡፡ ሌሎቹም አንበሳው ደክሟል ብለው የአራዊት ንጉሥ እኛ ነን ይላሉ፡፡ እንደ ዝንብ ያሉትም ይወርሩታል ‹‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጨዋቻ ይሆናል›› እንዲሉ፡፡ እርሱ ግን የሚያደርገውን ያውቃልና ዝም ይላቸዋል፡፡
ታሪክ እንደ አንድ አንበሳና አይጥ፡፡ ታሪኩስ እንደምን ነው ቢሉ እንዲህ ነው፡፡ በአንድ ጫካ የሚኖር አንበሳ ደከመውና አፉን ከፍቶ ተኛ፡፡ እንደተኛም አንዲት አይጥ መጣች፤ መጥታም አልቀረች ትዞረው ጀመር፡፡ ወደ ወገኖቿም ሄዳ አንበሳ ደክሞ ተኝቷል ብላ በሰፊው አወራች፡፡ ተመልሳም መጣችና ተጠጋችው፡፡ እርሱም ዝም አላት፡፡ እርሷም ጠጋ ብላ ጅራቷን በአፍንጫው ከተተችበት፡፡ እንዳያነጥስ ችሎ ዝም አላት፡፡ አይጧም ጠጋ ብላ አፉን ተመለከተችው፡፡ ምቹ ዋሻ መስሎም ታያት፡፡ አሁንም ተጠጋች፡፡ በመጨረሻም ያንን የተከፈተ ዋሻ ልትጎበኝ ወደ አፉ ውስጥ ዘው አለች፡፡ ያን ጊዜም አንበሳ አፉን ግጥም አደረገው፡፡ ሲጥ ብትል ሚጥ መውጫ አልተገኘም፡፡

ቀነኒሳም እንዲሁ ነው፡፡ እርሱ ከውድድር ሲርቅ ደከመ፣ ሰለቸ፣ መከነ፣ ተወ፤ ተብሎ ነበር፡፡ ሌሎችም እኛ የትራክ ላይ ንጉሦች ነን፡፡ የጎዳና ላይ ነገሥታት ነን ብለውም ነበር፡፡ እንደ አይጧም ብዙ ወሬ አውርተው ነበር፡፡ አፈፍ ብሎ ሲነሣ ግን እነዚያን ሁሉ ድል ያደርጋቸዋልና ቀነኒሳን አንበሳ ብለውታል፡፡

አንድም አንዱ አንበሳ ሲያድን ሌላው አንበሳ በሦስት ነገር ይረዳዋል፡፡ አንድም አካባቢውን በመጠበቅ፣ አንድም ታዳኙን በማድከም፣ አንድም አዳኙን በማጀብ፡፡ ኃይሌም እንዲሁ ነው፡፡ ቀነኒሳን በለንደኑ ሩጫ በሦስት ነገር ረድቶታል፡፡ አንድም የሩጫውን ሂደትና ድል በመጠበቅ፣ አንድም ሞ ፋራህን በማድከም፣ አንድም ቀነኒሳን በማጀብ፡፡ አንበሳ ሲያጠቃ በቡድን ነው፡፡ ኃይሌና ቀነኒሳም በቡድን አጥቅተዋልና አንበሶች ተብለዋል፡፡ ኃይሌ ከቀናት በፊት ስለ ሞ ፋራህ የሰጠው አስተያየትና ለቀነኒሳ የሰጠው ምክር ለለንደኑ የቀነኒሳ ድል ረድቶታልና ኃይሌን አንበሳ ብለውታል፡፡
አንድም ኃይሌን በስፖርተኛ የዕርግን ዘመኑ ባስመዘገበው ውጤት አንበሳ ብለውታል፡፡ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ አንበሳ ቢያረጅም እንኳን ፈጽሞ ካልወደቀ በቀር እንስሳት አይተው ይፈሩታል፡፡ እርሱም ተንቀሳቅሶ በዐቅሙ ያድናቸዋል፡፡ ኃይሌም ምንም በዕድሜ ቢገፋ ሯጮች አይተው ይፈሩታል፡፡ ሮጦም ድልን በዐቅሙ ያድናልና አንበሳ ብለውታል፡፡
ነገር እንደ ተረትና ምሳሌ
አንበሳ ተኝቶ ፍየል ዘለለችው
ንቆ ቢያሳልፋት ሞኝ አደረገችው
አንድም አንበሳ በሦስት ነገር ተፈርቶ ይኖራል፡፡ አንድ በድምጹ፣ ሁለት በግርማ ሞገሱ፣ ሦስት በክርኑ፡፡ በድምጹ እንደምን ነው ቢሉ አንበሳ ገና ከሩቁ ሆኖ ሲጮኽ ሲሰሙት እንስሳቱ ሁሉ ይርዳሉ፣ ይንቀጠቀጣሉ፡፡ በግርማ ሞገሱስ እንዴት ነው ብለው ቢጠይቁ አንበሳ ባይጮኽም ባይባላም በጫካው ውስጥ ጎምለል ጎምለል ሲል እንስሳቱ ፈርተው ይሸበራሉ፡፡ በክርኑስ እንደምን ነው ያሉ እንደሆን በእግሩ ርግጥ አድርጎ በክርኑ አድቅቆ ይመገባልና ነው፡፡ ቀነኒሳም አንበሳ ነው ሲሉ ምንም ባያሸንፍ እንኳን እዚህ ውድድር ላይ ሊወዳደር ነው፣ ሊሮጥ ነው ሲባል አብረውት የሚሮጡ ሁሉ ይፈራሉ ይርዳሉ፡፡ አንድም ምንም ባያሸንፍ እንኳን እርሱ በውድድሩ ውስጥ ገብቶ ሲሮጥ ሲያዩት ድል ይነሣን ይሆናል ብለው ብዙዎቹ ሯጮች ይሸበራሉ፡፡ አንድም አምርሮ የሮጠ እንደሆነ ደግሞ ኃያላኑን ከኋላው አስከትሎ ድል በኃያል ክንዱ ድል ያደርጋቸዋልና ነው፡፡
አንድም አንበሳ ከአፍሪካ ሄዶ በእንስሳት ማቆያ ውስጥ ካልሆነ በቀር በፈረንጅ አገር አይገኝም፡፡ እንደ ቀነኒሳ ያለ ሯጭም ከአፍሪካ ሄዶ ለሰው ሀገር ይሮጥ ይሆናል እንጂ በፈረንጅ አገር አይገኝምና ቀነኒሳን አንበሳ ብለውታል፡፡ አንድም አንበሳ የሀገራችን የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነትና የድል አድራጊነት ምልክቷ ነው፡፡ ኃይሌና ቀነኒሳም በረሃብ፣ በችግርና በጦርነት ስሟ በክፉ የሚነሣውን ሀገራችንን በጀግንነት፣ በድል አድራጊነትና በአልበገር ባይነት እንድትታወቅ አድርገዋታልና አንበሳ ተብለዋል፡፡
ያሉንን አናብስት እያወደስን ሌሎች አናብስትን እናፈራለን፡፡ 

47 comments:

 1. አንበሳ ተኝቶ ፍየል ዘለለችው

  ንቆ ቢያሳልፋት ሞኝ አደረገችው

  ReplyDelete
 2. we are united by these Lions.

  ReplyDelete
 3. ያሉንን አናብስት እያወደስን ሌሎች አናብስትን እናፈራለን፡፡

  ReplyDelete
 4. well explained sir.

  ReplyDelete
 5. እንደው ዳኒ ከወዴት አገኘኽው ባክህ ከላይቤት ነው ከታችቤት? መጻሕፍቶቻችን የጣፈጠ ዘዬ አላቸውና:: እንዴት ይጥማል! ለሥነ ጽሑፋችን እድገት እነዚያ ትምህርት ቤቶችና መጻሕፍቶቻቸው ገና ብዙ ያልተነገረ አስተዋጽኦ አላቸው:: ይበል ዳኒ! አናብስቱን ያቆይልን

  ለኃይሌ ክብር ግን የሚመጥን ቦታ እስካሁን አላገኘሁምና ቤተ መንግሥት መግባቱን ወድጄለታለሁ:: ምን ባይሠራ ስንት ዘመን ደስ ሲያሰኘን የኖረን ሰው ደስ ካለው ምናለ የቤተ መንግሥት አድባር ትቀበልህ ብንለው:: በዚያ ላይ ዓለማቀፋዊ እውቅናው ለሀገር የሚያተርፋቸው ብዙ ነገሮች መኖራቸውን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም::

  ሌላው ደግሞ የመረጠውን እንዲሆን ሰብአዊም ግላዊም መብት እንዳለው ማሰብ ጥሩ ነው:: እኔ ያልደገፍኩትን አትደግፍ እኔ የመረጥሁትን ተከተል ብሎ ሌላውን ያላግባብ መጫን አንባገነን አያሰኘንም? ይቅናህ አንበሳው!

  ReplyDelete
 6. አንበሳ ተኝቶ ፍየል ዘለለችው
  ንቆ ቢያሳልፋት ሞኝ አደረገችው

  ዳኒ የኛ ችግራችን ለጀግኖቻችን ክብር መስጠት አናውቅም፡፡

  ReplyDelete
 7. ዳንየ! እንዴት ሰነበትህ? ምነው ሰሞኑን ዘገየህብኝ ነፍሴ ስትቃትት ደረስህልኝ? ድንግል ትድረስልህ፡፡
  አይታችኋል ይህንን አንድምታ በአባቶቹ አካሄድ ሲተነትነው እንዴት እንዴት ተመሰጠረ ጎበዝ?! ‹ንባብ› ይገድላል፤ትርጓሜ ያድናል ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡ ወንድምየ ሺ ያድርግህ፡፡‹ላለው ይሰጠዋል› ነውና ፀጋውን ያብዛልህ ለኔም ጸልይልኝ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቤት አቤት አቤት! ያንት ያለህ ያንት ያለሀ!

   Delete
 8. አንበሳ ተኝቶ ፍየል ዘለለችው

  ንቆ ቢያሳልፋት ሞኝ አደረገችው

  ReplyDelete
 9. Dear Dn. Daniel,

  The way you use to write this article is disgusting. I am a silent reader and if I have to give a comment always i write a positive comment. but today I may not write good words, Sorry for that. Because I read this kind of article for the second time. So totally disagree the way you write the article. What I love about our church is its uniqueness. Her own melody, way of writing, .... but you are taking the unique way of writing of our church and throwing it to the rubbish world. Because I feel shocked when I hear/read The way we bless Virgin Mary, or Other Kidusan given to others outside of our church. You are the one who blames for those who opened our church doors for outsiders. What it is this today ? because you are teaching the way to do it for those who want to make our dirsanat, gedlat, andemta mesahefet as a useless book.
  Any way think of it Dear ?


  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህን ሰው የተጠናወተው የማህበረ ቅዱሳን ጣጣ ነው፡፡ እኔ ማህበረ ቅዱሳን አይደለሁም፡፡ ዳንኤል ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነው፡፡ አሁን ዳንኤልና የማህበረ ቅድሳን አባላት አንድ ፈለግ ፈጥረው ነበር፡፡ በፈጠሩት ፈለጋቸው ጎዳናም ኢላማ ያደረጉት ሠራዊት ነጎደላቸው፡፡ አሁን ደግሞ የከፋውን ጉድ በዚህ አስተያየት ሠጭ ውስጥ ተመለከትኩት፡፡
   እንደዚህ ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እንደተመሰረተ ከበርካታ ነገሮቹ መካከል በአንድ ነገር ታወቀ፡፡ በሙዚቃ መሳሪያና በያሬዳዊ ዜማ አመለካከቱ፡፡ ከሙዚቃ መሳሪያ ከበሮ፣ ማሲንቆ፣ በገና፣ ጸናጽልና ምናልባት ከእነዚህ ቢጨምር ሁለት ወይም ሶስት የሚሆኑት የተቀደሱ አላቸው፡፡ ጊታሩ፣ ኪ ቦርዱ፣ ሌላው የሠይጣን ነው ሲሉ ሲያሻቸውም የሕዝቅኤሉን ጥቅስ ሲያጣቅሱ ነበር፡፡
   በጣም ጥሩ፡፡ ታዲያ አሁን በሳልሽው ቢላዋ ተመተሪ ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህ ሰው ያለምንም ጥርጥር የማህበረ ቅዱሳን አባል ለመሆኑ አሻራው ይናገራል፡፡ እናም “ሥነ-ፅሁፋችንን” አረከስከው ዓይነት አስተያየት ሰንዝሮአል፡፡ ዳንኤልን በጣም እወደዋለሁ፡፡ ወዳጄን ካየሁት ብዙ ዘመን አልፎኛል፡፡ እየናፈቀኝም ነው፡፡ ያምሆኖ ግን ዳንኤል በወጣትነቱ የጀመራት ያች መንገድ አሁን እንቅፋት ሆና አላሳልፈው ስትል ተመለከትኩአት፡፡ ያሬዳዊ ዜማ ብሎ ጀመረላቸው እነርሱ ደግሞ የተቀደሰውን የሥነ-ፅሁፍ ለዛ አታርክስብን ዓይነት ብለው ሲቀጥሉለት ወዳጀ ዳንኤል መልስ ይኖረው ይሆን? እኔ ሽህ አለኝ! ስለያሬዳዊው ዜማም ቢሆን!
   አስተያየት ሠጭ ሆይ፡- ለአንተ ጥቂት ጥያቄዎች አሉኝ፡፡ አስበህበት ከሆነ አስተያየት የሰጠኸው፤ ታዲያ መንፈሳዊ መጻሕፍት ሁሉ በእንደዚህ ዓይነት ለዛ እንዲገለበጡ ትፈልጋለህ ወይ? የድርሳናት ጻህፈት በዚያኛው ዘመን ሳይሆን እኛ ባለንበት ዘመን የመኖር እድል ቢያጋጥማቸው ኑሮ፤ እንደነየታንጉት ምስጢር፣ እንደነየወዲያነሽ፣ እንደነፍቅር እስከመቃብር ባለ የሥነ-ፅሁፍ ለዛ ውዳሴ ማርያሙን - ሰኔ ጎለጎታውን - ድርሳነ ባልቴቱን ወዘተውን ሊጽፉት እንደሚችሉ የነበረ ልብ ብለኸዋል? ወይስ እንደዚያ ዓይነቱን የሥነ-ፅሁፍ ለዛ አመድ ነስንሰው - ጤዛ ልሰው - ማቅ ለብሰው - ድንጋይ ተንተርሰው በሱባዔ የተቀበሉት ዓይነት ነው የሚመስልህ? ወይስ መንፈሳዊ ካልሆኑት ጥንታውያን መጻሕፍት መካከል ቢያንስ ቢያንስ አንድ የማግኘትና የማንበብ ዕድል አጋጥሞህ አያውቅም?
   ለዳንኤል ዘጣና ዳር፡- አንዳንድ ጊዜ ግን ለጠንካራ አስተያየቶች መልስ ለመስጠት ብትሞክር የበለጠ ዐይናማ ያደርግሀል የሚል ምክር አለኝ፡፡ ሁሉም የምትጽፋቸው እንደድሮህ ሁሉ የጭነት ሳይሆን የእራስህ ሊሆን እንደሚችል አልጠራጠርም፡፡ ታዲያ አንድ በሳል ጸሐፊ ብቁ መሆኑ የሚለካው እንደምንም ብሎ አንድ ጊዜ አምጦ በሚያፈሰው አሳቡ ሳይሆን በሳል የሆኑት ሃያስያኑ ከሚሰጡት ትችት ማግስት በሚያቀርበው ብቁ ምላሽ ጭምር ነው የሚል ፍልስፍና አለኝ፡፡ ስለዚህ አንዳንድ ጊዜ ብቅ እያልክ መልስ ብትሰጥ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
   ቢያንስ ቢያንስ አንተ ልታነበው ስለምትችል አንድ በሳል ነገር ላጫውትህና በዚሁ ልዝጋው፡፡ አንድ የሳይንስ ፕሮፌሰር ነበሩ፡፡ ምንጊዜም ለሳይንሳዊ እሰጣ አገባ ሲጋበዙ ከአንድ ሹፌር ጋር ይሄዱ ነበር፡፡ ሹፌራቸውም ካደረሳቸው በኃላ የሚያቀርቡትን ሳይንስ ያዳምጥ ነበር፡፡ ቀስበቀስም አወቀው - ለመደው፡፡ አንድ ቀን ወደ አንድ የተለመደ ስብሰባቸው ሲሄዱ “ዛሬ የሚያቀርቡትን ትንታኔ እኔ ላቀረብልወት እንደምችል ያውቃሉ” በማለት ሊያቀርበው እንደሚችል አሳመናቸው፡፡ ከተስማሙ በኃላም ሁሉንም የእርሳቸውን አልባሳት ለብሶ ተሰብስቦ በሚጠባበቀው ህዝብ ፊት አሳምሮ አቀረበው፡፡ ከዚያም ተሰብሳቢው ካዳመጠ በኃላ እንደተለመደው ጥያቄዎችን ማቅረብ ሲጀምር ዓይኑ ፍጥጥ ብሎ ቀረ፡፡ ሆኖም ሹፌሩ ጮሌ ስለነበረ “ይህንን ተራ ነገር የማታውቁ ሰዎች እንደሆናችሁ ኣለውቅም ነበር፤ በጣም አዝናለሁ - ይህንንማ የእኔ ሹፌር አሳምሮ ይነግራችኃል” ብሎ ለዋናው ፕሮፌሰር ሰጥቶ ተገላገለ ይባላል፡፡ በል ወዳጄ ዳንኤል ዘጣና ዳር፡- ወይ ፕሮፌሰሩን አቅርብልንና እንሞግታቸው ወይም ሹፌሩ ከዚህ በኃላ እንዳይጽፍ ንገርልን!
   አመሰግናለሁ!
   ዘጣና ዳር፡፡

   Delete
  2. Well i see the other way round. I see it in a way that promotes our unique church. Whoever use this form of writing knows it is from our church. And I, personally, believes no one will dare to use this form of writing unless he/she is from our side. Endene Yibel Yiberta Beyalewu!

   Delete
  3. quchera You looked it on he right way. This may bring some thing unexpected tomorrow. Dn.Daniel U are not right today. Yebetekristiyanachin Legna Astemihirot Enji Lealemawiyan Mawedesha Metekem legizew minim bayihonim Lenegew tata eferalehu. Bizu tanakash wushoch betenesubet zemen meleyachinin bezih melik metekem tata yametal.

   Delete
  4. Dear Anonymmous,

   Lemin Mahiberekidusanin Tanesaleh Sew Asteyayet Ymistew Erasun Chilo new.Be Ergit Mahiberune Endemiteferaw Yetsafekew Yasabikbhal.

   Betekirstiyans Yetibeb balebiet Aydelechmine?

   Delete
  5. @Henok, you raised a good point. This is an IPR issue which is very immature in the country in all aspects. Nevertheless, the church obviously owns this methodology of writing... The anonymous guy who wrote a confused comment in Amharic above, please focus on the idea wherever it comes from instead of acting like you know a lot.

   Delete
  6. Hadis Alemayehu is an author. He tried to put the existing life style in that era, place and society in a fiction form. Several artists also tried to copy some Church treasures in their worldly work. I cant say anything about them. It is up to the person who follows them. But, when the preacher Deacon is manipulating the precious treasures of the church, in this case Andmeta, it is gross! Disgusting! ወይ ጎራውን ከአርቲስቶች ጋ ይመድብልን እና እኛም ትችታችንን እናንሳ። በነገራችን ላይ ዳንኤል እዚህ ብሎግ ላይ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ቀዝቀዝ ብለሀል። ምንድን ነው ነገሩ? አንድ ጥሩ ፅሁፍ ነበረህ "ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/፡የክርስትና ዘመናዊው ጠላት" አንተን እዛ ውስጥ ያገኘውህ መስሎኝ ነፍሴ ተጨነቀች።

   ቀነኒሳ አንበሳ፥ ሐይሌ አንበሳ፥ ቀነኒሳ እና ሐይሌ አንበሳ በቃ በቂ ነበር። ምንም ሚስጥር ሳይኖረው አንድምታዊ ለዛ መስጠት ትንሽ ቅር ያስብላል።

   ወልደ ስላሴ!

   Delete
  7. “ነገር ከስሩ ውሃ ከጥሩ” እንዲሉ አስተሳሰቤን ግልጽ ለማድረግ የተጠቀምኩበት መንገድ ግራ አጋብቶህ ሊሆን ይችላል እንጂ፤ እኔስ አንተ እንዳልከው ግራ የተጋባ ጽሁፍ እንዳዳበርኩ ወይም ብዙ እንደማውቅ ለማሳየት የተጠቀምኩበት እንደሆነ አላስብም፡፡ ደግሞስ ማንነቴ እስካልታወቀ ድረስ እንዴት አድርጌ ነው ብዙ እንደማውቅ ለማሳየት የምሞክረው፡፡ ወይ በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ተክለማርያም ንኝ ወይ ጋዜጠኛ ስብሀት ገብረ እግዚአብሔር ነኝ አላልኩ፡፡ ታዲያ እንዴት አድርጌ ነው እንደማውቅ አድርጌ ብዙ “አክት” የማደርገው፡፡ የሠጠኸኝ አስተያየት አስተሳሰብን ከመሞገት ይልቅ ግለሰብነቴን ለመድፈር ያለመ ሁኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
   ለምንድን ማህበረ ቅዱሳንን ታነሳለህ? ላልኸኝ፡- አንድ ጊዜ አንብበህ ወዲያው ለመረዳት ከጠጠረብህ ደግመህ ሁለቴ የማንበብ ልማድ ብታዳብር አንዳንዱ ነገር ጥያቄ ሳያስፈልግህ እራስህን መርዳት ትችላለህ፡፡ ማህበረ ቅዱሰኔን አትንካብኝ ከሆነ ስሜትህ ለዚህም አንድ ሁለት የምትለው በቂ ምክንያት ሊኖርህ ይገባል፡፡
   ሆኖም ማህበረ ቅዱሳን ባለፉት ዕድሜዎቹ በማህበረሰቡ ዘንድ የፈጠረው “ናሬቲቭ” ስላለው በዚያ መንገድ ያንን ዓይነት አስተያየት ከማህበረ ቅድሳን ብቻ እንደሚመነጭ እንዳወቅሁበት ለማሳየት የተጠቀምሁበት ነው፡፡ ማህበረ ቅዱሳንን እንደምትፈራ ያሳብቅብሃል? አወ እና አይደለም፡፡ አወ፡- ከተወሰነ ዘመን በኃላ የማህበረ ቅዱሳን አሻራ በአገራችንና በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደቅብአትና ጸጋ ሁሉ የተለየ ቡድን ይሆናል የሚል ፍርሃት አልኝ፡፡ ይህ ደግሞ ብግልጽ ሳይሆን አባላቱም እንኳን ባልነቁበት መንገድ ቤተ ክርስቲያናችንን እያዳከመ ሌላ እየበረታ እንዲሄድ የማድረግ የጠፍ ጎዳና መሆኑ ያሰጋኛል፡፡ ሌላው ፍራሃቴ ደግሞ ልክ እንደ አሁኑ ያለውን አመለካከት (ኦረቶዶክሳዊ ስነ ፅሁፍና ዓለማዊ ጽሁፍ በተጨማሪም የዜማ ሁሉ መሰረት ቅዱስ ያሬድ ነው ከማለት ይልቅ ኦርቶዶካሳዊ ዜማና ዓለማዊ ዜማ ማለት ) ከቀጠለ ቤተ ክርሰቲኗን እያራቆተ ሰው አልባ ያደርጋታል የሚል ፍራቻ አለኝ፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ በማህበረ ቅዱሳን ስር ካሉት አባላት ይልቅ በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት ከቤተ ክርስቲያናችን የተፈናቀሉ ብርቅየና ዓይናማ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ሳስብም ማህበረ ቅዱሳንን እፈራዋለሁ፡፡
   አይደለም፡- የማህበረ ቅዱሳንን ቅንዓት እወደዋለሁ፡፡ እኔንም ጨምሮ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያልሰራችውን ታላቅ ውለታ እንደሰራ አምናለሁ፡፡ በትክክለኛ ቅንዓት ባይሆንም ቢያንስ ቢያንስ ቤተ ክርስቲያኔ ቤተ ክርሰቲያኔ የሚል ወጣት እንዲኖር የተጫወተው ሚና የሚናቅ አይደለም፡፡ ይህ የሚያስደንቀኝ ይህን ለማድረግ ሙሉ መብትና ስልጣን ያላቸው ሹማምንተ ቤተ ክርስቲያን ያላደረጉትን እነርሱ ስላደረጉት ነው፡፡ ሆኖም ቅንዓቱ በብልሃትና በብስለት ለቤተ ክርስቲያናችን እንደሚጠቅም ሁኖ አልተያዘምና ከመጠምጠም መማር ይቅደም የሚል ምክር አለኝ፡፡
   ጎበዝ፡- ዳንኤል ደስ የሚሉ ነገሮችን ሲያቀርብ እየተመለከትኩት ነው፡፡ ከዚያ በመቀጠል ግን ሁለት ድክመቶችን እየተመለከትኩ ነው፡፡ አስተሳሰብን በአስተሳሰብ ከመሞገት ይልቅ ግለሰቡን መጨርገድ፡፡ የቱን ያክል ግለሰብነቱን ብንጨፈጭፈውም አስተሳሰቡን አንድ ሁለት እያልን እስካልሞገትነው ድረስ የእርሱ አስተሳሰብ ገዥ ሁኖ ይቀራል፡፡ “ለተናካሽ ውሾች መላያችንን አሳልፈህ ለምን ሠጠህ” የሚል አስተያየት ብሎ ነገር የለም፡፡ “መንፈሳዊ ነህ?፣ አርቲስት ነህ? ምንድን ነህ?” የሚል አስተያየት ፍሬቢስ ነው፡፡ እንዲያውም ተጠቂነትን የሚያንጸባርቅ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ይህንን ላልክበት አንድ ሁለት አሳማኝ ነጥብህን ብታስቀምጥ ጸሐፊው ደግሞ ሁለተኛ እንዳይደግመው ታኮ እንደማስቀመጥ ይሆንልህ ነበር፡፡ አሁን ግን ዳንኤል ይቅርና ይህ ጥንታዊ የኣጻጻፍ ዘይቤ እንደገና እንደአንሰራሩት እንደጎጃም አዘነው፣ ተነፋነፉ፣ እጀጠባቡ ሁሉ ይህ ጥዑም ስነ ጽሁፍም እንደሰደድ አሳት ሲያንሰራራ ታየዋለህ፡፡ ምነአለ በለኝ፡፡ ምናለ እንግዲያ እንደዚህ የተቀበሩና በመሞት ላይ ያሉትን ሌሎችንም ጌጦቻችንን ወደ አደባባይ የሚያወጣልን በተገኘ፡፡
   ሁለተኛው ድክመት የእራሱ የዳንኤል ድክመት ነው፡፡ ልብ ብለህ ካላስተዋልኸው ወይም ይህንንም አካሄድ ካልወደድኸው ወይም አዳሜ እንደፈለገው ይተንፍስ ካላልህ በቀር፤ አብዛኛውን ጊዜ ዋናው ነጥብህ እንዲቀየስ ይደረጋል፡፡ ለዚህም ሁኔታ እንደ አንድ መንስዔ አድርጌ የምወስደው በድጋሜ የመሳተፍ - የመሟገት ነገር ስለሌለህ ይመስለኛል፡፡ ምንአልባት ይህን ሁሉ የምታስተናግድበት ጊዜ ከሌለህ በቀር፡፡ እንደኔ እንደኔ ግን “ብላግህ” የእብድ ማሳ ዓይነት ከመሆን ብትከላከል ደስ ይለኛል፡፡ ምክንያቱም ብዙ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ታዳጊ ልጆችም ሲያነቡት በእርግጥም ጥሩ መስታዎት እንዲሆንላቸው፡፡
   እረ ጎበዝ ነጥብ በነጥብ እየተሟገትን ጥሩ ነገር እንቅረጽ፡፡ ምነው የተወለድንበት አገር እኮ የዛሬን አያድርገውና ሁሉም ነገር ጉባኤ እየተዘረጋለት ዳኛ እየተሰየመለት በውይይት የበሰለ ነበር፡፡ ዛሬ በእጃችን ላይ ያሉት ዶግማዎች፣ በርካታ ስነቃሎችና ወዘተዎች በውይይት የዳበሩ እንደሆኑ ልብልንል ይገባናል፡፡ በጥንት ጊዜ እንደዚያ ዓይነት የመሟገት ትልቅ ስብዕና ከነበረ ከእኛ ደግሞ እጥፍ ይጠበቃል፡፡ ድሮኮ የፍርድ ቤት ችሎት ያለበት ሰው ሳይቀር በጠበቃ ሳይሆን እራሱ ለራሱ ቆሞ ይሞግት እንደነበረ አናውቅም? ዶግ አመድ ይወልዳል የእሳት ልጅ አመድ እንዳይሆንብን እንጠንቀቅ፡፡ አሳብ ለአሳብ ነጥብ በነጥብ እንወያይ፡፡ መዘላለፍ አይቅናን፡፡
   ብርታት እንዲሰጥህ ጸሎቴ ነው፡፡
   ከጣና ዳር


   Delete
 10. Well said D/n Dani.

  ReplyDelete
 11. እንግዲህ ምን እንላለን ግሩም የሆነ አገላለጽ ነው፡፡


  "አንድም አንበሳ ከአፍሪካ ሄዶ በእንስሳት ማቆያ ውስጥ ካልሆነ በቀር በፈረንጅ አገር አይገኝም፡፡ እንደ ቀነኒሳ ያለ ሯጭም ከአፍሪካ ሄዶ ለሰው ሀገር ይሮጥ ይሆናል እንጂ በፈረንጅ አገር አይገኝምና ቀነኒሳን አንበሳ ብለውታል፡፡ አንድም አንበሳ የሀገራችን የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነትና የድል አድራጊነት ምልክቷ ነው፡፡ ኃይሌና ቀነኒሳም በረሃብ፣ በችግርና በጦርነት ስሟ በክፉ የሚነሣውን ሀገራችንን በጀግንነት፣ በድል አድራጊነትና በአልበገር ባይነት እንድትታወቅ አድርገዋታልና አንበሳ ተብለዋል፡፡
  ያሉንን አናብስት እያወደስን ሌሎች አናብስትን እናፈራለን፡፡"


  እግዚአብሔር እጆችህን ያበርታቸው ጣቶችህንም ያለምልማቸው፡፡

  ReplyDelete
 12. ቀነኒሳን አንበሳ አሉት፡፡ ኃይሌንም አንበሳ አሉት፡፡ እንደምን ነው ቢሉ፡፡ አንድም አንበሳ ሲተኛ የሞተ፤ የደከመ፣ የታመመ ይመስላል፡፡ እንስሳት እየመጡ ይጎበኙታል፡፡ ያዩታል፤ አንዳንዶቹም ይራመዱታል፡፡ ሌሎቹም አንበሳው ደክሟል ብለው የአራዊት ንጉሥ እኛ ነን ይላሉ፡፡ እንደ ዝንብ ያሉትም ይወርሩታል ‹‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጨዋቻ ይሆናል›› እንዲሉ፡፡ እርሱ ግን የሚያደርገውን ያውቃልና ዝም ይላቸዋል፡፡
  ዲ/ዳኒ በርታ መልካም እይታ ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. ይድረስ ለዳንኤል ክብረት!

  ለብሔራዊ ቡድኑ ትረካህን በጉጉት ስጠብቅ አስኮረፍከኝ! አቦ የሆነ ነገር በልና ሞራል ስጠና።

  BBC የሚሉት ጠንቋይ እንዴት እንደጠላሁት! ስለሩጫው ሲያወሩ የደከመችውን የተራበችውን ኢትዮጲያን አሳይተውን ነበር። ሩጫው ላይ ደግሞ የለንደንን ገነትነት ነገሩን። አዎ ደሃ ነን ግን ግን ለዓይን የሚማርክ ቦታ በሀገሬ የለም እንዴ?? ለንደንን አየነው ከግር እስከራሱ ገነት ነው ያለ ማን ነው?

  ይሄን ሞ ፋራ ማን አሸንፎት እያልኩ በጉጉት ስጠብቅ ጀግናው አንበሳ አሸነፈውና ይኸው ከልብ ተደሰትኩ።

  ReplyDelete
 14. Dear Writer of the article,
  I also felt disgusting and is embarrassing for our church as well as for our forefathers who teach the secret of the bible and "Awaled" in "Andemta". Pls. do not repeat such type of writing, give respect who deserves to be respected, it is our great Church and all her saints.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይህንን አስተያየት ሳልፈልግ ነው የፃፍኩት
   አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ከፅሁፉ ውስጥ ነቁጥ ቢያጡ አጻጻፉን ሲተቹ አየሁና ግር አለኝ፡፡ ለአንዱ ተቺ ሌላው የሰጠው ምላሽ ደግሞ ይበልጥ አናደደኝ ምክንያቱም ያልተገባ ርዕስና ትርጓሜ ለመጀመሪያው ተቺ ሰጥቶ ስለ ማኅበር ፖለቲክስ እንዲሁም የቤተክርስቲያን ዜማ ስርዓት ላይ ትችት መሰል አስተያየት በመሰንዘሩ፡፡ ያልገባኝን ነገር ግን ላንሳ የቤተክርስቲያን የአጻጻፍ ስልት ለዓለማዊ ህይወት ሥነፅሁፍ አይጠቅምም ወይ (በተለይም ለመልካም ነገር)?? እኔ በጥቂቱ እንደምገነዘበው በኢትዮጵያ ታሪክ በመልካም ስነፅሁፍ ስራዎቻቸው የሚታወቁ ሰዎች በቤተክህነት ትምህርት ውስጥ ያለፉ ናቸው፡፡ እንዲያውም ለአማርኛ ስነ ፅሁፍ መዳበር የቤተክርስትያን አስተዋጽኦ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ አንድ የሥነፅሁፍ ስልት ጥቅሙ ምንድነው እንዴትስ ነው ሁሉ ሊያውቀው ወይም ሊዳብር የሚችለው ወይስ ለቤተክርስቲያን ብቻ ተለይቶ የተሰጠ የአጻጻፍ ስልት አለ ወይ??
   እንደው ወደፊት ስለዚህ ነገር ወደፊት የምትለን ነገር ቢኖር ጥሩ ይሆናል፡፡
   በተጨማሪም ያልተገባ አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች ፅሁፍ እዚህ ባይታይ ወይምየጸሀፊው ምላሽ ከስር ቢኖር ጥሩ ነው፡፡

   Delete
  2. Why do we have to see things in a wrong and negative way? Dn Daniel write what he see and let us see things in a different and wonderful perspective. what is wrong in writing in such a wonderful way? Our church is the base for all education and writing in our country. So what is the bad thing to promote and keep it alive of our writing and way of teach? why do we have to see things in the wrong manner? I believe his writing will add a great thing and also promote Orthodox churches writing and teaching. It will be an answer for those who doesn't know the writing of "andemeta". May God bless us all.

   Delete
 15. is that forbidden to use andimta in other non religious article? don't be foolish this is the way how to describe tings in many ways and note that it is created by human being not Gods word. ena atakabidu beandimta yeminegerewun ewunet (yeegziabher kal)mekebel melkam new abatochim bihonu andimtan yefeterut sew mistirun bedenbi endiyawukew new enji lela neger yelewum. emnetina kuanquan ley eshi

  ReplyDelete
 16. ዳኒ ይሄ አካሄድ አያዋጣህም፡፡ በውኑ መንፈሳዊ ነገርን ከኣለማዊ ነገር ማዛመድ ይቻላልን፤ እንደ አንድ የወንጌል ሰባኪ እንደ መምቁ ዮሐሃንስ መንግሠተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሀ ግቡ ከማለት በቀር ስለስጋዊያን ሩዋጮችና ጎበዞች መስበክ ተገቢ አይደለም፤ እነርሱኮ ያሸነፉት እንደነርሱ ሥጋ የለበሱትን ወንድሞቻቸውን እንጂ ረቂቁን ጠላት ዲያቢሎስን አይደለም፤ ይልቅስ ዲያቢሎስን አሸንፈወው መ/ሰማያት የወረሱትን አድንቅ፤ ለክርስቲያን የሚጠቅመወው ክርስቶስን መምሰል ነው፡፡ አንዳንዴ ዘፈንና መዝሙርን የሚቀላቅሉ ሰዎች አሉ፡፡ ለምሰሳለሌ አንዳንድ ታዋቂ የበገና መዝሙር ዘማሪያን በዘፈን ውስጥም ገብተው ሲዘፍኑ እናያለን፤ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔርና ከዓለም መምረጥ ግድ ይላል፡፡ ባለፈው ስለ ባነንዲራ የጻፍከው ቅር አሰኝቶኛል፤ ምክንያቱም ከቤ/ክ አስተምህሮ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም በማለትህ፤ ማሰተካያ ብትጽፍበት መልካም ነው፤ አንተ እነንዳልከው ይህ ጉዳይ በመጻህፍት ያልተወሳ ሳይሆን በተለያዩ መጸኀፍት ውስጥ ተገልጾአል፤ በባንዲራው ኖህንና የተሰጠውን ቃልኪዳን እናስባለን የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነውና፤ በሌላ መልኩ ቀስተ ደመና የእመቤታችን ምሳሌ ነው፤ በማህሌተ ጽጌ መጸጽሐፈፍ ላይ ‹ቀስተ ደመና ማሪያም ትዕምርተ ኪዳኑ ለነኖህ... ይላል፤ ስለዚህ ባንዲራ በቤ/ከናችን መንፈሳወዊ ትርጉም አለው፤ ጨርቅ ነው... ምናምን እንደሚባለው አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 17. Daniel deg belehal.xehufoch bemanawem arest lay arki nachew .berta egziabher kant gara yehun.

  ReplyDelete
 18. Daniyee,long live my HERO!!! you are Anbessa too.You maight never run on the track or cross the finish line riven ,but you are running cross country to feed us this kind sweet articles.I hope you ignored those rubbish comments wrote by some rubbish people.

  Peace for you and your family.

  ReplyDelete
 19. Selam Bro

  andemtahen Gen....

  ReplyDelete
 20. Even if all us are from some groups, we can have our personal opinion. So Daniel can has his personal view on his private blog which does not belong to the church. If any one has personal or church case with him let it be at church not on the blog. moreover, the church itself should not be an island that no one can use it and no one can live in it. Church is for the people from God. Our forefathers were not writing in heavenly language. that was in our language at that time. Therefore, the language did not belong to the church, but the church writers used the language that belongs to all people of the time in just adding some spiritual context in it. He is the unbiased writer I have ever seen in my life. we should appreciate him for his good insights and constructive social criticism.

  ReplyDelete
 21. I thought he is talking about our hero athlets.did I get lost somewhere or what? they mix up his blog about athlets with church issue?

  ReplyDelete
 22. The-Tana Dar "shut your mouth" Kalcha....

  thank you Dane

  ReplyDelete
 23. እንደዚህ አይነት መድረኮች ሀሳባችንን እንድናንሸራሽርና የአስተሳሰብ አድማሳችንን እንድናሰፋ ይረዱናል፡፡ እንደሚመስለኝ አጥብበን ማሰባችን ላለማደጋችን ምክንያት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ጽሁፎቻችንን በአንድምታ የአጻጻፍ ዘይቤ ቢፃፉ ምኑ ላይ ነው የቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካው? በዚህ ዘይቤ የተላለፈው ምልእክት ፀያፍ ቢሆን ኖር ሀሳቡ ለአፃፃፍ ዘይቤው አይመጥንም በተባለ ነበር ነገር ግን የተላለፈው መልእክት መልካም ነው፡፡
  ቤተክርስቲያናችን ለሀገራችን ያበረከተቸው አንድምታን ብቻ ነው እንዴ? የዘመን አቆጣጠሩ፣ ፊደላት፣ የባእላት አከባበር(የሃይማኖት ሥርዓት የሆኑ ግን እንደባህል የተወሰዱ) ሌሎችንም አበርክታለች፡፡ ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያናችንን ከፍ የሚያደርግ እንጂ የሚያዋርድ አይደለም፡፡
  የቤተክርስቲያናችን ክብር ተነካ ተዋረደ የምንለው መቼ ነው? እንደሚመስለኝ የአምልኮ ሥርዓት የምንፈፅምባቸውን ነገሮች ለሥጋዊ አሰራር አሳልፈን የሰጠን ከሆነ ነው፡፡ ለምሳሌ ነዋየ ቅድሳቱን ለአለም አገልግሎት ብንጠቀም ወዘተ…
  አለማስተዋላችን ነው እንጂ የአፃፃፍ ዘይቤዎቻችን፣ የህንፃ አሠራር ጥበቦቻችን፣ የጨረቃና የከዋክብት ዑደት ጥናቶቻችን እንዲሁም ሌሎች ብዙ ስልጣኔዎችን ለአለም ያበረከተች ቤተክርስቲያናችን ነበረች፡፡ አለም ስልጣኔን ከአባቶቻችን ወስዶ ከአባቶቻችን የበለጠ በመሰለ ጊዜ የእኛ ድርሻ መሆን የነበረበት ይህ ጥበብ እኮ የአባቶቻን ነው ብለን ማረጋገጥ ሲለጥቅም አለም የሌላትን ቤተክርስቲያን ሀብት በማካፋል የቤተክርስቲያናችንን ቀደምትነትና የእውቀት ምንጭነት ማስተዋወቅ ዕውቀትን ማካፈል ይልቁንም እንደ ቀደምት የአገር ቋንቋችን ግዕዝ አሁን በቤተክርስቲያን አገልግሎት እንደተወሰነው፣ ሊጠፋም እንደሚዳዳውና ቀጣዩ ትውልድ እንደማያውቀውና እንደማፈልገው ከመሆኑ በፊት ሀብታችንን(እውቀታችንን) ከፍ ከፍ በማድረግ ልንጠቀምበትና ልናሳድገው የሚገባ ይመስለኛል፡፡ ደብቆ ማስቀመጥ ለቤተክርስቲያናችንንም ለእኛም የሚበጅ አይመስለኝም፡፡
  በድሮ ጊዜ ሃማኖት፣ ህዝብና መንግስት ብዙም ባልተራራቁበት ዘመን የቤተክርስቲያን ሀብቶች የአባቶችም ድካም የታወቀ የተከበረ እና የሚያገለግል የሚያስከበር ነበር፡፡ ሁኔታዎች ሲሰፉ ህዝብ የአባቶችን እውቀትና ጥበብ ከማወቅ በራቀ ጊዜ የሚሻለው ጥበብን መደበቅ ነው ወይስ በመጠቀም ህብቱን ሳያውቅ ሌላ ፍለጋ የሚኳትነውን ትውልድ መመለስ ነው? እባካችሁን ጠባቦች አንሁን አስተዋይነት አይራቀን!

  ReplyDelete
 24. አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎጭ የዚህን የአጻጻፍ ዘይቤ ለቅዱሳን እንጅ ለነሐይሌ … አይገባቸውም አይነትና የቤተክርስቲያኗን ክብርንም ይነካል ያሉ መሰለኝ፡፡ እኔ በበኩሌ ግን በዚህ አልስማማም፡፡ ተወደደም ተጠላም የኢትዮጵያ ማንኛውም ስልጣኔ አጻጻፍን ጨምሮ የሷ( የቤተክርስቲያኗ) ሐብት ነው፡፡ ስለዚህ ከሷ ብንዋስ የተዋስነውንም ለመልካም ነገር ብናውለው የሚያስነቅፍ አይደለም ያስመሰግናል እንጅ ፡፡
  ካሣ ዘራያ

  ReplyDelete
 25. You all are entitele to your opinions but,what is wrong in using the "andmta" description methods to describ other topic. I think that will develop the people klowledge of the method. However, I have fear that their is no thanksgiving to the olmighty throughout the article for helping them to achiev whatever they wer achieved. As if one can achieve any thing without God's will .If others believe that can be done it alon without God help we shouldn't .We shall prize God for allowing our people to shine in foreign land,espesly Daniel as I see you as an icon of the church! I am affred to say that I have seen this kind naked article of yours when team Ethiopia wins Sudan in Addis. No one was thanking God other than dancing around with groweshebaye. Therefore, the happyness dose not last long. "Don't forget God give to test the loyalty too". Sorry D/N Daniel you are still my best writer it is because essy to see other mistackes than owns. Perhaps,I could be the worst if I ever achieve what you are achived!
  Forgive me you all for any offence that I may cause by saying this?

  ReplyDelete
 26. K/DANIEL
  I LIKE YOUR WAY OF EXPRESSIONS,I WISH I CAN READ ONE ARTICLE A DAY
  THANKS AND GOD BLESS YOU !!

  ReplyDelete
 27. Dear k/ Daniel
  I love your way of expression and i wish i can read at leastto read one article a day !!
  God bless you dani

  ReplyDelete
 28. dear k/daniel well done !
  god bless you

  ReplyDelete
 29. ene yemigermegn silebetekrstian enkorekoralen yemilu sewoch yebetekirstianin agelgilot yegan mebelrat madreg yemifelgut,mebratnetuanm keatir mawtat yemaychilu sewoch nachew.eski ahun tekorekorn kalachihutna kezih tshuf yebetekirstianin talaknet yetenagere manew????

  ReplyDelete
 30. tnx ዳኒ አምላክ ብእርን እንደ ጦር ከሚፈሩ ሰዉሮ እንደ ግብረ_መልስ ለሚወስዱ ያጋልጥህ::

  ReplyDelete
 31. የኢትዮዽያ ስነ ፅሁፍ መሰረቱ ማን ሆነና በማን ላይ ሆነሺ ማንን.....የኢትዮዽያ የሆነ የኦርቶዶክስ ያልሆነ ምን አለ? ንባብ እና ትርጉም ያልገባዉ ወደ ፊደል ተራ እኔ ግን ለዳንኤል; ወረከብናሃ ለዕድ እንተ ትነዝህ ፍሬሃ: ክሱተ በንባብ ወሚስጥረ ፍካሬሃ:: /ዘሩባቤል ሸራህያ/

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሜን ወአሜን!
   ዘጣና ዳር

   Delete
  2. መአት ነገር አለ፡፡

   Delete
 32. ያንድምታን ቦታን በመልቀቅህ አዝናለሁ በቃ አንድምታ አነንዲህ ሆነ ወግ ሲበዛ......

  ReplyDelete
 33. Dn Dani bertalign!!!

  ReplyDelete
 34. Dani beregete dehere gezu sijemere yebetekrestanene guday yemimelekete nebere. Bezihe mekinyate enezihe asteyayetoch letelalefu chelewale. Hasabune tekeblehe ye kesarene lekesare mestetu melkam yemeselege.

  ReplyDelete
 35. ዲ/ዲያቆን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን።እግዚያብሔር ይባርክህ በርታ።

  ReplyDelete