Friday, August 9, 2013

ጉዞ ወደ ምድር ጥግ (ሦስተኛ ክፍል)

አውሮፕላኑ ወደ ምድር ዝቅ እያለ መሆኑን አስተናጋጇ በመናገር ላይ ናት፡፡ የምናርፈው ባንዳር ሰሪ ባጋዋን የሚባለው የብሩናይ ዓለም ዐቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ነው፡፡ ብሩናይ እስከ ዛሬ ስሟን እንኳን ሰምቻት የማላውቅ ትንሽ የደቡብ እስያ (ኦሺንያ) ሀገር ናት፡፡ ወደ እርሷ ለመድረስ ከዱባይ ተነሥተን የ8 ሰዓት ከ15 ደቂቃ በረራ ነው ያደረግነው፡፡ ብሩናይ ማለት ‹የሰላም ሀገር›› ማለት ነው ይላሉ ሀገሬዎቹ፡፡ ሲያቆላምጧትም ‹ብሩናይ ዳሩ ሳላም› ይሏታል - ብሩናይ ሀገረ ሰላም ለማለት፡፡
ይህች በደቡብ እስያ በቦርኒዎ (Borneo) ደሴት ላይ የምትገኘው ትንሽ ሀገር ከዋናው የእስያ መሬት በቻይና ባሕር በኩል ትለይና በሌላዋ ክፍሏ ደግሞ ከኢንዶኔዥያና ማሌዥያ ጋር ትዋሰናለች፡፡ የቦርኒዎ ደሴት የሚገርም ነው፡፡ ከብሩናይ በቀር በደሴቱ ላይ ሌላ ሉዓላዊ ሀገር የለም፡፡ ቦታውን ማሌዥያና ኢንዶኔዥያ ተካፍለውታል፡፡
ብሩናይ በንጉሣዊ አገዛዝ የምትተዳደር ሀገር ናት፡፡ ሡልጣኑ የሀገሪቱ የመጨረሻው ወሳኝ አካል ነው፡፡ የመንግሥቷ ይፋዊ እምነት እስላምና መሆኑን የአየር መንገዱ መጽሔት ይናገራል፡፡ የንጉሡ አንደኛው ተግባርም እስልምናን መጠበቅና ማስተማር መሆኑን ይገልጣል፡፡ በነዳጅ ምርቷ የምትታወቀው ይህቺ ትንሽ ደሴት ከ16ኛው መክዘ ጀምሮ ወደ አካባቢው በሄዱ የአውሮፓ አሳሾች ትታወቅ ነበር፡፡ በተለይም ደቾች ከጥንት ጀምረው የንግድ ግንኙነት መሥርተውባት ነበር፡፡ በማጅላን የ1521 እኤአ የዓለም ጉዞ ወቅት ስፔኖች ወደ አካባቢው መጥተው ያዟት፡፡ የሀገሬው ሕዝብ ግን በ1578 ስፔኖቹን ተዋጋቸው፡፡ በኋላ ደግሞ በ1888 ሀገሪቱ በእንግሊዝ ጥብቅ ቁጥጥር ሥር ሆነች፡፡ በ1959 ደግሞ የጃፓኖች የወታደር መሥፈሪያ ተደረገች፡፡

በ1984 ከእንግሊዝ ነጻነቷን ያገኘችው ብሩናይ እጅግ በጣም ሀብታም ሀገር ሆናለች፡፡ በሰብአዊ ዕድገት መለኪያ መሠረት ከደቡብ ኤስያ ሀገሮች ሁሉ ከሲንጋፖር ቀጥላ የምትጠቀስ ሀገር ነች፡፡ የአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቷ ከሕዝቧ ጋር ሲነጻጸር ብሩናይ በዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ናት፡፡ በ2011 የሀገሪቱ ብድር ዜሮ ነበር፡፡ በዚህ ትፎካከራት የነበረችው ሊቢያ ነበረች፡፡ በፎርበስ መጽሔት መሠረትም ብሩናይ በዓለም አምስተኛዋ ሀብታም ሀገር ናት፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን የሕዝቧ ብዛት 408 ሺ ብቻ መሆኑን አትርሱ፡፡ አሁን ሀገሪቱን የሚመራው ሥርወ መንግሥት ላለፉት 600 ዓመታት ሳይቆራረጥ ከልጅ ወደ ልጅ እየወረደ መምራቱን በኩራት ይነግሯችኋል፡፡
አሁን ወደዚህች ሀገር እየወረድን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ እዚህ ቢያንስ ለሁለት ሰዓት ተኩል ያህል እቆያለሁ፡፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ምሥራቅ ስትጓዙ ቀኑ ከእናንተ እየቀደማችሁ ይሄዳል፤ ወደ ምዕራብ ስትጓዙ ደግሞ ጨለማው እየተከተላችሁ ይሄዳል፡፡ እንዲያውም አንድ ፓይለት አንድ ጊዜ ‹‹ለመሆኑ እኛ እንዴት ነው መጾም ያለብን? ከኢትዮጵያ ወደ ምዕራብ ስንሄድ ሌሊቱ ይረዝማል፤ ወደ ምሥራቅም ስንሄድ ቀኑ ይረዝማል፤ የትኛውንስ ሰዓት ነው መጠቀም ያለብን? የተነሣንበትን ነው ወይስ የደረስንበትን?›› ሲል ጠይቆኝ ነበር፡፡ አሁንም እኔ ግራ ገብቶኛል፡፡ ለመሆኑ የሐዋርያት ጾም ተፈትቷል ወይስ እንደቀጠለ ነው?

ከአውሮፕላኑ ወርደን ወደ ዕንግዳ ማረፊያው ስንገባ ግድግዳው ሁሉ የሀገሪቱን መልክዐ ምድር፣ የንጉሣዊውን ቤተሰብ ተግባር፣ ታሪካቸውንና የወግ ዕቃዎቻቸውን በሚያሳዩ ትላልቅ ፖስተሮችና ፎቶዎች ተሞልቷል፡፡ ግን እናንተየ በኛ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የተጠና የሀገሪቱን ገጽታ በሚገባ የሚያሳይ ነገር የምናየው መቼ ነው? እዚህና እዚያ ከተለጠፉ፣ ተከታታይነትም ሆነ ተዋሕዶ ከሌላቸው ፎቶዎች ወጥተን፤ የታሰበበት፣ በባለሞያ የተዘጋጀና ሀገሪቱን ሊያሳይ የሚችል የሥዕል፣ የፎቶና የባሕል ዕቃዎችን ትርዒት አውሮፕላን ማረፊያችን ላይ መቼ ነው የምናየው? ከአውሮፕላኑ ወጥታችሁ በዋሻው በኩል ወደ ዕንግዳ ማረፊያ እስክትደርሱ ድረስ ግራ ቀኙ ሁሉ መልእክት ብቻ ነው፡፡ እንደ እኔ ያለው ተላላፊ መንገደኛ ሀገሪቱን ለመጎብኘት ባይችል እንኳን በአጭሩ ዐውቋትና ሌላ ቀን ለመመለስ ቃል ገብቶላት ይሄዳል፡፡
ዕንግዳ ማረፊያው ስትደርሱ ደግሞ ስለ ሀገሪቱ የሚገልጡ ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ ፖስተሮች፣ ካርታዎች እዚህም እዚያም ተቀምጠው ውሰዱኝ ውሰዱኝ ይሏችኋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሀገሬ አየር መንገድ ከሌላ ሀገር ስመለስ የሚገርመኝ ነገር አለ፡፡ በተለይ ከአሜሪካ መልስ፤ አውሮፕላኑ ውስጥ ስትገቡ ኒውዮርክ ታይምስ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ታይምስ መጽሔት ይሰጣችኋል፡፡ ሀገሩ ናፍቆት ለሚመጣ ሰው እነዚህ ምንድን ናቸው? ምናለ ቢያንስ አዲስ ዘመን ጋዜጣ (መቼም ሌላውን እንዳልል ዕዳው ብዙ ነው ብዬ ነው) እንኳን ቢያድሉ?
ሌላ ሀገር ያላየ ሰው በሁለት ነገር ዕድለኛ ነው፡፡ በአንድ በኩል ‹‹በዓለም አንደኛ በአፍሪካ ሁለተኛ ነን›› የተባለውን በሰላም ተቀብሎ በደስታ ለመኖር ይቻለዋል፡፡ እኔ ወደ ኬንያ በኩል እስክበርር ድረስ ‹‹ለምለሟ ሀገሬ፣ ጫካ የሞላብሽ›› የሚለውን እንጉርጉሮ በደስታ እሰማው ነበር፡፡ ኋላ ተበላሸሁ፡፡ በሁለተኛ ነገር ሌላ ሀገር ያላየ ሰው አይናደድም፡፡ እነዚያ በ30ዎቹ፣ 40ዎቹና በ50ዎቹ ወደ አውሮፓ እየሄዱ ይማሩ የነበሩ ልሂቃን እዚያ ያዩትን ከሀገራቸው ጋር ያነጻትሩና ‹‹ምን ነካን›› እያሉ በብስጭት ስንት መጽሐፍ ጽፈዋል፡፡ እነ ከበደ ሚካኤል ‹ጃፓን እንዴት ሠለጠነች›› የሚል መጽሐፍ ሲጽፉ ዓላማቸው ከጃፓን ሥልጣኔ እንድንወርስ ነበረ፡፡ የዚያን ዘመን ሰዎች ‹‹ሥልጣኔ ምንድን ነች›› ሲሉ ሞያ ከጎረቤት እንድንማር ነበር፤ እነረ ‹አርአያ› የተጻፉት ማኅበረሰቡን ለመሞገት ነበር፡፡ ኢትዮጵያን የምታክል የታሪክ፣ የእምነትና የተፈጥሮ ሀብት ሀብታም ሀገር ከእርሷ ያነሰ ታሪክና ሀብት ባላቸው ሀገሮች ተበልጣ ማየት ዋንጫ ከማጣት በላይ ጉበት ይልጣል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ባለ ሥልጣናት ለልምድ ልውውጥ እየተባለ ብዙ ሀገር ይዞራሉ፡፡ ለመሆኑ ምን ዓይተው ነው የሚመጡት? ምንስ ተምረው ነው የሚመለሱት? ወይስ ሌላ ውጭ ሀገር አለ እነርሱ ብቻ የሚሄዱበት፡፡ አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡ ቢያንስ ለመሥሪያ ቤታቸው ሰዎች ያዩትንና የሰሙትን በማካፈል እንኳን ዕውቀትና ልምድ አያሸጋግሩም፡፡ ሲመለሱ እንደዚያው እንደሄዱት ሆነው ነው፡፡ የቢሮአቸውን አሠራር እንኳን ለመቀየር አይሞክሩም፡፡
ምሁራኑስ ቢሆኑ፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ውጭ ሀገር ሄደው ሠርተው መጡ ይባላል፡፡ ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ አሠራር የተሻለ ነገር ይዘው የሚመጡት ግን ስንቶች ናቸው? ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የፈተና አወጣጣቸው፣ የማስተማር ዘዴያቸው፣ የውጤት አሰጣጣቸው ያው እንደ ድሮው ነው፡፡ ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡
ከውጭ ሀገር መጥተው ሀገር ቤት ድርጅት የሚከፍቱ አብዛኞቹ ዳያስጶራዎች ገንዘባቸውን እንጂ የነበሩበትን ሀገር አሠራር ይዘው አይመጡም፡፡ መሣሪያው የውጭ፣ ቅኝቱ ግን የኢትዮጵያ ይሆናል፡፡ ሆቴሉ ‹‹ኒውዮርክ ሆቴል›› መስተንግዶው ግን የአራት ኪሎ ሆኖ ቁጭ፤ ካፌው የስታር ባክስ መስተንግዶው ግን የሠፈራችን ሻሂ ቤት ይሆንባችኋል፡፡ ሌላ ውጭ ሀገር ይኖር ይሆን?
እንዲህ እያሰብኩ ቆይቼ ቀና ስል ኢትዮጵያዊ መልክ ያየሁ መሰለኝ፡፡ በማያውቁት ሀገር የሚያውቁት ሰው ማግኘት፣ በበረሃ ውስጥ የምንጭ ውኃ እንደማግኘት ነው ይባላልና ኮሽታ እንደሰማ እንሽላሊት ነቅቼ ማየት ጀመርኩ፡፡ ኧረ እንዲያውም የሐበሻ ልብስ ነገርም ያየሁ መሰለኝ፡፡
አንዲት ወጣት፣ የሐበሻ ነጠላ የመሰለ ሻርፕ ደረብ አድርጋ ወደ እኔ በመምጣት ላይ ናት፡፡ መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት፡፡
ብሩናይ- ዳሩ ሰላም

45 comments:

 1. "Lela wuchi hager yinor yihon?" Egziabher yiwokew.

  ReplyDelete
 2. Really Interesting! God bless you! Dengel Mariam Kefetena tetebekeh!

  ReplyDelete
 3. አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡

  ReplyDelete
 4. Dear Daniel Kibret

  Thanks for ur message
  I did have a chance to visit Brunai, I was there for transit back to Ethiopia, the transit was more than 2hrs, so the Brunai Airways arrange a tour to the city and take us inside the city and visit the main places like there is Top part is GOLDEN Mosque,they tour leader told us the Architect was the king himself it nice to see it, got a phto. and also there is a big market, they sell everything but u have to choose ur food wisely. There are houses besides and around the it is realy cool to take photos of them.

  No drugs pass through the airport, it is a death sentence if caught. The main export is Oil, education is free for every citizen, People enjoyed their life, the city is not crowded.
  Dear Daniel if u use the same route back to Ethiopia and if u stay more than 2hrs ask the receptionist if is there any tour today? if there is they will let u know.

  PLEASE Daniel, get the DVD or CD of ur preaching from Australia if u come to Wellington we will get it.

  Enjoy Ur Stay in Australia.

  MAY GOD BLESS U AND UR FAMILY.

  ReplyDelete
 5. እነዚህ ባለ ሥልጣናት ለልምድ ልውውጥ እየተባለ ብዙ ሀገር ይዞራሉ፡፡ ለመሆኑ ምን ዓይተው ነው የሚመጡት? ምንስ ተምረው ነው የሚመለሱት? ወይስ ሌላ ውጭ ሀገር አለ እነርሱ ብቻ የሚሄዱበት፡፡ አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡ ይገርማል ሌላ ምን ይባላል፡፡ እ/ር ይባርክህ

  ReplyDelete
 6. እነዚህ ባለ ሥልጣናት ለልምድ ልውውጥ እየተባለ ብዙ ሀገር ይዞራሉ፡፡ ለመሆኑ ምን ዓይተው ነው የሚመጡት? ምንስ ተምረው ነው የሚመለሱት? ወይስ ሌላ ውጭ ሀገር አለ እነርሱ ብቻ የሚሄዱበት፡፡ አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡ ይገርማል እ/ር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 7. "መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት፡፡"

  ስለሁሉም ነገር እግዚአብሄር ይስጥልን አመሰግናለሁ ሞክሸ!

  ReplyDelete
 8. አዲስ ዘመንን አልክ ዳኒ ሀ ሀ ሀ ሀ ሀ .......ወደው አይስቁ አሉ አያቴ እሱ ራሱ ለኛ ናፍቆናል ፡፡ እኔ እውነት ዩኒቨርsiቲ ለመግባት ስም ዝርዝሬን ለማየት ከተመለከትኩበት ቀን ወጪ አዲስ ዘመንNe አይቼው አላውቅም ፡፡ ምን አለውና YEtayal

  ReplyDelete
 9. አሁን ወደዚህች ሀገር እየወረድን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ you started using this "yalenibet huneta new yalew". why? are you going to be one of those who are mising amharic grammar? U have been criticizing this issue remember?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Don't forget it is continued from the last part. Don't rush to criticize!

   Delete
  2. I think he is making fun on those people who use the phrase inappropriately. that is funny!

   Delete
 10. የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የተጠና የሀገሪቱን ገጽታ በሚገባ የሚያሳይ ነገር የምናየው መቼ ነው? እዚህና እዚያ ከተለጠፉ፣ ተከታታይነትም ሆነ ተዋሕዶ ከሌላቸው ፎቶዎች ወጥተን፤ የታሰበበት፣ በባለሞያ የተዘጋጀና ሀገሪቱን ሊያሳይ የሚችል የሥዕል፣ የፎቶና የባሕል ዕቃዎችን ትርዒት አውሮፕላን ማረፊያችን ላይ መቼ ነው የምናየው?
  ምናለ ቢያንስ አዲስ ዘመን ጋዜጣ (መቼም ሌላውን እንዳልል ዕዳው ብዙ ነው ብዬ ነው) እንኳን ቢያድሉ?
  አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡
  ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡
  እንዲህ እያሰብኩ ቆይቼ ቀና ስል ኢትዮጵያዊ መልክ ያየሁ መሰለኝ፡፡
  በማያውቁት ሀገር የሚያውቁት ሰው ማግኘት፣ በበረሃ ውስጥ የምንጭ ውኃ እንደማግኘት ነው ይባላልና ኮሽታ እንደሰማ እንሽላሊት ነቅቼ ማየት ጀመርኩ፡፡ ኧረ እንዲያውም የሐበሻ ልብስ ነገርም ያየሁ መሰለኝ፡፡
  አንዲት ወጣት፣ የሐበሻ ነጠላ የመሰለ ሻርፕ ደረብ አድርጋ ወደ እኔ በመምጣት ላይ ናት፡፡ መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት፡፡

  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

  የሚገርም ዕይታ ነው ይቆጫል እውነት የሚመለከታቸው አካላት እንዳንተ ይሰማቸው ይሆን ወይስ ልባቸው ይደነድን ይሆን??? እንደ.......
  በመጨረሻ የኢትዮጲያን ትንሳኤዋን እግዚአብሔር ያሳየን!!!!!!!!
  በርታ በርታ እመብርሃን ከነ ልጅዋ ትከተልህ!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል ስለመረጃህ በጣም እናመሰግናለን የሐዋርያት ፆም ተጠናቆ የፍልሰታ ፆም ጀምረናል፡፡
  ጉዞ ወደ ምድር ጥግ ጉዞህ እስከ መጨረሻዉ መልካም እንዲሆንልህ ምኞቴ ነዉ፡፡


  ReplyDelete
 12. አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡ ቢያንስ ለመሥሪያ ቤታቸው ሰዎች ያዩትንና የሰሙትን በማካፈል እንኳን ዕውቀትና ልምድ አያሸጋግሩም፡፡ ሲመለሱ እንደዚያው እንደሄዱት ሆነው ነው፡፡ የቢሮአቸውን አሠራር እንኳን ለመቀየር አይሞክሩም፡፡ well said Dn.Daniel. yeah the problem so complex and at times i feel so deeply sad thinking that the out let to improvement is slam shut by those tenaciously controlling the saddle of power; be at national or organizational level. Any ways, always hoping and waiting for the blessings of the Almighty.

  ReplyDelete
 13. እንኳን በሰላም በሩኒ ደረስክ! እንዳልከው የኛ ባለስልጣናት እና ምሁራን ከውጭ ይዘው የሚመለሱት አንተ የጠቃቀስካቸውንና ሌሎች እርባናቢስ ነገሮችን ነው፡፡ እኔ ያለሁበት የመንግስት መ/ቤት ሲሆን የበላይ ኃላፊዎቹ አዘውትረው ወደውጭ ይሄዳሉ፡፡ ለመስሪያቤቱ አሰራር የሚሆን አዲስ ነግር ቀርቶ … ፡፡ በሰላም ተመለስ፡፡

  ReplyDelete
 14. cherisew enji Dan. Dani

  ReplyDelete
 15. .ሀገሩ ናፍቆት ለሚመጣ ሰው እነዚህ ምንድን ናቸው? ምናለ ቢያንስ አዲስ ዘመን ጋዜጣ (መቼም ሌላውን እንዳልል ዕዳው ብዙ ነው ብዬ ነው) እንኳን ቢያድሉ?..........በማያውቁት ሀገር የሚያውቁት ሰው ማግኘት፣ በበረሃ ውስጥ የምንጭ ውኃ እንደማግኘት ነው ይባላል Ere dani huletu ababalh betam new yetemechugn tebarek bel beselam temelesln

  ReplyDelete
 16. "አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ባለ ሥልጣናት ለልምድ ልውውጥ እየተባለ ብዙ ሀገር ይዞራሉ፡፡ ለመሆኑ ምን ዓይተው ነው የሚመጡት? ምንስ ተምረው ነው የሚመለሱት? ወይስ ሌላ ውጭ ሀገር አለ እነርሱ ብቻ የሚሄዱበት፡፡ አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡" Esun KeKeyeru Meche Anesachewu!!!

  ReplyDelete
 17. ምሁራኑስ ቢሆኑ፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ውጭ ሀገር ሄደው ሠርተው መጡ ይባላል፡፡ ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ አሠራር የተሻለ ነገር ይዘው የሚመጡት ግን ስንቶች ናቸው? ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የፈተና አወጣጣቸው፣ የማስተማር ዘዴያቸው፣ የውጤት አሰጣጣቸው ያው እንደ ድሮው ነው፡፡ ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡ክፍል አራት መቼ ይሆን…….እንጠብቃለን!!!

  ReplyDelete
 18. ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡

  ReplyDelete
 19. "...መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት" nice one.

  ReplyDelete
 20. Thank you, just I have read your continues paper.But, Dani for what purpose you have gone to 'Medere tege.'

  ReplyDelete
 21. Diakon Daniel how far is Australia? it's third part, how long it takes to get their? it's realy funny. i am living their but i flowen 20 hrs, i like the way you explain our journey. any way i am waiting until you arrive in Melbourne.

  ReplyDelete
 22. እንዲህ እያሰብኩ ቆይቼ ቀና ስል ኢትዮጵያዊ መልክ ያየሁ መሰለኝ፡

  ReplyDelete
 23. Thank you for sharing what you have seen.

  ReplyDelete
 24. ምሁራኑስ ቢሆኑ፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ውጭ ሀገር ሄደው ሠርተው መጡ ይባላል፡፡ ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ አሠራር የተሻለ ነገር ይዘው የሚመጡት ግን ስንቶች ናቸው? ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የፈተና አወጣጣቸው፣ የማስተማር ዘዴያቸው፣ የውጤት አሰጣጣቸው ያው እንደ ድሮው ነው፡፡ ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡

  ReplyDelete
 25. It is really awesome. I am dying to read the next. God bless You

  ReplyDelete
 26. ዓይን ካላዩበት ግንባር ነው አሉ!

  የሀገሬ አየር መንገድ ፣ ክቡራን ምሁራንና ባለሥልጣናት ዘመዶቼ ሆይ ለማየት የፈለገ አይኑን ይገልጣል እንዲሉ ዓይናችሁን ገለጥ አድርጋችሁ ከአውሮፓ ሥልጣኔን ወደ ሀገር ቤት ውሰዱ። ልምድ ቅሰሙ እንጂ በልማድ አትኑሩ። ልማድ ከሰይጣን ይከፋል አሉ!

  ReplyDelete
 27. "መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት"

  ReplyDelete
 28. ምሁራኑስ ቢሆኑ፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪያቸውን ውጭ ሀገር ሄደው ሠርተው መጡ ይባላል፡፡ ከተማሩበት ዩኒቨርሲቲ አሠራር የተሻለ ነገር ይዘው የሚመጡት ግን ስንቶች ናቸው? ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ የፈተና አወጣጣቸው፣ የማስተማር ዘዴያቸው፣ የውጤት አሰጣጣቸው ያው እንደ ድሮው ነው፡፡ ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡

  ReplyDelete
 29. "አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ባለ ሥልጣናት ለልምድ ልውውጥ እየተባለ ብዙ ሀገር ይዞራሉ፡፡ ለመሆኑ ምን ዓይተው ነው የሚመጡት? ምንስ ተምረው ነው የሚመለሱት? ወይስ ሌላ ውጭ ሀገር አለ እነርሱ ብቻ የሚሄዱበት፡፡ አለቆች ውጭ ሀገር ደርሰው ሲመለሱ ብዙ ጊዜ አለባበሳቸውና ስልካቸው እንጂ አመለካከታቸውና አሠራራቸው ሲለወጥ አይታይም፡፡"

  ReplyDelete
 30. "መቼም ማርስ ላይ ሰው አለ ከተባለ የሚገኘው አበሻ መሆን አለበት፡፡ "

  ReplyDelete
 31. LEB YALEW LEB YEBEL tel neber enate bel engdieh tekitoch yemikenubeten endieh bemastewal negeren. bemengedeh hulu cher yegtemeh

  ReplyDelete
 32. መልካሙን እመኝልሕ አለሁ። በርታ ! ጌታ ካንተ ጋር ይሁን።

  ReplyDelete
 33. Dani Egiziabiher yistilin
  Minew balesiltanochu kezih bimaru wuchi hager menor bicha sayihon melikamu limidachew binkesim des yilal endemitmelesibet ergitegna negn

  ReplyDelete
 34. ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡

  ReplyDelete
 35. ንብ እንኳን የተሻለውን አበባ ቀስማ ማር ትሠራለች፡፡ እንዴት ሀገርን በሥልጣንም በዕውቀትም የሚመራ ሰው የተሻለ አሠራር ከሌላው አይቀስምም፡፡
  Reply

  ReplyDelete
 36. it is the country which is not allowing educated people to apply what they have learned. so please done jump into conclusions. You dont know how frustrating it is to know a lot and dont know where to apply it.

  Ethiopia is a country who doesn't ex polite her educated people. everyone is going not only to europe but also to african countries like botswanna, sudan, south africa jsut only to be apperiacted. I am not talking just money

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dani it is nice to see your views. I think we lack the ability to adopt good things into Ethiopian culture be it politics, technology etc. The other problem may be lack of research and doing things simply for reporting purpose from government side. Hope to read more from you!!!1

   Delete
 37. you are one of the moral man ethiopia has produced. your indication is so important if the public officials read your text

  ReplyDelete
 38. It is good to read your message. But, don't make things associated with politics. We know you as a religious person and a citizen.

  ReplyDelete
 39. your views are really great and interesting too!Egziabehre Yebarekeh !waiting anxiously for your next view .  ReplyDelete