Tuesday, August 6, 2013

ባዶ አቁማዳ

click here for pdf
ነፍሱን ይማረውና ሀገራችን ካፈራቻቸው የቅርብ ዘመን ገጣምያን አንዱ ደበበ ሰይፉ ‹ከአኩስም ጫፍ አቁማዳ›› የሚል ግጥም ነበረው ፡፡በዚህ የኢትዮጵያዊነት ፍቅርና መነሻውን በውብ ትረካ በገለጠበት ግጥሙ ላይ እንዲህ የሚሉ የመዝጊያ አካባቢ ስንኞች አሉት፡፡
‹‹እኔ ና ወንድሞቼ›› አለ በለዘብታ
ለራሱ እንዲያወራ የራሱን ስሞታ
‹‹እኔና ወንድሞቼ ሁላችን ሁላችን
ከባዶ አቁማዳ ነው የሚዛቅ ፍቅራችን
ይህ ነው አንድነታችን
ይህ ነው ባህላችን››
(ደበበ ሰይፉ፣ የብርሃን ፍቅር፣ 1992 ዓም፣ ገጽ 60)
አንዳንድ ጊዜ እኛነታችንን ዝም ብላችሁ ስታስተውሉት ይኼ ባዶ አቁማዳ ይታያችኋል፡፡ ኢትዮጵያውያንን ከጥጋብ ይልቅ ረሃብ፣ ከሰላም ይልቅ ጦርነት፣ ከደስታ ይልቅ መከራ፣ ከማግኘት ይልቅ ማጣት፣ ከነጻነት ይልቅ እሥር፣ ከሥልጣን ይልቅ ተራነት፣ ከመሾም ይልቅ መሻር፣ ከዕውቀት ይልቅ ማይምነት፣ ከምሁርነት ይልቅ ሌጣነት ሲያፋቅረን ታያላችሁ፡፡ እኛው አበሾቹ ‹ውሾች ምን ጊዜ ነው የሚናከሱ - ጅብ አባረው ሲመለሱ› ብለን እንተርታለን፡፡ ደስታና ጥጋብ፣ ማግኘትና ነጻነት ከሌሎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከመርሖቻችንና ከዓላማዎቻችን ጋር ሳይቀር ሲያጣላን እናየዋለን፡፡ በበረሓ ትግል ተግባብተውም ይሁን ተሸካክመው የኖሩ ታጋዮች ከተማ ሲገቡ ነው ከመርሖቻቸውም ከመርሕ ወገኖቻቸውም ጋር የተጣሉት፡፡ ተከባብረውም፣ ተሸካክመውም፣ ተጣጥመውም የኖሩት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ድልና ሥልጣን ወደ ደጃቸው መቅረብ ስትጀምርና በክብርና ዝና መጥለቅለቅ ሲጀምሩ ነበር ሽንፍላቸውን ገልብጠው ያሳዩን የጀመሩት፡፡ ከባዶ አቁማዳ ነበረ ፍቅራቸው፡፡


ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባዮች ናቸው፤ አብረው የሚበሉ፣ አብረው የሚጠጡ ናቸው፤ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውቁ ናቸው፤ ዘመድ ጠያቂ ናቸው፤ በክፉም በደጉም የሚጠያየቁ ናቸው፤ በዕድርና በዕቁብ የሚረዳዱ ናቸው፤ ጎረቤት ከጎረቤቱ ተለይቶ አይበላም፤ እየተባለ ይነገርልናል፤ ይዘከርልናል፡፡ እኛም በየቦታው በኩራት እንናገረዋለን፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን እነዚህን ነገሮች የምናገኛቸው ባዶ አቁማዳ ያለበት መንደር ነው፡፡ ‹‹ባለ ጸጎች› ከሚኖሩባቸው መንደሮች በአንዱ የሚኖር አንድ ጓደኛዬ ለልጁ ልደት ጠርቶኝ ሄጄ ነበር፡፡ የተሰበሰብነው ጓደኞቹ ብቻ ነን፡፡ ‹‹ጎረቤቶችህን አትጠራቸውም?›› ስለው ‹‹አንተዋወቅም›› አለኝ፡፡ እዚያ ቤት ከገባኮ ሁለተኛ ዓመቱ ሊሆን ነው፡፡ ‹‹አትገናኙም›› ስለው ‹‹መኪና ሳስገባ አንዳንድ ቀን እንተላለፋለን›› ብሎኝ ዕርፍ፡፡ ‹‹መስቀል አብራችሁ አታከብሩም›› መልሼ ጠየቅኩት፡፡ ‹‹እኔ እንዲያውም እናቴ ጋ ነው የምሄደው›› አለኝ፡፡ ደበበ ሰይፉ ‹ከባዶ አቁማዳ ነው የሚዛቅ ፍቅራችን›› ብሎ ነበር፡፡ ጠርሙስ ውስጥ ውኃ ሲገባ አየሩ እንደሚወጣው ሁሉ ፣ ባዶው አቁማዳ ውስጥ ሀብት ሲገባበት ፍቅሩ ይወጣል መሰል፡፡
ቡና ቢበዛ ከምሳ በኋላና በበዓል ጊዜ ከቤተሰባቸው ጋር ካልሆነ በቀር ከጎረቤት ጋር የሚጠጣ ቡና በአማርኛ ፊልም ብቻ የሚያዩ ወገኖቼ ሞልተዋል፡፡ እንኳን አሁን የቀብር አስፈጻሚ ድርጅት መጥቶ ቀርቶ ድሮም ዕድር ገብቶባቸው የማያውቅ የሀብታም ሠፈሮች አሉ፡፡ ዕቁብማ ቃሉስ ይታወቃል ብላችሁ ነው? እንዲያውም ሀብቱና ዕውቀቱ ሲጨምር ከማኅበራዊነቱ ይልቅ ግላዊነቱ ሠልጠን ሳይል አይቀርም፡፡
ከኢትዮጵያ ወጣ ስትሉም ይህንን ነገር ታዩታላችሁ፡፡ ወገኖቻችን በነጻነት እጦት፣ በመብት ገፈፋና በሰቆቃ በሚኖሩባቸው የዐረብ ሀገራት እርስ በርስ ያለው መተሳሰብ፣ መከባበርና መፋቀር በገንዘብ ቢተመን የሀገራችን የዓመት በጀት የሚያስከነዳ ነው፡፡ ወደየ ቤተ እምነቶቹ ስትሄዱ ለመማር፣ ለማገልገል፣ ገንዘብ ለመስጠት፣ ለማልቀስና ራስን ለፈጣሪ ለማስገዛት እጅግ ብዙ የተከፈቱ ልቦችንና የተሰበሩ መንፈሶችን ታገኛላችሁ፡፡ አስደናቂና ፈዛችሁ የምትሰሟቸው የፍቅርና የመተሳሰብ ገድሎችን ትሰማላችሁ፡፡ ፍቅር ተጋግሮ ፍቅር ሲበላ ትደርሳላችሁ፡፡
ከዐረቡ ዓለም ሻል ያለ ነገር ግን ከሌላው የባሰ በሚሆነው የአፍሪካ አህጉር በስደት ላይ የምታገኟቸው ወገኖቻችንም መከራውንና ስደቱን፣ እንክርቱንና መገፋቱን ለመሸከምና ለማለፍ ሲሉ እንደ አፈርና ጭድ መረገጡ ሲያጣብቃቸው ታያላችሁ፡፡ በየስደተኞች ካምፕ የምታዩት ከአሮጌ አቁማዳ የሚዛቅ ፍቅር እዚያው ቅሩ የሚያሰኝ ነው፡፡ ከመከፋፈል ይልቅ መተባበር፣ ከመጣላት ይልቅ መፋቀር ቦታውን ተሻምተውት ታገኛላችሁ፡፡ ሁሉም ባለ ተስፋ ነው፤ ሁሉም መሄድን ይመኛል፤ ሁሉም ከዛሬ ይልቅ ለነገ ይተጋል፤ ሁሉም ተደጋግፎ መሻገር ይፈልጋል፡፡ እናም ሌላውን የመሸከም ዐቅሙ ታላቅ ነው፡፡
ወደ አውሮፓ ስትሻገሩ ፍቅሩና መተሳሰቡ፣ መሸካከሙና መከባበሩ፣ አንድነቱና ትብብሩ እየጠፋ እየጠፋ እየጠፋ ሲሄድ ታዩታላችሁ፡፡ በዘር፣ በፖለቲካ፣ በእምነት፣ በእምነት ዘውጎችና በቋንቋ የሚኖረው መለያየት ከስንጥቅ ወደ ንቃቃት ሲያድግ ይታያችኋል፡፡ አሮጌው አቁማዳ እየተቀደደ ይሄዳል፡፡ ተደማምጦ መነጋገር፣ ተግባብቶ መለያየት እየጠፋ ይሄዳል፡፡ የሚያግባባ ጉዳይ ይጠፋል፡፡ ሰው ልዩነት ብቻ ይኖረዋል፡፡ ያም ቢሆን ግን አውሮፓ እንደ አሜሪካና አውስትራልያ ኑሮው ያን ያህል አይደላም፤ ነጻነቱም ያን ያህል አያወላዳም፤ የመኖሪያ ፈቃዱም ያን ያህል በቀላሉ አይገኝም፤ በካምፕ የሚኖር አለ፤ የመኖሪያ ፈቃድ ከዛሬ ነገ አገኛለሁ እያለ በተስፋ የሚኖር አለ፡፡ የመኖርያ ፈቃድ ቢያገኝም የተትረፈረፈ ገንዘብ ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህም እዚህ አሮጌዋ አቁማዳ ለበረከት ያህልም አትጠፋም፡፡ በአውሮፓ የከረረ ዘረኛነት፣ የከረረ የቤተ እምነቶች መለያየት፣ የከረረ ጎሰኛነት፣ የከረረ የፖለቲካ ጡዘት አናይም፡፡
አሜሪካና አውስትራልያ ስንሻገር ግን መልኩ ፈጽሞ ይቀየራል፡፡አሮጌዋ አቁማዳ ብጥስጥሷ ወጥቶ ከጥቅም ውጭ ትሆናለች፡፡ የሰው ሁሉ ሥዕለት አሜሪካ/አውስትራልያ ላይ ያቆማል፡፡ ስለዚህም ከእግዜር ጋር በችግሩ ጊዜ የነበረው ወዳጅነት ይቀዘቅዛል፡፡ ተስፋ ያበቃል፡፡ የተስፋይቱ ምድር ገብቷል፡፡ የሌላው ርዳታ አያስፈልገኝም ብሏል፡፡ ግለኛነት የነገሠበት ሀገር ደርሷል፡፡ ያን ጊዜ ኢትዮጵያዊነት የተደበቀ መልኩን ብልጭ ያደርጋል፡፡ አብሮ መብላት፣ አብሮ መኖር፣ መተሳሰብ፣ ሰው አፍቃሪ፣ ለወገኑ ሟች፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውቅ የሚሉት ነገሮች ተረት ይሆናሉ፡፡ ጎሰኛነትና ጠባብነት፣ ጽንፈኛነትና አክራሪነት፣ ግለኛነትና ትዕቢት፣ እኔ ዐውቃለሁና የበላይነት ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡ ከፈረንጁ ጋር እየኖረ ከሐበሻው ጋር መኖር ይከብደዋል፡፡ በማያውቀው ሀገር እየኖረ ከሚያውቀው ሰው ጋር መስማማት ይሳነዋል፡፡ይበልጥ ሲሠለጥን ይበልጥ ይሠየጥናል፡፡ ይበልጥ ነጻነት ሲያገኝ ይበልጥ ይባልጋል፤ ይበልጥ ሲፈቀድለት ይበልጥ ይከለክላል፣ ይበልጥ ሲሰፋው ይበልጥ ይጠባል፡፡ በገንዘብ ሲበለጽግ በፍቅር ይበልጥ ይደኸያል፡፡ ለምን?
ፍቅራችን የሚመነጨው ከባዶው አቁማዳ ስለሆነ ይሆን? ታድያ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሀብት ጸጋ ነው መርገም? በድኽነታቸው በሰላምና በፍቅር የኖሩ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን፣ ነዳጅ፣ ወርቅና አልማዝ ተገኘ ሲባል ግን የጦርነት አውድማ ይሆናሉ፡፡ የእነርሱም እንደኛው ፍቅራቸው ከባዶው አቁማዳ የሚገኝ ነው እንዴ? ወይስ ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? ቻይናዎች ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ይላሉ፡፡ የኛ ግን የግልንቢጥ ነው መሰል፡፡
 ብሪዝበን፣ አውስትራልያ

43 comments:

 1. Good observation... who knows one day everything is going to be like before but It must to happen this thing and to be like this at this time .If I said wrong Danisho you know better than me correct it. Thank you Dani and please Keep up your nice work.

  ReplyDelete
 2. This is serious illness which requires treatment. Unfortunately the illness is getting worse and spreading to religions. As an example the ethiopian orthodox tewahdo church has passed through a lot of temptations and sufferings peacefully in the previous eras by uniting all of its followers with one spirit. How about now?? At this period of time christians will not have sacrification,intimidation,embarrasment,killings because of their religion but they are dividing for nonsense reasons,one blames the other,tries to collect people to make groups. Love is vanishing,honesty is fading ,politeness painfully disappearing...! This is a good piece to learn from our mistakes,to love GOD then humans irrespective of our failure and success,poverty and wealth,helth and disease. Thank u dani!

  ReplyDelete
 3. melkam new! Berta!!

  ReplyDelete
 4. ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ከባዶ አቁማዳ ከሚገኝ ፍቅር ይሰዉረን!!

  ReplyDelete
 5. ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ከባዶ አቁማዳ ከሚገኝ ፍቅር ይሰዉረን!!

  ReplyDelete
 6. ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም?

  ReplyDelete
 7. Yes! This is what is happening in Addis also. Everybody is becoming superficial ("gilib"). But God is tolerating us too much.

  ReplyDelete
 8. ዳንኤል ሥራዎችህ ምግብ ናቸው፤ ጣፋጭ ምግብ፡፡ ችግሩ በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ማቅረብህ ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. Eye of the eagle!!!
  Nice but u can say a lot with this title. I wish if u can write in parts! I live in US. Some times I hate being born in Eth, ask me why? I greet every habesha and the response is 'gilmicha'-----please say a lot on this issue my talented bro! God bless u!!

  ReplyDelete
 10. "... ታድያ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሀብት ጸጋ ነው መርገም? በድኽነታቸው በሰላምና በፍቅር የኖሩ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን፣ ነዳጅ፣ ወርቅና አልማዝ ተገኘ ሲባል ግን የጦርነት አውድማ ይሆናሉ፡፡ የእነርሱም እንደኛው ፍቅራቸው ከባዶው አቁማዳ የሚገኝ ነው እንዴ? ወይስ ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? ቻይናዎች ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ይላሉ፡፡ የኛ ግን የግልንቢጥ ነው መሰል፡፡"


  አስተዋይ ልቡና ላለው ሰው እጅግ በጣም አስተማሪና መካሪ ወደ ቀደመ ማንነታችን እንድንመለስ የሚያግዝ የማንቂያ ደወል ነው፡፡ ዲ/ን ዳንኤል አንተ ድርሻህን እየተወጣህ ነው የማንቂያ ደወሉ ከሩቅ እንዲሰማ አድርገሃል፤ ከዚህ በኋላ ልብ ያልው ልብ ይበል በጎ ኅሊና ያለውም ያስተውል፡፡
  እግዚአብሔር ጸጋህን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 11. "ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባዮች ናቸው፤ አብረው የሚበሉ፣ አብረው የሚጠጡ ናቸው፤ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያውቁ ናቸው፤ ዘመድ ጠያቂ ናቸው፤ በክፉም በደጉም የሚጠያየቁ ናቸው፤ በዕድርና በዕቁብ የሚረዳዱ ናቸው፤ ጎረቤት ከጎረቤቱ ተለይቶ አይበላም፤ እየተባለ ይነገርልናል፤ ይዘከርልናል፡፡ እኛም በየቦታው በኩራት እንናገረዋለን፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ግን እነዚህን ነገሮች የምናገኛቸው ባዶ አቁማዳ ያለበት መንደር ነው፡፡"...ገና እኔ ልጅ እያለሁ በሰሜን በኩል ድሮ ከ17 ዓመት በፊት አሳድሩን ብለው የሚመጡ እንግዶች ያሳድሯቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ …….. ከሚገርመው ነገር አ/አ ላይ ቤት ተከራይተን እንኳን ጓደኞቻችን ሲመጡ አታስገቡም እያሉን ይከለክሉናል፡፡ እና አንተ እንደገለጽኸው … ባዶ አቁማዳ እያልክ የጻፍከው ጽሁፍህ በጣም ይገልጸናል፡፡ የቀድሞ የአባቶቻችንን ፈለግ እንከተል ፡፡ገና እኔ ልጅ እያለሁ በሰሜን በኩል ድሮ ከ17 ዓመት በፊት አሳድሩን ብለው የሚመጡ እንግዶች ያሳድሯቸው እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ …….. ከሚገርመው ነገር አ/አ ላይ ቤት ተከራይተን እንኳን ጓደኞቻችን ሲመጡ አታስገቡም እያሉን ይከለክሉናል፡፡ እና አንተ እንደገለጽኸው … ባዶ አቁማዳ እያልክ የጻፍከው ጽሁፍህ በጣም ይገልጸናል፡፡ የቀድሞ የአባቶቻችንን ፈለግ እንከተል ፡፡

  ReplyDelete
 12. I remember here in South Africa one of the Ethiopian was saying Ethiopia should remain poor in economical like before.....that is not what make me to worry....what make me to worry is that nobody or no institution is working on cultural affairs how to balance economical growth with human relationships......we were told the Japanese was poorer than us....my point is I do not you to compare this two economical to enhance Deacon Daniel article , please compare them culturally! ....what the other thing bothering me is that our faith....is it only exist on our lips? If you say no our faith exist also in/on other parts of our body then please tell me why Deacon Danial has obligated to write such a wonderful observation of our society wheresoever they are.....God bless, Deacon Danial Kibret

  ReplyDelete
  Replies
  1. My brother faith in Ethiopia wey qertoal wey dirom alneberem. Egna yalebin neger min endehone tawqaleh elih. yemin sira yemin fiqir.kir banget bicha. You said it all- it exists only on our lips.

   Delete
 13. Dan.Dani gena bizu entebikaleh ke ante e/r edme yistih

  ReplyDelete
 14. God bless you dani i appreciate as usual

  ReplyDelete
 15. እ/ር ይባርክህ ጥሩ እይታ ነው ባልና ሚስት እንኳን በድህነት በፍቅር ኖረው ሃብት ሲመጣ ይጣላሉ ለምን ይሆን?

  ReplyDelete
 16. Betameeee tikikilgna melkekt D.n Dani ,yemigermew egna Ethiopiyaweyan be fiker lemenor yeged dehawoch mehon aleben?bewnet libe yalew libe yebel!

  ReplyDelete
 17. Oh God. Lezemenat wuste yetekatelebetin guday new enen honeh tenefeskelegn. America yalu habeshoch yalebachewun chigur kalastekakelu, beyekenu be hiwotachew eyetekesetu yeminayachew chigroch yezih hatiyat meketacha eyehone mehedu aykere new!

  ReplyDelete
 18. Dani, u said it! eski libona yisten!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ኢትዮጵያውያንን ከጥጋብ ይልቅ ረሃብ፣ ከሰላም ይልቅ ጦርነት፣ ከደስታ ይልቅ መከራ፣ ከማግኘት ይልቅ ማጣት፣ ከነጻነት ይልቅ እሥር፣ ከሥልጣን ይልቅ ተራነት፣ ከመሾም ይልቅ መሻር፣ ከዕውቀት ይልቅ ማይምነት፣ ከምሁርነት ይልቅ ሌጣነት ሲያፋቅረን ታያላችሁ፡፡

   Delete
 19. ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? This is true view God bless you.

  ReplyDelete
 20. melkam eyita new Dani

  ReplyDelete
 21. ዲ/ን ዳንኤል : ሃሳቦችህ ሁሌም ልዩ ናቸዉ :: ባነሳኸዉ ሃሳብ ላይ ግን በየትኛዉም የኑሮ ደረጃ ላይ ብንሆን የመጨረሻ ግዜ ላይ እንደመገኘታችን ፍቅር መቀዝቀዟ አትቀርም:: እየሆነ ያለዉ ይህ ይመስለኛል:: ባሁን ሰዓት ዘመድ ማለት እናትና አባት እህትና ወንድም ወደሚለዉ ብቻ አሽቆልቁሏል:: ሌላዉ ቀርቶ በዘመድ ሃዘን ግዜ እንኳን ሰዎችን እግዚአብሔር ያፅናናህ ለማለት አንደበታችን ታስሯል:: ምክንያቱም ዉስጣችን የሚነግረን በሃዘን ተጎድቷል ሳይሆን ተገላገለዉ የሚለዉ ስለሚያደላበት ሳይሆን አይቀርም::

  ReplyDelete
 22. እባክህ ሁሉን ነገር ተወው

  ReplyDelete
 23. በድኽነታቸው በሰላምና በፍቅር የኖሩ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን፣ ነዳጅ፣ ወርቅና አልማዝ ተገኘ ሲባል ግን የጦርነት አውድማ ይሆናሉ፡፡ የእነርሱም እንደኛው ፍቅራቸው ከባዶው አቁማዳ የሚገኝ ነው እንዴ? ወይስ ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? ቻይናዎች ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ይላሉ፡፡ የኛ ግን የግልንቢጥ ነው መሰል፡፡

  ReplyDelete
 24. በድኽነታቸው በሰላምና በፍቅር የኖሩ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን፣ ነዳጅ፣ ወርቅና አልማዝ ተገኘ ሲባል ግን የጦርነት አውድማ ይሆናሉ፡፡ የእነርሱም እንደኛው ፍቅራቸው ከባዶው አቁማዳ የሚገኝ ነው እንዴ? ወይስ ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? ቻይናዎች ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ይላሉ፡፡ የኛ ግን የግልንቢጥ ነው መሰል፡፡

  ReplyDelete
 25. በድኽነታቸው በሰላምና በፍቅር የኖሩ አፍሪካውያን ወዳጆቻችን፣ ነዳጅ፣ ወርቅና አልማዝ ተገኘ ሲባል ግን የጦርነት አውድማ ይሆናሉ፡፡ የእነርሱም እንደኛው ፍቅራቸው ከባዶው አቁማዳ የሚገኝ ነው እንዴ? ወይስ ድህነትን ለማስተዳደር ያለንን ልምድና ባህል ያህል ብልጽግናን ለማስተዳደር የሚሆን ልምድና ባህል የለንም? ቻይናዎች ‹‹ድህነት በበር ሲገባ ፍቅር በመስኮት ትወጣለች፣ተኩላ በበር ሲገባ ርግብ በመስኮት ትበራለች›› ይላሉ፡፡ የኛ ግን የግልንቢጥ ነው መሰል፡፡

  ReplyDelete
 26. a thoughtful idea. Let's learn from it.

  ReplyDelete
 27. ሆድ ሲጎድል ፍቅሩ ሌላ ሆድ ሲሞላ ሰው ያጋድል አሉ!


  ወደ አውሮፓ ስትሻገሩ ፍቅሩና መተሳሰቡ፣ መሸካከሙና መከባበሩ፣ አንድነቱና ትብብሩ እየጠፋ እየጠፋ እየጠፋ ሲሄድ ታዩታላችሁ አልከን? አዎ ለዚህ ምስክር ነኝ። ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል እንዲሉ በዚሁ እንለፈዋ። ይህች ለንደን በምትባል ከተማ ባስ ውስጥ አንድ ሐበሻ ስታገኙ ፊቱን እንደ ፎጣ እጥፍጥፍ ያደርጋታል። ደግነቱ የሰው ፊት አለመፋጀቱ አሉ!

  ReplyDelete
 28. loret tsegaye gebremedhin IIAugust 8, 2013 at 2:35 PM

  እግዜር ይስጥህ ዲያቆን ዳኔል።

  እኔ የተወለድኩት አምቦ ሸዋ ነው። ታዲያ አያቴም ሆኑ አባቴ እውነት ኦሮሞ እንሁን ወይንም አማራ በርግጥ አያውቁም። እንዴው ኢሃዴግ ከገባ በኋላ የጎሳ ነገር መካረር ሲጀምር፣ ከሁሉም ጋር ለመግባባት ሲባል "ለምን ጉራጌ አንሆንም?" ተባለና ቤተሰባችን በሙሉ ጉራጌዎች ተባልን።

  ይህ በንዲህ እንዳለ ፲፬ ዓመታት አለፉና የ፺፯ቱ ምርጫ ክልችው ብላ መጣች። አይ ጉድ! በዚያች የፈተና ወቅት ኢሃዴግ አይኗን ገልብጣ ጉራጌ እሚባል ካየሁ ውርድ ከራሴ ማለት ጀመረች። በዚህ ወቅት ነበር የዓያቴ መሞት የተሰማን። አባቴም ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያወጣ ሲያዎርድ (መታወቂያ ካርድ፣ የህዝብ ቆጠራ ወዘተ ላይ ጉራጌ ከተባልን በኋላ ደግሞ አሁን ኦሮሞ ነን ብንል ኢሃዴጊቱ ጥርጥር ትጀምራለች--እያለ ሲጨነቅ ዲቪ ዱብ አለና ገላገለን።

  አሁን ወሸንግተን ዲሲ እንንኖራለን። ግማሻችን አማራ ስንሆን ግማሻችን ኦሮሞ ነን። ጉራጌነቱ የት ጠፋ ያልክ እንደሆን የኢሃዲጊቱ ሚኒስተር ቪዛችንን እንዳይከለክለን ያችን የቤተሰብ ምስጢር ከሃገራችን ጋር እርግፍ አርገን ነው ዲሲ የገባነው። አሁን በነጻነት እፎይ ብለን እንኖራለን። አንበጣ እሚበረው ክንፉ እስኪወልቅ ነው እንዲሉ...እኛም እስረኛነታችን ኢሃዲጊቱ ቪዛ እስክትመታ ድረስ እንደነበር እስከዚያች ቀን አላወቅንም ነበር።

  ReplyDelete
 29. Wonderful view, Bezih guday lay yemisera Andem Tekuam Yelem, Belemadna Bewshet yeminor tiwled, Afu kibe eyantebatebe hodu tor yazegaje kifu tewled, Lezakonew Temariwochachen beye Universiitiw tebuwadnew dengay yemiwerawerut

  ReplyDelete
 30. Right, Let i tell you one pressurized thing, There are a lot of Ethiopians who hate to listen such idea. We are now Ethiopians with such generation,

  ReplyDelete
 31. Thanks Dani,

  In my opinion, we Ethiopian has a great problem in terms of personal dignity this means we highly worry to be superficial rather than being normal human being, related to this we need to be respected before respecting people who deserve respect, and also we are very keen to be financially secured in any means-this thinking already developed in the society with old saying " if you have money there is road to heaven" ...this is absolute greediness. That's why in every sector such as government, church, public area when you go the public servants are ready to hunt money. The best and the most negative factor for Ethiopians' in this generation is financial gap between the people...The only way to narrow this big gap is to let the people to learn all in all from end to end. TO be Educated in uneducated society is leading those educated society in wrong way, Thus, I strongly recommend to let first the people to learn all in all. I believe if people has pure mentality they start to think what is going on. Now what the people is seeing the money is going to those uneducated people and leaders...if this continues this way the country will be full of unethical leaders and business men as a result you cannot control thousands of immigrant people daily from Ethiopia, you cannot control greediness between the people, you cannot control corruption everywhere. These are a great assignment for the coming generation and leaders. God bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 32. ውድ ዳኒ ቸር ይመልስህ የወሰደህ ጠያራ::
  በ1857 ዓ/ም (ደብተራ) ዘነብ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ይህን ግሩም ሀሳብህን በሚያጠናክር ግሩም አገላለጽ በመጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ መጸሓፋቸው እንዲህ ተፈላስመዋል::
  "ጥጋብ"
  "ከባለጌ ፍቅር የንጉሥ ቁጣ ይሻላል፥ የረሀብ ጌትነቱ መቼ ነው? እህል በታጣ ጊዜ ነው:: ምነው ቢሉ የሌለውን አምጡ ይላልና:: የማጣትስ ጌትነቱ መቼ ነው? የፈለጉት ነገር በታጣ ጊዜ ነው፣ የጥጋብስ ጌትነቱ መቼ ነው? መብልና መጠጥ በተገኘ ጊዜ ነው:: የመብላትስ ትርፉ ምንድን ነው? ጥጋብ ነው::"

  ReplyDelete
 33. ዳኔ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ሁሉን መልእክቶችሕን አድናቄሕ ነኝ ፤ ከዜያም አልፎ ጌታ በፈቀደ ም ብዙ ለሔወቴ የሜጠቅመኝም ተምሬበት አለሁ ተባረክ።የከአሁኑ ጽሑፍሕ ግን የመሰለኝ ፌት ለፌት ቁመህ የምታወራ ነው ። እውነትም ከላይ ተሰጥቶሐል ። ግምትሕ ልክ ነው። ለካስ እኛ የሞላልን ሴመስለን፤ ከአገሩ ከባሕሉ ስንርቅ ፤ አውቀቱም ገንዘቡም ሴሞላ ለካስ እኛ እንደዜሕ ነን? አብይ ጾም መጠጥ ሳይቀምስ ቅዳሴ የሜያስቀድስ የነበረ ሰው ወንዝ በመሻገሩ ምክንያት ድሮም ለሰው ስል ነው ቤላቸሑ አያድርስ አትሉም? በሶስት አይነት ስም ባሉዋን ስትጠራ የነበረች ባልተቤት ሰማሕ ወንደም እሱን እንዲሕ ...እያለች በመብቴ ነው ሽፋን የከረመ ትዳር ሴናድ አልየም ሴንገዳገድ ማየት የተለመደ ሁንዋል ከዜያም ታልፎ እኛው ባሳየናቸው ፈለግ የልጆቻችንን ዘለቄታ ቆም ብለን ካሰብነው ከወዲሁ ደረት ያሰመታል። የሜገርመኝ ላይ ታች ተብሎ አምጥተህ ፤አልብሰሕ ፣ አጉርሰህ ብሎም አስተምረሕ ጠቅልሎ ማስረከብ ይሕንንስ ምን ትሉት አላችሁ? እንደኔ የዜሕ ሁሉ መንሴኤው ዳኔ እንዳለው እኛው ነን። እርስ በርሳችን ብንጠያየቅ ፤ በእምነታችን ብንገለምስ ፤ ግሩም ባሕላችንን ጣል ጣል ባናረግ .ወ. ዘ ተ ሁሉ ነገር ሙሉ በሙሉ ባይሆንም መልክ ይኖረው ኖሮ ይሆናል ብየ አምናለሑ። አባቶች ካለጯማ የወጣሕበትን አገር በጯማ መመለስ ይቸግራል ይላሉ። የስደት ነገር ጉዱ ብዙ ነው ። የድንግል ልጅ ይርዳን! አንተንም በሰላም ይመልስሕ።

  ReplyDelete
 34. ዳኔ ጽሑፍሕን ለሶስተኛ ግዜ አነበብኩት። እንዲት ታዝበኸናል ? አይገርምም? ወይ ስደት? እኛን፤
  ልጆቻቾንን፣ ባሕላችን ፣ እምነታችን ፣ ፍቅራችን ፣ ይሕ ሁሉ ያቇረጥነው ውቅያኖስ ውስጥ ገብቶ ሰጥሙዋል ማለት ነው ??? ከሃያ ዓመት የስደት ዘመኔ፣ በየዋሁ ልቤ እሩጨ እሩጨ ቀና ስል ለካስ ማሳረጌያው የስደት ይሕ ኑሮዋል። ይገርማል?
  እስራኤሎቾ እነሱ ባይገቡ ልጆቻቸው ቅድስቴቱን መሬት ረግጠዋል። ወገን ሆይ ! እኛ ይህ እድል የምናገኝ ይመስላችሁል?
  የድንግል ማርያም ልጅ ይርዳን። አሜን

  ReplyDelete
 35. dani i have learn alot.i think u have the ability to put profound impact in heart. God bless u.

  ReplyDelete
 36. እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ተባረክ፡፡ ይህን ጽሑፍ ኢትዮጰያዊ የሆነ ሁሉ ቢያነበው ተመኘሁ፡፡ ያልከው ሁሉ በሳይንሳዊ ጥናት እንደተረጋገጠ ሁሉ የሚያሳምን የሚታይ ማንም የማይክደው እውነት ነው፡፡ ለእግዚአብሔርም እኮ እንዲሁ ነን፡፡ ባጣን በነጣን፣ ባዘንን በተከዝን፣ በተበደልን በተገፋን ጊዜ የምንጸልየው ጸሎት የምናነባው እንባና ልመና የምንተጋው ትጋት ባገኘን በሞላልን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ ለምስጋና ጊዜያችን ያጥራል ጉልበታችን ያንሳል፡፡ ስለሁሉም ወንድማችን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥህ፡፡ ወደ መንገድ ወጥተሃል አሉ፡፡ በሰላም ተመለስ፡፡

  ReplyDelete
 37. I really appreciate this article. It is true.

  ReplyDelete
 38. Dani, you have a special way looking at issues. You must have been given the telescope!!!

  ReplyDelete
 39. Bro, Your reflection on this has touched my heart. It is true... and that is how we are. Why we are attached more in time of hardship and detach the lovely bond when we get to the wonderland? I feel that there is some ill root with in us. In time of difficulty, we share our burdens to people around...But, when prosperity, knock our door, we reject all people around us and try to consume it ALONE...' endet kifu nen..'. Bro, could you reflect on the solution...Thanks

  ReplyDelete
 40. You can find a true love in the poor villages, not in the rich.

  ReplyDelete
 41. uneducated society is leading those educated society in wrong way,

  ReplyDelete