Thursday, August 22, 2013

የኛ ሰው በካንጋሮ ምድር

7, 617, 930 ስኩዌር ኪሎ ሜትር በምታካልለው ሰባተኛ አህጉር፣ በስፋቷ የዓለማችን ስድስተኛ ሀገር በሆነችው አውስትራልያ ውስጥ እገኛለሁ፡፡  አንድ አህጉር አንድ ሀገር ሲሆን አውስትራልያ በዓለማችን ብቸኛዋ ትመስለኛለች፡፡ የሚገርመው ግን ይህንን የሚያህል ሰፊ ሀገር ውስጥ የሚኖሩት ሃያ ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ብቻ መሆናቸው ነው፡፡ ‹አይሆንም እንጂ ቢሆንማ› እንደሚባለው ቢቻል ኖሮ ከአውስትራልያ ይዤ ወደ ሀገሬ የምገባው የቤት መሥሪያ መሬት ነበር፡፡ እዚያ የወባ ክኒን የምታክል መሬት ለማግኘት የቀበሌ መታወቂያ፣ 10/90፣ 20/80፣ ባንክ ቤት፣ ወረፋ፣ ምዝገባ፣ ዕጣ፣ መከራ እያሳየን እዚህ መሬት የካንጋሮ መጨዋቻ ሆኖላችኋል፡፡ ‹አስወስጄ መጣሁ አስወስጄ› የሚለው ዘፈን ባህል ነውና እኛ የባሕር በራችንን አስወስደን ትንሷን ጅቡቲ ስንለማማጥ እንኖራለን፤ የዓለማችን ትልቋ ደሴት የምትባለው አውስትራልያ 34,218 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የባሕር ጠረፍ ባለቤት ናት፡፡ አውስትራልያ የሚለው ስም ከላቲኑ ‹‹አውስትራሊስ› የመጣ መሆኑንና ትርጉሙም ‹ደቡባዊ› ማለት እንደሆነ ይነገራል፡፡

በስድስት ክልሎችና በሁለት ልዩ ግዛቶች የተመሠረተችው ይህች ፌዴራላዊት ሀገር ራሳቸውን ‹አውሴ› ብለው የሚጠሩት የዛሬ ዋነኛ ነዋሪዎቿ ከመምጣታቸው በፊት ‹አቦርጅን›[አዳሙ ተፈራ የሚባል አውስትራልያ የሚኖር ደራሲ - ‹ኑር ተገኝ› ብሎ ጠርቷቸዋል፡፡] የተባሉ ጥንታውያን ሕዝቦች ይኖሩባት የነበረች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ከእስያ መጥተው ከብዙ ሺ ዓመታት በፊት የኖሩት ባላገሮቹ ዛሬ በሰሜናዊ አውስትራልያ በሚገኘው ‹የሰሜን ግዛት› በሚባለው ልዩ ክልል ውስጥ በብዛት ይገኛሉ፡፡ እንግሊዞች ወደዚች ሀገር ሲመጡ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ቁጥር ነበራቸው የሚባሉት አቦርጅኖች በደረሰባቸው ግፍና መከራ የተነሣ ቁጥራቸው መንምኗል፡፡ ለመሬታቸው ሲባል ተሰድደው፣ ተገድለውና በበሽታ እንዲያልቁ ተደርገው ሀገራቸውን አጥተዋል፡፡ በ1787 ዓም የተነሣውና መጤዎቹ ሆን ብለው ወደ አቦርጅኖች እንዲደርስ አድርገውታል የሚባለው ፈንጣጣ ብቻ ‹ዳሩግ› ከሚባሉት የአቦርጅን ጎሳዎች መካከል ዘጠና በመቶውን ፈጅቷቸዋል፡፡ [የኡጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ ነጮች በአፍሪካ ላይ በመድኃኒት ጥቁሮችን እንዳይጨርሱ ያደረጋቸው ከብት አርቢ መሆናችን ነው፡፡ ብዙውን በሽታ ከብቶቹ ወስደውታል፡፡ ከከብት ጋር በመኖራችንም የመቋቋም ውሳጣዊ ዐቅም ገንብተናል ብለው ነበር፡፡] ልጆቻቸውን ለጉልበት ሥራ አስገድዶ በመውሰድ፣ እንዳይወልዱ የማምከኛ መድኃኒት በመስጠት፣ የመጠጥ ሱሰኞች ሆነው እንዲቀሩ በማድረግ አቦርጅኖች ከሀገር እንዲጠፉና ቁጥራቸው እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ በዚህ ምክንያት በሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ እየጠፉ መጥተው በ1900 ዓም አካባቢ ቁጥራቸው ወደ 96 ሺ ወርዶ ነበር፡፡ አሁን ከጠቅላላው ሕዝብ 2 በመቶ ብቻ ናቸው፡፡ እሥር ቤት ስሄዱ ግን 25% እሥረኞች እነርሱ ሆነው ታገኛላችሁ፡፡ ልክ በአሜሪካ አፍሪካ አሜሪካውያን ከጠቅላላ ሕዝቡ 13.6 በመቶ ቢሆኑም እሥር ቤት ግን 60 ከመቶ እንደሆኑት ዓይነት ማለት ነው፡፡ 
አንዳንድ ጊዜ ለነጻነታችን ለተዋጉት አርበኞች ክብር የምትሰጡት ይህን መሰል የመከራ ታሪኮችን ስትሰሙ ነው፡፡ ‹በኋላ የመጣ ቀንድ በፊት የመጣን ጆሮ በለጠው› እንደተባለ በኋላ ሀገር የወሰዱት ዜጎች ክብሩንም፣ ነጻነቱንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ ሥልጣኑንም ነጥቀውት ባላገሩን ሁለተኛ ዜጋ ሲያደርጉት ስታዩ ‹ነጻነት ሆይ ዋጋሽ ምን ያህል ነው?› ትላላችሁ፡፡ አንዳንድ ወገኖቼ ‹ጥቂት ቅኝ ብንገዛ ኖሮ እንሠለጥን ነበር፣ እናድግም ነበር› ብለው ይቆጫሉ፡፡ በእሳት የሚጫወት የአበራሽን ጠባሳ ያላየ ብቻ ነው፡፡ ባይሆን እኛ ‹ነጻነትን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል›› ልንቀጣ የሚገባን ሕዝቦች ነን፡፡ ነጻነታችንን ለዕድገትና አንድነት፣ ለብልጽግናና ለመልካም አስተዳደር ከመጠቀም ይልቅ ለጦርነት ተጠቅመንበታል፡፡ የውጭ ወራሪዎችን ተከላክለን ራሳችን በራሳችን ስንዋረር ኖረናል፡፡ ነጻነትን ለጦርነት የመጠቀም ልማዱ አልለቀን ስላለም በአንጻራዊነት የመብት ነጻነት ተከብሮባቸዋል ወደሚባሉት ሀገሮች ስንገባ እንኳን ‹የዘሬን ያንዘርዝረኝ› ብለን ጦርነቱን ቀጥለነዋል፡፡ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭው ዓለም ያሉ የፓርቲና የኮሙኒቲ፣ የሚዲያና የኪነ ጥበብ፣ የቤተ እምነትና የማኅበራዊ ተቋማት አደረጃጀቶቻችን ሁሉ የጦርነት አደረጃጀቶች ናቸው፡፡ የህልውናችን መሠረቱ ጠላት ነው፡፡፡ ያለ ጠላት ህልው መሆን ስለማንችል ጠላት ካጣን ጠላት እንፈጥራለን፡፡
‹እንግዳ ሆነሽ ትመጭ ባለቤት ሆነሽ ትቆጭ› እንደሚባለው በኋላ ዘመን የመጡትና ባለቤትነቱን የወሰዱት እንግሊዞች እነዚህን ነባር ሕዝቦች እንዳይድኑ አድርገው ሰብረዋቸዋል፡፡ ዛሬ ምንም እንኳን ችግሩ የተቀረፈ፣ መንግሥትም ለተፈጸመው ግፍ ይቅርታ የጠየቀ፣ እነርሱን የሚደግፍ ሕግም ያወጣ ቢሆን አካላዊ፣ ባህላዊና ሞራላዊ ህልውናቸውን እንዲያጡ በመደረጉ የተነሣ ወደ ጥንቱ ክብራቸው ለመመለስ አልቻሉም፡፡ እንግሊዞቹ እነዚህን ሕዝቦች ከምቹ የመኖርያ ሥፍራዎች በማስለቀቅ ወደ በረሃማውና ለኑሮ አስቸጋሪ ወደሆነው አካባቢ ገፍተዋቸዋል፡፡ ለብዙ ዘመናት ትምህርትና ሥልጣኔ እንዳይቋደሱ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ይልቅ መጠጥና አደንዛዥ ዕጽ በአካባቢያቸው እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ የቤተሰብን ማኅበራዊነት በመበተን ወላጆችና ልጆች እንዲለያዩ አድርገዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ተደምረው ዛሬም የአውስትራልያ አቦርጅኖች በሀገራቸው ሙሉ በሙሉ የሚያዝዙ አልሆኑም፡፡
ከአውሮፓውያን መካከል አውስትራልያን ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኛት ሆላንዳዊው አሳሽ ዊልያም ጃንስዘን ነው፡፡ ዊልያምስ በሰሜን አውስትራልያ የረገጠውን መሬት ‹አዲሲቷ ሆላንድ› ብሎ ሰየመና የሀገሩ ግዛት አደረጋት፡፡ እርሱን ተከትሎ ወዲያው የመጣ አውሮፓዊ ሠፋሪ ግን አልነበረም፡፡ ከእርሱ በኋላ ዊልያም ዳምፐር የተባለ እንግሊዛዊ በሰሜናዊ ምዕራብ አውስትራልያ በ1688 ደረሰ፡፡ እንግሊዞች ወደ አውስትራልያ እግራቸውን መስደድ የጀመሩት ከዚያ ጊዜ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በ1770 ጄምስ ኩክ በተባለ መቶ አለቃ አማካይነት ወደ ምሥራቃዊው አውስትራልያ ክልል በመምጣት በእንግሊዙ ንጉሥ ጆርጅ ሦስተኛ ስም አካባቢውን ያዙና ‹ኒው ሳውዝ ዌልስ› ብለው ጠሩት፡፡
እንግሊዞች ወደ አውስትራልያ ፊታቸውን እንዲያቀኑ ያደረጓቸው ብዙ ምክንያቶች ነበሩ፡፡ በአንድ በኩል የአሜሪካ ግዛታቸው ነጻ መውጣት የእርሻ ቦታቸውን ነጥቋቸዋል፡፡ ስለዚህም ሌላ ቦታ በማፈላለግ ላይ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወንጀለኞቻቸውን ያሥሩባት የነበረችው አሜሪካ ነጻ መውጣቷ ሌላ የወንጀለኞች ማሠሪያ እንዲያፈላልጉ አስገድዷቸው ነበር፡፡
እንግሊዞች ወታደሮቻቸውንና ወንጀለኞችን ይዘው በ1788 ዓም ወደ አውስትራልያ በመምጣት በሲድኒ በኩል አካባቢውን እያጸዱ መቆጣጠር ጀመሩ፡፡ በአሜሪካ የባሮችን ጉልበት ያጡት እንግሊዞች በአውስትራልያ የእሥረኞችን ጉልበት መጠቀም ጀመሩ፡፡ እየቆዩም ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ ስደተኞች ተቀላቀሏቸው፡፡  
ዛሬ በአውስትራልያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ220 በላይ ሀገር ሰዎች ይኖሩባታል፡፡ ምንም እንኳን ዋናው ኦፊሴልዊ ቋንቋዋ እንግሊዝኛ ቢሆን ከ224 ቋንቋዎች በላይም ይነገሩባታል፡፡ የፌዴራል ሥርዓት የምትከተለው አውስትራልያ የሀገሪቱ ርእሰ ብሔር የእንግሊዟ ንግሥት ናት፡፡ (በነገራችን ላይ ንግሥቲቱ ካናዳን ጨምሮ የ16 ሀገሮች ርእሰ ብሔር ናት) የ2006 ዓም የሀገሪቱ የቆጠራ ውጤት እንደሚገልጠው ከሕዝቡ ቁጥር ሩብ ያህሉ ከተለያየ ሥፍራ መጥቶ የሚኖር ነው፡፡ ጣልያኖች፣ ቻይናዎች፣ ቬትናሞች፣ ሕንዶችና ፊሊፒኖች ከስደተኞቹ መካከል ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ ከአፍሪካ አህጉር ብቻ ከ48 ሀገሮች የመጡ ስደተኛ ነዋሪዎች በአውስትራልያ ይገኛሉ፡፡
በ2006 ዓም የተደረገው የአውስትራልያ ሕዝብ ቆጠራ በሀገሪቱ 7516 ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ ይገልጣል፡፡ ነባር ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ግን ቁጥሩን የዚህ ሦስት እጥፍ አካባቢ ያደርጉታል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ለቆጠራው ቅጽ ትኩረት ባለመስጠታቸው እንደማይሞሉት፣ አንዳንዶቹም የቋንቋው ችግር ሳይረዱት እንዲቀሩ እንደሚያደርጋቸው፣ ሌሎቹም ከቆጠራው በኋላ በብዛት መምጣታቸውን እንደ ምክንያት በመውሰድ የኢትዮጵያዊውን ቁጥር እስከ ሃያ ሺ ያደርሱታል፡፡ የአውስትራልያ መንግሥት ቆጠራ እንደሚያሳየው 26 በመቶዎቹ የሀገሬ ልጆች በሹፍርናና ማሽኖችን በማንቀሳቀስ፣ 24.3 በመቶዎቹ በጉልበት ሥራ፣ 16.3 በመቶዎቹ በአገልግሎት ዘርፍ፣ 33.5 በመቶዎቹ ደግሞ በአስተዳደር፣ በጸሐፊነት፣ በቴክኒክ ሥራ፣ እንዲሁም በሌላ ሞያ ነክ ሥራ መሠማራታቸውን ያሳያል፡፡ በሀገሪቱ ከሚኖሩት ኢትዮጵያውያን መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት እዚህ እኔ ያለሁበት ቪክቶርያ ግዛት፣ ሜልበርን ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው፡፡
አዳሙ ተፈራ ‹ገመናችን በሰው ሀገር› ብለው በጻፉት መጽሐፍ ላይ እንደገለጡት ወደ አውስትራልያ ለመጀመሪያ ጊዜ የገቡት ኢትዮጵያዊ አቶ አዲስ ታምሩ ይባላሉ፡፡ እኒህ በ1965 ዓም ወደ አውስትራልያ የገቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባልደረባ ለትምህርት መጥተው ነው በዚሁ የቀሩት፡፡ ዛሬ ከሀገሩ ነባር ነዋሪ (አቦርጅን) ጋር ተጋብተው ይኖራሉ፡፡
እዚህ የሚኖሩ የሀገሬ ልጆች ብዙ አስገራሚ፣ ብዙ አስቂኝ፣ ብዙም አሳዛኝ ገጠመኝ አላቸው፡፡ እድሜና ጤና ከሰጠን አብረናቸው እናዝናለን፣ እንስቃለን፣ እንሳቀቃለንም፡፡
ሜልበርን፣ አውስትራልያ

30 comments:

 1. ‹ነጻነት ሆይ ዋጋሽ ምን ያህል ነው?› ባይሆን እኛ ‹ነጻነትን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል›› ልንቀጣ የሚገባን ሕዝቦች ነን፡፡
  Dani egiziabihere yistih. yenetsanet waga befitsum ligeban yalchalin hiziboch honenal. ebakihin bichal benestanet zuriya yemiyatenetin tsihuf bitasnebiben.

  Yezewetir teketatayih negn.

  ReplyDelete
 2. [የኡጋንዳው ዩዌሪ ሙሴቪኒ ነጮች
  በአፍሪካ ላይ በመድኃኒት ጥቁሮችን እንዳይጨርሱ ያደረጋቸው ከብት አርቢ መሆናችን ነው፡፡ ብዙውን በሽታ
  ከብቶቹ ወስደውታል፡፡ ከከብት ጋር በመኖራችንም የመቋቋም ውሳጣዊ ዐቅም ገንብተናል ብለው ነበር፡፡ Betam girum ababale new. Dn. Daniel kalhiwot yasmalen

  ReplyDelete
 3. “….አቦርጅኖች በደረሰባቸው ግፍና መከራ የተነሣ ቁጥራቸው መንምኗል::… ልጆቻቸውን ለጉልበት ሥራ አስገድዶ በመውሰድ፣ እንዳይወልዱ የማምከኛ መድኃኒት በመስጠት፣ የመጠጥ ሱሰኞች ሆነው እንዲቀሩ በማድረግ አቦርጅኖች ከሀገር እንዲጠፉና ቁጥራቸው እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡… እኛ ‹ነጻነትን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል›› ልንቀጣ የሚገባን ሕዝቦች ነን፡፡ ነጻነታችንን ለዕድገትና አንድነት፣ ለብልጽግናና ለመልካም አስተዳደር ከመጠቀም ይልቅ ለጦርነት ተጠቅመንበታል፡፡…”

  ReplyDelete
 4. ”…እኛ ‹‹ነጻነትን አላግባብ በመጠቀም ወንጀል›› ልንቀጣ የሚገባን ሕዝቦች ነን፡፡” ትክክል ነህ ዳኒ! ነጻነታችንን የነበረንን መልካም ነገር እንኳን ጠብቆ ለማቆየት ያልተጠቀምንበት፡፡

  ReplyDelete
 5. Thanks Dani,it is interesting.

  ReplyDelete
 6. It is good article, but don't start new paragraph with number .... like this (7, 617, 930)

  ReplyDelete
 7. አንዳንድ ጊዜ ለነጻነታችን ለተዋጉት አርበኞች ክብር የምትሰጡት ይህን መሰል የመከራ ታሪኮችን ስትሰሙ ነው፡፡

  ReplyDelete
 8. one day I were talking with my friends about colonial period at our work place(America). we are about seven from seven different countries of Africa. one of our friend asked us which country got independency first. We all tried to answer. But two of our friends never agreed because both of them were saying "my country got independency first". They really argued, they really boosted that their country got independency first. In the mean wheal one of my friend questioned me about my country because I didn't say nothing. But all of my friends answered once saying "ETHIOPIA NEVER BEEN COLONIZED".I said 10qu.That time I was really felt something unknown because I didn't talked about my country in confident like them. They were proud of my country but I was not. It was that time I ashamed of my self because before I used to wish if my country was colonized.my reason was seek of modernization. But at that moment I totally cleaned my mislead thought and I tanked my fathers because all of my friends briefly explained that their countries never got nothing benefit except inferiority feeling.

  what do you say those of you who didn't give nothing value for our fathers sacrification.

  ReplyDelete
 9. Dani, it was good that we were not colonized by Europeans(I mean if we don't consider those 5 years as colonization). But practically, we have been colonized by the insiders, who were even more cleptocratic than the Europeans. The aborginals sacrified a lot, but now their few children have seen a better future. Our fathers also sacrified, but we are still in dark. So, nothing to be proud of. Rather get ashamed of living in poverty, internal conflicts etc..

  ReplyDelete
  Replies
  1. I live in Canada. It is a great country, but aboriginals still don't have a better future compared to new comers from middle East or Africa. Most private companies don't want to hire them that is the reality. I hope in future things will change for better for them. So Dear, if I was I wouldn't say that.

   Delete
 10. very interesting and as white as snow

  ReplyDelete
 11. .... እኛ የባሕር በራችንን አስወስደን ትንሷን ጅቡቲ ስንለማማጥ እንኖራለን፤ We (Ethiopians) could have been more intelligent had we have access to the marine food in our dish. Mintaregewaleh!!


  ReplyDelete
 12. እኒህ በ1965 ዓም ወደ አውስትራልያ የገቡት የኢትዮጵያ አየር
  ኃይል ባልደረባ ለትምህርት መጥተው ነው በዚሁ የቀሩት፡፡ ዛሬ ከሀገሩ ነባር ነዋሪ (አቦርጅን) ጋር ተጋብተው ይኖራሉ፡፡.... I am sure you will interview this man and tell us more about... focusing on how to scale up such ምርጥ temokiro....., I'm not joking!

  ReplyDelete
 13. "ETHIOPIA NEVER BEEN COLONIZED" God bless Ethiopia and you.D.Daniel Kibret

  ReplyDelete
 14. Nice article. Not to sidetrack but one minor correction though. African American population in the US was 12.6% in the 2010 census (not 30%). If you include Hispanic blacks, that number will be 13.6%. Also, they account for non-Hispanic blacks accounted for 39.4% of the total prison and jail population in 2009. [Source: Wikipedia]. I don't expect the numbers you mention to be accurate to the decimal point but I don't expect that much difference either where the data could easily be found on the web. That may negatively affect the trustworthiness of the other statistical points in this or other articles.

  ReplyDelete
 15. Leka Ulum Ager Yersu Asazag Tarik Aleu.

  ReplyDelete
 16. የራስህ የሆነ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በኖረህና ይህን የምትጽፍልንን ሁሉ በድምጽ ለመስማትና ያየኸውን ሁሉ ደግሞ በፊልም ለማየት ብንችል እንዴት መልካም ነበረ፡፡ ለማንኛውም ግን አውቀህ ለማሳወቅ ለምታደርገው ጥረት እናመሰግንሀለን፡፡

  ReplyDelete
 17. DANi, when I was grade 2 or 3 I heard that Atse Minilik got Bahir zaf(tree) from Australia,is that not true?

  ReplyDelete
 18. Great great thanks for our forefathers who shed their blood for their freedom, for their country for us. Those who do not know/really understand what slavery mean from practical point of view do not appreciate what freedom or independent country mean.
  So, shall we say you our forefathers, let your sole rest in Paradise or be in the hand's of Jesus Christ!!!
  And now what we see the extreme selfishness of few groups to deprive the absolute rights and freedom to live to work, etc in our country will shall one day be pushed aside and Ethiopia will be a free land of justice and democracy, a country comfortable for its citizens to live in.
  May the blessing of the Almighty God and the intersession of his Mother St.Mary be with Ethiopia and Ethiopians!!!
  Amen

  ReplyDelete
 19. ዳኔ በርታ ! በሰላም ይመልሰሕ።

  ReplyDelete
 20. ልብ ላለው ሰው በቀኝ ግዛት በተገዛን እናድግ ነበር ለሚሉት ጥሩ መልስ ነው፡፡
  Thank you very much
  ልጆቻቸውን ለጉልበት ሥራ አስገድዶ በመውሰድ፣ እንዳይወልዱ የማምከኛ መድኃኒት በመስጠት፣ የመጠጥ ሱሰኞች ሆነው እንዲቀሩ በማድረግ አቦርጅኖች ከሀገር እንዲጠፉና ቁጥራቸው እንዲቀንስ ተደርጓል፡፡ ......
  አንዳንድ ጊዜ ለነጻነታችን ለተዋጉት አርበኞች ክብር የምትሰጡት ይህን መሰል የመከራ ታሪኮችን ስትሰሙ ነው፡፡......
  ክብሩንም፣ ነጻነቱንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ ሥልጣኑንም ነጥቀውት ባላገሩን ሁለተኛ ዜጋ ሲያደርጉት ስታዩ ‹ነጻነት ሆይ ዋጋሽ ምን ያህል ነው?› ትላላችሁ፡፡ አንዳንድ ወገኖቼ ‹ጥቂት ቅኝ ብንገዛ ኖሮ እንሠለጥን ነበር፣ እናድግም ነበር› ብለው ይቆጫሉ፡፡.....

  ReplyDelete
 21. Great Dn Daniel, those who thinks ‹ጥቂት ቅኝ ብንገዛ ኖሮ እንሠለጥን ነበር፣ እናድግም ነበር› are those money minded people and lacks long thinking ability.
  ክብሩንም፣ ነጻነቱንም፣ ኢኮኖሚውንም፣ ሥልጣኑንም ነጥቀውት ባላገሩን ሁለተኛ ዜጋ ሲያደርጉት ስታዩ ‹ነጻነት ሆይ ዋጋሽ ምን ያህል ነው?› ትላላችሁ፡፡ አንዳንድ ወገኖቼ ‹ጥቂት ቅኝ ብንገዛ ኖሮ እንሠለጥን ነበር፣ እናድግም ነበር› ብለው ይቆጫሉ፡፡....
  anyways please pray for those who lacks confidence being Ethiopian. God bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 22. Danny the Man!!!much love and long live for you and for your amizing wife(family) who let you to do this amaizing job.Also people, pray for this family.

  ReplyDelete
 23. I am proud of our great fathers,

  ReplyDelete
 24. እግዚአብሔር እረጅም እድሜና ጤናውን ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 25. በሰላም ተመለስ::

  ReplyDelete
 26. i hope i see you soon back in addis fitsum from perth

  ReplyDelete