Thursday, August 15, 2013

‹መድኃኒቱ የትኛችንም ፋርማሲ ውስጥ የለም›

ግብጽ ከድጡ ወደ ማጡ እየተጓዘች ነው፡፡ ሀገርን ማናጋትና ማፍረስ ምንኛ ቀላል እንደሆነ እየተማርንም ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የአስተሳሰብ፣ የበሰለ አመራር፣ የዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና ብስለት፣ የታመነና የበሰለ ሚዲያ፣ መብቱንና ግዳጁን የተረዳና የሚወጣ ማኅበረሰብ፣ ልካቸውንና መልካቸውን የሚያውቁ የፍትሕ፣ የጸጥታና የውትድርና ተቋማት አጠቃላይ ውጤት እንጂ የምርጫ ሂደትና ውጤት ብቻ እንዳልሆነም እየተማርን ነው፡፡
የእሥራኤልና ፍልስጥኤምን የሰላም ድርድር አስመልክቶ በቅርቡ የተጠየቁት የእሥራኤል ፕሬዚዳንት ሺሞን ፔሬዝ ‹‹ድርድር ማለት እኛ መፍትሔ ነው ብለን የምናስበውን ለሌላ ለማሳመን የምናደርገው ውይይት አይደለም፤ ድርድር ማለት ሁለታችንም በጋራ የምንፈልገው ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ነው፡፡›› ብለው ነበር፡፡ ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ‹እንትን ወይም ሞት‹ ብለው የተሰለፉ የግብጽ ልጆች ሀገራቸውን ወደ ማትወጣበት ኪሣራ እየተከተቷት ነው፡፡
አንድ ‹ተረት  በሥዕል› የሚባል መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ የሚል ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡ ሁለት ውሾች መንገድ ላይ ሲሄዱ ከሥጋ ቤት መኪና የወደቀ ምርጥ ሥጋ ያያሉ፡፡ ሁለቱም ወደ ሥጋው ይፈተለካሉ፡፡ ሁለቱም ግን ሥጋው ጋ ከመድረሳቸው በፊት ይፋጠጣሉ፡፡ ሥጋውን እኔ ብቻ ነኝ መብላት ያለብኝ በሚል አባዜ ውስጥ ገብተው ከሥጋው ጎን መናከስ ጀመሩ፡፡ በእግር እየተገፋፋ፣በጥርስ እየተቧጨቁ ቀኑን ሙሉ ሲናከሱ ዋሉ፡፡ በመጨረሻም ተዳከሙ፡፡ ደማቸው ፈስሶ፣ ቆዳቸውም ተሰነጣጥቆ ምድር ላይ ተዝለፍልፈው ወደቁ፡፡

በዚህ መካከል እንዲት ቀን የሰጣት ቡችላ መጣች፡፡ ስታይ ሁለት ደቦል የሚያክሉ ውሾች መሬት ላይ ተጋድመው ያቃስታሉ፡፡ ከአጠገባቸውም ምን የመሰለ ጮማ ሥጋ ተጋድሟል፡፡ ብታያቸው ካሉበት የሚንቀሳቀሱ ዓይነት አይደሉም፡፡ መጀመሪያ ወደ ሥጋው ጠጋ አለች፡፡ በድካም ተገላብጦ ከማየት በቀር ለማስጣል ዐቅም ያለው አልነበረም፡፡ ሥጋውን መንጨት ስትጀምር ከሚያቃስት ድምጽ በቀር የከለከላት የለም፡፡ በመጨረሻም እየጎተተች ወሰደችው፡፡
ቀማኛ ሲጣላ
ተስማምቶ እንዳይበላ
መንትፋቸው ሄደች ዘዴኛ ቡችላ
የሚል በተረቱ መጨረሻ ላይ ሠፍሯል፡፡
በአብዮቱ ዘመን ልሂቃኑ መግባባት፣ ከሚከተሉት ርእዮተ ዓለም ውጭም ሌላ ሦስተኛ መፍትሔ ማምጣት አቅቷቸው እርስ በርሳቸው ሲባሉና ሲናከሱ ሀገሪቱን ለወታደራዊው ጁንታ አስረከቧት፡፡ በተግባቦትና በውይይት፣ በዕውቀትና በልምድ እንዴት መፍትሔ እንደሚመጣ ከመሥራት ይልቅ ከማርክስና ሌኒን፣ ከማኦና ከኤንግልስ መጻሕፍት ውስጥ መፍትሔውን ሲፈልጉ በጠመንጃው መፍትሔ አመጣለሁ ለሚለው ደርግ ሁሉንም አስረከቡት፡
አብዛኞቹ የግብጽ የፖለቲካ ኃይሎች ሙባረክን ሕዝቡ ሲያነቃንቀው የተደራጁ ናቸው፡፡ የተግባባ ኃልይ፣ አቋም ያለው አባል፣ የተዘረጋ መዋቅር፣ የተጠና ፕሮግራም፣ በሕዝቡ ልብ ውስጥ የገባ ሃሳብ አልነበራቸውም፡፡ የሙስሊም ወንድማማቾች ግን ይህንን በበጎውም በክፉውም ዘመን ሲሠራ ነው የኖረው፡፡ ሀገሪቱ ወደ ምርጫ ስትሄድ የአንዳንድ ፓርቲዎች ሰዎች የተማሩ፣ የታወቁ፣ የተከበሩ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሠሩ ስለሆኑ ብቻ ሕዝብ ይመርጠናል ብለው ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ የተደራጀ ኃይል፣ የተዘጋጀ መዋቅር፣ የተግባባ አባል ግን አልነበራቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ከፓርቲያቸው በላይ ሰዎቹ የገዘፉ ነበሩ፡፡ ፓርቲዎቻቸውም የሚጠሩት በፓርቲያቸው ስም ሳይሆን የእገሌ ፓርቲ እየተባሉ ነበር፡፡ ምርጫው ሲመጣ በሚገባ የሠራውና የተደራጀው የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አሸነፈ፡፡ ልሂቃኑም ሀገሪቱን አሳልፈው ሰጧት፡፡ ይኼው ዛሬ የመውጫ መንገዱ ጠባር በር ሆነ፡፡
ምንጊዜም ሀገራዊ መፍትሔ ውጤታማ የሚሆነው ሀገር ከመፍረሷ በፊት ከተከናወነ ነው፡፡ በኢራቅ፣ በአፍጋኒስታን፣ በሶማልያና በኮንጎ የምናየው ነገር ይኼንን ይነግረናል፡፡ ሀገር ከፈረሰች፣ ሰው ደም ከተቃባ፣ ሀገራዊ ተቋማትም የሚመጣውን ችግር ሊሸከሙት ከማይችሉበት ደረጃ ከደረሱ በኋላ መፍትሔው ከሁሉም ወገኖች እጅ ይወጣል፡፡ አንድ በሽተኛ ሊድን የሚችለው በተቻለው ፍጥነት በቶሎ ወደ ሕክምናው ቦታ ከደረሰ ነው፡፡ በዘገየ ቁጥር የመዳን ዕድሉ እየጠበበ ይሄዳል፡፡ ሀገራዊ ችግርም እንደዚሁ ነው፡፡
አውስትራልያውያን ‹መድኃኒቱ የትኛችንም ፋርማሲ ውስጥ የለም› የሚሉት ነገር አለ፡፡ ሰሞኑን በሀገራቸው የምርጫ ዘመቻው ተጀምሯል፡፡ ዋናው አጀንዳቸው የሆነውን የሕገ ወጥ ስደት ጉዳይ ሲከራከሩበት ነበር ይህን ያሉት፡፡ በሀገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች ሥልጣን በያዙ ቁጥር ሕገ ወጥ ስደትን ያስቆማል የሚሉትን መፍትሔ ሁሉ ወስደዋል፡፡ በየወሩ 1440 ስደተኞች በጀልባ ለሚገቡባት አውስትራልያ ግን የማንም ፓርቲ መድኃኒት ፍቱን መድኃኒት ለመሆን አልቻለም፡፡ ‹‹ችግሩን ለመፍታት የወሰድናቸው መንገዶችም አልፈቱትም፡፡ ሁሉንም መድኃኒት ሞክረናል፤ ግን በሽታው አልዳነም፡፡ ስለዚህ ሌላ መድኃኒት ነው የሚያስፈልገን፡፡ መድኃኒቱ ደግሞ በየትኛውም ፋርማሲ ውስጥ የለም›› ነው ነገሩ፡፡ አዲስን በሽታ በድሮ መድኃኒት ማከም በሽታውን ራሱን ማወሳሰብ ነው፡፡ እናስ? ከተባለ የተለመደውን የመድኃኒት ማዘዣ እየጻፉ የማያድን መድኃኒት ከመስጠት ይልቅ፣ አዲስ መድኃኒት እንፈልግ፣ እንፈልስፍ፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉም የመድኃኒት ዐዋቂዎችን ዕውቀትም፣ ትጋትም፣ ዐቅምም፣ ቆራጥነትም ይፈለጋል፡፡
ነባር መድኃኒት የሚሠራው በሽታው መድኃኒቱን ሳይለምደው ወይም በሽታ ከዐቅም በላይ ከመሆኑ በፊት ነው፡፡ ያን ጊዜ ከሆነ ከአንዱ ፋርማሲ የተሻለውን መድኃኒት ገዝቶ መውሰድ ይቻላል፡፡ በሀገራችን እንደሚደረገው የሕንድ ነው፣ የቻይና ነው፣ የጀርመን ነው፣ የእንግሊዝ ነው፣ የአሜሪካ ነው፣ የደቡብ አፍሪካ ነው? ብለን የተሻለውን መድኃኒት ገዝተን እንውጣለን፡፡ በሽታው ከዐቅም በላይ ሲሆን ግን ሌላ አዲስ መድኃኒት ነው የሚጠይቀው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሽታው ራሱ አዲስ ስለሚሆን፡፡ ያለበለዚያ አዲሱን ወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ይሆናል፡፡
ሞያ ከጎረቤት ነውና ሀገራችን ከጎረቤት ግብጽ መማር ያለባት ይመስለኛል፡፡ አሁን መድኃኒቱ ከሁሉም ወገኖች ፋርማሲዎች ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ ሀገራዊ ችግሮቻችንን ለማከም በድሮ መድኃኒቶች ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ አንዳንድ መድኃኒቶች በንጉሡ ጊዜ፣ በወታደራዊው መንግሥት ጊዜ፣ በነጭ ሽብርና ቀይ ሽብር ጊዜ፣ በአሲምባና በደደቢት፣ ተሞክረው ያልሠሩ ናቸው፡፡ በኢዲዩ፣ በኢሕአፓ፣ በመኢሶን፣ በኢጭአት፣ በወዝ ሊግ፣ በአኢሴማ፣ በአኢወማ፣ በ66ና በ97 ተሞክረው ማዳን ያቃታቸው ናቸው፡፡ በሽታው ግን አዲስ ነው፡፡
አሁን የሚበጀን የእኔ ፋርማሲ ውስጥ ያለው መድኃኒት ፍቱን ነው ማለቱን ትቶ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት ለመፍጠር መነሣት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁሉንም ዕውቀት፣ ትጋት፣ ቁርጠኛነትና ዐቅም ይጠይቃል፡፡ ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም፡፡ ያለበለዚያ ግን በግብጻውያን ላይ እንደምናየው ሁላችንም ወደ ጽንፍ ሄደን ‹እንትን ወይም ሞት› ካልን ሁላችንም ሥጋውን እናጣውና ያልታሰበ ቡችላ ነጥቆ የሚሄድበትን ዕድል እናመቻቻለን፡፡ መድኃኒቱ የሁላችንም ፋርማሲ ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ የሚበጀው የእኔን መድኃኒት ብቻ ካልዋጥክ አትድንም የሚለው አሮጌው መፍትሔ ሳይሆን መድኃኒቱን ሊያስገኙ የሚችሉትን አካላት ሁሉ ተጠቅሞ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት መፈለግ ነው፡፡   
ካሮላይን ስፕሪንግ፣ ሜልበርን፣ አውስትራልያ

25 comments:

 1. Nice article. Hulachenem kebetachen jemeren addis medehanit enefeleg.

  ReplyDelete
 2. ፔትሮቭ የተባለ አንድ እግር ኳስ ተጫዋች ከአመት በፊት በደም ካንሰር ህመም ምክንያት ጨዋታ ከማቆሙ በፊት አስቶነቪላ የተባለዉን ክለብ በአንበልነት ያገለግል ነበር 19 ቁጥር ማልያንም ያደርግ ነበር ዉለታዉን ያሰቡ በመጎዳቱም ያዘኑ የክለቡ ደጋፊዎች ታድያ አስቶነቪላ በሚያደርጋቸዉ ጨዋታዎች በሙሉ 19ኛዉ ደቂቃ ላይ ተነስተዉ ያጨበጭባሉ ዛሬ እንደሰማሁት ዜና ፔትሮቭ የክለቡ ደጋፊዎችን ካሁን በኋላ እንዲህ ያለዉን ድርጊት ተዉት እና ለክለባችን አዲስ ዘመን ይሁን እኔን ተዉና ክለባችን ላይ እናተኩርሲል እንዳሳሰብ ነገሩን፡፡ እኛስ መቼ ነዉ በቃ የምንባለዉ?

  ReplyDelete
 3. "ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም፡፡"

  "መድኃኒቱ የሁላችንም ፋርማሲ ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ የሚበጀው የእኔን መድኃኒት ብቻ ካልዋጥክ አትድንም የሚለው አሮጌው መፍትሔ ሳይሆን መድኃኒቱን ሊያስገኙ የሚችሉትን አካላት ሁሉ ተጠቅሞ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት መፈለግ ነው፡፡:
  Dn. Daniel, No words to express my feeling and perception when I read the article. Dear bro you are so blessed; May GOD bless You more. Long live to You and your beloved family too.

  ReplyDelete
 4. "ሀገራችን ከጎረቤት ግብጽ መማር ያለባት ይመስለኛል"

  ReplyDelete
 5. አሁን የሚበጀን የእኔ ፋርማሲ ውስጥ ያለው መድኃኒት ፍቱን ነው ማለቱን ትቶ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት ለመፍጠር መነሣት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁሉንም ዕውቀት፣ ትጋት፣ ቁርጠኛነትና ዐቅም ይጠይቃል፡፡ ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም፡፡ ያለበለዚያ ግን በግብጻውያን ላይ እንደምናየው ሁላችንም ወደ ጽንፍ ሄደን ‹እንትን ወይም ሞት› ካልን ሁላችንም ሥጋውን እናጣውና ያልታሰበ ቡችላ ነጥቆ የሚሄድበትን ዕድል እናመቻቻለን፡፡ መድኃኒቱ የሁላችንም ፋርማሲ ውስጥ ያለ አይመስልም፡፡ የሚበጀው የእኔን መድኃኒት ብቻ ካልዋጥክ አትድንም የሚለው አሮጌው መፍትሔ ሳይሆን መድኃኒቱን ሊያስገኙ የሚችሉትን አካላት ሁሉ ተጠቅሞ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት መፈለግ ነው፡፡ very true!

  ReplyDelete
 6. D/n Daniel it is so nice article and GOD bless you everyday

  ReplyDelete
 7. በውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ፣የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች … ለአገራችን ኢትዮጵያ ሠላም ከአሁን በኋላ ምን ይበጃት ይሆን? ብላችሁ ይህን በድህነት ማቅ ውስጥ ያለን ሕዝብ አድኑት እናንተም ዳኑ፣ አአይ የእኔ ብቻ ይበጃል የምትሉ ከሆነ የኢትዮጵያ አምላክ በሰጣችሁ ሥልጣን ሊያወርዳችሁ፣ ሊያዋርዳችሁ ይችላል፡፡ ይህ ሕዝብ ምስኪን ነው ዝም ስላለ ብቻ ምንም አያመጣም አትበሉ፡፡
  የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻችሁን ታደጉ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ አደራ ከሁሉም ይበልጣል፡፡ በሰማይም በምድርም ሁሉ ተሰጥቷችኋልና…የእኔ ፋርማሲ ውስጥ ያለው መድኃኒት ፍቱን ነው ማለቱን ትቶ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት ለመፍጠር መነሣት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁሉንም ዕውቀት፣ ትጋት፣ ቁርጠኛነትና ዐቅም ይጠይቃል፡፡ ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም፡… ጊዜው የፈቀደለት ፓርቲ ኢአህዴግ ከሁሉም የተሻለ ዕድል አላችሁ ኢትዮጵያንም ራሳችሁንም ለማዳን ከእጅ ሥልጣን ሣይወጣ የተወሳሰበውን የአገሪቷን መልክ በሃይማኖት አባቶችና በእምነት ውስጥ ባለመግባት ከሃይማኖት ነክ ሥራዎች ራሳችሁን አውጥታችሁ ሕዝቡን በሚገባ ምሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ቦታ ሰጥታችሁ ለአገር እድገት ለኢትዮጵያ በማሰብ ኢትዮጵያን ታደጉ ፡፡
  እግዚአብሔር በቸርነቱ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግልን፡፡

  ReplyDelete
 8. በውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ፣የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች … ለአገራችን ኢትዮጵያ ሠላም ከአሁን በኋላ ምን ይበጃት ይሆን? ብላችሁ ይህን በድህነት ማቅ ውስጥ ያለን ሕዝብ አድኑት እናንተም ዳኑ፣ አአይ የእኔ ብቻ ይበጃል የምትሉ ከሆነ የኢትዮጵያ አምላክ በሰጣችሁ ሥልጣን ሊያወርዳችሁ፣ ሊያዋርዳችሁ ይችላል፡፡ ይህ ሕዝብ ምስኪን ነው ዝም ስላለ ብቻ ምንም አያመጣም አትበሉ፡፡
  የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻችሁን ታደጉ ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁ አደራ ከሁሉም ይበልጣል፡፡ በሰማይም በምድርም ሁሉ ተሰጥቷችኋልና…እኔ ፋርማሲ ውስጥ ያለው መድኃኒት ፍቱን ነው ማለቱን ትቶ ለአዲሱ በሽታ አዲስ መድኃኒት ለመፍጠር መነሣት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሁሉንም ዕውቀት፣ ትጋት፣ ቁርጠኛነትና ዐቅም ይጠይቃል፡፡ ሀገር የአንዱ ወገን ብቻ ልትሆን አትችልም፡፡ ሀገር የሁሉም ካልሆነች የማንም አትሆንም… ጊዜው የፈቀደለት ፓርቲ ኢአህዴግ ከሁሉም የተሻለ ዕድል አላችሁ ኢትዮጵያንም ራሳችሁንም ለማዳን ከእጅ ሥልጣን ሣይወጣ የተወሳሰበውን የአገሪቷን መልክ በሃይማኖት አባቶችና በእምነት ውስጥ ባለመግባት ከሃይማኖት ነክ ሥራዎች ራሳችሁን አውጥታችሁ ሕዝቡን በሚገባ ምሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ቦታ ሰጥታችሁ ለአገር እድገት ለኢትዮጵያ በማሰብ ኢትዮጵያን ታደጉ ፡፡
  እግዚአብሔር በቸርነቱ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግልን፡፡
  የ፡

  ReplyDelete
 9. Thanks k Dani i wish i can listen or read as many things as wanted from you.
  I think the problem is that we don't accept that we don't know we never give chance for better people,so that we are trying to get the medicine while many people dies . The reason behind is most of the time we Ethiopians don't want to be overtaken by anybody even if we know that s/he has a better idea,MEDICINE that is the area where everyone,the people,the government work on.Then the medicine will be find in all PHARMACIES!!!

  ReplyDelete
 10. ልክ ነህ ዳኒ፤ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ በትክክል ሊገልጸው የሚችለው ይህ ይመስለኛል። ለሁሉም ያስቸገረው ግን ሁላችንም ሆዳችንም በለው ነፍሳችን እያወቀው የዕለቱን እንጂ ዘላቂውን ማሰብ ያለመቻላችን ነው። የችግራችን ቫይረስ የተሰጡትን መድኃኒቶች ሁሉ እየተቋቋመ ከልህቅ እስከ ደቂቅ እያጠቃን ነው። ለምሳሌ እንኳ የሚጠራ የሀገር መሠረታዊ ምሰሶዎች ሲናዱ እና ወደ መጠፋፋት ስንደረደር እያየ ተዉ የሚል አንድ ሰው በሀገሪቷ ውስጥ መታጣቱ ሁሌም እንቅልፍ ይነሳኛል። እውነተኛው መድኃኒት የእናንተም የእነእንቶኔም አይደለም ለማለት ድፍረት ያላቸው ምሁራን ድርቅ የመታን ይመሰላል።

  ReplyDelete
 11. lela buchela kgba eko koye

  ReplyDelete
 12. ዳኔ ተባረክ፤ በሰላም ይመልስሕ። እግዜአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ።

  ReplyDelete
 13. D/N Egziabhier amlak yebarikih gin D/N ere lemehonu ye Ethiopia meriwech meche yehon kom bilew yemasbubet? ehen tiyake lante bitewe yeshal ante gin bemigeba maletem lemimeleketew hulu tenagirhal Egziabhier bereket kante gar yehun amen.

  ReplyDelete
 14. well articulated...."ነባር መድኃኒት የሚሠራው በሽታው መድኃኒቱን ሳይለምደው ወይም በሽታ ከዐቅም በላይ ከመሆኑ በፊት ነው፡፡" this what we need from this generation. This era is the era of communication and dialogue not like the Mesafinet or the Derg regime. EPRDF is living 40 years behind the people of Ethiopia.

  ReplyDelete
 15. I heard a joke which is told from our celebrity singer. He is trying to explainig the woyanes' s(×) action. He put x as the owner of restaurant who invites his poor friends and others for lunch. And Mr x was passing the meal and asking how is the food. Almost all of them wouldn't eat the meal.Mr x getting angry by the them and ask them why they're not eating. They answered that the meal has too much salt, but Mr x refused and said, I have tested so that you have to eat it. You're not going anywhere untill you eat , said mr x.

  ReplyDelete
 16. ewnet new egzeabeher selamun yestachew

  ReplyDelete
 17. ዲ.ን ዳንኤል አዎ በጣም ተሞክሮ ያላደን መድሃኒት ቢጠቀሙት ህመሙ ይብሳል ለአዲስ በሽታ አዲስ መድሀኒት ካልተፈለገኘ እንዳልከው ይሆናል ግብፅን የሚያውኩአት ብዙ ናቸው እነሱ ግን መፍትሄው በጃቸው እያለ ሶስተኛ ወገን አስገብተዋል ብየ አስባለሁ በርቱ ብሎ በቀልን የሚያስተምር ወግን አይፈለግም ይቅርታን መቻቻልንና አንድነትን የሚያስተምር እንጂ በረታ በሎ ቦንቦ የሚያስታጥቅ ለውደቀት እንጂ ለእድገት አይሆንም ይሕ ማለት እሬቱን በማር አልብሶ እንደማጉረስ ነው እሪት ከቶ ምሪቱ የማይጠፋ የሆናል
  ጠላትነትን የሚሰብክ ጠመንጃ አስታታቂ እና በወንደሙላይ ጠመንጃ የሚያነሳ ሁለቱ አንድ ናቸው አስታጣቂው ድብቅ አላማ ሲኖረው ደም መፋሰስን ደስታው ያድርጋል ታጣቂውም እንዲሁ
  እንግዲህ ግብፅ መፍትሄ የምታገኘው ከትላልቅ መንገስስታት ሳየሆን ከራሷ ዜጎች ነው ማለትን በዳይ ቢኖር ይቅርታ ጠይቆ ተበዳይ ቢኖር እንኳ ምህረት አድርጎ ካልሆነ ጠላትነት ይፈጠራል ዘረኛነት የፈጠራል ማለት ነው፡፡
  እግዚአብሔር ለገብፅ ሰላሙን የስጥልን

  ReplyDelete
 18. Dan. the idea you posted is deep and on time i am afraid most of us on the road map thinking like this.we never say "i am foolish and ready to know better and new one".
  sorry, i am too far behind u. Hoping to follow

  ReplyDelete
 19. "Heger yehulum kalhonech yemanm athonm"betkkl.neger gn lebuchloch thonalech.

  we can remember the recent history which happened in Cotdevuar,Libya Mali& Syria. The people and the government couldn't find the solution for their country. But we have seen the "BUCHLAS" are interfering in their affair even up to removal of governments. But still these countries have not gotten the real medicine.

  ReplyDelete
 20. Daniel may the almighty God comes your dreams true.

  ReplyDelete
 21. Le adisu beshita addis medhanit mefelig new !!!  Thanks Dn. !

  ReplyDelete
 22. I like this argument than those written to discribe Egypt. I agree "If this country of us is not for all, It is for None!!!" Thanks

  ReplyDelete