Monday, August 12, 2013

የተባረኩ እግሮች


የሀገርን ክብር ከፍ የሚያደርጉ፣ ጽናትንና ብርታትን የሚሰብኩ፣ አልበገር ባይነትንና ተጋድሎን የሚያውጁ፣ ለዓላማ ቁርጠኝነትንና ትጋትን የሚናኙ የተባረኩ እግሮች፡፡ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው እንዲያ ተከበሽ ስትሮጭ፣ ምን ነበር ይሆን የምታልሚው እንዲያ ሀገርሽ አንድ ወርቅ እንኳን አጥታ ስሟ ከሠንጠረዡ ሲጠፋ፤ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው የእነ አበበና የነ ማሞ፣ የነ ምሩጽና የነኃሌሌ፣ የነ ቀነኒሳና የነ ገዛኸኝ ታሪክ ወደ ተረትነት ሲለወጥ፤ ተንታኙ ሁሉ እንዲህ ነበሩኮ የሚለንን ስትሰሚ ምን ነበር ይሆን የምታስቢው፡፡
የሮጥሽውን እንጂ ያሰብሽውን አላየነውም፡፡ ያደረግሽውን እንጂ የወሰንሽውን አልተመለከትነውም፡፡ ወደየት ነበር የሮጥሽው? ምን ነበር ከፊት የሚታይሽ? አበበ ነው ወይስ ኃይሌ? ባንዲራሽ ነው ወይስ ሕዝብሽ? መቼም ምንመ ሳታይ እንዲያ አልተፈተለክሽም፡፡ ምንስ ነበር የምትሰሚው? መቼም የሞስኮን ሕዝብ ጩኸት አይደለም፡፡ በማያውቁት ቋንቋ የሚነገር ጩኸት ምች እንዲያ ያስሮጣልና፡፡ ሂጂ፣ ሂጂ፣ ሂጂ ጥሩነሽ ሩጭ፤ ታሪክ ተረት ሆኖ እንዳይቀር ለሀገርሽ ወርቁን አምጭ› ‹ሂጅ አብረንኅ እየሮጥን ነው፣ ብቻሽን ከቶ አይደለሽም፤ ምሩጽ ቀድሞ ሰባብሮታል፣ ይህ አየር ለኛ አዲስ አይደለም› የሚለው የሕዝብሽ ድምጽ ነበር በሹክሹክታ የተማሽው? አርምሞኮ ቋንቋ ነው በውስጥ ከነፍስ ጋር የሚያወሩት፡፡


እነዚያ እግሮችሽ እንደ ሲላ ሲወረወሩ፣ እንደ ንሥር ሲበርሩ፣ እንደ አቦ ሸማኔ ሲፈተለኩ፣ እንደ ሚግ ሲምዘገዘጉ፣ እጆችሽ እንደ መልአክ ክንፍ አየሩን ሲሰነጥቁ፣ ደረትሽ እንደ ሚሳይል እየከፈለው ሲተኮስ፤ እንደታቀፈች ሰጎን ዓይኖችሽ ምድር ምድር ሲያዩ፣ ከአየር ጋር ስትሟገች፣ ከድል ጋር ስትጠራሪ፣ ከእልክ ጋር ተወራርደሽ፣ ከእምቢ ጋር አብረሽ ስትሮጭ፤ ልብና እግሮችሽ ተስማምተው እየተማከሩ ሲነጉዱ፤ ዓይንና እጆችሽ ተፋቅረው የርቀት መጠን ሲለኩ፤ እንደ ንብ አውራ ታጅበሽ፣ እንደ ንብ ንግሥት ስትከንፊ፤ ምነ ነበር ያኔ የምታስቢው?
ሀገር ነበረች ከኋላሽ፣ ሀገር ነበረች ከፊትሽ፤ እንዳንች ማልያ አጥልቀን፣ እንዳንቺ ሞስኮ ባንጓዝ፤ እንዳንቺ ሀገር ወክለን እንዳንቺ በመም ላይ ባንከፍ፤ ልባችን ካንች ጋር ነበር፣ ሁሉንም ዙር አብሮ ዞሯል፤ ኅሊናችንም ካንቺ ጋር ለአምላክ ሥዕለቱን አቅርቧል፡፡ እንዴት ደስ ይላል መሰለሽ አገር አስከትሎ መሮጥ፤ እያባረርሽን አልነበረም፣ እየተከተልንሽ እንጂ፣ በእጅሽ መሣሪያ አልያዝሽም፤ ውርደትን ቀዘፍሽው እንጂ፡፡ ሀገርን ሊያኮራ የሚሮጥ፣ ድሮም ሕዝብ አብሮት ይሮጣል፣ እግሮቹ ብሩካን ናቸው ብሎ ከጥንቱ መርቆታል፡፡ በሞስኮ አፈር ላይ አይደለም በብሩካን እግሮችሽ የሮጥሽው፣ በሚወድሽና በሚሳሳልሽ ሕዝብ በልቡናቸው ውስጥ ነው፡፡

አብረንሽ ባንሮጥ ኑሮ ድል ስታደርጊ ለምን አብሮ ደስ አለን? ድል አደረግን ሲሉንኮ አብረናቸው ያልተደሰትን ብዙዎች አሉ፡፡ ድሉ የራሳቸው ብቻ የሆነ፤ ብቻቸውን ያሸነፉ፤ ድላቸውን ያልገዛንላቸው፡፡ አንዳንዶች ወርቅ ከሀገራቸው ሲያወጡ አንቺ ግን ወርቅ ወደ ሀገርሽ አመጣሽ፤ ስለዚህ አብረንሽ ሮጥን፡፡ አብረንሽም ስለሮጥን አብረንሽ ተደሰትን፡፡ ሞስኮ ላይ ያዩሽ ሁሉ፤ ምሩጽ አልሞተም አሉ፡፡ አረንጓዴው ጎርፍ ቢደርቅም አረንጓዴ ወርቅ አላቸው አሉ፡፡ ሁሉንም የሚግባባ ሃሳብና ፕሮግራም፣ አስተዳደርና አመራር፣ አካሄድና መዋቅር በጠፋበት ጊዜ ምሥራቅ ከምዕራብ ሰሜን ከደቡብ አስተባብረሻልና የመግባቢያ ሰነዳችን ሆነሻል፡፡ በየጎራው የቆሙትን፣ በየተቃራኒው የተሰለፉትን ሁሉንም ሞስኮ አምጥተሸ አንድ አድርገሻቸዋልና የአንድነት ዓርማ ሆነሻል፡፡ 
ማጭበርበር በሌለው ምርጫ ተመርጠሻል፤ የምረጡኝ ዘመቻ ሳያስፈልግሽ በተግባር ሕዝብ አሰልፈሻል፤ ዙፋን ሳያስፈልገሽ ነግሠሽ፣ ሉል ሳያስፈልግሽ ገዝተሻል፡፡ ስም ወደ ግብር ይመራልና ጥሩነሽ ጀግና ሆነሻል፡፡
እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡ 

63 comments:

 1. "ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡ "

  ReplyDelete
 2. ማጭበርበር በሌለው ምርጫ ተመርጠሻል፤ የምረጡኝ ዘመቻ ሳያስፈልግሽ በተግባር ሕዝብ አሰልፈሻል፤ ዙፋን ሳያስፈልገሽ ነግሠሽ፣ ሉል ሳያስፈልግሽ ገዝተሻል፡፡ ስም ወደ ግብር ይመራልና ጥሩነሽ ጀግና ሆነሻል፡፡

  ReplyDelete
 3. አርምሞኮ ቋንቋ ነው በውስጥ ከነፍስ ጋር የሚያወሩት፡፡

  ReplyDelete
 4. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡

  ReplyDelete
 5. ግጥም ነበር ስድ ንባብ ያነበብኩት እሷንም እገዚአብሄር ይባርካት፡፡ አንተንም ጣቶችህን ከቁርጥማት ይጠብቅህ፡፡ እንዴት ዓይነት የተሳለ በዕር ነው

  ReplyDelete
 6. ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ

  ቀና እንዳረግሽን ቀና በይ
  ከፍ ከፍ ከፍ በይ
  ጸዳል ውበትሽ ሁለቱ እግሮችሽ
  ተምዘገዘጉና
  ከፍከፍ አሉና
  ከፍ አደረጉት ባንዲራውን
  ያ የተቃጠለውን ያ የተቀደደውን

  ReplyDelete
 7. yejegna lej jegna new
  How ever i like to comment Ethiopian Athletics Federation 1. Why they force athletes with out interest
  2. Why they fail to trainee all athletes in group rather than personal managers
  Because these are commented for our failure in 10,000 men

  ReplyDelete
 8. Wey Dn Daniel tadleh...simethin meglets tichilaleh!!Egziabher hulachinnm betesemaranbet lewutet yabkan!!

  ReplyDelete
 9. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡

  ReplyDelete
 10. እጅግ፡ አኮራሽን፡ ጥሩዬ!

  ባንድ፡ ባንዲራ፡ ተቃቅፎ፡ ፎቶ፡ መነሳቱን፣ እና፡ ተመልካቹን፡ እየተዟዟሩ፡ ማመስገኑን፡ ግን፡ ምነው፡ ለኬኒያውያኑ፡ ተውንላቸው? እንደ፡ ጃማይካዊው፡ ቦልት፡ ለብቻ፡ መቦረቅን፡ እነ፡ ሃይሌና፡ እነ፡ ደራርቱ፡ ስላላስለመዱን፡ ጥቂት፡ ግር፡ ብሎኝ፡ አመሸሁ። ሶስት፡ ባንዲራ፡ ይዘው፡ ሶስቱ፡ የኢትዮጲያ፡ ሯጮች፡ ሲታዩ፡ ያልተለመደ፡ ነው። ተቃቅፎ፡ የግል፡ ውጤታማነትንም፡ ሆነ፡ ሀገራዊውን፡ ደስታ፡ መግለጽ፡ እንደዋዛ፡ እየተረሳ፡ መምጣቱን፡ እንደ፡ እኔ፡ እናንተም፡ አስተውላችሁ፡ ይሆን?

  መልካም፡ እድል፡ ለቀሪዎቹ፡ ሯጮቻችን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Definitely, I was confused for the moment.

   Delete
  2. you are right!

   Delete
  3. wendme, siyashenfu abro medeset, beruchaw gize keredu athletoch gar sihon yamral.

   Delete
 11. አብረንሽ ባንሮጥ ኑሮ ድል ስታደርጊ ለምን አብሮ ደስ አለን? ድል አደረግን ሲሉንኮ አብረናቸው ያልተደሰትን ብዙዎች አሉ፡፡ ድሉ የራሳቸው ብቻ የሆነ፤ ብቻቸውን ያሸነፉ፤ ድላቸውን ያልገዛንላቸው፡፡

  Enkuan des Yalachihu, all Ethiopians

  ReplyDelete
 12. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡

  ReplyDelete
 13. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡

   Delete
 14. It is very sad for Ethiopian with out Gold, Thanks for Trunesh Finaly we got one Gold.

  ReplyDelete
 15. Running is also a mind game..ውዳሴ እግር በዛ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hey kine atawkem libel? Lewekesa atchekul!

   Delete
  2. We are waiting for your writing(an article) on mind. I am sure you can't even a reply for a letter.

   Delete
 16. ቅዱስ ጳውሎስ የግሪክን ባህላዊ ስፖርት አነጻጽሮ ሩጫዬን ፈፀምኩ አለ።

  ወቅቱ የሩጫ ነው። ሁል ጊዜ ኢትዮጲያዊያን የሚሳተፉበትን ሩጫ ስናይ ልባችን ስለምን ይመታል? ይህ የሀገር ፍቅር ሁል ጊዜ ይገርመኛል!

  ሩጦ ማሸነፍ ይቆየንና አሯሩጦ ማድከም የቡድን ስራ የት ገባ? ለእናት ሀገሩ መሥዋዕት የሚሆን ማን ይሆን?

  ባለፈው ዓመት ለጥሩዬ ከገጠምኩላት የተወሰደ፦

  “እውነትም ጥሩነሽ”

  (ጥ)ሩነሽ እውነትም ጥሩ ነሽ
  (ሩ)ጫን አስተማርሽ አፈትልከሽ ሮጠሽ!
  (ነ)ይ ተደሰቺ ባንዲራውን ይዘሽ
  (ሽ)ልማትሽ ይህ ነው ለፈሰሰው ላብሽ!

  ጥሩነሽ እውነትም ጥሩ ነሽ
  እጅግ ይደሰቱ የወለዱ እናትሽ!
  ጥሩነሽ እውነትም ጥሩ ነሽ
  ይህን ድንቅ ስምሽ ማን ይሆን የሰጠሽ!

  ጥሩነሽ እስኪ ልጠይቅሽ
  ምነው ቪቪያን ጥለሽ ብቻሽን ገሠገሥሽ!?
  እልልልል እኛን ደስ ብሎናል
  እጅግ ይደሰቱ የወለዱ አባትሽ!
  ጥሩነሽ እውነትም ጥሩ ነሽ
  ወርቅ ይዘሽ መጣሽ ለእናት ሀገርሽ!!

  http://yonas-zekarias.blogspot.co.uk/

  ReplyDelete
 17. ዳኔ፤ የሾለ ብዕር አለ እንደኔው አድናቄሕ ? ደግ በሉዋል ለዜያውስ ሁል ገብ ። ጥሩነሽንም ሆነ አንተን በሰላም ወዳገራችሁ ትመለሱ ዘንድ ምኞቴ ነው። በርቱ

  ReplyDelete
 18. Dani le Tirunesh kezihem belay mallet techelalehena tsafelen!! Lezignaw gin enameseginalen! Ashenafi

  ReplyDelete
 19. ሞስኮ ላይ ያዩሽ ሁሉ፤ ምሩጽ አልሞተም አሉ፡፡ አረንጓዴው ጎርፍ ቢደርቅም አረንጓዴ ወርቅ አላቸው አሉ፡፡

  ሙሉ ጽሁፉን ከእንባ ጋር ጨረስኩት! ማራኪ ነው ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ!!!

  ጥሩዬ ጥሩ ወርቃችን ነሽ፡ በልባችን ጽላት ስምሽን በወርቅ ጽፈሻል እንወድሻለን! ቀና አድርገሽናል አምላክ ዘመንሽን ይባርከው!!!

  ReplyDelete
 20. Amen Dani lantem edimena tena setito yakoyilin

  ReplyDelete
 21. እነዚያ እግሮችሽ እንደ ሲላ ሲወረወሩ፣ እንደ ንሥር ሲበርሩ፣ እንደ አቦ ሸማኔ ሲፈተለኩ፣ እንደ ሚግ ሲምዘገዘጉ፣ እጆችሽ እንደ መልአክ ክንፍ አየሩን ሲሰነጥቁ፣ ደረትሽ እንደ ሚሳይል እየከፈለው ሲተኮስ፤ እንደታቀፈች ሰጎን ዓይኖችሽ ምድር ምድር ሲያዩ፣

  ReplyDelete
 22. ምስጋናችንን ለመግለጽ ከዚህ በላይ ማለት ይቻል ይሆን? አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete
 23. ሁለተኛ አስሩጠኸናልና ሁለተኛም እንድናመሰግናት አድርገኸናልና አንተንም የንስር ዐይን ይስጥህ  ReplyDelete
 24. i like it very much.your hand is blessed and i wish much blessing on your hand.

  ReplyDelete
 25. ድል አደረግን ሲሉንኮ አብረናቸው ያልተደሰትን ብዙዎች አሉ፡፡
  ማጭበርበር በሌለው ምርጫ ተመርጠሻል፤

  ReplyDelete
 26. የሀገርን ክብር ከፍ የሚያደርጉ፣ ጽናትንና ብርታትን የሚሰብኩ፣ አልበገር ባይነትንና ተጋድሎን የሚያውጁ፣ ለዓላማ ቁርጠኝነትንና ትጋትን የሚናኙ የተባረኩ እግሮች፡፡

  ReplyDelete
 27. well said and really she deserves the gold because she was ,is and will remain GOLD

  ReplyDelete
 28. EGZIABHER YISTIH ENDEZIH LEHAGERU YEMIKOREKOR BIBEZA YET ABEDERESIN..............

  ReplyDelete
 29. ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ያክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡

  ReplyDelete
 30. አንዳንዶች ወርቅ ከሀገራቸው ሲያወጡ አንቺ ግን ወርቅ ወደ ሀገርሽ አመጣሽ፤ ስለዚህ አብረንሽ ሮጥን፡፡

  ReplyDelete
 31. Danie God bless Tiruyen and u!nice article

  ReplyDelete
 32. ሁሉንም የሚግባባ ሃሳብና ፕሮግራም፣ አስተዳደርና አመራር፣ አካሄድና መዋቅር በጠፋበት ጊዜ ምሥራቅ ከምዕራብ ሰሜን ከደቡብ አስተባብረሻልና የመግባቢያ ሰነዳችን ሆነሻል፡፡
  በየጎራው የቆሙትን፣ በየተቃራኒው የተሰለፉትን ሁሉንም ሞስኮ አምጥተሸ አንድ አድርገሻቸዋልና የአንድነት ዓርማ ሆነሻል፡፡

  ReplyDelete
 33. I can not stop crying! tnx dani

  ReplyDelete
 34. be Ewnetim Tiru nat. Tiruwoch hulem Wed Hagerachewin Yitebikalu Degenioch Hulem le Hagerachew Yewdikalu Yenesalu!

  ReplyDelete
 35. Egzabher ystlene Truyame Antem Tebreku betme ewdcualuge

  ReplyDelete
 36. D/N betikikl yemtimesegen wetat nech ye Ethiopia Nigist bitbalem ayansatim akorachin ye Egziabhier haile keswa gar yehun amen

  ReplyDelete
 37. ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡ "

  ReplyDelete
 38. የሮጥሽውን እንጂ ያሰብሽውን አላየነውም፡፡ ያደረግሽውን እንጂ የወሰንሽውን አልተመለከትነውም፡፡ ወደየት ነበር የሮጥሽው? ምን ነበር ከፊት የሚታይሽ? አበበ ነው ወይስ ኃይሌ? ባንዲራሽ ነው ወይስ ሕዝብሽ? መቼም ምንመ ሳታይ እንዲያ አልተፈተለክሽም፡

  ReplyDelete
 39. "ሁሉንም የሚግባባ ሃሳብና ፕሮግራም፣ አስተዳደርና አመራር፣ አካሄድና መዋቅር በጠፋበት ጊዜ ምሥራቅ ከምዕራብ ሰሜን ከደቡብ አስተባብረሻልና የመግባቢያ ሰነዳችን ሆነሻል፡፡
  በየጎራው የቆሙትን፣ በየተቃራኒው የተሰለፉትን ሁሉንም ሞስኮ አምጥተሸ አንድ አድርገሻቸዋልና የአንድነት ዓርማ ሆነሻል፡፡
  ......
  ......
  ......
  እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡"

  ReplyDelete
 40. Abrensh banrot noro dl stadergi lemn abren tedesetn.

  Dl arederegn silun abrenachew yltedesetn bzuwoch alu.

  ReplyDelete
 41. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግሮችሽን አበርትቶ፣ ጣቶችሽን ያለምልማቸው፣ ኅሊናሽን አንቅቶ፣ ለዓይኖችሽ ብርሃን ይጨምርላቸው፤ የልብሽን ምት ጠብቆ እጆችሽን አክናፍ ያርጋቸው፤ ሳትደክሚ ምትክሽን፣ ሳታርፊ ደቀ መዝሙርሽን ያሳይሽ፡፡ ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡

   Reply

   Delete
 42. እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ!!!!!!

  ReplyDelete
 43. Say something for Meseret Defar too, bante yamiral

  ReplyDelete
 44. ይህንን ብሩህ ጭንቀላትና ያልነተበ ብዕር ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ጣና ዳር ላይ ነበር የማውቀው፤ ስላልነጠፈ አምላኬን አመሰግናለሁ! የልቤን ስለገለጽከው ተባረክልኝ ብየሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 45. ይህንን ብሩህ ጭንቀላትና ያልነተበ ብዕር ከሃያ አምስት ዓመት በፊት ጣና ዳር ላይ ነበር የማውቀው፤ ስላልነጠፈ አምላኬን አመሰግናለሁ! የልቤን ስለገለጽከው ተባረክልኝ ብየሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 46. መሰረትን እና ሌሎቹንም ጀግኖች አመስግንልን ብዕር አያያዝህ ስለሚማርከኝ ነው

  ReplyDelete
 47. የሚያምር ምርቃት ወድጄዋለሁ

  ReplyDelete
 48. Wudassie Mariam aynet neger Almeselachuhum?

  ReplyDelete
  Replies
  1. wudase jegna new! why dont you do similar achievement for your country and get one for yourself. serto mewedes, sayseru kemewkes yishalal my friend.

   Delete
 49. I like it so much! God bless Tirunesh!! Yimiamesegenu brukan nachew ena Danielem egziabher yibarekeh! Amen!!

  ReplyDelete
 50. "ቀና እንዳደረግሽን ቀና በይ፣ እንዳከብርሽን ይክብርሽ፤ እንዳኮራሽን ያኩራሽ፤ እንዳደመቅሽን ያድምቅሽ፡፡ "
  Reply

  ReplyDelete
 51. ከሯጯ ጸሀፊው እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete