በቀደም በቀለበት መንገድ ላይ በመኪና ስሄድ ከጎናችን አንድ ነጭ ፒክ አፕ መኪና
ይጓዝ ነበር፡፡ ዘወር ብዬ ሳየው በሩ ላይ የመሥሪያ ቤቱን ስም ለጥፏል፡፡ ያየሁትን ለማመን ስላቃተኝ በሞባይል ፎቶ
አነሣሁት፡፡ የድርጅቱ ስም ግምማአድ (AISA) ይላል፡፡ ምን ሆነው ነው እንዲህ ያለ ለክፉ ትርጉም የሚያጋልጥ ስም የሚያወጡት፡፡
ለመሆኑ ድርጅቱ በአማርኛ ሲጠራ ምንድን ነው የሚባለው? ‹ግም ማአድ› ማለትኮ በአማርኛ መልካም ትርጉም የለውም፡፡ አሁን እዚያ
የሚሠራ ሰው የት ትሠራለህ ሲባል ‹ግምማአድ እሠራለሁ› ይላል ማለት ነው?
አንዳንድ ድርጅቶች የባለቤቶቹን ወይም የረጅዎችን ፍላጎት ማሳካታቸውን እንጂ
በባለቤቶቹ ላይ የሚያመጡት ተጽዕኖ ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ ያ ስም ከአካባቢው ባህልና እምነት አንጻር በተጠቃሚውም ሆነ
በሠራተኛው ላይ ተጽዕኖ ማድረሱ አይገመገምም፡፡ በአንድ ወቅት ጃፓኖች ያመረቱትን መኪና የሰየሙበት ስም በፈረንሳይኛ ‹ሞት ›
የሚል ትርጉም በመስጠቱ ምክንያት የነበረውን ክርክር አስታውሰዋለሁ፡፡
ባለፈው ጊዜ በደቡብ ጎንደር በንፋስ መውጫ ከተማ በኩል ስናልፍ ‹ዝሙት በኛ ይብቃ›
የሚባል የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ አየን፡፡ ስሙ ገረመንና ለመጠየቅ ጠጋ አልን፡፡ ሱቁ የተከፈተው ከዚህ በፊት በዝሙት አዳሪነት
ይተዳደሩ የነበሩ ሴቶችን ከዚህ ዓይነት ተግባር በማውጣት መሆኑ ተነገረን፡፤ ይሁን ሃሳቡ መልካም ነው፡፤ ነገር ግን አንድ ሰው
ምንስ ቢሆን ‹እኔ ዝሙት አዳሪ ነበርኩ› ብሎ በአደባባይ እንዲናገር እንዴት ይደረጋል? የእነዚያ ሴቶች ልጆችስ ‹ዝሙት በኛ
ይብቃ ሱቅ የኛ ነው› ብለው በኩራት ይናገራሉ? ሰዎችስ ‹ዝሙት በኛ ይብቃ ሱቅ አጠገብ እንገናኝ› ተባብለው ይቀጣጠራሉ? እዚህ
አልጽፈውም እንጂ የአካባቢው ሰዎች ሱቁን የሚጠሩት በሌላ ስም ነው፡፡
እስኪ ለዛሬ ‹ግምመአድ› የሚባለው ተቋም ወዳስታወሰኝ በሀገራችን ለንግድ፣ ለመንግሥታዊና
መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ስለሚወጡት ስሞች በተለይም ስለ የአሕጽሮት ስሞች እናውጋ፡፡ በታላላቅ ከተሞቻችን ውስጥ ድርጅትንና
ሕንፃን በእንግሊዝኛ አሕጽሮት መሰየም እየተለመደ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ስያሜዎች እንኳን እኛ ተመልካቾቹ ቀርተን ባለቤቱም ቢሆን
ለመጥራት የሚቸገርባቸው ዓይነት ናቸው፡፡ ESLPTYGQ ሕንፃ
የሚለውን እስኪ ምን ብላችሁ ትጠሩታላችሁ? አንድ ቦታ ደግሞ በአማርኛ ‹ትግድብም› የሚባል ሕንፃ አይቻለሁ፡፡ አሁን ይህንን
እንዴት አድርጎ ማስታወስ ይቻላል? በተለይም በሀገራችን አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የወከሏቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ
ለማካተት ሲጥሩ፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ ‹ዴግ› የሚል ሲጨምሩበት ስማቸውን ጠርቶ ከመጨረስ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አንብቦ መጨረስ
ቀላል ይሆናል፡፡
እንደ ፈረንሳይ ባሉ ባደጉት ሀገሮች ለድርጅቶች ስምን የሚያወጡ የታወቁ ኩባንያዎች
አሉ፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች የድርጅት ባለቤቶችን ሀሳብ፣ የስሙን ትርጉም፣ ለመጥራት ቀላል መሆኑንና ከሥነ ምግባር ጋር
አለመጋጨቱን በማየት ስም ያወጣሉ፡፡ እኛ ሀገር ግን ብዙ ጊዜ የድርጅቱን ባለቤቶች ወይም የቤተሰቦቻቸውን አለበለዚያም ደግሞ የትውልድ
ቦታቸውን ስም የመጀመሪያ ፊደሎች ብቻ በያዙ አሕጽሮቶች የሚጠሩ ድርጅቶችና ሕንጻዎች ናቸው ያሉት፡፡ እነዚህን ስሞች ራሳቸው
ባለቤቶቹ ይመስሉኛል የሚሰጧቸው፡፡ እነርሱ የፈለጉትን ማድረጋቸውን እንጂ እኛ ደንበኞቻቸው ይመቸን አይመቸን፣ ይስማማን
አይስማማን ግድ የላቸውም፡፡
የአሕጽሮት ስሞች እንዲሁ በፈቀደ የመጀመሪያ ስሞችን በመገጣጠም ብቻ የሚወጡ
አይደሉም፡፡ የራሳቸው የሆነ መንገድና ሥነ ምግባርም አላቸው፡፡ ባለሞያዎቹ የአሕጽሮት ስሞችን ለሚያወጡ ሰዎች ቢያንስ እነዚህን
አራት ነገሮች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ይመክራሉ፡፡
- አጭር መሆን፡- የአሕጽሮት ስም ሲወጣ በተቻለ መጠን ለመጻፍም ሆነ ለመጥራት አጭር የሆነ ቢሆን ይመረጣል፡፡ በእንግሊዝኛ ከሆነ ከሦስት እስከ ስድስት ፊደል፣ በአማርኛ ከሆነ ደግሞ ከሦስት እስከ ሰባት ፊደል ቢሆን ይመረጣል፡፡ UNESCO ከእንግሊዝኛው ጅንአድ ከአማርኛው መልካም ምሳሌዎች ናቸው፡፡
- ለመጥራት ቀላል የሆነ፡- የምንኖረው ኢትዮጵያ ውስጥ በመሆኑ የምናወጣቸው የአሕጽሮት ስሞች ለአንድ ኢትዮጵያዊ ለመጥራት ቀላል የሚሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ ከላይ እንዳየነው ESLPTYGQ እንደሚለው ዓይነቱን ስም አንድ ኢትዮጵያዊ እንዴት አድርጎ በቀላሉ ይጠራዋል? ይህንን መሰሎቹን አሕጽሮቶች ባለሞያዎቹ ‹የፊደላት ሾርባ› Alphabet soup ብለው ይጠሯቸዋል፡፡
- ሌላ ትርጉም የማይሰጡ፡- የምናወጣው አሕጽሮት የባለቤቶቹን ስም መያዙ ብቻ መታየት የለበትም፤ በእንግሊዝኛም ሆነ በአማርኛ ወይም በሌላም ቋንቋ ቢሆን ሌላ ዓይነት ትርጉም የማይሰጥ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ‹ግምመአድ› ለአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የመልካም ነገር መገለጫ አይደለም፡፡
- ልዩ የሆነ(ያልተደገመ) የምንሰጠው አሕጽሮት የራሳችን የሆነና ከዚህ በፊት ያልተደገመ ቢሆን መልካም ነው፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች አሕጽሮቶችን የሚመዘግቡ መዛግብት አሉ፡፡ የታወቁ አሕጽሮቶችን የሚይዙ ድረ ገጾችም አሉ፡፡ በመንግሥታዊም ሆነ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ ብሎም በታወቁ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የታወቁትን አሕጽሮቶች መጠቀም ክርክርና መምታታትን ያስከትላል፡፡
የአሕጽሮት ስሞችን ለድርጅቶቻቸው ማውጣት ለሚፈልጉ አካላት በዓለም ላይ የተሻሉ መንገዶች ተብለው የሚመከሩትን ዘዴዎች
ቢከተሉ ያዋጣቸዋል፡፡ ከእነዚህ የአሕጽሮት ማውጫ ዘዴዎች መካከል የሚከተሉት መንገዶች ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ናቸው፡፡
1.
ትርጉም የሚሰጥ ቃል
መፍጠር፡- ቃላቱን በማሳጠር አሕጽሮት ስናወጣ በተቻለ መጠን ትርጉም እንዲሰጡ አድርጎ ማውጣት ማለት ነው፡፡ ለዚህ በሀገራችን
ምሳሌ የሚሆነን ለረዥም ዘመን የምናውቀው ኩባንያ ‹በርታ› ነው፡፡ በርታ በአንድ በኩል በእንግሊዝኛው ‹ብርሃኔና ታደሰ›
የሚባሉት ባለቤቶቹ ስም አሕጽሮት ሲሆን በአማርኛ ደግሞ ‹ጎብዝ፣ ጀግን› ማለት ነው፡፡ አንድ ቦታም ‹ድንበሩና በርይሁን›
የተባሉ ጓኛሞች የመሠረቱትን ‹ድንበር› የተባለ ኩባንያ አይቻለሁ፡፡ በእንግሊዝኛም Radar - Radio
Detention and Ringing, Interpol- International Police, በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡
ይህንን ዓይነት ስያሜ ለመስጠት የግድ የስሞቹ የመጀመሪያ ፊደሎች ብቻ ሳይሆን ከስሞቹ የተወሰኑትን መውሰድ፣ ወይም አያያዦችንም
ማካተት ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ MATYAS ሕንፃ በአንድ በኩል
የባለቤቶቹ ስሞች አሕጽሮት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ትርጉም ያለውን የሐዋርያ ስም ይሰጣል፡፡
2.
የመጀመሪያ ፊደል አሕጽሮት፡- የስሞቹን የመጀመሪያ ፊደል ብቻ በመውሰድ
ቢቻል ትርጉም ያለው፣ ባይቻል ለአጠራር ምቹ የሆነ ስም መፍጠር ነው፡፡ ለዚህ በሀገራችን መልካም የሚሆነው ምሳሌ አዕማድ
(አነስተኛ ዕደ ጥበባት ማስፋፊያ ድርጅት) ነው፡፡ አዕማድ የሚለው ስም በአንድ በኩል የድርጅቱ ስም አሕጽሮት ሲሆን በሌላ
በኩል ደግሞ በግእዝና በአማርኛ ‹ምሰሦዎች› ማለት ነው፡፡ እነ FAO, WTO, FIFA, እና ሌሎቹ በዚህ መልክ የተፈጠሩ ናቸው፡፡
3. ድቅል አሕጽሮት፡- ፊደልን ከቃላት ጋር በማጣመር የሚፈጠሩ የአሕጽሮት ስሞች ናቸው፡፡ በእንግሊዝኛው Dformat - Digital format በዚህ መልኩ የተፈጠረ ሲሆን እስካሁን በአማርኛ የማውቀው ስም አላገኘሁም፡፡
እነዚህን መንገዶች እንዲያው ለማመላከት ያህል የጠቀስኳቸው አሕጽሮት እንዴው በደፈናው በዘፈቀደ የሚወጣ ሳይሆን አስበውበትና ተጠብበውበት የሚያወጡት መሆኑን ለመጠቆም ያህል ነው፡፡ ቢቻል ደግሞ ሞልቶ ከተረፈን ቋንቋ የራሳችንን ሀገር ቋንቋ አሕጽሮቶች ብንጠቀም ኩራትም ማንነትም ይሆንልናል፡፡ ባለሞያዎቹ እንዲያውም ቋንቋው ባለሆኑ ፊደሎች የተመሠረቱ አሕጽሮቶችን ‹‹Immigrant acronyms› ይሏቸዋል፡፡ የተሰደዱ አሕጽሮቶች እንደ ማለት ነው፡፡ ሰሞኑን እንዲያውም ሕገወጥ ስደት የሀገሪቱ መወያያ ጉዳይ እየሆነ ነውና እኛም ቢያንስ በሕገ ወጥ መንገድ እየተሰደዱ የሚመጡ ቃላትን ሃይ ብንላቸው ከመደናገረም፣ ከመወናገርም እንድን ይመስለኛል፡፡
ሰላም ወዳጄ ዲን ዳንኤል፤
ReplyDeleteመጣጥፍህ እንደ ተለመደው ማለፊያ ነው። ነገር ግን እርማት የሚያስፈልገው መሰለኝ። የሰጠኸው ርዕስ፤ አሕጽሮት ሲሆን በእንግሊዘኛው “Abstract‘‘ ተብሎ የሚጠራ ይመስለኛል። ፤ የአንድ የጥናት ሪፓርት ዋና ዋና ነጥቦች በአጭሩ፣ በአንድ አንቀጽ ተዘጋጅተው፤ አሕጽሮት የሚል ርዕስ ይሰጣቸዋል። ብዙውን ጊዜ ከመግቢያ በፊት ይሆናል። አንባቢው፤ አሕጽሮቱን ካነበበ በዃላ፤ የሚያጓጓ ነገር ከሆነ ወደ ውስጥ ይዘልቃል። የአሕጽሮት ትርጉም እንዲህ ከሆነ፤ አንተ በሙሉ ያብራራኸው፤ የአንድን ረጅም ቃል ወይም አረፍተ ነገር የማሳጠሪያ ስያሜ ወይም በእንግሊዘኛው (abbreviation) ተብሎ ስለሚጠራ ነገር ነው። ይህ ደግሞ በአማርኛ፤ ምህፃረ ቃል ብለን የምንጠራው ነው። ከቻልህ፤ አንባቢዎችህ እንዳይሳሳቱ እርማት ብትሰጥበት መልካም ነው።
ወንድምህ
የተፃፈን ለማረም ብዙም አይተቸግረም አቃቂሪ ለማዉጣት ማን ብሎን!
Deleteበበኩሌ የመተራረም ነውር የለውም:: ዲ/ን ዳንኤልም ሲጽፍ ለውይይትና ለለውጥ ተግባር መነሻ እንዲሆን ይመስለኛል::
DeleteAbstract ለሚለው እኔ በአማርኛ ከተጻፈ የምርምር ዘዴ መጽሐፍ ያነበብኩት ጭምቃሳብ የሚል ነው- "ጭምቅ ሃሳብ" ከሚለው የተወሰደ::
Ye Genet Zewde generation...i have never known whether abstract and acronym are synonyms
DeleteTkekel blehle Dn.Daniel
ReplyDeleteምህፃረ ቃል እና አሕጽሮት አንድ ናቸው
ReplyDeleteልጅ ሳለሁ የሰንበት ተማሪ ሆኜ አገለግል ነበር:: ታዲያ በአንድ ወቅት በጣም የምንወደውን አንድ መዝሙር እየዘመርን የስብከተ ወንጌል ኃላፊው በጣም ተናደዱ:: በወቅቱ ላያቸው ነገሩ ሃይማኖታዊ ሕጸጽ አግኘተው እንጂ እንዲህ ተረድተውት አይመስልም ነበር:: ካደግሁ በኋላ ይህን መዝሙር በሰማሁ ቁጥር መምህሩ ትዝ ይሉኛል:: መዝሙሩ "እኔስ በምግ ባሬ ደካማ ሆኛለሁ" የሚል ነበር::
ReplyDeleteby mg.bare or restuarante... ho ho gud eko new...i think it is just for fun
Deleteያለፈው ጽሑፍ ከፈጠረብኝ ሕሊናዊ ጫና ዘና የሚያደርግ ነገር ነው ይዘህ የመጣኽው:: ክፍል ሁለት እስኪመጣ በዚህ ዘና እንበል ያክብርልን ወንድማችን::
ReplyDeleteበአሕጽሮት ስም እንዲህ ከሚንዛዙደሙ አጥረው ቢሸመደዱ ይመረጣል:: እነዚህስ እናሳጥራለን ብለው ነው እኒህ ምን ነክቷቸው ይሆን? ዘይነባ አረብ ሀገር ሂዳ ያፈራችውን ሀብት አገር ቤት ገብታ ቁምነገር ላይ አዋለችው ሆቴል:: እስኪ በናታችሁ ይሄ ስም ነው? የአንቀጽ ምሳሌ ሊሆን ምን ቀረው? ሌላ ልጨምር ደግሞ አባቷ ተክሉ እናቷ ጽጌረዳ ልጅቷ ማንጠግቦሽ ተክሉ ዘመናዊ ዳቦ ቤት የሚልም አይቻለሁ:: ልጆቼን ዳቦ ገዝታችሁ ኑ የምለው ከየት ነው? እኔ ይሄንን ሁሉ ላጥና በናታችሁ? ምናለ አንድኛውኑ ቤተሰብ፣ ወይ በልጅቱ ማንጠግቦሽ ሌላም ቢባል:: አረፍተ ነገር የመሰለ ስም ከማውጣት::
ማሳረጊያ ሁለት የሚገርሙኝ የግሮሰሪ ስሞች አሉላችሁ:: አንተን አምኜ ቅዱስ ገብርኤል ግሮሰሪ:: ይሄ አሁን የንግድ ስም ነው? ያውም ግሮስሪ? በሰካራም ድምጽ የት ነበርክ ሲባል እስኪ የሚመልሰውን ስሙት? ጀሞ ደሞ ወረድ ካላችሁ ከፍልውኃ ከአራት ኪሎና ከሰንጋተራ የተነሱ የተባበሩት ግሮሰሪ:: ሰውየው የፈለገው የሁሉም ሰፈር ሰዎች እርሱ ቤት እንዲዝናኑነው:: ታዲያ ለዚህ መላ ይጠፋል? እንዲህ የወረዳ ስብሰባ የሚያስመስለው? አሁን እኔ እዚቤት ባመሽ የት ነበርኩ ነው የምለው?
ወደ ጠጅ ቤት ስንዞር ዘና የሚያደርግ ነገርም አለ ምን ታፈጥብኛለ ግባና ቅመሰኝ ጠጅ ቤትን የምታውቁ ወይም እዚያ የተዝናናችሁ እስኪ ምን ትላላችሁ?
LOOOOOOOL!Tear drops....
Deletesaqen maqom alchalkum...ምን ታፈጥብኛለ ግባና ቅመሰኝ ጠጅ ቤት;አንተን አምኜ ቅዱስ ገብርኤል ግሮሰሪ;ዘይነባ አረብ ሀገር ሂዳ ያፈራችውን ሀብት አገር ቤት ገብታ ቁምነገር ላይ አዋለችው ሆቴል:ባቷ ተክሉ እናቷ ጽጌረዳ ልጅቷ ማንጠግቦሽ ተክሉ ዘመናዊ ዳቦ ቤት ...ha ha ha
DeleteSO FUNNY!!
ReplyDeleteበተለይም በሀገራችን አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የወከሏቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ሁሉ ለማካተት ሲጥሩ፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ ‹ዴግ› የሚል ሲጨምሩበት ስማቸውን ጠርቶ ከመጨረስ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አንብቦ መጨረስ ቀላል ይሆናል፡፡
ReplyDeleteእኔ በምኖርበት አካባቢ ደግሞ አንድምግብ ቤት ስያሜው እንዲህ ይል ነበር - ቅዱስ ገብርኤል ተከተለኝ አቡየ ጻዲቁ አንተ ታውቃለህ ሥጋ ቤት-
ReplyDeleteበቀደም በቀለበት መንገድ ላይ በመኪና ስሄድ ከጎናችን አንድ ነጭ ፒክ አፕ መኪና ይጓዝ ነበር፡፡ ዘወር ብዬ ሳየው በሩ ላይ የመሥሪያ ቤቱን ስም ለጥፏል፡፡ ያየሁትን ለማመን ስላቃተኝ በሞባይል ፎቶ አነሣሁት፡፡
ReplyDeleteno no dani you don't mean it
የዲ/ን ዳንኢል አባባል እስከገባኝ በዘፈቀደ ስም ማውጠት ይቁም። ይህን የሜመለከት መንግስታዌ ተቇም ይኑር መሰለኝ። ምነው አንብቦ ለመረዳትም ቅን ልቦና አነሰን።
ReplyDeleteD/n Daniel Kibret Egziabher yisitilin. Tiru new
ReplyDeleteከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንበሳው አገሳ የሚል ማስታወቂያ አዲስ አበባ ባሉ መዝናኛዎች በር ላይ እያየሁ እየገረመኝ ነበር እንዴት የሚበላበት የሚጠጣበት ቦታላይ አገሳ/ ግሳት/ ይባላል በበኩሌ ባየሁት ቁጥር ይቀፈኛል....
ReplyDeleteወዳጄ አማርኛዋን ‹‹ብትበላት›› መልካም ነው፡፡ ‹‹አንበሳው አገሳ›› የሚለው ሀረግ የጀግኖች አባቶቻችንን ድንቅ ተጋድሎ የሚያስታውስ ቃል ነው፡፡ አንተ የተረጎምከው ከሰው ጋር በማዛመድ ነው (ሰውየው አገሳ እንደ ማለት - ይህ ከሆነ እውነትም አስቀያሚ ነው፡፡) አንበሳው አገሳ በአጭሩ ‹‹አንበሳው ጮኸ›› እንደማለት ነው፡፡ አንበሳ በሚጮህበት ጊዜ ፈሪዎች ይደነብራሉ፤ ጀግኖች ይነቃቃሉ (በነገራችን ላይ ሀረጉ የቢራ ማስታዎቂያ በመሆኑ ለመቀበል ሊከብድ ይችላል፡፡
Deleteከዚህ አንፃር ሁል ጊዜ የሚያሳቅቀኝ ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ›› የሚለው ስያሜ ታሪካዊ ቢሆንም ስያሜውና ግብሩ የማይገናኝ መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ መቼም ቢራ ጠጥቶ ፃድቅ መሆን ሲታሰብ አስቂኝ ነው፡፡
መልካም ቀን!
ነገሩን ስንመለከተው ቀላል ይመስላል ነገር ግን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው:: በተለይ ለማይገባ ቦታ ለስያሜ የሚመረጡት የቅዱሳን ስሞችን (አስማት) ስናስተውል እጅግ ያሳዝናል: አጋንንት የሚንቀጠቀጥለት ክቡር ስም ለስካርና ለዘፈን ቤት መጠሪያነት መጠቀም በደል ነው:: ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ትዝብትህን አታቋርጥብን:: እግሮችህን ከጉዞ ጣቶችህን ከብዕር አታስታጉልብን::
ReplyDeleteመልካም ጊዜ ለሁላችንም
የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት ነው ሲተነተን እይታህ ግን ሁሌም ይገርመኛል፡፡
ReplyDeleteዳኒ እኔ የማውቅህ ከብላቴ ጀምሮ ነው
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚለኝን ነገር ሁል ጊዜ ስለምትጽፍ ደስ ብሎኛል፡፡ በርታ እግዚአብሄር ይባርክህ!!!
ውድ ዳኒ፤
ReplyDeleteእንደምን ከረምክ! እውነት ነው በርካታ አህጽሮቶች አስቂኝም፣ አሳዛኝም ናቸው፡፡ በነገርህ ላይ ሰዎች እነዚህን ስያሜዎች አንዳንዴ ከወቅታዊ ሁኔታዎች በመነሳት በራሳቸው መንገድ ሲተረጉሙና ለጭውውት ሲያውሏቸው ታዝቤያለሁ፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን እጠቅሳለሁ፤
PhD: Permanent Head Damage (የአእምሮ ዘላለማዊ ልሽቀት - አንዳንድ ይህን ማዕረግ የያዙ ሰዎች ለዚህች ሀገር ያበረከቱትን ደካማ አስተዋጽኦ ለመግለጽ ይመስላል፡፡) (ትክክለኛው፤ Doctor of Philosophy)
GTP: Growth Threatening Plan (እድገትን የሚፈታተን/የሚጎዳ እቅድ - ከአባይ ግድብ መዋጮ ጋር በማያያዝ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡) (ትክክለኛው፤ Growth and Transformation Plan)
ስለሆነም አጭርና እጥር ምጥን ማለቱ ብቻ አንዳንዴ የከፋ ትርጉም ሊያሰጥ ስለሚችል ከብዙ መለኪያዎች አንጻር ማየቱ ተገቢ ነው፡፡ ወንድም ዳንኤል እ/ብሄር ይስጥልኝ!
በእውነት እግዚአብሔር ማስተዋልን ሲሰጥ እንደዚህ ነው፡፡እይታህ አስገራሚ እና አወያይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ሜክሲኮ አምስተኛ አካባቢም አንደድ የውጭ ድርጅት አለ፡፡ስሙ ምን እንደሚባል ታውቃላችሁ *አራም ሳፋሪያን *
ReplyDeleteይገርማል ! እይታህ የሚደንቅ ነው ፡፡ሜክሲኮ አምስተኛ አካባቢም አንድ የውጭ ድርጅት አለ ፡፡ስሙ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ *አራም ሳፋሪያን *
ReplyDeleteእይታህን በጣም ወድጀዋለሁ ፡፡ሜክሲኮ አምስተኛ አካባቢ አንድ የውጭ ድርጅት አለ፡፡ስሙ ማን እንደሚባል ታውቃላችሁ ? *አራም ሳፋሪያን * አይገርም ?
ReplyDeleteሜክሲኮ አካባቢም አንድ የውጭ ድርጅት አለ ፡፡ስሙ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ *አራም ሳፋሪያን* አይገርም ?
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል በዚህ ፅሁፍህ በጣም የሚገርም ነገር ነዉ ያስታወስከኝ ነገሩ የሆነዉ ከ 22 አምት በፊት ነዉ እኔ ከጉዋደኞቸ ጋር ከጎጃም ወደ አ/አ ለመሄድ መንገድ ላይ ቆመን መኪና እንለምናለን ከዛም አንድ "ግምምአድ" የሚል መኪና ይመጣል እኛም ተሩዋሩጠን ሾፌሩን እንዲወስድን ስንጠይቀዉ እምቢ ይላል በዚህ በጣም የተናደደዉ አንድ ጉዋደኛችን እንዲያዉም ግም ይላል በዚህ መኪና አልሄድም ብሎ እኛንም ሾፌሩንም እንዳሳቀን ትዝ ይለኛል
ReplyDeleteጤና ይስጥልኝ ዲያቆን ዳንኤል
ReplyDeleteየ"ወላጆች፡- ሁለት ጉዳዮች አሉኝ" ቀጣይ ክፍል ለምን አይወጣም? ዘንግተኸው ነው ወይንስ የሰዉን ልብ ለመስቀል አስበህ አድርገኸው? በቆየ ቁጥር አስተማሪነቱና መረጃ ሰጪነቱ መንምኖ ዓላማውን እንዳይስት ፖስት ብታደርገው!
what an observation!! BTW, there is what we call a 'hidden hunger' which is a common problem in a well to do families (including in the developed countries). In this hidden hunger, the person might have not missed meals and he don't feel hungry, but he misses the most essential micro-nutrients (not energy and protein) from his daily diets. This results a lot of messes in the mental and physical growth of children.Your case example (the two children), are examples of such a problem...your recommendation to include locally available foods in their diet is absolutely right(particular attention should be given for our children). Just to give you my experience, a friend of mine who is nutritionist by profession and working in FAO, has been feeding his own child (some years back) a home prepared infant food. He himself prepare the ingredients by mixing locally available cereals, animal source foods, vegetables, roots and the like...He could afford to buy infant foods from supermarket, but he knew what is best for his child. A lot of public awareness is needed for our food habits ...although major challenge for most people in Ethiopia is to find adequate food,some are still affected due to improper use of the available resources in hand. Keep updating us on such issues.
ReplyDeleteየምታነሳቸው ሀሳቦች ወቅታዊና ሰው ልብ ያላሉትን ነው ቀጥልበት
ReplyDelete