Tuesday, July 30, 2013

የበቅሎ ጥያቄበከበደ ሚካኤልኛ እንዲህ ይተረካል፡፡
አንዲት ግልገል በቅሎ እናቷን እንዲህ ብላ ጠየቀቻት፡፡ ‹‹እማዬ እኔ ግን ማነኝ››
እናቷም ገረማትና ‹አንቺማ በቅሎ ነሽ፤ ግን ለምን ጠየቅሽኝ››
ግልገሏም ጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ ‹‹መጀመሪያ ግን አህያ ነበርኩ ወይስ ፈረስ›› አለቻት፡፡ እናቲቱም አንገቷን ነቅንቃ፡፡ ‹‹እንስሳ ነሽ ልጄ፤ እንስሳ፡፡ ፈረስም አህያም እንስሳ ነው፡፡ ስንፈጠር እንስሳ ነበርን፡፡ የቤት የዱር፣ የሸክም የግልቢያ፣ የእርሻ የሜዳ፣ የንጉሥ የባሪያ የሚለው በኋላ የመጣ ነው፡፡ አዳምኮ ሲፈጠር ቤት አልነበረውም፡፡ ስለዚህ የቤት እንስሳ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ሁላችንም ይህቺን ምድር እንደልባችን እንጠቀምባት ነበር፡፡ ነገር የመጣው በኋላ ነው፡፡ ለመኖር የሚደረግ ትግል ነው ይህንን አሁን ያለንበትን ሁኔታ የፈጠረው፡፡››
‹‹ጓደኛዬ የአንቺ አያቶች ጨቁነውናል አለኝ፡፡››
 ‹‹እንዴት አድርገው ነው የጨቆኑት፤ ለመሆኑስ የአንቺ አያቶች ስንት ናቸው? እርሱ የተነገረውን ብቻ ነው የሚያውቀው፤ ያልተነገረውስ? ከታሪካችንኮ በጣም ጥቂቱ ነው የተጻፈው፤ ከተጻፈውም በጣም ጥቂቱ ነው የተነገረው፡፡ ባልተጻፈው ታሪካችን ውስጥ ማን ምን እንደነበረ ማን ያውቃል? ለምሳሌ በሀገረ እሥራኤል አህዮች እጅግ የሚወደዱ የቤት እንስሳት ነበሩ፡፡ ነገሥታቱም፣ ካህናቱም፣ ነቢያቱም ዘመኑ ዘመነ ሰላም ሲሆን በአህያ ነው ይሄዱ የነበሩት፡፡ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ የተሰደደችው በአህያ ነው፡፡ በጥንታውያን ግብጾች ዘንድ አህያ የመኳንንትና የነገሥታት ሀብት ማሳያ ነበር፡፡ የናርማር ወይም  ሖር - አሃ መቃብር እንደሆነ በሚታመነው ቦታ ላይ በተደረገ ቁፋሮ አህዮች ከነገሥታቱ ጋር በክብር ተቀብረው ተገኝተዋል፡፡ በዚያ ጊዜ አህዮች የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየተመገቡ፣ በቤተ መንግሥቱም እየተሸለሙ ኖረዋል፡፡ በሌላው ዘመን ደግሞ ይህንን ፈረሶቹ ወስደውታል፡፡››
‹‹ወደ ኋላ ተመልሰሽ ሁሉን እንስሳት ብታያቸው ታሪካቸው እንደዚሁ ነው ልጄ፡፡ በዘርሽ አትጨቁኝም፤ በዘርሽም አትጨቆኝም፡፡ የጭቆና መሠረቱ ኃይልና ሥልጣን ነው፡፡ አቤልን የገደለውኮ ቃየል ነው፡፡ የአንድ ማኅፀን ልጆች ናቸውኮ፡፡ ቃየል አቤልን የገደለው ለጥቅም ሲል ነው፡፡ እስኪ የሰዎችን ታሪክ እይው አፍሪካውያንኮ በራሳቸው በአፍሪካውያን ይጨቆኑ ነበር፡፡ ሥልጣን ላይ ያለው ሰው መሰሎቹን ይሰበስብና ሌሎቹን የሀገሩን ልጆች ይጨቁናል፡፡ መጀመሪያ የገዛ ወገኖቻቸውን ለዐረቦች በባርነት ሲሸጡ የነበሩት የሀገራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ አፍሪካውያን በባርነት ተሽጠው አሜሪካ ሲሄዱ ደግሞ ነጮቹ ጥቁሮቹን መጨቆን ጀመሩ፡፡ አየርላንዳውያን በእንግሊዞች መከራቸውን አይተዋል፡፡ ዓረቦች በዓረቦች ተሰቃይተዋል፡፡
አየሽ ቤተ መንግሥቱ ላይ ስትቀመጭ ሌላውን ለማግለል ሳጥን ትከፍቻለሽ፤ ከዚያ ሁሉንም በየሳጥኑ ታስቀምጭዋለሽ፡፡ የእምነት፣ የዘር፣ የመልክ፣ የአካባቢ፣ የቋንቋ ሳጥኖችን ከፍተው ሁሉንም እዚያ ስላስቀመጧቸው ተቀማጮቹ ሳጥኑን እንዳለ ተቀበሉት፡፡ ማንነታቸውም አደረጉትና ሳጥኑን ለማስቀረት ከመታገል ይልቅ ራሳቸውን ብቻ ከሳጥኑ ለማውጣት ይታገሉ ነበር፡፡ በሳጥኑ ዛሬ አህዮች ይገቡበታል፤ ነገ ፈረሶች፣ ከነገወዲያ ግመሎች፣ ከዚያም በጎች፣ ከዚያም ፍየሎች እየገቡበት ይቀጥላል፡፡ እኛም ዛሬ ያለሳጥን መኖር ከማንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ እኔን ሲያገኙኝ እንስሳ መሆኔን አይደለም የሚያዩት፤ የትኛው እንስሳ? ይላሉ፡፡ - ፈረስ፡፡ በዚህ አያቆሙም፡፡ ከዚያ ደግሞ የትኛው ፈረስ? የዱር ወይስ የቤት? ይቀጥላል፡፡ -የቤት፡፡ ለጭነት ወይስ ለግልቢያ? መቋጫ የለውም ልጄ፡፡ በትልቁ ሳጥን ውስጥ ራሳችን የሠራናቸው ትንንሽ ሳጥኖችም አሉ፡፡ በእነዚያም ውስጥ ሌሎች ትንንሽ ሳጥኖች አሉ፡፡››
‹‹ ለአንድ የገጠር ጉዞ በእኔ ላይ ይሄድ የነበረ አንድ ሰው ሲናገረው የሰማሁትን ታሪክ ልንገርሽ፡፡ ሰውዬው የከባድ መኪና ሾፌር ነበረ፡፡ ድሮ አሰብ እየተመላለሰ ዕቃ ይጭን ነበር፡፤ አንድ ጊዜ ወደ አሰብ ሲሄድ በረሃው ላይ መኪናው ይበላሽበታል፡፡ ከዚያም እዚያው ማደር ስለነበረበት ለምግቡ የሚሆን ፍየል ከአካባቢው የአፋር ሰው ይገዛል፡፡ አፋሩ ሰውዬው ፍየሏን መሸጥ ብቻ ሳይሆን አርዶ፣ ጠብሶ ያቀርብለታል፡፡ ሾፌሩ ምግቡን እየበላ የሸጠለትን የአፋር ሰው ‹‹እንግዲህ ትቼህ መብላቴ ነው፤ እንብላ እንዳልልህ የክርስቲያን ሥጋ አትበላም ብዬ ነው›› ይለዋል፡፡ አፋሩ ሰውዬ ይገርመውና ‹‹እኔው አዋልጄ፣ እኔው አሳድጌ፣ እኔው አርጄ፣ እኔው ጠብሼ ያመጣኋትን ፍየል ምንጊዜ ክርስቲያን አደረግካት?›› አለኝ ብሎ ሲያወራ ሰማሁት፡፡ አየሽ ሌላን ማግለል ስትፈልጊ የሆነ ነገር ትፈጥሪያለሽ፡፡ ማቅረብም ስትፈልጊ እንደዚያው፡፡››
‹ብዙ ዓይነት ነጻ አውጭዎች አሉ፡፡ እኔ አሁን የፈረስ ነጻ አውጭ ውስጥ ልግባ ወይስ የአህያ? ወይስ የበቅሎ?›› አለቻት ግልገሏ፡፡
‹‹የእንስሳት ነጻ አውጭ ካለ እዚያ ግቢ፡፡ አንቺ እንስሳ ነሽ፡፡ የቀረው ከመኖር የመጣ ስም ነው፡፡ እንስሳት ሁሉ ነጻ ሳይሆኑ በቅሎ ተለይታ ነጻ ልትሆን አትችልም፡፡ አንድን አካቢ ብቻውን ንጹሕ ማድረግ አትችይም፡፡ ምክንቱም ዝንቧ ከወዲያኛው ማዶ ትመጣለችና፡፡ ከእኛም ወገኖችኮ ሜዳ በመኖራቸው የተነሣ ‹የሜዳ ፈረስ›› ተብለው የቀሩ አሉ፡፡ እኛ ከሰው ተጠግተን ‹የቤት ፈረስ›› ለመሆን ቻልን፡፡ ‹‹የቤት አህዮች›› አሉ፡፡ ‹‹የሜዳ አህዮች›.ም አሉ፡፡ የስም ጉዳይ ነው፡፡ የአኗኗር ጉዳይ ነው፡፡ በቤተ መንግሥት ከነገሥታት ጋር የሚኖር አንበሳ ነበርኮ፡፡ የነገሥታቱ ዙፋን እንዲያውም የአንበሳ ቅርጽ ነበረው፡፡ በዚያው ዘመን ግን ንጉሡ ጫካ ወጥተው ሌላ አንበሳ ገድለው እየተዘፈነላቸው ይመጣሉ፡፡ ጀርባሽን ለመጋለብ ምቹ ካደረግሽው ምንጊዜም የተሻለ ተወዳጅ ትሆኛለሽ፡፡ እንግሊዞች ‹‹Better to ride on ass that carries me, than on a horse that throws me - የምትገለብጠኝን ፈረስ ከምጋልብ፣ የምትሸከመኝን አህያ ብጋልብ ይመረጣል›› ይላሉ፡፡
ቤት የቀረው ውሻ ዱር ከቀረው ውሻ ጋር በመለያየታቸው ዛሬ አንዱ አንዱን እንደ ጠላት ያባርረዋል፡፡ ሰው ብልጥ ነው፡፡ አንዱን ወደራሱ አቅርቦ ውሻ አደረገውና ‹‹ቦቢ›› እያለ በማቆላመጥ ነጻ የወጣ አስመሰለው፡፤ ሌላውን ደግሞ ቀበሮ፣ ተኩላ ብሎ ጫካ ተወውና እርሱን መግደል ጀግንነት እንዲሆን አደረገው፡፡ አሁን ውሾቹ የሠለጠኑና ነጻ የወጡ መስሏቸው ተኩላና ቀበሮ ሲያብርሩ ይኖራሉ፡፡ አየሽ ጉዳዩ የዘር አይደለም፡፡ በዘር ከሰው ተኩላ ለውሻ ይቀርበዋል፣ ቀበሮ ይዛመደዋል፡፡ ጉዳዩ የጥቅም ጉዳይ ነው፤ የመደብ ጉዳይ ነው፡፡ ከቀበሮውና ከተኩላው መካከል ደግሞ የተወሰነውን ይወስዱና ፓርክ ውስጥ አስገብተው ያለፈለት ያስመስሉታል፡፡ እርሱም ማግኘት የሚገባውን ሳይሆን ራሱን ከጫካው ኑሮ ጋር ስለሚያነጻጽር ‹ተመስገን› እያለ ይኖራል፡፡››
‹‹ነጻነት የፍጡር ሀብት ነው፡፡ ለእነ እገሌ ተብሎ የሚቆረስ አይደለም፡፡ ጨቋኙም ተጨቋኙም ነጻ ካልወጣ ሙሉ ነጻነት አይገኝም፡፡ ጨቋኝነት ከአስተሳሰብ ባርነት የሚመጣ ነው፡፡ ከአመለካከት ድህነት የሚከሰት ነው፡፡ ሙሉ ነጻነትን ለማግኘት እርሱን ነጻ ማውጣት አለብሽ፡፡ ካልሆነ ግን ጉዞው አንዱን ጨቋኝ በሌላ ጨቋኝ መተካት ነው የሚሆነው፡፡ አፍሪካውያንኮ ራሳቸውን ከአውሮፓውያን ነጻ ማውጣት አላቃታቸውም፡፡ ያቃታቸው ራሳቸውን ከራሳቸው ነጻ ማውጣት ነው፡፡ ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተኩ፡፡ ቅድም እንዳልኩሽ ሳጥኑን ካላጠፋሽው ታግሎ ከሳጥኑ የወጣው ሁሉ በፋንታው የተሸነፈውን እርሱ ወደወጣበት  ሳጥን መክተቱ የማይቀር ነው፡፡
‹‹ደግሞስ ለምን በማትቀይሪው ነገር ጊዜሽን ታጠፊያለሽ? አሁን አንቺ በቅሎ ሆነሻል፡፡ አለቀ፡፡ ከእንግዲህ አህያ፣ ፈረስ፣ አንበሳ፣ ጅብ ፣ ድመት ልትሆኝ አትችይ? መሆን ለምትፈልጊው ነው መታገል ያለብሽ? በእጅሽ ላይ ላሉት ዕድሎች ነው መታገል ያለብሽ፤ ልትለውጫቸው ለምትችያቸው ዕድሎች ነው መታገል ያለብሽ፤ ልታሸንፊያቸው ከምትችያቸው ነገሮች ጋር ነው መታገል ያለብሽ፡፡ ትናንትን በነገ ለመቀየር ታገዪ፤ ትናንት ውስጥ ገብተሸ ግን እቀይረዋለሁ አትበዪ፤ መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ከትናንቱ ውጭ፤ ያ ያለፈ ነገር ነው፡፡ ታሪክ አይታረምም፤ ሆኗልና፡፡ በታሪክ ውስጥ የተፈጠረ ችግር ግን በቀጣይ ታሪክ ይታረማል፡፡ ምን ሆነ? የሚለው አይለወጥም፤ ምን ይሁን? የሚለውን መለወጥ ግን ይቻላል፡፡ ዛሬ ላይ ሆነሽ የመጣሽበትን ማስተካከል አትችይም፤ የሚትሄጅበትን ግን ትችያለሽ፡፡ ብዙዎቹ ነጻ አውጭዎች ትናንትን ነጻ ለማውጣት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ አንቺ መግባት ያለብሽ ነገን ነጻ ሊያወጣ የተቋቋመ አካል ከተፈጠረ ብቻ ነው፡፡
‹‹አፍሪካውያን ‹‹until the lions have their own historians tales of hunt will always glorify the hunters- አንበሶች የራሳቸው ታሪክ ጸሐፊዎች እስኪኖሯቸው ድረስ ስለ አደን የሚጻፈው ታሪክ ሁሉ ምጊዜም አዳኞችን የሚያገንና የሚያከብር ይሆናል›› ይላሉ፡፡ ዛሬ ከአንድ ወገን ብቻ እየሰማን የምንፈርዳቸው ፍርዶች በታሪክ ተሠሩ ከምንላቸው ስሕተቶች በላይ እንድንሳሳት የሚያደርጉን ናቸው፡፡ የማናውቃቸውና ያልሰማናቸው፤ ምናልባትም ወደፊትም ልንሰማቸው የማንችላቸው ታሪኮችም አሉን፡፡ ትናንት ያለፈ በመሆኑ ለፍርድ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ሰሎሞን ዴሬሳ የተባለ ሰው ‹አንተ ዘርህ ምንድን ነው?› ሲባል ‹‹በቅድመ አያቴ ደጅ ማን እንዳለፈ እኔ ምን ዐውቃለሁ›› ይል ነበር፡፡ በአንቺስ ቅድመ አያት በር ማን እንዳለፈ ምን ታውቂያለሽ? መጠኑና ዘመኑ ይለያያል እንጂ ‹ሌላ› የሚለውን አካል ሳይገድል፣ ሳያጠፋ፣ ሳይጨቁን፣ ሳይቀማ እዚህ የደረሰ የለም፡፡ ግን ታሪክ እንደተራኪው ነው፡፡
‹‹ሁላችንንም መከራውና ግፉ፣ ጭቆናውና የደረሰብን ነገር ሁሉ አስተባብሮናል፡፡ በየዘመናቱ ቤተ መንግሥቱን የተጠጋ ተሸልሟል፡፡ አምሮበታል፡፡ ሌላውን ለማስገበርም ዘምቷል፡፡ እኛ አህዮች፣ ፈረሶችና በቅሎዎች ነንኮ ሌሎች እንስሳት እንዲታደኑ አብረን ከሰዎች ጋር የዘመትነው፡፡ በእኛ ዘምተው ሌላ ሀገር የሚገኙ ፈረሶችንና አህዮችን እንዲዘርፉ አድርገናልኮ፡፡ ከዘመቻው በኋላ ለእኛ የተሻለ ነገር ጣል ሲደረግልን እነርሱ ግን በባዶ ሜዳ አድረዋልኮ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ለእኛ እነርሱ ይቀርቡን ነበር፡፡ ነገር ግን ቤተ መንግሥቱን ስትጠጊ እንዲህ አታስቢም፡፡ በታሪካችን ውስጥ የደረሱብንንና ያደረስናቸውን ብንቆጥራቸው ከምንለያይበት የምንመሳሰልበት ይበልጣል፡፡ ግን ምን ያደርጋል ከሳጥኑ ወጥቶ የሚያስብ የለም፡፡ ሳጥኑ ውስጥ ስትሆኚ ደግሞ ያንቺ ብቻ ነው የሚታይሽ፡፡
‹‹መቼም በእንስሳት ታሪክ ቀደምት ከሚባሉት አንደኛዎቹ ቲቤታውያን ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ ‹‹አንጥረኛው ጥበበኛ ከሆነ ብረትና ነሐስ ሊዋሐዱ ይችላሉ››፡፡ አሁንም እኛ አንድ ልንሆን ያልቻልነው አንድ የሚያደረግን ነገር ስለሌለ ሳይሆን አንድ የሚያደርገን ጥበበኛ አንጥረኛ ስለሌለ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቺው፤ ቤተ መንግሥት የኖረውን አንበሳኮ ነው ‹‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጨዋቻ ይሆናል›› የሚሉት፡፡ ታድያ ከጫካው አንበሳ ምን የተለየ ነገር አገኘ? የቤት አህያም ሆነ የጫካ አህያ ሲያረጁ ሁለቱንም አውሬ ይበላቸዋል፡፡ ቤት ውስጥ የኖረውም ውሻ ሲያረጅ ዞር ብሎ የሚየው የለም፡፡ ስለዚህ ልጄ አሁን የሚያስፈልገን የእገሌ ነጻ አውጭ ድርጅት ሳይሆን ‹የአስተሳሰብ ነጻ አውጭ ድርጅት›› ነው፡፡ አስተሳሰብሽ ነጻ ሲወጣ ‹‹መጀመሪያ እኔ እንስሳ ነኝ ወይስ በቅሎ?›› የሚለውን ጥያቄ ራስሽ ትመልሽዋለሽ፡፡
ሲድኒ፣ አውስትራልያ

103 comments:

 1. EXCELLENT, EXCELENT, EXCELENT.

  ReplyDelete
 2. You are always smart.

  ReplyDelete
 3. God bless you Dn Daniel, this is a very interesting piece.

  ReplyDelete
 4. Thank you!!! nice advice for people who think that they are freedom fighters but practically freedom killers

  ReplyDelete
 5. We need more of this idea. Daniel, you should take a leading position in the media now. Flourish your thinking to reach us and the others.

  ReplyDelete
 6. to whom it may concern!

  ReplyDelete
  Replies
  1. all of us who are failed to think out of the box.

   Delete
  2. say to all of us please ?

   Delete
 7. ነበር፡፡ ነገር ግን መቼ ነው ከሳጥኑ ወጥተን የመናስበው?

  ReplyDelete
 8. ቤት የቀረው ውሻ ዱር ከቀረው ውሻ ጋር በመለያየታቸው ዛሬ አንዱ አንዱን እንደ ጠላት ያባርረዋል፡፡ ሰው ብልጥ ነው፡፡ አንዱን ወደራሱ አቅርቦ ውሻ አደረገውና ‹‹ቦቢ›› እያለ በማቆላመጥ ነጻ የወጣ አስመሰለው፡፤ ሌላውን ደግሞ ቀበሮ፣ ተኩላ ብሎ ጫካ ተወውና እርሱን መግደል ጀግንነት እንዲሆን አደረገው፡፡
  ‹‹ሁላችንንም መከራውና ግፉ፣ ጭቆናውና የደረሰብን ነገር ሁሉ አስተባብሮናል፡፡ በየዘመናቱ ቤተ መንግሥቱን የተጠጋ ተሸልሟል፡፡ አምሮበታል፡፡ ሌላውን ለማስገበርም ዘምቷል፡፡ Thank you D.Daniel God bless you....

  ReplyDelete
 9. ቤተ መንግሥቱን ስትጠጊ እንዲህ አታስቢም፡፡ በታሪካችን ውስጥ የደረሱብንንና ያደረስናቸውን ብንቆጥራቸው ከምንለያይበት የምንመሳሰልበት ይበልጣል፡፡ ግን ምን ያደርጋል ከሳጥኑ ወጥቶ የሚያስብ የለም፡፡ ሳጥኑ ውስጥ ስትሆኚ ደግሞ ያንቺ ብቻ ነው የሚታይሽ፡፡

  ReplyDelete
 10. Thanks a lot Dani. It is a very important article!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. ዳንኤል ፖለቲካ መጻፍ ጀመረ…..ዳኒ ከአውስትራሊያ የማትመለስ መስሎህ ነው?…..ልብህ ከቆረጠ ጥሩ……አለበለዚያ አንተ እራስህ “ታች በሌ” ን ልትሆን ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Why do you shut your mind for ever? I advice you to read the view of Dn. Daniel's letter again to clean your mind. God bless Dn. Daniel Kibret and you.

   Delete
  2. አፍህ ሲከፈት ጭቅላህ ይታያል።

   Delete
  3. Hahahahaaaaaaaaaaa kikikikii

   ዳንኤል ፖለቲካ መጻፍ ጀመረ…..ዳኒ ከአውስትራሊያ የማትመለስ መስሎህ ነው?…..ልብህ ከቆረጠ ጥሩ……አለበለዚያ አንተ እራስህ “ታች በሌ” ን ልትሆን ነው::

   Ethiopia needs such kind of thinking practices. really ,it is interesting.

   Delete
  4. ዳኒ …….‹‹ደግሞ እንደ ታች በሌ ሲርብህ እንዳትመጣ››

   Delete
  5. Dir my brother,i think you look the article in negative way.you are not right, please look the thing in the right way and positively.

   Delete
 12. አሁንም እኛ አንድ ልንሆን ያልቻልነው አንድ የሚያደረግን ነገር ስለሌለ ሳይሆን አንድ የሚያደርገን ጥበበኛ አንጥረኛ ስለሌለ ነው፡፡ እስኪ ተመልከቺው፤ ቤተ መንግሥት የኖረውን አንበሳኮ ነው ‹‹አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጨዋቻ ይሆናል›› የሚሉት፡፡ ታድያ ከጫካው አንበሳ ምን የተለየ ነገር አገኘ? የቤት አህያም ሆነ የጫካ አህያ ሲያረጁ ሁለቱንም አውሬ ይበላቸዋል፡፡ ቤት ውስጥ የኖረውም ውሻ ሲያረጅ ዞር ብሎ የሚÁ¾ው የለም፡፡ ስለዚህ ልጄ አሁን የሚያስፈልገን የእገሌ ነጻ አውጭ ድርጅት ሳይሆን ‹የአስተሳሰብ ነጻ አውጭ ድርጅት›› ነው፡፡ አስተሳሰብሽ ነጻ ሲወጣ ‹‹መጀመሪያ እኔ እንስሳ ነኝ ወይስ በቅሎ?›› የሚለውን ጥያቄ ራስሽ ትመልሽዋለሽ

  ReplyDelete
 13. Wonderful ... Keep it up brother.

  ReplyDelete
 14. timely article God bless you and heavenly peace for Dr. Kebed M.

  ReplyDelete
 15. kalat yateregnal excellent expresson!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 16. "ታሪክ አይታረምም፤ ሆኗልና"
  መልካም እይታ ነው፡፡

  ReplyDelete
 17. wow , mirit hasab new.

  ReplyDelete
 18. Thanks Daniel,

  እኔን ሲያገኙኝ እንስሳ መሆኔን አይደለም የሚያዩት፤ የትኛው እንስሳ? ይላሉ፡፡ - ፈረስ፡፡ በዚህ አያቆሙም፡፡ ከዚያ ደግሞ የትኛው ፈረስ? የዱር ወይስ የቤት? ይቀጥላል፡፡ -የቤት፡፡ ለጭነት ወይስ ለግልቢያ? መቋጫ የለውም ልጄ፡፡ በትልቁ ሳጥን ውስጥ ራሳችን የሠራናቸው ትንንሽ ሳጥኖችም አሉ፡፡ በእነዚያም ውስጥ ሌሎች ትንንሽ ሳጥኖች አሉ፡፡

  Always through your articles I get knowledge of life.

  Thanks again

  ReplyDelete
 19. በጣም በጣም እጅግ በጣም አስተማሪ የሆነ ጽሑፍ ነው።ይመችህ እግዚአብሔር አንተና ያንተ የሆኑትን ሁሉ ይባርክ።

  ReplyDelete
 20. ይህ ፅሁፍ ለ አንዲት እናት አገር ኢትዮጵያ በለው ላረፉ አና ላሉ መታሰብያ ይሁንልኝ! kb the Adigrat

  ReplyDelete
 21. ‹‹እኔው አዋልጄ፣ እኔው አሳድጌ፣ እኔው አርጄ፣ እኔው ጠብሼ ያመጣኋትን ፍየል ምንጊዜ ክርስቲያን አደረግካት?›› አለኝ ብሎ ሲያወራ ሰማሁት፡፡ አየሽ ሌላን ማግለል ስትፈልጊ የሆነ ነገር ትፈጥሪያለሽ፡፡ ማቅረብም ስትፈልጊ እንደዚያው፡፡››

  ReplyDelete
 22. በእውነቱ መምህር ዳንኤል ቅኔህን እጅግ እጅግ አድንቄዋለሁ ቅኔውን ተርጉሞ ለኔ ብሎ ለሚጠቀም መልካም እይታ ነው
  አንተን በዚህ ስሜት እንድትነካ ያደረገ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በእውነቱ አንተን ውስጥህ እንዲህ እነዲሰማህ ያደረገህም ነገር ምስጋና ይገባዋል ፡፡ ይሁን ይበል ብለናል !!

  ReplyDelete
 23. ‹‹መጀመሪያ እኔ እንስሳ ነኝ ወይስ በቅሎ?››

  God Job,Dani

  ReplyDelete
 24. yep----long live bro.

  ReplyDelete
 25. Tesfamariam good view, first everybody must free him self from old sentiment.

  ReplyDelete
 26. አስተሳሰብሽ ነጻ ሲወጣ ‹‹መጀመሪያ እኔ እንስሳ ነኝ ወይስ በቅሎ?›› የሚለውን ጥያቄ ራስሽ ትመልሽዋለሽ፡፡ nice, Thank you.

  ReplyDelete
 27. Great D/N Daniel.GOD bless u

  ReplyDelete
 28. በዘር ከሰው ተኩላ ለውሻ ይቀርበዋል፣ ቀበሮ ይዛመደዋል፡፡ ጉዳዩ የጥቅም ጉዳይ ነው፤ የመደብ ጉዳይ ነው፡፡ ከቀበሮውና ከተኩላው መካከል ደግሞ የተወሰነውን ይወስዱና ፓርክ ውስጥ አስገብተው ያለፈለት ያስመስሉታል፡፡ እርሱም ማግኘት የሚገባውን ሳይሆን ራሱን ከጫካው ኑሮ ጋር ስለሚያነጻጽር ‹ተመስገን› እያለ ይኖራል፡፡››

  ReplyDelete
 29. ዲያቆን ዳንኤል ይህ በእውት ልብ ለሚለው ሰው ሁሉ ባጉል ዘረኝነት ለተዘፈቁ ሰዎች ትልቅ ትምህርት ነው ለነገሩ ዘረኝነት ከእውቀት ማነስ የሚመጣ ጠባብ የሆነ አስተሳሰብ ነው

  ReplyDelete
 30. It's a Great view GOD bless you.

  ReplyDelete
 31. ውድ ዳኒ፤
  በጤና መድረስህንና መኖርህን ማወቄ ደስ ብሎኛል!
  ድንቅ አስተማሪ ጽሁፍ ነው!
  የዘር ማንዘር ጉዳይ እጅግ አስቀያሚ መልክ እየያዘ ነው፡፡ ምንም እንኳን ይህ አስተሳሰብ በ17ኛው ክ/ዘመን በአውሮፓ ጣራ የነካ ቢሆንም፤ እኛ ሀገር ግን በ21ኛው ክ/ዘመን እያጫረሰን ይገኛል፡፡ አንዳነዴ አስተሳስባችን ምን ያህል ውዳቂ እንደሆነ የምንረዳው ቋንቋዬን የሚናገር እርሱ የእኔ ነው በሚል የሚደረጉ መቀራረቦች፣ መጠቃቀሞች፣ ስናይ ነው፡፡
  ሰው በዘሩ ሲከበር፣ ሲናቅ፣ ሲጠቃቀም፣ ሲወገዝ … ስታይ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ መገመት አያዳግትም! ሁላችንም ከስጋ፣ ከደምና ከአጥንት የተሰራን መሆናችንን መገንዘብ አቅቶን፣ በአስተሳስባችን/በእውቀታችን ሳይሆን በዘር መታዎቃችን ያሳዝናል፡፡
  ለማነኛውም ሥልጣኔውን ያምጣልን!
  ከዓለም ጥግ ክፍል ሁለትን መለጠፍህን እንዳትረሳ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰው በዘሩ ሲከበር፣ ሲናቅ፣ ሲጠቃቀም፣ ሲወገዝ … ስታይ ምን ያህል አሳፋሪ እንደሆነ መገመት አያዳግትም! ሁላችንም ከስጋ፣ ከደምና ከአጥንት የተሰራን መሆናችንን መገንዘብ አቅቶን፣ በአስተሳስባችን/በእውቀታችን ሳይሆን በዘር መታዎቃችን ያሳዝናል፡፡
   ለማነኛውም ሥልጣኔውን ያምጣልን!
   ከዓለም ጥግ ክፍል ሁለትን መለጠፍህን እንዳትረሳ

   Delete
 32. አስተሳሰብ ነጻ አውጭ ድርጅት›› ‹ነጻነት የፍጡር ሀብት ነው፡፡ ለእነ እገሌ ተብሎ የሚቆረስ አይደለም፡፡ ጨቋኙም ተጨቋኙም ነጻ ካልወጣ ሙሉ ነጻነት አይገኝም፡፡ ጨቋኝነት ከአስተሳሰብ ባርነት የሚመጣ ነው፡፡ ከአመለካከት ድህነት የሚከሰት ነው፡፡ ሙሉ ነጻነትን ለማግኘት እርሱን ነጻ ማውጣት አለብሽ፡፡ ካልሆነ ግን ጉዞው አንዱን ጨቋኝ በሌላ ጨቋኝ መተካት ነው የሚሆነው፡፡ አፍሪካውያንኮ ራሳቸውን ከአውሮፓውያን ነጻ ማውጣት አላቃታቸውም፡፡ ያቃታቸው ራሳቸውን ከራሳቸው ነጻ ማውጣት ነው፡፡ ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተኩ፡፡ ቅድም እንዳልኩሽ ሳጥኑን ካላጠፋሽው ታግሎ ከሳጥኑ የወጣው ሁሉ በፋንታው የተሸነፈውን እርሱ ወደወጣበት ሳጥን መክተቱ የማይቀር ነው

  ReplyDelete
 33. Very (100000000000000) nice!!!!!!

  ReplyDelete
 34. ደስ የሚል የወቅቱ አንገብጋቢ እይታ

  ReplyDelete
 35. መልካም አስተማሪ ጥሁፍ ነው፡፡ ግን ምን ያደርጋል፡፡ የሚረዳው ከሳጥኑ የወጣ ጥቂት ብቻ ነው፡፡ እኔም እንደበቁለዋ ወዴት እንጠጋ እያልኩ አስባለሁ፡፡

  ReplyDelete
 36. It is amazing article. I like it the way you are put the point.we learn alot from this article. Thank you Dany

  ReplyDelete
 37. የበቅሎዋን ትረካ እንደ ጉድ ሰማነው!! በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት ፈረስ እናቴ ነው አለ አሉ! ምን አለ የተጠየቀውን ቢመልስ ኖሮ?

  በፑልቲካው ዓለም ልክ እንደ በቅሎዋ ጥያቄው ሌላ መልሱም ሌላ ነው። ሰሞኑን የሼሁ ሞት ድራማ ነው ያሉት ደጉ መንግሥታችን ገደላቸው ለማለት ነበር። ETV ግን ድራማ ነው ማለታቸው መቀለጃ አደረጉት ብሎ ሸወደን። ፑልቲካ ፑቲካ ብለንሃል። ወይ ፑልቲካ!

  ReplyDelete
 38. Hi Everyone here following this blog and Daniel Kibret,

  This is not the right place to ask such a question but i have no other choice as i need the information.It has been long time but i have read an article on this blog about Extremism("tsinfegnet"). I am not sure whether the article main topic was about it or it was mentioned as a paragraph consolidating the main topic which i don't remember. But i remember it was a very good insight and i wanted to read it again but it was difficult to look for it as there is no search tool in the blog as well as there is no forum to discuss it with others.I still need the article so i am asking if any one could remember that article to let me know which date it is written.

  It could have been very helpful or appropriate if there had been a forum associated with this blog.I could have asked and discussed it through the forum but there isn't. hence, i would also like to suggest to daniel if he can incorporate a forum with this blog.
  waiting for your replies.
  thanks

  ReplyDelete
 39. Dn.Danile ena mange yzmnacne teyka teru gelsa newe Egzbher yabrethe endma

  ReplyDelete
 40. Wow! Grate view!!!

  ReplyDelete
 41. God bless you Dani.

  ReplyDelete
 42. God bless u Danae it's so great article bertaaaaaaaass

  ReplyDelete
 43. አየሽ ቤተ መንግሥቱ ላይ ስትቀመጭ ሌላውን ለማግለል ሳጥን ትከፍቻለሽ፤ ከዚያ ሁሉንም በየሳጥኑ ታስቀምጭዋለሽ፡፡ የእምነት፣ የዘር፣ የመልክ፣ የአካባቢ፣ የቋንቋ ሳጥኖችን ከፍተው ሁሉንም እዚያ ስላስቀመጧቸው ተቀማጮቹ ሳጥኑን እንዳለ ተቀበሉት፡፡ ማንነታቸውም አደረጉትና ሳጥኑን ለማስቀረት ከመታገል ይልቅ ራሳቸውን ብቻ ከሳጥኑ ለማውጣት ይታገሉ ነበር፡፡ በሳጥኑ ዛሬ አህዮች ይገቡበታል፤ ነገ ፈረሶች፣ ከነገወዲያ ግመሎች፣ ከዚያም በጎች፣ ከዚያም ፍየሎች እየገቡበት ይቀጥላል፡፡ እኛም ዛሬ ያለሳጥን መኖር ከማንችልበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ እኔን ሲያገኙኝ እንስሳ መሆኔን አይደለም የሚያዩት፤ የትኛው እንስሳ? ይላሉ፡፡ - ፈረስ፡፡ በዚህ አያቆሙም፡፡ ከዚያ ደግሞ የትኛው ፈረስ? የዱር ወይስ የቤት? ይቀጥላል፡፡ -የቤት፡፡ ለጭነት ወይስ ለግልቢያ? መቋጫ የለውም ልጄ፡፡ በትልቁ ሳጥን ውስጥ ራሳችን የሠራናቸው ትንንሽ ሳጥኖችም አሉ፡፡ በእነዚያም ውስጥ ሌሎች ትንንሽ ሳጥኖች አሉ፡፡››

  ReplyDelete
 44. መቧደናችን ተፈጥሮዋዊ ይመስለኛል:: በዘር አቧደኑን እንጂ ቢተዉን እኛ እራሳችን የሆነ የሚያመሳስለን ነገር ፈልገን መቧደናችን አይቀርም ነበር:: ክፋቱ ከቡድኔ ዉጪ ያለዉ ጠላቴ ነዉ የሚለዉ ነዉ:: አሁን ባለዉ ሁኔታ ትልቁን [ሰዉ] የሚባለዉን ቡድን ለማስታወስ ከህዋ ላይ ሰዉን ነጥሎ የሚያጠቃ ዩፎ ሳያስፈልገን አይቀርም:: ያኔ በጥቃቅን ዘር ሳይሆን እራሳችንን ለመከላከል ስንል ሰዉ በሚባለዉ ዘር እንቧደናለን:: ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነገር ቢኖር ትንንሽ ቡድን ፈጣሪዎቹን ራሳቸዉን እናሳንሳቸዉ ነበር:: እናመሰግናለን ዲ/ን ዳንኤል

  ReplyDelete
 45. Long live...God bless u!!!!

  ReplyDelete
 46. Nice article. But why you always tell us from where you write? Do you think it matters for the reader?

  ReplyDelete
 47. Dani, I am happy not only by reading this idea but also, you are responsible person to us, that is the reason,you wort any where you are.Thank you. Would you post this comment by correcting the grammar.

  ReplyDelete
 48. "ዳንኤል ፖለቲካ መጻፍ ጀመረ…..ዳኒ ከአውስትራሊያ የማትመለስ መስሎህ ነው?…..ልብህ ከቆረጠ ጥሩ……አለበለዚያ አንተ እራስህ “ታች በሌ” ን ልትሆን ነው"

  ላለከው/ላልሺው አስተያየት ሰጪ የሚከተሉት ሁለት ነጥቦች የማይለወጡ ፍጹም እውነት ናቸው፡፡ እውነት ደግሞ ለሃሰተኞችና ለልበ ደንዳኖች መራራ ናት፡፡

  1. ጨቋኝነት ከአስተሳሰብ ባርነት የሚመጣ ነው፡፡ ከአመለካከት ድህነት የሚከሰት ነው፡፡ ሙሉ ነጻነትን ለማግኘት እርሱን ነጻ ማውጣት አለብሽ፡፡
  2. እንስሳት ሁሉ ነጻ ሳይሆኑ በቅሎ ተለይታ ነጻ ልትሆን አትችልም

  እነዚህን እውነታዎች በመናገር የሚደርስበት ቢኖር ታላቅ ጸጋ እንጂ መከራ ሊሆን አይችልም፡፡ ከሳጥንህ/ሽ ውጣ/ውጪ

  ReplyDelete
 49. ሰሚ የለም እነጂ ሰሚማ ቢኖር
  ትምህርቱም ተግሳፁም ተነግሮን ነበር
  እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 50. እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ

  ReplyDelete
 51. Daniel, there is no a rational book than bible in the world. But what we have seen from the previous regimes in Ethiopia is that they misuse it and represent them selves as a good character in the book. Just start from recent history, It was very difficult to separate Ethiopian Orthodox church from the regimes in power during Minilik and Hailesilasse and. They were consider them selves as a leaders appointed by God. They were doing several evil things against their people. May be for the good part of it, I didn't see any criticism on these regimes from the tribe they represented them.

  ReplyDelete
  Replies
  1. excellent, had the tribe that the previous regimes represent condemn the racist (apartheid) practices of those regimes, then that tribe wouldnt be considered as accountable for the mistakes. However we didnt see that yet. what we see is that some people from the tribe represented by the previous regime are so angry and jealous of the tribe that the current regime represent. They dont hate the concept of racist regime, they are only jealous of the ruling tribe. that is where all other scholars lack confidence! However, the root cause of all the evils of racism in Ethiopia is what you have tried to mention.

   Delete
 52. Dn. Dauniel ur article always impress me keep going

  ReplyDelete
 53. It is a good idea God bless you.you have a great mind

  ReplyDelete
 54. ....አሁን ባለዉ ሁኔታ ትልቁን [ሰዉ] የሚባለዉን ቡድን ለማስታወስ ከህዋ ላይ ሰዉን ነጥሎ የሚያጠቃ ዩፎ ሳያስፈልገን አይቀርም::

  ReplyDelete
 55. God blessed you for ever Dn Daniel! !! So interesting and educational for whom can read and critically thinking.

  ReplyDelete
 56. ብዙ አንባቢያን በሰጡት አስተያየት ጽሁፉን የጻፈው ዲ. ዳኒኤል የመሰላቸው አሉ፡፡
  ግን ከክቡር ዶክትር ከበደ ሚካኤል ትረካ የተወሰደ መሆኑን ወንድማችን በግልጽ አስቀምጣል፡፡

  ወቅታዊ በሆነ መልኩ ግን ስላስነበበን ማመስገን አለብን፡፡

  ReplyDelete
 57. ብዙዎቹ ነጻ አውጭዎች ትናንትን ነጻ ለማውጣት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ አንቺ መግባት ያለብሽ ነገን ነጻ ሊያወጣ የተቋቋመ አካል ከተፈጠረ ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 58. ብዙዎቹ ነጻ አውጭዎች ትናንትን ነጻ ለማውጣት የተቋቋሙ ናቸው፡፡ አንቺ መግባት ያለብሽ ነገን ነጻ ሊያወጣ የተቋቋመ አካል ከተፈጠረ ብቻ ነው፡፡

  ReplyDelete
 59. thanks dani interesting

  ReplyDelete
 60. Diakon Daniel Kibret,i really appreciate you,keep it up!

  ReplyDelete
 61. "Tadiya minu lay new yegna ariko maseb....." alech zefagnau..... ene gin ensisa mohon bicha yibekagnal. Beklom, ahiyam, feresim.... mehon alfeligim (beshita new). Dani, ye Matusala edme yistih!

  ReplyDelete
 62. dedicated for JaM fool

  ReplyDelete
 63. I dedicated this for Jawar Mohammed

  ReplyDelete
 64. የድንግል ልጅ በሰላም ይመልስህ።በርታ!

  ReplyDelete
 65. SEW MEHON NEKI NEW
  ETHIOPIAWI MEHON BEKI NEW
  EDIMENA TENA YISTIH

  ReplyDelete
 66. የብዙዎቹ አድናቆትና ምስጋና አልገባኝም

  ....አሁንም እኛ አንድ ልንሆን ያልቻልነው አንድ የሚያደረግን ነገር ስለሌለ ሳይሆን አንድ የሚያደርገን ጥበበኛ አንጥረኛ ስለሌለ ነው፡፡...

  ብሎ ፈጣሪውን ለረሳ ሰው መሆኑ ነው የገረመኝ
  ከዚህች ከተቀደሰች አገር ለራቀ ሰው በእውነት ልናዝንለት ይገባል፡፡
  ፈጣሪያችን አንድ አድርጎ ባገራችን እንዲያኖረን ነው ምኞታችንና ፀሎታችን ሊሆን የሚገባው፡፡

  ReplyDelete
 67. የድንግል ልጅ በሰላም ይመልስህ።በርታ!

  ReplyDelete
 68. ከላይ አንዱ ... ከማን እንደተማረው አይታወቅም....

  ..›asbet dnglAugust 4, 2013 at 2:52 AM‹..

  ..›የድንግል ልጅ በሰላም ይመልስህ።በርታ!‹..

  የድንግል ልጅ አንድ እሱ ብቻ ነው፡፡ ይህው ልጅሽ የተባለውም ዮሓንስ ነው፡፡ የሱን ስራ እንካን ልንሰራ የሰራውንም ስራ ለመስማት የነፍስ ብርታቱ የለንም ደካሞች ነን፡፡
  መፅሐፍ ስላነበብን አዋቂዎች ነን ማስተማር እንችላለን ማለት አይደለም፡፡ መንፍሳዊ አባቶቻችን ያዩትን ታአምር ለማየት አለመታደል እኮ አንዱ ምልክት ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ድቁና ካለው ሰው የምንጠብቀው አለማዊ ጉዳይ ቢሆንም ከመንፈሳዊ ጋር አያይዞ ሲመልስ ነበር፡፡
  ካገር ሳይወጡ ስለተገፉ ብቻ ከቤተክርስቲያን ውጭ ሆነው በትግስት የሚነኖሩ አሉ መውጣት አቅቶአቸው ግን አይደለም ከዚህች ሌላ የተሸለ አገር እንደሌ ስለሚያምኑ እንጂ፡፡፡፡

  ReplyDelete
 69. "አሳዛኙ ዜና" you wrote on this topic however he is the one responsible for current and coming Ethiopian problem you know what he build Ethiopia on sand not by cement he destroy our unity. As you said if he made any mistake no matter but he played on major thing on our identity our flag our moral our collaboration የታማበት ባንዲራ ዝቅ ብሎ አለከሰለት

  የሀገራችን ሰው እንዲህ ይላል “(……………………………………. አገር የሌለለት ወዴት ይደረሳለ ) unity( አገር )is major than any road, contraction ... . I am telling you the truth i am really afraid when i think about our children and the future of Ethiopia. You know what the only thing make my hope/rest/ Ethiopia is under control of God. God gives us back our unity i believe that. when we got our unity we can face any thing . if you time please please listen fm 102.1 ትዝታ ዘዓራዳ ተፈሪ አለሙ ሐምሌ 27,2005 specially what he said at the lasy
  Again and again the son of St. Mary God bless Ethiopia forever

  ReplyDelete
 70. Your comment will be visible after approval.

  like "Animal Farm" he talk using animals. what?? are you MANIAC
  If you are a truth speaker why don't you write face to face answer.
  Merry go-round.....
  It seems to get some relief from stress..
  thgh EBS, site ..... what you write and speak is not that much interesting,please try some other thing to yourself interesting by your viewers not by your 'Tifozo'.

  Your comment will be visible after approval.
  i dont like this your msg, you post only what you like & your supporters comment only. that is shitty it doesn't participate & invite others to see you site again. Think over it...

  ReplyDelete
 71. ‹‹እንዴት አድርገው ነው የጨቆኑት፤ ለመሆኑስ የአንቺ አያቶች ስንት ናቸው? እርሱ የተነገረውን ብቻ ነው የሚያውቀው፤ ያልተነገረውስ? ከታሪካችንኮ በጣም ጥቂቱ ነው የተጻፈው፤ ከተጻፈውም በጣም ጥቂቱ ነው የተነገረው፡፡ ባልተጻፈው ታሪካችን ውስጥ ማን ምን እንደነበረ ማን ያውቃል? ለምሳሌ በሀገረ እሥራኤል አህዮች እጅግ የሚወደዱ የቤት እንስሳት ነበሩ፡፡ ነገሥታቱም፣ ካህናቱም፣ ነቢያቱም ዘመኑ ዘመነ ሰላም ሲሆን በአህያ ነው ይሄዱ የነበሩት፡፡ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ የተሰደደችው በአህያ ነው፡፡ በጥንታውያን ግብጾች ዘንድ አህያ የመኳንንትና የነገሥታት ሀብት ማሳያ ነበር፡፡ የናርማር ወይም የሖር - አሃ መቃብር እንደሆነ በሚታመነው ቦታ ላይ በተደረገ ቁፋሮ አህዮች ከነገሥታቱ ጋር በክብር ተቀብረው ተገኝተዋል፡፡ በዚያ ጊዜ አህዮች የቤተ መንግሥቱን ምግብ እየተመገቡ፣ በቤተ መንግሥቱም እየተሸለሙ ኖረዋል፡፡ በሌላው ዘመን ደግሞ ይህንን ፈረሶቹ ወስደውታል፡፡››

  ReplyDelete
 72. May Allah bless you bro

  ReplyDelete
 73. betam des yemil new ....sew hoy what u fill about freedom?????

  ReplyDelete
 74. wow temrenal enamesegnalen berta

  ReplyDelete
 75. good article
  but do not say tarik aykeshfim
  like u did to prof. Mesfin
  tarik eyekeshefe new

  ReplyDelete
 76. ቤት የቀረው ውሻ ዱር ከቀረው ውሻ ጋር በመለያየታቸው ዛሬ አንዱ አንዱን እንደ ጠላት ያባርረዋል፡፡ ሰው ብልጥ ነው፡፡ አንዱን ወደራሱ አቅርቦ ውሻ አደረገውና ‹‹ቦቢ›› እያለ በማቆላመጥ ነጻ የወጣ አስመሰለው፡፤ ሌላውን ደግሞ ቀበሮ፣ ተኩላ ብሎ ጫካ ተወውና እርሱን መግደል ጀግንነት እንዲሆን አደረገው፡፡
  ‹‹ሁላችንንም መከራውና ግፉ፣ ጭቆናውና የደረሰብን ነገር ሁሉ አስተባብሮናል፡፡ በየዘመናቱ ቤተ መንግሥቱን የተጠጋ ተሸልሟል፡፡ አምሮበታል፡፡ ሌላውን ለማስገበርም ዘምቷል፡፡ Thank you D.Daniel God bless you....

  ReplyDelete
 77. ሁለት ነጥቦችን በአንድ የያዘ ፅሁፍ:: በጣም አመሰግናለሁ ዳንኤል! ያለፈ ታሪክ እንዴት መታየት እንዳለበትና የወደፊት አቅጣጫ ምን መምሰል እንዳለበት:: የታሪክ አጋጣሚ የአንድ ሀገር ሰዎች አድርጎናል: አስተሳስሮናል: አንድ ታሪክ ፈጥሮልናል:: ከዚህ በኅላ ላለው ግን እኔ ከእንትና ወገን ነኝ: የእንትን ሰፈር ሰው ነኝ ብሎ ማሰብ ሳይሆን ያለብን እኔ ሰው ነኝ የሚለው መሆን አለበት::

  ReplyDelete
 78. በቅሎ - እማዬ ትልልቆቹ ሳጥኖቹስ ፈረሱ በትልቁ ሳጥን ውስጥ እንዳንቺ ላሽካካ ወይስ እንዳባዬ ላናፋ፣ የትልቁ ሳጥን አጠገብ ያለው ሳጥን እኔን የመሰለች ግልገል በቅሎ አለች፣ ትልቁን ሳጥን አፍርሽው . . .

  ReplyDelete
 79. "Tarik honal ena aytarememna"yaa dani you are my hero. Bless you

  ReplyDelete
 80. God bless you, you are being the model of all Ethiopians

  ReplyDelete
 81. ዲ/ን ዳንኤል ግሩም እይታ ነው፡፡ ግን ይህን አስተሳሰብ
  Anonymous


  በሕዝቡ ዘንድ ማስገንዘብ እንዴት ይቻላል? ሁሉም በዘረኝነት ቫይረስ ተጠቅቷልና፡፡ እስቲ እግዚአብሔር ይፈውሰን ሁላችንንም፡፡

  ReplyDelete
 82. betam betam kebade agelelets new mert beka lela men elalehu yehen tomare meketatel kejemerku jemero be buzu neger tekeyeryalehu

  ReplyDelete
 83. A wonderful article.May God bring the time of King Teodros who will lead the world .Ethiopia.++++Africa++++

  ReplyDelete