Tuesday, July 23, 2013

ጉዞ - ወደ ምድር ጥግ( ክፍል አንድ)

ከአዲስ አበባ ወደ አውስትራልያ ልጓዝ ነው፡፡
ትነሣላችሁ የተባልነው ከምሽቱ አራት ሰዓት ከ15 ነበር፡፡ ‹ነበር› ካልኩ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ የመሳፈሪያው አዳራሽ ውስጥ ተቀምጠን ግን የመሳፈሪያው ሰዓት በረረ፡፡ ሰዓቱ እኛን ጥሎን በሌላ አውሮፕላን ይብረር፣ ወይም የመሳፈሪያውን ሰዓት ያደረገው የአየር መንገዱ ሠራተኛ ሳይመጣ ይቅር የታወቀ ነገር የለም፡፡ ደግነቱ የአየር መንገዱም ሠራተኞች የተሰጣቸው መመሪያ ‹‹የመሣፈሪያ ሰዓት ካለፈ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሳታስነቁ ወዲያ ወዲህ ማለት ነው› የሚል ሳይሆን አይቀርምና አንዳቸውም ምን አልተነፈሱም፡፡
መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ ለማግኘት የሚታወቅ መንገድ (system) ስለሌለ የሚታወቅ ሰው መፈለግ ነው፡፡ አንዱን የማውቀውን ሰው ጠጋ ብዬ ስጠይቀው ለንደን ላይ አውሮፕላናችን መጠነኛ ችግር እንደገጠመው ሹክ አለኝ፡፡ ምናልባት በዚያ ተደናግጠው ይሆናል ብዬ ይቅር አልኳቸውና መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላም ሕዝቡን ወደ ስታዮም እንደሚገባ ተመልካች አንጋግተው ይዘውት ወረዱ፡፡ ‹‹ሕጻናት ያላችሁ፣ የቢዝነስ ክፍል አባላት፣የሼባ ማይልስ የወርቅ አባላት›› ብሎ ነገር የለም፡፡ ‹‹እየየ ሲዳላ ነው›› አሉን፡፡ የሰው ጎርፍ ወደ ታችኛው ፎቅ በደረጃው ፈሰሰ፡፡ 

በአውቶቡሱ በኩል ተሸጋግረን ወደ አውሮፕላኑ ገባን፡፡ የመቀመጫ ለውጥ እንጂ የሰዓት ለውጥ አልነበረውም፡፡ ለነገሩ ብዙ ጊዜ በሀገሪቱ የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና አልተገረምንም፡፡ ‹መሣፈሪያ አዳራሹ ውስጥ መቀመጥ ሰለቸን› ያልናቸው ይመስል አውሮፕላኑ ውስጥ አንድ ሰዓት አስቀመጡን፡፡ ደግነቱ አብራሪው እየደጋገመ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ከተለያየ ሀገር የሚመጡ ተሸጋጋሪ መንገደኞች እየተጠበቁ መሆኑንም ይነግረናል፡፡ መቼም የመጣውን አስቀምጦ ያልመጣውን መጠበቅ የተለመደ ነውና አላዘንኩበትም፡፡ ሠርግም ላይ፣ ስብሰባም ላይ፣ ጉባኤም ላይ፣ ግብዣም ላይ በሰዓቱ አክብረው የመጡት የዘገዩት እስኪመጡ እንዲጠብቁ በሚደረግበት ባህል ውስጥ ስላለን የሚገርም አይደለም፡፡
ከመቅረት መዘግየት ይሻላል ብሎ አውሮፕላኑ ወደ ዱባይ ተነሣ፡፡ ከጎኔ አንዲት እንደኔ አፍሪካዊት የሆነች፣ እንደ እኔ ግን ኢትዮጵያዊት ያልሆነች ሴት ተቀምጣለች፡፡ እርሷ እቴ ወደ አውሮፕላኑ እየገባች ሳይሆን አይቀርም ዕንቅልፍ የጀመራት፡፡ ደግሞ ስፋቷ ለሚኒ ባስ ታክሲ የመጨረሻው ወንበር እንጂ ለአውሮፕላን ወንበር የሚሆን አይደለም፡፡ ከመደገፊያው ተርፎ እኔ ጋ እየመጣ አስቸገረኝ፡፡ ሦስት ትራስ ደራርባ፣ በዚያ ላይ ፎጣ መሳይ ነገር ለብሳ ትለጥጠዋለች፡፡
እኔን መከራ ያሳየኝ ዕንቅልፏ አይደለም፡፡ እየተረፈ የሚመጣው ሰውነቷ አልበቃ ብሎ እንደ ፔንዱለም ስትወዛወዝ ትከሻየ ላይ እየመጣች ዘፍ የምትለው ነገር ነው፡፡ ሴትዮዋ የመጣችው ‹ሶሪ› ከሌለበት ሀገር ነው መሰለኝ ትከሻዬን ገጭታው ስትመለስ ከጥቁሩ ፊቷ መካከል ብልጭ የሚል ባለ ቀይ ድድ ጥርሷን ብቻ አሳይታኝ ‹ካለፈው የቀጠለ› ብላ ወደ ዕንቅልፏ ትገባለች፡፡ ትቆይና ደግሞ ክላሲካል ትለቃለች፡፡ ‹‹ፉርርርርርር›› የሚል የኩርፊያ ክላሲካል፡፡
መቼም በዚህ ክላሲካል ታጅቦ እንኳን ዕንቅልፍ መተኛት ቅዠት መቃዠትም አይቻልምና ከያዝኳቸው መጻሕፍት አንዱን አወጣሁ፡፡ ‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የሚል ካሕሣይ አብርሃ በተባለ የኢሕአሠ(የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ሠራዊት) ታጋይ የተጻፈ መጽሐፍ፡፡ መጽሐፉ ከሥነ ጽሑፍ አንጻር ብዙ የሚቀሩት ነገሮች ቢኖሩም የዚያን ዘመን ወጣቶች ታሪክ በማሳየት አንጻር ግን ማራኪ ነው፡፡  መቼም ሰው በአውሮፕላን ሲሄድ አውሮፕላኑ እንዳይወድቅ እንጂ ከአውሮፕላኑ ውስጥ ሰው እንዳይወድቅ የሚሰጋ አይመስለኝም፡፡ እኔ ግን አንድ ገጽም ሳላነብብ በቀኝ ትከሻዬ በኩል የሆነ ነገር ዘፍ አለብኝና ሰጋሁ፡፡ ተጠንቅቄ ዘወር ስል ሴትዮዋ ሳታስፈቅደኝ ትከሻዬን ተንተርሳዋለች፡፡ እንደምንም ታግዬ ሳስለቅቃት ነቅታ ጥርሷን ብልጭ ታደርግና ዕንቅልፏን ከተቋረጠበት ትቀጥላለች፡፡
አሁን ምን ተብሎ ይጸለያል? እኔ እስካሁን በቀኝ ትከሻ በኩል ዘፍ ለምትል ሴት መከላከያ የሚሆን ጸሎት የነገረኝ ሰው የለም፡፡ ከኔ መለስ ሳደርጋት በወዲያኛው በኩል ወደተቀመጠው ፈረንጅ ሄዳ ዘፍ አለች መሰል ‹ኦ ማይ ጎድ› ሲል ሰማሁት፡፡ ‹‹እስኪ ያንተ ጸሎት ከሠራ እኔም እጠቀምበታለሁ›› ብዬ ጠበቅኩት፡፡ ሲብስበት ጊዜ ከወንበሩ ተነሥቶ ወደ መጸዳጃ ቤት አመራ፡፡ የፈረንጅ ነገር፣ ለሁሉም ችግር ወደ መጸዳጃ ቤት ነው፡፡ ‹ከአፍርንጅ የምንለይበት›› የሚለው የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሀገራችን መጽሐፍ ትዝ አለኝ፡፡   
‹‹የአሲምባ ፍቅር›› የዚያ ዘመን ወጣቶች ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ለነጻነት የነበራቸውን ታጋይነት፣ ላመኑበት ነገር ይከፍሉት የነበረውን መሥዋዕትነት፣ በሌላው ዓለም ያዩትንና ያነበቡትን በሀገራቸው ለማምጣት የነበራቸው ሕልም፣ ለአብዮት የነበራቸውን ጽኑ ፍቅር ያሳያችኋል፡፡ ያንን የመሰለ ትውልድ በጦርነት፣ በእሥርና በግድያ፣ በስደትና በጉስቁልና ማጣት ሀገሪቱን ምን ያህል እንደ ጎዳት ታዩበታላችሁ፡፡ ውጊያና ትግል፣ ስብሰባና ግምገማ፣ ኮንፈረንስና የእርምት ንቅናቄ፣ ተሐድሶና የፖለቲካ ትምህርት፣ ቋንቋው የነበረ አንድ ትውልድ እንዴት እንደጠፋ ትታዘባላችሁ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የአመራር እጦት፣ የብስለት መጥፋት፣ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ የትግል ስልት፣ የግለሰብን ነጻነት ያጠፋ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ ችግሮችን ሁሉ በመሣሪያ አፈሙዝ ለመፍታት የነበረው አመለካከት፣ ራስን በምሁራዊ አምባ ላይ አስቀምጦ ሌላውን የመናቅ አባዜ፣ ከተማ ላይ ተቀምጦ የገጠርን ትግል የመምራት ድንግርግር፣ በሀገሪቱ ትውልድ ላይ ያመጣውን ምስቅልቅልም ታያላችሁ፡፡
እነዚህን መሰል መጻሕፍት ሳነብ እጅግ የሚገርመኝ ነገር ያ ትውልድ ፈጽሟቸዋል ብለን የምናስባቸው ስሕተቶች ዛሬም እንደገና እየተመላለሱ መፈጸማቸው ነው፡፡ አሁንም ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ስንሞክር፣ አሁንም ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ ፓርቲዎች ከግለሰብ ነጻነት በላይ ሲሆኑ፣ አሁን የፓርቲ መሪዎች ችግሮችን በመከፋፈልና በመለያየት ሲፈቱ፣ አሁንም ሕዝብና ፀረ ሕዝብ፣ አንድነትና ፀረ አንድነት፣ አብዮታዊና ሊበራል፣ ኮሙኒስትና ካፒታሊስት የመከፋፈያ መሣሪያዎቻችን ሲሆኑ፣ አሁንም በጠላት መቃብር ላይ ሕንጻ የመሥራት አባዜ አልለቀን ሲል፣ አሁንም የተቃራኒያችንን አመለካከት ለማዳመጥ ትዕግሥት ሲያንሰን፣ ምን ያህል ከዚያኛው ዘመን ስሕተት እንዳልተማርን ያሳዩናል፡፡
ተዋጊዎቹ ወጣቶች በአንዳንዶቹ ውጊያዎች አይስማሙም፣ በአንዳንዶቹ ውጊያዎች ደግሞ ከአመራሮቻቸው ተቃራኒ የሆነ መረጃ አላቸው፣ ፓርቲውና ድርጅቱ እየተሳሳተ ያዩታል፣ ስሕተቶቹ የሚያስከፍሉትን ዋጋ በርግጠኛነት እያገኙት ነው፤ ነገሮች እንደማይሁኑ ሲሆኑ እየታዘቡ ነው፤ በተሳሳተ አመራር፣ በተሳሳተ የመፍትሔ ጉዞ፣ በተሳሳተ አሠራር የተነሣ ውድ የሀገሪቱ ልጆች ሕይወታቸውን ከጎናቸው ሲሠው እያዩ ነው፡፡ ነገር ግን ድርጅት፣ ፓርቲ፣ አመራር የሚባሉት ሰዎች አይሳሳቱም፣ እነርሱ ያሉት ሁሉ ቅዱስ ነው፣ እኔ ካየሁት ያላየው አመራር ይበልጣል፤ እኔ ስሕተት መሆኑን ባውቅም ፓርቲው ትክክል ነው ካለ ትክክል ነው፤ ሁለትና ሁለት ተደምሮ አራት የሚሆነው ፓርቲው ወይም ድርጅቱ አራት ነው ካለ ብቻ ነው፡፡ ያለበለዚያ ግን ሦስትም አምስትም ሊሆን ይችላል ብሎ የማሰብ አባዜ ዋጋ ሲያስከፍል እናያለን፡፡ ዛሬም ግን ይሔው አስተሳሰብ በዚህች ሀገር ውስጥ ሥሩን ተክሎ ቅጠል አውጥቶ፣ አብቦና አፍርቶ እየታየ ነው፡፡ ካለፈው ተምሮ እርሱን ለማረም የሚተጋ አይታይም፡፡
አውሮፕላናችን ሁለት ሰዓት ያህል ዘግይቶ ዱባይ ገባ፡፡ እኔ ዱባይ የገባሁት ቀጣዩን አውሮፕላን ለመያዝ 15 ደቂቃ ብቻ ሲቀረኝ ነው፡፡ ምድር ከወረደ በኋላ የበረራ አስተናጋጆች የተወሰን ሰዎችን ስም ጠርተው ውጭ የአየር መንገዱን ሰዎች እንድናነጋግር አሳሰቡን፡፡ እሺ ብለን ስንወጣ አገኘናቸው፡፡ የሆነች ወረቀት ሰጡንና እንዲህ ያለ ቦታ ሄዳችሁ የሆነ ሰው ታገኛላችሁ ሩጡ አሉን፡፡ መቼም አበበና ማሞ፣ ምሩጽና መሐመድ ከድር፣ ኃይሌና  ቀነኒሳ ከተወለዱበት ሀገር የመጣን ነን ብለን ወደተባለው ቦታ ሮጥን፡፡ ሲዖል ይዘጋላችሁና የነገሩን ቦታ ሁሉ ዝግ ነው፡፡ አንዳች ሰው በአካባቢው የለበትም፡፡ ‹አይ አየር መንገዳችን፤ እነ ክበበው ገዳ የት ሄደው ነው እርሱ እንዲህ ያለ ቀልድ የሚቀልደው› ብዬ ተገረምኩ፡፡ ማንን እናናግር፡፡ በኋላ አንድ የአውሮፕላን ማረፊያውን ፖሊስ አገኘነውና ችግራችንን ስንነግረው በፍተሻ ማለፊያው በኩል አድርጎ ወደ ምድር ቤት ወሰደን፡፡
 ምድር ቤት ወርደን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ስንደርስ እነርሱ ምን አለባቸው አራት ሆነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ምናለ አንዳችሁ እንኳን እዚያ ተገኝታችሁ ብትረዱን›› አልኳቸው፡፡ ‹‹እገሊትኮ ነበረች›› አሉን፡፡ ትኬታችንን ተቀብለው አየት አደረጉና ‹‹አሁንማ ረፍዷል ቀጣይ አውሮፕላን ካለ እንይላችሁ›› አሉን፡፡ ለእነርሱ እየተባበሩን ነው፡፡ ስሕተቱን የፈጸሙት እነርሱ፣ የዘገዩት እነርሱ የምንቀጣው እኛ፡፡ እንዴው ግን እስከ መቼ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የደንበኞቹ ግንኙነት የባላባትና የጢሰኛ የሚሆነው? በባላባቶች ፍርድ ‹‹ምን ባላባት ቢያጠፋ ጢሰኛ ይክሳል›› ይባላል፡፡ አየር መንገዳችንም እንዲህ ሆነብንኮ፡፡ ‹‹ይቅርታ፣ እስኪ ዐረፍ በሉ፣ ችግሩን እንፈታዋለን›› ከአማርኛችን ውስጥ የሌሉ ይመስል ምነው ከአንደበታቸው አልወጣ አሉ?
‹‹እናንተ ባጠፋችሁ ቁጥር እኛ መቀጣት አለብን?›› አልኳቸው ኃላፊ የመሰሉትን ሴትዮ፡፡ምንም አልመሰላቸውም፡፡ ከሌላው አየር መንገድ ጋር በስልክ ተነጋገሩ፡፡ ደግነቱ ያኛው አውሮፕላን አርፍዷል፡፡ ‹‹ትደርሳላችሁ ሂዱ አሉን፡፡›› ሄድን፡፡ እንደተባለውም ደረስን፡፡ ዛሬ ከአየር መንገዳችን ጋር የሚወዳደሩም የሚፎካከሩም አየር መንገዶች በበዙበት ጊዜ እንዲህ በደንበኞች አገልግሎት ላይ መቀለድ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ለአየር መንገዳችን ኃላፊዎች ደጋግሞ ማሳሰብ ይገባል፡፡ የያዛችሁት አየር መንገድ ‹የኢትዮጵያ› ነው፡፡ የእናንተ አይደለም፡፡ እናንተ በምትፈጥሩት ስሕተት ግን የምትቀጣው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ዛሬ እነ አልጀዚራ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራ ክፉ ነገር ፍለጋ አሰፍስፈው በሚጠብቁበት ዘመን እናንተ ተባባሪ ሆናችሁ ክፉ ዜና የምትሰጡበትን ምክንያት እንኳን እኛ እናንተም የምታውቁት አልመሰለኝም፡፡
አሁን ከዱባይ ወደ ብሩናይ ለመጓዝ በሮያል ብሩናይ አውሮፕላን የመንገደኞች ማስተናገጃ ክፍል እገኛለሁ፡፡ ‹‹ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም›› ይባል ነበር፡፡ እዚህ ግን ፉርሽ ተደረገ፡፡ አየር መንገዳችን ያቃለለንን መንገደኞች የብሩናይ አየር መንገድ ሰዎች ጋብዘውና ተከባክበው ካሱን፡፡ ‹‹ብሩናይ የሚባል ስም ከዚህ ጉዞ በፊት ሰምቼ አላውቅም፡፡ በዙሪያየ የተቀመጡት እስያውያን ናቸው፡፡ ሰውነታቸው ቀጨጭ፣ ዓይናቸው ሰለምለም፣ ልብሳቸው ደመቅመቅ፣ ፀጉራቸው ወረድረድ ያሉ ሕዝቦች፡፡ በአካባቢው ያለሁት አፍሪካዊ እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ከዐርባ ደቂቃ በኋላ እንነሣለን ተብሏል፡፡ እስኪ ቀጣዩን መንገድ ደግሞ ሰላም ያድርገው፡፡
ዱባይ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዐረብ ኤምሬት  

71 comments:

 1. መቼም የመጣውን አስቀምጦ ያልመጣውን መጠበቅ የተለመደ ነውና አላዘንኩበትም፡፡ ሠርግም ላይ፣ ስብሰባም ላይ፣ ጉባኤም ላይ፣ ግብዣም ላይ በሰዓቱ አክብረው የመጡት የዘገዩት እስኪመጡ እንዲጠብቁ በሚደረግበት ባህል ውስጥ ስላለን የሚገርም አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 2. ዳኒ አንተም እያየህ ከመፃፍ እኛም ጉዳችንን እየሰማን ከመናደድ እግዜአብሄር ያውጣን ፡፡

  ReplyDelete
 3. "‹አይ አየር መንገዳችን፤ እነ ክበበው ገዳ የት ሄደው ነው እርሱ እንዲህ ያለ ቀልድ የሚቀልደው› ብዬ ተገረምኩ፡፡ ማንን እናናግር፡፡ በኋላ አንድ የአውሮፕላን ማረፊያውን ፖሊስ አገኘነውና ችግራችንን ስንነግረው በፍተሻ ማለፊያው በኩል አድርጎ ወደ ምድር ቤት ወሰደን፡፡
  ምድር ቤት ወርደን የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስኮት ስንደርስ እነርሱ ምን አለባቸው አራት ሆነው ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ምናለ አንዳችሁ እንኳን እዚያ ተገኝታችሁ ብትረዱን›› አልኳቸው፡፡ ‹‹እገሊትኮ ነበረች›› አሉን፡፡ ትኬታችንን ተቀብለው አየት አደረጉና ‹‹አሁንማ ረፍዷል ቀጣይ አውሮፕላን ካለ እንይላችሁ›› አሉን፡፡ ለእነርሱ እየተባበሩን ነው፡፡ ስሕተቱን የፈጸሙት እነርሱ፣ የዘገዩት እነርሱ የምንቀጣው እኛ፡፡ እንዴው ግን እስከ መቼ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድና የደንበኞቹ ግንኙነት የባላባትና የጢሰኛ የሚሆነው? በባላባቶች ፍርድ ‹‹ምን ባላባት ቢያጠፋ ጢሰኛ ይክሳል›› ይባላል፡፡ አየር መንገዳችንም እንዲህ ሆነብንኮ፡፡ ‹‹ይቅርታ፣ እስኪ ዐረፍ በሉ፣ ችግሩን እንፈታዋለን›› ከአማርኛችን ውስጥ የሌሉ ይመስል ምነው ከአንደበታቸው አልወጣ አሉ?"

  Girum Yehone Akerareb new. Betam tedesichebetalehu. Bertalin wondimachin Dn. Daniel. Yemiqetilewun kifl begugut entebiqalen

  ReplyDelete
 4. ‹እናንተ ባጠፋችሁ ቁጥር እኛ መቀጣት አለብን?

  ReplyDelete
 5. ለነገሩ ብዙ ጊዜ በሀገሪቱ የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና አልተገረምንም፡፡

  ReplyDelete
 6. የያዛችሁት አየር መንገድ ‹የኢትዮጵያ› ነው፡፡ የእናንተ አይደለም፡፡ እናንተ በምትፈጥሩት ስሕተት ግን የምትቀጣው ኢትዮጵያ ናት፡፡ ዛሬ እነ አልጀዚራ ስለ ኢትዮጵያ የሚወራ ክፉ ነገር ፍለጋ አሰፍስፈው በሚጠብቁበት ዘመን እናንተ ተባባሪ ሆናችሁ ክፉ ዜና የምትሰጡበትን ምክንያት እንኳን እኛ እናንተም የምታውቁት አልመሰለኝም፡፡

  ReplyDelete
 7. ለነገሩ ብዙ ጊዜ በሀገሪቱ የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና አልተገረምንም፡፡ ‹መሣፈሪያ አዳራሹ ውስጥ መቀመጥ ሰለቸን› ያልናቸው ይመስል አውሮፕላኑ ውስጥ አንድ ሰዓት አስቀመጡን፡፡ ደግነቱ አብራሪው እየደጋገመ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ ከተለያየ ሀገር የሚመጡ ተሸጋጋሪ መንገደኞች እየተጠበቁ መሆኑንም ይነግረናል፡፡ መቼም የመጣውን አስቀምጦ ያልመጣውን መጠበቅ የተለመደ ነውና አላዘንኩበትም፡፡ ሠርግም ላይ፣ ስብሰባም ላይ፣ ጉባኤም ላይ፣ ግብዣም ላይ በሰዓቱ አክብረው የመጡት የዘገዩት እስኪመጡ እንዲጠብቁ በሚደረግበት ባህል ውስጥ ስላለን የሚገርም አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 8. ዳኒ አንተም እያየህ ከመፃፍ እኛም ጉዳችንን እየሰማን ከመናደድ እግዜአብሄር ያውጣን ፡፡

  ReplyDelete
 9. ዳንኤል እንደምን ነህ )

  ምነው ጥሩ ባህላችንን ለዓለም ህዝቦች እናሳይ
  ሲባል መጥፎ አመላችንን በአደባባይ ለትምህርት ቤት ክፍያ፤
  ለመብራት፤ ለውሀ፤ መታወቂያ ለመውሰድ ተሰልፈን ስናበቃ
  በቃ ነገ ኑ ወይም ይሔኛው ሰልፍ ቀርቶአል ተበተኑ
  ሩጡ ስንባል መጨረሻ የነበረው ሰው አጋጣሚውን ተጠቅሞ
  በጉልበት ወደፊት ሲሰለፍ እንዲሁም በልጅነታችን የነበረውን እቃቃ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ
  ብለን ሮጠን በየቤታችን አንደምንገባው ማለት ነው፤፤
  ስለዚህ በእናትዋ የለመደች ባማትዋ ሆኖብን ነወ፤፤

  ወለተ ሚካኤል

  ReplyDelete
 10. Only left!
  If the once graceful and loyal to his customer Airline of Ethiopia is in declining state, then whats up, what is remaining for us and our country which is not destroyed by tplf?

  they may form tplf airline sooner or latter with the billion money they are accumulating using the looter machine EFFORT!

  ReplyDelete
 11. ዳኒ እግዚአብሄሔር በሰላም ወደ አሰብክበት ያድርስህ
  ለ2ኛ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥምህ እግዚአብሔር ሀገርን ከሚያሶቅስ ስራ ይጠብቀን፡፡
  መነጋገር፣ መወያየት ስለሚጠቅም ከብዙ አስተያየት ሰጪዎችም ብዙ እንማራለን፡፡መልካም ጊዜ ይሁንልህ፡

  ReplyDelete
 12. ውድ ዳኒ፤
  ከሁሉም በፊት መልካም በረራና ሰናይ ጊዜ ይሁንልህ!
  ያነሳኸው ርዕሰ ጉዳይ በተደጋጋሚ የምናዬውና (እንደኔ) ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ የደረሰ ይመስለኛል፡፡ እኔም ከአዲስ አበባ ወደ ሌላ የአፍሪካ ሀገር ለመብረር የኛው አየር መንገድ በመዘግየቱ ቀጣዩን በረራ በማጣቴ ምክንያት ደቡብ አፍሪካ (ጆሃንስበርግ) ኤርፖርት ወለል ላይ አንድ ቀን ተኝቼ ማደሬን ስገልጽልህ እጅግ በማዘን ነው፡፡ ያኔ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የሰጡኝ መልስ አጅግ የሚያሳዝንና ኢትዮጵያዊነቴን የሚፈታተን ነበር - ‹‹የኛ ችግር አይደለም›› - ነበር ያሉኝ፡፡ ይህን ምላሽ ከጊዜ በኋላ በሌሎች ችግሮች ዙሪያም ተመሳሳይ መፍትሄ አልቦ ምክንያቶች ሲሰጥ ስለማይ ሀገራችን እየሄደች ያለችው ‹‹በምን ታመጣለህ አቅጣጫ ይሆን?›› አስብሎኛል፡፡ ይህንስ የሰይጣን ጆሮ አይስማ!
  እባካችሁ አትፍረዱብኝ! የመፍትሄ ነገር እንደጉም አልጨበጥ ሲለኝ እያየሁ ስለሆነ ነው፡፡ በምሳሌ ላስረዳ፤
  1. በበጋው ላይ መብራት እየጠፋ ሲያስቸግረን ጥያቄ በማብዛታችን የመብራት ኃይል ባለስልጣን በአንድ ለናቱ ቲሌቪዥናችን ብቅ ብሎ ‹‹የውሃ እጥረት ገጥሞን ነው›› አለን፡፡ እኛም በውሃ ማማ ላይ ተኝተን እንቅልፋችንን የምንለጥጥ መሆኑን ጠንቅቀን ብናውቅም ‹‹ይሁን እውነት ሊሆን ይችላል›› አልን፡፡
  2. እንዳይደርስ የለምና ክረምቱ መጣና በውሃ አጥለቀለቀን፤ መብራት ግን እንደ አንዳንዶች አገላለጽ የናይት ክለብ መብራት እስኪመስል ብልጭ ድርግም ማለት አበዛ፡፡ ይህን ጉዳይ ወንድሜ ዳኒም ከዚህ በፊት ትንሽ ነካክተኸዋል፡፡ እኛም መጠየቅ የማይታክተን ህዝቦች (የእግዜር በጎች) ነንና ጩኸት አበዛን፡፡ በበጋው ያጽናኑን ሰውዬ ብቅ ብለው ‹‹የክረምቱ ዝናብ/አየር ጸባይ አስቸግሮን ነው፤ ይስተካከላል›› አሉን፡፡ ይህኔ ነው መሸሽ! በጋ የዝናብ እጥረት፤ ክረምት ዝናብ የሚያስተጓጉለው የመብራት መሰረተ ልማት ያላት ሀገር ማናት ብንባል አሁን የ1ኛ ክፍል ፈተና ለማለፍ የሚያስችል በቂ እውቀት አግኝተናል፡፡ ግን ግን ጎበዝ ይህ ነገር ያቀባብራል? አረ ነውር ነው! አሳፋሪ ነው! እኒህ ሰዎች ወይ ወደ ትምህርት ቤት ይላኩ፤ ወይም ወንበር ይቀይሩ! እኛ ሀገር እኮ ወንድሜ ዳኒ እንዳለው ‹‹የመቀመጫ ለውጥ ነው የሚመጣውና›› አይገርመንም! ‹
  3. ቀደም ሲል የሞባይል ስልክ መደወልና መቀበል እጅግ በማስቸገሩ ለባለሙያዎችና ባለስጣኖች አቤት አልን፡፡ የሰጡን መልስ ‹‹ያለን ኔትዎርክ ከህዝቡ ፍላጎት ጋር ስለማይመጣጠን በቅርቡ እንፈታዋለን›› ተባልን፡፡ እሺ እንጠብቃለን ግዴለም አልን፡፡ ይኼው ሁለት ዓመት አለፈው፡፡ ባሰበት እንጅ ለውጥ የለም!
  4. ሰሞኑን (ትላንት) በዚህ ሞባይልና ኢንተርኔት ጉዳይ መቸገራችንን እጅግ ዘግይተው የሰሙ የሚመስሉ የቴሌ ባለስልጣን (ህዝብ ግንኙነት) በተለመደው አሰልቺ መስኮት ብቅ ብለው ‹‹ረዣዥም ህንፃዎች ስለተሰሩ የስልክ መቆራረጥና መጥፋት አስቸገረን፤ 3 ወር ታገሱን እንፈታዋለን!›› አሉን፡፡
  እጅግ አስደንጋጭ ነገር ነው! በዝናብ/በነፋስ የሚጠፋ መብራት፣ በረዣዥም ህንፃ የሚቆራረጥ ኔትዎርክ! ወቼ ጉድ፤ ይህች አገር የምትመራው በይትኛው የእውቀት መስክ ይሆን! ግን በአዲስ መስመር ጥያቄ ልጠይቅ፤
  እኛ ኢትዮጵያውያን መቼ ነው ጥያቄያችንን የተማረ ሰው የሚመልሰው? የተማረ ሲባል ወይ በእ/ብሄር የእውቀት መስኮት የተከፈተለት፤ አልያም በሣይንስ የበሰለ ማለቴ ነው፡፡ እጅግ አስፈሪ ነው!
  እኒህ የቴሌው ሰውዬ የኔትዎርክ አንቴናዎችን በህንፃዎች አናት ላይ እንተክላቸዋለን ነው ያሉት? ባለ ህንፃዎች ምህረቱን ይላክላችሁ! እንደ ጀሞ ኮንዶሚኒዬም ህንፃዎቻችሁ እንዳይናዱ እስኪ በሣይንስ እውቀት ያለው ሰው አፈላልጉ፡፡ ቴሌና መብራት ኃይልን ማመን ወይ ‹‹ቀብሮ›› ወይ ‹‹አስሮ›› ነው ያለው ማን ነበር?
  መልስ ያላገኙ፤ የተማረ የሚሹ ችግሮቻችን የትየለሌ ናቸው! ወንድሞቼ ሆይ ብታምኑም ባታምኑም የተሸከምነው ችግር የሰማይ ስባሪ ያክላል፤ የሚፈቱት ግን የት እንዳሉ ውሉ ጠፍቶብናል! የተማረ ያለህ! የእውቀት ያለህ! መጮህ ችግር ይሆን? እባካችሁ ለእግዜር እንጩህ፤ ማን ያውቃል የችግራችን ተራራ እንደ ኢያሪኮ ግንብ ይናድ ይሆናል!
  ዳኒ በሠላም ይመልስህ! ግን የእውቀቱን ነገር አደራ፤ ከቻልክ ከአገር ጥግ ይዘህልን ና! አንተ ሰው ከእውቀት ጋር ቶሎ ና! እኛ መሄጃው ጠፍቶብናል፡፡
  ምንጊዜም ያንተው
  ‹‹ብሶተኛው››

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewent belehale/shale Besotegnawe.

   Delete
  2. i agree , it seems to me that much of our authorities are ignorant of knowledge management in today's knowledge economy.

   Delete
 13. አንተ ሰው የመርካቶ አራዳ ነበርኩ እንደ ሞኝ ብቻዬን የምታስቀኝ ለምንድን ነው?? ሁሉን ቢናገሩ ሆድ ባዶ ይቀራል እንዲሉ ቁም ነገሩን አንብቤ ደስ አለኝ። እማ ሆይ ቦታ ጠበቦት ወይ እንዲሉ የሴትየዋ ትረካ እንደ ሞኝ ስላሳቀኝ እጅግ አኩርፌያለሁ! ሰላም !

  ReplyDelete
 14. "... ደግሞ ስፋቷ ለሚኒ ባስ ታክሲ የመጨረሻው ወንበር እንጂ ለአውሮፕላን ወንበር የሚሆን አይደለም፡፡ ከመደገፊያው ተርፎ እኔ ጋ እየመጣ አስቸገረኝ፡፡...እኔን መከራ ያሳየኝ ዕንቅልፏ አይደለም፡፡ እየተረፈ የሚመጣው ሰውነቷ አልበቃ ብሎ እንደ ፔንዱለም ስትወዛወዝ ትከሻየ ላይ እየመጣች ዘፍ የምትለው ነገር ነው፡፡"

  ይህን ንግግር ዳንኤል አለ ቢሉኝ አላምንም ነበር። በሴትዮዋ ውፍረት መሳለቅህ በጣም ትልቅ እና ካንተ የማይጠበቅ ስሕተት ነው። አንድ ነገር ማወቅ ያለብህ ላንተ በግለሰቦችም ሆነ በማህበራዊ እሴቶች ላይ ለመሳለቅ ትንሽም ቢሆን እድል የለህም። በተረፈ አየር መንገዱ የሚሰማ ድርጅት ከሆነ ጥሩ ሒስ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mr. Maranatha this isn't your theology class. If you r sufferin from obesity just come&join my gym for free.

   Delete
  2. Your Right I did not like the comments on her physical character

   Delete
  3. እኔም ሴትየዋን የገለጸበት አገላለጽ የዳንኤል አልመስልሽ ነው ያለኝ

   Delete
  4. "Theology", "Obesity". ይህን አይነት የሞራል ጥያቄ ቲዎሎጂ ወይም ሐይማኖታዊ ከሆነብህማ በጣም ያሳዝናል።

   ከይቅርታ ጋ ያንተ ጂም አያስፈልገኝ።

   Delete
  5. Dear Maranata, I share your comment. Better not to write like that, but it can be expressed politely about the problem. Last but not least is your name, it is not organic. It is poorly taken from Bible, it does not fit your comment too. It looks fanatic religious person with very little religious knowledge. You better change it.

   Delete
  6. Zemenachenen hulu netebun nager eyawetan kumenagerun wdahula yetibeb gyta tibaben yeseten.Dani selamu hulu kante yehun ,you did great appreciate it.

   Delete
  7. I do not see any discourtesy in my comment. I am not against Daniel. I like his critics.

   My name is not only a name; it is a faith and I am not changing it. I am sure you have a Hebrew name, you are either Eliyas or Ermiyas. Does it make you a fanatic?

   Delete
  8. ወዳጆቼ ማራናታ የተናገረችው ወይንም የተናገረው የመሰላትንና አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው። መጀመሪያ ሴትዮዋ ፈልጋ ያላመጣችውን ውፍረትና ማንኮራፋት ዳኒ እንደ መወረፍ አድርጎ ማስቀመጡ እኔንም ገርሞኛል። ወንድሜ ደግሞ እኔ ጅም ነይ ላልከው ይህ ያንተ ጅም ማስተዋወቂያ ስአይሆን የዳኒ ብሎግ እና የእኛ ግልጽ የሆነ መወያያ መድረክ ነው።

   ሰው የምንፈልገውን ሰው አይናገርብን ማለት ያሰው ቢሳሳት እንኳን እደተሳሳተ ይኑር ብሎ እንደመፍረድ ነው...

   Delete
  9. lek bilewal Maranata

   Delete
  10. ዳንኤል ስለሴትየዋ ውፍረት የገለጸበት ኣገላለጽ ከእሱ እንደ መምህር ከምንቆጥረው ሰው ኣይጠበቅም። እኛ እንኩዋንስ እንደነ ዳንኤል ካሉ ጸሃፊያን ሰምተነው ይቅር አና የሰውን ስብእና ስለማክበር ግድ የሌለን ብዙዎች ነን።

   Delete
  11. sewoch ebakachu tiru tiru negere temelketu . Dont be a Pessimist . ke mulu gane mare tinesh tinegn agegnetachu marun alibelam betelu mogn yasegnachehual esti sele bego negere eneweyay

   Delete
 15. Dani I wish you a nice journey.Ethio Airlines please take necessary action.Dani I will go to China(Beijing)next week.I hope I may suffer like you any way thanks Dn.Dani.
  God bless you.

  ReplyDelete
 16. በሰላም ያድርስህ ዲን ዳንኤል
  እንደውም አንተስ ያየኸው የውጭ ሀገሩን በረራ ነው(አየር መንገዱ ትኩረት የሚሰጥበትን) የሀገር ውስጡ በረራ አገልግሎት አሰጣጥማ ምን ያህል እንደሆነ መግለፅ ያዳግታል...

  ReplyDelete
 17. Dani, I live in North America, and I get tired off specially in our community. We live in most developed nations, but no one seems want to change his/her attitude about time.

  If you invited to Ethiopian/Eritrean wedding, it is common for brides to arrive after 3 or 4 hours. In most wedding there are many guests from different different. These fernj people wait for a little bit then they leave. It is a sham for our community. People laugh at our culture. I don't understand why not the church or mosques work on this issue.

  It is a common problem in church too. I noticed only Kidassie starts on time. If you have sebeka gubaye or Sunday school meeting or gubaye, sometimes it gets started after one hour. Because disgraceful culture a person like me forced to wait for hours, and damage our relationship and precious time.

  I think the solution is to wait a maximum of 15 to 30 minutes then LEAVE, don't wait any more. This will force people to change their attitude. Then between 1 to 5 years our country will be as developed nations for being on time. BTW our church tradition reflects how our father used consider being on time a mandatory thing. Kedassie and Nigs celebration used to be started on time every day based on church schedule.

  ReplyDelete
 18. watch out brother about fat poeple they will give you hard time.think about there is alot like maranata they will fill about their body.take care man.

  ReplyDelete
  Replies
  1. For the record, I am not suffering from Obesity or overweight. It just seemed devoid of any moral virtues to write about the woman that way. If we cant accept it, we arent any different than the materialist media. You could argue that obesity is not healthy. How unhealthy it is then to make fun of it!

   Delete
  2. Good point, maranata

   Delete
  3. I normally disagree with Daniel when he exaggerates on religious issues. But, that doesn't mean he lack writing skills. Especially, he is well gifted to describe what he observed. There is no moral values failure when he describe the experience on board Ethiopian Airlines. Neither he insulted the obese. He just helped us visualize what happened next seat. This has nothing to do with being healthy or unhealthy, nor woman. Sometime we want to overstep by complicating minor issues.

   Delete
 19. EGZIABHER YIBARKEH

  ReplyDelete
 20. eiyawaza ye miyastemir dinq tsihuf! be cher yadirsih kb

  ReplyDelete
 21. EHTEWEYEM WENDEME MARANATA:
  ene yemidenqegn sew mehon yemilewen teresutalachehu yehe agul MENFESAWINET asfelagie aydelem D.n Daneal gazetegna new abeqa endet adrego yetsafew!!!!!! yegna sera anbebo qumnegerun meredat new.
  keahun befit daneal lemen endieh yetsfal belew bezu sinageru anbebyalehu HULACHENENEM YEMETEYQEW TEYAKE bemezemerachen weym betekerestian bemehedachen demoz yemiasgenenen sera metew yelebenem selezieh ahunem egziabher besetew setota(bewer, begundesch) eskalkeleden deres yehe hatyat weyem sereat matat aydelem!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትርሲተወልድ እስከ ዛሬ ዳንኤል ጋዜጠኛ መስሎሽ ጽሁፎቹን ስትከታተይ ከነበረ በጣም ተሳስተሻል። የገፁን መግቢያ አስተውለሽው ከሆነ 'ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፥ባህል፥እምነት፥ፖለቲካና ትውፊት ምልከታዎች ይቀርቡበታል'ይላል እንጂ ፌዝና ቧልትን ይጨምራል አይልም።

   አጉል መንፈሳዊነት ላልሽው፥ እኔ ከመንፈሳዊነት አንጻር አልነበረም የተናገርኩት፥ ከሰባዊነት እንጂ።

   Delete
  2. maranata getere sewe nek meselegn

   Delete
  3. 'አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል።'

   I have to admit that such moral values reflect my origin from geter.

   Delete
  4. tadiya lemin geter yale aquam tiyezaleh

   Delete
 22. ዳኒ፡ መቼም፡ የኢትዮጲያ፡ አየር፡ መንገድን፡ ደህና፡ አድርገህ፡ ታውቀዋለህ። ቋሚ፡ ደንበኛቸው፡ በመሆንህ፡ ማለቴ፡ ነው። እኔ፡ የምኖረው፡ አየር፡ መንገዳችን፡ በሳምንት፡ የስድስት፡ ቀናት፡ በረራ፡ ከሚያደርግበት፡ የአፍሪካ፡ ሀገር፡ ሲሆን፡ ትናንትና፡ ድንገት፡ ካንዱ፡ የሀገሩ፡ ዜጋ፡ ጋር፡ ካሽ፡ ማሽን፡ አጠገብ፡ ተራ፡ እየጠበቅን፡ ሰላምታ፡ ተለዋወጥን። ቀጠለናም፡ ከየት፡ እንደሆንኩ፡ ሲጠይቀኝ፡ በኩራት፡ "ከኢትዮጲያ" ስለው፡ "ኢትዮጲያን አልወድም" ብሎ፡ በቁጣ፡ ሲጮህብኝ፡ ያን፡ ሁሉ፡ ኩራቴን፡ ወደኋላ፡ ሰበሰብኩና፡ እንዲህ፡ ያስከፋው፡ ምን፡ እንደሆነ፡ በተራዬ፡ ጠየኩት። እርሱም፡ የኢትዮጲያ፡ አየር፡ መንገድ፡ ያደረሰበትን፡ በደል፡ የአየር፡ መንገዱን፡ ማኔጀር፡ የሚያናግር፡ እስኪመስል፡ ድረስ፡ ይዘከዝክልኝ፡ ገባ። ጉዳዩ፡ በዲሴምበር፡ 2012 የተሰረዘ፡ ቲኬት፡ እስካሁን፡ ድረስ፡ ሪፈንድ፡ ሳይደረግለት፡ በመቆየቱ፡ ምክንያት፡ የተከሰተ፡ ችግር፡ ሲሆን፡ ወደመኪናው፡ ወስዶ፡ መረጃ፡ የሚሆኑትን፡ የኢ-ሜይል፡ መልዕክቶች፡ እያሳየኝ፡ ሲንጨረጨር፡ ሳየው፡ ከልቤ፡ ነበር፡ ያዘንኩት። በመጨረሻም፡ የትልቅ፡ ድርጅት፡ ሲ.ኢ.ኦ. እንደሆነና፡ አየር፡ መንገዱን፡ ለመክሰስ፡ እየተዘጋጁ፡ ስለመሆኑ፡ ሲገልጽልኝ፡ እንዳቅሜ፡ ሃገራዊ፡ ግዴታዬን፡ ለመወጣት፡ የኤሪያ፡ ማኔጀሩን፡ ስልክ፡ በመስጠትና፡ ይህንኑ፡ ግለሰብ፡ አግኝቶ፡ (እስካሁን፡ እንዳላገኘው፡ ስለገለጸልኝ) ቢያናግረው፡ በቶሎ፡ መፍትሄ፡ ሊያገኝ፡ እንደሚችል፣ ("መቼም ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃ ለማግኘት የሚታወቅ መንገድ (system) ስለሌለ የሚታወቅ ሰው መፈለግ ነው" የሚለውን፡ ዲያቆን፡ ዳንኤልን፡ ትክክለኛ፡ አባባል፡ መሰረት፡ በማድረግ) ስለማኔጀሩ፡ ቀና፡ ስብዕና፡ በዝርዝር፡ ለማስረዳት፡ ሞከርኩ። ይሄ፡ ጥረቴ፡ ውጤት፡ ያመጣ፡ አያመጣ፡ እንደሁ፡ የማወቂያ፡ መንገዴ፡ እጅግ፡ ያነሰ፡ ቢሆንም፡ በዚሁ፡ ተሰናብቼው፡ ሄድኩ።

  እስቲ፡ ለድርጅቱ፡ መሪዎች፣ እና፡ ለሠራተኞቹ፡ መልካሙን፡ ያመላክትልን።

  ReplyDelete
 23. ዳኒ በጽሑፍ ውስጥ ብዙ ነገሮችን እድንመለከት አድረገህናል፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ገመገምን፣ የሰዎችን የግል ባህሪ ተመለከትን፣ በዋነኝነት ደግሞ አየር መንገዳችንን ችግሮች እንዲንመለከት ስላደረክ እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡
  እኔ ግን በአየር መንገዱ ላይ ይህ ብቻ ችግር አይደለም በተለይ በዋነኝነት HR ላይ ያለው ችግር ለማን አቤት እንደሚባል እንኳን በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይለጉዳይ ነው፡፡ለስሙ መስታወቂያ አውጥቶ የሚቀጠሩት ግን ቤተሰብ ያለቸው ነው፡፡ ያለበቂ ምክንያት አላለፋችውም የሚባሉት ሰዎች ቁጥራቸው የበዛ ነው፡፡ ለማን እንደሚጠየቅ እንኳን ሲያነጋግሯቸው መልስ የሚሰጥ አካል የለም፣ በፅዳት ስራ የተሰማሩትን ልጆች እቃ ሰረቃችዋል በለው ችግሩ HR መፍታት ሲገባው በፖሊስ ጣቢያ የሚመላለሱ ልጆች ባገራቸው መስራት ብረቅ ሆኖባቸው ያሉት ቤት ይቁጠራቸው፡፡ አየር መንገዱ ለዚህ መድረስ አስጠዋፅኦ ያደረገው እኮ ጨዋው የኢትዩጰያ ሕዝብ ነው፡፡ በሕዝብ እና በሀገር ላይ መቀለድ ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ለማን ይከሰሳሉ???? ለአሜሪካ ፍረድቤት የአገራቸውን ፍረድ ቤትማ የናቁ ናቸው፡፡ እድሜ እና ጤና ጌታዬ ስላሴ ይስጡህ፡፡

  ReplyDelete
 24. አየር መንገዳችን ካወቀበት ራሱን የሚያስተካክልበት ሂስ ይመስለኛል፡፡ ክብር መስጠት ከራስ ሲጀምር ደስ ይላል፡፡

  ReplyDelete
 25. ዲ/ን ዳንኤል ፅሁፎችህ ሁሌም በዉስጣቸዉ የዉስጥህን ጩኽት : መሆን ሲገባን ያልሆነዉን ማየት ሲገባን ያላየነዉን ስለሚነግሩኝ በጉጉት እጠብቃቸዋለሁ::እንደ መንፈሳዊነትህ ሰዎች ሃይለቃልና ተግሳፅ እንጂ ቀልዶች ላይጠብቁ ይችላሉ:: አንተ ግን የዉስጥህን ብስጭትና እሳት ለማቀዝቀዝ የምትጠቀምባቸዉ እንጂ ለማፌዝና ለማሳቅ ብቻ የምትጠቅምባቸዉ ባለመሆናቸዉ ዘና ብለን የፅሁፎቹ አላማ ላይ እንድናተኩር አድርጎናል:: ብዕርህ ይባረክ

  ReplyDelete
 26. እኔን መከራ ያሳየኝ ዕንቅልፏ አይደለም፡፡ እየተረፈ
  የሚመጣው ሰውነቷ አልበቃ ብሎ እንደ ፔንዱለም
  ስትወዛወዝ ትከሻየ ላይ እየመጣች ዘፍ የምትለው
  ነገር ነው፡፡ ሴትዮዋ የመጣችው ‹ሶሪ› ከሌለበት ሀገር
  ነው መሰለኝ ትከሻዬን ገጭታው ስትመለስ ከጥቁሩ
  ፊቷ መካከል ብልጭ የሚል ባለ ቀይ ድድ ጥርሷን
  ብቻ አሳይታኝ ‹ካለፈው የቀጠለ› ብላ ወደ ዕንቅልፏ
  ትገባለች፡፡ ትቆይና ደግሞ ክላሲካል

  ‹‹ፉርርርርርር›› የሚል የኩርፊያ ክላሲካል፡

  ReplyDelete
 27. ዳኔ ከሔድክበት በሰላም ይመልስህ። በርታ!!!

  ReplyDelete
 28. ዳኒ ክፍል አንድ የጉዞ ማስታዎሻህን አንብቤዋለሁ ከጉዞህ ጋር ተያይዞ ከአጋጠመህ ችግር በመነሳት በኢትዮጵያ አየር መንገድ መነሻነት ለአየር መንገዱና እኛም እንድንማርባቸው ማህበራዊ ሂሶችን ለማቅረብ ሞክረሃል ጥሩ ሂስ ነው ሆኖም ስትጽፍ ከማህበራዊ ሰውነትህ ባሻገር መንፈሳዊና የስነ ጽሁፍ ሰውነትህን አትርሰው በማስታወሻህ መነሻ የጠቀስካት ወፍራም ሴት ለአቀረብከው ማህበራዊ ሂስ ምንም አጋዥ አልነበረችም እስኪ እርሷን የገለጽክባቸውን አንቀጾች አውጥተህ የፅሁፍህን ፍሬ ሃሳብ መጓደልና አለመጓደል ተመልከተው እንደኔ እንደኔ በመንፈሳዊና በስነጽሁፍ አይን ሳየው የሴትዮዋ ቦታ ሰጥተህ መግለጽህ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ አይሎብኛል ቢቻል አንተ በምትጽፋቸው መጣጥፎች ላይ መንፈሳዊነት ከማህበራዊነትን ጋር ተዋህደው እንጂ ተቃርነው ባይቀርቡ ጥሩ ይመስለኛል አንተ መንፈሳዊ ሰው ነህ አንተ ማህበራዊ ሰው ነህ ሁለቱ በአንተ ውስጥ ተስማምተው ይኖራሉ ጽሁፍህም አይህን እውነት በጠበቀ መልኩ ቢወጣ የተሻለ ይሆናል ምናልባት ስራ የሚበዛብህ ከሆነ ጽሁፍህን ለአንድ እውቀቱ ላለው ወንድም ወይም እህት አስቀድመህ ብታሳየው ጥሩ ይሆናል ካለበለዚያ ብዙዎችን እጠቅማለሁ ስትል በትንሽ መንፈሳዊ ባልሆነ ቃላት ብዙዎችን ታሸሻለህ ሰላም ጉዞ ይሁንልህ

  ReplyDelete
 29. Thanks Daniye, ha ha ha ho ho ho, yesetyowa, betam new yasakegn. I was imagining ur & her situations.

  ReplyDelete
 30. ግነቱ ባይበዛ ምናለ
  አውስትራሊያ- የምድር ጥግ- እንዴት ተብሎ! እነሳን ሆዜ፣ እነ ዴቪስ፣ እነ ሳንፍራንሲስኮም አልተባሉም
  ከወንበሩ የተረፉ፣ የኩርፊያ ክላሲካል፣ በቀኝ ትከሻ በኩል ዘፍ ለምትል የሚጸለይ ፀሎጽ…- ለማንበብ የሚሰቀጥጥ
  ዳኒ ሙት አንዳንዴ ጭሰትህ እየቆየ ጭረት እየሆነ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. መሳቂያ... ይህን ሁሉ አገር መዘርዘርህ አገር አዋቂ መሆንህን ለማስረዳት ነው?

   Delete
 31. Dani, I couldn't stop laughing. You made my day. GOD bless you.

  ReplyDelete
 32. Dear Daniel

  Excellent way of writing the problem of Our Ethiopian Airlines, Here is my situation, I went to Ethiopia to bring over my wife using Brunai Airways connected to Ethiopian Airlines, The Brunai Air ways treat u nicely, when I got to Ethiopian airlines it was ok, but the problem started when I tried to out from Ethiopia. The first flight cancelled, again the second flight cancelled finally the third one succeed, it messed up all our connected flight and slept on lounge of Dubai, after taking Brunai Airways finally I arrived my destination, vowed for my self never ever use Ethiopian Airlines. Sorry to say that I love my country and airlines but can't help doing business this way. They have to listen to the customers and take measures otherwise they going to loose good customers.

  Good Critics for the Airlines if they use it.they benefit from that.

  Daniel, may GOD bless u, Pls make a copy of your preaching on DVD, The Australian one.

  GOD be with u. DINGILE Titebkeh

  ReplyDelete
 33. It is funny that this country has gotten a funny proliferation of "men" whose fun profession is making more fun to their funny pocket than to the fun-full society. That the proportion of men who "say" fun is very funnily larger than that of those who actually produce fun is funnily funny. The fun lies on the fun that the fun is funnily funning on the fun that is not funnily funning!

  ReplyDelete
 34. እኔ ምለው አይር መንገዳችን እንደዚህ ደንበኛ የሚይዝ ከሆነ፣ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የለኝም የሚለው እንዴት ስለሆነ ነው?

  ReplyDelete
  Replies
  1. tesafarin bemagulalat yihonala...

   Delete
 35. Hay Danie,
  i sometimes prefer the land transport because of the problems of Eth. Airlines services! any how i am waiting you to hear the second part of another surprising!!
  i wish you a happy journey!!!!

  ReplyDelete
 36. ውድ ማራናታ፣
  ዳንኤል የሴትዮዋን ውፍረት የገለጸበትን መንገድ ”ትልቅ እና ከእርሱ የማይጠበቅ ስህተት” አንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንዴት ”ስሕተት ” እንደሆነ ግን አላብራሩትም፡፡ ምናልባት እንደ አንዳንዶች ዳንኤልን መንፈሳዊ ብቻ እንዲሆን መፈለግ ይሆን? እንደሱ ከሆነ አጥጋቢ የ”ስሕተት” መንስኤ አይመስለኝም፡፡ ዳንኤል እኮ በጉዞው ላይ በሴትዮዋ እንቅልፍ እና ተያያዥ ድርጊቶች ምክንያት የደረሰበትን መንገላታት እና በወቅቱ የተሰማውን ስሜት በተዋዛ መንገድ ብቻ ነው የገለጸው፡፡ መሳለቅ ይህ አይደለም፡፡ ስሜቱን ብቻ ገለጸ፣ በቃ!
  እርስዎም ሆኑ እኔ፣ ወይም ሌላ ሰው በዳንኤል የደረሰው ቢደርስብን ሳንበሳጭ፣ ወይም ሴትዮዋን ሳናማርር አንቀርም፡፡ የባሰበት ወደሌላም ነገር ይሄዳልኮ! እኛ የሚሰማንን ስሜት ዳንኤል እንደዚህ አድርጎ ሲገልጸው ”ትልቅ ስህተት” የሚሆንበት ምክንያት አልታየኝም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Asnake

   Let alone using that kind of expressions, calling someone fatty is a hate crime.

   http://www.telegraph.co.uk/health/healthnews/9297496/Calling-someone-fatty-could-become-a-hate-crime.html

   Delete
  2. Dear Anonymous,
   It seems to me like you haven't fully read or understood Telegraph's piece. First of all, calling someone “fatty” isn't a hate-crime yet. The statement you quoted from Telegraph is a recommendation from a report by “the All Party Parliamentary Group on Body Image and the central YMCA” to the British Parliament. Secondly, this recommendation highlighted the scale of the problem of “appearance-based discrimination,” and there hasn't been any kind of discrimination sighted in Daniel’s article. It’s just a description of a person’s physique.

   Delete
 37. ሰላም።

  እኔ በአለፈው ሳምንት ለ5 ሰአት ዘግይተን ነው የተነሳነው። የሚገርመው ግን አማርኝ የሚሰማው አለ ብለው ሳይጠረጥሩ ቀስ ብላክ አስገባቸው እንዳይነቁ ጊዜ ወስደክ ሲል ሰማነው እና ሄደን አነገርነው። ይቅርታ እንኳ አላለኝም በማን አለብኝነት ጥሎኝ ሄደ። One of the foriegn passenger said this" Fucked up ethiopia and ethiopian i will never get back to u. I saw who you are and how you think. At least the others are honest and tell you the reason for the delay in flight. I saw the country in your eyes and i dont think there are others better than you". I just heard his words and cant resist them. I just go to the passenger and say sorry on behlaf of the air lines and told him all. But the funny thing is that i dont think the ethiopian facilitator in the air port do properly listine english cause he didnt feel anything and come back to him. I realy shame of being an ethiopian on that flight date. All the words comes out of the passengers really hears our airlines and the country as a whole.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I think the the CEO of ET has to take appropriate measures as a leader to correct this corrupted organizational culture.

   Delete
 38. Enkwan Reyna metak Australia yetehadso gore mmesebaseby eyehonech newena ebakehen yemttsedabeten meftehe felegelat.

  ReplyDelete
 39. Last year I used Ethiopian airlines from Europe to Addis & air Canada from Canada to Europe. My experience was with ET was good. For my surprise ET employees helped and they took care off my 8 month child. I really appreciated their help.

  As many people commented here the company has to give his employees a customer service course and need to take correct measures on the bad apples. Because bad apples can be the reasons for the company time bombs.

  ReplyDelete
 40. Dn.Dani Egzabher ybarkh ewnte kmnager aunem atbozen ayer mngdacen yezara 7 amet le extra lagage ktnsubt state 135 dollar ke Dc endgna 135 dollar askfloge hgera gebaw manen newe ymntykw snele tktacue laye balw selke dwlacue teyku tbalne gene semi algnen 940 dollar twsdbge keza beuala 2 giza hgera gbcaluge be Ethiopia air lines gene aydlme ulame gene aznalue ykrtam ybat newe aylume yengda akbablacen bezu sera ytbkbtal Abo Egzbher ybarkh knbtsbeh bselam ymlseh.

  ReplyDelete
 41. ስብሰባና ግምገማ፣ ኮንፈረንስና የእርምት ንቅናቄ፣ ተሐድሶና የፖለቲካ ትምህርት፣ ቋንቋው የነበረ አንድ ትውልድ እንዴት እንደጠፋ ትታዘባላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 42. ዳኒ ለሚማረበት ሰው ጥሩ ጥቆማ ነው ነገረ ግን ስህተትን ከመቀበል ይልቅ ንግግሩን ወይም አስተያቱን ለምን እንዲህ ተባልን ሁሌ ደካማ ጎናችን ብቻ ነው የሚናገረው ተልኮ ሊኖረው ይችላል ሀገራችን እያደገች ነው ከዕድገት ጋር ተያይዞ የመጣ ችግር ነው ማለት እንጅ ያሁኑ ትውልድ ድከመቱን መቀበል በአንድነትን
  የዚያ ዘመን ወጣቶች ለሀገራቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ለነጻነት የነበራቸውን ታጋይነት፣ ላመኑበት ነገር ይከፍሉት የነበረውን መሥዋዕትነት፣ በሌላው ዓለም ያዩትንና ያነበቡትን በሀገራቸው ለማምጣት የነበራቸው ሕልም፣ ለአብዮት የነበራቸውን ጽኑ ፍቅር ያሳያችኋል፡፡ ያንን የመሰለ ትውልድ በጦርነት፣ በእሥርና በግድያ፣ በስደትና በጉስቁልና ማጣት ሀገሪቱን ምን ያህል እንደ ጎዳት ታዩበታላችሁ፡፡ ውጊያና ትግል፣ ስብሰባና ግምገማ፣ ኮንፈረንስና የእርምት ንቅናቄ፣ ተሐድሶና የፖለቲካ ትምህርት፣ ቋንቋው የነበረ አንድ ትውልድ እንዴት እንደጠፋ ትታዘባላችሁ፡፡ ያ ትውልድ ፈጽሟቸዋል ብለን የምናስባቸው ስሕተቶች ዛሬም እንደገና እየተመላለሱ መፈጸማቸው ነው፡፡ አሁንም ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ስንሞክር፣ አሁንም ድርጅቶች፣ ማኅበራት፣ ፓርቲዎች ከግለሰብ ነጻነት በላይ ሲሆኑ፣ አሁን የፓርቲ መሪዎች ችግሮችን በመከፋፈልና በመለያየት ሲፈቱ፣ አሁንም ሕዝብና ፀረ ሕዝብ፣ አንድነትና ፀረ አንድነት፣ አብዮታዊና ሊበራል፣ ኮሙኒስትና ካፒታሊስት የመከፋፈያ መሣሪያዎቻችን ሲሆኑ፣ አሁንም በጠላት መቃብር ላይ ሕንጻ የመሥራት አባዜ አልለቀን ሲል፣ አሁንም የተቃራኒያችንን አመለካከት ለማዳመጥ ትዕግሥት ሲያንሰን፣ ምን ያህል ከዚያኛው ዘመን ስሕተት እንዳልተማርን ያሳዩናል፡፡

  ReplyDelete
 43. ዳኒ. ስኳር ከቀበሌ ወስደህ ታውቃለህ?
  ካላወቅህ እስኪ ከአ.አ. ወጣ ባለ በአማራ ክልል ከተማ ሂድና እንዴት እንደሚያስተናግዱ ተመልክተህ ጻፍልን

  ReplyDelete
 44. Dear Dani, I agree with what you said about Ethiopian Airlines. First of all I want to tell the truth that once you got on board ET, the hostess and pilots are nice people in handling their clients. They will in general try to show you respect. But, when it comes to people in ground services (ticket office, check-in desk handlers, others at the airport)every thing is quit shameful. Sometime, I feel doubt whether these people are grown in our culture. They are totally arrogant and disrespectful. (there might be few nice people) Every time you have international guest, they would want to make something that upsets out visitors. If the CEO of ET has the opportunity to listen this cry let him teach his employees the word "SORRY". They never show regret. Sometime they would walk away while you try to explain them your problems. Anyone who travels abroad will always be sensitive to any changes. Employees of ET have to understand that and calm their clients at least by saying "SORRY"! I do remember the only person I heard saying that was an ET staff from Diredawa. Years ago, our flight to Addis was cancelled. The person by the name Amanuel (Aman?)was handling all those angers. Some of the passengers have connection flights the same day. We all shouted at him. But, the well trained employee was calm enough to say "SORRY". We were all really moved by his words.

  If the CEO of ET listens to our cry, let him visit the customers services. They are destroying our image!

  ReplyDelete